አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#በክፍለማርያም

በነፋሻዉ አየር በንፋሱ ዉልብታ ቅርንጫፎቹን ከወዲህ ወድያ የሚዉረገርገዉን የባህርዛፉን ግንድ ተደግፋ
ቤዛዊት የቀጠረችዉን ፍቅረኛዋን በጉጉት አይኖቿ አሻግረዉ እያዩ ትጠብቃለች።
እማማ ስንቅነሽ ትመጣለች ብለዉ ያልጠበቋትን የበፊትዋን እብድ ጤነኛ ሆና በመምጣቷ እየተደሰቱ እና አምላካቸዉን እያመሰገኑ በጠዋት መጥታ እንግዳ ስለሆነችባቸዉ ቁርስ ቢጤ ሊሰሩላት ደፋ ቀና እያሉ ነዉ።

በእርግጥ ከህልማቸዉ ጠፍታ አታዉቅም እርቃኗን ሆና በብርድ ስትንሰፈሰፍ አይናቸዉ ላይ ስለተቀረፀች
ድቅን ትልባቸዋለች በወለደ አንጀታቸዉ አፈር አልብሰዉ የቀበሯት ልጃቸዉን ያዩ ይመስል ቤዛዊትን
ሲያዩ ስፍስፍ ብለዉ ያዝኑላታል።

ፍፁም ነግቶ ልቡም በጭንቀት እንደተወጠረ ቤዛዊት ካለችዉ ቦታ ለመሄድ ለባብሶ ጨርሶ የአንድ እጁን ክራንች
ትቶ በአንዱ ብቻ እየተጠቀመ በሩን ቆልፎ ከወጣ በኋላ የፃፈችለት ወረቀትን ከኪሱ አዉጥቶ በድጋሜ ተመልክቶ
ኪሱ ዉስጥ መልሶ ሊከተዉ እየሞከረ ከጀርባዉ አከራዩ ጉሮሮአቸውን እየጠረጉ

"እህህ እንዴት አድረሀል አቶ ፍፁም?"

ፍፁም ሳያስበዉ ስለጠሩት ደንገጥ እያለ እና የቤት ኪራይ ቀን መድረሱም ትዝ እያለዉ ኪሱ ዉስጥ ከያዘዉ ዳጎስ
ያለ ገንዘብ መሀል ቆጥሮ እያወጣ ለአከራዩ እየሰጣቸዉ
"ይመስገን"
አላቸውና ስዓት እንዳያረፍድ እና ቤዛዊትን እንዳያጣት አስቦ እየተቻኮለ ወጣ።

የቤዛዊት አባት ቤዛዊት ቦርሳ አንግባ እንደወጣች ከእንቅልፋቸዉ እንደነቁ ሰራተኛቸዉ ስለነገረቻቸዉ ተናደዉ
"እዚች ልጅ ላይ ያለዉ ሴጣን መች ይሆን እረፍት የሚሰጠን"
እያሉ እያጉተመተሙ ወደ ቤዛዊት መኝታ ክፍል ደርሰዉ እንደገቡ መጀመርያ አይናቸዉ ጠረጴዛ ላይ የተቀመጠ
ወረቀት ላይ ስለሆነ በእጃቸዉ ሳይነኩት በእርቀት ቆመዉ ለማንበብ አንገታቸዉን ሰገግ አርገዉ አይኖቻቸውን
ሰደዱ
"አትፈልጉኝ በፈጠራችሁ አምላክ ተዉኝ"
የሚሉ ቃላቶችን ሲያነቡ ወረቀቱን አንስተዉ ጨምድደዉ እየወረወሩት
"ጥርግ በያ ለኔ ስትይ ገደል ለምን አትገቢም"
እየጮሁ ተናግረዉ በሀሳብ እና በንዴት እየተዉረገረጉ ወደ ሳሎን አምርተዉ ተለቅ ያለዉ ሶፋ ላይ
ዘፍ ብለዉ ተቀምጠዉ ቤዛዊትን ማማረር እና መራገም ጀመሩ
"የእራሷ ጉዳይ"
አሉና ስለ ቤዛዊት ላለማሰብ ፂማቸዉን በእጇቻቸዉ ሲነካኩ ቆይተዉ አይናቸዉ ከሳሎኑ ግድግዳ ላይ ከተሰቀለዉ
የቤተሰብ ፎቶ ላይ ተተክሎ ቀረ
እሳቸዉ ባለቤታቸዉን አቅፈዉ ፎቶዉ ላይ ይታያሉ የቤዛዊት ታላቅ እህት እናቷን ተደግፋ ከጀርባ ቆማለች
ፊቷ ላይ ፈገግታ ይነበባል ቤዛዊት ከረሜላ አልገዛልህም እንደተባለ ህፃን አኩርፋ አባቷን ተደግፋ ትታያለች
የቤዛዊት አባት ፎቶዉን እያዩ ቆይተዉ ቤዛዊት ላይ መጨከን እና መተዉ አላስችል ስላላቸዉ
በሀዘን ተዉጠዉ ለአቶ ፍቃዱ እርዳኝ ለማለት ስልካቸዉን አዉጥተዉ መደወል ጀመሩ።

ተንኮለኛ እና ሞኝ ሰዉ አይጥመድህ ከህይወትህ ለማሶጣት በጣርክ ቁጥር የጠራከዉ ይመስለዋል
ስለዚህ ሁሌም ሲከተልህ ይኖራል
ፍቃዱ እየተጣደፈ ስራዉን ትቶ የፍፁምን እና የቤዛዊትን ህይወት ለማመሰቃቀል ወደ ፍፁም የተከራየበት ቤት
አመራ ወደ ግቢዉ ሲደርስ ቤዛዊት ኖራ እንዳትመታዉ እራሱን ለመጠበቅ እየተንሿከከ ወደ ግቢዉ ዉስጥ ዘለቀ።

የፍፁም በር ጋር ሲደርስ ከጀርባዉ ሰዉ መኖር እና አለመኖሩን ለማረጋገጥ ዙርያዉን ቃኝቶ ጆሮዉን የፍፁም በር
ላይ ለጥፎ ሲያዳምጥ ድምፅ በማጣቱ እየተገረመ በሩን ሲያንኳኳ እና ቆይቶም ለመክፈት ሲታገል ማንም አለመኖሩን ሲያዉቅ እየተበሳጨ ወደ መጣበት ሊመለስ ሲል መሬት ላይ የወደቀ ወረቀት አይቶ ጎንበስ ብሎ
ካነሳዉ በኋላ ለማንበብ ሞከረ
የቦታ አድራሻ የቀጠሮ ሰአት መልሶ መሬት ላይ ጥሎት ሹክክ ብሎ ወደ ዉጪ ወጣ
" የት ሄደዉ ይሆን "
ሲል ብዙ ካሰበ በኋላ ወረቀቱ መልስ ያለዉ ስለመሰለዉ ወረቀቱን ፍለጋ
ወደ ፍፁም ግቢ ፈገግ እያለ ተመለሰ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

.... የተከመረ የብር ብዛት በዓይነ ህሊናቸው ላይ ሄደና በደስታ ሰክረው ተቃቀፋ፡፡

አንድ ሺህ የአሜሪካን ዶላር ፖስፖርት፣ ልዩ ልዩ ሰነዶች ነበሩበት፡፡ ፖስፖርቱንና ሰነዱን ቢቻል ለመመለስ ባይቻል ሊጥሉት ተስማሙ።

ቀይዋን ሲትሮይን መኪና እያከነፈ ከስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደደረሱ በንዴት ደም ስሮቹ የተገታተሩትና፤ ፀጉሩ እንደ ጃርት እሾህ የቆመው ነጭ! የበለጠ ነጭ ሆኖ፣ አስተርጓሚውን ይዞ ወደ ግቢ ዘለቁ፡፡እባክህ ወንድም ዕለታዊ የወንጀል ሪፖርት መቀበያውን ብትጠቁሙን”
ሲል ከበር ላይ የቆመውን ፖሊስ አስተርጓሚው ጠየቀው፡፡ ፖሊሱ
ሪፖርቱን የሚያስመዘግቡበትን የቢሮ ቁጥር በጣቱ አመለከታቸውና ተያይዘው ሄዱ፡፡ ከገንዘቡ የበለጠ ያበሳጨው የጠቃሚ ሰነዶቹ እና የፖስፖርቱ ጉዳይ ነበር፡፡

የዕለት ሁኔታን መዝጋቢው የተፈፀመውን ስርቆሽ በአስተርጓሚው አማካይነት ከመዘገበ በኃላ በተለይ ወንጀሉ የተፈጸመበት ሰው የውጭ ሀገር ዜጋ መሆኑና ይህ ድርጊት ከወትሮው ለየት ያለ በመሆኑ፤የጉዳዩን ክብደት ከአገር ደህንነት ጋር በማገናዘብ፤ ስለሁኔታው
ለምርመራ ሹሙ ሪፖርት ሊያደርግ ፈለገ፡፡
“አንድ ጊዜ እዚሁ ጠብቁኝ ” አለና የምርመራ ክፍል ሹም የሚል ጽሑፍ የተጻፈበትን የቢሮ በር አንኳኩቶ ወደ ውስጥ ዘለቀ፡፡

አምሽቶ በመስራት ላይ የነበረው የምርመራ ክፍል ሹም ሁኔታውን እንደሰማ አመልካቾች እንዲገቡ አደረገ፡፡ ከዚያም የተፈጠረውን ሁኔታ፤
የወንጀሉን ሂደት፤ የሌቦቹን የእንቅስቃሴ ስልት፤ አንድ በአንድ ከመዘገበ በኋላ ከበድ ያሉ ወንጀሎችን መርምሮ ተጨባጭ ውጤት በማስገኘት ረገደ ተደጋጋሚ ድል ያስመዘገበው የ፶ አለቃ ውብሸት አየለን አስበው....
“ወንጀልን ሪፖርት ማድረግ ቀላል ነው፡፡ ወንጀለኛን አድኖ በቁጥጥር፤ ስር ማዋል በተለይም በቀላሉ ዱካውን ለመያዝ አስቸጋሪ የሆነ ወንጀለኛን ፈልጎ ለማግኘት ግን ትዕግስት፤ ዘዴንና፤ጊዜን ይጠይቃል፡፡
ምናልባት በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደርስበታለን ብለን በእርግጠኝነት
ባንደፍርም፤በትዕግሥት በምናካሂደው ምርመራ የሚያመልጠን ነገር ይኖራል ብዬ አልገምትም፡፡ ለማንኛውም ጉዳዩ ልዩ ትኩረት የምንሰጠው ይሆናል፡፡” ይህንን ከተናገረና የስልክ ቁጥሩን
ለእንግዳው ሰው ሰጥቶ ካሰናበታቸው በኋላ፣ በእልህና በቁጭት ከንፈሩን ነክሶ፣ የዚህን ወንጀል ፈጻሚዎች ጉዳይ በአስቸኳይ ከውጤት ላይ
እንደሚያደርስለት በመተማመን ፤
ጉዳዩን ለሃምሣ አለቃ ውብሸት
ለመስጠት ወሰነ....

ፈጣኑ የ፶ አለቃ ውብሸት አየለ እምነት ጥሎበትና እሱን መርጦ አለቃው ይህንን ኃላፊነት ከሰጠው ቀን ጀምሮ ሃሣቡ ሁሉ በዚህ ጉዳይ ላይ ሆነ፡፡

ቁርስና ምሣውን ሳያስታውስ፤ ቀንም ሆነ ምሽት የማጣራቱን ሥራ ሲያከናውን እያንዳንዷን ጥቃቅን መረጃ ጭምር ሳይንቅ፤የወንጀሉን ሂደትና የወንጀለኞቹን ሁኔታ ሲያነፈንፍ፤ ከቆየ በኋላ ወደ አንድ ግብ የሚያመራው ፍንጭ አገኘ፡፡ በተለይ “ጋሪ” በሚል ቅጽል ስሙ
የሚታወቀው ጉጭማው ቱለማ ተደጋጋሚ የስርቆሽ ሪኮርድ ያለበት
መሆኑንና: በዚያን ዕለትም በአካባቢው ሲያንዣብብ የቆየ ጆፌ መሆኑን
ደረሰበት፡፡ አብረውት ስለነበሩትም መጠነኛ መረጃ አገኘ፡፡
ይህ ሁሉ አደን ዛሬ እንደሚያበቃና አዳኝና ታዳኝ በግልጽ ሊያፋልማቸው ወደሚያስችል አዲስ ምዕራፍ መሸጋገራቸውን አዳኝም ታዳኝም አላወቁም ነበር፡፡

መላኩ በአካባቢው ስለሚካሄደው ሁኔታ እንዲያጠናና፤ አዲስ የፖሊስ እንቅስቃሴ ካለ እንዲያስታውቃቸው ፤ ለአሰሳ ተልኳል፡፡በዛሬው ዕለት በስንዱ ቤት ልዩ ፕሮግራም ተይዟል ስንዱ ከመኖሪያ ቤቷ አንዱን ክፍል ለዛሬ የጫት ዕድምተኞቿ
አዘጋጅታላቸዋለች፡፡
ከዳር እስከ ዳር የተገጠገጠው ስጋጃ፤ በላዩ ላይ እዚህም፧ እዚያም ፈንጠር፤ ፈንጠር፤ ተደርገው በተቀመጡ አሸብራቂ ትራሶች ደምቋል።
ክፍሉ በርከት ያሉ የጫት ታዳሚዎችን ለማስተናገድ ዝግጁ ሆኖ እየተጠባበቀ ነው፡፡
የሰሞኑ በሽበሽ የሰሞኑ መጠጥ የስሞኑ ደስታና ጭፈራ፣ ሲታሰብ ይህ ለእነ ጋሪ ቢያንስ እንጂ በዛ የሚባል አይደለም፡፡
ስፋ ያለው የመኝታ ክፍሏ ወለሉ ላይ ቄጠማ ተጐዝጉዞበት፤
እመሃሉ ጉብ ብሎ የሚታየው ባለሸክላው የክሰል ማንደጃ፤ በደሬ ክሰል ፍም ነዶ! እዚህም፧ እዚያም፤ ሰንደሉ ተለኩሶ ሲታይ፤ እንኳንስ የቃመውን ተመልካቹን የሚያስመረቅን ነበር፡፡

የጫቱ ፕሮግራም የሚጀመረው ከምሽቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ላይ ሲሆን፤ ምርቃናው ተጋግሞ ሲያበቃ፤የጨብሲው ፕሮግራም
ይቀጥላል።
ጨብሲው ደግሞ እንደዚህ የዋዛ አይደለም፡፡ ወንድ ነኝ ያለን በእግርና በእጁ ዳዴ ብሎ እስከሚሄድ ድረስ በሚንቆረቆረው የቢራና የውስኪ ፏፏቴ መጠመቅንም የሚያጠቃልል ነበር፡፡

በዚህ የጫት ፕሮግራም ላይ የሦስቱም የሴት ጓደኞቻቸው ተጋብዘዋል፡፡ በአንድ ወቅት ከጋሪ ጋር በፍቅር አብዳ የከነፈችውና አሁን በካዛንችስ አካባቢ የመንገድ ላይ ዝሙት አዳሪ የሆነችው ሂሩት ጥሪው የተደረገላት በጓደኛዋ በሜርኩሪ አማካኝነት ነበር፡፡ሂሩት በዚህ የጫት ፕሮግራም ላይ ጋሪ የሚገኝ መሆኑን እንዳወቀች ልታስቀናው ፈለገች፡፡ አጋጣሚውን ለመጠቀም በሃሣቧ የወንድ ጓደኞቿን በሰልፍ ከደረደረች በኋላ አንደኛውን መረጠችው፡፡
ከጓደኛዬ ጋር ካልሆነ ብቻዬን አልመጣም” አለቻት ለሜርኩሪ፡፡ሂሩትዬ አንድ አይደለም ከፈለግሽ ሦስቱን መጋበዝ ትችያለሽ”አለቻት በኩራት፡፡
ሜርኩሪ ይህንን ለማለት የደፈረችው፤ የሰሞኑ ርዝቅ ፤የሰሞኑ በሽበሽ
የዋዛ እንዳልሆነ ስለምታወቅ ነበር፡፡
እንግዲያው ሦስት ሣይሆን ከቦይ ፍሬንዴ ጋር እመጣለሁ” አለቻትና በዚህ ተስማሙ፡፡
ሂሩት ለዛሬው ግብዣ የመረጠችው መልኩ እንኳንስ የሴቱን የወንድ ልጅ
ልብ የሚያስደነግጠውንና፤ የወንድነት ድንግልናውን የወሰደችለትን ሰው
ነው፡፡ይህ ሰው ለዛሬው ግብዣ በጣም ተስማሚ እንደሚሆንና ያንን እሷ በፍቅር ከንፋለት ሳለ ፍቅሯን ሳያስጨርሳት...
“ጥፊ ከዚህ ብሎ ” ያባረራት ጋሪን ሊያስቀናው ይችላል ብላ ያመነችበት
አንዱአለም ድንበሩ ነው፡፡ለአሥራ ሁለት ሰዓት ሩብ ጉዳይ ሲሆን ታዳሚዎች በቀጠሮ ቦታቸው ደረሱ፡፡ዛሬ ስንዱ ለሁሉም የምትጋብዛቸው ፈገግታ እህል ትዝ አያሰኝም፡፡ ሁለመናዋ ስቆ፤ ያ ንቅሳታም ጥርሷ የበለጠ ተውቦ፤ ጥርስ
በጥርስ ሆናለች፡፡ በተለይ ጋሪን ከንፈሩን ነው የሳመችለት፡፡

በአጭር የታጠቀችው ጉርድ ቀሚስ ያንን ጠብደል ጭኗን በስፋት ያስቃኛል፡፡ በዚህ ላይ ማታ ማታ በፖርቲው ውስጥ በጨረታ የማትገኘውና፤ በበርካታ ጠጪዎች የምትታሸዋ ቆንጅዬዋ ማርታ ነች ለካዳሚነት የተመረጠችው ::ብቻ ዛሬ ምርጥ ምርጡ ሁሉ ለእነ ጋሪ ሆኗል።
ኪሣቸው ሲመነምንና፤ ዝንብ ሊወራቸው ሲጀማምር፤ ጀርባዋን እንደማትሰጣቸው ሁሉ፤ ዛሬ አፋሽ ፤አጉንባሽ ሆናላቸዋለች፡፡
በአንድ መቶ ብር የተገዛው ለምለም ጫት በእንሰት ተጠቅልሎ እዚያ እመሃላቸው ተገንድሶ፤ ሲታይ ለፋሲካ የተጣለ ሙክት ይመስላል።

ሂሩት የአንዱዓለምን ክንድ በክንዷ ቆልፋ፤ ከሜርኩሪ ጋር ከተቀጣጠሩበት ቦታ ተገናኙ፡፡ ሜርኩሪ አንዱዓለምን በእነዚያ ቀዥቃዣ ዐይኖቿ ላጠችው፡፡ በውበቱ ተደንቃ ፈዝዛ ቀረች፡፡
እንዴት ደስ የሚል ልጅ ነው በእግዚአብሔር? አደነቀችው፡፡ብዙም ሳይጓዙ ወደ ውስጥ ታጥፈው ስንዱ ቤት ደረሱ፡፡ ሦስቱ የመጨረሻ እድምተኞች ተያይዘው ሲገቡ፤ ቤቱ ተሟሙቆ ነበር፡፡ ሂሩትን እንዳየ ጋሪ ዓይኖቹ በቅናት ተበለጠጡ፡፡ በተለይ በአንዱዓለም ላይ
ፈጠው ቀሩ፡፡ ልታስቀናው እንደፈለገች ገባው፡፡
“ማን አባቷ ጠራት ይህችን ውሻ በልቡ ሰደባት፡፡

ሂሩት የጋሪ ዐይኖች በቅናት መቅላታቸውን ስትመለከት አንጀቷ
👍1
#ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

...የሐኪሙ የስሜት ሕዋሳቶች ክፉኛ ተነቃቁ ስሟን ሳያውቁ ሳያነጋግሩ ዝም ብሎ እያዩ መውደድ ? ! እንዴት?

"ፈጽሞ አነጋግረሃት አታውቅም ? "
"እንዲያዉም ። ”
“ ስንት ጊዜ ሆናችሁ ? ”

"ስንተያይ አራት ወር ገደማ ሆኖናል"

"እሷ ከሩቅም ቢሆን ላንተ ያለት ሁኔታ እንዴት ነው?"

"እንጃላት ! መጥፎ ጓደኞች ናቸው ያሏት ።

ፊቱ ተለዋወጠ ። አርዕስተ ነገሩ ወስጥ እያሰመጠ በሄደ ቁጥር ዐይኖች እየቀሉ መጡ።

"ትወዳታለህ ? ”

“ እንዴ አዎ ! ግን ደግሞ ጠላቴም ነች እጠላታለሁ ትምህርቴን እንዳላጠና አድርጋኛለች ። ”

የቀሉት ዐይይኖቹ እንባ ሲያቀሩ ሐኪሙ ተመለከተ።

"ኳስ ጫዋታ ትወዳለህ ? ”

አቤልን ከሰመጠበት ተመስጦ ለማውጣት የቀረበ የማዘናጊያ ጥያቄ ነበር ። እውነትም አቤል ግር አለው። የማያስፈልግ ጥያቄ !

“ አ....ዎ ፥ የእጅ ኳስ ዐልፎ ዐልፎ ። ብቻ ይሄን ያህል አይደለሁም ፥ አለ ዐይኑ ላይ ያቀረረውን እንባ ወደ ውስጥ እየመለሰ።

"ሌላ ምን ጨዋታ ትወዳለህ ? በትርፍ ጊዜህ ? ”
በቃ ብዙም ጨዋታ አልወድም በትርፍ ጊዜዬም መፅሐፍ ማንበብ ነው የማዘወትረው።

ሐኪም ለጥቂት ሴኮንዶች በዝምታ የአቤልን ገጽታ ሲያጠና ከቆየ በኋላ መረጋጋቱን ሲገምት ወደ አርዕስትቱ
ነገሩ ገባ።
“ ግን አቤል ለምን ልጅቷን ቀርበህ አታነጋግራትም ? ”

“ አልችልም ! ”

ስሜቱ እንደ ገና ተለዋወጠ ቁጣ ቁጣ አለው።

ሐኪም ዘልቆ ማነጋገር እንዳማይችል ተረዳና በዚህ ጉዳይ ላይ ጥያቄውን አበቃ ሆኖም የአቤል አመላለስ አስገርሞት ሣቁን በሆዱ አፍኖ ነበር የያዘው እወዳታለሁ ግን አላናገራትም ዝግ ፍቅር !

ሐኪሙ አቤልን የሚረዳበትን መንገድ አሰላሰለ ልጅቷን አምጥቶ የማገናኘት ሐሳበ መጣለት ፡ ሆኖም አቤል ለልጅቷ ያለው ፍቅር ሙሉ በሙሉ ጤናማ እንዳለሆነ ስለ ገመት ይህ የማያዋጣ ሃሳብ ሆነበት የባሰ ችግር ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት ያዘው ። አንዴ በተመሳሳይ ሁኔታ ያፈቀረ አንድ ወጣት ልጅቷን ፊቱ አቅርበው ሊያጨባብጡት፡ ካልገደልኩሽ ብሎ እንዳነቃት ሐኪሙ አስታወሰ። ለጊዜው መፍትሄ በማጣት በረዥሙ ተነፈሰ።

"እሺ ልጅ አቤል እንቅልፍስ አዴት ነዉ• ? ደግና ትተኛለህ፥ ?

“ አልተኛም ታግዬ ታግዬ በመከራ ነው የሚወስደኝ።

ሐኪሙ በትንሽ ፓኮ ኪኒኖች ጨምሮ ሰጠውና የሚውጥበትን ጊዜና መጠን ነግሮት ፡ “ ለእንቅልፍ ይረዳሃል ።
አለው ።

ሐኪሙ አቤልን ከማሰናበቱ በፊት የሆነ ነገር አስቦ ከመቀመጫው ተነሣና “እንድትጠብቀኝ፥ መጣሁ ” ብሎት
ወጣ ። ለአቤል ቋጠሮ ከመስጠቱ በፊት ቀደም ብሎ ተመሳሳይ ሁኔታ ያከመ አንድ ሥራ ባልደረባውን ለማማከር፤ወደ ሌላ ክፍል መሄዱ ነበር ።

በሩን ከፍቶ ሲወጣ፥ሰዎች ተኮልኩለው ተመለከተ አንድ ግዙፍ ራሰ በራ ሰውዬ ተጠግተውት “እርስዎ ጋ ነበር ዶክተር ” አሉት ።

“ ምንድነው?” እላቸው በተሰላቸ ስሜት ። በራቸውና ግዙፍ ሰውነታቸው ከብዶት ነው እንጂ ገፍቶአቸው ሊያልፍ ነበር ።

አቤል የሚባል ተማሪ ለምርመራ እርስዎጋ መግባቱን ሰምቼ ነው ። ከዩኒቨርስቲ ነው የመጣሁት ፡ እዚያው
መምህር ነኝ ” ዮናታን እንዲህ ራሳቸውን ካሰተዋወቁ በኋላ ከሐኪሙ ግጽታ ክብር ያለው ምላሽ አገኙ ።

እስክንድር አጠገባቸው ቆሞ ሁኔታውን ታዝቦአል ።ዮናታን ራሳቸውን ከማስተዋወቃቸው በፊትና በኋላ በሐኪሙ የተደረገላቸው መስተንግዶ ልዩነት እያስገረመው "የእያንዳንዱ ሰው የውስጣዊ ማንነቱ ግንባሩ ላይ መነበብ
ቢችል ምን ነበረበት ? ” ሲል አሰበ ።

“ አሁን እንዴት ነው አቤል ? አሉት ዮናታን የሐኪሙን ዐይን ዐይን እያዩ ።
ደኅና ነው ።

“ ማለቴ ፡ የሚያስተኛው ይመስልዎታል ? ምናልባት ከባሰባቸው የአዕምሮ ሕመምተኞች ጋር መቀላቀሉ መጥፎ
ይሆናል የሚል ሥጋት ይዞኝ ነው” አሉ ዮናታን ፈራ ተባ በሚል ድምፅ ።

እሱ የእኔ ሥራ ነው ” እሳቸው ሐኪሙ ቆጣ ፡ ኮራ ብሎ ፡ “ ለማንኛውም ልጁ ደኅና ነው አናስተኛውም ጠብቁትና ይዛችሁት ትሄዳላችሁ ” ብሏቸው ሔደ ።
የዮናታን ልብ ተረጋጋ ። ሥጋታቸው የለየላቸው ዕብዶች መሐል ገብቶ አቤልም እንዳይለይለት ነበር ።

የአቤል ወደዚህ ሐኪም ቤት መምጣት የነገራቸው እስክንድር ነበር ። መልእክቱን እንደ ሰው ተደናግጠው ቢሮአቸውን እንኳ ሳይቆልፉ ነበር የወጡት ከእስክንድር
ጋር ሆነው በቦልስ መኪናቸው ሲከንፉ የትራፊክ መብራቶች ሕግ መጠበቃቸውን ይጠራጠራሉ ።

እስክንድር ራሱ ከጸቡ ቦታ የደረሰው ዘግይቶ ነበር።አቤል ወደ ሐኪም ቤት ከተወሰደ በኋላ ሳምሶን ጉልቤው
ሚስተር ሆርስን ካልገደልኩ ብሎ እየተጋበዘ አስቸግሮ ነበር እስክንድር ነው አባብሎ ያስታግሠው ። ሚስተር
ሆርስ የጸቡን መነሻና ሁኔታ ረጋ ብሎ ለእስክንድር አጫወተው ያልጠበቀው ትንሽ ነግር ይህን ያህል መጉላቱን
በተመለከተ ጊዜ ፥ ሚስተር ሆርስ ራሱ ተደናግጦ ነበር ።

ዮናታን የጸቡን ሁኔታ ከእስክንድር ሲሰው ነገሩ ከትግሥት ጋር የተያያዙ መሆኑን መገመት ብዙ ጊዜ አልመወሰደባቸዉም ። “ በት ! በላት ! ” የሚለው የአቤል የተደጋገመ ጩህት የቅርብ ሚስጢሩን ለሚያውቁት ሰው በቂ ማስረጃ ነበር ።

ዮናታን አሁን አቤል ሐኪም ቤት ውስጥ እንደማይተኛ ካረጋገጥን በኋላ ሌላው ጥድፊያቸው የጸቡን መረጃ ለቢልልኝ ለመስጠት ነበር ። ሥነ ልቡናው ጥናት የሚጠቅም ነገር እንዳገኙ በመገመት ተቻኩለዋል ።

« አሁን የፈተናውን ነገር አቤል እንዴት ቢያደርግ ይሻላል ? ” አላቸው እስክንድር ዮናታንን ሐኪሙ በር ላይ እንደ ቆሙ ። አቤልን ያመጡት የዩኒቨርስቲው ባልደረቦችም አብረዋቸው የሐኪሙ በር ላይ ቆመው ነበር ።

“ ፍቃዱ ቢሆን ባይፈተን ይሻላል ግን እንጃ ” እሉ ዮናታን ፥ የአቤልን ፈቃደኝነት በተጠራጠረ ስሜት ።

አቤል ከሦስት ቀን በኋላ ለመመለስ ከሐኪም ቀጠሮ ተቀብሎ ወጣ ። በሩ ላይ ዮናታንን ሲያያቸው የቆመበት
መሬት ቁልቁል ቢውጠው በወደደ ነበር ፡ ቢሮአቸው ጠርተሎ ካነጋግሩት ወዲህ ሲገናኙ የመጀመሪያ ጊዜያቸው ነው ። ዐይኑን ሰብሮ መሬት መሬቱን ይመልከት ጀመር ።

አሁን እንዴት ነው ? ” አሉት ዮናታንና እስክንድር በዜማና በብሩህ ድምፅ ።

“ደህና ነኝ የእንቅልፍ ኪኒንም ተሰጥቶኛል አላቸው አቤል አንገቱን እንደሰበረ ።

መደናገጡን ስለ ተመለከቱ ሁሉም ብዙ
እንዳያናግሩት ተቆጠቡ ። የማኅበራዊ ሥራ ባልደረባቸውና የዩኒቨርስቲው
ሹፌር ቀድመው እንዲሔዱ ዮናታን ነገሯቸው አቤል ከእሳቸው ገር ለመሄድ ወደ ውጪው በር አመራ።

አቤልን መሃል አድርገው ዮናታንና እስክንድር የውጭውን በር እንዳለፉ ዕርቃነ ሥጋውን የተቀመጠ አንድ ለማኝ አጋጠማቸው

አይታችሁ አትለፉኝ ፡ ዓለሞቼ ! ”

ዮናታን ዐይናቸውን ጨፍነው አስር ሳንቲም ጣሉለት። የተጎዳ ኃፍረተ ሥጋውን አጋልጦ ነበር የሚለምነው ብልቱ አብጦ ትልቅ ኳስ አክሏል።

አቤልን ለማኙን አትኩሮ ሲመለከተው አንድ ነገር ስሜቱን ጠቅ አድርጎ ወጋው መኪናው ውስጥ ገብተው ሲንቀሳቀሱም ሐሳቡ ከለማኙ ጋር ቀርቶ ነበር ።

“ ለካ አጸያፊውን የውስጥ ማንነታችንን ደብቀን የምንይዘው ገንዘብ ሲኖረን ብቻ ነው አለ በሐሳቡ የተጎዳ አፍረተስጋ እየታየው ሚስጢር የሚሸፍነው በገንዘብ ነው።ድህነት ሚስጢራችንንም ሆነ አፀያፊ ማንነታችንን አጋልጦ ያወጣዋል። ገንዘብ ባለን ጊዜ ሀፍረተ ስጋን ቀርቶ የጣት ቁስላችንን ለመደበቅ ነው የምንጥረው። ድህነት ሲመጣ ግን መደበቁ ቀርቶ በይፋ መለመኛ ይሆናል። ከሰው በኋላ ተፈጥረው የሰውን ውስጣዊ መንፈስ
👍1