#የታካሚው_ማስታወሻ
፡
፡
#ክፍል_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)
አልደነቀውም፡፡ጭራሽ፣ወሬ ሊያስቀይረኝ ይሞክራል። እርሷ ጋር ደውሎ፣ በስልክ ስለኔ ያወሩትን ነገር ነገርኩት፡፡
"ጠብቄው ነበር!”
“ምኑን?”
“ይሄንን ነዋ፡፡ ልጅቷ ነገሯ አላማረኝም ነበር፡፡”
እንዴት?”
“በቃ አለባበሷ፣ ቢሮህ መመላለሷ፣ ብቻ ነግሬህ ነበር፡፡”
“ምን ብለህ?”
“ቀስ በል! አትቸኩል፡፡ የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል!' ብዬ ነግሬህ ነበር፡፡”
“እና ማሂ ያለችው እውነት ነው፡፡ ሰውዬው እንዲህ ያደርጋል?”
“ወንድሜ፣ ሰውየው በተወለደበት ቀዳዳ ተለክፏል፡፡ መሞቻውም እዛው እንደሚሆን ግልፅ ነው፡፡ ካ...ካ...ካ...፡፡ በዚህ እድሜ፣ሚስትና ልጆቹን አስቀምጦ ግቢ ውስጥ ያሉትን ሴቶች ሁሉ አትንኩብኝ ማለት...፣ እንደውም ደግ አደረክ! አንተ ወጣት ነህ፣ አላገበህም፣
መዝናናቱም፣ ሁሉም ባንተ ያምራል፡፡ እርሳው ባክህ፡፡ እንደውም ምሳችንን በልተን ሶደሬ እንሂድና ፈታ እንበል፡፡ ማሂንም ይዘናት እንሂድና ስትደጋግማት ታድራለህ፡፡ የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም፡፡
ካ...ካ...ካ...”
“ትቀልዳለህ አንተ፡፡”
“የምሬን ነው፡፡” አሁን እኔም በአለቃዬ ድርጊት መናደድ ጀምሪያለሁ፡፡ እልህ እተሰማኝ ነው፡፡
“እሺ ደውልላት፡፡”
ለማሂ ደወለላት። አታነሳም፡፡ የኔን መኪና አቁመን በሱ መኪና ሶደሬ ሄድን፡፡ በፍልውሃ ታጠብን፣ እኔ ዋኘሁ፡፡ ሶደሬ ብቻችንን ስንመጣ እንደሚያደርገው፣ በሲጋራው ምትክ ሺሻ አጨስ፡፡ ወደ መዋኛው ገንዳ ተመልስን ዶሮ አሩስቶ አዘን በቢራ እያወራረድን በላን፡፡ ሰውዬው ለሰው ያለው ንቀትና ድርጊቶች አበሳጭተውኛል። የሳሚ አይዞህ
ሲጨመርበት፣ ውስጤ ተጋፈጠው ተጋፈጠው እያለኝ ነው፡፡ “ድርጅቱ
የቤተሰቡ ሀብት ቢሆን ሰራተኞቹንም የግል ንብረቱ አደረጋቸው እንዴ?፣
ቀጠራቸው እንጂ አላገባቸው...፣ ደግሞ አንዷ ብትበቃውስ፣ ሁሉን አትንኩብኝ፣ ጭራሽ የጣልኩትንም አታንሱ..? ቅሌታም! ደስ ያለኝን አማርጣለሁ፡፡ እንደውም፣ ማሂንም ጨምሬ እልሁን አስጨርሰዋለሁ።”ለራሴ አልኩኝ፡፡ ማታ እቤት ስገባ ምሽት ሶስት ሰአት አልፎ ነበር፡፡ደክሞኝ ስለነበር ወዲያው እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡
የተፈጠረውን ነገር አዕምሮዬ ሊረሳው አልቻለም፡፡ የሆነ ድራማ እየተሰራብኝ እንደሆን አሰላስላለሁ፡፡ “የት ነሽ...? ከማን ጋር ነሽ...? ካልተገናኝን...?” ያለጥርጥር ከሰውየው ጋር ግንኙነት ነበራቸው፡፡ያለምክንያት እንደዛ አላንጓጠጠችውም፡፡ ሰውዬው ከእርሷ ጋር ከርሞ፣ እንደዘበት አሽቀንጥሮ በሜሪ ተክቶ አቃጥሏታል፡፡ ለዛ ነበረ ሜሪን ጅል፣
ነፈዝ እያለች ስታጣጥላት የነበረው፡፡ መጫወቻ ኳሷ አድርጋ፣ አለቃዬን
በኔ እያስቀናችና እያበሸቀችው ነበር፡፡ እኔ ጅሉ፣ እንደፈለገችው ተወንኩላት፡፡ ወይኔ ተኩቻው! አጠምዳታለሁ ብዬ ሄጄ፣ የእርሷ ወጥመድ ውስጥ ሰተት ብዬ ልግባላት? ፀባዩን የቀየረብኝ ይሄን አውቆ
ነበር ለካ..። ግን ቀንቶ ነው? ወይስ አሁንም ይፈልጋታል..? ወይኔ፣ ተኩቻው!! እቺ ብሽቅ እንዲህ ትጫወትብኝ፡፡
ስራ መሄድ ያስጠላኝ ጀምሯል። ግን እንደምንም እመላለሳለሁ፡፡ ተነሳሽነቴምና ትኩረቴም ከሞተ ቆይቷል። ከአለቃዬም ሆነ ከሌላ ሰራተኛ፣ ምንም ያየሁት አዲስ ነገር የለም፡፡ ውስጤ ግን እንደ ክረምት
ቀዝቅዟል፡፡ ተኮማትሯል፡፡ ሳሚ ቢሮ እየመጣ ሻይ እንድንጠጣ ይዞኝ
ይወጣል፡፡ እንደበፊቱ መሳቅ መጫወቴ ጠፍቷል። ውስጤ መጥፎና አስጨናቂ ሃሳቦችን እየመረጠ ያመነዥጋል፡፡ ስትስልልህ ነበር የከረመችው፤ ሰውየው ሊያጠቃህ አድፍጧል!' እያለ ጭንላቴ
ያስጨንቀኛል፡፡ አሁን፣ ለጨዋታዎች ስሜት አልባ ሆኛለሁ፡፡ ማሂም ማኩረፌን ስታይሉ ፣ ቢሮዬ ተመላልሳ፣ ይቅርታ ጠየቀችኝ፡፡ ሻይ እንድንጠጣ ጠየቀችኝ፡፡ አይሆንም አልኳዋት፡፡ እንደውም፣ ሁለተኛ
ቢሮዬ እንዳትመጣ፣ ላገኛት እንደማልፈልግ አምርሬ ነገርኳት፤ ቢሮዬ
መምጣት አቆመች፡፡
ከግዜ ወደግዜ ያለ በቂ ምክንያት መናደዴ፣ መበሳጨቴ እየተባባሰ መጣ፡፡ ስራ ስለመልቀቅ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ከዚህ በፊት ስራ በማቆሜ ምክንያት ያደረስኩትን ጉዳት በማስታወስ ውስጤን እንዲረጋጋ ታገልኩት። ስራዬ ግን እንደቀደመው አስደሳች አልሆን አለኝ፡፡ ከነ ሳሚ ጋር ወጥቼ መዝናናትን አቆምኩኝ፡፡ በምትኩ ደብረዘይት እየተመላለስኩ ጫት በመቃም ከድባቴዬ ለመሸሽ ሞክራለሁ፡፡ በተደጋጋሚ ምቅምበት ጫት ቤት አሌክስና ሃብታሙ ሚባሉ ጉደኛሞችን ተግባባሁ፡፡ አሌክስ
ሃብታሙን ዶክ እያለ ይጠራዋል። አሌክስ በጣም ፈጣን፣ ተጫዋችና ከሰው ጋር መግባባት ደስ ሚለው ሰው ነው፡፡ ቀልድ ሲያወራ አጠገቡ የተቀመጡ ሁሉ እንዲሰማው ጮክ ብሎ እንድናዳምጠው በዐይኑ እየጋበዘ ነው፡፡
“ትናንት ማታ የተዋወኳት ቺክ ውበት!፣ ወይኔ...!” ብሎ አሌክስ ለሁላችንም እንደሚያወራ በየተራ ተመለከተን፡፡
“ስንት ሰዓት? ትናንት እዚህ አብረን አልነበርን?” ሃብታሙ ጠየቀ፡፡
“ከዚህ እንደወጣን፣ ጨብሲ ሳንል ጥለኸኝ ላሽ አላልክም?”
“እ...፣ እሺ፡፡”
“የጨብሲ ስላልነበረኝ፣ በወክ ልሰብረው ብዬ ስዞር፣ የሆነች ልዕልት ምትመስል ቺክ አላገኝም፡፡ ወይኔ..፣ ወይኔ..፣ ወይኔ ዐይን! ስታያት በድንጋጤ ደንዝዘህ ትቀራለህ፡፡” ሲያወራ በመደነቅ ግንባሩን
ይዞ እያወዛወዘ ነው፡፡
“እሺ፡፡ ከዛስ ከምን አደረስካት ታዲያ?”
“በስማም ፣ ሞትኩባታ! ጭውቴው ደግሞ እንዴት ስክት ስክት እንዳለልኝ፡፡ ነገረ ስራዬ ለራሴ ገርሞኝ፣ እቤት ከገባሁ በኋላ ስስቅ ነበር።”
“ወሬ አታጣ ! ድሮስ ምላሳም አይደለህ? ምን ብለሃት ነው፣እንዲህ የተገረምከው?”
“ድንገት እጇ ላይ ተጠምጥሜ፣ 'የኔ ልዕልት መሳይ፣ በናትሽ ምሪኝ በናትሽ?” ብዬ ስለምናት፣ መጀመሪያ “ምን ሆንክ?” አለችኝ ደንግጣ፡፡ 'ይኼን ውብ ዐይንሽን ሳይ፣ የእኔ ዐይን አፍሮ ነው መሰል
አላይ አለኝ፣ ብዥ አለብኝ፡፡ ዐይኔን ልጨፍነውና፣ እባክሽን ምሪኝ?” ስላት በሳቅ ሞተች?!” ብሎ ሲስቅ፣ ሁላችንም በድርጊቱ አብረነው ሳቅን፡፡ አሳሳቁ ሰው ላይ ይጋባል፡፡ የዐይኖቹን ትንንሽነትና በራሱ ላይ መቀለዱ ደግሞ፣ የበለጠ እንድንስቅ አደረገን፡፡ ስግባባቸው፤ ሃብታሙ፣ የእንስሳት ሃኪም እንደሆነ አወኩ። አሌክስ ደግሞ የተገኘውን ተባራሪ ስራ ሚስራ አፈ ቀላጤ።
አንድ ቅዳሜ ምሽት፣ አሌክስ ወጥተን የጨብሲ አንድ ሁለት ካልጋበዝኩህ ሞቼ እገኛለሁ ብሎ ድርቅ አለብኝ፡፡ እሺ ብዬው አብረን ወጣን፡፡ እየጠጣን በአስቂኝ ጨዋታዎች የታጀበ ደስ ሚል ምሽት
አሳለፍኩ፡፡ እርሱ ልጋብዝህ ብሎ ይዞኝ ወጥቶ፣ ሂሳቡን ጓደኛው ሃብታሙ ከፈለ፡፡ ስልክ ተለዋወጥን፡፡ ጓደኛሞች ሆንን፡፡ አሌክስ በቀላሉ ጎትቶ ከነሱ ጋር ቀላቀለኝ፡ከነሱ ጋር ስሆን፣ ከአስጨናቂ ሃሳቦቼ
እረፍት ስለማገኝ እኔም ደስተኛ ሆንኩ፡፡ ቅዳሜና እሁድ ውሎና አዳሬ ቢሾፍቱ ሆነ፡፡ ገና ሰኞ ስራ ስገባ ቅዳሜ ትናፍቀኛለች፡፡ ከነማሂ ጋር ካሳለፍኩ፣ ስድስት ሳምንት አለፈኝ፡፡ ሳሚ በተደጋጋሚ በአካልም በስልክም ምነው ጠፋህ ሲለኝ፣ ቢሾፍቱ የራሴን ስራ ለመጀመር ስላሰብኩ፣ ቅዳሜና እሁድ ያን ለማመቻቸት እዛ እንደማሳልፍ ነገርኩት።
ምን ስራ ልትጀምር ነው?' ሲለኝ፣ ሲያልቅ ብታየው ይሻላል፤ አልኩት፡፡ እሺ ብሎ ተወኝ፡፡
ከእንቅልፌ ስነቃ ከንጋቱ አንድ ሰዓት ተኩል ሆኗል፡፡ ማታ ስጠጣ ያደርኩበት ጭንቅላቴን ይወቅረኛል፡፡ ከፍተኛ ድካምና ድባቴ እየተሰማኝ ነው፡፡ የሰውነቴ መዛል ከእንቅልፍ የተነሳሁ ሳይሆን፣ ሃያ አራት ሰዓት ካለረፍት ስስራ ያደርኩ ነው ሚመስለው፡፡ ስራ መሄድ እንዳለብኝ ሳስብ እንባዬ መጣ፡፡ የፈለገው ይምጣ ብዬ

👍4
#የታካሚው_ማስታወሻ
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)
ስራ አርፍጄ ገባሁ፡፡ ላለባበሴ ትኩረት መስጠት አቁሚያለሁ።ትንሽ እንደተቀመጥኩ ማሂ ቢሮዬ ገባች፡፡
“እንዴት ነህ?”
“አለሁ፡፡ ምን ልታዘዝ?”
“ማወራህ ጉዳይ አለኝ፡፡ ሻይ ቤት መሄድ እንችላለን?”
“የሚያገናኘን የቢሮ ጉዳይ መሰለኝ፣ እዛ አልሄድም፡፡የምታወሪው ካለሽ፣ እዚሁ ማውራት ትችያለሽ፡፡”
“የቢሮ ጉዳይ አይደለም፡፡ የእኔና ያንተ የግል ጉዳይ ነው።”
“ማለት?"
“ግንኙነታችንን ማቆም ማንችልበት ነገር ተፈጥሯል፡፡ ላወራህ ፈልጋለሁ፡፡” ምን ለማለት እንደፈለገች ገመትኩ፡፡ አዞረኝ። ለቅፅበት በውስጤ ያሰብኩትን እውነት አታድርገው ብዬ ፀለይኩ፡፡ ደሜ ቀዝቅዞ
በድን ስሆን ተሰማኝ፡፡ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ፣ ቀስ ብዬ ተነስቼ እንዳለችኝ ሻይ ቤት ሄድን፡፡ ፈንጠር ያለ ቦታ መርጬ ተቀመጥኩና፣
አረገዝኩ ልትዪኝ ባልሆነ...!” አልኳት እንደተቀመጥን፡፡
“አዎ ልልህ ነው፡፡ የወር አበባዬ ከመጣ ወር አልፎታል፡፡ አርግዣለሁ፡፡”
“ስለዚህ ያንተ ነው ልትዪኝ ነው?” ዐይኔ ጨለመብኝ::
“እና ከማን ሊሆን ይችላል? ምን ማለት ፈልገህ ነው? ቆይ ግን አንተ እኔን እንዴት ነው ምታስበኝ?” ተንጨረጨረች፡፡
“ቀስ በይ አትጩሂ! ይኸውልሽ ማሂ፣ አሁን ከማን ነው ሚለውን እንርሳው፣ ያንተ ነው ካልሽኝ ግን፣ እኔ በዚህ ሰዓት አባት
ለመሆን በአቅምም በስነ ልቦናም ዝግጁ አይደለሁም፡፡”
“ስለዚህ?” ብላ አፍጥጣ ተመለከተችኝ፡፡
“ሌላው ቢቀር ያለ አባት ፍቅር ሚያድግ ልጅ ለመውለድ ባታስቢው ይሻላል። አንድ ነገር ብታደርጊ ጥሩ ነው፡፡”
“ምን?! አንተ ሰው መሳይ ሰይጣን ምን አልከኝ? አላደርገውም፡፡አላደርገውም...! የነገርኩህም ሰው መስለኸኝ ነው እሺ፡፡ እንደዚህ አይነት ጭራቅ መሆንህን አላውኩም ነበር፡፡ አባትነትህ እንጦሮጦስ መግባት ይችላል፡፡” ተስፈንጥራ ተነስታ በተቀመጥኩበት ጥላኝ ሄደች፡፡
ወደ ቢሮዬ ተመለስኩ፡፡ በህይወቴ ምን እየሆነ እንዳለ ግራ ገባኝ፡፡ በራሴ ዝርክርክነት፣ አጥምደው እየተጫወቱብኝ ነው። እራሴን ጠላሁት፡፡ እንደዛ በላዬ ላይ ስትጫወት ከርማ፣ አሁን ደግሞ እንዲህ
ትለኛለች፡፡ እውነቷንም ቢሆን፣ ወደዚህች ትርጉም አልባ፣ ጭለማ አለም ሌላ ህይወት ለማምጣት በጭራሽ ምክንያት መሆን አልፈልግም፡፡
ተሰምቶኝ ማያውቅ ጥልቅ ብስጭትና ሃዘን ወረሰኝ፡፡ ቢሮዬን ቆልፌ ወጣሁ።
ወደ ቤት ገብቼ ስልኬን አጥፍቼ፣ ለቀናት ተሸሸግሁ፡፡ ማንንም ማግኘት አልፈልግም፡፡ ወደ ስራ መሄድ ሳስብ አስፈሪ ጭንቀት ይሰማኝ ጀመር። አሁን የሚሰሙኝ ስሜቶች፣ ከዚህ በፊት ስራ ልለቅ ስል የሚሰሙኝ ስሜቶች ናቸው፡፡ መሸሽ፣ መደበቅ፣ መሸሸግ፡፡ ከዚህ ቀደም
ያጠፋሁትን ላለመድገም፣ ለራሴ የገባሁትን ቃል ለመጠበቅ፣ በመከራ
ያገኘሁት ስራ ላለመልቀቅ፣ ስራዬን እንደምንም ለመቀጠል፣ ለቀናት
ከውስጤ ጋር ታገልኩ፡፡ ግን፣ አልሆነም፡፡ አልቻልኩም፡፡ ለአራተኛ ግዜ ስራዬን መልቀቅ ግድ ሆነብኝ፡፡ ቢሮ ሄጄ፣ ቁልፍና ንብረት ለማስረከብ ምትሆን እንጥፍጣፊ ትዕግስት አልነበረኝም፡፡ መልቀቂያ እንኳን
ሳልወስድ፣ ድንገት በብስጭት እንደወጣሁ ቀረሁ፡፡ ለካ ውስጤ፣
ሳይታወቀኝ ሞልቶ ነበር፡፡ እየጠጣሁ እብሰከሰካለሁ። እብከነከናለሁ።
ሁሌም እንደዛ ነበር፡፡ “ለምድን ነው ሁሌም እኔ ላይ እንዲህ ሚሆነው?
ለምንድን ነው ነገር ሚደራረብብኝ፣ በአንዴ ሚጨልምብኝ? ምን ብረገም
ነው?”
ህይወቴን ወደኋላ መለስ ብዬ መመልከት ጀመርኩ፣ ሁሉም ጥቁርና አድካሚ ሆኖ ታየኝ፡፡ በመውጣትና በመውረድ፣ በስቃይ ብቻ የተሞላ ሆኖ ተሰማኝ፡፡ ህይወት በአንዴ ላይ ታወጣኝና መልሳ ከአፈር
ትደባልቀኛለች፡፡ እንደዚህ አይነት ህይወት ሰለቸኝ፡፡ ታከተኝ፡፡ ቢበቃኝ
ይሻለኛል ብዬ ማሰብ ጀመርኩ፡፡አዕምሮዬ “ከዚህ እስስት ከሆነ ኑሮ ሞት በስንት ጣዕሙ' አለኝ፡፡ ያስፈራል፡፡ ያስጨንቃል፡፡ እንደዛ ማሰብ አልፈልግም፡፡ ማሰቤን ግን ማስቆም አልቻልኩም፡፡ አዕምሮዬ ደጋግሞ በማስረጃ ይሞግተኛል፡፡ መሞት መፍትሄ እንደሆነ ይነግረኛል፡፡ እራሴን
ስለማጥፋት ደጋግሜ አስባለሁ፡፡ ለቀናት ምን ማድረግ እንዳለብኝ አሰብኩ። ከዚህ ከተማ መውጣት፣ መሄድ እንዳለብኝ ወሰንኩ፡፡ ቢሾፍቱን እወዳታለሁ፡፡ የነፍሴ እስትንፋስ ገመድ እዛ የተቋጠረች እስኪመስለኝ ድረስ፡፡ ሲከፋኝም፣ ስደስትም ወደሷ እበራለሁ፡፡ የሀይቆቿ የማይረበሽ፣ የማይናወጥ ውሃ፣ ተረጋግቶ ያረጋጋኛል፡፡ ለግዜውም ተረጋግቼ
ለማስብ፣ ከጥቂት አስፈላጊ ካልኳቸው እቃዎች በስተቀር ያለኝን የቤት እቃ ባገኘሁት ዋጋ ሸጬ፣ ወደ ቢሾፍቱ ለመጓዝ ተነሳሁ፡፡
ከአዳማ ከተማ ወጥቼ ትንሽ እንደተጓዝኩ፣ መንዳት አቃተኝ፡፡
በአይኔ የሞላው እንባ እይታዬን ጋረደኝ፡፡ መኪናዋን ጠርዝ አስይዤ፣ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ፡፡ አዳማን ብቻ ሳይሆን ህይወትን ተሰናብቼ እየወጣሁ እንደሆነ ተሰማኝ፡፡ በዚህ ሰዓት እንዲህ እየሆንኩ እንዳለ ሊገምት የሚችል አንድም እንኳ ሰው እንደሌለ ሳስብ፣ ሆድ እቃዬ
እስኪበጠበጥ አለቀስኩኝ፡፡ በቁሜ ለራሴ ለሞተ ሰው እንደሚለቀስ ተንሰቀሰኩ፣ በቀብሩ ማንም እንዳልተገኘ ብቸኛ ሰው ለራሴ አነባሁ፡፡ሲወጣልኝ ተነስቼ ወደ ቢሾፍቱ ሄድኩኝ፡፡ ነገሮችን እስክወስን፣ ቤት መከራየት አልፈለኩም፡፡ መለስተኛ ሆቴል አልጋ ይዤ መቆየትን መረጥኩ፡፡ ሁሉ ነገር፣ ሰልችቶኛል፡፡ አስጠልቶኛል፡፡ ቤተሰቦቼንም ጨምሮ፡፡ አሁን እነ አሌክስንም ማግኘት አልፈልግም፡፡ ስለዚህ ሌላ መዋያ ዱከም ፈልጌ አገኘሁ፡፡ ደብረዘይት ማደሪያዬ ብቻ ሆነች፡፡ ማታ ማታ አብዝቼ እጠጣለሁ፡፡ ስሰክር በለሊት ነድቼ አዲስ አበባ ሄጄ
አጨፍር አድራለሁ። ሲነጋ እንዴት እዛ እንደመጣሁ እንኳ ትዝ እስከማይለኝ፡፡ አንዳንዴም፣ እራሴን መኪና ውስጥ አድሬ አገኘዋለሁ፡፡
አንድ ቀን በመኪና አደጋ ልሞት እንደምችል አስባለሁ፡፡ እሱማ እድል
ነው፣ እንደዛማ ከሆነ እግዜር ይወደኛል እላለሁ፡፡ እራሱን አጠፋ ከምባል፣ በመኪና አደጋ ሞተ መባል በስንት ጣዕሙ ብዬ አስባለሁ፡፡ የመጠጡ ብዛት ጨጓራዬን ነካው፡፡ ስጠጣ ያስመልሰኛል፡፡ ከሚሰማኝ አስጨናቂ ስሜት ለመውጣት ከመጠጣት ውጪ አማራጭ የለኝም፡፡
አላቆምኩትም፡፡ የመጠጥ አይነት እየቀያየርኩ እጠጣለሁ፡፡በየቀኑ ዱከም እየተመላለስኩ እየቃምኩ መንገደኛ ሃሳቦችን ሳስብ እውላለሁ። በምመለከተው ነገር ድንገት በሚመጡ ሃሳቦች እነጉዳለሁ፡፡ ይመለከተኛል፤ ይጠቅመኛል፤ ሳይል አዕምሮዬ ያገኘውን
ያላምጣል። አንዱን አነሳለሁ፤ እጥላለሁ። ሲመሽ እጠጣለሁ። ካደለኝ ክፍሌ ገብቼ እተኛለሁ፡፡ መሽቶ ይነጋል፤ ሌላ ቀን፡፡ አንዳንዴ፣ ለመኖር በሚደረግ ጥረት የሚፈጠር ግርግር ለቅፅበት ቀልቤን ያዝ ያደርገኝና ስለ ኑሮ አስባለሁ፡፡ ሰዎች ለመኖር ይወጣሉ፤ ይገባሉ፤ ይጭናሉ፤
ያወርዳሉ፤ ይመጣሉ፤ ይሄዳሉ፡፡ ይህ ግርግር አንዳንዴ እንደሰመመን ይታየኛል፡፡ነገሮች ላይ ትኩረቴ በጣም ቀንሷል፡፡ እያሰብኩ የነበረውን ሁሉ ቶሎ እረሳለሁ፡፡ ጭንቅላቴ በፍጥነት ወደ ተለመደው፣ አስጨናቂ ሀሳቦች ይመልሰኛል፡፡
ዱከም ቤተኛ እየሆንኩ ነው፡፡ ባለቤቷ ጠፋህ፣ አረፈድክ ማለት ጀምራለች፡፡
ስራ ለቅቄ እዚህ ከመጣሁ ሶስት ሳምንት ሆነኝ፡፡ ማታ ስጠጣ፣ ከነ አሌክስ ጋር እንገናኝ ጀመር፡፡ ስንጠጣ ጨዋታቸው፣ ዘፈኑ፣ ጭፈራው፣ ጭጋጋማ ህይወቴን የብርሃን ጭላንጭል ይፈነጥቅልኛል፣
ቅንጥብጣቢ ደሰታ፡፡ ሲነጋ ግን፣ የተለመደው ከፍተኛ ድብርት፣ ባዶነት፣
ተስፋ ቢስነት ቦታቸውን ይረከባሉ፡፡ ቀኑን እንደምንም አሳልፈውና ማታ እነ አሌክስን እየፈለኩ ድብርቴን እዋጋው ጀመር፡፡ አሌክስ ጨዋታ አዋቂ