አትሮኖስ
282K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
490 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አስር


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


....ዲላ ሆስፒታል ውስጥ አንድ አነጋጋሪ የሆነ ክስተት ተፈጠረ፡፡ ሰበቡ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከየጤና ተቋማቱ ነርሶች አወዳድሮ ከሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ጀምሮ በጤና መኮንንነት ለማሰልጠን ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ዲላ
ሆስፒታል የተመረጠውን ነርስ የማውቅ ውጤት ነው፡፡ የመወዳደሪያው ዋንኛ
መስፈርት የአገልግሎት ዘመን ሲሆን በማስታወቂያው ላይ የተጠየቀው አነስተኛ
የአገልግሎት ዘመን አምስት ዓመት ሆኖ ሳለ የተመረጠው ነርስ ግን ሦስት ዓመት እኳ ያልሞላው ሆኖ ተገኘ፡፡ ይህ ሁኔታ እንኳንስ መስፈርቱን የሚያሟሉ ነርሶችን
ውድድሩ የማይመለከታቸውንም የሆስፒታሉ ሠራተኞች ሁሉ ክፉኛ አስቆጫቸው።

ተመራጩ ነርስ የውድድሩን መስፈርት ካለማሟላቱም በላይ በሆስፒታሉ ውስጥ የሙያ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ቀናት እንኳ እጅግ የተወሰኑ ነበሩ።
በአውራጃው የወጣቶች ማህበር ዕህፈት ቤት ውስጥ የአንድ ዘርፍ ሃላፊ በመሆኑ በመደበኛ ስራው ላይ አዘውትሮ አይገኝም። ከጤና ባለሙያነቱ ይልቅ ፖለቲከኛነቱ
ያመዝናል። ከዚሁ ማንነቱ የተነሳ በሠራተኞቹ ዘንድ አይወደድም፡፡ ጆሮ የሚል ቅጽል ስም ወጥቶለት ሰዎች ሁሉ ይሸሹታል። እሱ ባለበት ቦታ ወሬ አይሞከርም፡፡
እንዲያውም ወደ ሆስፒታሉ ብቅ ባይል የብዙ ሠራተኞች ፍላጎት ነው፡፡ ዛሬ ለከፍተኛ የሙያ ስልጠና የተመረጠበት ሁኔታ ቢያስቆጫቸውም በዚህ ሰበብ
ከመሀላቸው በመውጣቱ የተደሰቱም አይጠፉም።

ለአስቻለው ግን ይህ አይዋጥለትም፡፡ ጆሮ ለሁለትና ለሦስት ዓመታት ከአካባቢው ገለል ቢልም ኮርሱን ሲጨርስ ይበልጥ አብጦ እና ተኮፍሶ መመለሱ እንደማይቀር ይገነዘባል። የእሱ ጭንቀት ጆሮ በማይመለከተው ውድድር ውስጥ
ገብቶ ጭራሽ አሽናፊ የሆነበት ሁኔታ ነው፡፡ ፍላጎቱም የራሱን መብትና ጥቅም ለማስከበር መንቀሳቀስ ነው:: ይህን ጥረት ለብቻው ከማድረግ ይልቅ እንደ እሱ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ለማስተባበር ምክሮ ነበር፤ ነገር ግን አልተሳካለትም፡፡ሁሉም የሰጡት ምላሽ ማን ሊሰማኝ? ምን ለውጥ ሊመጣ? ምን ህግ አለና?...ወዘተ የሚሉ ተስፋ አስቆራጭ ቃላቶችን ነበር፡፡

ይህ ዓይነቱ የሰዎች አመለካከት የአስቻለው የዘወትር ራስ ምታቱ ነው። ገዢዎች በህዝብ ላይ ከሚፈጽሙት ግፍና በደል የበለጠ የዜጎች ልበ ሙትነት ያበሳጨዋል፡፡ መብትና ጥቅምን በፈቃደኝነት አሳልፎ የመስጠት ጅልነት
ያንገበግበዋል። አሁን ሲቆሏት ኋላ እንደሚቆረጥሟት እንደማታውቅ ጥሬ መብቱ ሲረገጥ፣ ጥቅሙ ሲጨፈለቅ ዝም ብሎ የሚመለከት ሰው አንጀቱን ያቆስለዋል።ሰው እንዴት ሰሚ በሌለበት፣ ህግ በማይከበርበት፣ ግፍና በደል በተንሰራፋበት፣
አድሎና ጭቆና በነገሰበት፥ አቤት ቢባል ፍትህ በማይጎኝበት ሥርዓት ውስጥ ለመኖር ፈቃደኛ ይሆናል? በዚህ ሁኔታ ውስጥ እየኖረስ እንዴት ስው ነኝ ብሎ
ያስባል? ይላል ዘውትር። ምንም እንኳ ሰውን ሁሉ ለዚህ ዓይነቱ የአመለካከትና የአስተሳሰብ ዝቅጠት ያበቃውን ታሪካዊ መነሻ የሚያውቀው ቢሆንም ግን እስከ
መቼ? ለሚል ጥያቄ መልስ እያጣ በእጅጉ ያዝናል፣ ይበሳጫል፡፡

ያም ሆኖ አስቻለው ወትሮም እንደሚያደርገው ሁሉ የበኩሉን ድርሻ ከመወጣት ወደ ኋላ አላለም። በዕለተ ሐሙስ ከጠዋቱ አንድ ሠዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ ዘጠኝ ሠዓት ባለው ፈረቃ ስራውን ሲያከናውን ውሎ ወዲያው ወደ ቤቱ መሄድ አልፈለገም፡፡ በቀጥታ ወደ ሆስፒታሉ የአስተዳደር አገልግሉት ሃላፊ ቢሮ አመራ፥ ወደ ባርናባስ። በሩን ከፈት አድርጎ ወደ ውስጥ አየት ሲያደርግ ባርናባስ
ወየሶ በጠረጴዛው ላይ አጎንብሶ ይጽፋል፡፡ አለባበሱ ያው የተለመደው ነው፡፡ በሩ ሲከፈት ሰምቶ ዞር ሲል አስቻለው የበሩን እጀታ እንደያዘ በር ላይ ቆሞ አየው፡፡

«አቤት!» አለው ዓይኑን በአስቻለው ላይ እንደተከለ፡፡
ላነጋግርህ ፈልጌ ነበር፡፡»
ባርናባስ ፈጥኖ መልስ አልሰጠውም። ለአፍታ ያህል መልከት ካለው በኋላ እጅግ በቀዘቀዘ ስሜት ትችላለህ» አለና በእጁ ወደ እንግዳ ወንበር አመለከተው፡፡አስቻለው ገባ። ከእንግዳ ወንበሮች መካከል አንዷን ሳብ አድርጎ ቁጭ አለና
ባርናባስን በጥርጣሬ ዓይን ያየው ጀመር።

«ምን ልርዳህ?» ሲል ጠየቀው ባርናባስ መነፅሩን አውልቆ ጠረጴዛ ላይ ቁጭ እያደረጉ፡፡
«ለእጩ ጤና መኮንንነት ኮርስ ውድድር ተመዝግቤ ነበር።»
«እህ!» አለው ባርናባስ በሾፍ አነጋገር።
«በውጤቱ አልተደሰትኩም!»
«ምን ጠብቀህ ነበር?»
«እመረጣለሁ ብዬ ነበራ!»
«እህ! ዝም ብሎ መመረጥ አለ እንዴ?»
«ዝም ብዬማ አይደለም፡፡ በወጣው ማስታወቂያ መሠረት ከሆነ በአገልግሎት እኔ እበልጣለሁ፡፡ እንዲያውም ሁለት ዓመት ትርፍ አለኝ:: የተመረጠው ነርስ ግን ጭራሽ ከመስፈርቱ አነስተኛ መነሻ እንኳ ለመድረስ ሁለት ዓመት እንደሚቀረው አውቃለሁ፡፡ ታዲያ እንዴት ዝም ብለህ ትለኛለሀ?» ሲል ግንባሩን ቋጠር አድርጎ ጠየቀው::
ለመሆኑ በማስታወቂያው ላይ የተጠየቀው መስፈርት የአገልግሎት ዘመን ብቻ ነው እንዴ?
«ልጥፎችማ አሉ፤ ነገር ግን ዋናው መስፈርት የአገልግሎት ዘመን መሆኑን ማስታወቂያው በግልጽ አስቀምጧል።»
«ልጣፍ ስትል?» አለና ባርናባስ ዓይኑን ፈጠጥ አደረገ፡፡
«በቃ! ልጣፎች ማለቴ ነው፤ ለፍርደ ገምድልነት ምክንያት የሚሆኑ እንጂ ዋናውን መስፈርት የማያሽሩ!»
ቀይ ፊቱ የባሰ ደም መምሰል ጀመረ::
ባርናባስም ዓይኑ ፈጠጠ።
አፍንጫው ነፋ ሞሸሽ አለ። ወደ ጠረጴዛው መለስ ብሎ እጆቹን አቆላልፎ ተደገፈና
“ጉልህ እብዮታዊ ተሳትፎ ያደረገ የሚለውን መስፈርት ማለትህ ነው?» ሲል አስቻለውን ጠየቀው።
«ያ ይኼ አላልኩም፡፡ ግን ከሙያው ጋር የማይሄዱትን በሙሉ ማለቴ ነው::» አለው አስቻለው እሱም ጠረጴዛውን እየተደገፈ፡፡
ሁለቱም ተፋጠጡ:: ዓይን ማን ይስበር? ማን ይስበር? በሚል የሚጠባበቁ ይመስላሉ። ባርናባስ እንደገና ወደ ኋላ ወንበሩን ተደግፎ በረጅሙ ተነፈሰና
«ለማንኛውም አንተና የተመረጠው ጓድ በምንም መንገድ አንድ ልትሆነ አትችሉም።» አለው፡፡
«ምን አገናኝቶን?» አለ አስቻለው ፈርጠም ባለ አነጋገር፡፡ «የኔስ ችግር ይኸ አይደል?» አለና ባርናባስን አከታትሉ ይመለከተው ጀመር።
«ታዲያ ይኸን ካወቅህ ሌላ ምን ፈለክ?»
«እኔ እያለሁ እሱ እንዴት ተመረጠ ብዬ ነዋ!»
«ባላችሁ ልዩነት ምክንያት
ውድድሩ እኮ ለባለሙያነት እንጂ ለካድሬነት አይደለም አቶ ባርናባስ»
ባርናባስ ድንገት ቁጥት አለና «ጓድ በል! ደሞ የምን አቶ ነው?» በማለት በአስቻለው ላይ አፈጠጠ፡፡
አስቻለው ሳያስበው ፈገግ አለና ረጋ ለስለስ ባለ አነጋገርን “ ጓድ የሚለው ቃል እኮ በዓላማና
በተግባራቸው የሚመሳሰሉ
ግለሰቦች የሚጠራሩበትና
የሚሞካሹበት ቃል ነው:: ታዲያ እኔና አንተ…» ብሎ ሳይጨርስ ባርናባስ አቋረጠው፡፡
«የመጣህበትን ጨርሰሃል?»
«አልጨረስኩም!»
«ምን ቀረህ ደግሞ?»
«አመራረጡ ትክክል ስላልሆነ እንደገና ይታይ ነው የምለው! በዚህ ላይ ያለህን ኣስተያየት ስጠኝና እንጨርስ።» አላ አስቻለው ፊቱ በብስጭት ልውጥውጥ እያለ።
«በቃ! ጓዱ ባበረከተውና እያበረከተ ባለው አብዮታዊ አስተዋጽኦ ምክንያት
👍31
#ምንትዋብ


#ክፍል_አስር


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

...እሷም አያቷም ታጥበው እንደተመለሱ፣ ራት በልተው በየክፍላቸው ገብተው ተኙ።
ወለተጊዮርጊስ፣ ጠዋት ከእንቅልፏ ስትነቃ የት እንዳለች ግራ ገባት።ቀስ በቀስ ጐንደር ቤተመንግሥት፣ እንግዳ ማረፊያ ክፍል ውስጥ መሆኗ ተገለጠላት። በመስኮቱ ቀዳዳዎች የገባውን ብርሃን አይታ ፀሐይ መውጣቷን አወቀች። አርፍዳ እንደነቃች ገባት፡፡ ምን ማድረግ እንዳለባት ግራ ገብቷት እዛው አረፍ ብላ ቆየች። ሲሰለቻት ተነስታ ስትወጣ፣ በር ላይ ቆመው የእሷን መውጣት የሚጠባበቁ ሁለት
ደንገጡሮች አያቷ ወዳሉበት ክፍል ወሰዷት።

አያቷ መስኮቱን ከፍተው አልጋው ላይ ጋደም ብለው የጸሎት
መጽሐፍ ያነባሉ። ስትገባ መጽሐፉን አስቀምጠው፣ “አድረሽ ነው? ሲሏት ደሕና ማደሯን ለመግለጽ እግራቸው ላይ ተጠመጠመች።በይ ተነሽ አሏት፣ ስሜታቸው ተነክቶ። ትንሽ እንደቆዩ ደንገጡሮቹ መጡላቸው። መፀዳጃ ቤት ወስደዋቸው ሲመለሱ ቁርስ አደረጉ።
ዮልያና ያረፉበት ክፍል ተመልሰው ስለ ምሳው ተወያዩ።

“ዛሬ እንግዲህ ኸጃንሆይ ጋር ማድ ምቀርቢበት ቀን ነው። እናም የነገርሁሽን ሁሉ ልብ እንድትይ። እንደገባሽ ኸደሽ በቅጡ አጎንብሰሽ እጅ ትነሽና እግር ትስሚያለሽ። ተቀመጭ እስቲለሽ ትጠብቂና ያመላከቱሽ ቦታ ኸደሽ ትቀመጫለሽ...”

የጀመሩትን ሳይጨርሱ ሁለት ደንገጡሮች በር ላይ ሆነው ለጥ ብለው እጅ ከነሱ በኋላ፣ አንደኛዋ፣ “እመቤቶቼ እንፋሎት እጥበት
እንኸዳ” አለቻቸው።

ወለተጊዮርጊስና አያቷ በደንገጡሮቹ ተከታይነት የአፄ ፋሲልንና የታላቁ ኢያሱን ቤተመንግሥታት ከኋላቸው ትተው ወደ ታች ወረዱ። የጻድቁ ዮሐንስን ቤተመዛግብት በግራ በኩል፣ ቤተመንግሥታቸውን
ወለተጊዮርጊስ በወሬ እንጂ በአካል አይታቸው የማታውቃቸውንና በስተቀኝ አልፈው፣ አንበሶቹ ቤትጋ ሲደርሱ አያቷ፣ “አንበሶች” ሲሉ ጠዋት ላይ ሲያገሱ የሰማቻቸውን አንበሶች ለማየት ቆም አለች። በአድናቆት ካስተዋለቻቸው በኋላ፣ከአንበሶቹ ቤት ጀርባ ያለውን የሣልሳዊ ዳዊትን የሙዚቃ አዳራሽ አሁንም በቀኝ በኩል ትተው ወደ ፊት አመሩ። ወለተጊዮርጊስ በየቤተመንግሥታቱ መተላለፊያ ላይ የተሰደሩት ወታደሮችና በየበሩ ላይ የቆሙት እልፍኝ አስከልካዮች
ቁጥር አስገረማት፣ ከእነሱ ጋር የመፋጠጥ ያህል ተሰማት። በመጨረሻም ቁመቱ አጠር ያለ ነገር ግን ሰፋ ያለ ግንብ ውስጥ ገቡ።

“እመቤቶቼ እኼ ንጉሦቹና እቴጌዎቹ እንፋሎት ሚገቡበት ነው” አለቻቸው፣ ከደንገጡሮቹ አንዷ ። ቀጥላም፣ “አጤ ፋሲል ናቸው ያሠሩት። እኼኛው የእቴጌዎቹ ነው። የንጉሦቹ በያኛው በኩል ነው።ልብሳችሁን ታወልቁና እነዝኸ መንጠቆዎች ላይ ትሰቅላላችሁ።ጌጦቻችሁን ደሞ እነዝኸ ውስጥ ታኖራላችሁ” አለቻቸው፣ ትንንሾቹን የድንጋይ ፉካዎች በሌባ ጣቷ እያመለከተቻቸው።

“በዝኸ በር ግቡና ኸነዛ ዳርና ዳር ያሉ መቀመጫዎች ላይ ተቀመጡ። ያ ሚጨሰው አረግ እሬሳና ጦስኝ ነው። እኛ ከውጭ ሁነን እንጠብቃለን” ብላቸው ከሌላዋ ደንገጡር ጋር ተያይዘው ወጡ።

ወለተጊዮርጊስና ዮልያና ጌጦቻቸውን አስቀምጠው፣ ልብሳቸውን አውልቀው የተባለው ክፍል ውስጥ አጎንብሰው ገብተው ተቀመጡ።ክፍሉ መሃል ላይ የተደረደሩት ድንጋዮች ሲግሉ፣ “አየሽ ያነን ምታይውን ወናፍ በዚያች በምታያት ቀዳዳ አሳልፈው፣ ኸውጭ ሁነው
ደንጊያዎቹን ያግላሉ” አሏት።

ድንጋዮቹ ሲግሉ፣ ከውጭ በቀርከሀ ዋሽንት ውሃ ድንጋዮቹ ላይ ፈሰሰ። ላብ አጠመቃቸው። እንደመታፈን ሲሉ ከጣሪያው ላይ ያሉት ትንንሽ ቀዳዳዎች ከውጭ ተከፈቱላቸው።

“አየር እንዲገባ ቀዳዳዎቹን ከፈቱልን። አለያማ ታፍነን እንሞት
ነበር” አሏት።

ቀዳዳዎቹ ተመልሰው ተዘጉ።

“እንፋሎት ተመልሶ እንዲመጣልን መልሰው ዘጉት” አለች፣ ነገሩ
የገባት ወለተጊዮርጊስ።

“እንዲህ አይሁን እንጂ እኛም እኮ በእንፋሎት መታጠብ እናውቃለን
አሉ፣ ዮልያና።

እሷ ይህን ዓይነቱን ነገር ከእሳቸው ቀርቶ ከማንም ጋር አድርጋው
ባለማወቋ እፍረቱ አላስቀምጥ አላት። ሰውነቷ እየተሟሟቀ ሲመጣ ግን ዘና አለች። ከፊቷና ከራሷ ላይ የሚፈልቀውን ላብ አስር ጊዜ ስትጠራርግ አዩና፣ “አይዞሽ አሁን ያነን ሁሉ የምንገድ ድካም ድራሹን ነው ሚያጠፋልሽ” አሏት።

ሲጨርሱ ወደ ገላ መታጠቢያው ክፍል ሄደው ዙርያውን የተከበበ
ገንዳ ውስጥ መጀመሪያ እሳቸው፣ ቀጥሎ እሷ ታጥበው የክት ልብሳቸውን ለብሰው ሲወጡ፣ ወለተጊዮርጊስ ከመቼውም ጊዜ በላይ አለምልማለች።

ዕረፍት እንዲያደርጉ ማረፊያ ክፍሎቻቸው ተወሰዱ።

ብዙም ሳይቆዩ ደንገጡሮቹ ለወለተጊዮርጊስ በእቅፋቸው ነጭ ረጅም የሐር ቀሚስ፣ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች ያጌጠ ጥቁር ካባ፣ የቆዳ ጫማ፣ ነጭ የሐር ሻሽና ከወርቅ የተሠሩ የአንገትና የጆሮ ጌጦች ይዘው መጡ። አንደኛዋ ታጥቦ የነበረውን ፀጉሯን ሾርባላት ሄዱ።ወለተጊዮርጊስ የመጣላትን ልብስ፣ ካባ፣ ሻሽ፣ ጫማና ጌጦች ግልጽ በሆነ አድናቆት አገላብጣ ስታይ፣ ጋደም ብለው የነበሩት አያቷ አይዋት።
በለጋ ዕድሜዋ እዚህ ደረጃ በመድረሷ ተደስተው እንባቸው ቀረር አለ። እንባቸው እንዳታይባቸው በነጠላቸው ተሸፍነው ፊታቸውን ወደ
ግድግዳው አዞሩ። ራሳቸውን አረጋግተው ነጠላቸውን ከፊታቸው ላይ ገለጥ አደረጉና ወደ እሷ ዞሩ። አሁንም የመጣላትን ዕቃ ታገላብጣለች።

“ጥሎሽ የመጣልሽም ኸዝኸ ይበልጥ እንጂ አይተናነስም። እሱን ልበሺ ስልሽ ለመንገድ አይሆንም ብለሽ የኔን ለበሽ። ለማንኛውም ጥሎሽ ይለቅ። አሁን እሱን አስቀምጭና ወደ ጃንሆይ ስትኸጂ እንዴት እንደሆነ አንዴ ተወጪልኝ” አሏት።
ልብሶቹን አልጋው ላይ በጥንቃቄ አኑራ፣ ክብ ዐይኖቿን ሰበር አድርጋ
በተመጠነ፣ ንግሥታዊ በሚመስል እርምጃ ወደ እሳቸው ስትጠጋ፣ “እኼ ነው የኔ ልዥ ። ያሳየሁሽን ሁሉ አረሳሽም። እንዲያውም አክለሽበታል” አሉና ጠጋ እንድትላቸው በእጃቸው ጠቆሟት። ተጠግታቸው
ስታጎነብስ፣ “እንዲህ ያለች ምሽት ኸየትም አያገኙ” ብለው ጉንጫን
መታ አደረጓት።

ቀና አለችና የእፍረት ሳቅ ሳቀች። “ስንት መልከ መልካም ወይዛዝርት
አለ በሚባልበት... ስንት የንጉሥ ዘር ባለበት አገር?” አለቻቸው።

በስጨት እንደማለት ብለው፣ “አንቺ ደሞ እንግዲህ ሰው ሚልሽን ስሚ አሉና ከተጋደሙበት ተነሥተው ተቀመጡ። ወገባቸውን በሁለት እጃቸው ይዘው፣ “የንጉሥ ዘር የሆነ ሁሉ መልክ አለው መሰለሽ? አንቺ ሁሉን አሟልቶ ሰቶሻል። ደሞ ጃንሆይ የንጉሥ ዘር ቢፈልጉ አጥተው? አንቺስ ብትሆኚ የንጉሥ ዘር ማዶለሽ? አንድ መኰንን አልገዛም ብሎ
ሲያውክ በጋብቻ ለማሰር፣ ጥቅም ለማስጠበቅ አሊያም ደሞ አመጥ
ለማብረድ ሲሉ መሰለሽ አንቺን ማግባት የፈለጉ? ወደውሽ ነው።
ትምርትም ቢሆን ዳዊት ደግመሻል። ጥፈትም ቢሆን ሚደርስብሽ የለ። የጐንደር ወይዛዝርት እኩሌታዎቹ ስንኳ ዳዊት አልደገሙም...
ይቅር ኻንቺ ሊተካከሉ... ኧረ እንዲያው ምንሽም አይደርሱ።”

“አየ እሚታዬ ልዥሽ ስለ ሆንኩ ነው እንደሱ ምትይው። ግና ኣንድ
ጥያቄ ልጠይቅሽ... ጃንሆይ ኸዝኸ በፊት አላገቡም ነበር እንዴ?”

“አግብተው ነበር እንጂ።”

“እህስ?”

“በእንዴት ያለ ወግ ተጋብተው እሷ የሠርጉ ምሽት እንደ ወጉ ግብር
አብልታ፣ እህል ውሃ ስንኳ ሳትቀምስ በጥኑ ታማ በበነጋው ሞተች።እደብረብርሃን ሥላሤ ነው የተቀበረች፤ ኸዛው እናታቸው ኻሉበት። መርዝ ነው ይላሉ። እንዴት ያለች አለላና ብርቱ ሴት ነበረች አሉ። ደማምና ብርቱ ይሆናቸዋል።”

“እንዴ?” አለች ወለተጊዮርጊስ፣ ሰውነቷን ያልታወቀ ነገር ወረር
አድርጓት። ተነስታ ቆመች። “እኔስ ፈራሁ። እኔንስ በመርዝ ቢገሉኝ?"
👍171🔥1