አትሮኖስ
286K subscribers
117 photos
3 videos
41 files
566 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
A:
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


....እሑድ ከሰዓት በኋላ.….ስለ ለጎ ሐይቅ ከተማና አካባቢዋ ኣንድ ባንድ ካወራችልኝ በኋላ የሕሊናዋን ትዝታ ወደ ደሲ መልሳ ስለ በርበሬ ገንዳ ሙጋድ፣ ዳውዶ ገራዶ፣ ሆጤ፤ ሶሳ፣ አዘዋ ገደል ሰኞ ገበያ…. ነገረችኝ፡፡ «ቆየኝ ደግሞ ሥራዬን ጨርሼ ልምጣና አወራልሃለሁ» ብላ ካልጋው ጫፍ ላይ ሸርተት ብላ ሔደች፡፡ ከግማሽ ሰዓት በኋላ ሥራዋን አጠናቃ ከተፍ አለች::ነጣ ያለ ቦላሌና ሰማያዊ ሸሚዝ ለብሼ አልጋው ላይ በጀርባዬ ተንጋልዬ
የጋሻዬነህን ሥዕል አንጋጥጬ ስመለከት ደረሰች፡፡ ሲሠውረኝ አላየችብኝም፡፡
ትከሻዬ ሥር ጣል አድርጌ ተኛሁበት፡፡ አልጋው ጫፍ ላይ ተቀምጣ በሆዴ
ላይ እጂን አሻግራ በመመርኮዝ ከደረቷ ዘንበል አለች፡፡ ትከሻዋ ላይ የነበረችው ባለ አረንጓዴ ጥለት ያንገት ልብስ ተንሸራተተችና የተዘረጋችውን እጅዋን ሸፈነቻት፡፡ ከደረቴ በታች የሆዴ አካባቢ በድንኳን ውስጥ ያላ ነጭ አግዳሚ መቀጫ መሰለ፡፡

ያን በሆዴ ላይ ዐልፎ አልጋው ላይ እንደ ካስማ የተተከለውን እጅዋን በቀኝ እጄ እያሻሽሁ ምናልባት ቅር ይላት ይሆን? በማለት ስፈራ ስቸር ከቆየሁ በኋላ የወዲያ፣ አንድ ነገር ብጠይቅሽ ቅር ይልሻል?» አልኳት፡፡ አሽቆልቁላ ዐይን ዐይኔን ትክ ብላ እያየች ምንስ ነገር ብትጠይቀኝ ምን ብዬ እቀየማለሁ? ስል ጠይቀኝ ልንገርህ? ብላ አቀማመጡዋን አመቻቸች።

ለሁለት ደቂቃ ያህል ውስጥ ውስጡን ሐሳቢን አንቀረቀብኩ፡፡ እንግዲህ
ያለችውን ትበል አልኩና «የወዲያ! ለምን አስታወስከኝ ኣትበይና፣ እናትና
አባትሽ ሲሞቱ የስንት ዓመት ልጅ ነበርሽ?» አልኳት። ፈገግታዋን የቅሬታ
ደም ስለ በረዘው ፊቷ ፈዞ የክረምት ዋዜማ መሰለ፡ ውስጥ ውስጡን ራሴን
«ጌታነህ! የተዳፈነ የኅዘን ረመጥ ጫርክ፣ ያንቀላፋ ኀዘን ቀሰቀስክ» ብዩ ወቀስኩ፡፡ ደቂቃዎች ሠገሩ። ትንሽ ፈነከነክ ብላ «ምነው ምን ነካሀና ኖረሀ ኖረህ ጠየቅኸኝ?» ብላ ፊቷን የትካዜ ዐመድ ነሰነሰችበት፡፡ ካኣሁን አሁን ትጀምራለች በማለት አሰፍስፌ ጠበቅሁ፡፡ ያን እንደ አተር እምቡጥ እበጥ ብሎ የቆየ የታች ከንፈሯን በላይኛው ውብ ጥርሷ ረመጠጠችው። አንድ ጊዜ
አፈትልኮ የተነገረን ሐሳብ መልሶ መዋጥ የማይቻል በመሆኑ ችሎታዩ ከዝምታ ሊያልፍ አልቻለም። እየር ስትስብና ስታስወጣ ከፍና ዝቅ የሚለውን
ደረቷን በመመልከት ላይ እንዳለ «አባቴ ሲሞት አንዲት ፍሬ ልጅ ነበርኩ
አሉ፡፡ ትንሽ ትንሽ እንደ ሕልም ትዝ ይለኛል፡፡ እናቴም አባትሽ ከልጆቹ
ሁሉ አንቺን ይወድሽ ነበር፡፡ ሳይንት እሚባል አገር ካሉት ዘመዶቹ መኻል
የሚወዳትን አክስቱን ስለምትመስዪ የእርሷ ነገር ሆነበትና 'የወዲያነሽ የወዲያ
ሰው ብሎ ስም አወጣልሽና የወዲያዬ የወዲያነሽ አልንሽ ብላ ነገረችኝ። ልጅ
ስለ ነበርኩ ሁሉንም ኣላስታውስም እንጂ አባቴ ብዙ ጊዜ ታሞና ማቆ ማቆ
ነው የሞተው። የሞተ ዕለት ሰዎች ሁሉ ሲያለቅሱ አይቼ እኔም ትንሽ
አልቅሻለሁ፡፡ ሞት ምን እንደሆነ ስለማላውቅ ሄዶ የሚመለስ እንጂ በዚያው የሚቀር አይመስለኝም ነበር፡፡ ሬሳውን በአልጋ ይዘው ከቤት ሲወጡ ምንም ስላልመሰለኝ ጉድሮዬን እያዘናፈልኩ ከመንደሩ ልጆች ጋር እቦርቅ ነበር፡፡
ታናሽ እኅቴ እማዋይሽ ክርስትና የተነሣች ዕለት መጥተው የነበሩት ቄሶች ራሱ የቀብሩም ዕለት መጥተው ስለነበር ለደስታ የመጡ እንጂ ለሌላ ነገር
የመጡ አልመሰለኝም። እያደር ግን ዋል አደር ስል ዕንጨት ለቀማም ይሁን
ዋርማ ይዤ ጅረት ስወርድ ጓደኛቼ እንደ ቀልድ 'አንቺዬ ማሳዘኗ' አንድ ቀን እኮ የሞቱት የዚች አባት ናቸው” እያሉ ሲያንሾካሽኩ እየሰማሁ ግራ ግብት ይለኝ ነበር። አባቴ ከሞተ በኋላ እዚያው አገር ቤት ከእናቴና ከእኅት ወንድሞቼ ጋር ቆየሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ግን የእናቴ ታላቅ እኅት ከአገር ቤት ወደ ከተማ ይዛኝ መጥታ ትምህርት ቤት አስገባችኝ ብላ ዝም ስላለች ያ በኀዘን ጉም ተሸፍኖ የቆየው ዐይኔ ቦግ ብሎ ወደ የወዲያነሽ ዐይኖች ተወረወረ፡፡እንባዋ እንደ አሸንዳ ጠፈጠፍ እየተንከባለለ በጉንጯ ላይ ተንኳለለ፡፡ ልብሴ ላይ የተንጠባጠበውን ዕንባዋን ደረቁ ሸሚዜ እንደ ግንቦት አፈር ጠጣው፡ የደቀነችውን ወሬ ለመጨረስ እንባዋን ካባበሰች በኋላ «አሁንም ቢሆን እነዚያ የትምህርት ቤት ጓደኞቼ ትዝ ይሉኛል። እነ የሻረግ፣ ዘነበች፡ አሚናት፡
ይመር፣ አያሌው፣ ገበያነሽ፣ ሰኢድ ኧረ ስንቱ ስንቱ... እክስቴ ከልጆቹ ሁሉ እኔን መርጣ የወሰደችኝ የረጋች ልጅ ነች፣ ደስ ትለኛለች» ብላ ነበር። ሁለት ሦስት ጊዜ ላግባ ባይ መጥቶ ሲጠይቅ ቆይ እስኪ ጥቂት ተምራ ነው ነፍስ ትወቅ» ብላ እምቢ አለቻቸው፡፡

እኔና እርሷ ብቻችንን ተቀምጠን በምናወራበት ጊዜ ግን፡ ያም የሸማኔ ልጅ ነው፣ ያኛው መናጢ ዘረ ድሃ ነው፣ የዚያኛውም እናት ዘር ማንዘሯ ሸክላ ሠሪ ነው የጠዳ የጨዋ ልጅ እስኪመጣ ሰጥ ብለሽ ትምርትሽን ተማሪ» ትለኝ ነበር፡፡ አክስቴ ከምላሷና ከንዝንኳ በስተቀር ሆዷ ባዶ ነው::ባልዋ አይዋ ዘለቀ አንድ ሲናገሩ ሁለትና ሦስት ነበር የምትመልስላቸው:: ችለው ችለው አንድ ቀን የተነሡ ለታ ግን ቀሽልደው ቀሽልደው ሲለቋት ውሃ ውስጥ የገባች አይጥ ትሆናለች። እሷ ታዲያ የሳቸውን እልክ በኔ ላይ ነበር የምትወጣው::

«አንቺ መድረሻ ቢስ ግንባረ ነጭ» ብላ ከጀመረች በርበሬ ሳታጥነኝና በጥርሷ ሳትበተብተኝ እንገላገልም፡፡ «አፈር ብይ! አፈር ያስበላሽ! ያባትሽን ቀን ይስጥሽ» ስትለኝ ግን አይመኙ ነገር ያስመኘኝ ነበር። ለጎ-ሐይቅ በሔድኩ በአራተኛው ዓመት አገር ቤት ወረርሽኝ ገባ ተባለና እናቴ በጠና ታመመች።ያኔውኑ ትምህርት ቤት በመዘጋቱ ካልሔድኩ ብዬ አገር አመስኩ፡፡ ቢሉኝ ቢፈጥሩኝ እዚያቹ ከናቴ
ጋር እሞታታለሁ እንጂ እይደረግም ብዬ
አስቸገርኩ፡፡ በማይረባው ነገር ሁሉ ካክስቴ ጋር መነታረኩ መሮኝ ስለ ነበር
ለጥቂት ጊዜም ቢሆን ከፊቷ ገለል ብዬ እፎይ ማለት ፈልጌ ነበር። ወሬ
አበዛሁብህ መሰል? ላሳጥርልህ፣ እናቴ ቡሄ በዋላ ልክ በሳምንቱ ሞተች። ያን
እለት የሆንኩትን አኳኋን ግን ባትሰማው ይሻላል። እናቴ ፀሐይነሽ አማረ ትባል ነበር። ከዘመዶቻችን ጋር ዕርባዋን አውጥቼ ትምህርት ቤት የተከፈተ
በሳምንቱ ከዚያቹ ከአክስቴ ጋር ወደ ከተማ ተመለስኩ፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ወደ
አገር ቤት አልተመለስኩም» ብላ ጋደም አለች፡፡ ያ የቀድሞ ውበታዋም ርዝማኔውን ሊይዝ ጥቂት የቀረው የሴትነቷ ግርማ የሆነው ዞማ ጸጉሯ በአንገቷ ዙሪያ በተንተን ብሎ ተነሰነሰ። ድንገት
ቀና ብላ እግሯን ኮርምታ ተቀመጠች፡፡ «አልጨረስኩልህም እኮ» ብላ
ቀጠለች። በበኩሌ የሕይወቷ ምሬት አንገፍግፎኝ ነበር፡፡» ያክስቴ ባል ዘኃ
ነጋዴ ነበሩ። ከደሴ ዘኃ ያመጡና፣ ከሐይቅ ደግሞ አንጋሬና ቆዳ ይዘው
ይመለሳሉ። የኋላ ኋላ ግን ደሴ መሬት ገዝተው ቤት ስለሠሩና ንብረት ስላበጁ ሁላችንም ወደዚያው ሄድን። ደሴ ወይዘሮ ስሒን ትምህርት ቤት አምስተኛ ክፍል ገባሁ፡፡ ያነዩ ገና ዐሥራ አራት ዓመቴ ነበር፡፡ አክስቴ ውሃ ቀጠነ፣ ጪስ በነነ፣ እያለች ስለምትነዛነዝ ይብስ እሳትና ጭድ ሆንን። እልህ ማብረጃ አረገችኝ፡፡ ስወጣም ስገባም ስድብና ዱላ ሆነ፡፡
ለጊዜውም ቢሆን ሌላ የሚያስጠጋኝና የምገባበት ዘመድ ስላልነበረኝ ያለችውን ብትል ታግሼ ዝም አልኩ፡፡ እንደ ምንም ብዬ ተፍጨርጭሬ ሰባተኛ ክፍል እንደ ገባሁ ከነከተቴው ሒጂልኝ! ውጪልኝ! ዐይንሽን ላፈር! ማለት አመጣች። ንግግሯ ሁሉ አንገሸገሸኝ፡፡ የዓመቱ ትምህርት ባሳር በመከራ ካለቀልኝ በኋላ ብሞትም ልሙት ብዩ ቆርጬ ተነሣሁ አንድ ቀን
ጎረቤታችን የነበሩ አንድ የጦር
👍7
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

....በዝናሙ ምትክ ፀሃይዋ ክርር ያለ የሚያቃጥል ጨረሯን መፈንጠቅ
ጀምራለች። ዶሮዎች በየስራስሩ፣ በየበረቱ አጥር ስር እየተሹለከለኩ ይለቃቅማሉ.. አልፎ አልፎ ከቤት ወስጥ የታሰሩ ጥጆች ድምጽ ይሰማል።
ከብቶች በየዛፉ ጥላ ስር ቆመዋል፡፡ ከዚህ ሌላ ግን ምንም አይነት ድምፅ አይሰማም፡፡ ጭር... ያለ ጭውው…. ያለ ፀጥታ!! የጌትነት መንደር በሬሳ! ሰሞኑን ጤናዋ በይበልጥ የተቃወሰውና ሃሳብ ያመነመናት አስካለ ልብሷን እንደለባበሰች ከአልጋዋ ላይ ጋደም ብላለች። ዘይኑ ከቤት አልነበረችም፡፡ ከወዲያኛው መንደር ተልካ ሄዳለች፡፡

"ካ ካ.!ካ ኩ!ኩ.ኩ!.ካ!.ካክ! ኩ! ኩክ! " ዶሮዎቹ ተንጫጩ።
“ድመት!ድመት! ሸለምጥማጥ! ሽለምጥማጥ ወስዳት ይዟት ሮጠ" የወይዘሮ አስካለ ጎረቤት የወይዘሮ ተዋበች ትንሿ ሴት ልጅ ጮኽች።
የአስካለ ዶሮ ናትኮ! ጠልፏት ሄደ? እነሱ ቤት የሉም እንዴ? እዚህ ቤቶች! ዘይኑ ኽረ ዘይኑ!.ማንም ሰው የለምንዴ?" ወደ በሩ ተጠጉ፡፡

"ማነው? ይግቡ አለሁ ይክፈቱት በሩን..." አለች በደከመ ድምፅ፡፡
“ምነው? ባሰብሽ እንዴ? አይይ.. በጣም አሞሻል ለካ?! ደምሽ ሁሉ ከፊትሽ ላይ ምጥጥ ብሎ የለምንዴ?! ዘይኑ የለችምንዴ? እኔ ኮ አሁን ልጅቷ ዶሮዋን ወስዳት ብላ ስትጮህ ነው የወጣሁት። እሳት ላይ ምናምን ጥጃለሁ"
"ምን ወስዳት?” አለች በቀሰስተኛ ድምጽ።
"ሽለምጥማጥ ነዋ! ድመት! ድመት! ስትለኝ ሮጬ ብወጣ ይዟት ቁልቁል
ሲሮጥ አየሁት። ለትንሽ አመለጠኝንጂ ቀድሜ ብወጣ ኖሮ አስጥለው ነበር። ደግሞ መርጦ ያንን ወስራውንኮ ነው የጠለፈው"
"ይልቀማቸው ጥርግ ያድርጋቸው!.." አለች በታከተ አነጋገር፡፡
"አንቺ ሴት ራስሽ ነሽኮ ይሄንን ሁሉ ችግር በራስሽ ላይ የምታመጪው። ከበሽታው የበለጠ የጎዳሽ ሀሳቡ ነውኮ! ለመሆኑ ከዚያ ወዲህ ስለ ጤንነቱ የሰማሽው ነገር አለ?"
“ምን እስማለሁ እትዬ ተዋቡ?ጋሼ አለሙም ይኸውና ብቅ አላሉም፡፡
ምን አባቴ እንደማደርግ ግራ ግብት ብሎኝኮ ነው። አገሩን አያውቅ ሰው
አያውቅ አንድ ቶሎሳን ብሎ ነው እኮ እንደ ወፍ ብርር ብሎ የወጣው።
እኔን ብርር ያድርገኝ፡፡ እኔ ልንከራተት። የአባቱ ሀዘን ከአንጀቱ ሳይወጣለት ከአገሩ ወጥቶ ሄዶ በማያውቀው አገር ቶሎሳ ደጅ አውጥቶ ከጣለው ምን ይውጠዋል እትዬ ተዋቡ? ምን አልኩት ፈጣሪዬን? አይይ”በትኩስ እንባ ምክንያት ማዲያት በጀማመረው ፊቷ ላይ እምባዋ ክንብል አል።
ተይንጂ የጌትነት እናት ምን እያደረግሽ ነው? በደህና ውለሽ እኔ ስመጣ ነውንዴ የሚብስብሽ? እስቲ ምን ሰማሁ ብለሽ ነው እንዲህ የምትሆኚው? ለትንሽዋም ቢሆን እዘኝላት እንጂ! ባንቺ ለቅሶ ትጨነቅ? በወንድሟ ናፍቆት ትጨነቅ? ወይስ በአባቷ ሀዘን? ተይ የኔ እህት እንደዚህም አይደል ጠና ጠና እያልሽ የሆድሽን በሆድሽ ይዘሽ ሀዘንሽን ደብቀሽ
ደስተኛ መስለሽ እሷንም አጽናኛትንጂ!. ዘይኑ ዕድሜዋ ትንሽ ሆነንጂ
አስተሳሰቧ ትልቅ ነው። ወይኔ አባቴ ወይኔ እናቴ እንድትል አታድርጊያት፡፡ አመዛዝኝ

“አይ እትዬ ተዋቡ መቼ እሱን ሳላስበው ቀረሁ ብለው ነው? ሆዴ እያረረ ጥርሴ ለመሳቅ እየታገለ አቃተኝንጂ፡፡ እንቅልፍ በዓይኔ አልዞር እያላ እህል አልዋጥልሽ እያለ አስቸገረኝንጂ ጉልበቱ ጥናቱ ከዳኝንጂ ለዘይንዬ መቼ ሳላስብ ቀረሁ? እህህህ.."

“በይ ነግሬሻለሁ ለቅሶሽን አቁሚ! ፈጣሪሽን እየለመንሽ አንተ ርዳው
እያልሽ በፀሎትሽ መበርታት ነው የሚያስፈልገው፡፡ ደስ ደስ ሲልሽ ደስ
የሚል ዜና ትሰሚያለሽ፡፡ በበሽታሽ ላይ ሌላ በሽታ መጨመሩ ላኔ አይታየኝም፡፡ እስቲ በወጉ ጋደም በይና የሚቀመስ እህል ይዤልሽ ልምጣ ነጠላውን አለባበሷትና ወጡ። ወዲያውኑ ዘይኑ ከተላከችበት ተመለሰች::

“እማምዬ ምን ሆነሽ ነው ዐይንሽ ያበጠው? አልቅሰሻል አይደለም?” አኮረፈች።
አይደለም! አላለቀስኩም! ዶሯችንን ሸለመጥማጥ ይዟት ሲሮጥ እሷን
ለማስጣል ስወጣ ጨረር ዐይኔን ወጋኝ መሰለኝ" ልትዋሻት ሞከረች::
"አላውቅም ውሽትሽን ነው፣ ውሸትሽን ነው እያለቀስሽ ነው ፊትሽ እንደዚህ የተበላሸው።አንቺ እያለቀስሽ ለመሞት ነው የምትፈልጊው" ከንፈሯን የበለጠ ጣለች፡፡
“ዘይንዬ አላለቀስኩም ስልሽ? ለምን አለቅሳለሁ? ደስ ይለኛልንጂ! አሁን
ጋሼ አለሙ ሲመጡ ጌትዬ የጻፈልንን ደብዳቤ ይዘውልን ይመጣሉ።
ከቶሎሳ ጋር ታርቀናል ሥራም ይዣለሁ ብሎ የጻፈውን ደብዳቤ ይዘውልን እንደሚመጡ አትጠራጠሪ! ከዚያም ጌትዬ አንቺን አዲስ አበባ ወስዶ
ሲያተምርሽ ይታየኛል” እንደ ልማዷ እቅፍ አድርጋ ስታረሳሳት የእናቷ ጉያ ሞቃት። ፀጉሯን እያከከችላት እቅፍ ስታደርጋት በዚያው ልጥፍ እንዳለችባት እንቅልፍ ያባብላት ጀመር፡፡
“እማምዬ ወንድም ጋሻ ሥራ ሲይዝ ሁለታችንም እሱ ጋ አዲስ አበባ
ሄደን አብረን እንኖራለን አይደል?" የሟች ባለቤቷን የአደራ ቃል አስታወስቻት አስካልዬ ባለተራ ሆነሽ ወደኔ ስትመጪ ከጎኔ እንዳትርቂ አደራ! " ከባሏ ጋር ብዙ ትዝታ ያሳለፈችባትን ጎጆ ጥላ የትም እንደማትኖር ታውቀዋለች፡፡ ሬሳዋ ከዚያው ባለቤቷ ካረፈበት አልጋ ላይ እንደሚነሳ በልቧ ቢታወቃትም ዘይኑን ልታስደስታት ፈለገች።

“ታዲያስ ምን ጥርጥር አለው? ጌትዬ ሥራ ይዞ እኔንም አንቺንም አዲስ አበባ ወስዶን ደስ ብሎን አብረን እንኖራለን ምን ይጠየቃል?”
ስትላት ዘይኑ በደስታ ተፍነከነከች። በዚሁ መሀል.. "ሴቶች" አሉና ገቡ።
ወይዘሮ ተዋቡ ነበሩ።
“ዘይኑ መጣሽ እንዴ? በይ እስቲ ቀና በይ የጌትዬ እናት ይህችን ቅመሽ በሽሮ ፈትፈት አድርገው ያመጡትን እንጀራ በግድ ያጎርሷት ጀመር መቼም ከሩቅ ዘመድ የቅርብ ጎረቤት መድሀኒት ነው የሚባለው እውነት ነው። የምግብ ፍላጎቷ ጠፍቶ ባዶ ሆዷን ነበረች፡፡
አይ እትዬ ተዋቡ ምን አሳሰበሁ? አልበላ አለኝንጂ ዘይንዬ የሰራችው ሽሮ ነበርኮ አይ የርስዎ ነገር?” የምግብ ፍላጎቱ ባይኖራትም የሚያስቡላት ጎረቤቷን ላለማስቀየም ስትል ጎራረስች፡፡ እናቷ በጤናዋ ምክንያት እንደ ልቧ ወዲህ ወዲያ ማለት ባለመቻሏ ከትምህርት ቤት ሰዓት ውጭ ዘይኑ ወደ ገበያ ትሄድና ሽንኩርቱን፣ ድንቹን፣ ቃሪያውን፣ ጎመኑን እየሽጠች በምታገኛት ሳንቲም እናቷን ታስታምማለች። ካሉት ሁለት ላሞች
መካከል አንዷ የምትታለብ ስለሆነች ወተቷን ያጠራቅሙና ከተናጠ በኋላ
ለአናት የሚሆን ቅቤ በኩባያ እያደረጉ ወደ ገበያ ይወጣሉ፡፡ አሬራው ይቀ
ቀልና አይቡ ይሽጣል። አጓቷን እነሱ ይጠጣሉ፡፡
“እማማ ይህቺ እማዬን ለምንድነው የማይመክሯት? ሁልጊዜ እያለቀስች ፊቷን አበላሸችውኮ የምሰራላትን ደግሞ አልበላም እያለች ታስቸግረኛለች፡፡ ሁል ጊዜ ቡና ብቻ ነው የምትጠጣው" እንደ ልማዷ ከንፈሯን ጣል አድርጋ ወቀሳዋን ሰነዘረች። ወይዘሮ ተዋቡ የልጅቷ ነገር አንጀታቸውን በላው። ዘይኑ በአስተሳሰቧና በአነጋገሯ የአስራ ሁለት ዓመት ልጅ
አትመስልም፡፡ ነገረ ስራዋ እንደ አዋቂ ነው።

"የውልሽ የጌትነት እናት እንኳን እኛ አሮጊቶቹ ትንሽዋ ልጅሽ የምትልሽን ትሰሚያለሽ? እሷኮ እየበለጠችሽ ነው። መኩሪያንም ቢሆን መከራሽን አይተሽ አስታመሽው የግዜር ፈቃዱ ሆኖ ነው ወደ እውነቱ ቦታ የሄደው፡፡ መቼም ሰው ጊዜው ከደረስ ምን ይደረጋል? በሀዘን ብዛት
በለቅሶ ብዛትም ከአፈር የሚነሳ የለም፡፡ ጌትነትንም ቢሆን የልቡ እንዲሳካለት መርቀን የሸኘነው ራሱን ችሎ ላንችም አለኝታ እንዲሆንሽ ነው።
ባለበት ጤና ይሁን እንጂ ምን እንዳይሆን ብለሽ ነው? ሰው ሆኖ ችግርን
የማይቀምስ የለም ችግርን አሽንፎ ደካማ እናቱን መጦር እህቱን ማስተማር እንዲችል በፀሎትሽ ያለመርሳትንጂ
1👍1