#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ከቀኑ አሥር ሰዓት ተኩል ሆኗል፡፡ ዶክተር ባይከዳኝ በዛሬው ዕለት ከመሰል የሥራ ባልደረቦቹ ጋር ከፍተኛ የቀዶ ጥገና ሕክምና አጋጥሞት ነበር የዋለው፡፡ የቀዶ ጥገናው የተደረገላት ሴት በማኅፀን ዕጢ
በሽታ የምትሰቃይ ነበረች፡፡የሆድ ዕቃዋ ተከፍቶ ተከፈፍቶ የተገመተውና፤ በተግባር የታየው የሰማይና ምድር ያህል
ልዩነት ነቀረው።
በማህፀኗ ላይ ለአራት ሰአት የተደረገው የቀዶ ሕክምና ከሁለት ኪሎ ግራም በላይ ዕጢ እንዲወጣላት አስቻለ፡፡ ዶክተር ሰውነቱ በሥራ ደክሞ ስለዛለ በቂ ዕረፍት ለመውሰድ በጊዜ ወደ ቤቱ ገብቶ አልጋው ላይ ጋደም ለማለት ፈልጓል፡፡
ከድካሙ ቀለል እንዲለው ፤ በቀዝቃዛ ውሃ ገላውን ሙልጭ አድርጉ ከታጠበ በኋላ፤ የጥጥ ፒጃማውን እንደለበሰ ነበረ የተኛው፡፡በዚሁ መሀል ትህትና ገርበብ ያለውን የመኝታ ክፍሉን በር ከፍታ ገባች::
በዛሬው ዕለት ያለወትሮዋ የተርከፈከፈችው ሽቶ ቀድሟት ገባና
ክፍሉን በመዓዛው አወደው:: የዱር ጽጌረዳ፣ ጣፋጭ መዓዛ፤ እሷም
የጽጌረዳ አበባ መስላለች። ወትሮ ከሚያውቃት ትህትና በእጥፍ አምራ
ተውባለች፡፡ ኮቴዋን ሳታሰማ ወደሱ ትመጣለች፡፡
ቁልቁል ትመለከተዋለች፡፡ ገርበብ ባሉት ዐይኖቹ ሰረቅ አድርጎ አያት፡፡ በልቡ ውበቷን አደነቀ። ቀጭን ሳቋ ጆሮውን ሰረሰረው፡፡ ዐይኖቹን ገለጥ አድርጉ በሚያየው ነገር ተደንቆ፤ ሽቅብ ተመለከታት፡፡ እሷም በፈገግታ ተሞልታ እየተፍለቀለች ጐንበስ ብላ ጉንጬን ሳመችው፡፡
ከበላዩ ቆሞ፤ ውብ ፈገግታን የሚለግስ፤ በኋላም በአካል የሚዳስስ፤ መልአክ መስላ ታየችው፡፡
የዛሬው አመጣጧ ድንገተኛ ሆኖበታል። የተቀጣጠሩት ለዛሬ አልነበረም፡፡ እንዴት ቀድማ መጣች? ገረመው። ከቀጠሮ በፊት መምጣቷ ምናልባትም በፍቅሩ ወጥመድ እየወደቀችለት ለመሆኗ ፍንጭ ስለሰጠው የደስታ ስሜት የሠራ አካላቱን አዳረሰው፡፡
“የደብረዘይቱ የሽርሽር ውጤት እየታየ ነው” አለ በልቡ፡፡ የሚገርመው ደግሞ አንጀቱን ለመብላት ያላደረገችው ጥረት የለም፡፡ የለበሰችው ስስ ተካፋች ጃኬት እኒያ ገና ከሩቅ ሲያያቸው ውሃ
የሚሆንላቸው! ጡቶቿን፤ አጋልጦ ያሳያል። በዚህ ላይ እኒያን ውብ ባትና ጭኖቿን፣ በግልጽ የሚያሳይ አጭር ቀሚስ ነው የለበሰችው፡፡
“በቃ በፍቅር ወድቃልኛለች ማለት ነው”
በስሜት እንደሰከረ ፍዝዝ ባሉት ዐይኖቹ ይመለከታት ጀመር። ጭውው አለበት፡፡ ሽውው የሚል ነፋስ ሲነፍስ፣ የፍቅር አማልክት በያሬዳዊ የሙዚቃ ቅኝት
ስለፍቅር ሲያዜሙ ፧ ተሰማው፡፡ ድብት የሚያደርግ የድካም ስሜት..ድቅቅ
ያለ ሰውነት በደስታ የሰከረ ቀልብና ልብ፡፡
አሁንም ከት ብላ ሳቀች። አሳሳቋ እንደ ገደል ማሚቶ አስተጋባ፡፡ ሁኔታዋ ሁሉ ግርም ብሉት፤ አፉን ከፍቶ ይመለከታት ጀመር፡፡ ዐይን አፋራ፣ ቅልስልሷ ፤ ትህትና መሆኗን ተጠራጠረ፡፡ ፍቅር ያንን ሁሉ
የእፍረት ማቅ አሽቀንጥራ እንድትጥል አድርጓታል ማለት ነው? ፍቅር እውር ነው ወይስ እውር ያደርጋል? በትክክል እውር እንደሚያደርግ ከሷ እንደዚህ የውቦች ቁንጮ ሆናለት፤ ከቀጠሮአቸው በፊት ሹልክ ብላ ስትመጣለት ምን ይባላል? ማመን አልቻለም፡፡
ዐይኖቹን አሸት አሸት አድርጉ ሁለት እጆቹን ወደላይ ዘረጋና
“ትሁትዬ” አላት በደከመ ድምጽ።
ቀስ በቀስ ያ ሰውነቱ እየጋለ መሄድ ጀምሮ ነበር፡፡ በተለይ የዘረጋላት እጆቹን ወደዚያ ውርውር አድርጋ..
“ከቀጠሮ በፊት ስለመጣሁ መዘነጥህ ነው?” ብላ ከተሰቀለው መስታወት
ውስጥ ፊቷን ለማየት ዘወር ስትል፤ አጭሩ ቀሚስ እላይ ድረስ ዘልቆ እኒያ የሚያማምሩ ጭንና ባቶቿን ወለል አድርጉ ሲያሳየው አልቻለም፡፡ቀስ በቀስ እንደ ካውያ እየጋለ በመሄድ ላይ የነበረው ሰውነቱ የሚያደርገውን ያሳጣው ጀመር፡፡
በተለይ የምትሽኮረመም ሴት ይወዳል። እንዲያ ግፍትር አድርጋው ስትሽኮረመም፧ እልህ ያዘው። በዚህ ላይ ባቶቿ ኑ ብሉኝ! ኑ ብሉኝ! እያሉ ይጋብዛሉ። በዚያ ባዶ ቤት ውስጥ፤ በዚያ ሰፊ የሞዝቦልድ አልጋ ላይ እየተንከባበሉ፤ ያንን ባለፈው ጊዜ ተልፈስፍሶ ያመለጠውን ሲሳይ ዳግም እንዳያመልጠው ሊሞክር ቸኩሎ ተነሳና...
“ከቀጠሮ በፊት መምጣትሽ ምን ያህል ልቤን እንዳስደሰተው ከፍተሽ ባየሽው የኔ ቆንጆ?” በጀርባዋ በኩል ሄዶ፤ በሁለት እጆቹ እቅፍ አድርጓት፤ አንገቱን በአንገቷ ውስጥ ቀበረና! ጡቶቿን ያሻሻቸው
ጀመር..
ቀስ በቀስ እየሞቀች ስትሄድ ግለቷ ተሰማው። ከዚያም አፏ እንደተከፈተ ዘወር ስትልለት፤ በተከፈተው አፉ ቀለባት፡፡ ከዚያም እጆቹ ወገቧ ላይ ሲጠመጠሙ፤ እጆቿ ደግሞ በአንገቱ ዙሪያ እንደ ድር
ተጠንጥነው፤ ሰስሜት ተዋህደው ነጐዱ.....
እኒያ ውብ አይኖቿ ስልምልም ብለው ጠፉ፡፡ ከዚያም ቀስ ብለው እየተደነቃቀፉ፤ እየተደጋገፉ፤ ወደ አልጋው ሄዱና ወደቁ፡፡ ዛሬ ትህትና እንደዚያን ዕለቱ ዐይኖቿ በእንባ አልተሞሉም፡፡ ይልቁንም በደስታ እየተፍለቀለቀች፤ በፍቅር፤ ለፍቅር፤ ስትል ሁለመናዋን በግልጽ እየሰጠችው ነው፡፡
ዶክተር በዛሬው ዕለት ብር አምባር ለመስበር በእርግጠኝነት መንፈስ ተሞልቷል፡፡ በደብረ ዘይቱን የሽርሽር ወቅት በተለይም በሆራ ራስ መኝታ ክፍል ውስጥ ሲልፈሰፈስ ያመለጠው
እንዳያመልጠው በመስጋት፤ ኃይሉን የአንበሳ፤ አድርጎ ትግሉን ቀጠለ፡፡
የታጠቀችው የውስጥ ሱሪ ከዚህ በፊት የሚያውቀው ነጩ ባለወንፊቱ ነበር፡፡ በስሜት ደርተው ሲታገሉ፣ በፍቅር ስሜት ተውጣ የሆነ ነገር እያቃሰተች በጆሮው ሹክ አለችው፡፡ “አስገ...ው...ባ..ው..ው."
በዚህ ጊዜ ዶክተር በሲቃ ስሜት ተውጦ ካሰበበት ለመድረስ ጥድፊያውን ቀጠለ፡፡
እሷ ለሚሆነው ነገር ሙሉ ለሙሉ እራሷን ዝግጁ አድርጋ ሲመለከት፤ ደስታው እጥፍ ድርብ ሆነ፡፡ ዶክተር ላብ በላብ ሆኗል።ትህትናም በላብ ተነክራለች። ከረጅም ጊዜ ትግል በኋላ ...
“ዋ!!.......ይ!! !” ብላ ጮኸችና የዶክተር ባይከዳኝን ሰውነት በጥፍሮቿ ግጥም አድርጋ ይዛ አለቀሰች፡፡ ዶክተር ስለተቧጠጠ ገላው ደንታም ሳይሰጠው በድል አድራጊነት እርካታ ተውጦ ግዳዩን ለማየት ተጣደፈ፡፡
በእርግጥም ድል አድርጓል፡፡ በዚያው ስሜቱ እስከሚረካ ድረስ ቆየ። ከዚያም ተዘርራ ተመለከታት፡፡ ይህ ውስጥ ለውስጥ ያደርገው የነበረው ስሜታዊ ትግል፤ ቀስ በቀስ በውስጡ ሲሯሯጥ ከቆየ በኋላ፤ አንድ ደረጃ ላይ ሲደርስ፤ ወደ ገሀዳዊው ዓለም ተለወጠ፡፡
በዚህ ለውጥ ሰዓት ከእግር ጥፍሩ፤ እስከራስ ጠጉሩ ድረስ የነዘረው ንዝረት አባነነውና፤ በላብ እንደተዘፈቀ ከገባበት የቅዠት ዓለም ወጣ! እግዜኦ! ዶክተር በዚያን ሰዓት የተሰማውን የስሜት ስብራት በቃላት ማስቀመጥ ይከብዳል።
ያ ሁሉ ዓለም፣ ያ ሁሉ ደስታ፤ እንዲህ እንደዋዛ እንደጉም በንኖ ጠፋና፤ የሱን ስሜት እንዳይሽር አድርጎ አቁስሎት በፀፀት ጉድቶት አለፈ፡፡ ያ ሁሉ የድል አድራጊነት ስሜት በቅጽበት ቦታውን ለሽንፈት ለቀቀና፤ በዶክተር ባይከዳኝ ልብ ውስጥ ሀዘን ጥቁር ደመናውን አጥልቶበት ሄደ...
“ቡል ሺት! ” አለና ትራሱን በቡጢ ጠልዞ የሆነውን ነገር እንደ አዲስ አስተዋለ፡፡ በቅዝቃዜው ስሜት ተጠራጥሮ ሲዳብስ፤ ፒጃማውን ረጥቦ አገኘው፡፡ ከዚህ በኋላ ሁኔታዎችን ቀስ ብሎ ይመረምር ጀመር።
በቀላሉ የሚልፈሰፈሰው አካሉ አሳድሮበት የነበረው ሥነ ልቡናዊ ተጽዕኖ
ለጥቂት ጊዜ እራሱ በፈጠረው ትንሽ የቅዠት ደሴት ውስጥ ጠፍቶ፤ነበር
ጊዜያዊ የተስፋ ጮራ በልቡ ውስጥ እንደፈነጥቅበት፤ እሱም ጓደኞቹ
ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ ለማድረግ እንደሚችል፤ አረጋግጦለት ነበር።.....
ድንግልናን መግሰስ በማይችል አካላዊ ብቃቱ ለዘመናት አዝኖ እንዳልኖረ ሁሉ፤ በዚህች ቅጽበት፤

❤2👍2🔥1
#ቆንጆዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አራት
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
..... “የኔ ልጅ” አሉ ቀረብ ብለው ቆመው የነበሩ ነጭ “ጥምጥም የጠመጠሙ ቄስ፡፡ “እዚህ ላይ የሚጣፈውን ትጥፊልኝ… አላወቅበት ብዬ
እንዳላዟዙረው ሰጋሁ::” የያዙትን የታሸገ ፖስታ ወደ ልጅቷ ፊት አስጠጉት፡፡ ሲናገሩ ድምጻቸው ይንቀጠቀጣል፡፡ ወረቀቱን ሲያቀበሏት ምርኩዛቸው አምልጧቸው ወደቁ፡፡
“ምንድነው የፈለጉት?” እለች ልጅቷ ቄሱ ሲደነጋገሩባት ግራ ተጋብታ፡፡
“የኔ ልጅ ይህን ቦስጣ ልልከው ፈልጌ ነበር፡፡ ታዲያ ከይህና ከይህ የሚጣፈውን እንዳላበላሽ አሉ ቄሱ ያሽጉትን ፖስታ እያገላበጠ፡፡ “እምን ከምን እንደሚሰፍር አላውቅት ብዬ ትጥፈልኝ፡፡” ለሳምንታት
የሸመደዱትን ተረተሩላት።
“የሚልኩለትን ሰው አድራሻ ያውቁታል?” አለች ልጅቷ ፖስታውን ልትቀበል እጁን እየዘረጋች::
“እንዴታ ቄስ ገብረክርስቶስ ጋ”
“አይደለም… አይደለም… ማለቴ ሙሉ አድራሻውን” አለች ልጅቷ ፈገግ ብላ፡፡
“እነግርሻለሁ፡፡ ብቻ እንቺ ከሥፍራ ከስፍራው ጣፊልኝ::”
ልጅቷ ወረቀቱን ከተቀበለቻቸው በኋላ ወረቀቱ ላይ አቀርቅራ የሚነግራትን ለመፃፍ ትጠባበቅ ጀመር።
“ቄስ ገበዝ ገብረክርስቶስ በይማ::”
ልጅቷ በፖስታ ከረጢቱ ጀርባ ላይ ቄሱ ያሏትን ማስፈር ጀመረች፡፡ ቄሱ ጠጋ ብለው ከጠረጴዛው ላይ ተደራርበው የተቀመጡትን የመታወቂያ ወረቀቶች ሰብሰብ ስብራብ አደረጓቸው፡፡
“እንዲያ ደብረሊባኖስ ገዳም በይ አዎ..ደብረ…” ቄሱ ከጠረጴዛው ላይ የሰበሰቧቸውን አራት መታወቂያች አጋብሰወ ከጋቢያቸው ስር ከኪሳቸው ውስጥ ጨመሯቸው። “ሸዋ... በይበት... እንዲያ ተባረኪ!” አሉ ድምጻቸው እየተንቀጠቀጠ፡፡
“የእርሶስ አድራሻ? ” አለች ልጅ:: ቀና ብላ እየተመለከተቻቸው፡፡እኔማ ምን አድራሻ አለኝ? መንገደኛም አደለሁ?” አሏት ቄሱ
ፖስታቸውን ተቀብለው ለመሄድ እየተጣደፉ፡፡
“ቢሆንም ስሞትን እንኳን ልጻፈው፡፡”
“ልክ! ልክ! ቄስ ዘነበ ዘነበ ወልደሰማያት በይልኝ፡፡ አንዲያ ዘነበ፡፡” አሉ ድንገት የተቻኮሉት ቄስ፡፡
የፈለጉትን አድራሻ በታሸገው ፖስታ ላይ ጽፋ እንደጨረሰች ቄስ መርቀዋት ፈጠን ብለው ከፖስታ ቤቱ አዳራሽ ወጡ፡፡ ገልመጥ አላሉም፡፡መንገዱን ተሻግረው ታክሲ ውስጥ ገብተው ወደ ክፍለሃገር አውቶብስ መሳፈሪያ ሲያምሩ ነበር ምርኩዛቸውን ረስተው መምጣታቸው
የታወሳቸው፡፡ ክው አሉ፡፡ ለመመለስ ግን አልደፈሩም::
ናትናኤል የገጠር አውቶቡስ መሳፈሪያ ደርሶ እንደወረደ ወደ ተከራየው ወደ ዘውዲቱ ቤት አልሄደም፡፡ ወደ አንድ ሱቅ ገባና ስልክ ጠይቆ ርብቃ መሥሪያ ቤት ደወለ፡፡
ሃሎ ምህረት?”
“ናትናኤል!” አለች ምህረት ገና ድምፁን ስትለየው፡፡
“እንደምንድነሽ ምህረት ደህና ነሽ?”
“አንተ! ምን እንዲህ አጠፋህ? በጤናህ ነው?”
“አለሁ እለሁ፡፡ ምህረት እባክሽ ርብቃን ትጠሪልኝ…”
“የለችም፡፡ ለመሆኑ አዲስ አበባ ነው ያለኸው?”
“ስራ ኣልገባችም?” አለ ጥያቄዋን ችላ ብሎ፡፡
አዎ ከትላንት ጀምራ አልገባችም፡፡ ቤቷ ደውዬ ነበር የሚያነሳ የለም:: ደጋግሜ ሞክሬ ነበር፡፡”
ናትናኤል ምህረትን ተሰናብቶ ስልኩን ዘግቶ ወደ ዘውዲቱ ቤት መንገድ ጀመረ፡፡ ሃሳብ ገባው፡፡ አሟት ይሆን? እንዴት ሁለት ቀን በተከታታይ ከሥራ ትቀራለች.… በጤና ብትሆን? ቤቷ ሊደውል አሰበና ፈራ ስልኳ ተጠልፎ እንደሆንስ ድጋሚ አደጋ ላይ ሊጥላት አይገባም:: ቆያይቶ ሰሞኑን እዚያው ምህረት ቢሮ ደውሎ ቢያነጋግራት ይሻላል፡፡
ናትናኤል ዘውዲቱ ቤት ሲደርስ በሩ እንደተቆለፈ ነበር፡፡ ዘውዲቱ የለችም ማለት ነው፡፡ የሰጠችውን ተለዋጭ ቁልፍ አውጥቶ በሩን ከፍቶ ገባና ከውስጥ ቆለፈው:: ወዲያ ጋቢውን ወርውሮ ጥምጥሙን አውልቆ ጥሎ ከኪሱ ውስጥ ከፖስታ ቤት የሰረቃቸውን አራት የመታወቂያ ወረቀቶች አወጣና ተራ በተራ እየከፈተ አነበባቸው፡፡
ሻለቃ ብርሃኑ ገብረማርያም አቶ ጀማል አብዱልከሪም ዶክተር አለሙ ገዛኸኝ ሲስተር ሠናይት አሽኔ፡፡ ሀሳብ ገባው የትኛውን ሊያቀስ እንደሚችል ግራ ገባው::
ምርጫ አልነበረውም፡፡ዶክተር አለሙ ገዛኸኝ የሚለውን መታወቂያ ነጥሎ አንስቶ በጥንቃቄ ፎቶግራፉን ነቀለና ቀን ከተነሳቸው ፎቶግራፎች መሃል አንዱን ተካበት፡፡ ወዲያው ቶሎ ብሎ ከመሬት አንስቶት ወደ ቤት ገባና ጭቃውን በጨርቅ ያፀዳ ጀመር፡፡ የመታወቂያ ወረቀቱን በጥንቃቄ ጠራረገው፧ አፀዳው፡፡እንደ በፊቱ ንፁህ ባይሆንም..መቼስ.….አለሙ ገዛኸኝ የሚለው ይነበባል፡፡ያንን ነበር የሚፈልገው:: 'ዶክተር የሚለው አስፈላጊ አልነበረም፡፡ ለተቀሩት መታወቂያዎች ደግሞ ሰኑን ሌሎች ፎቶግራፎች ይነሳላቸዋል፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በሩ..የመኝታ ቤቷ በር ወደ ውስጥ ሲገፋ ጠረጴዛውን ደገፉ እንዳለች ቀረች፡፡በሩ ተከፍቶ የሰው ቅርጽ ታያት፡፡ ሰውየው ወደ ውስጥ ገብቶ በሩን ዘጋው፡፡ ከጀርባው ባለው መስኮት የሚገባው ስስ የጨረቃ
ብርሃን ቀጠን ረዘም ካለው ሰውነቱ ላይ ሲያርፍ ሰው ሳይሆን ህይወት ያለው ጥላ መሰላት፡፡ ግራ ጉንጩን ከላይ እስከታች የገመሰው ኣስጠሊታ ጠባሳ የአካሉ አንድ ክፍል እንዳልሆነ ሁሉ በጨረቃዋ ብርሃን ውስጥ ጎልቶ ታያት፡፡ አተኩራ ትናንሽ አይኖቹን ተመለከተቻቸው፡፡ ሰውነቷ ይንቀጠቀጥ ጀመር፡፡ ሆዷ ውስጥ ያለው ሽል የተላወሰ መሰላት ሊያስመልሳት እንደፈለገ ሁሉ አንጀቷ ሲመናተቀል ለራሱ ነፍስ የዘራ ይመስል ሲቋጠር ሲፈታ.. ሳይታወቃት ወደፊት ዘላ ጉብ አለችበት፡፡
“ገደላችሁት! ገደላችሁት አይደል?
አታለላችሁኝ!” አውቃ አስባ ሳይሆን ከውስጥ የሚነዳትና የሚጋልባት ዛር እንዳለ ሁሉ ዘላ ፀጉሩን ጨመደደችው፡፡ ፊቱን በጥፍሮቿ ገባችበት::
“ርብቃ!” ጥፍሮቿን አሹላ አይኖቹን ልትጓጉጠው ስታሻቅብ ባለ በሌለ ሃይሉ እራሱን እየተከላከለ ጮኸ፡፡ “ርብቃ! አልገደልነውም! ማንም አልደረሰበትም... እሱን ለመግደልም አላሰብንም... ርብቃ አዳምጪኝ!” ሁለት እጆቿን ወደኋላ ጠምዝዞ ደረቷን ደረቱ ላይ ለጥፎ አገጯን በቀኝ እጁ ግጥም አድርጎ ይዞ ጮኸባት፡፡
“ውሽታም! ውሸታም! አታላችሁኛል፤ ገድላችሁታል.…ቱፍ” ፊቱን በምራቅ አለበሰችው::
“አልሞተም አለ፡፡ ስላመለጠን ነው ወደ አንቺ የመጣነው:: ርብቃ ረጋ በይ!”
ለአንድ አፍታ ረጋ ያለች መሰሰች፡፡ቀና እንዳለች ቁና ቁና እየተነፈሰች አፈጠጠችበት:: ድንገት ፡ እጆቿን መንጭቃ ከእቅፉ ወጣች፡፡ ከፊቱ ተጋርጦ አይኖቿን አጉረጠረጠችበት፡፡
“ልትገድሉት ነበር የጠራችሁት፥ ጓደኛውን እንደገደላችሁት እሱንም ልትገድሉት ነበር፡፡ አትዋሽ! አሁን ደግሞ ወር ሙሉ እናገኘዋለን ታገሽ ስትለኝ ቆይተህ አመለጠን ትለኛለህ! ”
“ርብቃ እመኝኝ፡፡ እሱን የመግደል ሃሳብ አልነበረንም፡፡ አስፈላጊም አልነበረም:: ምንም አያውቅም፡፡ በድንግዝግዝ ጨረቃ ብቻውን እንደሚሮጥ እብድ ነው::” አለ ሰውየው ከኪሱ ወስጥ መሃረብ አውጥቶ ፊቱ ላይ የትዝረበረበውን ምራቅ እየጠረገ፡፡
“ጓደኛውን አልገደላችሁትም? አትዋሽ!”
“ገድለነዋል፡፡ አስፈላጊም ነበር መሞቱ:: ምሥጢሩን ከሞላ ጎደል ደርሶበታል፡፡ በማንኛውም ሰዓት ሊያወጣው ይችል ነበር፡፡ ኣደገኛ ሰው ነበር፡፡
“እሱን የገደላችሁት ሌሊት ናትናኤልን ጠርታችሁታል:: ልትገድሉት ነበር፡፡ አትዋሽ!” ከሥሯ ያለውን ወለል በእግሯ ደቃችው፡፡
“ርብቃ እመኝኝ፡፡ የዛን ቀን ጓደኛው አደገኛ የሆነ እርምጃ ወሰደ፡፡ገደልነው:: ምንም ምርጫ አልነበረም... እርግጥ በጥድፊያ ውስጥ ነበርን የዛን ማታ ሁለቱም እንዲገደሉ ነበር የተላለፈው ትዕዛዝ፡፡ እንደ አጋጣሚ ያንቺ ሰውዬ አመለጠ.. ትራፊክ ፖሊስ

👍2