#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_አንድ
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
hቦትውድ ወደ ሼዲያክ
ኤዲ ዲኪን የበረራ ባልደረቦቹ ወደ ጀልባው ሲገቡ ሲያይ ሊፈጽመው
ያሰበው ክህደት በዓይነ ህሊናው ድቅን አለበት፡ መቼም ሊያደርግ ያሰበውን
ቢያውቁ ዓይንህን ላፈር እንደሚሉት ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ነዳጁ ባዶ መሆኑን እያወቀ አይሮፕላኑ ባህር ውስጥ ገብቶ ሁሉም እንዲያልቅ ሊያደርግ እንደነበር ያወቁበት መሰለው፡፡
የነዳጅ መጠኑን መቆጣጠር የበረራ መሀንዲሱ ስራ ነው፡፡ ስለዚህ ሰው በዚህ ምክንያት ቢያልቅ ተጠያቂ እሱ ነው፡፡
ሰሞኑን ያሳይ የነበረውን እንግዳ ባህሪ ቢያውቁ ምን ይላሉ? እነሱ በማያውቁት ነገር አዕምሮው ተወጥሮ ቆይቷል፡፡ ትናንት ማታ ራት ላይ ቶም ሉተርን ሲያስፈራራው ነው ያመሸው፡፡ የወንዶች መፀዳጃ ቤት ውስጥ
መስኮት ሲሰበር እሱ
እዚያው ነበር፡፡ ስለዚህ ኤዲን ቢጠረጥሩ
አይፈረድባቸውም፡፡ እንዲህ አይነት ነገር ቢታወቅ ወሬው በአንድ ጊዜ ነው
አይሮፕላኑ ውስጥ የሚዛመተው፡፡
የስራ ባልደረቦቹ በእሱ ላይ ከእንግዲህ እምነት ሊጥሉ እንደማይችሉ ማወቁ በራሱ የኮሶ መድኃኒት እንደመዋጥ ነው የሆነበት፡፡ ከሁሉም
የአይሮፕላኑ ሰራተኞች አቋመ ጽኑ መሆኑ ያኮራው ነበር፡ የሌሎችን ስህተት በቀላሉ ማለፍ ስለማይችል አንዳንዴ ሰዎች በግል ችግራቸው ምክንያት ግዴታቸውን መወጣት ሲያቅታቸው የሚሳደብበት ጊዜ አለ፡፡በይቅርታ ሊታለፍ አይችልም ይላቸዋል ስህተት ሲፈጽሙ ከተገኙ፡፡ አሁን ግን እሱ ራሱ የሚታመን ሰው አልሆነም፡፡
አሁን ለእንደዚህ አይነት ጉዳይ የሚጨነቅበት ጊዜ አይደለም፡፡ ሚስቱን
ለማዳን የማይፈነቅለው ድንጋይ የማይምሰው ጉድጓድ የለም፡፡ ስለዚህ
ሚስጥሩን በሆዱ ይዞ ለብቻው ሊፈጽም ቆርጦ ተነስቷል፡ ስለሌሎች ስሜት
አሁን መጨነቅ የለበትም፡፡ ሆነም ቀረ ህይወታቸውን አንዴ አደጋ ላይ ጥሏል፡፡ ውጤቱም እንዳሰበው ሊሆን ነው፡ አቋመ ጽኑው መሀንዲሱ ዲኪን
ወደማይታመነው ዲኪን መቀየሩ ነው፡፡
በርካታ ተሳፋሪዎች ትንሽ እንቅልፍ ብናገኝ ብለው አይሮፕላኑ ውስጥ
ቀርተዋል፡ የኤፍ.ቢ.አዩ ኦሊስ ፊልድና እስረኛው ፍራንክ ጎርዲኖም ከአይሮፕላኑ አልወረዱም፡፡ ቶም ሉተር ባለጸጉራም ጃኬቱን ለብሶና ቆቡን አናቱ ላይ ደፍቶ ጀልባው ላይ። ወጣ፡፡ ኤዲም ከኋላው መጣና ጠጋ ብሎ
‹‹የአየር መንገዱ ህንጻ ጋ ሂድና ስልኩ ያለበት ቦታ እወስድሃለሁ›› አለው፡
ቦትውድ ከእንጨት የተሰሩ ቤቶች የተገጠገጡባት ትንሽ ከተማ ስትሆን
የአይሮፕላኑ ተሳፋሪዎች በየሱቁ ብዙም የሚገዛ ነገር አላገኙም፡፡ መንደሪቱ
የስልክ አገልግሎት አላት፡፡ ኒውፋውንድ ላንድ አሁንም በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ስር ስለሆነች መኪኖች የሚሄዱት ግራቸውን ይዘው ነው፡፡
ተሳፋሪዎቹ ወደ ፓን አሜሪካ አየር መንገድ ህንጻ ሄዱ፡፡ ኤዲ ከቦትውድ ሰላሳ ስምንት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ አየር ማረፊያ ላይ ካረፈ አይሮፕላን በሬዲዮ የተላከ የአየር ጠባይ መረጃ አነበበ፡፡ ከዚያም ለሚቀጥለው ጉዞ የሚያስፈልገውን የነዳጅ መጠን ስሌት ሰራ፡
ሲሰራ አፉን ደም ደም አለው፡፡ ከዚህ በኋላ የበረራ መሀንዲስ አይሆንም።
ካፒቴኑ የኤዲን የነዳጅ ፍላጎት መጠን ስሌት አምኖ መቀበል ይኖርበታል፡፡ የሰራው ስራ እንዲታመንለት ስሌቱን ሁለት ጊዜ ቼክ አደረገና
‹‹ሌላ ሰው ቢያጣራው እወድ ነበር›› ብሎ ለካፒቴኑ ሰጠው።
‹‹ችግር የለውም›› አለ ካፒቴኑ ለነገሩ ትኩረት ባለመስጠት፡ ‹‹እስቲ
ተናፍሼ ልምጣ›› አለና ወጥቶ ሄደ፡ ኤዲም ካፒቴኑን ተከትሎ ወጣና ቶም ሉተርን ፓን አሜሪካን ህንጻ አጠገብ ሁለት እጁን ኪሱ ከቶ አገኘው፡፡ ‹‹ወደ ስልኩ እንሂድና ከጓደኞችህ
ጋር እንድትነጋገር አድርጌ ቶሎ ወደ ስራዬ እመለሳለሁ›› አለው፡ ሉተር
በመጀመሪያ ጎተት እያለ ነበር የሚሄደው፡፡ በኋላ ግን የትናንት ማታውን
ግብግብ አስታወሰና ቶሎ ቶሎ መራመድ ጀመረ፡፡ ኤዲን እንደገና ማናደዱ
ትርፉ ራስን መጉዳት መሆኑን ተረድቷል፡፡
በመንገዳቸው ላይ መርቪንና ናንሲን አገኙና የአንገት ሰላምታ
ሰጥተዋቸው አለፉ፡፡ ሁለቱም አንድ ላይ በመሆናቸው የተደሰቱ ይመስላሉ፡ሰዎች እሱና ካሮል አን አንድ ላይ ሲሆኑ እንደሚያስቀኑ ይነግሩት ነበር፡ እሷን ሲያስታውስ ብስጭቱ እንደገና ተቀሰቀሰበት፡፡
ስልክ ቤት ገቡና ሉተር የስልክ ቁጥሩን በብጣሽ ወረቀት ጽፎ ለስልከኛው ሰጠው:፡ ኤዲ የሚናገረውን እንዲሰማ አልፈለገም፡፡ ኦፕሬተሩ እስኪያገናኛቸው ድረስ የስልክ መደወያው ክፍል ውስጥ ገብተው ጠበቁ ማለዳ በመሆኑ ብዙ ስልክ ደዋይ የለም፡፡
ኤዲ ካሮል አንን አይሮፕላኑን የሚያሳርፍበት ቦታ ድረስ ይዘዋት እንዲመጡ ሉተር እንደሚነግራቸው ገምቷል።
ካሮል አንን በእጁ ካስገባ
በኋላ ደግሞ ሌላ ያሰበውን ነገር ለመስራት ነጻነት ያገኛል ነገር ግን ምን
ሊያደርግ ነው ያሰበው? ወዲያው ለፖሊስ ማሳወቅ? ሉተር ከጠረጠረ ድረስ ደግሞ ዝም ብሎ መጠበቅ የግድ ነው፡፡ ታዲያ በዚህ ጊዜ ውስጥ የሬዲዮ መገናኛውን ከመስበር አይመለስም፡፡ የፖሊስ እርዳታ እስኪደርስ
ጎርዲኖና ሉተር ከአይሮፕላኑ ወጥተው በመኪና ያመልጡና አንዱ ጋ
ይሸጎጣሉ፡፡ ካናዳ ይግቡ አሜሪካ ማንም የሚያውቅ አይኖርም፡፡ ኤዲ
እንዳያመልጡ አስቀድሞ ለፖሊስ ቢነግር ደግሞ ከፖሊሶች ጋር ሲታኮሱ
የካሮል አን ህይወት አደጋ ላይ ይወድቃል፡፡ ኤዲ እንዲህ እንዲሆን
አይፈልግም::
ስልኩ ሲጮህ ሉተር አነሳና ‹‹እኔ ነኝ የዕቅድ ለውጥ መኖሩን ልነግራችሁ የደወልኩት፡፡ ሴትየዋን በጀልባ አይሮፕላኑ ድረስ ካላመጣችሁ የምትፈልጉትን አልፈጽምም ብሏል ሰውየው፡፡ እኔ በበኩሌ ያለውን አምኜ
ተቀብያለሁ፡ ስለዚህ ይዛችኋት እንድትመጡ›› አለና መልሳቸውን ጠበቀ፡፡
ከዚያም ‹‹ሊያናግሩህ ይፈልጋሉ›› አለው ኤዲን፡፡
ሉተር በመጀመሪያ ትዕዛዝ ሲሰጠው ልክ የወሮበሎቹ መሪ መስሎ ነበር የሚታየው፡፡ ካነጋገሩ ግን ካሮል አንን ወደ መገናኛቸው ቦታ እንዲያመጣለት
ለማዘዝ ስልጣን የሌለው ሆኖ ታየው፡፡
‹‹ሊያናግረኝ የሚፈልገው አለቃችሁ ነው?››
‹‹እኔ ነኝ አለቃ›› አለ ሉተር እየከበደው ‹‹ነገር ግን ግብረ አበሮች አሉኝ››
የሉተር ግብረ አበሮች ካሮል አንን ቦታው ድረስ ማምጣት እንደማይፈልጉ ይታወቃል፡፡ ከእነሱ ጋር መነጋገሩ የሚፈይድለት ነገር አለ? የለም፡፡ ካሮል አንን ስልኩጋ ያመጡና አስለቅሰው የመንፈስ ጽናቱን ይፈታተኑታል፡፡ ‹‹ስትፈልጉ ገደል ግቡ በላቸው›› አለ ጮክ ብሎ
እንዲሰሙት፡፡
ሉተር የኤዲ አነጋገር አስደንግጦት እነዚህን ሰዎች እንዲህ ልትናገራቸው አትችልም›› አለ እሱም ጮክ ብሎ፡፡
ሉተር የወሮበሎቹ መሪ ከሆነ ምን አስፈራው? አሁን የሉተርን ስልጣን መገምገም አይረባውም፡፡ ዕቅዱን ማሳካት ነው ያለበት፡፡ ሉተርም ‹‹ወይ አናግራቸዋለሁ ወይም አላናግራቸውም በል›› አለው ኤዲን፡፡
ላናግራቸው እንደማልፈልግ ንገራቸው ለእነዚህ ድንጋይ ራሶች አለው።
አይ አምላኬ አለና ሉተር የስልኩን እጀታ አንስቶ ‹‹አላናግራችሁም
ብሏል፡፡ ሰውየው አስቸጋሪ ነው:›› ንግግሩን ቆም አደረገና ‹‹ጥሩ ሃሳብ ነው እነግረዋለሁ››ብሎ የስልኩን እጀታ እንደያዘ
‹‹ሚስትህ ቀርባለች
ታናግራታለህ?›› አለው ኤዲን፡፡
ኤዲ ስልኩን ሊቀበል እጁን ዘረጋና መልሶ ተወው፡፡ ከእሷ ጋር ከተነጋገረ ምህረት ጠያቂ ሊሆን ነው ነገር ግን ድምጿን ቢሰማ አይጠላም እንደማያነጋግራት በራስ ንቅናቄ ለሉተር አመለከተው፡፡
ሉተር ኤዲ ላይ አፈጠጠና ‹‹አላናግርሽም ብሏል ባልሽ፡፡ ዞር በይ አንቺ
ሸርሙጣ!›› አላት ካሮል አንን፡፡

👍14❤1
#ባል_አስይዞ_ቁማር
፡
፡
#ክፍል_አርባ_አንድ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ጎነኛው መቃብር ስር አንድ ሰው እንደሀውልት ተገትሮ ቆሟል...እዛ ያለ ይመስላል እንጂ በድኑ ብቻ እንዳለ ያስታውቃል። ሀዘኑ ሀዘኗን ቀሰበሰባት። ምኑ ይሆን የሞተበት"የማወቅ ጉጉት አደረባት።አንገቷን አሰገገችና ሀውልቱ ላይ የተፃፈውን ፁሁፍ አነበበች ወ/ሮ ቅድስት ሀምሳሉ 1980 ፡፡ 2015ዓ.ም ይላል።እድሜዋን በአእምሮዋ አሰላችው ።የሰውዬው እድሜ ገመተች ..አርባ አመት ቢሆነው ነው በቃ ፍቅረኛው ወይም ሚስቱ ነች ስትል አሰበች።እንዲህ ካሠበች በኋላ ለሰውዬው ያላት ሀዘኔታ ጨመረ፡፡
ለማታውቀው ሰው በዚህ መጠን ሰታዝን ይሄ የመጀመሪያ ገጠመኞ ነው። ምን አልባት እሷ ገና ለገና ፍቅረኛ እንዲሆናት የፈለገችው ሰው ጥሏት ስለተሠወረ እንዲህ እንቅሽቅሽ ካለች እሱ ደግሞ ፍቅረኛው ወይም ሚስቱ ለዘላለም ጥላው ሞታ ከምድር በታች አፈር ለብሳ ስትቀበር እንዴት ሊያዝን እንደሚችል አሰላችና ሰቀጠጣት...?ያው ለእሱ እያዘነች ቢመስላትም በተዘዋዋሪ ለራሷ እያዘነች ነው። ወደኋላ ተመለሰችና ለቃል አባት አምጥታ ሀውልቱ ላይ ካስቀመጥቻቸው አምስት የፅጌረዳ ዝንጣፊዎች መካከል ሁለቱን አነሳች ‹‹ይቅርታ በሚቀጥለው ስመጣ የእነዚህንም ፋንታ ይዤ መጣለሁ... ብድር ነው›› በማለት...ወደሰውዬው ሄደች.. አጠገቡ ቆመች...ከደቂቃዋች በኃላ ዞር ብሎ አያት አየችው. ።
ጎንበስ አለችና አበባውን በሀውልቱ መሀከል ላይ አስቀመጠችው...፡፡ይደሰታል ..ያመሰግነኛል ብላ ስትጠብቅ በቅፅበታዊ ንዴት አይኖቹን አጉረጠረጠባት... ፊቱ በአንዴ ደም ለበሰ...አይኑ ውስጥ የሚንቀለቀል ከገሀነም እሳት የረገፈ ፍም ነው ያየችው..በዚህ መጠን ሰው አስፈርቷትም አስደንግጧትም አያወቅም....፡፡ጎንበስ አለና ያስቀመጠችውን አበባች አነሳና ብጥቅጥቅ አድርጓ ቆራረጣቸው፤ ተበታትነው መሬት ከመርገፍ የዳኑትን ወደ አፍ ከቶ እያኘከና እየበጣጠቀ መትፍት ጀመረ…፡፡አንድ አምስት እርምጃ ወደ ኃላ ሸሸት አለችው...
‹‹እሷ አበባ ፈፅሞ አይገባትም.››."አሁን ይሄን መቃብር ብንከፍተው ስጋዋን እንዳለነው የምናገኘው..አፈር አይበላትም߹ ከበላትም ለአፈሩ አውዳሚ አሲድ ነው የምትሆንበት ፤ምስጦችም አይበሏትም ከበሏትም ሰውነታቸው ተመርዞ ያልቃሉ"አላትና ጥሏት ሄደ...በህይወቷ በሞተ ሰው ላይ ሲሰነዘር የሰማችው በጣም መራርና አስከፊው ወቀሳ ነው ፡፡በመሄዱ እፎይ አለች ..እዛ ከእሷና እሱ ውጭ ሰው በሌለበት የቀብር ስፍራ ሲጥ አድርጎ የሚገላግላት መስሏት በፍራቻ መንቀጥቀጥ ጀምራ ነበር ።አይ የሠው ልጅ ከደቂቃዎች በፊት ለመኖር ያላት ጉጉት ተሟጦ አልቋል ስትል ነበር ..አሁን ደግሞ ህይወቷ ላይ ጥቃት እንዳይደርስ እየሠጋች ነው።እራሷን አረጋጋችና ኩስ ኩስ እያለች ከኋላ ተከተለችው፡፡
ከመቃብር ቅጥር ጊቢ ወጥቶ አስፓልት ጠርዝ ላይ ሲደርስ እርምጃዋን ከእሱ እርምጃ ጋር ማስተካከል ቻለች....ዝም ብሎ መራመድን ቀጥሏል"ማኪያቶ ልጋብዝህ›› አለችው ..ሀሳብ ድንገት ነው የመጣላት፡፡
"አይ ማኪያቶ አልወድም...አሁን ጂን ነው ምጠጣው"
‹‹ጥሩ ሀሳብ ነው.. እንደውም እኔም እሱን ብጠጣ ጥሩ ይመስለኛል።››
"ጥሩ"
"መኪናዬን ግን ፊታችን ያለው ሆቴል ነው ያቆምኩት… እዛ ብንጠጣ ቅር ይልሀል..?."ዝም ብሎ አቅጣጫውን ወደነገረችው ሆቴል አስተካከለ።ያ ማለት በሀሳቧ መስማማቱን ማሳያ አድራጋ ወሰደችውና ተከተለችው፡፡እንደዛው ጎን ለጎን እየተራመዱ ምንም ሳያነጋገሩ ሆቴል ደረሱ.. በፅድ ተክሎች የተከበች ከለል ያለች ቦታ መርጠው ተቀመጡ የሚቀመጡበትንም ቦታ የመረጠችው እሷ ነች..)እሱ ለመጠጡ እንጂ ለቦታው ግድም ያለው አይመስልም፡፡
"ስለደረሰብህ ሀዘን በጣም አዝናለሁ››አለችው ፈራ ተባ እያለች፡፡
የእሷን አስተያየት ችላ አለና"አባትሽ ናቸው?"ሲል ጠየቃት…ደነገጠች
"ምን? ማን?"
"ቀብሩን ነው ያልኩሽ"
"እ...የእጮኛዬ አባት ናቸው...ማለቴ የፍቅረኛዬ... ማለቴ የማፈቀረው ልጅ አባት"
"በአንድ ፅኚ እንጂ..የምን መወነባበድ ነው?"
"ወድጄ ይመስልሀል"
"የት ነው"
"ማ ?"
"እሱ...የምታፈቅሪው ልጅ"
"ገዳም ገባ"
መልሷን ከሰማ በኃላ ያዝንልኝና ያፅናናኛል ብላ ስትጠብቅ
‹‹ተገላገለ" ብሎ እርፍ።
"እንዴት እንደዛ ልትል ቻልክ?"
"ያው አንድ ቀን ልቡን ሰብረሺው ስቃይ ውስጥ ከሚገባ እንዲ በደህናው ጊዜ ገዳም መግባቱ ይሻለዋል"
"እንዴት ልቡን ልሰበር እችላለሁ ከራሴ በላይ እኮ ነው የማፈቅረው"
"እዛ የተኛችው ማለት ቅድም አበባ የሠጠሻት ሴትም ከአመታት በፊት እንዲሁ አንቺ ያልሺውን ቃል መቁጠር ከምችለው ጊዜ በላይ ብላኝ ነበር"
"ታዲያ ምን ተፈጠረ?"
"ያው እንዳልኩሽ ነዋ የልብ መሠበር"
"ሁሉም ታሪኮች ፍፃሜያቸው እንደምታስበው አይደሉም"
"ናቸው..ቆይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ?"
"ጠይቀኝ"
"አሁን ጥሎሽ ገዳም ከገባው ልጅ በፊት ፍቅረኛ ነበረሽ"
"አዎ ነበረኝ"
"ታፈቅሪው ነበር?"
"በወቅቱ አዎ አፈቅረው ነበር"
"ጥሩ ...እንደምታፈቅሪውስ ነግረሽው አታውቂም"
"በወቅቱማ እንዴት አልነግረው ...ፍቅረኛዬ ነበር...እንደማፈቅረው ብዙ ጊዜ ነግሬው አውቃለሁ።"
"በቃ መልሴ ተመልሶልኛል"
ድንግርግሯ ወጣ ።ምን ለማለት እንደፈለገ ምንም አልገባትም።
‹‹የምኑ መልስ?"
"ያው መጨረሻውን አየሽው߹ ከዛ ፍቅረኛሽ ጋር አሁን አብረሽ የለሽም...የሌላ ወንድ ፍቅር ፍለጋ በየመቃብር ሀውልቱ ትዞሪያለሽ ߹ያ ፍቅረኛሽ ግን ምን እየተሠማው እንደሆነ ምን ያህል እንዳዘነ ?በምን ያህል መጠን እየናፈቅሽው እንደሆነ ?ምንም ትዝ ብሎሽ አያውቅም አይደል?።"
ለወንዶች ያለው ውግንናና ለሴቶች ያለው ጥላቻ ጠርዝ የወጣ ነው ብላ ስላሰበች አበሳጫት።
"ምን እያልክ ነው..?ቺት ስላረገብኝ እኮ ነው የተለያየነው"
"እ እንደዛ ነው?" አለና ጅኑን አንስቶ ተጋተው
‹‹ምነው? በቂ ምክንያት አይደለም?"
"ለወንድ አዎ .ለሴት ግን አይደለም"
"አልገባኝም?
"ሴት መጀመሪያውኑ ለመለየት አቀባብለ እየጠበቀች ካልሆነ በስተቀር ፍቅረኛዋ ችት ስላደረገባት ብቻ አታባርረውም"
ዝም አለች። ይሄ የአስፈሪው እንግዳ ሰው ንግግር ለሌሎች ሴቶች ይስራ አይስራ ባታውቅም እሷን በተመለከተ ዝንፈት የለበትም...እናም ገፍታ ልትከራከረው አቅም አላገኘችም።ለተወሰነ ደቂቆች በዝምታ እያሰላሠለች ጅኑን መሳብ ጀመረች።ድንዝዝ እንዲላት ፈልጋለች። ለዛሬም ቢሆን እንኳን ሁሉን ነገር መርሳት።
"እስቲ ስለራስህ ንገረኝ...ስለእሷ...አበሳጭታህ ስለሞተችው ሴት"
‹‹እርግጠኛ ነሽ መስማት ትፈልጊያሽ?››
‹‹አዎ በደንብ›› አለችና ለመስማት አቆብቆበች….አቀማመጧን አስተካከለች…ማውራት ጀመረ
‹‹የሶስት አመት ፍቅረኛና የአራት አመት ባለቤቴ ነች፡፡ከባለጉዳይ ጋር ስዳረቅ እና ከሀለቃዬ ጋር ስጨቃጨቅ ቆይቼ በድካም ውልቅልቅ ብዬ ወደ ቤቴ ስመጣ በገዛ አልጋዬ ላይ ከገዛ ጓደኛዬ ጋር ተኝታ ደረስኩ።ከመተኛቷ በላይ ያበሳጨኝ ከእኔ ጋር ስትተኛ ሰምቼው የማላውቀውን በደስታ የመቃተት ድምፅ መስማቴ ነው። የወሲብ ፊልም አክተሮች እራሱ እሷ እያለከለከች እንዳለው አያለከልኩም። ለማንኛውም በአፍላ ስሜት ነቅናቂ ሙዚቃ በታጀበ ተራክቦ ላይ እያሉ ደረስኩባቸው።
እሱ በመስኮት ዘሎ ፈረጠጠ..እሷን ያዝኳት..።

👍84❤6😁2👏1
#ተአምረተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_አርባ_አንድ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//
በ25ኛው ቀን ጥዋት ቁርስ ከበሉ በኃላ
‹‹ዛሬማታ ልሄድ ነው››
‹‹የት ነው የምትሄደው…..?››ደንገጥ ብላ ጠየቀችው ሰሚራ
‹‹ከከተማ ወጣ ብዬ ትንሽ ራቅ ብዬ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ማሰብ እፈልጋለሁ….››
‹‹ስለምንድነው የምታስበው..…..?ክፉ ነገር አይደለም አይደል…..?››
‹‹እኔ እንጃ …ለጊዜው ምንም የመጣልኝ ነገረ የለም..እንደገደሉኝ ልግደላቸው…ወይስ ይቅር ልበላቸው …..?የማውቀው ነገር የለም…ገንዘቤን ግን ልጅነቴን የሰዋሁበትና ብዙ ፈተና ያየሁበት ስለሆነ ሰባራ ሳንቲም እንደማልተውላቸው እርግጠኛ ነኝ..ምን አልባት እስከዛው በደንብ ቢደሰቱበት ጥሩ ነው››
‹‹እንዴት አድርገህ ታስመልሳቸዋለህ……..?አሁን እኮ ንብረትህ በእነሱ እጅ ነው..በህይወት መኖርህን ካወቁ ባለ በሌለ ኃይላቸው ነው አሳደው የሚያስገድሉህ››
‹‹አይዞሽ አታስቢ… እጠነቀቃለሁ….ለዛም ነው ከዚህ ከተማ ራቅ ብዬ በጽሞና ምን ማድረግ እንደምችል ማሰብ አለብኝ የምልሽ››
‹‹ካልክ እሺ ..ቆይ መጣሁ›› ብላ ከነበሩበት ሳሎን ተነስታ ወደመኝታ ቤቷ ከሄደች ከ5 ደቂቃ በኃላ ተመልሳ መጣችና ቼክ እጁ ላይ አስቀመጠችለት፣..ግራ ገብቶት አንዴ የሰጠችውን ቼክ አንዴ ደግሞ እሷን በማፈራረቅና በመገረም ሲያያት ከቆየ በኃላ
‹‹ምንድነው ይሄ…..?››ጠየቃት
‹‹የራስህ ብር ነው..አንተን እንድገድልላቸው የከፈሉኝ ነው…ሁኔታዎችን እስቲስተካከሉልህ ለመንቀሳቀሻ ይሆንሀል››
‹እንዴ ምን አይነት ሰው ነሽ….?እንዲህ አይነት ሰው እኮ በዚህ ጊዜ አይገኝም››
‹‹አይ እንደምታስበኝ ደግ ሴት ሆኜ አይደለም..ለአንተ ብቻ ነው እንዲህ የሆንኩት..››
በንግግሯ ውስጡ ተነካና‹‹ለእኔ ለምን…..?››ጠየቃት
‹‹እኔ እንጃ….. ›አለችው
..ከተቀመጠበት ተነሳና ስሯ ተንበረከከ..ደነገጠች፡፡ አቀፋት …አንገቷ ሰር ገብቶ ሳማት…. ውርርር አደረጋት፣..አላቆመም… ወደታች አስጎንብሶ ግንባሯን …አይኖቾን… ጉንጮቾን በመጨረሻ ከንፈሯ ላይ ተጣበቀባት…አይኗን ከመጨፈን እና ከንፎሯን ከማነቃነቅ ውጭ ምንም ተቃውሞ አላሰማችም…ደስ የሚሉ እልፍ መሰል ሁለት ደቂቆች አለፉ….
የሚያደርገውን አድርጎ ከተቀመጠበት ተነስቶ ሲቆም እሷ አፍራ አቀረቀረች…
የሰጠችውን ቼክ መልሶ ጉልበቷ ላይ እያስቀመጠላት..ይሄ ምን አልባት እኔን ለገደልሽበት ቢከፍሉሽም.. አንቺ ግን እኔን ለማዳን ለህክምና ይሄን ቤት ለመከራየት ላወጣሽው ወጪ መሸፈኛ ይሁንሽ…ውለታሽ ግን በዚህ ብር የሚመለስ ወይም የሚጣጣ ፍጽም አይደለም…በሕወቴም ጭምር ከፍዬ አልጨርሰውም››
‹‹ህይወትህን ስፈልግ ያኔ ትከፍለኛለህ …አሁን ግን ከእኔ ይልቅ አንተ ነህ ችግር ላይ ያለህው … ደግሞ ከራሴ ገንዘብ ምንም ያወጣሁት ነገር የለም…ከዚህ በተጫማሪ መቶ ሺ ብር ቦነስ ብለው ሰጥተውኝ ነበር…እርግጥ ከላዩ ላይ አንተን ለማሸሽ እና የሬሳ ሳጥኑን ቀይረው ለሰጡኝ አቶ ተካ 50 ሺ ብር ከፍያለሁ..ሌላውን 50 ሺብር ደግሞ እስከአሁን እየተጠቀምኩበት ነው ፡፡››
‹‹አይዞሽ ለእኔ አትስቢ አልኩሽ እኮ …እነሱም ሆነ ማንም የማያውቀው 5 ሚሊዬን ብር ባንክ አለኝ…..በዛ እጠቀማለሁ፡፡››
‹‹ግን ባረብሽህ ምትሄድበት ይዘህኝ ብትሄድ …..?››
‹‹አረ ደስ ይለኛል..ስራሽን ብዬ እኮ ነው…..?››
‹‹ስራው ይደርሳል››
‹‹በያ ተዘጋጂ….መኪና እንከራይ ››
‹‹ወደየት ነው ግን ምንሄደው…..?››
‹‹እግራችን ወደመራን….››
✨ይቀጥላል✨

👍112❤10👎5👏2
#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_አርባ_አንድ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ዶ/ር ሶፊያ ግማሽ ልቧን ታዲዬስ ጋር ጥላ እሩብ ልቧን ወደ ትንግርት ልካ በሩብ ልቧ ነው ከሀዋሳ ተመልሳ ቤቷ የደረሰችው፡፡የሳሎኑን በር ከፍታ ስትገባ ፕሮፌሰር ዬሴፍ ሶፋ ላይ ጋደም ብሎ ፊልም እየተመለከተ ነበር፡፡ እንደገባች በፍቅር እና በመፍቀለቅለቅ ተጠመጠመባት ..ከንፈሯን ሳመት…ዝም ብላ ሳትስመው ተሳመችለት፡፡ ሰላምታውን ከጨረሱ በኃላ የፊቷን መገባበጥ ሲመከት በጣም ደነገጠ ‹‹እንዴ ቤቢ.… ምንድነው ይሄ.....? ምን አጋጠመሽ?::<<
‹‹ትንሽ የመኪና ግጭት ነው፡፡››ዋሸችው፡፡
‹‹ታዲያ ተረፍሽ..…?››
‹‹አዎ ቀላል ግጭት እኮ ነው ..ግን አንተ እንዴት መጣህ?››
‹‹አንቺ ጋር ነዋ፡፡››
‹‹እሱማ በስልክ ነገርከኝ ...ማለቴ እንምትመጣ አልገርከኝም ብዬ ነው?››
‹‹ሰርፕራይዝ ላደርግሽ ፈልጌ ነዋ፡፡››
‹‹እብድ እኮ ነህ.....ሰው እንኳን ከአሜሪካ ከደብረዘይት ሲመጣ ይናገራል…፡፡››
‹‹ልጅቷስ የት ሄደች ?››አለችው..ከመጣች ሰራተኛዋን ስላላየቻት ግራ ተጋብታ፡፡
‹‹አለች ..ቢራ እንድትገዛልኝ ልኬያት ነው፡፡››
‹‹ፍሪጅ ውስጥ የለም እንዴ?››
‹‹ጨረስኩታ... ከመጣው እኮ ሶስት ቀን ሆነኝ፡፡››
‹‹እስቲ መጣው በጣም ሞቆኛል... ሰውነቴን ለቅለቅ ልበል››አለችና ከተቀመጠችበት ተነስታ ወለሉ ላይ አስቀምጣ የነበረውን ሻንጣዋን እየጎተተች ወደ መኝታ ቤት ገባች፡፡
ዬሴፍ ከኃላዋ መላ አቋሟን እና የሚሞናደለውን መቀመጫዋን በአትኩሮት ተመልክቶ‹‹አማላይ ነሽ….›አለና ምራቁን ዋጠ፡፡ በእድለኝነቱም አምላኩን አመሰገነ፡፡ በአንድ ወር ውስጥ ደስ በሚል ሁኔታ ድል ባለ ሰርግ ያገባትና መልሶ ወደአሜሪካ ይዟት ይሄዳል..ወደአሜሪካ የመሄዱን ሀሳብ አልቀበልም ብትለው እንኳን ከእሷ የሚበልጥበት ነገር ስለሌለ እሱ ጓዙን ጠቅልሎ ወደ ሀገር ውስጥ ተመልሶ ከእሷ ጋር ይኖራል ..፡፡አሁን በሱ ህይወት የጎደለችው እሷ ብቻ ነች፡፡የሚፈልገውን አይነት ትምህርት ተምሯል፣የሚፈልገውን ዓይነት ስራ እየሰራ ነው፣የሚፈልገውን ያህል ገንዘብ አጠራቅሟል፣በዚህ ሁሉ ስኬት ላይ ሶፊን ማግባት ከቻለ…እሷ ደግሞ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ልጅ ከወለደችለት ..በቃ በዚህ ምድር ላይ ከእሱ በላይ ዕድለኛ ሰው ከየት ይገኛል?፡፡
ሶፊ መኝታ ቤቷ እንደገባች በቁሟ ነበር አልጋዋ ላይ የተዘረረችው፡፡የሶስት ዓመት
ፍቅረኛዋ በእሷ ትልቅ ተስፋ አድርጎ ውቅያኖስ ተሻግሮ በመምጣት ሳሎኗ ውስጥ ይገኛል፡፡ እሷ ግን በአካል ስታገኘው ውስጧን ደስታ አልተሰማትም…እንደውም በተቃራኒው የቅሬታና የመረበሽ ስሜት ነው በደም ስሯጰየተሰራጨው..በውስጧ የተፈጠረውን ስሜት ልትቆጣጠረው የምትችለው ዓይነት አይደለም፡፡ብቻ ውስጧ በነውጥ እየተናጋ ነው፡፡በልቧ ኃይለኛ ወጀብ ሲደበላለቅ ይሰማታል፡፡ከሚጡ ፣ከሰላም፣ ከሄለን ፣ከሀሊማ እና ከሙሴ ጀርባ የታዲዬስ ምስል በትልቁ ይታያታል፤ፅዬን ደግሞ እሱ ጭንቅላት ላይ ጉብ ብላ ስትደባብሰው.. በውስጧ የተፈጠረው ብስጭት ጭንቅላቷን አቃጠላት፤ከእዛ ሀሳብ ስትሸሽ ደግሞ ትንግርት ተቀበለቻት...ተፈናጥራ ከመኝታዋ ተነሳችና ልብሷን በማወላለቅ ወለሉ ላይ አዝረክርካ ወደ ሻወር አመራች ..የሰውነቷን ሙቀት ብቻ ሳይሆን በአዕምሮዋ የሚተረማመስ ሀሳብ ለማቀዝቀዝ፡፡
ፀጉሯን በላስቲክ ሸፍና ቧንቧውን ከፈተች፤ውሀው ካላይ እየተንፎለፎለ ሰውነቷን ሲያረጥበው ቀስ በቀስ የጋለው ገላዋን አቀዘቀዘላት..ያም ብቻ ሳይሆን የተረበሸ መንፈሷም እየተረጋጋላት መጣ፡፡ በመሀከል ‹‹ቤቢ..ቤብ››የሚለው የፕሮፌሰር ዬሴፍ የጥሪ ድምፅ ከነበረችበት የተመስጦ ድባብ አናጠባት፡፡
‹‹...ቤቢ አልጨረሽም እንዴ?››እያለ መኝታ ቤቱን አልፎ ወደ ሻወር ቤቱ ተጠጋ፡፡
እዛው እንዲጠብቃት በሚፈልግ ስሜት ‹‹ጨርሼያለሁ ...መጣሁ›› አለችው፡፡ እሱ ግን የሻወር ቤቱን መዝጊያ ገፋ አደረገና አንገቱን ወደውስጥ አሰገገ....ዕርቃን ሰውነቷን ሲያይ በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደተመለከታት ሁሉ ድንዝዝ በሚያደርግ ስሜት ተውጦ የፈጠጡ ዓይኖቹን እንደተከለባት ለደቂቃዎች ቆመ…፡፡ እሷን ግን ከበዳት፤ ለማታውቀው መንገደኛ ሰው ዕርቃን ሰውነቷን ያሰጣች መሰላት..የተቀሰሩት ጡቶቿን በእጆቿ ሸፈነቻቸው፡፡
‹‹ዬሲ መጣሁ አልኩህ እኮ..!! ሳሎን ጠብቀኝ››ሳታስበው እንደመቆጣት አለች፡፡
‹‹ሶሪ.…››አለና ከደነዘዘበት በመከራ ነቅቶ በራፉን ዘጋላትና በፍቅረኛው ያልተለመደ ሁኔታ ግራ እየተጋባ ወደ ሳሎን ተመለሰ..በፊት ቢሆን ጎትታ ነበር ወደ ውስጥ ምታስገባው.፡፡
.‹‹አይ ጥሩ ስሜት ላይ ስላልሆነች ይሆናል፡፡››ሲል እራሱን አፅናና፡፡
ሁሉን ነገር ጨርሳ ቢጃማዋን ለብሳ ሳሎን ስትመለስ...ሰራተኛዋ ሲኒ ደርድራ ቡና እየቆላች ነበር፡፡ ዬሴፍ ደግሞ እንደበፊቱ ሶፋው ላይ ጋደም ብሎ ቢራውን ይጐነጫል፡፡
‹‹ቤቢ መጣሽ..?›› አለት..ዩሴፍ በፊት
ከኢትጵያ ወደ አሜሪካ ሄዶ ከሶፊያ ጋር በተገናኙ እና ፍቅር በጀመሩበት ጊዜ ‹እናት› ብሎ ነበር የሚጠራት ...እናቴን ትመስያለሽ ለማለት..ከዓመታት በኃላ ግን አገሩን ሲላመድ እና የፈረንጆቹ ባህሪ ሲጋባበት..እናትን እረሳውና በቤቢ ቀየረው…ምሁራዊ የባህል ዕድገት …፡፡
‹‹አዎ ፡፡ >>አለችውና ከእሱ ፈንጠር ብላ ተቀመጠች፡፡
‹‹ቢራ ይከፈትልሽ ቤብ?››
‹‹አይ ይቅርብኝ ..ቡና ነው ያሰኘኝ፡፡››
‹‹እራት ቀርቦ በልተው የተፈላውን ቡና ጠጥተው አጠናቀቁና ተያይዘው ወደ መኝታ ቤት ገቡ፡፡ዮሴፍ ለ7 ወራት ያላገኘው ... በጣም የናፈቀውን ገላ ዳግም የሚያጣጥምበት ሰከንድ መቅረቡን ሲያስብ ውስጡ በደስታ ተጥለቀለቀ….የሰውነቱ ግለትም ለራሱ ተሰማው፡፡ከሁሉም በፊት ግን ያመጣላትን ስጦታ ሊያበረከትላት ፈለገ ፡፡
መኝታ ቤት አስገብቶ ካስቀመጣቸው 3 ሻንጣዎች ውስጥ ግዙፉን ሻንጣ ከፈተ‹‹ቤብ እነዚህ ልብሷች እና ጫማዎች ያንቺ ናቸው..ከግምቴ ትንሽ ወፈር ብለሽ ነው ያገኘሁሽ ስለዚህ አንዳንዶቹ ሊጠቡሽ ይችላሉ››አላት፡፡
ደስ እንዲለው ለቁጥር ከሚያዳግቱ ልብሶች መካከል አንድ ሶስቱን አንሳችና እንደነገሩ ሞከረች..ግን ውስጧን ደስ አላለውም... ‹ከሚያስፈልግሽ በላይ መሰብሰብ ስግብግብነት ነው፤፤››የሚለው የሰላም ንግግር አእምሮዋን ወቀራት፡፡አይደለም ባላት ላይ ተጨምሮ ይቅርና አሁን ፊት ለፊቷ በሻንጣው የታጨቀው ልብስ ብቻ ለሀያ ሴቶች በደንብ ይበቃል‹‹እውነትም ስግብግብነት…፡፡››አለች ..ሳይታወቃት ድምፅ አውጥታ፡፡
‹‹አናገርሽኝ ቤቢ..?››አላት ያናገረችው መስሎት፡፡
‹‹አይ... ያምራል ማለቴ ነው..ለማኛውም ሌሎቹን ነገ ተረጋግቼ እለካቸዋለሁ... አሁን ደክሞኛል፡፡››
‹‹አንደርእስታንድ አረግሻለሁ....ግን ከመተኛታችን በፊት ሌላ አንድ ነገር ላሳይሽ እፈልጋለሁ››
‹‹ምንድነው ዬሴፍ..አሳየኝ ?›አለችው ፡፡
ሁለተኛውን ሻንጣ ከፈተ..ውስጡ ያለውን አወጣ… በጣም ደነገጠች ‹‹..ምንድነው ?››
‹‹ለሰርጋችን ቀን የምትለብሽው ..ከፓሪስ በትዕዛዝ የተሰራ ልዩ ቬሎ..፡፡››
ሰውነቷ ዝልፍልፍ አለባት.. የምትለውን የምትናገረውን አጣች፡፡ዬሴፍም ግራ ገባው..በፊቷ ላይ ያረበበው ድንጋጤ የደስታ ነው ወይስ የቅሬታ? መለየት አልቻለው…፡፡
‹‹ቤብ..ምነው? ፈዘዝሽ እኮ!!!››
‹‹ይሄንን ከማድረግህ በፊት ልታማክረኝ ይገባ ነበር..እኔና አንተ እኮ ስለፍቅር እንጂ ስለጋብቻ አውርተን አናውቅም፡፡››

👍55❤7