አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
457 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ገረገራ


#ክፍል_ስድስት


#በታደለ_አያሌው

...ወደ መኪናዬ ሽምጥ እየሮጥሁ ሳለ ነበር፣ የንስሐ አባቴን እንኳን
እንዳልተሰናበትኋቸዉ ያወቅሁት፡፡ እንደ ልማዴ በጥድፊያ ወደ ሲራክ፯ አሽከረከርኩ። መቼም ከባልቻ የተደበቀ ነገር የለም፡፡ እሱን አግኝቼ እስከማማክረዉ ድረስ ትንፋሼን እንኳን ወደ ዉስጥ መሳብ አልሆነልኝም፡፡ ቸኩያለሁ። አይደርሱት የለም ደረስሁና ቢሮዉን በርግጄ ስገባ፣ ባልቻ በወንበሩ ላይ ለጠጥ ብሎ እንቅልፍ አሸልቦት አገኘሁት።
በተለይም የሲራክ ፯ ዋና ኃላፊ ከሆነ በኋላ የግል መኖሪያ ቤቱን አይቶት የሚያዉቅ አይመስለኝም። ዉሎዉም አዳሩም እዚሁ ሆኗል። እዚሁ ምግብ ያስመጣል፣ እዚሁ ወንበሩ ላይ ትንሽ ዕረፍት ያደርጋል። ከስንት አንድ ወደ ዉጪ ቢወጣ እንኳን ምክንያቱ ለዚሁ ለሲራክ ጉዳይ ብቻ
ነዉ፡፡

“ባልቻ!” ብዬ ስጮህበት፣ ብርግግ ብሎ ብድግ አለልኝ።
“ዉብርስት?” አለ ተጨናብሶ፣ እጁን ለሰላምታ እየዘረጋልኝ፡፡
“እሰይ! ‹ዉብርስት?” አልሁት፣ ልጃለሜ የሚለዉ ቁልምጫዉ
መቅረቱ ከንክኖኝ፡፡ እኔ ደግሞ ከእሱ ብቻ ሳይሆን ከማንም ቁልምጫ የለመድሁ ሰዉ ነኝ። ቁልምጫዉን ሳይቀር እንደገና በሚያቆላምጥ ቤተሰብ መሀል ነዉ ያደግሁት። ያዉም ዉብዬዋ፣ ‹ዉቤዋ፣ የኔ ዉብ፣ ዓለሜዋ፣ ‹ልጃለሜ› እየተባልሁ። ባልቻ እንዲሁ እንደ ወረደ በስሜ ጠርቶኝ ካለማወቁ የተነሳ፣ ስሜን ሁሉ የሚያዉቀዉ አይመስለኝም
ነበር። ትዝ ሲለኝ እኔ ራሴ ባልቻ ብዬ ነዉ የጠራሁት ለካ። «አባታለም» የሚለዉ ቁልምጫዬስ? የት ተዉሁት?

“ይኸዉ መጣሽ። በስንት ጊዜሽ? ስደዉል ሳታነሺ፣ ሳስጠራሽ ሳትመጪ፣ ስፈልግሽ ሳትገኘ፤ ዛሬ ምን አመጣሽ በይ?”

“እሸቴ ጠፍቷል”

“ጠፋ? ማን እፍ ብሎት ይሆን በናትሽ? ቀድሞስ በርቶ ኖሯል እንዴi” ሲል አላገጠብኝ፡፡

“ማላገጥህ ነዉ?”

“ራስሽ ከመሀል ጀመርሽዋ! እኔና አንቺ እኮ ገና እንደገና መተዋወቅ
አለብን። ቆይ የት አዉቅሻለሁ? አንቺ ታዉቂኛለሽ?”

“በማርያም አባታለም? ፈርቻለሁ። እሽቴ በመንግሥት ደኅንነቶች እጅ
ወድቆ እንዳይሆን ልቤ ሰግቷል”

“እና ምናገባኝ እኔን?”

“ኧረ ባዛኝቱ? እንዴት ነዉ የማያገባህ፤ እሽቴ እኮ ነዉ!”

"የሆነስ እንደሆነ!”

“አዉቃለሁ አሳዝኜሃለሁ። ለዚያም እንዴ ት ይቅርታ መጠየቅ እንዳለብኝ አላዉቅም። ቢሆንም ግን በዚህ መሀል እሸቴ በጨካኞች እጅ ወድቆ
ከሆነ አያሳዝንህም?”

“ያሳዝነኛል”

“እኮ አንድ ነገር አድርጋ”

“ምን ላድርግ?”

“የማታስፈልገዉ?”

“እሺ። አስፈልጌ ሳገኘዉስ?”

“ያንተን አላዉቅም። እኔ ግን ተንበርክኬ ይቅርታ እለምነዋለሁ”

“ለምን?”

“ስለሚገባዉ”

“እሺ። መጀመሪያ ግን እንስማማ”

“ንገረኝ በምን?”

“ተንበርክከሽ የምትጠብቀዉ ከሆነና፣ ተሳክቶልኝ ካገኘሁት ደግሞ ወደ ሆስፒታል ለመሄድ ቃል ከገባሽልኝ.…”

“ይኼዉ!” ብዬ ጉልበቴ ግዉ እስከሚል ድረስ ወድቄ ተንበረከክሁ፡፡
“ብቻ አንተ እሺ በለኝ። እገባለሁ። እሄዳለሁ፤ አሁኑኑ ፈልግልኝ!”

“ዉዉዉ-ዉቤ?” የሚል ድምፅ ከኋላዬ ሰማሁ። ማን በተብታባ ድምፁ እንደ ጠራኝ ለማጣራት ዞሬ ማየት ያስፈልገኝ ኖሯል? ኧረ በጭራሽ በጠረኑ ብቻ አዉቀዋለሁ፡፡ እሸቴ ነዉ፡፡ ወይ ባልቻ! ምን ዓይነት ልብ
ነዉ የታደለዉ ግን? መቼም ጨክኖ ማኩረፉን አያውቅበት! ሆነ ብሎ ኖሯል ለካ እሸቴን ከሁላችንም እይታ እንዲጠፋ ያደረገዉ፡፡ እኔ እንደሆነ
እንዳልሞተ ሰዉ የማራክስዉ ነገር የለኝም፡፡ ጊዜ እንኳን ዉድ
የሚሆንብኝ ካለፈ በኋላ ዞሬ ሳየዉ ብቻ ነዉ። እቃም ቢሆን ከእጅ አምልጦ ካልተሰበረ ወይ ደግሞ ካልተሰረቀ በቀር ዉድነቱ አይታወቀኝም።እሸቴንም ባላጣዉ ኖሮ አልፈልገዉም ነበር። ለዚህ ይመስለኛል ባልቻም
እሸቴን ከዓይኔ እንዲጠፋ ያደረገብኝ። የእሽቴን ዉድነት እንዳምን፣ ከዓይኔ ሠወረብኝ፡፡ እንኳንም ሠወረብኝ፣ እንኳንም ናፈቅሁት፣ እንኳንም
አገኘሁት። ተሳክቶለታል።

ባልቻን በስስትም በኩራትም እያየሁት ሳለ፣ እሸቴ ከፊት ለፊቴ መጥቶ እንደኔዉ በጉልበቱ ወደቀ። ጥዉልግ ብሏል። ከንፈሩ ሳይቀር ኩችር ብሎ ደርቆ ታየኝ፡፡

“እሽቴ?”

“ጨጨጨ ጨከንሽብኝ እኮ
ዉቤ”

“ኹለተኛ አላደርገዉም”

“አአአ አአ አለሽልኝ ግን?”

“አለሁልህ። አለህልኝ?”

የባልቻን መኖር ሁሉ ረስተን፣ አንገት ለአንገት ተቆላልፈን ቆየን፡፡
እንደዚሁ እንዳለን፣ ልክ እሸቴን እንዳገኘልኝ ወደ ሆስፒታል ለመሄድ የገባሁት ቃል ትዝ አለኝ። እስከሚነጋ ቸኮልሁ።

ከአምስት ወር በላይ በሆዴ ፅንስ ይዤ፣ ያዉም እኔ ራሴ የሕክምና
ባለሙያ ሆኜ ፤ እስከ አሁን ግን የሕክምና ክትትል አለመጀመሬ ለግድ የለሽነቱ ወደር የማይገኝልኝ ሴት መሆኔን መስክሮብኛል፡፡ ይኼንን ማንም ሳይነግረኝ አዉቄዋለሁ። ሲሆን ሲሆን እርግዝና ከመፈጠሩ ከዓመት ወይ
ከወራት ቀደም ሲል ጀምሬ ዝግጅት ማድረግ ነበረብኝ፡፡ እንደኔ እንኳን እርግዝናዉ በድንገት ለተፈጠረበትም ቢሆን፣ ከመጀመሪያዉ ጀምሮ
ሙሉ ምርመራ እና ክትትል ማድረግ የግድ ነዉ። እኔ ግን ቢያንስ ቅሪት መሆኔን ያወቅሁት ቶሎ ቢሆንም፣ ይኼዉ 22ኛ ሳምንቴን ጭልጥ አድርጌ ነዉ ገና ነገርዮዉን እንኳን በበጎነቱ የተቀበልሁት።

ዛሬ ነዉ ወደ ሆስፒታል ለመምጣት የወሰንሁት። ዛሬ ገና።

ዛሬ ግን ቆርጬ መጥቻለሁ።

በእናቶች እና ሕጻናት ሕክምና ዝነኛ ወደ ሆነዉ ሐሚያሉ ሆስፒታል ገብቼ ካርድ አወጣሁና ወደ ተጠቆምሁት የዶክተር ክፍል አመራሁ። ብዙም ሳልቆይ ወረፋዬ ደረሰኝና፣ መለስ ያለዉን በር ገፍቼ ወደ ዉስጥ ገባሁ። ሆስፒታሉን በበጎ ስሙ መረጥሁት እንጂ፣ የተለየ የሐኪም ምርጫ አላደረግሁም ነበር። ሆኖም ከዉስጥ የጠበቀችኝን ሐኪም ካየሁ በኋላ፤ ሕይወት የአጋጣሚዎች ጋን መሆኗን አመንሁ።

ሐኪሟ ስንቱን አብራኝ ያሳለፈች፣ የቀድሞ ጓደኛዬ ሆና እርፍ!

“ሸዊት!” አልኋት፣ ለረዥም ደቂቃ እጄን አፌ ላይ ጭኜ ስደነቅ ከቆየሁ በኋላ።

"የፈጣሪ ያለህ! ዉብዬ ?” አለች እሷም፣ አሁንም አሁንም ዓይኖቿን
ጨፍና እየገለጠቻቸዉ። ከመልኬ እኩል በሆዴ ያለዉን አስተዉላለች፡፡ ከነጭራሹ የምንገናኝ፣ ያዉም እንዲህ ሆኜ፣ አልጠበቀችኝም ነበር። ለነገሩማ እኔስ እንዴት ብዬ እጠብቃለሁ? በጎንደር ዩኒቨርስቲ የሕክምና
ዶክትሬት ዲግሪያችንን አብረን በተማርንበት ወቅት የነበረንን ጓደኝነት አይቶ ትንሽ ትልቁ እንደዚያ ከዓይን ያዉጣችሁ እንዳላለን ሁሉ፣ እንደዚህ በአንድ ከተማ መኖራችንን እንኳን እስካለመተዋወቅ ድረስ
መራራቃችን ዋዛ ነዉ፡፡ ምን ሆነን ነዉ ግን? ምንም፡፡ ለነገሩ ዩኒቨርስቲ ካስተዋወቀኝ ወዳጆቼ ማንን አግኝቼ አዉቃለሁ? ከስንት አንድ በአጋጣሚ ካልሆነ በቀር፣ አብዛኞቹ የት እንዳሉ እንኳን አላዉቅም፡፡

“ዋዉ!” አለችኝ፣ እንደ ታቦት እየዞረችኝ፡፡

“እሩ እስኪ ሰላም በዪኝ መጀመሪያ”

“እንኳን ለዚህ አበቃሽ ዉብዬ” ብላ መጥታ አንገቴ ሥር ሰረገች፡፡
እንደገና ሆድ ሆዴን ትኩር ብላ አየችኝና፣ ጭምጭም አድርጋ ሳመችኝ፡፡የምር ደስ ብሏታል። እንባዋ ሳይቀር ጠይም ጉንጮቿን እያራሰ በብርቅዬ አንገቷ በኩል ፈሰሰ።

ሀገር ዉስጥ ነዉ የምትኖሪዉ? ጭራሽ እዚሁ አዲስ አበባ?” አልኋት፣

ደስታዋ እንዲጋባብኝ ልቤን እየደቃሁት።

“አይ፤ ቅርብ ጊዜ ነዉ የመጣሁት። ጀርመን ነበርሁ፣ ትምህርት ላይ”

“ተዪ እንጂ? ጀርመን፤ ምን ስፔሻላይዝ አደረግሽ ታዲያ?”

“ይኸዉ እያየሽኝ? ለእር ግዝና ክትትል አይደል እንዴ እኔ ጋ
የመጣሽዉ?”

“አይ አጅሪት! እንዲያ ነዉ እንጂ የኔ እህት! ደግሞ ጥሩ ምርጫ ነዉ”

“አንቺስ ምን አጠናሽ?”
👍481
#ገረገራ


#ክፍል_ሰባት


#በታደለ_አያሌው


...“በይ እሺ፡፡ በይ ደርሰሽ ነይ”

የምርመራ ማዘዣዎችን ተቀብያት ስወጣ፣ ለአልትራሳውንድ ምርመራዉ ጨመር ያለ ዉሃ መጠጣቱ እንደሚጠቅመኝ ስለማዉቅ፣ ወደ ሆስፒታል
ስመጣ ጀምሬዉ ያጋመስሁትን ኹለት ሊትር ዉሃ እየተጎነጨሁለት
ወደ ቤተ ሙከራዉ ተመለስሁ። እንደ ፈራሁት ስዓቱ ሰዉ የማይበዛበት ሰዓት ሆኖ ይመስለኛል፣ የሚያማርር ወረፋ አልገጠመኝም። በመሆኑም፣
ደሜን ጨምሮ የሚያስፈልጉ ዋና ዋና ናሙናዎችን ሰጥቼ በግማሽ ሰዓት ዉስጥ ዉጤት ደረስልኝ። ዉጤቴን ይዤ እንደገና ወደ ቀድሞዋ የልቤ ሰዉ፣ የአሁኗ ደግሞ ሐኪሜ ቢሮ ወጥሮ የያዘኝን ሽንቴን እንደ
ቆነጠጥሁ ተመለስሁ። ገለጥ አድርጌ እንኳን ወረቀቱን የማየት ሐሳብ ብልጭ አላለልኝም።

ሆስፒታላችሁ ብርሃናዊ አይደል እንዴ አንቺ፣ ፍጥነቱ!”

“ዉጤቱ ደረሰልን?”

“ይኼዉ” አልኋት፣ ጠረጴዛዋ ላይ እንደ ከባድ እቃ በኹለት እጄ
እያስቀመጥሁላት።

“ደፈንሽዉ ኣ?” አለችኝ፣ ትኩረቷን አድርጋበት ከነበረዉ ኮምፒዉተሯ
ወደ ዉጤት ወረቀቴ እያመጣችዉ።

“እረ እኔ ምኑንም አላየሁት”

ለመጨረሻ ጊዜ ሆዴን ሰረቅ አድርጋ አየችዉና ወረቀቱን ገለጠችዉ፡፡ድንገት ፊቷ እብጥ አለብኝ። ዉጤቱ ላይ ደስ የማይል ነገር እንዳገኘች ጠረጠርሁ። ቢሆንም ግን ራሷ እስከምትነግረኝ ድረስ ብጠብቅ ይሻላል ብዬ ያላየኋት መሰልሁ። እሷም ያልደነገጠች ለመምሰል የሆነ ያልሆነዉን ቀበጣጠረች፡፡ እንደገና በሚያደናግር ትኩረት አስተዋለችዉና ወደ አልትራሳዉንድ ክፍሉ እንድከተላት ነገረችኝ፡፡ ስንገባ ያገኘነዉን ራዲዮሎጂስት እንኳን በቅጡ ሰላም አላለችዉም። ቶሎ ብዬ ሆዴን ገልጬ አልጋዉ ላይ እንድንጋለል አዘዘችኝ፡፡ ለወትሮዉ በልዩነት የተማረዉ ባለሙያ ያለበትን አልትራሳዉንድ ይቅርና ተራ ነገርም ቢሆን
ሐኪም ያለሙያዉ ገብቶ አይፈተፍትም፡፡ እሷ ግን እጅግ ከመቻኮሏ የተነሳ እሱን ጨምራ በጥድፊያ ከፍ ዝቅ አደረገችዉ። የእዉር ድንብሯ ወጥቷል። ሌላዉ ቀርቶ ገና በመመርመሪያዉ (ultrasound probe)
እንኳን ሳይዳብሰኝ ነበር ዓይኖቿን ወደ ምስል መከሰቻዉ የተከለቻቸዉ።

ችኮላዋን በበጎ የተረዳት የክፍሉ ባለሙያ፣ ሳይቀየማት የሚደረገዉን ሁሉ አድርጎ የፅንሱን ጥላማ ገጽ ፊት ለፊታችን ባለዉ ዝርግ መከሰቻ አመጣልን። ይኼ ሁሉ ሲሆን የእሷን አድራጎት ብቻ ነበር የምከታተለዉ።
እስኪበቃት ድረስ እያጎላች እና እያሳነሰች ስትመለከተዉ ቆየች። እኔንም እንዳየዉ ጋበዘችኝ፡፡

አየሁት።

ችግር አለ። ከባድ ችግር!
“አይ፤ ያን ያህል እንኳን አንገት የሚያስደፋ አይደለም” አለችኝ፣
ከአልጋዉ ላይ እንድነሳ እየደገፈችኝ። ድንገት ሰዉነቴ እየከዳኝ፣ የበለጠ ድጋፍ እየፈለግሁ መጣሁ። ደግነቷ፣ እጇን አልከለከለችኝም።
“በእርግጥ የማልደብቅሽ ነገር ቢኖር፤ እኔም ልክ የላብራቶሪ ዉጤትሽን ሳየዉ ደንግጫለሁ። በዚያም ላይ ከእኔ ባልተናነስ ስለ ሁኔታዉ ልታወቂ እንደምትችይ ስለማዉቅ በማይመስልሽ ቃል አንቺን አልሸነግልሽም።እንኳንስ የሕክምና ሥነ ምግባር ለማገባት ላንቺ ለጓደኛዬ ይቅርና፣
ለታካሚዎቼ ሁሉ የሆነዉን በግልጽነት የማስረዳት ኃላፊነት አለብኝ። የምልሽ ይገባሻል መቼስ”

ጓደኛዬም ሐኪሜም በሆነችዋ ሸዊት ፊት፣ ግብኔ ብቻ ያልቀረ ለመምሰል ተጣጣርሁ። ጠንካራ ለመምሰል እየሞከርሁ የዉጤት ወረቀቱን እንድትመልስልኝ እና የሆነዉን ሁሉ በራሴ ዓይን እንዳየዉ እጄን ዘረጋሁላት። ሐኪሜ ለምን እንደዚያ እንደሆነች ገባኝ፡፡ ምክንያቱም የፎሊክ አሲድ መጠኑ ከሚጠበቀዉ መጠን እጅግ የወረደ ኖሯል።
እንደዚህ ሲሆን ደግሞ በፅንሱ ላይ የነርቭ ክፍተት የማስከተል ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑን እንኳንስ ሥራዬ ብላ ያጠናችዉ እሷ ትቅርና፣ እኔ ዉብርስትም አዉቀዋለሁ። የፎሊክ አሲድ እጥረት ከተከሰተ፣ የነርቭ
ዘንግ ከአፈጣጠሩ ጀምሮ በወቅቱ እንዳይዘጋ ያደርገዋል። በመሆኑም፣ የፎሊክ አሲድ እጥረት እንዳያጋጥም፣ እርግዝና ከመፈጠሩ አስቀድሞ ወይ ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ከተመረጡ ምግቦች፣ ወይ ደግሞ ሰዉ ሰራሽ እንክብሎችን መዉሰድ ያስፈልጋል። ያለበለዚያ ይኼዉ በእኔ የምርመራ ዉጤት ላይ እንደ ታየዉ፣ ልክ ያልሆነ ነገር በፅንሱ ላይ ይፈጠራል።

ምን ዋጋ አለኝ? አርፍጃለኋ!

“በእርግጥ ሌሎችም መነሻዎች ስላሉት፣ የፎሊክ አሲድ እጥረቱ ነዉ ይኼን ያመጣዉ ብሎ አፍን ሞልቶ መደምደም አይቻልም። ሆኖም እኔን ደጋግመዉ ከገጠሙኝ ዐሥር የፎሊክ አሲድ እጥረት ያየሁባቸዉ ነፍሰ
ጡሮች፣ ቢያንስ የስድስቱ ወደ ነርቭ ክፍተት ያደርሳል። የነርቭ ክፍተት ስልሽ የተለመዱትን፣ በተለይም ስፓይናቢፊዳ(አከርካሪው ላይ ያለው ነርቭ ወደ ውጭ መውጣት) ማለቴ ነዉ። ይኼ ደግሞ ያልሰለጠነ ሀገር በሽታ እየሆነ መጥቷል። ምክንያቱም የበለጸጉት ሀገራት ምግባቸዉን በጠቅላላ በፎሊክ እንዲበለጽግ ስላደረጉት፣ ብዙም አያጋጥማቸዉም። የእኛን ሀገር ግን አታንሺዉ”

“በናትሽ መፍትሔ አለዉ በዪኝ”

“ደግሞ በኛ ዘመን መፍትሔ የሌለዉ ነገር ምናለና ዉቤ”

“እኮ ምን?”

“በተአምር ታምኛለሽ?”

የጭንቅ ዝልዝል የተንጠለጠለበትን ፊቴን መለስሁላት።

“ተአምር?”

“አሁን አንዴ ፅንሱ ቅርጽ ይዟል። ተአምር ካልተፈጠረ በቀር፣ ሕጻኗ... በነገራችን ላይ ጾታዋን አልነገርሁሽም አይደል ቅድም? ሴት ናት። እና፤ከላብራቶሪም ሆነ ከአልትራሳዉንድ ባገኘነዉ ዉጤት መሠረት፣ በወሊድ ጊዜ ሊገጥሙን የሚችሉ የነርቭ ዘንግ ክፍተቶች ይኖራሉ፡፡ በተለይ
ስፓ ይናባይፊዳ የሚባለዉ ለብቻዉ ወይም ደግሞ ሀይድሮሴፋለስ(ጭንቅላት ውስጥ ውሃ መቋጠር) ጭምር
ሊሆኑ ይችላሉ። ግን እንዳልሁሽ ነዉ፤ ተወልዳ በዓይናችን እስከምናያት ድረስ መቶ በመቶ እርግጠኛ መሆን አንችልም”

“እንዲያዉ አይበልብኝና ይኼ ነገር እዉነት የሚሆን ከሆነ ምንድነዉ
የሚሆነዉ ግን?”

“እንደምታዉቂዉ፤ ለሐቅ የቀረበ ግምት እንጂ ፍጹም የሚባል ያለቀ
የደቀቀ ሐቅ የለም በሳይንስ፡፡ አንቺም ሐሳቤን የምትጋሪዉ ይመስለኛል።ሆኖም አብዛኛዎቹ የዚህ ክፍተት ተጠቂዎች የታወቁ ጉዳቶች ይገጥሟቸዋል። ለምሳሌ ሽንትና ሰገራ ያለመቆጣጠር፣ የእግርና የእጅ ሽባነት፣ የዓይን መንሸዋረር ወይ መጥፋት እና ሌሎችም ጭምር።እንዲያዉም አልፎ አልፎ የከፋዉ ሲመጣ፣ እነዚህ ያልሁሽ ሁሉም አንድ
ላይ የሚከሰቱበት አጋጣሚ ሁሉ አለ። ታዲያ እንዳልሁሽ፣ በኛ ዘመን
መፍትሔ የሌለዉ ችግር የለም። ቢፈጠርም እንኳን ሕክምና አለዉ”

“አለዉ?” አልሁኝ፣ ለእፎይታ ራሴን እያመቻቸሁ። አንደኛዬን ግልብ
ሆኜ የለ አሁንማ? አሁን መሳቅ አሁን ማልቀስ፣ አሁን ማመን አሁን
መካድ። ስስ ሆኛለሁ።

“አዎ። ቀዶ ጥገናም እኮ አለዉ። አንቺን መምከር ሳይገባኝም፣ ከዚህ በላይ መጨነቅ ግን አይኖርብሽም። ጭንቀት ራሱ ሌላ ጣጣ ስላለዉ፣ እዉነታዉን የምነግርሽ እንድትጨነቂበት ሳይሆን ለግልጽነት ብዬ ነዉ።
በዚያ ላይ አንቺ ጠንካራ ሰዉ መሆንሽን ለእኔ ለጓደኛሽ እንዲነግሩኝ አልጠብቅም። አዉቅሻለኋ!”

ቀዝቃዛ ትንፋሽ ተነፈስሁ። ገና ዛሬ፣ አሁን ገና የእግዚአብሔርን ይቅር ባይነት ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠራጠርሁት። ወይ ስለ ንስሐ ምንም አላዉቅም፣ ወይ ደግሞ እግዚአብሔር ቂመኛ ነዉ
ስል አሰብሁ። እኔ የተማርሁት ሰዉ ፍጹም ተጸጽቶ ንስሐ ከገባ
ኃጢአቱ ሁሉ ፍጹም ይሰረይለታል የሚለዉን ነበር። ከእግዚአብሔር
ጋር የሚያደረገዉም እርቅ ፍጹም ይሆንለታል ሲባል አዉቃለሁ። ታዲያ እኔ ፍጹም የሆነ ጸጸት ተጸጽቼ ንስሐ አልገባሁም? ቀኖናዬንስ በሚገባ ወይስ እግዚአብሔር ፍጹም አምላክ መሆኑን አላመንሁም?
👍391