#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
....ሎው ጉድማን ስታር ተብሎ ከሚጠራው የሎስ አንጀለስ መንገድ ላይ መኪናውን ሲያስገባ ፀሐይ መጥለቅ ጀምራ ነበር። የሴንቸሪ ሲቲ ትልቅ ፎቅ
ደግሞ በሎስ አንጀለስ ሐምራዊ ብርቱካናማ የምሽት ፀሐይ የሆነ ህልም
ውስጥ የሚገኝ ፎቅ መስሎ ቆሟል።
በመንገዱ ዳር እና ዳር የሚገኙት
የዘንባባ ዛፎችም በሞቃታማው ንፋስ ልክ እንደሰከረ ሰው ይወዛወዛሉ።
የፖሊስ ባጁን እንደያዘም የህንፃው እንግዳ ተቀባይ ዴስክ አጠገብ
በመድረስ “መርማሪ ፖሊስ ሉው ጉድማን የግድያ ወንጀል ምርመራ ፖሊስ
ነኝ፡፡ ክፍል ቁጥር 706 ን ለማየት ነው የመጣሁት እና ቁልፉን ትሰጪኝ”
አላት ላላቲኖዋ እንግዳ ተቀባይ ፈገግ እያለ፡፡ ልክ እንደሁልጊዜው የፍርድ
ቤት ማዘዣ ወረቀት ሳይዝ እንደሚያደርገው ማለት ነው፡፡
ልጅቷም የአፀፋ ፈገግታዋን ለግሳው እና በውስጧም ኮሌምቢያ ውስጥ ከምታውቃቸው ፖሊሶች የተሻለ መልካም ፀባይ እንዳለው እያሰበችም “ አለኝ፡፡ ግን አያስፈልግህም፡፡ ዶክተር ሮበርትስ ቢሮዋ ከገባች አንድ ሰዓት አልፏታል። አሁንም ቢሮዋ ውስጥ ትገኛለች፡፡ በግራ በኩል ያለውን አሳንስር መጠቀም ትችላለህ አለችው።
"አመሰግናለሁ” አላት መብሸቁን ለመደበቅ ፈገግ እያለ፡ ጉድማን የኒኪ
ቢሮ ውስጥ ብቻውን በመግባት ቢሮዋን መበርበር ነበር የፈለገው፡፡ በዚህ
ሰዓት ምን ትሰራለች? ብሎ ራሱን ጠየቀ፡፡ ግን ቢሮዋ ውስጥ እሷ መኖሯ ጥሩ ነው ብሎም አሰበ፡፡ ምክንያቱም ቀን ላይ ባልደረባው ጆንሰን እሷን ስላበሸቃት ብዙ ልትነግራቸው የምትፈልጋቸውን ነገሮች መናገር ትታ ነበር::ምናልባት አሁን እሱ ብቻውን ስለሆነ ይበልጥ ግልፅ ሆና ልታወራኝ ትችላለች ብሎ አሰበ እና ተረጋጋ።
በአሳንሰሩ ሰባተኛው ፎቅ ድረስ ወጣና በኮሪደሩ ላይ እየተራመደ የዶክተር ኒኪ ሮበርትስ ቢሮ ጋ ሲደርስ ቆመ፡፡ በሩ ገርበብ ብሎ ስለተከፈተም ወደ ውስጥ መሰስ ብሎ ገባ፡፡ ኒኪ ጀርባዋን ሰጥታ በወረቀት መክተፊያው ማሽን ውስጥ ወረቀቶችን እያስገባች ወረቀቶችን እየከተፈች ነበር፡፡ እግሯ ሥር ካስቀመጠችው ካርቶን ውስጥ ዶክመንቶችን እያነሳች ወደ ማሽኑ እየከተተች እና እየከተፈች ልትጨርስ ስትል
“እንዴት ነሽ?” የሚል ሰላምታን ስጣት፡፡
ኒኪም ድምፁን ስትሰማ በከፍተኛ ድንጋጤ ቀለሙ የተለወጠውን ፊቷን
ወደ እሱ በማዞር ፍርሃት በተሞላ አይን ተመለከተችው፡፡
“በእግዚአብሔር! በፍርሃት ነፍሴ ልትወጣ ነበር!” አለችው፡፡
“ይቅርታ” አላት እና እጇ ላይ የቀረውን ለማሽኑ ልታጎርሰው ያዘዘችውን
ፋይል በጉጉት እየተመለከተ
“ምንድነው የያዝሽው?” አላት፡፡
“ምንም አይደለም። ፅዳት እያካሄድኩኝ ነው::” አለችው እና ወረቀቱን ወደ ማሽኑ አፍ ከተተችው:: ማሽኑም ወረቀቱን እየሸረካከተ በዚያኛው ጎን
በኩል ሲተፋው ኒኪ “አታስብ ጠቃሚ የሆኑ የታካሚዎቼ ፋይሎች አይደሉም። ባልደረባህ መጥቶ ይህንን ሲያይ ይበልጥ የማያምንበት ነገር እንዳገኘ እንዳያስብ እና ይበልጥ እንደ ወንጀለኛ
ሌላ እኔን እንዳይመለከተኝ ደግሞ”
“እውነቱን ስለነገርሺኝ አመሰግናለሁ::” ብሎ ፈገግ አለ። ደግሞስ እንዲ
ዶክተር ኒኪ ያሉ ቆንጆ ሴቶች ፊት ሥርዓት ያለው ፖሊስ ሆኖ መተወን እንዴት ያቅተዋል?
“እና ቅዳሜ ምሽት እዚህ ምን እግር ጣለህ መርማሪ ፖሊስ ጉድማን?”
ብላ ማሽኑን እያጠፈች ጠየቀችው።
“ጠዋት ላይ ስለተፈጠረው ነገር ይቅርታ ልጠይቅሽ ነው የመጣሁት” አላት እና ውሸቱን በመቀጠልም መርማሪ
ፖሊስ ጆንሰን አንቺን እንደዚያ መናገር
አልነበረበትም።” አላት።
“መልካም” አለች እና ኒኪ በመቀጠልም “ግን እኮ ለጥፋቱ ይቅርታ መጠየቅ ያለበት እሱ እንጂ አንተ መሆን አልነበረብህም። አይመስልህም?”
ጉድማንም ትከሻውን ሰብቆ “እኔ እና እሱ ባልደረቦች አይደለንም። በዚያ
ላይ ደግሞ ለጥፋቱ ይቅርታ መጠየቅ አንደኛው የእሱ ችግር ነው እና እኔ
ልጠይቅለት ብዬ ነው” አላት።
ኒኪም ሳቀች እና “አሁን ገባኝ” አለችው። መርማሪ ፖሊስ ጉድማን ለማውራት ቀለል የሚል ሰው ስለሆነ ደስ ብሏታል “መቼስ እየዋሸሁ እንዳልሆነ ይገባሃል ብዬ አስባለሁ።” ብላ በማስከተልም “ባለፈው ምሽት እኔ የምኖርበትን ቦታ የሚያውቅ ሰው መኖርያ ሰፈሬ ድረስ መጥቶ በመኪና ገጭቶ ሊገድለኝ ነበር” አለችው፡፡
አምንሻለሁ” አላት እና ጉድማን በማስከተልም “ጆንሰንም ቢሆን
ያምንሻል። ምክንያቱም የምርመራ ቴክኒሽያኖችን ብዙ ብዙ ማስረጃዎችን
ከአካባቢው ላይ ሰብስበዋል”
“እውነትህን ነው?” ብላ ኒኪ የመገረም ፊት እያሳየች “ታዲያ ለምንድን ነው እኔን የቀን ቅዠተኛ እያለ የሚወነጅለኝ? እኔ ምን አድርጌ ነው?”
“እሱን እንኳን አላውቅም” ብሎ ለሰኮንዶች ያክል ዝም ብሎ ቆየ፡፡
ከዚያም “ምናልባት እኔ እና አንቺ ሆነን እሱ አንቺን ለምን እንደዚህ
እንደሚመለከትሽ ኋላ ላይ እንደርስበታለን፡፡ መጠጥ ልጋብዝሽ ዶ/ር
ሮበርትስ?”
ሎስ አንጀለስ ውስጥ ብዙ ሰው ወደማይበዛበት ጎዳና ታናስ ወደ ተባለ
ባር ይዟት ሄደ:: ኒኪ ጃክ ዳንኤልን አዘዘች እና ሲቀዳላት ብርጭቆውን
( ጉድማን አስተናጋጁ ሙሉውን ጠርሙስ ጠረጴዛው ላይ ትቶት እንዲሄድ
ሙሉውን መጠጥ በአንድ ትንፋሽ ጨለጠችው። በዚህም የተበረታታው
በምልክት ነገረው እና ትቶላቸው ሄደ፡፡
“ባለፈው ምሽት ላይ እኔን መኪና ገጭቶ ሊገድለኝ የነበረው ሰው ሊዛን እና ትሬይን የገደለው ሰው ነው ብለህ ታስባለህ?” ብላ በቀጥታ ጠየቀችው።
“ምናልባት እራሱ ወይንም እነርሱን ከገደለው ሰው ጋር ግንኙነት ያለው ሰው ነው ብዬ አስባለሁ ብሎ ጉድማን
መጠጡን ተጎንጭቶ ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ ገዳዩ አላማ ያደረገው አንቺን ነው ብዬ ነው የማምነው።” አላት፡፡
ኒኪ ለሊዛ ፍላንገን ባዋሰቻት የዝናብ ኮቷ የተነሳ ኒኪን መስላቸው በስህተት እንደገደሏት ጭምር ግምቱን ነገራት፡፡ በዚያ ላይ ባለፈው ማክሰኞ የተሞከረባት ግድያ የሚያመለክተው ኒኪ ከሊዛ እና ከትሬይ ጋር ባላት ግንኙነት ምክንያት ግድያዎቹ እንደተከወኑ ጭምር አስረዳት፡፡
“ልክ ነህ እንበል እሺ” ብላ ኒኪ በእርጋታ መለሰችለት እና “እሺ እነዚህ ሰዎች እኔን ለመግደል እየተከታተሉኝ ነው ልበል። ግን እነዚህ ሰዎች እኔን ለመግደል ለምንድነው የሚፈልጉት? ምንድነው ምክንያታቸው?”
“አሁን ላይ አንቺን ለመግደል ምክንያታቸው ምን እንደሆነ አላውቅም”
ብሎ ጉድማን በመቀጠልም “ግን ሊዛን እና ትሬይን የገደሉት ሰዎች ሁለቱንም ሰዎች አሰቃይተዋቸው ነው። ሰዎቹ ደግሞ ሰዎችን የሚያሰቃዩት
የሆነ መረጃን እንዲሰጧቸው ስለሚፈልጉ ነው። አይመስልሽም?” ብሎ
ጠየቃት፡፡
ኒኪም ለአፍታ ያህል ስታስብ ቆይታ “እኔም እንደዚያ አስቤው ነበር።
ግን ደግሞ ገዳዮቹ በሰዎች ስቃይ የሚደሰቱ ሳዲስቶች ቢሆኑስ?” ብላ
ጠየቀችው፡፡
ጉድማንም መጠጡ ያለበት ብርጭቆ ላይ እንዳፈጠጠ ይህም ሊሆን
ይችላል ብሎ አሰበ፡፡
“የሞቱት ሰዎች ላይ የሌለ የሞተ ሰው ህዋስ ተገኝቷል የሚባለው ነገር
እውነት ነው?” ብላ ኒኪ ጠየቀችው፡፡
ጉድማንም በጥያቄዋ በጣም ደንግጦ “ይህንን ደግሞ ማነው የነገረሽ?”
“ከኢንተርኔት ላይ አንብቤው ነው” ብላ ኒኪ በመቀጠልም “የዞምቢ ገዳይ በሚል ርዕስ ዙሪያ በኢንተርኔት ላይ ሰዎች ዜናውን እየተቀባበሉት ነው” አለችው፡፡
ጉድማንም በሰማው ነገር በጣም በሸቀ። ይህን የመሰለ መረቅ መረጃቸው ከእነርሱ አፈትልኮ ከወጣ በኋላ ደግሞ ነገሩ እየሰፋ ይሄድ እና የአሽሙር ጋዜጣ ገፆች ላይ ይወጣል ብሎ አሰበ፡፡
“እውነት ነው ነገሩ” ብላ ኒኪ ተጭና ጠየቀችው፡፡

👍1
#የወድያነሽ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል
...ለቤት ወጪ እያልኩ ከምሰጣት ገንዘብ ላይ እያብቃቃች ልዩ ልዩ ተጨማሪ የማድ ቤት ቁሳቁሶች ገዛች፡፡ ዕቃዎቹ ሳይሆኑ ቁጠባዋ አስደሰተኝ።
የወዲያነሽ' ዛሬ የማድረው ወላጆቼ ቤት ነው፡፡ ስለዚህ እንዳትሠጊ ትፈሪያለሽ እንዴ?» ብያት በምሄድበት ጊዜ «ለእኔ ብለህ እኮ ተሠቃየህ ወይ አበሳህ» በማለት ራሷን ታማርራለች፡፡
ከዋል አደር የወህኒ ቤቱን ሕይወቷን እየረሳች አዲሱን ኑሮ ተላመደች::
ፈገግታዋ" ለዛና ጨዋታዋ ቀስ በቀስ ጎረፈ፡፡ እኔ ግን ወላጆቼ እንዳሰቡትና
እንደ ተመኙት ሳይሆን፣ ማንም ሳያውቅና ሳይሰማ፣ ጠላ ሳይጠመቅ፣ ጠጅና
ፍሪዳ ሳይጣል፣ ድንኳን ሳይተከል፣ ዕልልታና ሆታው ሳይቀልጥ፣ ጉልበት ስማ ሳልመረቅ፣ ከአንዱ የመከራ ጊዜ ጓደኛዬ በስተቀር ሚዜ ሳልመርጥና
ሳልመለምል፣ ሞላ ጎደለ ብዬ ሳልማስን፣ የእኔ ናት ብዬ ያመንኩባትንና ሕሊናዬ
ሙሉ በሙሉ የተቀበላትን የወዲያነሽን የኑሮ ጓደኛዪ ኣድርጌ ጎጆ ወጣሁ፡፡
ወደዱም ጠሉም የወዲያነሽ የሕይወቴ ምሰሶ ሆና በይፋ ብቅ የምትልበት ብሩህ
ቀን መምጣቱ አይቀርም፡፡
የተከራየነው የጉልላት አጎት ቤት አርጀትጀት ያለ በመሆኑ ግድግዳው
ላይ የተለጠፉት የአዲስ ዘመንና የሰንደቅ ዓላማችን ጋዜጦች ተገሽላልጠው ፀሐይ
እንዳጠቃው የሙዝ ቅጠል ዐልፎ ዐልፎ ተሽመልምለዋል። ምርጊቱ ላይ ተለጥፈው የተጋደሙት የጤፍ ጭዶች ይታያሉ፡፡ ያም ሆነ ይህ የወዲያነሽ
አብራኝ ስላለችና አብሬያት ስላለሁ ያለሁትና ያለችው በፍቅር ውብ እልፍኝ
ውስጥ ነው፡፡ ከፋ ሲለኝና ሐሳብ ሲያስጨንቀኝ ግን «የሕይወት ጥቀርሻ» ማለቴ አይቀረም፡፡
ምንጊዜም ቢሆን ጉልላትና የወዲያነሽ ባንድ ላይ ተቀምጠውም ሆነ ቆመው ሲያወሩ ደስ ይላሉ። የናቴ ልጅ እንኳ እንደ ጋሼ ጉልላት አይሆንልኝም፣ ጋሼ ጉልላት! ጋሼ ጉልላት ያንጀት ናቸው» ትላለች፡፡
ዓርብ ማታ ነበር፡፡ የወዲያነሽ ከተፈታች 17 ቀን ሆኗታል፡፡ ጉልላት ጀምሮልኝ የነበረውን ሐሳብ «ያም ሆነ ይህ ያለፈው ሁሉ ዐልፏል። የመጪውን ጊዜ ኑሮ ለማስተካከል ከባድ ጥረት ያስፈልጋል» አለና ዝም አለ። ዝም የማለትም
አመል አለበት። ይህን ተናግሮ እንደ ጨረሰ ሐሳቡን እያሰላሰልኩና እየሸነሸንኩ
በማሰብ በቆምኩባት መሬት ላይ የተተከልኩ ይመስል ውልፍት ሳልል ብዙ
ደቂቃዎች ቆየሁ፡፡ የሰበሰቡን አራት ማዕዘን አግዳሚ ዕንጨት እንደያዝኩ ትንሽ ቀና ብል ምሥራቃዊውን የበጋ ሰማይ ባዘቶ የሚመስል ደመና እዚህና እዚያ ጉች ጉች ብለውበታል። በውስጡ በሚከናወነው የአየር ግፊት ሜክንያት ደመናው ተለዋዋጭ ቅርፆች እየሰራ ወደ ምእራብ ተጓዘ።ደመናው ወደ ምእራብ በገሠገሠ ቁጥር የተለያየ ውበትና መጠን ያላቸው ከወክብት ወደ ምስራቅ የሚጓዙ ይመስላሉ ደመናው ጥርግ ብሎ ከሄደ በኋላ ግን እንደ ነባር አቀማመጣቸው በየነበሩበት ቀጥ ብለው ይቀራሉ።የእኔም ሐሳብ ይጓዝ ይክነፍ ይመጥቅ ይውዘገዘግና አንዲት ተራ የሐሳብ ድንበር ሳያገኝ ቀጥ ይላል።
የእናቱን ጡት እያነፈነፈ እንደሚፈልግ የውሻ ቡችላ ሐሳብ ሲያነፈፍ የቆየው ጉልላት እንግዲህ» ብሉ ንግግሩን ጀመር ሲያደርግ ወደ እርሱ መለስ ብዬ ማዳመጥ ጀመርኩ። በሕይወት ውስጥ ባሉት የኑሮ ጐዳናዎች በምትጓዝበት ጊዜ የሚያጋጥሙህን ፈተናዎችና ትግሎች ሁሉ ሳትሸሽና ሳታመነታ መታገል ይገባሃል፡፡ በዕንባዋ የሚረጥቡት ዐይኖቿ ያሳዝኑኛል፡፡ሥቃይዋ ይመረኛል' ማለት በቂ አይደለም፡፡ ማዘን ቢሉህ ማዘን አይምሰልህ።አንድ ምጽዋት ሰጪ ሃይማኖተኛ የሰማይ በር ያስከፍትልኛል ለሠራሁት ኃጢአት መደምሰሻ ይሆንልኛል ብሎ ለአንድ ለማኝ ቁራሽ ሲሰጥ ያዝናል፤ ያን በማድረጉ የራሱን የማይታይ ሥውር ጥቅም ጨመረ እንጂ ለማኙን ከራሱ
ጋር አላስተካከለውም፡፡ አድርግም ቢባል እሺ አይልም፡፡ አንተ ግን ከዚህ የተለየህ
ሁን። አሁን በምትኖርበት ኅብረተሰብ ውስጥ የመልካም ኑሮዋ ጀንበር
እንድትወጣና እንድትጠልቅ የምታደርጋት አንተ መሆንህን ዕወቅ።
«እኔም ራሲ ማን መሆኔን ለማወቅ የምችለውና ምግባሬን አሻግሬ
በማየት እኔነቴን ለማወቅ የምበቃው የአንተን የትግል አረማመድና ውጤት
እየተመለከትኩ ነው» ብሎ በእኔ ላይ ሙሉ እምነትና ተስፋ እንዳለው ለማረጋገጥ ረጋ ባለ ሁኔታ ምራቁን ውጦ ዝም እለ፡፡ እንደገና ከወደ ምሥራቅ የመጣው ደመና የከዋክብቱን ብርሃን እየጋረደው ሲሄድ አካባቢያችን ግራጫ ጨለማ አለበሰው።
በየወዲያነሽ ሕይወት ላይ የደረሰውን የመጥፎ ልማድ ውጤት ሁሉ በማስወገድ ሌላ አዲስ ትርጉምና ይዞታ እንዲያገኝ ለማድረግ የገባሁትን የተግባር ቃል አሳጥፈውም፡፡ መሸከም የሚገባኝን ቀንበር ከዛሬ ጀምሬ እሸከማለሁ፡፡ ሆኖም
ድል ማድረግ አለብህ ማለት ሳይሆን የሚጠብቀኝን ተቃውሞና የቤተሰብ መራር አንካሰላንትያ እንድታውቅልኝ ያስፈልጋል” አልኩና እንደ አዲስ ትክል የቤት ምሰሶ ቀጥ ብዬ ቆምኩ፡፡
ጉልላት ራሱን እየነቀነቀ ወደ ቤት ገባ፡፡ ተከትዬው ገባሁና አጠገቡ ተቀመጥኩ፡፡ የወዲያነሽ የጣደችው ሻይ እየተንተከተከ እንፋሎቱ አየር ውስጥ እየገባ ይዋጣል፡፡ እሷ እንገቷን ደፍታ በጎድጓዳ ሳህን ውስጥ የሻይ ስኒ ታጥባለች፡፡
አሮጊቷ ሠራተኛ ትንሽ ራቅ ብለው ጉልበታቸውን ኣቅፈው ያንጎላጃሉ፡፡
በጣም ጫን ሲላቸው ለሰስተኛ ንፋስ እንደምታወዛውዛት መቃ ወደ ጎን ወይንም ወደ ፊት ጠንቀስ ይሉና ደንገጥ ብለው ቀና ሲሉ ትናንሽ ዐይኖቻቸው ብልጭ ብለው ይከደናሉ፡፡ ሻዩ ተቀድቶ ቀረበልን፡፡
ጉልላት እንፋሎቱ እየተነነ የሚወጣውን ሻይ እየተመለከተ «እኔ እኮ የምልህ» ብሎ ንግግር ጀመረ የሁለታችን ጠንካራ ፍቅርና አንድነት ብዙ ነገር መጀመርና መፈጸም የሚችል መሆን አለበት፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ እብራችሁ
መታገልና የሚያጋጥማችሁ የጋራ መሰናክል ሁሉ ሽንጣችሁን ገትራችሁ
መቋቋም እንጂ መሽሽና ያላግባብ ማፈግፈግ የእናንተ ድርሻ መሆን የለበትም፡፡
በተለይም አንተ እሷን እያጠናከር ክና ሳትነጠል ለአዲስ ዘላቂ ግብ
የሚገሠግሥ እውነተኛ ዓላማ እንዳለሁ አሳይ። አንተ በኑሮህ እና በትምህርትህ
ምክንያት የተሻለ ዕውቀትና ችሎታ አለህ፡፡ ምሳሌዩ ቅር እንዳያሰኝህ እጂ
ቀላዋጭ የሚቀላውጠው የአስቀልዋጩን ያህል ስለሌለው ወይም በግልጽ በሥውር ስለ ተነጠቀ ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ አግዛት፣ አብራህ ትሠለፋለች::
ዓርማህን በፅናት ለመትከል ካልተጣጣርህና አካባቢህንም ለመለወጥ እምነትህን ካላስፋፋህ የጥንቱ ልማድ እንደ ክፉ አውሬ አሳዶ ይበላሃል። የበሰለ ሕሊና ያለው ሰው የምትሰኘውም ብዙዎችን ላስቸገረ ከባድ ጥያቄ መልስ ለማግኘት ስትል ከራስህ አልፈህ በተግባር የሚተባበሩህን መልካም ሰዎች በማፍራት ለዘላቂ መፍትሔ ስትታገል ነው፡፡ የዚህን የአሁኑን ሕይወት ቅርፅና ይዘት መለወጥ ያስፈልጋል። አሮጌውንና ለሕዝብ የማይጠቅመውን ነገር ሁሉ እያፈራረሱ በአዲስ የአኗኗር ስልት መተካት ይገባል፡፡ ግን አፈጻጸሙ እንደ አወራሩ ቀላል አይደለም» ብሎ በንግግሩ መኻል በረድ ያለችውን ሻይ መጠጣት ጀመረ፡፡
የወዲያነሽ ጉልላት ስለ እኔና ስለ እርሷ እንደ ተናገረ ስለ ገባት የመጨነቅ ሁኔታ ፊቷን ወረረው:: በስኒው ውስጥ የቀረችውን ሻይ ጨለጠና
የወዲያነሽን አሻግሮ እያየ «አንቺም ከእንግዲህ ወዲህ ነቃ ነቃ በይ! ይኸ ዐይን እስኪያብጥ እያለቀሱ አጉል መተከዝ በፍፁም አይጠቅማችሁም፡፡ ምንም እንኳ እንዳንቺ ወህኒ ቤት ገብተን ባንታሰርም እኛም ያንችኑ ያህል ከውጪ ሆነን ተሠቃይተናል። ሐሞትሽን ኮስተር አድርገሽ ለመታገል ከበረታሽ መልካሟ
የቤትሽ እመቤት አንቺ ብቻ ነሽ» ብሎ ጠበል እንዳልጠቀመው በሽተኛ ሻይ
እንዳስሞላለት

👍4