አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_አስራ_ሦስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ሶራ የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘው በሺ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ዓመተ ምህረት ነው። ከዚያም በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶችና በረጂ ድርጅቶች ሰርቷል። ሥራ መቀያየሩ ግን ሆዱን እንደ እንቁራሪት ሆድ ከማሳበጥ በስተቀር ያገኘው የሕይወት እርካታ
የለም። የት ቢሄድ ምን
ቢሆን የህሊና እርካታ እንደሚያገኝ
አያውቅም ዩኒቨርስቲ ውስጥ እያለ  ኢኮኖሚክስ ዲፓርትመንትን የመረጠው በጓደኞቹ ምክርና ግፊት ነው።

"...አትሞኝ! ጥሩ ደመወዝ ለማግኘት አዲሳባ ለመመደብ ዕድልተህ እንዲሰፋ ከፈለግህ" እያሉ የሰማይ ጥገት የሚመኙ ጓደኞቹ እየነዱ ወደ አልተመኘው ዲፓርትመንት
ሃሳቡን አኮላሽተው
አስገቡት።

ከአደገበት· ቀዬ ከተንቦራቸበት የኤርቦሬ ምድርም ዳግመኛ ሳይመለስ የውሃ ሽታ ሆኖ ወደ መጣበት ተመልሶ መግባት የማይታሰብ ገደል ሆነበት። በልጅነቱ ወደ ዘመናዊ ትምህርት ሊሄድ
ጥብቆ ሲለብስ
ሽማግሌዎችም ሲመርቁት

“…እንደ ጅብ በነጋበት የምትቀር አትሁን። የአያት የቅድመ አያቶችህን ደንብ አክባሪ ለወገንህ ተቆርቋሪ መሆንህን የምታስመሰክር ሁን ብትጠፋ እንኳ የእነሱ ዘር ነው የሚያሰኝህን
ኤርቦሬነትህን አታጥፋ።
ኤርቦሬ ውስጥ  ሪስ  ፋርቶ ሃልዝጋለች አልሞቅ  ሩፍ ህፀንቴ ኤቡሬ ጋሮራ
ጋራንጉዶ ጋርሌ ዲሳ የሚባል ዘር አለ ወደምትሄድበት አገር ስትደርስ የከብት ጆሮ
አበሳሳችሁ እንዴት ነው? ህፃን ልጅ እንደ ተወለደስ መጀመሪያ የምታቀምሱት ምንድን ነው?ብዙ ጊዜ የምትጋቡትስ ከማን
ከማን ጋር ነው?..." ብለህ ጠይቅ።

“...የአንተ ዘር የከብት ጆሮ አበሳስ ታችኛውን የጆሮ ክፍል ከውስጥ ወደ ውጭ በመብሳት ሲሆን! ህፃን ልጅ እንደተወለደ የቡና
ፍሬ ማሽላ የከብት ጥፍር ከህፃኑ ልጅ ሽንት ጋር ተቀላቅሎ ይሰጠዋል። ብዙ ጊዜ ጋብቻ ከቦረናና ፀማይ ጋር ነው። ስለዚህ
ይህን በሄድህበት ሁሉ እየነገርህ ዘርህን ብትጠይቅ ካለጥርጥር
ታገኛቸዋለህ: ከዚያ የቤተስባችሁ አባል ከሌላ  አገር ስለመጣ ተቀበሉት ብለው ከዘሮችህ ያደባልቁሃል:

ወደ ሌላ አገር የሄደና የሞተ አንድ ነው እስካልታዩ ድረስ:: ልዩነቱ ያልሞተ ከሄደበት ይመለሳል ! ያኔ ወደ ቤተሰቡ ከመቀላቀሉ በፊት የመንደሩ ሰዎች ማንም ሰው ጠጥቶበት
በማያውቅ ቅል ውሃ ሞልተው ይይዙና ከፊት ለፊቱ ውሃውን እየደፉ መሬቱን በማርጠብ እርጥቡን  እግር"  ከቤተሰቡ ጋር ይደባልቁታል! ካለበለዚያ ግን ማንም የቤተሰቡ አባል ቢያየውም
ሰላም አይለውም:: እና!  አንተም ክሄድክበት ስትመለስ ይኸ ደንብ
እንደሚሰራልህ አትርሳ: ከደንቡ በኋላ ከኤርቦሬ ወንድሞችህ ጋር ጫካ ትወርድና ያገኘኸውን አውሬ ገለህ ስትመጣ ከወላጆችህ በር ፊት ለፊት የእድሜ ጓደኞችህ "ዘውትር ምሽት እየዘፈኑ እያቅራሩ አንዱ የሌላውን ጀርባ ሸፍኖ እየተቀመጠ የአባትህ ቤት የጀግና ቤት መሆኑን እያወደሱ ሲያደምቁት ይሰነብታሉ… ከዚያ ተድረህ ወልደህ ከብደህ ጋንደሩባ ኡላም ሙራል ወይም እጉዴ ትኖራለህ።

“ ኤርቦሬ በአሁኑ ጊዜ ስልጣን የያዘው የኦጌልሻ ሄር ሲሆን ኦጌልሻ ሄር ስልጣነን የተረከበው ከሜልባሳ ሄር ነው።

“በአባትህ ባህል በአርባ ዓመት አንድ ጊዜ አሮጌው ገዥ ሄር በአዲሱ ገዥ ሄር ይተካል:: ይህም ኦቤርሻ ጂም ጊድማ ጂም
ማሮሌ ጂምና ዋተኛ ጂም ሲሆን የመጀመሪያው ጂም ከአስር እስከ አስራ ስምንት ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወጣቶች ሲሆኑ ኦቤርሻ ጂም ይባላሉ: ከዚያ ከጨቅላነት እስከ ዘጠኝ ዓመት ያሉት ህፃናት
አድገው ከአስር እስከ አስራ ስምንት አመት ሲሞላቸው ጊድማ ጂም ይሆናሉ። ያም ማለት ከኦቤርሻ ጂም እስከ ጊድማ ጂም ዘጠኝ ዓመት
ይሆናል ቀጥሎ ደግሞ ከጊድማ ጂም በታች ካሉት ጨቅላዎች እስከ ዘጠኝ ዓመት ያሉት አድገው ከአስር አመት እስከ አስራ ስምንት  ዓመት ሲሞላቸው ማሮሌ ጂምን ይመሰርታሉ።
ይህም ዘጠኝ ዓመት
ይፈጃል። ከማሮሌ በታች ያሉት ከጨቅላነት እስከ "ዘጠኝ ዓመት ያሉት አድገው ከአስር እስከ አስራ ስምንት ዓመት ሲሞላቸው ደግሞ ዋተኛ ጂም ይባላሉ።

“ስለዚህ ኦቤርሻ ጂም ዘጠኝ ጊዴማ ጅም ዘጠኝ ማርሌና የአራቱን ጂም
ዋተኛ ጂም እያንዳንዳቸው ዘጠኝ ዘጠኝ ስለሚቆዩ
ለመፈፀም ሰላሳ ስድስት አመት የሚፈጅ ሲሆን አሮጌውን የገዥ ሄር
ከተለያዩ እድሜ ከሴትና ወንድ በእኩል የተሰባሰበውን አዲስ ሄር
አጠቃላይ የኤርቦራ ማህበረሰብ በተሰበሰበበት በተለያዩ ባህላዊ ስነስርዓቶች ስልጣን ከአሮጌው ሄር ይረከብና በጋንደሩባ ኩላም
ሙራልና እጉዴ አንዳንድ ከርነት (ጠቅላይ ሚኒስቴር) ይመረጣል። ከርነት ሆኖ የተመረጠው ሰው ካለ  ግልድም በስተቀር ልብስ
አይለብስም። ባህሪውም የተመሰገነ ትሁት... መሆን ይገባዋል። ይህ ሰው የአባት ደንብና አሁን ያለው የኤርቦሬ ህዝብ የአደራ ቀንበር የሚጫንበት በሬ ነው: ጎረምሶችም የራሳቸውን የጦርነት ጊዜ
አዝማች 'መሪናኔት' መርጠው የነብር ቆዳ ያለብሱታል: ይህም ሰው
በጦርነት ጊዜ ስልት አውጭና ደረቱን ለጦር ሰጥቶ ለህዝቡ መከታ
የሚሆን ነው።

“ከዚያ የፖለቲካ መሪ የሚሆኑት አራቱ ከርነቶች
ከመንፈሳዊ መሪዎች (ቃውቶች) የአገር ሽማግሌዎች (ጃላቦች) ጋር
ስልጣናቸውን ለሚቀጥለው ወጣት ሄር ያስረክባሉ። ስለዚህ አንተ አሁን በስልጣን ላይ ያለው የኦጌልሻ ሄር አባል በመሆንህ ቶሎ ተመልሰህ
ማህበረሰብህን መርዳትህን አትዘንጋ: እስከዚያው ግን
ወገኖችህ ፀሐይ ወጥታ እስክትገባ ሳንሰለች እንጠብቅሃለን፡፡ ይህ ኸሊናህ ሳይጎድፍ ተመልሰህ ናና ከማህበረሰብህ ተቀላቀል...” ብለውት ነበር።

አካሉ እያደገ ህሊናው እየበሰለ ሲሄድ ግን ከዘመዶቹ አደራ በላይ የአገሩ የአህጉሩ ባጠቃላይ የሰው ልጆችን የመርዳት አደራ ፕላኔቷን የመጠበቅ ግዴታ... እንዳለበት እንኳን ተረድቶ ነበር። በጎ
አስተሳሰቡን ግን ውሃ በላው። አፍንጫው ጥቅም ውስጥ እየተሰነቀረ
ሆዱ ለእለት ደስታ እየተነጠፈ አስቸገረው መቆፈሪያ አንስቶ
የድህነት ተራራ ለመናድ የማንዴላ እናት አምጣ እንድትወልደው ኃይልን እንድታቀብለው ፈለገ እየቆየ ግን አንድ ሃሣብ በህሊናው
ማውጣት ማውረድ ጀመረ።: ቢያንስ በግሉ አንድ ሆዝብን ሊረዳ
ድርጅት መክፈት። ለዚህም ደግሞ ገንዘብ ያሻዋል። ገንዘብ ያላቸው ሰዎች መዳፍ ገብቶ እንደ ቆሎ እያሹ ጉልበቱን ቆረጣጥመው ምስጥ
እንደበላው ግንድ ገንድሰው እንዲጥሉት ግን አልፈለገም
ነፃ መሆንን መረጠ፡

ለዚህ ግን አልታደለም። ያለበት ዘመን ህይወት በገንዘብ የሚተመንበት የገንዘብ ኃይል ነጋሪት እየተጎሰመ በሚለፈፍበት ጊዜ ነው። ዓላማውን ለማሳካት ግን አንድ አማራጭ አለው: ሰርቶ
የማግኛ ስደት: "ስደት ግን ሽሽት ነው" ብሎ ያምን ነበር: ከዚህ ህዝብ ጋር የበላውን በልቶ የጠጣውን ጠጥቶ ከንፈር እየመጠጡ
ማስተዛኑም ደግሞ ድፍረት እንዳልሆነ ተረዳ። ኤርቦሬ አደራ ይዞ ወጣ፤ አልተመለሰም እና! አደራውን በላ: ከአገሩ ሰርቶ
ለማግኘት ብሎ ሄዶ ፍርፋሬ ቢጥመውስ፤ አዲስ ምኞት ህሊናው ቢያረግዝስ እንደገና ክህደት ሊፈፅም? ስለዚህ ለመወሰን ብዙ
አማጠ ከወሰነ በኋላም ህልሙን እውን ለማድረግ ብዙ ጣረ፤ ግን ተሳካለት። እንደ ደረቀ እንጨት የተለዬ ሆነ እንጂ።
👍21