አትሮኖስ
279K subscribers
109 photos
3 videos
41 files
457 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ለኀጥአን_የመጣ

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#ክፍል_ሁለት

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው


ከስዓታት በኋላ ማታሩ ጆንግ ደረስን ከ ጓደኞቻችን ገብሪላ፣ ካሎኮ እና ካሊሎ ጋር ተገናኘን። ምግብ ገዝተን ከበላን
በኋላ የተሰጣኦ ውድድር መለማመጃ ቦታውን ለማየት እቅድ ያዝን። በነ ካሊድ ቤት ጠባብ ክፍል ውስጥ ትንሽየ አልጋ ላይ አራታችን በአንድ ላይ ተደራርበን አደርን፡፡ በሚቀጥለው ቀን ጅንየር፣ታሎ እና እኔ ቤት ስንቆይ ሌሎቹ ትምህርት ቤት ሄዱ። እስከ ስምንት ስዐት ይቆያሉ ሰንል ቶሎ መጡ። ቶሊ “እንዴት ቶሎ መጣቹህ ?" ብሎ ጠየቃቸው።ገብሪላ አማጺዎች ከተማችን ሞግሚሞን ላይ ጥቃት መስንዝራቸውን ከመምህራን
እንደሰማ ነገረን :: ትምህርት ላልተወሰነ ጊዜ እንደተዘጋ ሲነግረን ደነገጥን እየሰራን የነበረውን አቆምን።

አማጺዎቹ ከስዓት በኋላ የማዕድን ቦታዎችን እንዳጠቁ ከመምህራን ሰማን። የጥይት እሩምታ ህዝቡን ወደ ተለያዩ አቅጣጫ በተነው:: አባቶች ስራቸውን ጥለው ቤታቸውን ለመጠበቅ መጡ። ቤተሰቦቻቸው የት እንደሄዱ አያውቁም።
እናቶች ልጆቻቸውን ፍለጋ እያለቀሱ ወደ ትምህርት ቤት፣ወንዞች እና የውሃ ጉድጓዶች ሮጡ። ልጆች ደግሞ በየ መንገዱ ቤተሰቦቻቸውን ይፈልጋሉ። ተኩሱ ሲባባስ ሰዎች መፈላለጉን
ትተው እግሬ አውጭኝ ሆነ! ከተማውን ለቀው ወጡ።

"መምህራን ይሄ ከተማ ቀጣይ እንደሆነ ነግረውኛል" አለ ገብሪላ ከተቀመጠበት እየተነሳ። ጅንየር ፣ታሉ እና እኔ ቦርሳችንን ይዘን ከሌሎች ጓደኞቻችን ጋር ወደ ባህር ዳርቻ ሄድን፡፡
ብዙ ሰዎች ከማዕድን ቦታዎች ወደ ባህር ዳርቻ ይተማሉ።አንዳንዶቹ የምናውቃቸው ሰዎች ነበሩ ነገር ግን ቤተሰቦቻችን
የት እንዳሉ ሊነግሩን አልቻሉም፡፡ ተኩሱ በጣም ድንገተኛ እና አስደንጋጭ ስለነበር ሁሉም የአካባቢው ሰው በድንገት እንደሽሽ ነበር ነገሩን።

ለሶስት ስዓታት ያህል ቤተሰቦቻችን ይመጣሉ ወይም ያሉበትን የሚያውቅ ሰው ይመጣል ብለን በጭንቀት በወንዙ
ዳርቻ ላይ ቆየን። ነገር ግን ምንም ወሬ የለም፡፡ የውሃ ሽታ ሆኑብን! ቀኑ አንዳች ጉድ ያላየ የተለመደ ቀን ይመስላል።
ፀሐይዋ በነጩ ጉም ላይ ትንሳፈፋለች፣ ወፎች በዛፎች ጣሪያ ላይ ሁነው ይዘምራሉ ዛፎችም በለሆሳስ ንፋስ ይወዛወዛሉ።
ማመን አልቻልኩም! ጦርነቱ በዚህ ፍጥነት ቤታችን ይደርሳል ብየ አልገመትኩም:: በፍጽም! ትናንት ከቤት ስንወጣ አማጺዎቹ ከኛ ቅርብ መሆናቸውን የሚያሳይ አንድም ምልክት
አልነበረም::

"ምንድን ነው የምናድርገው?" ሲል ገብሪላ ጠየቀ፡፡ ለተወሰነ ጊዜ ሁላችንም ዝም አልን። በኋላ ቶሊ "ወደ ቤት እንሂድ፤ ሳይመሽ ቤተሰቦቻችን እንፈልጋቸው" አለ፡፡ ጅንየር እና እኔ ራሳችንን በመነቅነቅ ስምምነታችንን ገለጸን፡፡

ከሶስት ቀናት በፊት አባቴን በዝግታ እየተራመደ ከስራ ሲመለስ አይቸዋልሁ:: ባርኔጣውን በእጆቹ መሐል ይዟል ፤
ረጂም ፊቱ በጋለ ፅሐይ ተመቶ በላብ ተጠምቋል:: በቤቱ ደጃፍ ላይ ነበርኩ:: ካየሁት ቆይቻልሁ። 'ምስጋና ለእንጀራ እናቴ በእኔና በሱ መሃል የነበረውን ግንኙነት አበላሽታዋለች። ያን ቀን
ግን አባቴ ወደ ቤቱ ደረጃ ሲደርስ ፈገግ ብሎ አየኝ። ፊቴን፣ መላ ሰውነቴን አትኩሮ ተመለከተ። የእንጀራ እናቴ ስትመጣ ፊቱን
አዞረ፤ ከዛ ወደ እሷ ተመላከተ። ትንሽ ቆይቶ ወደ ውስጥ ገባ። እንባየን ቋጥሬ ወደ ጁንየር ሮጥኩ። ወደ እናታችን ቤት
ለመሄድ ዝግጅት ላይ ነበርን። በፊት አባታችን የትምህርት ክፍያ በሚከፍልን ጊዜ እናታችንን ከባዕላት በተጨማሪ በየሳምንቱ እንጠይቃት ነበር፡፡ አሁን አባታችን አልከፍልም ስላለ ትምህርት
ቤት የለም ስለዚህ በየሁለት እና ሶስት ቀናት እንጠይቃታለን::

ያን ቀን ከስዓት በኋላ እናታችንን አስቤዛ እየገዛች ገበያ ቦታ አገኘናት:: ደክሟት ፊቷ ከስሉ ዳምኖ ነበር። እኛን ስታየን
ስታቅፈን ግን በቅጸበት ፊቷ በራ። ታናሽ ወንድማችን ኢብራሂም ትምህርት ቤት እንደሆነ እና ስንመለስ እንደምናገኘው
ነገረችን። እጃችንን ይዛ ወደ
ኢብራሂም ትምህርት ቤት መራመድ ጀመርን፡፡

እናታችንን ፊትዋን ወደ እኛ አዙራ "ይቅርታ ልጆች በቂ ገንዝብ ስለሌኝ ነው እናንተን ወደ ትምህርት ቤት ያልመለስኳችሁ። እየጣርኩ ነው።” አለች፡፡ ከዛ ትንሽ ቆይታ
”አባታችሁ እንዴት ነው?” ስትል ጠየቀች::

"ደህና ይመስላል፡፡ ዛሬ አይቸው ነበር።" አልኩ
ጅንየር ምንም አልተናገረም:: ዝም አለ።

እናቴ ጅንየርን ትኩር ብላ አይን አይኑን እያየች” አባትህ ጥሩ ሰው ነው፤ በጣም ይወድሃል። መጥፎ እንጀራ እናቶች
ስለሚገጥሙት ነው” አለች::

ትምህርት ቤት ስንደርስ ትንሹ ወንድሜ ኳስ እየተጫወተ ነበር፡፡ ስምንት አመቱ ነው:: ልክ ሲያየን እየሮጠ መጥቶ ተጠመጠብን፡፡ በቁመት በልጦኝ እንደሆነ ለማወቅ ከእኔ ጋር ለማነጻጸር ሞከረ፡፡ እናቴ ሳቀች:: የትንሹ ወንድሜ ትንሽ ክብ
ፊት በራች፡፡ ሁላችንም ወደ ቤት ሄድን። ትንሹ ወንድሜ እጁን ይዥ ስራመድ ስለ ትምህርት ቤት አወራኝ፤ ማታ ደግሞ
ኳስ ተጫወትን፡፡ እናቴ ሁሉን ነገሯዋን ለኢብራሂም ሰጥታለች፣
ብቻዋን እሱን ትንከባከባለች ። ኢብራሂም አንዳንዴ ስለ አባቱ እንደሚጠይቅ ነገረችን፡፡ አባቱን እንዲያይ የተወሰኑ ቀናቶች ወስዳዋለች። ሁለቱ ሲገናኙ አባቱ ኢብራሂምን ሲያቅፈው ስታይ
ግን ታለቅሳለች። ሁለቱም በጣም ደስተኛ ይሆናሉ ትላለች፡፡በሃሳብ ትወሰዳለች::

ከዛ ጥየቃ ሁለት ቀናት በኋላ ከቤት ወጣን። አሁን ማታሩ ጆንግ ባህር ዳርቻ ላይ ቁመናል። አባቴ ባርኔጣውን በእጆቹ ይዞ ከስራ በሩጫ ሲመለስ በአይነ ሕሊናየ ይታየኛል። እናቴም ስታለቅስ ወደ ትንሽ ወንድሜ ትምህርት ቤት ስትሮጥ በአይነ ህሊናየ ተመላለስ፡ የፍርሃት ስሜት ተቆጣጠረኝ፡፡

ጅንየር፣ታሎ እና እኔ ወደ ጀልባ ዘለን ገባን ፤ በድንገት ጀልባው ሲንቀሳቀስ ለጓደኞቻችን እጆቻችንን አውለበለብን።
ጀልባዋ ከማታሩ ጆንግ ይዛን ወጣች:: በወንዙ ሌላኛው ጫፍ ደርሰን መሬት ስንረግጥ ብዙ ብዙ ሰዎች ሸሽተው እየመጡ ነበር፡፡ መጓዝ ስንጀምር ነጠላ ጫማ ራሱዋ ላይ የተሽከመች ሴትዮ እኛን ሳታየን መናገር ጀመረች" የምትሄድበት ቦታ ብዙ ደም ፈሶበታል። መልካሙ መንፈስ እንኳ ሸሺቷል ”እያለች
አልፋን ሄደች:: በወንዙ ዳር ባለው ጫካ የብዙ ሴቶች ደምጽ ይሰማል። ” ጌታ ሆይ እርዳን” የልጆቻቸውን ስሞች ይጠራሉ፡
የሱፍ፣ጃቡ፣ ፎዳይ..." ልጆች ብቻቸውን ሲጓዙ ፤ በተቀደደ ልብስ አንዳንዶቹ ያለ ውስጥ ሱሪ ”እናቴ” ፣ ”አባቴ” እያሉ
ሲጣሩ ፤ ውሾችም በህዝቡ መሃል ሲሮጡ ፤ ባለቤታቸውን ሲፈልጉ ስናይ ፈራን :: የደም ስሬ ተገታተረ፡፡

ከስድስት ኪሎ ሜትር በኋላ ከአያቴ ሰፈር ካባቲ ደረስን፡፡
ኦና ሁኗል። ከሰፈሩ እስከ ማዶ ያለው ጫካ የተዘረጋው የሰዎች ዱካ ብቻ ይታያል።

ምሽቱ ሲቃረብ ግን ብዙ ሰዎች ከማዕድን ቦታ መምጣት ጀመሩ። የጠንቋዮች ፣ በጉዞ ወላጆቻቸውን በመፈለግ የደከሙ
ና የራባቸው ልጆች ለቅሶ የምሽት ወፎች እና የዶሮዎች ዝማሬ የተካው ይመስላል። በአያቴ ቤት ደጃፍ ተቀምጠን መጠበቅ ማዳመጥ ጀመርን።

ትክክል ነን ግን፧ ወደ ማግቦ መመለስ ጥሩ ሃሳብ ነው ትላላቹህ?” ሲል ጅንየር ጠየቀን። ከመመለሳችን በፊት ግን
ቮልስዋግን ጩህት ሲሰማ ሁሉም ሰው ወደ ጫካው መሮጥ ጀመሩ። እኛም መሮጥ ጀመርን ብዙም ግን አልራቅንም። ልቤ መታ፤ ትንፋሼ ጨመረ፡፡ መኪናው አያቴ ቤት ፊት ለ ፊት ቆመ። አሽከርካሪው አልታጠቀም። ከመኪናው ወጥቶ ደም
መትፋት ጀመረ። እጁ ደም በደም ሁኗል። መትፋቱን ሲያቆም ማልቀስ ጀመረ። አዋቂ ሰው እንደ ህጻን ልጅ ሲያለቅስ
ለመጀመሪያ ጊዜ
👍2
#ለኀጥአን_የመጣ

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#ክፍል_ሶስት

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው

የምታውቅ ይመስላል።

..ቀጥሎ በጥይት የተበሳሱ ወንዶች እና
ሴቶች መጡ፡፡ አንዳንዶቹ ሰዎች እንደ ቆሰሉ እንኳ አያውቁም ነበር፡፡ አንዳንዶቹ ራሳቸውን ሳቱ ሌሎቹ ደግሞ አስታወኩ። አቅለሸለሸኝ ራሴም ዞረብኝ መሬት ሲሽከረከር ፤ የሰዎች ድምጸ ሩቅ ሁኖ ይሰማኛል።

በቀኑ መጨረሻ ያየነው ሌላው ጉዳት በጀርባዋ ህጻን ልጅ ያዘለች አንዲት ሴት ናት። ደም በልብሷ ከላይ እስከ ታች
ወርዶ በጀርባዋ መስመር ሰርቷል። ልጆዋ በጥይት ተመቶ ሙቷል። ቁማ ልጅዋን አውርዳ አስቀመጠቻት። በኋላ ወደ
ልጅዋ ቀርባ ወዘወዘቻት። በብዙ ስቃይ እና ድንጋጤ ውስጥ ስለነበረች አለቀሰች።

ጅኒየር፣ታሎ እና እኔ ተያየን ወደ ማታሩ ጆንግ መመለስ እንዳለብን ገባን። ማግቦ ከእንግዲህ ቤታችን እንደማይሆን ወላጆቻችንንም ከዛ ሊሆኑ እንደማይችሉ
ተገነዘብን፡፡ አንዳንድ የቆሰሉ ሰዎች ካባቲ ቀጣይ የአማጺዎች መዳረሻ እንደሚሆን ይናገራሉ። አማጺዎች እንዲያገኙን
አንፈልግም:: በደንብ መራመድ እንኳ ማይችሉ ሰዎች ከካባቲ ለመውጣት የቻሉትን ሁሉ እያረጉ ነው:: ወደ ማታሩ ጆንግ ስንመለስ የዛች ሴትዮዎ እና የልጅዋ ሁኔታ አእምሮየን አስጨነቅው:: ጉዞው ብዙም አልተሰማኝም። ውሃ ጠምቶኝ ጠጥቼ እንኳ ምንም ጥሩ ስሜት ሊሰማኝ አልቻለም፡፡ ያቺ ሴት
ወደመጣችበት መመለስ አልፈልግም ፤ ሁሉም ነገር እንደጠፋ የልጅዋ አይን ይናገራል።
"አንተ ነጌትቭ አስራ ዘጠኝ አመትህ ነው” ይለኝ ነበር ባባ።አባቴ ከ ነጻነት በኋላ በ1961 የሴራሊዎን ሕይወት ምን
እንደምትመስል ስጠይቀው ሁሌም መልሱ ይሄ ነበር፡፡ ምኑ ይገባሃል የሚል ምፀት ያለው መልስ! ከ1808 ዓ/ም ጀምሮ ሴራሊዮን የብሪታንያ ግዛት ነበረች::

ሚልተን ማርጋይ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስቴር በመሆን የሴራሊዮንን ህዝብ ከዚህ አለም በሞት እስከ አረፈበት 1964 ድረስ ሃገሪቱን መርቷል::
ወንድሙ አልበርት ማርጋይ እሱን ተከትሎ እስከ 1967 ማለትም በሲያካ ስቲቨን በምርጫ እስከ ተሸነፍበት ደረስ መምራት ቻለ፡፡ ሲያካ ስቲቨን ወዲያው መፈንቅለ መንግስት ቢያጋጥመውም በ1968 እንደገና ወደ ስልጣን ተመለሰ። ከብዙ
አመታት በኋላ ሃገሪቱ የአንድ ፓርቲ ብቻ ሃገር እንደሆነች አወጀ:: የሁሉም ህዝቦች ኮንግረስም የሃገሪቱ ብቸኛው ህጋዊ
ፓርቲ ሆነ። የ”ፖለቲካው መበላሸት የሚጀመረው ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው ይል ነበር አባቴ።ስለዚህ ጦርነቱ ምን እያለ ይሆን?! አዋቂዎች አቢዮታዊ ጦርነት እንደሆነ እና ህዝቡን ከሙሰኛ
መንግስት ነጻ ለማውጣት የ ሚደረግ ጦርነት እንደሆነ ሲያወሩ ሰምቻለሁ፡፡ የትኛው የነጻነት እንቅስቃሴ ነው ንጹሃንን ህጻናትን የሚገድል? ይህንን የሚመልስ ማንም የለም::ባየሁት ነገር ልቤን ይከብድዋል ያስጨንቀኛል!
የሚታየውን ተራራ ዱሩን ሁሉ ፈራሁ።

በጣም ከመሽ ማታሩ ጆንግ ደረስኩ፡፡ ጅኒየር ና ታሎ ያየነው አስከፊና አስቃቂ ክስተት በሙሉ ለጓደኞቻችንን ነገሩዋቸው። እኔ ግን ያየሁትን ማመን ስላልቻልኩ ዝምታን መረጥኩ። ማታ ማንቀላፋት ስጀምር በህልሜ ጎኔን በጥይት ተመትቼ ቆስዬ ሰዋች ምንም ሳይረዱኝ የራሳቸውን ህይወት ለማትረፍ አልፈውኝ ሲሮጡ አየሁ።

ተንፏቅቄ ወደ ዱር ለመግባት ስሞክር ከየት እንደመጣ የማይታወቅ ሰው ራሴ ላይ መሳሪያ ደቅኗል። ተኮሰ፡፡ባትቼ ከእንቅልፌ ተነሳሁ፡፡በጥርጣሬ ጎኔን ነካሁ። ፈራሁ! ህልም እና እውነታን መለየት ስላቃተኝ ፈራሁ።

ሁሌም ጥዋት ጎህ ሲቀድ ስለ ቤተሰቦቻችን ወሬ ካለ ለመስማት ወደ ማታሩ ጆንግ ባህር ዳርቻ እንወርዳለን።
ከሳምንት በኋላ ወደ ማታሩ ጆንግ የሚመጡ ስደተኞች ቁጥር ቀነሰ። ስለ ቤተሰቦቻችን ምንም ወሬ የለም። ድጋሚ የውሃ ሽታ ሆኑብን! የመንግስት ወታደሮች በማታሩ ጆንግ ተሰማርተው ኬላዎችን በባህር ዳርቻ እና በከተማው ዋና ዋና አቅጣጫዎች አቁመዋል::

ወታደሮቹ ከባድ መሳሪያዎችን አዘጋጅተው አማጺዎቹን ለመምታት ይጠባበቃሉ። አማጺዎቹ በባህር ዳርቻው በኩል እንደሚመጡ ገምተዋል። ህዝቡ በጊዜ እንዲገባ የስዓት እላፊ ከምሽቱ አንድ ስዐት በኋላ መንግስት አውጇል። ከባድ ምሽት ነበር፤ መተኛት አልቻልንም:: ሁላችንም በጊዜ ተሰባሰብን ከበን
ማውራት ጀመርን፡፡

ይሄ ነገር፦ ይሄ እብደት መቼ ይሆን የሚያበቃው? "በጥቂት ጊዜ ውስጥ የሚያበቃም አይመስለኝም፡፡" አለ ጅኒ የር ”ምን አልባት ለአንድ ና ሁለት ወር ይቆይ ይሆናል።” አለ ታሎ ጣሪያ ጣሪያ እያየ።

ገብሪላ ደግሞ ወታደሮች አመጺዎችን ከማዕድን ቦታ ለማባረር እየገሰገሱ እንደሆነ ሰምቻለሁ አለ። ጦርነቱ ወደ
የፍጻሜው ምዕራፍ ላይ እንዳለ እና ከሶስት ወር በላይ እንደማይቆይ ተማመን፡፡
ጅኒየር፣ታሎ እና እኔ ነገሮችን ለመርሳት ራፕ ሙዚቃ ማደመጥ ጀመርን፡፡ የ ሙዚቃ ካሴቶች እና ልብሶቻችንን ብቻ
ይዘን ነበር ከቤት የወጣነው:: ከቤት ደጃፍ ላይ ተቀምጨ Now That We Found Love ” ፍቅርን አሁን አገኘነው” የሚለውን የሄንሪ ዲ እና ዘ ቦይዝ ሳዳምጥ ትዝ አለኝ ። አይኔን ጨፈንኩ። ካባቲ ያየሁዋቸው አሰቃቂ ነገሮች ሁሉ
በአዕምሮዬ መጡ። ምስሎቹን ከአዕምሮዬ ለማውጣት የድሮውን
በሰላሙን ጊዜ የነበረችውን ካባቲ ማሰብ ጀመርኩ።

በአያቴ መንደር ባንድ በኩል ጥቅጥቅ ያለ ደን ሲኖር በሌላው ደግሞ የቡና እርሻ ነበር፡፡ በጫካው በኩል የሚመጣው ወንዝ ሰፈሩ ዳር፣ በወይራ ዛፎች አደርጎ ወደ ረግረጉ ይገባል። ከረግረጉ በላይ የሙዝ ማሳው እስከዛኛው አድማስ ይታያል። ብዙ ሰው ከቤቱ ጀርባ የማንጎ ዛፎች አለው።

ጥዋት ከጫካው በስተጀርባ ፅሐይ ትወጣለች። መጀመሪያ ጨረሯ በቅጠሎች መሃል ያልፋል። ከዛ አውራ ደሮ ይጮሃል፤ ድንቢጥ ወፎች በዝማሬ አዲስ ቀንን ሲያውጁ ወርቃማ ፅሐይ
ከጫካው ራስ ላይ ጉብ ብላ ትታያለች። ምሽት ላይ ዝንጀሮዎች ወደ ማደሪያቸው ለመመለስ ከዛፍ ዛፍ ሲዘሉ ይታያል። በቡናው ማሳ ደሮዎች ጫጩቶቻቸውን ከጭልፊት ይሸሽጋሉ። ከማሳው
ወዲያ ማዶ ደግሞ የወይን ዛፎች በንፋስ ሲወዛወዙ ይታያል።
አንዳንዴ የወይን ፍሬ ለቃሚ ዛፎች ላይ ወጥቶ ይታያል።
ምሽቱ በዛፎች ውዝዋዜ ድምጽ ( ቀ ቀ ቀ ቀ ) እና በሩዝ መውቀጥ ድምጽ (ድው ዱ ዱ) ታጂቦ ይገባደዳል። ድምጹ በመንደሩ ያስተጋባል። ወፎች በጥንቃቄ እንዲበሩ፣ ዶሮዎች፣እንቁራሪቶች ጉጉቶችም ወደ ማደሪያቸው እንዲመለሱ ያደርጋል። የመንደር ሰዎች ፋኖስ ወይም የተቀጣጣለ እንጨት እያበሩ ከ እርሻ ማሳቸው ይመለሳሉ፡፡

"እንደ ጨረቃ ለመሆን እንትጋ” ይላል አንድ ሽማግሌ ሰውየ ውሃ ሲቀዳ፣ ለአደን ሲሄድ ወይም የወይን ፍሬ ዛፎቹ ላይ ሲቆርጥ። አንድ ቀን አያቴን ምን ማለት እንደሆነ ጠየኳት። አባባሉ ሰዎች ሁሌም ጥሩ እንዲሆኑ እና ለሌሎች መልካም እንዲሆኑ ያስታውሳል። ስዎች የፅሐይን ግለት ፤ ከባድ ዝናብን እና ብርድን ያማርራሉ። ነገር ግን ጨረቃ ስትወጣ
ማንም አያጉረመርምም፡፡ ሁሉም ደስተኛ ነው፤ እንደየራሳቸው ሁኔታ ጨረቃን ያደንቃሉ። ህጻናት ጥላቸውን ያያሉ፤ ሰዎች ተሰባስበው ይጫወታሉ ለሊቱን በጭፈራ ያሳልፋሉ። ጨረቃዋ
ስታበራ ደስታ ይሆናል። ለዛ ነው እንደ ጨረቃ ለመሆን የምንተጋው።
።።
አየሩ ደም ደም እና የተቃጠለ ስጋ በሚሸትበት ከተማ መሐል የዛገ ካሬታ እየገፋሁ ነበር። : ንፋሱ የሲቃ ድምጾችን ያመጣል::
ተመሰቃቅለው በወደቁ ሬሳዎች መካከል ሳልፍ እጃቸውን እና እግራቸውን ያጡ ሰዎች፤ ሆዳቸው ውስጥ ቅልሃ ገብቶ
አንጀታቸው የተዘረገፈ እና በአፍንጫቸው በጆሮቻቸው ደም የፈሰሳቸውን አየሁ። በራሪዎች
👍2🥰1