አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
461 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


...«አስቻለው የሔዋን አባት መሆኑን ማን ነገረሽ አንቺ?» ስትል ጠየቀቻት።
«ነዋ! እንዴ ሆእ!» አለች ሕጻኗ አሁንም፡፡
ሸዋዬ የበለጠ ግራ ገባት፡፡ ህጻኗ ያለ አንድ መነሻ ያን ንግግር
እንዳልተናገረች ገመተች፡፡ ወይዘሮ ዘነቡንና ሰራተኛ'ቸውን አስበቻቸው፡፡ ለጊዜው
ግን «እንዴ! እንዴ.! እንዴ.! እያለች ቤቷን ከፍታ ገባች። አልጋዋ ላይ ቁጭ አለችና
«እንዴት ነው ይኸ ነገር? በማለት ቁና ቁና እየተነፈሰች ለረጂም ጊዜ ቆየች።
ሔዋን የገዛቻቸውን የወጥ ቅመማ ቅመሞች በዘንቢል ይዛ ወደ ቤት ስትገባ የሽዋዬ ዓይን ፈጥጦ አገኘችው፡፡ ሁኔታዋ አላማራትም'ና
«እት አበባ አለቻት ዘንቢሏን እንደያዘች ከፊቷ በመቆም። ሸዋዬ ግን ገልመጥጥ ከማድረግ በቀር ምላሽ ሳትሰጣት ቀረች::
«ምነው?» አለቻት ሔዋን አሁንም፡፡
«አትተይኝም? አለቻት ሽዋዬ ቁጣ በተቀላቀለበት አነጋገር፡፡ ወዲያው ወደ አልጋዋ በመውጣት አንሶላና ብርድ ልብስ ውስጥ ገብታ ሽፍንፍን ብላ ተኛች።
ሔዋን የእህቷ ሀኔታ ግራ አጋባት፡፡ በዚያው ልክ ፈራች፡፡ ድንጋጤም
ተሰማት፡፡ ወደ ጓዳ ገብታ ዘንቢሏን ከአስቀመጠች በኃላ ጓዳው በር በኩል አንገቷን ብቅ እያረገች የሸዋዬን ሁኒታ ትከታተል ጀመር፡፡ አይታ አይታ ምንም ለውጥ
ልታገኝ ባለመቻሏ የምሣሤ ወጥ ስራዋን ጀመረች፡፡
ሽዋዬ ከተኛች ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀስቀስ ያለችው የወይዘሮ ዘነቡ የቀትር ቡና ሲወቀጥ ነው፡፡

ወትሮም ቢሆን በተለይ ቅዳሜና እሁድ ከምሳ በኋላ ለሚጠጣው ቡና ሽዋዬ ወደ ወይዘሮ ዘነቡ ቤት ትጠራ ነበር፡፡ ዛሬ ግን ገና ሳትጠራ ለመሄድ ብድግ አለች፡፡ ያቺ ህጻን በዚያ ቤት ውስጥ ሲወራ ያልሰማችውን ነገር
ከየትም ከምጥታ ልትነግራት እንዳልቻለች ገምታ የወሬዉን ምንጭ ከስሩ ለመጎርጎር ወስነኝ፡፡ ፒጃማ ዓይነት ጀወለል ቢጤ የቤት ልብስ እንደለበሰች ነጠላ
ጫማ አድርጋ ወደዚያው አመራች በጓሮ በኩል ወደ ሳሎን በሚያስገባው የወይዘሮ
ዘነቡ ቤት በር በኩል እየገባች፡-
ደህና ዋላችሁ» አላቻቸው፡፡
ወይዘሮ ዘነቡ ነጭ በነጭ የሆነ የሐገር ልብሳቸውን ለብሰው ሶፋ ላይ ጉብ ተብለዋል ፡፡ ቀይ ናቸው:: የአንገታቸው ንቅሳት ከቅላታቸው ጋር አለላ መስሎ ይታያል። የአገጭ ስር ጅማቶቻቸው ገተር ገተር ማለት የዕድሜያቸውን መግፋት ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ጥቁር መነፅራቸው ከቀይ ፊታቸው ጋር ደምቆ ሲታይ ዕድሜያቸውን ወደ ኋላ ለመመለስ የሚታገል ይመስላል፡፡ ኑሮአቸውን የቤታቸው
ሁኔታ ያመለክታል፡፡ በዘመናዊ ዕቃ የተሞላ ነው። የሳሎኑ ስፋት ፈረስ ያስጋልባል የሚባል ዓይነት ነው፡፡ በቡና ንግድ የናጠጡ ሀብታም የነበሩት ሟቹ ባለቤታቸው
ያደራጁላቸው ንብረት ነው።
‹ደህና ዋልሽ የኔ ልጅ!» አሉና ወይዘሮ ዘነቡ «ይኸውልሽ፣ የጎረቤት ደንቡ ይኸ ነው፡፡ ጥሪ የሚፈልግ ከሆነ ግን ንፉግነቱን ያመለክታል፡፡» እሷት ሸዋዬ
ሳትጠራ በመምጣቷ የተሰማቸውን ደስታ ለመግለጽ::
«አንዳንዴም ቀላዋጭ ያሰኛል!»
«እሱም የስስታም ሰው አባባል ነው፡፡ በእኛ ቤት ደሞ እንደዚያ ብሎ ነገር የለም፡፡ ለወደፊቱም ይልመድብሽ፡፡» ብለው ፊታቸውን ከሶፋው አጠገብ በነጭ ረኮበት ላይ ወደ ተደረደረው ሲኒ መለስ አደረጉ ሰራተኛቸው ፋንትዩ ቡናውን ጀበና ውስጥ እየጨመረት ናት፡፡
ጉዳይ ስላለኝም ነው ቀድም ብዬ የመጣሁት፡፡» አለች ሽዋዩ በወይዘሮ ዘነቡ ፊትለፊት ሶፋ ላይ ተቀምጣ ዓይን ዓይናቸውን እያየች፡፡
"ምነው" ድህና አሏት ወይዘሮ ዘነቡ ፊታቸውን ወደ ሽዋዩ መለስ
አድርገው
«ተቀይሜብዎታለሁ::»
«ውይ ነኔ ልጅ!ድንግል ትባርክሽ ቅያሜሽን ፊት ለፊት ተነገርሽኝማ
ድንግልም ትወድሻለች፡፡» አሉና «ግን ሳላውቅ ምን እጥፍቼ ይሆን ሲሉ አንገታቸውን ዘመም አድርገው እያዩ ጠየቋት።
«አንድ ነገር እያወቁ ደብቀውኛል።»
«ምን ይሆን የኔ ልጅ»
«በኔ ሰበብ ግቢዎት ሲደፈር እያዩ ዝም ማለትዎ!»
«ምን ያገባው ሰው ነው ግቢዩን የሚደፍረው?»
ብልግና ከተፈጸመበት ያው ተደፈረ ማለት አይደል?»
«የምን ብልግና?»
«አይዋሹኝ እማማ ዘነቡ!»
«ድንግል ትመስክር ምንም የምዋሽው ነገር የለም፡፡ ከንቺ ግን ምን ሰምተሸ ነው?» ሲሉ መነፅራቸውን ወለቅ አድርገው እያዩ ጠየቋት::
«ይቺ የኔ እህት ከዚያ አስቻለው ከሚባል ልጅ ጋር እየባለገች መሆኑን ሳያውቁ ቀርተው ነው?» ስትል ጠየቀቻቸው አንገቷን ጠመም አድርጋ በጎ አስተያየት እየተመለከተቻቸው::
«ውይ! ይኼ ነው እንዴ ነገሩ?» አሉና ወይዘሮ ዘነቡ ቀለል አድርገው
«ለመሆኑ አንቺ እስተ ዛሬ ምንም የምታውቂው ነገር አልነበረም?» ሲሉ ጠየቋት፡፡

«ምኑን?» አለች ሸዋዬ እንደ አዲስ፡፡ ነገሩ እርግጥ መሆኑ ሲገባት በድንጋጤ ሰውነቷ ሁሉ ክፍልፍል ያለ መሰላት።
«ስለ ሁለቱ ልጆች ፍቅር ነዋ!»
ምናልባት እኩያሞች ስለሆኑ ነው መሰል የእነሱን ፍቅር ልቤ
ይወደዋል፡፡»
«እማማ ዘነቡ!» ስትል ጮኸች ሸዋዬ ድንገት። ዓይኗ በወይዘሮ ዘነቡ ላይ ፍጥጥ አለና መላ ሰውነቷንም ያንቀጠቀጣት ጀመር።
«ወይ የኔ ልጅ!»
«ምን እያወሩ እንደሆነ ያውቃሉ?»
«ዘባርቄ ይሆን እንዴ ልጄን» አሉና ወይዘሮ ዘነቡ እውነትም ድንግጥ
ብለው ሽዋዬን ትኩር ብለው ያዩዋት ጀመር።
«ቀላል!»
«ምን አልኩኝ?»
«ሊያጋቧቸው እስበዋል እንዴ?»
«ኧረ ምን ቁርጥ አድርጎኝ ልጄ! ቢሆን አይከፋም ማለቴ ነው
እንጂ!»
ሸዋዬ ውስጧ ተቃጠለ፡፡ አረረች። በወይዘሮ ዘነቡ ሀሳብ ከመበሳጨቷ የተነሳ ያን ከሰል ላይ የተጣደ ጀበና ብድግ አድርጋ በመሀል እናታቸው ላይ
ብትከስክሰው እየተመኘች «የሚሉት ነገር ሁሉ ሊገባኝ አልቻለም!» አለቻቸው
ዓይኗን ፍጥጥ፣ ጥርሷን ግጥጥ አድርጋ እያየቻቸው፡፡
ግልጥልጥ አድርጌ እየነገርኩሽ! እንዴት እይገባሽም?» አሏት የሸዋዬ የወስጥ ስሜት ያልገባቸው ወይዘሮ ዘነቡ፡፡
«ቆይ ግን አለችና ሸዋዪ ንዴት ያወላከፈውን ጉሮሮዋን «እህህ» ብላ ሞረደችና የሁለቱን መፋቀር እንዴት አወቁ?» ስትል ጠየቀቻቸው፡፡
«ድንግል ምስክሬ ናት፤ በበኩሌ ክርና መርፌ ሆንሁ በዓይኔ አላየሁም፡፡ ግን መቸም ትንሽ ሳይያዝ ብዙ አይወራም ብዬ ነው፡፡» ብለው ፊታቸውን ወደ
ረከቦቱ መለስ አደረጉ፡፡
ወይዘሮ ዘነቡ አንድ ነገር በሆዳቸው አለ። አንድ ቀን አስቻለውና ሔዋን ተዘናግተው ሳይሆን አይቀርም በሩን መለስ እንኳ ሳያደርጉት ቆመው ሲሳሳሙ
ሰራተኛቸው ፋንዩ በበር በኩል አለፍ ስትል አይታቸው ኖሯል። ወይዘሮ ዘነቡ በአቅራቢያዋ ስለነበሩ ወደ ጆሮትእው ጠጋ ብላ በሽንሹክታ ዓይነት እማማ ሂዱ
ወደ እታ አበባ በር አጠገብ፤ የሚያዩት ነገር አለ ብላቸው ነበር፡፡ እሳቸውም ሌላ ነገር መስሏቸው ቤቱን ሰለል እያረጉ በበሩ አጠገብ አለፍ ሲሉ ፋንትዩ ያየችውን
ያያሉ፡፡ በእርግጥ በወቅቱ በፋንትዪ ድርጊት ተቆጥተው ነበር፡፡ ግን ደግሞ ያዩትን
ማመን ችለዋል፡፡

«ለመሆኑ ይህን ወሬ የሚያወራው ማነው?» ስትል ሽዋዬ ጠየቀቻቸው፡፡
ሠፈር ሙሉ ነዋ! እኔ እንደውም የስማሁት በወይዘሮ እልፍነሽ ቤት
ውስጥ ሲወራ ነው፡፡» አሏት።
👍3
#ምንትዋብ


#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ


....“ጉድ! ጉድ!” አለ፣ ወይዘሮ ጌጤነሽ ሳይቀደሙ ለመቅደም። ቆመው እጅና እግራቸውን በእርጥብ እጃቸው ያባብሳሉ።

ባላምባራስ ዝም አሉ።
ወይዘሮ ጌጤነሽ ባላቸው፣ “ምንድርነው?” ሳይሏቸው በመቅረታቸው ቅር ተሰኙ። ወሬውን ለማውራት የነበራቸውን ጉጉት ስለአመከኑባቸው
ወሽመጣቸው ተቆረጠ። የባላቸውን ዝምታ አሰቡና ነገሩ ከነከናቸው።.

“ምንድርነውም አይሉ?” አሏቸው፣ የጎሪጥ እያይዋቸው።
“የትም አምሽተሽ መተሽ ደሞ ጉድ ትያለሽ?” አሉ፣ ባላምባራስ።

“ነገረኛ፣ ታሞ አይተኛ አሉ” አሉ፣ ወይዘሮ ጌጤነሽ፣ ድምፃቸውን
ዝቅ አድርገው።

“ምን አልሽ?”

“ምን እላለሁ ሳናግርዎ መልስ አይሰጡም ወይ ነው ያልሁት። ሌላ ምን እላለሁ?” አሉ፣ ራት ለመሥራት ምድጃ ላይ ድስት የጣደችውን የቤት አገልጋይ እያዩ።

“ሚሰማሽ ካገኘሽ ምላስሽ ረዥም ነው።”

“ኸርሶ አይበልጥ” አሉ፣ አሁንም ቀስ ብለው።

ባላምባራስ ቆጣ ብለው፣ “ምን አልሽ?” ካሉ በኋላ፣ ጉድ ከሰሙ
ስለ ሰነበቱ ጉዱን የመስማት ፍላጎት አደረባቸው። ቁጣቸውን ገታ አድርገው፣ “እና ምንድርነው ጉዱ?” አሉ፣ ለጠጥ ብለው እምብዛም ለወሬ የጓጉ እንዳይመስሉ።

ወይዘሮ ጌጤነሽ እንዳልሰማ ዝም አሉ፤ እንደ ማኩረፍ አድርጓቸዋል።

“ምንድርነው ጉዱ አልሁሽ እኮ” አሉ ባላምባራስ፣ ቆጣ ብለው።

ወይዘሮ ጌጤነሽ አሁንም ያልሰሙ መሰሉ።

“ሳናግርሽ መልስ 'ማሰጪ?” የባላምባራስ ቁጣ እየተጋጋለ ነው።

“ምን አሉኝ?” አሉ ወይዘሮ ጌጤነሽ። ፊታቸው ላይ ስስ ፈገግታ ይነበባል። ዛሬ አነስተኛ ቢሆንም ባላቸው ላይ ድል ተቀዳጅተዋል።

እነዚህን መሳይ ጥቃቅን ድሎች ናቸው አንዳንዴ ባላቸውን ያሸነፉ
እንዲመስላቸው የሚያደርጓቸው።

“ጉድ እያልሽ ገባሽ። ምንድርነው ብልሽ አለመጥሽ።” አሁንም
ድምፃቸው ገኗል፣ ባላምባራስ ሁነኝ።

“አልሰማሁ ሁኜ ነው” አሉ፣ ወይዘሮ ጌጤነሽ። የባላቸው ቁጣ
የሚገነፍልበትን አፍታ ስለሚያውቁ ያገኙትን ድል እያጣጣሙ፣
“የግራማች ልዥ ...” ሲሉ ጀመሩ።

“ግራማች?” ሲሉ አቋረጧቸው፣ ባላምባራስ። ወሬውን ለመስማት
ቸኩለዋል።

“ግራማች መንበር ናቸዋ።”

“ኸሷው ጋር ስታወሪ እንደቆየሽ አውቄያለሁ። ወልደልዑል ምንን
ሆነ?”

“ሴቷ ወለቴ።”

ጥላዬ፣ የሆነ ነገር እንዳለ ደመነፍሱ ነገረው። ነፍሱ ከዳችው። ጉዱን ለመስማት ቤት ውስጥ መግባት ፈልጎ፣ ወገቡ አልታዘዝ፣ ጉልበቱ አልንቀሳቀስ አለው። እንደምንም ብሎ ተነስቶ ውስጥ ገብቶ መደብ
ላይ ተቀመጠ።

ባላምባራስ በመገረም ተመለከቱት። እሳቸው ሳይተኙ ቤት ውስጥ ስለማይገባ፣ ዐይኑን ካዩት ከርመዋል። ሆዳቸው ተገላበጠ።

“እና ምንን ሆነች?” አሉ፣ መባባታቸው እንዳይታወቅባቸው
እየታገሉ።

ወይዘሮ ጌጤነሽ ከመናገር ተቆጠቡ። ጥላዬን ሰረቅ አድረገው አዩት።እሱ የሚሉትን ለመስማት ቢጓጓም ጎንበስ ብሎ መሬቱን በስንጥር መጫጫር ጀመረ።

“ዛሬ ምንን ነክቶሻል? ምንን ሆነች ስልሽ መልስ ማሰጪ?”

“በያ ሰሞን ንዳድ ይዟቸው ኸነሱ ዘንድ ተኝተው የነበሩት ለካስ
ንጉሡ ኑረዋል...”
“ንጉሠ?”
“አዎ።”
“አጤ በካፋ?”
“እሳቸው። ሌላ ንጉሥ አለ?”
“ምንድርነው ምታወሪው?” አሉ ባላምባራስ፣ የሚስታቸውን ትንኮሳ
ችላ ብለው።
መንን
“አጤ በካፋ ራሳቸው። ወለቴ አስታማቸው ስታበቃ ዛሬ ሰዎች
ኸጥሎሽ ጋር ሰደዱ።”
“ሊያገቧት?”
“ኋላ?”
ጥላዬ ዱብ ዕዳ ሆነበት፣ ድንጋጤ ሰውነቱን አብረከረከው። ተነስቶ
ሊወጣ ፈልጎ ወሬ ለመስማት ተቀመጠ።

“ሰው ለማንጓጠጥ ማን ብሎሽ። ወረኛ! ደሞ ማታመጪው የለ” አሉ
ባላምባራስ፣ ተደናግጠዋል፣ ንዴትም ተናንቋቸዋል።
“እንዴት በሉ? ምን ያልሆነ አምጥቸ አውቃለሁ? ኸመሽ አገር ሁሉ ሚያወራው እኼንኑ ማዶል? የጣ ፈንታ ነገር ይገርማል።”

“ውነት ነው፤ ዕጣ ፈንታ ነው” አለ ጥላዬ፣ የሞት ሞቱን። ሰውነቱ
እየራደ ነው። ለራሱ፣ እኔ ዕድል ፈንታየ ሁኖ ያልታደልሁ ሁኘ
የወፍታው እኼን አሰማኝ ብሎ በዐይኑ ውሃ ሞላ። እንባው እንዳይታይበት እደጅ ሲወጣ፣ አባቱ በዐይናቸው ተከተሉት።

“ያቺ አያትየው ኸደብተሮቹ ነው ውሎዋ። ኸተኙበት ቀባብታቸው
ይሆናል ይላል ድፍን ቋራ” አሉ ወይዘሮ ጌጤነሽ፣ አገልጋይዋ ራት
እንድታቀርብ በእጃቸው ምልክት እይሰጡ።

“ድፍን ቋራ ኸምኔው ሰምቶ ነው እኼን ሁሉ ሚለው? አንቺና
ጓደኞችሽ ጓሮ ሁናችሁ ያቦካችሁት ነው እንጂ። ለነገሩ ልዥቱ
ምንም አይወጣላት። ደማም... ቆፍጣና... ይገባታል፤ ይገባታል ::
ሚገባትን ነው ያገኘች። እኔ ለተክለሃይማኖት ተዋጋህ እየተባልሁ ስወቀስ የተክለሃይማኖትን ወንድም በካፋን አገባች?” አሉ ባላምባራስ፣
በመገረም ራሳቸውን እየነቀነቁ።

አገባች! እርምዎን ያውጡ እንግዲህ! በርሶው አጓጉል ጠባይ ነው እኼ ሁሉ የመጣው። እርስዎንስ ይበልዎ፣ ልጄን ጎዱብኝ እንጂ አሉ ወይዘሮ ጌጤነሽ፤ ለራሳቸው። ጮክ ብለው ሊናገሩ ፈለጉና በማታ ኸሳቸው ጋር ምን አጫጫኸኝ ብለው፣ “ኸቤታቸው ንግርት አለ ይባላል። ዘመዳቸው የሆነ ሰው ኸወለቴ ግንባር ጠሐይ ስትወጣ አይቷል” አሉ።
ባላምባራስ መልስ አልሰጧቸውም። ቁጭት ላይ ናቸው። ልዥህን ለልዤ ስባባል ቆይቶ፣ በትንሽ ነገር ኸጥብቅ ወዳጄ ተቀያይሜ፣ አሁን
እኼው ሌላ...ያውም ንጉሥ ወሰዳት። እንግዲህ ኸንጉሥ መንጋጋ አላስጥላት! ያቺ ቀን እንዴት ያለች የተረገመች ናት አሉ፣ ግራዝማች መንበርን የተቀየሙበትን ቀን አስታውሰው።

የጊዮርጊስ ማኅበር ነው። ግራዝማች መንበር ቤት ይበላል፤ ይጠጣል። ጨዋታው ደምቆ፣ እንደወትሮው ስለ ጦር ሜዳ ጀግንነት ይወሳል። ባላምባራስ ሁነኝ ራሳቸውን እንደ ጀግና ቢቆጥሩም፣ ስለ ጦር ሜዳ
ሲወራ አይወዱም።ከዚህ በፊት ሰድበውት የሚያውቁት ደብተራ ሞቅ ብሎታል። “አሁን በወፍታው ኸጦር ሜዳ ቋንጃውን የተመታ ዠግና ይባላል?” ብሎ በሳቅ
ተንተከተከ።

ማንም አልሳቀ። ሁሉም አንገቱን ደፋ። ሳቅና ቁም ነገር የሰፈነበት
ስብስብ ወደ መሸማቀቅ ተለወጠ።

ደብተራው የሳቀለት ሲጠፋ፣ “እኛ ባገራችን ምናቀው ሰው ቋንጃውን
ሚመታው ሲሸሽ ነው” አለ፣ የፌዝ ሳቅ እየሳቀ።
ባላምባራስ ከዓመታት በፊት ቋንጃቸውን ተመትተው ያነክሳሉና
እሳቸውን ሊነካ መሆኑን አውቀው ከተቀመጡበት ተነሥተው
ከዘራቸውን እየወዘወዙ፣ “አንት መተተኛ ደብተራ። እኔ ሁነኝ በንዳንተ ያለ ድግምተኛ አልሽረደድም። የት አባህ ጦር ሜዳ ውለህ ታውቃለህና
ስለ ጦር ሜዳ ታወራለህ? ጋን እያሸተትህ ኸድግስ ድግስ ዙር እንጂ።

ጥፋተኛው አንተ ሳትሆን አንተን ኸሰው መኻል የቀላቀለህ ነው” ብለው ከዘራቸውን ግራዝማች መንበር ላይ እየወዘወዙ፣ “መንበር አሰደብኸኝ ...
ያውም በዝህ በድውይ። ግድ የለም። እንዲህ ኻሰደብኸኝ ወዲያ እመቃብሬ እንዳትቆም... ኸዚህ ያላችሁ ሁሉ ቃሌን ቃል እንድትሉ”
ብለው እያነከሱ ወጡ።
ከዚያን ቀን ጀምሮ የግራዝማችና የባላምባራስ የረጅም ዘመን ጓደኝነት አከተመ፣ አብሮም የጥላዬና የወለተጊዮርጊስ ዕጮኛነት። ባላምባራስ፣
“በቤቱ አሰደበኝ” ብለው ቂም ያዙ። ግራዝማች፣ “ደብተራው ለሰደበው እኔ ምን አረግሁ?” ብለው ቅር ተሰኙ። አስታራቂ መሃከላቸው ቢገባ ባላምባራስ፣ “ሙቼ ነው ቁሜ ኸሱ ጋር ምታረቅ” አሉ። “ልዥህን
ለልጄ” የተባባሉት ጓደኛሞች ተቀያየሙ።

ግራዝማች መንበር፣ ሁነኝ ምንም ቢሆን የረጅም ጊዜ ወዳጄ ነውና
አንድ ቀን እንታረቅ ይሆናል እያሉ የወለተጊዮርጊስን እጅ ለጠየቀ ሁሉ አይሆንም እያሉ መለሱ።
👍15