አትሮኖስ
282K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
494 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

....ታክሲው ውስጥ የሚጮኸው ሙዚቃ ጭንቅላቱን በጠበጠው፡፡ማታ እንቅልፍ አልወስድህ ብሎት ሲጨነቅ ነበር ያደረው::

“ምንድነው የሆንከው? ለምን አትነግረኝም?” አለች ዘውዲቱ
ከሆቴል ገዝታ ካመጣችው ምግብ እያጎረሰችው፡፡ “ምስኪን አሁንስ ሚስትህ
ናፈቀችሁ መሰለኝ::

ያጎረሰችውን እያላመጠ ዝም አላት:: ወሬ አላሰኘውም:: ምግቡም እንዳያስከፋት ብሎ ነው እንጅ ቢቀርበት በወደደ፡፡
እራት በልተው ተጣጥበው መብራቱን አጥፍተው አልጋ ላይ ከወጡ በኋላ ናትናኤል በጀርባው እንደተንጋለለ አያኖቹን ጣሪያው ላይ ተክሎ ቀረ፡፡

ምን ሆና ይሆን? እንዴት ሁለት ቀን ሙሉ ስራ ሳትገባ ትቀራለች በጤናዋ ባትሆን ነው እንጅ:: ደግሞ ምህረት እቤቷ: ደወዬ
የሚያነሳ አጣሁ ማለቷ ምን ማለቷ ነው? ቤቷን ዘግታ የት ትሄዳለች? ምናልባት አሟት ወላጆቿጋ ሄዳ ይሆን እንዴ? የወላጆቿን ቤት ደግሞ አያውቀውም ! ጉለሌ እንደሆኑ ነግራዋለች፡፡ ግን በደፈናው ጉለሌ ተብሎ አይኬድ፡፡ ቤቷ ሄዶ ይሞክር ይሆን?

ሌሊቱን ሲጨነቅ አደረ፡፡ አሁን ደግሞ ታክሲው ውስጥ ያለው ሙዚቃ አይሉት ጩኽት

“ሲጋራ ፋብሪካ ነው ያሉኝ?” አለው ባለታክሲው፡፡

“እ? አዎ የኔ ልጅ፡፡ ከዚህ ይበቃኛል፡፡” ናትናኤል የታክሲውን በር ከፍቶ ወረደ፡፡

“አባ ገንዘበስ?!” ባለታክሲው የመኪናውን ጥሩንባ ተጭኖ ጮኹ፡፡

“ይቅርታ! ይቅርታ!” አለ ናትናኤል ከሄደበት ተመልሶ ከጋቢው ስር
ከደረት ኪሱ ገንብ እያወጣ “ይቅርታ የኔ ልጅ፡፡ ሃሳብ ገብቶኝ ተዘንግቶኝ
ነው::” ገንዘቡን ለባለታክሲው አቀበለው

ዘውዲቱ የገዛችላት ላስቲክ ቦት ጫማ መንገደኛ ቢያስመስለውም እላይ ከፈፉ እግሩን ከርክሮት ክፉኛ አቁስሎታል። በተራመደ ቁጥር የጫማው ክፈፍ ቁስሉን ሲነካበትና ሲፈትግበት ይለበልበዋል፡፡
ከመንገዱ ባሻገር የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ህንፃ ብቻውን ተገትሯል ... ሥራ ፈት፡፡ ናትናኤል ይህንን ፎቅ ሲመለከት ምንም ትርጉም አይሰጠውም በፎቁ ቅርፅ ውስጥ መልዕክት ካለ አንድ የሚል መሆን አለበት ቀጥ ያለ ፎቅ እንድ፡፡

ናትናኤል አይኖቹን ከፎቁ ላይ ነቅሎ ሃሳቡን አሰባሰሰ፡፡ ለጥያቄው መፍትሄ የሚያገኝለት ካልቨርትን ቢያገኝ ብቻ እንደሆነ ከተረዳ ቆይቷል፡፡
ካልቨርትን : እግኝቶ የአውሬውን ማንነት ይፋ እስካላወጣ ድረስ የተደበቀውንና የተሸሸገውን ምሥጢር እስካላዝረከረከው ድረስ አንድ ቀን ከአንዱ ጥግ ነው የሚደፉት፡፡አብርሃምን እንደደፉት፡፡

ይህ ከመሆኑ በፊት ካልቨርትን ማግኘት አለበት፡፡ ግን ካልቨርትን ለማግኘት ከየት ሀ ብሎ እንደሚጀምር እንቆቅልሽ ሆነበት::

መረጃ የውስኪ ጠርሙስ ሾፌር ቤላ
መጠጥ ቤት…ሴት ሞሳድ ኤም አይ
ስድስት…ካዛንቺስ ወዳጁ ቤት… የሴት ልብስ ለብሶ ተሰወረ::

ቁልፉ የግድ እዚህ ውስጥ መሆን አለበት መፍትሄው እዚህ ውስጥ ከሌለ ካልቨርትን ሊያገኘው አይችልም:: ምክንያቱም እሱ የሚያውቀው ይህን ብቻ ነው አብርሃም የነገረውን፡፡

ያለጥርጥር ካልቨርት እንዲሰወር የካዛንቺሷ ወዳጁ ረድታዋለች፡፡ በመጨረሻ የታየው ከእሷ ቤት ሲወጣ ነው፡፡ ምናልባት የት እንደሚገኝም
ታውቅ ይሆናል፡፡ በተቻለው መንገድ ሴትየዋን ማግኘት አለበት:: ካልቨርትን
ለረዳው እንደሚፈልግ ሊያሳምናት ይገባል፡፡ ትጠረጥረው ይሆናል፡፡ ግን
ሊያሳምናት ከቻለና ካልቨርት ያለበትን ቦታ ከነገረችው ድብብቆሹ አበቃ ማለት ነው፡፡ ያን ጊዜ ያለጥርጥር አውሬውን መረቡ ውስጥ ይከተዋል፡፡

ካልቨርት የሚያውቀው ነገር እንደሌለስ? ማወቅ አለበት ምንም የማያውቅ ከሆነ ለምን ተሸሽገ? ያውቃል፡፡ ለሕይወቱ የሚያሰጋው ምሥጢር ይዟል፡፡ ያንን ምስጢር ማግኘት አለበት፡፡ ካልቨርትን ለማግኘት ደግሞ መጀመሪያ የካዛንቺሷን ሴት አግኝቶ ማሳመን፤ ማግባባት ማሽነፍ፡፡፡ እሷ ብቻ ነች ዕድሉ፡፡

ግን አውሬው ለምን ሴትየዋን አቆያት? ያለጥርጥር ወደ ካልቨርት
የምትመሪ መንገድ ነች:: ይህንን ደግሞ አውሬው ሳያውቀው የሚቀር አያደለም:: ታዲያ ለምን አሰነበታት? ለምን አስገድዶም በሆን የካልቨርትን
እድራሻ አላወጣጣትም? ወያም ለማንኛውም ወገን ምሥጢሩን የካልቨርትን አድራሻ እንዳትጠቁም ለምን እንደ አብርሃም አሳስወገዳትም?

ምናልባት ሴትየዋ ራሷ ወጥመድ እንደሆነችስ? የካልቨርትን አድራሻ የሚያነፈንፍ፡ አይጥ ወደ ካዛንቺስ እንዲመጣና ከወጥመድ እንዲገባ
የተንጠለጠለች የሥጋ ቁራጭ እንደሆነችስ? ካዛንቺስ ከመድረሱ እንገቱን ቆርጠው ቢጥሉትስ?'፡ ናትናኤል ሰጋ:ዠ ኣብርሃም ያለው ትዝ አለው

“… ሁለቱን የክትትል ሰዎች ባሰማራን በሶስተኛው ቀን አንደኛው ሰዋችን በስለት ታርዶ እዛው ካዛንቺስ ቱቦ ውስጥ ተጥሎ ተገኘ.…”

ህ! “እዛው ካዛንቺስ” ወጥመድ

ያለጥርጥር ካዛንቺስ ወጥመድ ተጠምዶለታል፡፡ ቢሆንም ምርጫ
የለውም፡፡ ወደ ካልቨርት ሊቀርብ የሚችለው የካዛንቺሏን ሴት ሲያገኝ ብቻ
ነው:: የግድ ካዛንቺስ መሄድ አለበት፡፡
'ካዛንቺስ፡፡ ካዛንቺስ ምኑጋ? ካዛንቺስ ስንት አውራ መንገዶች አሉ?… ካዛንቺስ ስንት መጠጥ ቤቶች አሉ? የትኛዋ ነች የካልቨርት ወዳጅ? “የፈጣሪ ያለህ!' የካዛንቺስ ስፋቱና የቀሚስ ለባሹ ብዛት ታየው::

ሌላ ጥያቄ! እንዴት ሊያገኛት ይችላል? ማን ሊመራው ይችላል? አብርሃም ምንድነው ያለው.…?
የቅብብሎሹን ሠንሠለት መስበር ነው
ካልቨርት የሰረቀውን መረጃ…በውስኪ ጠርሙሶች…በሾፌርነት ለማያገለግል ኢትዮጵያዊ ያቀብላል..ሹፌሩ ቤላ መጠጥ ቤት ላላት.…”

ሹፌሩ ሹፌሩ ሌላ መጠጥ ቤት ያላትን ሴት ያውቃታል ማለት ነው፡፡ የካዛንቺሷንስ? ሊያውቃት ይችላል? ምናልባት ካልቨርት የሚቀርበው ከሆነ ሊያውቃት ያችላል፡፡ ያለው ምርጫ ሾፌሩ ነው:: ሾፌሩን አአግኝቶ የካዛንቺሷን ሴት እድራሻ እንዲሰጠው መጠየቅ::

ሾፌሩ የኛ ሰወ ነው በእሱ በኩል ነው
መረጃውን የምናገኘው...” ነበር ያለው
አብርሃም::
ሌላ ወጥመድ፡፡ ሾፌሩም አደገኛ ነው፡፡ ካዛንቺስ ያለችውን የካልቨርትን ወዳጅ ሆቴል ኣሳየኝ።” ሲለው መቼም መጠራጠሩ አይቀርም፡፡
“እሺ ና” ብሎ ገመድ አንገቱ ቢያስገባለትስ? መሬት ለመሬት እያንሻተተና እየጎተተ ቢያስይዘውስ? እርግጥ ያለው ምርጫ ወደ ካዛንቺሷ እመቤት የሚደርሰው ብቸኛ መንገድ የላይቤርያው ኤምባሲ ሾፌር ብቻ ነው:: ለይቶ የሚያውቀው አድራሻ የእርሱን ብቻ ነዋ! ቢሆንም ሰውየውን በአካል
መገናኘት የለበትም፡፡አንድ ዘዴ መፍጠር አለበት፡፡ ናትናኤል ለበርካታ ቀናቶች ሲያወጣ ሲያወርድ መልስ ሲሻለት የቆየው ጥያቄ ይህ ነበር፡፡መልሱን
አግኝቷል። አቅዶ ወጥኖ ጨርሷል፡፡ ትከሻው ላይ አላርፍልህ ያለውን ጋቢ
እያስተካከለ ከመንገድ ወዳለ ትንሽ ቁርስ ቤት ገባ፡፡

“የኔ ልጅ እባክሽ ስልክ ታስደውይኝ…እከፍላለሁ::ችግር አጋጥሞኝ ነው ልጅ ታማብኝ፡፡” አላቸው እናቱ የሚሆኑትን የቁርስ ቤቷን ባለቤት ጠጋ ብሎ። ያቀደውን ደረጃ በደረጃ ይፈጽም ጀመር፡፡

ሴትየዋ ስልክ ማስደወሉን ባይወዱትም ከቄስ ጋር! ከእግዚኣብሄር ሰው ጋር ክፉ መነጋገሩን አልፈለጉትም፡፡ ከባልኮኒው ስር አንድ ሰማያዊ ስልክ አውጥተው ቄሱ ፊት ቆለሉትና “ያው” ብለው ፊታቸውን አዙረው ሄዱ፡፡ · ደረታቸው ላይ የተቆለለው የጡት ተራራ የዘውዲቱን ጋራ
ያስንቃል፡፡

ናትናኤል ሴትየዋ ዞር እንዳሉለት የስልኩን መነጋገሪያ አንስቶ በመጀመሪያ ወደ ማዞሪያ ደውሎ የላይቤርያ ኤምባሲን የስልክ ቁጥር ከጠየቀና ካገኘ በኋላ ወደ ኤምባሲው ደወለ። በላይቤርያው ኤምባሲ ውስጥ ከአንድ በላይ ሾፌር ሊኖር ይችላል የትኛውን አቅርቡልኝ ሊል ነው? ብቻ ማናቸውም ቢሆኑ የካልቨርት
👍32🥰1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

......ብዙም ሳይቆይ አንድ ቀጭን አጭር ሰው መንገዱን ተሻግሮ ወደ ቢጫዋ ቁርስ ቤት ሲጣደፍ ተመለከተ፡፡ኮቱን ትከሻው ላይ እንጠልጥሎታል፡፡ ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት ካለው የላይቤርያ ኤምባሲ እስከ ቁርስ ቤቷ ለመድረስ ብዙ ባያስኬድም ወደፊት ደፋ
ደፋ የሚለው ሰው ረዥም መንገድ የተጓዘ ይመስላል፡፡ ሰውየው ከቁርስ ቤቷ እንደደረስ ወደውስጥ ከመግባቱ በፊት ቆም ብሎ ዙሪያውን ተገላምጦ
ተመለከተ፡፡ ወዲያው ዘው ብሎ ወደ ውስጥ ገባ፡፡

ሰውየው ወደ ውስጥ ሲገባ ናትናኤል ፈጠን ብሎ ከጥግ ወዳለ
የህዝብ ስልክ አመራና አንብቦ በጭንቅላቱ የያዘውን የቢጫዋን ቁርስ ቤት ቁጥር ደወለ፡፡

“አ.ቤት::” አለ የሴት ወይዘሮ ድምፅ፡፡
ያ ክምር ጡታቸው መጥቶ ፊቱ ላይ ድቅን አለበት ናትናኤል፡፡

“እንደምን ዋሉ...ደህና ኖት?” ሴትየዋ መልስ ከመስጠታቸው በፊት አጣደፋቸው “ገብረየሱስ ነኝ..እንደምን ኖት?!” አለ እንደሚያውቃቸው ተዝናንቶ፡፡ “እባኮት ስዩም ጋር ቀጠሮ ነበረን እርሶ ቤት
ያገናኙኝ…ስዩም ይበሉልኝ…እቤትዎ ውስጥ ነው ያለው…ደህና ኖት ግን
እርስዎ..በሉ ስዩምን ያገናኙኝ..” በላይ ቀላይ አጣደፋቸው፡፡

“የማን ስዩምን? አሉ ሴትየዋ ፋታ ሲያገኙ፡፡

“እንዴ!.. ረሱን እንዴ? እቤትዎ በልተን ጠጥተን? አይ የርሶ ነገር! ይብሉ ስዩም ይበሉልኝ፡፡ አይ የርሶ ነገር! ደንበኞቾንም ይረሱ ጀመር?” አጣደፋቸው፡፡

“ኧረ ንሽቴ! የምን መርሳት አመጣህብኝ::!” አሉ ሴትየዋ ድፍረት
አሰባስበው:: “ደሞ እናንተን ደንበኞቼን ልርሳ? ሄ! ሄ! ሄ! ገና ሳላረጅ ምነው
ባክህ! ደህና ነህ ግን አንተ ጠፋህሳ?”
ሴትየዋ ሲጣሩ “ስዩም የሚባል! ስልክ?” ሲሉ በስልኩ ውስጥ ተሰማው፡፡ ነፍሱ መለስ አለችለት:: ስልኩን ጆሮው ላይ እንዳይጠራቅምበት ሰግቶ ነበር፡፡

“ሀሎ… ” አለው ያው ነፍናፋ ድምፅ፡፡
“ስዩም? ” ናትናኤል ቆፍጠን ባለ ድምፅ ጠየቀ፡፡
“ነኝ.የት…?”

“ዝም ብለህ አዳምጠኝ::ቁርስ ቤቷ ውስጥ ይጠብቀኛል ብለህ አስበህ
ከሆነ ሞኝ ነህ፡፡ መልዕክቱን ብቻ እሰጥሀለሁ፡፡ ትስማማለህ?” አለ ናትናኤል ጥድፊያ በተቀላቀለው ድምፅ፡፡

“አዎ አዎ፡: ቀጥል፡፡”

“ጥሩ…. እንዳልኩህ ካልቨርት ለአንተ የማደርስለትን መልዕክትና፡ በርከት ያለ ገንዘብ ሰጥቶኛል፡፡ መልእክቱን ከመስጠቴ በፊት ግን አንተነትህን ማረጋገጥ አለብኝ፡፡”

“ነኝ..ነኝ ግድ የለም:: ስዩም ነኝ፡፡”

“ዝም ብለህ አዳምጠኝ! ለምጠይቅህ ጥያቄ ብቻ ኣጫጭር መልስ ነው የምፈልገው፡፡” አለ ናትናኤል ሰውየውን ይበልጥ ለማደናገር ቱግ ብሎ:: “ካልቨርት በየትኛው ጣቱ ላይ ነው ቀለበት የሚያደርገው?” ያዘጋጃትን ማስመሰያ ጥያቄ አስቀደሙ:: በአውራጣቱ፡ ላያ ቢለውም ግድ አልነበ
ረውም፡፡ ነገር ግን ወደ ዋናዎቹ ጥያቄዎች ከመግባቱ በፊት የሰውየውን
ጭንቅላት ማሟሸት አለበት፡፡
“ቀለበት አያደርግም ካልቨርት::” አለ ሰውየው በሚያስደንቅ ፍጥነት::

“ጥሩ፡፡ አሁንም ፈጣን መልስ እፈልጋለሁ:: ተጠንቀቅ ብትሳሳት
ወይ ብትጠራጠር፡፡ ብትዘገይ ስልኩን ዘግቼ ነው የምሄደው:: የምፈልገው
ትክክለኛውን ስዩም ነው:: የያዝኩትን በርካታ ገንዘብ ላልሆነ ሰው ማስታቀፍ፣
አልፈልግም:: አድምጥ:: የካዛንቺሷ ሴት ስም ማነው?” ናትናኤል በጭንቀት
ትንፋሹን ያዘ፡፡

“የምሥራች ይልማ!” አለ ሰውየው ሌላ ሰው እንዳይቀድመው የፈራ ይመስል በጥድፊያ፡፡
“የስልክ ቁጥሯስ?” አከታትሉ ጠየቀው፡፡
“ትዝ አይለኝም::?”
“እንግዳው ስዩም አያደለህም፡፡ደህና ዋል።”
“ቆይ! ቆይ አለ ነፍናፋው ድምፅ በጭንቀት ተወጥሮ፡፡ቆይ
ስልኩን እንዳትዘጋው። ”
ማስታወሻዬን ልይ… ቆይ አንዴ. እ…ኤ… አዎ ...ይኸው..”

ናትናኤል ስልኩን በጆርውና በትከሻው መሃል ይዞ ሰውየው የነገረውን የስልክ ቁጥር በወረቀት ላይ ይጽፍ ጀመር፡፡ ድንገት ላይ ከሜክሲኮ አደባባይ አቅጣጫ ኣንድ ነጭ ፎርድ መኪና በከፍተኛ ፍጥነት መጥታ ከቢጫዋ ቁርስ ቤት በር ላይ ቆመች:: ወዲያው ከውስጥ የነበሩ ሁለት ሰዎች በሮቻቸውን እየከፈቱ፡ ወረዱ። ሁለቱም የመኪናዋን በሮች
ለመቆለፍ አንኳን ሳይሞክሩ. እየተጣደፉ ወደ ቁርስ ቤቷ አመሩ። ጥቋቁር ኮትና ሱሪ ለብስው የኮታቸውን ቁልፎች ቆልፈዋቸዋል። ናትናኤል ፈሊጡ ገባው:: ቶሎ ዘዴ መቀየስ እንዳለበት ተረዳ፡፡

“ጥሩ፡፡” አለ ድምፁን ሳይቀይር ረጋ ባለ መንፈስ፡፡ “ስዩም ያለሁት ናዝሬት ነው:: ነገ ከጠዋቱ ልክ በአራት ሰዓት ናዝሬት ከቴሌመኒኬሽን ሕንፃ ፊት ለፊት 'ግሪር ሆቴል' የሚል ቤት አለ እዛ እጠብቅሃለሁ:: ነጭ ኮትና ጥቁር መነጸር አደርጋለሁ፡፡ ፒፓ አጨሳለሁ፡፡ ኣደራ ያወራነውን በምሥጢር ያዘው ናትናኤል ስልኩን ዘግቶ እራቅ ብሎ ይጠባበቅ ጀመር፡፡

ወንዲያው ከቢጫዋ ቁርስ ቤት የላይቤርያው ኤምባሲ ሾፌር ሁለቱን
ስዎች አስከትሎ ብቅ አለ፡፡ ሦስቱ" ተከታትለው ወደ መኪናዋ ገቡ፡፡
መኪናዋ ግን አልተንቀሳቀሰችም፡፡ ከኋላ የተቀመጠው የላይቤርያው ኤምባሲ
ሾፌር እጆቹን እያወናጨፈ ሲያወራ ሁለቱ ሰዎች ፊታቸውን ወደኋላ መልሰው ሲያዳምጡት ቆዩ፡፡

ከጥቂት ደቂቃዎች ሰኋላ ስዩም ከመኪናዋ ዕርዶ ለብቻው መንገዱን ተሻግሮ ወደ መሥሪያ ቤቱ አቅጣጫ ሲያመራ ነጯ ፎርድ ተጠምዝዛ ሽቅብ በሜክስኮ አደባባይ አቅጣጫ ተፈተለከች፡፡
ፈገግ አለ ናትናኤል፡፡ “ነገ ናዝሬት እንገናኝ” አለ ከራሱ ጋር፡፡ ወዲያው ኪሱ ከቷት የነበረችውን ወረቀት አወጥቶ አነበባት፡፡ ካዛንቺስ የምሥራች ይልማ
የፈለገውን ይኸን ነበር፡፡ስሟንና የስልክ ቁጥሯን፡፡የፈለገውን ሁሉ አግኝቷል።

የላይቤርያው ሾፌር ያለጥርጥር ለበላይ አለቆቹ አስታውቋል፤ ለአብርሃም አለቆች:: ቢሆንም ለጊዜው አትኩሮታቸው ናዝሬት ከተማ ውስጥ ስለሚሆን እዛው ነው የሚሄዱት፡፡ የአውሬውም ጆሮ በአካባቢው ካለ የእውሬውም አይን ናዝሬት ላይ ነው የሚያፈጥ:: ሁሉም ናዝሬት ነው የሚንጋጉት፡፡ አሁን ነው ጊዜው:: አሁን ነው መነቃነቅ ያለባት፡፡

ሃሎ። “ የህዝብ ስልኩ ውስጥ ሳንቲም ጨምሮ ደወለ፡፡
ሃ..ሎው” ሙልቅቅ ያለ የሴት ድምፅ ጆሮው ውስጥ ዥረር አለበት፡፡

“እ... የምሥራች ይልማ ሆቴል ነው. እባኮት…”
“አዎ ነው፡፡ ማንን ላቅርብሎት?” ሙልቅቅቅ አለችበት፡፡

“እንደምንዋልሽ የኔ እመቤት፡፡ እ...ከባህር ዳር ነበር የመጣሁት፡፡
ባልንጀራዬ መስተንግዷችሁን አድንቆ እናንተጋ እንዳርፍ የስልክ ቁጥራችሁን
ሰጥቶኝ ነበር፡፡ እ... ለባለቤቲቱም ደብዳቤ ይዤ ነበር፡፡ ግን ቤታችሁን
ላገኘው አልቻልኩም፡፡ ባክሽ..
“እይውሎት…. " አቋረጠችው:: “ሞቢል ነዳጅ ማደያው አለ አይደል ካዛንቺስ?” የልጅቷ ድምፅ ሲወርድ እንደ ተልባ ነው፡፡
“ያውቁታል...? በቃ በሱጋ ቀጥታ ሲሄዱ እንደዚህ በስተቀኝ ወደ ላይ ወደግራ የሚታጠፍ መንገድ አለ.. አ..ዎ! እሱን ትተው በስተቀኝ ትንሽ እንደሄዱ በትልቁ
'የምሥራች ሆቴል' የሚል ማስታወቂያ አለ፡፡ አጥሩ ሮዝ ቀለም የተቀባ..”
እቅጣጫውን ከነምልክቱ ጥርት አድርጋ ነገረችው::

ናትናኤል ወዲያውነ ታክሲ ተሳፍሮ ወደ ካዛንቺስ በረረ፡፡ እዚያ ሲደርስ ምን እንደሚያደርግ ግን ለራሱም ግልፅ አልሆነለትም:: በሁለት ታክሲ አሳብሮ የምሥራች ሆቴልን ደጃፍ አለፍ እንዳለ የታክሲውን ሂሣብ ከፍሎ ወረደና ጋቢውን ትከሻው ላይ ቆልሎ ዘውዲቱ የገባችለትን አዲሱን ምርኩዙን እያስቀደመ እሱ እየተክተለ መንገድ ባሻገር ያለውን ሆቴል
እያጠና አለፈ፡፡ እራቅ ብሎ ከሄደ በኋላ ከአንድ የአውቶቡስ ፌርማታ ከለላ
አድርጎ ተቀምጦ
👍2