#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
ድንገት ሮሐ ወደ ፊት ሰገግ ብላ ሹከሹክታ በሚመስል ድምፅ “ለምን መሐሪ …ለምን?” አለችው፡፡ ፊቷ ተቀያይሮ እንደ ቲማቲም ቀልቷል፡፡
“ለምን ምን አላት ምንም ሳይመስለው ፈገግ እንዳለ፡፡
ለምን ሳሌምን.....
ባኮሽ አታካብጅው ያጋጥማል!” አለ ትከሻውን ወደላይ በግዴለሽነት ጎፋ እድርስ፡፡
የመሐሪን ቆዳ ለብሶ የለየለት ወንጀለኛ ከፊታችን የተቀመጠ እስኪመስለኝ ድረስ፣ ፊቱ ላይ ትንሽ እንኳን ጸጸት አልነበረም፡፡ መሐሪ የዕድሜ ልክ ጓደኛዬ በአንድ ወር በምን ተአምር እንዲህ ዓይነት አስፈሪ ሰው እንደሆነ ሳወጣ ሳወርድ አልገባህ አለኝ፡፡ቢጨንቀኝ፣ ቀጥሎ ምን ይፈጠር ይሆን በሚል ግርምት፣ አንዴ ሮሐን አንዴ መሐሪን ማየት ጀመርኩ፡፡
“ምኑ ነው የሚያጋጥመው ሕፃን'ኮ ናት፣ እናተን አምና የተጠጋች ምስኪን ሕፃን
ትንሽዬ ልጅ…ትንሽ …" ሮሐ የምትለው ጠፍቶባት ፍጥጥ ብላ ከንፈሯ እየተንቀጠቀጠና ዓይኗ እንባ ሞልቶ ስትመለከተው፣ ምንም በማይነበብበት ፊት ትክ ብሎ እያያት፣
ጠጥቸ ነበር፣ አንች ያመጣሽውን ውስኪ ጠጥቼ ነበር፡፡ በዚያ ላይ ትንሽ አሰሳጭተሸኝ ነበር፡፡ሁለታችሁም አበሳጭታችሁኝ ነበር” ብሎ ወደ እኔም ወደሷም ጠቆመና፣ “…በቃ የሆነው ሆነ…ይኼ አዲስ ነገር አይደለም፡፤ በኔ አልተጀመረም ብሎ ተራ በተራ አየን፡፡
ፈገግታው እስከዚያ ሰዓት ድረስ ሙሉ ለሙሉ አልከሰመም ነበር፡፡
እና ደፈርካት….” ብላ አንባረቀችበት፡፡ ድምፅዋ፣ እንኳን ድንገት የሰማውን፣ እኔም ጉዳዩን እየተከታተልኩ ያለሁትን የሚያስደነብር ነበር፡፡ በዙሪያችን የነበሩት ሁሉ ወደ እኛ ዙረው አዩን፡፡ መሐሪ አቀርቅሮ የእጁን መዳፍ እያገላበጠ ተመለከተና፣ ድንገት ተነስቶ
ቆመ፡፡
“ተቀመጥ አልጨረስንም? አለች ከመጀመሪያው በባሰ ጩኸት! ፖሊሶቹ ወደኛ እየመጡ ነበር፡፡
መሐሪ ልክ እንደሷ ጮሆ “ሁለተኛ እንዳትመጡ እዛው የራሳችሁን ሕይወት ኑሩ አለን፡፡ ግራ ተጋብቼ እንደተቀመጥኩ፣ ሮሐ ዘላ ተነስታ ቲሸርቱን ጨምድዳ አነቀችና፣ ባለ በሌለ ኃይሏ ቱ!” ብላ ምራቋን ፊቱ ላይ ተፋችበት፡፡ ከዚያ በኋላ እንደ እብድ መጮህ ጀመረች፡፡ ግራና ቀኝ የቆሙት ፖሊሶች አንቀው ወደኋላ ሲጎትቷት እካባቢው ድብልቅልቁ ወጣ፡፡
አንተ ደደብ! ምንም የማታውቅ ሕፃን ገድለህ፣ ደረትህን ትነፋለህ! መሃይም …ቱ! እዚህ ልትሸለም የመጣሀ መሰለህ? እስር ቤት የሚያኮራህ አንተ ማንዴላ ነህ? ለነፃነት ስትታገል ታስረህ ነው?…ወንጀለኛ ወንጀለኛ ሁነህ ነው! አንዲት ደሀ ቆሎ ሸጣ ያሳደገቻትን ሕፃን ደፍረህ! ዕድሜ ልክህን እዚህ ትበሰብሳለህ ቆሻሻ ኢዲየት! ልቀቁኝ ይኼን ውሻ ድንገት ጫማዋን ባልተያዘው እጁ አውልቃ ስትወረውር፣ መሐሪ ደረት ላይ አረፈ፡፡ ጥሩ ምት ነበር! ሌላ የሚወረወር ነገር ስትፈልግ፣ አንዱ ፖሊስ ሁለት እጇን አነባብሮ ጠፍንጎ ያዘና፣ እየገፈተረ ከእስረኛ መጠየቂያው ክልል ወደ ውጭ ወሰዳት፡፡ እየጮኸች ነበር
“ቆሻሻ ነህ! ራስሆን ነው የናከው! እብድ! ትንሽ ለቤተሰቦችህ አታዝንም? ውሻ
በተቀመጥኩበት እንደ ጨው አምድ ደርቄ ቀረሁ፡፡ መሐሪ የተወረወረበት ጫማ፣
ያረፈበት ቦታ ላይ ቲሸርቱን ተረጋግቶ አራገፈና፣ ጫማውን አንስቶ “ውሰድላት” ብሎ ሰጠኝ፡፡ ተቀበልኩት፡፡ በተረጋጋ እርምጃ ወደ ውስጥ ሲገባ፣ ከዓይኔ እስኪሰወር ተመለከትኩት፡፡ ዞር እንኳን አላለም፡፡ ፈጽሞ የማያውቀኝ ሰው ነበር የሚመስለው፡፡ በቃ የእድሜ ልክ ጓደኝነት ይኼው ነው …ጫማውን እንከርፍፌ እንደያዝኩ፣ እግሬን እየጎተትኩ ወደ ሮሐ ሄድኩ፡፡ አራት የሚሆኑ ፖሊሶች ከበዋት በየአፋቸው ይጮሁባታል፡፡ “አንች ያምሻል እንዴ? …የሕግ ታራሚ ልትደበድቢ ነው? ምኗ ጥጋበኛ
ናት! " ድንገት ቁጭ ብላ እራሷን ይዛ እዬዬዋን አስነካችው፡፡ ሌላኛው ፖሊስ ነገረ ሥራው አለቃ የሚመስል በእጁ መገናኛ ሬዲዮ የያዘ፣ ወደኔ በሬዲዮው አንቴና እየጠቆመ
“የጋሽ ግርማ ልጅ ናት አይደል” አለኝ፡፡ እራሴን በአዎንታ ነቀነቅሁ፡፡
“በል ይዘሃት ውጣ፡፡ ተነሽ አንች ውጭ !…” ብሎ ኮስተር አለ፡፡ ልይዛት ስሞከር እጇን መንጭቃ ተነሳችና፣ ጫማዋን አድርጋ ቀድማኝ መንገድ ጀመረች፡፡ ተከትያት ወጣሁ፡፡
ከዋናው በር እንደወጣን በጩኸት “አንድ ወር በሥርዓት እንኳን መተኛት አልቻልኩም በሽተኛ ነው የሆንኩት፣ ልክ አይደለሁም! ራሴን ስረግም ስጸጸት ነው የከረምኩት፡፡ ቢያንስ ትንሽ ጸጸት ፊቱ ላይ የማይ መስሎኝ ነበር፡፡ ራሴን ተጭኜ ይቅር ልለው፣ በዚህ ሰዓት ማንም ከጎኑ የለም ብዬ” ድንገት ወደ እስር ቤት የሚገቡ ስዎች አፍጥጠው እንደ
እብድ ሲመለከቷት ቆም ብላ፣
“ምን ሆናችሁ? ሰው አይታችሁ አታውቁም?” ብላ ስታምባርቅባቸው እንደ እብድ ሸሹን፡፡
"ሮሐ ተረጋጊ"
አታረጋጋኝ ..አልፈልግም፤ ማንም ተረጋጊ ምናምን እንዲለኝ አልፈልግም፡፡ ያሳለፍኩትን ራሴ ነኝ የማውቀው …”
“ይገባኛል…”
አይገባህም?
“ምንድነው የሚገባህ? ዳዲ፣ ሽጉጥ…ሽጉጥ ነው ያወጣብኝ! ለምን እሱን አፈቀርሽ ብሎ፡፡ እንደዛ ስላስፈራራኝ አቆምኩ? አላቆምኩም! ለምን? እወደው ነበራ! ምንድነው ችግሩ? ምንድነው እየሆነ ያለው? ምንም ሊገባኝ አልቻለም! …ምንም!! ታምነኛለህ? አፍ
አውጥቼ ሴክስ እናድርግ ብዬው አውቃለሁ፣ የፈራ መስሎኝ ልብሱን ላስወልቀው ታግዬዋለሁ፡፡ ሴት እንደዛ ታደርጋለች? አታደርግም! ሁሉን ነገሬን ለሱ መስጠት የመጨረሻ ደስታዬ ነበር፡፡ ምን ስለሆነ? ቆንጆ ስለሆነ…ምን ቆንጆ ነው? ጥሙጋ! ሃብታም ስለሆነ?…ምንም! በቃ ስላፈቀርኩት፡፡ ከመሳሳም አልፎ አያውቅም! እንደፈለክ አድርገኝ ብየዋለሁ …ከዚህ ወዲያ ምን ላድርግለት? ለምን ይቀናል? ለምን? እንደሚያፈቅረኝ ይነግረኛል፣ ቆንጆ እንደሆንኩ ይነግረኛል፡፡ አንችን ካላየሁ፣ ነፍሴ መንፈሴ ሲለኝ ነው የኖረው፡፡ የፈለገ ቢጠጣ በርሚል ሙሉ ቢጠጣ …ምን ሁኖ ነው አንዲት ሕፃን….በሽተኛ ነው! …በሽተኛ አስተዳደጉም ምኑም በሽተኛ በራሱ
የማይተማመን ስቱፒድ ያ እኔም በሽተኛ ነኝ በዚህ ዕድሜው መጸዳጃ ቤት ለመሄድ
እንኳን አባቱን የሚያስፈቅድ ልጅ፣ ጤነኛ አለመሆኑን እንዴት አላውቅም !በራሱ ቤት በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ የሚኖር በሽተኛ ቱ.. ጮሃ ጮሃ ሲወጣላት ትከሻዬ ላይ ተደፍታ ስቅስቅ ብላ አለቀሰችና፣ እኔ ምንም አላልኩትም የዛን ቀን ምሽት በእኔ
ምክንያት የሆነ እየመሰለኝ በጭንቀት ልሞት ነው. ያንን ውስኪ ማምጣቴ፣ በየቀኑ በየቀኑ ይጸጽተኛል” አለችና ማልቀስ ቀጠለች፡፡
“የዚያን ቀን ምሽት ነበርኩኮ እኔ ምስክር ነኝ …ሁሉም ነገር፣ የራሱ ችግር ነው፤ አንድም ነገር አላጠፋሽም፡፡ እመኝኝ፣ ላፅናናሽ እይደለም እንዲህ የምለው! ምንም ያጠፋሽው ነገር የለም፡፡ ራስሸን የምትወቅሽበት ምንም ምክንያት የለም! ውሸቱን ነው የቀባጠረው፤ የራሱ
ችግር ነው፣ የራሱ!” ከልቤ ነበር እንዲህ ያልኳት! ንግግሬ አጽናንቷት ይሁን፣ አልያም ለቅሶዋን ጨርሳ የዚያን ቀን እንባዋን ጠራርጋ ወደቤቷ ሄደች፡፡
ልቤ በመሐሪ ማዘኑን ትቶ “የራሱ ጉዳይ!” የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሶ ነበር፡፡
እግዚአብሔር የመሆን ፍላጎቴን ትቼ እንዲያውም ቀሪ ዘመኔን ሁሉ እንደ ሰይጣን በሰዎች ሁሉ ላይ ከፉ ለመሆን ተመኘሁ፡፡ ሰው የሚባል ፍጥረት ተለቃቅሞ ሲኦል ቢወረወር ሲያንሰው ነው፡፡ ሰበበኛ ሁሉ፡፡ መሐሪ ሳሌም ላይ ላደረገው ነገር ሁሉ እኔና ሮሐን መውቀሱ፣ ውስጤን ቢያቃጥለውም፣ በዚህ ጉዳይ በቃ አያገባኝም ብልም፣ ሳሌም ግን ትናፍቀኝ ነበር፡፡ የእውነት ትናፍቀኛለች፡፡ ሳቋ ይናፍቀኛል፣ ከእናቷ እቅፍ
ጀምሮ በዓይናችንና በነፍሳችን እቅፍ

👍4😁1
ያደገች ውብ ነፍስ፡፡ ትንሽ ደግሞ በተፈጠረው ነገር እጄ ያለበት መሰለኝ፡፡ ሌላው ይቅር፣ መሐሪን አትጠጣ ማለት አልችልም ነበር? ውስኪውን አልጠጣም ሲልና ሮሐ እንዲጠጣ ስትገፋፋው ዞር ብሎ አይቶኝ ነበር፡፡ ፈገግ ብያለሁ! መሐሪ ምን ጊዜም አንድ ነገር ሊያደርግ ሲፈራ፣ ዞር ብሎ ያየኛል፡፡ ፈገግ ካልኩ ያደርገዋል በየትኛውም መዝገበ ቃላት ያልተመዘገበ ጓደኝነታችን ገጽ ለይ ብቻ የተጻፈ ቃል ነበር አድርገው የሚል፣ ምናለበት የሚል፣ ሞክረው የሚል፣ የይለፍ ፈገግታ፡፡
ወደ ዩኒቨርስቲ ከመሄዴ በፊት፣ ሳሌምን አንዴ ላያት ብፈልግም አልተሳካልኝም፡፡
የተደፈረች ሕፃን ልጅ ምን ትመስል ይሆን እያልኩ ብዙ አስቢያለሁ … ከዚያ በኋላ ቁማ ትሄዳለች? ከሰው ጋር ታወራለች? ትስቃለች? ምን መስላ ይሆን? በጣም ላያት እፈልግ ነበር፡፡ ግን እንደገና ሳሌምን የማየት ዕድል የገጠመኝ ከአስራሦስት ዓመታት በኋላ ነበር፡፡ የሷም ልጅነት የእኔም ወጣትነት አልፎ፣ ሌላ ዓለም ውስጥ ሌላ ሰዎች ሆነን፣ ግን ደግሞ ነበራችን ላይ በተዘረጋች ቀጭን ክር ላይ ስንራመድ፣ ያኔ ነው እንደገና የተገናኘነው አንዴ በሕይዎት ውስጥ ያወቅናቸውን ሰዎች ከናካቴው መርሳት እና፣
ከሕይወታችን ማስወጣት አንችልም፡፡ ሌላው ሁሉ ቢቀር፣ እንደ ሸረሪት ድር የቀጠነች ነፋስ የሚወዘውዛት የትዝታ ክር ቀመካከላችን ትኖራለች፡፡
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ

👍1
#አይቆምም_ዘፈኑ
የመከራ ሰርዶ
የመከራ ተክል
አንድ ርምጃ ሲሳብ፣ አምሳ መሰናክል
ሲገጥመው የኖረ
ጨርሶ መክሰምን፣ በትግሉ የሻረ
ሰው የፍጥረት ቁንጮ፣ የተሰጥዖ ሀብታም
እንደ ያሬድ ትል ነው፣ ጨርሶ አይረታም።
ቢወድቅ፣ ከንብል ቢል
ከዘመን መዳፍ ላይ
መች ሊፈርጥ እንደ እንቧይ
እድሜውስ መች አጥሮ
በተስፋ ገንትሮ
በኑሮ ጠጥሮ
ይነሳል ከምድር፣ እንደ ጎማ ነጥሮ።
የሞት ቀንዳም ፈረስ
ላዩ ላይ ቢሰግር
ለያንዳንዱ ጣጣ
ብልሀት ቢቸግር
መፍትሔ ቢታጣ
ደሞ ሲደርስ ቀኑ
ለተዘጉ በሮች
መበርገጃ ቁልፎች
ግልጥልጥ ይላሉ፣ ዛሬ ሲዳፈኑ
ባንቀልባ ይተካል፣ የዛሬው ከፈኑ
ሕይወት ማህሌታይ
ቴፑ ተሰባብሮም፣ አይቆምም ዘፈኑ።
የመከራ ሰርዶ
የመከራ ተክል
አንድ ርምጃ ሲሳብ፣ አምሳ መሰናክል
ሲገጥመው የኖረ
ጨርሶ መክሰምን፣ በትግሉ የሻረ
ሰው የፍጥረት ቁንጮ፣ የተሰጥዖ ሀብታም
እንደ ያሬድ ትል ነው፣ ጨርሶ አይረታም።
ቢወድቅ፣ ከንብል ቢል
ከዘመን መዳፍ ላይ
መች ሊፈርጥ እንደ እንቧይ
እድሜውስ መች አጥሮ
በተስፋ ገንትሮ
በኑሮ ጠጥሮ
ይነሳል ከምድር፣ እንደ ጎማ ነጥሮ።
የሞት ቀንዳም ፈረስ
ላዩ ላይ ቢሰግር
ለያንዳንዱ ጣጣ
ብልሀት ቢቸግር
መፍትሔ ቢታጣ
ደሞ ሲደርስ ቀኑ
ለተዘጉ በሮች
መበርገጃ ቁልፎች
ግልጥልጥ ይላሉ፣ ዛሬ ሲዳፈኑ
ባንቀልባ ይተካል፣ የዛሬው ከፈኑ
ሕይወት ማህሌታይ
ቴፑ ተሰባብሮም፣ አይቆምም ዘፈኑ።
#ኢየሱስ_ሚስቴን_ቀማኝ
እንዲህ እንደዛሬው
ደሞ እንደሁል ጊዜው
የማያውቀው መንፈስ ፥ ወሰድ እያረገው
በሰዎች ተከቦ ; አንድ ሰው ሲነፍገው
የህይወት ታሪኩን...
በቃሌ እስክይዘው ፥ ነግሮኝ የሚወጣ
ከጎኔ ቁጭ ያለ...
አንድ ጎልማሳ አለ ፥ አረቄ እየጠጣ፡፡
"አልወደውም" ይላል...
ስለጌታ ኢየሱስ ፥ ቸርነት ስነግረው
አምነው ነበር” ይላል...
ደግሞ ይነግረኛል !
የበዛ እምነቱ ፥ ብዙ እንደሰበረው፡፡
አያምንም ስብከቴን
ይንቃል እምነቴን ፥ አይሰማኝም ምክሬን
"ያመንኩት ኢየሱስ...
ቀምቶኛል “ይላል : የምወዳት ፍቅሬን፡፡
“መልስልኝ ' ይላል...
የሞተች ፍቅሩን ፥ ስሟን እየጠራ
ያንጋጠል ወደላይ
ይታየዋል ሰማይ
ለሱ አይጋርደውም ያረቄው ቤት ጣራ፡፡
ደግሞ
ደግሞ
ደግሞ
ልጅ አለችው ደግሞ ፥ እናቷን ምትመስል
ፍቅሩን ማታስረሳው ፥ ረስቷት ሊኖር ሲል፡፡
ጠጥቶ ሲሰክር ...
ስሟን እየጠራ ፥ ሁልጊዜ ያለቅሳል
ማመኑን አያምንም ፥ እንደሞተች ያውቃል
"አልሞተችም” ይላል ፥ ከሞተች ቆይቷል
ወደላይ አንጋጦ
ስሙን እየጠራ ፥ “መልስልኝ” ይላል
አሁንም አሁንም
ባረቄ ሊደበቅ ፥ ደጋግሞ ይጠጣል
ደናደር ሳይለኝ
“ከቤት አለች” ብሎ
ወደ ኦና ቤቱ ፥ ለመሔድ ይወጣል
ቤቱ ደርሶ ሲያጣት ፥ ሊጠጣ ይመስል
ይሰጣል
ይጠጣል
“መልስልኝ “ ይላል፡፡
የሚወዳት ሚስቱን ፥ ኢየሱስ ቀምቶት
ረስቷት እንዳይኖር...
እናቷን ምትመስል ፥ አስታዋሽ ልጅ ሰጥቶት
ብዙ ቀን በዙ አመት
አረቄ እየጠጣ ፥ ደም እንባ ያነባል
ከሞተች ቆይቷል ፥ እንዳለች ያስባል
“ይቅርታ ጠይቀህ...
ያወሰድካት ሚስቴን ፥ ልትሰጠኝ ይገባል።”
ይለዋል ለኢየሱስ ፥ አንጋጦ ወደላይ
ጥያቄ ይጭራል
አርፋ በምታምን ፥ በአማኝ ልቤ ላይ፡፡
ያለቅሳል
ያለቅሳል
ያለቅሳል
ያለቅሳል
ሁል ጊዜ ብዙ ዓመት ፥ እምነቴን ሊንደው
እኔ ግን በእምነት ...
“ሁሉን ምትችል አምላክ
ወይ እሷን መልሳት ፥ ወይ እሱን ውሰደው!”
እላለሁ በፀሎት
ሁል ጊዜ ብዙ ዓመት
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
እንዲህ እንደዛሬው
ደሞ እንደሁል ጊዜው
የማያውቀው መንፈስ ፥ ወሰድ እያረገው
በሰዎች ተከቦ ; አንድ ሰው ሲነፍገው
የህይወት ታሪኩን...
በቃሌ እስክይዘው ፥ ነግሮኝ የሚወጣ
ከጎኔ ቁጭ ያለ...
አንድ ጎልማሳ አለ ፥ አረቄ እየጠጣ፡፡
"አልወደውም" ይላል...
ስለጌታ ኢየሱስ ፥ ቸርነት ስነግረው
አምነው ነበር” ይላል...
ደግሞ ይነግረኛል !
የበዛ እምነቱ ፥ ብዙ እንደሰበረው፡፡
አያምንም ስብከቴን
ይንቃል እምነቴን ፥ አይሰማኝም ምክሬን
"ያመንኩት ኢየሱስ...
ቀምቶኛል “ይላል : የምወዳት ፍቅሬን፡፡
“መልስልኝ ' ይላል...
የሞተች ፍቅሩን ፥ ስሟን እየጠራ
ያንጋጠል ወደላይ
ይታየዋል ሰማይ
ለሱ አይጋርደውም ያረቄው ቤት ጣራ፡፡
ደግሞ
ደግሞ
ደግሞ
ልጅ አለችው ደግሞ ፥ እናቷን ምትመስል
ፍቅሩን ማታስረሳው ፥ ረስቷት ሊኖር ሲል፡፡
ጠጥቶ ሲሰክር ...
ስሟን እየጠራ ፥ ሁልጊዜ ያለቅሳል
ማመኑን አያምንም ፥ እንደሞተች ያውቃል
"አልሞተችም” ይላል ፥ ከሞተች ቆይቷል
ወደላይ አንጋጦ
ስሙን እየጠራ ፥ “መልስልኝ” ይላል
አሁንም አሁንም
ባረቄ ሊደበቅ ፥ ደጋግሞ ይጠጣል
ደናደር ሳይለኝ
“ከቤት አለች” ብሎ
ወደ ኦና ቤቱ ፥ ለመሔድ ይወጣል
ቤቱ ደርሶ ሲያጣት ፥ ሊጠጣ ይመስል
ይሰጣል
ይጠጣል
“መልስልኝ “ ይላል፡፡
የሚወዳት ሚስቱን ፥ ኢየሱስ ቀምቶት
ረስቷት እንዳይኖር...
እናቷን ምትመስል ፥ አስታዋሽ ልጅ ሰጥቶት
ብዙ ቀን በዙ አመት
አረቄ እየጠጣ ፥ ደም እንባ ያነባል
ከሞተች ቆይቷል ፥ እንዳለች ያስባል
“ይቅርታ ጠይቀህ...
ያወሰድካት ሚስቴን ፥ ልትሰጠኝ ይገባል።”
ይለዋል ለኢየሱስ ፥ አንጋጦ ወደላይ
ጥያቄ ይጭራል
አርፋ በምታምን ፥ በአማኝ ልቤ ላይ፡፡
ያለቅሳል
ያለቅሳል
ያለቅሳል
ያለቅሳል
ሁል ጊዜ ብዙ ዓመት ፥ እምነቴን ሊንደው
እኔ ግን በእምነት ...
“ሁሉን ምትችል አምላክ
ወይ እሷን መልሳት ፥ ወይ እሱን ውሰደው!”
እላለሁ በፀሎት
ሁል ጊዜ ብዙ ዓመት
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሰባት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
አንዴ በሕይወት ውስጥ እያወቅናቸው ሰዎች ከናካቴው መስራት እና፣ከሕይወታችን ማስወጣት አንችልም። ሌላው ሁሉ ቢቀረሸ እንደ ሸረሪት ድር የቀጠነች ንፋስ የሚወዘውዛት የትዝታ ክር በመካከላችን ትኖራለች።
ጥሩም ይሁን መጥፎ ትዝታዬን በልቤ እንደተሸከምኩ ወደ ተመደብኩበት ዩኒቨርስቲ ተጓዝኩ፡፡ ያለፈ ታሪኬ ሁሉ በየአጋጣሚው እየመጣ ቢረብሸኝም የዩኒቨርስቲ ቆይታዬ ነገሮችን ወደኋላ እንድተዋቸውና በብዙ አዳዲስ ጓደኞች ተከብቤ አዲስ ሕይወት እንድጀምር አድርጎኝ ነበር፡፡ ሕይወቴ በማስታወስና በመርሳት መካከል የቆመች ነበረች፡፡
እጠናለሁ፡፡ብዙ ብዙ ነገር አጠናለሁ፤ ያጠናሁትን ላለመርሳት እታገላለሁ፡፡ በትምህርት ዓለም አለመርሳት ነበር ሰው የመሆን መሠረቱ፡፡ በተለይም በኔዋ አገር የትምህርት ዋጋው አዲስ ነገር ከመፍጠር በላይ፣ የሸመደዱትን አለመርሳት ነበር፡፡ በዚያው ልክ ያለፈ
ታሪኬን ለመርሳት እታገላለሁ፤ ሕይወት ውስጥ ወደፊት የመቀጠል መሠረቱ መርሳት ነበር፡፡ግን ደግሞ ልንረሳ ከምንሞከረው ትላንታችን ለይቶልን እንዳንርቅ፣የሚያስተሳስሩን ቀጫጭን ክሮች አይጠፉም፡፡ ሮሐ አንዷ ክር ነበረች፡፡ ሁለታችንም ዩኒቨርስቲ ከገባን
በኋላ፣ ቶሎ ቶሎ እንደዋወል ነበር፡፡በአምስት ዓመት የዩኒቨርስቲ ቆይታዬ ከመደዋወል በአካል እስከ መገናኘት እንደ ሮሐ የምቀርበው ሰው አልነበረም፡፡ በየጊዜው ስንደዋወል አብዛኛው ወሬያችን ስለየቀኑ ውሏችን ነበር፡፡ ብዙ እናወራለን፣ ሳቅ ለመፍጠር እንታገላለን፡፡
ዩኒቨርስቲ ተጋባሁ በወራት ውስጥ፣ መሐሪ የአስራ ስድስት ዓመት እስር እንደተፈረደበት ሰማሁ፡፡ ተውኩት፣ ረሳሁት፣ ያልኩት የመሐሪ ነገር አንጀቴን አንሰፍስፎት፣ የዚያን ቀን ምሽት ብቻዬን የሆነ ዛፍ ሥር ተቀምጨ አለቀስኩ፡፡ ያዘንኩት አንድ ወንጀል በሠራ ሰው
ላይ ስለተፈረደ ፍርድ አይደለም፣ እኔ እንደጓደኛ፣ ማሚና ጋሽ ዝናቡ ብዙ ዋጋ
ከፍሎ እንዳሳደገ ወላጅ፣ ሮሐ እንደፍቅረኛ፣ አገር እንደ አገር አንድ እንደላባ የሳሳ ንጹህ ነፍስ በአንድ ምሽት አጣን፡፡ ትልቅ ተስፋ፣ ያውም ተስፋውን እውን ከሚያደርግበት አቅም የነበረው ልጅ፣ አሥር ደቂቃ ባልሞላ ስሕተት ከገጸ ምድር ጠፋ፡፡ የመሐሪ ትንንሽ እጆች፣ ፍርሃቱ፣ ከልጆች ጋር ስንጣላ እንኳን፣ በፍርሃት እኔ ሥር መጥቶ ሽጉጥ የሚለው
ነገር፣ ሁሉም ነገር በየተራ እየታወሰኝ …አለቀስኩ:ማልቀስ ብቻ ሳይሆን፣ ብጮህ፣ኡኡ! ማለት አማረኝ፡፡
እዚያው እንደተቀመጥኩ ለሮሐ ደወልኩላት፡፡ በጋራ ለተነጠቅነው ፍቅር ቢያንስ ስሜት እንጋራለን ብዬ፡፡ቀድማኝ ሰምታ ነበር፡፡ ፍልቅልቅ ብላ ያንን ውሻ አስራ ስድስት ዓመት እከናነቡት ሲያንሰው ነው! አለችና በንግግሯ ተበሳጨሁ? ኤልተበሳጨሁም አዘንኩን
አላዘንኩም! ግን ፍቅር የሚባለው ነገር እንዴት ነው ትንሽ እንኳን ቅሪት ሳይተው
እንዲህ ጥርግርግ ብሎ የሚጠፋው? ብዬ ፍቅርን ተጠራጠርኩት፡፡ በዓለም ላይ የነበሩ የሰው ልጅ ሥልጣኔዎች ሁሉ ከምድር ላይ ለደመሰሱ፣ የሆነ ቅሪት ትተዋልኮ፣ ያንን ቅሪት ነው ቅርስ የምንለው፡፡ ስዎች ይህችን ዓለም ሲሰናበቱ፣ ቢያንስ ለሆነ ሰው ልብ
ውስጥ የሆነች ክር ይተዋሉ፣ ወንዞች ሲደርቁ፣ በደረቀ ምድር ላይ የሚተውት ዱካ አለ፡፡በዚያ መልካ ላ ነው ስዎች የሚሻገሩት፡፡ ምንም አሻራ የማይተው ጉዳይ፣ ሲጀመርም የሌላ ነገር ብቻ ነው፡፡ ወይስ የከሸፈ ፍቅር የሚተወው ዳና ጥላቻ ይሆን?
ለዕረፍት ወደ ቤተሰብ ስመለስ፣ ማሚንም ሆነ ጋሽ ዝናቡን ሂጄ አላየኋቸውም፡፡ እናቴ ሂድና ጠይቃቸው ብልግና ነው ብትለኝም፣ እሽ እያልኩ ሳልሄድ ቀረሁ፡፡ ወደ ዩኒቨርስቲ ከተመለስኩ በኋላ፣ አልፎ አልፎ ለማሚ የመደወል ሐሳብ ውል እያለብኝ፣
ስልኬን አንስቼ እንደስሜ ነፍሴ ላይ የታተመውንና መቼም የማልረሳውን የነመሐሪ ቁጥር ከደወልኩ በኋላ፣ ሲጠራ የዘጋሁበት ጊዜ ብዙ ነበር፡፡ ወደኋላዩ ከመዞር ይልቅ፣ ወደፊት ብቻ ለመራመድ ስታገል፣ ከፊቴ የሚያጋጥሙኝ ደማቅ የሕይወት ገጠመኞች ረድተውኝ፣
ትላቴን አደበዘዙት፡፡ ድብዛዜው ከመርሳት የማይተናነስ ነበር፡፡
የሦስተኛ ዓመት ተማሪ ሆኜ አንድ ቀን እቤት ስልክ ስደውል፣ እናቴ በብዙ መንጠራዘዝና የረዘመ ማለሳለስ (እንዲህ ስትሆን ይጨንቀኛል) አሳዛኝ ነገር ነገረችኝ፡፡
ምን ሁነሻል? አባባ ደህና አይደለም እንዴ?” አልኳት፡፡ ቀስ ብላ ጋሽ ዝናቡ ማረፉንና ቀብር ውለው መግባታቸው እንደሆነ ነገረችኝ፡፡ መጀመሪያ ጋሽ ዝናቡ አረፈ ማለት፣ሞተ ማለት መሆኑን፣ ልክ ከሌላ ቋንቋ እንደሚተረጎም ለራሴ ተረጎምኩ እና እየፈራሁ
“ጋሽ ዝናሱ ሞተ” ብዬ ጠየቅኋት፡፡
“አዎ ትላንት ማታ አረፈ"
“ምን ሆነ? ታሞ ነበር እንዴ?
"አረ ድንገት ነው።"
በኋላ ቆይቼ ስሰማ፣ ጋሽ ዝናቡ የሞተው ራሱን አጥፍቶ ነበር፡፡ በተለይም መሐሪ
ከተፈረደበት በኋላ፣ አእምሮው ጤነኛ አልነበረም አሉኝ፡፡ብቻውን ያወራል፤ ሥራውንም በአግባቡ መሥራት ስላልቻለ ለጊዜው ጡረታ አስወጥተውት ነበር፡፡ በዳኝነት ተሠይሞ የሚቀርብለትን ፋይል ሁሉ፣ ትልልቅ ወንጀል የሥሩ ወንጀለኞችን ሳይቀር ነፃ ናችሁ እያለ መልቀቅ ጀምሮ ነበር፡፡ አንድም ቀን መሐሪን እስር ቤት ሂዶ አልጠየቅም፡፡
በመጨረሻም ያ ባለ ነጎድጓዳማ ድምፅ፣ጋሽ ዝናቡ ራሱን አጥፍቶ ይችን ዓለም በዝምታ ተሰናበታት፡፡ ውስጤ ተንገበገበ፡፡ ቢያንስ እየሄድኩም ሆነ እየደወልኩ ብጠይቀው፣ትንሽ
መጽናናት ይሆንለት እንደነበር ማን ያውቃል፡፡
"መሐሪ ሰማ ብዬ እናቴን ጠየቅኋት።
"እሱ ልጅማ ጤናም አይመስለኝ፣ አንዳች ነገር ለከፎታል”
እንዴት?”
“በፖሊስ ታጅቦ አባቱን እንዲቀብር የሰፈሩ ሰው ሁሉ ተሯሩጦ አስፈቅዶ፣ ና ውጣ
አባትህን ቅበር ቢሉት፣ ኤልሄድም አለ አሉ፡፡ በቃ አባቱን ላይቀብር ቀረ፡፡ እወደው
ነበር፡፡ በዚህ ነገር ትንሽ ቅር አለኝ፡፡ አይ ልክ አልሠራም
የዚያን ቀን ሁለት ሦስት ጊዜ ለማሚ ደውዬ ለቅሶ ለመድረስ አስቤ ተውኩት፡፡ ለእረፍት ወደ ቤተስብ ስመለስም፣ አልጠየኳትም፡፡ እሸሽ ነበር፡፡ አጥብቄ እሸሽ ነበር። መሐሪ እኔና ሮሐን እስር ቤት ከወቀሰን በኋላ ውስጤ፣ ትንሽ ይጨናነቅ ነበር፡፡ “የእውነት እኔና ሮሐ ሳሌም ላይ ያ ነገር ለመፈጠሩ ምክንያት ነበርን? እያልኩ አስባለሁ፡፡ ይኼን ነገር አንዳንዴ ለሮሐ ላነሳባት እፈልግና፣ ከአፌ ላይ እመልሰዋለሁ፡፡ ብቻዬን ራሴን ዕውቅስና
ሳጽናና ለዓመታት ኖሬያለሁ፡፡ ማጽናኛዬ ሁልጊዜም እንድ ዓይነት ነው፡፡መሐሪ ደደብ ነው የሚል፡፡ ራሱን ገደለ፣ አንዲት ሕፃን ገደለ፣ ይኼ አልበቃው ብሎ እንዴት እኔን ይወቅሳል?
።።
ሮሐ ከእኔ ቀድማ ነበር የተመረቀችው፡፡ በአካውንቲንግ፡፡ በዚያው በተመረቀችበት
ዓመት አዲስ አበባ መጣች፡፡ አዲስ አበባ በመምጣቷ፣ ከልቤ ተደስቼ ነበር፡፡ ውስጤ በደስታ ሲፍነከነክ በስልክ የገነባነው ጓደኝነት ግዝፈት ያኔ ገባኝ፡፡ ሥራ አልጀመረችም።ሀብታም ዘመዶቿ “ትምህርት ላይ ከርመሽ የምን ወደሥራ መሮጥ ነው” አሉኝ አለች።ያለው ማማሩ፡፡ በየቀኑ እንደዋወላለን (ለነገሩ እሷ ነች የምትደውልልኝ አንዳንዴ ድንገት ግቢ ትመጣለች፡፡ ጓደኞቼ ሁሉ አውቀዋት ነበር፡፡ “መልአክህ መጥታለች
ይሉኛል፡፡ እዚህ ግቢው በር ላይ
አቁመህ ቀክፍያ ብታስጎበኛትኮ፣ በሳምንት ውስጥ በቃ፣ ሚሊየነር ትሆናለህ” ይሉኛል፡፡
"በጣም ጥ፣ ያበደራችሁኝን ሁሉ በዚሁ ይጣጣ፣ አይታችኋታል” ብዬ በራሳቸው ቀልድ ሂሳብ ሠራሁ፡፡ ሮሐ ታዲያ ስትሰማ ስንት አበድረውህ ነው? አለችኝ እየሳቀች “ሦስት ብር
“በሦስት ብር፣ እንኳን እኔ፣ ድንቢጥ አይጎበኝም፣ ጥሩ ነጋዴ

አይደለህም
“ለጽድቅ ነው ዲፓርትመንታችን ያሉ ኮንክሪት የመሳሰሉ ሴቶችን ሲያዩ የከረሙ ልጆች አይተውሽ ደስ ይበላቸው
እያደነከኝ ነው ታውቆሃል ከብዙ ሳቅ ጋር፡፡
ከሮሐ ጋር ተያይዘን እንወጣና፣ የባጥ የቆጡን እያወራን ስንዞር፣ አልያም አንዱ ካፍቴሪያ ተቀምጠን ስናወራ አምሽተን፣ ሸኝቻት ወደ ግቢ እመለሳለሁ፡፡ ቅዳሜ ከሰዓት አብረን ነበር የምንውለው፡፡ አብረን ምሳ አንበላለን፣ ቲያትር እንገባለን፡፡ አንዳንዴም አብረን
አምሽተን ራት በልተን እንለያያለን፡፡
አንድ ቅዳሜ ቀን ራት ስንበላ ድንገት “እስካሁን ጓደኛ አልያዝኩም” አለችኝ፡፡
አንች ምንድነሽ ታዲያ”
"ኖ... ሴት ጓደኛ"
“ይቅርታ፣ ወንድ መሆንሽን እላወኩም!”
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
“ለጽድቅ ነው ዲፓርትመንታችን ያሉ ኮንክሪት የመሳሰሉ ሴቶችን ሲያዩ የከረሙ ልጆች አይተውሽ ደስ ይበላቸው
እያደነከኝ ነው ታውቆሃል ከብዙ ሳቅ ጋር፡፡
ከሮሐ ጋር ተያይዘን እንወጣና፣ የባጥ የቆጡን እያወራን ስንዞር፣ አልያም አንዱ ካፍቴሪያ ተቀምጠን ስናወራ አምሽተን፣ ሸኝቻት ወደ ግቢ እመለሳለሁ፡፡ ቅዳሜ ከሰዓት አብረን ነበር የምንውለው፡፡ አብረን ምሳ አንበላለን፣ ቲያትር እንገባለን፡፡ አንዳንዴም አብረን
አምሽተን ራት በልተን እንለያያለን፡፡
አንድ ቅዳሜ ቀን ራት ስንበላ ድንገት “እስካሁን ጓደኛ አልያዝኩም” አለችኝ፡፡
አንች ምንድነሽ ታዲያ”
"ኖ... ሴት ጓደኛ"
“ይቅርታ፣ ወንድ መሆንሽን እላወኩም!”
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
#ፍቅር_አያሸንፍም
ህፃን
ልጅ
አዋቂው
ወጣት ሽማግሌው ፥ ረጋሚ መራቂው
በአንደበቱ ማህፀን
“ፍቅር ያሸንፋል”
የሚል ጥቅስ አርግዞ ፥ በምላስ ይወልዳል
ፍቅር ግን ሁል ጊዜ
እየተሸነፈ ፣ መሸነፍ ይወዳል።
አቅመ ቢስ ነው አቅሙ ፥ ወዋረድ ነው ልኩ
ሁሌም መሽነፍ ነው
ሁልጊዜ መውደቅ ነው ፥ የፍቅር ታሪኩ።
ርሐብተኛ ነው
አይበላም አይጠጣም ፣ ንብረት አያፈራም
አይደፍርም አይፈራም
አይጠፋም አይሰራም
ፎቅ አይደረድርም ፥ ቪላ ቤት አይሰራም
ማደሪያው በረት ነው ፥ ሲታይ ስጋ ለብሶ
ባሪያ ነው አንግሶ
ሁሌም ዝቅ ያለ ነው ፥ ከፍታ ላይ ደርሶ።
ፍቅር ይሸነፋል!
መንገድ ምራን ላሉት ፥ መንገድ ሆኖ ያርፋል
ሁሉ ይረግጠዋል
መልኮት ኋይል አለው ፥ በሰው ይገረፋል
በሰማይ ሲሾሙት ፥ ወደምድር ይጠፋል
አንድ ሀገር የለውም
የትም ቦታ አለ ፥ እየተሰደደ
ሁሌ እንደተገፋ ፥ እንደተዋረደ
ዝቅ ይሎ ይኖራል
ዝቅ ብሎ ያድራል
ቃል አይናገርም ፥ ስንጥለው ጠልፈን
እርቃን ስናስቀረው
ልብሱን ከአደባባይ ፥ ከገላው ላይ ገፍፈን
ፀሐይ ላይ ተጥደን
ውርጭ ስናስመታው ፥ ስናለብሰው ቆፈን
ከሀገር ስናስወጣው ፥ ካንጀት ተፀይፈን
ጥለነው ስንሔድ ፥ ስናገኘው አልፈን
ትንፋሽ አይወጣውም
ለሁሉ መንገድ ነው ፥ መሔጃ የለውም።
ሁሉን ይከተላል
ለሁሉ ዝቅ ይላል
እረኛ ሲያደርጉት ፥ በግ መሆን ይመርጣል
ዘጠና ዘጠኝ በግ
ሜዳ ላይ በትኖ
አንድ የጠፋ በጉን ፥ ፍለጋ ይወጣል
አይቀድም ይሮጣል
አይሸሽም ያመልጣል
አይተኛም ያደፍጣል
ሲሰድቡት ቃል ያጣል
ቃል ሆኖ ይመጣል
ህያው ነው ስንለው
መቃብር ይወርዳል ፥ በሙታን ተገድሎ
ይነሳል ሲቀብሩት ፥ ከሞት ተነጥሎ
ባሪያ ነው ለሁሉ
መንግስቱን የሚያወርስ ፥ ከምንዱባን ውሎ።
አቅሙ አቅመ ቢስ ነው ፥ ሽንፈት ነው እድሉ
ወርዶ መገኘት ነው
ማጎንበስ ነው እጣው ፥ መረታት ነው ውሉ
ዝቅ ብሎ መኖር ነው ፥ እቅድና አቅሉ
ዝም ነው ስንገርፈው
ዝም ነው ስንዘልፈው
ጭጭ ነው ስንጠልፈው
ቃላት አይወጣም
ራሱ ግን ቃል ነው ፥ የቃሉ እስረኛ
ፍቅር ሲሸነፍ ነው
ፍቅር ያሸነፈ ፥ የሚመስለን ለኛ!
ያንሳል ስናገዝፈው
ቀድሞ ይጠብቃል ፥ ትተነው ስናልፈው
እየተሸነፈ
በመሸነፉ ነው ፣ ፍቅር ያሸነፈው።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
ህፃን
ልጅ
አዋቂው
ወጣት ሽማግሌው ፥ ረጋሚ መራቂው
በአንደበቱ ማህፀን
“ፍቅር ያሸንፋል”
የሚል ጥቅስ አርግዞ ፥ በምላስ ይወልዳል
ፍቅር ግን ሁል ጊዜ
እየተሸነፈ ፣ መሸነፍ ይወዳል።
አቅመ ቢስ ነው አቅሙ ፥ ወዋረድ ነው ልኩ
ሁሌም መሽነፍ ነው
ሁልጊዜ መውደቅ ነው ፥ የፍቅር ታሪኩ።
ርሐብተኛ ነው
አይበላም አይጠጣም ፣ ንብረት አያፈራም
አይደፍርም አይፈራም
አይጠፋም አይሰራም
ፎቅ አይደረድርም ፥ ቪላ ቤት አይሰራም
ማደሪያው በረት ነው ፥ ሲታይ ስጋ ለብሶ
ባሪያ ነው አንግሶ
ሁሌም ዝቅ ያለ ነው ፥ ከፍታ ላይ ደርሶ።
ፍቅር ይሸነፋል!
መንገድ ምራን ላሉት ፥ መንገድ ሆኖ ያርፋል
ሁሉ ይረግጠዋል
መልኮት ኋይል አለው ፥ በሰው ይገረፋል
በሰማይ ሲሾሙት ፥ ወደምድር ይጠፋል
አንድ ሀገር የለውም
የትም ቦታ አለ ፥ እየተሰደደ
ሁሌ እንደተገፋ ፥ እንደተዋረደ
ዝቅ ይሎ ይኖራል
ዝቅ ብሎ ያድራል
ቃል አይናገርም ፥ ስንጥለው ጠልፈን
እርቃን ስናስቀረው
ልብሱን ከአደባባይ ፥ ከገላው ላይ ገፍፈን
ፀሐይ ላይ ተጥደን
ውርጭ ስናስመታው ፥ ስናለብሰው ቆፈን
ከሀገር ስናስወጣው ፥ ካንጀት ተፀይፈን
ጥለነው ስንሔድ ፥ ስናገኘው አልፈን
ትንፋሽ አይወጣውም
ለሁሉ መንገድ ነው ፥ መሔጃ የለውም።
ሁሉን ይከተላል
ለሁሉ ዝቅ ይላል
እረኛ ሲያደርጉት ፥ በግ መሆን ይመርጣል
ዘጠና ዘጠኝ በግ
ሜዳ ላይ በትኖ
አንድ የጠፋ በጉን ፥ ፍለጋ ይወጣል
አይቀድም ይሮጣል
አይሸሽም ያመልጣል
አይተኛም ያደፍጣል
ሲሰድቡት ቃል ያጣል
ቃል ሆኖ ይመጣል
ህያው ነው ስንለው
መቃብር ይወርዳል ፥ በሙታን ተገድሎ
ይነሳል ሲቀብሩት ፥ ከሞት ተነጥሎ
ባሪያ ነው ለሁሉ
መንግስቱን የሚያወርስ ፥ ከምንዱባን ውሎ።
አቅሙ አቅመ ቢስ ነው ፥ ሽንፈት ነው እድሉ
ወርዶ መገኘት ነው
ማጎንበስ ነው እጣው ፥ መረታት ነው ውሉ
ዝቅ ብሎ መኖር ነው ፥ እቅድና አቅሉ
ዝም ነው ስንገርፈው
ዝም ነው ስንዘልፈው
ጭጭ ነው ስንጠልፈው
ቃላት አይወጣም
ራሱ ግን ቃል ነው ፥ የቃሉ እስረኛ
ፍቅር ሲሸነፍ ነው
ፍቅር ያሸነፈ ፥ የሚመስለን ለኛ!
ያንሳል ስናገዝፈው
ቀድሞ ይጠብቃል ፥ ትተነው ስናልፈው
እየተሸነፈ
በመሸነፉ ነው ፣ ፍቅር ያሸነፈው።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ወደድኩህ_ያልሽኝ_ቀን
ሸኝቼሽ ስመለስ
ያልሽኝን እያሰብኩ ፥ አልፌው ሰፈሬን
አልፌው መንደሬን
ላልፋት ስል ሀገሬን
ድንበር ጠባቂዎች ፥ በሰደፍ ግንባሬን
ነርተው ዘረሩኝ : ከሀሳቤ አነቁኝ
“ወዴት ነው ምትሔደው?” ፥ በማለት ጠየቁኝ ።
ወዴት ልበላቸው?
ተደቅነውብኝ ፥ ፍርጃና ጠብመንጃ
የምለው ጠፋብኝ ፥ ምን እንዳልሽኝ እንጃ
ብቻ ሰምቻለሁ
ብቻ ግን አውቃለሁ
ወደ ተለየ ዓለም
ፍቅር ይወስዳል” ይላል ፥ ያ'ፍቃሪ አፍ መፍቻ
ያ የተለየ ዓለም ፥ እዚ እንዳይሆን ብቻ
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
ሸኝቼሽ ስመለስ
ያልሽኝን እያሰብኩ ፥ አልፌው ሰፈሬን
አልፌው መንደሬን
ላልፋት ስል ሀገሬን
ድንበር ጠባቂዎች ፥ በሰደፍ ግንባሬን
ነርተው ዘረሩኝ : ከሀሳቤ አነቁኝ
“ወዴት ነው ምትሔደው?” ፥ በማለት ጠየቁኝ ።
ወዴት ልበላቸው?
ተደቅነውብኝ ፥ ፍርጃና ጠብመንጃ
የምለው ጠፋብኝ ፥ ምን እንዳልሽኝ እንጃ
ብቻ ሰምቻለሁ
ብቻ ግን አውቃለሁ
ወደ ተለየ ዓለም
ፍቅር ይወስዳል” ይላል ፥ ያ'ፍቃሪ አፍ መፍቻ
ያ የተለየ ዓለም ፥ እዚ እንዳይሆን ብቻ
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
👍1
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
....አንድ ቅዳሜ ቀን ራት ስንበላ ድንገት “እስካሁን ጓደኛ አልያዝኩም” አለችኝ፡፡
አንች ምንድነሽ ታዲያ”
"ኖ... ሴት ጓደኛ"
“ይቅርታ፣ ወንድ መሆንሽን እላወኩም!”
ለዛ ቢስ …ገብቶሃል እስካሁን ፍቅረኛ ለምን አልያዝዘከም ኮስተር አለች፡፡
"እኔጃ ትከ ብላ አየችኝና፣
“መቼም እየደስከኝ አይደለም፣ አይደል?”
ለምን እደብቅሻለሁ? እኔጃ! በቃ ሙሉ ለሙሉ ትኩረቴ ትምህርት ላይ ነበር፡፡ ብዙም ርሌሽን ሽፕ ላይ ድፍረቱ አልነበረኝም፣ እፈራለሁ፣ በጣም እፈራለሁ፡፡ ወይም እኔጃ አልኳት፡፡ ዝም ብላ ቆየችና፣
እኔን አልጠየከኝም አራት ዓመት ሙሉ በስልክ ስናወራ ለዕረፍት ስንገናኝ አንድም ቀን ጓደኛ ልያዝ አልያዝ ጠይቀኸኝ አታውቅም፣ ምናገባኝ ነው፣ ወይስ አንዱ አንጠልጥሎ ወደዛ በወሰዳት ነው …ምንድነው?”ብላ አንገቷን ሰበር አድርጋ አየችኝ፡፡ ይኼን
አስተያየቷን ስወደው፡፡
አንዳንዴ ልጠይቅሽ አስብና …አለ አይደል
“ከመሐሪ ጋር የነበረንን ነገር የምታስታውሰኝ እየመሰለህ ወይም ምን አስቦ ነው ትለኛለች ብለህ ትፈራለህ?”
እንደዛ ነገር መሰለኝ
“ለማንኛውም ጓደኛ የለኝም … ወንዶችን መቅረብ አልቻልኩም
“ከመሓሪ ጋር በተያያዘ ነው? …”
አላውቅም! ከሆኑ ወንዶች ጋር እቀራረብና፣ ድንገት ዓይናቸውን ማየት ያስጠላኛል።በቃ ውስጤ ምንም የተረጋጋ አልነበረም፤ እረበሻለሁ፡፡ ለረዥም ጊዜ እንቅልፍ በማጣት ተቸግሬ ነበር፡፡ ሕከምና ሁሉ ወስጃለሁ"
ኧረ ባክሽ አልነገርሽኝም
"ለማንም አልተናገርኩም”
እንኳን ማንም መሆኔን ነገርሽኝ”
“ኖ..ብላ እጄን በሁለት እጆቿ አፈፍ አድርጋ ያዘችኝ! የእጆቿ ልስላሴና ሙቀት መቼም አይረሳኝም፡፡እጆቼን እንደያዘችኝ ትከ ብላ እያየችኝ “በእነዚህ አራት ዓመታት በሕይወትሽ ውስጥ የነበረ ብቸኛ ሰው ጥሪ ብባል አንተ ብቻ ነበርክ” ዝም ብዬ እየኋት፤ ለእንደዚህ ዓይነት ወሬዎች ባዕድ ነኝ፡፡ በውስጤ ግን ያለፉትን ዓመታት ተመልሼ ሳስብ፣ እኔም
ከእርሷ ሌላ ከልቤ የምቀርበው ሰው ማስታወስ አልቻልኩም፡፡
“እኔም ከአንች ውጭ የቀረብኩት ሰው አልነበረም ዝም ተባባልን፡፡ እጆቼን
እንደያዘቻቸው ነበር፡፡ በረዥሙ ተንፍሳ እጆቼን ለቀቀችና ቦርሳዋን አንስታ እንሂድ
አለችኝ፡፡
ከተለያየን በኋላ ስለ ሮሐ ሳስብ አመሸሁ፡፡ እንግዳ ነበር ስሜቱ፡፡ የተዘበራረቀ፡፡ እንደ
ማዕበል ውስጤን ያናወጠ ስሜት፡፡ አብሪያት የመሆን ፍላጎት ውስጤን ለጉድ
ይገፋዋል፡፡ ሁለት ሦስት ጊዜ ልደውልላት ስልኬን አንስቼ ተውኩት፡፡ የዚያን ቀን ሌሊት መሐሪን በሕልሜ አየሁት፡፡ ብዙ ጊዜ ሰሕልሜ አይቼው አውቃለሁ፡፡ ሁሉም ሕልሞቼ አብረን ካሳለፍናቸው ጊዜዎች ኣንዱ ላይ የሚያርፉ ነበሩ፡፡ የዚያን ጊዜው ግን የሚጨቅ
ዓይነት ሕልም ነበር፡፡ መሐሪ ጋር አብረን ታስረን ይመስለኛል፡፡አንነጋገርም፡፡
አንቀሳቀስም፡፡ ፊት ለፊት ተቀምጠን ዝም ብሎ ያየኛል፡፡ በቃ ማየት ብቻ!! ፊቱ ላይ ሳቅ የለ፣ ኩርፊያ የለ ዝም ያለ ፊት!
።።
ሮሐ ጋር ግንኙነታችን በየቀኑ ሆነ፡፡ የዘመዶቿ ቤት ቅርብ ነበር አራት ኪሎ አካባቢ፡፡ብዙ ጊዜ ከዩኒቨርስቲው ፊት ለፊት ያለች ባለ አንድ ፎቅ ካፌ ውስጥ ተቀምጣ ትጠብቀኛለች። እናወራለን፣ እንሳሳቃለን፡፡ እንዴት ፊት ለፊት ከመቀመጥ ጎን ለጎን ወደ መቀመጥ እንደተሸጋገርን ትዝ አይለኝም፡፡ እንዴት እጅ ለእጅ ተያይዞ መንገድ ላይ
መሄድ እንደጀመርን ትዝ አይለኝም፡፡ በሁለት እጆቿ ክንዴን ይዛ፣ ትከሻዬ ላይ እራሷን ጣል ማድረግ የጀመረችው መቼ እንደነበር አላስታውስም፡፡ራሳችንን ወደ ምንም አልገፋነውም፡፡ ከምንም አልከለከልንም፡፡ ልክ የሆነ ባሕር ላይ ያለች ጀልባ ውስጥ ነፍሳችንን እንደ ማስቀመጥ ነበር፡፡ ድንገት ማዕበል ተነስቶ ወደማናውቀው ቦታ
አሽቀንጥሮ ወሰደን፣ ዓይኖቻችንን ስንገልጥ፣ ያበደ ፍቅር ውስጥ ነበርን፡፡
ማዕበሉ የተነሳባትን ቅጽበት ግን አስታውሳለሁ፡፡ አንድ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ቲያትር ልናይ ጎን ለጎን በተቀመጥንበት ጨለማ አዳራሽ ውስጥ ልክ ስማችን የተጠራ ይመስል፣
ሁለታችንም ድንገት ዙረን ተያየን፡፡ የማስታውሰው ዓይኖቼን ስጨፍንና የሮሐ
ከንፈሮች ከንፈሬ ላይ ሲያርፉ ነበር፡፡ ልክ ርችት እንደሚለኮሰው በዚያች ቅጽበት የሆነ ነገር በመሀላችን ተጫረ፡፡ ስማያትን በብዙ ብርሃንና ቀለማት ተጥለቀለቀ ደንግጨ ነበር፡፡ ስንወጣ አልተነጋገርንም ከንዴን ይዛኝ ቀዝምታ ሸኘኋት! ውስጤ ግን በጸጸት እየተጥለቀለቀ ነበር፡፡ ክሕደት ነው አልኩ ለራሴ፡፡ ብዙ ሚሊዮን ሴቶች ባሉባት ዓለም፣ ጊዜ የጣለውን የጓደኛየን ፍቅረኛ መንጠቅ ምን የሚሉት ከፋትና ስግብግብነት ነው? እያልኩ፣ በራሴ አፈርኩ፡፡ ምናልባትም ሳላውቀው ውስጤ ያደገ የበታችነት ስሜት ሳይሆን አይቀርም አልኩ፡፡ መሐሪን በዚህ የበለጥኩ መስሎኝ፡፡ ተብከነከንኩ፣ ግን
በዚያው ምሽት ሮሐ ደውላልኝ ገባህ ስትለኝና ምንም እንዳልተፈጠረ ስናወራ ሁሉም ነገር ከአእምሮዬ ጠፋ፡፡ ድምፅዋን ስሰማ እንቅዥቅዥ የሚያደርገኝ ነገር ነበር፡፡
ሮሐ ስታፈቅር ሁሉን ነገሯን የምትሰጥ ልጅ ነች፡፡ ሁሉ ነገሯን፡፡ ምናልባት ባይሳካስ ብላ የምታስቀረው ነገር የለም፡፡ ካፈቀረችው ሰው ውጭ ህይወት በምድር ላይ ስለመኖሩም ትዝ አይላትም፡፡ በሕይወቷ ውስጥ ምንም የተወሳሰበ ነገር የለም፡፡ የኑሮ ቀመሯ ግልጽ
ነው ካፈቀረች ታፈቅራለች፣ ከጠላች ትጠላለች በቃ ነፍሷ ወዶኝ ነበር፡፡ለምን
ይመስልሃል ጓደኛ ያልያዝኩት? ስለወደድኩህ ነው ስላፈቀርኩህ እወድሃለሁ የእውነት
እወድሃለሁ!" የተሰማትን ቃል በቃል ሳታፍር ትናገራለች፡፡“የዶርም ልጆች ሁሉ
ያውቃሉ፥ ካልተደዋወልን ስነጫነጭባቸው ነበር የምውለው፡፡”
ነፍሷ ያለፈውን ሁሉ ረስቶ እኔ ጋር ነበር .…መሐሪ የሚባል ሰው በምድር ላይ መኖሩን ሁሉ ስለማስታወሷም እንጃ፡፡ እኔ፣ ፍቅሬም ፍርሃትና ጸጸቴም በጥልቅ ዝምታ ውስጥ ነበሩ፡፡ ከልቤ ባፈቅራትም ጸጸት በየደቂቃው ውስጤ መጫሩ አልቀረም፡፡ ተገናኝተን በተለያየን ቁጥር፣ ያንገበግበኛል፡፡ አብረን ስንቀመጥ የሰው ሚስት ሰርቄ የተገናኘሁ ያህል፣ አካባቢዬ ምቾት አይሰጠኝም፡፡ በዚህ በኩል ኃይለኛ ጸጸት፣ በሌላ በኩል አቅሌን የሚስት ፍቅር እንደ ድፎ ዳቦ ከላይና ከታች የሚንቀለቀል እሳት ውስጥ ነበርኩ፡፡
ከአንድ ዓመት በላይ ሮሐ ጋር በፍቅር አበድን፡፡ ሲቆይ የኔውም ህሊና ዓይኖቹን ጨፈነ መሰለኝ፣ እኔ ብሽ ቁጭ አልኩ፡፡ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ጠበቡን፤ “…ከአምስት ኪሎ እስከ አራት ኪሎ ያሉት መንገዶች፣ ብዙ የተራመደባችሁ ማነው?” ቢባሉ አንዲት የሳበችውን አየር እንደ አኮረዲዮን ሙዚቃ እድርጋ ወደ ውጭ የምትተነፍስ ውብ ልጅና፣ ከዓመት እስከ ዓመት የማትቀየር ኦሞ ከለር ጅንስ ሱሪ የሚለብስ፣ እንደ ሌባ ዙሪያውን እየተገላመጠ የሚሄድ ልጅ” የሚሉ ይመስለኛል፡፡ መንገዱ ለምዶናል
መንገደኛው ለምዶናል፡፡ አምስት ኪሎ ታከሲ ተራው አጥሩ ሥር የሚቀመጥ የኔ ቢጤ፤ሮሐ በመጣች ቁጥር ምጽዋት አስለምዳው ኖሮ አንድ ቀን “ምነው አረፈድሽ” አላት፡፡ልክ ደመወዙን ይዛ እንዳረፈደችበት ዓይነት፡፡ እዚህ ድረስ መንገዱ የኛ ሆኖ ነበር፡፡
አዲስ አበባ የመቆየቷ ምክንያት እኔ ብቻ ነበርኩ፡፡ አትሠራም አትማርም፡፡ ዕድሜ
ለሀብታም ዘመዶቿ፣ ዘና ብላ እየኖረች፣ የመኖሯን ምክንያት ግን እኔን አድርጋ ነበር፡፡የአዲስ እበባ ሕዝብ ቁጥር ስንት ነው ብትባል አንድ” ብላ ወደ እኔ የምትጠቁም ነው የሚመስለኝ፡፡ ደስ ባላት ሰዓት፣ ድንገት ተነስታ ትመጣለች፡፡ ድንገት ስትመጣ፣ ነፍሴ በደስታ የሚያደርጋትን

👍2
ያሳጣታል፡፡ ጥበቃ አልወድም፡፡ ለዚያ ነው ድንገተኛ መገኘቷ
ጮቤ የሚያስረግጠኝ፡፡ ጧት አትል ማታ፣ ደስ ካላት ትመጣለች፡፡ ፈተና አለብኝ አልል፣ መመረቂያ ጽሑፍ በማዘጋጀት ተጠምጃለሁ አልል፣ አብሪያት መከነፍ ነው፡፡ አንዴ ይች ልጅኮ እዚሁ ተማሪ ትመስለኝ ነበር” እስኪሉ ደጋግመው ነው የሚያዩዋት፡፡ ዙሪያየን ነበረች፡፡ ማፍቀር የሚሆንለት ስው አለ፡፡ ልክ እንደ ውብ ልብስ የሚያምርበት፡፡ ሮሐ እንደዚያ ነበረች፡፡ እኔ ብቻ ነበርኩ ጎልቼ የምታያት፡፡ ማፍቀር ማለት በጨለማ ሰማይ
ላይ ከፈሰሱት ኅልቆመሳፍርት ከዋክብት፣ አንዷን መርጦ እንደ ጨረቃ ማግዘፍ ነው፡፡አግዝፋኝ ነበር፡፡
በዚሁ ስሜት እየተላጋሁ፣ ከዩኒቨርስቲ ተመርቄ ወጣሁ፡፡ ምሕንድስና፡፡ የተመረኩ ቀን ከእኔ ይልቅ ሮሐ የሚያደርጋትን አሳጥቷት ነበር፡፡ ሰውነቷ ላይ ጥብቅ ያለ አጭር ቀሚስ ለብሳ የሚያልፈው ወንድ ሁሉ እነዚያ ውብ እግሮች ላይ ሲያፈጥ “መሐሪ ወዶ ነው እንዴ የዛን ቀን ማታ የቀናው¨ ሳልል አልቀረሁም፡፡ሦስት እንደሷው የኑሮ ምቾትና የፈጣሪ ጸጋ ያስዋባቸውን የአክስቶቿን ልጆች ይዛ መጥታ፣ ምርቃቴን ሰርግ አስመስለችው፡፡ የዚያን ቀን ምሽት አንድ ትልቅ ሆቴል ወስደው ራት ጋበዙኝ፡፡ ከምሽቱ
ሦስት ሰዓት አካባቢ ሦስቱም ተሰናብተውን ሲወጡ እና ሁለታችን ብቻ ስንፋጠጥ
(ትንሽ በግሩፕ የተመሳጠሩ ይመስለኛል)
እሽ፣ ዛሬም ልሸኝሽ ነው?” አልኩ እንደቀልድ፡፡
ማሬ መሽኛኘት የለም… መሐንዲስ ሆንክ አይደል …እስቲ የዚህን ሆቴል ሕንጻ አሠራር እንገምግመው” ብላ እየሳቀች እዚያው ሆቴል አራተኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኝ ክፍል እጄን ይዛ ወሰደችኝ፡፡ ፈጽሞ ባላሰብኩት ቀን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሮሐ ጋር አብረን ያደርነው እንደዚያ ነበር፡፡ የመጀመሪያ ነበረች፡፡ ለእርሷም የመጀመሪያዋ፡፡ ጧት ፊቷን የሸፈናትን
ሉጫ ጸጉሯን እንደመጋረጃ ከፊቷ ላይ ወደኋላ እየሰበሰበች፣ ሐፍረት በቀላቀለበት ፈገግታ አየችኝና “ባለጌ ነህ እሽ” አለችኝ፡፡ ከዚያ ቀን በኋላ ብልግና ቀን ወጣለት፡፡የአዲስ አበባ አልቤርጎዎች እንደ አዲስ አበባ መንገዶች ሁሉ ዳናችን ታተመባቸው።በጠረናችን ነበራችን ተጻፈባቸው፡፡በፍቅር አብደን ነበር፡፡ስላለፈውም ስለ ወደፊቱም አላወራንም፡፡ማዕበሉ ወደፈለገበት እንዲወስደን ራሳችንን በፍቅር ጀልባ ላይ አስቀምጠን
ተውነው፡፡ በዚህ በኩል እንሂድ ብለን መንገድ ስላልመረጥን፣ የተሳሳተ መንገድ የሚባል ነገር በሕይወታችን አልነበረም፡፡ ምንም መዳረሻ ስላላለምን፣ የደረስንበት ሁሉ ልክ ነበር፡፡ ሮሐ ለፍቅር የተፈጠረች ልጅ ናት፡፡ ዝባዝንኬ ሳታበዛ በማፍቀር ብቻ፡፡የሕይወትን ደስታ ለምርኮ መውሰድ ተሰጥቷታል፡፡ ምርኮኛ ልሁን፣ አብሬያት ልሰለፍ ባይገባኝም፣ ብቸኛ ፍላጎቴ ሁልጊዜ የትም ቦታ አብሪያት መሆን ብቻ ነበር፡፡

#አትናፍቂኝም
ኖረውት አልፈውት ፥ መኖር የሚመኙት
አግኝተው አጥተውት ፥ አሁን 'ማያገኙት
ቢሆንም እውነቱ ፥ የመናፈቅ ትርጉም
እስከሌለ ድረስ
ፀሐይነትሽን ፥ የሚጋርደኝ ጉም
አትናፍቂኝም!
ይልቅ ስትርቂ ፥ አቀረብኩሽ በጣም
ስትሔጂ አወኩት ፥ የመምጣሽን ጣም፡፡
በመለያየት ውስጥ ፥ አብሮነትሽ ጎላ
ብትሔጂም ቀርተሻል
ሁሌም ከኔ ጋ ነሽ ፥ ካጣሁሽ በኀላ፡፡
ይልቅ ስትሔጂ
ባብሮነታችን ውስጥ
ያልታየኝ ውብ ፍቅርሽ ፥ ነፍሴን አጠመቀው
“ተለያዩ" ሲባል
እንደተገናኘን
እኔ ውስጥ እንዳለሽ ፥ ለልቤ ታወቀው
ለካንስ አንዳንዴ
ለመቀራረብ ነው ፥ ሰው የሚራራቀው
እና እንዴት ብዬ ነው
እኔ ውስጥ እያለሽ
ከኔ ላይ ለይቼሽ ፥አንቺን ምናፍቀው?!!
ይልቅ ስትሔጂ
በቁሜ
በህልሜ
በደም ዝውውሬ ፥ እያመላለስኩሽ
ከአብሮነት በላይ አብሬ እየሳልኩሽ
መናፈቄ ናፍቆኝ ፥ መናፈቅ ብመኝም
በአብሮነትሽ በላይ
አብረሽኝ ስላለሽ ፣ አዎ አትናፍቂኝም
ስላላወቅሽ እንጂ
እየቀረብሽኝ ነው ፥ አንቺ ብትርቂኝም!
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
ኖረውት አልፈውት ፥ መኖር የሚመኙት
አግኝተው አጥተውት ፥ አሁን 'ማያገኙት
ቢሆንም እውነቱ ፥ የመናፈቅ ትርጉም
እስከሌለ ድረስ
ፀሐይነትሽን ፥ የሚጋርደኝ ጉም
አትናፍቂኝም!
ይልቅ ስትርቂ ፥ አቀረብኩሽ በጣም
ስትሔጂ አወኩት ፥ የመምጣሽን ጣም፡፡
በመለያየት ውስጥ ፥ አብሮነትሽ ጎላ
ብትሔጂም ቀርተሻል
ሁሌም ከኔ ጋ ነሽ ፥ ካጣሁሽ በኀላ፡፡
ይልቅ ስትሔጂ
ባብሮነታችን ውስጥ
ያልታየኝ ውብ ፍቅርሽ ፥ ነፍሴን አጠመቀው
“ተለያዩ" ሲባል
እንደተገናኘን
እኔ ውስጥ እንዳለሽ ፥ ለልቤ ታወቀው
ለካንስ አንዳንዴ
ለመቀራረብ ነው ፥ ሰው የሚራራቀው
እና እንዴት ብዬ ነው
እኔ ውስጥ እያለሽ
ከኔ ላይ ለይቼሽ ፥አንቺን ምናፍቀው?!!
ይልቅ ስትሔጂ
በቁሜ
በህልሜ
በደም ዝውውሬ ፥ እያመላለስኩሽ
ከአብሮነት በላይ አብሬ እየሳልኩሽ
መናፈቄ ናፍቆኝ ፥ መናፈቅ ብመኝም
በአብሮነትሽ በላይ
አብረሽኝ ስላለሽ ፣ አዎ አትናፍቂኝም
ስላላወቅሽ እንጂ
እየቀረብሽኝ ነው ፥ አንቺ ብትርቂኝም!
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
👍1
#ምን_እውነት_ኖሮኝ_ልንገርሽ?
ታሪኬ ቢገለጥ
ግዙፍ መፅሐፍ ነው !
ተፅፎ ተነቦ ፥ ገና ያላለቀ
ገፁ ዘልዓለም ነው!
ብዙ እውነት አለው ፥ ከውሸት ያልራቀ
ገፅ እድሜልክ ላይ
ብዙ ውሸት አለው ፥ ከእውነት የላቀ
ገፅ ምንም ላይ
እኔነቴ አለ ፥ ታሞ እየማቀቀ፡፡
ተመልከች እኔ ላይ!
ሲቃና ሰቆቃ
የሚያርፍበት ቦታ ፥ የሌለው ይመስል
የሰዎች ሁሉ ግፍ
ወደቡ ሲደርገኝ!
ጠባሳ መልኬ ላይ ፥ አዲስ ቁስል ሲስል።
ተመልከችው ቁስሌን
“እናክምህ “ ብለው ፥ ህመሜን ሲያብሱት
የበቃ ጩኸቴን ፥ በዘፈን ሲያነሱት
የሰቆቃ ትግሌን
የኔን መንፈራገጥ ፥ ሌሎች ሲደንሱት።
ተመልከች ሌሎችን !
እኔ ካንቺ በፊት ፥ ማውቃቸውን ሁሉ
የእውነት ታሪኬን
እየነገርኳቸው ፥ “ውሸት ነው” እያሉ
ጠባሳ መልኬ ላይ ፥ ጠባሳ እየጣሉ
ሀቄ ቢከብዳቸው ፥ ጥለውኝ ነጎዱ
ያላመኑት እውነት
ውሸት እንደሆነ ፥ ጠቁመውኝ ሔዱ፡፡
ይኸው ከዛ ወዲህ...
"እውነቴ ነው” ያልኩት ፥ እውነት አልመስል አለኝ
ያመኑት ውሸት ነው ፥ እውነት የሚመስለኝ!
ምን እውነት ልንገርሽ?
“ቤቷ ላዩዋ ፈርሶ ፥ ሞታለች እናቴ
ሰው ሀገር ገረድ ናት ፥ ቀን ገፍቷት እህቴ
መንድሜ ሽፍታ ነው !
እራሱን የሚያቆም ፥ ሒያጅ እየገደለ
ምን እውነት ልንገርሽ?
የሰዎች ሁሉ ግፍ ፥ ታሪኬ ላይ አለ
የሰው ሁሉ በደል
በኔ ላይ ነው ሚያልፈው ፥ ጠባሳ እየጠለ፡፡
ምን እውነት ልንገርሽ?
“ወታደር አባቴ
ድንበር በመጠበቅ ፥ ብዙ ዘመን ኖሯል
በጡረታ እድሜው
የመኖሪያ ቦታ
እገዛለሁ ብሎ ፥ ሀገር ሲሸጥ ታስሯል።”
ብዬ አልነግርሽ ነገር ፥ መስማትሽ አይበጅም
ለኔ እውነት ማለት...
ያመንሽኝ ውሸት ነው ፥ ውሸታም ባትወጂም !
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
ታሪኬ ቢገለጥ
ግዙፍ መፅሐፍ ነው !
ተፅፎ ተነቦ ፥ ገና ያላለቀ
ገፁ ዘልዓለም ነው!
ብዙ እውነት አለው ፥ ከውሸት ያልራቀ
ገፅ እድሜልክ ላይ
ብዙ ውሸት አለው ፥ ከእውነት የላቀ
ገፅ ምንም ላይ
እኔነቴ አለ ፥ ታሞ እየማቀቀ፡፡
ተመልከች እኔ ላይ!
ሲቃና ሰቆቃ
የሚያርፍበት ቦታ ፥ የሌለው ይመስል
የሰዎች ሁሉ ግፍ
ወደቡ ሲደርገኝ!
ጠባሳ መልኬ ላይ ፥ አዲስ ቁስል ሲስል።
ተመልከችው ቁስሌን
“እናክምህ “ ብለው ፥ ህመሜን ሲያብሱት
የበቃ ጩኸቴን ፥ በዘፈን ሲያነሱት
የሰቆቃ ትግሌን
የኔን መንፈራገጥ ፥ ሌሎች ሲደንሱት።
ተመልከች ሌሎችን !
እኔ ካንቺ በፊት ፥ ማውቃቸውን ሁሉ
የእውነት ታሪኬን
እየነገርኳቸው ፥ “ውሸት ነው” እያሉ
ጠባሳ መልኬ ላይ ፥ ጠባሳ እየጣሉ
ሀቄ ቢከብዳቸው ፥ ጥለውኝ ነጎዱ
ያላመኑት እውነት
ውሸት እንደሆነ ፥ ጠቁመውኝ ሔዱ፡፡
ይኸው ከዛ ወዲህ...
"እውነቴ ነው” ያልኩት ፥ እውነት አልመስል አለኝ
ያመኑት ውሸት ነው ፥ እውነት የሚመስለኝ!
ምን እውነት ልንገርሽ?
“ቤቷ ላዩዋ ፈርሶ ፥ ሞታለች እናቴ
ሰው ሀገር ገረድ ናት ፥ ቀን ገፍቷት እህቴ
መንድሜ ሽፍታ ነው !
እራሱን የሚያቆም ፥ ሒያጅ እየገደለ
ምን እውነት ልንገርሽ?
የሰዎች ሁሉ ግፍ ፥ ታሪኬ ላይ አለ
የሰው ሁሉ በደል
በኔ ላይ ነው ሚያልፈው ፥ ጠባሳ እየጠለ፡፡
ምን እውነት ልንገርሽ?
“ወታደር አባቴ
ድንበር በመጠበቅ ፥ ብዙ ዘመን ኖሯል
በጡረታ እድሜው
የመኖሪያ ቦታ
እገዛለሁ ብሎ ፥ ሀገር ሲሸጥ ታስሯል።”
ብዬ አልነግርሽ ነገር ፥ መስማትሽ አይበጅም
ለኔ እውነት ማለት...
ያመንሽኝ ውሸት ነው ፥ ውሸታም ባትወጂም !
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
👍1
በተጓዥ የበግ መንጋ መሀል በኋለኛው ሰልፍ ያሉ በጎች ያሳዝኑኛል።
መሪዎቹ በጎች እንሂድ ባሏቸው አቅጣጫ ሲሄዱ ይገረፋሉ። ባሻቸው አቅጣጫ
ለመሄድ ሲሞክሩም ይገረፋሉ
ሲታዘዙም ይገረፍሉ። ሲያፈነግጡም ይገረፋሉ። ገራፍያቸው ጅራፍ ስለያዘና መግረፍ ሱስ ስለሆነበት ብቻ ይገረፋሉ።
....በተጓዥ የበግ መንጋ መሀል በኋለኛው ሰልፍ ያሉ በጎች ሁሌም ያሳዝኑኛ..
ባለጅራፉ አጋጅ ፣ መንጋው እየተነዳ መሆኑን፣ እንዳይዘነጋ ለማስታወስ
ስከሚፈልግ ብቻ ፣ በሚጮህ ጅራፍ የኋለኞቹን በጎች ይገርፋል ፡ ፡
ባለጅራፍ አጋጅ ከመሪዎቹ ርቆ ፣ ለእነሱ ቀርቦ ስከሚገኝ ብቻ የኋለኞቹን
በጎች ይገረፋሉ።
ባለጅራፉ አጋጅ ፣ "መሪን መግረፍ ተከታይን ይበትናል" ብሎ ስለሚሰጋ ፣ መሪዎቹ ቢያጠፉም የኋለኞቹ በጎች ይገረፋሉ።
ስለዚህ በተጓዥ የበግ መንጋ መሀል በኋለኛው ሰልፍ ያሉ በጎች ሁሌም በጣም ያሳዝኑኛል።
ሕይወት እምሻው

#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
....ማሬ መሽኛኘት የለም… መሐንዲስ ሆንክ አይደል …እስቲ የዚህን ሆቴል ሕንጻ አሠራር እንገምግመው” ብላ እየሳቀች እዚያው ሆቴል አራተኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኝ ክፍል እጄን ይዛ ወሰደችኝ፡፡ ፈጽሞ ባላሰብኩት ቀን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሮሐ ጋር አብረን ያደርነው እንደዚያ ነበር፡፡ የመጀመሪያ ነበረች፡፡ ለእርሷም የመጀመሪያዋ፡፡ ጧት ፊቷን የሸፈናትን
ሉጫ ጸጉሯን እንደመጋረጃ ከፊቷ ላይ ወደኋላ እየሰበሰበች፣ ሐፍረት በቀላቀለበት ፈገግታ አየችኝና “ባለጌ ነህ እሽ” አለችኝ፡፡ ከዚያ ቀን በኋላ ብልግና ቀን ወጣለት፡፡የአዲስ አበባ አልቤርጎዎች እንደ አዲስ አበባ መንገዶች ሁሉ ዳናችን ታተመባቸው።በጠረናችን ነበራችን ተጻፈባቸው፡፡በፍቅር አብደን ነበር፡፡ስላለፈውም ስለ ወደፊቱም አላወራንም፡፡ማዕበሉ ወደፈለገበት እንዲወስደን ራሳችንን በፍቅር ጀልባ ላይ አስቀምጠን
ተውነው፡፡ በዚህ በኩል እንሂድ ብለን መንገድ ስላልመረጥን፣ የተሳሳተ መንገድ የሚባል ነገር በሕይወታችን አልነበረም፡፡ ምንም መዳረሻ ስላላለምን፣ የደረስንበት ሁሉ ልክ ነበር፡፡ ሮሐ ለፍቅር የተፈጠረች ልጅ ናት፡፡ ዝባዝንኬ ሳታበዛ በማፍቀር ብቻ፡፡የሕይወትን ደስታ ለምርኮ መውሰድ ተሰጥቷታል፡፡ ምርኮኛ ልሁን፣ አብሬያት ልሰለፍ ባይገባኝም፣ ብቸኛ ፍላጎቴ ሁልጊዜ የትም ቦታ አብሪያት መሆን ብቻ ነበር፡፡
ወደ ቤተሰብ ልመለስ ስዘጋጅ፣ ሮሐ አብረን እንሄዳለን ብላ መዘጋጀት ጀመረች፡፡ ከእንደገና የተዳፈነ ፍርሃቴ ሁሉ ተመለሰ፡፡ አንድ ላይ መሄዳችን ቢያንስ ለቤተሰቦቻትን ወሬው ጥሩ አይደለም፣ አንች ቆይተሸ ተመለሽ፣ ከሳምንት በኋላ መምጣት ትችያለሽ
አልኳት፡፡
ትክ ብላ እያየችኝ፣ “የራሱን መንገድ ተከትሎ የሄደ ሰው፣ ስእኔም ሆነ በአንተ ግንኙነት እንዲወስን አልፈልግም፡፡ ወላ ቤተሰብ፣ ወላ የአገሩ ሰው በሙሉ፡፡ ስለራሳችን ራሳችን ብቻ እንወስናለን
“ማለት የፈለኩት …"
“ማለት የፈለከውማ የጓደኛውን ገርል ፍሬንድ ቀማ ይሉኛል ነው፡፡ አይደል? ይበሉህ!አልቀማህም! ሲጀመር እኔ እንደ ኳስ የሚቀባበሉኝ መጫዎቻ አይደለሁም! ከልቤ ስላፈቀርኩህ የእውነት ስለወደድኩህ ነው አብሬህ የሆንኩት! መሐሪ የሚባል ጓደኛ ከአምስት ዓመት በፊት ነበረኝ፡፡ ለአንተም ጓደኛህ ነበር፡፡ አምናው ነፍሷን የሰጠችውን ሴት ቆሻሻ ላይ ሲወረውራት እክብረህ አነሳሃት ስላነሳሃት ሳይሆን፣ ከልቧ ስለወደደችህ
አብራህ ሆነች፣ በቃ! በራስህ ልትኮራ ነው የሚገባህ” የምትናገረው በቁጣ ስለነበር፣
የምላትን ነገር አጣሁ እናም ዝም ብዬ ስመለከታት
እሽ ሁሉም ነገር ይቅር፣ ተወልጀ ወዳደኩበት ከተማ መሄድ አልችልም እንዴ? ብላ ሳቀች፡፡
"አብሪያት ሳቅሁ"
“ግን በአጋጣሚ አውቶብስ ውስጥ ጎን ለጎን ካለ ወንበር ላይ አብሮኝ የተማረ ልጅ ጋር ተገናኘሁ፡፡ ይኼ መቼም አያስውግር አያሰቅል ወደኔ ጎትቸ አቀፍኳት፡፡ ጥብቅ አድርጌ አቀፍኳት፣ የእዉነት አፈቅራታለሁ፡፡ ምናባቴ እንደሚሻለኝ አላውቅም፡፡ ምን
እንደሚጠብቀን ደግሞ እርሷ አታውቅም
ቸኮ ነገር ነሽ”
በአንድ አውቶብስ ያውም የማውቃቸው የከተማችን ነጋዴዎች የታጨቁበት አውቶብስ በተደገፈችኝና በነካችኝ ቁጥር እየተሳቀቅሁ አብረን ተጓዝን፡፡ አዲስ አበባ ቆይቼ ስመለስ ሁልጊዜም ተወልጄ ያደኩባት ከተማ ትጠበኛለች፤ እታፈናለሁ፡፡ ሐሳቤ ከቤተሰቦቼ ጋር የተወሰነ ጊዜ ቆይቼ ወደ አዲስ አበባ ለመመለስና፣ሥራ ለመፈለግ ነበር ግን ያላሰብኩት ነገር ሆነ፡፡ በትውልድ ከተማዬ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ ሥራ አግኝቸ ጀመርኩ፡፡ ሥራዬ
መጀመሪያ አካባቢ አሰልቺ ነበር። የማንንም አጥርና ድንበር ስለካና ጓሮ ለጓሮ ስዞር እውላለሁ፡፡ ያውም ድንበሬ ተገፋ በሚል ነገረኛ እየተዘለፍኩና እየተዛተብኝ፡፡ የአገሬ ሰው ከአገሩ ድንበር የበለጠ፣ ለመኖሪያ ቤቱ ድንበር ልቡ ስስ መሆኑን ያወቅሁት ያኔ ነው፡፡ ለአገሩ የታፈሩ የተፈሩ የሚባሉ ሽማግሌ፣ የቡና ስኒ የማታስቀምጥ መሬት ከድንበሬ ሄደችብኝ ብለው፣ ሰው ካልገደልኩ ሲሉ አይቻለሁ፡፡ እንዲያውም እኔን ዝቅ
ያደረጉ መስሏቸው “ድንበሬን ማወቅ ከፈለከ ይኼን አባይ ሜትርህን ወዲያ ጣልና፣ አባትህን ሂድና ጠይቀው አጥሩን የሠራው እሱ ነው አሉኝ
ቤተሰቦቼ አብሪያቸው በመሆኔ በጣም ደስተኞች ስለነበሩ፣ እዚያው መቆየቴ ብዙም አላስከፋኝም፡፡ ከሮሐ ጋር መጀመሪያ አካባቢ ሰው አዬን አላዬን እያልን (እሷ እንኳን ግድ አልነበራትም ያው እኔው ነኝ አሳቻ ሰዓትና ቦታ፣ እየቆየን ግን ሰውም አውርቶ ሲወጣለት፣ በግልፅ መገናኘት ጀመርን፡፡ ያኔ ከሚተቸን ይልቅ “አይለያችሁ ባዩ ነበር የበዛው! መሐሪ ከነመፈጠሩም ተረስቶ ነበር፡፡ አንድ ሰው ብቻ መቆሚያ መቀመጫ አሳጥቶኝ ነበር ጋሽ አዳሙ የሚባል የሰፈር ሰካራም፡፡ ስለ እኔና ስለ ሮሐ እንዴት እንደሰማ እንጃ፣ ጠምዶ ያዘኝ፡፡ ቀን ላይ ሳይሰክር አግኝቸው ስላም ስለው፣ ዘግቶኝ
አለፈ፡፡ በቃ አኮረፈ፡፡ ማታ ታዲያ በዚያ ሲያልፍ …ልክ በራችን ላይ ቁሞ፣
“ያምባሰል ማር ቆራጭ ይወጣል
በገመድ፣ አደራ ቢሰጡት ይበላል ወይ ዘመድ ብሎ ይጮሃል፡፡ ትንሽ ይሄድና፣ ጅብ እንኳን የጓደኛውን ሚሰት አይነካም፡፡ በርግጥ ጓደኛው ቆስሎ ካገኘው ይበለዋል” ይላል፡፡ ብስጭት እላለሁ ሁል ጊዜ ይችኑን ነው የሚደጋግመው ከእኔ ወጭ እናቴም ሆነች አባባ አይገባቸውም ተራ የሰካራም ልፍለፋ ነበር የሚመስላቸው ።በእርግጥ የእኔ
ቤተሰቦች ከሮሐ ጋር የነበረንን ነገር አያውቁም ነበር፡፡ ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው እንዲሉ፣ አገር ምድሩ ሰምቶ ቤተሰቦቼ አልሰሙም፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ ከሮሐ ጋር ለመጋባት ስንወሰን ነው የነገርኳቸው
ላገባ ነው !" አልኳቸው
እልልልልልልል፡ እሰይ እንዲያው ከዛሬ ነገ እነግርሃለሁ ስል እሰይ! " አለች እናቴ
በደስታ፡፡
የጥሩ ሰው ልጅ አገኘህ ?አለ አባባ፡፡
“ታውቋታላችሁ፣ የጋሽ ግርማ ልጅ”
ግርማ የቱ" አለች እናቴ ፊቷ ላይ ያለው ፈገግታ ልከ እንደ አምፑል ባንዴ ድርግም ብሎ ጠፍቶ፡፡
“ሮሐ"
"እኮ ሮሐ የመሐሪ"
"አንቺ ደግሞ የመቼውን ታሪክ ነው የምታወሪው …”
“የመቼስ ቢሆን እታደረግውም!” አለችና ዘላ ተነስታ ጆርዋን በሁለት እጇ ይዛ ወደ
ውስጥ ገባች፡፡እናቴ እንዲህ ስትሆን አይቻት አላውቅም! እንደ ኣንዳች ነገር ተቀያየረች፡፡ ተከትዬት ላሳምናት ብዙ ሞከርኩ፡፡ ወይ ፍንክች! እንዲያውም ሦስት ቀን ሙሉ ዘጋችኝ፡፡
አባባ ምኑም አልገባውም፣ አላስታወሳትም፡፡ ሮሐ በበኩሏ ለቤተሰቦቿ ስትነግራቸው አበዱ፡፡ ስንገናኝ ልክ እንደ አባቷ እየተንጎራደደች ያሉትን ሁሉ እየሳቀች ነገረችኝ “አንች
ለመሆኑ እዚያ ሰፈር የሚያልከሰክስሽ ምንድነው? ያስነኩሽ ነገር አለ? ሌላው ይቅር እንዴት ኅሊናሽ እሽ ይልሻል፣ ጓደኛውን? የዝናቡ ልጅ ከአባቱ ጋር ጠበኞች ነን፡፡
ቢሆንም ሞራል የሚባል ነገር አለ፡፡ እሱስ ምናይነት አንገት የሌለው ሰው፣ ነው ጓደኛው ታስሮ ምናይነት ዘመን ላይ ደረስን ባካችሁ? ሆሆሆሆሆሆሆሆ!”
በዚያ ብንል በዚህ የሁለታችንም ቤተሰቦች ባንገታችን ገመድ ቢገባ ይኼን ቅሌት አንፈቅድም አሉ፡፡ በተለይ እናቴ አታንሱብኝ አለች፡፡ ገና ነገሩን ሳነሳው ልክ እንደ ወባ ያንዘፈዝፉታል፡፡ ነውር የነውር ነውር መታሰቡስ አልውለደው እንጅ መሐሪ ልጄ ነው እስካሁን ልቤ አብሮት ታስሯል ልጀ ! ትላለች በቁጣ፡፡
አንድ ቀን ሮሐ እቤታችን መጣች፡፡ የቤተሰቦቼን ቤት በአንድ በኩል አስፈርሽ ሰፋ አስደርጌ ሰርቸላቸው ስለነበር፣ ልይላችሁ በሚል ሰበብ፣ ፍጥጥ ብላ መጣች፡፡ አሳዘነችኝ፡፡ እኔን ለማግባት እየተለማመጠች ነበር

👍4
፡፡ እናቴ ታዲያ ገብቷታል፡፡ ሮሐን ይዛት ወደ ውስጥ ገባችና እንዲህ አለቻት “ሮሐዬ !አንቺን የመስለች ቆንጆ አግብቶ አስር
ልጅ ወልዳችሁልኝ፣ አስሩንም እኔ ባሳድግ ደስታየ ነበር፣ በምን ዕድሌ፡ ፀባዩንም
መልኩንም ሳይሰስት የሰጠሸ ጥሩ ልጅ ነሽ …ግን ምናባቴ ልሁን! የመሐሪ እናት ማለት እህቴ ናት …የእድሜ ልክ ጓደኛዬ፣ የክፉ ቀኔ በችግሬ ደራሽ ለመሐሪም ለአብርሽም ልብስ እየገዛች ያሳደገች፣ ደብተር እየገዛች ያስተማረች፣ ቢታመም እንደራሷ ልጅ አቅፋ ሆስፒታል ስታሳከም የኖረች፣ በዚህ ነገር እንዴት ልቧን ልስብራት ነውርኮ ነው! እድሩስ
ሰው ያደርገኛል እንዴ? መንደሩ ሰው ያረገኛል …የአንች ጥፋት አይደለም፣ ጥፋቱ የኔው ልጅ ነው! አንችማ ምን ታውቂዋለሽ" አለቻት…
“አብርሽ ምንም አላለም፣ እኔ ራሴ ነኝ የወደድኩት አለች ሮሐ እንባ እየተናነቃት፡፡
“ወይ ጣጣ …! እንግዲህ እምቢ ካላችሁ ሰዎቹ ወደሚሄዱበት ውጭ አገር ሩቅ አገር፣ ዓይኔ የማያይባችሁ አገር ሂዱና፣ እንደፈለጋችሁ ሁኑ፡፡ በኩሌ ሞቴን እመርጣለሁ፡፡እዚህ እናንተ ተጋብታችሁ፣ ሰው ቀና ብዬ አላይም፣ እፍረቱም ይገድለኛል ብላ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች፡፡ ሮሐም እናቴ ፊት በእንባ ታጠበች፡፡ ተቃቅፈው ተላቀሱ፡፡ ቅስሟ ተሰብሮ እቤቷ ሄደች፡፡እኔም ቃል ሳልተነፍስ ገብቼ ተኛሁ፡፡እንቅልፍ አልወሰደኝም፡፡
ማታ ላይ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ይሆናል፣ ጋሽ አዳሙ እየጮኸ መጣ፡፡ ገና ድምፁን
ስሰማው ነበር ውስጤ የተቆጣው፡፡ ስራችን ላይ ሲደርስ ቆም ብሎ ተቀብል” ብሎ ጨኾና፣ መዝፈን ጀመረ፡፡ ደግሞ ድምፁ እንዴት ያምራል፣ እንዴት ያበሳጫል፡፡
ያምባሰል ማር ቆራጭ ይወጣል በገመድ፣
እደራ ቢሰጡት ይበላል ወይ ዘመድ፡፡
አምባሰል ተንዶ ግሸን ደግፎታል፣
ግሽን መደገፉ የኔ ቃል ማከበር ነው፣
እምባሰል መናዱ ያንች ቃል ፈርሶ ነው፣
ይብላኝልሽ ላንች ቃልሽ ለፈረሰው፣
የጁን መች ያጣዋል ቁሞ ከሄደ ሰው !!.…
ዘልዩ ተነሳሁና በሩን ከፍቼ ወጣሁ፡፡ እናም ቀጥ ብዬ ሂጄ “ሰው መተኛ ያጣል እንዴ?
ለምን አፍህን እትዘጋም ሰውዬ!?” ብዬ እምባረኩበት። እናቴ ተንደርድራ ወጥታ
እየጎተተት አስገባችኝ ምንም አልተናገረችም፡
“እጮኻለሁl ተይው አትጎትችው ይምጣ ይደብድበኝ የኔ የአዳሙ ጩኸት
እንዳይመስልሽ እንቅልፍ የነሳው! የራሱ ኅሊና ነው፣የራሱ ኅሊና አፍ ቢዘጋ ኅሊና ዝም እይልም የጅብ አገር ሕግ ባይምር፣ እንዴት ጓደኛ ጓደኛውን እይምርም? እንዴት ነው የሚኖረው እዚች ምድር ላይ? .…ድንበር መለካት ብቻ አደደለም መሐንዲስነት፣
ለራሳችን ስግብግብነትም ድንበር ማበጀት ነው:: ሁሉ ነገር ድንበር እለው፡፡ አቶ መሐንዲስ እኔም መሐንዲስ ነኝ፡፡ ሰው የሞራል ድንበሩን ሲያልፍ፣ እዚያ ነው
ድንበርህ እላለሁ፡፡ በሕግ አምላከ እላለሁ፡፡ በሕግ አምላክ ፍቅር በተዛነፈ መሠረት ላይ ሲቆም፣ ነገ ተንዶ ትውልድ ከመጫኑ በፊት በሕግ አምላክ እላለሁ ” እስኪበቃው ደንፍቶ በጨለማው ውስጥ ድምፁ እየቀነሰ …እየቀነሰ እየቀነስ ሄዶ ሰፈሩ ፀጥ ረጭ አለ፡፡ ዓይኖቸ በእንባ ተሞሉ፡፡

👍3
#ከጎርፍ_የተቀዳ_ዜማ
ዝናቡ ዘነበ ፥ ደጁ ረሰረሰ
በአልጋዬ በኩል ፥ ጣሪያዬ አፈሰሰ
ጭጋግ ቤቴ ገብቶ ፥ ቆፈን አላበሰው
ጎርፍ በበሬ ላይ
ትዝታ እያዜመ ፥ ይሔዳል እንደሰው።
እየተመሰጥኩኝ
በመደፍረሱ ውስጥ ፥ በሚያወጣው ዜማ
ድንገት ሲያልፍ አየሁት
የአንድ እግር የሆነ ፥ የነጠላ ጫማ።
እህህ ትዝታሽ
አንድ አመት በሚያህል ፥ በሆነ አንድ ቀን
አየር ለመቀበል ፥ ከከተማ ርቀን
እጄ አንገትሽ ላይ ፥ ሊያሞቅሽ ተጥዶ
እጅሽ ወገቤ ላይ ፥ ሊያሞቀኝ ተማግዶ
በዛፎች እስክስታ
ባበቦች ውብ ሽታ
በአእዋፍ ዜማ ፥ እንዳዲስ ታድሰን
በራሳችን አለም ፥ አንዲት ዳስ ቀልሰን
ከቆየን በኃላ
ወደ መጣንበት ፥ ስንሔድ ተመልሰን
ደመና ሳይዳምን
ሰማዩ ሳይጠቁር ፥ ዶፍ ዝናብ ጥሎብን
እንጠለልበት ፥ ሰፈር እርቆብን
እየበሰበስን
እየገሰገስን
ትንፋሽሽ ሲያሞቀኝ ፥ ገላሽን ሳይበርደው
ጭቃ ሲያዳልጠን
መንገዱን ስንወድቀው ፥ መንገዱን ስንሄደው
ያንድ እግርሽን ጫማ
ከእግርሽ ላይ መንትፎ ፥ ጎርፍ እንደወሰደው
አስታወሰኝ ጎርፉ
ለዛ ነው መሰለኝ
ትዝታሽን ሲያዜም ፥ በበሬ ማለፉ፡፡
እህህ ትዝታሽ...
ዝናብ ዘንቦ ዘንቦ ፥ ያባራል ሲበቃው
እስከሚያባራ ነው
ጣሪያው ቢያንጠባጥብ
አልጋዬ ቢረጥብ ፥ ቢያዳልጠኝ ጭቃው፡፡
ትዝታሽን ለቅሞ
ትዝታን አዚሞ
ግሳንግሱን ሁሌ ፥ ኬ'ትም አጠራቅሞ
በበሬ 'ሚያልፍ ጎርፍ ፥ ጫማ ተሸክሞ
ይሄው አሁን ደሞ
ፌስታልና ኮዳ ፥ አመጣልኝ ገፍቶ
ሳርና ቅጠሉን ፥ ወሰደ ጎትቶ።
እህህ ትዝታሽ
ካንድ አመት በሚበልጥ ፥ በሆነ አንድ ቀን
አየር ለመቀበል ፥ ከከተማ ርቀን
የሔድንበት ቦታ ፥ ከዋልንበት ቀዬ
ሙዝና ቡርትካን
ያረገዘ ፌስታል ፥ ባንድ እጄ አንጠልጥዬ
አንዱን እጄን ደሞ ፥ አንገትሽ ላይ ጥዬ
የፕላስቲክ ውሃ ፥ በጅሽ አንጠልጥለሽ
አንድ እጅሽን ደሞ ፥ ወገቤ ላይ ጥለሽ
ያረፍንበት ቦታ
ካንድ ዛፍ ገላ ላይ ፥ ቅርንጫፍ መልምለሽ
እሱ ላይ ተቀምጠን ፥ ቆይተን ቆይተን
ሚበላውን በልተን ፥ ውሃውን ጠጥተን
ፌስታሉን
ቅጠሉን
የውሃ ኮዳውን ፥ ያለንበት ትተን
እንደተመለስን ፥ አስታወሰኝ ጎርፉ
ለዛ ነው መሰለኝ
ትዝታ እያዜመ ፥ በበሬ ማለፉ።
እህህ ትዝታሽ
ዝናብ ዘንቦ ዘንቦ ፥ ያባራል ሲያበቃ
እስከሚያባራ ነው
ቆፈን ቢቆፍነኝ ፥ ቢያዳልኝ ጭቃ
እስከሚያባራ ግን
ጎርፍ ያመሽ እንደው
አለሁ በትዝታሽ ፥ አለሁ በጥበቃ።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
ዝናቡ ዘነበ ፥ ደጁ ረሰረሰ
በአልጋዬ በኩል ፥ ጣሪያዬ አፈሰሰ
ጭጋግ ቤቴ ገብቶ ፥ ቆፈን አላበሰው
ጎርፍ በበሬ ላይ
ትዝታ እያዜመ ፥ ይሔዳል እንደሰው።
እየተመሰጥኩኝ
በመደፍረሱ ውስጥ ፥ በሚያወጣው ዜማ
ድንገት ሲያልፍ አየሁት
የአንድ እግር የሆነ ፥ የነጠላ ጫማ።
እህህ ትዝታሽ
አንድ አመት በሚያህል ፥ በሆነ አንድ ቀን
አየር ለመቀበል ፥ ከከተማ ርቀን
እጄ አንገትሽ ላይ ፥ ሊያሞቅሽ ተጥዶ
እጅሽ ወገቤ ላይ ፥ ሊያሞቀኝ ተማግዶ
በዛፎች እስክስታ
ባበቦች ውብ ሽታ
በአእዋፍ ዜማ ፥ እንዳዲስ ታድሰን
በራሳችን አለም ፥ አንዲት ዳስ ቀልሰን
ከቆየን በኃላ
ወደ መጣንበት ፥ ስንሔድ ተመልሰን
ደመና ሳይዳምን
ሰማዩ ሳይጠቁር ፥ ዶፍ ዝናብ ጥሎብን
እንጠለልበት ፥ ሰፈር እርቆብን
እየበሰበስን
እየገሰገስን
ትንፋሽሽ ሲያሞቀኝ ፥ ገላሽን ሳይበርደው
ጭቃ ሲያዳልጠን
መንገዱን ስንወድቀው ፥ መንገዱን ስንሄደው
ያንድ እግርሽን ጫማ
ከእግርሽ ላይ መንትፎ ፥ ጎርፍ እንደወሰደው
አስታወሰኝ ጎርፉ
ለዛ ነው መሰለኝ
ትዝታሽን ሲያዜም ፥ በበሬ ማለፉ፡፡
እህህ ትዝታሽ...
ዝናብ ዘንቦ ዘንቦ ፥ ያባራል ሲበቃው
እስከሚያባራ ነው
ጣሪያው ቢያንጠባጥብ
አልጋዬ ቢረጥብ ፥ ቢያዳልጠኝ ጭቃው፡፡
ትዝታሽን ለቅሞ
ትዝታን አዚሞ
ግሳንግሱን ሁሌ ፥ ኬ'ትም አጠራቅሞ
በበሬ 'ሚያልፍ ጎርፍ ፥ ጫማ ተሸክሞ
ይሄው አሁን ደሞ
ፌስታልና ኮዳ ፥ አመጣልኝ ገፍቶ
ሳርና ቅጠሉን ፥ ወሰደ ጎትቶ።
እህህ ትዝታሽ
ካንድ አመት በሚበልጥ ፥ በሆነ አንድ ቀን
አየር ለመቀበል ፥ ከከተማ ርቀን
የሔድንበት ቦታ ፥ ከዋልንበት ቀዬ
ሙዝና ቡርትካን
ያረገዘ ፌስታል ፥ ባንድ እጄ አንጠልጥዬ
አንዱን እጄን ደሞ ፥ አንገትሽ ላይ ጥዬ
የፕላስቲክ ውሃ ፥ በጅሽ አንጠልጥለሽ
አንድ እጅሽን ደሞ ፥ ወገቤ ላይ ጥለሽ
ያረፍንበት ቦታ
ካንድ ዛፍ ገላ ላይ ፥ ቅርንጫፍ መልምለሽ
እሱ ላይ ተቀምጠን ፥ ቆይተን ቆይተን
ሚበላውን በልተን ፥ ውሃውን ጠጥተን
ፌስታሉን
ቅጠሉን
የውሃ ኮዳውን ፥ ያለንበት ትተን
እንደተመለስን ፥ አስታወሰኝ ጎርፉ
ለዛ ነው መሰለኝ
ትዝታ እያዜመ ፥ በበሬ ማለፉ።
እህህ ትዝታሽ
ዝናብ ዘንቦ ዘንቦ ፥ ያባራል ሲያበቃ
እስከሚያባራ ነው
ቆፈን ቢቆፍነኝ ፥ ቢያዳልኝ ጭቃ
እስከሚያባራ ግን
ጎርፍ ያመሽ እንደው
አለሁ በትዝታሽ ፥ አለሁ በጥበቃ።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
👍1