#የወድያነሽ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል
....የውስጤን ሥቃይና የሕሊናዬን ሰፊ ጠባሳ ጠልቀው ያላዩ የቅርብ
ዘመዶቻችን «ዛሬማ ተበላሽቶ፣ የሱ ነገር እንዲህ ሆኖ ቀረ፡፡ ያየህይራድን የመሰለ
አንበሳ አባት እያለው ወግ ማዕረግ ያለማየቱ...» እያሉ ያጉመተምታሉ፡፡ ከቤት
ውጪ ማደሬ ያለ ማቋረጥ በመዘውተሩ ሁኔታውን መላው ቤተሰብ ከዳር እስከ
ዳር ዐወቀ፡፡ ደግማ ደጋግማ እናቴ እያፈረች፣ እኅቴ በተለይም የእናቴ
ምስጢረኛና የቅርብ ጓደኛ ወይዘሮ አማረች መኝታ ቤት ድረስ እየገቡ፣ ተው
ደግም አይደል የትልቅ ሰውና የጨዋ ልጅ እንዲህ አይደለም፡፡ እናትህ ብታለቅስ
ታደርስብሃለች» እያሉ ለወጉ ያህል ገሠጹኝ፡፡
እኔን የምመክራትና የምዳኛት ወደ ፊትም ሆነ ወደ ኋላ የማስኪዳት እኔው ራሴ ብቻ በመሆኔ የእነርሱን ምክር ሁሉ እንደሚያልፍ የበረዶ ውሽንፍር
ቆጠርኩት። በጠቅላላ መጻሕፍቶቼንና ልብሶቼን ውስጥ ውስጡን አንድ በአንድ
እግዥ ጨረስኩ፡፡ ከሁለትና ከሦስት ቀን አዳር በኋላ ወደ ወላጆቼ ቤት ስገባ ዘና
ብሎ የሚያናግረኝ ሰው አልነበረም፡፡
አባቴም ከቤት ውጪ በተደጋጋሚ ማደሬንና እንደ እናቴም አባባል «መዛተሌን» ቀስ በቀስ ሰማ።
«አግባ! ትዳር ንብረት ያዝ፣ እንደ ማንም የባለጌ ልጅ ሰፈር ለሰፈር
እትልከስከስ፣ ጎጆ ያስከብራል፣ ትዳር ግርማ ሞገስ ነው ያልኩህ ለዚህ ብዬ ነበር፡፡ያለበለዚያ ግን አካለ መጠን ከደረሰ ጐረምሳ ጋር ምን ያታግለኛል» ብሎ
ከነከተቴው ችላ አለኝ፡፡
ዋል አደር ብሎም «አደጋ ብቻ እንዳያገኘው እንጂ ልቡ መለስ
ሲልለትና ያበጠው ልቡ ሲሟሽሽ እንዳረጀች ውሻ ክትት ይላል» አለና ይብሱኑ ስለ እኔ የነበረውን 'አለና የለም ወይ?” እርግፍ አድርጎ ተወ፡፡
የሐሳቤ ተፃራሪ የሆነው አባቴ እንደ አህያ ሬሳ ቢጠላኝም ቅር አላለኝ፡፡ እኔ ግን «ይህ ነው ለሰው ልጅ የሚሰጠው ታላቅ የመኖር ጸጋ ብዬ ከጥላቻው ውስጥ ብርታትና እፎይታ የተሸለምኩ መሰለኝ።
ወደ ወላጆቼ ቤት ባሰኘን ጊዜ ገብቼ ባስፈለገኝ ሰዓት ውልቅ ማለት
ለመድኩ፡፡ እንደ ምኞቴ ሳልዘጋጅና ሳላስበው፣ የኑሮዬንም አዝማሚያ በሚገባ ሳላቅድ ድንገት ባለትዳር በመሆኔ ኑሮ በመጠኑ ተደናገረኝ። ሆኖም ትዳራችን የተመሠረተው በጽኑ ፍቅር ላይ በመሆኑ ፍላጎቴና ጉጉቴ ሁሉ ነጋ ጠባ
ለመሻሻልና አስደሳች ለውጥ ለማግኘት ሆነ። ወትሮ በቀላሉ ደንግጦ ይበረግግ
የነበረው አእምሮዬ የድፍረትና የወኔ ካፈያ ተርከፈከፈበት።
የየወዲያነሽን ቀኝ እጅ ያዝ አደርግና «ዛሬ ምን ያስፈልገናል?» ስላት ዐይን ዐይኔን እያየች እና የኮቴን አዝራሮች በጣቶቿ እየጠራረገች «ካለህማ....ያህል ይበቃኛል» ብላ ገንዘብ ስትጠይቀኝ የትዳርን አያያዝና አመራር ቀስ በቀስ
ለመድነው። በየወዲያነሽ በኩል የተቸገርኩበት ጉዳይ ቢኖር፡ ስትተኛም ይሁን ስትነሣ ስትበላም ይሁን ስትጠጣ አረ ተው ጌታነህ፡ ኧረ ተው! እረ ተው
ልጄን አሳየኝ? ሞቶም እንደሆነ ቁርጡን ንገረኝ ባይኖር ነው እንጂ ቢኖርግ
መቼ እንዲህ ዝም ትለኝ ነበር?» እያለች ስለምትጨቀጭቀኝ ነበር፡፡ ምንም እንኳ
አንዳንድ ነገርን አገላብጠው የማያዩ ቀባጣሪዎች «ጨካኝ አረመኔ ነች» እያሉ
እንደሚያሟትና ወደ ፊትም እንደሚያባጥሏት እያሰብኩ ለጊዜው ብበሳጭም እኔ ከማንም ይበልጥ የእኔዋን እና ቅኗን የወዲያነሽን አሳምሬ ስለማውቃት አባባላቸው ሁሉ ከወሬ እንኳ የነፈሰበት ተራ ወሬ ነው ብዬ እንደ ቤት ጉድፍ ጠራርጌ ጣልኩት።
ያን በማሕፀኗ ዘጠኝ ወር ሙሉ ተሽክማ በስንት የኑሮ ሥቃይ እና ውጣ ውረድ የወለደችውን ልጅዋንና አካሏን ለማየት እያለቀሰች ብታስቸግረኝም
የእናትነት ወጓ በመሆኑ ምንም ቅር አላለኝም፡፡
አንድ ቀን እሑድ ጥዋት ለቁርስ እንደ ተቀመጥን ሳላስበውና
የሚያጋጥመኝን ሳልጠራጠር ከኪሴ እንድ ትንሽ ሰማያዊ ማኅደር አወጣሁ፡፡
በውስጡ የነበሩትን ልዩ ልዩ ሥዕሎች ተራ በተራ ስመለከት የወዲያነሽም
እጅዋን ትከሻዬ ላይ ጣል አድርጋ ትመለከት ነበር፡፡ የልጃችንን ሥዕል ኣየት
እንዳደረገች «ይኸውና» ብላ ባስደንጋጭ ሁኔታ ጮኸች፡፡ ከእጄ ላይ መንጭቃ
ደረቷ ላይ ለጠፈችው።
እነዚያ በእንባ ተኮትኩተው ያደጉት ዐይኖቿ የእንባ ኩልልታ እንጠፈጠፉ፡፡ ሥዕሉን ጠረጴዛው ላይ ወርውራ እግሬ ላይ ዘፍ አለች፡፡ እግሬን ባላት ጠቅላላ ኃይል ቁልቁል ጨምድዳ ስለ ያዘችው ጎትቼ ማላቀቅ አቃተኝ።
«ብዙ ሥቃይና መከራ ያየሁበት፣ ተንገላትቼ የተንከራተትኩበት የበኸር
ልጂ ነውና አለበት ድረስ ወስደሀ እሳየኝ፡፡ እናት አባትሀም ቤት ከሆነ ከሩቅ
ልየው:: ዐይኑን አይቼና ኣንድ ጊዜ ስሜው ልሙት!» ብላ ጫፈ ድልዱሙን
ጥቁር ጫማዩን ዕንባ አርከፈከፈችበት። የምይዘውና የምለቀው ጠፋኝ፡፡ ቁርጡን
ለማወቅ ቆርጣ መነሣቷን ስላወቅሁ ኣበይ ተነሽ ልብስሽን ቀያይሪና እንሂድ!
እይተሽው ለመመለስ እንጂ ይዘነው መምጣት አንችልም» አልኳት። እግሬን
ሳትለቅ አሻቅባ እያየች «እኔም ይዤው ልምጣ አልልም፣ ዐይኑን ብቻ አንድ ጊዜ
ልየው፣ በሕይወት መኖሩን ብቻ ልይ!» ብላ የልቧን አውጥታ ተናገረች።
በጉንጫ ላይ የሚንኳለለው ትኩስ እንባ የልቤን የፍቅር ወለል ቦረቦረው።ተነሥታ ወደ ጓዳ ስትገባ አረማመዷ እንኳ አሳዘነኝ። የባዕድ ሀላፊ አግዳሚ ያህል
እንኳ የማይተዋወቀችን እናትና ልጅ እንዴት አድርጌ እንደማስተዋውቅ ጭንቅ
ጥብብ አለኝ፡፡ እማምዬ እያለ በእናቱ ክንዶች ላይ ያልተዘናከተን' አልቅሶ
ያልተባበለን ሕፃን፣ ዐይኑ አይቶ ሕሊናው ያልመዘገባትን፣ አልቅሶም ይሁን በማቅ
ተንከትክቶ ዕቅፏ ላይ ያልተዘረገፈን ልጅ እንዴት አድርጌ እማማዬ እማማ
ለማሰኘት እንደምችል አጀማመሩም ሆነ አፈጻጸሙ ስማይን መቆንጠር መስሎ
በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ልብሷን ቀይራ ብቅ አለች፡፡ ኣጭር ዞማ ጸጉሯ በሚያምር ሐምራዊ ሻሽ ሽብ ተደርጓል፡፡ ኣጠገቤ መጥታ ቆም ካለች በኋላ በል አታጓጓኝ ይኸው መጣሁ! እንሂድ! » ብላ አሰፈሰፈች፡፡
የረሳችውን ሕፃን፡ ልጅሽ ይኸ ነው ብዬ ሳሳያት፣ ኣቅፋው በደስታ ስታለቅስ እና የልጁም በሁኔታው መደናገጥ ገና ከሩቁ አሽቆጠቆጠኝ፡፡
«የምንሄድበት ቦታ እኮ በጣም ሩቅ ነው» አልኳት፡፡ ግድ የለህም ስለ መንገዱ ሰማይ ጥግ ይድረስ፣ እንሂድ ብቻ' » ብላ ቆርጣ መነሳቷን ወደ በሩ በመራመድ ገለጸች፡፡ ከአስራ አምስት ደቂቃ ጉዞ በኋላ በታክሲ ዕጓለ ማውታ ግቢ ደረስን። ለሁለተኛ ጊዜ ከሴት ጋር ያዩኝ የድርጅቱ ዘበኞችና ሌሉች ሠራተኞች እርስ በርሳቸው በመተያየት ተጎሻሽሙብኝ፡፡
ሕፃናቱ ሁሉ ልዩ ልዩ ቅርዕና መልክ ያላቸው መጫወቻዎችና አሻንጉሊቶች ይዘው በምድረ ግቢው ሜዳ ላይ እንደ እውድማ ዳር ጥሬ ፈስሰዋል፡፡ ኳስ እያንከባለለ የሚጫወተውን፣ ጅዋጅዌ የሚገፈትረውን፣ ወለሉ ላይ
በተሽከርካሪዎቿ እየተገፋች የምትሽከረከር መኪና ይዞ ራን ራን ጵጵ! ቢብ! የሚለውን፣ ሜዳ መኻል እየተሯሯጡ ድብብቆሽ የሚጫወቱትን ሁሉ አየናቸው::
ለጊዜው ልጃችንን ስላጣሁት ዐመዴ ቡን አለ፡፡ እጄን ኮት ኪሴ ውስጥ
ወሽቄ ከቤት እንደ ወጣን የገዛሁለትን ከረሜላ ማሻሸት ጀመርኩ፡፡ የየወዲያነሽ
ዐይኖች በተስፋ ብርሃን ተከበቡ። የናፍቆት ጎተራቸው አፉን ከፈተ። የጉጉቷ ጥም ተንሰፈሰፈ። ዐይኖቿን ቅርብና ሩቅ ድረስ እየላከች ኣየች፡፡ ሰውነቷ የሚንቀጠቀጥ መሰለ። ውሪ ብጤ ሩጭሩጭ እያለ ባጠገቧ ባለፈ ቁጥር ዐይኖቿ እግሮቹን ተከትለው ይጓዙና በዚያው ፈዝዘው ይቀራሉ፡፡
በመኻሉ አንድ አጠር ጠበብ ያለች ነጭ ሱሪ የታጠቀና ዐመድማ ሹራብ
የደረበ ድምቡል ያለ የሚያምር ልጅ ዝንጉርጉር ቢራቢሮ በግራ እጁ ይዞ
እያንደፋደፈና እፍ እያለባት ከፊት

👍3
#የወድያነሽ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሦስት
፡
፡
#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል
...አሮጊቷ ሠራተኛችን ነጋ ጠባ እየታመሙ መውደቅ መነሣት ስለ
በዛባቸው «እስኪ በጠበሉም በምኑም ልሞካክረው» ብለው ከሔዱ ወሩ ተጋመሰ::በእርሳቸው እግር እንዲት ልጅ እግር ሠራተኛ ተካን፡ የወዲያነሽም ያሳለፈችው ችግርና መከራ ቁጣና ግልምጫ ረሃብና እርዛት ሁሉ ከአእምሮዋ ላይ የማይደመሰስና የማይረሳ የኑሮ ትምህርት አስጠንቷታል። በዚሁ የተነሣ አዲሷን ሠራተኛችንን በርኅራኄና በደግነት ታያታለች። በትምህርትም ረገድ ከቀን ወደ
ቀን በመበርታቷ በእርሷ ላይ ያለኝ ተስፋ እንደ አበባ እምቡጥ በየጊዜው ይፈነዳ
ጀመር። የደመወዜ ከፍ ማለት የቤታችንን ዕቃዎች በአዳዲስ ምርጥ ቁሳቁሶች
ለመተካት ረዳ፡፡ ለውጥ የኑሮ መስተዋት ነው። የየወዲያነሽ መልክና ውበትም
የቀድሞ ደረጃውን ሊይዝ ስንዝር ታህል ቀረው፡፡ በክርክርና በውይይት
እንድትመራና እንድታምን ያደረግሁት ጥረት ከጊዜው ሁኔታ ጋር እየተቀራረበ
የሚራመድ የልፋት ውጤት እስገኘልኝ። ጸጉሯ እንገቷ ላይ እየተገማሸረ
የቀሚሷን እንገትያ መዳሰስ ጀመረ፡፡ ዕድሜዋ ኻያ ሰባት ገደማ በመድረሱ
ደርባባና ጐዝጉዝ ያለች ወጣት ሆነች፡፡ እንዲያውም በምኗም በምኗም በከፍተኛ
ምቾትና ድሎት ካደገችው እኅቴ ይልቅ የእኔዋ የወዲያነሽ በእጅጉ ላቀች፡፡
የውብነሽ የንግድ ሥራ ትምህርቷን ጨርሳ ከንግድ ትምህርት ቤት
ከተመረቀች ሦስት ወር ዐለፋት፡፡ ነገር ግን መስከረም ሲጠባ ሥራ ትጀምሪያለሽ
ተብላ ቦዝና ከረመች፡፡ አባቴ ከግሼን ማርያም በተመለሰ በሳምንቱ በደኅና ደሞዝ ሥራ ጀመረች።
አንድ ቀን እሑድ ከቀኑ አምስት ሰዓት ገደማ ላይ እኔና የወዲያነሽ በእግራችን ወደ አፍንጮ በር ስናዘግም ቅድስት ማርያም ቤተ-ክርስቲያን ደረስን።
በቤተ ክርስቲያኑ ዐውደ ምሕረትና አካባቢ እጅግ በጣም ብዙ ሕዝብ ተሰብስቧል።
በሕዝቡ መኻል እየተጋፋን ወደ ሰሜን አቅጣጫ ስንጓዝ የኅዳር ማርያም መሆኗ
ትዝ አለኝ፡፡ ሕዝቡ እየተግተለተላ ወዲያ ወዲህ ሲሔድ ድንጋዩ የተፈነቀለበት
ቁጫጭ መስሏል፡፡ የወዲያነሽ ግንባሩን በጥንግ እንደ ተመታ ገነኛ ቀጥ ብላ
ቆመች፡፡ የቀኝ እጀን ይዛ ወደ ኋላ እየጎተተች «ጌትዬ ጉድፈላልህ! የዛሬን
አውጣኝ! » ስትል ትንፋሿ በድንጋጤ ወደ ውስጥ ሠረገ፡፡
ከወደፊታችን አንዳች አደጋ የመጣ መስሉኝ አፍጥጬ ተመለከትኩ፡፡
አገር አማን ነበር፡፡ ለካስ ነገሩ ወዲህ ኖሯል፡፡ ከፊት ለፊታችን ትንሽ ራቅ ብሎ
አንድ ቀጠን ረዘም ብለው ጥቁር ሱፍ የለበሱና አሽከር ያስከተሉ የቀይ ዳግ
አዛውንት ወደ እኛ ሲመጡ አየሁ። አባቴ ነው።
የወዲያነሽ እጅ በዱላ የተመታ ይመስል ተዝለፈለፈ። የበደነ አካል የያዝኩ መሰለኝ፡፡ እጅዋን ለቅቄ ወደ ጎን ገፋኋት። አልራቀችም፡፡ ከአባቴ በስተጀርባ እናቴና እኅቴ አንዲት ነባር ሠራተኛ አስከትለው ይከተላሉ፡፡የወዲያነሽ ትንሽ ፈንጠር ብላ በግራ ጎናቸው ዐልፋ ሄደች። በከዘራ በጥፊና በክርን ደብድበው ካባረሯት ወዲህ እናቴንና እህቴን ስታያቸው የመጀመሪያ የመጀመርያ ጊዜዋ ነበር።
ሁለት እጆቼን ወደኋላዩ አድርጌ ልምጥ ብዬ እጅ ነሳሁ፡፡ እሱ ግን ሌላም እላለ። «እንተ ከሃዲ! ወይኔ ያየህ ይራድ! የማታ ማታ እንዲህ ታደርገኝ?
በቁሜ ቀብረኸኝ ትሄድ? አዝኘብሃለሁና ወላዲተ አምላክ በዕለተ ቀኗ ትመስክር
አይቀናህም!! እንዲሁ አውታታ ሆነህ ትቀራለህ! በል ሒድ!» አለና ከእግር
እስከ ራሴ በጥላቻ ግርምሞኝ ሄደ፡፡
ከአባቴ በስተጀርባ ቆማ የነበረችው እናቴ ዐይኔን ከማየት ብላ ከሠራተኛዋ ጋር ታወራ ነበር። ነጭ ጋቢ የለበሰችው የውብነሽ በፍርሃት ዐይኗን እያቁለጨለጨች ጨበጥ አድርጋኝ ወደ እነርሱ ተመለሰች፡፡ ሆድና ጀርባ ሆነን
እነርሱ ወደ ደቡብ እኛ ወደ ሰሜን ተጓዝን፡፡ የወዲያነሽ ምን አሉህ?' እንኳ ብላ አልጠየቀችኝም፡፡ እኔም አላነሣሁላትም፡፡ የወጣንበትን ጉዳይ ፈጽመን ወደ ልጃትን ዘንድ ሄድን፡፡
ከዚያ ቀደም በወሰድንለት የመላያ እርሳሶች እየተጠቀመ በአንድ መስመር አልባ ወረቀት ላይ የምታምር ሰማያዊ አበባ ሥሉ ቅጠሎቿን አረንጓዴ ቀለም እየቀባ ሲያሳምራት ቀስ ብለን ከበስተጀርባው ቆመን አየን።እኔና የወዲያነሽ እርስ በርሳችን ተያየን፡፡ ፊቱን ወደ ምዕራብ አዙሮ በመቀመጡ ለመጥለቅ የጥቂት ጊዜ ጉዞ ብቻ የቀራት ፀሐይ ብርሃኗን በስላች ለቃ በነጩ ወረቀት ላይ ደማቅ ቦግታ ፈጥራለች። ዐይኖቹ እንዳይጎዱ ሠጋሁ፡፡ ከበላዩ እንደ ታቦት ድባብ ጉፍ ብሉ ቅርንጫፎቹን በቅጠሎች ፤ያሳመረው የባሕር ማዶ ተክል ለሰስ ባለው የምሽት ነፋስ ይወዛወዛል።ከበስተጀርባችን ባላው መሬት ላይ ያረፈው የዛፍ ጥላ በውዝዋዜ እየተመራ በቅርንጫፎቹና በቅጠላ ቅጠሎቹ ሥዕል ይሥላል። አንድ ሉክ ገለጠ። አራት ረዘም ረዘም ያሉ የተሰናሰሉ ተራሮች በተጉበጠበጡ መስመሮች ተያይዘው ቡናና ጥቁር ቀለም ተቀብተዋል፡፡ ዕጫፍ ጫፋቸው ላይ ሁለት ሁለትና አልፎ ልፎም ሦስት ዛፎች ጉች ጉች ብለዋል። ከተራሮቹ እግር አንሥቶ እስከ ወረቀቱ የታች ጠርዝ ድረስ አረንጓዴና ቀይ፣ ቢጫና ሰማያዊ መስመር
ከወዲያ ወዲህ ተመሳቅለው ጭራሮ መሰል ውስብስብ መረብ ጥረዋል።
ከየተራራው መኻል ላይ ደግሞ እየተጥመዘመዙ የሚወርዱ ደማቅ ሰማያዊ መስመሮች አሽቆልቁለዋል። ጅረቶች መሆናቸው ነው፡፡
እኔና እርሷ ደረቁ ፀደይ አፈር ላይ እግሮቻችንን ዘርግተን ተቀመጥን። ጋሻዬነህ በሁለታችን መኻል ፊቱን ወደ እኛ አዘሮ በመቀመጡ ሁለታችንም በወሬና በጥያቄ ተሻማነው። ዐልፎ ዐልፎ ኮልተፍ ይላል፡፡ ፀሐይ ያላትን ሙቀትና ብርሃን ዘክዝካ የጨረሰች ይመስል ቀስ በቀስ ሙቀትና ብርሃን እየነፈገች ከተራራው በስተጀርባ ተሰወረች። ዳግማኛ የማትመለሰዋ ቀንም አብራ ለዘልዓለም ጠለቀች። ሕፃናቱና ከፍ ከፍ ያሉት ልጆች ሁሉ ወደ መኝታ ክፍላቸው የሚዝብት ጊዜ በመድረሱ ልጆች ሁሉ ሊገቡ ነው፡ልሂድ እኔም» ብሎ በየተራ አየን። ያመጣንለትን ዕቃ በቀኝ እጁ ዐቅፎ
የሥዕል ደብተሩንና እርሳሶቹን በግራ እጁ ጨብጦ ተነሣ፡፡ እኛም ጉንጩን
ስመን ተለየነው:: ከዚያን ዕለት ወዲህ ስለ ልጃችን ጉዳይ ሐሳብ ገባን፡፡ከእኛው ጋር ቢሆን ለአስተዳደጉ እንደሚበጅ ስንወያይበት ሰነበትንና ከእጓለ
ማውታ ልናወጣው ተስማምተን ዝግጅቶች ጀመርን።
በዚህ መኻል የዘመዶቼን ሁኔታ ለማወቅ ስለ ጓጓሁ እስኪ የሚባለውን ልስማ በማለት ከሩቅ ዘመዶቼ ውስጥ ጠንቃቃውን መርጬ አንድ ቀን ወደ
ቤት ይዤው መጣሁ፡፡ እንግዳዩ እንግዳዋ በመሆኑ አንጀት በሚያርስ አኳኋን ተቀብላ አስተናገደችው፡፡ ለመሄድ ሲነሣም የእንግዳ ወጉ ሁነኛ ጥቂት ልሸኝህ ብዩው አብረን ወጣን፡፡ ሳይታወቀን ብዙ ተጓዝን፡፡ በጨዋታችን መኻል«መቼም ስለዚህ ጉዳይ ወላጆችህ ምንም አልሰሙ፣ ሰምተዋል እንዴ?» ብሎ ጠየቀኝ፡፡
ለካስ አንድ ቀን እነጉልላት ቤት በእንግድነት እንደተቀመጠ እኔና
ጉልላት ስንነጋገር አንዳንድ የቃላት ፍንጣሪ ወሬ ሰምቶ ኖሯል። «አዎ እስከ
ዛሬ ድረስ አልሰሙም ያም ሆነ ይህ መስማታቸው አይቀርም የእኔ ውሳኔ ግን
አይለወጥም» ብዬ ሐተታ ሳላበዛ ዝም አልኩ፡፡ “ታዲያ ነገ ጧት አባትህ
ባድራጎትህ ተናደውና ተበሳጭተው ከዚህ ሁሉ ሀብት ንብረታቸው ላይ ቢነቅሉህስ?» አለኝ፡፡ “ይኸ ቀላል ጉዳይ ነው። ሁልጊዜ ሰዎች ሸምጥጠው ያወረዱትን ፍሬ መመገብ የለብኝም፡፡ እኔም በድርሻዬ መሽምጠጥና የመሽምጠጥን ልፋት ማየትና መቅመስ አለብኝ፡፡ ዛሬ ተወዝፈ ነገ በሚወረስ ነገር አልተማመንም፡፡ እሱ ያፈራውን ንብረትና ሀብት ያህል እኔም በዘዴና በቆራጥነት ከሠራ አገኘዋለሁ። ከዚያ በኋላ እኔም በፈንታዩ አውራሽ ሆንኩ ማለት ነው፡፡ ይህ ነው

👍3❤1