አትሮኖስ
286K subscribers
117 photos
3 videos
41 files
566 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሮዛ_2


#ክፍል_ሀያ_ሶስት( 🔞)
(የመጨረሻ ክፍል)


#የሰው_ ልጅ_ዓለምን_ አትርፎ #ነፍሱን_ቢበድል....

ቤይሩት፣ ራፊቅ ሀሪሪ አየር መንገድ

አርብ ሌሊት

በምድር ላይ እጅግ ከምጠላቸው ሕዝቦች መሀል እገኛለሁ፤ ሊባኖስ ቤይሩት አየር መንገድ ውስጥ፤
ወደ አቡዳቢ ለመብረር። አየርመንገዱ በአረቦች ታፍኗል። አረብ አረብ ይሸታል። የተቀቡት ሽቶ አልተስማማኝም፤ እነሱን እንዲህ በጅምላ ማየት ራሱ ያቅለሸልሻል። አመመኝ።

ክትፎ የሚወድ ሰው ጣባውን ሲከፍተው የሚዝለገለጉ ትላትሎች ታጭቀው ቢያይ ሊሰማው የሚችለው ስሜት እኔ አረቦችን እንዲህ ብዙ ሆነው በማየቴ ተሰምቶኛል። አዲስ አበባ በተናጥል አገኛቸው ስለነበር
ለነሱ ያለኝ የጥላቻ ስሜት የዛሬውን ያህል አልበረታብኝም ነበር። አሁን አንድ ሙሉ ተርሚናል በሺ በሚቆጠሩ አረቦች ተሞልቶ ብመለከት ምግብ አልረጋ አለኝ። አመመኝ።

ከአረቦቹ መሀል ብዙ መልካምና ደጋግ ሊኖሩ እንደሚችሉ እረዳለሁ፤ የበርካታ ሺህ ወገኖቼ ህይወት በነሱ ላይ እንደተመሰረተም አውቃለሁ፤ ወላጅ አልባ ህጻናት የሚያሳድጉ ደጋግ አረቦች ብዙ አሉ፤ ይህንንም አልከድም። በሀገሬም ሆነ በሀገራቸው ከወገኖቼ ጋ ፍቅር መስርተው የወለዱና የከበዱ አረቦች
እንዳሉም አልክድም።ለወደዱት ሰው ቤት ንብረታቸውን በሙሉ የሚሰጡ፣ ሀበሻ ሰራተኞቻቸው ሲታመሙ ሚሊዮን ብር ከስከሰው ያሳከሙ አረቦች እንዳሉም ከዚያ የተመለሱ ጓደኞቼ ሲያወሩ
ሰምቻለሁ። እርግጥ ነው፤ የትኛውም ህዝብ ሰናይና እኩይ ሰዎች አሉት፤ አረቦቹም ከዚያ የተለዩ እንዳልሆኑ ጠንቅቄ አውቀዋለሁ።ይህን ሁሉ እየተረዳሁ ግን ለአረቦች ስር የሰደደ ጥላቻ ደሜ ዉስጥ ገብቷል፤ ምን ላድርግ?

ህሊናዬን በብርቱ ከፈተነ ማሰላሰልና መብሰልሰል በኋላ የህይወቴ ቀጣዩ ምእራፍ በአረብ ምድር እንዲሆን ወሰንኩ። በተባበሩት ኢምሬትስ ርእሰ መዲና አቡዳቢ ሬስቶራንትና የውበት ሳሎን ያላትን የአብሮ አደጌን የቢዝነስ አጋርነት ግብዣ ለአመታት አሻፈረኝ ብልም ሰሞኑን ውሳኔዬን ከብዙ የአእምሮ
ጂምናስቲከ በኋላ ቀየርኩ፤ ከዚህ በኋላ እንዴትም ብዬ የህይወት አቅጣጫዬን መለወጥ እንዳለብኝ ተሰምቶኛል።

#ተርሚናሉ_ዉስጥ
.
አረብ ወንዶች ያለመጠን የተርከፈከፉት ሽቶ ራሴ ላይ ወጣ። ተርሚናሉ ዉስጥ እየተዝለገለጉ ወዲያ ወዲህ ሲሉ ሆዴ ታወከ። መታጠቢያ ቤት ሄጄ ፊቴን በቀዝቃዛ ዉኃ ነከርኩ። ትንሽ ሻል ያለ
ስሜት ሲሰማኝ በወርቅ የተለበጠ ከሚመስል አግዳሚ ወንበር ላይ አንድ ጥግ ይዤ አረፍ አልኩኝ።
ለጊዜው በዙርያዬ የሚሆነውን ከማየት ዉጭ ሌላ እድል አልነበረኝም። አይኔን ብጨፍንም አረቦችን አያለሁ። አይኔን ብገልጥም አረቦችን አያለሁ። አማራጭ አልነበረኝም። ለካንስ አይንን መጨፈን ማየት የሚፈልጉትን ከማየት አይጋርድም። ዳያሪዬን ከእጅ ቦርሳዬ ዉስጥ ብታቀፈውም አእምሮዬ ባልተለመደ ሁኔታ ደንዝዞብኛል። በአየር መንገዱ አግዳሚ ቁጭ ብዬ ወጪ ወራጁን ስሜት አልባ ሆኜ አያለሁ።
የአረብ ጎታታ ወንዶች፣ በዚያ በሚዝለገለግ ነጭ ቀሚሳቸው ዉስጥ ሆነው አውሮፕላን ለመሳፈር እንደ
ግመል ይጎተታሉ። የቀሚሳቸው መጎተት ላያንስ በሩዝ የተወደረ ከርሳቸውን ይጎትታሉ፤ የከርሳቸው ሳያንስ ኩንታል ሻንጣቸውን ይጎትታሉ። የሻንጣቸው ሳያንስ ነጠላ ጫማቸውን ይጎትታሉ፤ የነጠላ ጫማቸው ሳያንስ ከረፈፍ ሚስቶቻቸውን ይጎትታሉ፣ የሚስቶቻቸው ሳያንስ ያልተቆነጠጡ አስራ ምናምን ልጆቻቸውን ይጎትታሉ። አራት ሚስቶቻቸውን እየነዱም ቢሆን አምስተኛ ሴት ከማየት አይመለሱም። ከአንድም ሁለት ሦስት አጁዛ አረቦች ከወዲያኛው የተርሚናሉ ሬስቶራንት ሆነው

እየሰረቁ ሲመለከቱኝ ዐይቻለሁ፡፡

በድጋሚ መታጠቢያ ቤት ሄጄ ተመለስኩ። ዛሬ ምግብ አልረጋ ብሎኛል።

ቀልቤ አይወዳቸውም። በተለይ እንዲህ ነጭ ቆብ በነጭ ቀሚስ ለብሰው ሳያቸው፣ በነጭ ኩባያ ወተት ከአናታቸው እየፈሰሰባቸው ስለሚመስለኝ የዝንብ አየር ማረፍያዎች እንጂ ሰዎች ሆነው አይታዩኝም።ሰው ነጭ ለብሶም ንፁህ ሆኖ ካልታየኝ መቼስ የሆነ ችግር አለበት ማለት ነው። ለምንድነው ፈጣሪ እኛን
ድሐ እነሱን ሐብታም ያረገው? እግዜር ምናቸው ማርኮት ይሆን አሻዋቸውን የባረከው? በረሃቸውን ያረጠበው?!

“የአረብ ጥላቻ የተፈጠረብኝ መቼ ነው?” ብዬ ለማስታወስ ሞከርኩ። ትዝ የሚለኝ ነገር የለም። ምናልባት ኡስማን ዘ ፒምፕ ስለሚጠላቸው እሱ ሳያውቀው አጋብቶብኝ ይሆን? አይደለም። ኡስማንን
ሳላውቀው በፊት አረብ የሚባል ፍጥረት ያስጠላኝ ነበር። ልጅ እያለሁ የጀመረኝ ይመስለኛል። አያቴ በነበረችበት ሰፈር። ባደኩበት ሰፈር፣ በነእማማ ዙበይዳ ሰፈር።

ልጅ እያለሁ ለተወሰነ ጊዜ ሴት አያቴ ታሳድገኝ ነበር። በሰፈራችን የምንወዳቸው፣ እማማ ዙበይዳ
የሚባሉ ሴት ነበሩ። የሆኑ ደርባባ አሮጊት ሴትዬ። ሰው ዝም ብሎ ይወዳቸው ነበር። ጎመን መንገድ ላይ ይሸጣሉ። በክረምት ደግሞ በቆሎ ይሸጣሉ። እማማ ዙበይዳን ሰፈሩ ሁሉ ለምን ይወዳቸው እንደነበር ግን በትክክል አላውቅም። እኔም እወዳቸው ነበር። ለምን እንደነበር ግን አላውቅም። “ነይ እስቲ አንቺ
ጎራዳ!" እያሉ ግንባሬን ይስሙኝ እንደነበር ብቻ ነው ትዝ የሚለኝ።

እማማ ዙበይዳ ባልም ዘመድም የላቸውም። በምድር ላይ ያለቻቸው ፋጤ ቀጮ ናት። የሳቸው ብቸኛ ልጅ ፉጤ ቀጮ ጅዳ ሄደች ተባለ። ሰፈሩ ሁሉ እማማ ዙበይዳ በቃ ሻሩ፣ አሁን ወርቅ በወርቅ ሊሆኑ ነው ብሎ ተነበየ። እሳቸውን ያገኘ ሰው ሁሉ “ፋጤ ቀጮ ጅዳ ነው አይደል የሄደችው?”፣
ትደውላለች”፣ “ደህና ናት ታዲያ፣ “አሁን ለመድኩ አለችፖ፣ ግህም፣ “በርቺ በሏት እንግዲህ!
ይለመዳል.ይለመዳል”፣ “ዋናው መበርታት ነውታዲያ”፣ “እ!” እያለ ከእማማ ዙበይዳ የበቆሎ እሸት
ወይ ጎመን ገዝቷቸው ያልፋል። በበጋ ጎመን በከረምት የበቆሎ እሸት በመሸጥ ነበር የሚተዳደሩት።
በዚያ ሁሉ የሰፈር ሰው ሳይታክቱ በዚያ እናታዊ ፈገግታቸው ታጅበው ስለ ልጃቸው ደኅንነት ምላሽ ይሰጣሉ። “እላሙዲሊላ አላሂ ወላሂ ደህና ናት!ዱዋ አርጉላት." ይላሉ፤ መልሰው መላልሰው።

ሲኖሩ ሲኖሩ.…የሆነ ጊዜ ላይ ልጃቸው ስልክ ደውላ አለቀሰች ተባለ። “ምን ሆንሽ” ሲሏት አትናገርም
ሲኖሩ ሲኖሩ…የሆነ ጊዜ ላይ ደግሞ መደወል አቆመች ተባለ። ደህንነቷን የሚነግራቸው ጠፋ። ጎመን ወይ
በቆሎ ለሚገዛቸው የሰፈር ሰው ሁሉ “አረብ አገር ስልክ ማድረግ ታውቅበታለህ?” እያሉ ይጠይቃሉ።
የተማረ የሚመስል ወጣት ሲመለከቱ ደግሞ “ልጄ! እስኪ ባክህ የጅዳ ስልክ ቁጥር ጽፈህ አምጣልኝ? ልጄ ናፈቀችኝ ይሉታል። የሷ ስልክ ቁጥር ግን የላቸውም። አንዳንድ ሰው ነገሩን ሊያስረዳቸው ሞከረ።ኾኖም ሊገባቸው አልቻለም። የሰፈሩን ሰው መሄጃ መቀመጫ አሳጡት። እርስዎ ስልኳን ፈልገው ያምጡ! እኛ እንደውልሎታለን” ሲባሉ እኔ ቁጥሯን ከየት አዉቄ” ነው መልሳቸው። እሷ ካልደወለች
እሳቸው ወደየት ብለው ይደውላሉ? አድራሻዋ አይታወቅ ነገር።

የሰፈሩ ሰው በሙሉ እማማ ዙበይዳ ሲያዝኑ አይቶ አዘነ። እማማ ዙበይዳ የደግነት ምሳሌ ነበሩ። ፋጤ
ቀጮ እጅግ ስትናፍቃቸው ግን ሰው ሰላም ሳይሉ ማለፍ ሁሉ ጀመሩ። የሚሸጡት ጎመን ጠወለገ።
ወዲያው ደግሞ ወገባቸው ጎበጠ። ከመቼው በእድሜያቸው ላይ ምዕተ ዓመት እንደጨመሩ። ሰው የልጁ ናፍቆት እንደ ኤድስ አመንምኖ ሊገድለው እንደሚችል ያየሁት በእማማ ዙበይዳ ነው።

ከ5 ዓመታት በኋላ ልጃቸው ፋጤ መጣች ተባለ። በዊልቸር ላይ ሆና። በጣም ከመወፍሯ የተነሳ ዊልቸሩ ጠበባት። ፋጤ ቀጮ ትባል የነበረችው የሆነች ሲንቢሮ በረሮ ስለበረች ነበር።ታዲያ ለምን ወፈረች? ተስማምቷት ነበር ማለት ነው?
👍4
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#በክፍለማርያም

...ወደ ሆስፒታል ገሰገሰች
ፍፁም የህክምና ሰወች ተረባርበዉ ትንሽ ነብሱ መለስ አለች
ህመሙን የሚቀንስ መድሀኒት ተሰጥቶት ከዋጠ በኋላ
ከትራሱ ጋር ድጋሜ ጭንቅላቱን አገናኘዉ
እንደ ህመም ከባድ ወቅት የለም በጤነኝነት ስንኖር ዋጋ ሰጥተን
ባናስበዉም ስንታመም እና ስቃይ ዉስጥ ስንሆን ግን ሁሉ ነገራችን ተወስዶ ጤናችን ቢመለስ እንለምናለን
አብዛኞቻችን ለጤናችን አስበን አናዉቅም ጥንቃቄም የለንም
ምኞታችን ብር ላይ ያተኮረ ይሆናል ይለፋል ይለፋል በስተመጨረሻ ጤና ጠፍቶ ስንሰቃይ በህመም እጅ ዉስጥ
ስንወድቅ ብራችንን በሙሉ ለጤናችን መልሰን እናዉላለን
እንደ ፍፁም በአደጋ ህመም ላይ ሲወደቅ ግን ምን ይደረጋል
ሳያስበዉ እና ሳይጠብቀዉ ለዚህ በቃ የዚህ ሁሉ ጦስ ደግሞ
የፍቃዱ ተንኮል በተጨማሪም የቤዛዊት ማገናዘብ አለመቻል ናቸዉ።

እንቅልፍ መተኛት ባይፈልግም አልጋዉ ላይ ጋደም ብሎ
አይኖቹን ያንከራትታል
"እግሬ ለወደፊቱም መራመድ ባይችልስ?"
በድን እግሮቹን ለማንቀሳቀስ እየሞከረ
በፊት ልጅ እያለ ከጉዋደኞቹ ጋር እሩጫ ሲወዳደሩ አንደኛ እንደሚወጣ አስታዉሶ ፈገግ አለ ወደ አሁኑ ያለበት ህይወት ሲያስብ ግን እንባ እና ተስፋ መቁረጥ
ስለሚከቡት ላለማሰብ በብርድ ልብሱ ተጠቅልሎ ተኛ።

ቤዛዊት ብቻዋን እንድትሄድ ቤተሰቦቿ አልፈቀዱላትም ነበር
እህቷ አብራት ነበረች የተኛበትን አልጋም ስለምታዉቀዉ ልታሳያት ተከተለቻት።

ከቦታዉ ደርሰዉ አልጋዉ አጠገብ ቆሙ ተጠቅልሎ የተኛ አካል
በብርድ ልብሱ ቅርፅ ሰርቶ ይታያል ፍፁምን ለማየት የጓጓችዉ
ቤዛዊት እንዲነሳ እግሩን በእጆቿ ነካ ነካ ነረገችዉ አልሰማ አላት

"ፍ ፁ ም ..."

እህቷ የፍፁም እግሮች እንደማይሰሩ እንደማይሰሙ
ብታዉቅም ለመንገር ግን
ከብዷት እህቷ የምታረገዉን በሀዘኔታ ታያለች።

"ፍ ፁ ም ፍፁም..."

የሚሉ ቃላቶች የእዉነት እየሆኑ በቅዠት መልክ ስለተሰሙት
አቤት ለማለት አይኖቹን ከፍቶ ከብርድ ልብሱ ተገለጠ
ፊት ለፊቱ ቤዛዊት ቆማለች የጠቆረች የከሳች የተጎዳች መሰለዉ
ለማማተብ የዘረጋዉን እጁን አይኑን ባለማመን ጠራረገበት
እሷ ፊት ላይ ለስለስ ያለ ፈገግታ እየታየ ቀረበችዉ
ወደ ጉንጮቹ ከመጠጋቷ በፊት እህቷን አየት አርጋት ሳመችዉ
እህቷም ስለገባት እንዲያወሩ ጥላቸዉ ወደ ዉጪ ወጣች
የደረቀ እና የተጣበቀ ከንፈሩን እያለያየ
"እንዴት ነሽ ቤዚ..."
"ደህና ነኝ አንተስ አልተጎዳክም አደል ..."
በእጆቿ እየደባበሰችዉ
"ምንም አልተጎዳሁም..."
ህመሙን ዋጥ እያረገ እሷ ስለመጣች ደስ እያለዉ
ፊቷን አተኩሮ እያየ ፈግታዋ እንደድሮዋ አልደምቅልህ አለዉ
ደህንነቷ አሰጋዉ ጠፍታ ነበር የተባለዉን አስታዉሶ ልጠይቃት
አልጠይቃት እያለ በዉስጡ ማሰብ ጀመረ።

በእስዋ በኩልም ፍፁምን ታሞ አልጋ ላይ ስታየዉ ዉስጧ እርብሽ ብሏል ከትምህርት ቤት እንደተባረረ ወሬ
ስለሰማች በእሷ ምክንያት መሆኑን ገምታለች
የተገጨዉም ይሄኔ እኔን ለማዋራት ትምህርት ቤት ሲመጣ
ነዉ እያለች ሁለቱም በራሳቸዉ ሀሳብ ሰምጠዉ ቆይተዉ
"ቀሚስሽ ደሞ እንዴት ያምራል .."
ጨዋታ ለመጀመር አስቦ ለየት ስላለበት አለባበሷ
"የእማማ ስንቄ ነዉ እንዴት ጥሩ ሰዉ መሰሉክ የሆነ ቀን አብረን ሄደን አስተዋዉቅሀለዉ..."
መራመድ እንደማይችል ትዝ ስላለዉ ማዉራት እየከበደዉ
በመስማማት አንገቱን ነቀነቀ
"ምግብ በልተሀል ለምን ከአልጋ ወርደህ አትቀመጥም "
ፈጠን ያለ ጥያቄ ጠየቀችዉ
"በልቻለሁ.."
ተስፋ በቆረጠ አነጋገር
ቤዛዊት መቀመጥ ብቻ ሳይሆን ተነስቶ ተቃቅፈዉ
የሆድ የሆዳቸዉን እያወሩ ከሚጨንቀዉ ሆስፒታል
ፍፁምን ይዛዉ ብትወጣ ደስታዋ ነዉ
ነገር ግን ፍፁም መንቀሳቀስ የፈለገ አልመሰላትም
"ተቀይመሀኛል እንዴ መጥቼ ስላልጠየኩህ"
ከንፈሯን እያጣመመች
"አረ አልተቀየምኩሽም"
እጆቹን ሰዶ እጆን ያዛት
"እሺ ተነስ..."
አይኖቹን እስዋ ላይ ተክሎ እግሮቹን ለማንቀሳቀስ መታገል ጀመረ
"እ ህ ..........አ"
እየከበደዉ እልህ እየተናነቀዉ በእጆቹ ታግዞ
አልጋዉ ጠርዝ ላይ በመከራ ተቀመጠ
ቤዛዊት ግራ ተጋብታ እያየችዉ ነዉ ልታግዘዉ እየሞከረች
እንዳትረዳዉ በእጆቹ ምልክት ስላሳያት ፈዛ በሀዘኔታ ታየዋለች
በደንብ አልተሻለዉም በማለት እንባዋን ለመቆጣጠር እየታገለች
ከጀርባዋ ያለዉን ዊልቸር እየጠቆማት
"እሱን ጠጋ አርጊልኝ"
አዘዛት
ላለ ማልቀስ እየታገለች አስጠጋችለት ከአልጋዉ ወርዶ
ዊልቸሩ ላይ ሊቀመጥ ሲል ግን
የዊልቸሩ ጎማወች ስለሚንቀሳቀሱ ለመቀመጥ ሲታገል
ሚዛኑን ሳቶ ከመዉደቅ ቤዛዊት በእጆቿ ደግፋ አተረፈችዉ
ተደናግጠዉ ተያዩ ወድያዉ እንዲቀመጥ ካገዘችዉ በኋላ መሳቅ ጀመሩ።

የቤዛዊት እህት ተመልሳ ወደ ፍፁም እና ቤዛዊት ተጠጋች
ልብ አላሏትም ሁለቱም የሞቀ ጨዋታ ላይ ናቸዉ
እስከ አሁን ይነግራታል ብላ በማሰብ
"እግርህ አሁን ለዉጥ አለዉ..."
ወሬያቸዉን አቋርጠዉ ተመለከቷት
"ጥሩ ነዉ ለዉጥ አለዉ "
አላት እና ፈገግ አለ ቤዛዊት ባትኖር መዉደቁ እንደ ነበር
እያስታወሰ የቤዛዊት እህትም ፊቱ ላይ ፈገግታ ስታይ ሳቀች
ፈገግታዋ ከቤዛዊት ጋር ይመሳሰላል ፍፁም ተገርሞ አያት በልቡ
"ቁጭ ቤዛዊትን" እያለ
ቤዛዊት የእህቷን አሳሳቅ አልወደደችዉም ደስ አላላትም
ዉስጧ ንዴት እየተቀጣጠለ ነዉ ህመሟ መንስኤ ነዉ የሚፈልገዉ
በተለይ የፍፁምንም እህቷን እያየ መሳቁን ስታይ
"እገላታለሁ"
ስትል በታመዉ ህሊናዋ እህቷ ላይ ዛተች።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍5