#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰተ_በዘሪሁን_ገመቹ
___
//
ዛሬ ጠዋት ሎዛን ከስራ መባረሯን ለመናገር ፀጋን ይዛ ወደ ፋውንዴሽን ቢሮ ሄዳ ነበር፡፡
የሎዛ ክህደት አሁንም እያመማት ነው፣እሷን በመገላገሏ ደስ ብትሰኝም ከእስከአሁኑ በባሰ ሁኔታ፣ የስራ ጫናው ሊጠነክርባት እንደሚችል ተሰምቷታል።እሷ የምትፈልገውን ስራ በእቅዳቸው መሰረት እንዲከወንላት ከፈለገች ሁለት ተጨማሪ ጥንድ እጆች፣ አይኖች እና ጆሮዎች ያስፈልጋታል።
ራሄል በቁጭት እና በንዴት ቢሮ ቁጭ ብላ ከሮቤል ጋር እያወራች ነው፡፡
‹‹ ሮቤል በሆነው ነገር በጣም አዝኛለው…የማፍያ ፀባይ ካላቸው የበጎ አድራጎት ድርጅተች ጋር ተመሳጥራ በእኔ ድርጅት ስም ልትዘረፍ ስትል ነው የያዝኳት››
‹‹አዎ..ከዚህ በፊት የምታደርጋቸው አንዳንድ ሁኔተዎች ሳላላማሩኝ ጥንቀቄ እንድታደርጊ ጠቆም አድርጌሽ ነበረ….ይመስለኛል እንደቁምነገር ወስደሸሽ አላዳመጥሽኝም››
‹‹አዎ ትክክል ነህ…በጣም እኮ ነበር የማምናት››
‹‹ለማንኛውም ከፍተኛ ኪሳራ ሳታስከትል በጊዜ ስለደረሽባት ጥሩ ነገር ነው….ለወደፊቱ ትምህርት ይሆንሻል››አላት፡፡
‹‹ አዎ ትክክል ነህ…ለማንኛውም አሁን ሌላ ጎበዝ እና ታማኝ ረዳት ማግኘት አለብኝ ፡፡››
‹‹ያንን ስራ በንዑስ ኮንትራት ማሰራት የሚሻል ይመስለኛል››የሚል ምክር ሰጣት፡፡
‹‹አይ ይህ በራሴ ማድረግ አለብኝ።ብቻ በፋውንዴሽኑ ላይ ሌላ ጉዳት እንዳላደረሰች ተስፋ አደርጋለሁ።››
የቢሮውን ስራ ለሮቤል በአደራ ሰጥታ ፀጋን ይዛ ከቢሮ ወጣችና ወደሆስፒታል ነው የሄደችው፡፡ፀጋ ታማ ሳይሆን መደበኛ ክትትል የምታደርግባትን ቀን ስለሆነ ነበር ወደ ሆስፒታል የወሰደቻት..ከዛ በኋላ ነው ወደቤታቸው የተመለሱት፡፡
ራሄል በምትወደው ሶፋ ላይ ተቀምጣ ትራስ በመደግፋ ወረቀቶች እያገላበጠች ሳለ ስልኳ ጠራ..አነሳችና አየችው፡፡አባቷ ናቸው፡፡በጭኗ ላይ ያሉትን ወረቀቶች ማገለባበጧን ሳታቆም አባቷን ማውራት ጀመረች፡፡
‹‹አባዬ እንዴት ነህ..እማዬስ?››
‹‹እናትሽ በጣም ቆራጥ ነች እና ዶክተሮቹ በጤናዋ መሻሻል በጣም ተደስተዋል.››አላት አባቷ፡፡
‹‹ደስ ብሎኛል አባዬ..እኛጋም ነገሮች ጥሩ ናቸው….ስራዬንም ወደቤት አዘዋውሬ አንተ ቢሮ ስሰራ ነው ምውለው››
‹‹አንዳንድ ስራዎችሽን አሁን ለቀጠርሻቸው ረዳቶችሽ መስጠት አልቻልሽም?››ሲሉ ጠየቋት፡፡
ስለ ሎዛ እስካሁን አልነገረቻቸውም። አሁን በትከሻቸው ላይ ምንም ተጨማሪ ሸክም ልትጭንባቸው አልፈለገችም።
‹‹አባዬ ስራውን ለሌሎች ለማከፋል እየሞከርኩ ነው..ቢሆንም ታውቃለህ አመታዊው የገቢ ማሰባሰቢያ በአላችን እየደረሰ ነው..በዚህ ጊዜ ስራ ይበዛብናል›› አለች.፡፡
‹‹በዛ ላይ እህትሽን መንከባከቡ በጣም ፈታኝ ስራ ነው››
‹‹ኖ…ኖ አባዬ….አሁን ከእህቴ ጋር በጣም እየተግባባን ስለሆነ ነገሮች የምታስበውን ያህል ከባድ አይደሉም…እናንተ ምንም አታስቡ››
‹‹ይሁን ልጄ…በጣም ነው የምኮራብሽ››
‹‹አመሰግናለው አባዬ…ለመሆኑ ዶክተሮቹ እናቴ ከሆስፒታል መች ትወጣለች ብለው ያስባሉ?››
‹‹ግምቱን አሻሽለዋል፤ከአሁን በኋላ ቢያንስ ሁለት ሳምንት ሳያቆዬት አይቀርም፡፡ ከፀጋ ጋር መነጋገር እችል ይሆን?››
‹‹ይቅርታ አባዬ አሁን ተኝታለች ››
.የእለቱ ተግባራቸውን ሁሉ አከናውነው ወደ ቤት እስኪመጡ ድረስ የፀጋ ባህሪ ከንጭንጭ የራቀና በፈገግታ የተሞላ ሆኖ በመታየቱ አመስጋኝ ነበረች። ግን ወደቤት ከተመለሱ በኃላ መነጫነጭ ጀመረች ከዛ ሰውነቷን አጥባ እራቷን ካበላቻት በኋላ አልጋ ላይ አስቀመጠቻት… ከዛ ትንሿ ልጅ በሰከንዶች ውስጥ ተኛች። ይህም ራሄል ምስኪኗን ልጅ ከወዲህ ወዲያ እያሽከረከረች ስታንገላታት ስለዋለች የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማት አድርጎታል።..እና አሁን ልትቀሰቅሳትና የበለጠ ልታበሳጫት አልፈለገችም፡፡
አባቷን ለተጨማሪ ጥቂት ደቂቃዎች አወራቻቸው፣ አባቷን ስትናገር እንኳን ስራዋ እያንገበገበባት ነበር ..ትኩረቷን የሚከፋፍልባት ምንም ነገር ባይኖር ደስተኛ ነች ።ወዲያው ሌላ ስልክ ተደወለላት.. ቃተተች እና ማን እንደሚደውል ሳታረጋግጥ አነሳችው..ቁጣ በሚመስል የድምፅ ቃና ‹‹ራሄል ነኝ.››አለች
‹‹ሄይ ራሄል… እንዴት ነሽ?››ዔሊያስ ነበር…ፍስስ የሚለውን ድምፁን ስትሰማ ብስጭቷን አቃለላት። ራሄል ዛሬ ወደቤት ከተመለሰች በኋላ ዔሊን ለማየት ፈልጋ ከአሁን አሁን በራፉን ያንኳኳል እያለች በናፍቆት ስትጠብቅነበር፡፡
‹‹ስልክሽ ለረጅም ጊዜ ተይዞ ነበር››
‹‹ከአባቴ ጋር እያወራው ነበር ››አለችው።
‹‹ነገሮች እዛ እንዴት እየሄዱ ነው…?ሄጄ ካየዋቸው እኮ ሳምንት ሊያልፈኝ ነው››
‹‹እናቴ ጥሩ እያገገመች ነው። ግን እስከሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ወደ ቤት እንደማትመጣ ነው የሰማሁት››
‹‹አይዞሽ…ዋናው የመዳን ሂደታችው እድገት እያሳየ መሄዱ ነው››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው….ታዲያ አሁን ምን እያደረክ ነው? ››ብላ ጠየቀችው
‹‹ምንም…ሶፋዬ ላይ ጋደም ብዬ ስለአንቺና ስለፀጋ እያሰብኩ ነበር››አላት፡፡
ደስ አላት‹‹እየፎገርክ ነው?››
‹‹አረ እውነቴን ነው…መቼስ ማል አትይኝም››
‹‹መምጣት ትፈልጋለህ?›› ቃላቶቹ ድንገት ነው ከአንደበቷ ያመለጧት….የአእምሯዋን ሳይሆን የልቧን ምኞት ነው አንደበቷ ያሳበቀባት….
‹‹ከስራ ከወጣው በኋላ ከሶስት ጊዜ በላይ ልመጣ ተነስቼ ነበር ከዛ ‹‹አረ ኤልያስ እግርና አብዝተሀል…..ሰዎቹን እያጨናነቅካቸው እንዳይሆን ››ብዬ ራሴን በመገሰፅ ያቆምኩት፡፡
‹‹እባክህ ና:: እዚያ ባገኝህ ደስ ኀይለኛል።›› ድጋሚ አመለጣት…በራሷ ሽምቅቅ አለች፡፡
‹‹እንዲህ ከሆነ››አለ ዔሊ በፈገግታ ‹‹ መምጣት የምችል ይመስለኛል….››
‹‹ቆንጆ እራት ሰርቼ ጠብቅሀለው››
‹‹በጣም ደስ የሚል ነገር ነው..በዛውም የሞያ ብቃትሽ ይፈተሻል››
‹‹አንተ የእማዬ ልጅ እኮ ነኝ..በሞያዬማ ምንም ጥርጣሬ ሊገባህ አይገባም››
‹‹እኮ ላየው አይደል?››
‹‹አይ ዛሬ እንኳን አታየውም…ይሄንን ዙሪያዬን የተቆለለ ወረቀት ባለበት ጥዬ ኪችን አልገባም››
‹‹እና እራቱ የለም እያልሺኝ ነው?››
‹‹እሱማ አለ ..ግን አለም ነች የምትሰራው››
‹‹ይሁን እሺ…..እስክንገናኝ ቻው››
‹‹ቻው››ስልኩን ዘጋች፡፡እንደገና ዘና ያለ ስሜት ተሰማት ፡፡
አለምን ተጣራችን እንግዳ ስለሚመጣ ቆንጆ እራት እንድታዘጋጅ አዘዘቻት እና ትኩረት ሰበሰበች እና ወደ ስራዋ ተመለሰች፡፡
///
ረዳቷ ሮቤል ወደእነ ራሄል ቤት መጥቶ አባቷ ቢሮ ውስጥ ተቀምጠው ስለፋውንዴሽኑ አመታዊ የገቢ ማሰባሰ
ቢያ ዝግጅት እየተወያዩ ነው፡፡
‹‹የትኛውን ስራ በማን እንደማሰራ እና …የተወሰኑ ስራዎችን ውክልና መስጠት ከየት እንደምጀምር አላውቅም።››ራሄል በንዴት ተነፈሰች።
‹‹ እኔም ስለእሱ እያሰብኩነበር…ሁሉንምነገር በራስሽ ለመስራት በመሞከር በራስሽ ላይ አላስፈላጊ ጫና ማሳደር የለብሽም…እኔ አለሁ››
‹‹እኔ ካንተ የበለጠ ጊዜ አለኝ ብዬ አስባለሁ… ።››
ሮቤል ንግግሯ አልተዋጠለትም፡፡ቢሆንም ብዕሩን በፋይሉ ላይ ሰክቶ እያዳመጣት ነው፡፡በሁሉም ነገር ትዕግስት እያጣ እንደመጣ በሁኔታው መታዘብ ይቻላል፡፡
‹‹ራሄል እህትሽን በመንከባከብ እንደተጠመድሽ አውቃለሁ…የደከመሽ ትመስላያለሽ ።አሁን የሎዛን ስራ የሚሰራ ሌላ ሰው መፈለግ አለብሽ እና ጊዜ እንደሌለሽ አውቃለሁ። ››በማለት የሚያስበውን በግልፅ ነገራት፡፡

❤57👍1🔥1😁1
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////
አለም መተኛት አቅቷት እየተገለበጠች ባለችበት ጊዜ ነበር ስልኩ የጮኸው፡፡ሰዓቱ እኩለ ለሊት በመጠጋቱ የተነሳ ጥሪው በጣም ነበር ያስደነገጣት ። የራስጌ መብራቱን በማብራት የስልኩን እጄታ አነሳችና ጆረዋ ላይ ለጥፋ ጎላ ባለ ድምፅ "ጤና ይስጥልኝ" አለች፡፡ቀደም ብሎ ስታለቅስ ስለቆየች ድምጿ የሻከረ ነበር
"ሰላም ››መለሰላት፡፡
"አወቅሽኝ ወ.ሪት አለም "
ልቧ በደስታ ዘለለ፣"አንተ እንደገና? በዚህ ውድቅት ለሊት ከእንቅልፍ ያስነሳኸኝ ደህና ነገር ልትነግረኝ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ" አለችው።እምቢተኛ ምስክሮች ብዙ ጊዜ የሚናገሩትን ነገር አስፈላጊነት ሲጠቀስላቸው ለመናገር እንደሚበረታቱ ከልምድ ታዝባለች፡፡
"ከኔ ጋር ድብብቆሽ አትጫወቺ …. ማወቅ የምትፈልጊውን በጠቅላላ አውቃለሁ። "
"ለምሳሌ ምን?"
"ለምሳሌ እናትሽን ማን እንደገደላት››
አለም አተነፋፈስዋን በመቆጣጠር ላይ ትኩረት አደረገች።
" ይመስለኛል ዜናው አስደምሞሻል››
"ታዲያ ንገረኝ ማን ነበር?"
"እመቤት ደደብ እመስልሻለሁ እንዴ? ኩማንደሩ ቀደም ሲል ስልክሽን አለማስጠለፉን በምን አውቃለው ?"
"ይመስለኛል….በጣም ብዙ ፊልሞችን አይተሃል?››
‹‹ተረቡን አቁሚና ይልቅ በፅሞና አድምጪኝ ….ነገ ማታ አንድ ሰዓት ሸዋበር የሚገኘው ደንበል ሆቴል እንገናኝ" በማለት ሰዓቱንና ቦታውን ነገራት፡፡
"እንዴት ላውቅህ እችላለሁ?"
"እኔ አውቅሻለሁ"
ሌላ ነገር ከመናገሯ በፊት ስልኩን ዘጋው። አለም በአልጋው ጠርዝ ላይ ለጥቂት ጊዜ ተቀምጣ ጨለማውን እያየች ደርቃ ቀረች። ልትጎዳ እንደምትችል የነገራትን የኩማንደሩ ማስጠንቀቂያ አስታወሰች። የእርሷ ምናባዊ አእምሮ በሴት ላይ ብቻ ሊደርስ የሚችለውን አሰቃቂ ነገር ሁሉ አስተናገደ። በተኛችበት ሆና በላብ ተጠምቀው ነበር።
///
የከተማው የፖሊስ አዛዥ እንፋሎት የሚትገለግበትን ቡናውን አንስቶ ጠጣ። ምላሱን አቃጠለው። ግን ግድ አልነበረውም። በጣም በከፋ መንገድ የካፌይን ማነቃቂያ ያስፈልገዋል
‹‹ስለማን ነው የምናወራው?›› ሲል በግል ቢሮው ደጃፍ ላይ ቆሞ የነበረውን ምክትሉን ጠየቀ ..
" ስለአቃቢ ህግ ፅ/ቤት ነው››
"ስለ ወ.ሪት አለም እያወራህ ነው ?" ምክትሉ መለሰ " አዎ ጌታዬ ስለእሷ ነው።" "እሺ ምን አዲስ ነገር አለ?"
" የእናቷን የሬሳ ምርመራ መዝገብ አስወጥታ ዠለመመርመር ወደ ተክለሀይማኖት ቤ/ክርስቲያን ሄዳለች ››
"ምን?"
"አዎ ጌታዬ እንዲከታተሏት የመደብናቸው ፖሊሶች ናቸው ደውለው የነገሩኝ፡፡››
‹‹በል አሁኑኑ ደውልላቸውና ወደእነሱ እየመጣሁ እንደሆነ ንገራቸው››
ገመዶ ኮቱን ከተሰቀለበት አንስቶ ቢሮውን ለቆ ወጣ…፡፡ ትምህርት ቤቶችን እና አብዛኛዎቹን የንግድ ድርጅቶች እንዲዘጉ ያደረጋቸውን የፀጥታ ችግር ቢኖርም ግድ አል ነበረውም። ሰልፈኛውን እየሰነጠቀ እና ወንበር እያሳበረ ወደሆስፒታል ነዳው፡፡
"የት ነው ያለችው?" እንደደረሰ ኩማንደሩ ጮኸ፣..አንድ አነስተኛ ቢሮ መሰል ክፍል ውስጥ ቁጭ ብላ ከአስተዳዳሪው ጋር ስታወራ ተመለከታ…ወደእዛው ተንደርድሮ ሄደ፡፡
ምንም ፍቃድ ሳይጠይቅ ሰተት ብሎ ገባና " ምን እየሰራሽ ነው ?"አንቧረቀባት፡፡ "እንደምን አደርክ ኩማንደር"አለችው ለስለስ ብላ፡፡
"ጥያቄዬን መልሺልኝ?"
‹‹ምን እያደረኩ እንደሆነማ በደንብ ታውቃለህ?››
"በአንቺ ምክንያት ሴትዮዬ ስራዬን መስራት አልቻልኩም….ከተማዋ በበጥባጭ ጎረምሶች ተረብሻ ያንን ማረጋጋት ሲጠበቅብኝ እኔ አንቺን በየመቃብር ቤቱ እከታተልሻል። ለማንኛውም እንዴት እዚህ ደረስሽ?"
" እየነዳሁ።"
በንዴት በጠረጴዛው ላይ የተበተኑትን ፋይሎች አያመለከተ"ይህ ሁሉ ምንድን ነው?"ሲል ጠየቃት፡፡
" መዛግብት ነዋ…..እናቴ ስትቀበር ለአገልግሎት የተከፈሉ ካርኒዎች እና መሰል መረጃዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ ያንን እያዩልኝ ነው፣ ፡፡
"አስገድደሽው ነው?::"
‹‹እኔ እንደዚህ ያለ ነገር አላደረኩም..እንዴት ነው ምታስበኝ…?ደፍሬ አባቶቼን የማስገድድ ይመስልሀል?."
" ታዲያ የፍተሻ ማዘዣ ፍቃደሽን አልጠየቁሽም?"
ካህኑ‹‹ልጆቼ ይቅርታ እስኪ እናንተ አውሩ እኔ መጣሁ››ብለው ከመቀመጫቸው ተነሱና ክፍሉን ለቀውላቸው ወጡ … ገመዶ ወደሷ ቀረበና በንዴት ክንዷን ጨምድዷ ያዘ፡፡
‹‹ምን እያደረክ ነው?››
‹‹ቄሱን የሆነ ነገር ብዬ ከማስቀየሜ በፊት ቀጥ ብለሽ ቦታውን ለቀሽ ውጪ››
‹‹ለምንድነው እንደዛ የምታደርገው?››
‹‹ነገርኩሽ እኮ..አሁን ተከትለሺኝ ትሄጂያለሽ ወይስ…የማደርገውን ቆመሽ ትመለከቻለሽ?››
ትኩር ብላ አየችው … ፊቱ እንደ ተራራ ሰንሰለታማና ወጣ ገባ ነው፣በአጭሩ ቋጥኝ ይመስላል፣ ነገር ግን እስካሁን ካጋጠሟት በጣም ማራኪ ወንዶች ውስጥ አንዱ ነው።አብረው በሚሆኑበት ጊዜ ሁሉ፣ ስለ እሱ፣ ስለ ሰውነቱ ታስባለች፡፡ የእሷ ለእሱ ያላት መስህብ ሥነ ምግባር የጎደለው እና ከዛም አልፎ እንዝላልነት እንደሆነ ታውቃለች። መጀመሪያ የእናቷ ፍቅረኛ ነበረ።ያንን በደንብ ታውቃለች ..ሆኖም ብዙ ጊዜ እሱን ለመንካት ትፈልግ ነበር። ትናንት ማታ በምታለቅስበት ጊዜ እንዲያባብላት ትፈልግ ነበር። ወደመኝታ ቤቷ ተከትሏት እንዲገባም ፈልጋ ነበር…ደግነቱ እሱ በተሻለ ብቃት እራሱን የመቆጣጠር ችሎታ ነበረው እና ምንም ሳያደርግ ትቷት ሄደ።
‹‹የሰሎሜ ሬሳ እንደተቃጠለ ነግሬሻለሁ።››
"አንተ እና ዳኛው ጭንቅላታችሁን አንድ ላይ አድርጋችሁ እያሻጠራችሁ መሆኑን ማወቄ የተመቸኝ ይመስልሀል?።››
"ነገሮችን መገመት ያስደስትሻል?."
"ጁኒየር እናቴ ሬሳ መቃጠሏን ለምን አልነገረኝም?እንደተቀበረች ነበር የነገረኝ ››
‹‹እኔ እየዋሸሁሽ ይምስልሻል….?ለምን ብዬ?" " አስከሬኑ እንዳይወጣ ስለምትፈልግ ነዋ።"
"ሬሳው እንዳይወጣ ለምንድነው የምፈልገው? በእኔ ላይ ምን ለውጥ ያመጣል?"
ፍርጥም ብላ "የእድሜ ልክ እስራት" በማለት መለሰችለት፡፡ "የፎረንሲክ ሪፖርቱ አንተን ነፍሰ ገዳይ መሆንህን የሚያመለክት ፍንጭ ከሰጠን ወደወህኒ መወርወርህ የማይቀር ነው።››
" “አህ...” አለ..ደም ስሯቹ ሲግተረተር እየታዘበች ነው፡፡ "አንቺ ጠበቃ አይደለሽም, ጠንቋይ አዳኝ ነሽ."
"ወንጀል ባይኖር ኖሮ ያ እውነት ሊሆን ይችላል….ግን አንድ ሰው ወደዚያ በረት ውስጥ ገብቶ እናቴን ወግቶ ገድሏታል..እና እስከአሁን ለጥፋቱ የሚመጥን ቅጣት አላገኘም።››
"በእስክሪፕት ደረጃ ትክክል ነሽ" አለ እየተሳለቀ።
"ጋሽ ፍሰሀ ፣ ጁኒየር ወይስ እኔ የቀዶ ጥገና መሳሪያ ይዘን እናትሽን እንደወጋናት ነው ግምትሽ? ለምን በባዶ እጃችን አንገቷን አንቀን አንገድላትም??"
"ሁላችሁም ጎበዝ ስለሆናችሁ።ከመካከላችሁ ወንጀሉን የፈፀመው ሰው እንደዛ ያደረገው ወንጀሉን የአእምሮ ሚዛናዊ የተዛባ ሰው ያደረገው እንዲመስል ፈልጎ ነው።››
‹‹አመንሽም አላመንሽም …እኔ አላደረግኩም
"በብስጭት መለሰላት፡፡
"ታዲያ ማን እንዳደረገው ማወቅ አትፈልግም? ወይስ ነፍሰ ገዳዩ የምትወደው ሌላ ሰው እንዳይሆን ትፈራለህ ?"ስትል ሞጋች ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹አይ ማወቅ አልፈልግም" ሲል በአጽንኦት መለሰላት፡፡
"እኔ ግን ገዳዩን እስካገኝ ድረስ ምርመራዬን አላቋርጥም..››
ሊመልስላት አፉን ሲከፍት አንድ ግራ እግራቸው ሸንከል የሚል አዛውንት አንድ ያረጀች መዝገብ ይዘው ወደውስጥ ሲገቡ ሲመለከት አፉን መልሶ ከደነ፡፡

❤43👍1