አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
566 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ምንትዋብ


#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ


....“ጉድ! ጉድ!” አለ፣ ወይዘሮ ጌጤነሽ ሳይቀደሙ ለመቅደም። ቆመው እጅና እግራቸውን በእርጥብ እጃቸው ያባብሳሉ።

ባላምባራስ ዝም አሉ።
ወይዘሮ ጌጤነሽ ባላቸው፣ “ምንድርነው?” ሳይሏቸው በመቅረታቸው ቅር ተሰኙ። ወሬውን ለማውራት የነበራቸውን ጉጉት ስለአመከኑባቸው
ወሽመጣቸው ተቆረጠ። የባላቸውን ዝምታ አሰቡና ነገሩ ከነከናቸው።.

“ምንድርነውም አይሉ?” አሏቸው፣ የጎሪጥ እያይዋቸው።
“የትም አምሽተሽ መተሽ ደሞ ጉድ ትያለሽ?” አሉ፣ ባላምባራስ።

“ነገረኛ፣ ታሞ አይተኛ አሉ” አሉ፣ ወይዘሮ ጌጤነሽ፣ ድምፃቸውን
ዝቅ አድርገው።

“ምን አልሽ?”

“ምን እላለሁ ሳናግርዎ መልስ አይሰጡም ወይ ነው ያልሁት። ሌላ ምን እላለሁ?” አሉ፣ ራት ለመሥራት ምድጃ ላይ ድስት የጣደችውን የቤት አገልጋይ እያዩ።

“ሚሰማሽ ካገኘሽ ምላስሽ ረዥም ነው።”

“ኸርሶ አይበልጥ” አሉ፣ አሁንም ቀስ ብለው።

ባላምባራስ ቆጣ ብለው፣ “ምን አልሽ?” ካሉ በኋላ፣ ጉድ ከሰሙ
ስለ ሰነበቱ ጉዱን የመስማት ፍላጎት አደረባቸው። ቁጣቸውን ገታ አድርገው፣ “እና ምንድርነው ጉዱ?” አሉ፣ ለጠጥ ብለው እምብዛም ለወሬ የጓጉ እንዳይመስሉ።

ወይዘሮ ጌጤነሽ እንዳልሰማ ዝም አሉ፤ እንደ ማኩረፍ አድርጓቸዋል።

“ምንድርነው ጉዱ አልሁሽ እኮ” አሉ ባላምባራስ፣ ቆጣ ብለው።

ወይዘሮ ጌጤነሽ አሁንም ያልሰሙ መሰሉ።

“ሳናግርሽ መልስ 'ማሰጪ?” የባላምባራስ ቁጣ እየተጋጋለ ነው።

“ምን አሉኝ?” አሉ ወይዘሮ ጌጤነሽ። ፊታቸው ላይ ስስ ፈገግታ ይነበባል። ዛሬ አነስተኛ ቢሆንም ባላቸው ላይ ድል ተቀዳጅተዋል።

እነዚህን መሳይ ጥቃቅን ድሎች ናቸው አንዳንዴ ባላቸውን ያሸነፉ
እንዲመስላቸው የሚያደርጓቸው።

“ጉድ እያልሽ ገባሽ። ምንድርነው ብልሽ አለመጥሽ።” አሁንም
ድምፃቸው ገኗል፣ ባላምባራስ ሁነኝ።

“አልሰማሁ ሁኜ ነው” አሉ፣ ወይዘሮ ጌጤነሽ። የባላቸው ቁጣ
የሚገነፍልበትን አፍታ ስለሚያውቁ ያገኙትን ድል እያጣጣሙ፣
“የግራማች ልዥ ...” ሲሉ ጀመሩ።

“ግራማች?” ሲሉ አቋረጧቸው፣ ባላምባራስ። ወሬውን ለመስማት
ቸኩለዋል።

“ግራማች መንበር ናቸዋ።”

“ኸሷው ጋር ስታወሪ እንደቆየሽ አውቄያለሁ። ወልደልዑል ምንን
ሆነ?”

“ሴቷ ወለቴ።”

ጥላዬ፣ የሆነ ነገር እንዳለ ደመነፍሱ ነገረው። ነፍሱ ከዳችው። ጉዱን ለመስማት ቤት ውስጥ መግባት ፈልጎ፣ ወገቡ አልታዘዝ፣ ጉልበቱ አልንቀሳቀስ አለው። እንደምንም ብሎ ተነስቶ ውስጥ ገብቶ መደብ
ላይ ተቀመጠ።

ባላምባራስ በመገረም ተመለከቱት። እሳቸው ሳይተኙ ቤት ውስጥ ስለማይገባ፣ ዐይኑን ካዩት ከርመዋል። ሆዳቸው ተገላበጠ።

“እና ምንን ሆነች?” አሉ፣ መባባታቸው እንዳይታወቅባቸው
እየታገሉ።

ወይዘሮ ጌጤነሽ ከመናገር ተቆጠቡ። ጥላዬን ሰረቅ አድረገው አዩት።እሱ የሚሉትን ለመስማት ቢጓጓም ጎንበስ ብሎ መሬቱን በስንጥር መጫጫር ጀመረ።

“ዛሬ ምንን ነክቶሻል? ምንን ሆነች ስልሽ መልስ ማሰጪ?”

“በያ ሰሞን ንዳድ ይዟቸው ኸነሱ ዘንድ ተኝተው የነበሩት ለካስ
ንጉሡ ኑረዋል...”
“ንጉሠ?”
“አዎ።”
“አጤ በካፋ?”
“እሳቸው። ሌላ ንጉሥ አለ?”
“ምንድርነው ምታወሪው?” አሉ ባላምባራስ፣ የሚስታቸውን ትንኮሳ
ችላ ብለው።
መንን
“አጤ በካፋ ራሳቸው። ወለቴ አስታማቸው ስታበቃ ዛሬ ሰዎች
ኸጥሎሽ ጋር ሰደዱ።”
“ሊያገቧት?”
“ኋላ?”
ጥላዬ ዱብ ዕዳ ሆነበት፣ ድንጋጤ ሰውነቱን አብረከረከው። ተነስቶ
ሊወጣ ፈልጎ ወሬ ለመስማት ተቀመጠ።

“ሰው ለማንጓጠጥ ማን ብሎሽ። ወረኛ! ደሞ ማታመጪው የለ” አሉ
ባላምባራስ፣ ተደናግጠዋል፣ ንዴትም ተናንቋቸዋል።
“እንዴት በሉ? ምን ያልሆነ አምጥቸ አውቃለሁ? ኸመሽ አገር ሁሉ ሚያወራው እኼንኑ ማዶል? የጣ ፈንታ ነገር ይገርማል።”

“ውነት ነው፤ ዕጣ ፈንታ ነው” አለ ጥላዬ፣ የሞት ሞቱን። ሰውነቱ
እየራደ ነው። ለራሱ፣ እኔ ዕድል ፈንታየ ሁኖ ያልታደልሁ ሁኘ
የወፍታው እኼን አሰማኝ ብሎ በዐይኑ ውሃ ሞላ። እንባው እንዳይታይበት እደጅ ሲወጣ፣ አባቱ በዐይናቸው ተከተሉት።

“ያቺ አያትየው ኸደብተሮቹ ነው ውሎዋ። ኸተኙበት ቀባብታቸው
ይሆናል ይላል ድፍን ቋራ” አሉ ወይዘሮ ጌጤነሽ፣ አገልጋይዋ ራት
እንድታቀርብ በእጃቸው ምልክት እይሰጡ።

“ድፍን ቋራ ኸምኔው ሰምቶ ነው እኼን ሁሉ ሚለው? አንቺና
ጓደኞችሽ ጓሮ ሁናችሁ ያቦካችሁት ነው እንጂ። ለነገሩ ልዥቱ
ምንም አይወጣላት። ደማም... ቆፍጣና... ይገባታል፤ ይገባታል ::
ሚገባትን ነው ያገኘች። እኔ ለተክለሃይማኖት ተዋጋህ እየተባልሁ ስወቀስ የተክለሃይማኖትን ወንድም በካፋን አገባች?” አሉ ባላምባራስ፣
በመገረም ራሳቸውን እየነቀነቁ።

አገባች! እርምዎን ያውጡ እንግዲህ! በርሶው አጓጉል ጠባይ ነው እኼ ሁሉ የመጣው። እርስዎንስ ይበልዎ፣ ልጄን ጎዱብኝ እንጂ አሉ ወይዘሮ ጌጤነሽ፤ ለራሳቸው። ጮክ ብለው ሊናገሩ ፈለጉና በማታ ኸሳቸው ጋር ምን አጫጫኸኝ ብለው፣ “ኸቤታቸው ንግርት አለ ይባላል። ዘመዳቸው የሆነ ሰው ኸወለቴ ግንባር ጠሐይ ስትወጣ አይቷል” አሉ።
ባላምባራስ መልስ አልሰጧቸውም። ቁጭት ላይ ናቸው። ልዥህን ለልዤ ስባባል ቆይቶ፣ በትንሽ ነገር ኸጥብቅ ወዳጄ ተቀያይሜ፣ አሁን
እኼው ሌላ...ያውም ንጉሥ ወሰዳት። እንግዲህ ኸንጉሥ መንጋጋ አላስጥላት! ያቺ ቀን እንዴት ያለች የተረገመች ናት አሉ፣ ግራዝማች መንበርን የተቀየሙበትን ቀን አስታውሰው።

የጊዮርጊስ ማኅበር ነው። ግራዝማች መንበር ቤት ይበላል፤ ይጠጣል። ጨዋታው ደምቆ፣ እንደወትሮው ስለ ጦር ሜዳ ጀግንነት ይወሳል። ባላምባራስ ሁነኝ ራሳቸውን እንደ ጀግና ቢቆጥሩም፣ ስለ ጦር ሜዳ
ሲወራ አይወዱም።ከዚህ በፊት ሰድበውት የሚያውቁት ደብተራ ሞቅ ብሎታል። “አሁን በወፍታው ኸጦር ሜዳ ቋንጃውን የተመታ ዠግና ይባላል?” ብሎ በሳቅ
ተንተከተከ።

ማንም አልሳቀ። ሁሉም አንገቱን ደፋ። ሳቅና ቁም ነገር የሰፈነበት
ስብስብ ወደ መሸማቀቅ ተለወጠ።

ደብተራው የሳቀለት ሲጠፋ፣ “እኛ ባገራችን ምናቀው ሰው ቋንጃውን
ሚመታው ሲሸሽ ነው” አለ፣ የፌዝ ሳቅ እየሳቀ።
ባላምባራስ ከዓመታት በፊት ቋንጃቸውን ተመትተው ያነክሳሉና
እሳቸውን ሊነካ መሆኑን አውቀው ከተቀመጡበት ተነሥተው
ከዘራቸውን እየወዘወዙ፣ “አንት መተተኛ ደብተራ። እኔ ሁነኝ በንዳንተ ያለ ድግምተኛ አልሽረደድም። የት አባህ ጦር ሜዳ ውለህ ታውቃለህና
ስለ ጦር ሜዳ ታወራለህ? ጋን እያሸተትህ ኸድግስ ድግስ ዙር እንጂ።

ጥፋተኛው አንተ ሳትሆን አንተን ኸሰው መኻል የቀላቀለህ ነው” ብለው ከዘራቸውን ግራዝማች መንበር ላይ እየወዘወዙ፣ “መንበር አሰደብኸኝ ...
ያውም በዝህ በድውይ። ግድ የለም። እንዲህ ኻሰደብኸኝ ወዲያ እመቃብሬ እንዳትቆም... ኸዚህ ያላችሁ ሁሉ ቃሌን ቃል እንድትሉ”
ብለው እያነከሱ ወጡ።
ከዚያን ቀን ጀምሮ የግራዝማችና የባላምባራስ የረጅም ዘመን ጓደኝነት አከተመ፣ አብሮም የጥላዬና የወለተጊዮርጊስ ዕጮኛነት። ባላምባራስ፣
“በቤቱ አሰደበኝ” ብለው ቂም ያዙ። ግራዝማች፣ “ደብተራው ለሰደበው እኔ ምን አረግሁ?” ብለው ቅር ተሰኙ። አስታራቂ መሃከላቸው ቢገባ ባላምባራስ፣ “ሙቼ ነው ቁሜ ኸሱ ጋር ምታረቅ” አሉ። “ልዥህን
ለልጄ” የተባባሉት ጓደኛሞች ተቀያየሙ።

ግራዝማች መንበር፣ ሁነኝ ምንም ቢሆን የረጅም ጊዜ ወዳጄ ነውና
አንድ ቀን እንታረቅ ይሆናል እያሉ የወለተጊዮርጊስን እጅ ለጠየቀ ሁሉ አይሆንም እያሉ መለሱ።
👍15
#ትኩሳት


#ክፍል_አምስት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

...ካንድ ስምንት ቀን በኋላ፣ ማታ ተመስገን ክፍል ቁጭ ብዬ
ስስራ፣ ተመስገን መጣና አልጋው ላይ ዘጭ ብሉ ተጋደመ፡፡ እፎይ!
ብሎ ተነፈሰ
«ሲኒማ የገባችሁ መስሉኝ» አልኩት
«ሌሎቹ ገቡ፣ እኔ ግን ተውኩት»
«ለምን ተውከው?» አልኩት። ድምፄ «አንተ ተንኮለኛ!»
እንደሚል አይነት ነበር
«ደስ አላለኝማ!» አለኝ፡፡ ትንንሽ አይኖቹ ሊደበቁ ጀምረዋል፣
ግን ጥርሶቹ ገና መታየት አልጀመሩም
«ውሸታም! ቀጠሮ ቢኖርህ ነው እንጂ» አልኩት
«ከማን ጋር?»
«እኔ አውቃለሁ እንዴ ያንተን ተንኮል? ወይ ካንዷ ብሎንድ
(ፀጉሯ ብጫ ወይም ነጭ ብጤ) ጋር፣ ወይ ከሲልቪ ጋር»
«ሲልቪ!? አላወቅክምና!»
«ምን?»
«ቀርቶ!»
«ምነዋ?»
«ምን እባክህ የሴት ነገር» አለ «አገር ጤና ብዬ እንደ ሁልጊዜያችን ወዲህ አመጣሁዋት፡፡ ከሰአት በኋላ ነበር። የከሰአት በኋላው እንዴት እንደሚጣፍጥ ታውቅ የለ? ልብሷን አወላለቀችና
አልጋው ውስጥ ገባች። እየተንገበገብኩ ተከትያት ልገባ ስል፣
ከትራሱ ላይ ኣንዲት ፀጉር እንስታ አቀበለችኝ። ረዥም የፈረንጅ
ፀጉር ነው፤ ግን ጥቁር አይደለም፣ ቡና አይነት ነው»
«ይሄ የኔ ፀጉር እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ አለችኝ»
«ዝም ኣልኩ። አልገባኝም አየህ
«ተናገር እንጂ» አለችኝ። እግዜር ያሳይህ፡፡ በመጀመሪያ
አልጋው ውስጥ ልገባ ጎምበስ እንዳልኩ ኣሁንም አለሁ፡፡ ይታይሀል? ራቁቴን አልጋው ላይ ባራት እግሬ ቆሜ? እንደሚድህ ልጅ:: ልብሷን ስታወልቅ እያየሁና የሚጠብቀኝን ደስታ እያሰብኩ ግትር አድርጎ ቅንዝር ወጥሮኛል፡፡»

የተመስገን አይኖች ጨርሰው ጠፉ፣ ጥርሶቹ ተገለጡ፣ ይሰቅ
ጀመር፡፡ ከት ብሎ እየሳቀ፣ ሳቅ በሚቆራርጠው ንግግር
ገና አሁን ታየኝ ሀ! ሀ! ሀ! እንዴት እንዴት - ሀ! ሀ! U! እንዴት እንደነበርኩ ሁ! ሁ! ሁ! አንዲህ ነበርኩ» አለና በጀርባው ከተጋደመበት ተነስቶ ዞሮ በጉልበቱና በእጁ ተንበረከከ፡፡
ከስሩ ትራሱን አስተካከለና፣ ሌባ ጣቱን እያነጣጠረበት

«እኔ እንዲሀ ነኝ፣ ሂሂ!!» ትራሱን «እቺ ሲልቪ ናት።
ያቀበለችኝን ፀጉር ባንድ እጄ እንደዚህ ይዣለሁ። እንዳትበጠስ
ወይም ወድቃ እንዳትጠፋ እየተጠነቀቅኩ፣ ያቺን ነጃሳ ፀጉር እንዲህ ይዣለሁ። ቁላዬ ደሞ እዚህ ጋ ቆሞ ሲልቪን ቁልቁል ያያታል።አይ የኔ ቁላ! ቂል ነውኮ፡፡ ያንተም ቂል ነው?» እንደገና ሳቅ
አሸነፈው። አልጋው ላይ ተንከባለለ። ሳቁ ሲያልፍለት

«በኋላስ?» አልኩት

«በኋላማ ምን ልበልህ ልጄ? ቃል ሳትናገር ተነስታ ልብሷን
መልሳ ለበሰች፡፡ ረጋ ባለ ድምፅ 'የኔና ያንተ ነገር በዚሁ አለቀ”
ብላኝ ልትወጣ ስትል፣ እኔ እዚች ጋ ራቁቴን እንደቆምኩ
«ምን ነካሽ?» አልኳት፡፡ ሲያቀብጠኝ'ኮ ነው:: እስቲ ዝም ብላትስ?
«ዘወር አለችና፣ እሱ ጠረጴዛ ላይ ያለውን መፃህፍትና ደብተር
በአጇ አንዴ ገፍታ መሬት ላይ አዝረከረከችው:: እና ጠረጴዛውን
በተጨበጠ እጇ ደጋግማ እየመታች

«እኔ የእስላም ሀሪም ሴት - አይደለሁም!» ብላኝ ስታበቃ፣ ወጥታ በሩን በሀይል ጓ! አርጋው ሄደች። ልብሴን ልለብስ
ካናቴራዬን ሳነሳ በሩ ብርግድ ብሎ ተከፈተ። ማን ገባ መሰለህ?»
አለኝ

«ማን?» አልኩት

«ሲልቪ ራሷ ነቻ! የሴት ነገር! ከመቼው ሀሳቧን ለወጠች?!
እያልኩ ልገረም ስጀምር፣ ኣጠገቤ መጣች። አቅፋ ልትስመኝ
እንደሆነ ገባኝ፡፡ ትንሽ ልኮራባት አሰብኩ። ታድያ እሷ ምን አረገች
መሰለህ? እወቅ : ስቲ።»
«በጥፊ መታችህ?»
«ብጭራሽ!»
«አቅፋ ሳመችህ?»
«ትቀልዳለህ?»
«እንግዲያው ምን አረገች?» አልኩት
«ጫማዋን አረገች»
«ምን?»
«በንዴት ጫማዋን ረስታው ሄዳ ነበር፡፡ ተመልሳ አረገችውና
ወጣች። እኔ ራቁቴን ቆሜ ቀረሁ፡፡ ቁላዬ እስካሁን ተኝቷል፡፡ ከዚያ
በኋላ አናግራኝ አታውቅም»
«ጥፋቱ ያንተ ነው» አልኩት
«እንዴት?» አለኝ
«ያመጣሀቸው ሴቶች ሊሄዱ ሲሉ «ፀጉሮችሽን ሁሉ ይዘሻል?
ቁጠሪ እስቲ ለምን አትላቸውም?» አልኩት
«መቼ ሴት አመጣሁና?» አለኝ
«እ-ህ? ቡናማው ፀጉርሳ?»
«ከየት እንደመጣ እንጃለት:: ምናልባት ቤት የምትጠርገው
አልጋ የምታነጥፈው አሮጊት ያን እለት ታማ ኖሮ፣ በሷ ምትክ
ባለቡናማ ፀጉር ሴት አልጋዬን አንጥፋልኝ ይሆናል»
«ምስኪን ተመስገን!» አልኩት
ምስኪን ትላለህ ምስኪን። ይኸው እስከዛሬ ዖም ላይ እገኛለሁ
«ዛሬ ማታ ግን ለመግደፍ ያሰብክ ትመስላለህ»
«ነበር እባክህን። ፀጉሯን እንደ ወንድ ነው 'ምትቆርጠው፣
ቢሆንም ምንም አትል። ብቻ »
«ብቻ ምን?»
«የት እንደምወስዳት ጨንቆኛል»
ሲመሽ ፈረንሳዮች concierge
የሚሉት ዘበኛ ይመጣና' ወደመኝታ ቤቶቹ የሚያስገባው በር አጠገብ አንዲት ቢሮ አለችው፣ እዚያች ቁጭ ብሉ ወጪ ገቢውን ሁሉ ይመለከታል። ወንዶች መኝታ ቤት ሴት ማስገባት ክልክል ነው፡፡)

«የኔ ሆቴል አለልህ አይደለም እንዴ?» አልኩት
«አትጠቀምበትም?»
«እዚህ ልተኛ እችላለሁ»
እሱማ ጥሩ ነበር»
“ብቻ እንዳታስጮሀት አደራ፡፡ ካስጮህካትም ፎጣ አጉርሳት።
ብዬ የሆቴሌን ቁልፍ ሰጠሁት
ተመስገን ወደ ቀጠሮው ከሄደ በኋላ ተመልሼ ልስራ
በጠበጠኝ። ተነስቼ አሜሪካዊቷ ቤት ሄድኩ፡፡ ጉዳዬን አስረዳኋት።
አልቻልኩም፡፡ ሲልቪ ለኔ ስትል እንደተወችው ገባኝ፡፡ ይህ ሀሳብ
ከዚህ በፊት አገሬ እጮኛ አለችኝ ብያት ነበር፡፡ አሁን፣ እጮኛዬ
ካንቺ ጋር ያለኝን ግንኙነት አወቀች፡፡ ማን እንደነገራት እንጃ፡
ወረቀት ፃፈችልኝ። በአንድ ሳምንት ውስጥ ኣሜሪካንህን ትተሀታል
የሚል ወሬ ካልደረሰኝ ሌላ እኛ ፈልግ አለችኝ፣ ብዬ ነገርኳት።
«i derstand የዚህ መጥፎ ዜና ምክንያት በመሆኔ በጣም
አዝናለሁ» አለችኝ። ያቀድኩት ይህን ነግሬያት ደህና እደሪ ብያት
ሲልቪን ፍለጋ ለመሄድ ነበር። ግን ልጅቱ ጥቁር ስስ የሌሊት ልብስ
ለብሳ ስትራመድ በጣም ታስጎመጃለች፣ ገላዋን ታጥባ ቆዳዋን በታልከም ዱቄት አሻሽታው፣ ሽታው ይማርካል፡፡ ከሷ ጋር አደርኩ
«ራሷን በጣም ታዘብኩት። በጣም ፀፀት ተሰማኝ፣ ሲልቪን
የበደልኳት መሰለኝ»
በነጋታው ሲልቪን ከምግብ ቤት ስትወጣ ጠብቄ ኣገኘኋት።
ቡና ልጋብዝሽ አልኳት። ኤክስ ውስጥ የምወደው ካፌ የለኝም
አልኩህ? አለችኝ፣ እሺ ማርሰይ ልውሰድሽ አልኳት። መኪናዬ
ጋራዥ ናት አለችኝ፡፡ በኦቶቡስ ልውሰድሽ አልኳት። አልፈልግም
አለችኝ። እንግዲያው ምን እናርግ? አልኳት፡፡ እኔ ቡና ላጠጣህ፣ራሴ አፍልቼ፣ አለችኝ፡፡ ቤቷ ወሰደችኝ፣ ከኤክስ ትንሽ ወጣ ብሎ ባላገሩ ውስጥ ነው

«የሴዛን የነበረው ቤት በዚህ በኩል ነው። መሄድ ትፈልጋለህ?»
አለችኝ
«አልፈልግም» አልኳት
«እኔም ሄጀ አላውቅም» አለችኝ
እየሳቅኩ «Tut'en fous, ch?» አልኳት («ደንታ የለሽም፣ እ?»)
እየሳቀች፣ «Je m'en fous eperdument!» አለችኝ («እቺን ያህል እንኳ ደንታ የለኝም»)
ቤቷ ገባን። ሁለት ክፍል (አንድ መኝታ፣ አንድ ሳሎን) ወጥ
ቤት፣ መታጠቢያ ክፍል። በየግድግዳው የልዩ ልዩ አቢይ ስእሎች እትም ተለጥፏል። የቤት እቃው ዘመናዊ ነው፣ ሰማያዊና ወይን ጠጅ ቀለማት ይበዙበታል
👍25