#የወድያነሽ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል
...ለቤት ወጪ እያልኩ ከምሰጣት ገንዘብ ላይ እያብቃቃች ልዩ ልዩ ተጨማሪ የማድ ቤት ቁሳቁሶች ገዛች፡፡ ዕቃዎቹ ሳይሆኑ ቁጠባዋ አስደሰተኝ።
የወዲያነሽ' ዛሬ የማድረው ወላጆቼ ቤት ነው፡፡ ስለዚህ እንዳትሠጊ ትፈሪያለሽ እንዴ?» ብያት በምሄድበት ጊዜ «ለእኔ ብለህ እኮ ተሠቃየህ ወይ አበሳህ» በማለት ራሷን ታማርራለች፡፡
ከዋል አደር የወህኒ ቤቱን ሕይወቷን እየረሳች አዲሱን ኑሮ ተላመደች::
ፈገግታዋ" ለዛና ጨዋታዋ ቀስ በቀስ ጎረፈ፡፡ እኔ ግን ወላጆቼ እንዳሰቡትና
እንደ ተመኙት ሳይሆን፣ ማንም ሳያውቅና ሳይሰማ፣ ጠላ ሳይጠመቅ፣ ጠጅና
ፍሪዳ ሳይጣል፣ ድንኳን ሳይተከል፣ ዕልልታና ሆታው ሳይቀልጥ፣ ጉልበት ስማ ሳልመረቅ፣ ከአንዱ የመከራ ጊዜ ጓደኛዬ በስተቀር ሚዜ ሳልመርጥና
ሳልመለምል፣ ሞላ ጎደለ ብዬ ሳልማስን፣ የእኔ ናት ብዬ ያመንኩባትንና ሕሊናዬ
ሙሉ በሙሉ የተቀበላትን የወዲያነሽን የኑሮ ጓደኛዪ ኣድርጌ ጎጆ ወጣሁ፡፡
ወደዱም ጠሉም የወዲያነሽ የሕይወቴ ምሰሶ ሆና በይፋ ብቅ የምትልበት ብሩህ
ቀን መምጣቱ አይቀርም፡፡
የተከራየነው የጉልላት አጎት ቤት አርጀትጀት ያለ በመሆኑ ግድግዳው
ላይ የተለጠፉት የአዲስ ዘመንና የሰንደቅ ዓላማችን ጋዜጦች ተገሽላልጠው ፀሐይ
እንዳጠቃው የሙዝ ቅጠል ዐልፎ ዐልፎ ተሽመልምለዋል። ምርጊቱ ላይ ተለጥፈው የተጋደሙት የጤፍ ጭዶች ይታያሉ፡፡ ያም ሆነ ይህ የወዲያነሽ
አብራኝ ስላለችና አብሬያት ስላለሁ ያለሁትና ያለችው በፍቅር ውብ እልፍኝ
ውስጥ ነው፡፡ ከፋ ሲለኝና ሐሳብ ሲያስጨንቀኝ ግን «የሕይወት ጥቀርሻ» ማለቴ አይቀረም፡፡
ምንጊዜም ቢሆን ጉልላትና የወዲያነሽ ባንድ ላይ ተቀምጠውም ሆነ ቆመው ሲያወሩ ደስ ይላሉ። የናቴ ልጅ እንኳ እንደ ጋሼ ጉልላት አይሆንልኝም፣ ጋሼ ጉልላት! ጋሼ ጉልላት ያንጀት ናቸው» ትላለች፡፡
ዓርብ ማታ ነበር፡፡ የወዲያነሽ ከተፈታች 17 ቀን ሆኗታል፡፡ ጉልላት ጀምሮልኝ የነበረውን ሐሳብ «ያም ሆነ ይህ ያለፈው ሁሉ ዐልፏል። የመጪውን ጊዜ ኑሮ ለማስተካከል ከባድ ጥረት ያስፈልጋል» አለና ዝም አለ። ዝም የማለትም
አመል አለበት። ይህን ተናግሮ እንደ ጨረሰ ሐሳቡን እያሰላሰልኩና እየሸነሸንኩ
በማሰብ በቆምኩባት መሬት ላይ የተተከልኩ ይመስል ውልፍት ሳልል ብዙ
ደቂቃዎች ቆየሁ፡፡ የሰበሰቡን አራት ማዕዘን አግዳሚ ዕንጨት እንደያዝኩ ትንሽ ቀና ብል ምሥራቃዊውን የበጋ ሰማይ ባዘቶ የሚመስል ደመና እዚህና እዚያ ጉች ጉች ብለውበታል። በውስጡ በሚከናወነው የአየር ግፊት ሜክንያት ደመናው ተለዋዋጭ ቅርፆች እየሰራ ወደ ምእራብ ተጓዘ።ደመናው ወደ ምእራብ በገሠገሠ ቁጥር የተለያየ ውበትና መጠን ያላቸው ከወክብት ወደ ምስራቅ የሚጓዙ ይመስላሉ ደመናው ጥርግ ብሎ ከሄደ በኋላ ግን እንደ ነባር አቀማመጣቸው በየነበሩበት ቀጥ ብለው ይቀራሉ።የእኔም ሐሳብ ይጓዝ ይክነፍ ይመጥቅ ይውዘገዘግና አንዲት ተራ የሐሳብ ድንበር ሳያገኝ ቀጥ ይላል።
የእናቱን ጡት እያነፈነፈ እንደሚፈልግ የውሻ ቡችላ ሐሳብ ሲያነፈፍ የቆየው ጉልላት እንግዲህ» ብሉ ንግግሩን ጀመር ሲያደርግ ወደ እርሱ መለስ ብዬ ማዳመጥ ጀመርኩ። በሕይወት ውስጥ ባሉት የኑሮ ጐዳናዎች በምትጓዝበት ጊዜ የሚያጋጥሙህን ፈተናዎችና ትግሎች ሁሉ ሳትሸሽና ሳታመነታ መታገል ይገባሃል፡፡ በዕንባዋ የሚረጥቡት ዐይኖቿ ያሳዝኑኛል፡፡ሥቃይዋ ይመረኛል' ማለት በቂ አይደለም፡፡ ማዘን ቢሉህ ማዘን አይምሰልህ።አንድ ምጽዋት ሰጪ ሃይማኖተኛ የሰማይ በር ያስከፍትልኛል ለሠራሁት ኃጢአት መደምሰሻ ይሆንልኛል ብሎ ለአንድ ለማኝ ቁራሽ ሲሰጥ ያዝናል፤ ያን በማድረጉ የራሱን የማይታይ ሥውር ጥቅም ጨመረ እንጂ ለማኙን ከራሱ
ጋር አላስተካከለውም፡፡ አድርግም ቢባል እሺ አይልም፡፡ አንተ ግን ከዚህ የተለየህ
ሁን። አሁን በምትኖርበት ኅብረተሰብ ውስጥ የመልካም ኑሮዋ ጀንበር
እንድትወጣና እንድትጠልቅ የምታደርጋት አንተ መሆንህን ዕወቅ።
«እኔም ራሲ ማን መሆኔን ለማወቅ የምችለውና ምግባሬን አሻግሬ
በማየት እኔነቴን ለማወቅ የምበቃው የአንተን የትግል አረማመድና ውጤት
እየተመለከትኩ ነው» ብሎ በእኔ ላይ ሙሉ እምነትና ተስፋ እንዳለው ለማረጋገጥ ረጋ ባለ ሁኔታ ምራቁን ውጦ ዝም እለ፡፡ እንደገና ከወደ ምሥራቅ የመጣው ደመና የከዋክብቱን ብርሃን እየጋረደው ሲሄድ አካባቢያችን ግራጫ ጨለማ አለበሰው።
በየወዲያነሽ ሕይወት ላይ የደረሰውን የመጥፎ ልማድ ውጤት ሁሉ በማስወገድ ሌላ አዲስ ትርጉምና ይዞታ እንዲያገኝ ለማድረግ የገባሁትን የተግባር ቃል አሳጥፈውም፡፡ መሸከም የሚገባኝን ቀንበር ከዛሬ ጀምሬ እሸከማለሁ፡፡ ሆኖም
ድል ማድረግ አለብህ ማለት ሳይሆን የሚጠብቀኝን ተቃውሞና የቤተሰብ መራር አንካሰላንትያ እንድታውቅልኝ ያስፈልጋል” አልኩና እንደ አዲስ ትክል የቤት ምሰሶ ቀጥ ብዬ ቆምኩ፡፡
ጉልላት ራሱን እየነቀነቀ ወደ ቤት ገባ፡፡ ተከትዬው ገባሁና አጠገቡ ተቀመጥኩ፡፡ የወዲያነሽ የጣደችው ሻይ እየተንተከተከ እንፋሎቱ አየር ውስጥ እየገባ ይዋጣል፡፡ እሷ እንገቷን ደፍታ በጎድጓዳ ሳህን ውስጥ የሻይ ስኒ ታጥባለች፡፡
አሮጊቷ ሠራተኛ ትንሽ ራቅ ብለው ጉልበታቸውን ኣቅፈው ያንጎላጃሉ፡፡
በጣም ጫን ሲላቸው ለሰስተኛ ንፋስ እንደምታወዛውዛት መቃ ወደ ጎን ወይንም ወደ ፊት ጠንቀስ ይሉና ደንገጥ ብለው ቀና ሲሉ ትናንሽ ዐይኖቻቸው ብልጭ ብለው ይከደናሉ፡፡ ሻዩ ተቀድቶ ቀረበልን፡፡
ጉልላት እንፋሎቱ እየተነነ የሚወጣውን ሻይ እየተመለከተ «እኔ እኮ የምልህ» ብሎ ንግግር ጀመረ የሁለታችን ጠንካራ ፍቅርና አንድነት ብዙ ነገር መጀመርና መፈጸም የሚችል መሆን አለበት፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ እብራችሁ
መታገልና የሚያጋጥማችሁ የጋራ መሰናክል ሁሉ ሽንጣችሁን ገትራችሁ
መቋቋም እንጂ መሽሽና ያላግባብ ማፈግፈግ የእናንተ ድርሻ መሆን የለበትም፡፡
በተለይም አንተ እሷን እያጠናከር ክና ሳትነጠል ለአዲስ ዘላቂ ግብ
የሚገሠግሥ እውነተኛ ዓላማ እንዳለሁ አሳይ። አንተ በኑሮህ እና በትምህርትህ
ምክንያት የተሻለ ዕውቀትና ችሎታ አለህ፡፡ ምሳሌዩ ቅር እንዳያሰኝህ እጂ
ቀላዋጭ የሚቀላውጠው የአስቀልዋጩን ያህል ስለሌለው ወይም በግልጽ በሥውር ስለ ተነጠቀ ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ አግዛት፣ አብራህ ትሠለፋለች::
ዓርማህን በፅናት ለመትከል ካልተጣጣርህና አካባቢህንም ለመለወጥ እምነትህን ካላስፋፋህ የጥንቱ ልማድ እንደ ክፉ አውሬ አሳዶ ይበላሃል። የበሰለ ሕሊና ያለው ሰው የምትሰኘውም ብዙዎችን ላስቸገረ ከባድ ጥያቄ መልስ ለማግኘት ስትል ከራስህ አልፈህ በተግባር የሚተባበሩህን መልካም ሰዎች በማፍራት ለዘላቂ መፍትሔ ስትታገል ነው፡፡ የዚህን የአሁኑን ሕይወት ቅርፅና ይዘት መለወጥ ያስፈልጋል። አሮጌውንና ለሕዝብ የማይጠቅመውን ነገር ሁሉ እያፈራረሱ በአዲስ የአኗኗር ስልት መተካት ይገባል፡፡ ግን አፈጻጸሙ እንደ አወራሩ ቀላል አይደለም» ብሎ በንግግሩ መኻል በረድ ያለችውን ሻይ መጠጣት ጀመረ፡፡
የወዲያነሽ ጉልላት ስለ እኔና ስለ እርሷ እንደ ተናገረ ስለ ገባት የመጨነቅ ሁኔታ ፊቷን ወረረው:: በስኒው ውስጥ የቀረችውን ሻይ ጨለጠና
የወዲያነሽን አሻግሮ እያየ «አንቺም ከእንግዲህ ወዲህ ነቃ ነቃ በይ! ይኸ ዐይን እስኪያብጥ እያለቀሱ አጉል መተከዝ በፍፁም አይጠቅማችሁም፡፡ ምንም እንኳ እንዳንቺ ወህኒ ቤት ገብተን ባንታሰርም እኛም ያንችኑ ያህል ከውጪ ሆነን ተሠቃይተናል። ሐሞትሽን ኮስተር አድርገሽ ለመታገል ከበረታሽ መልካሟ
የቤትሽ እመቤት አንቺ ብቻ ነሽ» ብሎ ጠበል እንዳልጠቀመው በሽተኛ ሻይ
እንዳስሞላለት

👍4
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...በደሳሳዋ ጎጆ ውስጥ ከወዲያ ማዶ ጥጉን ይዞ ተቀምጧል። ጋቢውን
አፍንጫው ድረስ ተከናንቦ አረቄውን ይጨልጣል። የሚያውቀው ሰው
ድንገት መጥቶ እንዳያየው እየተጠራጠረ ዐይኑን ብቻ በጋቢው አልሽፈነም እንጂ ሁለመናው ጋቢ ለብሶ እሱነቱን ለማወቅ እጅግ አስቸጋሪ ነበር፡፡ ከፊት ለፊቱ የተገተረውን የአረቄ ጠርሙስ አንገት አሁንም አሁንም እያነቀ በብርጭቆው ውስጥ ከደፈቀው በኋላ እንደ ጠላ አናቱ
ድረስ እየሞላ ቁልቁል ያንደቀድቀዋል፡፡ ጎንቻ ቦሩ በሌብነት ያገኘውን ገንዘብ እንደ ልቡ እየተምነሸነሸበት ነው። የዐይኑ ሲሳይ ዓለሚቱ፥ የልቡ ትኩሳት ዓለሚቱ፣ የስሜቱ ረመጥ ዓለሚቱን በተስፋ እየተመኘ፣ ዐይን ዐይኖቿን በማየት ብቻ ርካታ እያገኘ ስለሚውል ከዚያች ቤት ጠፍቶ አያውቅም፡፡ በውርርድ ከዚያች ቤት አይታጣም። ዋ! የአይን ፍቅር ክፉ...
ጎንቻን ክፉኛ ለክፎት የጎጆዋ ጠባቂ የዓለሚቱ ፍቅር የቁም እስረኛ ሆኖ
ተተብትቧል።
ጎንቻ የቶላን ከብቶች ሰርቆ እጅ ከፍንጅ በመያዙ ከፍተኛ የውርደት ስሜት ተሰምቶታል።የዘረፋቸውን ከብቶች ሳይቸበችባቸው በመቅረቱ በቀል እና ቁጭት ሲያተክኑት ሰንብተዋል። የቶላ ሁኔታ እጅግ አድርጎ አንገብግቦታል፡፡ በህይወቱ ሙሉ የዚያን አይነቱ ክፉ ቅሌት ደርሶበት አያውቅም ነበረና ያንን በአደባባይ ያጋለጠውን፣ ለገበያ በወጣ ህዝብ መሀል የለበሰው ጋቢ በአየር ላይ ብን እስከሚል ድረስ እየወደቀ እየተነሳ እንዲፈረጥጥ ያደረገውን ሰው ለመበቀል ሌላ የወንጀል ጥንስስ ሌላ የውንብድና ስራ ለመፈፀም ተመኘ፡፡ ሌብነቱ የወለደውን ቅሌት ሌብነቱ ያስከተለበትን ውርደት ለማካካስ የሰው ህይወት ማጥፋትን የሰው ጉሮሮ ፈጥርቆ
የመግደል ምኞትን አሳደረበትና የበቀል ካራ በልቡ መሳል ጀመረ፡፡
ቶላ ንብረቱን ለማዳን፣ ትዳሩን ለመታደግና ባሳደጋቸው ከብቶቹ አንገት
ላይ ካራ እንዳይገባባቸው መሯሯጡ በጎንቻ ዘንድ ይቅር የማያስብል
ወንጀል ሆኖ ተገኘና ህይወቱን ሊቀጥፈው በሆዱ ማለ፡፡ ይህን በሚያስብበት ጊዜ ደግሞ የዓለሚቱ ነገር አለና ልቡ ለሁለት ተከፈለ።ግድያ ከፈፀመ አረቄ ቤት ሄዶ ዐይን ዐይኖቿን በማየት የአይን ፍቅሩን መወጣት አይችልምና ልቡ ፈራ። ዓለሚቱ በላይነህ ጠይም የሚያጓጓ መልክ እና ቁመና ያላት የአረቄ ሻጫ የወይዘሮ ባንችይደሩ ልጅ ስትሆን የሁለት ልጆች እናትና ባለትዳር ነች። ዓለሚቱ እናቷን በስራ ለመርዳት ምንጊዜም ከቤታቸው አትጠፋም፡፡ በተለይ መልከ ቀናነቷ የብዙ
ዎቹን ጠጪዎች አይን ስለሚስብ ለገበያቸው መድራት ዓለሚቱ አይነተኛ ምክንያት ነበረች፡፡ ጎንቻ ግን ይህንን ሁሉ አያውቅም ነበር፡፡ ባለትዳር መሆኗን ሳያውቅ በፍቅር ወደቀ፡፡ ያውም በህይወቱ ውስጥ የመጀመሪያው በሆነው የሴት ልጅ ፍቅር ጎንቻ በቶላ ከብቶች ስርቆት ላይ ተይዞ ከደነበረ ጊዜ ጀምሮ በፍፁም ያልቀናው ቢሆንም አረቄ የሚጠጣበት ገንዘብ ግን አላጣም፡፡ ጠዋትና ማታ ከዚያች አረቄ ቤት ውስጥ በመመሸግ በቋሚ ደንበኛነቱ የወይዘሮ ባንቺደሩን ልብ መማረክ ቻለ፡፡ ከዚያም
ዓለሚቱን ቀስ በቀስ እየቀረባት እየተላመዳት ሄደ። አንደበቱን እያፍታታ
የዐይን ፍቅር እስረኛነቱ ቀስ በቀስ እየለቀቀው ድፍረት እያገኘ ያጨዋውታት አልፎ አልፎም ይጋብዛት ጀመር፡፡ እናቷም ቋሚ ደምበኛቸው በመሆኑና ተጋባዦችን ይዞ እየመጣ ገበያቸውን ስላሟሟቀላቸው ለጎንቻ ልዩ አክብሮት እየሰጡት ሄዱ፡፡ በዚህም ምክንያት ዓለሚቱ ቀስ በቀስ ጎንቻን እየቀረበችው መጣች፡፡
ጎንቻ በውበቷ ተማርኮና በፍቅሯ ተለክፎ በመሰቃየት ላይ መሆኑን አላወቀችም ነበር፡፡ እየዋለ ሊያደር ግን ሁኔታዎች ግልፅ እየሆኑ መጡ። በሚያገኘው የስርቆሽ ገንዘብ ለዓለሚቱ ሽቶ፣ቅባት፣ ጌጣጌጥ እየገዛ በድብቅ በገፀበረከትነት ያቀርብላት ጀመር፡፡ ይህ ሁኔታ እየተደጋገመ ሲሄድ የጎንቻ ውለታ
እየከበዳት መጣ፡፡ ቀንና ለሊት ስለሱ ማስብ ጀመረች። ከዚያም ቀስ በቀስ በሱ ላይ መንደድ የጀመረው የፍቅር እሳት እሷንም ሊገርፋት ወላፈኑ በሷም ላይ ተሻግሮ ሊለበልባት እየዳዳው መሆኑ ታወቃት አረቄ ጠጥተው በሞቅታ ውስጥ መጎሻሸሙ፣መተሻሸቱ፣ መላፋቱ እየተዘወተረ ሄደ። ባሏ እርሻ ስለሚውል ዓለሚቱን እንደ ልቡ ለማጫወት
ተመቸው። ዓለሚቱ ባለትዳር መሆኗን
ፍቅሩን ሊያቀዘቅዘው እነደማይችል በመሀላ አረጋገጠላትና በስርቆሽ ለመቀማመስ ተፈቃቀዱ ከዚያም መዳራቱ መላፋቱ የደረጃ እድገቱን ጠበቀና በዚያው በእናቷ ጎጆ በጓዳ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ጨርቅ ለመጋፈፍ በቁ፡፡ ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል ነውና ቀስ በቀስ በስውር
በምስኪኑ ባሏ በገበየው ቆጥ ላይ እንደ ዶሮ መስፈር ጀመሩ።
ዓለሚቱ የስርቆሽ ቅምሻው የበለጠ እየጣፈጣት ሲመጣ ጎንቻም በጣፋጫ
ዓለሚቱ ልቡ ተሰወረች…ከዛ በኋላማ ምን ይጠየቃል? ጎንቻ አባወራ ቀረሽ ቅናት እና ፍቅር ያግለበልበው ጀመር፡፡ “የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ” እንዲሉ በፍቅር ከመቃጠሉ የተነሳ የሁለት ልጆች አባትና
የሰማንያ ባሏ ገበየሁ እያለ በዓላሚቱ የሚቀናው ጎንቻ፣ ለዓለሚቱ አሳቢው ጎንቻ፣ ስለዓለሚቱ አድራጊ ፈጣሪው ጎንቻ ሆነና አረፈው። ዓለሚቱም የጎንቻን ድንግልና ከወሰደች በኋላ ትኩስ ጉልበቱ አዲስ የጉርምስና ጠረኑ ቁመናው በልቧ እያደላ ፍቅሯን ለባሏ መሰሰት ጀመረች።
ያለወትሮዋ ንጭንጭ፣ ጭቅጭቅ አመጣች፡፡ ከገበየሁ ሰርቃ ፍቅርን
ለጎንቻ በገፍ መመገብ ጀመረች። ጎንቻም እየተሰረቀ የሚሰጠው ፍቅር ከሚገባው በላይ ጣፈጠውና ገበየሁን የፍቅሩ ተሻሚ አድርጎ መቁጠር ጀመረ። ፍቅሩን ለብቻው በመመገብ ብቻውን ለመጥገብ ፈለገ፡፡ ተስገበገበ፡፡ መቼም የሰው ልጅ በተፈጥሮ ራስ ወዳድ ነውና ጎንቻ ራሱን በጣም
ወደደ። ምርጥ ምርጡን ለግሉ ብቻ ተመኘ፡፡ ከገበየሁ አስበልጣ እንድትወደው ዓለሚቱን እያንበሸበሻት ልቧን እየሰለበው ሄደ፡፡ የሚገዛላት
የጆሮ ጉትቻ የእግር አልቦ የሱዳን ሽቶ ቀሚስ ለጉድ ሆነ፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው? ጌጣጌጡ ሽቶው ሁሉ በብዛት በእናቷ ሙዳይና በሳጥን ውስጥ ተቀምጦ እየዛገ እየተበላሸ ሄደ እንጂ ልታጌጥበት ልትደምቅበት አልቻለችም፡፡ ብታጌጥበት፣ ብታምርበት፣ብትታይበት ደግሞ መዘዝ ይዞ እንደሚመጣ ገመተች፡፡ ባሏ ገበየሁ “ከየት መጣ? እንዴት ሊሆን ቻለ?”
እያለ ሊጠይቅና ጥርጣሬ ውስጥ ሊገባ ነው፡፡ ስለዚህ ይሄንን እንድታምር፣ እንድታጌጥ፣ እንድትደምቅና እንድትሽቀረቀር ስትፈልግ ደንቃራ፣
ምቀኛ የሆነባትን ባሏን እየጠላችው መጣች። በዚህ ላይ ጎንቻ ችሮታው በገፍ ፍቅሩ በእጥፍ እየጨመረ በመሄድ ላይ ነበረና በገበየሁ የድህነት ትዳር ሰንሰለት የፊጥኝ ታስራ የኖረችበትን ጊዜ እያማረረች፣ የምትፈልገውን ማድረግ ባለመቻሏ ትዳሯን የበለጠ እየጠላች፣ ገበየሁን ከልቧ እያስወጣች በምትኩ ጎንቻን እያስገባች መሄዷን ቀጠለች ...
የገበየሁ ጣፋጭነት ወደ ምሬት ሊለወጥ ጎንቻ ወደር የሌለው ጣፋጭነቱንና የበላይነቱን እያረጋገጠ ሄደ።አዲስ እየተወደደ አሮጌው እየተጠላ ይሄዳልና ገበየሁ ተጠላና ጎንቻ ተወደደ። ለትዳሩ ቀን ከለሊት ደፋ ቀና የሚለው ጉዱን ያላወቀው ገበየሁ በጎንቻ በጥባጭነት ንፁህ ትዳሩ እየደፈረስ መጣ:: ባለቤቱ ያልተለመደውን ጭቅጭቋንና ንጭንጫን እያባባስችው ሄደች
“ስማ! ልጆቼን ብዬ በልጆቼ ታስሬ እንጂ ላንተ ገረድ ሆኜ የምቀመጥ ሴት አልነበርኩም! የፈለኩትን ለብሼ! በፈለኩት አጊጬ! ጓደኞቼን በልጬ
እንጂ ከጓደኞቼ በታች ሆኜ የምኖር ሰው እንዳልነበርኩ ማወቅ ይኖርብሀል!አንተ ግን ይሄ ሁሉ አይገባህም!” ይሄ የመረረ ንግግር ይሄ ታይቶ የማይታወቅ የሚስቱ ፀባይ መለወጥ ያሳሰበው ባል ሚስቱ

👍5