#ኢትዬጵያዊ_ ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ካርሎስና እና ኑሀሚ በአምስተኛ ቀናቸው ነበር ከአከባቢው የተንቀሳቀሱት፡፡በዛን ወቅት ኑሀሚ የተመረዘችው መርዝ ሙሉ በሙሉ ከሰውነቷ ተወግዶ… የሟሸሸ የነበረም ሰውነቷ ተነቃቅቶ….ጥንካሬዋም በተወሰነ ፐርሰንት ተመልሶ ነበረ፡፡ ባለውለታቸውን የሆነችውን ጎጆ በፍቅር ተሰናብተው አካባቢውን ለቀው የአማዞንን ወንዝ ደርቻ ተከትለው በምስራቅ አቅጣጫ ለአንድ ሰዓት ተኩል በእግር ከተጓዙ በኃላ አንድ እሮጌ ጀልባ የያዘ ግለሰብ አጋጠማቸው፡፡ከእሱ ጋር በገንዘብ ተደራደሩና ታብቲንጋ ከተማ ድረስ እንዲያደርሳቸው ተስማምተው ጉዞ ጀመሩ፡፡የዛኑ ቀን አመሻሽ ላይ ያሰቡበት ቦታ ደረሱ፡፡
‹‹ይህቺ ከተማ የአየር ትርንስፓርት አገልግሎት አላት ነው ያልከኝ..?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹አዎ አላት..ማኑሳ ድረስ መሄድ ይቻላል፡፡››
‹‹ታድለን…በቃ ነገሮች ወደመጨረሻው ምዕራፍ እየተቃረበ ነው ማለት ነው…ተዲያ ወደከተማው እንግባና የአየር ትኬት ካገኘን እንሞክራ››
‹‹አይ ወደከታማ መግባት አንችልም..፡፡እንደምታያት ይህቺ አንስተኛ የጠረፍ ከተማ ብራዚል ውስጥ ትገኝ እንጂ ለኮሎምቢያ ቅርብ መሆኗን እንዳትረሺ..ያ ማለት ደግሞ የዳግላስ ተፅእኖ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ይኖራል ማለት ነው፡፡ በተለይ ወደ ብራዚል ከገባን ቀጥታ የአየር ትራንስፖርት የሚገኝባት ከተማ ይህቺ ስለሆነች ቀጥታ ወደእዚህ እንደምንመጣና ወደአየር መረፊያ ጎራ እንደምንል በቀላሉ ይገምታል..ስለሆነም ከተማው ውስጥ ዋና ዋና ቦታዎች እና በተለይ ደግሞ አየር ማረፊያ ላይ ሰዎቹን እንደሚያስቀምጥ እርግጠኛ ነኝ፡፡
‹‹እና ምን ይሻለናል?፡፡››በስጋት ጠየቀችው፡፡
‹‹ረጅሙን መንገድ ነው የምንመረጠው..ማለት አሁንም ወደ ምስራቅ ጉዞችንን እንቀጥልና ወደ ቤንጃሚን ኮንስተንት ከተማ ነው የምንሄደው፡፡››
‹‹ቤንጃሚን ኮንስተንት ደግሞ ማን ነች?››
ቤንጃሚን ኮንስተንት አማዞን ደን ውስጥ ከበቀሉ የብራዚል የጠረፍ ከተሞች ውስጥ አንዷ ስትሆን ከተማዋ ጃዋሪ በተባለ ወንዝና በአማዞን ወንዝ ተከባ የምትገኝ ትንሽ ከተማ ነች፡፡ከዚህ አሁን ካለንበት ከተማ በጀልባ የሁለት ሰዓት ቢፈጅብን ነው፡፡ማንም ወደ ዛች ከተማ ይሄዳሉ ብሎ እይገምተንም…እዛ ከደረስን በኃላ የተሻለ የተባለ ዘመናዊ ጀልባ እንከራይና ቀጥታ ወደ ማናአስ እንጓዛለን፡፡
‹እንዳልክ …ግን የሆነ ቻርጅ ያለበት ቦታ ፈልግን ስልኬን ቻርጅ ማድረግ አለብኝ፡››የምታስበውን ነገረችው፡፡
‹‹ምን ሊያደርግልሽ?››
‹‹ትቅዳለህ..ለወንድሜ ደውዬ ቢያንስ እስከሁን በጤና መሆኔን ላሳውቀው ነዋ፡፡››
‹‹አይ አይሆንም…ስልክሽን አብርተሸ ለወንድምሽ ደወልሽለት ማለት ያለሽበትን አካባቢ ቀጥታ ለሀገርሽ መንግስት እናም ጉደዩን ለሚከታተሉ ለአካባቢው መንግስታት አሰወቅሽ ማለት ነው..ያ ሆነ ማለት ደግሞ ዳግላስም በቀላሉ ዜናውን አገኘ ማለት ነው፡፡እና ሁሉም እኛን ለማግኘት በአካባቢው አሰሳ ይጀምራሉ…ከዚህ በፊት እንዳለኝ ልምድ ደግሞ ከየትኛውም መንግስት ቀድሞ ደጋላስ አፈፍ እንደሚያደርገን እርግጠኛ ነኝ››
‹‹እና ምን ይሻላል?››
‹‹የሚሻለውማ..ማናስ እስክንገባ መቻል….ነው…ወንድምሽም ዘላለም ከሚያጣሽ…ስድስት ሰባት ቀን በናፍቆት እና በትካዜ ቢሰቃይ ይሻላል፡፡አሁን አንቺ እዚሁ አካባቢ እራስሽን ከሰው እይታ ከልለሽ ትጠብቂኛለሽ… እኔ እራሴን ለውጬ ከታማ ገብቼ እመለሳለሁ››
‹‹እንዴ… እኔን እዚህ ብቻዬን ጥለኸኝ ምን ትሰረለህ?››
እጁን ወደኪሱ ሰደደና የሆነ መሀረብ አውጥቶ ቋጠሮውን ፈታና ሁለት የጨው አንኳር የሚመስል አብረቅራቀ መአድን አነሳና በእጇ መዳፍ ላይ አስቀመጠ፡
‹‹ምንድነው?››በመገረም እያየች ጠየቀችው፡፡
‹‹እንቁ ነው..በደኑ ውስጥ በአጋጣሚ በስራ ላይ እያለው በእጄ የገባ ነው..እንደዚህ አይነት ንብረት በምንም አይነት ሁኔታ ቢሆንም በእጅ ከገባ ለገዛ ጥቅም ደብቆ መስቀመጥ በሞት የሚያስቀጣ አደገኛ ወንጀል ነው..በወቅቱ ለዳግላስ ማሰረከብ ነበረብኝ…እኔ ግን ደመነፍሴ አንድ ቀን አጣብቂኝ ውስጥ ስገባ ይጠቅምሀል ብሎ ሹክ ስላለኝ..የመጣው ይምጣ ብዬ ደብቄ አስቀምጬው ነበር፣.እና አሁን ወደከተማ ሄጄ ወደገንዘብ ልቀይረው...እረጅም የጀልባ ጉዘ ስለሚጠብቅ ብዙ ገንዘብ ያሰፈልገናል…››
መጀመሪያ እንቁውን መለሰችለት..መልሶ በመሀረቡ ቋጠረውና ወደኪሱ ከተተው..፡፡
ከሷ የእጅ ቦርሳዋን አነሰችና ዚፕን ከፈተች፣ከላይ ያሉትን እቃዎች አወጣች ፡፡ፊቱን አዙሮ ሊሄድ ሲል ከስር እንደታሸገ የተቀመጠውን ዶለር መዥርጣ አወጣችና እጁ ላይ አስቀመጠችለት፡፡
‹‹ይሄ አይበቃም?››
አይኖቹ በመገረም ደመቁ‹‹አንቺ ይሄን ሁሉ ብር ከየት አመጣሽ?››
የዛሬን አያድርገውና ሀለቃህ ዳግስ ነበር የሰጠኝ..እና አይበቃም›››….ብላ እንዴት እንዳገኘች ታሪኩን አስረዳችው
‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ..ይሄ እኮ በጣም ብዙ ብር ነው….በይ አሁን ጀልበ እንፈልግ››አለና ብሩን መልሶላት ቦርሳ ውስጥ ከከተተ በኃላ ተያይዘው ወደፊት ለፊት መራመድ ጀመሩ፡፡
እንደተነጋገሩት እዛው አድረው ንጊት ላይ ወደ ቤንጃሚን ኮንስተንት ከተማ በጅልባ ተጓዙ፡፡ እዛ አንድ ሰዓት ብቻ በማሳለፍ ሌላ ዘመናዊ የተባለ ጀልባ ተከራዩና ወደአማዞኒያ ግዛት ዋና ከተማ ማናአስ ጉዞ ጀመሩ፡.ያው ጉዞ ቀላል አልነበረም….6 ቀን ነው የፈጀባቸው ፡፡ግን ደግሞ በህይወት ረጅም ዘመን ለመኖር ስድስትና ሰባት ቀን መስዋት ማድረግ ያን ያህል ክፉ የሚባል ስላልሆነ አላማረረችም ፡፡
…ታብቲንጋ….ሳኦ ፍረንሲስኮ…ኮረንቲዛ….ዲ አማተራ…ሳኦ ዶሚንጎ….ሳንታ አንቶኒኦ….ሳኦ ፍሊክስ… ሳንታ ሉዚያ… የመሳሰሉን አያሌ ታዋቂ ቦታዎችንና የኣማዞን ወንዝ ዳር ከተሞችን አቋርጠው ማናአስ ከተማ ደረሱ ፡፡
ማናአስ(Manaus) በሀገረ ብራዚል የኣማዞኑያ ግዛት ዋና ከተማ ነች፡፡በብራዚል 2.2 ሚሊዬን ኑዋሪዎች የሚኖሩበት 7ተኛው ትልቋ ከተማ ስትሆን ከተማዋ በአማዞን ደን ውስጥ ከተቆረቆሩ ከ1 ሚሊዬን በላይ ኑዋሪዎች ካሏቸው ሁለት ትልልቅ ከተሞች መካከል አንዶ እና ዋነኛዋ ነች.››
በዛ ላይ የአማዞን ደንን እና የአማዞን ወንዝን ሚስጥር ለመበርበር እና ጥናት ለማጥናት ከመላው አለም የሚሰባበሰቡ ሳይንተስቶችና ተመራማሪዎች በዋናነት የሚከትሙባት ከተማ ነች፡፡በዚህ የተነሳ የአማዞን ልብ የሚል ቅፅል ስም ይሰጧታል፡፡በተጨማሪ አንዳንዶችም የትርፒካሎ ፓሪስም እያሉ ያሞካሻታል፡፡
ማናአስ ከተማና አካባቢው በኬሚካል ፕሮጀክት..በለውዝ ምርት ….በሳሙና ምርት….በመርከብ ግንባታ እና በጎማ ተክል ምርት በጣም የታወቀች ነች፡፡፡በተለይ በጎማ ምርት ከ1800 አመት በፈት ጀምሮ የታወቀች በመሆኗ ከሀገሪቱ ሀብታም ከተሞች ግንባር ቀደሞ እንድትሆን አስችሏታል፡፡ማናአስ ከተማ በ2014 እ.ኤ.አ የአለምን ዋንጫ ካስተናገዱ 12 የብራዚል ከተሞች አንዷ እንደሆነች ይታወቃል፡፡በከተማዋ ምስራቅ አቅጣጫ ድፍርሱ የኒግሮ ወንዝ እና ሰማያዊው የሶሊመስ ወንዝ አንድ ላይ ተቀላለቅሎ ወደአማዞን በገባርነት የሚፈስባት ልዩና አስደማሚ ስፍራንም በመደመም ማየት ይቻላል፡፡

👍85❤14👏1