አትሮኖስ
281K subscribers
110 photos
4 videos
41 files
489 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የወድያነሽ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል


....«ስለ ልጅሽ አታስቢ አንቺንም በሚገባ እረዳሻለሁ። አየሽ አእምሮዩ ባንዲት ተስፋ ብቻ ትደሰታለች። ይኸውም ካንቺ ጋር እንደገና እንገናኛለን የሚለው ተስፋ ነው» ብያት ሳልወድ በግድ ዝም አልኩ።

ምላሴ ተቆልፋ እምቢ ባትለኝ ኖሮ በውስጤ የማግበሰበሰው ሐሳብስ ስፍር
ቁጥር አልነበረውም። በብስጭት ከመለብለብ ብዬ ጥያቸው ገለል አልኩ።
ጉልላትም ካሦስት ደቂቃ በኋላ ተለይቷት መጣ፡፡ የእሱን መኪና እንደ ተደገፈን
ብዙ ደቂቃዎች ዐለፉ። እንሒድ ተባብለን ወደ ፍርድ ቤቱ በር አካባቢ ተጠጋን፡፡

አንድ ወፈር ያለ ድምፅ «የወዲያአሉሽ አሸናፊ!» ብሎ ተጣራ፡፡ ለፈተና
እንዳልተዘጋጀ ሰነፍ ተማሪ ተርበተበትኩ፡፡ ሮጥ ሮጥ ብለን ሴቷን ወታደር
ደረስንባትና ስንተኛ ችሎት ነው የምትቀርበው?» ብለን ጠየቅናት።

«አንደኛ ወንጀል ችሎት» ብላ የወደያነሽን ለዕርድ እንደሚነዳ ሠንጋ ነዳቻት። በረዶ የመታኝ ያህል ተንዘፈዘፍኩ፡፡ ወደ ፍርድ ቤቱ ለመግባት ከባለጉዳዮችና ከአቸፍቻፊዎች ጋር ተደባልቄ ዘለቅሁ፡፡
የፍርድ ቤቱን ደፍ ራመድ እንዳልኩ፣ ልክ ከፊት ለፊቴ ድንገተኛ መብረቅ የወደቀ ይመስል አካላቴ በታላቅ ድንጋጤ ተተረተረ። ወዲያም ወዲህ ሳላይ ቀንዷን እንደ ተመታች ላም ወደ ኋላ ተመለስኩ፡፡ ተከታትለው የሚይዙኝ ይመስል ሽሽቴን ቀጠልኩ፡፡ የምገባበት ጨነቀኝ፣ ተቅበዘበዝኩ፡፡ መሬት ተሰንጥቃ
ብትውጠኝ ባልጠላሁ ነበር። መለስ ብዬ ብመለከት የጉልላትም ፊት ቡን ብሏል፡፡
ጭንቅላቴን ይዤ አፈሩ ላይ ተጎለትኩ፡፡ መላ ሰውነቴን አሳከከኝ። ዐይኔ ውስጥ
አሽዋ የገባበት ይመስል ቆረቆረኝ፡፡ ዙሪያው ጨለመብኝ። አተነፋፈሴ ፈጠነ፡፡
የእጮኛውን ሞት እንዳረዱነት ወጣት መላ አካላቴ በውስጣዊ የኃዘን ማረሻ
ታርሶ ተበረቃቀሰ፡፡

«የወዲያነሽ ስንት ዓመት ይፈረድባት ይሆን?» እያልኩ ከእግር እስከ ራሴ በፍርሃትና በሥጋት ማጥ ውስጥ ተዘፈቅሁ፡፡

የፍርድ ቤቱን ደፍ ገና ረገጥ ስናደርግ እኔንና ጉልላትን ያስበረገገን ግን
ከሦስቱ ዳኞች አንዱ ያውም የመኻል ዳኛው የእኔው አባት ባሻ ያየህይራድ
መሆኑ ነበር፡፡ ከዚያ ቀደም እንደዚያ ያለ ድንጋጤ አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡
አቀርቅሮ የክስ ፋይል ይመለከት ስለነበር አላየኝም፡፡ እነዚያ በሕይወቴ ውስጥ
ዕድሜ እየሆኑ የተቆጠሩት አስደንጋጭ ደቂቃዎች እንደ ማንኛውም ደቂቃ
ዐለፉ፡፡ በዚያ ቅፅበት በእእምሮዬ ውስጥ የጎረፈውን የስጋት ሽብር በተግባር
ለቀመሰው እንጂ በወሬ ለሚሰማው ክብደት የለውም፡፡

አቃቤ ሕጉ በየወዲያነሽ ላይ የሚያቀርበውን ክስና አባቴ ከሁለቱ ዳኞች ጋር ሆኖ የሚሰጠውን የቅጣት ፍርድ ፊት ለፊት ለማየትና ለመስማት ባለመቻሌ ምን ጊዜም የማልበቀለው ጉዳት አጨቀየኝ።

የየወዲያነሽ ሰውነት በጣም በመኮስመኑና ስሟም በመጠኑ ተለውጦ
የወዲያ አሉሽ በመባሏ አባቴ ሊያውቃት አይችልም፡፡ አለባበሷና አንገተ
ሰባራነቷ እንደሚያዛልቅ ወለል ብሎ ታየኝ፡፡ ጭንቅላቴን ይዤ እንዳቀረቀርኩና
ከተቀመጥኩበት ሳልነሳ ጉልላትም እንደ ማማ ተገትሮ እንደ ቆመ ግማሽ ሰዓት
ያህል ነጎደ። ወዴት እንደሚሔድ ባላውቅም የእግሩ ኮቴ ድምፅ ከወደ ኋላዬ እየራቀ ሄደ። አሁንም ጥቂት ደቂቃዎች ዐለፉ፡፡ እፎይታ ሳይሆን የመከራ ነዲድ በውስጤ ተግፈጠፈጠ።

የአባቴን ጠቅላላ የሕሊናና የአካል አቋም ከልጅነት እስከ ዕውቀት የማውቀውን ያህል እያሰላሰልኩ ከፊት ለፊቴ አቆምኩት፡፡ እርሱ በሚያነብበው
የሃይማኖት ታሪክ መጽሐፍ ውስጥ የሚነገርለት ሰው በላው ሰው ሰባ ስምንት
ሰዎች በልቷል እየተባለ ይነገራል። አባቴም በላዔ ሰብ እየተባለ የሚነገርለትን የክፉ ሰው አምሳል መስሎ ታየኝ።

እሱም እንደ ሰው በላው ሰው የሰው አካል አወራርዶና ግጦ የሰው ሥጋ ባይበላም ሰው በላ ነው:: የሰውን ሕይወት በማጥፋትና የሰውን ሕሊና በመግደል
መካከል ምንም ልዩነት የለም፡፡ ስለ እውነተኛ ርትእና ፍትሕ እየተናገረ
ከሓሰተኞች ጎን ቆሞ ፍርድ ያዛባል፡፡ ከሐቅ ጋር ለቆመ ድሃ ሳይሆን ከሐሰትና
ከክህደት ጋር ጡት ለተጣቡ ባለጊዜና ባለ ገንዘብ ይፈርዳል። ስለዚህም «ሰው
በላ» ነው፡፡

ስለ ድሀ መጨቆንና መበደል ሲያወራ ማንም የሚስተካከለው አይመስልም፡፡ የየአካላችን ደም ስለየሕሊናችን ቅንነትና መሠሪነት መስካሪ ቢሆን ኖሮ ከአባቴ ኣካል የሚንጠፈጠፍ ደም ምንኛ ባጋለጠው!

ከጥቅምና ከኑሮው ላይ ቅንጣት ታህል የሚነካ ሰው ከመጣ፡ አንዷ ሰው
በላው ሰው የሰው አካል ዘነጣጥሎ ባይበላም ነገር ሽርቦና ጉንጉኖ ዓመት ሳይተኩስ ጥርኝ ዐፈር ያደርገዋል።

«ጨርቅ ለባሽ፣ አጥንተርካሽ በማለት የሚጸየፋቸውን ሰዎች ስለ ስምና
ክብሩ ብሉ ያንገላታቸውን ድሆች ሳስታውስ አባቴ እንደዚያ እንደ ታሪኩ ሰው
በቀጥታ የሰው ሥጋ ሳይሆን የሰው ሕይወት በልቷል። ስለ ሰው ችግርና ሥቃይ ፍጹም ደንታ የለሹ አባቴ፣ ማንም ቢንገላታና በጊሳቆል የቁጫጭ ሞት ያህል አያሳዝነውም፡፡ በአባቴና በመሰሎቹ አካባቢ ግዙፍ በደል በድሉ፣ በእጅ አዙር ሰው አስገድሉ፣ ከድሆችና ከከልታሞች ዲቃላ ደቅሎ ምስጢርን መቅ መጨመር የመሠሪነት ሳይሆን «የትልቅ ሰውነት» መለዮ ነው:: ለዚህ ዐይነቱ ደባ የሹም ምልመላ ቢካሔድ አባቴ ያላንዳች ቀዳሚ በትራሹመቱን ይጨብጣል።

«እሳቸው የሞቱ ዕለት ስንቱ ዲቃላ ከየሥርቻ ስርኩቻው ይጎለጎል ይሆን?» በማለት ውስጥ ውስጡንና የሚያማው ብዙ ነው:: እንደ ሰው ሐሜትማ ከሆነ ከልዩ ልዩ ሴቶች ተወልደው በአባቴ የተካዱትን እኀት ወንድሞቼን በግምት ሳሰላስል፣ አባቴ ከሰው በላው ብሶ ታየኝ። በተለይም ጠለቅ ብሎ ሥር ከፍ ብሎ ግንድ የለሽ» እያለ ሌሎችን በማኮሰስ የራሱን የዘር ሐረግ ሲያሳምር ታየኝና አስተሳሰቡን ሁሉ ተፀየፍኩት፡፡

ጉልላት ተመልሶ ከፊት ለፊቴ ቆመ፡፡ በእጆቹ ጎትቶ አስነሣኝ፡፡ በፊቱ ላይ አደናጋሪ ፈገግታ እየታየ «የምሥራች ጌታነህ!» አለኝ፡፡

በዚያች አስጨናቂ ጊዜ ውስጥ አንዳችም የምሥራች ይገኛል ብዬ ስላልጠረጠርኩ ነገሩን ችላ አልኩት፡፡ ቀጠል አደረገና «ምነው ዝም አልክ? የወዲያነሽ እኮ ተፈረደባት። የምሥራች ያልኩህ ግን እጅዋ ከተያዘበት ቀን አንሥቶ አምስት ዓመት እንድትታሠር ስለተፈረደባት ነው:: 'የፈረዱብኝ የጌታነህ አባትና አብረዋቸው ያሉት ናቸው” አለችኝ፡፡ የቅጣቱን ውሳኔ ግን በንባብ ያሰሙት ያንተ አባት ናቸው አለች፡ በስሜ መለወጥና በመጎሳቆሌ
አላወቁኝም በማለቷ በጣም ተደስቻለሁ፡፡ አለቀ። በፍርሃት የሚጠብቁት ሥቃይ
ካለፈ እፎይታ ነው» ብሎ ከሚተናነቀው ምስቅልቅል ሲቃ ጋር ዝምታውን ቀጠለ።

ከፍርዱ በኋላ የወዲያነሽ ወደ ነበረችበት አካባቢ አብረን ሄድን፡፡ ያ የዐይኗ ቋንቋ የሆነው እንባዋ ገነፈለ። ሴቷ ወታደር ትካዜያችንን አይታ አዘነች፡፡ እኔና ጉልላት እንደገና ጠጋ ብለን ለማነጋገር አዲስ ፈቃድ አልጠየቅንም፡፡

«አይዞሽ! ብዙ ጊዜ አይደለም፡፡ በወህኒ ቤት ውስጥም ሆነ እስራትሽን ጨርሰሽ ስትወጪ የእኔ ነሽ። እኔም ያንቺ እንጂ የማንም የሌላ እይደለሁም፡፡ የልብሽ አዳራሽ በዚህ እውነተኛ በሆነ የቃል ኪዳን ተስፋ ይሞላ። ይህን በላይሽ ላይ የጫንኩትን የመከራ ቀንበር አብሬሽ እሸከመዋለሁ፡፡ በመጨረሻም አብረን
እንሰባብረዋለን፡፡ ያጠቆርኩትን ሕይወትሽን በአዲስ የኑሮ ብርሃን እንዲደሞቅ እስከ መጨረሻው እታገላለሁ» ብዬ የልቤን ፅላት ሰጠኋት። አፏ ባይናገርም ልቧ ተቀብሉኛል፡፡ ያደረግሁት ንግግር ተፅፎ የተጠና እንጂ እዚያው ተቀናብሮ የተነገረ ስለማይመስል እኔኑ መልሶ ገረመኝ፡፡

መለስ ብዩ ለሴቷ ወታደር ምናምን ጨበጥ እደረኩላት፡፡ የማይፈቀድ
ነገር
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


ትላንት በፅሁፍ ስህተት ክፍል 26 የተባመው ክፍል 16 ተብሎ ይነበብ።


..ዕለቱ ቅዳሜ ነው::መርካቶ የተለመደ የትርምስ የግርግርና የጫጫታ ሂደቷን ቀጥላለች። የገበያ ልውውጡ ተጧጡፏል። የበዓል ሰሞን ሩጫ
ጥድፊያ ግፊያ መዋከብ ነው፡፡ የቅቤ ተራም እንደዚሁ። ቅቤ በገረወይና እየወረደ እየተመዘነ አንዱ በሌላው ላይ ይመረጋል። የቅቤ ተራራ ገዥው በጣቱ ይቧጥጥና ወደ አፍንጫው እየወሰደ ለጋ ነው?ስማ ነው
?የቱ ይሻላል?" ይላል።
“እዚህ ይምጡ!ቆንጆ የወለጋ ቅቤ አለ!"
“ይኸው ለጋ የጎጃም! ለወጥ ከፈለጉ ደግሞ ዋጋው ይቀንሳል። ወደዚህ!'የ
ቅቤ ነጋዴዎች ከፊት ለፊታቸው በተከመረው የቅቤ ተራራ አናት ላይ እየ
ትንጠራሩ ይጣራሉ፡፡ በዚሁ መሀል ቅቤ ለመግዛት ሳይሆን የቅቤ ነጋዴ
የሚፈልግ ወጣት እዚህም እዚያም ይራወጥ ነበር፡፡ ጌትነት መኩሪያ. ..
“እባክህ የኔ ወንድም ከባሌ ጠቅላይ ግዛት ቅቤ የሚያመጡ ነጋዴ አቶ
ዓለሙ ተመስገን የሚባሉ ታውቃለህ?"
“አላውቃቸውም" ይሄንን ይተውና ደግሞ ሌሎቹን ይጠይቃል። "አናውቅም ይሉታል፡፡ ደግሞ ያስረዳል ልዩ ምልክታቸውን ቀይ ሽማግሌ መካከለኛ ቁመት ፀጉራቸው ትንሽ ወደ ውስጥ ገባ ያለ" ከዚህ ሁሉ መባዞንና ውትወታ በኋላ ባይቀናው ኖሮ አንጀቱ በተቃጠለ ነበር፡፡ በመጨረሻ ላይ አንድ የባሌ ሰው አገኘ፡፡
“እንዴ? ጋሼ አለሙ! ደንበኛዬ ናቸው ሰሞኑን ይመጣሉ ምነው በሰላም
ፈለካቸው?" የቅቤ ነጋዴው ከዲር ነበር፡፡
“ዘመዴ ናቸው በጣም ነው የምፈልጋቸው እንዴት አድርጌ ላገኛቸው እች
ላለሁ ባክህ?"
“ምን ችግር አለ ታዲያ ? እኔ አገናኝሃለሁ። ደንበኛዬ ናቸው እኔጋ ሳይደርሱ አይመለሱም። እስከዛሬ ድረስ መቆየታቸው ራሱ ገርሞኛል።
ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንደሚመጡ እርግጠኛ ነኝ"
“እንግዲያውስ እየተመላለስኩ እጠይቅሃለሁ። ለማንኛውም ጌትነት
መኩሪያ ብለህ ንገርልኝ" የከዲርን አድራሻ ተቀብሎ የራሱን አድራሻ ትቶ ተመለሰ፡፡ ጌትነት እንደዚያ በደስታ እየፈነደቀ ሽማግሌውን ፍለጋ የተሯሯጠው ያለምክንያት አልነበረም። የምስራቹን ሊያበስር ተጣድፎ ነበር፡፡ በሯን ጥርቅም አድርጋ ዘግታ ደጅ ስታስጠናው የከረመችው የስራ እድል የተረታችበት ያ ሁሉ ጭንቀት በሀሴት የተደመደመበት የሽመልስ ድካም በድል የተቋጨበት አስደሳች ቀን ነበር፡፡ ፈፅሞ ውድድር ሊባል በማያስችል ልዩነት ፈተናውን በማለፍ አድልዎ ወዳጆቿን ክፉኛ እንድ
ታጋልጣቸው ያደረገበት ልዩ ቀን... የዘመናት ወዳጃቸው ሀሰት ለነአቶ
አባይነህ ጀርባዋን የሰጠችበት ቀን! ጌትነት የተሰማው ደስታ ይህ ነው
አይባልም፡፡ በደስታው ላይ ደስታ የተሰማው ደግሞ ፀሀይ አስፋው ክፍት
ቦታ ሲገኝ በምትመጥንበት የስራ ደረጃ ላይ እንድትቀጠር የተሰጠውን
ተያያዥ ውሳኔ ሲሰማ ነበር። አንዱ ሲደሰት ሌላው መከፋቱ የማይቀር
ነው። ፀሀይ ፈተናውን አልፈሻል ተብላ ሥራውን ለመጀመር በተዘጋጀችበት
ወቅት በተፈጠረ ውዝግብ ምክንያት በጅዋ የገባው ሲሳይ ሲያመልጣት
ማዘኗ መሳቀቁ የማይቀር ነው። በሷ እግር ተተክቶ እሱ ኑሮውን ሲያሻሽል እሷ ደግሞ ልታዝን ልትከፋ በመሆኑ ደስታው ሙሉ ደስታ አይሆንለትም ነበር፡፡ ሽመልስ የፈተናውን ውጤትና የተወሰነውን ውሳኔ እንደ ሰማ ሳይውል ሳያድር ነበር ስልክ ደውሎ የጠራው፡፡

“እንኳን ደስ አለህ ጌትነት ዛሬ መንፈሴ እጅግ የረካበት ቀን ነው። ዛሬ ለኔ ትልቅ የድል ቀን ነው፡፡ ዐባይነህን ከመሰለ ዝሆን ጋር ታግዬ ልጥለው የቻልኩት በፈጣሪ ድጋፍና ባንተ ጥረት ነው። ሰራተኛው
በሙሉ ውጤቱን በጉጉት ሲጠባበቅ ነበር የከረመው፡፡ ግማሹ አድናቆቱን
ሲገልፅ ግማሹ ደግሞ የአቶ አባይነህ ቲፎዞ በመሆን ጭፍን ጥላቻውን
ሲያንፀባርቅ ቆይቷል። እንደዚያ መሆኑ ግን በነገሩ እንድገፋበት ብርታት
ሆኖኝ እንጂ አላንበረከከኝም፡፡ አንተም አላሳፈርከኝም፡፡ ይሄ የጋራ ድካማችንና የጋራ ውጤታችን ነው፡፡ ከዚህ በሁዋላ
የዚህ ድርጅት አባል ነህ ትንሽ ነገር ልበልህ፡፡ በተቻለህ መጠን ከስራህ በስተቀር ሰዎች ለተንኮል
ለሌለብነት እንዲያመቻቸው ከሚፈጥሩት ቡድን ራስህን ጠብቅ። ስራህን
አክብር፡ ስራህ ያከብርሀል፡፡ በአለቃህ ፊት ብቻ ሰራተኛ መስለህ ለመታየት አትሞክር፡፡ አለቃህን በስርዓቱ ማክበር የሥራ ድርሻህን በብቃት መወጣት ተገቢ ነው፡፡ በማጎብደድ በእወደድ ባይነትና በወሬ አቀባባይነት ለመሾም ወይም ለማደግ የሚፈልጉ ሰዎች አርአያም ተከታይም ከመሆን ግን ራስህን ጠብቅ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ አለቃህ ስራህ መሆኑን ጠንቅቅህ መረዳት ይኖርብሃል፡፡ የአቶ አባይነህ ቲፎዞዎችና አንዳንድ ጭፍን አመለካከት ያላቸው ሰራተኞች ሊጠሉህና ሊተናኮሉህ ይችሉ ይሆናል።
መተናኮል ብቻም ሳይሆን ፊት ለፊት ሊበድሉህ ወይም ሊያጠቁህ ይሞክሩም ይሆናል ነገር ግን ጥቃትን በመፍራት ህሊናህ የማይፈቅደውን ነገር ከመስራት መቆጠብ ይኖርብሃል። አንተም አንድ ቀን በሃላፊነት ቦታ ላይ ስትቀመጥ ምን ማድረግ እንዳለብህ ከዚህ ትምህርት ልትወስድ ይገባል። ለማንኛውም መልካም የስራ ዘመን ይሁንልህ" በማለት የምስራቹን ካበሰረውና ተገቢውን ምክር ከለገሰው በኋላ አቅፎ ጀርባውን ቸብ
ቸብ አደረገው።

"በእውነት ነው የምልህ ሽመልስ አዲስ ህይወት የፈነጠቅክልኝ ስለኔ ሆነህ ራስህን ጎድተህ የተሟገትክልኝ ምንጊዜም የማከብርህ ወንድሜ
ነህ፡፡ ዓላማዬ የተሰጠኝን የሥራ ሀላፊነት በአግባቡ በመወጣት ትምህርቴን መቀጠልና የተሻለ ዕውቀት በመገብየት ራሴንም ቤተሰቤንም አገሬንም መርዳት ነው። ወደፊት ይህ ሁሉ ምኞቴ ተሳክቶ ለበለጠ ሀላፊነት በቅቼ ስዎችን ለመጥቀም ወይንም ለመጉዳት በሚያስችል የሥራ ሀላፊነት ላይ የመገኘት ዕድሉ የሚገጥመኝ ከሆነ ካንተ ከወንድሜ ያገኘሁት ትልቅ ትምህርት ምንጊዜም ከአእምሮዬ የሚጠፋ አይደለምና ስለ እውነት ለመሥራት ቃል እገባልሃለሁ" አለው።

ጌትነት የቅጥር ፎርማሊቲውን አሟልቶ ጨረስ፡፡ ስራ ይዞ ስው ለመሆን
ያደረገው ረጅም ሩጫ ዳር በመድረሱና ራሱን ችሎ ሌላውን የመርዳት ህልሙ እውን በመሆኑ ደስታው ወደር አልነበረውም፡፡ ልቡ ወደ ባሌ ወደ እናቱ ዘንድ በረረች፡፡ እህቱ ዘይኑን በቅርብ ክትትል የማስተማር ዕቅዱን በማሳካት ጉጉት ተውጦ ወደ ትውልድ መንደሩ በሀሳብ ከነፈ ያንን አስደሳች ዜና ለእናትና እህቱ ሊያሰማቸው ተጣድፎ አቶ አለሙን ለማግኘት በየቀኑና ቅቤና ነጋዴው ከዲር ዘንድ ሲመላለስ ከቆየ በኋላ ቀናው። በመጨረሻ ላይ አቶ አለሙ ዠ መምጣታቸውን አረጋገጠና በከዲር
አማካኝነት ተገናኙ።

“ጌትዬ! አንተ?! ደህና ነህ?! እንደው ነፍስህ አለ ልጄ?" የእናቱን ናፍቆት
ጭምር እቅፍ አድርገው አገላብጠው ሳሙት፡፡
"ደስ ብሎኛል አባባ ደስ ይበልዎ! የድሃዋ እናቴ አምላክ ጥሎ አልጣለኝም። ሥራ አገኘሁ! ሁሉንም ነገር ጨረስኩ! ሁሉንም ነገር ጨረስኩ!”
ሁለመናው ስቆ ደስታውን ገለፀላቸው፡፡ አቶ ዓለሙ በደስታ ዘለሉ፡፡
"ጎሽ! ጎሽ! እሰይ የኔ አንበሳ! እንኳን ደስ አለህ! እንዴት ያለውን የምስራች ነው የነገርከኝ ባክህ?! እሰይ! እስይ! እኔም ገዳም ሆንኩ ማለት ነው፡፡ የምስራች ሰምቼ የምስራች አብሳሪ ሆንኩ ማለት ነው። ጭንቅጰሲለኝ የከረመው የሷ ጉዳይ ነበር፡፡ መልካም ዜና አመጣልሻለሁ እንዳልኳት እንደፎከርኩት ተሳካልኝ ማለት ነው። ደስታው የሁላችንም ነው!” ፍንድቅድቅ አሉ።

"አባባ ለመሆኑ የጤናዋ ነገር እንዴት ነው? ሃሳቡ ገድሏታል መቼም
ጭንቅ ጥበብ እያለው ጠየቃቸው
“ደህና ነች ምንም አትልም ያንተ ነገር ነበር ሲያሳስባት የከረመው ከንግዲህ በኋላማ ምን ትጠይቀኛለህ?
👍3