አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ

‹‹አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ግድ የለኝም፡፡ ጦርነት አውድማ ውስጥ ገብቼ ፋሺዝምን ከሀገሬ ለማባረር እዋጋለሁ›› አለች በልበ ሙሉነት፡ ፊቷ ላይ
የሚነበበው ገፅታ ለህይወት ግድ እንደሌላት ያሳያል፡ ሄሪ ይህን ሲያይ ጎበዝ ናት› አለ በሆዱ፡፡

‹‹የቆረጥሽ ትመስያለሽ››

‹‹በዚህ እምነቱ የተነሳ የስፔን ፋሺስቶችን ሊዋጋ ሄዶ አፈር በልቶ የቀረ ፍቅረኛ ነበረኝ፡፡ የእሱን አርማ አንስቼ አላማውን ዳር ለማድረስ እታገላለሁ››ደ አለች በወኔና በሀዘን፡

‹‹ትወጂው ነበር?»

በአዎንታ ራሷን ነቀነቀች፡፡

አይኗ እንባ እንዳቀረረ ተመለከተና በሀዘኔታ ክንዷን ያዝ አደረጋት
‹‹አሁንም ትወጂዋለሽ?›› ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ምን ጊዜም ከልቤ አይጠፋም›› አለች የሹክሹክታ ያህል ‹‹ስሙ ኢያን ይባላል፡››

ሄሪ አሳዘነችው፡፡ ማርጋሬትን ደረቱ ውስጥ ወሽቆ ሊያፅናናት
ቢፈልግም በየት በኩል። ውስኪያቸውን እየጨለጡ ጋዜጣ የሚያነቡ በርበሬ
ፊት አባቷ ፊት ለፊት ተቀምጠዋል፡ እንደ ምንም እጁን ሰደደና አጇን ጨመቅ አደረገው፡፡ እሷም ለማፅናናት መሆኑ ገብቷት
ፈገግ አለች።

‹‹እራት ደርሷል ሚስተር ቫንዴርፖስት›› አለ አስተናጋጁ፡ ሄሪ አስራ
ሁለት ሰዓት ከምኔው እንደደረሰ ገርሞታል፡ ከማርጋሬት ጋር የጀመረውን
ጭውውት ማቋረጡ አሳዝኖታል፡፡ እሷም የእሱ ጭንቀት ገባትና ‹ብዙ
የምንጫወተው ነገር አለ›› አለች ‹‹ለሚቀጥሉት ሃያ አራት ሰዓታት አብረን
እንሆናለን››

‹‹ልክ ነሽ›› አለና ፈገግ አለ፡፡ እንደገና እጇን ዳበስ አደረገና ‹‹በኋላ
እንገናኝ›› አላት፡፡

ምስጢሩን በሙሉ የነገራት አጋሩ ሊያደርጋት ነው፡፡

ወደሚቀጥለው ክፍል ሲገባ ክፍሉ ከሳሎን ቤት ወደ መብል ቤትነት ተለውጦ ሲያይ ተገረመ እያንዳንዳቸው አራት ሰዎች የሚቀመጡባቸው
ሶስት ጠረጴዛዎች የተዘረጉ ሲሆን ሌሎች ሁለት ትንንሽ ጠረጴዛዎችም ይታያሉ፡፡ የእቃው አደራደር እንደ ምግብ ቤት ሲሆን ጠረጴዛዎቹ ጨርቅ
ለብሰዋል፡፡ በላያቸው ላይ የፓን አሜሪካ አየር መንገድ ስምና ምልክት ያለባቸው ብርጭቆዎች፣ ሰሃኖችና ናፕኪኖች ተቀምጠዋል። የመብል ክፍሉ ግርግዳ የአለም ካርታ ተለጥፎበታል አስተናጋጁ ሄሪን አንድ ሱፍ የለበሰ አጠርና ደልደል ካለ ሰው አጠገብ ወስዶ አስቀመጠው: ሄሪ የሰውዬው አለባበስ አስቀናው፡ ሰውዬው ክራቫት ያደረገ ሲሆን ውድ በሆነ ማያያዣ ጌጥ ከሸሚዙ ጋር አያይዞታል፡ ሄሪ እራሱን አስተዋወቀ፡ ሰውዬውም እጁን ለሰላምታ ዘረጋና ‹ቶም ሉተር እባላለሁ›› አለ፡፡ እጁ ላይ ያለው የወርቅ አምባር ከክራቫት ማያያዣው ጋር ይሄዳል፡፡ ለውድ ጌጣጌጥ ገንዘቡን
መበተን የሚወድ ሰው ማለት ይሄ ነው፡፡

ሄሪ የታጠፈውን ናፕኪን ዘረጋ፡፡ ሉተር አነጋገሩ የአሜሪካዊ ነው።
‹‹ከየት ሀገር ነው የመጣኸው?›› ሲል ሄሪ ጠየቀው ሰውዬውን
‹‹ፕሮቪደንስ ሮድ አይላንድ፧ አንተስ?››
‹‹ፊላደልፊያ›› አለ ሄሪ፡ ፊላደልፊያ የት እንዳለ እንኳን አያውቅም፡፡
አሜሪካ ውስጥ ያልኖርኩበት ቦታ የለም፡፡ አባቴ የኢንሹራንስ ሰራተኛ
ነበር፡››

ሉተር አንገቱን ነቀነቀ፡፡ ነገር ግን ከዚህ በላይ ማውራት አልፈለገም የሰውዬው ዝምተኛነት ለሄሪ ተስማምቶታል፡ ስለአኗኗሩ ሰው እንዲጠይቀው
አይፈልግም: በዝምታ ማለፍ ጥሩ ነው፡
ሁለት የአይሮፕላኑ ሰራተኞች በመጡና ራሳቸውን አስተዋወቁ፡ የበረራዐመሀንዲሱ ኤዲ ዲኪን ትከሻው የሰፋ፣ የደስ ደስ ያለው ፀጉረ ነጭ ሰው
ነው፡ ሁለተኛው ጃክ አሽፎርድ የሚባል ናቪጌተር ነው ፀጉረ ጥቁር ሲሆን
የለበሰው ዩኒፎርም ሄዶበታል።

ሰዎቹ እንደተቀመጡ በሉተርና በመሃንዲሱ መካከል የሆነ ጠብ እንዳለ
ሄሪ አስተዋለ።እራት ቀረበ፤ ሁለቱ የአይሮፕላን ሰራተኞች ኮካ ኮላ ሲመጣላቸው ሄሪ
ነጭ ቪኖ ቀረበለት፡ ቶምሉተር ማርቲኒ አዘዘ
ሄሪ እራት እየበላ ሳ
በአይሮፕላኑ መስኮት እያየ ስለማርጋሬትና ስፔን
ሄዶ ስለቀረው ቦይ ፍሬንዷ ያስባል፡፡ ስለእሱ አሁን ምን ያህል እንደምታስብ ማወቅ ፈለገ፡፡ ከእሷ እድሜ አንጻር አንድ አመት ትንሽ ጊዜ አይደለም፡፡

ጃክ አሽፎርድ ሄሪ በመስኮት እያየ መሆኑን ተገነዘበና ‹‹እስካሁን አየሩ
ጥሩ ስለሆነ እድለኞች ነን›› አለ፡

‹‹ሁልጊዜ እንዴት ነው አየሩ?›› ሲል ጠየቀ ሄሪ

‹‹አንዳንድ ጊዜ ከአየርላንድ እስከ ካናዳ በዝናብ የምንሄድበት ጊዜ አለ፡፡
‹‹አንዳንዴ ደግሞ በረዶና መብረቅ ያጋጥማል፡››

ሄሪ አንድ ጊዜ ያነበበውን አስታወሰና ‹‹በረዶ ከዘነበ ለአይሮፕላኑ አደገኛ አይደለም?›› ሲል ጠየቀ፡

‹‹በተቻለን መጠን ቀዝቃዛው የአየር ንብረት እንዳያገኘን እንጥራለን፡፡ለማንኛውም ተብሎ ግን አይሮፕላኑ ክንፎች ላይ የበረዶ ማቅለጫ ሸራ
ተደርጎለታል፡››

የመጪው የአየር ትንበያ ምን ያመለክታል?››

ጃክ ይህን መልስ ለመስጠት ሲጠራጠር አየና ስለአየሩ ባልጠየቅ ይሻል
ነበር›› ሲል አሰበ፡፡ ‹‹አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ዶፍ ዝናብ ይጠብቀናል››
አለ፡፡

‹‹ይህን ያህል መጥፎ ነው?›› ጠየቀ ሄሪ፡

‹‹ዶፍ ዝናቡ መሃል ከገባን መጥፎ ነው፡ ሆኖም እኛ ከዶፍ ዝናቡ ራቅ ብለን እንበራለን›› አለ በሰጠው መልስ ብዙም ባለመተማመን፡፡

ቶም ሉተርም ቀጠለና ‹በዶፍ ዝናብ ውስጥ መጓዝ ምን ችግር አለው ሲል ጠየቀ።

ጃክ በዝርዝር አልተናገረም፤ ነገር ግን የበረራ መሀንዲሱ ኤዲ፣ ቶም ሉተርን ለማስፈራራት ሲል ወደ እሱ እያየ ‹‹ልክ ባልተገራ ፈረስ የሚጋልቡ ይመስል ያነጥራል›› አለ፡

ሉተር ኤዲ ያለውን ሲሰማ በድንጋጤ አመድ መሰለ፡፡ ኤዲ በተሳፋሪው
ፊት አፉ እንዳመጣ በመናገሩ ጃክ ገላመጠው:

ተሳፋሪዎቹ ሁለተኛ ዙር የእንቁራሪት መረቅ መጣላቸው:🤮

አሁን የሚያስተናግዱት ሁለቱ አስተናጋጆች ኒኪና ዴቪ ናቸው፡ ኒኪ ድብልብል ሲሆን ዴቪ ደግሞ ከአፍ የወደቀች ጥሬ ነው የሚያክለው፡፡

ሄሪ ሁለቱም ወንዳገረዶች ሳይሆኑ አይቀሩም› ሲል ገመተ፡ ታዲያ ቅልጥፍናው አስደስቶታል፡፡

ሄሪ በድብቅ እንደተከታተለው የበረራ መሀንዲሱ አዕምሮው በአንድ ነገር የተጠመደ ይመስላል፡፡

‹ሄሪ መሀንዲሱ ባህሪው አኩራፊ አይመስልም፡፡ ሲያዩት ተጫዋችና
ግልፅ ይመስላል› ሲል አሰበና እንዲናገር ለማበረታት ‹‹አንተ ምግብ በምትበላበት ጊዜ የበረራ ምህንድስናውን ስራ ማን ይሰራል?›› ሲል ጠየቀው
‹‹ረዳት የበረራ መሀንዲሱ ሚኪ ፊን ነው›› አለ፡ ‹‹በፈረቃ ነው የምንሰራው፡፡ ጃክና እኔ ከሳውዝ ሃምፕተን በረራ ከጀመርንበት ከቀኑ
ስምንት ሰዓት ጀምሮ ስንሰራ ቆይተናል፡፡ ስለዚህ ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት
ላይ እረፍት እናደርጋለን፡፡››

‹‹ካፒቴኑስ?›› ሲል ጠየቀ ቶም ሉተር ሀሳብ ገብቶት።
‹‹እንቅልፍ እንዳይዘው መድሃኒት ይውጣል፡ ከቻለ በተቀመጠበት ትንሽ ያንቀላፋል›› አለ ኤዲ፡ ‹‹ወደኋላ የማንመለስበት ሁኔታ ላይ ስንደርስ
ፓይለቱ ምን አልባት ረጅም እረፍት ያደርጋል፡››

‹‹ስለዚህ በሰማይ በምንበርበት ጊዜ ፓይለቱ ይተኛል ማለት ነው?››
ሲል ጠየቀ ሉተር ሳያስበው ጮክ ብሎ፡

‹‹አዎ›› አለ ኤዲ በፈገግታ:፡ ሉተር ፍርሃት ፍርሃት እንዳለው ያስታውቅበታል፡፡ ሄሪ ጨዋታው ሰላማዊ እንደሆነ በማሰብ ‹‹ወደኋላ
የማንመለስበት ሁኔታ ማለት ምንድን ነው?›› ሲል ጠየቀ፡፡
👍19
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ


ማርጋሬት ደስ ደስ ብሏታል፡ ከእውነተኛ ሌባ ጋር መወዳጀቷን ማመን
እያቃታት ነው፡ አንድ ሰው ‹‹እኔ ሌባ ነኝ›› ቢላት አታምነውም፡ ነገር ግን
ሄሪ አንድ ጊዜ ፖሊስ ጣቢያ ተከሶ ስላየችው ‹‹እኔ ሌባ ነኝ›› ቢላት እውነቱን መሆኑን አወቀች።

ከስርዓት ውጭ የሚኖሩ ሰዎች ማለትም ወንጀለኞች ለህግና ለመንግስት የማይገዙ ሰዎች፣ ሴተኛ አዳሪዎችና በረንዳ አዳሪዎች ሁልጊዜ
ያስደንቋታል፡ እነሱ ነጻ ሰዎች ናቸው፡፡ በእርግጥ በህብረተሰቡ የተተፋ ሰው
ጥሩ ነው የሚል አመለካከት የላትም፡፡ ነገር ግን እንደ ሄሪ ያሉ ሰዎች አድርጉ የተባሉትን ሁሉ ለማድረግ አይፈቅዱም፡ይህ ነጻነታቸው ነው ማርጋሬትን የሚያስቀናት፡፡ አንዳንዴ የወታደር ልብስ ለብሶ ጠመንጃውን ታጥቆ በየመንደሩ እየዞረ ህዝብ የሚዘርፍ ሽፍታ መሆን ያምራታል እንደዚህ አይነት ሰዎች ገጥመዋት አያውቁም: አንድ ጊዜ በለንደን ጎዳናዎች
ላይ ሴተኛ አዳሪ መስላቸው ሊደፍሯት የመጡትን ሰዎች ባታይ የምታውቅበት ሁኔታ አልነበረም፡፡

ሄሪ እሷ የምትመኘውን ነገር ሁሉ ያሟላ ሆኖ ነው ያገኘችው የፈለገውን ማድረግ የሚችል ሰው! ዛሬ ጧት አሜሪካ ለመሄድ ወሰነና ዛሬ ከሰዓት በኋላ አይሮፕላኑ ላይ ተገኘ፡፡ ሌሊቱን በሙሉ መደነስና ቀኑን በሙሉ መጋደም ከፈለገ ያደርገዋል፡ ከልካይ የለበትም፡፡ መብላት የፈለገውን ይበላል፧ መጠጣት የፈለገውን ይጠጣል፡ ገንዘብ ከፈለገ ገንዘባቸውን መጣያ
ካጡ ባለጸጎች ይሰርቃል፡ እሱ ነጻ የሆነ ሰው ነው፡
ስለሄሪ በይበልጥ ማወቅ ፈለገች፡ ከእሱ ጋር ራት ሳትበላ ያሳለፈቻቸው
ቀናት ቁጭት ውስጥ ጣሏት፡፡

ባሮን ጋቦንና ካርል ሃርትማን ከኦክሰንፎርድ ቤተሰብ ቀጥሎ ተቀምጠዋል እነዚህ ሰዎች ይሁዲ ስለሆኑ ነው ገና ወደ መብል ክፍሉ እንደገቡ ሎርድ ኦክሰንፎርድ ክፉኛ የገላመጧቸው፡አብረዋቸው
የተቀመጡት ኦሊስ ፊልድና ፍራንክ ጎርደን ናቸው፡፡ ፍራንክ ጎርደን በዕድሜ
hሄሪ ብዙም የማይበልጥ መልከ መልካም ወጣት ነው፡፡ ኦሊስ ፊልድ ደግሞ
ኑሮ የጠመመበት የመሰለ በዕድሜ ገፋ ያለ ራሰ በራ ሰው ነው፡፡

ፎየንስ ላይ አይሮፕላኑ ሲያርፍ ሁሉም ሰው ከአይሮፕላኑ ወጥቶ
በየፊናው ሲበታተን እነዚህ ሁለት ሰዎች አይሮፕላኑ ውስጥ በመቅረታቸው
የለው ሁሉ መነጋገሪያ ሆነው ነበር፡፡

ሶስተኛው የመመገቢያ ጠረጴዛ ላይ ሉሉ ቤልና ሾርባው ጨው የበዛበት ነው እያሉ ሲያማርሩ የዋሉት ልዕልት ላቪኒያ ተቀምጠዋል ከነሱ ጋር ፎየንስ ላይ የተሳፈሩት ሚስተር ላቭሴይና ሚስስ ሌኔሃን ተቀምጠዋል። ወሬ መለቃቀም የሚወደው ፔርሲ እነዚህ ሰዎች ባልና ሚስት ባይሆኑም የሙሽሮቹን ክፍል እንደሚጋሩ ወሬ ለጠማቸው አውርቷል
ባልና ሚስት ያልሆኑ ሰዎች ይህን ክፍል እንዲይዙ ፓን አሜሪካን አየር
መንገድ እንዴት እንደፈቀደላቸው ማርጋሬት ገርሟታል። አየር መንገዱ ብዙ ሰዎች ወደ አሜሪካ መሄድ ስለፈለጉ ህጉን መጋፋት የግድ ሆኖበታል፡

ፔርሲ ጥቁር የይሁዲዎች ኮፊያ አናቱ ላይ ደፍቷል፡ ማርጋሬት ይህን ስታይ በሳቅ ተንፈቀፈቀች፡፡ ከየት ነው ያመጣው! አባቱ ግን ‹‹ጅል!›› ብለው ተሳድበው ኮፍያውን መንጭቀው ወረወሩት፡፡

ሌዲ ኦክሰንፎርድ ኤልሳቤት ተለይታቸው ከሄደች ወዲህ ለመጀመሪያ
ጊዜ ፊታቸው በመጠኑ ፈካ ብሏል፡፡

ሌዲ ኦክሰንፎርድ ‹‹የራት ሰዓታችን ገና ነው›› አሉ፡፡
ሎርድ ኦክሰንፎርድ ደግሞ ‹‹አንድ ሰዓት ተኩል ሆኗል እኮ›› አሉ፡፡
‹‹ለምንድነው ታዲያ ያልጨለመው?››
‹‹እንግሊዝ አገር አሁን ጨለማ ነው፡ አሁን ግን ከአየርላንድ ባህር
ጠረፍ ሶስት መቶ ማይል ርቀት ላይ ነው የምንገኘው ጸሃይዋን እያሳደድን
ነው›› አለ ፔርሲ፡፡

‹‹መቼም መጨለሙ አይቀርም››
‹‹ምናልባት ሶስት ሰዓት ላይ የሚጨልም ይመስለኛል›› አለ ፔርሲ
‹‹ጥሩ›› አሉ እናት፡፡
እንደማይጨልም
‹‹ጸሃይዋን ተከትለን በፍጥነት ብንጓዝ
እንደማይጨልም ታውቃላችሁ? አለ ፔርሲ፡፡

‹‹እንደዚህ አይነት ፍጥነት ያለው አይሮፕላን የሰው ልጅ ይሰራል ብዬ አልገምትም›› አሉ አባት ከኔ በላይ አዋቂ የለም በሚል ግብዝነት፡
ቦትውድ ካናዳ ለመድረስ አስራ ስድስት ሰዓት ተኩል ይፈጃል›› አለ ፔርሲ ‹‹እዚያ በግሪንዊች ሰዓት አቆጣጠር ከጧቱ ሶስት ሰአት እንደርሳለን››
‹‹ካናዳ ስንት ሰዓት ይሆናል ማለት ነው?,,
‹‹የኒውፋንድላንድ ካናዳ የሰዓት አቆጣጠር ከግሪንዊች የሰዓት አቆጣጠር ሶስት ሰዓት ወደ ኋላ ነው›› አለ ፔርሲ፡፡

እናት የፔርሲን ችሎታ አጤኑና ‹‹ወንዶች የቴክኒክ እውቀት ላይ ጎበዞች ናቸው›› አሉ፡፡

ማርጋሬት በእናቷ አነጋገር ተናደደች፡፡ እናት የቴክኒክ ነገሮች ሴቶች አይገባቸውም ብለው ያምናሉ፡፡ ‹‹ወንዶች ሴቶች ጎበዝ ሲሆኑ አይወዱም››
ብለዋታል ብዙ ጊዜ፡ በዚህ ጉዳይ ማርጋሬት ከእናቷ ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ መግባት ባትፈልግም እሷ ግን አታምንበትም፡ ይህን የሚቀበሉ ወንዶች ደደቦች ናቸው ብላ ነው የምትገምተው ጎበዝ ወንድ ጎበዝ ሴት ይወዳል፡

አጠገባቸው ካለው ጠረጴዛ ዙሪያ የተቀመጡት ባሮን ጋቦንና ካርል ሃርትማን ክርክር ገጥመዋል አጠገባቸው ያሉት የጠረጴዛ ተጋሪዎች
ባይገባቸውም በጸጥታ ያዳምጣሉ: ሁለቱ ሰዎች አይሮፕላኑ ላይ ከወጡ
ጀምሮ ጥልቅ ውይይት ሲያደርጉ ይታያሉ፡፡ በዓለም ከታወቀ ሳይንቲስት
ጋር እንደዚህ ያለውን ውይይት የምታደርጉ ከሆነ ውይይቱ ጥብቅ መሆኑ
አያስደንቅም፡፡ በክርክራቸው ውስጥ ፍልስጤምንና እስራኤልን በተደጋጋሚ ያነሳሉ፡ ማርጋሬት የውይይት ርዕሳቸውን ስትሰማ
‹‹አባባ ምን ይል
ይሆን?›› እያለች አስሬ ታያቸዋለች፡፡ እሳቸውም የሁለቱ ሰዎች ውይይት
አልጥም ብሏቸው አኩርፈዋል፡፡ አባቷ ነገር እንዳይጭሩ ርዕስ ለማስለወጥ
‹‹አይሮፕላኑ የሚጓዘው ኃይለኛ ነፋስ በቀላቀለ ዝናብ ውስጥ ነው›› አለች
‹‹እንዴት አወቅሽ?›› አለ ፔርሲ አነጋገሩ ቅናት ያለበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በበረራ መረጃ ከማርጋሬት ይልቅ እሱ ነው ኤክስፐርቱ።
‹‹ሄሪ ነገረኝ››
‹‹እሱ እንዴት ያውቃል?››
‹‹እሱ ዛሬ ራት የበላው ከበረራ መሃንዲሱና ከናቪጌተሩ ጋር ነው፡››
ማርጋሬት ዝናቡ ችግር ይፈጥራል ብላ አልገመተችም፡፡ በእርግጥ
በዝናብ ውስጥ መጓዝ ምቾት ቢነሳም ለክፉ አይሰጥም፡፡

ሎርድ ኦክሰንፎርድ ብርጭቋቸው ውስጥ የቀረውን ቪኖ አጋቡና ሌላ
እንዲጨመርላቸው ቆጣ ብለው ጠየቁ፡፡ ዝናቡ ችግር ያመጣል ብለው ፈሩ
እንዴ? ከተለመደው በላይ እየጠጡ መሆናቸውን ማርጋሬት ተገንዝባለች።
ፊታቸው ከመጠጥ ብዛት ፍም መስሏል: ዓይናቸው ፈጧል፡ ምናልባትም
ነርቭ ሆነዋል፡፡በኤልሳቤት መኮብለል ክፉኛ ተበሳጭተዋል
እናትም ማርጋሬትን ‹‹ሚስተር መምበሪን አጫውቺው›› አሏት፡
ማርጋሬት የእናቷ አባባል ገርሟት ‹‹ለምን?›› ስትል ጠየቀች፡ ሲያዩት
ሰው እንዲያናግረው የሚፈልግ አይመስልም፡

‹‹ምናልባትም አይናፋር ሳይሆን አይቀርም›› አሉ እናት፡፡

እማማ ከመቼ ወዲህ ነው ለአይናፋሮች መቆርቆር የጀመረችው?የሚሆን ነገር አይደለም፡፡ ‹‹ግን ምን ማለትሽ ነው?›› ስትል ጠየቀች ማርጋሬት።
👍13🔥1