#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
የሰው ልጆች የህይወት ጉዞ ልክ እንደ ሸረሪት ድር ነው፡፡እርስ በርሱ የተቆላለፈ.. የተሳሰረ እና የተወሳሰበ፡፡
…ሶፊያ ዲያስፖራ ነች፡፡የኢትጵያውያን ሲያኮሩፉ ሆነ ፈጣን በሆነ የህይወት ጉዞ ወጤታማ መሆን ምኞት በልባቸው ሲፀነስባቸው ግን ደግሞ ያንን ወደ ተግባር
ለመመንዘር የእኔ የሚሏት ሀገራቸው ዕድልና
አጋጣሚውን አላመቻችላቸው ስትል በኩርፊያ መልክ ከሚከትሙባት ሀገረ አሜሪካ ተመልሳ ወደሀገር ቤት ከገባች ገና አራት ወር
አልሞላትም፡፡
የተመለሰችበት ምክንያት ወደ ሀገር ተመልሳ ልማቱን እንድታፋጥን መንግስታዊ ጥሪ ተደርጎላት አይደለም፤ የአሜርካ ኳኳታ ሰልችቷት እንጂ፡፡
የሀገሯ አየር፣የሀገሯ ሰው፣የሀገሯ ፍቅር ናፍቆት
እንጂ፡፡ግን ይሄን እንዲሁ ሰዎች ለምን ተመለሽ
ብለው ሲጠይቋት ምትመልላቸው መልስ
ነው፡፡ትክክለኛው ምክንያቷ ግን እሷ ብቻ ነች ምታውቀው፤ምህረትን ፍለጋ ነው የመጣችው፡፡የዕድሜ ልኳን ፀፀት ከልቧ ለማራገፍ የሚያግዛትን ይቅርታ ለማግኘት፤ግን ከመምጣቷ በፊት እንዳሰበችው መንገዶች ቀላል አልሆኑላትም፡፡ከፀፀት ደዌ ልትፈውሳት የምትችለዋን ሴት በቀላሉ መቅረብ አልቻለችም፡፡
ዶ/ር ሶፊያ ወደ ሀገር ቤት ከተመለሰች በኃላ አንድ ዓለምአቀፍ ግብረሰናይ ድርጅት ውስጥ ነው ተቀጥራ የምትሰራው፡፡ቋሚ የስራ ቦታዋ አዲስ አበባ ቢሆንም አሁን ወደ ሀዋሳ ለመሄድ ዝግጅት ላይ ነች ፡፡አንድ አለም አቀፍ ድርጅት ለሶስት ቀናት ባዘጋጀው ሴሚናር ላይ ለመሳተፍ ፡፡
ሁሉንም ዝግጅቴን አጠናቅቄያለሁ ብላ እንቅስቃሴ ልትጀምር ስትል ነበር ያላሰበችው እክል የገጠማት፡፡ከግቢው ሳትወጣ መኪናዋ ተበላሸባት፡፡እዛ ጠብራራ አለቃዋ ጋር ደውላ የገጠማትን ችግር በዙሪያ ጥምዝ አስረድታ ሌላ መኪና እንዲቃይርላት ለማሳመን አሰበች፡፡
ግን አስባ ሳትጨርስ ደከማትና ተወችው፡፡
ሴሚናሩ የሚጀምረው ደግሞ ነገ ጥዋት ነው፤ስለዚህ ዛሬ ገብታ ማደር አለባት፡፡
መካኒክ አስመጥታ ለማሰራትም የማይታሰብ
ነገር ነው፡፡ለዛ የሚሆን በቂ ጊዜ የላትም፡፡
በትራንስፖርት ለመሄድ ወሰነች፡፡በሻንጣ ይዛ
የነበረውን ልብስ ወደ ቤት መለሰችና አስፈላጊ የሆኑትን ብቻ ወደ ቦርሳዋ ቀነሰች፡፡ አንድ መኪና ያለው የቅርቧ የሆነ ሰው ጋር ደውላ ቃሊቲ መነኸሪያ ድረስ ስለሸኛት ሚኒባስ ተሳፍራ ወደ ሀዋሳ ጉዞ ጀመረች፡፡ቢሾፍቱን አልፈው ሞጆን ተጠምዝዘው ቆቃን ተሸግረው መቂ አካባቢ ሲደርሱ ረዳቱ ሂሳብ መሰብሰብ ጀመረ….፡፡
ዶ/ሶፊያ ጋር ደረሰ ‹‹ሂሳብ›› አላት፡፡ቦርሳዋን ከፈተች... ፈለገች... በረበረች.. የእጅ ቦርሳዋ የለም፡፡
ረዳቱ‹‹እህት ሂሳብ ››ሲል ጥያቄውን ደገመው፡፡
‹‹እዚ ውስጥ ነበር.. ቤት ረስቼው መጣሁ መሰለኝ››በጣም ደነገጠች፡፡ጠይም ፊቷ ላይ ላቧ ቸፍ አለባት፡፡
‹‹ገንዘብ አልያዝኩም..።››
‹‹ባክሽ ሙድ አትያዢ፡፡››
‹‹እውነቴን ነው፡፡ ሞባይሌም፣ገንዘቤም፣ የእጅ ቦርሳዬ ውስጥ ነበር..እዚህ ውስጥ የከተትኩት መስሎኝ ነበር፡፡››
‹‹እኔ ጭቅጭቅ አልፈልግም…ሂሳቤን ስጪኝ፡፡››ረዳቱ ፊት ነሳት፡፡
‹‹ወንድም አንዴ ሞባይል ብታውሰኝ››ስትል ከጎኗ የተቀመጠውን ወጣት ጠየቀችው፡፡ ጥቁር ቆዳ ጄኬት ለብሶ ጥቁር መነፅር ፊቱ ላይ የሰካ ደልደል ያለ ሰው ነው፡፡
‹‹ይቅርታ ባትሪ ዘግቷል››አላት፡፡ይሄንን የሰማው ከፊት ለፊት የነበሩ አንድ አዛውንት ሰጧት፡፡
ደወለች‹‹ሄሎ ሰኒ ..ሶፊያ ነኝ፡፡››
‹‹የእጅ ቦርሳዬ አለ..?እስቲ እይልኝ፡፡››
‹‹አዎ በናትሽ ....ባንክ ደብተሬም መታወቂያዬም ውስጡ ነው፡፡››
‹‹ምንም ብር አልያዝኩም፡፡››
‹‹ምን ማድረግ እደምችል አላውቅም፡፡ ብትልኪልኝ እራሱ እንዴት አወጣለሁ..? መታወቂያ የለኝም..፡፡››
‹‹በቃ ለማንኛውም ከፈለኩሽ ሚስኮል አደርግልሻለሁ..››ብላ ስልኩን ዘጋችና ለባለቤቱ በመመለስ ‹‹ወንድም ሀዋሳ የማውቃቸው ሰዎች አሉ፤ እንደደረስን እሰጥሀለሁ››ስትል መልሳ ወያላውን መለማመጥ ቀጠለች፡፡
‹‹ባክሽ ..ዝዋይ ላይ ትወርጂልኛለሽ››ውሳኔውን አሳወቃት፡፡
በጣም ተጨናነቀች፡፡አንገቷ ላይ ያንጠለጠለችው የእናቷን ማስታወሻ ሀብል ትዝ አላት፡፡ ከዚህ በላይ መጨነቅ እንደሌለባት ወሰነች ፤ሀብሉን የማስያዝ ሀሳብ መጣላት፡፡ ኔትወርኩ በመሀል ከሰራላት ለምታውቃቸው ሰዎች ደውላ መነኸሪያ እንዲጠብቋት በማድረግ ሀብሏን ታስለቅቃለች፡፡ እስከእዛ ግን እራሷን ከስቃይ ለማላቀቅ ወሰነች፡፡
ሀብሉን ከአንገቷ አወጣችና‹‹ እንካ ይሄንን ያዝ፡፡ ሀዋሳ ደርሰን ብርህን ስሰጥህ ትመልስልኛለህ፡፡››በማለት እጁ ላይ አስቀመጠችለት፡፡ መቼም ይሄ ሁሉ ተሳፋሪ እያየ አይክደኝም ስትል ተስፋ አደረገች፡፡
የሰጠችውን ሀብል በእጆቹ ላይ እያገላበጠ ፈተሸና‹‹ሲስቱ ..አርቴ እንዳይሆን ብቻ፡፡፡››አላት፡፡
‹‹ባክህ ሃያ አራት ካራት ሆኖ 14 ግራም ወርቅ ነው፤ይልቅ በጥንቃቄ ያዘው፡፡››አለችው፡፡ በዚህን ጊዜ ከጎኗ ተቀምጦ የነበረው
እስከአሁን ነገሮችን በዝምታ ሲከታተል የቆየው ባለ ጥቁር መነፅሩ ወጣት ሁለት ድፍን የመቶ ብር ኖት አወጣና ሠጣት፡፡
‹‹ክፈይና ሀብልሽን ተቀበይው፡፡ለእኔ እዛ ስትደርሺ ትሰጪኛለሽ፡፡››
የወጣቱን ንግግር የሰማው ረዳት ተበሳጨበት፡፡እጁ የገባውን ዕድል ነው የነጠቀው<<የሆነ ምጥማጥ መልክ..የእርጐ ዝንብ ››በውስጡ አጉረመረመ፡፡
‹‹እግዜር ይስጥልኝ፡፡አመሰግናለሁ፡፡››በማለት ተቀበለችውና ለወያላው ወርውራለት ሀብሏን ተቀበለች፡፡ሠማንያ ብር መለሰላት፡፡ መልሱን ለወጣቱ ስትሰጠው‹‹ለውሃ ምናምን መግዣ ይሆንሻል..ያዢው፡፡ አንድ ላይ ትመልሺልኛለሽ፡፡››
‹‹የት ድረስ ነው የምትሄደው?››
‹‹ሀዋሳ ድረስ፡፡››
‹‹እንደደረስን እሰጥሀለሁ፡፡››
‹‹በማግስቱም ልትሰጪኝ ትችያለሽ፡፡››
እስኪሪፕቶና ወረቀት ከቦርሳዋ አውጥታ ሙሉ ስሟን ፤ ምትሰራበትን ቦታ እና ሁለቱንም የስልክ ቁጥሮቿን ፅፋ አቀበለችው፡፡ተቀበላትና እስኪሪፕቶውን ከእጇ በመውሰድ ወረቀቱን ገልብጦ ባልተፃፈበት በኩል የራሱን ጻፈና አጣጥፎ አቀበላት፡፡››
‹‹ምንድነው?››
‹‹ሲመችሽ አንቺው ደውይና ትሰጪኛለሽ፡፡››
ግራ ገባት ‹‹ባልደውልልህስ..?ብሸውድህስ?››
‹‹ብትደውይም አይደንቀኝ ..ባትደውይም አይገርመኝም፡፡››
‹‹አልገባኝም..፡፡››
‹‹ሁለቱም የሰው ልጅ ባህሪዋች ናቸው፡፡››ብሎ ብዙም ማውራት እንዳልፈለገ በሚገልፅ ስሜት ፊቱን ወደመስታወቱ አዙሮ ውጭ ውጩን ማየት ጀመረ፡፡
‹‹ሀብታም ወይም የሀብታም ልጅ ቢጤ ነው መሰለኝ፡፡ለዛ ነው የሚንጠባረርብኝ፡፡›› ስትል በውስጧ አሰበች፡፡
‹‹አይ አሁን ይህቺን ሁለት መቶ ብር አበደርኩሽ ብሎ በጅንጀና ያደርቀኛል፡፡›› ስትል ገመተች፡፡ ቆዳውን አዋዶ የእሷን ትኩረት
ለመሳብ እንዳቀደ እርግጠኛ ሆናለች፡፡‹‹ወንዶች እንኳን ይህቺን አይነት መግቢያ መንገድ አግኝተው ቀርቶ ድሮም ድሮ ናቸው፡፡›.አለች በልቧ፡፡
ዝዋይ ደረሱና ሚኒባሷ ለሻይ እረፍት ቆመች፡፡ ተሳፋሪዎች ሁሉ ወረዱና ሚያስፈልጋቸውን ነገር ገዛዝተው በመመለስ ጉዞው ቀጠለ፡፡ እሷም ወርዳ ውሀና መስቲካ ገዝታ ነበር፡፡አንድ ውሃ እና አንድ መስቲካ እያቀበለችው ‹‹በብድር ብር የተገዛ ቢሆንም እስኪ ልጋብዝህ፡፡››አለችው፡፡
ውሀውን ተቀበለና‹‹ጣፋጭ ነገር አልወድም፤ለውሀው ግን አመሰግናለሁ፡፡ >> አላት፡፡

👍89❤9😁4🔥1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ሳባ እጅ አወጣች…በስልጠናው እየተሰጠ ባለው የዕለቱ ትምህርት በጣም ተመስጣለች…እና በውስጧ የሚጉላላ ጥያቄ ስለነበረ እሱን ለመጠየቅ ነው እሺ ሳባ ጠይቂ
‹‹አንድ ሴት ከወንዱ ጋር ወሲብ ስትፈፅም እሱን ማርካት ላይ ነው ማተኮር ያለባት ወይስ ለራሷም የእርካታ ስሜት.መጨነቅ ይጠበቅባታል››
በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው ያነሳሽው፡፡ የሴቶች ቆዳ ከወንዶች 10 እጥፍ በላይ ንቁ ነው፡፡ ወንዱ በወሲብ አማካይነት ከስሜቱ ይገናኛል፤በስሜቱ አማካይነት ደግሞ ወደነፍሱ ይመለሳል ሴቷ ግን በአብሮነት ውስጥ ድጋፍ እንዳገኘች ሲገባት ልቧ ውስጥ ተቀብሮ የነበረው ፍቅር ፈንቅሎ ይወጣና በዛ መንገድ መንፈሳዊ ፍላጎቶቿ ሲሟሉላት ወሲባዊ ፍላጎቶቿን ለማሟላት መዘጋጀት ትጀምራለች፡፡ ሴቷ የወሲብ እርካታ ለማግኘት ከወንዱ እጥፍ የሆነ ጊዜ ያስፈልጋታል ቢያንስ ለ20-30 ደቂቃ ያስፈልጋታል፡፡ የወንድ ልጅ መንፈስ ግን ለወሲብ ከተነቃቃ በኋላ መተንፈስ ካልቻለ መንፈሱ ብቻ ሳይሆን አካሉም ምቾት ያጣል ሴቷ ግን ባትረካም በወሲብ አማካይነት በሚፈጠረው ቅብ ብቻ ጥሩ ስሜት ሊሰማትና ደስተኛ ልትሆን ትችላለች፡፡
እንግዲህ ምን ማለት ነው የወንድና የሴት የወሲብ ዝግጅት ቆይታና እይታ ጭምር ይለያያል ማለት ነው፡፡ እና ወሲብ የምትፈፅሚው ከምን አይነት ሰው ጋር ነው እንዴት ነው ወንድዬውን ከጥድፊያ እንዲወጣና ነገሮችን በስክነትና በእርጋታ እንዲያደርግ ማድረግ ትችያለሽ.. አንቺስ ፈጥነሽ ወደ ወደሪቲሙ ለመግባት ምን ምን ዘዴዎችን መጠቀም አለብሽ እነዚህን መሰረታዊ መልስ የሚፈልጉ ጥያቄዎች ናቸው ምክንያቱም ወንዱ በፍጥነት ይግላል በፍጥነት ይበርዳል አንቺ ዝግ ብለሽ ትግያለሽ ዘግየት ብለሽ ትበርጂያለሽ፡፡ ከእሱ ቀነስ ከአንቺ ጨመር አድርጋችሁ መሀከል ላይ ስትገናኙ ነው እኩል መርካት የምትችሉት፡፡ ግን ምንም አደረጋችሁት ምንም ሁል ጊዜ ሴቷ ከወንድ እኩል መርካት አትችልም ቢሆንም ያ ችግር የለውም ምክንያቱም ሴቷ ከእርካታው በላይ ለፕሮሰሱ ትልቅ ትርጉም ትሰጣለች፡፡ ዋናው ነገር በወሲብ ጥምረታቸው ግንኙነታቸው ይበልጥ መጠንከሩና ፍቅራቸውም ይበልጥ እየጎለበት መሄዱ ነው፤ያ ከእርካታ እኩል ውስጣዊ ደስታን ይፈጥርላታል፡፡ ለዛሬ እዚህ ላይ እናቁምና በተከታታይ ቀናቶች ብዛት ያላቸውን በወሲብ ላይ የተሰሩ ዶክመንተሪ ፊልሞችን እየተመለከትን እያንዳንዱን በጥልቀት እንፈትሸዋለን፡
‹‹ሌላ ጥየቄ ያለው አለ?›› ሌላኛዋ ሴት እጅ አነሳች
‹‹አንድ ጥያቄ ነበረኝ…ፍቅረኛዬ ሌላ ሀገር ነው የሚኖረው በሶስት ወርም ሆነ በአራት ወር ይመጣል.. እና እንደመጣ እሱ ዘሎ ወሲብ ላይ ጉብ ማለት ነው የሚፈልገው እኔ ደግሞ እንዲያወራኝ እፈልጋለሁ ከሱ ውጭ ስላሳለፍኩት ልነግረው እፈልጋለሁ..እሱም እንዲነግረኝ እፈልጋለሁ…እና ይሄ ሰው እኔ ናፍቄው ሳይሆን የወሲብ ስሜቱን ለማርካት ይሆን እንዴ የሚመጣው ብዬ በማሰብ ቅሬታ ውስጥ እገባለሁ…ይሄ ነገር ሊብራራ ይችላል፡››
አሰልጣኟ ‹‹ጥሩ ጥያቄ ነው…››፡፡በማለት ማብራራቷን ቀጠለች
‹‹ሁለት ጥንዶች ከቀናቶች በኋላ ተነፋፍቀው ሲገናኙ ወንዱ ተጣድፎ ወደወሲብ ጫወታ መግባትያፈልጋል፤እንደዛም ለማድረግ ይቁነጠነጣል ሴቷ ደግሞ ተቀምጦ ማውራትና በጫወታቸው መንደርደሪያነት ናፍቆትን መወጣት ትፈልጋለች፡፡ ቶሎ ክንዷን ጨምድዶ ወደ አልጋው ይዟት ከሄደ…ልክ ከውጥረቱ ለመርገብ እንደመጠቀሚያ እየተገለገለባት እንደሆነ እንድታስበ ያደርጋታል፡፡ በተቃራኒው የእሷ ወደአልጋ ለመሄድ ዳተኛ መሆን ለእሱ ሌላ ትርጉም ይሰጠዋል…ብዙም እንዳልፈለገችው…በመመለሱ ብዙም ግድ እንዳልሰጣት በመገመት የመገፋት ስሜት ያስተናግዳል፡፡ ይሄንን በወንድና በሴትነት ምክንያት ያለን የባህሪ ልዩነት መረዳት ግን ለሁለቱም በመተጋገዝ ወደመሀል እንዲመጡና እርስ በእርስ የተሳሳተ ትርጉም በመስጠት በግንኙነታቸው ላይ ጥቁር ነጥብ እንዳይጥሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ሴት ለወሲብ ልቧን ለመክፈት ፍቅር እንደሚያስፈልጋት ሁሉ ወንዱም ወደ ፍቅር ስሜት ዘልቆ ለመግባት ወሲብ እንደሚያስፈልገው መታወቅ አለበት፡፡ ወንድም ሆነ ሴት የመንፈስ ረሀብ አለባቸው፡፡ ግን ከዚህ ረሀባቸው ለመርካት የሚመገቡት የምግብ አይነት ግን የተለያየ ነው፡፡ ሴቷ ፍቅርን በመመገብ ከመንፈስ ርሀቧ ስታገግም ወንድ ደግሞ ወሲብን ተመግቦ ነው ረሀቡን የሚያባርረው፡፡ ከዛ ሴቷ ፍቅርን ተመግባ ከመንፈስ ርሀቧ ከጠገበች በኋላ ለማወራረጃ ቆንጆ ወሲብ ስታገኝ በጣም ደስተኛና ፍፁም የረካች ሴት ትሆናለች፡፡ በሌላ ጎኑ ወንዱም ሆድን ከሚቆርጠውና አጨናንቆት ከነበረው የመንፈስ ረሀብ ወሲብን ከተመገበ በኋላ ተነፈስ ይልና ቀጥታ በውስጡ የሚንቆረቆረውን የጋለ ፍቅር ልክ እንደውሀ በላዩ ላይ መከለስ ይጀምራል…ከዛ አጅግ ደስተኛ፤ዘና ያለና አይኖቹ የሚያበሩ ይሆናል፡፡ አለችና የእለቱን ትምህርት ዘጋች፡፡ ከዛም እንዳለችው ለ10 ቀናት ያላዩት የወሲብ ፊልም፤ ያላወሩትና ያልተወያዩበት የወሲብ አይነት አልነበረም ሙሉ በሙሉ ነበር ስለወሲብ የነበራትን እይታ የቀየረባት፡፡ ወሲብ እሷ ከምታስበው በጣም በሰፋና በጠለቀ ሁኔታ በሰው ልጅ ዘመናት ታሪክ ሂደት ውስጥ አስኳል ድርሻ እንዳለው ተረዳች አሁን ለዚህች አለም እንደጨው. እንደሆነ. ተገነዘበች ...ወሲብ. ለፍቅር፤ ወሲብ. ለገንዘብ፤ወሲብ.ለደስታ፤ወሲብ.ለስለላ…ወሲብለአምልኮ..ወሲብ.ዘርን.ለማስቀጠል…ወሲብ.ለበቀል….ብዙ ብዙ
በሚቀጥለውም ወደመጨረሻው የሰልጠና ርዕስ ተሸጋገሩ
ተግባቦት ማለት በሁለት አዕምሮዎች መካከል ወይም በአንድ አዕምሮ ከሌሎች ብዛት ያላቸው አዕምሮዎች ጋር የሚደረግ የመረጃ ልውውጥ ነው፡፡ የሰው ልጅ ከሌላው እንስሳት የተሻለ ነው የሚባለው በመግባባት ችሎታው ራሱን በመግለፅና በማስረዳት ክህሎቱ ነው፡፡፣አብዛኛው እንስሳት እርስ በርሱ ይግባባል…ከእኛ ከሰው ልጅ የሚጠበቀው የመግባባት ችሎታ ግን እንስሳቱ ከሚያደርጉት በላይ የላቀ እና ከዚህ በላይ የመጠቀ መሆን አለበት….ለአንድ ሰው ሀሳባችሁንና ፍላጎታችሁን ስትገልፁ አፋችሁን ከፍታችሁ ከንፈራችሁን አንቀሳቅሳችሁ በቋንቋ ብቻ በመጠቀም መሆን የለበትም፡፡ ከምንናገረው ቋንቋ ጋር አብሮ የሚሄድ የፊት ገለፃ፤የእጅ አንቅስቃሴና የመሳሳሉት መጣመርና ተመሳሳይ መልዕክት ማስተላለፍ አለባቸው፡፡
በጣም የሚወዳችሁ ሰው አበባ ይዞ ያላችሁበት ድረስ መጥቶ ‹‹የእኔ ፍቅር በጣም አፈቅርሻለሁ›› ሲላችሁ ምንድነው የምታደርጉት?፡፡ አንድም አበባውን ቀና ብላችሁ ሳታዩት ሰውዬውን ባለበት ጥላችሁ ትሄዳላችሁ፡፡ ሁለተኛ ስላፈቀርከኝም ሆነ ይሄንን አበባ በስጦታ መልክ ልታበረክትልኝ ስለመጣህ አመሰግናለሁ….ግን አዝናለው አልችልም ሌላ ፍቅረኛ አለኝ ብላችሁ በተከዘ ፊትና በአዘነ የድምፅ ቃና ትመልሱለታላችሁ፡፡ ሌላው አማራጭ ደግሞ አበባውን ትቀበሉና ግን ፊታችሁን አጨማዳችሁ በሻከረ የድምፅ ቃና እኔም እወድሀለሁ...አመሰግናለሁ ልትሉት ትችላላችሁ፡፡ ወይ ደግሞ አበባውን ተቀብላችሁ በሚፍለቀለቅና በደስታ በሰከረ ፊት አጅባችሁ የእኔ ማር!! በጣም ደስ የሚል አበባ ነው…በእውነት ነፍሴን ነው ያስደሰትካት...እኔም ውደድድ ነው የማደርግህ ››ትሉታላችሁ ወይ ደግሞ አበባውን ትቀበሉና እጆቻችሁን እንደክንፍ ዘርግታችሁ ትከሻው ላይ በመንጠልጠል ጉንጮቹን አገላብጣችሁ በመሳም…‹‹የእኔ ፍቅር ይህቺን ቀን ስጠብቅ ነበር

👍61❤11👏1
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ናኦልና ኑሀሚ ብራዚል ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ ይገኛሉ.. ከኢትዬጵያ ደህንነት መስራቤት ተልእኮ ተሰጥቶችው የመጡ ሁለት የደህንነት ሰዎች አብረዋቸው አሉ…ሁለቱ መንትዬች በኮንክሪት ግግር እንደቆመ ሀውልት ጎን ለጎን ተጣብቀው ቆመዋል…ከፊት ለፊታቸው በአንድ ሜትር ርቀት አንድ የታሸገ የሬሳ ሳጥን ወለል ላይ ተቀምጦ ይታያል…እሬሳውን ጭኖ ወደኢትዬጵያ የሚበረው አውሮፕላን በሰላሳ ሜትር ርቀት ላይ ይታያል…እዛ ሬሳ ሳጥን ውስጥ ለዘላለም አሸልባ የተኛችው ምስራቅ ነች፡፡
ናኦል እና ኑሀሚ ከዳግላስ ወጥመድ አምልጠው የሲኦል ወጥመድ ከሆነው ከእዛ ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ወጥተው እንሆ አስተማማኝን ቦታ ላይ ቆመዋል…ከአንድ ሰዓት በኃላ በአገራቸው አየር መንገድ ወደሀገራቸው ለመብረር ዝግጅታቸውን ሁሉ አጠናቀዋል…ግን እዚህ ለመድረስ የከፈሉት መሰዋዕትነት ሁለቱንም እስከወዲያኛው ያፈራረሳቸው ነው፡፡አሁን በድናቸው ነው የሚንገዋለለው፡፡እግዚያብሄር በእድሜያቸው መጀመሪያ በዛ በህፃንነታቸው ጊዜ ሚወዱዋቸውን ወላጆቻቸውን በመንጠቅ አሸማቆቸው ነበር በእድሜያቸው አጋማሽ ደግሞ በእድሜ ልካቸው አብራቸው የነበረችውን፤ ከጎዳና አንስታ ህይወት የሰጠቻቸውን፤የተዘረፈውን የወላጆቻቸውን ንብረት ያስለመለሰልችላቸውን.. እናም ከዛም አልፍ እሷን ለማትረፍ አህጉር አቆርጣ እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ የገባችላቸውን የዚህችን ሴት ህይወት ማጣት ለሁለቱም ቅስም ሰባሪ ነው፡፡ለናኦል ደግሞ ነገሩ የተለየ ነው….ይህቺን ሴት ገና የ12 ዓመት ልጅ እያለ እዛ በረንዳ ፤ላይ ካያት ቀን ጀምሮ በልዩ ሁኔታ ይወዳት ነበር…እዚህ ነገር ውስጥ ያስገባት እራሱ ነው፡፡እህቴ ጠፋችብኝ አፋልጊኝ ብሎ ደወላላት..እሱን ለመርዳ ከጎሬዋ ወጣች..ለብቻው ልትተወው ስላልፈለገች አህጉር አቋርጣ ተከትላው መጣች ..አንድ ወር ሊደፍን ትንሽ ቀን ለቀረው ቀናት በመከራና በስጋት ውስጥ ቢሆኑም እንኳን እጅግ ጣፋጭ የሆነ የፍቅር ህይወት አሳልፈዋል….የህይወትን ጣእም እና የፍቅርን ትርጉም አሳይታዋለች ..አስተምራዋለች፡፡….ከእሷ ጋር የመሰረቱት የውሸት ትዳር ለእሱ በህይወቱ ካጋጠመው ተጨባጭ እውነቶች መካከል ምን እልባትም ዋነኛው ነው…በሰላም ወደሀገራቸው ሲመለሱ ለምኖና እግሯ ላይ ወድቆ ጋብቻቸው ባለበት እንዲቀጥልና በእሷ እቅፍ ውስጥ ለዘላለም መቅለጥ ነበር የሚፈልገው፡፡እቅዱ እንደዛ ነበር….ብቸኛ ምኞቱም ያ ነበር..፡፡ግን አሁን ሁሉ ነገር እንዳልነበረ ሆኗል….፡፡በሰልም እየሰቀችና እተፍለቀለቀች አብራው የመጣችው ሴት ይሄው ህይወት አልባ በድን እሬሳ ሆነ በሳጥን ውስጥ ታሽጋ ወደሀገሯ እየተመለሰች ነው፡፡እና ደግሞ በጣም እያበሳጨው ያለው ነገር ምንም እንዳልተፈጠረ በህይወት ቆሞ አየር እየሳበ መሆኑን ሲያስብ ነው….ደግሞ እኮ የእሱን ሞት ነው ሞተችው፡፡
ነገሩ እጌት ነው የተከሰተው ብለን ወደኃላ ዞረን ስናስታውስ……
..
ከአራት ቀን በፊት ነው፡፡ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ የታገቱበት ክፍል ተከፈተ….የመጣው የተለመደው የዳግላስ ተላላኪ ነው፡፡
ወደኑሀሚ አትኩሮ እየተመለከተ ‹‹ጌታዬ እየጠበቀሽ ነው››አላት፡፡
ኑሀሚ ከ30 ደቂቃ በፊት አምጥቶ የሰጣትን ውብ የራት ቀሚስ ለብሳና ተዘጋጅታ የጠበቀችው ነበር፡፡ምስራቅንና ወንድሟ ናኦልን ተራ በተራ ጉንጫቸውን ሳመችና በዝግታ እርምጃ ልጁን ተከትላ ወጣች፡፡ቀደም ብሎ የተላከላትን ቀሚስ ለብሳ ወደታባለችው የእራት ግብዣ መሄድ የምርጫ ጉዳይ አይደለም…ግዴታ ነው..፡፡በሰዓቱ እያስጨነቃት የነበረው ከእራት ቡኃላስ ሚለው ነበር?….ወደአልጋ እንሂድ ቢለኝስ?እንደዛ ስታስብ ዝግንን የሚያደርግ ቀፋፊ ስሜት ነበር የተሰማት፡፡እሷ ግን እኮ እንደዛ አልነበረችም፡፡ለአላማዋ ጥቂትም ጥቅም ይኑረው እንጂ ከማንም ወንድ ጋር ተጋድሞ ወሲብ መፈፀም ልክ እንደካርታ ጫወታ ዘና ብላ ምትፈፅመው ቀላልና ትርጉም የማይሰጣት ጉዳይ ነበር…ደግሞም በሰላይነት ሕይወቷ እንዲጠቅማት በእንደዚህ አይነት ጉዳይ ላይ በቂ ስልጠና ወስዳለች…አሁን ግን አንድ ነገር ገብቷታል..ለካ በዛን ጊዜ ነገሩ ቀላልና የማያስጨንቅ ሆኖ የሚታያት ስለሰለጠነችበት ብቻ አልነበረም…ልቧ ኦናና ባዶ ስለነበረ ነበር እንጂ፡፤አሁን ግን አንድ ሰው ገብቶበታል…ያ ሰው ደግሞ እሷን ለማዳን በቅርብ ርቀት ባለ ጫካ ውስጥ ሆኖ እቅዱን ስለሚያሳካበት ዘዴ እየተጨነቀና እያሰበ ነው…እና እሷ ካለፍላጎቷም ቢሆን ከሌላ ሰው ጋር ወደአልጋ የመሄድን ጉዳይ በቀላሉ ምታየው አይደለም….ይሄ ነው ያስጨነቃት…የተንጣለለው ሳሎን ውስጥ ስትገባ ግዙፉ ጠረጴዛ በምግብና በመጠጥ ተሞልቶ ተመለከተች፣አንድ ሴትና ሁለት ወንድ አስተናጋጆች ፈንጠር ብለው ግድግዳውን ተደግፈው ትእዛዝ በመጠባበቅ ላይ ናቸው…እንደገባች ዳግላስ ከተቀመጠበት ተነሳና ወደእሷ ተራመደ…ቀለል ያለ አለባበስ ነው የለበሰው…ከላይ ሰማያዊ ሸሚዝ ከዳለቻ ጅንስ ሱሪ ጋር አድርጎል…በፈገግታ ተጠጋትና እጁን ለሰላምታ ዘረጋላት…ፈራ ተባ እያለች እጇን ሰነዘረችና ጨበጠችው፡፡
እጇን ሳይለቅ እየጎተተ ወደ ጠረጴዛው ወሰዳትና ወንበር ስቦ አስቀመጣት..ከዛ ራመድ አለና ከፊት ለፊቷ ሄዶ ተቀመጠ፡፡ወዲያው ለአስተናጋጆች በእጁ ምልክት ሲያሳይ ተንደርድረው መጡና ብርጭቆቸውን በመጠጥ ሞልተውላቸው ወደቦታቸው ተመለሱ፡፡
ከተቀዳለት መጠጥ አንዴ ጠቀም አድርጎ ከተጎነጨለት በኃላ‹‹እንዴት ነው ቆይታ ?››ሲል ጠየቃት፡፡
ያለምንም ማስተባበል‹‹በጣም አሰልቺ ነው››ስትል ፍርጥም ብላ መለሰችለት፡፡
‹‹እንግዲህ የአጋጣሚ ጉዳይ ሆነና ለስራ ጉዳይ ወጣ ማለት ነበረብኝ…አሁን ግን ተመልሼለው…ከዚህች ደቂቃ ጀምሮ ፍፅም ደስተኛ እንድትሆኚ የተቻለኝን አደርጋለሁ…ከነገ ጀምሮ የአማዛንን ድንቅ ውበት ጎዲያ ጎድጓዳዋን እያዞርኩ አሳይሻለው..እንስሳቱን ፤ወፎችን ፤ፏፏቴዎችንና ወንዙን ሁሉንም አንድ በአንድ አሳይሻለው..እናም ከቦታው ጋር በፍቅር እድትተሳሰሪ የተቻለኝን እጥራለው..ከቦታው ብቻ ሳይሆን ከእኔም ጋር ፍቅር እንዲይዝሽ እፈልጋለው››ሲል ተናዘዘላት፡፡
‹‹እርግጠኛ ነህ ከአንተ ፍቅር እንዲይዘኝ ማድረግ ትችላለህ?››
‹‹እንግዲህ እቅዴ እንደዛ ነው››
‹‹ጥሩ ነው››ብላ በአጭሩ መለሰችለት
‹‹ምኑ ነው ጥሩ?››በጫወታው እንዲገፉበት ስለፈለገ ጥያቄውን ቀጠለበት፡፡
‹‹እስከማውቅህ ድረስ ሁሉንም ነገር በጉልበትና በማስግደድ ነው የምታደርገው…..ቡኃላ እንዳፈቅርህ ማድረግ ሲያቅትህ እንዳትተኩስብኝ ነው የምፈራው…፡፡››ስትለው ከጣሪያ በላይ ተንከትክቶ ሳቀ..‹‹በይ በባዶ ሆዴ ከዚህ በላይ መሳቅ አልችልም ..እራት እንብላና ወደበረንዳ ወጣ ብለን መጠጣችንን እየተጎነጨን የጀመርነውን ጫወታ እንጨርሰዋለን…››አለና ሰሀን አነሳ …እሷም እንደእሱ አደረገኝ..እራት በልተው አስኪያጠናቅቁ ሀያ ደቂቃ አካባቢ የፈጀባቸው ሲሆን በዛን ጊዜ ውስጥ ብዙም የረባ ነገር እልተነጋገሩም…፡፡.እራቱ እንደተጠናቀቀ ዳጋላስ እጁን ሊታጠብ ቀድሞ ወደመታጠቢያ ክፍል ገባ …ወዲያው ከአስተናጋጆቹ አንዱ እቃ የሚያነሳሳ መስሎ ተጠጋት እና ጎንበስ ብሎ‹‹ነገ በዚህን ሰዓት››አላት፡፡፡አልገባትም‹‹ዋት››አለችው፡፡ደገመላት‹‹ነገ በዚህን ሰዓት..ተዘጋጁ››ብሎ የተበላበትን ሰሀን ሰበሰበና እንዳቀረቀረ ከሳሎን ወጥቶ ሄደ፡፡

👍81❤7👎2🥰1👏1
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ሰለሞንና የበፀሎት ቤተሰቦችን አብዛኛውን ጊዜያቸውን አካባቢውን ያለውን እያንዳንዱን መስህብ በመጎብኘት ነው የሚያሳልፉት….እያንዳንዱ ውይይትና ምክረ-ሀሳብም በመዝናናት ውስጥ ሆነው የሆነ ቦታ አረፍ ሲሉ ወይም ቡና ለመጠጣት የሆነ ካፌ ሲቀመጡ በውይይትና በጫወታ መልክ የሚሰጥ ስለሆነ እንደ ቢሾፍቱ አስጨናቂና ጭንቅላት የሚይዝ አይነት አልነበረም፡፡
በወንጪ ኢኮ ቱሪዝማ ማዕከል ውስጥ ከሚገኙት እና ለጉብኝት ዝግጁ ከሆኑት ዋና ዋና አይን ሳቢና ቀልብ አስደንጋጭ የቱሪስት መስህቦች ውስጥ ጥቂቶቹ
ጎሮ በሚባለው ስፍራ የተገነባው ጎሮ ካልቸራል ሴንተር የወንጪ ኢኮቱሪዘም ፓርክ አንዱ መገለጫና ውበት ነው፡፡ በህንፃው ላይ ባህላዊ ምግቦች የሚገኙበት ውብ የሆነ ሬስቶራንት..ባህላዊ የሆኑ የእጅ ስራ ውጤቶች የሚሸጥባቸው ሱቆች…የተለያዩ ዝግጅቶችን ለማዘጋጀት የሚያገለግል እስከ 3መቶ ሰዎች ማስተናገድ የሚችል ውብ የሆነ አምፊ ትያትር ከአካባቢው ከሚገኙ አገልግሎቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ እና አካባቢው ላይ ሆኖ ቁልቁል ወደታች ሀይቁንና ከማዶው ያለውን ተራራ ሲያዩት ልብን ስውር የሚያደርግ የተለየ አይነት አስደማሚ እይታ አለው፡፡
ከጎሮ 2.3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ነዲ ካልቸራል ሴንተር ደግሞ ሌላው ልብ ሰዋሪ ቦታ ነው፡፡ነዲ ከስሙም መረዳት እንደሚቻለው በአካባቢው የሚመረት የወንጪ ማር እና የማር ውጤቶች እንደብርዝና ጠጅን ጨምሮ መሸጫ እንዲሆን ታስቦ የተገነባ ህንጻ ነው…የህንፃው ጠቅላላ ዲዛይን አገልግሎቱን ታሳቢ ተደርጎ የተሰራ ስለሆነ ውብ ነው፡፡በማር እንጀራ ቅርፅ የተሰራ ሁለት ሶስት ጓደኛሞች ተቀምጠው ቁልቁል ሚታየውን ውብ እይታ ዘና እያሉ ወሬያቸውን የሚጠረቁበት ውብ ስፍራ አለ፡፡
ሙለታ ወንጪ ሬስቶራንት ሌላው በስፍራው የሚገኝ ውብ ቦታ ነው …በዚህ ስፍራ ሬስቶራንቶችና ሱቆች የፈረስ ማስዋቢያና ባህላዊ እቃዎች የሚሸጡበት ሱቆች ሲኖሩ ኩኪስ ብስኩት የመሳሰሉትም ቀላል ምግቦችን ማግኘት ይቻላል ፡፡
ነዲ ሰስፔንድድ የመስታወት ቴራስ ሌላው በአካባቢው ያለ ውብ ህንፃ ነው፡፡ይህ የመስታወት ወለል ግማሽ ክብ አይነት ቅርፅ ሲኖረው በሶስት ድርብርብ ተደርጎ የተሰራና እላዩ ላይ ወጥታው በመስታወቱ አሻግረው ወደታች ሲመለከቱ ከስር የሚታየው አስፈሪ ገደል መሳይ ግን በአረንጓዴ ሳርና ተክሎች የተሸፈና ውብ ስፍራ በማዶ የሚገኘው የጠራ ሀይቅ …በቃ አስፈሪ ግን ደግሞ አስደሳች እይታ ነው፡፡ይህ የመስታወት ቴራስ በአንድ ካሬ ሜትር ላይ 400 ኪ.ግራማ የመሸከም አቅም እንዳለው ቢታወቅም በርከት ያለ ሰው ከወጣበት ግን ከአሁን አሁን መስታወቱ ተፈርክሶ ሾልከን ወደገደሉ ብንንከባለልስ? የሚል የፍራቻ ስሜት ሰቅዞ የሚያሲዝ አይነት ነው፡፡ከዚህ አስደማሚ የመስታወት ቴራስ ጎን አምፊትያትር ያለ ሲሆን በተያያዥነትም…ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚሰጥ ካፍቴሪያ አለ፡፡ከዚህ ስፍራ ቀጥታ ወደሎጅ የሚወስድ የመኪና መንገድ ከላይ የመስታወት ቴራሱ ላይ ሆነው ከስር ማየት ይቻላል፡፡
ከዛ ደግሞ የተፈጥሮ ፍል ውሀ ያለበት በደን የተሸፈነ ሲሆን በአካባቢው ጉሬዛ ፤ጦጣ አእዋፍት ፤አምቦ ውሀ የተፈጥሮ ፏፏቴ ይገኛል …ጎን ለጎን ያሉ ሙቅና ቀዝቃዛ ኩሬ የኬብል ድልድይ ፤ወንዝ ..ብዙ ብዙ አስደማሚ ተፈጥሯዊ ነገር ይገኛል፡፡የነዲ መዝነኛ ስፍራን እና የተፈጥሮ ፍል ውሀን የሚያገናኝ በብረት የተሰራ እስካይ ብሪጅ አለ፡፡ብሪጁ 72 ሜትር ርዝመትና ኖሮት ሀምሳ ሜትር ከፍታ እንዲኖረው ተደርጎ የተሰራ አስፈሪ ግን ደግሞ የራሱ የሆነ ውበትና የተለየ ስሜት የሚያጭር ልዩ ድልድይ ነው፡፡
እነዚህን ሁሉ ባለፈው አንድ ሰምንት ውስጥ የጎበኞቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ በስምንተኛው ቀን ከቀኑ 9ሰዓት አካባቢ ለበፀሎት ደወለላት
‹‹ሄሎ..እንዴት ነሽ?››
‹‹አለሁልህ…ገነት ገብቼለሁ››
‹‹ወደድሽው ማለት ነው››
‹‹እንዴ ትቀልዳለህ እንዴ …?አካባቢው እኮ እንኳን እንደእኔ አፍጥጠው የሚያዩ ሁለት አይኖች ላሉት ሰው ይቅርና አይነ-ስውር ቢመጣበት እንኳን ውበቱ በሽታ ሳይቀር ይታወቀዋል፡፡››
‹‹ዋው ድንቅ አገላለፅ ነው….በጣም ማርኮሻል ማለት ነው…እኔንም አንድ ቀን ወስደሽ እንደምታስጎበኚኝ ትስፋ አለኝ፡፡››
‹‹በደንብ እንጂ…ለዛውም በቅርብ ነዋ››
‹‹አሁን የት ነሽ…?ላለፉት አንድ ሰዓት ለሊሴ ጋር በሳይክል አካባቢውን ስናካልል ነበር.. አሁን ድክም ብለን ነዲ ካልቸራል ሴንተር የሚባለው ስፍራ ላይ ነን ፡፡
‹‹ምነው…ጠጅ እየጠጣችሁ ነው እንዴ?››ሲል ጠየቃት
‹‹አይ ትኩስ ወለላ ማር እየበላን››
‹‹በቃ ..ሰዓታችሁን አልውሰድባችሁ…..ዘና በሉ››
‹‹እሺ ቸው…ለሊሴ ሀይ እያለችህ ነው፡፡››
‹‹ሀይ በይልኝ‹‹ስልኩ ተዘጋ፡፡
‹‹አንቺ ሀለቃዬን ምን ልታደርጊው ነው?››ለሊሴ በመገረም ውስጥ ሆና ጠየቀቻት፡፡
‹‹ምን አደረኩብሽ…?››
‹‹እንዴ እያየሁ…ከተዋወቃችሁ ገና ሳምንት ነው..ግን ይሄውና በየቀኑ ይደውልልሻል፣ ገባሽለት እንዴ?››
‹‹አረ አንቺ ደግሞ…››በፀሎት እንደማፈር ብላ ተሸኮረመመች፡፡
‹‹ምነው..ቢሆን ደስ ይለኛል..ምርጥ ሸበላና የተማረ ሰው ነው..በዛ ላይ ትህትና አለው…እና አንቺን እህቴን ብድርለት በጣም ደስ ይለኛል››
‹‹በይ አንቺ ካዳመጡሽ …ብዙ ታወሪያለሽ››
ለደቂቃዎች ሁለቱም ዝም ተባባሉና በየግላቸው ሀሳብ መብሰልሰል ጀመሩ፣…በፀሎት ድንገት‹‹አካባቢው ግን አያስደንቅም?››ብላ አዲስ የመወያያ ርዕስ ከፈተች፡፡
‹‹ በጣም እንጂ…እያንዳንዱ ስፍራ የራሱ የሆነ እይታ አለው…አሁን ጎሮ ጋር ሆነሽ ቁልቁል ስታይ የተለየ አይነት እይታ..ከሊበን ሆነሽ ስታይው ደግሞ የተለየ አይነት እንደምታይው እዚህ ሆነሽ ስትመለከቾ ደግሞ ሌለ አይነት…በእውነት ይሄ በጣም አስገራሚ ነው፡፡ቦታ በቀየርሽ ቁጥር የምታይውም ነገር ይቀየራል…››
‹‹አዎ እንግዲህ …አምላክ ሲጠበብ ወሰን የለውም….››
‹‹እውነት ነው አምላክ ሲጠበብ ወሰን የለውም››የሚል ጣልቃ ገብ ዓ.ነገር ሁለቱንም ከተቀመጡበት በርግገው እንዲነሱ አደረጋቸው፡፡ሌላ ሰው ነበር ከጀርባቸው የተናገረው፡፡
‹‹አንተ….እንዴት?››
‹‹ያው እንደዚህ››አለና ሁለቱንም በየተራ ሰላም አላቸው፡፡ተያይዘው ተቀመጡ፡፡
‹‹እዚህ ሆነህ ነበር እንዴ የምትደውልልኝ…?››በፀሎት በገረሜታና ባለማመን ጠየቀችው፡፡
‹‹አዎ…››
‹‹እኔ ደግሞ ምን አይነት ሞኝ ነኝ ..የት ነሽ ስትለኝ ያለሁበትን በየዋህነት መዘርዘሬ››
‹‹ምነው ስለመጣው ከፋሽ እንዴ?››
‹‹አረ በፍፅም››
የሰለሞንንና የበፀሎትን የማያቆርጥ ጥያቄና መልስ በዝምታ እየታዘበች በውስጦ እነዚህ ሰዎች ምንድነው እንዲህ ያቀራረባቸው..?ሰውዬውስ እሷን ፍለጋነው እንዴ እዚህ የመጣው
?እያለች በውስጦ ተብሰለሰለች ፡፡ልክ ልቧን እንዳነበበ ለጥያቄዎቾ መልስ ይሰጣት ጀመር…‹‹ያው ባለፀጋዎቹ ደንበኞቼ እዚህ ካልመጣን ሲሉ ተከትያቸው መጠሁ..ያው አስገድደው ሲያስደስቱኝ ምን ላድርግ..እየመጣሁ ሳለሁ ደግሞ እናንተ እዚህ እንዳላችሁ ትዝ ሲለኝ..የበለጠ ዘና አልኩ››
‹‹እና ታዲያ ሰዎችህ የታሉ?››በፀሎት ከወላጆቾ ጋር ድንገት ፊት ለፊት የመፋጠጥ ስጋት አስጨንቋት ጠየቀች
‹‹አሁን ክፍላቸው አረፍ ብለዋል….ለሚቀጥሉት ሁለት ሶስት ሰዓት እረፍት ነኝ….›› በፀሎት‹‹እና ታዲያ ወደፍል ውሀ ለምን አንሄድም?››የሚል ሀሳብ አቀረበች፡፡

👍69❤14
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
፡
፡
===============
በሶስተኛው ቀን አለማየሁና ሰሎሜ ተደዋውለው ተገናኙ፡፡ማታ አስራሁለት ሰዓት አካባቢ ሆቴል ነው የተገናኙት…ዝንጥ ብላ ነው የመጣችው፡፡በሞቀና በጋለ ሰላምታ ተቀበላት ፡፡ምግብ አዘው በልተው መጠጥ እየተጎነጩ ወሬ ጀመሩ ፡፡
‹‹እሺ እንዴት ነሽ..?ነገሮች እንዴት እየሄዱ ነው?››ሲል ለጫወታ መጀመሪያ የሚሆን አ.ነገር ሰነዘረ፡፡
‹‹ቆይ እስኪ የእኔ ጉዳይ ይቆይ…ለመሆኑ አንተ እንዴት ነህ?››መልሳ ጠየቀችው፡፡
‹‹ማለት..እኔ ደግሞ ምን እሆናለሁ?››ሲል መለሰላት፡፡
‹‹ማለቴ በቀደም ሳልጠይቅህ ….አገባህ እንዴ?››
‹‹አረ..በፍጽም፣ባገባ ኖሮ ቢያንስ ለእቴቴ ነግራት ነበር..ለእሷ ከነገርኩ ደግሞ ያው ልጇ ስለሆንሽ አትደብቅሽም ነበር፡፡››
‹‹አውቄዋለሁ….!!››
‹‹እንዴት .?ምኑን ነው ያወቅሽው?››
‹‹አንተ በቀላሉ የምትጨበጥ ወንድ አይደለህማ..አንድ ሴት አንተን አሳምና ወደ ጋብቻ ለመውሰድ በጣም ነው የሚከባዳት፡፡እርግጠኛ ነኝ ለማንም ሴት ከባድ ነው የሚሆንባት ፡፡››
‹‹እንዴ ያን ያህል አስቸጋሪ ሰው ነኝ እንዴ?››እሱን በተመለከተ በሰጠችው አስተያየት የእውነት ገርሞት ነው የጠየቃት ፡፡
‹‹አዎ እኔ እስከማውቅህ ድረስ፣ሀሳብህና ፍላጎትህ በደቂቃ ውስጥ ነበር የሚቀያየረው…መቀሌም ሞያሌም በአንድ ጊዜ መገኘት የምትፈልግ ለመረዳት አስቸጋሪ አይነት ሰው ነህ፡፡ማለቴ ነበርክ..አላውቅም ምን አልባት ባለፉት አምስት.. ስድሰት አመታት ተቀይረህ ሊሆን ይችላል..እኔ የማውቀው አሌክስ ግን እንደዛ ነበር፡፡››
‹‹በእውነትን እንደዛ አይነት ሰው መሆኔን አላውቅም ነበር፡፡ደግሞም አንድ እህት ወንድሟን በተመለከተ ይሄንን የመሰለ አስተያየት መስጠት ያልተለመደ አይነት ነው፡፡፡››
‹‹እንዴት ..ትክክለኛ ባህሪህን እኮ እየነገርኩህ ነው፡፡ለምሳሌ አስራሁለተኛ ክፍል ጨርሰን ማትሪክ እንደወሰድን አብረን ተማክረን ተግባረእድ ተመዝግበን ነበር፡፡ትምህርት ሲጀመር ግን ብን ብለህ ቤቱንም ከተማውንም ለቀህ ጠፋህ .ፖሊስ ለመሆን ተመዝግበህ ማሰልጠኛ መግባትህን እንኳን ለእኔ መንገር አልፈለክም..ከእናቴ ነበር የሰማሁት፡፡ሁል ጊዜ የሆነ ነገር አብረን እናቅዳለን..ትግበራው ላይ ግን ድንገት ታፈነግጣለህ፡፡በዚህ በዚህ ሁሴንና አላዛር ካንተ በጣም የተሻሉ ናቸው፡፡እነሱ በቃላቸው ይፀናሉ…በተለይ አላዛር››
‹‹ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ..ለገዛ ባልሽ እያደለሽ ነው..?ለመሆኑ ሁሴን አሁን የት ነው ያለው?››
‹‹ያው ከመሀካላችን የተሻለ ጭንቅላት ያለው እሱ ነበር ፡፡አሁን እንግሊዝ ሀገር የህክምና ዶክተር ሆኖ እየሰራ ነው…ግን በቅርብ ሳይመጣ አይቀርም፡፡››
‹‹አዎ ውጭ መሄዱንማ ሰምቼለሁ….ለማለት የፈለኩት ትደዋወላላችሁ ወይ ለማለት ነው?››
‹‹ከአላዛር ጋር እስክንጋባ ድረስ እንደዋወል ነበር፡፡ከዛ በኃላ ግን ደውሎልኝ አያውቅም፡፡.እኔም አንድ ሁለቴ ልደውልለት ሞክሬ ነበር ስልኩን ቀይሮታል መሰለኝ አልሰራ አለኝ፡፡››
‹‹ተበሳጭቶብሽ ነዋ?››
‹‹ምን ያበሳጨዋል?››
‹‹በጣም ያፈቅርሽ ነበር እኮ…!!››
‹‹ያፈቅርሽ ነበር ወይስ ይወድሽ ነበር?››
‹አንቺ ደግሞ …ሶስታችንም ነበር የምናፈቅርሽ..ይሄንን ደግሞ አንቺም በደንብ ታውቂያለሽ፡፡›.
የመደንገጥና ግራ የመጋባት ስሜት በፊቷ ላይ ተንፀባረቀባት ‹‹ምን እያልከኝ ነው…? እየቀለድክ ነው አይደል?››
‹‹አንቺ ነሽ እንጂ እየቀለድሽ ያለሽው…፡፡ ሶስታችንም ገና ማፍቀር እራሱ ምን እንደሆነ ሳናውቅ በፊት እናፈቅርሽ ነበር፡፡እድሜያችን በሙሉ ማነው በይበልጥ ሚያፈቅራት እያልን ስንፎካከለርብሽ ነው ያሳለፍነው፡፡››
‹‹እኔ ትምህርት ጨርሰን እስክንበታተን ድረስ አራታችንም እርስ በርስ የምንዋደድ የልብ ጓደኛሞች እንደሆን ብቻ ነበር የማውቀው፣በተለይ አንተ ወንድሜም ጭምር ስለነበርክ በዚህ መልኩ ላስብህ አልችልም፡፡ ››
‹‹ይሄን አላዛር እስከአሁን እንዴት ሳይነግርሽ…?ለነገሩ ምን ብሎ ይነግርሻል፤ አውቀሽ እሱ እንዳይከፋ በማሰብ ያላወቅሽ መስለሽ እንደምታስመስይ ነው የሚያስበው፡፡››
‹‹እሺ የሁሴንስ ይሁን ..አንተ የእውነት ታፈቅረኝ ነበር?››
‹‹ለዛውም ልክ በሌለው መጠን ነዋ….ለአንቺ ስል የማላደርገው ምን አለ..ቢያንስ የሞዴሱ ታሪክ ትዝ አይልሽም?››
‹‹አንተ ..ደግሞ ታስታውሰኛለህ እንዴ?ስንት አመት ሙሉ አንተ ምትገዛልኝ እየመሰለኝ አንጀቴን ስትበላው ኖረህ…አለችና በሳቅ ፈረሰች..እሱም ተከተላት፡፡
ሁለቱም በምናባቸው ወደኃላ ተጓዙና ትካዜ ውስጥ ገቡ
ሰሎሜ የወር አበባዋ የመጣው በ14 አመቷ ነበር፡፡ያንን ደግሞ ከግሩፑ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ያወቀው አለማየሁ ነበር፡፡የዛም ምክንያት ከሰሎሜ ጋር አንድ ቤት በመኖራቸው ነው፡፡ወር በመጣ ቁጥር ግን ለሞዴስ የሚሆን ብር እናትዬውን መጠየቅ እያሳቀቃት ስትበሳጭ ይሰማና ..ይሄንን ችግር የሚፈታበትን ዘዴ ማሰላሰል ይጀምራል፡፡
ከዛ ፡አላዛር በዛን ጊዜ ከትምህር ሰዓት ውጭ የሱቅ ስራ ይሰራ ስለነበረ ወደእዛው ነው የሄደው፡፡
‹‹እሺ ቱጃሩ እንዴት ነህ?››
‹‹ያሄው እንደምታየው ነው....ምነው ብቻህን?››
‹‹ማለት?››
‹‹ሰሎሜን ወይም ሁሴንን አስከትለህ ይምትመጣ መስሎኝ ነበር፡፡››
ከሁለቱን ማንን ይዤ ብመጣ ነበር የምትደሰተው?››ሲል መልሱን እያወቀው ጠየቀው፡፡
‹‹ምን ለማለት ነው…?ሁለቱም ጓደኞቼ ናቸው …ለምን መርጣለሁ?››
‹‹ተው እንጂ …አታስመስል፡፡››
‹‹አንተ ደግሞ…!››ብሎት ዝም አለ
‹‹ቆይ ..ሞዴስ አለህ እንዴ?››
አላዛር ደንግጦ‹‹የምን ሞዴስ?››ሲል ነበር መልሶ የጠየቀው፡፡
‹‹ሞዴስ ነዋ ..ሴቶች የወርአበባ ሲመጣባቸው ሚጠቀሙበት፡፡››ሲል ብራራለት፡፡
‹‹የለኝም፡፡››
‹‹ለምን አታመጣም..ሴቶች አይጠይቁህም?››
‹‹እሱማ አልፎ አልፎ ይጠይቁኛል፡፡››
‹‹እና ለምን አታመጣም?››
‹‹እንዲሁ…ብዙም አስቤበት አላውቅም…ግን አልገባኝም. .እንዴት ልትጠይቀኝ ቻልክ?፡››
‹‹አይ ሰሎሜ እኮ አላዛር ሞዴስ የሚሸጥ ቢሆን እኮ በየወሩ አንድአንድ ይሰጠኝ ነበር…በየወሩ እቴቴን አላስቸግርም ነበር ስትል ሰምቼት ነው፡፡››
በመደነቅ‹‹በእውነት እንደዛ አለች…?››ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹አዎ ብላለች››ሲል ነበር ፍርጥም ብሎ የዋሸው፡፡
‹‹ግን የወር አበባ ታያለች ማለት ነው?››
‹‹እንዴ ለምን አታይም ሴት አይደለች?››
‹‹ማለቴ ገና ልጅ ነች ብዬ እኮ ነው፡፡››
‹‹ምነው አንተ መርጨት አልጀመርክም እንዴ?››
‹‹አንተ ደግሞ ታበዛዋለህ፡፡››
‹‹እንደውም ቆየች ..ባይሎጂ ላይ አልተማርክም እንዴ ..?አንድ ሴት እኮ ከ12 ዓመቷ ጀምሮ የወርአበባ ልታይ ትችላለች፡፡››
‹‹እሱማ አውቃለሁ…በቃ አሁን አደገች ማለት ነው?››
‹‹አዎ ..በደንብ እያደገችልን ነው፡፡››
‹‹በቃ…ከነገ ጀምሮ አመጣለሁ፡፡››
‹‹ጥሩ ..ለዚህ ወር ተገዝቶላታል..ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ትሰጣታለህ፡፡››
‹‹አዎ..ምንም አታስቢ በላት፡፡››
‹‹እሺ እላታለሁ..የወር አበባዋ የሚመጣው በ22 ወይም በ23 አካባቢ ነው…ስለዚህ በ20 በ20 እየመጣሁ ወስድላታለሁ፡፡››
‹‹ችግር የለውም..ግን እራሷ መጥታ ለምን አትወስድም፡፡››

👍45❤8