አትሮኖስ
279K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
461 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

......ብዙም ሳይቆይ አንድ ቀጭን አጭር ሰው መንገዱን ተሻግሮ ወደ ቢጫዋ ቁርስ ቤት ሲጣደፍ ተመለከተ፡፡ኮቱን ትከሻው ላይ እንጠልጥሎታል፡፡ ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት ካለው የላይቤርያ ኤምባሲ እስከ ቁርስ ቤቷ ለመድረስ ብዙ ባያስኬድም ወደፊት ደፋ
ደፋ የሚለው ሰው ረዥም መንገድ የተጓዘ ይመስላል፡፡ ሰውየው ከቁርስ ቤቷ እንደደረስ ወደውስጥ ከመግባቱ በፊት ቆም ብሎ ዙሪያውን ተገላምጦ
ተመለከተ፡፡ ወዲያው ዘው ብሎ ወደ ውስጥ ገባ፡፡

ሰውየው ወደ ውስጥ ሲገባ ናትናኤል ፈጠን ብሎ ከጥግ ወዳለ
የህዝብ ስልክ አመራና አንብቦ በጭንቅላቱ የያዘውን የቢጫዋን ቁርስ ቤት ቁጥር ደወለ፡፡

“አ.ቤት::” አለ የሴት ወይዘሮ ድምፅ፡፡
ያ ክምር ጡታቸው መጥቶ ፊቱ ላይ ድቅን አለበት ናትናኤል፡፡

“እንደምን ዋሉ...ደህና ኖት?” ሴትየዋ መልስ ከመስጠታቸው በፊት አጣደፋቸው “ገብረየሱስ ነኝ..እንደምን ኖት?!” አለ እንደሚያውቃቸው ተዝናንቶ፡፡ “እባኮት ስዩም ጋር ቀጠሮ ነበረን እርሶ ቤት
ያገናኙኝ…ስዩም ይበሉልኝ…እቤትዎ ውስጥ ነው ያለው…ደህና ኖት ግን
እርስዎ..በሉ ስዩምን ያገናኙኝ..” በላይ ቀላይ አጣደፋቸው፡፡

“የማን ስዩምን? አሉ ሴትየዋ ፋታ ሲያገኙ፡፡

“እንዴ!.. ረሱን እንዴ? እቤትዎ በልተን ጠጥተን? አይ የርሶ ነገር! ይብሉ ስዩም ይበሉልኝ፡፡ አይ የርሶ ነገር! ደንበኞቾንም ይረሱ ጀመር?” አጣደፋቸው፡፡

“ኧረ ንሽቴ! የምን መርሳት አመጣህብኝ::!” አሉ ሴትየዋ ድፍረት
አሰባስበው:: “ደሞ እናንተን ደንበኞቼን ልርሳ? ሄ! ሄ! ሄ! ገና ሳላረጅ ምነው
ባክህ! ደህና ነህ ግን አንተ ጠፋህሳ?”
ሴትየዋ ሲጣሩ “ስዩም የሚባል! ስልክ?” ሲሉ በስልኩ ውስጥ ተሰማው፡፡ ነፍሱ መለስ አለችለት:: ስልኩን ጆሮው ላይ እንዳይጠራቅምበት ሰግቶ ነበር፡፡

“ሀሎ… ” አለው ያው ነፍናፋ ድምፅ፡፡
“ስዩም? ” ናትናኤል ቆፍጠን ባለ ድምፅ ጠየቀ፡፡
“ነኝ.የት…?”

“ዝም ብለህ አዳምጠኝ::ቁርስ ቤቷ ውስጥ ይጠብቀኛል ብለህ አስበህ
ከሆነ ሞኝ ነህ፡፡ መልዕክቱን ብቻ እሰጥሀለሁ፡፡ ትስማማለህ?” አለ ናትናኤል ጥድፊያ በተቀላቀለው ድምፅ፡፡

“አዎ አዎ፡: ቀጥል፡፡”

“ጥሩ…. እንዳልኩህ ካልቨርት ለአንተ የማደርስለትን መልዕክትና፡ በርከት ያለ ገንዘብ ሰጥቶኛል፡፡ መልእክቱን ከመስጠቴ በፊት ግን አንተነትህን ማረጋገጥ አለብኝ፡፡”

“ነኝ..ነኝ ግድ የለም:: ስዩም ነኝ፡፡”

“ዝም ብለህ አዳምጠኝ! ለምጠይቅህ ጥያቄ ብቻ ኣጫጭር መልስ ነው የምፈልገው፡፡” አለ ናትናኤል ሰውየውን ይበልጥ ለማደናገር ቱግ ብሎ:: “ካልቨርት በየትኛው ጣቱ ላይ ነው ቀለበት የሚያደርገው?” ያዘጋጃትን ማስመሰያ ጥያቄ አስቀደሙ:: በአውራጣቱ፡ ላያ ቢለውም ግድ አልነበ
ረውም፡፡ ነገር ግን ወደ ዋናዎቹ ጥያቄዎች ከመግባቱ በፊት የሰውየውን
ጭንቅላት ማሟሸት አለበት፡፡
“ቀለበት አያደርግም ካልቨርት::” አለ ሰውየው በሚያስደንቅ ፍጥነት::

“ጥሩ፡፡ አሁንም ፈጣን መልስ እፈልጋለሁ:: ተጠንቀቅ ብትሳሳት
ወይ ብትጠራጠር፡፡ ብትዘገይ ስልኩን ዘግቼ ነው የምሄደው:: የምፈልገው
ትክክለኛውን ስዩም ነው:: የያዝኩትን በርካታ ገንዘብ ላልሆነ ሰው ማስታቀፍ፣
አልፈልግም:: አድምጥ:: የካዛንቺሷ ሴት ስም ማነው?” ናትናኤል በጭንቀት
ትንፋሹን ያዘ፡፡

“የምሥራች ይልማ!” አለ ሰውየው ሌላ ሰው እንዳይቀድመው የፈራ ይመስል በጥድፊያ፡፡
“የስልክ ቁጥሯስ?” አከታትሉ ጠየቀው፡፡
“ትዝ አይለኝም::?”
“እንግዳው ስዩም አያደለህም፡፡ደህና ዋል።”
“ቆይ! ቆይ አለ ነፍናፋው ድምፅ በጭንቀት ተወጥሮ፡፡ቆይ
ስልኩን እንዳትዘጋው። ”
ማስታወሻዬን ልይ… ቆይ አንዴ. እ…ኤ… አዎ ...ይኸው..”

ናትናኤል ስልኩን በጆርውና በትከሻው መሃል ይዞ ሰውየው የነገረውን የስልክ ቁጥር በወረቀት ላይ ይጽፍ ጀመር፡፡ ድንገት ላይ ከሜክሲኮ አደባባይ አቅጣጫ ኣንድ ነጭ ፎርድ መኪና በከፍተኛ ፍጥነት መጥታ ከቢጫዋ ቁርስ ቤት በር ላይ ቆመች:: ወዲያው ከውስጥ የነበሩ ሁለት ሰዎች በሮቻቸውን እየከፈቱ፡ ወረዱ። ሁለቱም የመኪናዋን በሮች
ለመቆለፍ አንኳን ሳይሞክሩ. እየተጣደፉ ወደ ቁርስ ቤቷ አመሩ። ጥቋቁር ኮትና ሱሪ ለብስው የኮታቸውን ቁልፎች ቆልፈዋቸዋል። ናትናኤል ፈሊጡ ገባው:: ቶሎ ዘዴ መቀየስ እንዳለበት ተረዳ፡፡

“ጥሩ፡፡” አለ ድምፁን ሳይቀይር ረጋ ባለ መንፈስ፡፡ “ስዩም ያለሁት ናዝሬት ነው:: ነገ ከጠዋቱ ልክ በአራት ሰዓት ናዝሬት ከቴሌመኒኬሽን ሕንፃ ፊት ለፊት 'ግሪር ሆቴል' የሚል ቤት አለ እዛ እጠብቅሃለሁ:: ነጭ ኮትና ጥቁር መነጸር አደርጋለሁ፡፡ ፒፓ አጨሳለሁ፡፡ ኣደራ ያወራነውን በምሥጢር ያዘው ናትናኤል ስልኩን ዘግቶ እራቅ ብሎ ይጠባበቅ ጀመር፡፡

ወንዲያው ከቢጫዋ ቁርስ ቤት የላይቤርያው ኤምባሲ ሾፌር ሁለቱን
ስዎች አስከትሎ ብቅ አለ፡፡ ሦስቱ" ተከታትለው ወደ መኪናዋ ገቡ፡፡
መኪናዋ ግን አልተንቀሳቀሰችም፡፡ ከኋላ የተቀመጠው የላይቤርያው ኤምባሲ
ሾፌር እጆቹን እያወናጨፈ ሲያወራ ሁለቱ ሰዎች ፊታቸውን ወደኋላ መልሰው ሲያዳምጡት ቆዩ፡፡

ከጥቂት ደቂቃዎች ሰኋላ ስዩም ከመኪናዋ ዕርዶ ለብቻው መንገዱን ተሻግሮ ወደ መሥሪያ ቤቱ አቅጣጫ ሲያመራ ነጯ ፎርድ ተጠምዝዛ ሽቅብ በሜክስኮ አደባባይ አቅጣጫ ተፈተለከች፡፡
ፈገግ አለ ናትናኤል፡፡ “ነገ ናዝሬት እንገናኝ” አለ ከራሱ ጋር፡፡ ወዲያው ኪሱ ከቷት የነበረችውን ወረቀት አወጥቶ አነበባት፡፡ ካዛንቺስ የምሥራች ይልማ
የፈለገውን ይኸን ነበር፡፡ስሟንና የስልክ ቁጥሯን፡፡የፈለገውን ሁሉ አግኝቷል።

የላይቤርያው ሾፌር ያለጥርጥር ለበላይ አለቆቹ አስታውቋል፤ ለአብርሃም አለቆች:: ቢሆንም ለጊዜው አትኩሮታቸው ናዝሬት ከተማ ውስጥ ስለሚሆን እዛው ነው የሚሄዱት፡፡ የአውሬውም ጆሮ በአካባቢው ካለ የእውሬውም አይን ናዝሬት ላይ ነው የሚያፈጥ:: ሁሉም ናዝሬት ነው የሚንጋጉት፡፡ አሁን ነው ጊዜው:: አሁን ነው መነቃነቅ ያለባት፡፡

ሃሎ። “ የህዝብ ስልኩ ውስጥ ሳንቲም ጨምሮ ደወለ፡፡
ሃ..ሎው” ሙልቅቅ ያለ የሴት ድምፅ ጆሮው ውስጥ ዥረር አለበት፡፡

“እ... የምሥራች ይልማ ሆቴል ነው. እባኮት…”
“አዎ ነው፡፡ ማንን ላቅርብሎት?” ሙልቅቅቅ አለችበት፡፡

“እንደምንዋልሽ የኔ እመቤት፡፡ እ...ከባህር ዳር ነበር የመጣሁት፡፡
ባልንጀራዬ መስተንግዷችሁን አድንቆ እናንተጋ እንዳርፍ የስልክ ቁጥራችሁን
ሰጥቶኝ ነበር፡፡ እ... ለባለቤቲቱም ደብዳቤ ይዤ ነበር፡፡ ግን ቤታችሁን
ላገኘው አልቻልኩም፡፡ ባክሽ..
“እይውሎት…. " አቋረጠችው:: “ሞቢል ነዳጅ ማደያው አለ አይደል ካዛንቺስ?” የልጅቷ ድምፅ ሲወርድ እንደ ተልባ ነው፡፡
“ያውቁታል...? በቃ በሱጋ ቀጥታ ሲሄዱ እንደዚህ በስተቀኝ ወደ ላይ ወደግራ የሚታጠፍ መንገድ አለ.. አ..ዎ! እሱን ትተው በስተቀኝ ትንሽ እንደሄዱ በትልቁ
'የምሥራች ሆቴል' የሚል ማስታወቂያ አለ፡፡ አጥሩ ሮዝ ቀለም የተቀባ..”
እቅጣጫውን ከነምልክቱ ጥርት አድርጋ ነገረችው::

ናትናኤል ወዲያውነ ታክሲ ተሳፍሮ ወደ ካዛንቺስ በረረ፡፡ እዚያ ሲደርስ ምን እንደሚያደርግ ግን ለራሱም ግልፅ አልሆነለትም:: በሁለት ታክሲ አሳብሮ የምሥራች ሆቴልን ደጃፍ አለፍ እንዳለ የታክሲውን ሂሣብ ከፍሎ ወረደና ጋቢውን ትከሻው ላይ ቆልሎ ዘውዲቱ የገባችለትን አዲሱን ምርኩዙን እያስቀደመ እሱ እየተክተለ መንገድ ባሻገር ያለውን ሆቴል
እያጠና አለፈ፡፡ እራቅ ብሎ ከሄደ በኋላ ከአንድ የአውቶቡስ ፌርማታ ከለላ
አድርጎ ተቀምጦ
👍2
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

...“ናትናኤል የቆርቆሮውን የአጥር በር ገፋ አድርጎ ሲገባ ያጋጠመው ሰፊ ግቢ ነበር፡፡ በግራና በቀኝ አያሌ መኪኖች ተደርድረዋል፡፡ የሆቴሉ ህንፃ ውስጥ ገብተው መስተናገድ ያልፈለጉ ደንበኞች ያማራቸውን እዚያው ከየመኪናዎቻቸው ውስጥ አዘው ይጋበዛሉ፡፡ ፍጥነቱን ሳይቀንስ ወደፊት በሆቴሉ ዋና በር እቅጣጫ ገሰገሰ፡፡

ግቢው በጨለማ ቢዋጥም ከፊት ለፊት የሆቴሉ አዳራሽ ብርሃን እውጭ በረንዳው ላይ የምሽቱን እየር እየተነፊሱ የሚጋበዙ እንግዶችን ያሳያል፡፡

በዋናው በር መግባት አደገኛ ነው፡፡ ያለጥርጥር እሱን የሚጠብቅ ድንገት የሚወነጨፍ ወጥመድ ሊኖር ይችላል፡፡

ወደቀኝ እጥፍ ብሎ በሆቴል ቤቱ በስተቀኝ ወደጓሮ ዞረ፡፡

ጭስ፡፡ እዚያና እዚህ ተፍ ተፍ የሚሉ የወጥ ቤት ሴቶች፡፡ማናቸውም ቀና ብለው አላዩትም:: በጨለማው ውስጥ ዘና ብሎ ከኋለኛው በር ደጃፍ ወጣ ብላ ወደቆመች ሴት ጠጋ አለ፡፡

“ታዲያስ!” አላት እንደቤተኛ ተዝናንቶ::
“አለን!” አለች በጨለማው ውስጥ ፊቱን ለማየት እየሞከረች፡፡
“የምሥራችን ምን ነካት ዛሬ?” አለ ጎንበስ ብሎ የእግር ሹራብን ሳብ ሳብ እያደረገ ፊቱን እንዳታየው:: ጨለማው ፊቱን እንደሚከልልለት ቢረዳም መንፈሱ አልረጋጋልህ አለው፡፡

“እንዴት ምን ሆኑ?” አለች ሴትየዋ የእመቤቷ ስም ሲነሳ፡፡
“አላየኋትም፡፡” አለ ፊቱን ወደ ማዕድ ማዘጋጃው ቤት መልሶ፡፡
“ኧረ አሉ፡፡ ከዋናወ ቤት ናቸው ኮ፡፡”
“ከዋናው አዳራሽ?” አለ ለጥቂት ሴኮንዶች ፊቱን መለስ አድርጎ
አይቷት ወዲያው ዞር ብሎ እየተንጠራራ፡፡ ሴትየዋ የምታወቀው ሰው የዘነጋችው ደንበኛ ይሆናል ብላ እንድትጠራጠር አለቅጥ እየተዝናናባት፡፡
“ዋናው አዳራሽማ ገብቼ ነበር፡፡ የለችም፡፡ ክፍል ጨርሳችኋል እንዴ?” አላት
አከታትሎ፡፡

“አልጨረስንም፡፡ ልያዝሎት? ” አለችው::
“አዎ፡፡” ከኪሱ ገንዘብ አውጥቶ ሰጣት፡፡
ሴትየዋ ወደ ውስጥ ስትገባ እያፏጨ እየተንጎራደደ ጠበቃት፡፡
ከወዲያ ወዲሀ የሚሯሯጠትን ብቅ ጥልቅ እያሉ እንግዶቻቸውን የሚያስተናግዱትን ሴቶች እየተመለከተ ቆየ::
“አዛሉ! ሁለት ጥብስ አንድ ክትፎ ሶስት ፍርፍር ቶሎ በይ!” አለች አንድ ሴት ከጀርባው ካለ መስኮት ብቅ ብላ፡፡ “ዓለም! ዓለምነሽ! ለሦስት ቁጥር ሰዎች አምቦ ውሃ ወሰጂላቸው እንጂ!” ወደ ውስጥ የገባችው ሴት መልሳ በዛው መስኮት ብቅ ብላ ተጣራች፡፡

“መጣሁ መጣሁ! እዚህም'ኮ ስራ ነው:: ጭቅጭቅ?” ዓለምነሽ እያልጎመጎመች ከማዕድ ቤቱ ወጥታ የአምቦ ውሃ ጨብጣ ወደ ዋናው ቤት ሮጠች፡፡

“ይኽው ሰባት ቁጥርን ያዝኩሎት፡፡” አለችው ቁልፉንና መልስ ገንዘብ የያዘችበትን እጇን ወደፊት ዘርግታ፡፡
ቁልፉን ብቻ ተቀብሎ “ተይው” አላት መልሱን ልትሰጠው ስትከጅል፡፡
“እግዜር ይስጥልኝ፡፡" አለች በጨለማው ውስጥ ፈገግታ ደርባ፡፡
“ምስር ከአዲስ ደንበኞች ጋር ነች መሰለኝ? እኛን ረሳችንሳ፡፡” አለ
የተከራየውን ክፍል ቁልፍ፡ ሌባ ጣቱ ላይ እያሽከረከረ፡፡
“አይ..ከነጋሼ ኪዳኔ ጋር ናቸው...ጓዳ፡፡”
“ኪዳኔ የኛ?” አላት በጭፍን፡፡
“አዎ፡፡” አለችው:: ቤተኛ ነው ብላ እንደደመደመች ግልጽ ሆነለት::
“አይ እነሱስ .. ከሆነ ችግር የለም፡፡ አንድ ሰው ይፈልግሻል በያት፡ክፍሌ ውስጥ ነኝ፡፡” ለመመለስ ጊዜ ሳይሰጣት ፊቱን መልሶ መደዳ ወደተሰሩት የመኝታ ቤቶች አመራ…4..5.6..7 ቁልፉን ከቶ በሩን ከፈተና ወደ ውስጥ ገባ፡፡ በሩን ከዘጋው በኋላ መብራቱን አበራው፡፡

የክፍሉን አብዛኛ ቦታ የያዘው ቀይ ጨርቅ የለበሰ አንድ ሰፊ አልጋ በሁለት ኮመዲኖዎችና ቁምሳጥን ታጅቦ መሃል ላይ ተንጋሏል፡፡ አነስተኛ የፊት መታጠቢያ ሳህን ከነፊት መስታወቱ በስተቀኝ ይታያል፡፡ ከክፍሉ ጀርባ ከአልጋው ራስጌ አንድ የተዘጋ የእንጨት መስኮት አላ:: ናትናኤል ክፍሉን ካጠና በኋላ ወደፊት ራመድ እልና በኮርኒሱ መሃል
የተንጠለጠለችውን አምፖል አላላት፡፡ ጨለማ፡፡

አልጋው ላይ ተቀምጦ መጠባበቅ ያዝ፡፡ ልቡ እየተነሳ ሲፈርጥ ደረቱን ሲነርተው እራሱን ኣሳፈረው፡፡ለሳምንታት አንድ በአንድ ሲያስኬደው የቆየው ዕቅድ ቀላል ሆኖ እንዳልታየው ሁሉ ሰዓቱ ሲደርስ በላብ ይዘፈቅ ጀመር፡፡ …ምንድነው የሚላት? ካልቨርት ያላትን ነው መድገም ያለበት፡፡የካልቨርት ቢጤ ምስኪን ተባራሪ ነው መሆን ያለበት፡፡ ያኔ ነው ካልቨርትን
ባየችበት አይኗ ልታየው የምትችለው፡፡ ባታምነውስ? ብትጮኽስ? ኡ! ኡ!
ብትልስ? ወይ አባብላ የተስማማች መስላ ብታስያዘውስ?. አንዱ ክፍሉ
ውስጥ ከገባች በኋሳ መውጣት የለባትም፡፡ መጀመሪያ መውጣት ያለበት እሱ ነው፡፡ ግን ብትጮህ ምን ያደርጋታል? አፏን አፍኖ ይዞ ማስፈራራት?
አጥፍቷል፡፡ ጩቤ ቢይዝ ጥሩ ነበር፡፡ ቀደም ብሎ ያላሰበው ያልጠረጠረው
ሁኔታ ሲከሰትላት ደንገጥ አለ፡፡ ለጥቂት ደቂቃዎች አሰላሰለና ድንገት አፈፍ
ብሎ ተነስቶ በሩን ከፍቶ ወደ ማዕድ ቤት ሮጥ ብሎ ሄደ፡፡

“እዛሉ! ዓለምነሽ! ማናችሁ... ምነው ዛሬ ችላ አላችሁን?” ጭንቅላቱን በማዕድ ቤቱ ጠባብ መስኮት ገባ እድርጎ ታጣራ፡፡ ከውስጥ የክፍሉ ብርሃን ሴቶቹን ቁልጭ አድርጎ ቢያሳየውም ከውጭ የቆመው
የእርሱ ፊት ግን በጨለማው ውስጥ እንደተዋጠ ነበር፡፡

“አቤት...ምንድነው?” አለች ኣዛለች ትሁን ዓለምነሽ ያልለያት ሴት በግራዋ መጥበሻ በቀኟ ሳህን እንደያዘች ፊቷን ወደ እርሱ መልሳ፡፡

“ስንቴ ነው የምንልክባችሁ? ቢላ ቢላ! ቢላ! በይ አሁን አንድ ስጪኝ!” አለ እጁን ዘርግቶ እያራገበ::

ዞር ብላ ከጠረጴዛው ላይ የተቀመጠ የገበታ ቢላ አንስታ አቀበለችው ቢላውን ከተቀበላት በኋላ ፊቱን መልሶ እየተጣደፈ ወደ ተከራየው ክፍል ሲመለስ ከጀርባው ድምጽ ተሰማው፡፡ የክፍሉን በር ከፍቶ እንደያዘ ዞር ብሎ ተመለከተ፡፡

“ማን ነው? ብለዋል እትዬ…ማን ልበላቸው ስሞትን?” አለች የላካት
ልጅ ስሙን ባለማስታወሷ እያፈረች፡፡
“ይሻላል? ህ ህ! ሀ! ሀ!” ልጅቷ ላይ አንቧረቀባት፡፡ “ብላ ብላ ደግሞ ማነው ትለኝ ጀመር? እንደምትያት መታወቂያ ወረቀቴን ብልክ አይሻልም ወይ? ብሏል በያት” ጊዜ ሳይሰጣት ወደ ክፍሉ ገባ፡፡ “ማነሽ…ደሞ
ሻማና ክብሪት ይሽልኝ ተመለሽ፡ አምፖላችሁ ተቃጥሏል፡፡ እንደው ነው'ኮ
እዚህ የምንመጣ፡፡ የናንተ አስተናጋጅነት ድሮ ቀረ::” በሩን ዘጋው፡፡

አለቅጥ መዝናናቱ ልጅቷን ግራ እንደማያጋባትና እመቤቷ በቅርብ
የሚያውቁት ሰው ነው ብላ እንድታስብ እንደሚያደርጋት ገብቶታል፡፡ ክፍሉ
ውስጥ ከገባ በኋላ ቢላ የጨበጠ ቀኝ እጁን ኪሱ ውስጥ ከትቶ አልጋው ላይ
ተቀመጠና ጨሰማው ላይ ኣፈጠጠ፡፡
ቢላውን የጨበጠበት እጁ በላብ ሲጠመቅ አውጥቶ ሱሪው ላይ
ሞዥቀው፡፡ መፍራት የለበትም ቀፍፁም! አሳዳጆቹ ፍርሀት የሚገባቸው ፤
ርህራሄ የሚውጣቸው አይደሉም። አንገቱን አርደው ቱቦ ውስጥ ሊጥሉት
የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ፍርሀት አይበጀውም:: ፍርሀት አያዋጣውም፡፡

ምንድነው የሚላት? ሊያስፈራራት አይገባም፡፡ እሰም እንደ ካልቨርት ተባራሪ መሆኑን ነው ሊያሳምናት የሚገባው፡፡ ያን ጊዜ ነው የምታምነው! ካልቨርትን ባየችበት እይኗ የምታየው:: እንቢ ካለች ግን በራሷ ቢላዋ ያባብላታል፡፡

ያለበት ክፍል በር ወደ ውስጥ ተከፈተ፡፡
“እንዴ! ምነው ጨለማ ውስጥ ?!” ለሴት ጎርነን ያለ ድምፅ፡፡

“አምፖልሽ ተቃጥሏል ምስርዬ፡፡ ሻማ በያት ልጅቷን፡፡” አለ ናትናኤል በጭለማ ውስጥ እንደተቀመጠ ተዝናንቶ፡፡ ልቡ ትቼህ ልብረር ልብረር አለው፡፡

“ማነህ?” አለ ያው ጎርነን ያለ የሴት ድምፅ ጥርጣሬ የገባው በሚመስል ቃና

“እስቲ ሻማው ይምጣና
👍1