አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሰባት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ(MD)

...ደግሞ፣ እኔ አለሁ፤ ስለዚህ እመኑት፣ አትፍሩት። ግልጽ ነው?”በአዎንታ ጭንቅላታቸውን ነቀነቁልኝ፡፡“በጣም ጥሩ፡፡

አሁን ደግሞ እመኚው ማለት ምን ማለት
እንደሆነ ላስረዳ፡፡ ውሃ ውስጥ ጠፍጣፋ ነገር ይሰምጣል?”

“አይ፣ አያሰምጥም፡፡”

“እንደማይሰምጥ ከልብ ታምናላችሁ?”

“አዎ፣አናምናለን፡፡”

“ስለዚህ እንዳንሰምጥ ሚጠበቅብን ሰውነታችንን እንደጣውላ ጠፍጣፋ ማድረግ ነው፡፡ አይደል?”

“አዎ።”

“ቬሪ ጉድ!”

“አሁን እዩኝ! እጆቼንና እግሮቼን እንደሚንጠራራ ሰው በደንብ ውጥርጥር፣ ግትር ሳደርጋቸው፣ ሰውነታችን እንደጣውላ ይሆናል፡፡ አንሰምጥም፡፡” እንዳልኩት፣ እጆቼን ወጥሬ ዘርጋሁና ወደ
ኋላ ውሃው ላይ ተንሳፍፌ ተኛሁበት፡፡ አላሰመጠኝም፡፡ እንደ ቅጠል ተንሳፈፍኩኝ። በአድናቆትና በአግራሞት ተመለከቱኝ፡፡ልብ በሉ፣እጆቼም እግሮቼም ምንም እያደረጉ አይደሉም፡፡ ውሃውን አምነዋለሁ፡፡አናንተም እንዲህ ውሃውን ማመን አለባችሁ፡፡››
“ኧረ በጣም ያስፈራል ያቡዬ፣” ማሂ እየሳቀች ነው::

“ምን ያስፈራል፡፡ እኔ አለሁ አይደል። የመጨረሻውን ልንገራችሁና እኔ ይዣችሁ ትለማመዳላችሁ፡፡ የመጨረሻው ህግ
ውሃውን ምቺው ነው፡፡ ምን ማለት መሰላችሁ፣ ዋና መንሳፈፍ ብቻ
አይደለም፡፡ በውሀው ላይ መሄድም ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለመሄድ
ደግሞ፣ ውሀውን በእግሮቻችንና በእጆቻችን መምታት ወይም መቅዘፍ
ያስፈልጋል፤ ለምሳሌ፣” ብዬ፣ በጀርባዬ ተንሳፍፌ፣ እነሱን እያየኋቸው በእግሮቼና በእጆቼ ውሃውን እየገፋሁት ካጠገባቸው እየራኳቸው አሳየኋቸው፡፡ ለመቻል ባለ ጉጉት ውስጥ አትኩረው ይመለከቱኛል፡፡ ዋና ለመልመድ ጥሩ ፍላጎት እንዳላቸው አረጋገጥኩኝ፡፡ ወዲያው ተመለስኩና፣

“አሁን በተራ በተራ ብረቱን ትለቁትና፣ እኔ እጆች ላይ ተኝታችሁ፣ እንደነገርኳችሁ ትዋኛላችሁ፤” አልኳቸው፡፡ እንዳልኳቸው
አደረጉ፡፡ ከሶስትና አራት ሙከራዎች በኋላ ጥቂት መንሳፈፍ ቻሉ፡፡
“ኧረ ፍጥነት!” እያልኩ አበረታታኋቸው፡፡ ለቅቄያቸው ወደኔ እንዲመጡ
ጋበዝኳቸው፡፡ እያምቦጫረቁ እኔ ጋር ሲቀርቡ፣ ትንሽ እንዲሞክሩ ቀስ ብዬ እሸሻለሁ፡፡ ተንጠራርተው እላዬ ላይ ይለጠፋሉ፡፡ ዞረው እየዋኙ የመጡትን ሲያዩ፣ በደስታ ይፈነድቃሉ፡፡ ፍርሃቱ ለቋቸዋል፡፡ ቤቲ ደፋር ስለሆነች የተሻለ ቶሎ ለመደች፡፡ መላልሰው በደስታ ብዙ ሙከራዎችን አደረጉ፡፡ ሳሚ ለብቻው ሚችለውን ያህል ሲሞካክር ቆየ፡፡ ሳናስበው በጣም ደስ የሚል ቀን አሳለፍን፡፡

“እንዴት ቀላል እንደሆነ አያችሁት?”

“የምር ደስ ይላል፡፡ ሁለት ሳምንት ብንመጣ በቃ::”

“ስለዚህ አሜን አይደል፡፡”

“ኪ.ኪ.ኪ... ኧረ አሜን ነው፡፡ አሁንማ ከሳሚ አናንስም፡፡”እየተበሻሸቅን፣ እየተሳሳቅን ወደ አዳማ ተመለስን፡፡

#አልጓጓም

ዕሁድ እረፋዱ አምስት ሰዐት ነው፡፡ አዳማ ሳፋሪ ሎጅ፣ ጭር ብሏል፡፡ መዋኛ ገንዳው አጠግብ ያለ ወንበር አስተካክለን ተቀመጥን።እብድ ምሽትና አድካሚ ለሊት ነበር፡፡ የረጋውን ንፁህ የመዋኛ ገንዳ ውሃ እያየን፣ ማታ በመጠጥ የደረቀ አንጀታችንን ለማራስ፣ ለሊቱን በስሜት ልፊያ ያንጠፋጠፍነውን ሀይላችንን ለመተካት፣ ሁለታችንም ፓፓያ በማንጎ ጁስ እየጠጣን ነው፡፡ የመልካሙ ተበጀ ሙዚቃ በስሱ ተከፍቶ ይሰማል፡፡

አልጓጓም...
አልጓጓም.....
አ..ል....ጓ....ጓ...ም......አም..
አል-ጓጓ-ም........መኖር በአለም ላይ....

ጠረጴዛው ላይ ያለው የማሂ ስልክ፣
ጥዝ...ዝ...ዝ...ጥ...ዝ...ዝ..፣ እያለ ይንቀጠቀጥ ጀመር፡፡ ስልኩን ሳብ አድርጋ
የሚደውለውን ቁጥር ካየች በኋላ፣ ወደኔ ዞራ በሌባ ጣቷ አፏን ተጭና፣ዝም በል እንደማለት ምልከት ሰጥታኝ፣ ስልኩን አነሳችው፡፡

“ሄለው...” አለች በሚሞላቀቅ ድምፅ፡፡

“ደህና ነኝ፡፡”

ቁርስ እየበላሁ።”

“ደብረ ዘይት።”

“ከሰው ጋር፡፡”

“ማታውቀው ሰው፡፡”

“እንዴ ምነው የፖሊስ ጥያቄ አደረከው?” ድምፅ ሳላወጣ፣ አፌን እያንቀሳቀስኩ ማን እንደሆነ ለመጠየቅ ሞከርኩ፡፡ ጥያቄዬ ገብቷት፣ እርሷም እንደኔው በአፍ እንቅስቃሴ ብቻ፣ ማን እንደሆነ ነገረችኝ፡፡

“አሁን መምጣት አልችልም፡፡”

ማታ ወይም ነገ ነው ምመጣው፡፡” ዐይን ዐይኗን እያየሁ፣ምታወራውንና የፊቷን እንቅስቃሴ ማገናኝት እየሞከርኩ ነው፡፡ ማሂ ቆንጆ፣ ፊቷ በደስታ በርቶ በፈገግታ ነው ምታወራው፡፡

“የምመጣ አይመስለኝም፡፡”

“ነገርኩህ እኮ፣ ከሰው ጋር ነኝ፡፡” ስልኩን ላውድ ሰፒከር ላይ አደረገችው፡፡ የደዋዩ ድምፅ ይሰማኝ ጀመር፡፡

“ከያቤዝ ጋር ነሽ አይደል...?” የአለቃዬ ድምፅ...! በምልክት የነገረችኝ፣ እውነቷን ነበር፡፡ ከምፈራቸውና ከማከብራቸው አለቃዬ ጋር ነው የምታወራው፡፡ ግን፣ እንዴት ከእኔ ጋር እንደሆነች ሊገምቱ
ቻሉ...? ሰው ፈርቼ ባላውቅም፣ እርሳቸው ግን ይከብዱኛል።አከብራቸዋለሁ ሰሞኑን ባለን ሁኔታ ደግሞ የባሰ፡፡

“እንዴ...፣ እንዴት እንዲህ ልትል ቻልክ?” አሁን ድምፅ አውጥታ መሳቅ ጀመረች፡፡

“ንገሪኝ አትዋሺ! ትክክል ነኝ አይደል?”

“ያምሃል እንዴ ሃይሌ? ከማታውቀው ሰው ጋር ነኝ አልኩህ እኮ፡፡”

“እሺ፣ በጣም ደብሮኛል፡፡ ላገኝሽ እፈልጋለሁ።”

“የምመጣ አይመስለኝም፡፡ ሜሪን ካስተዋወኩህ በኋላ፣ እኔ እንዲህ አስፈልጌህ አላውቅም እኮ፡፡ ዛሬ በምን ትዝ አልኩህ?፣ የለችም እንዴ እርሷ?”

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ