#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
"አዎ ገብቶኛል....ግን ይቀረፃል ያልሺው?"
"አዎ ይሄንን በከፍተኛ ሚስጥር ነው....ድንገት ተስቶሽ በህልምሽ እንኳን ብታወሪ ህይወትሽን ያስከፍልሻል።ምክንያቱም ደንበኞቻችን እንደሚቀረፁ ቢያውቁ እዚህች ቤት ዳግመኛ ዝር አይሉም።እኛ ግን በጣም ምስጢራዊና ማንም በቀላል ፍተሻ ማግኘት በማይችልበት ቦታዎች ካሜራዎች አሉን።ይሄ በዎናነት ሰራተኞቻችንን ከአደጋ ለመጠበቅ ነው። ማንኛውም ሰው አጉል እመል ኖሮት ጥቃት ልፈፅም ቢል በፈጥነን እንደርሳለን፡፡ ከእንደገና ሰውዬው በሂደት ከእኛ ጋር ተቃቅሮ ድርጅታችንን ሊያጠቃ ቢንቀሳቀስ ያ ሚስጥር መከላከያ ጋሻችን ነው።
"አሁን ገባኝ"
"አዎ...ግን ላስጠንቅቅሽ...ስራ ስትጀምሪ ፈፅሞ ስለካሜራው በአእምሮሽ ማሰብ የለብሽም...ልክ አንድ የፊልም ተዋናይ ስትተውን ፊት ለፊቷ ስለተደቀነው ካሜራ ቁብ እንደማይሰጣት ሁሉ አንቺም ተመሳሳዩን ማድረግ አለብሽ፤ ይሄንንን ከመጀመሪያው ቀን ጀምረሽ መልመድ አለብሽ"
"እሺ እንዳልሺኝ አደርጋለሁ።
"እሺ አሁን ጨርሰናል...ክፍልሽን ያሳዩሻል ግቢና እረፊ... ልክ 9.30 ላይ ከክፍልሽ ወደማሳጅ ቤቱ ይወስድሻል። አስር ሰዓት ላይ የመጀመሪያ ደንበኛሽ ይመጣል። ዝግጁ ሆነሽ ጠብቂው ።ከእኔ ጋር ነገ ጠዋት እንገናኛለን ብላ ከመቀመጫዋ ተነሳችና ጉንጯን ስማት በተቀመጠችበት ጥላት ሄደች።
ሳባ በህይወቷ ዘመኗ የከፋው ፍርሀት ነው በመላ ሰውነቷ ተሰራጭቶ እያንዘፈዘፍት ያለው እርግጥ ይህ ፍራቻ ገና ጠዋት ስለፕሮግራሙ ከተነገራት ጀምሮ ነው ሲረብሻት የዋለው ። ሰአቱ ሲቃረብ እንዲያደፋፍራት መድሀኒት ነገር ወይም መጠጥ ጠጣ ጠጣ አድርጋ ለመሄድ ፈልጋ ነበር።ግን ስልጠና ላይ እንደተነገራት ወደስራ መጠጥ ጠጥቶ አይደለም ቀምሶ እንኳን መግባት አይቻልም።ባይሆን በስራ ላይ እያለች ደንበኛው መጠጥ እንዲቀርብለት ካዘዘና ለእሷም ከጋበዛት የዛኔ ነፃ እንደሆነች ነው የተማረችው።በመጀመሪያ ቀን የሙከራ ጊዜዎ ደግሞ ስህተት በመስራት ልትጀምረው አልፈለገችም። ቢያንስ እያወቀች መሳሳት አትፈልግም"ሰገን
ሰገን ነች ማሳጅ መስጫ ክፍል ድረስ ይዛት የሄደችው። እያንዳንዱ ለማሳጅ የምትገለገልበት እቃ የት የት እንዳለ ምን ማድረግ እንዳለባት ምን አለማድረግ እንዳለባት ከ20 ደቂቃ በላይ ክፍል ውስጥ እየተንጎራደደች አንድን ዕቃ እየያዘች መልሳ እያስቀመጠች አብራራችላትና መልካም እድል ተመኘችላትና ተሰናብታት ወጣች።
ጥላት ከሄደች ከ10 ደቂቃ በኃላ በራፍ ተቆረቆረ ከተቀመጠችበት በመበርገግ ቆመች...መልሳ ቁጭ አለች...የኋላ መውጫ በር ቢኖረው በራ ለመውጣት ሁሉ ተመኘች።
ደግሞ በራፍ ተቆረቆረ..እንደምንም መቀመጫዋን ለቃ ወደበሩ ተራመደች ከፈተችው…በድንጋጤ ላይ ድንጋጤ የሚጨምር ሁኔታ ተከሰተ በራፋ ላይ የገጠማት አንድ ግዙፍ አስፈሪ መልክና ኮስታራ ፊት ያለው ሰው ፊቷ ተጋረጠ" ወይኔ በጌታ አሁን ይሄ ምኑ ይታሻል?"ስትል በቅፅበት ውስጥ አሰበች"አሽቀንጥሮ.ገፈተራትና.ወደውስጥ.ገባ።በድንጋጤ.አይኖቿን.በለጠጠች።
በየክፍሉ እየገባ ይፈትሽ ጀመር።ቁም ሳጥኖቹን ሁሉ እያንዳንድን መሳቢያ ሳይቀር እየከፈተ እየዘጋ ማየቱን ቀጠለ
"ይሄ ምን የሚሉት ደንበኛ ነው? "ስትል በውስጧ አሰበች። በሁኔታው ተበሳጨች፤ስትበሳጭ.በመጠኑ.ፍራቻዋ.ቀነስ.አለላት።
"ጌታዬ ምን ፈልገው ነው?"
መሀል ወለል ላይ ቆመና ዙሪያ ገባውን ኮርኒሱንም ሳይቀር በጥንቃቄ ካየ በኋላ ለእሷ ጥያቄ ምንም መልስ ሳይሰጥ እንደ አመጣጡ መልሶ ወጣ። ይበልጥ ግራ ተገባች፡፡ ይሄ ጠረንገሎና አስቀያሚ እዛ የማሳጅ ጠረጴዛ ላይ ተኝቶ እሺኝ ስላላላት እግዚያብሄር ይመስገን ብላ አመስግና ሳትጨርስ በራፍ ተከፈተና ያው ሰውዬ መልሶ አንገቱን አሰገገ...ሀሞቷ ፍስስ አለ...በራፉን ሙሉ በሙሉ ከፈተው ሌሎች ሰዎች ታያት።ሶስት መሆናቸውን አየች።
"በአንዴ ሶስት ሰው ማሸት ይቻላል እንዴ? እንዲህ አይነት ነገር እንዳለ አልተነገረኝም...ምን ነካቸው ቢያንስ ለተለማማጅ ሰራተኛ እንደዚህ ማድረግ ይገባል?"በውስጧ አጉረምርማ ሳትጨርስ ግራና ቀኝ የነበሩ ሁለት ወጠምሾች መሀል ያለውን ሰውዬ ወደውስጥ አስገቡትና እነሱ ወደኋላ ሸሽተው ከክፍሉ ወጡ። በራፉ ከውጭ ተዘጋ።
ግድግዳውን ተለጥፋ እንደቆመች ሰውዬው ላይ አፈጠጠችበት። ሰውዬውን ታውቀዋለች..አዎ በደንብ ታውቀዋለች። ሮጣ ሄዳ ልትጠመጠምበት ነበር።ትዝ ሲላት ለካ የምታውቀው በመገናኛ ብዙሀን ነው።ማን ነበር..አዎ አስታወሰችው። እንዴ እዚህ ምን ይሰራል?"
‹‹ጤና ይስጥልኝ ቆንጆ?››አላት በሚያምር ግን አስገምጋሚ በሆነ ድምፅ።
በፍጥነት ወደቀልቧ ለመመለስ ጥረት አደረገች። ፊቷን በፈገግታ አደመቀችና እጇን ለሰላምታ ዘረጋች….በተመሳሳይ ድምቀት ጨበጣት ...
‹‹ጌታዬ ትንሽ አረፍ ትላለህ...ወይስ?››
"ቆይ ትንሽ ትንፋሼን ልሰብስብ... ካንቺም ጋር በደንብ ልተዋወቅ።"አለና ወደሶፋው ሄደና ተቀመጠ፡፡
"ጌታዬ ቀለል እንዲልህ ኮትህን ታወልቀው?"
"አዎ ትክክል ነሽ..››ብሎ በተቀመጠበት ሶፋ ሆኖ ኮቱን አወለቀ.. በፍጥነት ተቀብላ ወደመስቀያው ሄደችና በጥንቃቄ ሰቀለችና ወደ ሰውዬው ተመለሰችና ፊት ለፊቱ ተቀመጠች።
‹‹ስምሽን ማን ልበል?›› ጠየቃት፡፡
‹‹ቬሮኒካ"አለችው፡፡ ይሄ ስም ድንገት አፏ ላይ የመጣላት ስም ነው…ለዚህ ስራ ትክክለኛ ስምን መጠቀም አግባብ መስሎ ስላልተሰማት ነው እንዲህ ያደረገችው፡፡
‹‹የእኔ ክብሮም››አላት ሰውዬው፡
‹‹ጌታዬ አንተን የማያውቅ ኢትዬጴያዊ ማን አለ?››
‹‹እንደዛ ከሆነ ጥሩ...››አለና ከኪሱ ሞባይሉን አወጣና ደወለ፡፡
"የሚጠጣ አስመጣልን እስቲ"አለና ትዕዛዝ ካስተላለፈ በኃላ ሞባይሉን ዘግቶ ቦታው መለሠና።
"ከነገሩኝ በላይ ቆንጆ ነሽ"አላት
ከት ብላ ሳቀች.‹‹..እንዴ ማነው እንዲህ አይነት ጥብቅ ሚስጥር ያሾለከው?" አለችው፡፡
"የውስጥ ሰላይ አለኝ...ከዛሬ ጀምሮ ሙሉ ስራው ያንቺን እንቅስቃሴ መከታተል ይሆናል››
"እንግዲህ እኛም ቀዳሚ ስራችን ውስጣችንን ከሰላዬችና ከሰርጎ ገቦች ማፅዳት ይሆናል" ስትለው በራፍ ተቆረቆረ ፡፡ መቀመጫዋን ለቃ ተንቀሳቀሰችና ከፈተች፡፡ ከጋርዶቹ አንዱ ነው። በሰርቪስ ትሪ ሙሉ ጠርሙስ ውስኪ ከሁለት ብርጭቆ ጋር ይዟል። አልፏት ወደ ውስጥ ገባና ጠረጴዛ ላይ አስቀምጦ ወጥቶ ሄደ ...ተከትላው ሄደችና በራፉን ከውስጥ በመቀርቀር ወደ ጠረጴዛው ተመለሰች። ውስኪውን ጠርሙስ ከፈተችና በአንድ ብርጭቆ በመቅዳት አቀረበችለትና ቦታዋ ተመልሳ ቁጭ አለች።
"እንዴ ላንቺስ?"
"እኔማ ስራ ላይ ነኝ...ሰክሬ ሰውነትህን ብቦጫጭቅህስ? "
"ነፍሴን አትቦጫጭቂያት እንጂ ለቆዳዬ ችግር የለም...በሰርጀሪ ይድናል "
"አረ ተው ...አንተን ማሳከም አይደለም ከእኔ ከድርጅቴም አቅም በላይ ነው"
"አልገባኝም...ቆዳ ቆዳ ነው?ምኑ ነው የሚከብድ››
‹‹ኸረ ጌታዬ ቆዳ ሁሉማ ቆዳ አይደለም..››
ራሱ ተነሳና ጠርሙሱን አንስቶ በባዶው ብርጭቆ ቀዳና "በይ እንደውም ጠጪና የምታደርጊኝን አድርጊኝና የሚሆነውን አብረን እናያለን....እግረ መንገዴንም የእኔ ቆዳ እንዴት የተለየ እንደሆነ እንዳውቅ ታደርጊያለሽ።
"ጌታዬ በአንድ ምስኪን ላይማ ይሄን ያህል አትጨክንባት››

👍53❤6👏3👎1
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ድክምክም ብሎታል፡፡ግን ደግሞ አልጋው ላይ ተኝቷ በሀሳብ እየተንገላታ ነው፡፡ ሰለሞን በሁለት በኩል ስለት ባለው ሰይፍ የሚጫወት ህፃን አይነት ሰው እንደሆነ እየተሰማው ነው፡፡ሞያውን በተመለከተ ለሶስት አመት በከፍተኛ የፕሮፌሽናል ደረጃ በምድረ-አሜሪካ ሲሰራ አንድም ጊዜ እንደዚህ አይነት ክፍተት ተከስቶበት አያውቅም..በዛም በራሱ ሲመካና ሲኮራ ኖሮ ነበር፡፡አሁን ግን ወደሀገሩ ተመልሶ ባጋጠሙት የመጀመሪያ ደንበኞቹ ከፍተኛ የሚባል ሽንቁር ተከስቶበታል፡፡አንድ ባለሞያ የሞያውን ስነምግባር አክብሮ ስራውን መስራት የሚገደደው ለደንበኞች ደህንነትንና ጥቅም ሲባል ብቻ አይደለም…ለራሱ ለሞያው ክብርና ተቀባይነትም እያንዳንዱ ባለሞያ የስራ-አፈፃፀም ሁኔታ ትልቅ ድርሻ አለው፡፡በሙስናና በጥቅማጥቅም የሚታለሉ ዳኞችና አቃቢ-ህጎች በሞሉበት ሀገር ፍርድቤት ሊከበርና ሊታመን አይችልም፡፡ሌላውም ሞያ እንደዛው ነው፡፡ ይህን ስራ ከጀመረ ያጋጠመችው ትልቋ ደንበኛው በፀሎት ነች፡፡እርግጥ ቀጥታ ደንበኛው እሷ ሳትሆን ወላጆቾ ናቸው፡፡ከእነሱ ጋር እየሰራ ያለውን ስራ የሞያው ስነምግባር በሚፈቅደው መንገድ ጥርትና ጥልል አድርጎ እየሰራ ነው፡፡ቢሆንም ቀጥታ ቀጣሪው ልጃቸው በፀሎት ነች፡፡እሷ ፍላጎቱን ተረድታ አፈቅርሀለው ብትለው እንኳን ፍቅሯ እሱ ለወላጆቾ በሚያደርገው የሞያ ድጋፍ ተፅዕኖ ስር የወደቀ ወይንም በይሉኝታ ስሜት የተቀነበበ ሊሆን ይችላል…ይሄንን ማንም በእርግጠኝነት ማወቅ አይችልም…በዚህም ምክንያት ከእሷ ጋር ደግሞ ያለው ግንኙነት እየሄደ ያለበት መንገድ ትክክል እንዳልሆነ ያውቃል፡፡ከሞያ ስነምግባር ውጭም እንደሆነ ያምናል፡፡ይሄ ጉዳይ ነው በጣም እያስጨነቀው ያለው፡፡ ከበፀሎት ጋር የፍቅር ስሜት በተሰማበት ቅፅበት ሁለት ምርጫ ነበረው፡፡አንድም በእሷ ቀጣሪነት ወላጆቾን ለማከም የተዋዋለውን የስራ ውል አፍርሶ ነፃ መውጣትና.. ከልሆነም ልቡን ገስፆ እና ፍቅሩን በውስጡ አክስሞ ስራው ላይ ብቻ አትኩሮ መቀጠል፡፡ቢያንስ ስራውን በተዋዋለው መሰረት ሙሉ በሙሉ አጠናቆ እስኪጨርስ ድረስ እንደዛ ነበር ማድረግ ያለበት፡፡ግን ይሄው ሁለቱንም ማድረግ አልቻለም፡፡ ‹‹ግን እኮ ይሄ በስራ አለም ቆይታዬ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈፀምኩት የሞያ ስነምግባር ጥሰት ነው››ሲል እራሱን ለማፅናናት ሞከረ…..፡፡ንግግሩ ግን እራሱንም ሊያሳምነው አልቻለም፡፡ ‹‹ስህተት የመጀመሪያም ሆነ የመጨረሻ ያው ስህተት ነው››የገዛ አእምሮ መልሶ የነገረው ነበር፡፡ ‹‹አሁን ወደኃላ መመለስ አልችልም…ይሄንን ጉዳይ ከዳር ላድርስና ..ከእሷ ጋር ያለኝ የፍቅር ግንኙነት የሚደርስበትን ከፍታ አይቼ ውጤታማ የሚሆን ከሆነ ምን አልባት ሞያውን በክብር ብለቅና ወደሌላ ዘርፍ ብሸጋገር እንኳን ያዋጣኛል››ሲል ለጊዜው የታየውን መፍትሄ አስቀመጠ…የገዛ አእምሮው ግን ወዲያው ነበር አፍራሽ የሆነ ሀሳብ የሰጠው‹‹ሰውዬ ምን ነካህ..?ይሄንን ሞያ ለቀህ…ነጋዴም ብትሆን …ወይም ደራሲ… ሁሉም ሞያ አይነቱ እና ተጋላጭነቱ በመጠኑ ይለያይ እንደሆን እንጂ የራሱ ህጋዊም ሆኑ ሞራላዊ የስነምግባር ገደቦች አሉበት…በተለይ ፍቅርን በተመለከተ ሁሉም ሞያ ይፈተናል…አስተማሪ ብትሆን ተማሪህ ላይ አይንህን መጣል የለብህም…ማናጀር ሆነህ ፀሀፊህን መጎነታተል ስህተት ነው፡፡ሞያህን ሳይሆን አመለካከትህን ነው መቀየር ያለብህ… ራስህን አታሞኝ፡፡››አለው…. ለጊዜው በዚህ ጉዳይ ላይ ከዚህ በላይ ማሰብ አልፈለገም….ጉዳዩን ለጊዜ አሳልፎ ሰጠና ብድርብሱን ተከናንቦ እራሱን ለእንቅልፉን አሳልፎ ሰጠ ....ወዲያው ነበር ያሸለበው…የሚገርመው ደግሞ አይኖቹ በተከደኑ ከሁለት ደቂቃ በኃላ ነበር በፀሎት ነጭ ቬሎ ለብሳ ጭንቅላቷ ላይ የሚያብረቀርቅ የወርቅ አክሊል አጥልቃ ግራና ቀኝ ጎኗ ላይ የበቀሉ ውብ ክንፏቾን እያማታች ከሰማዩ ላይ ሰንጥቃ መጥታ እቅፉ ውስጥ ስትገባ በህልሙ ያየው፡፡
///
በፀሎትና ለሊሴ ከወንጪ ከተመለሱ ሁለት ቀን ሆኗቸዋል፡፡መሽተዋል…አንድ ሰዓት ተኩል አካባቢ ነው…በፀሎት እና ፊራኦል ግቢው ውስጥ ካለ ግዙፍ የመንጎ ዛፍ ስር ጎን ለጎን ቁጭ ብለው እያወሩ ነው፡፡
‹‹እንዴት ነበር ወንጪ?››
‹‹ውይ ሲዊዘርላድ በለው፡፡››
‹‹እኔ ወንጪን እንጂ ሲዊዘርላንድን አላውቃትም፡፡››
‹‹አኔ ደግሞ አውቃታለዋ ለዛ ነው ያነፃፀርኩልህ..ደግሞ ዘመዶቻችን እንዴት ደግና ቀሽት መሰሉህ?፡፡››
‹‹የእኔም ዘመዶች እኮ ናቸው አውቃቸዋለው››
‹‹አይ ቢሆንም ..አንተ ምንአልባት ከልጅነትህ ጀምሮ ስለምታውቃቸው …ብዙም ጣእም ላይሰጥህ ይችላል..ማለት ሁለም ሰው እንደእነሱ አይነት ዘመድ ያለው ስለሚመስልህ ተራ ነገር አድርገህ ልትቆጥረው ትችላለህ….እንደእኔ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደዛ አይነት ዘመድ ሲኖርህ ግን በቃ ..ከአሁኑ እንዴት እንደናፈቁኝ ብታውቅ››
‹‹ገና በሁለት ቀን››
‹‹አዎ በሁለት ቀን››
‹‹አሁን ከእኛ ስትለይና ወደቤትሽ ስትሄጂ እንናፍቅሻለን ..?ማለት እኔ ናፍቅሻለሁ?››ለቀናት በውስጡ ሲያብሰለስለው የነበረውን ጥያቄ ጠየቃት፡፡
‹‹ምን ማለት ነው….?ወደየትኛው ቤቴ ነው የምሄደው?››
‹‹ወደቦሌው ቤትሽ››
‹‹ምን….ለሊሴ ነገረችህ››
‹‹እሷ ታውቃለች እንዴ?››
‹‹እሷ ካልነገረችሽ ታዲያ ማን ነገረህ?››
‹‹እራሴ ነኝ የደሰረስኩበት ..ወደ ወንጪ ከመሄዳችሁ በፊት ነው ያወቅኩት››
‹‹እኮ እንዴት ልታውቅ ቻልክ?››
‹‹ያው እንዳልኩሽ የእህቴን ልብ ከተቀበልሽ በኃላ በሩቅ ሆኜ ለረጅም ጊዜ ስከታተልሽ ነበር..ስለዚህ በደንብ አውቅሻለው…እዚህ ቤት ከመጣሽ ከሳምንት በኃላ ጀምሮ ከፍተኛ ጥርጣሬ አድሮብኝ ነበር..ከዛ ምን አደረኩ አንድ ቀን ስትተኚ ሻርፕሽን ሙሉ በሙሉ ከፊትሽ ላይ ገፍፌ ተመለከትኩሽ…እና ኦርጅናለዋ በፀሎት መሆንሽን አረጋገጥኩ፡፡
‹‹ትገርማለህ..ከዛ ፀጥ አልክ?››
‹‹ምን ላድርግ…ምንም ማለትና ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላወቅኩም ነበር፡፡››
‹‹አሁንስ አወቅክ?››
‹‹አይ….አንቺ ንገርኝ እስኪ …ምን ልታደርጊ ነው…?እስከመቼ ነው ከወላጆችሽ ምትደበቂው?››
‹‹ወላጆቼን በቀደም አግኝቼቸዋለው..እዚህ መሆኔን ያውቃሉ››ብላ ያልጠበቀውን ዜና ነገረችው፡፡
‹‹ጥሩ..እሺ እነአባዬን እንዴት ልታደርጊ ነው….?እንደዋሸሻቸው ሲያውቅ በጣም ነው የሚያዝኑብሽ…በአንቺ ብቻ ሳይሆን እኛም አውቀን ከነሱ ደብቀን ዝም በማለታችን ምን እንደሚወጥን አላውቅም? በጣም ጨንቆኛል›ብሎ እውነተኛ ስሜቱን ነገራት፡፡
‹‹ይቅርታ ፊራኦል..እንደዚህ አይነት ነገር ውስጥ ስላስገባዋችሁ በጣም አዝናልው…ግን በዚህ ሁለት ሶስት ቀን ውስጥ እፈተዋለው…ማለት እናንተ ቀድማችሁ እንደምታውቁ ሳላሳውቅ እፈተዋለው››
‹‹እስኪ እናያለን…››
‹‹እኔ የእህትህን ልብ የተሸክምኩ በፀሎት መሆኔን እርግጠኛ ስትሆን ምን ተሰማህ?››
‹‹ግማሽ ሀዘን ግማሽ ደስታ››
‹‹አልገባኝም››
‹‹ለረጂም ጊዜ ላናግርሽና ቀርቤ ላወራሽ የምመኝሽ የእህቴን ከፊል አካል የተሸከምሽው በፀሎት የገዛ ቤቴ መጥተሸ ከእኔ ጋር አንድ መአድ እየቆረሽ መሆንሽን ሳውቅ ፍጽም ድስታ ነው የተሰማኝ…በሌላ ጎኑ ደግሞ ያችኛዋን በፀሎት አፍቅሬት ስለነበር….ሌላ በፀሎት እንዳልሆንሽ ሳውቅ ቅር ብሎኛል››
‹‹ከመቀመጫዋ ተነሳችና እላዩ ላይ ተጠምጥማ ጉንጩን እየሳመችው‹‹….የእኔ ወንድም

👍66❤14🥰2👏2
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ
================
አለማየሁ በቀጠሮው መሰረት ከአላዛርና አለማየሁ ጋር ከተገናኘ በኋላ ‹‹እሺ ባላና ሚስቶች ለምንድነው የፈለጋችሁኝ….?ለጥሩ ነገር እንደሚሆን እገምታለሁ፡፡››ሲል የመጀመሪያ ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡
ሁለቱም እርስ በርስ ተያዩ..አንተ ንገረው አንቺ ንገሪው እየተባባሉ የሚገባበዙ ይመስላል አላዛር ቅድሚያውን ወሰደ‹‹በሚቀጥለው ሳምንት ሁሴን እንደሚመጣ ታውቃለህ አይደል?››
ያልጠበቀውን ርዕስ ነው ያነሳበት‹‹ትክክለኛውን ቀን አላውቅም እንጂ እንደሚመጣ አዎ በቀደም ደውሎልኝ ነበር..››
‹‹ጥሩ እንግዲህ ..እናቱም አባቱም እንደሞቱ ታውቃለህ…..እዚህ ሌላ ዘመድ የለውም ..ከፋም ለማም የልጅነት ጓደኞቹና የቅርቡ ሰዎች እኛ ሶስታችን ነን››
በውስጡ ‹‹የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች›› የሚለውን ተረት እየተረተበት ‹‹አዎ ትክክል››ሲል መለሰ፡፡
‹‹እና እንዴት እንቀበለው የሚለውን ለመነጋገር ነው፡፡››
‹‹በጣም ጥሩ ሀሳብ ነው፡፡ይሄ የድሮ ጓደኛችንን የመቀበል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን እኛም መልሰን ለአመታት ተራርቀን ከቆየንበት ለመቀራረብና መልሰን ጓደኝነታችንን ለማደስ ያግዘናል….››አለ
…እንደዛ ሲል በውስጡ ያለው ከአላዛር ወይም ከሁሴን ጋር ይበልጥ ተቀራርቦ ድሮ ጓፈደኛነታችው የመመለስ ጉጉት ኖሮት አይደለም..ከዛ ይልቅ ስለሰሎሜ በውስጡ እያሰበ ነው፡፡
‹‹በጥሩ ሁኔታ ብንቀበለው ደስ ይለኛል…እኔ የሚጠበቅብኝን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ….ዝግጅቱን እኔ ቤት ማድረግ እንችላለን››አለ…
‹‹አይ ከአንተ ቤት የእኛ ቤት ይሻል ይመስለኛል….ማለት የወንደላጤን ቤት ማድመቅ ይከብዳል›› ሰሎሜ ነች ተናጋሪዋ፡
‹‹እሺ እንዳልሽ…እኔ ቤት ብንቀበለው በዛውም የራሱን ነገር እስከሚያመቻች አኔ ጋር መቆየት ይችላል ብዬ ነው፡፡››
‹‹እኛ ጋርስ ለመቆየት ምን ይከለክለዋል…?እቤታችን እንደሆነ እንኳን እሱንና አንተም ብትጨመር በቂ ክፍት ክፍሎች አሉን ….እንደምታውቀው እዛ አፓርታማ ቤት ውስጥ እኔና እሱ ብቻ ነን....ልጅ የለን ምን የለን››
በሰሎሜ ንግግር አላዛር ሽምቅቅ አለ..ሆነ ብላ አስባበት የተናገረችው እንደሆነ ያውቃል….ግን ዋጥ አድርጎ በትዕግስት ከማሳለፍ ውጭ ምርጫ እንደሌለው ያውቃል፣ያደረገውም እንደዛ ነው፡፡
አለማየሁ‹‹በቃ እሺ እጅ ሰጥቼለው››ሲል በሀሳባቸው ተስማማ፡፡
‹‹ጥሩ በቃ …እንደዛ ከሆነ በፊታችን እሁድ ቤት ናና ስለዝርዝሩ እንነጋገርበታለን››
‹‹ጥሩ..እንደውም በሰበቡ ቤታችሁን አያለሁ››
‹‹አዎ ››
ከዛ በኃላ ብዙም ያወሩት ነገረ የለም ፡፡ተሰነባብተው ተለያዩ፡፡
‹‹አላዛር እና ሰሎሜ በአንድ መኪና ገብተው ወደቤታቸው እየተጓዙ ወሬ ጀመሩ‹‹ግን እርግጠኛ ነህ..?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹ምኑን?››
‹‹ማለቴ የሁሴን እኛ ቤት ማረፍ….ነው ወይስ አንድ ሁለት ቀን እኛ ጋር ካደረ በኃላ ሌላ ማረፊያ ፈልግ ልንለወው ነው፡?››
‹‹ለምን …አንቺን ካልደበረሽ እቤታቸን ሰፊ ነው…ሁሴን የማናውቀው ሰው አይደለም ….ለሁለታችንም ቅርብ የሆነ ሰው ነው፡፡››
‹‹ገባኝ….በደንብ አስበህበታል ወይ ለማለት ነው…?.እኔማ ደስ ይለኛል..ግን እወቅ እንደነገረኝ ከሆነ እስከሶስት ወር ሊቆይ ይችላል፡፡››
‹‹ችግር የለውም..ታውቂያለሽ የሆነ የእኛ የምንለው ሰው አብሮን እንዲኖር እንዴት እፈልግ እንደነበረ…እህቶቼም ሁለቱም ስላገቡ ወደቤታችን ላመጣቸው አልቻልኩም…የአንቺም እናት አሻፈረኝ ብላለች..እስኪ አሁን በጓደኛችን እንሞክረው፡፡››
‹‹እማዬ እኮ ከእናንተ ጋር አልኖርም አላለችም..እሷ ያለችው ልጅ ስትወልዱ እሱን ለማሳደግ መጣለሁ…አሁን ግን መጥቼ የእናንተ ሞግዚት መሆን አልፈልግም ነው ያለችው››።
‹‹እና በሞግዚት ኑሪ እንጂ ሞግዚት ሁኚን መች አልናት?››
‹‹ተወው አሁን… ለምን የማይሆን ጭቅጭቅ ውስጥ እንገባለን…ቁርጥ አድርጋ አቋሟን አሳውቃለች…መውለድ ስንችል ትመጣለች››
‹‹ይሁን እሺ… ለማንኛውም ስለሁሴን አትጨነቂ… ሁኔታዎች ካልተመቹት እኮ እራሱ አማራጭ ይፈልጋል፡፡››በማለት የተጣመመውን ርእስ እንደምንም ብሎ አቃናው፡፡
‹‹ጥሩ..ለእኛም ከብቸኝነት ጋር ከመታገል በተወሰነ መንገድ ይታደገናል…›› ስትል መለሰች፡፡
‹‹እኔም እሱን አስቤ ነው ››አላት..ግን ሁለቱም ስጋታቸው ሌላ እንደሆነ ግልፅ ነው…ሁሴን ልክ እንደአላዛር ሁሉ የሰሎሜ የልጅነት አፍቃሪዎ እንደሆነ ሁለቱም ያውቃሉ፡፡ለሁለቱም እኩል ጓደኛቸው ቢሆንም ለእሷ ግን በተለየ መልኩ አፍቃሪዋም ጭምር ነው…እና አሁን አንድ ቤት እሱን ጎትቶ ማምጣት ለዛውም አሁን ባልና ሚስቶቹ ባሉበት ሁኔታ ላይ አደጋ እንዳለውና የልታሰበ መዘዝ ሊያመጣ እንደሚችል…ለሁለቱም ግልፅ ነው….እና ሰሎሜ ደጋግማ ስለውሳኔው እርግጠኝነት እየጠየቀችው ያለው..ነገ አንድ ነገር ቢከሰት ኃላፊነቱን እንዲወስድ በማሰብ ነው፡፡
እሷ ያላወቀችው ግን የእሱን እቅድ ነው…እሱ ሁሴን ወደቤት እንዲመጣ ሲወስን መዘዙንም አስቦና አስልቶ ነው፡፡ምን አልባት የጀመረው የህክምና ጉዳይ ባይሳካለት ሊያደርግ የሚችለውን እቅድ አስቦና አስልቶ ጨርሷል..በቃ እራስ ወዳድ መሆን እንደሌለበት ገብቶታል…እየወደደም ቢሆን ከሰሎሜን ህይወት ሾልኳ መውጣት እንዳለበት ወስኗል.. ከህይወቱ ሲሸኛት ግን በተሰበረ ልብ ሆና ስነልቦናዋ ተጎድቶ መሆን እንደሌለበትም ነው የሚያምነው..ለእሱ መሆን ካልቻለች ከሁለት የልጅነት ጓደኞቾና ከልብ ከሚያፈቅሯት መቼም ቢሆን ሊጎዶት ለማይችሉት ለአንዱ ሊያስረክባት ነው ያሰበው….ለዛም ጥሪጊያ መንገድ ለመፍጠር ሁሴን በእንግድነት እሱ ቤት ማረፍ እንዳለበት ማድረግ እንዳለበት ተሰምቶታል፡፡፡ያንን ካደረገ ደግሞ አለማየሁም በተደጋጋሚ ወደእሱ ቤት ለመመላለስና ከሰሎሜ ጋር በተደጋጋሚ ጊዜ የመገናኘት እድል ይኖራዋል፣በሂደት ከሁለት አንዱ ከእሷ ጋር በተሻለ መቀራረብ ይፈጥሩና ልቧን ማግኘት ይችሉ ይሆናል….ከዛ አንዱ ያገኛታል ማለት ነው፡፡ከዛ እሱ ሀዘኑን ለብቻው ያዝናል..ማጣቱን በማስታመም ቀሪ የብቸኝነት ዘመኑን ይገፋል…….፡፡እግዚያብሄር ቀንቶት ከተፈወሰ ደግሞ በቃ ምን ይፈልጋል…እና አሁን እያደረገ ያለው ቅድመ ዝግጅት ነው፡፡ይሄ ነው ሰሎሜን ያልገባት፡፡
ይሄ ጉዳይ ደግሞ ከሰሎሜ ይልቅ አለማየሁን ነው ፍፅም ግራ ያጋባው‹‹ሰውዬው ምን እየሰራ ነው?››የሚለው ሀሳብ በውስጡ መጉላላት የጀመረው ገና ከእነሱ እንደተለየ ነው፡፡እና ደግሞ አልተመቸውም….በመጀመሪያ ደረጃ በዚህ ወሳኝ ወቅት የሁሴን ወደሀገር ቤት ተመልሶ መምጣት ደስ አላሰኘውም ነበር፡፡፡በእሱ እምነት አላዛር ካልተሳካለት ቀጥታ ሰሎሜን የእሱ የማድረጉን ትግል በብቸኝነት ለመወጣት ነበር ዕቅዱም ምኞቱም..ሁሴን ደውሎ እንደሚመጣ ከነገረው በኋላ ግን ሌላ ተፋላሚ እየመጣበት እንደሆነ ነው ወዲያው የገባው…እንደውም መምጣቱ እራሱ ያጋጣሚ ነገር ሳይሆን ሆነ ብሎ የታሰበበት እንደሆነ ነው የሚጠረጥረው…ሰሎሜ አላዛርን ከማግባቷ በፊት ከእሱ ጋር ለረጅም ጊዜ እንደምትደዋወል ነግራዋለች..በእሷ እና በባሏ መካከል ያለውን ቦንብ ሚስጥር ለእሱ በተገናኙበት በመጀመሪያው ቀን ከነገረችው…ለረጅም ጊዜ ስትደዋወል ለነበረው ለዛውም ከባህር ማዶ ላለው ሁሴን ላትነግረው የምትችልበት ምክንያት ምንም እየታየው አይደለም…እንደጠረጠረው ነግራው ከሆነ ደግሞ በተለይ የሰሞኑን ግር ግር አብራርታለት ከሆነ የሆነ ምክንያት ፈጥሮ አጋጣሚውን ለመጠቀም እንደመጣ ነው የሚያምነው..እና ከእሱ ጋር

👍60❤14😁4
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///
‹‹ጋሽ ፍሰሀ..አንተ ነህ…?››
‹‹አዎ አለም…እዚህ ምን ትሰሪያለሽ?››አውሬው ካስደነገጠው በላይ የእሷ በዚህ ሰዓት እዚህ አካባቢ መገኘት አስደነገጠው፡፡
‹‹እንዴ ስልክ እያወራን ነበር እኮ የተቆረጠው….መኪናህ እንደተገለበጠች እርግጠኛ ስለነበርኩ ወዲያውኑ ወደእዚህ የመጣሁት…መኪናህን ቀድሜ ባገኛትም ውስጡ የለህም..ግን የሚንጠባጠበውን ደም እየተከተልኩ ደረስኩብህ››
‹‹ስሩ ደርሳ ደገፈችው››
‹‹አብሮሽ ማን አለ?››
‹‹አረ ማንም የለ….መንገድ ላይ ሆኜ ለጁኒዬር ደውዬለታለው..ይሄኔ እየመጡ ይሆናል፡››
‹‹ይገርማል..የሆነ ነገር ቢያጋጥምሽስ?››
‹‹ሀሳቤ ሁሉ ያንተን ደህንነት ማረጋገጥ ላይ ስለነበር እሱን አላሳብኩትም ነበር…እውነቱን ንገሪኝ ካልከኝ ግን አሁን በፍራቻ እየተንቀጠቀጥኩ ነው፡፡››
‹‹በጣም ነው ያስገረምሺኝ..አይዞሽ አሁን አምስት ደቂቃ ነው ደርሰናል….እንደውም እዛ መብራት ጭልጭል የሚልበት ቦታ ይታይሻል …?እዛ ነው ጎጆው…በአቅራቢያው የእኔ ሰራተኞች ቤትም አለ…››
‹‹ በአንድ እጇ ደግፋው በሌላ እጇ ደግሞ የስልኳን ባትሪ ከፊት ለፊት እያበራች ወደፊት በዝግታ መራመዳቸውን ቀጠሉ፡፡
አቶ ፍሰሀ ከአውሬው ጋር የነበረው መፋጠጥ አሁንም ከምናብ ሊደበዝዝ አልቻለም… ልቡ ለምን እንዲህ ከመጠን በላይ መታ? ጉዳዩ ምን ነበር? የዱር አውሬው በጣም አስፈርቶት ነው? አይደለም፡፡ እሱ ስለእነሱ አላሰበም። በህይወቱ የበለጠ አስፈሪ ነገሮችን አሳልፎ ያውቃል። ወዲያው ከኃላቸው እየተንሾካሾኩ የሚመጣ የእግር ኮቴ ሰሙ…መንገዱን ለቀቁና ጢሻውን ተከልለው ቆሙ..ሲጠጎቸው ማንነታቸውን በድምፅ ለዩ…‹‹ገመዶ››
ባትሪውን ሲያበራባት ፈጽሞ እዚህ አገኘዋለሁ ብሎ ያላሰበውን አቶ ፍሰሀን በአለም ተደግፋፎ ልክ እንደተወዳጅ ልጁ ስሩ ተሸጉጣ ሲያይ አይኑን ማመን አልቻለም፡፡
ሁሉም ተንደርድረው ከበቧቸው‹‹ጋሼ ምን እየተካሄደ ነው?››
‹‹አይዞችሁ አትደንግጡ… ተርፌለው››
‹‹ተርፌለው ማለት?››ኩማንደሩ በመገረም ጠየቀ፡፡
‹‹የመኪና አደጋ እንደደረሰብኝ ሰምታችሁ አይደለም እንዴ የመጣችሁት?››
‹‹አረ በፈጣሪ..ተርፍክ ታዲያ…?እኛ አልሰማንም..እሷን ከከተማ ስትወጣ አይተን ተከትለናት ነው የመጣናው…ከጠላቶቻችን ጋር ልትገናኝ መስሎን ነበር››
‹‹አይ እሷ እኔን ለማትረፍ ነው የመጣችው››
‹‹እንዴት ከእኛ ቀድማ ልትሰማ ቻለች?..ነው ወይስ በአደጋው ላይ የእሷ እጅ አለበት?››
‹‹እሱን ጎጆው ጋር ደርሰን ትንሽ ካረፈ በኃላ ብትጠይቀው አይሻልም?››አለችው አለም በንዴት፡፡
‹‹ለምን ወደጎጆ እንሄዳለን? መኪናችንን እኮ በቅርብ ርቀት ላይ ነው ያቆምናት..እዚሁ ጠብቁኝና ይዣት ልምጣ..ቀጥታ ወደከተማ ሄደህ ህክምና ማግኘት አለብህ››
‹‹አይ ደህና ነኝ..አሁን ማረፍ ነው የምፈለገው..ወደጎጆ ውሰዱኝ››
‹‹ተው እንጂ ፍሰሀ ..ሀኪም ሊያይህ ይገባል››ዳኛው ጣልቃ ገብተው ለኩማንደሩ ድጋፋቸውን ሰጡ፡፡
‹‹የበለጠ እያደከማችሁኝ መሆኑን ልብ አላላችሁም እንዴ..?ወደጎጆ መሄድ ነው የምፈልገው›› በማለት የማይቀየር አቋማቸውን አሰሙ፡፡
‹‹ይቅርታ ጋሼ..አንተ ካልክ እሺ ወደጎጆ እንወስድሀለን….እነ ጁኒዬርም አሁን ደውለውልኝ ነበር …መገንጠያው ጋር ደርሰዋል….ከደቂቃዎች በኃላ ይደርሳሉ..››አለና ሄዶ በሌላ ጎኑ አቶ ፍሰሀን ደገፈ….ከ5 ደቂቃ በኃላ ጎጆዋ ደረሱ፡፡ፋኖስ አበሩ፣ መኝታው ተስተካክሎ እንዲተኛ ተደረገና በቅርብ ርቀት ያሉ ሌላ የሳር ቤት ውስጥ ወደሚኖሩት የእነሱ ሰራተኞች ተቀስቅሰው መጡ..እሳት እንዲቃጣጠል ተደረገ…ጁኒዬርና ሳራ የመጀመሪያ ለእረዳታ መስጫ የሚያለግሉ ቁሳቁሶች ይዘው እያለከለኩ ደረሱ…ለተወሰነ ጊዜ ለቅሶና ግርግር በጠባቧ ጎጆ ነገሰ..ከዛ ቀስ በቀስ ወደመረጋጋት ቢመጣም በሰው ብዛት በታፈነችው ጎጆ ውጥረትና ጭንቀት ነግሶ ነበር፡፡
‹‹ቆይ እኔ ያልገባኝ…ምንድነው የሚያስጠብቀን..?ለምንድነው ወደከተማ ይዘነው ሔደን ሀኪማ የማያየው?››ሳራ ነች ግራ በመጋባት ተመሳሳይ አይነት ጥያቄ ለሶስተኛ ጊዜ ያነሳችው፡፡
‹‹ጋሼ አልፈልግም ስላለ እኮ ነው…ጋሼ አሁን ትንሽ አርፈሀል፣ብንሄድ ምን ይመስልሀል?››ኩማንደር ነው ተናጋሪው፡፡
‹‹አይ ዛሬ ማንም ከዚህ አይሄድም…አሁን ሰዎቹን ሸኞቸውና የምንነጋገረው ነገር አለ››ሲል ሁሉም በቀጣይ ምን ሊፈጠር ነው በሚል እርስ በርስ ተያዩ፡፡
ጁኒዬር ከጎረቤት ጎጆ የመጡትን ባልና ሚስቶች ከነልጆቻቸው አመስግኖ ወደቤታቸው እንዲሄዱ ካደረገ በኃላ የጎጆዋ ቤት ተዘጋ፡፡አሁን ስድስት ሰዎች ፊት ለፊት ተፋጠጡ …ሁለቱ ሴቶች እና አዛውንቱ ዳኛ አቶ ፍሰሀ ጎን የተቀመጠችውን አለምን በከፍተኛ ጥላቻን መጠየፍ ነበር የሚመለከቷት፡፡
አቶ ፍሰሀ ከትራሱ ቀና አደረገና አስተካክሎ በመደገፍ መናገር ጀመረ‹‹ዛሬ እየሆነ ያለው ሁሉ ነገር ተአምር ነው…እኔ እቅዴ እንደማንኛውም ቀን ስራ ውዬ ወደቤቴ መግባት ነበር….ነገር ግን የሰሞኑን ውጣ ውረድ እያሰላሰልኩ ሳላስበው ከከተማ ወጣሁና እራሴን እዚህ ሶሌ ደን አካባቢ አገኘሁት..እንዴት እዚህ ልደርስ ቻልኩ? ብዬ እየተገረምኩ ሳለ ያልጠበቅኳት አለም ደወለችልኝ..ከእሷ ጋር እያወራው ሳለ ድንገት ሳላስበው አውሬ ገባብኝና እሱን አድናለው ስል መኪናዬ መንገድ ስታ ተገለበጥኩ…እንደአደጋው መሞት ነበረብኝ..ግን ከተወሰነ ጭረት በስተቀር ምንም አልሆንኩም…እግዜር አሳይቶ ከሞት ደጃፍ መለሰኝ..ከመኪናው ወጥቼ በጫካው እያሳበርኩ ወደእዚህ እየመጣው ሳለ ከጅብ ጋር ፊት ለፊት ተፋጠጥኩ…እሱንም ወደሰማይ ተኩሼ አስበረገግኩትና ሁለተኛውን ፈተና አለፍኩ..ከዛ ወዲያው አለምን ከፊት ለፊቴ አገኘኃት..ወዲያው እነ ገመዶና መጡ…ጎጆው እንደደረስን ደግሞ ልጄና ባለቤቴ መጡ …እኔ ለማናችሁም አደጋ ደረሰብኝ ብዬ አልደወልኩም..በአደጋው ጊዜ ስልኬ ወደየት እንደጠፋም አላውቅም..ግን ሁላችሁም እዚህ ተገኝታችኃላ..ሁላችንን እዚህ ያለነው ለምክንያት ነው፡፡ከአለም ጋር የጀመርነው ድብብቆሽ እዚህ ጋ ማብቃት መቻል አለበት፡፡
‹‹አዎ ማብቃት አለበት …ይህቼ ሴት ከዚህ በፊት ንብረቴ እንዲቃጠል አደረገች… ዛሬ ባለቤቴን ገድላብኝ ነበር….››ሳራ ተንዘረዘረች…ዳኛውና ስርጉት አይናቸውን በማጉረጥረጥ እና በመገላመጥ ለሳራ ያላቸውን እገዛ አሳዩ ፡፡
‹‹ሳራ ተይ ..ዛሬ የምንበሳጭበትና ራሳችንን ሀጥያት ለመሸፈን ሌላ ስው በሀሰት የምንወቅስበት ቀን አይደለም..እኔ አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከሁለት ሞት ነው የዳንኩት…ይሄ ያለምክንያት አይደለም..ይህቺን ልጅ ሁላችንም በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ በድለናታል…ሁላችንም ለእሷ መናዘዝ መቻል አለብን..እውነቱን ልንነግራት ይገባል..ከዛ አመዛዝና ከፈለገች ትበቀለን… ከፈለገች ደግሞ ወደፍትህ አደባባይ ወስዳ ታሰቅለን፡፡
የአቶ ፍሰሀን ንግግር የሰሙት ዳኛው ጫንቃቸውን አላባቸው፡፡ይሄ ሰውዬ በተገበጠበት ወቅት ጭንቅላቱን ተመቶ ማሰቢያው ላልቶ ይሆን እንዴ?››ሲል አሰበና አይኑን ገመዶና ጁኒዬር ላይ አንከራተተ…የሆነ ነገር ብለው የጀመረውን ቅዠት የመሰል ድርጊት እንዲያስቆሙት ነው ፍላጎቱ.

❤45👍4