#ቆንጆዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
....የክፍሉ ፀጥታ ክመቃብር ከበደ፡፡
“በዛን ወቅት መንገዱን አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ
በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ ነበር፡፡” ሰውየው ቀጠሉ… “የከማሪካው ልጅ!
የጋናው ነብይ ንክሩማ 'ዋ! ነበር ያለው ዋ! ከፊታችን የተጋረጠውን የአፍሪካ ችግር ተባብረን በአንድነት ከመጋፈጥ ወደኋላ ብንልና ተበታትነን ብንቆም በድጋሚ በሌላ የቅኝ ግዛት ስር ወድቀን ለከፋ ምሬትና ሰቆቃ መከተል መሣሪያ እስክንሆን ድረስ እርስ ሰርሳችን ስንጎነታተልና
ስንቦጫጨቅ እንቆያለን፡፡ ነበር ያለው፡፡”
“ተሳስቶ ኖራል ያ ሰው? ተሳስቶ ኖራል ያ ነብይ? ”
ሽማግሌው መልስ ይፈልጉ ይመስል በክፍሏ ውስጥ የተሰበሰቡትን
ሁሉ በተራ ተመለከቷቸው፡፡ ተጠባበቁ፡፡ መልስ አላገኙም፡፡
“ዛሬ ምን እያደረግን ይሆን?!ያ ሰው እንዳለው እርስ በርሳችን እየተጎናታልን አይደለም? ዛሬ ምን እያደረግን ይሆን? . እርስ በርሳችን እየተቦጫጨቅን አይደለም? ያኔ ክዋሜ ንክሩማን ተቃውመው የቆሙ የሪጅናል ውሀደት አቀንቃኞች የጥንቃቄና የእርጋታ መነኮሳት የት ገቡ? ዛሬ ምን ይላሉ? ምነው ድምፃቸው ጠፋ? በከፋ የቅኝ ግዛት ስር! በረሃብና በድንቁርና ስር በእንብርክክ የሚድኸው የዛሬው የአፍሪካ ህዝብ ተጠየቁ ቢላቸው ያ ሰው ተሳስቶ ነበርን? ቢላቸው ምን ይሆን መልሳቸው?”
አዛውንቱ ለአፍታ አቀርቅረው ቆዩ፡፡ መልሰው ቀና ሲሉ ፊታቸው
እልህና ቁጭት ለብሶ ነበር፡፡
“ለወቀሳ ጊዜ የለንም፤ለቁጭት ጊዜ የለንም ለምሬት ጊዜ የለንም ፤ሰላሳ ዓመት አምጠናል፡፡ እንወልዳለን ቆንጆ ቆንጆ ልጆች፡፡ ዛሬ እዚህ የተሰበሰባችሁ ሁሉ እዋላጆች ናችሁ፡፡ አዲስ የመጣችሁትን እንኳን ጨለማው ተገፈፈላችሁ እላለሁ፡፡ በተረፈ ከፊት የምንጋፈጠውን ሁሉ በሙሉ ልብ ልትቋቋሙት ቃል ትገባላችሁ፡፡”
ርብቃ የገባችው ቃል ምን ያህል አስፈሪና ጥልቅ እንደሆነ እየሰረፀባት የመጣው ጊዜ ከሄደ በኋላ ነበር፡፡
“ብዙ አወራሁ” አሉ ሽማግሌው : ዝግጅቱ አልቆ ሊሄዱ ሲነሱ
“ስለአፍሪካችን ሲነሳ ብዙ ዝም ማለት ይቀናኛል፡፡ እኔ ብቻ ሳልሆን እኩዮቼ
ሁሉ በዕድሜያችን ያየነው ልሳን የሚያደርቅ ነው፡፡ ዛሬ ግን ሃላፊነቴን
መወጣት ነበረብኝ፡፡ ብዙ አወራሁ:: ይበቃል፡፡”
ተነሱ፡፡
በክፍሉ ውስጥ የነበሩት ሁሉ ተነስተው ቆሙ:: ሰውየው በክፍሉ ውስጥ ያሉትን ወጣቶች በተራ ጨብጠው ሲያበቁ አብረዋቸው ከመጡት በዕድሜ ከሚቀርቧቸው ሰዎች ጋር ተከታትለው ወደ በሩ አመሩ፡፡ ከክፍሉ ከመውጣታቸው በፊት ቆም አሉና በክፍሉ ውስጥ ሰብሰብ ብለው በአክብሮት የሚመለከቷቸው ወጣቶች ላይ አተኮሩ…
“ተጠንቀቁ!” አሉ አዛውንቱ ፈገግ ብለው፡፡ “እዚህ ያወራነውን ጮክ ብላችሁ አታውሩ። አፍሪካችን ተኝታለች። እንዳትባንን፡፡”
ርብቃ ወዲያው የተሰጣት ትዕዛዝ ወይም ኃላፊነት አልነበረም፡፡
“ጊዜው ሲደርስ ስትፈለጊ ትጠሪያለሽ፡” ተብላ ቆየች፡፡ ቢሆንም በወር አንዴ እሷ የምትገኝበት ህቡዕ ህዋስ በሚያደርገው ስብሰባ ላይ እየተገኘች ስለአፍሪካ ሁለገብ ችግር የሚደረጉትን ውይይቶች ስትካፈል ቆየች፡፡
ከሁለት ወር በኋላ ነበር የመጀመሪያው ትዕዛዝ በምሥጢር የተላሰፈላት፡፡ በሬድዮ “የአፍሪካ ምጣኔ ሃብት” በሚል ርዕስ ሣምንታዊ ኘሮግራም እንድታዘጋጅ ተነገራት፡፡ በመጀመሪያ ሃሳዑን ለአለቃዋ እንዴት እንደምታቀርብ ቸግሯት ነበር፡፡ ነገር ግን በማግስቱ አለቃዋ እራሳቸው
እቢሮኣቸው ድረስ አስጠርተዋት ማክሰኞ ማታ የሚቀርበው የሙዚቃ ክፍለ
ጊዜ ስለሚቋረጥ በምትኩ ሊቀርቡ የሚችሉ ፕሮግራሞች ሰብስሲና
እንነጋገርባቸዋለን፡፡” አሏት፡፡
ደነገጠች፡፡ ነገሩ ገባት፡፡ አባል የሆነችበት ህቡዕ ድርጅት ምን ያህል ውስጥ ለውስጥ ስር የሰደደ እንደሆነ ተገነዘበች፡፡
“እ...የአፍሪካ ምጣኔ ሃብት
ላይ… ” አለች ሳታውቀው፡፡
“ግሩም” አሉ አለቃዋ ፈገግ ብለው ከመቀመጫው እየተነሱ እየጨበጧት፡፡ “በርቺ፡፡ ማንኛውም ችግር ሲገጥምሽ ቀጥታ እኔጋ ነይ፡፡ አይዞሽ፡፡”
ከአለቃዋ ቢሮ ስትወጣ ጉልበቶቿ እየተብረከረኩ ነበር፡፡ ሃላፊነቱ
ከወፍጮ ከብዶ ታያት፡፡
ሁለተኛው ትዕዛዝ ከሁለት ወራት በኋላ ተከተለ፡፡
“እና ምንድነው ማለት ነው የማደርገው?”
ባጭሩ በፈለግሽው መንገድ በእህትነትም ፡ ሆነ በሌላ ታጠምጅዋለሽ እንዳልኩሽ በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በአፍሪካ ጉዳይ ቢሮ ውስጥ ሁለተኛውን ወንበር የያዘ ሰው ነው::እያንዳንዱን ነገር ለማግኘት እንፈልጋለን፡፡በተቻለሽ እለቢው... እ..ቤቱ ይዟቸው የሚመጡ ወረቀቶችን አጥኚ፡፡ ያገኘሽውን ሁሉ፡፡ ከዚህ በተረፈ…በየጊዜው ተጨማሪ መመሪያ ይተላለፍንልሻል።” የህቡዕ ህዋሷ መሪ ነበር ማርቆስ፡፡
“እንዴት ነው ሰውየውን የማገኘው? ማለቴ
የሚቀጥለው ቅዳሜ ሶስና የልደት በዓሌ ነው ብላ ትጠራሻለች ግብዣው ላይ ትገኛለሽ አብረው ስለሚሰሩ እሱንም ትጠራዋለች፡፡ ታስተዋወቅሻለች። ከዚያ በኋላ እኔና አንቺ እየተረዳዳን እንቀጥላለን፡፡” ትከሻዋን ቸብ አድርጎ ተነሳ “በነገራችን ላይ የሰውዬሽ የምሥጢር ስም "ዱርዬወ" ነው:: ገባሽ? '
ዱርዬው ” አለ ማርቆስ በጠባሳ የተገመሰ ፊቱን በቀኙ ፈተግ አድርጎ “ተግባባን?”
“ገባኝ፡፡”
እንደተባለችው ሶስና በልደት በአሏ ላይ አስተዋወቀቻቸው፡፡ ናትናኤልን “ዱርየው”ን የህዋሷ መሪ ማርቆስ እንዳላት መረቧን ዘርግታ ፍቅረኛዋ አደረገችው፡፡ ሰርስራ ሕይወቱ ውስጥ ገባች፡፡ ምስጢሯን ነግራው
ምረሥጠርህን አለችው:: ያገኘችውን ሁሉ አሳልፋ ሰጠች፡፡ ጊዜ ሲሄድ እሷው ያዘጋችው መረብ እሷኑ ተቀተባት፧ አደናቀፋት፤ ወደደችው፡፡ሆኖም ሳታቋርጥ ቡድኑ መረጃዎችን ስታቀብል ቆየች፡፡ ይህ ብዙም አላሳሰባትም:: ምክንያቱም ናትናኤል ለአፍሪካ የነበረው ግለት ከማናቸውም የደበዘዘ አልነበረም፡፡ ለዚህም ነበር ላህዋሷ መሪ በሳምንት አንዴ በምታቀርበው ዘገባ ላይ ዱርዬው' በህቡዕ ድርጅቱ ውስጥ ቢመለመል ጉዳት እንደማያስከትል ደጋግማ ያመለከተችው፡፡ ለምን እንደፈሩት ባይገባትም ምክሯን ሊጠቀሙበት አልወደዱም፡፡ ቢሆንም እንደዚህ ዓይነት ነገር ውስጥ ይገባል ብላ ጠርጥራም አታውቅ፡፡ ናትናኤልን እንደ ወንጀለኛ ማሳደድ! መጀመሪያ ነገር ነፍስ ማጥፋትንስ ምን አመጣው? ጓደኝየውንስ ለምን ገደሉት? ፈጣሪዬ የት ገብቶ ይሆን የተሰወረው? እውነት ቢያገኙት አይጎዱትም ይሆን? እንዴት ልታምናቸው ትችላለች? ቢገድሉትስ? ቢቀር
ይሻላል፡፡ እንዲይዙት ብትረዳቸውና አይኖቿ ስር አንድ ነገር ቢያደርጉትስ?
ገብሬልዬ፤ ግን ደግሞ ራሳቸው ፈልገው ቢያገኙትስ? ዘገነናት፡፡ ዘገነናት
ያለፈው ትዝታ ሁሉ መጣባት::እና ቀና ብላ ተመለከተችው በሩ አጠገብ ካለ ወንበር ላይ ተቀምጦ እያከታተለ በላይ በላዩ ሲጋራ የሚያጨሰውን ሰው፡፡ በትዝብት መልሶ ተመለከታት:: ባንዳ!' ያላት መሰላት ድጋሚ።
“ማርቆስ” አለችው አይኖቿ ላይ እንባዋ አቆርዝዞ፤ “ማርቆስ ግን ምን አደረጋችሁ? ናትናኤል'ኮ ምንም አያውቅም፡፡ ማርቆስ እውነቴን ነው፣ ምንም አያውቅም:: እመነኝ አብረን ብዙ ሰርተናል፡፡ አውቅሃለሁ ታውቀኛለህ:: አልዋሽህም:: ምንም አያውቅም ናትናኤል፡፡”
“ነገርኩሽኮ:: ምንም እንደማያውቅ እኛም ደርሰንበታል፡፡ ግን ሊደርስበት ወደማይገባ ቁልፍ እያነፈነፈ እየተጠጋ ነው።ሊያገኘው ይችላል። ሰውዬሽ ቀላል ሰው አይደለም፡፡ ምሥጢሩን ካገኘ ደግሞ ዕቅዱ ሁሉ እጁ ገባ ማለት ነው፡፡ያ ደግሞ ለእኔና ለአንቺ ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም
ለአፍሪካ…ውድቀት ነው ብጥብጥ ነው…ሁከት ነው፡፡ማንም ይቅርታ አያደርግልንም፡፡አንድ በአንድ በየአገሩ እየታደንን በየአገሩ

👍3
#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
.... የቢሊየነሩ ዊሊ ባደን ውሽማ የነበረችው ሊዛ ፍላንግ ከዚህች ከዶክተር ሮበርትስ ጋ ህክምና ትወስድ እንደነበረ
ለማወቅ ያገዙት እነዚያ የግድያ ዜናውን የሚያራግቡት ሚዲያዎች ነበሩ።
ለሃያ ደቂቃ ያህል ጎግል ላይ ስለ ዶክተር ኤኮላስ ሮበርትስ የሰበሰበው መረጃ
ዶክተሯ በምዕራብ ሎስ አንጀለስ ውስጥ የምትኖር፣ በሙያዋ የምትከበር እና
ባለፈው ዓመትም ባሏ ዶክተር ዶውግላስን በሞት ያጣች ሴት እንደሆነች
ለማወቅ ችሏል፡፡ ይሄ ደግሞ እሷን የተጠየቀችውን መክፈል የምትችል ሰው
ያደርጋታል። በዚያ ላይ ደግሞ እስር ቤት እንዳይገባም ያቺ የተረገመች ዳኛ
የወሰነችለትን የልጁን ተቆራጭ ገንዘብ ማቋረጥ የለበትም፡፡ እናም ጥሩ
ገንዘብ ያስፈልገዋል። እንግዲህ ዕድሉን ቡናውን ሽሚዙ ላይ በመድፋቱ የተነሳ ያበላሸ አይመስለውም፡፡ ኒኪ እሱን ደንጋጣ ነው ብላ ካሰበችው ችግር
ሊፈጠርበት ይችላል፡፡
ለማንኛውም ኒኪ ሮበርትስ በራሷ ሀሳብ ውስጥ ስለነበረች ሊሆን ይችላል
እሱ እንደፈራው ቡና የደፋበትን ሁኔታ አላስተዋለችም፡፡ አጠገቡ ከሚገኝ
አንድ ወንበር ላይ ቁጭ አለች እና ከቦርሳዋ ውስጥ አንድ ኤንቨሎፕ
አውጥታ ሰጠችው።
“ከየት መጀመር እንዳለብኝ እርግጠኛ አይደለሁም። ስለዚህም ኢንቨሎፕ
ውስጥ ትናንሽ ማስታወሻዎችን ትቼልሀለሁ።” ብላ በመቀጠልም “ሚስተር ዊሊያምስ ያንተን እርዳታ እፈልጋለሁ። ያው ትላንትና ማታ እንደነገርኩህ ፖሊሶች ነፍሰ ገዳዩን ለመያዝ ምንም አይነት የተሻለ ነገር ሲያደርጉ አልታየኝም::” አለችው፡፡
“ዶክተር ሮበርትስ ኒኪ ይህንን የፖሊሶቹን የማይረባ ሥራ ለብዙ ጊዜ ሰምቼያለሁ” አላት እና ወደ እሷ አንገቱን አስግጎ በመጠጋትም “ኢንቨሎፕ ውስጥ ያለውን ነገር በኋላ ላየው እችላለሁ፡፡ ለአሁኑ ግን አንቺ ራስሽ ለምን ያለውን ነገር አትነግሪኝም?” አላት እና ዝም ብሎ ይመለከታት ጀመር።
ኒኪ ሁለመናውን መገምገም ጀመረች፡፡ ወፍራም፣ ፈዛዛ ቢጫ ቀለም ያለው ፊት፡፡ ዘገም ያለ የአካላዊ እንቅስቃሴን የሚያደርግ ሰው ነው።በውስጧም ምናልባት እሱ ሰካራም ምናልባትም ፈት እና ገንዘብ የሚያጥረው ሰው ነው ብላ ደመደመች። በእርግጥ ይህንን ግምቷን
ለማስቀመጥ የግድ አልበርት አንስታይንን መሆን አይጠበቅባትም።ምክንያቱም ማንም በከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ፕሮፌሽናል ሰው የቁርስ ላይ ቀጠሮውን እዚህ ርካሽ ከሆነው አይ ሆፕ ውስጥ እንደማይዝ መቼስ ይታወቃል አይደል?
ማታ ላይ ስለ ዴሪክ ዊሊያምስ የቀድሞ ደምበኞቹ ስለ እሱ ለማግኘት የማይፈነቅለው ነገር የለም። በዚህም የተነሳ ከአንድም ሁለት ጊዜ ከነገሮች በላይ (ከህግ በላይ) በጣም ገፍቶ በመሄድ የሚፈልገውን መረጃ
ፍርድ ቤት ቀርቧል። ይህንን አደጋን የመጋፈጥ እና ነገሮችን በጣም ገፍቶ
በመሄድ የሚሰራ ሰው እንደሆነ ስለምታውቅ ነበር ኒኪ እሱን የፈለገችው።
ወደ እሱ ደውላ ቀጠሮ የያዘችበት ዋነኛ ምክንያቷም የግል መርማሪውን ደፋርነት በማንበቧ ነው።
“እንደ ነገርኩህ እኔ ከየት መጀመር እንዳለብኝ አላውቅም” አለችው፡፡
“መጀመሪያ ነው ብለሽ ካሰብሽው ነገር ለምን አትጀምሪም?” አላት እና ዊሊያምስ ባልኮኒው ጋር ወደምትገኘው አስተናጋጅ አንድሪያን ዞሮ “የኔ ቆንጆ ቁርሴን የተጠበሰ እንቁላል ከጎኑ ደግሞ ፓንኬክ አድርጊልኝ፡፡ ለጓደኛዬ ደግሞ?” ብሎ ኒኪን ተመለከታት፡፡
“እኔ ቡና ብቻ ነው የምወስደው”
“ለእሷም እንቁላል ጥብስ ይሁንላት” አላት እና ዊሊያምስ በግርምት ወደምታየው ኒኪ ፊቱን መልሶ “የእኔ እመቤት መብላት ይኖርብሻል። ሰዎች
በኑሯቸው ዙሪያ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ደውለው እኔን ካገኙ እና ጭንቀታቸውን ካረገፉ ምን ይቀራቸዋል? ስለዚህ አንቺ ምን ማድረግ አለብሽ መሰለሽ? በቃ በደንብ መብላት እና ሀሳብሽን ለእኔ ጥለሽ መተኛት ነው የሚኖርብሽ” አላት፡፡
ዴሪክ ዊሊያምስ በቅንነት ሀሳቡን ስለነገራትም ነው መሰል ኒኪ ተበረታታች እና ማውራት ጀመረች፡፡ “መልካም እንግዲህ... ከመጀመሪያው ጀምረሽ ንገሪኝ ብለኸኛል አይደል? ለእኔ እውነተኛው የመጀመሪያው ነገር
ምን መሰለህ? ሟቹ ባለቤቴ ከትዳሩ ውጪ የፍቅር ግንኙነት ነበረው” ብላ
ነገሯን ጀመረች፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ቫላንቲና ባደን የጂ 6 አውሮፕላኗ ጎማዎች ሜክሲኮ ካቦ ውስጥ
ከሚገኘው የሳን ሉካን አየር ማረፊያ ወለል ሲነኩ አምላኳ በሰላም ስላስገባት
የምስጋና ፀሎትን በውስጧ አደረገች፡፡
ቫለንቲና ብዙ ነገሮችን የምትፈራ ሴት አይደለችም። እህቷ ከ 50 ዓመት
በፊት ከጠፋችበት ጊዜ ጀምሮ በደንብ እስካሰበችባቸው ጊዜ ድረስ ያለፈቃዷ
ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ነገሮች በጣም ጥቂት እንደሆኑ ለማወቅ ችላለች።
ወዳጆቿ በአውሮፕላን የመጓዝ ፍርሃቷ የመነጨው ነገሩን መቆጣጠር
እንደማትችል ከማመኗ የተነሳ እንደሆነ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ።ምናልባት ትክክል ሊሆኑ ይችላሉ። ምክንያቱም ከበፊት ጀምሮ ቫለንቲና በትዳሯ፣ በቤተሰቧ፣ በምትሰራቸው ቢዝነሶቿ እና ከሰዎች ጋር ያሏትን ግንኙነቶች በሙሉ እሷ ሙሉ በሙሉ ስትቆጣጠራቸው ነው የኖረችው።
የሎስ አንጀለስ ቆይታዋ ስኬታማ ነበር። ሳይጠብቋት በድንገት ወደ በጎ
አድራጎት ድርጅቶቿ ቢሮዎች ጎራ ብላ ነበር። ቢሮዎቹ ውስጥ ገብታም
የድርጅቱን የተሳኩ የፍለጋ ሥራዎችን እንዲሁም ደግሞ የስድስት ወሩን
የተዘበራረቀ የባንክ ሂሳብ ሪፓርትን እንዲያሳዩአት ጠይቃ ለማየት ችላለች።
የአሜሪካ ውስጥ የገቢዎች ቢሮ የድርጅቱን ከውጪ የሚገቡለትን ገቢዎች
ምንጭ ማነፍነፍ ከጀመረ ወዲህ ቫለንቲና ራሷ ናት እነዚህ አይነት ነገሮችን
የምትቆጣጠረው። በድርጅቱ ውስጥ የሚሰሩ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው
እውነተኛው የሥራ አካሄዳቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁት እና ሥራቸው
ሚስጥሩ ተጠብቆ መስራት እንዳለበት የሚገነዘቡት። ዊሊ ባሏ ደግሞ ሰነፍ
ስለሆነ እሷ የምትሰራቸው ሥራዎች ላይ አትኩሮት ሰጥቶ አያውቅም።ባለፈው ጊዜ ዊሊ ለኤል.ኤ ፖሊስ ክፍያ በመፈፀም ይደረግባቸው የነበረው
ምርመራ እንዲቋረጥ አድርጓል። የአሁኑ የአሜሪካ የውስጥ ገቢዎች አካሄድ
ግን ይለያል እና ቫለንቲና መጠንቀቅ እንደሚኖርባት ታውቃለች።
በዚያ ላይ ደግሞ እሷ በድንገት ቢሯቸው ውስጥ ገብታ እሷን ንግስታቸውን ለማስደስት የሚራኮቱትን ሰራተኞችን መመልከት ደስ ይላታል፡፡ የበጎ አድራጎት ሥራዎችም ልክ እንደ ሌሎች ለትርፍ የሚሠሩ ድርጅቶች ሁሉ የራሳቸው የሆነ መለኪያ እንዳላቸው፣ መለኪያዎቹም
ድርጅቱ የሚያስመዘግባቸው በጎ ውጤቶች መሆኑን ለሰራተኞቿ በየጊዜው
ነው የምትነግራቸው።
ለባለፉት አሥራ አምስት ዓመታትም በጣም በጣት ከሚቆጠሩት የፍለጋ
ሥራዎቻቸው በስተቀር ሁሉም በጥሩ ሁኔታ እንደተጠናቀቁ ስታስረዳቸው
በኩራት ነበር። ሬቼ ላምብ የተባለ ድክ ድክ የሚል ህፃን ቱርክ ውስጥ
ቤተሰቦቹ ለመዝናናት በሄዱበት ጊዜ ላይ ጠፍቶ አልተገኘም። የቻርሎቴ
ክላንሲ መጥፋት፣ የዚህች ወጣት ያለመገኘት ደግሞ ራሷን ቫለንቲናን
ጭምር ያሳዝናታል፡፡ ምክንያቱም ልጅቷ የጠፋችው ልክ እንደ ቫለንቲና መንታ እህት ሜክሲኮ ውስጥ ስለነበረ ቫለንቲና ልቧ ተነክቶ ነበር። ምንም እንኳን ውጤታቸው ፍሬ አልባ ቢሆንባቸውም፤ ከሌሎች የማፈላለግ ሂደቶች
በተለየ መልኩ በየሚድያዎቹ ላይ ስለ ክላንሲ እንዲነገር አድርጋ ነበር
ድርጅቷ በሁሉም የፍለጋ ሥራዎቻቸው ላይ መቋጫን ሳያበጁ ፍለጋውን
አያቋርጡም። ለምሳሌ ያህል የብራንዶን ግሮልሽን ፍለጋ የሚመስሉ አይነት
ሥራዎቻቸው ላይ የፈላጊ ቤተሰብን ልብ የሚሰብር አሳዛኝ ነገርንም መናገር
(ማሳወቅ)

👍2🔥1🥰1