አትሮኖስ
286K subscribers
117 photos
3 videos
41 files
566 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


ትላንት በፅሁፍ ስህተት ክፍል 26 የተባመው ክፍል 16 ተብሎ ይነበብ።


..ዕለቱ ቅዳሜ ነው::መርካቶ የተለመደ የትርምስ የግርግርና የጫጫታ ሂደቷን ቀጥላለች። የገበያ ልውውጡ ተጧጡፏል። የበዓል ሰሞን ሩጫ
ጥድፊያ ግፊያ መዋከብ ነው፡፡ የቅቤ ተራም እንደዚሁ። ቅቤ በገረወይና እየወረደ እየተመዘነ አንዱ በሌላው ላይ ይመረጋል። የቅቤ ተራራ ገዥው በጣቱ ይቧጥጥና ወደ አፍንጫው እየወሰደ ለጋ ነው?ስማ ነው
?የቱ ይሻላል?" ይላል።
“እዚህ ይምጡ!ቆንጆ የወለጋ ቅቤ አለ!"
“ይኸው ለጋ የጎጃም! ለወጥ ከፈለጉ ደግሞ ዋጋው ይቀንሳል። ወደዚህ!'የ
ቅቤ ነጋዴዎች ከፊት ለፊታቸው በተከመረው የቅቤ ተራራ አናት ላይ እየ
ትንጠራሩ ይጣራሉ፡፡ በዚሁ መሀል ቅቤ ለመግዛት ሳይሆን የቅቤ ነጋዴ
የሚፈልግ ወጣት እዚህም እዚያም ይራወጥ ነበር፡፡ ጌትነት መኩሪያ. ..
“እባክህ የኔ ወንድም ከባሌ ጠቅላይ ግዛት ቅቤ የሚያመጡ ነጋዴ አቶ
ዓለሙ ተመስገን የሚባሉ ታውቃለህ?"
“አላውቃቸውም" ይሄንን ይተውና ደግሞ ሌሎቹን ይጠይቃል። "አናውቅም ይሉታል፡፡ ደግሞ ያስረዳል ልዩ ምልክታቸውን ቀይ ሽማግሌ መካከለኛ ቁመት ፀጉራቸው ትንሽ ወደ ውስጥ ገባ ያለ" ከዚህ ሁሉ መባዞንና ውትወታ በኋላ ባይቀናው ኖሮ አንጀቱ በተቃጠለ ነበር፡፡ በመጨረሻ ላይ አንድ የባሌ ሰው አገኘ፡፡
“እንዴ? ጋሼ አለሙ! ደንበኛዬ ናቸው ሰሞኑን ይመጣሉ ምነው በሰላም
ፈለካቸው?" የቅቤ ነጋዴው ከዲር ነበር፡፡
“ዘመዴ ናቸው በጣም ነው የምፈልጋቸው እንዴት አድርጌ ላገኛቸው እች
ላለሁ ባክህ?"
“ምን ችግር አለ ታዲያ ? እኔ አገናኝሃለሁ። ደንበኛዬ ናቸው እኔጋ ሳይደርሱ አይመለሱም። እስከዛሬ ድረስ መቆየታቸው ራሱ ገርሞኛል።
ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንደሚመጡ እርግጠኛ ነኝ"
“እንግዲያውስ እየተመላለስኩ እጠይቅሃለሁ። ለማንኛውም ጌትነት
መኩሪያ ብለህ ንገርልኝ" የከዲርን አድራሻ ተቀብሎ የራሱን አድራሻ ትቶ ተመለሰ፡፡ ጌትነት እንደዚያ በደስታ እየፈነደቀ ሽማግሌውን ፍለጋ የተሯሯጠው ያለምክንያት አልነበረም። የምስራቹን ሊያበስር ተጣድፎ ነበር፡፡ በሯን ጥርቅም አድርጋ ዘግታ ደጅ ስታስጠናው የከረመችው የስራ እድል የተረታችበት ያ ሁሉ ጭንቀት በሀሴት የተደመደመበት የሽመልስ ድካም በድል የተቋጨበት አስደሳች ቀን ነበር፡፡ ፈፅሞ ውድድር ሊባል በማያስችል ልዩነት ፈተናውን በማለፍ አድልዎ ወዳጆቿን ክፉኛ እንድ
ታጋልጣቸው ያደረገበት ልዩ ቀን... የዘመናት ወዳጃቸው ሀሰት ለነአቶ
አባይነህ ጀርባዋን የሰጠችበት ቀን! ጌትነት የተሰማው ደስታ ይህ ነው
አይባልም፡፡ በደስታው ላይ ደስታ የተሰማው ደግሞ ፀሀይ አስፋው ክፍት
ቦታ ሲገኝ በምትመጥንበት የስራ ደረጃ ላይ እንድትቀጠር የተሰጠውን
ተያያዥ ውሳኔ ሲሰማ ነበር። አንዱ ሲደሰት ሌላው መከፋቱ የማይቀር
ነው። ፀሀይ ፈተናውን አልፈሻል ተብላ ሥራውን ለመጀመር በተዘጋጀችበት
ወቅት በተፈጠረ ውዝግብ ምክንያት በጅዋ የገባው ሲሳይ ሲያመልጣት
ማዘኗ መሳቀቁ የማይቀር ነው። በሷ እግር ተተክቶ እሱ ኑሮውን ሲያሻሽል እሷ ደግሞ ልታዝን ልትከፋ በመሆኑ ደስታው ሙሉ ደስታ አይሆንለትም ነበር፡፡ ሽመልስ የፈተናውን ውጤትና የተወሰነውን ውሳኔ እንደ ሰማ ሳይውል ሳያድር ነበር ስልክ ደውሎ የጠራው፡፡

“እንኳን ደስ አለህ ጌትነት ዛሬ መንፈሴ እጅግ የረካበት ቀን ነው። ዛሬ ለኔ ትልቅ የድል ቀን ነው፡፡ ዐባይነህን ከመሰለ ዝሆን ጋር ታግዬ ልጥለው የቻልኩት በፈጣሪ ድጋፍና ባንተ ጥረት ነው። ሰራተኛው
በሙሉ ውጤቱን በጉጉት ሲጠባበቅ ነበር የከረመው፡፡ ግማሹ አድናቆቱን
ሲገልፅ ግማሹ ደግሞ የአቶ አባይነህ ቲፎዞ በመሆን ጭፍን ጥላቻውን
ሲያንፀባርቅ ቆይቷል። እንደዚያ መሆኑ ግን በነገሩ እንድገፋበት ብርታት
ሆኖኝ እንጂ አላንበረከከኝም፡፡ አንተም አላሳፈርከኝም፡፡ ይሄ የጋራ ድካማችንና የጋራ ውጤታችን ነው፡፡ ከዚህ በሁዋላ
የዚህ ድርጅት አባል ነህ ትንሽ ነገር ልበልህ፡፡ በተቻለህ መጠን ከስራህ በስተቀር ሰዎች ለተንኮል
ለሌለብነት እንዲያመቻቸው ከሚፈጥሩት ቡድን ራስህን ጠብቅ። ስራህን
አክብር፡ ስራህ ያከብርሀል፡፡ በአለቃህ ፊት ብቻ ሰራተኛ መስለህ ለመታየት አትሞክር፡፡ አለቃህን በስርዓቱ ማክበር የሥራ ድርሻህን በብቃት መወጣት ተገቢ ነው፡፡ በማጎብደድ በእወደድ ባይነትና በወሬ አቀባባይነት ለመሾም ወይም ለማደግ የሚፈልጉ ሰዎች አርአያም ተከታይም ከመሆን ግን ራስህን ጠብቅ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ አለቃህ ስራህ መሆኑን ጠንቅቅህ መረዳት ይኖርብሃል፡፡ የአቶ አባይነህ ቲፎዞዎችና አንዳንድ ጭፍን አመለካከት ያላቸው ሰራተኞች ሊጠሉህና ሊተናኮሉህ ይችሉ ይሆናል።
መተናኮል ብቻም ሳይሆን ፊት ለፊት ሊበድሉህ ወይም ሊያጠቁህ ይሞክሩም ይሆናል ነገር ግን ጥቃትን በመፍራት ህሊናህ የማይፈቅደውን ነገር ከመስራት መቆጠብ ይኖርብሃል። አንተም አንድ ቀን በሃላፊነት ቦታ ላይ ስትቀመጥ ምን ማድረግ እንዳለብህ ከዚህ ትምህርት ልትወስድ ይገባል። ለማንኛውም መልካም የስራ ዘመን ይሁንልህ" በማለት የምስራቹን ካበሰረውና ተገቢውን ምክር ከለገሰው በኋላ አቅፎ ጀርባውን ቸብ
ቸብ አደረገው።

"በእውነት ነው የምልህ ሽመልስ አዲስ ህይወት የፈነጠቅክልኝ ስለኔ ሆነህ ራስህን ጎድተህ የተሟገትክልኝ ምንጊዜም የማከብርህ ወንድሜ
ነህ፡፡ ዓላማዬ የተሰጠኝን የሥራ ሀላፊነት በአግባቡ በመወጣት ትምህርቴን መቀጠልና የተሻለ ዕውቀት በመገብየት ራሴንም ቤተሰቤንም አገሬንም መርዳት ነው። ወደፊት ይህ ሁሉ ምኞቴ ተሳክቶ ለበለጠ ሀላፊነት በቅቼ ስዎችን ለመጥቀም ወይንም ለመጉዳት በሚያስችል የሥራ ሀላፊነት ላይ የመገኘት ዕድሉ የሚገጥመኝ ከሆነ ካንተ ከወንድሜ ያገኘሁት ትልቅ ትምህርት ምንጊዜም ከአእምሮዬ የሚጠፋ አይደለምና ስለ እውነት ለመሥራት ቃል እገባልሃለሁ" አለው።

ጌትነት የቅጥር ፎርማሊቲውን አሟልቶ ጨረስ፡፡ ስራ ይዞ ስው ለመሆን
ያደረገው ረጅም ሩጫ ዳር በመድረሱና ራሱን ችሎ ሌላውን የመርዳት ህልሙ እውን በመሆኑ ደስታው ወደር አልነበረውም፡፡ ልቡ ወደ ባሌ ወደ እናቱ ዘንድ በረረች፡፡ እህቱ ዘይኑን በቅርብ ክትትል የማስተማር ዕቅዱን በማሳካት ጉጉት ተውጦ ወደ ትውልድ መንደሩ በሀሳብ ከነፈ ያንን አስደሳች ዜና ለእናትና እህቱ ሊያሰማቸው ተጣድፎ አቶ አለሙን ለማግኘት በየቀኑና ቅቤና ነጋዴው ከዲር ዘንድ ሲመላለስ ከቆየ በኋላ ቀናው። በመጨረሻ ላይ አቶ አለሙ ዠ መምጣታቸውን አረጋገጠና በከዲር
አማካኝነት ተገናኙ።

“ጌትዬ! አንተ?! ደህና ነህ?! እንደው ነፍስህ አለ ልጄ?" የእናቱን ናፍቆት
ጭምር እቅፍ አድርገው አገላብጠው ሳሙት፡፡
"ደስ ብሎኛል አባባ ደስ ይበልዎ! የድሃዋ እናቴ አምላክ ጥሎ አልጣለኝም። ሥራ አገኘሁ! ሁሉንም ነገር ጨረስኩ! ሁሉንም ነገር ጨረስኩ!”
ሁለመናው ስቆ ደስታውን ገለፀላቸው፡፡ አቶ ዓለሙ በደስታ ዘለሉ፡፡
"ጎሽ! ጎሽ! እሰይ የኔ አንበሳ! እንኳን ደስ አለህ! እንዴት ያለውን የምስራች ነው የነገርከኝ ባክህ?! እሰይ! እስይ! እኔም ገዳም ሆንኩ ማለት ነው፡፡ የምስራች ሰምቼ የምስራች አብሳሪ ሆንኩ ማለት ነው። ጭንቅጰሲለኝ የከረመው የሷ ጉዳይ ነበር፡፡ መልካም ዜና አመጣልሻለሁ እንዳልኳት እንደፎከርኩት ተሳካልኝ ማለት ነው። ደስታው የሁላችንም ነው!” ፍንድቅድቅ አሉ።

"አባባ ለመሆኑ የጤናዋ ነገር እንዴት ነው? ሃሳቡ ገድሏታል መቼም
ጭንቅ ጥበብ እያለው ጠየቃቸው
“ደህና ነች ምንም አትልም ያንተ ነገር ነበር ሲያሳስባት የከረመው ከንግዲህ በኋላማ ምን ትጠይቀኛለህ?
👍3
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


... ታፈሡና መርዕድ መናኸሪያ ሲደርሱ ከምሽቱ አሥራ አንድ ሠዓት እየተጠጋ ነው:: ሁኔታው ግን የበለጠ ተባብሷል። እንዲያውም ሁለተኛው በራሪ
አውቶብስ ገብቶ ነገር ግን አሁንም ተላልፈው ኖራልና የተጠበቀው መረጃ ባለመገኘቱ ህገቡ ግራ ተጋብቶ ወለሌ ይላል። ይተረማመሳል፡፡ ይላቀሳል፡፡
ታፈሡ በሕዝቡ መሀል ክወዲያ ወዲህ እየተሯሯጠች «እህ እንዴት ነው? ምን ሰማችሁ! እንዴት ሰማችሁ ሰው ተርፎ ይሆን?» በማለት ስትርገበገብ ከኳኋኗን ይመለከት የነበረ አንድ ቀደም ብሎ ያውቃት የነበረ ሰው እጇን ያዝ አደረገና «ወይዘሮ ታፈሡ፣ አንቺም ሰው ሸኝተሽ ኖሯል? » ሲል ጠየቃት
«አዎ ጋሽ ዓለሙ! ወንድሜን፡፡» አለችው እጆቿን እያርገበገበች::
እግዜር ይጠብቅልሽ እንጂ የጉዳቱ መጠን እንኳ በጣም አሳሳቢ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ይኸው እስከ አሁን እንኳ የሰባት ሰው መርዶ ደረሰ፡፡»
ታፈሡ ወዲያው እጆቿን ወደ ላይ ዘርግታ «ወየው! ወየው ወየው
እያለች ልክ መርዶ የደረሳት ያህል ለይቶላት ታለቅስ ጀመር፡፡ እንባዋ በጉንጫ ላይ ቦይ ሰርቶ ይንቆረቆር ጀመር፡፡ ጭንቅ ጥብብ፣ ብክን ክርትት ስትል የሚያያት ሁሉ
ልክ እንደ እሷው እንባውን ያዘራው ጀመር። በከተማው ውስጥ ታዋቂ እንደ መሆኗ ሴት ወንዱ ዙሪያዋን እየከበበ ሊያጽናናት ቢሞክርም እሷ ግን አንጀቷ እየተንሰፈሰፈ
አልረጋጋ ብላ አስቸገረች፡፡

ጀምበር ጠልቃ ለዓይን መያዝ ጀምረ፡፡ ቀሪው የዚያ ቦታ ትርዒች ስለ ነገው አስክሬን ፍለጋ ጉዞ መነጋገር ብቻ ሆነ። አንዱ ከሌላው ጋር ይመካከር ጀመር፡፡ ታፈሡና መርዕድም ሊሄዱ በጋራ ወሰኑ፡፡
ታፈሡና መርዕድ ወደ መናኸሪያ ከሄዱበት ሠዓት ጀምሮ ሄዋን ቢያንስ አሥር ጊዜ ከቤት እደጅ ወጣ ገባ ስትል ቆይታለች። ስጋት እያቁነጠነጣት ከተቀመጠችበት ይልቅ ስትቆም ስትራመድ ያሳለፈችው ጊዜ ይበልጣል:: መርዶ ይሆን ብሥራት የሚመጣላትን አታውቀውም፡፡ እነሱ ደግሞ ለእሷ ምንም ዓይነት
ፍንጭ ላለመስጠት እየተዘጋጁ ናቸው:: ሁለቱም ወደ ቤት እየተመለሱ በአሉባት ሰዓት ታፈሡ ያለቀስችበትን ዓይኗን ጭምቅ፣ ፊቷን ጥርግርግ አረገች። እንዲሁም ስለ ሁለት ሠዓት ዜና አስማም ተመካከሩ። በታፈሡ ቤት ሬዲዮ ላይከፈት፣ በዚያ ምትክ መርዕድ ቴፕ ሊከፍት፣ ታፈሡ ወደ ጎረቤት ሄዳ ዜና ሰምታ ልትመለስ።
የጠዋቱን ጉዞ በተመለከተ ታፈሡ ከባለቤቷ መልዕክት ተልኮላት ያን ልትቀበል ወደ አዲስ ኣበባ ልትሄድ መሆኗንና መርዕድ ጠዋት ይሸኛት ዘንድ እሷው ቤት ሊያድር ሆኖ የሔዋንን ጥርጣሬ ለመቀነስ ተዘጋጅተዋል፡፡
ከምሽቱ አንድ ሠዓት ላይ ታፈሡና መርዕድ ከቤት ሲደርሱ ሔዋን በር
ላይ ቆማ ስትጠብቃቸው አዩዋት፡፡ ታፈሡ የመጀመሪያውን ሔዋንን “ማረጋጊያ ዘዴ ወዲያው ፈጠረችና “ሔዩ! ቡና አላፈላች ይሆን? ብታይ የረባ ወሬ ላይገኝ ነገር ወዲያ ወዲህ ስንከራተት ስለ ቆየን ራሴን እንዴት ቀስፎ ይዞኛል መስለሽ አለቻት ወደ በር እየተራመደኝ፡፡ መርዕድ አጎንብሶ ከኋላዋ ይከተላል፡፡

«ምንም የለም?» አለች ሔዋን የበሩን መቃን ደገፍ ብላ እንደቆመች።
«ወሬማ ሞልቷል!ግን እርስ በእርሱ ይጋጫል»
«ምን ምን ይባላል ታፈሡዬ?»
«ጭራሽ የትኛው መኪና እንደተጋጨ እንኳ እልታወቀም»
ሦስቱም ወደ ቤት ገቡ፡፡ ሔዋንና መርዕድ ሶፋ ላይ ሲቀመጡ ታፈሡ ወደ ጓዳ ገባች ሠራተኛዋ የእራት ወጥ እየሰራች ነበርና ቶሎ በይና ቡና አፍይልኝ አለቻት ድምጿ ወደ ሳሎን እንዲሰማ አድርጋ ጮክ በማለት፡፡ ልብሷን ቀያይራ ወደ ሳሎን እየተመለሰች ሳለች መርዕድን «አዲስ እበባ የምትልከኝ ነገር ካለ አሁኑ ተዘጋጅ መርዕድ እያላችው ወደ ሶፋ ሄዳ ከሔዋን ጎን ተቀመጠች።
«መቼ ልትሄጂ?» አለቻት ሔዋን አዲስ ወሬ ሆኖባት በርገግ ብላ፡፡
ባለቤቴ ከርሞ ከርሞ ከውጭ ሀገር የሆነ ነገር ሳያልክ አይቀርም አዲስ አበባ መጥተሽ ወሰጂ ብለው ዛሬ በትምህርት ቤት በኩል ስልክ ደወሉልኝ»
«እና ነገ ልትሄጂ» አለች ሔዋን አሁንም ጭንቅ ጥብብ እያላት፡፡
«አዎ፣ ግን በጠዋት እንድትቀስቅሱኝ። መርዕድም እንዳሸኘኝ ብዬ እዚሁ ላሳድረው ነው ይዤው የመጣሁት። አለቻት ወደ መርዕድ አየት እያደረገች፡፡
«የኔስ ነገር ታፈሡዬ?»
«የአስቻለው ቁርጥ ሳይታወቅ ትሄጃለሽ እንዴ?» አለችና ታፈሡ እኔም እኮ ነገ ሄጂ ከነገ ወዲያ እመጣለሁ፡፡ እስከዚያው እዚሁ እኔ ቤት ሆነሽ ጠብቂኝ፡፡ አለቻት።

ሔዋን ነገሮች ሁሉ ተምታቱባት፡፡ ቀደም ሲል ያየችባቸው አስደንጋጭ ሁኔታና የአሁኑ እርጋታቸው ፈጽሞ ሊጣጣምላት አልቻለም። ጭራሽ የአስቻለውን
ነገር ማንሳት የነገር ደባል መፍጠር ሊመስልባት እንደሚችል እስከ መስጋት ደረሰች፡፡ ግን ደግሞ ሆድ ሆዷን በላትና «በዚያው ስለ አደጋውም ትሰሚያለሽ?» ስትል ታፈሡን ጠየቀቻት።

«የሆነ ነገር ካለማ ማየቴም አይቀርም፡፡ »አለችና ታፈሡ በተለይ ወደ መርዕድ አየት እያደረገች። «ግን እንደው ወሬው ሁሉ የማይጨበጥ ሆነና ግራ አጋባን እንጂ» አለች።

«ሰው ደሞ ዝም ብሎ ማዳነቅ ይወዳል፡፡» አለ መርዕድም ጣሪያ ጣሪያ እያየ የምንተ እፍረቱን ወዲያው ብድግ አለና ወደ ብፌው በመሄድ ሙዚቃ ከፈተ።
ከሌለህማን አለ እጀፈደጅህ ኪስህ ነው የቅርብ ወዳጅ» የሚለው ዜማ ሠሰማት ጀመረ።

እራት በልተው ሲጨርሱ ሁለት ሠዓት ሊሆን ተቃርቧል። የታፈሡ
"ሠራተኛ ቡና እያፈላች ሳለች ታፈሡ በጉጉት የምትጠብቀው የዜና ሠዓት ደረሰና መጣሁ ብላ ከቤት ውልቅ አለች፡፡ ከጎረቤቶቿ ቤት ስትደርስ ሬዲዮ ተከፍቶ የዜና
ንባብ ተጀምሯል። ታፈሡ በዚያ ቤት የተከበረች እንግዳ ናትና ከቤት ስትገባ ቤተሰቡ በሙሉ ተነስቶ ተቀበላት፡፡ ከሰላምታ በኋላ ሬዲዮው ሥር ቁጭ አለች።
ዜና ንባበ ቀጠለ። ዋና ዋና ዜናዎች ከአለቁ በኋላ «በመጨረሻም» እለ ዜና
አንባቢው ጋዜጠኛ
ዛሬ ከዲላ ወደ አዲስ እበባ ይጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ከሞጆ ወደ ሻሸመኔ ይጓዝ ከነበረ መለስተኛ የህዝብ ሚመላለሻ ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭቶ በደረሰ አደጋ በትንሹ ሰላሳ ሶስት ሰዎች ሲሞቱ አርባ ስምንት ያህሉ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የዝዋይ ከተማ ትራፊክ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ገለፁ:: ጽፈህት ቤቱ እንዳለው» ብሎ ሳይጨርስ ታፈሡ
ያንን ቤት በጨኸት አደበላለቀችው
እየዩ እኔ.. እየየ እኔ.. እየየ እኔ እያለች በወለሉ ላይ ድፍት አለች
ከዜናው ይልቅ በታፈሡ ሁኔታ የደነገጠው የዚያ ቤት ቤተሰብ በሙሉ ተረባርቦ ከተደፋችበት ቀና አድርጎ አስቀመጠ፡፡ «ምነው? ምነው?» አለ ሁሉም ሰው በማክታትል። ታፈሡ ምላሽ መስጠት የሚያስችል ፋታ አላገኘችም፣ ስቅስቅ ብላ ታለቅስ ጀመር። አስቹ አርፈኸዋል! ተገላግለሃል ወንድሜ! የኔ ግልቱ የኔ ብስጨ! ወይኔ ! ወይኔ ! ወይኔ!» አለች በማከታተል::
«ምነው ወይዘሮ ታፈሡ ገና በግምት?» አሏት የቤቱ አባወራ ቀደ ብለው። «ምንሽ ነው ወይዘሮ ታፈሡ?» ሲሉ የቤቱ እማወራ ቀጠሉ፡፡ታፈሡ ግን ወደ ዝርዝር መግባት አልቻለችም፡፡ ተዉኝተዉኝ ተዉ በቃ ሌላ ሰው እይስማብኝ!» አለችና አደራ ጎረቤቶቼ ነገ እኔ እዚህ አልውልም ወደ ናዝሬት እሄዳለሁ:: ግን እዚህ እኔ ቤት ወስጥ ይኸን ጉድ መስማት የሌለባት ልጅ አለችና አደራ! የአሁኑን አኳኋኔን ለሠራተኛዬ እንኳ እንዳትነግሩብኝ አለቻቸውና እያለቀሰች ተስናብታቸው ወደ ቤቷ ተመለሰች::
👍7