#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
...ከጆይስ ክፍል ደረስና መብራት በርቶ ሚስቱ ከአልጋው ጐን ተቀምጋ እንደ ሚያገኛት በመተማመን በሩን ቀስ አድርጎ ከፈተው በጁ ከያዘው ጧፍ በቀር ምንም
መብራት አልበረም » የሚስቱ ምልክትም የለም ከምን ገባች ? ምናልባት ጆይስ ልትነግረው ትችል ይሆን? ቀረብ አለና ቀሰቀሳት
ጆይስ ዶንግጣ ብድግ አለች " ጌታዋ መሆኑን ስታውቅ ድንጋጤዋ ወደ መገረም
ተለወጠ ሳቤላ ወደሷ መጥታ እንደሆነ ጠየቃት
ጆይስ መልስ አልሰጠችውም " ለካ ሲቀሰቅሳት ስለ ሳቤላ ሕልም ስታይ ኖራለች አሁን የሱ መምጣትና መጠየቅ ከህልሟ መለየት ተስኗት ግራ ገብቷት ዝም አለች።
“ ምን አሉ ጌቶች ? እሜቴን አመማቸው ?
“ ከዚህ መጥታ እንደሆነ እኮ ነው የምጠይቅሽ ? ላገኛት አልቻልኩም "
“ እንዴ አዎ ከዚህ መጡና ቀሰቀሱኝ ልክ ስድስት ሰዓት ሲደወል " ግን ወዲያው ወጥተው ሔዱ ”
“ ቀሰቀሰችኝ ? ምን አርጋ ? ምን ልትል ከዚህ መጣች?” አላት "
ጆይስ አሳብ ያዛት ያሳብ ሥዕል ተደቀነባት የእመቤቷ የብሶት ቃሎች በአእምሮዋ ጥርቅምቅም አሉ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት እስኪሆን ወደ መኝታዋም አልገባችም ከቤት ውስጥም ተፈልጋ አልተገኘችም ! ይህ ነው የማይባል ታላቅ ይህ ነው የማይባል ታላቅ ድንጋጤ ያዛት " ዐይኖቿ ግልብጥ ብለው የወጡ እስኪመስሉ ድረስ አፈጠጠች የታመመው እግሯንና ካጠገቧ ቁሞ የነበረውን ጌታዋን ረስታ አንድ ሙቀት ያለው ለስላሳ ቀሚስ ከወንበር ላይ አፈፍ አድርጋ አንሥታ አጠለቀች ከአልጋዋ ዘላ ወረደች አሰቃቂ ፍርሃት መጣባት ሌሎች ጥቃቅን ይሉኝታዎችና ሐሳቦች እልም ብለው ጠፉ
ሞቃቱን ልብስ በአንድ እጅዋ ከሰውነቷ አጣብቃ ይዛ በሁላተኛው እጅዋ ከሚስተር ካርላይል ክንድ ላይ ጣል አደረገችው "
“ ጌቶች ጌቶች .... እሜቴ ራሳቸውን ገድለዋል ! አሁን ነገሩ ገባኝ ”
ጆይስ ! አለና አቋረጣት ።
ምንም አይጠራጠሩ ጌታዬ እሜቴ ራሳቸውን ገድለዋል በፊት ሲናገሩ አልገባኝም ነበር እንጂ! አሁንማ አነጋገራቸውን ሁሉ በደንብ ተረዳሁት " እዚህ
ድረስ መጥተው እሳቸው በማይኖሩበት ጊዜ ከልጆቻቸው እንዳልለይ ቃል እንድግባላቸው ጠየቁኝ " እኔ ደግሞ ነገሩ አልገባኝም ነበር " ታመው እንዶሆነ ብጠይቃቸው አዎን አሞኛል መሮኛል አሉኝ » ጌታዬ ከዚህ አሰቃቂ መከራስ እሱ ራሱ ይሰውርዎ …”
ሚስተር ካርላይል ግራ ገባው " የጆይስ ጤንነት አጠራጠረው " ምክንያቱም
የተናገረችው ነገር በጭራሽ የማይታመን ሆነበት "
“ ነገሩ የማይታመን ቢመስልዎትም ይኸው ነው ... ጌታዬ ?” አለችው
ጆይስ እጆቿን አያፍተለተለች እሜቴ ያለ መጠን ምርር ብለው ያዝኑ ነበር "በዚህ ምክንያት ራሳቸውን ኀድለዋል ማለት ነው”
ጆይስ ዐብደሻል ወይስ በጤናሽ ነሽ ? እንደዚህ ስትይ ምን ማለትሽ ነው።
ጆይስ መልስ ከመስጠቷ በፊት •ሚስ ካርላይል ጥቁር የግር ሹራብ አጥልቃ ያንገት ልብስ ደርባ ረጂም የሌት ቆብ ደፍታ ብቅ አለች " የጆይስ መኝታ ቤት ከሷ
መኝታ ክፍል በላይ ስለነበር ድምፅ ሰማችና የሚባለው ነግር እዳያመልጣት ነበር ቶሎ ብላ የደረሰች "
እንዴት ነው ነግሩ ! አመቤት ሳቤላ ተግኘች ?
« አልተግኙም እሳቸው እንግዲህ በአንሶላቸው ተጠቅልለው ካልሆነ በቀር
አይግኙም ” አለች ጆይስ " የነበራት ትሕትናና ሥነሥርት ከግለቷ የተነሣ ጠፍቷል።
"እማቴ...እርሶም እንኳን መጡ ከፊትዎ ለመናገር እፈልጋለሁ አሁን እመቤቲቱ ሙተው ሬሳቸው ከፊታችን ቢጋደም ምን ይጠቀማሉ ጌቶች ለሚስታቸው የሚገባቸውን አድርገዋል " እርስዎ ግን መድረሻ አሳጡዋቸው " የቁም ስቃይ አሳዮቸው።
“ ምን ትዘበዝባለች ! ” አለች ሚስ ካርላይል በቁጣ “የት ነው ያለችው?
“ ሔዶዋል ማጥፋት የማይገባቸውንም ሕይወት ለማጥፋት ተገደዋል” አለች
ጆይስ እየተንሰቀሰቀች።
“ ኢስት ሊን ከገቡ ጀምሮ በገዛ ቤታቸው የሠራተኛቹን ያህል እንኳን ነፃነት አልነበራቸውም ማዘዝ የፈለጉትን መፈጸም አይችሉም " ሲናግሩ እርስዎ አፍ አፋቸውን እያሉዋቸው አንድ ነገር ሲይዙ ጣልቃ ግብተው እየከለከሉዋቸው በእርስዎ ፍላጎትና ትእዛዝ ሥር አድረው ራሳቸውን እንደ ባርያ ቆጥረው የእርስዎን ጠባይና ጭቆና በትዕግሥት ችለው ኑረዋል እኛ ሁላችን እንወዳቸውና እናከብራቸው ነበር " በደላቸውም ይሰማን ነበር " ጌቶችም ካመት እስካመት ምን ያህል በደልና ግፍ ተሸክመው እንደኖሩ ትንሽ እንኳን ቢጠረጠሩ ኖሮ ልባቸው በኀዘን ብዛት ይደማ ነበር ።”
የሚስ ካርላይል ምላስ ከትናጋዋ ተጣበቀ "
“ ምንድነው የምትይው ጆይስ ? ነገሩ አልገባኝም ” አለ ሚስተር ካርሳይል
“ እኔ ብዙ ጊዜ ልነግርዎ እየፈለግሁ እስካሁን ኖርኩ አሁን ደግሞ ፍጻሜው
ይህ ከሆነ ሊሰሙት የሚገባ ነው " እመቤቴ ሳቤላ ሚስትዎ ሆነው እዚህ ከገቡበት ቀን ጀምሮ በኢስት ሊንና በእርስዎ ስላስከተሉት ተጨማሪ ወጭ ሲነዘነዙበትና ሲወቀሱበት ነው የኖሩ " ትንሽ ነግር ቢፈልጉ ባልሽን ከድህነት ለመጣል ነው ተብለው ይከለhሉ ነበር። ዛሬ ለነበረው ጥሪ አዲስ ቀሚስ አዘዙ " እርስዎ እኔ ነኝ የማዝ ብለው ከለከሉ ባልሽ እንደ ውሻ እየሠራ አንቺ እንደ ፈለግሽ እያጠፋሽ አከሰርሽው እያሉ ይጨቀጭቁዋቸው ነበር " ገንዘብ አባካኝና ቅንጦት
ፈላጊ እንዳልሆኑ ግን ልብዎ ያውቅ ነበር ከእርስዎ
ጭቅጭቅ ሸሽተው
መኖር ከዐቅም በላይ አንደ ከበዳቸው ደረታቸውን በሁለት እጃቸው ደግፈው ሲያለቅሱ በዐይኔ አይቻቸዋለሁ የጨዋ ልጅ
ትዕግሥተኛ ወይዘሮ ቢሆኑም የኑሮ ፈተናው
ከሚታሡት በላይ ስለሆነባቸው ይህንን አሳዛኝ የተስፋ መቁረጥ ድርጊት ለመፈጸም ተገደዱ
ጠፋት "
“ እውነት ነው ? አለ ሚስተር ካርላይል ወደ እኅቱ ምልስ ብሎ "
ምንም አልመለስችለትም ኮርኒሊያ በሕይወቷ ያን ለት ብቻ የምትናገረው ጠፋት።
“ ይቅር ይበልሽ ኮርኒሊያ ! አላትና ወጥቶ ወደ ክፍሉ ወረደ “ ሚስቱ ሕይወቷን ታጠፋለች የሚለውን ነገር የሚስተር ካርላይል ሊና አልተቀበለውም
ምናልባትም ከመመረርዋ የተነሣ ከምድረ ግቢው አንዱ ላይ ተጠግታ
ይሆናል የሚል ሐሳብ መጣበት ቤተሰቡ በሙሉ ተነሣ ሚሰተር ካርላይል ምድረ ግቢውን ለማሰስ በጅምር የተወውን መልበስ ሲያጠናቅቅ ጆይስ ከሳቤላ መልበሻ ክፍል ገባች ከዚያ አንድ ወረቀት ይዛ ጠንቀስ እያለች ወደ ሚስተር ካርላይል ዘንድ ገብታ “
ይህ ከእመቤት መልበሻ ክፍል ከመስተዋቱ ኪስ አገኘሁት ጽፈቴ የሳቸው ነው
አለችው።
ተቀበለና አድራሻውን ሲመለከተው ለአርኪባልድ ካርላይል የሚል ነበር "
ያ በቀላሉ የማይርበተበተው መንፈሱ የተደላደለ የስሜቱን መገንፈል መቈጣጠር ይችል የነበረው ልበ ሙሉ ሰውዬ የፖስታውን እሽጋት ሲከፍት ጣቶቹ ተንቀጠቀጡ "
“ ከዘመናት በኋላ ልጆቹ እናታቸው የት እንዳለችና ለምንስ ጥላቸው እንደሄደች
ቢጠይቁህ አንተው የገዛ አባታቸው ገፋፍተህ እንዳባረርካት ንገራቸው ምንነቷን ቢጠይቁህ
ፈቃድህ ቢሆን ንግራቸው " ግን አንተን አበሳጭተህ አስመርረህ አሰቃይተህ ተስፋ አስቆርጠህ ይህን አማራጭ የሌለውን የመጨረሻ ድርጊት እንድትፈጽም እንዳደረግሃትም ሳትረሳ ንገራቸው ”

👍16
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
..ለአስር ደቂቃ ያህል ከተጓዙ በኋላ አንድ ከእንጨት የተሰራ ቤት አገኙና ጥልቅ አሉ፡፡ ናንሲ ስልኩ አጠገብ ያለ ወንበር ላይ ተቀምጣ እጇ እየተንቀጠቀጠ የስልኩን እጀታ አነሳችና ‹‹ናንሲ ሌኔሃን ነኝ›› አለች፡፡
ኦፕሬተሩም ‹‹የቦስተን ስልክ ፈላጊ መጥታለች ስልኩን አትዝጉት›› አለ።
ትንሽ ቆይቶ ‹‹ናንሲ ነሽ?›› አለ ከወዲያኛው አገር የመጣ ድምጽ ስልኩን የደወለው ማክ መስሏት ስለነበር የሰማችው ድምጽ የዳኒ ሪሌይ መሆኑን ለማወቅ ትንሽ ጊዜ ወስዶባታል ‹‹ዳኒ ሪሌይ ነህ?,,
‹‹ናንሲ ችግር ውስጥ ውድቄልሻለሁ እባክሽ እርጂኝ›› አለ፡
የስልኩን እጀታ አጥብቃ ያዘች፡፡ የሸረበችው ሴራ ግቡን ሊመታ ይመስላል፡፡ የዳኒ ስልክ የረበሻት ለመምሰል በተሰላቸና ረጋ ባለ ድምፅ
‹‹የምን ችግር ዳኒ?›› አለችው፡፡
‹‹ሰዎች በቀድሞ ጊዜ ላጠፋሁት ጥፋት ከዚህም ከዚያም ስልክ እየደወሉ አስቸገሩኝ››
ይሄማ ጥሩ ብስራት ነው፡፡ ማክ ዳኒ ላይ ሽብር ነዝቷል ማለት ነው› አለች ሆዷ በደስታ እየሞቀ፡፡ ዳኒ ድምፁ ይንቀጠቀጣል፡ እሷም ይህን ነው
የፈለገችው፡፡ ነገር ግን እንዳያውቅባት ስለምን እንደሚያወራ እንደማታውቅ
አስመስላለች፡ ‹‹የምን ችግር ነው? ምንድን ነው እሱ?››
‹‹በስልክ ልነግርሽ አልችልም››
‹‹ታዲያ ጉዳዩ በስልክ የማይነገር ከሆነ ለምን ደወልክልኝ?››
‹‹ናንሲ እንደ ቆሻሻ አትቁጠሪኝ ከጉድ እንድታወጪኝ ነው
የደወልኩልሽ››
‹‹እሺ ተረጋጋ›› በሚገባ ተሸብሯል፡፡ ይህን ፍርሃቱን ደግሞ ልትጠቀምበት ወስናለች፡ ‹‹የሰው ስምና አድራሻ ሳትገልፅ የሆነውን ብቻ ንገረኝ የምትፈልገውን ነገር መገመት አያቅተኝም››
‹‹የአባትሽ ሰነዶች በሙሉ አንቺ ጋ ናቸው?››
‹‹አዎ እኔ ቤት ካዝና ውስጥ ናቸው››
‹‹ሰዎቹ ሰነዶቹን ማየት ሳይፈልጉ አይቀሩም››
ዳኒ ራሷ የቀመረችውን ታሪክ እየነገራት ነው፡ ሴራው እስካሁን በዕቅዱ መሰረት እየተከናወነ ነው፡፡ ለጉዳዩ ትኩረት የሰጠች በማይመስል ሁኔታ ‹‹እነዚያ ሰነዶች ውስጥ አንተን የሚያስጨንቁህ ነገሮች ያሉ
አይመስለኝም››
‹‹እንዴት እርግጠኛ ሆንሽ?›› ሲል አቋረጣት በንዴት።
‹‹እኔ እንጃ››
‹‹ሰነዶቹን በሙሉ አይተሻቸዋል?››
‹‹አይ ብዙ ሰነዶች ነው ያሉት››
‹‹ምን እንዳለ ማንም አያውቅም፡፡ ሰነዶቹን ገና ድሮ አቃጥለሻቸው
ቢሆን ኖሮ ጥሩ ነበር፡››
‹‹ልክ ነህ የሆነስ ሆነና ሰነዶቹን መመርመር የፈለገው ማነው?››
‹የጠበቆች ማህበር ነው፡፡ እነሱ ሰነዶቹን ለማየት መብት አላቸው››
‹‹የላቸውም፡፡ ነገር ግን እኔ አልሰጥም ካልኩ ጥሩ አይመጣም››
‹‹አንቺ ጠበቃ አይደለሽ ሊያስገድዱሽ አይችሉም››
ናንሲ ንግግሯን ትንሽ ቆም አደረገች ልቡን ልትሰቅለው፡ ‹‹ስለዚህ ችግር አይኖርም›› አለችው
‹‹አልሰጥም ትያቸዋለሽ?››
‹‹ከዚያም በላይ ማድረግ እችላለሁ። ነገ አሜሪካ ስመጣ አቃጥላቸዋለሁ››
ዳኒ ሳግ እየተናነቀው ‹‹ናንሲ አንቺ እውነተኛ ጓደኛ ነሽ›› አለ፡፡
ከልቧ ልትረዳው እንዳልሆነ ህሊናዋ እየነገራት ‹‹ሌላስ ምን ላድርግልህ?››
‹‹ይሄ ይበቃኛል እንዴት አድርጌ እንደማመሰግንሽ አላውቅም››
‹‹አንተ ካነሳኸው ደግሞ ውለታ ልጠይቅህ ነው›› አለችና ከንፈሯን
በጥርሷ ነከሰችው::
‹‹መቼም ለምን እንዲህ
እንደፈለግኩ ሳታውቅ አትቀርም››
እንዲህ በአስቸኳይ ወደ አሜሪካ ለመመለስ
‹‹አላውቅም ምንድን ነው?›› አላት፡
ፒተር ኩባንያውን እኔ ሳላውቅ ሊሸጥ ተዘጋጅቷል››
ዳኒ ፀጥ አለ፡፡
‹‹ዳኒ አለህ?››
‹‹አለሁ አንቺ እንዲሸጥ አትፈልጊም?››
‹‹እኔ እንዲሸጥ አልፈልግም፡፡ ለግዥ የቀረበው ዋጋ በጣም ዝቅ ያለ ነው፡፡ ከተሽጠ እኔም ቦታ የለኝም: ስለዚህ እንዲሸጥ የማልፈልገው ለዚህ ነው ፒተር ኩባንያው የሚሸጥበት ዋጋ በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ ያውቃል፡
ነገር ግን እኔን ለመጉዳት ስለሆነ ቢሸጥ ግድ የለውም:፡››
‹‹የሚሸጥበት ዋጋ ጥሩ አይደለም? ኩባንያው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ
አክሳሪ እየሆነ እኮ ነው››
‹‹ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? አታውቅም››
‹‹አንድ የምገምተው ነገር አለ››
‹‹ታውቃለህ፡፡ ምክንያቱን ተናገረው እና ይውጣልህ፡ ፒተር የማይረባ ማኔጀር ስለሆነ ነው››
‹‹እሺ››
‹‹ኩባንያውን በርካሽ ዋጋ ከምንሸጠው ለምን ከኃላፊነት አናነሳውም፡፡
እኔ የኃላፊነቱን ቦታ ልውሰድና ወደ ቀድሞው ስሙ ልመልሰው፡፡ እንደ
ምመልሰውም ታውቃለህ፡፡ ኩባንያው ደህና ደረጃ ላይ ሲደርስ በከፍተኛ ዋጋ
እንሸጠዋለን ከፈለግን››
‹‹እኔ አላውቅም››
‹‹ዳኒ አሁን በድፍን አውሮፓ ጦርነት እየተቀጣጠለ ነው፡ ይህ ማለት አቅርቦት ጥያቄ ይጎርፍልናል፡፡ ሁለት ሶስት ዓመት ብንቆይ ደግሞ
ቢዝነስ ይጧጧፋል ማለት ነው፡፡ ከምናመርተው ጫማ በላይ የጫማ ኩባንያውን አሁን ከተሰጠው በሁለት ሶስት እጥፍ ዋጋ መሸጥ እንችላለን፡›››
‹‹ነገር ግን ከናት ሪጅዌይ ጋር የፈፀምኩት የጥብቅና ውል ለኔ ጠቃሚዬ ነው›› አለ ዳኒ፡፡
‹‹ጥቅም የምትለውን ተወው፡፡ እኔ እንድትረዳኝ ነው የጠየኩv››
‹ይህን ሁሉ የምትጠይቂኝ ለራስሽ ጥቅም አይደለም?›
አንተ እልም ያልክ ውሸታም ነክ አንተስ ስለራስክ ጥቅም አደለም የምታወራው? ልትለው ፈልጋ ላለመናገር ከራሷ ጋር ታገለችና ‹አባባ ጋ ያሉትን ሰነዶች እንዳትረሳ›› አለችና ትንፋሿን ያዝ አደረገች
‹‹ምንድን ነው ያልሽው?››
‹‹ባጭሩ እንረዳዳ ነው የምልህ፡፡ እንዲህ ያለ ነገር መቼም የሚገባህ
ይመስለኛል››
‹‹አዎ ገብቶኛል ይሄ ዛቻ ይባላል››
እያደረገችው ያለችው ነገር በሙሉ የሚያሳፍር ነው፡፡ ነገር ግን ከማን ጋር እንደምትወያይ አስታወሰችና ‹‹አንተ አስመሳይ ሽማግሌ! እንደዚህ ያለ ነገር ህይወትህን ሙሉ
ስትፈፅም ኖረሃል››
ዳኒ ሳቀና ‹‹ዛሬ እጅሽ ላይ ወድቂያለሁ፡›› ይህን ተናግሮ ሲያበቃ አንድ
ነገር አዕምሮው ውስጥ አቃጨለና ‹‹እኔ ላይ ግፊት ለማድረግ ብለሽ ራስሽ
ሳትሆኚ አትቀሪም ይህን የጠነሰስሽው›› አላት፡፡
አሁን ወደ እውነቱ ተጠግቷል፡፡
‹‹አንተ ብትሆን እንዲህ
እንደምታደርግ አውቃለሁ፡፡ ከዚህ በላይ አትመርምረኝ፡፡ አንድ ማወቅ የሚገባህ ነገር በነገው የቦርድ ስብሰባ እኔን ከደገፍክ ከችግር ነጻ ነህ ካልደገፍከኝ ግን አለቀልህ›› ስትል ቁርጡን ነገረችው:፡ አሁን በግልጽ
ማስፈራራቱን ተያያዘችው፡፡ እሱ ደግሞ የሚገባው ቋንቋ እንዲህ ያለው ነው፡፡ ከዚህ በኋላ እግሯ ስር ይወድቃል ወይስ ዞር በይ› ይላል?
‹‹እኔን እኮ እንዲህ ልትናገሪኝ አትችይም! እኔ ቂጥሽን ያልጠረግሽ ልጅ
ሳለሽ ጀምሮ ነው የማውቅሽ››
ናንሲ ድምጿን ለስለስ አድርጋ ‹‹ታዲያ እኔን ለመርዳት ይሄ ምክንያት
ሊሆን አይችልም›› አለች፡፡
ትንሽ ቆየና ዳኒ ‹‹ሌላ ምን ምርጫ አለኝ!›› አለ፡፡
‹‹ያለህ አይመስለኝም እኔ ያልኩህን ከማድረግ ውጭ።››
‹‹እሺ›› አለ በገነገነ ሁኔታ፡ ‹‹ነገ ለአንቺ ድምፅ እሰጣለሁ አንቺ
እነዚያን ሰነዶች የምታጠፊ ከሆነ፡፡››
ናንሲ ያሰበችው በመሳካቱ ልታለቅስ ምንም አልቀራትም፡፡ ዳኒን
ከእግሯ በታች አዋለችው፡ አሁን ድሉ የእሷ ሊሆን ነው፡፡ የብላክ የጫማ
ኩባንያ በእሷ ቁጥጥር ስር ሊገባ ነው፡፡

👍24❤2
#ባል_አስይዞ_ቁማር››
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ክረምቱ ሲመጣ ሰውነቷ ይሸማቀቃል።ዝናብ ትወዳለች ግን ነጎድጓድና መብረቅ ያስፈራታል። በሰማዩ ላይ ቀስተደመና ሲነጠፍ ልቧ ላይ የተጠመጠመ ኒሻን ይመስለትና ትፈነጥዛለች፡፡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለሙ ከኢትዬጰያ መቀነት ጋር መመሳሰሉ ሁሌ እንዳስደመማት ነው።እርግጥ ሳታድግ የቀሰት ደመና የተሸመነባቸው ቀለሞች ሶስት ብቻ ሳይሆኑ ሰባት እንደሆኑ ማወቅ ችላለች።ግን ደግሞ ማወቅና ማመን ይለያያል...ዛሬም አይኖቾን አንጋጣ ቀስተደመናውን ሳታይ በትክክል ወደውስጧ ደምቀው በመግባት የሚውለበለብት እነዛው በልጅነቷ የምታውቃቸው ሶስቱ ቀለማት ብቻ ናቸው።አረንጓዴ ቢጫ ቀይ..."አንዴ አትለከፍ"ትላለች አክስቴ አዎ ልክፍት ነው።››አለች
በማግስቱ ጥዋት መድህኔ መጥቶ ጊፍቲን ወሰዳት….ስራ ስለምትገባ ቅያሪ ልብስና ለሁለቱም የሚሆን ቆንጆ ቁርስ አሰርቶ ነበር ይዞ የመጣው….ልክ የእሷ እንዳልነበረና ከዚህ በፊት እንደማታውቀው ወንድ አይነት ትክ ብላ አየችው…አሳዛኝና እንስፍስፍ ወንድ ሆኖ ነው ያገኘችው...እንስፍስፍ ያለችው አፍቃሪ ላለማለት ጎርብጦት ነው….‹‹አሁን ጊፊቲን ካገኘ በኃላ ተቀይሮ ነው ወይስ በፊትም ከእኔ ጋር እያለ እንዲህ ነበር ..?››በወፍ በረር ወደኃላ መለስ ብላ ለእሷ የሚያደርግላትን እንክብካቤዎች ለማስታወስ ሞከረችና ሽምቅቅ ብላ ቶሎ ተመለሰች‹‹…ከእሱ ምንም የተለወጠ ነገር የለም ልዩነቱ እኔ መሆኔና ጊፊት መሆኗ ላይ ነው…እሷ ከእሱ የሚሰጣትን ፍቅርና እንክብካቤ በትህትና እና በምስጋና ተቀብላ በፈገግታ ምላሽ ስትሰጥ እኔ ግን በወቅቱ አደርግ የነበረው በብስጭት በመግፋትና በተቃውሞ ነበር ሞራሉን የምሰብረው….እንደውም አሁን መጠየቅ ያለብኝ ያን ሁሉ ጊዜ እንዴት ታግሶኝ ኖረ….?. ›ስትል ድምዳሜ ላይ ደረሰች፡፡
ልብሷን ቀየረችና ካመጣው ቁርስ አንድ ሁለቴ ጎርሳ ጉንጩን ሳመችውና ስትወጣ መድህኔ ደግሞ ወደልዩ ዞሮ‹‹…እንዴት ነው ግፍቲን ቢሮ ካደረስኮት በኃላ መጥቼ ወደቤት ልውሰድሽ እንዴ.?.››ሲል ጠየቃት
‹‹አይ አልፈልግም..አላየህም እንዴ .?.መኪናዬ እኮ እዚህ ግቢ ውስጥ ነች…››
‹‹እንዴ..ለመንዳትም አቅም የለሽ ..መጥቶ ይውሰድሽ››ጊፍቲ መሀከል ገባች…‹‹.ይቺ ልጅ በፊት ሳገኛት እንደገመትኮት አይነት አይደለችም..ቀናና ጥሩ ሰው ነች..አሁን ሌላ ሴት ብትሆን እኮ ጭራሽ እንዲህ ስላለ ፍቅረኛዋን በግልምጫ ነበር የምታደባየው..መልሳ ብትወስድብኝስ በሚል ስጋት እራሷ ደንብራ አካባቢዋ ያለውን ሰዎች ሁሉ ታስደነብር ነበር…››ስትል አብሰለሰለች
አይ ..አልፈለግም..እኔ በአሰኘኝ ሰዓት መንዳት እችላለሁ..ደግሞ ብሔድም ከሰዓት ነው››
‹‹እሺ በቃ ቁረሱን ተነሺና ብይ..እና ከፈለግሺኝ ደውይልኝ››አለና ቤቱን ዘግተውላት ተያይዘው ሄዱ ፡እሷም መልሳ እራሷን ትራስ ውስጥ ቀበረችና ወደትካዜዋ ገባች..እራሷን ትራስ ውስጥ ስትከት የቃልን ጠረን በአፍንጫዋ እየተሹለከለከ ወደመላ ሰውነቷ በደምስሯ አማካይነት ተሰራጨና የንዝረት ስሜት በሰውነቷ ለቀቀባት፣
//
በሶስተኛ ቀን እናቷ መድሀኔ እየመራት ያለችበት ድረስ መጣች....ስታያት እንባዎን መቆጣጠር ነው ያቃታት....፡፡
"ምነው መድህኔ ..ምነው ልጄ እንዲህ እስክትሆን እንደው ሁሉ ነገር ቢቀር እህትህ አይደለች?"በማለት ወቀሰችው፡
"እትይ...ከገባችበት ነገር እንድትወጣ በተቻለኝ አቅም ያልጣርኩ ይመስልሻል...?..ሰሞኑን ስራ እንኳን በቅጡ መስራት አልቻልኩም...በቀን ከሶስት ጊዜ በላይ እየተመላለስኩ ለምናታለሁ..ግን ያው እንደምታይው ነች"አለ ..ጥረቱና ልፋቱ መና ስለቀረበት ቅር እንዳለው በሚያሳብቅ የምሬት ንግግር
የልዩ እናትም ከጠንካራ ንግግሯ መለስ አለችና"ልጄ የቻልከውን እንደምትሞክር አውቃለሁ ..የምናገረውን አትይብኝ ደንግጬ ነው"አለችው
"ችግር የለም ይገባኛል....አሁን እናንተ አውሩ ...እዚሁ አካባቢ ነኝ… ስትጨርሺ ደውይልኝ።"ብሎ እናትና ልጅን አፋጦ ወጥቶ ሄደ...እንደዚህ ያደረገው በነፃነት እንዲያወሩ በማሰብ እንደሆነ ሁለቱም ገብቷቸዋል ።ልዩ ግን ምንም የምታወራበት ጉልበት የላትም...ለዛውም ከእናቷ ጋር"
"ልጄ በራሴ አፍሬያለሁ...እኔ እኮ እራሴን እንደዘመናዊና ግልፅ እናት ነበር የምቆጥረው ..ግን ተመልከቺ ልጄ በዚህ ልክ የምታፈቅረው ሰው ኖሮ እንኳን አላውቅም...."
"እማዬ እሱ የእኔ ጥፍት ስለሆነ አትዘኚ..."አለቻት።
‹‹አይ ልጄ ...ለነገሩ ተይው አሁን ነገሮች ከተበለሻሹ በኃላ ብናወራው ምን ፋይዳ አለው....?..አሁን ይበቃሻል ማልቀሱም ማዘኑም በገዛ ቤት ያምራል...ልጄ ወደ ቤታችን እንሂድ"አለቻት ፈራ ተባ እያለች...ልዩ ምንም አላለቻትም… የውስጧን ጥንካሬ አሰባስባ ቀስ ብላ ተነሳችና እግሯን እየጎተተች ወደ መኝታ ቤት ስትራመድ ውስጥ ገብታ በራሷ ላይ ልትቆልፍ መስሏት የሰጋችው እናት"ወዴት እየሄድሽ ነው ልጄ?"ስትል ጠየቀቻት፡፡
"መጣሁ… የማሳይሽ ነገር አለ›› በማለት ወደ ውስጥ ገባችና ማንጠልጠያ ላይ ከተንጠለጠለው ቦርሳዋ ውስጥ እጇን ሰዳ የምትፈልገውን እቃ ያዘችና ወደሳሎን ተመለሰች..."
እናቷ ፊት ለፊት አስቀመጠቻት ...እናቷ ደንግጣ አንዴ እሷን አንዴ ጠረጰዛው ላይ ያለውን ዕቃ በማፈራረቅ ታየው ጀመር… ‹እማ ..በቀደም ለት ዝግጅት አለብኝ ብዬ እንደዛ ለግማሽ ቀን አምሬና ተሽቀርቅሬ እነዚህን ሁለት ቀለበቶች ገዝቼ ወደ እዚህ ቤት የመጣሁት ለቃልዬ ቀለበት ላስርለት ነበር..፡፡.በድፍረት እንዳፈቀርኩት ነግሬው እንዲያገባኝ ልጠይቀው ነበር...ስደርስ ግን ሁሉን ነገር ጣጥሎ ገዳም እንደገባ የሚገልፅ ደብዳቤ ጥሎልኝ ሄዷል...ይሄ ሁሉ የእኔ ጥፍት ነው ። አረባም ፡፡››
"ምን አጠፋሽ የእኔ ማር....?.."
‹‹ምን ይሄን ሁሉ ጊዜ አዘገየሸ...ከ15 ቀን በፊት ላደርገው እችል ነበር እኮ...ከወር በፊትም ባደርገው ጥሩ ነበር"
"ልጄ እንደው ቢጨንቅሽ ነው...ይሄ እንደሚመጣ በምን ልታውቂ ትቺያለሽ....?.."
"ደግሞ የዛሬ ሳምንት በጣም አበሳጭቼዋለሁ..››
"ምን አድርገሽ ልታበሳጪው ትቺያለሽ?"
‹‹ሰርቄ ነዋ...ሆቴል ልጋብዝህ ብዬ ወስጄ ሰረቅኩ...በእፍረት አንገቱን ደፍቶ የሠረቅሽውን መልሺ አለኝ .....እኔም መለስኩ ..ከዛ ሲመክረኝ ዋለ ..በማግስቱ ይቅርታም ልጠይቀው እንደማፈቅረውም ልነግረው ቀጥሬው በሰዓቱ ብገኝ እንዳልኩሽ ሆነ...ዳሩ ሌባን ማን ማፍቀር ይፈልጋል?"
"ልጄ አሁን እኮ ባለፈ ነገር ዝም ብለሽ ነው የምትጨናነቂው... እንዳልኩሽ ተነሽና ወደቤታችን እንሂድ፤ከዛ በእርጋታ እንደ እናትና ልጅ አናውራ። የሚስተካከለውን እናስተካክላለን"
"የምለውን አልሰማሽም እንዴ እማዬ?"
"ምን አልሽ?"
"እሱ ሸሽቶ ቢሄድም እኔ እኳ አግብቼዋለሁ ....ከተቀመችበት ተንጠራራችና ቀለበቶቹን አነሳች የራሷን ቀለበት አጠለቀች
"...እማዬ ደግሰሽ ባትድሪኝም እኔ አግብቼያለሁ...እና እዚሁ ሆኜ መጥቶ ይሄን ቀለበት እስኪያጠልቅ እጠብቀዋለሁ።"
"ምን ነካሽ...?በግልፅ እኳ መቼም ላይመለስ አንደኛውን ወደ ገዳም እንደገባ ነግሮሻል?..እና ምንድነው የምትጠብቂው ?እስከመቼስ ነው የምትጠብቂው?"
"እማዬ ልቤ ተመልሶ እንደሚመጣ እየነገረኝ ነው...ከሁለት አመትም ሆነ ከሀያ አመት በኃላ አንድ ቀን ተመልሷ ይመጣል...እና እዚሁ ቤት ሆኜ እጠብቀዋለሁ።››

👍82❤7🥰5😁5
#ተአምረተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//
በማግስቱ….
ከምሽቱ 1 በሰዓት አካባቢ ነው ሰሚራም ሆነች ዶ/ር እስክንድር የእለቱ የማታ ተረኛ ሆነው ስራቸው ላይ ተስማርተዋል፡፡
ሰሚራ ለመላኩ ዘመዶች ደወለችላቸው…ሰሎሞን ነበር ስልኩን ያነሳው
‹‹ሄሎ››
‹‹ሄሎ..ሰላም ነሽ?››
‹‹አዎ ሰላም ነኝ …እንድትመጡ ፈልጌ ነው››
‹‹ማን…..? ››
‹‹እናንተ ናችሁ…. ሁለታችሁም››
‹‹ለምን…..? ምን ተፈጠረ…..?››
‹‹ላደርገው ነው…ማድረግ የምፈልገው ደግሞ እያያችሁ ነው..እናንተ ባላችሁበት››
‹‹አረ ችግር የለውም ..ሁሉን ነገር ካጠናቀቅሽ በኃላ ብትደውይልን ይሻላል››
‹‹እንደዛ አላደርግም…በቃ አሁን በነፍስ ነው ብዬ እንደደወልኩላችሁ አስቡትና እቤትም ሆነ መንገድ ላይ ለገኛችሁት ሰው እንዲሁም ለሌሎች ዘመዶቻችሁ እየደወላችሁ በነፍስ ነው ተብሎ ተደውሎልናል እያላችሁ ንገሩ ፣እናንተም በ20 ደቂቃ ውስጥ ድረሱ›
‹‹አዎ… በቃ ገባኝ እንመጣለን..ትክክል ነሽ››ስልኩ ተዘጋ
ሁለቱ ብቻ ሳይሆኑ በሌሎች ከስድስት በማያንሱ ሰዎች ታጅበው ለመምጣት ከ15 ደቂቃ በላይ አልፈጀባቸውም…..ሰላም ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት ሆስፒታሉን አተረማመሰችው….ሰሎሞንም እንባውን እየዘራ ወንድሜን እያለ በማጎራት ግቢውን መዞር ጀመረ…
ለስድስት ቀን በኮማ ውስጥ የሰነበተው መላኩ ምን እንደነካው ከዶክተሩና ከሰሚራ ውጭ ማንም በማያውቀው ምክንያት በጣር ነፍስ ጊቢ ነፍስ ውጭ እያቃተተ ነው…ዶ/ር እስክንድር ሲስተር ሰሚራ እና ሌሎች ሁለት ነርሶች ዙሪያውን ከበው ሊረዱት እየሞከረ ነው..
‹‹ሲስተር ሰሚራ ቶሎ ብለሽ ይሄንን መድሀኒት ውጊው ››ብሎ በወረቀት ላይ የመድሀኒቱን ስም ጽፎ ሰጣት… እሷም ተቀብላ ቶሎ ብላ ወጥታ ሄደችና በሶስት ደቂቃ ውስጥ ይዛ መጣች… መዳሀኒቱን በተንጠለጠው ግሉኮስ ከረጢት ውስጥ በስሪንጅ መጣ ለቀቀችበት ..ቀስ እያለ በቱቦ ውስጥ በመንጠባጠብ ከደም ስሩ ተቀላቀለ…. ከደቂቃዎች በኃላ የበሽተኛው ጣር እየቀነሰ …መንፈራገጡም እያቆመ መጣ….ከዛ ፀጥ አለ …ሰው ሲሸነፍ ወይም ሲያፈገፍግ ፀጥ ይል የለ….ዶ/ር እስክንድር በማዳመጫ ትንፋሹ አዳመጠው…እጆቹና እያወናጨፈ አንገቱና ቀብሮ በብስጭት ክፍሉን ለቆ ወጣ …ኮሪደር ላይ እነ ሰሎሞን እና አጃቢዎቻቸው ከበቡት.
‹‹ዶክተር..እንዴት ነው በሽተኛው…..?››
‹‹ዶክተር ይሻለዋል ..ፍቅሬ ይድናል…..?››
ለበራካታ ሰከንዶች ተገትሮ ሰላምን አፍጦ ከማየት ውጭ ምንም መናገር አልቻለም፣‹‹….….ይቺን ላየ ሰው እነ ሰላም እና መሀደር ምኑን አክተር ተባሉት ?››ሲል በውስጡ አሰበ…መለስ ብሎም ስለራሱ አሰበ …ወየው ጉድ እኔም ለካ ሌላ ተዋናይ ሆኜያለሁ…አለም ሰፊ መድረክ እኛም ኑሪዎቾ ተዋናዬች ነን ያለው ማን ነበር …..? ለካ እውነት ነው…›አለና ወደቀልብ በመመለስ ለእነሱ ጥያቄ መልስ መስጠት ጀመረ
‹‹አዝናለሁ የተቻለንን አድርገናል…ግን አልተሳካልንም..አርፏል ››ብሎ በተገተሩበት ጥሎቸው እግሮቹን አንቀሳቀሰ … ግቢውን በጩኸት እና በለቅሶ ሲያደበላልቁት በውስጡ እየተጠየፋቸው እና እየረገማቸው ጥሎቸው ወደ ቢሮው ሄደ
ሰላም…
..ፍቅሬ ፍቅሬ…
እንጋባለን ብለሀኝ አልነበረ ወይ…
ሙሽራዬ ነሽ አላልከኝም ነበር ወይ..
ለማን ተውከኝ..ለማን ተውከኝ
ሰሎሞን……
ወንድም ጋሻዬ ….ወንድም ጋሻዬ
የእኔ ብቸኛ..የእኔ ብቸኛ
የአባቴ ምትክ ..የአባቴ ምትክ
የዓይን ማረፊያዬ….
/////
ከደቂቃዎች በኃላ ሬሳው እየተገፋ ተመላካቹን በእንባ በሚያራጭ እንግሩጉሮአዊ ዜማ እና አንጀት በሚበላ ሁኔታ በሚያለቅሱት እና ኩርምት ጭብጥ በሚሉት በወንድሙ ሰሎሞን እና በፍቅረኛው ሰላም መካከል አልፎ ወደሬሳው ክፍል ተወሰደ…..ሰሚራም እየተንቀጠቀጠች እና እየዘገነናት እራሷን ለማረጋጋት በትርምሱ መሀል ተሹለክልካ ከሁሉም ነገር በመሸሽ ቢሮዋ ገብታ ተሸጎጠች
እስከአሁን የሰራችው ስራ እና የፈጠረችው ተግባር ትልቅ ድንጋጤ ውስጥ ከቷት እየተንቀጠቀች ነው..የሚገርመውና ይበልጥ የሚጨንቀው ግን ከአሁን በኃላ የምትሰራው ስራ ነው…
በበቀልም ሆነ በጥላቻ ተነሳስቶ ሰውን ድፍት አድርጎ መግደል በጣም ቀላል ነው…ሳያስበው በሆነ ብረት ማጅራቱን መጠቅለል እና ዝርግፍ ብሎ ሲወድቅ ጭንቅላቱን በድልዱም ብረት መድገም ነው…አዎ እንደዛ ማድረግ ቀላል ነው… የሚከብደው ከገደሉት በኃላ ያለው ነገር ነው፡፡ሬሳውን ምን ላድርገው…?ግቢው ውስጥ ቆፍሬ ልቅበረው..….?ረሀብ ያንገላታው ውሻ ቆፍሮ አውጥቶ ቢያጋልጠኝስ…?በጆንያ አድርጌ ከከተማ አውጥቼ ራቅ ያለቦታ በመውሰድ ጫካ ውስጥ ልጣለው…?.መንገድ ላይ ፖሊስ ለፍተሻ ቢያስቆመኝስ……..?እንደዛ ሳደርግ ሰው ቢያየኝስ……..?ስቃይ ነው….በዛን ቅጽበት ከሟቹ በላይ ገዳዩ ያሳዝናል…በተለይ ገዳዩ እንደእሷ አማትር ገዳይ ሲሆን ......ሁኔታው እንደቅዣት ሆኖባት፤ በውስጧ ስትብሰለሰል ስልኳ ተንጫረረ….
ከፈጣሪ የተደወለባት ነው የመሰላት….በርግጋ ከተቀመጠችበት በመነሳት ተፈናጥራ ቆመችና የደዋዩን ማንነት ለደቂቆች አትኩራ ተመለከተች…. በፈራ ተባ ስሜት አነሳችው
‹‹አቤት››
‹‹የት ገባሽ…..?››
‹‹አለው ፈርቼ ቢሮዬ ቁጭ ብዬ ነው››
‹‹ምን ያስፈራሻል.…..?.››
‹‹እንዴ ድመት እኮ አይደለም ሰው ነው ያስገደላችሁኝ…..››
‹‹ማለቴ መግደልሽን ማን ያውቃል..…..?እንደውም ስትፈሪና ስትንቀጠቀጪ የስራ ባለደረቦችሽ እንዳይጠረጥሩሽ…በተለይ ዶክተሩ እንዴት ሞተ ……..?ይሞታል ብለን አልገመትንም ነበር ሲል ሰምቼዋለሁ››
‹‹እ!! እንደዛ አለ እንዴ…..? ››
‹‹አዎ ብሏል…ለማንኛውም አሁን ምን እናድርግ.››
‹‹ምን ለማድረግ አሰባችሁ?››
‹‹ሬሳውን አሁኑኑ ብትሰጡንና በጥዋቱ ቶሎ ብለን ብንቀብረው ጥሩ ነው፡፡››
‹‹ሬሳውንማ ላሰጣችሁ አልችልም …ጥዋት ነው መውሰድ የምትችሉት››
‹‹አይ አሁኑኑ መውሰድ አለብን… አሁን ሬሳ ሳጥን ገዝተው እንዲመጡ ሰዎች ልኬያለሁ…አንቺ ብቻ ደክተሩን አሳምነሽ እንዲፈርምልኝ አድርጊ…››
‹‹ዶክተሩ እኮ መሞቱን ብቻ ነው የሚያረጋግጥልህ….ሬሳውን በዚህ ምሽት እንድታወጣ የመፍቀድ ስልጣን ያላቸው ግን ሌሎች ናቸው››
‹‹ሌሎቹን ተያቸው ..ዶክተሩ ብቻ ካስፈረምሽልኝ ካንቺ ምንም አልፈልገም…..ወደቤትሸ ሄደሽ ተረጋግተሸ በድል መተኛት ትችያለሽ…የስራ ኮንትራታችንን እዛ ላይ ይጠናቀቃል….››
‹‹እዛ ላይማ አይጠናቀቅም … መቶ ሺ ብር ጨምርልሻለው ብለኸኝ ነበር››
‹‹ሀይለኛ ብር ወዳድ ልጅ ነሽ… አይዞሽ አረሳሁትም ግን እንደምታይኝ አሁን ሀዘን ላይ ነኝ ፡፡ ከሶስት ቀን በኃላ ያው እንደምንም መጽናናቴ ስለማይቀር አቀብልሻለሁ…››
‹‹ዋ እንዳትረሳ››
‹‹አረሳም አሁን ያልኩሽን ጨርሺና ደውይልኝ››
ስልኩ ተዘጋ……
✨ይቀጥላል✨

👍122❤14👎9👏4🔥1🥰1
#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ትንግርት ዶ/ር ሶፊ ክስ ስላልመሰረተችባት ሰሎሞን እና ኤልያስ ተሯሩጠው ከእስር እንድትፈታ አደረጉ፡፡አሁን ስለቀጣይ እቅዳቸው ያረፉበት ፔንሲዬን ውስጥ ።ቁጭ ብለው እተመካከሩ ነው፡፡
‹‹ቀጣይ እቅዳችን እንዴት ነው?፡፡››ኤልያስ ጠየቀ፡፡ጥያቄው ለትንግርት ነው የተሰነዘረው፡፡
‹‹ሰሎሞንና ሶፊያ ወደ አዲስ አበባ ይመለሱ፤እኔና አንተ የመጣንበትን ስራ መስራት እንቀጥላለን፡፡›› ውሳኔው የትንግርት ነው፡፡
‹‹እኛ ከመሄዳችን በፊት ከልጅቷ ጋር ያለውን ነገር መጨረስ አለብን፡፡›› አለ ሰሎሞን፡፡
‹‹እንዴት አድርጋችሁ ነው የምትጨርሱት?››
‹‹እናስታርቃችኋለና፤ይቅር ተባባሉ፤ከይቅርታ በላይ ምን አለ.?››ሰሎሞን ነው ተናጋሪው፡፡
‹‹እኔና እሷ በራሳችን የጀመርነውን ጊዜው ሲደርስ በራሳችን እንጨርሰዋለን፡፡ለድርድር የሚያመች ችግር አይደለም በመሀከላችን ያለው፡፡››
‹‹እኛ እኮ ኢትዮጵያዊያን ነን፤ምን አልባት ለአቅመ ሽምግልና አልደረሳችሁም ካላልሽን በስተቀር በባህላችን መሰረት በሽማግሌ የማይፈታ ምንም አይነት ችግር የለም፡፡››አላት ኤልያስ፡፡
‹‹ለሽምግልና ብቁ ናችሁ፤እንዳልከውም እኛ ኢትዬጵዊያን በሽምግልና የማይፈታ ችግር የለንም፤ክፋቱ የእኔና የእሷ ችግር ኢትዬጵያዊ አለመሆኑ ነው፡፡››
‹‹ስለዚህ የፈረንጅ ሽማግሌ ካልመጣ አሻፈረኝ እያልሽ ነው?››አላት ሰሎሞን፡፡
በዚህ መካከል የትንግርት ስልኳ ጠራ ..ከውጭ ነው፤ወደ ውጭ ወጣችና አነሳችው፡፡
‹‹ሀይ ማሬ፡፡››
‹‹አለሁ ...ተፈታሽ አይደል?በጣም ተጨንቄ ነበር፡፡››
‹‹አይዞኝ ..አሁን ሁሉ ነገር ተስተካክሏል፡፡ ተፈትቼያለሁ፡፡››
‹‹በዋስ ነው የተለቀቅሽው?››
‹‹አይደለም ..ስላልከሰሰችኝ በነፃ ነው የለቀቁኝ፡፡››
‹‹እሺ በቃ ከአምስት ቀን በኃላ እመጣለሁ፡፡››
‹‹ምን? ወዴት ነው የምትመጣው?››
‹‹ወደ ኢትዮጵያ ነዋ፡፡››
‹‹ለምን ?ትምህርቱስ ?››
‹‹ለጊዜው አቋርጬው፡፡ >>
«ለምን?»
‹‹በቃ ..በዚህ ጊዜ ከጎንሽ መሆን እፈልጋለሁ?››
‹‹አልገባኝም ሁሴን?››
‹‹በቃ ወደ አንቺ መመለስ እፈልጋለሁ፤ከትምህርቱ በላይ አንቺ ታስፈልጊኛሽ፡፡››
‹‹እኔማ አለውልህ..ትምህርትህን ጨርሰህ በመጣህ ጊዜ ታገኘኛለህ፡፡››
‹‹በዛ እርግጠኛ መሆን አልቻልኩም…<ጅብ ካለፈ..... >እንዳይሆንብኝ መምጣት ይሻለኛል፡፡››
‹‹ፈፅሞ እንዳታደርገው፡፡ይሄንን ትምህርት በጣም ትፈልገው እንደነበረ፤ የተሳካልህም ከብዙ ጥረት በኋላ መሆኑን አውቃለሁ፡፡
በምንም አይነት ሰበብ እንድታበላሸው አልፈልግም፤እኔ እኮ ትንግተርት ነኝ አትርሳ፡፡ በጣም አፍቅሬህ ነው ያገባውህ፤ላጣህም አልፈልግም፡፡››
‹‹የእኔ ፍቅር ..እንደምታፈቅሪኝ በጣም አውቃለሁ…ግን?››
‹‹ግን ምን…?››
‹‹እሷንም ከአቅም በላይ xxxx "እንደነበረ አውቃለሁ፡፡››
‹‹እና ስጋትህ ወደእሷ ትመለሳለች ብለህ ?>>
‹‹እኔ እንጃ፤ ብቻ ውስጤን ፍርሀት ፍርሀት ብሎኛል፤ስሜቴ በረህ አጠገቧ ሁን እያለኝ ነው፡፡››
‹‹እንዳታደርገው፡፡እንኳን አንተ በህይወቴ ኖረህልኝ ብቻዬን ብሆን እንኳን አልሞክረውምከጥፋቱ የማይማር ፈንጅ አምካኝ ብቻ ነው። ይባላል፤ ለማንኛውም ማታ ደውልልኝና እናወራበታለን፡፡››
‹‹ማር አትልፊ... ትኬት ሁሉ ቆርጪያለሁ፡፡››
‹‹እብድ እኮ ነህ.... በጣም የማትረባ እብድ፤በል ቻው፡፡››
‹‹ቻው አፈቅርሻለሁ፡፡››
ስልኩን ዘግታ በንዴት ጬሳ፣ደም ስሯ ተወጣጥሮ ወደክፍል ስትመለስ ሁሉም ደነገጡ‹‹ምን ሆንሽ ደግሞ ?››አለቻት ፎዚያ፡፡
‹‹ምን ሆናለሁ….ይሄ እብድ ወንድምሽ ነዋ!!››
‹‹እሱ ደግሞ ምን አረገሽ?››ጠየቃት ሰሎሞን፡፡
‹‹እመጣለሁ እያለ ነው?››
<<ለምን?»
‹‹እኔ እንጃለት?››
ሁሉም ፀጥ አለ፡፡‹‹...በቃ ሁለታችሁ ተነሱና ሂዱ..ኤልያስ አንተ ደግሞ ታዲዬስ ጋር ደውልለት እና ቀጠሮ አሲዝልን፡፡››
‹‹ደውዬለት ነበር ፤1ዐ ሰዓት ይመቸኛል ብሏል፡፡››
‹‹ጥሩ ነው፤በሉ ተነሱ እንውጣ›› ብላ ቀድማ ክፍሉን ለቃ ወጣች፤ ሶስቱም ተከተሏት፡፡
ትንግርትና ኤልያስ በትንግርት መኪና ፣ ፎዚያ እና ሰሎሞን ደግሞ በሰሎሞን መኪና ሆነው የፔኒሲዬኑን ግቢ ለቀው ወጡ፡፡ምሳ በልተው ሊለያዩ ነበር ዕቅዳቸው፤ምሳ ለመብላት የፈለጉበት ሆቴል ከመድረሳቸው በፊት የሰሎሞን ስልክ ጠራ፤ከአዲስ አበባ ነው ፡፡ የኤደን እህት ነች የደወለችለት፡፡መኪናውን ጥግ አስይዞ አቆመውና ስልኩን አነሳው፡፡
‹‹ሄሎ ሂሩት ሰላም ነው?››
‹‹ሰላም አይደለም.፤ኤዲን አሞት ሆስፒታል ተመልሳለች፡፡›››
‹‹ምን ሆነች..?ማለቴ እንዴት አደረጋት?››
‹‹እኔ እንጃ ሶል፤ጠንከር ያለ ይመስለኛል ፤ኦፕራሲዬን መደረግ አለባት ብለዋል››
<<ምን>?>>
‹‹አዎ !!በአንድ ሰዓት ውስጥ ኦፕራሲዬን መደረግ አለባት እያሉ ናቸው፡፡››
‹‹ምነው ? ጽንሱ ሰላም አይደለም እንዴ? >>
‹‹እኔ እንጃ ፤ ስለእሱ ምንም አላሉኝ፤መምጣት ብትችል ?>>
<<እየመጣሁ ነው..ቻው፡፡ እስክደርስ ሁኔታውን እየተከታተልሽ ደውይልኝ፡፡›› ብሎ ስልኩን ዘጋውና መኪናውን አስነሳ፤ እነትንግርትም ከኋላው መኪናቸውን አቁመው ሲጠብቆቸው ነበር ፤መኪናውን ሲያንቀሳቅስ እነሱም አንቀሳቀሱ፡፡
‹‹ሰላም አይደለም እንዴ?››ፎዚያ ጠየቀችው ፡፡
<< አዎ ኤደንን በጣም አሞታል ነው ምትለኝ፤ ለእነ ትንግርት ደውይና ንገሪያቸው.. ምሳው ይቅርብን ፡፡››
‹‹እሺ ችግር የለም፡፡›› ብላ ሞባይሏን አወጣችና ኤልያስ ጋር ደወለችለት፡፡
‹‹ምሳው ይቅርብን ልንወጣ ነው፡፡››
‹‹ምነው ?››
‹‹ኤደን አሞታል ብለው ከአዲስ አበባ ደወሉልን ፤ በቃ ቻው እናንተ ብሉ፡፡››ብላ ተሰናበተችው፡፡
ሰሎሞን በመጨረሻ ፍጥነት እየከነፈ ሻሸመኔ ከተማ ሊገባ 3 ኪሎሜትር ያህል ሲቀረው ድንገት ወደኃላው በአስፖኪዬ ሲመለከት የትንግርትን መኪና ተመለከታት፡፡
‹‹እንዴ እነትንግርት ተከትለውናል፡፡››ብሎ ለፎዚያ እየነገራት የመኪናውን ፍጥነት ዝግ አደረገ ፎዚያም አንገቷን ወደኃላ አዞረችና ተመለከተች ‹‹እውነትም እነሱ ናቸው፡፡››
ጠበቃቸውና አንገቱን በመስኮት በማውጣት‹‹ምን እየሰራችሁ ነው?››ሲል ጠየቃቸው፡፡
‹‹ወደ አዲስ አበባ እየሄድን ነዋ››
«ለምን?»
‹‹ባክህ ቀጥል.. ኤደን ታማለች እያላችሁን እንድንቀር ትፈልጋለህ?››
‹‹ስራውስ... ?››
‹‹ይደርሳል ፤እንደውም ተረጋግተን ሌላ ጊዜ እንመለሳለን ፤ይልቅ ቀጥል ጊዜ አታባክን >> ብላው አልፍው ሄደች፡፡
‹‹አዲስ አበባ ጋንዲ ሆስፒታል ሲደርሱ ከቀኑ 11 ሰዓት ሆኖ ነበር፡፡››
የኤደን እና የእሱ ጓደኞች፤የእሷ ቤተሰቦች ኮርደሩን ሞልተውታል፡፡የሁሉም ፊት ጨልሟል ፡፡የሆነ የተበላሸ ነገር እንዳለ ወዲያው ገባው፡፡
በነትንግርት እንደ ታጀበ ተንደርድሮ ወደ እህቷ ቀረበ‹‹ሂሩት ምንድነው የተፈጠረው? ኤደን ደህና ነች?››
ቃላት ከማውጣቷ በፊት እንባዋ ቀደመ..ሳግ ተናነቃት፡፡
‹‹ምን ሆነች ...?ምን ተፈጠረ ….?ንገሪኝ እንጂ?>
‹‹እሷ ደ..ህና ነች፡፡››
‹‹እና ታዲያ…?››
‹‹አዝናለሁ ሶል..…ልጁ ጠፍቶባታል፡፡››
<<ምን?>>
‹‹አዎ ሶል…፡፡››

👍87❤11