#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
ወጀቡ እስኪጠፋ ወለሉ ላይ ተቃቅፈው ቆዩና ‹‹መርቪን አልጋው ላይ
እንውጣ ከወለሉ ይልቅ እዚያ ይመቸናል›› አለ፡
ናንሲ በመስማማት ራሷን ነቀነቀች፡፡ ከዚያም በጉልበቷ እየዳኸች
አልጋው ላይ ወጣች፡፡ መርቪንም ተከተላትና አልጋው ላይ አብሯት ወጣ፡፡
እሱም እቅፍ አድርጎ ያዛት፡፡
በወጀቡ ምክንያት አይሮፕላኑ በተናወጠ ቁጥር ልክ መርከበኛ የጀልባ
ውን ምሰሶ እንደሚይዝ ሁሉ ናንሲ መርቪንን ጭምቅ አድርጋ ትይዛለች፡፡
ወጀቡ ሲቀንስና ዘና ስትል እሱም ሰውነቷን በፍቅር ይነካካቸዋል ከዚያ ትንሽ ቆየችና እንቅልፍ ይዟት ሄደ፡፡.
በሩ ተቆርቁሮ «አስተናጋጅ መቷል» የሚል ድምፅ ስትሰማ ከእንቅልፏ ነቃች።
ዓይኖቿን ስትከፍታቸው መርቪን ደረት ላይ መተኛቷን አወቀች
‹ወይ አምላኬ! አለች እየተርበተበተች፡
መርቪን ከተኛችበት እንድትነሳ በእጁ ገፋ አደረጋትና ‹‹ትንሽ ጠብቀን
አስተናጋጅ›› አለ፡፡
ከበሩ ውጭ የቆመው አስተናጋጅ በተደናገጠ ድምፅ እሺ ጌታዬ
እጠብቃለሁ›› አለ፡፡
መርቪን ከአልጋው ወረደና በአልጋ ልብስ ናንሲን ሸፈናት::
በዚህ አድራጎቱ በሆዷ አመሰገነችው፡፡ አስተናጋጁ እንዳያያት ፊቷን ወደ ግድግዳው አዞረች፡፡
መርቪን በሩን ሲከፍት አስተናጋጁ ገባና ‹‹እንዴት አደራችሁ›› አለ በፈገግታ፡፡
የትኩስ ቡና መዓዛ ናንሲን አወዳት፡፡ ‹‹በእንግሊዝ የሰዓት አቆጣጠር
የሶስት ሰዓት ተኩል ወደ ኋላ ነው ማለት ነው?›› አለ አስተናጋጁን
‹‹ልክ ነው ጌታዬ የኒውፋውንድ ላንድ የሰዓት አቆጣጠር ከግሪንዊች
የሰዓት አቆጣጠር ሶስት ሰዓት ተኩል ወደ ኋላ ይዘገያል፡››
‹‹መቼም የአየር መንገዶችን የጉዞ መርሃ ግብር ለሚያዘጋጁ ሰዎች ይህ የሰዓት አቆጣጠር ችግር
ሳይፈጥርባቸው አይቀርም፡፡ ባህር ላይ ለማረፍ ምን
ያህል ሰዓት ይቀረናል?›› ሲል ጠየቀ መርቪን
‹‹ከግማሽ ሰዓት በኋላ እናርፋለን፡ ከመርሃ ግብሩ አንድ ሰዓት ጉዟችን
የዘገየው በወጀቡ ምክንያት ነው›› አለና አስተናጋጁ በሩን ዘግቶ ወጣ፡
ናንሲ በሩ ከተዘጋ በኋላ ‹የመስኮቱን መጋረጃ ክፈተው፡ ነግቷል››
አለችው:፡ መርቪን ቡና ሲቀዳ የትናንት ምሽት አዳራቸው ፊቱ ላይ መጥቶ
ድቅን አለ፡፡ ወጀቡ በተነሳ ቁጥር መርቪን እጇን የሚይዛት፣ ወለሉ ላይ
የሚወድቁት፣ የመርቪን እጆች ጡቶቿን ሲጨብጥ፣ አይሮፕላኑ ሲናወጥ፣
እሱ ደረት ላይ ልጥፍ የምትለውና እየደባበሰ የሚያስተኛት ትዝ አላት:
ይህን ሰው በጣም ወድጄዋለሁ› አለች በሆዷ።
‹‹ቡና እንደወረደ ወይስ ከወተት ጋር ነው የምትፈልጊው?›› ሲል
ጠየቃት፡፡
‹‹ጥቁር ቡና ይሁንልኝ፡ ስኳር አልፈልግም››
‹‹እንደ እኔ›› አለና ቡናዋን አቀበላት ናንሲ አመስግና ቡናዋን ጠጣች፡፡
ናንሲ ስለ መርቪን በደንብ ማወቅ ፈለገች፡፡ ቡናውን እየጠጣ ስለእሱ ልማዶች ግምቷን አስቀመጠች፡፡ ቴኒስ ይጫወታል፣ ልብ ወለድ ብዙ ማንበብ አይወድም፣ ገበያ መሄድም እንደዚሁ፣ ቁማር ጨዋታ የሚሳካለት ይመስላል፣ ዳንስ ግን የሚችል አይመስልም፡፡›
‹‹ምንድን ነው የምታውጠነጥኚው?›› ሲል
ጠየቀ ለሕይወት ኢንሹራንስ አደገኛ እንደሆንኩ አድርገሽ የምታይኝ መሰለኝ፡፡››
ናንሲ ቀልዱ አሳቃት፡፡ ‹‹ምን አይነት ሙዚቃ ነው የምትወደው?›› ለሙዚቃ ጆሮ አልሰጥም›› አለ ‹‹መደነስ ባልጠላም ጥሩ ደናሽ ግን አይደለሁም፡፡ አንቺስ?››
እኔ ድሮ ደንሼያለሁ፡መደነስም ነበረብኝ፡፡ እሁድ እሁድ ሱፍ ከሚለብሱ ወንዶች ልጆች ጋር በዳንስ ትምህርት ቤት ዳንስ እማር ነበር፡፡ከላይኛው መደብ የቦስተን ማህበረሰቦች ጋር ለመግባባት ብቸኛው መንገድ ይህ ብቻ እንደሆነ እናቴ ትነግረኝ ነበር፡ እኔ ግን ከዛ ማህበረሰብ ውስጥ
ብገባ ባልገባ ግድ አልነበረኝም፡: የኔ ቀልብ ያለው ከአባቴ ፋብሪካ ጋር ነው፡፡ እናቴ ደግሞ ይሄን ባህሪዬን አትወደውም ነበር፡››
ሁለቱ አዲስ ፍቅረኛሞች ተያዩ፡፡ መርቪንም ትናንት ማታ እንዴት ሲላፉና ሲላላሱ እንዳመሹ እንደሚያስብ ነቃችበት፡፡ ይህም ሀሳብ እፍረት
ውስጥ ከተታትና ፊቷን ወደ መስኮቱ ስታዞር መሬት ታያት፡፡ አይሮፕላኑ
ቦትውድ ሲያርፍ ህይወቷን የሚለውጠውን የስልክ ጥሪ ማድረግ እንዳለባት ትዝ አላት፡ ‹‹ደርሰናል›› አለችና ከመኝታዋ ዘላ ተነሳች ‹‹ልብሴን ልልበስ›› አለች፡፡
‹‹እኔ ቀድሜ ልውጣ›› አለ መርቪን ‹‹ለአንቺ ጥሩ ነው››
እሺ፧ አሁንስ ምን ቀልብ አለኝ አለች በሀሳቧ። ይህን ለእሱ አልነገረችውም፡፡ መርቪን ልብሱን ስበሰበ፡፡ በሩን ከፍቶ ሊወጣ ሲል
ተጠራጠረና ቆመ፡፡ እሷም እንደገና ሊስማት እንደፈለገ አውቃ ወደ እሱ ሄደችና ከንፈሯን ሰጠችው፡፡ ‹‹ሌሊቱን በሙሉ እቅፍ አድርገህ ስላስተኛኸኝ
አመሰግንሃለሁ›› አለችው:
መርቪን ከአንገቱ ዝቅ አለና ሳማት፡፡ አሳሳሙ ልስልስ ያለ ነበር፡ አፏን በአፉ ግጥም አድርጎ ነው የሳማት፡፡ እየተሳሳሙ ትንሽ ቆዩና ተላቀቁ፡፡
ናንሲ በሩን ከፍታ ያዘችለትና ወጥቶ ሄደ፡፡
በሩን እንደዘጋች የደስታ ሲቃ ተናነቃት፡ ከዚህ ሰው ፍቅር ሊይዘኝ ነው አለች፡ በመስኮቱ ስታማትር አይሮፕላኑ ቀስ በቀስ እየወረደ ነው፡፡
መፍጠን አለባት፡፡
መስታወቱ ፊት ቆማ ፀጉሯን ቶሎ አሰረችና የመዋቢያ ዕቃዎቿን ይዛ የሙሽሮቹ ክፍል አጠገብ ወደሚገኘው ወደ ሴቶች መታጠቢያ ቤት ሄደች፡፡እዚያ ሉሉ ቤልንና አንድ ሌላ ሴት አገኘች፡፡ የመርቪን ሚስት ግን የለችም:
ናንሲ ፊቷን እየታጠበች ጧት ከመርቪን ጋር ያደረገችውን ውይይት
አስታወሰች፡፡ እሱን ስታስብ ደስታ ቢሰማትም ደስታው የተሟላ ባለመሆኑ
ከጭንቀት ሊገላግላት አልቻለም፡፡ ስለሚስቱ ምንም አላለም፡፡ ትናንት ማታ ስለእሷ ስትጠይቀው ድንግርግር እንዳለው ነው የነገራት፡፡ ከዚያ በኋላ ግን
ይወዳት ይሆን? ትናንት ማታ ሌሊቱን ሙሉ ደረቱ ላይ ለጥፎ ነው ያሳደራት ይህ ብቻውን ጋብቻን ይፍቃል ማለት ግን አይደለም፡
እኔ የምፈልገው ምንድን ነው? ስትል ራሷን ጠየቀች፡፡ ‹መርቪንን እንደገና ማግኘት እፈልጋለሁ ከእሱ ጋር ድብቅ ወዳጅነት ልመስርት?ታዲያ ለኔ ብሎ ጋብቻውን እንዲያፈርስ እፈልጋለሁ? ከአንድ ሌሊት
ወሲባዊ ልፊያና መሳሳም በኋላ ይህን እንዴት ማወቅ እችላለሁ?
ሊፕስቲክ ለመቀባት መስታወቱ ላይ አፈጠጠች ናንሲ መጠራጠርሽን አቁሚ
ስትል ለራሷ አሳሰበች እውነታውን ታውቂዋለሽ፤ ይሄን ሰው በጣም ፈልገሽዋል፧ ከአስር ዓመት ወዲህ እጅሽን የሰጠሸው ለዚህ ሰው ነው፡:
አሁን አርባ አመትሽን ደፍነሻል፡ አሁን ተገቢውን ሰው አግኝተሻል፡ እዚህ
እዚያ መርገጥሽን ትተሽ ይህን ሰው በእጅሽ አድርጊ፡፡›
ሰውነቷ ላይ ሽቶ አርከፈከፈችና ወጣች፡
ስትወጣ ከመታጠቢያ ቤቱ አጠገብ የተቀመጡትን ናት ሪጅዌይና ወንድሟን ፒተርን አገኘቻቸው ናት ‹‹ደህና አደርሽ ናንሲ›› አላት::
ይህን ስትሰማ ከአምስት ዓመት በፊት በዚህ ሰው የነበራትን ስሜት
አስታወሳት፡፡ እኔ ከእሱ ፍቅር ይዞኝ ነበር፡፡ እሱ ግን ከእኔ ይልቅ የፈለገው
ብላክ ቡትስ ኩባንያን ነበር፡፡ አሁንም ኩባንያውን በእጁ ለማስገባት
የሚፈልገውን ያህል እኔን አይፈልገኝም፡፡ ለሰላምታው በራስ ንቅናቄ ብቻ
አፀፋዊ ሰላምታ ሰጥታው ወደ ክፍሏ ሄደች፡፡
አስተናጋጆቹ መኝታዎቹን ወደ ሶፋነት ለውጠዋቸዋል። መርቪን ጢሙን ተላጭቶና በነጭ ሽሚዝ ላይ ሱፍ ልብሱን ለብሶ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሏል፡፡ ‹‹በመስኮት ተመልከች ደርሰናል›› አላት፡፡

👍19
#ባል_አስይዞ_ቁማር
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
..ይገርማል እሱ በማንኛውም አእምሮዋ በሚያመርታቸው ሀሳቦች ውስጥ የሆነ ቦታ ፈልጎ ተሸንቅሮ ሲወጣ ነው የምታየው....ስለሰማይም ታስብ ስለምድር…ስለእግዚያብሄር ይሁን ስለሰይጣን እሱ አለበት….፡፡.ደግሞ በሀሳቧ ብቻ አይደለም በህልሟም ጭምር እንጂ…..ህልሟ እኮ ስለ ምንም ሊሆን ይችላል ብቻ እሱ አለበት…ለምሳሌ እሷ እናቷ መኝታ ቤት አልጋዋ ላይ ወጥታ ፀጉሯን ስትዳብሳት በህልሟ ብታይ እሱም ወይ በመስኮት ተደብቆ ሲያያት..ወይ ደግሞ እራሱን ወደቢራቢሮ ቀይሮ ክንፉን እያማታ መጥቶ ግንባራ ላይ ሲያርፍ ታየዋለች፡፡ይሄ ሁሌ ለራሷም ሳታስበው ግርም ይላታል፡፡እንዴት የሆነ ቦታ ላይ አትረሳውም…እንዴት የሆነ ሀሳብ አሰናድታ አጣጥፋ ስትጨርስ ድንገት ከሆነ ቦታ ተስፈንጥሮ መጥቶ ከላይ በቀላሉ ይደረባል…?ይሄ እንግዲህ በዚህ ከተማ በዚህ ቤት ውስጥ ሲኖር ነበር..አሁንስ ሁሉን ነገር ጣጥሎ ከሄደ በኃላ…….ምንድነው የምትሆነው?የቀንም ሆነ የሌት ህልሟ እንደሆነ ይቀጥላል? ከቀጠለስ እንዴት ልትቋቋመው ትችላለች?
እጇን ዘረጋችና አጠገቧ የተኛችውን የጊፊቲ ሆድ ላይ በቀስታ አሳረፈች…ጊፍቲም ከትራሷ ገልበጥ አለችና ፊቷን ወደእሷ ዞራ በሀዘኔታ አየቻት፡፡
‹‹ምን አለ እኔም እንደአንቺ ለቃልዬ አርግዤ ቢሆን…ማለት ልጅ አስረግዞኝ ጥሎልኝ ቢሄድ?››
‹‹እኔም አንድ ነገር ልንገርሽ…››
‹‹ምንድነው ንገሪኝ››
‹የቃልዬን እስከ ወዲያኛው ጥሎኝ መሄድን ስሰማ ወደውስጤ ከመጣው የፀፀት ሀሳብ አንዱ ምን አለ ይሄ የፀነስኩት ልጅ የቃልዬ በሆነ የሚል ነበር..እርግጥ መድህኔ በጣም ጥሩ ኃላፊነት የሚሰማው መልካም አባት እንደሚሆን አውቃለሁ…እሱን ስላገኘሁም እራሴን እንደእድለኛ ነው የምቆጥረው…የልጅነት ህልሜንና የዘመናት ፍላጎቴን ሁሉ ሊያሞላልኝ የሚችል ሰው ነው…ግን መድህኔን የማፈቅርበት ጥልቀት የኩሬ ያህል ሲሆን የቃልዬ ግን ውቅያኖስ አይነት ነው..እና ለዛ ነው እንደዛ ልመኝ የቻልኩት››
ዝም ብዬ ፈዛ አየቻት..ይሄን የተናገረችው ከቀናቶች በፊት በሰላሙ ጊዜ ቢሆን ኖሮ በርግጠኝነት ልዩ አንገቷን ፈጥርቃት ልትገላት ሁሉ ትችል ነበር..አሁን ግን ያንን ማድረጉም ብቻ ሳይሆን እንደዛ አይነት ስሜት ማስተናገዱም ጥቅም አልባ እንደሆነ ተረድታለች....በዛ ለይ በመንፈስም ሆነ በስጋዋ ደንዝዛለች…
‹‹ግን ከቃልዬ ይሄን ሁሉ አመት ሳታረግዤ እንዴት በዚህች በጥቂት ወራት ከመድህኔ ልታረግዢ ቻልሽ?፡፡››
‹‹ከቀል ጋር በትንፋሽ ነው ማረግዘው?…››
‹‹ማለት….?››
‹‹እኔና ቃል እኮ ወሲብ ፈፅመን አናውቅም››
‹‹ማለት…ብዙ ቀን እኮ እሱ ጋር አድረሽ እንደወጣሽ… ሲያደክመኝ እንዳደረ ምናምን እያልሽ ስትጎሪርብኝ ነበር››
‹‹ፈርቼሽ ነዋ…..ቃልዬን እንዳትመኚውና እንዳትቀሚኝ ..ተስፋ ላስቆርጥሽ ብዬ ነው…ማለት ከአመታት በፊት አብሬው ብዙ ጊዜ አድር ነበር..በኃላ ግን ዝም ብሎ ማደሩ ስቃይ ስለሆነብኝ ወስኜ አቆምኩ…..››
‹‹አረ የምን ጉድ ነው..ቆይ ለምን…..?››
‹‹ምነው ገረመሽ..አንቺስ ከመድህኔ ጋር ለምን;?››
‹‹እኔ እንጃ ብቻ የእናንተን በጣም ደጋግሜ ስላመነዠግኩት ነው መሰለኝ አልተዋጠልኝም…››
‹‹መድህኔን ስለወደድኩት..ወይም ቃልዬ ሀብታም ስላልሆነ ይመስልሻል ከቃልዬ ጋር አቋርጬ ከመድህኔ ጋር የሆንኩት ነው ወይስ አንቺ ስላለስፈራራሺኝ…?››
‹‹እና ለምንድነው?››
‹‹ሳላውቅ ድንገት ከመድህኔ ጋር ተሳሳትኩና ወሲብ ፈፀምኩ..ድንግልናዬን አስረከብኩት ….ወደቃልዬ ጋር እንዴት ልመሰለስ .. ?ሌላ ሰው ቢሆን ችግር የለውም ቃልዬ ግን?
‹‹ቃል ምን ይልሻል..?ምንም አይልሽም እኮ ነበር አንደውም በግልፅ ነበር ይቅርታ የጠየቀሽ፡››
‹‹አውቃለሁ ..ችግሩም እሱ ነው….እኔ በአእምሮው ካለሁበት ቦታ ተንሸራትቼ ወርጄያለሁ.ቃልዬ...የወርቅ ካባ አድርጎ በብር የተለበጠ ጫማ ተጫምቶ ወደቤቴ ሲመጣ ውስጤ በሀሤት ትደንሳለች ...ድንግልናዬን በክብር ልሰጠው ለዘመናት ጎጉቼያለሁ ።.እሱ ፍጽም ድንግል እንደሆነ አውቃለሁ.....ማወራሽ ስለስጋዊ ድንግልና አይደለም….ለዛ ግድ የለኝም...ልብ ከቆሻሻ ሀሳብ ጋር ያልተዋሰበ ንፅህ ፤ከክደትና ከማጭበርበር ጋር ያልተጋደመ ክብር ነው ።ለዚህም ማረጋገጫው እስሬ ሆኖ ሲያወራኝ ልቤ ውስጥ ብርሀን ሲፍለቀለቅ ይታወቅኛል….የሆነ አካሉ የሰውነቴን ጫፍ ሲነካው ነፍሴ ድረስ የሚዘልቅ ደስታ ይሰማኛል……ድንገት አግኝቼው ሰላም ሊለኝ ከንፈሩ ጉንጬን በስሱ ሲነካው እንኳን .....ከልቤ የፍቅር ደም ሲንጠባጠብ ይሰማኛል ...
‹‹ከዚህ በፊት ስለእሱ ምን እንደሚሰማኝ ነግሬሽ ነበር …? የእኔን ስሜት እኮ ነው እየነገርሺኝ ያለሽው…››
‹‹አየሽልኝ..ቃልዬ ማለት እንዲህ ነው..ሁለት ሴቶችን ጫፋቸውን ሳይነካ በተመሳሳይ የእብደት በሚመስል ስሜት አንዲያፈቅሩት ማድረግ የሚችል የተለየ ሰው ነው፡፡እሱ ለእኔ መስታወቴ ነው.. ፊት ለፊቴ ተቀምጦ በተመስጦ ሳየው በጥልቀት ርቄ ሄዳለሁ…. እያንዳንዷን የልጅነት ጊዜዬን በምልስት አስታውሳለሁ… ሀዘኔንና ደስታዬን መልሼ አጣጥማለሁ…. እንዴት እንደተሰራው…? የት ጋር ማደግ እንደጀመርኩና? የት ጋር ደግሞ እንደተሰበርኩ? ሁሉ እንዳስታውስ ያደርገኛል…እናም በዛ ምክንያት ቃልዬን ሳገኝ ነፍሴ ሀሴት ታርጋለች…ውስጤ ይፍነከነካል..፡፡ግን ይሄ ስሜት ሁሌ አይደለም የሚያስደስተኝ ..አንዳንዴ ትናንቴ ፈፅሞ የሚያስጠላኝ ጊዜ አለ..አንገቴን ወደኃላ አዙሬ አይኖቼን ትናንቴ ላይ ተክዬ ማሰላሰል የሚያስከትልብኝን ህመም መቋቋም አቅም በማጣበት ጊዜ እሱን ለማግኘት ከራሴ ጋር ትግል እገባለሁ …ምክንያት ፈጥሬ እሸሸዋለሁ….
ግን የሰዓታ ክፍተት እንኳን መቆየት ተስኖኝ ግራ ይሁን ቀኝ ልቤ ላይ ብቻ በማለውቀው ቦታ በሆነ የልቤ ክፍል ብቸኝነት ይለበልበኛል…መለብለብ ብቻም ሳይሆን እብጠትና ጥዝጣዜም አለው…ግን ደግሞ መቻል እስከምችል ደረስ እችለዋለሁ…ለአንድ ወይም ለሁለት ቀን..ከዛ መተንፈስ ሲያቅተኝና ከአቅሜ በላይ ሲሆን ያለምን ማቅማማት ወደ አለበት በርሬ እሄዳለሁ ፡፡ፊቱ እገተራለሁ…የተጨማደደ ፊቱ በደስታ ፀደል ሲፈካ…ተከርችሞ የነበረ ጥርሶቹ ተፈልቅቀው መሳቅ ሲጀምሩ አይና እደሰታለሁ....ተንደርድሬ ሄጄ እንጠለጠልበታለሁ….ያለምንም ቅሬታና ወቀሳ ወደላይ አንጠልጥሎ ልክ እንደእርግብ በአየር ላይ ያንሳፍፈኛል…..እና አሁን ያ የልጅነተ መስታወቴ ነው የተሰነጣጠቀዉ… የትዝታ ድልድዬ ነው ተንዶ የተሰበረው…..ወደትናንቴ ለመሻገር በጣም ይከብደኛል….ግማሽ ሆኜያለሁ
‹እውነትሽን ነው…..አሁን ሳስበው ቢነካንስ ኖሮ…ማለቴ ያው ነካክቶን ጥሎን ሂዶ ቢሆንስ..?››
‹‹እሰከ መጨረሻ ያበቃልን ነበራ…››ብላ መለሰችላት፡፡
‹‹እኔ እኮ አሁንም እስከመጨረሻው ነው ያበቃልኝ…›
‹‹ቆይ ግን ወደ ወሬሽ ልመልስሽና..ቃልዬንም እኮ ከዚህ በፊት ማለቴ አንቺ ከመድሀኔ ጋር ተገናኝተሸ ከመጀመርሽ በፊት ስለሁለታችሁ ግንኙነት ጠይቄው ነበር…››

👍89❤10😁1
#ተአምረተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//
ሰሚራ ለዚህ ሀሳብ ውል ሳታበጅለት ማደር አልፈለገችም….. ቦርሳዋን አንጠልጥላ ተመልሳ ወደስራዋ ቦታ ተመለሰች….መመለሷ ምን እንደሚጠቅማት ለራሷም አልገባትም ..ግን በቃ ተመለሰች..እንደደረሰች ቀጥታ መላኩ ወደተኛበት ክፍል ነበር የገባችው…በሽተኛው የተኛበት ክፍል ውስጥ የተኙ ሌሎች ሶስት ታካሚዎችና እነሱን የሚያስታሙም አስታማሚወች ነበሩ…
ቀጥታ ወደተኛበት አልጋ ተጠግታ አስተዋለችው…አይኖቹ እንደተጨፈኑ ናቸው… ጥቁር ፊቱ ላይ የሰላምና የመረጋጋት መንፈስ አርብቦበታል…በታዋቂ ቀራፂ በጥንቃቄ የተቀረፀ የሚመስለው አፍንጫው ለፊቱ ውበት አጎናጽፎት ትልቅ ግርማ ሞገስ ሆኖታል…የዓይኖቹ ሽፋ ሽፍቶች ድምቅ ያሉና የተለየ ስሜት የሚያጭሩ ሆነው ነው ያገኘቻቸው..
‹‹እንዴ እስከዛሬ ለምን እንደዚህ እትኩሬ አላስተዋልኩትም…..?›› ስትል እራሷን ጠየቀች ….እስከዛሬ ባለ እይታዋማ ከማንኛውም በሽተኛ የተለየ ምንም ነገር አልነበረውም….አሁን ግን ሁኔታዎች ተቀያይሩባት..አሁን ስሩ ቆማ የምታየው ጥቁር ቆንጆ ወጣትን ለመግደል ግማሽ ሚሊዬን ብር ተቀብላለች…ስለዚህ አሁን ለእሷ ዝም ብሎ ሰው አይደለም….‹‹ደግሞ እንዴት አባቱ ነው የሚያምረው ….…..?››አለችና ክፍሉን ለቃ ወጣች …
ወደ ዶክተር እስክንድር ቢሮ …ዶ/ር እስክንድር በእሷ እድሜ ክልል የሚገኝ አስተዋይ ወጣትና ጓደኛዋ ነው ..ይሄንን ነገር በምትፈልገው መጠን ሊረዳት እንደሚችል ያሰበችው እና ሚስጥር ጠባቂ ነው ብላ ያመነችው እሱን ነው፡፡እሱን ብቻ፡፡
ቢሮው ብቻው ቁጭ ብሎ የበሽተኞችን ፋይል እየመረመረ ነበር ያገኘችው….
‹‹እንዴ ወደቤት የሄድሽ መስሎኝ?››
‹‹ሄጄ ነበር››
‹‹ታዲያ ምን ገጠመሽ እና ተመለሽ…?››
‹‹ታአምር ተፈጥሮ››
‹‹እስቲ ቁጭ በይ እና ተአምሩን ንገሪኝ .››
በድካም ስሜት ከፊት ለፊቱ ያለውመን ወንበር ስባ ቁጭ አለች….
‹‹እሺ አጫውቺ……..?ምን ተፈጠረ…..?››
‹‹እንድታግዘኝ ነው የመጣሁት… በጣም እርዳታህን እፈልጋለሁ…››
‹‹አልገባኝም ምንድነው የምረዳሽ…..?››
‹‹ልናግር አይደል››
‹‹እያዳመጥኩሽ ነው››አላት ትኩረቱን ሰብስቦ ተመቻችቶ እየተቀመጠ
ከሰዓታት በፊት ያጋጠማትን እና እያበረረ ወደእሱ ያስመጣትን ጉዳይ ከመጀመሪያው አንስታ በዝርዝር አስረዳችው…በገረሜታ አፉን ከፍቶ አዳመጣት…ስትጨርስ
‹‹ወይኔ ጉዳችን.!!!.እንዴት ቼኩን ትቀበያለሽ…..?››
‹‹አልቀበልም ብል ዝም ሚሉኝ ይመስልሀል…ሚስጥራቸውን እንደማጋልጥባቸው ስለሚጠረጠሩ ሊያጠፍኝ ይችላሉ ብዬ ፈራኋ…››.
‹‹እሱስ ትክክል ነሽ …ለገዛ ዘመዳቸው ያላዘኑ ላንቺ አይመለሱም…..እና ምን እናድርግ›መልሶ እሷኑ ጠየቃት፡፡
‹‹እርዳኛ››
‹‹እኮ እንዴት ልርዳሽ…?››
‹‹እኔ እንጃ››
ትኩር ብሎ በጥርጣሬ አይን አይኗን እየያያት ቆየና‹‹…ልጅን እንዲሞት ትፈልጊያለሽ እንዴ….?ማለቴ በመግደል እንዳግዝሽ ነው የምትፈልጊው…..?››ሲል ጠየቃት
‹‹አረ በአላህ…..!!እንዴት እንደዛ አሰብክ..…..?››
‹‹እኔ እንጃ… ምን አልባት ብሩ ብዙ ስለሆነ….››ንግግሩን አላስጨረሰችውም
‹‹የፈለገ ብዙ ብር ቢሆን ይህን ለግላጋ ጥንቅሽ ወጣት ለመግደል ጭካኔውን ከየት አመጣለሁ…..?››
‹‹እንዴ ለግላጋ ወጣት ነው ያልሺኝ..…..? ቆንጆ ነው እንዴ..…..?››
ከንግግሩ ተነስታ የተናገረችውን ነገር በምልሰት ስታስታውስ እፈረት ተሰምቷት ‹‹….አንተ ደግሞ በዚህ ሰዓት እንዲህ አይነት ቀልድ ይቀለዳል…..?››አለችው
‹‹ቀልድ እኮ አይደለም ..አንቺው ስላልሽ ነው…ለግላጋ ባይሆን እንዲሞት ትፈቅጂ ነበር ማለት ነው.…..?ንግግርሽ እኮ እንደዛ የምትይ ነው የሚመስለው››
‹‹ይሁንልህ እስቲ አሁን እንዴት እናድርግ….…..?››
አምስት ለሚሆኑ ደቂቆዎች ሁለቱም በየፊናቸው አሰብ …ከዛ ደ/ር እስክንድር ከሀሳቡ ባኖ በፈገግታ መናገር ጀመረ‹‹…አሪፍ ሀሳብ መጣልኝ ››
‹‹ምን አይነት ሀሳብ ንገረኝ……..?.››
‹‹አሁን አልነግረሽም… መጀመሪያ እራት ጋብዢኝ››
‹‹ንገረኝና ጋብዝሀለሁ…..?››
‹‹እዚህ አልነግረሽም… በዘመናችን ምንም በነፃ የሚሰጥ ነገር የለም….ሁሉም ነገር ያስከፍላል…ስለዚህ ጋብዢኝና ልንገርሽ ወይም ደግሞ ይቅርብሽ››
‹‹ይሁንልህ እሺ … አሪፍ ምክር ይሁን እንጂ በደስታ ጋብዝሀለሁ››
‹‹አይ አንቺ ብዙ ቀን ጋብዢኝ ብዬሽ አሻፈረኝ ብለሽ ነበር..ዛሬ እጄ ገባሽ›››
‹‹ስለተሳካልህ እንኳን ደስ ያለህ››አለችውና ተያይዘው ወጡ
እራት በልተው እንዳጠናቀቁ ያሰበውን ይነግራት ጀመር
‹እንግደለው››
‹‹ምን አይነት ብሽቅ ሀሳብ ነው››
‹‹ማለቴ ለተወሰኑ ደቂቃዎች የሞተ እንዲመስል እናደረግና መሞቱን አይተው እንዲያምኑ እናድርግ››
ከቁጣዋ መለስ ብላ‹‹ከዛስ?››ስትል በጉጉጉ ጠየቀች፡
‹‹‹ከዛማ በቃ ሳጥን አምጡ እንላቸውና የሆነ ነገር አሽገን እንሰጣቸዋለን….››
‹‹ከዛስ…?››
‹‹ከዛማ ሰውዬውን የሆነ ቦታ ወስደን እስኪድን እንጠብቅና ለምን ሊገድሉት እንደፈለጉ ከራሱ እናጣራለን…ከእሱ በምናገኘው መረጃ የሆነ ነገር እናደርጋለን…ወይም እራሱ ሲድን የሆነ ነገር ያደርጋል››
ተነስታ ተጠመጠመችበት ‹‹..እንዲት ይህ ሀሳብ መጣልህ?››
‹‹እድሜ ለሆሊውድ ፊልም …ሊዚህ ለዚህ ካልተጠቀምንበት ለምን ይጠቅመናል?››
‹‹እና መቼ እናድርገው…››
ነገ ተነጋግረን የሚሆነውን እናደርጋለን››
✨ይቀጥላል✨

👍129❤17😁5😱2👎1
#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ዶ/ር ሶፊያ የተኛችበት ሆስፒታል አልጋ ላይ ሆና በኤልያስ በኩል ከትንግርት የተላከላትን ዲያሪ ማንበብ ጀመረች፡፡
ጥቅምት 25 1999ዓ.ም
የሁለተኛ አመት የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ከጀመርን አንድ ወር ሊሞላን ነው፡፡አምና ፍቅረኛ ነበረኝ፡፡ጌዲ ከኔ ጋር ነበር..አሁን ግን ብቻዬን ነኝ፡፡ቢሆንም ምርጥ የሴት ጓደኛ ማግኘት ችያለሁ፡፡ሶፊያ ትባላለች፡፡አንድ ዶርም ነው የምንጋራው፡፡እርግጥ ሌሎች አራት ልጆችም አብረውን ይኖራሉ..በአርባ ምንጭ ሙቀት አንድ ዶርም ውስጥ ስድስት ሰው ታጭቆ መኖር ይከብዳል..ቢሆንም እየኖርን ነው፡፡
ሶፊ የምትገርም ልጅ ነች…የተወለደችውም ያደገችውም አሜሪካ ነው፡፡ በዲሞሽን ወደ
ኢትዬጵያ ከተወረወረች ሶስተኛ አመቷ ነው፡፡ አንድ አመት ሃይስኩል የተቀሩትን ሁለት ዓመት እዚህ ዩኒቨርሲቲ እንዳሳለፈች አጫውታኛለች፡፡
ስለእሷ ሳስብ ሚገርመኝ የኢትዬጵያ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ውጭ ለመላክ አፈር ድሜ ይግጣሉ..የእሷ ወላጆች እሷን ባህሏን እረሳች..ፀባዮ ተበላሸ ...መረን ለቀቀች በሚል ሰበብ ወደ ኢትዬጵያ ላኳት..ልክ እንደ ፀባይ ማረሚያ..አይ ሚስኪኗ ሶፊያ፡፡
ህዳር-5 1999 ዓም
ከሶፊ ጋር ዛሬ ወደ ከተማ ወጥተን ነበር..ሲቀላ ፡፡ ዋናው የሄድንበት ምክንያት አባቷ ከአሜሪካ ዶላር ልኮላት ስለነበር ያንን ለመቀበል ነው፡፡ አንድ ሺ ዶላር ነበር የላከላት፡፡ከዛ ምሳ ጋበዘችኝ..ወይን ጠጣን…ለእሷ አንድ ሱሪ ብቻ ስትገዛ ለእኔ ሁለት ሱሪና ሁለት ቀሚስ ገዛችልኝ፡፡ግርም ነው ያለኝ፡፡ ማነው ለጓደኛው እንዲህ የሚያደርገው…?በዛ ላይ የእሷን ያህል አይሁን እንጂ እኔም ከውጭ በሚላክ ዶላር የምማር ልጅ ነኝ፤ሌላው ደግሞ አንድ ደርዘን የሚያማምሩ ፓንቶች ገዛችና ስድስቱና ለእኔ ስድስቱን ለራሷ ወሰደች፡፡በእውነት የዋህ ነች እንዳልል ለሌሎች ጓደኞቿ እንደዛ ስታደርግ አይቼት አላውቅም፡፡ብቻ እኔ ወደድኳት፡፡ጥሩ ጓደኛዬም አድርጌ ከልብ ተቀብዬታለሁ፡፡
ህዳር 29 1999 ዓ ም
የሚቀርቡን የዩኒቨርቲ የወንድ ጓደኞቻችን ከተማ ካልወጣን አሉን፡፡አስር ሆነን ወጣን.... አራት ሴት ስድስት ወንድ፡፡ከግቢ ስንወጣ እራሱ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ሆኖ ነበር፡፡ከግቢ በታክሲ ሲቀላ... ከሲቀላ ደግሞ ሼቻ አመራን፡፡ በመጀመሪያ ወደ በቀለ ሞላ ሆቴል ነው ያመራነው፡፡፡
ሆቴሉን ጥለን ወደ ጓሮ አለፍንና ውጭ ወንበር ከበን በመቀመጥ እራት አዘዝን፡፡ከፍታ ቦታ ላይ ያለው የበቀለ ሞላ ሆቴል ወደ ታች የነጭ ሳርን የተንጣለለ ደን፤ በእግዜር ድልድይ የተከፈሉትን አባያና ጫሞ ሀይቅን፤ በግሩም
ሁኔታ ማየት የሚያስችል እስትራቴጂካዊ ቦታ ላይ ነው የታነፀው ..ከዛ ከዝቅታው የተፈጥሮ ሙዚዬም ወደ ላይ ሚነፍሰው ቀዝቃዛና ነፋሻማ አየርም ልብን ስውር ያደርጋል፡፡ እራታችንን በልትን ስናጠናቅቅ እና የበቀለ ሞላን ሆቴል ለቀን ስንወጣ 2፡45 ሆኖ ነበር፡፡ ቀጥሎ ሞቅ ወዳለው ጫሞ ሆቴል ነው የገባነው፡፡በተለያ አጋጣሚዋች ሶስት ቀን እዚህ ቤት መጥቼያለሁ....በተለይ ከጊዲዬን ጋር የመጣሁባቸው ሁለት ቀናት አይረሱኝም፡፡
መጠጥ መጠጣት በቢራ ነው የተጀመረው፡፡ ጨወታው፣ ተረቡ ደስ ይል ነበር፡፡ በተለይ የሶፊ ደስታ ልዩ ነበር፡፡በፊትም እኔ ስለማጣጥልባት እንጂ እንዲህ አይነት ቸበርቻቻ ነፍሷ ነው፡፡ ..አራት ሰዓት አካባቢ መቀመጫው ላይ ማንም አልነበረም፡፡ ሁሉም በሙዚቃ ምት በመታገዝ ጭፈራውን እየቀወጠው ነው፡፡አንዳንዱም መጠጡን ከቢራ ወደ አልኮል ቀይሮታል….. እየሰከረ ያለም አለ፡፡ወንዶቹ የመረጧትን እና ቀልባቸውን የተመኛት ሴት ዙሪያ ይሽከረከራሉ… ይጎነታትላሉ ...ይጀነጅናሉ፡፡
ሁለቱ ሴቶች ከሁለቱ ወንዶች ጋር ተግባብተው እየተላላሱ ነው፡ኃይሌ የሚባል የመቀሌ ልጅ እኔን እየጀነጀነኝ ነው..በጣም ያምራል..፡፡ለምን እንደሆነ አላውቅም ይሄን ልጅ ካወቅኩት ቀን ጀምሮ የሆነ ነገሩ ይመቸኛል፡፡እና እንዲሁ በሴትነቴ እግደረደራለሁ እንጂ ቀልቤ ፈቅዶታል..፡፡እሱም እየተግደረደርኩ መሆኔ ገብቶት መሰለኝ ጥረቱን አጠናከረ..ቀስ በቀስ እየደከምኩለት መጣሁ..<በቃ ዛሬ አብሬው ማደሬ ቁርጥ ነው› ስል አስቤ ነበር በውቅቱ ፡፡ ባዛ ላይ ከጌዲዬን ከተለያየው ስድስት ወር ሆኖኛል ...ስድስት ወር ሙሉ ምንም አላገኘሁም ..በጣም አምሮኛል፡፡
ሶፊያ ሶስት ወንዶች እየተሻሙባት ነው፡፡የሆነ ሙድ እየያዘችባቸው መሰለኝ፡፡እዚህኛው ላይ ትንጠለጠላለች.... ያኛውን ትጠቅሰዋለች.. ደግሞ ከዛኛው ጋር ትጎነታተላለች፡፡በመጨረሻ ጓደኛ የሆኑት ሶስቱ ወንዶች እርስ በርስ
መገለማመጥ ጀመሩ…..ስድስት ሰዓት ሲሆን
ሁላችንም በስካር ጥንብዝ ብለን ሆቴሉን ለቀን
ወደ ቤርጓችን ሄድን ፡፡አምስት ክፍል በመደዳ
ነበር የተያዘው፡፡እንዲህ እንዲሆን የወንዶቹ
ዕቅድ ነው ፡፡ዕድል የቀናቸው አራቱ ወንዶች
አንዳንድ ሴት ይዘው ይተኛሉ ምስኪኖቹ ሁለት ወንዶች የቀረችው አንድ አልጋ ላይ አብረው ያድራሉ.. በሚል ስሌት ነበር የተሰላው፡፡....
.......................
እዚህ ጋር ከደረሲው እውቅና ውጪ ቢሆንም ለአንባቢው የሚጎረብጡ ሐሳቦች የተነሱበት ክፍል ስለሆነ ቆርጬ አውጥቼዋለሁ ለምን ተቆረጠ የሚልም አይጠፋምና ከወዲሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ
........"በየጓዲያችን ቀስ በቀስ እየገባ ያለ ነገር ሆኖ ሳለ ቃሉን አናንሳ ..ጭራሽ በጆሮችን አንስማ ማለት አግባብም አይደለም አያዋጣንምም ብዬ አምናለሁ ፡፡
ይልቅ ችግሩ በቤታችን አለ...? አዎ አለ ፡፡… አግባብ ያልሆነ እና መቅረት ያለበት አካሄድ ነው ወይ..? አዋ ነው፡፡..ስለዚህ ውስጡ ያሉትን እንዴት አግዘናቸው ከህይወቱ እንዲወጡ ማድረግ እንችላለን…?ሊገቡ ቋፍ ላይ ያሉትንስ ሳይቃጠል በቅጠል እንዴት ነው ከገደሉ አፋፍ ልንመልሳቸው የምንችለው…? መልሱ ችግሩ በመሀከላችን መኖሩን በግልፅ ስናምን..በችግሩ ላይ በግልፅ መነጋገር
መወያት እና መግባባት ስንችል ነው መፍትሄውን በእጃችን መጨበጥ የምንችለው፡፡ እራሳችንንም ከችግሩ የምናድንበት መድሀኒት ማግኘት የምንችለው ... መጪውን ትውልድንም መታደግ የምንችለው የዛን ጊዜ ነው፡፡››
ካለበለዚያ እንዲሁ በጭፍን ባህላችን አጎደፉት .... እርኩሶች ናቸው፤ ይጨፍጨፉ….ይመንጠሩ በማለት ቅንጣት ውጤት ማምጣት አንችልም፡፡እንደውም ስለዚህ ነገር ሳስብ
1980ዎቹ ቤት አካባቢ የነበረውን የኤች. አይ ቪ ጥፋት ያስታውሰኛል ፡፡የዛኔ ጊዜም ስለበሽታው በአደባባይ አውጥተን መወያየትና መፍትሔ መፈለግ ሲገባን በየጓዲያው በማንሾካሾክ ....አውሬ መጣላችሁ፣ጭራቅ መጣላችሁ እያልን ለተጠቂዎች ሲኦልን
ስንሸልማቸው..እኛም በፍርሀት ታፍነን በቁም
ስንንዘፈዘፍ ስንት እና ስንት ህይወት ረገፈ ….?
ስንቱ አፍላ ወጣት ለውይይትና ለምክክር ዝግ
በሆነው ባህላችን ምክንያት በየጓዳው ባክኖ ቀረ...?ቤት ይቁጠረው፡፡ዛሬም ከዛ ውድመት አልተማርንም፡፡መቼም እርግማን ሆኖብን አንድ ችግር የህዝባችንን እሩብ ካልጨረሰ በስተቀር መፍትሄው አይገለፅልንም፡፡
‹‹ትክክል ነህ .…እኔም ባንተ ሀሳብ እስማማለሁ፡፡›› አለችው ዶ/ር ሶፍያ፡፡
‹‹ጥሩ.. በይ አሁን ተነሺ እንውጣ፡፡››
‹‹ጨረስክ እንዴ ፕሮሰሱን?››

👍73❤4👎1😁1