#ህመም_ያዘለ_ፍቅር
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_አምስት
፡
፡
#በክፍለማርያም
..ፍቃዱ የሚወጣዉን ሰዉ ተመለከተዉ
ፍፁም የጀመረዉን አጋምሶ ፍቃዱ እስካሁን ስለጠፋሁበት ተመልሶ ይሆናል በማለት ለጥቂት ደቂቃ ስለተቀመጠ እግሩን እያስነከሰዉ በክራንቹ እየተመረኮዘ ሰበር ሰካ እያለ ሲወጣ
ፍቃዱ ከቅድሙ ሰዉዬ ጋር ቆሞ እያወራ ፊት ለፊት ተፋጠጡ።
ቤዛዊት በሽታዋ እያገረሸ እየተብከነከነች ብቻዋን እያወራች ወደ ፍፁም ቤት አምርታ አለመኖሩ ስታረጋግጥ አከራዩ ጋር ሄዳ
"የት ነዉ የሄደዉ?"
ለእሳቸዉ የማይጠየቅ ጥያቄ አይኖቿን እያጉረጠረጠች ጠየቀቻቸዉ
"እኔ ምን አዉቃለዉ የሚሄድበትን ነግሮኝ አይሄድ"
ሲሉ አኩዋሀኗ ያላማራቸዉ የፍፁም አከራይ መለሱላት
"እሺ እኔን የምትመስል ቁመት ብቻ የምትበልጠኝ ሴት መጥታ ነበር"
አጉረጠረጠችባቸዉ
የፍፁም ቤት አከራይ በልባቸዉ ምኗ ለካፊ ናት እያሉ
"የኔ እመቤት ማንም የመጣ ሰዉ አላየሁም አቶ ፍፁም ግን ብቻዉን ጠዋት ሲወጣ ተገናኝተን ነበር"
ይህን ሲሏት ትንሽ ተረጋጋች ከእህቴ ጋር ነዉ ስትል የነበረዉን ትታ እየከነፈች ወደ እማማ ስንቅነሽ ቤት አመራች።
ወደ እማማ ስንቅነሽ ቤት ደርሳ ከመግባቷ በፊት ለአፍታ ፍፁምን አሰበችዉ
"የት ሄዶ ይሆን ምን ገጠመዉ"
አይምሮዋ ግን አልተረጋጋም በቆመችበት ቦታ አንፑላንስ ድምፁን እያሰማ በአጠገቧ ሲያልፍ ጩሀቱ ስለቀፈፋት በእጆቿ ጆሮወቿን ደፍና ለደቂቃ ቆመች
መኪናዉ አልፎ ጩሀቱ እየቀነሰ ሲመጣ ተስፋ በመቁረጥ ስሜት አስፓልቱ ዳር ዝርፍጥ ብላ ተቀምጣ በአይኖቿ የፍፁምን መምጣት ትጠባበቃለች።
እማማ ስንቅነሽ የቤዛዊት መጣሁ ብላ መጥፋት አሳስቧቸዉ ወደ ዉጪ ወጣ ሲሉ መንገድ ዳር ተቀምጣ አይኖቿ ሲንከራተቱ ስላዩዋት ደረታቸዉን እየደቁ እየደገፉ ወደ ቤት ለማስገባት የቤዛዊትን ሰዉነት መጎተት ጀመሩ።
"አይመጣም ቀረ..."
እያለቻቸዉ እየተሳበች እየተጎተተች ተነስታ የእማማ ስንቅነሽን ቀሚስ ጨምድዳ ይዛ እየቆመች
በታመመ አይምሮዋ የቅድሙን ቃል ደገመችላቸዉ
"አይመጣም ቀረ..."
እማማ ስንቅነሽም በዝምታ ወደ ቤት እንድትገባላቸዉ እየጎተቷት
ቅድም ያለፈዉ አንፑላንስ ተመልሶ እየጮሀ አለፈ በአሁኑ ግን ጆሮወቿን አልያዘችም በድንገት ግትር ብላ ቆማ
"ያ ዉ ያዉና መጣ"
የቀኝ እጇን የመጠቆምያ ጣት ወደ ታች ወደሚወርዱ ብዛት ያላቸዉ ሰወች ቀስራ
ፍፁም እያነከሰ በሁለት ፖሊሶች ተከቦ ከጀርባቸዉ ወሬ አድማቂ ሰዉ አጅቦት አንገቱን ደፍቶ እየተራመደ ነዉ መሬት መሬቱን እያየ ሸንከል ሸግከል እያለ ይራመዳል ፖሊሶቹ እንዲፈጥን ኮሌታዉን ይዘዉ ይጎትቱታል
ፍፁምን ካጀቡት ሰወች መሀከል
"ገድሎታል አረ አልሞተም"
እየተባባሉ ይከራከራሉ
ቤዛዊት እማማ ስንቅነሽ እጅ ላይ አይኖቿ ፍዝዝ ብለዉ በድን ሆና ቆማለች መናገር አቁማለች የምትሰማም አትመስልም የአይኖቿ ብሌኖች ብቻ በቀስታ ይንከዋለላሉ።
(ከደቂቃወች በፊት)
ፍፁም ፊት ለፊቱ የቆመዉን ፍቃዱን ሲያየዉ እያዘነ አይቶ እንዳላየዉ መስሎ ሊያልፈዉ ሲል ፍቃዱ ከጀርባዉ ደርሶበት
"የት ለመድረስ ነዉ የምታነክሰዉ"
ይለዋል በንቀት እግር እግሩን እያየ
ፍፁም መልስ ሳይሰጠዉ መራመዱን ሲቀጥል ፍቃዱ ደግሞ ደርሶበት እየሳቀ
"ቤዛዊትን መቼም አታገኛትም የኔ ናት አንተ ዉሻ እያዋራሁክ ደሞ የምን ንቀት ነዉ ጥለሀኝ የምትሄደዉ..."
ፍፁም መታገስ አልቻለም ክራንቹን ወደ ሰማይ አንስቶ ፍቃዱ ላይ ሳያቋርጥ ማሳረፍ ጀመረ።
ሳያስበዉ በእልህ ፍቃዱን ክፉኛ ስለመታዉ መቆም ያቃተዉ ፍቃዱ ተዝለፍልፎ ወደቀ።
💫ይቀጥላል💫
ምዕራፍ #1 በዚህ ተጠናቋል ምዕራፍ #2 በቅርቡ እንጀምራለን እስከዛው በሌሎች ጣፋጭ ድርሰቶች እንቀጥላለን እስካሁን በሄደው ድርሰት ላይ ያሎትን አስተያየት አድርሱን
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏

👍3
#ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ
...“ እንዲያው ምን ምን ይላት ይሆን?እኔ እሱ ለሴት ልጅ የሚያወራውን ነገር ለመስማት እጓጓለሁ " ግን አንተ ባል
ከው ዐይነት አገጣጥሞኝ አያውቅም ። ”
“አጅሬ ምኑ ሞኝ ነው ላንተ የሚታየው ?!እሷን ሲያገኛት ቦታው ጭር የሚልበትን ጊዜ ጠብቆ ነው ።
“ ወይ ጉድ ! መቼም ፍቅር የማያሸንፈው ልብ የለም ”አለ እስክንድር በልቡ ። ስለ ድብርት የበለጠ ለማወቅ ጓጉቶ ነበር ። ሆኖም ጨዋታው በተዘዋዋሪም ቢሆን አንዳንድ የአቤልን ድርጊቶች እንደሚንካ ስለ ገመተ አርዕስቱን ለመለወጥ ፈለገ ሳምሶንም ይህንን ሁሉ ልብ ሳይል እንደ መጣለት ነበር የሚጫወተው ። እስክንድር ግን የአቤል ስሜት
እየተለዋወጠ እንደ መጣ በሥርቆት ከገጽታው ላይ አንብቦአል ድብርት የሴት ጓደኛውን ለማግኘት ጭር ያለ ጊዜ
መጠበቁ የአቤልን ስሜት ክፉኛ ነክቶታል እሱም ትዕግሥትን ለማየት የሚጠቀምባቸውን ጊዜያቶች ያውቃል ።
ስማኝ ላምሶን ! ግን ለምንድነው አንተ ብዙ ጊዜ ድብርትን የምትለክፈው ? ” በማለት እስክንድር አርዕስቱን አሸጋገረው
“ ለተንኮል አይደለም ። ግን የሚነፋነፍ ሰው መልከፍ እንዲሁ ደስ ይለኛል ። እንዴት ብዬ ላስረዳህ ? ለምሳሌ
ቀርቦ መናከስ የማይደፍር ውሻ በሩቁ እያፈገፈገ ሲጮህብህ እልሁን ለማስጨራረስ በዱላ እንደምትተናኮለው ዐይነት ነው ። ብቻ እንዲሁ ስለክፈው ደስ ይለኛል እንጂ ለድብርት መጥፎ አመለካከት የለኝም ለየት ያለ ተፈጥሮ ስላለው ያስገርመኛል ” አለና አሳላፊዋን ለመጥራት ጠረጴዛውን ጠበጠበ።
“ አቤት ! ምን ልታዘዝ? ” እያለች አንገቷ በንቅሳት የተዥጎረጎረ ሴት ከፊታቸው መጥታ ቆመች ።
“ ቢራ ድገሚን ሦስት ቢራ ! ” አላት ሳምሶን በዚያው ቁጡ ድምፁ
“ እኔ ይብቃኝ ! ” አለ አቤል "
“ አትቀልድ እባክህ ። አንቺ እኔ የማዝሽን አምጪ!” አለና ሳምሶን አሳላፊዋ ላይ ጮኸባት ።
"ጥርስሽን እንዳያወልቅ ” አለና እስክንድር በልቡ ሳቀ ።
“ እኔኮ ያንተም ተፈጥሮ ያስገርመኛል ” አለው እስክንድር ሳምሶንን
“ እንዴት ?”
“ አሁን ሚስተር ሆርስ ከአቤል ጋር ከታረቀ በኋላ ለምን ትዝትበታለህ ?”
“ አዎ ! የማታውቀው ነገር አለ እስክንድር እየዛትክ የምትተው ከሆነ ዛቻው ሲደጋገም ሰው ይንቅሃል ።ወንድ ከሆንክ አንዴ ማቅመስ አለብህ ። እንዲያውም አንተን ብዬ ነው እንጂ እሱን ልጅ አንድቀን ብሰብረው ደስይለኛል ። ከፈለገ የገዛ ጥርሱን ከመሬት አሰለቅመዋለሁ ።
“ጡንቻህን ፈትነኝ እያለ ያስቸግሃል መሰለኝ” አለና እስክንድር እየሣቀ ከእሱ መልስ ሳይጠብቅ ፡ “ ብቻ ያለንበትንም ጊዜ አትዘንጋ : ሀያኛው ክፍለ ዘመን ላይ ነን ” አለው ።
“ እና ? ” የብሽቀት ድምፅ ነበር ።
“ እናማ ስፖርተኝነትህን እወድልሃለሁ ። ይህችን በጡንቻ መመካትህን ግን ...
“ እንግዲህ አትልከፈኝ ፡ ልጠጣበት ! ” አለና ቢራውን ተጎነጨ
ሳምሶን ሌላ ሰው እንዲህ ቢናገረውም ካልተደባደበ በዋዛ እይላቀቁም ነበር ። ለእስክንድር ያለው ክብር ግን ብዙ ዓመት ከቆየ የልጅነት የአስተሳሰብ ተጽዕኖ የመጣ ነው ። የሠፈር ልጆች እንደ መሆናቸው መጠን ሳምሶን ስለ እስክንድር ብዙ ነገር ያውቃል ። እሱ ገና ልጅነቱን ሳይጨርስ እስክንድር በሠፈራቸው ውስጥ ስመ ጥር ጎረምሳ
ነበር ። እንዲህ እንዳሁኑ ከመስከኑ በፊት እናቱ በእስክንድር ያላዩት አበሳ የለም ። ከለውጡ በፊት ጸብ አሽትቶ ነበር
የሚፈልገው ። እስር ቤትን ቤቱ አድርጎት ነበር ። አንዴ ጸበኞቹ በቡድን ሆነው ከደበደቡት በኋላ ሆዱ ላይ በጩቤ
ወግተውት ለጥቂት ነው ከምት የተረፈው ከለውጡ በኋላ ደግሞ በወቅቱ በተፈጠሩት የፖለቲካ ድርጅቶች ሳቢያ
ያልቀመሰው፡ አበሳ የለም ። ችኩል ነበር ። ሰው አይገራውም ፣ ያየሁት አይለፈኝ የሚል ስሜት ያሸንፈዋል ።
የጀብደኝነት ስሜት ያጠቃዋል ። ትኩስ ኃያልነቱ፡ መንፈሱን ያቅበጠብጠዋል ። አሁን ግን በዕድሜም በብስለትም ሰክኖ
እንኳን ለራሰ ሌሎችንም ይመክራል ። ከአፍላነት ቅብጥብጥነት ጊዜው ይዞ የመጣውና አሁንም ያልተወው ነገር ቢኖር
የሲጋራ ሱስ ብቻ ነው። ይህ ሁሉ ሁኔታ በሳምሶን ላይ የሚኖረው ተጽእኖ ቀላል አይደለም። በፀጉሩ ኪንኪነት እየለከፈው ከእስክንድር ጋር መቃለድ የጀመረው እንኳ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው።
አቤል እባክህ ተጫወት ይሄንን ተወው
አለ ሳምሶን እስክንድርን በመንቀፍ አይነት
“ እየሰማኋችሁ “ኮ ነው ? ” አለ አቤል በጨዋታቸው ውስጥ የቆየ ለመምሰል ጥርሱን በውሸት ብልጭ አደረገ።
ሐሳቡ በከፌል ወደ እነ ትእግስት ዘምቶ ነበረ። ፈተና ከጨረሰች በኋሳ ወዴት ትሔድ ይሆን ? አርፎ መተኛት ወይስ
ዙረት መውጣት ? እያለ ሲያሰላስል ነው የቆየው።ሁለተኛውን ጠርሙስ ቢራ ግማሽ አድርሶታል ። ከቻቻታው ጋር
ቢራው ሞቅ አድርጎት ውስጥ ውስጡን እየሰከረ መምጣቱ ይሰማው ነበር። የመጠጣት ልምድ ስለሌለው ጭንቅላቱ ቶሎ መረታት ጀምሯል ። ድፍረትም ተሰማው ማንንም ያለመፍራት ሃይነት ስሜት !
“ ለምን ሙዚቃውን አይቀይሩልንም ? ” ሲል ድምፁን አሰማ ። የእንግሊዝኛ ሙዚቃ ነበር አዳራሹን የሚነቀንቀው፤“ ማስቀየር እንችላለን ። የማን ክር ይደረግ ? ” አሉ እስክንድርና ሳምሶን በአንድ ድምፅ አቤል ከዝምታ ወደ
ተሳትፎ መምጣቱ ደስ አሰኝቶአቸው ነበር
•የ... የመልካሙ ተበጀ ክር ቢሆን
ይሻላል” አለ አቤል በተሰባበረ ድምፅ
እስክንድርም ሆነ ሳምሶን በፍጥነት የጠረጠሩት ነገር አልነበረም ። አሳላፊዋን ጠርተው ክሩ እንዲቀየር አዘዟዋት።
ባለቤትየዋ እሷ የመረጠችው ዘፈን ካልሆን እሺ አትልም ግን ልሞክርላችሁ ” አለች አሳላፊዋ ።
“ ንገሪያት ! ለምን እሺ አትልም ? ” አለና ሳምሶን አፈጠጠበት እሷ ዘፈኑን ልታዝዝ ስትሔድ አቤል ቀድሞ በልቡ
ያንጐራጉር ጀመር።
አረ መላ ምቱ ወዳጅ ዘመዶቼ
ዐይናፋር ሆኛለሁ ፡ ዐይናፋር አይቼ
ሰሳምታ አልሰጠኋት አላነጋገርኳት
በዐይን ብቻ እያየሁ አንድ ዓመት ወደድኳት።
ልቡ ይህን እያዜመ፥ ጆሮው የሚሰማው ግን ሌላ ሙዚቃ ነበር ቢጠብቅ ፥ ቢጠብቅ የተለወጠ ነገር የለም ጥቂት
ቆይታ አሳላፊዋ ተመልሳ መጣች።
የመልካሙ ክር የለም ብላለች ባለቤትየዋ ! ”
አቤል በሽቆ “ ገደል ግቢ በያት ! ” ከማለቱ ዐይኑ እንባ አቀረረ ። የሰው ስሜት የማይጠበቅበት ዓለም ! ባለቡና ቤቶች ፍቅረኛውን የሚያስታውስበትን ዘፈን አይከፍቱለትም "መምህራን ትምህርት ምን ያህል እንዳስጠላው አይረዱለትም ። ወላጆቹ ልጃቸው ከድህነት ቀንበር እንዲያላቅቃቸው
ይመኛሉ እንጂ እሱ ያለበትን ችግር አያውቁለትም ። ጓደኞቹ ብቸኝነቱን አይፈቅዱለትም ።
“ እሷ ከሙዚቃዋ ጋር ገደል ትግባ ! አንቺ ቢራ ድግሚን ” አላት ሳምሶን በሽቆ ።
“ኧረ ይብቃን ! ሰዓቱም መሽቷል የካምፓስ ፖሊሶች አያስገቡንም ” አለ እንክንርድ ኪሱን እየዳበሰ ።
አምጪልን እባክሽ እንጠጣው ዛሬ ካምፓስ ማን ይገባል? ” አለ ሳምሶን በሞቅታ ስሜት ።
“በይ እንግዲያው አንቺንም እንጋብዝሽ የምትጠጪውን ነገር ይዘሽ ነይ ” አላትና እስክንድር ፡ ወደ ሳምሶን ዘወር ብሎ ፥ “ ከጠጣን አይቀር መሐላችን አንዲት አንስታይ ስትኖር ይሻላል” አለው ። ከሳምሶን ሁኔታ ገንዘብ እንደያዘ
ገምቶ ነበር "
እቤል ምንም አስተያየት አልሰጠም ። የያዘውን ቢራም አልጨረሰም ። ከዚያ በላይ መጠጣት አልፈለገም ። ሆኖም
አልተከላከለም ። ሕይወትን የመሰልቸት ዐይነት ነበር የሚሰማው ። ለምንም ነገር ያለመጨነቅ ። ስካር ማለት ይሄ ይሆን እንዴ?

👍1