#ኢትዬጵያዊ_ ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ካርሎስና እና ኑሀሚ በአምስተኛ ቀናቸው ነበር ከአከባቢው የተንቀሳቀሱት፡፡በዛን ወቅት ኑሀሚ የተመረዘችው መርዝ ሙሉ በሙሉ ከሰውነቷ ተወግዶ… የሟሸሸ የነበረም ሰውነቷ ተነቃቅቶ….ጥንካሬዋም በተወሰነ ፐርሰንት ተመልሶ ነበረ፡፡ ባለውለታቸውን የሆነችውን ጎጆ በፍቅር ተሰናብተው አካባቢውን ለቀው የአማዞንን ወንዝ ደርቻ ተከትለው በምስራቅ አቅጣጫ ለአንድ ሰዓት ተኩል በእግር ከተጓዙ በኃላ አንድ እሮጌ ጀልባ የያዘ ግለሰብ አጋጠማቸው፡፡ከእሱ ጋር በገንዘብ ተደራደሩና ታብቲንጋ ከተማ ድረስ እንዲያደርሳቸው ተስማምተው ጉዞ ጀመሩ፡፡የዛኑ ቀን አመሻሽ ላይ ያሰቡበት ቦታ ደረሱ፡፡
‹‹ይህቺ ከተማ የአየር ትርንስፓርት አገልግሎት አላት ነው ያልከኝ..?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹አዎ አላት..ማኑሳ ድረስ መሄድ ይቻላል፡፡››
‹‹ታድለን…በቃ ነገሮች ወደመጨረሻው ምዕራፍ እየተቃረበ ነው ማለት ነው…ተዲያ ወደከተማው እንግባና የአየር ትኬት ካገኘን እንሞክራ››
‹‹አይ ወደከታማ መግባት አንችልም..፡፡እንደምታያት ይህቺ አንስተኛ የጠረፍ ከተማ ብራዚል ውስጥ ትገኝ እንጂ ለኮሎምቢያ ቅርብ መሆኗን እንዳትረሺ..ያ ማለት ደግሞ የዳግላስ ተፅእኖ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ይኖራል ማለት ነው፡፡ በተለይ ወደ ብራዚል ከገባን ቀጥታ የአየር ትራንስፖርት የሚገኝባት ከተማ ይህቺ ስለሆነች ቀጥታ ወደእዚህ እንደምንመጣና ወደአየር መረፊያ ጎራ እንደምንል በቀላሉ ይገምታል..ስለሆነም ከተማው ውስጥ ዋና ዋና ቦታዎች እና በተለይ ደግሞ አየር ማረፊያ ላይ ሰዎቹን እንደሚያስቀምጥ እርግጠኛ ነኝ፡፡
‹‹እና ምን ይሻለናል?፡፡››በስጋት ጠየቀችው፡፡
‹‹ረጅሙን መንገድ ነው የምንመረጠው..ማለት አሁንም ወደ ምስራቅ ጉዞችንን እንቀጥልና ወደ ቤንጃሚን ኮንስተንት ከተማ ነው የምንሄደው፡፡››
‹‹ቤንጃሚን ኮንስተንት ደግሞ ማን ነች?››
ቤንጃሚን ኮንስተንት አማዞን ደን ውስጥ ከበቀሉ የብራዚል የጠረፍ ከተሞች ውስጥ አንዷ ስትሆን ከተማዋ ጃዋሪ በተባለ ወንዝና በአማዞን ወንዝ ተከባ የምትገኝ ትንሽ ከተማ ነች፡፡ከዚህ አሁን ካለንበት ከተማ በጀልባ የሁለት ሰዓት ቢፈጅብን ነው፡፡ማንም ወደ ዛች ከተማ ይሄዳሉ ብሎ እይገምተንም…እዛ ከደረስን በኃላ የተሻለ የተባለ ዘመናዊ ጀልባ እንከራይና ቀጥታ ወደ ማናአስ እንጓዛለን፡፡
‹እንዳልክ …ግን የሆነ ቻርጅ ያለበት ቦታ ፈልግን ስልኬን ቻርጅ ማድረግ አለብኝ፡››የምታስበውን ነገረችው፡፡
‹‹ምን ሊያደርግልሽ?››
‹‹ትቅዳለህ..ለወንድሜ ደውዬ ቢያንስ እስከሁን በጤና መሆኔን ላሳውቀው ነዋ፡፡››
‹‹አይ አይሆንም…ስልክሽን አብርተሸ ለወንድምሽ ደወልሽለት ማለት ያለሽበትን አካባቢ ቀጥታ ለሀገርሽ መንግስት እናም ጉደዩን ለሚከታተሉ ለአካባቢው መንግስታት አሰወቅሽ ማለት ነው..ያ ሆነ ማለት ደግሞ ዳግላስም በቀላሉ ዜናውን አገኘ ማለት ነው፡፡እና ሁሉም እኛን ለማግኘት በአካባቢው አሰሳ ይጀምራሉ…ከዚህ በፊት እንዳለኝ ልምድ ደግሞ ከየትኛውም መንግስት ቀድሞ ደጋላስ አፈፍ እንደሚያደርገን እርግጠኛ ነኝ››
‹‹እና ምን ይሻላል?››
‹‹የሚሻለውማ..ማናስ እስክንገባ መቻል….ነው…ወንድምሽም ዘላለም ከሚያጣሽ…ስድስት ሰባት ቀን በናፍቆት እና በትካዜ ቢሰቃይ ይሻላል፡፡አሁን አንቺ እዚሁ አካባቢ እራስሽን ከሰው እይታ ከልለሽ ትጠብቂኛለሽ… እኔ እራሴን ለውጬ ከታማ ገብቼ እመለሳለሁ››
‹‹እንዴ… እኔን እዚህ ብቻዬን ጥለኸኝ ምን ትሰረለህ?››
እጁን ወደኪሱ ሰደደና የሆነ መሀረብ አውጥቶ ቋጠሮውን ፈታና ሁለት የጨው አንኳር የሚመስል አብረቅራቀ መአድን አነሳና በእጇ መዳፍ ላይ አስቀመጠ፡
‹‹ምንድነው?››በመገረም እያየች ጠየቀችው፡፡
‹‹እንቁ ነው..በደኑ ውስጥ በአጋጣሚ በስራ ላይ እያለው በእጄ የገባ ነው..እንደዚህ አይነት ንብረት በምንም አይነት ሁኔታ ቢሆንም በእጅ ከገባ ለገዛ ጥቅም ደብቆ መስቀመጥ በሞት የሚያስቀጣ አደገኛ ወንጀል ነው..በወቅቱ ለዳግላስ ማሰረከብ ነበረብኝ…እኔ ግን ደመነፍሴ አንድ ቀን አጣብቂኝ ውስጥ ስገባ ይጠቅምሀል ብሎ ሹክ ስላለኝ..የመጣው ይምጣ ብዬ ደብቄ አስቀምጬው ነበር፣.እና አሁን ወደከተማ ሄጄ ወደገንዘብ ልቀይረው...እረጅም የጀልባ ጉዘ ስለሚጠብቅ ብዙ ገንዘብ ያሰፈልገናል…››
መጀመሪያ እንቁውን መለሰችለት..መልሶ በመሀረቡ ቋጠረውና ወደኪሱ ከተተው..፡፡
ከሷ የእጅ ቦርሳዋን አነሰችና ዚፕን ከፈተች፣ከላይ ያሉትን እቃዎች አወጣች ፡፡ፊቱን አዙሮ ሊሄድ ሲል ከስር እንደታሸገ የተቀመጠውን ዶለር መዥርጣ አወጣችና እጁ ላይ አስቀመጠችለት፡፡
‹‹ይሄ አይበቃም?››
አይኖቹ በመገረም ደመቁ‹‹አንቺ ይሄን ሁሉ ብር ከየት አመጣሽ?››
የዛሬን አያድርገውና ሀለቃህ ዳግስ ነበር የሰጠኝ..እና አይበቃም›››….ብላ እንዴት እንዳገኘች ታሪኩን አስረዳችው
‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ..ይሄ እኮ በጣም ብዙ ብር ነው….በይ አሁን ጀልበ እንፈልግ››አለና ብሩን መልሶላት ቦርሳ ውስጥ ከከተተ በኃላ ተያይዘው ወደፊት ለፊት መራመድ ጀመሩ፡፡
እንደተነጋገሩት እዛው አድረው ንጊት ላይ ወደ ቤንጃሚን ኮንስተንት ከተማ በጅልባ ተጓዙ፡፡ እዛ አንድ ሰዓት ብቻ በማሳለፍ ሌላ ዘመናዊ የተባለ ጀልባ ተከራዩና ወደአማዞኒያ ግዛት ዋና ከተማ ማናአስ ጉዞ ጀመሩ፡.ያው ጉዞ ቀላል አልነበረም….6 ቀን ነው የፈጀባቸው ፡፡ግን ደግሞ በህይወት ረጅም ዘመን ለመኖር ስድስትና ሰባት ቀን መስዋት ማድረግ ያን ያህል ክፉ የሚባል ስላልሆነ አላማረረችም ፡፡
…ታብቲንጋ….ሳኦ ፍረንሲስኮ…ኮረንቲዛ….ዲ አማተራ…ሳኦ ዶሚንጎ….ሳንታ አንቶኒኦ….ሳኦ ፍሊክስ… ሳንታ ሉዚያ… የመሳሰሉን አያሌ ታዋቂ ቦታዎችንና የኣማዞን ወንዝ ዳር ከተሞችን አቋርጠው ማናአስ ከተማ ደረሱ ፡፡
ማናአስ(Manaus) በሀገረ ብራዚል የኣማዞኑያ ግዛት ዋና ከተማ ነች፡፡በብራዚል 2.2 ሚሊዬን ኑዋሪዎች የሚኖሩበት 7ተኛው ትልቋ ከተማ ስትሆን ከተማዋ በአማዞን ደን ውስጥ ከተቆረቆሩ ከ1 ሚሊዬን በላይ ኑዋሪዎች ካሏቸው ሁለት ትልልቅ ከተሞች መካከል አንዶ እና ዋነኛዋ ነች.››
በዛ ላይ የአማዞን ደንን እና የአማዞን ወንዝን ሚስጥር ለመበርበር እና ጥናት ለማጥናት ከመላው አለም የሚሰባበሰቡ ሳይንተስቶችና ተመራማሪዎች በዋናነት የሚከትሙባት ከተማ ነች፡፡በዚህ የተነሳ የአማዞን ልብ የሚል ቅፅል ስም ይሰጧታል፡፡በተጨማሪ አንዳንዶችም የትርፒካሎ ፓሪስም እያሉ ያሞካሻታል፡፡
ማናአስ ከተማና አካባቢው በኬሚካል ፕሮጀክት..በለውዝ ምርት ….በሳሙና ምርት….በመርከብ ግንባታ እና በጎማ ተክል ምርት በጣም የታወቀች ነች፡፡፡በተለይ በጎማ ምርት ከ1800 አመት በፈት ጀምሮ የታወቀች በመሆኗ ከሀገሪቱ ሀብታም ከተሞች ግንባር ቀደሞ እንድትሆን አስችሏታል፡፡ማናአስ ከተማ በ2014 እ.ኤ.አ የአለምን ዋንጫ ካስተናገዱ 12 የብራዚል ከተሞች አንዷ እንደሆነች ይታወቃል፡፡በከተማዋ ምስራቅ አቅጣጫ ድፍርሱ የኒግሮ ወንዝ እና ሰማያዊው የሶሊመስ ወንዝ አንድ ላይ ተቀላለቅሎ ወደአማዞን በገባርነት የሚፈስባት ልዩና አስደማሚ ስፍራንም በመደመም ማየት ይቻላል፡፡

👍86❤14👏1
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ _ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ባልና ሚስቶቹን ቤታቸው ወስዶ እንደጣላቸው ቀጥታ የመኪናውን መሪ ወደአስቴር ቢሮ ነው የጠመዘዘው…ገብቶ ምሳ እንዲበላ ቢለምኑት እንኳን እሺ አላለቸውም፡፡እንደሚመጣ አልነገራትም ቀጥታ ከቢሮዋ ፊት ለፊት አቆመና ደወለ
‹‹ሄሎ ወንድሜ….እንዴት ነው ቢሾፍቱ በጣም ተመችታሀለች መሰለኝ?፡፡››
‹‹መጥቻለው….ምሳ አትጋብዢኝም?፡፡››
‹‹የእውነት መጣህ?››
‹‹አዎ ቢሮሽ ፊት ፊት መኪናዬን አቁሜያለው፡፡››
‹‹በቃ መጣሁ››ብላ ስልኩን ዘጋች….5 ደቂቃ ነው ያስጠበቀችው፡፡ገና የቢሮዋን የህንፃ ደረጃ ስትወርድ ጀምሮ ነው አይኑ ውስጥ የገባችው…ሙሉ ሮዝ ቀለም ያለው ጉረድ ቀሚስና ኮት ለብሳለች…ፀጉሯ ወደኃላዋ ትከሻዋ ላይ እንዲተኛ ተደርጎል…ውብ ሆናለች….መኪናዋን ስለምታውቃት ብዙም ሳትደነጋገር ቀጥታ ወደእሱ ነው ያመራችው…ይህቺ ሴት እህቱ እንድትሆን አይደለም የሚፈልገው…ጓደኛም እንድትሆነው አይደለም…የፍቅር አጋሩ ሚስቱ ሊያደርጋት ነው ምኞቱ..ይሄ ምኞቱ ደግሞ አሁን በቅርብ በውስጡ የበቀለ ስላልሆነ ህመሙ ቀላል አይደለም…ገና አፍ ፈቶ በኮልታፋ አንደበት መንተባተብ በጀመረበት በጮርቃነት እድሜው ጀመሮ እሷ ሚስቱ እንደሆነች ያስብ ነበር፣እርግጥ በዛን እድሜ ሚስት ማለት እራሱ ትርጉሙ ምን ማለት አንደሆነ አያውቅም ነበር፣ቢሆንም ጭላንጭል የሆነ ግንዛቤ ነበረው…ሚስት ማለት አንድ ክፍል ውስጥ አንድ አልጋ ላይ ሁሌ አብራ
የምትተኛ ሴት እንደሆነች ከአባትና ከእናቱ ግንኙነት መረዳት በቻለበት ጊዜ ነው፣ከእሱ ጋር ለዘላለም መተኛት ያለባት ሴት አስቴር እንደሆነች ወስኖ የነበረው፣በዛን የልጅነት ጊዜ እናቷ የቤታቸውን እንጀራ ልትጋግር ስትመጣ አስከትላት ስትመጣ ጀምሮ እዛው እሷን ማስቀረት ምኞቱ ነበር…እና ያ ምኞት ግለቱን ጠብቆ እየፋመ ነበር የቀጠለው…
ጊዜው ሲደርስ ግን ነገሮች ቀደም ብሎ እንዳሰባቸው ቀላል አልነበሩም…ገቢናውን ከፈተላት ገባች.. ጉንጩን አገላብጣ ሳመችው…ሁል ጊዜ የእሷ መሳም ከሌላው መሳም በጣም ይለይበታል…ወፈር ብሎ ወደፊት ግልብጥ ያለው ፍም ከንፈሯ ሰውነቱ ላይ ሲርፍ የተለየ ሙቀት ነው ሰውነቱ የሚያመነጨው…ልክ የጋለ ቢላዋ አካል ላይ ሲያርፍ የሚሰማው አይነት ትሽሽሽ..የሚል የማቃጠል የመለብለብና የመላጠ ስሜት……
‹‹አንተ ወፍረህ ነው የመጣሀው….ስራ ላይ ነበርክ ወይስ ጫጉላ ሽርሽር ላይ?››
‹‹በይው…አንቺም ተመችቶሻል…ምሳ የት አንብላ?››
‹‹ወደ እኔ ቤት ንዳው››
‹‹ምነው ከሰዓት ስራ የለሽም እንዴ?››
‹‹ዛሬ ቅዳሜ እኮ ነው…ግማሽ ቀን ነው የምንሰራው››
‹‹እና አራበሽም ..በልተን ብንሄድ አይሻልም?››
‹‹አይ ሰራተኛዬ አዘጋጅታ እየጠበቀችን ነው…ዘና ብለን ቤታችን ብንበላ ይሻላል….ወንድሜ ስለመጣህ ደስ ብሎኛል››
‹‹እኔም ከሰዓት ስራ ስለሌለሽ ደስ ብሎኛል››ብሎ መኪናዋን ወደ አስፓልት መሀል አስገባና ነዳት….የእውነትም ከሰዓት ስራ የለኝም ብላ ወደቤቷ ይዛው እየሄደች በመሆኑ ከፍተኛ ደስታ ተስምቶታል…ከአመታት በኃላ መልሶ ዛሬ እድሉን ይሞክራል፡፡አዎ በስደት ከሄደበት ባእድ ሀገር ተመልሶ የመጣውም ለዚሁ ነው፡፡ከባሎ እንደተለያየችና እሱም በዛ ንዴት ከሀገር ውጭ መሰደዱን ሲሰማ ነው ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጎ የመጣው…አንሆ ተመልሶ በመጣበት ባለፉት ስድስት ወሮች እሷን ከገባችበት ድባቴ እንድትወጣና ያልተሳካ ትዳሯ ከፈጠረባትን የስነልቦና መሰበር እንድታገግም እንደወንድም እንደ ጓደኛም ከዛም አልፎ እንደባለሞያም ከጎኗ ሆኖ ሲያግዛትና ሲደግፋት ነበር…አሁን ግን ልቧ ሌላ ፍቅር
ለማስተናገድ ዝግጁ ነው ብሎ ያስባል..በዛ ላይ የእሱ እና የእሷ ፍቅር አዲስ ዛሬ የበቀላ ሳይሆን ድሮ በየሁለቱም ልብ ተዳፍኖ ያለ ነው…አሁን ያንን መቆስቆስና መልሶ እንዲቀጣጠል ትንሽ የፍቅር ቤንዚል ማርከፍከፍ ነው…ለዚህ ድርጊት ያበረታታው ሰሞኑን ያየው በአቶ ሃይለልኡል እና በወ.ሮ ስንዱ መካከል የተከሰተው የፍቅር ግርሻ ነው፡፡
‹‹አዎ…አስቴርን አገባታለሁ…ከበፊት ባሏ የወለደችውን አንድ ልጅም እንደልጄ አድርጌ አሳድገዋለው››በውስጡ አልጎመጎመ…‹‹እና በቅርብ ቀን እሷም ወንድሜ የምትለውን ጥሪ ትተውና ባሌ ብላ ትጠራኛለች…ልጇም አጎቴ ብሎ የሚጠራውን አቁሞ አባቴ እንዲለኝ
አደርጋለው››ይሄንን ስላሰበ ብቻ ውስጡ በደስታ ተፍነከነከ..ቤት ሲደርሱ እውነትም እንዳለችው ቆንጆ ምሳ ተዘጋጅቶ ነበር የጠበቃቸው፡፡እየተጎራረሱ በሉ፡፡ከምግብ በኃላ ብና ተፈላላቸው..እሷ ሁለት ሲኒ እሱ አንድ ሲና ጠጡና ተጠናቀቀ፡፡
‹‹እዚሁ ልንገራት ወይስ ይዣት ወጣ ልበልና ዘና ያለ ቦታ ወስጄ ዘና ባለ ስሜት ላይ ከሆነች በኃላ ልንገራት ››እያለ ሲወዛገብ ቆየና‹‹እ…ፕሮግራማችን እንዴት ነው….?ወጣ እንበል ወይስ እዚሁ ነው የምንቆየው?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹አይ…ወጣ እንላለን..ሱፐርማርኬት ወጥቼ መሸማመት አለብኝ..መጠነኛ ድግስ ደግሳለው፣ማታ እንግዳ አለብኝ››
ንግግሯ ግራ አጋባውም.. ደነገጠም፡፡
‹‹የማታ እንግዳ ምን አይነት ነው?›› our
‹‹አንተም አለህበት…ዛሬ እዚህ ነው አይደል የምታድረው?››
እሷ ጋር እንዲያድር ስለጠየቀችው ደስ ብሏታል ..ግን እንግዳውስ…?ለመሆኑ ማን ነው
…?ሴት ነው ወንድ?፡፡‹‹እሺ ..እዚህ ነው የማድረው…ግን እንግዳውስ?››
‹‹እንግዲህ እሱን ከመጣ በኃላ ነው የምናውቀው…ልደር ካለ ግን እምቢ ማደር አትችልም የምለው አይነት ሰው አይደለም››በማለት ግራ አጋቢ መልስ ሰጠችው፡፡መልሷ ይብልጥ ቁርጠት ለቀቀበት…ይሄኔ ከመስሪያ ቤቷ ባለደረቦች አንዱ ነው….ሀለቃዋ ይሆን እንዴ…?ቢሆንስ ልደር ስላለ እንዴት እሺ ልትለው ትችላለች..?››ወይ ሴቶች ምን አይነት ቅኔ የሆኑ ፍጡሮች እንደሆኑ ሁሌ እንደደነቀው ነው፡፡ወንድም ሴትም በአንድ ላይ ሰው ተብሎ
መፈረጁ አግባብ አይደለም….አስተሳሰባችን እምነትና ፍላጎታችን ምኑም እኮ አይገናኝም››ሲል በውስጡ አብሰለሰለና..ነገሮች እስኪደርሱ ጠብቆ ለማየት ወሰነ…
‹‹ከዛ በፊ የተመቻቸ ጊዜ ካገኘው ነግራታለሁ…እንደውም ከማታው ፕሮግራሞ በፊት የእኔን ሀሳብ መስማት አለባት››የሚል ድምዳሜ ላይ ደረሰ‹‹በቃ እንሂዳ››አላት፡፡
‹‹እሺ፣ተነስ ብላ ቦርሳዋን አንጠለጠለችና ተነሳች..ተያይዘው ወጡ ..ያለችው ሱፐር ማርኬት ይዛው ከገባች በኃላ ምትፈልገውን ነገሮች ሁሉ ተገዝተው በመኪናው ከተጫኑ በኃላ.. ማኪያቶ እንጠጣ ብሎ አንድ ፀጥተኛ ካፌ ይዞት ገባና..ፊት ለፊት እንደተቀመጡ እንደምንም እራሱን አጠንክሮ ወደነጥብ መንደርደር ጀመረ
‹‹ለምን ወደውጭ እንደሄድኩ ታውቂያለሽ አይደል?››
‹‹ሁለተኛ ዲግሪህን ለመማር ነዋ››
‹‹አይ ያማ ሽፋን ነው….እውነተኛ ምክንያቴን አንቺም በደንብ ታውቂዋለሽ..ወደውጭ የሄድኩት ባንቺ ተበሳጭቼ ነው፡፡››
‹‹አንተን ለማበሳጨት ብዬ ግን ምንም ያደረኩት ነገር የለም››
‹‹እሱን ማግባት አልነበረብሽም››
‹‹ለምን …ታዲያ አንተን ወንድሜን ማግባት ነበረብኝ?››
‹‹ምን ችግር አለው?እርግጥ እንደወንድምና እህት አንድቤት አድገናል..ግን የስጋ ትስስር አልነበረንም››

👍86❤9😁2🔥1
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================
አላዛር ቀኑን ሙሉ ሚስቱን ፍለጋ ሲባዝን ውሎ ሰባት ሰዓት አካባቢ ስልክ ተደወለለት..ቁጥሩን አያውቀውም…ግን ደግሞ ሰሎሜን ካገኛችሁ ደውሉልኝ ብሎ አደራ በማለት ስልኩን ለብዙ ሰው ስለሰጠ በትልቅ ተስፋና ጉጉት ነበር በፍጥነት ያነሳው፡፡
‹‹ሄሎ አላዛር ነህ?››ጎርናና ሻካራ የወንድ ድምፅ፡፡
‹‹አዎ ነኝ ፡፡ማን ልበል?››
‹‹ይሄንን ድምፅ አታውቀም?››
ተበሳጨ…ዛሬ የማንንም ሰው ድምፅ ለማወቅ ለአእምሮው የቤት ስራ የሚሰጥበት ሁኔታ ላይ አይደለም፡፡አንኳን የማያውቀውን ሰው ድምፅ የራሱንም ማንነት ለመርሳት ትንሽ ነው የቀረው‹‹ይቅርታ ማን ልበል..?እየነዳሁ ነው››አለ ኮስተር ብሎ፡፡
‹‹አሌክስ ነኝ››
በታላቅ ድንጋጤ መኪናውን ወደ ዳር አወጣና አቆማት…..
‹‹አሌክስ አልኬስ…አሌክሶ የእኛ እንዳትሆን?››
‹‹አዎ አሌክስ ነኝ…አሌክስ የእናንተው…የልጅነት እናም የጉርምስና ጊዜ ጓደኛችሁ››
‹‹ይገርማል…ፈፅሞ ያልጠበቅኩት ጉዳይ ነው…ለመሆኑ አለህ…?
ድሬደዋ እንዳለህ ሰምቼ ነበር..ግን ስልክህን ማግኘት ስላልቻልኩ ልደውልልህ አልቻልኩም፡፡››
‹‹አዎ አሁን ግን አዲስ አበባ ገብቼለሁ››
‹‹በጣም ይገርማል…አሌክሶ አሁን የሆነች ችግር ገጥሞኝ እሷን ለመፍታት እየተሯሯጥኩ ነው…..ይህ ያንተ ቁጥር ከሆነ ቆይቼ ልደውልልህ?››
‹‹ቆይ..እኔም ስለችግርህ ለማውራት ነው የደወልኩልህ››
አላዛር ድንግርግር አለው‹‹አልገባኝም?››
‹‹ችግርህ ስለሰሎሜ አይደለች..ማለቴ እሷን እየፈለክ አይደለህ?›››
የሚስቱን ስም ሲጠራ ይበልጥ ደነገጠ‹‹አዎ ግን እንዴት አወቅክ..ነው ወይስ እቴቴ ደውላልህ ነው?››
‹‹አይ…ከቴቴ ጋር አልተደዋወልንም.ሰሎሜ እኔ ጋር ነች››
አላዛር ይሄንን አረፍተ ነገር ሲሰማ ጭንቅላቱ ላይ ስል ሰይፍ አርፎ ለሁለት የሰነጠቀው ነው የመሰለው..በሰከንዶች ሽርፍራፊ ብዙ ብዙ ነገር ነው ያሰበው፡፡‹‹እንዴት እንዴት ብለው ተገናኙ?ከዚህ በፊትም በድብቅ ይገናኙ ነበር ማለት ነው…?እሱ እጅ ከገባች እንዴት ነው መልሼ የራሴ ላደርጋት የምችለው..?ነው ወይስ እስከወዲያኛው እያጣኋት ይሆን?፡፡››ሲል የስጋት ሀሳብ አሰበ፡፡
አለማየሁ ለረጅም ደቂቃዎች መልስ ሳይሰጠው ዝም ስላለበት ግራ ተጋብቶ ‹‹አላዛር…ምነው ዝም አልክ ..?ሰምተኸኛል?››
‹‹አዎ ሰምቼሀለው…ግን ምንም አልገባኝም…እንዴት ልታገኛት ቻልክ?››
‹‹እሱ ታሪኩ ረጅም ነው ..ናና እንነጋገራለን››
‹‹የት ነው የምመጣው?››
‹‹ፓሊስ ጣቢያ..ማለቴ…›› ብሎ ትክክለኛ አድራሻውን ነገረው፡፡
‹‹ፖሊስ ጣቢያ ምን ትሰራለች?››
‹‹አንተን ልትከስ መጥታ ልበልህ..?ለማንኛውም እየጠበቅኩህ ነው.. ፈጠን ብለህ ና››ብሎት ስልኩን ዘጋበት፡፡
አላዛር ድንዝዝ ነው ያለው…መኪናውና አንቀሳቅሶ በፍጥነት መሄድ እንዳለበት እንኳን ማስታወስ አላቻለም….‹‹የምን ክስ …?መቼስ ምንም አይን አውጣ ብትሆን ባሌ ከእኔ ጋር ግንኙነት አላደርግም አለኝ ›ብላ አትከሰኝም…..እንደዛማ አታደርግም…ደግሞ ካልጠፋ ቦታ ስንት ክፍለከተማ አቋርጣ እንዴት እዛ ድረስ …?እስከዛሬ እያወቀች እንዴት መቀየሩን ሳትነግረኝ ..?እንዲሁ እንደተብከነከነ እና የተንዛዙ ጥያቄዎች አእምሮውን አንዳጨናነቀ የተባለው ፓሊስ ጣቢያ ደረሰና መኪናውን ፓርክ አድርጎ ወደፖሊስ ጣቢያው ተጠጋ ፡፡በየት እንደሚገባ ግራ ተጋባ በራፍ እንዳለ ሆኖ በሆነ ሜትር ጠጋ ብሎ ደግሞ 5 ሜትር የሚሆን የተደርመሰ አጥር በግማሽ ቀልቡ እያየ ወደውስጥ ዘለቀና ለአለማየሁ ደወለለት፡፡
የቢሮውን ቁጥር ሲነግረው ፈራ ተባ እያለ አንኳኳና ወደውስጥ ገባ…ከስድስት አመት በፊት የተለየው የልጅነት ጓደኛውና አብሮ አደጉ ፊቱ በፂም ተሸፍኗ ትልቅ ሰው መስሎ እና የደንብ ልብሱን ለብሶ ተሸከርካሪ ወንበር ላይ ቁጭ ብሏል፡፡ከእሱ ውጭ ክፉሉ ውስጥ ማንም የለም.ሰሎሜንም አገኛታለሁ ብሎ ጠብቆ ነበር…ግን እየታየችው አይደለም፡፡‹‹የት ወስዶ አስቀምጧት ነው?››በውስጡ አጉረመረመ፡፡
እንዴት ብሎ ሰላም እንደሚለው ግራ ገባው…‹‹ጓደኛዬን ለማግኘት ነው የመጣሁት ወይስ ተከስሼ ቃል ልሰጥ….?››ሲል እራሱን ጠየቀና ተደነጋሮት በራፍ ላይ ፈዞ ቆመ፡፡ አለማየሁ መቀመጫውን ለቆ መጣና ተጠመጠመበት…ከፍራቻው ጋር ሳይፋታ እሱም አቀፈውና የሞቀ ሳላምታ ተለዋወጡ ፡፡ይዞት ወደ ውስጥ ዘለቀና የሚቀመጥበት መቀመጫ ሰጠው..እሱም ከፊቱ ተቀመጠ….፡፡
አለማየሁ ደቂቃዎችን ወሰደና አላዛርን በትኩረት አየው፡፡አለባበሱ እንዳአንባሳደሮች ሽክ ያለ ነው..ደግሞ ልክ እንደድሮው …እንደውም ከዛም በላቀ ደረጃ ልቅም ያለቆንጆ ሆኗል፡፡ወንድን ልጅ ቆንጆ ነው ብሎ አያውቅም ፡፡ጓደኛውን የአላዛርን ቁንጅና ግን ፍጥጥ ያለ ስለሆነ ችላ ተብሎ የሚታለፍ አይነት አይደለም፡፡፡
ለንግግሩ አላዛር ቅድሚያውን ወሰደ‹‹በቅርብ ነው እዚህ የገባሀኸው?››
‹‹አዎ ገና ሁለት ወሬ ነው››
‹‹ሁለት ወር ሙሉ ስትቀመጥ እንዴት አስቻለህ? ነው ወይስ እኔ ብቻ ነኝ ያላገኘሁህ›?›
‹‹አይ ..እዚህ የተመደብኩት በሀላፊነት ቦታ ስለሆነ ነገሮችን እስክለማመዳቸውና እስኪዋሀዱኝ ወዲህ ወዲያ ማለት አልቻልኩም ነበር…መቼ እና እንዴት ላግኛቸው እያልኩ እያሰብኩ ሳለ ነው ድንገት ዛሬ ጥዋት ሰሎሜን ያገኘኋት፡፡››
‹‹ጥዋት?››
‹‹አዎ ጥዋት››
አላዛር ረጅም ትንፋሽ ወደ ውስጡ ሳበና እፎይ አለ…‹‹ለሊት ቀጥታ ከቤት እንደወጣች ወደእሱ ቤት ሄዳ ቢሆንስ ?››የሚል ጥርጣሬ ነበረው…እንደዛ ከሆነ ደግሞ ብዙ የሚፈጠሩና ወደኃላ ሊመለሱ የማይችሉ ችግሮች ይኖሩ እንደነበር ሲያሰላስል ስለቆየ ከአለማየሁ የሰማው መልስ በጣም ነው ያስደሰተው፡፡
‹‹ታዲያ አሁን የታለች?››
‹‹እስር ላይ ነች››
‹‹ምን?››የሚሰማውን አምኖ ለመቀበል ተቸገረ፡፡
የተሳሳተ ቃል የሰማ ነው የመሰለው….‹‹እሷ እስር ላይ !!እንዴት ተብሎ?››
‹‹ስትገባ ያየሀው መሰለኝ..አጥራችንን ለሊት የናደችው እሷ ነች››
‹‹ተረፈች ታዲያ ..?ተጎድታለች..?ሀኪም ቤት ወሰዳችሃት?››
‹‹አታስብ ..ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰባትም….››መኪናዋ ብቻ ትንሽ ተጫራለች…መንገድ ስለዘጋብን አንስተን ወደጎሮ አቁመናታል፡፡››
ከድንጋጤው ትንሽ ተንፈስ ብሎ‹‹መኪናዋ የራሷ ጉዳይ .እሷ ብቻ እንኳን ተረፈች››አለ ፡፡
‹‹አዎ..ተርፋለች››
ልመና ሳይሆን ትዕዛዝ በመሰለ ቃላት‹‹ላያት እፈልጋለሁ..››ሲል ተናገረ፡፡
‹‹ደህና ነች አልኩህ እኮ››
‹‹በፈጣሪ ካላየኋት አልረጋጋም…..በጓደኝነታችን..እባክህ?››
አለማየሁ ከዚህ በላይ ሊጨክንበት አልፈለገም፡፡‹‹አረ ችግር የለውም… እዚሁ አስመጣታለሁ…››አለና ከመቀመጫው ሳይነሳ ጠረጴዛው ላይ መጥሪያውን ተጫነው… ወዲያው አንድ ፖሊስ መጣና ወታደራዊ ሰላምታ ሰጥቶት የሚለውን ለመስማት ዝግጁ ሆኖ ይጠብቅ ጀመረ
ኩማደር አለማሁም‹‹እስረኛ ሰሎሜ ግርማን ይዘህልኝ ና››ብሎ ትዕዛዙን አስተላለፈ፡፡
ፓሊሱ ወጥቶ ሄደ‹‹እስረኛ ሰሎሜ ግርማ ››ብሎ ሲናገር አላዛር ስቅጥጥ አለው፡፡
‹‹ኩማንደር ቆይ ግን አጥሩን እኔ በሁለት ቀን ውስጥ ሙሉውን ከበፊቱ በበለጠ አሳምሬ እስገናባዋለሁ….አስፈላጊም ከሆነም አሁኑኑ ደስ ያላችሁን ብር አስይዛለው..እሷ ማሰር እኮ አስፈላጊ አይደለም….››

👍59❤14👏1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////
ዶ/ር ኤልያስ ዛሬ ምን አልባትም በህይወቱ ፍፁም የሆነ ደስታ የተሰደሰተበት ቀን ስለሆነ ስሜቱን መቆጣጠር አቅቷት ጥንቅቅ ብሎ ባለቀ ውብ ቤቱ ውስጥ ከክፍል ክፍል እየተመላለሰ እንደህፃን እየቧረቀ ነው፡፡ስልኩን አነሳና ደወለ…፡፡ከአራት ጥሪ በኃላ ተነሳ፡፡
‹‹ውድ ባለቤቴ እንዴት አለሽልኝ››
‹‹አንተ ያንን ቃል መጠቀም የምትችለው እኮ ሰማንያ ፈርመህ ቤትህ ስታስገባኝ ነው››አለችው እየሳቀች፡፡፡
‹‹ያው በይው..ዜናውን አልሰማሽም እንዴ…..?ሽማግሌዎቼ እኮ ወላጆችሽ ልጃቸውን ሊሰጡኝ በደስታ መስማማታቸውን አሁን ነግረውኝ በደስታ እያበድኩ ነው፡፡››
‹‹ከአንተ ቀድሜ ሰማሁ…ምነው ይከለክሉኛል ብለህ አስበህ ነበር እንዴ?››
‹‹እንዴ ምን ይታወቃል…..ምን አልባት ቅድሞ እደጅ እየጠና ያለ ብረት መዝጊያ አማች ኖሮ ሀሳባቸው ወደእሱ ቢያጋድልስ?››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው …ለአሁኑ ግን ተርፈሀል››
‹‹እኔም መትረፍ የምፈልገው ለአሁኑ ብቻ ነው…የማገባው አንዴ ብቻ እኮ ነው…››ተሳሳቁ፡፡
‹‹እና ይሄንን ደስታ አብረን ማክበር የለብንም ትያለሽ…?››
‹‹አንተ ..ከአሁን ወዲህ እኮ እስከሰርጌ ቀን ድረስ ልታየኝ አይገባም…››
‹‹እንደዛ ከሆነማ ሰርጉን ነገውኑ ደግስ በይኛ››
‹‹አዎ ..ያን ያህል ከቸኮልክ አድርገው››
‹‹እሺ..አስበብበታለው..እውነት ግን በጣም ላገኝሽ ፈልጌለሁ…››
እሷም ከአንደበቷ አውጥታ አትናረው እንጂ በጣም ልታገኘው ፈልጋለች፡፡‹‹ ይቻላል..የትና መቼ?፡፡››
‹‹ምሳ ልጋብዝሽ …ሰባት ሰዓት ስካይ ላይት እንገናኝ፡፡››
‹‹ሰባት ሰዓት ..አሁን እኮ አራት ተኩል ሆኖል…..ለመዘጋጃጀት በቂ ጊዜ አይኖረኝም፡፡››
‹‹አንቺ ደግሞ..እንደውም ምንም መዘገጃጀት አያስፈልግሽም… እዛ ሆስፒታል በነበርሽበት ጊዜ ያለምንም ዝግጅት ምን እንደምትመስዬ እኮ አውቃለው…ለእኔ ብለሽ ለመቆነጃጀት ከሁለት ሰዓት በላይ ማጥፋት የለብሽም…ከዛሬ ወዲህ ባልሽ ነኝ፡፡ማለቴ ለጊዜው እጮኛሽ ነኝ..ግን ለጥቂት ጊዜ ብቻ ነው፡፡››
‹‹‹ይሁንልህ እሺ…..ግን ቅር ካላለህ አንድነገር ልጠይቅህ ››
‹‹ምን ጠይቂኝ››
‹‹ጸጋን ይዣት ብመጣ ቅር ይልሀል?››
‹‹አረ በፍፅም ..እንደውም በተቃራኒው ደስ ነው የሚለኝ …እሷ ከመጀመሪያው ጀምሮ የፍቅራችን ብቸኛ ምስክር ነበረች..ዛሬ መገኘት ይገባታል….ጫጉላ ቀናችን ላይ አብራን ወደመኝታ ትግባ እንዳትይ እንጂ ለዛሬው ደስ ይለኛል››
ስለጫጉላ ሲያወራ እፍረትም ሙቀትም ተሰማት‹‹አንተ ምን እያልክ ነው..?በል ቸው››ብላ ስልኩን ዘጋች፡፡
እሱም ወዲያው ወደሻወር ቤት ገባና ሰውነቱን በፍጥነት ተለቃለቀ…ከዛ ፂሙን ላጨ…ሙሉ ሱፍ ለበሰና ዝንጥ አለ…፡፡ለመውጣት ዝግጁ ሆነ…፡፡ሰዓቱን ሲያይ 5 .ከሩብ ይላል….ከራሄልና ከፀጋ ጋር ወደሚገናኝበት ቀጠሮ ከመሄዱ በፊት ማግኘት የሚገባው አንድ ሰው አለ…ከአመት በፊት በሆስፒታል አብራው ትሰራ የነበረች የህጻናት ሀኪም ነች ትናንትና ደውላ ላገኝህ እፍልጋለው ያለችው፡፡ለዚህች ዶ/ር የስራ ባለደረባው ነበር…ያለፈውን አንድ አመት ተጨማሪ ትምህርት እድል አግኝታ ኖሩዌይ ነበር ያሳለፈችው፡፡አሁንም ለሁለት ሰምንት ረፍት እንደመጣች እና መመለሻዋ እንደደረሰ እናም ከመሄዶ በፊት አንድ እቃ ልትሰጠው እንደምትፈልግ ነግራው ነው እግረመንገዱን ሊያገኛት የወሰነው፡፡
ሀያ ሁለት ነበር ቀጠሮቸው…እሷም ቸኩላ ስነበረ ቀጥታ ወደጉዳዩ ነበር የገባችው፡፡አንድ የታጠፈ ነጭ ፖስታ አውጥታ እጁ ላይ አደረገች፡፡ግራ ገብቶትም ደንግጦም‹‹ምንድነው ሲል?››ጠየቃት፡፡
‹‹ትዝ ይልሀል ከመሄዴ በፊት አብረን የምንከታተላት አንድ ታማሚ ልጅ ነበረች…እናቷ ከአንተ ጋር ትግባባለች…እንደውም የልጅነት ጓደኛዬ ነበረች ብለሀኛል››
‹‹ኦኬ ትክክል ነሽ..ስለፀጋ ነው…ማለቴ የዛን ጊዜ ስሟ ትሁት ነበር..ስለእሷ ነው የምታወሪው››
‹‹አዎ ስለእሷ ነው…ለመሆኑ እንዴት ነች…?አሁንም በህይወት አለች?››
‹‹አዎ በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይ ነች…ግን ፖስታው ምን እንደሆነ አልገባኝም››
‹‹ፖስታውማ እናትዬው እዛ ሆስፒታል ውስጥ ህጻኗን ጥላ ከመሄዶ በፊት ይህንን ፖስታ ለአንተ እንድሰጥ አደራ ብላ ሰጥታኝ ..ነበር….እርግጥ በወቅቱ ልጇን ጥላ እንደምትሄድ አልገመትኩም እና እሺ ብዬ ተቀበልኮት….ግን በዛው ሰሞን አንተም ለሆነ ስራ ወደክፍለሀገር ወጥተህ ነበር..እኔም ውጭ ለመሄድ በጣም እየተዋከብኩ ስለነበረ እቤቴ ወስጄ እንደቀልድ እንዳስቀመጥኩት እረሳሁት እና ሳልሰጥህ ሄድኩ ..በቀደም ነው የድሮ ወረቀቶቼን ሳስተካክል ድንገት አገኘሁት..አድራሻውን ሳነብ ትዝ አለኝ….መጀመሪያ አፍሬ እንደተረሳ ልተወው ነበር›..በኃላ ሳስበው ግን ምን አልባት በጣም አስፈላጊ ነገር ቢሆንስ ብዬ…አይኔን በጨው አጥቤ አግኝቼ ልሰጥህ ወሰንኩ….ይቅርታ እሺ››
‹‹አረ ችግር ለውም…ያው ልጄን አደራ..ተከታተላት ምናምን የሚል መልዕክት ነው የሚሆነው….ያንን ደግሞ እሷ ባትለኝም አደርገዋለው››በማለት ፖስታውን ኪሱ ውስጥ ከተተና ከእሷ ተሰናብቶ መኪናው ወደ እስካይ ላይት አዞረ፡፡
ከቀጠሯቸው 10 ደቂቃ ቀድሞ ነበር የደረሰው፡፡ ወንበር ይዞ በጉጉት ይጠብቃቸው ጀመር..፡፡ድንገት ፖስታው ትዝ አለው፡፡ አወጣና አየው…፡፡ከጀርባው ለማከበርህ ደ/ር ኤልያስ ከፅጌረዳ ይላል፡፡
እነ ራሄል እስኪመጡ ቀዶ ሊያነበው ፈለገ…መቅደድ ከመጀመሩ በፊት ፖስታውን ጠራጴዛው ላይ አስቀምጦ ስልኩን ከኪሱ አወጣና ተመለከተው…ራሄል ነች፡፡አነሳው፡፡
‹‹እሺ የእኔ ፍቅር››
‹‹ቀድመንህ ደርሰናል መሰለኝ››
‹‹አረ እንዴት ተደርጎ…››አለና ያለበትን ቦታ ነገራቸውና እስኪያዩት ቆሞ ጠበቃቸው…. ራሄልን ሲያያት ልቡ ትርክክ አለ….ወደፊት ተራምዶ ፀጋን ከእቅፏ ተቀበለና..ጉንጭ ለጉንጭ ተሳሳሙ…. ወደ ጠረጴዛቸው ሄደው ተቀመጡ….ምሳ ታዘዘ እና እስኪመጣ ሞቅ ያለጫወታ ጀመሩ…..ራሄል ድንገት ፊት ለፊቷ የተቀመጠ ፖስታ አየችና በመገረም አነሳችና አየችው…፡፡
‹‹ፅጌረዳ ማን ነች?››ኮስተርተር አለች፡፡
‹‹ቀናሽ እንዴ?››
‹‹በኢንተርኔት ዘመን ፖስታ በምትልክልህ ሴት እንዴት ብዬ ነው የምቀናው?››
‹‹በፖስታው አድራሻ ላይ የተጠቀሰችው ፅጌረዳ ማለት የፀጋ እናት እንደሆነችና ፖስታው ከተፃፈ ከአመት በኃላ እንዴት እንዳገኘው… በእንግሊዘኛ ነገራት››ይሄንን ያደረገው ፀጋ ፊት ስለእናቷ በምትሰማው ቋንቋ ለማውራት ስላልደፈረ ነው፡፡
‹‹እና..አልተከፈተም እኮ››
‹‹አዎ…አሁን ስለፀጋ እኔን ብቻ ሳይሆን አንቺንም ስለሚመለከት አብረን እናነበዋለን››
‹‹እርግጠኛ ነህ?››
‹‹ አዎ እርግጠኛ ነኝ››
‹‹እና እናንብበዋ››ብላ ልትቀደው ስትዘጋጅ፡፡
‹‹አይ …ይሄንን ጊዜያችንማ ለሌላ ጉዳይ አንጠቀምበትም…››ብሎ ፖስታውን ከእጇ ተቀበለና ከጎኗ ካለው ወንበር ላይ የተቀመጠው የራሷ ቦርሳ ውስጥ ከተተው፡፡
‹‹በቃ አንቺ ጋር ይሁንና ..ሰሞኑን አንድ ላይ ሆነን እናነበዋለን፡፡››ተስማማች…ምሳ ቀረበላቸው በሉ…ከዛ ወጥተው ወደአለም ሲኒማ ጎራ አሉና ፊልም አዩ….አሪፍና ጣፋጭ ቀን አሳለፉ….

❤53👍3👏1
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////
ከኪሊንኩ ጀርባ ያለው የዶ/ር ኤሊያስ ቢሮ ምናልባት አለም ከዚህ በፊት ካየቻቸው ቢሮዎች ሁሉ የተዝረከረከ ሆኖ ነው ያገኘችው፡፡
"ዶክተር ኤሊያስ እኔን ለማየት ስለተስማማህ አመሰግናለሁ።"
"ችግር የለም …ዛሬ ብዙም ስራ አልነበረኝም " ከቀጥታ ከጠረጴዛው አጠገብ ያለውን የእንጨት ወንበር ላይ ያሉትን መጽሔቶችን አስነሳና ጠረጴዛ ላይ በማድረግ ለአለም እንድትቀመጥበት አመቻቸላት፡፡
"አንቺን ሳይሽ ብዙም አልተገረምኩም
"አላት በቅንነት ።
"ለምን?"
"ዋና አቃቢ ህጉ ደውሎ አንዳንድ ጥያቄዎችን ልትጠይቂኝ እንደምትፈልጊ ነግሮኝ ነበር።"
"ዛሬ ከከተማ ውጭ ያለ መስሎኝ ነበር."
"አይ ከቀናት በፊት ነበር ሰሞኑን ትመጣለች ቡሎ የነገረኝ ።"
"ገባኝ…ለሊት የእሳት ቃጠሎ ቦታው እንስሳቶችን ለመርዳት ስትሯሯጥ ስለነበርክ…ዛሬ እንዲህ ንቁ ሆነህ ቢሮህ አገኝሀለው ብዬ አላሰብኩም ነበር።"
በመደነቅ‹‹እንዴ እዛ እንደነበርኩ በምን አወቅሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹እኔም እንዳጋጣሚ እዛ ነበርኩ…አሁን ጊዜህን ሳልሻማብህ ቀጥታ ወደጉዳዬ ልግባ …የእናቴ የሰሎሜን ግድያን በተመለከተ መረጃዎችን እየሰበሰብኩ ነው….እባክህ አንተ በአቶ ፍሰሀ የእንስሳት እርባታ ድርጅት ውስጥ የእንስሳት ሀኪም ሆነህ እንደመስራትህ የምታውቀው ነገር ይኖር ይሆን ?" ስትል አሳዛኝ በሆነ የድምፅ ቅላፄ ጠየቀችው፡፡
"በእርግጥ እናትሽን አውቃታለው . እሷ በጣም አስደማሚ ሴት ነበረች. በእሷ ሞት ያላዘነ ሰው የለም ››
"አመሰግናለሁ፣ በዛን ወቅት በአቶ ፍሰሀ የእርባታ ድርጅት ውስጥ የእንስሳቱን ጤንነት ሚከታተሉት አባትህ እንደነበሩ ማወቅ ችያለው፡፡ "
" ልክ ነው …በዛን ወቅት አባቴ ነበር….እሱ ከሞተ በኋላ ግን ስራውን እኔ ተረክቤያለሁ." "አባትህ ስለ ሰሎሜ ግድያ ሁኔታ የሆነ ነገር ነግሮህ ይሆን?››
"በቀዶ ጥገና ቢላዋ መገደሏን በሰማ ጊዜ እንደ ሕፃን ነበር ተንሰቅስቆ ያለቀሰው››
"አባትህ እናቴ የተገደለለችበት መሳሪያ ከየት እንደመጣ አውቋል›?›
"አዎ …ያ አባቴ እንስሳቱን ለማከም የሚጠቀምበት መሳሪያ ነበር፣እናቴ ነበረች የሸለመችው የስሙ የመጀመሪያ ፊደል ተቀርፆበት ነበር ፡፡እንዴት አድርጎ ከቦርሳው እንደወደቀበት ነው ግራ የገባው፡፡››
"እንደዛ አይነት ግድ የለሽነት ከእሱ ባህሪ ጋር አይሄድም አይደል?"
"ትክክል ነሽ….አባዬ ለህክምና እቃዎቹ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያደርግ አይነት ሰው ነው
…በቆዳ በተለበጠ የእንጨት ሣጥን ውስጥ ነበር የሚያስቀምጣቸው…ያ ስለት ከሳጥኑ እንዴት እንደወደቀ ፈጽሞ ማወቅ አልቻለም ነበር, ››
"እናቴ በሞተችበት ቀን አንተ እዚያ ነበርክ?"
"ይህን ቀድመሽ ታውቂያለሽ ብዬ አስባለሁ። አባዬን ለመርዳት ትምህርት ከሌለኝ በስተቀር እዛ እገኝ ነበር …በዛም ቀን አብሬው ሄጄ ነበር።››
"ገመዶ እዚያ ነበር?"
"በእርግጥ ኩማንደር እዚያም ነበረ።››
"ለሊቱን ሙሉ."
‹‹እሱን እርግጠኛ አይደለሁም…በመሀል አቋርጦ የሄደ ይመስለኛል››
"አባትህ የህክምና ቁሳቁስ የሚይዝበትን ሳጥን የሆነ ቦታ አስቀምጦ ዞር ብሎ ያውቃል?" ኤሊያስ ማሰላሰል ጀመረ … መልስ መስጠት እንደማይፈልግ ነገራት፡፡
‹‹ በዚያ ቀን በዛ አካባቢ ሌላ ማን ነበር?"ስትል ሌላ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
ለማስታወስ ሲጥር ተመለከተች‹‹‹ጁኒየር፣ ገመዶ፣ ጋሽ ፍሰሀ….እናትሽ….ስርጉት."
‹‹ ማን… ስርጉት ነበረች? ››
‹‹አዎ ነበረች …ከዛ ወደ ቤት መሄድ እንዳለባት ተናገረች እና አካባቢውን ለቃ ሄደች፡፡
‹‹ከግቢው ወጥታ ስትሄድ አይተሃታል….››
‹‹አይ መሄድ አለብኝ ብላ ስታወራ እንጂ ወጥታ ስትሄድ አላየኋትም….›› " ስለ ሊቁ ምን ማለት ይቻላል? እሱ በአካባቢው ነበር?"
‹‹እሱ ሁሌ በሁሉም ቦታ የሚዞር..በሄድሽበት ቦታ የማታጪው አይነት ንክ ነበር ፣እውነቱን ንገረኝ ካልሺን ግን በዛን ቀን እሱን እዛ ቦታ እንዳየሁት አላስታውስም››
"እርሱን ካላየኸው በሰሎሜ ደም በተሸፈነ ልብሱ በቁጥጥ ስር ሲውል አልተገረምክም?"
‹‹በእርግጥ አልተገረምኩም…. ምን አልባት እኔ ሳላየው ጊቢ ውስጥ ሲዞዞር ከአባዬ ቦርሳ የወደቀውን ቢላዋ እንዳገኘው ገምታለው፣ ከዛ እናትሽን ገድሏታል ብዬ አስባለው.››
‹‹ነገር ግን ከዛ ሁሉ የአባትህ የህክምና መሳሪያዎች መካከል አንድ ቢላዋ ብቻ ሾልኮ መውደቁ ግራ መጋባት ውስጥ አይከትም… ?››
ዝም አላት…..፡፡
ይህ ዶ.ር የሶስቱም ተጠርጣሪዎች ጓደኛ ነው። በዛ ላይ በቋሚነት ለአቶ ፍሰሀ ተቀጥሮ የሚሰራ ሰው ነው፡፡የሚያውቀው ነገር እንኳን ቢኖር በምንም አይነት ተአምር አሳልፎ ሊሰጣቸው እንደማይፈቅድ አወቀች፡፡ከዚህ በላይ ጊዜዋን ማባከን ፋይዳ እንደሌለው ስላመነች ከመቀመጫዋ ተነሳችና አመስግናው ወደ ሁለተኛ ጉዳዮ አመራች፡፡
///
የእርባታ ድርጅት የእንቅስቃሴ አልባ ሆኗል ። የጽዳት ሠራተኞች ከቃጠሎ የተረፈውን ፍርስራሹን እና አመዱን እየሰበሰቡ እና እየጠረጉ በአካባቢው የቆመው መኪና ላይ እየጫኑ ነው። ኩማንደሩ በአካባቢው ወዲህ ወዲያ እየለ የሚሰራውን እየተመለከተ ነው፡፡ አለም ከመኪናዋ ስትወርድ አይቶታል፣ ነገር ግን እሷን ለማናገር ሲሞክር በአካባቢው የነበረው የእሳት አደጋ ተቆጣጣሪ ሰለጠራው ወደእዛ ለመሄድ ከተንቀሳቀሰ በኋላ ሀሳቡን ቀይሮ ቆሞ ጠበቃት፡፡ ደረሰችበት…ሰላም ይለኛል ብላ ስትጠብቅ
"እዚህ ምን እየሰራሽ ነው?"ብሎ ጠየቃት፡፡
‹ከሳራ ጋር ሻይ ልጠጣ ነው የመጣሁት።››
በመደነቅ አፍጥጦ ተመለከታ‹‹ከእሷ ጋር ደግሞ ከመቼ ወዲህ ነው ጓደኛ የሆናችሁት?››
“ሃሳብ የእኔ ሳይሆን የእሷ ነበር” አለችው።
"እሺ ተዝናኑ" አለና ፊቱን አዙሮ ሲጠራው ወደ ነበረው ሰውዬ ሄደ፡፡
እሷም ወደማረፊያ ቤቱ ተራመደች..አቶ ፍሰሀ በቤቱ በረንዳ ላይ ቆሞ ነበር፣ ስትጠጋ ፍርሃቷ እንዳይታይ ለማድረግ ሞክራለች።
"እንዴት ነህ … ጋሽ ፍሰሀ?"
" ሰዓት አክባሪነትሽ የሚደነቅ ነው…እናትሽም ልክ እንደዚህ ነበረች››አላት፡፡ለምን እንደመጣች እንደሚያውቅ ተረዳች
‹‹አመሰግናለው››አለችው፡፡
‹‹ምንም አይደል››
"ኩማንደሩ እሳቱን ያስነሳውን ሰው በቁጥጥር ስር እንደሚያውለው ተስፋ አደርጋለሁ። እኔም ተገቢን ፍትህ እንድታገኙ አስፈላጊውን ሁሉ አደርጋለሁ።"ስትል ቃሏን ሰጠችው፡፡
"አዎ፣ እኔም ተስፋ አደርጋለው… ሁሉንም ነገር ችላ ማለት እችላለሁ። ነገር ግን ያን የመሰለ ተወዳጁን የገመዶን ፈረስ እንዲሞት ያደረገውን ሰው ግን ይቅር አልለውም።ያን ፈረስ በማሳደግና በመንከባከቡ ይሰማው የነበረውን ኩራት እኔ ነበርኩ የማውቀው።"
በዚህ ጊዜ ጁኒዬር ከውስጥ ወጣ…በውብ ፈገግታ ተሞልቶ የሞቀ ሰላምታ ሰጣት፡፡ አለም"ወደ ውስጥ ብገባ ይሻለኛል… እናትህን ብዙ አላስጠብቃት" አለቸው ።
ጁኒየር እጁን ትከሻዋ ላይ ጫነና "እናቴ የትላንት ማታውን ጥፋቷን ማረም ትፈልጋለች። ግብዣዋን ስለተቀበልሽ በጣም ተደስታ ነበር። አንቺን ለማየት በጉጉት እየጠበቀችሽ ነው።››አላት
‹‹ጥሩ››ብላ ወደ ውስጥ ገባች፡፡
አገልጋይዋ በራፉ ድረስ መጥታ ተቀበለቻት።‹‹ግቢ።››ብላ ወደ ውስጠኛው ክፍል እየመራች ወሰደቻትና ከሳራ ጋር አገናኘቻት፡፡
ከሳራ ጋር ተጨባበጡና ጉንጭ ለጉንጭ ተሳሳሙ፡፡
አለም የክፍሉን ዙሪያ ገባ እየተመለከተች"እንዴት የሚያምር ክፍል ነው?!"
"ወደድሽው?።"
‹‹በጣም እንጂ…››

❤43👍7👏2