#አላገባህም
፡
፡
#ክፍል_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
፡
፡
////
‹‹ቆይ ዘሚካኤል የት ነበር የጠፋው?፡፡››
‹‹እናቱና እህቱ የሞቱ ቀን ነው የተሰወረው፡፡ሁለቱ በመልክም ሆነ በአመካከት ፍጹም ተቃራኒ የሆኑት ወንድማማቾች ከከተማ ተያይዘው ወደቤት ሲገቡ ..ሳሎኑ ፍፁም ትርምስምስ ብሎ ያያሉ ..ግራ በመጋባት ወደውስጥ ዘልቀው ሲገቡ እናታቸው ልቧ ላይ ነጭ አብረቅራቂ ቢላዋ ተሰክቷባት ወለሉ ላይ ዝርግትግት ብላ ተኝታለች..አባትዬው ስሯ በደም በተጨማለቀው እጇቻቸው ጭንቅላታቸውን ይዘው ደንዝዘዋል….፡፡
‹‹እንዴ አባዬ ምንድነው..?እናቴን ምን አደረካት?›› ብለው ሲጮሁ ከፊት ለፊት ኮርኒሱን ከደገፈው ብረት ላይ በታሰረ ሲባጎ አንገቷ የታነቀው እህታቸው በድኗ 360 ዲግሪ ሲሽከረከረከር ይመለከታሉ፡፡ሁለቱም ወንድማማቸች ወደእህትዬው እየሮጡና ሁለት እግሮቾን አንድ ላይ ይዘው ወደላይ ከፍ ያደርጎታል….‹‹ቶሎ በል ቢላዋ አምጣና ..ገመድን ቁረጥ…››
.ዘሚካኤል ይንደረደርና እናትዬው ደረት ላይ የተሰካውን ቢላዋ ይነቅልና ወንበር ላይ ቆሞ ገመዱን ይበጥሳል…እህትዬው ተዝለፍልፍ ሚካኤል ተከሻ ላይ ታርፋለች… ቀስ ብለው ወለል ላይ አሳርፈው በፍጥነት አንገቷ ላይ ያለውን ገመድ አላቀው ትንፋሿን ቢያዳምጡም በውስጧ የቀረ ምንም እንጥፍጣፊ እስትንፋስ አልነበረም….ከዛ ዘሚካኤል ቀጥታ እህቱ የተንጠለጠለችበትን ገመድ የቆረጠበትን እና እናቱ የተገደለችበትን ቢላዋ ይዞ ወደአባትዬው ሲንደረደር…ሚካኤል በደመነፈስ ሮጠ ይጠመጥበታል…
‹‹ልቀቀኝ..እናቴንና እህቴን ገድሎ እሱ በህይወት አይኖርም››
‹‹አይሆንም….ስለሆነውን ምንም ምናውቀው ነገር የለም››ሲል ይመልስለታል፡፡
‹‹እንዴት አናውቅም..?አታይም እንዴ …?እጁ በደም ተጨማልቆ……ልቀቀኝ ልግደለው›› ሲል ይጋበዛል፡፡
‹‹አባቴንም ማጣት አልፈልግም››
‹‹እንግዲያው ሁለታችሁንም እገድላችኃለው…››ይለውና ድብድብ ይጀምራሉ…ይሄ ሁሉ ሲሆን አባትዬው ደንዝዘው ከተቀመጡበት ቦታ ንቅንቅ አላሉም ነበር….ወንድማማቾቹ አባቴን ልግደል አትገድልም በሚል ጠብ እርስ በርሳቸው ተቦቅሰውና ተደባድበው ሳይለይላቸው ቤቱ በፖሊስ ይሞላል፡፡
አባትዬ እነሱ ከመድረሳቸው በፊት ስልክ ደውለው ሚስታቸውን እንደገደሉ ነግሮቸው ነበር፡፡ፖሊሶቹ ወንድማማቾቹን አገላግለው ሶስቱንም ወደእስር ቤት ከወሰዷቸው በኃላ ሬሳዎቹን አንሰተው ለምርመራ ወደሆስፒታል ይልካሉ..በማግስቱ አባትዬው ሚስታቸውንም ሆነ ልጃቸውን የገደሉት እራሳቸው እንደሆነ ቃል ስለሰጡ በዛ መሰረት ሁለቱ ልጇች ይፈታሉ፡፡
ከአራት ቀን በኋላ የእናትና እህታቸውን ሬሳ ተረክበው ከቀበሩ በሆላ ዘሚካኤል በከተማው አልታየም፡፡‹‹አንተ ያንን አውሬ ሰውዬ ገድዬ የእናቴንና የእህቴን ደም እንዳልበቀል ያደረከኝ ጠላቴ ነህ..ከእሱ በላይ እጠላሀለው ..እና ደግሞ መቼም ቢሆን ይቅር አልልህም፡፡››የሚል ማስታወሻ ለወንድሙ ጥሎ ነበር የጠፋው፡፡ቆይቶ እንደሰማነው ከጓደኞቹ ጋር በቦረና በኩል ወደኬኒያ ከዛም ወደጣልያን ከተሻገረ በኋላ…በፊትም ልጅ እያለ ጀምሮ ይሞካክረው በነበረው ሙዚቃ ገፋበትና በትምህርትም አሳድጎ ጥሩ ሙዚቀኛ ሆነ ፡፡ለመጀመሪያ ጊዜ በህይወት መኖሩን ያወቅነው የዛሬ 3 አመት የሙዚቃ ክሊፑን ሲለቅ ነው፡፡
….የዛን ጊዜ ሚካኤል የተደሰተው መደሰት ያው አንቺም አብረሺን ስለነበርሽ ታውቂዋለሽ፡፡ከዛ በሀገር ውስጥ በጣም ተቀባይነት ስላገኘ ..ጓዙን ጠቅልሎ ገባ፡፡በሙዚቃ ብቻ ሳይሆን በፊልም ትወና ላይ መስራት ቀጠለ…እንግዲህ ባለፉት አምስት አመታት የገነባውን ስምና ዝና እኩል ነው የምናውቀው፡፡››
‹‹ይገርማል….ግን ከመጣ በኃላ ወንድሙን ለማግኘት አልሞከረም…?››
‹‹ወይ ማግኘት..እኔ አንኳን ላገኘው ሄጄ ስለወንድሙ ሳነሳበት እንዴት እንደተንገሸገሽ እስከዛሬ ሳስበው ይዘገንነኛል..አሁንም ጥላቻው እንዳለ ነው፡፡አልፎ አልፎ በድብቅ እየመጣ የእናቱንና የእህቱን መቃብር እየጎበኘ እንደሚሄድ አውቃለው….በዛው ልክ ስለአባቱም ሆነ ስለወንድሙ ምንም መስማት እንደማይፈልግ እና ቢሞቱም ግድ እንደሌለው አውቃለው፡፡››
‹‹ተይ እንደዛ አትበይ…..››
‹‹ወይ አንቺ ልጅ ስንት ነገር ውስጥ አስገባሺኝ..ስለእሱ ለማወቅ ለምንድነው የፈለግሽው?፡››ስትል ዳግመኛ ጠየቀቻት፡፡
‹‹እንደምንም ብዬ በሰርጋችሁ ላይ እንዲገኝ ለማድረግ አስቤለው››
‹‹ምን?››አዲስአለም ክፉኛ ነው የደነገጠችው፡፡
‹‹ምነው መጥፎ ሀሳብ ነው እንዴ?››
‹‹አረ በፍጹም…ግን የሚሳካ እቅድ አይደለም….››
‹‹ከተሳካልኝስ?››
‹‹ከተሳካልሽማ….ለሚካኤል በሰርግ ላይ ሌላ ሰርግ ደገሽለት ማለት ይሆናል….በፊቱንም ይወድሻል በቃ የዘላለም ባለውለታው ነው የምትሆኚው››
ፀአዳ ‹‹ለማንኛውም ጉዳዩ በእኔና አንቺ መሀከል በሚስጥር ይያዝ …..ሚካኤል ሰምቶ ካልተሳካ ቅር እንዲሰኝ
አልፈልግም፡፡››ስትል አስጠነቀቀቻት፡፡
‹‹አታስቢ እኔም ባሌ በሰርጉ ሰሞን እንዲያዝንብኝ ስለማልፈልግ ..አልነግረውም…ለአንቺ ግን እንዲቀናሽ በቻልኩት መንገድ ሁሉ አግዝሻለው፡፡››
በዚህ ሁኔታ ነበር ከአዲስ አለም ስለዘሚካኤል የተወሰነ ነገር ማወቅ የቻለችው..ከዛ ወደ ሶሻል ሚዲያ ሄደችና እና ስለእሱ የተፃፉ የጋዜጣ አምዶችና በተለያየ ጊዜ የሰጣቸውን ቃለ መጠይቆችን ሰብስባ ማንበብና ማዳመጥ ነው የቀጠለችው…ይሄ ሂደት አንድ ሳምንት ነው የፈጀባት፡፡በዚህ ጊዜ በአምስት አመት ውስጥ ያወጣችውን ሶስት አልበሞችና ፤ከስምንት በላይ ነጠላ ዜማዎችን እየደጋገመች ያደመጠች ሲሆን እሱ የተሳተፈባቸውን ስምንት የሚሆኑ ፊልሞችንም በጽሞና መመልከት ችላለች፡፡
እና በዚህ አንድ ሳምንት ውስጥ ለአመታት የምታውቀው የቅርቧ ሰው እንደሆነ እንዲሰማት አድርጎታል..ያንን ስሜት ግራ አጋቢ ነው፡፡‹አይ በጣም የምወደው ወንድሜ የሚካኤል ወንድም ስለሆነ በእሱ እይን እሱንም ማየት ጀምሬለው ማለት ነው..›ስትል ለራሷ ማብራሪያ መስጠት ብትሞክርም ሊያሳምናት ግን አልቻለም፡፡
ደግሞ ስለሴሰኝነቱ..በየጊዜው ስለሚቀያይራቸው ሞዴል መሳይ ሴቶች፤ ከዝነኛ እንስቶች ጋር ስለሚጀምረው የፍቅር ግንኙነትና ስለመለያየቱ …ከስራው እኩል አንዳንዴም ከስራው በላይ ነው ሚያወራው፡፡እና ለእንደዚህ አይነት ሴት አውል የማይጨበጥ ሙልጭልጭ ወንድ ምን አይነት ስሜት ነው እየተሰማት ያለው….?መልስ የላትም፡፡ግን አሁን ልታገኘውና ልትጋፈጠው ወስናለች..ዝግጅቷንም ጨርሳለች፡፡
///
ፀደይ ባደረገችው ጥናት እና በሰበሰበችው መረጃ መሰረት የሚካኤል መንታ ወንድም የሆነው ዘሚካኤልን ለማናገር አንድ ብቸኛ መንገድ ብቻ እንዳላት ተረድታለች፡፡በሳምንት ሶስት ቀን በሚሰራበት በከተማዋ ታዋቂ ናይት ክለብ ተገኝታ እድሏን መሞከር ፡፡ከእሷ ባህሪ አንጻር እንደዛ አይነት ቦታ ተገኝታ የማታውቀውን ሰው ማናገር በጣም ከባድ የቤት ሰራ ነው፡፡ቢሆንም የግድ ልትወጣው የሚገባ ተግባር እንደሆነ እራሷን አሳምናለች፡፡
ባለፉት ሁለት ቀን ውስጥ የተባለው ናይት ክለብ ውስጥ በውድቅት ለሊት በመገኘት እሱ ሲዘፍን እና በቀበጥ አድናቂዎቹ ሲሞገስና ሲሸለም መመልከት ብትችልም እሱን ተጠግቶ ለማናገር ያደረገችው ሙከራ ግን ሙሉ በሙሉ አልተሳካላትም ነበር፡፡ዛሬ ግን የግድ ሊሳካላት ይገባል..ምከንያቱም ሰርጉ ከአምስት ቀን በኃላ ነው፡፡ዛሬ አግኝታ ካላናገረችው…ወደእዚህ መጥታ ሌላ ሙከራ የምትሞክርበት ሌላ እድል የላትም፡፡

👍62❤20🥰3👏1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
ከወ.ሮ ላምሮት ጋር የተደረገው ስብሰባ በጣም ረጅም ጊዜ ወስዶ ነበር እና ውጤቱ በጣም ጥቂት የሚባል ነበር፡፡
ራሄል በጣም የደክማት ቢሆንም ቢሮዋ ገብታም ስራዋን ቀጥላለች፡፡
‹‹ጥሩ ነው…በብሮሹሮች ላይ ስህተቶችን አግኝቻለሁ.››
ሎዛ ወረቀቶቹን በመካከላቸው ባለው የእንጨት ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠች። ራሄል በተቀመጠችበት የቆዳ ሶፋ ላይ ወደ ኋላ ተደግፋ ከፊቷ ያለውን ብሮሹር ቃኘች። ‹‹ይህ ሰማያዊ ቀለም በጣም ደማቅ ነው….እና ይህ ቢጫው ደግሞ እንዲጠናከር እፈልጋለሁ። የቀረውን ደግሞ ደውዬ አሳውቃቸዋለሁ››
‹‹ለምን ያን እኔ ራሴ እንድከታተል አትፈቅጂልኝም?›› አለች ሎዛ
‹‹አመሰግናለሁ ሎዛ.. ግን ማየት የምፈልገውን በትክክል አውቃለሁ።››
ሎዛ ራሷን በይሁንታ ነቀነቀች፣ ራሄል ግን በእሷ ውሳኔ ደስተኛ እንዳልነበረች አይታለች።
‹‹ለአሁን እንዳደርግ የምትፈልጊው ሌላ ነገር አለ?››ሎዛ ጠየቀች።
‹‹ አይ ምንም የለም… በቃ እጅሽ ላይ ያሉ ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጊ።››የሚል ትእዛዝ ሰጠቻት፡፡
ራሄል ወረቀቶቹን በጠረጴዛዋ ላይ አስቀመጠች እና ሎዛ ቢሮዋን ስትለቅ ወደ ሮቤል ዞረች።
‹‹ሮቤል አንተ የሆነ ነገር አንድታደርግልኝ እፈልጋለው››አለችው፡፡
ሮቤል ጎንበስ ብሎ ከቆዳው ቦርሳ ውስጥ አንድ ወረቀት አወጣና‹‹ጥቂት ስልክ ደዋውዬ ከምንጩ ያገኘሁት መረጃ ነው።›› በማለት ተጨማሪ ወረቀቶችን አቀበላት።
‹‹ከስብሰባው ጥቂት ቀደም ብሎ ከድርጅቱ ኃላፊ ጋር በግል ተወያይቼ ነበር።››
‹‹ጉልበቱን ከየት አመጣው?››ስትል አሞገሰችው፡፡ ራሄል ከወ.ሮ ላምሮት ጋር ከተገናኘ በኋላ ስላከናወናቸው ውይይቶችና ስለተለዋወጦቸው ቃላቶች በማሰብ ደክሞት ነበር።‹‹ይህ በጣም ጥሩ ነው፣ቀጣዩ እርምጃችን የበጎ አድራጎት ልገሳ ሁኔታቸውን ማረጋገጥ እና ከቻልን በእነሱ ላይ አንዳንድ ጥልቅ የጀርባ ስራዎችን መስራት ነው።››
‹‹እንደተፈጸመ ቁጠሪው.››ሲል ሮቤል ፈገግ አለ። በዚህ ጊዜ ስልኳ ጠራ…እናቷ መስመር ላይ ነበረች።‹‹እንደገና አመሰግናለሁ ሮቤል።በቅርብ ጊዜ ፋውንዴሽኑን እንደተቀላቀለ ሰው ምርጥ ስራ ሰርተሃል.›› ብላ ስልኩን አነሳች፡፡
ራሱን ነቀነቀና ዞር ብሎ ከቢሮ ወጣ።ራሄል ከኋላው ባለው ትልቅ የቆዳ ወንበር ላይ ለመቀመጥ በጠረጴዟ ዙሪያ ዞራ ሄደች።
‹‹ጤና ይስጥልኝ እናቴ››
‹‹ደህና ነኝ የእኔ ልጅ››
‹‹ እየሮጥኩ ያለሁት ባንቺ ጉዳይ እንደሆነ ከግምት ውስጥ በማስገባት ልትደሰቺ ይገባሻል።››ስትል ራሄል ወንበሯ ላይ በመቀመጥ ተሸከረከረች፡፡
‹‹ውዴ፣ ሁሌም በአንቺ ደስተኛ ነኝ ፡ ታውቃያለሽ?››
‹‹እማዬ አውቃለው…የቸኮሌት ኬኩ በጣም ጥሩ ነበር. ሮቤል እና ሎዛ አመስግኚልኝ ብለዋል.››
‹‹እንደተካፈላችሁት በማወቄ ደስተኛ ነኝ። ግን አንቺን አንድ ውለታ ልጠይቅሽ ነው። አያቶችሽ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ወደ አድዋ ሄደን እንደንጠይቃቸው ይፈልጋሉ፣ ነገር ግን ፀጋን ይዘን ለመሄድ መድፈር አልቻልንም ።እስክንመለሰ እሷን ለመጠበቅ ፈቃደኛ ነሸ?››ስትል ጠየቀቻት፡፡ራሄል በድንጋጤ ስልኩ ሊያመልጣት ነበር..በመከራ ነው አጥብቃ የያዘችው።
‹‹ፈቃደኛ? ምናልባት…ቆይ እስኪ ፕሮግራሜን ልመልከት››አለችና የቀጠሮ ደብተሯን ለማየት ማስታወሻ ደብተሯን ከፈተች። በዛን ወቅት የማይሰረዝ ፕሮግራም ኖሯት ያንን እንደምክንያት ማቅረብ እንድትችል በውስጧ ፀለየች፡፡
የወሩ የመጨረሻ ቅዳሜና እሁድ…..ቢንጎ …የበጎ አድራጎት ፈንድ የመሰብሰብ ፕሮግራም አለባት። ‹‹ይቅርታ እማዬ ባልሻቸው ቀናት መሰረዝ የማልችላቸው ፕሮግራሞች አሉብኝ…በነዛ ቀናት አመታዊ የፋውንዴሽኑ ፈንድ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አለብኝ ።››
‹‹ኦህ ውዴ፣ አያትሽ ቤት የሚውለው ቅዳሜና እሁድ ብቻ ነው።›› በለሆሳስ ተነፈሰች። እና ፀጋን ከማንም ጋር ልተዋት እችላለው? ….እንደምታውቂው እስካሁን በጣም ደካማ ነች።››
‹‹ለምን ስለችግርሽ ከዶክተር ዔሊያስ ጋር አታወሪበትም››ስትል ሀሳብ አቀረበች።
‹‹በእርግጥ ትክክል ብለሻል .. እሱ የግል ነርሲንግ ኤጀንሲን ወይም ተመሳሳይ ነገርን ሊመክረኝ ይችላል?››
ራሄል አሰበች፤ የጥፋተኝነት ስሜት ሊሰማት አይገባም። ወላጆቿ ይችን ልጅ ለማሳደግ መወሰናቸው የሷ ሀሳብ አልነበረም። እና ፀጋ ብቃት እንደሌላት እና አቅመ ቢስነት እንዲሰማት ያደረጋት የሷ ስህተት አልነበረም።
‹‹እሷን መንከባከብ ካልቻልሽ ችግር የለውም…›› እናቷ ቀጠለች‹‹እርግጠኛ ነኝ ዔሊ ፀጋን የት ልንወስደት እንደምንችል ያውቃል።››
‹‹እንደሚያውቅ እርግጠኛ ነኝ››ስትል ራሄል ተስማማች፣ እፎይታም ተሰማት።
‹እና ስለ ዶክተር ዔሊያስ ምን አሰብሽ? ››እናትዬው እንደቀልድ ሌላ ርዕስ ከፈተች፡፡
‹‹እሱ በጣም ደስ የሚል ሰው ነው…. ከፀጋ ጋር በጣም ጥሩ ግንኙነት አለው ››
ከእሷ ጋር ሊጣመር የሚችልበት ምንም እድል እንደማይኖር ለእናቷ ግልፅ ለማድረግ ጊዜው አሁን እንደሆነ ተሰማት ‹‹ግን እሱ የእኔ ምርጫ አይደለም ።››ስትል መለሰችላት፡፡
‹‹ምን አልሽ?››
‹‹እማዬ… እባክሽ አሁን ለማንም ቢሆን ጊዜ የለኝም… ታውቂያለሽ››
‹‹ባለፉት ስምንት አመታት ውስጥ ለማንም ጊዜ አልነበራሽም። ብዙ ማህበራዊ ህይወት የለሽም። የምታደርጊው አንድ ነገር ቢኖር ስራ መስራት ብቻ ነው።››
ራሄል ወንበሯን ትንሽ እያወዛወዘች ፊቷን ከሰከሰች። ‹‹ይህን ስራ እፈልገዋለሁ እናቴ…ለህይወቴ ትርጉም የሰጠኝ ስራዬ ነው››
‹‹ከጌታ ጋር ያለሽ ግንኙነትስ? ያ እንዴት አድርጎ ነው ስራሽን የሚጋፋው?››ወደ ማትፈልገው ሌላ ርዕስ ከተተቻት፡፡
‹‹‹እናቴ ሆይ፣ የእኔ ስራ የተቸገሩ ህፃናትንና አቅመ ደካሞችን መርዳት ነው። ኢየሱስ በዚህ ምድር እንድናደርግ የሚፈልገውን ተግባር ነው እያደረኩ ያለሁት።››ራሄል እናቷን የሚያስደስት ትክክለኛ ቃላቶችን ታውቃለች እና ያለ እፍረት ተጠቀመችባቸው፡፡
‹‹ያለ እምነት ሥራ የሞተ ነው ውዴ።›› እናቷ ወደ እምነቷ ሲመጣ…ጥልቅ የማሰብ ችሎታ ስላላት ሁሉንም የልጇን የማጭበርበሪያ ስልቶች ታውቃለች።
ራሄል በመጨረሻ ‹‹እኔ ማድረግ የምችለው ይህን ብቻ ነው እናቴ››አለች. ቀጠለችናም ‹‹ለወንድ ጓደኛ ጊዜ የለኝም እና ለአንድም ሰው ፍላጎት የለኝም። ስለዚህ እባካችሁ ከአሁን በኋላ የማልፈልገውን አይነት አስጨናቂ እራት ለማዘጋጀት አትሞክሩ።››ስትል ንግግሯን በመኮሳተር ደመደመች፡፡
የእናቷ ዝምታ እጅ የመስጠት ምልክት እንደሆነ ተስፋ አድርጋ ነበር።‹‹ደስተኛ ነኝ እማማ›› እናቷ ብርሃኑን እንድታይ ለማድረግ ቆርጣ ገፋችበት። ‹‹ዓላማ እና ትርጉም ያለው ንቁ ህይወት ነው እየኖርኩ ያለሁት ። ጓደኞች አሉኝ እናም በማህበረሰብ ውስጥ አስፈላጊ የሚባል ስራ አለኝ። እና አንቺ እና አባዬ እና ፀጋም አለችሁልኝ። ተጨማሪ አያስፈልገኝም።››
‹‹እሺ፣ ይቅርታ፣ አንቺና ዔሊ ትመጣጠናላችሁ ብዬ ስላሰብኩ ነው። እሱ ጥሩ እና ደግ ሰው ነው..ለዛ ነው ከእሱ መዛመድ የፈለኩት ።››
ራሄል ፊቱ ላይ ስለተመለከተችው ፈገግታ አሰበች‹ደህና፣ ለአንድ ሌላ ሴት ግሩም ባል እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ። ግን ያቺ ሴት እኔ አይደለሁም፣ እማማ።››
ወ.ሮ ትርሀስ ቃተቱ። ‹‹ካስከፋሁሽ ይቅርታ።››
‹‹አስቸጋሪ ሁኔታ ፈጠርሺብኝ እንጂ አላስከፋሺኝም።››

❤77👍6
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///
በፍርድ ቤቱ የስብሰባ ክፍል ውስጥ የነበረው ትእይንት መቀበል ከምትፈልገው በላይ አንቀጥቅጧታል።ግን ደግሞ ጭንቅላቷን ወደ ላይ ቀና አድርጋ እና ደረቷን ነፍታ ነበር ቢሮውን ለቃ የወጣችው ።እራሷን ለመቆጣጠርና የድንጋጤዋንና የፍራቻዋን ቅንጣት እንኳን ለእነሱ ሳታሳይ ስብሳባውን በድል ለማገባደድ ያደረገችው ጥረት የመታፈን አይነት ስሜት እንዲሰማት ነበር ያደረጋት፡፡ስብሰባው ባቀደችው መሰረት ነው የተካሄደው፣ እስኪጠናቀቅ ድረስም በጣም እንደተረጋጋች ነበር።
አለም ወደ ሆቴሏ ከተመለሰች በኃላ ሱፍ ኮቷን አልጋ ላይ ወረወረች።እጆቿ በላብ ተጠምቀው ስለነበረ እርጥብ ነበሩ እና ጉልበቶቿ መንቀጥቀጣቸው አሁንም አላቆሙም
ከመደንገጧ የተነሳ የማቅለሽለሽ ስሜት ነበራት። አልጋዋ ለይ ተዘርራ ተኛችና ስለቆይታዋ በምልሰት ማሰላሰል ጀመረች፡፡
በጣም መጥፎው ጉዳይ ወደፊት የሚከሰተው እንደሆነ ብታስብም ለጊዜው ደስ ብሏታል፣ ቢሆንም ነገ ተነገ ወዲያ ስለሚሆነው ነገር መፍራቷ አልቀረም። ዛሬ ያገኘቻቸው ሶስት ሰዎች በዋናነት ዳኛው ደግሞ በተዘዋዋሪ ከእናቷ ጋር የሚያያይዝ ታሪክ ያላቸው ናቸው። ከዘመናት በኋላ እነሱን መጋፈጥ ቀላል ውሳኔ አልነበረም እና በምንም አይነት ሁኔታ እሷን በማየታቸው ደስተኞች ሊሆኑ እንደማይችሉ መጀመሪያም ግምቷ ነበር፣ እናም ካገኘቻቸው
በኃላም የተረዳችው ያንን ነው..ትንሽም ቢሆን ጁኒዬር ካልሆነ በስተቀር ኩማንደሩና አቶ ፍሰሀ ጥላቻቸው በግልፅ ግንባራቸው ላይ ይነበብ እንደነበረ ታዝባለች፡፡
አቶ ፍሰሀ በሻሸመኔ ከተማና በአካባቢው በጣም ሀብታም እና ኃያል ሰው ነው። ያንን ደረጃ ያገኘው ደግሞ በመልካም አመራር እና በስራ ትጋቱ ብቻ አይደለም። ዕድሜ ልኩን ያካበተውን ሀብት ጠብቆ ለማቆየት ባለው ኃይል ሁሉ በስውርም ሆነ በግልፅ ሲዋጋ እና ሲፋለም ኗሯል።አቶ ፍሰሀ እና ቤተሰቡ ላይ እያቀረበችውን አይነት ክስ ማቅረብ እንደእብደት እንደሚቆጠር ታውቃለች..ከዳኛው ፊት ላይ ያነበበችውም ያንኑ ስሜት ነው፡፡ አይደለም በጥርጣሬ ግድያ ቀርቶ እጅ ከፍንጅ ተኩሰው ሲገድሉ ቢታዩ እንኳን ባርቆባቸውን ነው በሚል ተስተካክሎና ለዛም ምስክርና ማስረጃ ተጠናክሮ በቀላሉ ነፃ እንዲወጡ እንደሚደረግ በቀላሉ መገመት ትችላለች፡፡ግን ከእሷ ጋር መጋፈጥም ቀላል እንዳልሆነ በሂደት እንዲረዱ እንደምታደርገቻው እርግጠኛ ነች፡፡
ስለ ጁኒየር ስታስብ የተሰማት የተለየ ነገር ነው፡፡በሴቶች ዙሪያ ያለው አመለካከት የተለየ ስለሆነ አቀራረቡም ከአባቱና ከኩማንደር ጓደኛው በመጠኑም ቢሆን የሚለይ ማራኪ ሆኖ ነው ያገኘችው። አለም በጉርምስና ዕድሜው ላይ እያለ ካያቸው ፎቶ ግራፉ ብዙም አልተለወጠም። መልከ መልካምነቱን ፍላጎቱን ለማሳካት እና እንስቶችን ለማማለል ሲጠቀምበት እንደኖረ ታውቃለች። ለእሱ ሰውን ከመግደል ይልቅ በፍቅር መውደቅ ቀላል እንደሚሆንለት አሰበች፡፡እናም በገዛ ሀሳቧ ፈገግ አለች፡፡
ቀጥሎ ወደአእምሯዋ የተሰነቀረው ኩማንደር ገመዶ ነው፡፡እስከአሁን ኩማንደሩን ለማንበብ እና እንዲህ ነው ብሎ ለመተንበይ በጣም ከበድ ነው የሆነባት.. እርግብ ይሁን እባብ… ወይንም ሁለቱንም አዳብሎ የያዘ እስስት ለመለየት ከባድ ነው የሆነባት፡፡ ስለ እሱ የነበራት ግንዛቤ ትንሽ የተለየ ነው።በስብሰባ ክፍል ውስጥ እንደሌሎቹ አይኖቹን ማየት አልቻለችም። እሱ ከአያቷ የፎቶ ማከማቸ ሳጥን ውስጥ የልጅነት ፎቶውን ካየችው ከዛ ወጣት ልጅ በእጅጉ የተቀየረ ….የበለጠ ከባድ እና ጠንካራ የሆነ መስሎ ታየት። የመጀመሪያ እይታው ተንኮለኛ፣ ወዳጃዊ ያልሆነ እና አደገኛ መስሎ ነበር የተሰማት።ከእነዚህ ሰዎች መካከል አንዱ እናቷን እንደገደለ እርግጠኛ ነች። እናቷ ሰሎሜ በተከሳሹ ሊቁ እጅ አልተገደለችም።
"አለም ክሱን ከእንደገና ማስከፈት እና የእናትሽን እውነተኛ ገዳይ ለፍርድ ማቅረብ የአንቺ ኃላፊነት ነው፡፡" በየቀኑ ለራሷ የምትነግረው ጉዳይ ነው።"ይህ ለእናትሽ ልታደርጊው የምትችይው ትንሹ ነገር ነው."
ብዙውን ጊዜ አያቷ በቤቱ ውስጥ ተበታትነው ከነበሩት ብዙ የድሮ ፎቶግራፎች ውስጥ አንዱን በተደጋጋሚ ጊዜ በጥንቃቄ ይመለከቱ ነበር።ያ ፎቶ ደግሞ እናቷ ሰሎሜ በአፍላ ወጣትነቷ ዘመን ከእድሜ እኩዬቿ ጁኒዬር እና ገመዶ መሀከል ቆማ የተነሳችው አሮጌ ፎቶ ነው፡፡ ፎቶውን መመልከት ሁልጊዜ እንድታዝንና እና በናፍቆት እንድታለቅስ ያደርጋታል፣ እና የልጅ ልጇ ምንም ነገር ብታደርግ ሊያስደስታት አይችልም ነበር።ይሁን እንጂ እስከ ጥቂት ወራት ድረስ አለም ጎበና እናቷ ሰሎሜን በመግደል ተጠርጣሪው ማን እንደነበረ አታውቅም ነበር።ያንን ሚስጥር ያወቀችበት እለት በአለም ሕይወት ውስጥ በጣም ጨለማው ቀን ነበር።
ትዝ ይላታል በወቅቱ የስራ ገበታዋ ላይ ሆና እየሰራች ሳለ….ከሜቅዶኒያ ተደውሎላት በአስቸኳይ ድረሺ ስትባል በፍጥነት ነበር የሄደችው… ፡፡ተቋሙ ጸጥ ያለ፣ በበጎ ፍቃደኞች እና በተንከባካቢ ባለሙያዎች የተሞላ ነበር። አያቷ ወደ ሆስፒታል ተወስደው ነበር…. ወዲያው ወደሆስፒታል አመራች፡፡ በሽታዋ የእርጅና በሽታ የተጫጫነው ነበረ፡፡ተስፋ መቁረጥ እና እርጅና ከካንሰር በሽታቸው ጋር ሲደመር የመጨረሻ እስትንፋሳቸውን እየሳቡ እንደሆነ ገባት፡፡ ዶክተሮቹንም ስታናግር አያቷ አስጊ ሁኔታ ላይ እንዳሉ ተነገራት። ፀጥ ወዳለው የአያቷ ክፍል ገብታ ወደ አልጋቸው ተጠጋች። የአያቷ አካል በሚታይ ሁኔታ ተዳክመው ነበር።አለም የጎበኘቻቸው ከሳምንት በፊት ስለሆነ በነዛ ጥቂት ቀናት ውስጥ እንደዛ አይነት ጉልህ ለውጥ ማየቷ አስደነገጣት።አያቷ መላ አካላቸው ድቅቅ ብሎ ቢደክምም ዓይናቸው ግን ህያው ነበር፣
"እዚህ አትግቢ" ትንፋሿቸውን አጠራቅመው ጮሁባት "አንቺን ማየት አልፈልግም
…በአንቺ ምክንያት ነው!"
"ምንድነው አያቴ?" አለም በጭንቀት ጠየቀች።
"ምንድን ነው የምታወሪው?" "እዚህ አልፈልግሽም."
አለም አያቷ እሷ ላይ ባሳዩት ብስጭት እና ጥላቻ በመሸማቀቅ ወደ ሐኪሙ እና ወደ ነርሶች ዞር ብላ ተመለከተቻቸው። "ልታየኝ ለምንድነው የማትፈልገው? ያለዋት ብቸኛ ዘመድ እኔ ነኝ…የልጅ ልጇ ነኝ፣››በእፍረት ተውጣ ልታስረዳቸው ሞከረች፡፡
አያትዬው ወቀሳቸውን ቀጠሉ"እናትሽ ባንቺ ጥፋት ነው የሞተችው፣ ታውቂያለሽ፣ ባንቺ ምክንያት ባይሆን ኖሮ ልጄ አትሞትም ነበር. . " አያቷ ማልቀስ ጀመሩ…..አለም ምታደርገው ነገር ጠፋት ፡፡
"ለእናቴ ሞት ተጠያቂዋ እኔ ነኝ እንዴ?"
የአይቷ አይኖች ከተደበቁበት ፈጠው ወጡ። "አዎ" ብላለው በቁጣ አረጋገጡላት።
"እኔ እናቴ ስትሞት ገና ሕፃን ነበርኩ እኮ፣ ጨቅላ ህፃን" ስትል ተከራከረች፣የአያቷን የአእምሮ ጤንነትም መጠራጠር ጀመረች፡፡"እንዴት በጨቅላ እድሜዬ የምትይውን ማድረግ እችላለሁ?"
" ጠይቂያቸው።"
‹‹ማንን አያቴ? ማንን ልጠይቅ?"
"የገደሏትን...ፍሰሀ… ልጁ ጁኒዬር እና ኩማንደር ገመዶን… እናም አንቺም ነበርሽ አንቺ ነሽ "አያቷ ንግግራቸውን ሳይቆጩ ጥልቅ ኮማ ውስጥ ገቡ፡፡ ከዛ በኋላ አለም ከክፍሉ በዶክተር እየተመራች ወጣች። በገዛ አያቷ የቀረበባት አስቀያሚው ክስ እስክትደነዝዝ ድረስ ነበር ያስጨነቃት፡፡ በአንጎሏ ውስጥ ተንሰራፍቶ ማሰቃየት ብቻ ሳይሆን ነፍሷ ድረስ ዘልቆ ነው ያጠቃት ።አያቷ ለእናቷ ሞት እሷን ተጠያቂ አድርገው እንደሚያስቧት ከሰማች ጊዜ በኋላ ስለእናቷም ሆነ ስለአስተዳደጓም ወደኋላ መለስ ብላ እንድታስብ ተገደደች፡፡ አያቷ ከእሷ ጋር የነበራት ግንኙነት ለምን የሻከረ እንደነበረ ሁል ጊዜ

❤42👍3🔥2