አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
566 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ትኩሳት


#ክፍል_አራት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

ሲልቪ
ላይ ላዩን


..ተመስገን ክፍል ውስጥ ቁጭ ብዬ ስሰራ አንዳንዴ ውቢቱ ሲልቪ ትመጣና «Salut Castro noire» ትለኛለች። («ሰላም፣ ጥቁር ካስትሮ») (ፂም ስላለኝ ነው፡፡)

«Que la paix soit avec toi Scheherazade Blanche» እላታለሁ
(«ሰላም ላንቺ ይሁን፣ ፃእዳይቱ ሻህራዝድ ሆይ»)

ትስቃለች። በምስራቃውያን አነጋገር እንቀጥላለን። ቀልድ
ነው። ከሲልቪ ጋር ሁልጊዜ ቀልድ ነው:: እውነተኛ ፈረንሳዊት ናት፣ ስለምንም ነገር ቢሆን «Moi je men fous!» ነው የምትለው
(«እኔ ስለዚህ ነገር ደንታ የለኝም»)
ታድያ ደስ ትላለች። ሰፊ አፏ
ሳሙኝ ሳሙኝ ይላል፡፡ አብረሀት ስትሆን ሳቅ ቀልድ ታበዛለህ፣

«ዠማንፉቲዝሟ» ይጋባብሀል፤ ስለምንም ነገር ደንቴ አይኖርህም
አንድ ቀን ግን
«ምንድነው ሁልጊዜ ስትፅፍ የማገኝህ?» አለችና ደብተሬን
አየችው:: የምን ፅህፈት ነው ይሄ? ያገራችሁ ነው?» አለችኝ
«አዎን»
«ምኑም አይገባም»
«ቀላል ነው፡፡ ሁለት መቶ አርባ የሚሆኑ ፊደላት አሉት»
«Quel horreur! (ኧረ የጉድ ያለህ!) እንግዲያው አታስረዳኝ
ይቅርብኝ .. ምንድነው ምትፅፈው?»
«ምንም አይደለም»
«ልብወለድ ነው?»
«ብጤ ነው»
«እንዴት ማለት ብጤ?»
«እንዴት ልበልሽ? ልብወለድ ነው፣ ግን ፈጥሬው አይደለም፣
ያየሁትን የሰማሁትን ነገር ሰብስቤ ቅርጹን እለዋውጣለሁ እንጂ፣
ላንባቢ እንዲጥም»

«ቆይ ቆይ፡፡ አሁን መፃፍ አለብህ ወይስ ለጊዜው ልትተወው
ትችላለህ»
«ልተወው እችላለሁ»
«እንግዲያው ከዚህ እንሂድና ቡና ልጋብዝህ:: እና ስለድርሰት
እናውራ። ይስማማሀል?»

«በደምብ ነዋ! ቆንጆ ሴት ቡና ስትጋብዘኝ ሁልጊዜ
ይስማማኛል»
«Malin Castro noir va!» («ሂድ ወድያ! ፎሌ ጥቁር ካስትሮ!»)
Deux Chevaux መኪናዋ ውስጥ ከገባን በኋላ
«ኤክስ ውስጥ የምወደው ካፌ የለኝም፡፡ ማርሰይ እንሂድ?»
አለችኝ
እየቀለድን እየሳቅን ደጋግማ «Moi, u sais je m en fous!»
እያለች፣ በሆዴ ውበቷን እያደነቅኩ፣ ማርሰይ ደረስን፡፡ የንግድ ሳይሆን የግል የመደሰቻ ልዩ ልዩ አይነት ጀልባዎች ከተደረደሩበት ወደብ አጠገብ አንድ ካፌ ገብተን ቢራ ካዘዝን በኋላ፣ ጉልህ ሰማያዊ
አይኖቿ በፈገግታ እያዩኝ
«ንገረኛ ስለምትፅፈው» አለችኝ
«ምን ልንገርሽ?»
«ስለሰዎቹ፣ ስለጊዜው፣ ስለግንኙነታቸው፣ ማን ማንን እንደ
ሚወድ፣ ማንስ ማንን እንደሚጠላ፣ መፅሀፍህ አንዴት እንደ ሚጀመር፣ አሁን የት እንደደረሰ፣ በኋላ እንዴት እንደሚያልቅ፣
ምን ምን ነገር እንደሚያስቸግርህ፣ መፅሀፍህ ምን እንዲል እንደ
ምትፈልገው፣ ሁሉን ንገረኝ
ቆንጆ ስለሆነች ይሁን፣ አጠያየቁን ስላወቀችበት ይሁን ወይ ሌላ ያልተገለፀልኝ ምክንያት ይኑር እንጃ፣ ስለመፅሀፌ ሁሉን
ነገርኳት። ለማንም ነግሬ የማላውቀውን ለሷ አጫወትኳት፡፡ ችግሩን ደስታውን፣ ብስጭቱን፣ የድል አድራጊነት ስሜቱን፣ ምንም
ሳልደብቅ አዋየኋት። ፈረንሳይኛው ሲያስቸግረኝ ልክ ልናገረው
የፈለግኩትን ቃላት ታቀብለኛለች፣ ምክንያቱም ሀሳቤ ቃላቱን
ቀድሞ ደርሷት ይቆያል። አንዳንድ ቦታ አንድ ሀሳብ ተናግሬ
ጨርሼ ሌላ ሀሳብ አልመጣልህ ሲለኝ አንድ ጥያቄ ትጠይቀኛለች
እሱን ጥያቄ ስመልስ፣ ሌላ ሀሳብ ይመጣልኝና እቀጥላለሁ፡፡ እንደዚህ ብዙ ካወራሁ በኋላ

«ይገርምሻል፣ ይህን ለማንም ነግሬ አላውቅም» አልኳት
«Jen suis lattee» አለችኝ (ክብር ይሰማኛል።)
«እኔ እውነቴን ነው»
«እኔም እውነቴን ነው»
«አሁን ተራሽን አውሪልኝ
«ቆይ» አለችና ከያዘችው የመፃህፍት ቦርሳ አንድ አስር የሚሆኑ ባንድ በኩል ብቻ በታይፕ የተፃፈባቸው ነጠላ ወረቀቶች ሰጠችኝ።
አንብበው አለችኝ፡፡ አነበብኩት፡፡ አጭር ልብ ወለድ ታሪክ ነው።
ስጨርስ ምን ይመስልሀል?» አለችኝ
«አንቺ ነሽ የፃፍሽው?» አልኳት
«አዎን» አለችኝ
«አዝናለሁ። ጥሩ ታሪክ አይደለም»
«ምንድነው የጎደለው?»
«እርግጠኛ አይደለሁም። አየሽ፣ አንድ ሰው የሚወዳትን ሴት
ሊገድል ይችል ይሆናል፡፡ ግን ባስር ገፅ ውስጥ ይህን መናገር
የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ሁለት መቶ ገፅ
ያስፈልገዋል»
«ይህንንም አንብብ እስቲብላ ሌላ አስራ ሶስት ገፅ ሰጠችኝ።
አነበብኩት። ግሩም ታሪክ ነበር፡፡
«ይህንንም አንቺ ነሽ የፃፍሽው?»
«አዎን»
«ታሪክ ይሉሻል ይሄ ነው! ይህን ጊ ደ ሞፓሳን ራሱ ነው የፃፈው ቢሉኝ አምናለሁ» አልኳት
ጉልህ ሰማያዊ አይኖቿ ልዩ አስተያየት ሰጡኝ፣ እንደማቀፍ ያለ
አስተያየት፣ ሙቀት ያለው አስተያየት

«Merci»አለችኝ

«Je ten prie (ኧረ ምንም አይደለም) ይህን የመሰለ ለመፃፍ
ስትችዪ፣ እንዴት አርገሽ የቅድሙን ፃፍሽው?» አልኳት
መሳቅ ጀመረች (ጥርሶቿ ትክክል ሆነው ነጫጭ ናቸው። ነጭ
የፈረንጅ ጥርስ ብዙ እይታይም) «እኔ እንጃ አለችኝ «በምፅፍበት
ሰአት ሁሉም እኩል ጥሩ ሆኖ ይሰማኛል። ካንድ ሁለት ወር በኋላ
ሳነበው ነው እውነተኛው ዋጋው የሚታየኝ»
«ይሄ መጥፎው መቼ ነው የተፃፈው?»
«ካንድ አመት ተኩል በፊት
«እንግዲያው መጥፎ መሆኑ
ድሮ ገብቶሻል። ለምን
እስነበብሽኝ?»
«ላውቅህ ስለፈለግኩ። ማንም ሰው ቢሆን፣ እንደምፅፍ ካወቀ
ወይም እንዲያውቅ ከፈለግኩ፣ መጀመሪያ መጥፎ ታሪኬን
አስነብሰዋለሁ። አንብቦት ጥሩ ነው ካለ በቃው። ሁለተኛ እኔ
የፃፍኩትን አያነብም። እስካሁን ለአንድ ስምንት ሰው አስነብቤያለሁ።
አንተና አንድ የፓሪስ ጓደኛዬ ብቻ ናችሁ መጥፎውን መጥፎ
ያላችሁት። ስለዚህ ሁለታችሁ ብቻ ናችሁ ጥሩውን ያነሰሳችሁ»
«ሌላ የፃፍሽው አለ?»
«ሃያ ሶስት አለኝ፡፡ አስራ አንዱ ጥሩ ይመስሉኛል። ሰባቱ
በጣም መጥፎ ነው:: አምስቱ ግን ጥሩም አይደል፣ መጥፎም
ኣይደል እንደኔ እስተያየት። ስለዚህ አንተ እነዚህን አምስት
አንብበህ ምን እንደሚመስልህ ብትነግረኝ፣ ተስፋ የሌለውን
እጥለውና ተስፋ ያለውን እየመከርከኝ አሻሽለዋለሁ»

«ክብር ይሰማኛል፣ ግን ልመክርሽ መቻሌን እንጂ
«ትችላለህ። ታግዘኛለህ? »
«ከቻልኩማ በደስታ! አሁን ስለራስሽ ንገሪኝ፡፡ ቅድም እኔ
እንደነገርኩሽ»
ነገረችኝ፡፡ የምንፅፍበት ቋንቋ ተለያየ 'ንጂ ሙከራችን፤
ችግራችን፣ አስተያየታችን በጣም ይመሳሰላል፡፡ ስንወያይ መሸ፡፡
«እማውቃት ጥሩ ርካሽ ምግብ ቤት አለች» ብላ ሳን ሻርል
ባቡር ጣቢያ አጠገብ ወስዳ እራት ጋበዘችኝ። በፈረንሳይ ደምብ ከምግቡ ጋር አንድ ጠርሙስ ወይን ጠጣን፡፡ ሲኒማ ላስገባሽ አልኳት፡፡ ሁለታችንም እንደዚህ ልንጨዋወት የምንችልበት ጊዜ
መቼ ተመልሶ እንደሚመጣ አይታወቅም አለችኝ፡፡ እውነትሽን ነው አልኳት
ወደ ወደቡ ተመልሰን በእግር እየተዘዋወርን ወሬያችንን ቀጠልን። በተርታ የቆሙ ጀልባዎች የሚወዛወዙበት ውሀ ውስጥ የማርሰይ መብራት ይጫወታል። የባህር ሽታ ይዞ ከባህር በኩል የሚመጣው ነፋስ ቅዝቅዝ ያለ ሆኖ ይለሰልሳል። እንደኛው እያወሩ
የሚዘዋወሩ ሰዎች አሉ፤ አብዛኛዎቹ ተቃቅፈዋል፡፡ መንሽራሽር ሲበቃን አንድ ካፌ ገብተን ቁጭ ብለን ቢራ አዘዝን
👍271👏1
#ምንዱባን


#ክፍል_አራት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

...ለአሥራ ዘጠኝ ዓመት እስር ቤት ውስጥ ሲቀመጥ ኣንድ ቀን እንኳን እንባ አልወጣውም::
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከቤተክርስቲያን አናት ላይ የተሰቀለው ሰዓት ስምንት ሰዓት ሲደውል ዣን ቫልዣ ከእንቅልፉ እንደገና ነቃ፡፡ ከአራት ሰዓት በላይ ጥሩ እንቅልፍ ወስዶት ተኝቷል፡፡ ድካሙ ሁሉ ወጣለት:: ለዚህን ያህል ጊዜ የእረፍት ሰዓት ኣግኝቶ አያውቅም፡፡ ዓይኑን ገልጦ በአካባቢው በሰፈነው ጨለማ
ዘልቆ ለማየት ሞከረ፡፡ ለማየት ባለመቻሉ እንደገና እንቅልፍ እንዲወስደው ዓይኖቹን ጨፈነ፡፡

ቀኑን ሙሉ አእምሮ በብዙ ነገሮች ተበጥብጦ ከዋለና የተለያዩ ነገሮች ከተመላለሱበት አንድ ጊዜ እንጂ ሁለት ጊዜ እንቅልፍ ሊወስድ እንደማይችል
ሁሉ ዣን ቫልዣንም ሊወስደው አልቻለም:: እንቅልፍ መጀመሪያ ሲመጣ ያዳፋል፡፡ ሁለተኛ ግን ቢለማመጡትም በዓይን አይዞርም:: እንደገና እንቅልፍ
ሊወስደው ስላልቻላ ማሰብ ጀመረ::
ብዙ ዓይነት አሳብ ከኀሊናው ውስጥ ገባ፡፡ ግን ሌሎቹን ሁሉ እየዋጠ እርሱ ብቻ እየተመላለሰ ያስቸገረው አንድ አሳብ ነበር፡፡ እነዚያ መዳም ማግልዋር ከጠረጴዛው ላይ የደረደሩዋቸው የሚያማምሩ ስድስት ከብር
የተሠሩ ሣህኖችና ትልቅ የብር ጭልፋ በዓይኑ ዞሩ፡፡ በጣም ወዷቸዋል:: አጠገቡ ከጳጳሱ ትራስጌ በኩል ቡፌ ውስጥ ሴትዬዋ ሲያስቀምጧቸው
አይቶአል፡፡ ከብር የተሠሩ ጥንታዊ ቅርስ በመሆናቸው ከነጭልፋው እስካ 200 ፍራንክ እንደሚያወጡ ያውቃል፡፡

ኅሊናው ከወዲያ ወዲህ እየዋለለ አንድ ሰዓት አለፈ፡፡ በአሳብ እየዋተቱ አንድ ሰዓት ማሳለፍ፤ ያውም ሌሊት በጨለማ ምን ያህል ረጅም እንደሆነ
የደረሰበት ያውቀዋል፡፡ የቤተክርስቲያኑ ሰዓት ደወል ዘጠኝ ሰዓት መሆኑን አበሰረ:: ዓይኑን በድንገት ገልጦ ከአልጋው ዘልሉ ወረደ:: ስልቻውን በእጁ
እየዳሰሰ ፈለገና እንደያዘው ከአልጋው ጠርዝ ቁጭ አለ፡፡ ሳያውቀው ብዙ ተቀመጠ፡፡ ሰዓቱ በየአሥራ አምስት ደቂቃና ግማሽ ሰዓት ደወል እየደወለ ባይቀሰቅሰውማ እስኪነጋ ድረስ በተቀመጠ፡፡ ደወሉ «አይዞህ፣ በርታ» የሚለው መሰለው::

ተነስቶ ቆመ፤ ለመራመድ ግን አመነታ:: አንድ እርምጃ ወደፊት
ተራምዶ አዳመጠ፡፡ ሁሉም ነገር ጸጥ ብሎአል:: ቀስ ብሎ በጥንቃቄ ወደ መስኮቱ ተጠጋ፡፡ ሌሊቱ ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ የተዋጠ ኣልነበረም:: ጨረቃ
በሩቁ ትታያለች:: ሆኖም ደመና ዞሮባታል፡፡ ደመና ጨረቃዋን በጋረዳት ቁጥር ቤቱ ትንሽ ጨለም ይላል፡፡ ውጪው በደምብ ሲታይ እቤት ውስጥ ግን ያንገዳግዳል፡፡ መስኮቱ አጠገብ ደርሶ መስኮቱን ሲመለከት በቀላሉ
እንደሚከፈት ስለተገነዘበ ከፈተው:: ሆኖም ኃይለኛ ብርድ ስለገባ መልሶ ዘጋው:: መስኮቱ መስታወት ስለነበር እንደተዘጋ ግቢውን ቃኘ፡፡ ግቢው
በአነስተኛ ግምብ መከለሉን ተመለከተ:: ከግምቡ ውጭ ረጃጅም ዛፎች ነበሩ፡፡ በሁለት ዛፎች መካከል ያለውን ርቀት ሲያጤን ርቀታቸው ተመሳሳይ
ሆኖ ስላየው ምናልባት ማዘጋጃ ቤቱ የተከላቸው ዛፎች መሆናቸውን በመገመት ከአጥሩ ውጭ ያለው መንገድ አውራ ጎዳና መሆን አለበት ብሎ ደመደመ::

ወደ ውሳኔ አሳብ እንደደረሰ ሰው በቆራጥነት ወደ አልጋው ተመለሰ፡፡ አቆማዳውን አንስቶ ከፈተውና ከውስጠ ምናምን ፈለገ፡፡ ኣንድ ነገር አውጥቶ
አልጋው ላይ አስቀመጠ፡፡ ጫማውን ኪሱ ውስጥ ከተተ፡፡ ኣልጋው ላይ ካስቀመጠው እቃ ሌላ የተቀሩትን እሳስሮ ትከሻው ላይ አኖረ፡፡ ቆቡን አጠለቀና ዱላውን ፈልጎ ከያዘ በኋላ ያሰረውን እቃ ከመስኮቱ ሥር
አስቀመጠው:: ወደ ኣልጋው ተመልሶ ያስቀመጠውን እቃ አነሳ:: እቃው ከአንድ ጫፍ እንደ ጦር የሾለ፣ ከሌላው ጫፍ ቋር ያለው ወፍራም ብረት ነበር፡፡ በዚያ ጨለማ ብረቱ ለምን ሥራ እንደተዘጋጀ ለመለየት አስቸጋሪ
ነበር፡፡ ዱላ ነው ወይስ እቃ ማንሻ? አይታወቅም:: ቀን እንኳን ቢሆን
የማዕድን ሠራተኞች መቆፈሪያ ነው ለማለት ያስችላል፡፡ በዚያን ጊዜ ቱሉን ከተባለ ቦታ አካባቢ በሚገኙ ከፍተኛ ኮረብታዎች ላይ ድንጋይ እንዲፈልጡ
የተፈረደባቸው ወንጀለኞች ይቀጠሩ ነበር፡፡ ወንጀለኞቹ ብዙውን ጊዜ የዚያን ዓይነት ብረት የመሰለ መፍለጫ ይይዛሉ፡፡

ዣን ቫልዣ ያን ብረት በቀኝ እጁ ያዘ፡፡ ትንፋሹን ውጦ በዝግታ
ተራመደ:: ወደ ጳጳሱ መኝታ ቤት አመራ:: ወደ በሩ ሲጠጋ አለመቀርቀሩን ተመለከተ፡፡ «አባታችን በራቸውን ሳይቆልፉ ነው የሚተኙት» አለ በልቡ፡፡
ዣን ቫልዣ ጆሮውን አቅንቶ አዳመጠ፡፡ ድምፅ የሚሉት ነገር
የለም:: በሩን ከፈት አድርጎ ሲፈራ ሲቸር በጣቶቹ ጫፍ ቀስ ብሎ ገፋው::ጥንቃቄው ከድመት ይበልጣል:: በሩ ምንም ድምፅ ሳያሰማና ለመንቀሳቀሱ
እንኳን በሚያጠራጥር ሁኔታ በዝግታ በመገፋቱ ከመጀመሪያው ይበልጥ ጥቂት ከፈት አለ፡

ለጥቂት ጊዜ ከበሩ አጠገብ ቆም አለ፡፡ አሁን ግን በይበልጥ ድፍረቱ
ስለተሰባሰበለት ከቀድሞ በበለጠ ጉልበት በሩን ገፋ አደረገው:: በዚህ ጊዜ የበሩ ማያያገዥ የዛገ ብረት ረዘም ያለ የሚሰቀጥጥ ድምፅ አሰማ፡፡

ልቡ የተሰነጠቀ መሰለው:: እንደ እንጨት ደርቆ ከቆመበት ሐውልት
ይመስል ሳይንቀሳቀስ ለጥቂት ጊዜ ተገተረ:: ለመነቃነቅ አቅም አነሰው ድፍረትም አልነበረውም:: ጥቂት ደቂቃዎች አለፉ:: በሩ ወለል ብሎ ተከፍቷል:: ወደ ክፍሉ ተመለከተ:: የተንቀሳቀሰ ነገር የለም:: አዳመጠ፤ የሚንቀሳቀስ ወይም ድምፅ የሚሰጥ ነገር አሁንም ከጆሮው ኣልገባም::
የበሩ ድምፅ ማንንም አልቀሰቀሰም ማለት ነው::

የመጀመሪያው አደጋ አለፈ:: ልቡ ግን በጣም ፈርቷል ፤ ሆኖም
አላወላወለም:: የፈለገውን ቶሎ ለመጨረስ ቁርጥ አሳብ አደረገ፡፡ በአንድ እርምጃ ከክፍለ ውስጥ ገባ፡፡ ክፍሉ ውስጥ ጸጥታ ሰፍኖበታል፡፡ ዣን ቫልገዣ ከወንበርና ጠረጴዛ ጋር እንዳይጋጭ እየተጠነቀቀ ወደፊት ተራመደ::ጳጳሱ ክፍለ ውስጥ ጥግ ይዘው ተኝተው በኃይል ሲተነፍሱ አዳመጠ፡፡በድንገት ቆም አለ:: ከጳጳሰ አልጋ አጠገብ ደርሷል፡፡

ቶሉ የደረሰ መሰለው::አንዳንድ ጊዜ ተፈጥሮ የምንሠራውን ሥራ ለማራገብ ከእኛ ጋር ታብራለች:: ለግማሽ ሰዓት ያህል ደመና ጨረቃን በመጋረድዋ አካባቢው
ጨልሞ ነበር፡፡ አሁን ግን ልክ እንደተማከረ ሰው ዣን ቫልዣ ከጳጳሱ አልጋ አጠገብ እንደቆመ ደመና ለጨረቃ ቦታዋን ለቀቀች:: የጨረቃ ብርሃን በመስኮት በኩል ዘልቆ በመግባት ከጳጳሱ የገረጣ ፊት ላይ አበራ:: ጭልጥ
አድርጎ እንቅልፍ ወስዷቸዋል። የሌሊቱ ብርድ ከባድ ስለነበር ወፈር ያለ የሌሊት ልብስ ለብሰው በጀርባቸው ተዘርረው ነው የተኙት፡፡ ስንት ደግ ሥራ የሠራው ታማኙና ነዳያን የሳሙት እጃቸው ካልጋው ጠርዝ አልፎ ወደመሬት ተንጠልጥሎአል፡፡ ሌላው እጃቸው ከደረታቸው ላይ በማረፉ
የጵጵስና ቀለበታቸው ያበራል፡፡ እዚያ ተጋድመው ሲያይዋቸው መላ አካላቸው የተስፋ ፣ የደስታና የእርካታ ማኅደር እንደሆነ ይናገራል:: በቃላት ለመግለጽ የሚያዳግት የማይታይ ብርሃን ከግንባራቸው ላይ አርፎአል፡፡

የጨረቃው በሰማይ ላይ መንጣለል፤ የምድር በከፊል የተኛች መምሰል ፤ የግቢው አትክልት እርጭ ማለትና የቤቱና የዚያች ሰዓት ፀጥታ እኚህ መለኮት የቀረባቸውን ሰው «አክብሩ አትድፈሯቸው» የሚያሰኝ
ነበር፡፡ ዓይናቸውን ጨፍነው እንደተኙ የነበራቸው ግርማ ሞገስና ለተስፋ ምንጭ የሆነውና በጨርቅ ያልተሽፈነው ግንባራቸው ሲያዩት በፍርሃት የሚያርበደብድ ነበር፡፡
👍191