#ምንትዋብ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ
...ጥላዬ፣ ከአለቃ ሔኖክ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እየመሠረተ ሲመጣ፣ብዙ ጊዜ አብሯቸው መቀመጥና መጫወት ሥዕል ከመሣል ቀጥሎ የሚያስደስተው ነገር ሆነ። ወደፊትም እንደሳቸው ጥበበኛ መሆን አበክሮ ተመኘ። ላደረጉለት ሁሉ ሲያመሰግናቸው ቢውል አላጠግበው አለ።
“አለቃ ላረጉልኝ ሁሉ እመቤቴ ምላሹን ትስጥዎ” አላቸው፣ አንድ
ቀን እንደወትሮዋቸው ግቢ ውስጥ ተቀምጠው ሲያወሩ።
“እኔኮ ማስተምረው ኸተማሪዎቸ ጥቅም አገኛለሁ ብየ ማዶል። ልክ
መምህሬ የነበሩት አለቃ ወልደሰንበት ደከመኝ ሳይሉ፣ ሚያውቁትን ሁሌ ሳይሸሽጉ እንዳሳተማሩኝ ሁሉ ተማሮቸን ማስተማር ፈልጋለሁ።ዋጋየ እናንተ ተማሮቸ ጥሩ ተምራችሁ ለጌታችን ያላችሁን እምነት፣ ክብርና ፍቅር በሥራችሁ ስታሳዩ፣ የመጻሕፍትን ምሥጢር አንብባችሁና ተረድታችሁ በሥዕል ስትገልጡ ነው። ሥዕል ዋናው ዓላማው ቤተስኪያንን ማስጌጥ ማዶል። ሥዕል እኮ ታሪክ ነው ሚነግር፤
ሥዕሉ ራሱ እኮ ወንጌል ነው። ምእመኑ የመጻሕፍቱን ምሥጢር
አውያቁም፣ አያነቡም፡ አይረዱም። ስለዝኸ የእናንተ ሥራ የመጻሕፍቱን ምሥጢር... ወንጌሉን በሥዕል እንዲረዱና መንፈሳዊነት፣ አክብሮትና
ፍራት በልባቸው እንዲያድር ማረግ ነው። ባለፈው እንደነገርኩህ ካህናቱ አምስቱን አዕማደ ምሥጢር በንባብ በሐተታ ይማራሉ።ምእመኑ ግን በሥዕል ነው ሚማር። ቀዳሚው ምሥጢረ ሥጋዌ ነው፣ኸገብርኤል ብሥራት ትጀምራለኽ። ገብርኤል ማርያምን ትፀንሲ ይላታል። ኸዚያ ልደቱን ትሥላለኸ። ልደቱን ስትሥል ሰብአ ሰገል እረኞቹም አሉ። ግዝረቱን ደሞ ቀጥለኽ መሣል ነው፤ ስምዖን አለ አሉ፣ አድግና ላሕም አሉ... ጌታን በትንፋሻቸው ያሞቁት፣ መልአኩም አብሮ ሚጠቀስ፤ ዓይኖቼ ማዳንህን ስላዩ በል ውሰደኝ ብሎ ጸልዮ
ይሞታል ። ኸዚያ ምሥጢረ ጥምቀቱ፣ ተአምራቱ፣ ቃና ዘገሊላው፣ አስተምህሮቱ አለ። ኸዚያ ምሥጢረ ቁርባንን ትሥላለህ፤ ሥቅለቱን አብረህ። ቀጥለህ ትንሣኤውንና ዕርገቱን ትሥላለህ። መጻሕፍት
በስንትና ስንት ምዕራፍ ያካተቱትን ታሪክ ሠዓሊው በጥቂት ብራናዎች አሣምሮ ቀምሮ ያስቀምጠዋል። ስለዚህ ምሥጢራቱን፣ የቱ ቀድሞ
የትኛው ሚከተል መሆኑን መመርመር ያስፈልጋል፤ የቀለም ማሳመር ብቻ ለሠዓሊነት አይበቃም።”
ጥላዬ፣ በተመስጦ አዳመጠና “እሺ የንታ፤ ንባቤንም ሥራዬንም
ተግቼ እቀጥላለሁ፤ ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ” አላቸው፣ ትምህርታቸውን ከልቡ አዳምጦ።
“ዋናው ነገር እሱ ነው... ትጋት” አሉት፣ ሌባ ጣታቸውን እያወዛወዙ። “አንተን ትጉ ሁነህ አግኝቸኻለሁ። ምን ስጦታ ያለው ቢሆን ትጋት የሌለው ተማሪ አልወድም። ሥዕል ችሎታ ቢኖርህ ትጋት ኻላሳየህ ለሥራህ ጥሩ አይሆንም። አሁን በየቦታው ያሉት የተከበሩት ሠዓሊዎች አለሱ ሌላ ንሮ የላቸውም። አንዳንድ ተማሪ ይመጣል ኸኔ ዘንድ።እንዳው ብቻ ጫር ጫር አርጎ ቤተክሲያን ውስጥ ገብቶ ሥዕል
መሣል ይፈልጋል። ይኸ እንዴት ብሎ ይሆናል? ሥዕል ቀልድ ነው
እንዴ? እኔማ እንደዚያ ያለውን ተማሪ ኸኔ ዘንድ አላቆየውም። አንተ ለሥዕልም ለቤተክሲያንም አትሆንም ብየ ነው ምሰደው። ችሎታ አለ ትጋት ምንድርነው? አይምሰልህ ጥላዬ ሥራን ትልቅ ደረጃ ሚያደርሰው ትጋት ነው። እኔስ ብሆን አንድ ተማሪ ትጋት ካላሳየ ኸሱ ጋር ስለምን
እደክማለሁ? እስቲ በል ንገረኝ?”
“ውነት ነው... ውነት ነው” አለ፣ ጥላዬ ራሱን በአዎንታ እየነቀነቀ።
ልቡ ተነካ። ሥዕል እየሣለ ቤተክርስቲያንን ማገልገል እንዳለበት ይመኝ እንጂ፣ እንደዚህ ጠለቅ ብሎ ነገሩን አስቦበት አያውቅም።በአካባቢው የሚያያቸውን ቤቶች፣ ሰዎችና እንስሳት ቤታቸው ግድግዳ
ላይ ሲሥል ቢቆይም፣ የሚሥላቸውን ምስሎች ለዘላለም ቀርጾ ማስቀመጥ ከሚመኛቸው ነገሮች አንዱና ዋነኛው ምንትዋብን ነው። በተለይም
ደግሞ ነጠላ ተከናንባ ከቤተክርስቲያን ስትወጣ ያያት የነበረውን።
“ለሥዕል ያለኝ መውደድ ለብቻ ነው። ኸርሶ ዘንድ መማሬ ደሞ
ይበልጥ እንድወደው አድርጎኛል።”
“እኔም ለሥዕል ይኸ ነው ተብሎ ማይነገር ፍቅር አለኝ” አሉት።
“አለሱ ሌላ ሕይወት የለኝም። ሥዕል ሳይ እመራመራለሁ። የሠራሁትን ሥራ መልሼ ሳየው 'በውነት ይኸን የሠራኹ እኔ ነኝ ወይስ በኔ እጅ ራሱ ባለቤቱ ሣለው ብዬ እደነቃለኹ። ሥዕል የእዝጊሃር ወይም የደቂቀ
አማልክቱ ሥራ እንጂ የእኛ የደካሞቹ ፍጥረት አይመስለኝም። ጥላዬ...ሥዕል እኮ እንደ ቅኔ ከሳቴ ብርሃን ነው... የተደበቀውን ምሥጢር ሁሉ ሚገልጥ... ብርሃን ሚሰጥ። ለዝኽ ነው ቅኔን ብዙ ሊቃውንት ልሳነ መላእክት ነው ሚሉት።
ጥላዬ፣ መስማማቱን ለማሳየት ራሱን ነቀነቀ። “የንታ ሥዕል ለመማር እንደዛ ስመኝ ቆይቸ አሁን መማር በመቻሌ ዕድለኛ ሁኛለሁ።”
“ዕድል ኸሰማይ አይወድቅም” አሉት፣ ፊታቸውን ወደሱ መልሰው።
“ዕድል እንደ ሥዕል ነው። ሚገባው ዘንድ ነው ሚኸድ። ማይሆነው... ዝግጁ ሁኖ ማይጠብቀው ዘንድ አይኸድም። ወይም ማይሆነውን አይጣራም። ዕድል ልክ እንደ ሥዕል ሚፈልገውን ያውቃል፣ አውቆም
ይጣራል፣ ወይም ራሱ ወደሱ ይኸዳል። እንዳንተ ያለውን... የነፍሱን ጥሪ ሚያቀውን ኻለበት ፈልጎ ያወጣዋል። አንተም ዛዲያ ስትፈልገው፣ እሱም ሲፈልግህ... ስትፈላለጉ ቆይታችሁ ተገናኛችሁ።”
“አየ የንታ የእዝጊሃር ቸርነት ተጨምሮበት ነው።”
እዝጊሃር እኮ ማትችለውን አይሰጥህም። ጎበዝ ብትሆን ነው የሰጠህ።”
ውነት ነው አለ፣ ለራሱ።
“አሁን ይልቅ ምመክርህ” አሉት፣ ሌባ ጣታቸውን እያወዛወዙ፣ “ደብረ ወርቅ ኸደህ ሌሎች አስተማሮች ዘንድ መማርን ነው። እንደ ሌላው ትምርት ሁሉ ሥዕል እየተዘዋወርህ ስትማር ብዙ ትምርት ትቀስማለህ፣
ችሎታህንም ታዳብራለህ። ደብረ ወርቅ ታላላቅ የሥዕል መምህሮች
አሉ። እኔ እንደምታየው እያረዥሁ ነው። ኸንግዲህ እንደድሮው
ማስተማር አልችልም። አንተንም ገና ሳይህ ቀልቤ ስላረፈብህ
ተቀበልኩህ እንጂ ማስተማር እተዋለሁ እያልሁ ነበር” አሉት።
“የንታ ኸርሶ ዘንድ በቆየሁ። ኸርሶ መለየቱ ይከብደኛል።”
“ምን ይደረግ። እየደከመኝ መጣሁ።”
“ኸዝሁ ሌላ መምር ዘንድ ብቆይስ?”
“ሊቀጠበብት ኣዳሙ ዘንድ ነው እንድትማር የፈለግሁት። አዳሙ
ወደር ማይገኝለት መምህር ነው። ለኔም የረዥም ግዝየ ወዳጄ
ነው። እስታሁንም ብዙ ተማሮቸን ወደሱ ልኬያለሁ። አንተም ኸሱ
ዘንድ እንድትማር ነው ምፈልግ። ትምርትህን ስትጨርስ ተመልሰህ
ትመጣለህ።”
ጥላዬ፣ ጐንደር የዕድል በር ከፈተችልኝ፣ አለቃን መምህሬ፣ ጐንደርን ቤቴ ብሎ ተመቻችቶ ተቀምጦ፣ እንደዚህ ዓይነቱ ዱብ ዕዳ ሲመጣበት ደነገጠ፤ ሆድ ባሰው፤ መንፈሱ ተረበሸ፤ ተስፋ ሊቆርጥ ቃጣው።ከአለቃ ሔኖክ ሥር ሆኖ ታላቅ ሠዓሊ ለመሆን ያደረበትን ምኞት፣ከቤቱ ሲወጣ የሥዕል ንጉሥ ለመሆን የነበረውን ሕልም ሁሉ ጉም ሸፈነው። ደብረ ወርቅ ይሂድ ወይንም እዛው ጐንደር ሌላ አስተማሪ ዘንድ ይማር ለመወሰን አቃተው፤ ግራ ገባው። ምንትዋብን በአካል
ባያገኛትም እንኳ ከእሷ ርቆ መኖሩ ደግሞ አሳሰበው፣ አሳዘነው።....
።።።።።።።።።።፡፡።።።።።።።።።።።።
“ቁስቋም ብዙ ነገር ሰጥታኛለች፣ ወንድ ልዥ ደሞ ብትሰጠኝ።”

👍13😁1
#ትኩሳት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር
ባህራም
ሞት
ያን ሰሞን ጀምሺድ ታሞ ተኛ፡፡ ልጠይቀው ወደ ቤቱ ሄድኩ።
ሌሎቹ በሚጠይቁት ሰአት ብሄድ ምንም አልጠቅመውም በማለት፣
በትምህርት ሰአት ሄድኩ። ፎቁን ወጥቼ በሩን ብሞክረው ተቆልፏል። ደወሉን ተጫንኩት፣ ውስጥ ሲደውል ተሰማኝ፡፡ ቆየሁ
የጀምሺድ ቤት ሳይሆን፣ በግራ በኩል ያለው የጎረቤቱ በር
ተከፈተ። መነፅር ያደረገ መላጣ ሽማግሌ ሀኪም አንገቱን ብቅ ከርጎ አየኝ፡፡ አየሁት። ከበሩ ወጣ፡፡ ነጭ የሀኪም ኮቱ በጣም ንፁህ ነው፡፡በእጁ መርፌ ይዟል። ጀምሺድ የነገረኝን ታሪክ አስታወስኩ ሀኪሙ ዙሪያውን ተገላመጠና ሲያበቃ፣ ማንም እንደሌለ ካረጋገጠ በኋላ፣ በሹክሹክታ
«ይምጡ ልውጋዎት» አለኝ
ዝም ብዬ አየሁት
ካልፈለጉ ላስገድድዎት አልችልም፡፡ ነፃነትሳ? ዳሩ፤ ለኔ ያው ነው፡፡ ደሞ ደንታ የለኝም እንጂ» እያለ ለራሱ እያጉረመረመ ወደ ጀምሺድ ተኝቷል መሰለኝ ብዬ ደረጃውን መውረድ ስጀምር
በሩ ተከፈተ። ዘወር ስል ኒኮል ነች
“ይቅርታህን። አስጠበቅኩህ? ሽንት ቤት ነበርኩ» አለችኝ::
አመዳም ፀጉሯ ተሞነጫጭሯል። ሸሚዟ በአንድ በኩል ከጉርዷ
ወጥቷል። ገባኝ፡፡ ጀምሺድ አልጋው ውስጥ ትራስ ተደግፎ
እንደተቀመጠ፣ እየሳቀ
ዶክተር ሽቫይትዘር መርፌ ይውጉህ?» አለኝ፡፡ የሱም ፀጉር
ተሞነጫጭሯል ግምባሩ ላይ ወድቋል፡፡ ግን ፈፅሞ የታመመ
አይመስልም።
ኒኮልና ጀምሺድ እየተሻሙ ስለዶክተሩ ነገሩኝ። ሰውን
የማይጎዳ ሰላማዊ እብድ ነው፡፡ የመጣውን ሁሉ መርፌ ልውጋዎት? እያለ ይጠይቃል፣ አሉኝ። አነጋገራቸው አንድ ነገር ለመደበቅ የፈለገ ሰው አነጋገር ይመስላል
ትንሽ ቆይታ ኒኮል ከፍል አለብኝ ብላ ሄደች፡፡ ጀምሺድ
ስለጎረቤቱ ዶክተር ኮሚክ ወሬ እያወራ ሲያስቀኝ ቆየና ተነስቶ ወደ ሽንት ቤት ገባ
በፍጥነት በፀጥታ ተነስቼ የራስጌውን ፍራሽ አነሳሁ፡፡ አልጋው ሽቦ ላይ አንድ ጥቁር የሴት ሙታንቲ፡፡ ሙታንቲው ኣጠገብ አንድ አምስት የተጨማደደ ለስላሳ ክሊኔክስ ወረቀት ወረቀቶቹ ፅጌረዳ አይነት ስለሆኑ ርጥበታቸው ለአይን ያስታውቃል። ጎምበስ
ብዬ ወረቀቶቹን አሸተትኩ፡፡ የግብረ ስጋ ሽታ። ያለጥርጥር፡፡
ተመልሼ ወምበሬ ላይ ከተቀመጥኩ በኋላ፣ ተነስቼ የሰው ጉድ ሳሽት ታየኝና፣ ለራሴ ሸርሎክ ሆምዝ!» ብዬ በሀይል መሳቅ
ጀመርኩ ጀምሺድ ከሽንት ቤቱ «ለምን መሳቅ?» አለኝ
«መርፌ መውጋት» አልኩትና ሳቄን ቀጠልኩ
ሉልሰገድ ስለኒኮል ባይነግረኝ ኖሮ፣ ኒኮልንና ጀምሺድን እጠረጥር ነበር? አይመስለኝም
በጀምስድ አገር ደምብ የሚያፈላው ሻይ በጣም ይጣፍጣል።
እሱን እየጠጣን ወሬ ጀመርን
ጀምሺድ እንደሚለው ከሆነ፣ በቁማር መክበር አይቻልም።
በቁማር የሚከብር ቁማር ቤቱ ብቻ ነው፡፡ ምንም ያህል ብትበላ
ያችን የበላ ሀትን ተመልሰህ እስክታስበላ ያቁነጠንጥሀል። በቁማር ለመክሰር እንጂ ለመክበር አይቻልም። እንዲህ ከሆነ ጀምሺድ ለምን
ቁማር ይጫወታል? ... ሰካራሙ ለምን ይጠጣል?ለጀምሺድ እንደሚታየው፣ ኑሮ ጨቅጫቃ ሚስት ናት፡ ና ምግብ ብላ፣ ና ተኛ፣ ና ሽንት ቤት ሂድ፣ ና ትምህርት ተማር፣ ና ይህን አድርግ፣ ና ያንን ፈፅም፣ እያለች መነዝነዝ ነው ስራዋ፡፡ ታድያ የሰው ልጅ ከዚህ ሁሉ ጭቅጭቅ ለመሸሽ አንዳንድ ጊዜ ቢሰክር ይፈረድበታል?
ጀምሺድ ዮኑሮን ችኮነት ሊረሳ የሚችለው ቁማር ቤት የሄደ
እንደሆነ ነው። ቁማር ቤት ውስጥ ያለችው ኑሮ፣ ነዝናዛ ችኮ ሚስት
ሳትሆን፣ የማትጠገብ፣ ለዛዋ ሁልጊዜ የሚታደስ ውሽማ ናት። ኮት የምታስሽጥ ውብ ውሽማ!
«እኔ ቁማር ስጫወት መኖሬን እረሳለሁ፡፡ መኖሬን ሲረሳ፣ ያን
ጊዜ ኑሮን ኖርኳት ነኝ ማለት ነው:: ሌላ ጊዜ ኑሮን ሲኖራት፣ እኔን
እያታለልኩ ነው ችኮ ናት ደስታ የለም፡፡ ቁማር ጊዜ ግን፣ ቁማር
ፈፅሞ ሲውጠኝ ሳለ። ኑሮ መሀል ውስጥ እገባ፣ ከንቱ አይደለች፣
እላያትም እኖራታለሁ ማለት»
ጀምሺድ ስለቁማር ሲያወራ አይኖቹ አይስቁም
እንስሳ ኑሮ አይሰለቸውም (ይሄ የጀምሺድ አስተሳሰብ ነው)
ምክንያቱም እንሰሳ ይኖራል እንጂ መኖሩን አያውቅም። ስለዚህ ኑሮ
አይመረውምም አይሰለቸውምም። ስለዚህ ነው እንሰሳ ራሱን የማይገለው። «በሬ ወይም አህያ ወይም አይጥ ወይም ውሻ ወይም ሌላ፣ ራሱ ገደለ እሱ ሰምተሀቸዋል ታውቃለህ?» ሰውን ከእንሰሳ
የሚለየው ማሰቡ አይደለም፡፡ በመጠኑ ይሁን እንጂ እንሰሳም
ያስባል። ሰው ከእንሰሳ የሚለየው በመሳቁ አይደለም። ዝንጀሮም
ይስቃል። ሰው ከእንሰሳ የሚለየው፣ ህይወቱን እየኖራት እንደሚኖራት በማወቁ፣ ከህይወት በኋላ ሞት መከተሉን በማወቁ፤ እነዚህም እውቀቶች ለሰው ልጅ ኑሮን ከንቱ፣ ሞትን መራራ በማድረጋቸው በዚህ ነው ሰው ከእንሰሳ የሚለየው
በመሰረቱ ህይወት ግሩም ስጦታ ናት። ኑሮ ግን ይሰለቻል።
ሀዘን ሞልቶበታል፡፡ ብስጭት ይበዛበታል፡፡ በሽታ ወሮታል። ሞት
ደሞ ይቆያል እንጂ አይቀርም። ስለዚህ መሞት ላይቀር፣
ብስጭት ሊበዛ፣ ለምን አሁኑኑ
አንሞትም? ለምን ራሳችንን አንገድልም? ችኮ የሆነ ሀዘን፣ ብስጭት የወረሰው እውቀት ምኑ ይወደዳል? ራሳችንን የማንገድለው ሞትን
ስለምንፈራ ብቻ ነው። ፈሪ ነን በቃ፡፡ ይኸው ነው ስለዚህ፤ ልናደንቀው የሚገባ ሰው ማን ነው? ራሱን ለመግደል የደፈረ ሰው ነው፡፡ እሱ ብቻ ነው። እኛሳ ዋናው አላማችን ምን መሆን አለበት? ይህን የመሰልቸት ቀሚስ አውልቀን ወዲያ መጣል
በተቻለ ፍጥነት ራሳችንን መግደል
«እኔ ራሴ ለመግደል ዋና ምኞት፡፡ ግን እስካሁን ድፍረት የለም፡፡ አንድ ቀን ግን ለመድፈር ተስፋ! ያን ጊዜ እኔ ሰው::እውነተኛ ሰው፡፡ እስከዚያ ድረስ ግን ከንቱ ቁማርተኛ።»
ጀምሺድ ራስን ስለመግደል ሲያወራ አይኖቹ አይስቁም
በልግ ከዛፎቹ ላይ ቡናማ፣ ቀይና ወርቃማ ቀለማቱን ሰብስቦ
የሙቀትና የውበት ጓዙን ጠቅሎ ኤክስን ለቆ ሊሄድ ተነሳ የኤክስ አየር መብረድ ጀመረ። ሽማግሌዎቹ፣ አሮጊቶቹና
ጥቁሮቹ፣ ሹራብ መደረብ ካፖርት መልበስ ጀመርን። ወጣቶቹ
ፈረንጆች ግን ገና ብርዱ ሊሰማቸው አልጀመረም
ሉልሰገድን ኒኮል እምቢ ስትለው እኔጋ መጥቶ «ካፌ ኒኮል»
ይወስደኝና፣ እየቀረበን በመጣው የክረምት ብርድ ምክንያት፣ ቤት
ውስጥ ገብተን ቁጭ ብለን ስለኒኮል ያወራልኛል። የጭገሯ ፀጉር እንደራሷ ፀጉር አመዳም ሳይሆን፣ ንፁህ ወርቅ ቀለም የተቀባ ነው፤ወተት የመሰለው ነጭ ቆዳዋ ላይ ረዣዥም የተጠላለፈ ውብ ወርቃማ ሀረግ መስሎ በቅሏል። ታዲያ እምሷ ዳር የበቀሉት ፀጉሮች፣ ውሀ ዳር እንደበቀለ ቄጠማ ናቸው፤ አንዳንዶቹ ከሁለቱ ከናፍር ተንጠራርተው ተጠላልፈው፣ ጎምበስ ብለው እምሷ ውስጥ
የፍቅር ውሀ ይጠጣሉ. .. ወዘተርፈ
አንድ ቀን ግን፡ ስለሷ ያወራልኛል ብዬ ስጠብቅ ስለጀምሺድ
ሊነግረኝ ጀመረ፡፡ ሁለቱ ጓደኛሞች ሆነዋል። ጀምሺድ ቁማር
ለመጫወት ካዚኖ ሲሄድ ሉልሰገድን ይዞት ይሄዳል። ከዚህም በላይ ሉልሰገድ የጀምሺድ ሻይ ሱስ ይዞታል። ሁለቱም ሻይውን የሚጠ
ጡት በኢራን አገር ወግ ነው። በፊት ከአራት ማእዘኑ ስኳር ላይ
ይገምጡና፣ ቀጥሎ ሻይ ፉት ይሉበታል፣ እንጂ ስኳሩን ሻይው
ውስጥ አይጨምሩትም

👍23❤2
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
እኔ እባ ሻምፕማትዩ ነኝ:: የኖርኩትም አአሀገሪዩ ከመሴይ ባሉ ቤት ነው፡፡ እኔ አሁን የሰለቸኝ እናንተ የምትሉትን ታሪክ መስማት ነው:: ልክ እብድ ውሻ እንደሆንኩ ዓይነት ሰው ሁሉ እኔን የሚከታተልበት ምክንያት
አይገባኝም፡፡»
አቃቤ ሕጉ የመሐል ዳኛን እያየ ተናገረ፡፡
«ጌታዬ፣ ይህ ሰው አላዋቂ በመምሰል የጮሌ ተግባር እየፈጸመ ነው:: ሆኖም የጀመረው የብልጠት ሥራ ፍሬ እንደማያፈራለት አውቃለሁ::
አሁንም የዚህን ሰው ብልጠት ለማክሸፍ የፍርድ ቤቱ፡ መልካም ፈቃድ ከሆነ አራቱ ምስክሮች ተጠርተው እንደገና በአንድነት እንዲመሰክሩበት
ይደረግ ዘንድ በአክብሮት እጠይቃለሁ::»
«አቃቤ ሕጉን ለማሳሰብ የምፈልገው ግን የፖሊሱ አዛዥ ዣቬር የምስክርነት ቃሉን ከሰጠ በኋላ አጣዳፊ ሥራ ስለነበረበት ይቅርታ ጠይቆ ሄዷል፡፡ የሄደውም ፍርድ ቤቱ ስለፈቀደለት ነው» አሉ የመሐል ዳኛው::
«እውነት ነው» አለ አቃቤ ሕጉ፧ መሴይ ዣቬር እዚህ ሊገኙ
አይችሉም፤ ሆኖም እርሳቸው ለፍርድ ቤቱ ያሰሙት የምስክርነት ቃል በድጋሚ ማሰማት ይቻላል:: መሴይ ዣቬር የተከበሩ ሰው ናቸው::ሥራቸውን የሚያከብሩና ለእውነት የቆሙ ሰው ናቸው:: ስለዚህ እርሳቸው የሰጡት የምስክርነት ቃል የሚጠራጠሩት አይሆንም:: እርሳቸውም ሲናገሩ
«የተከሳሹን ክህደት ለማስተባበል የመሐላ ቃል ወይም የተለየ ማረጋገጫ አያስፈልገንም:: ይህን ሰው በግልጽ ለመለየቴ ጥርጥር የሌለው ነው። የዚህ ሰው ስም ሻምፕማቲዩ ሳይሆን ወንጀለኛውና እጅግ የሚፈራው ዥን ቫልዣ ነው:: ቱሉን ውስጥ የሚገኘው እስር ቤት ዘቦች እዛዥ በነበርኩበት ጊዜ ሰውዬውን ብዙ ጊዜ አይቼዋለሁ:: ቃሌን እንደገና ብደግም ገና ሳየው ነው ያወቅሁት» ብለዋል፡፡
የዚህ ሰው አገላለጽ በዳኞቹና ከዚያ በነበረ ሕዝብ ላይ የማሳመን
ኃይል ነበረው፡፡ የመሴይ ዣቬርን የምስክርነት ቃል አስተዋጽኦ ካሰማ በኋላ ከእስር ቤት የመጡት እስረኞች ቃላቸውን በድጋሚ እንዲሰጡና አንዳንድ ጥያቄ እንዲቀርብላቸው አቃቤ ሕጉ ጠየቁ፡፡
የጠባቂዎች ኃላፊ ምስክሮችን በድጋሚ እንዲያስገባ ዳኛው አዘዙ።ዣን ቫልዣ ከእስር ቤት ካመለጠ በኋላ የእስራት ዘመኑን ጨርሶ የወጣውን ብሪቬት የተባለው ሰው በመጀመሪያ ተጠራ:: ብሪቬት እድሜው ስልሣ
ዓመት ነበር፡፡
«ብሪቬት» አሉ ዳኛው፤ «
ለመድገም የሚቀፍ የረጅም ጊዜ ቅጣት ተቀብለሃል፤ ስለዚህ መሐላ ለመማል አትችልም» ሲሉት ብሪቬት አቀረቀረ፡፡
ሆኖም» በማለት ዳኛው ንግግራቸውን ቀጠሉ፤ «አንድ ሕግ ያዋረደውና ሥራው ያስቀጣው ወንጀለኛ በውስጡ ሌላውን የማክበርና የሌላውን
መብት የመጠበቅ ስሜት ይኖረዋል፡፡ ምናልባት ቀደም ሲል በሰጠኸው የምስክርነት ቃል በሕሊናህ ዳኝነት የምታሻሽለው ነገር ቢኖር እንድታሰማን
እጠይቅሃለሁ፡ ተከሳሹም ተነስቶ እንዲቆምና መስካሪውም ተከሳሹን እያየ እንዲናገር እንዲሁም ጊዜው በመቆየቱ መስካሪው አስቦና አሰላስሎ አሳቡን እንዲሰጠን እያስታወስኩ ይህ ሰው ቀደም ብላችሁ እስር ቤት ውስጥ አብራችሁ የነበራችሁት ዣን ቫልዣ የሚባል እስረኛ ለመሆኑ አረጋግጠህ
በድጋሚ ለመመስከር ትችል እንደሆነ የምስክርነት ቃልህን እንድትሰጥ በድጋሚ እጠይቃለሁ፡፡
ብሪቬት እስረኛውን አተኩሮ ተመለከታቸው:: ከዚያም ፊቱን ወደ ዳኞቹ አዞረ:: ብሪቬትና ሻምፕማትዩ ዓይን ለዓይን ተፋጠጡ፡፡
«አዎን ጌታዬ፤ ይህ ሰው ዣን ቫልዣ ለመሆኑ በመጀመሪያ የለየሁት እኔ ነኝ፡፡ አሁንም ቢሆን ቃሌን አልለውጥም:: ይህ ሰው ዣን ቫልዣ ራሱ ነው:: ቱሉን ከሚገኝ ወህኒ ቤት የገባው በ1796 ዓ.ም ሲሆን ከዚያ ያመለጠው በ1815 ዓ.ም. ነው:: እኔ ከእስር ቤት የወጣሁት እርሱ ባመለጠ በዓመቱ ነበር፡፡ ሰውዬው አሁን ሲያዩት በመጠኑም ቢሆን ለውጥ አለው:: ግን ይህ
ከእድሜ ጋር የሚሄድ በመሆኑ ያሳየው ለውጥ ሊያሳስተኝ አይችልም፤ዣን ቫልዣ ራሱ ነው፡፡»
«ቁጭ በል» አሉ ዳኛው:: ተከሳሹ ግን እንደቆመ ይቆይ::
ሸነልዲዩ የሚባል ምስክር እንዲገባ ተደረገ፡፡ ቱሉን ውስጥ ከሚገኝ እስር ቤት የእድሜ ልክ እስረኛ ነው:: የምስክርነት ቃሉን እንዲሰጥ ነው ከእስር ቤት የተጠራው:: ቁመቱ አጠር ያለ የሃምሣ ዓመት አዛውንት
ነው:: ምንም እንኳን ፊቱ የተጨማደደ ቢሆንም በሁኔታው ነቃ ነቃ ያለና ተቅበጥባጭ ሰው ነው፡፡ ዳኛው ለብሪቬት ያሉትን ለእርሱም ደገሙለት:: «በሠራኸው ወንጀል
የተነሣ በመማል ቃልህን ታከብራለህ ለማለት ስለማያስደፍር መማል
አትችልም» ሲሉት ሻምፕማቲዩ ቀና ብለው ተመልክተው ከዚያ የነበረውን ተመልካች በዓይን ቃኙት:: ዳኛው አሳቡን እንዲሰበስብና እስረኛውን በትክክል ያስታውሰውና ያውቀው እንደሆነ ጠየቁት፡፡
ሺኒልዲዩ ከት ብሎ ሳቀ፡፡
“ታውቀው እንደሆነ አሉኝ! አምስት ዓመት ሙሉ በአንድ ሰንሰለት
እኮ ነው ታስረን የነበረው አንተ በአንድ ብረት ታስረን አልነበረም?
‹‹ቁጭ በል» አሉ ዳኛው፡፡
የጠባቂዎች ኃላፊ ኮሽፔል የተባለውን መስካሪ አስገባ፡፡ ይህም ሰው የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት እስረኛ ሲሆን ኮሽፔል ከብቶችን የሚያግድ ገጠሬ ነበር፡፡ ወደኋላ ግን ከብት ማገዱን ትቶ ወደ ሽፍትነት የተዘዋወረ ሰው ሲሆን ይህ ሰው ሲያዩት ከተከሳሹ ይበልጥ የቂላቂል መልክ ነው
ያለው፡፡ ገና ሲፈጠር ተፈጥሮ ፊትዋን ያዞረችበት፧ የአውሬ መልክ ያለውና እስር ቤት እጣ ርስቱ የሆነ ፍጡር ይመስላል፡፡ ዳኛው ለሌላቹ ያሉትን የተናገሩትን በመድገም እርሱንም ጠየቁት::
«ይህ ከፊትህ የቆመውን ሰው ሳትጠራጠርና ሳታወላውል ትለየዋለህ፤ ታውቀዋለህ?»
«ዣን ቫልዣ ነው» አለ ኮሽፔል፡፡ «ዣን ቫልዣ እያለም ሰዎች
ይጠሩት ነበር፡፡ ጉልበት ያለው ሰው ነው::»
እያንዳንዱ መስካሪ በተናገረ ቁጥር ከዚያ የነበረ ሁሉ ተከሳሸ «ዣን ቫልዣ ነው ወይስ አይደለም» የሚለውን ጥርጣሬ እየተወ ወደ ማመን ደረጃ እየተቃረበ ሄደ፡፡ ሁሉም በየፊናው አጉረመረመ፡፡ መስካሪዎች ተመሳሳይ የሆነ የምስክርነት ቃላቸውን ሲሰጡ ሰው በይበልጥ ተንጫጫ፡፡ ሁሉም በያለበት በሻምፕማቲዩ ላይ ፈረደ:: ኣንድ ምስክር ያለወን ሌላው
እያጠናከረው ሲሄድ ተከሳሹ ጆሮአቸውን ማመን ተስኖአቸው በይበልጥ ፈዘዙ፡፡ የመጀመሪያው ምስክር ቃሉን እንደሰጠ «አያ ግድ የለም፧ ሌላ ምስክር አለ» በማለት እርስ በራሳቸው ሲነጋገሩ ከአጠገባቸው የነበረው
ምስክር ሰማቸው:: የሁለተኛው ምስክር ቃሉን ሲሰጥ ድምፃቸውን ትንሽ ከፍ አድርገው «ይሁና፣ ጥሩ ነው» አለ:: የመጨረሻውና ሶስተኛው ምስክር ቃሉን ሲሰጥ በጣም ጮክ ብለው «በጣም ጎበዝ ሲሉ ተናገሩ፡፡
ዳኛው ወደ ተከሳሹ ፊታቸውን አዞሩ፡፡
«መስካሪዎች ያሉትን ሰምተዋል፤ ታዲያ ምን ይላሉ?
«ምን እላለሁ! ሁሉም ጎበዞች ናቸው!»
ሁሉም በያለበት ተንጫጫ ፤ ሁሉም በየፊናው የግሉን ፍርድ
በመስጠት ይህ ሰው አለቀለት» አለ፡፡
«ፀጥታ እባካችሁ» አሉ ዳኛው፤ «አሁንስ አጠቃልለን የውሳኔ አሳብ
መስጠት ይኖርብናል፡፡»
ዳኞች ከተቀመጡበት አካባቢ ጎርነን ያለ ድምፅ ተሰማ፡፡
«ብሪቬት፣ ሽኔልዲዩና ኮሽጌል እስቲ አንድ ጊዜ ወደዚህ ተመልከቱ፡»
መስካሪዎች ገና ድምፁን ሲሰሙ ክወ አሉ:: በጥፊ የተመቱ መሰላቸው፡፡ ሦስቱም በአንድ ጊዜ ፊታቸውን አዞሩ:: ባለስልጣኖች
ከሚቀመጡበት ወንበር ላይ ተቀምጦ የነበረ አንድ ሰው ተነስቶ ወደ ችሎቱ፡፡መሐል ቀረበ፡፡ የመሐል ዳኛው፣ ሕግ አስከባሪውና ሌሎች አንድ ሃያ
የሚሆኑ ሰዎች ይህ ሰው ማን እንደሆነ አወቁት::
«መሴይ ማንደላይን!»

👍15👎1
#ገረገራ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#በታደለ_አያሌው
...እንደ ክራሞቴ ቢሆን፣ ይኼን ስሰማ ጸጥ ብዬ መሞት ነበረብኝ፡ ያን ያህል ግን ከብዶ አልታየኝም፡ ብሎ ብሎ ድንጋጤ ሁሉ ከዉስጤ
ተሟጥጦ አለቀ መሰለኝ፣ የሐኪሜን ያህል ቀርቶ እንዲች ብዬ አልደነገጥሁም ጭራሽ እሷን ለማበረታታት ሁሉ ምንም አልቀረኝም
“ዉብዬ፣ መገናኛ አካባቢ ዶክተር ሙደያን ሻምሩን የሚባል አንድ ስመ ጥሩ ሐኪም አለ: he is a senior neurosurgeon. ለሰባት ዓመታት ያህል በሙያዉ ላይ ቆይቶበታል። እሱ ዘንድ እልክሻለሁ። ያዉ እዚህም
ሌሎች ታካሚዎች ስለቀጠርሁ ነዉ እንጂ፣ አብሬሽ መሄድ ነበረብኝ: ቢሆንም ግን በዶክተር ሙደያን ፊት ያን ያህል እንግድነት አይሰማሽም፣ እንደኔ ልትቆጥሪዉ ትችያለሽ”
ከሁኔታዋ አንጻር የተለየ ቀረቤታ እንዳላቸዉ ከመጠራጠር ባለፈ፣ እስከ ምን ድረስ እንደሆነ ግን አልጠየቅኋትም
“ያም ሆኖ ግን ታዲያ፣ ከዚያ የምናገኘዉን ምክርም ሆነ ዉጤት እንደ ተጨማሪ ግብአት እንጠቀምበታለን እንጂ፣ዉሳኔዉን የምንወስነዉ እኛዉ ነን። እኔ፣ አንቺ እና እሸቴ ብቻ” አለችኝ፣ እኔ ሥጋት እንዳይገባኝ ራሷ ሰግታ
ከተባለዉ ዶክተር ዉጤቱን እንዳገኘሁ ወደ እሷ እንድመለስ ለነገ ተቀጣጥረን ተለያየን፡
ከሆስፒታሉ ስወጣ፣ መጨላለም ጀምሯል፡በምሳ ሰዓት እመዋን ካገኘኋት ጀምሮ የነበረኝ በጎ ስሜት እስከ አሁንም ድረስ ባለመቀዝቀዙ እየተደነቅሁ፣ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ በፈገግታ ተሞልቼ ለባልቻ ደወልሁለት። ከደወልሁለት፣ በተለይም በዚህ ስሜት
ሆኜ ካናገርሁት ሰንበት ብያለሁ።
“አባትዮዉ”
“ልጅዮዋ”
“ማግኘት ይቻላል?”
“ክራርሽን ይዘሽ ከመጣሽ?”
“በደስታ ነዋ ያዉም!”
“እንደሱ በይኛ! በይ ነይ: እንግዲህ አንቺ ከቢሮዬ እስከምትደርሽ ድረስ
ዓይኔን ከበሩ እንደማላነሳዉ ልባርጊ። ነዪልኝ ቶሎ” ከእሱ ይልቅ እኔ ራሴ እያንጎራጎርሁ ክራሬን መግረፍ፣ የዉሃ ጥም ያህል ቢያሰኘኝም፣ የእመዋን ነገር አንስቼለት በሚያወራልኝ ተጨማሪ ምስጢር ለመደመም ካለኝ ጉጉት አንጻር ግን ምኑም ላይ አይደርስም፡ ምን እና ምን! የእሷን ነገር ባሰብሁት ቁጥር አግራሞት ከደሜ ጋር በሠራ አካላቴ
ይዘዋወርብኛል ቅድም እንኳን ከሐኪሜ ጋር እንዲያ ሆነን ሁሉ፣
በየመሀሉ ትዉስ እያለኝ እንዲሁ ሲያደርገኝ ነበር
ወይ ጉድ!
ከእሱ አፍ እስከምሰማዉ እንደ ቸኮልሁ፣ በፊቴ ያገኘሁትን ታክሲ
ተኮናትሬ አቋራጭ አቋራጭ ቅያሶችን ለሾፌሩ እየጠቆምሁት ወደ ዋናዉ የማኅበሩ ሕንጻ አንከብክቦ አደረሰኝ፡፡ ወደ ሕንጻዉ ከገባሁ በኋላ፣ ጻድቃን መንግሥተ ሰማያትን ለመዉረስ ከሚያልፉበት መከራ ትንሽ መለስ ያለ ፍዳ የሚያቀምሰዉን ጠባቡን የሲራክ፯ መግቢያ እንደ ወትሮዬ በጥንቃቄ
አለፍሁበት፡
“አባትዮዉ” አልሁ ለራሴ፣ ወደ ባልቻ ቢሮ መሬቱን በኃይል እየረገጥሁ ብደርስም ቢሮዉ ዉስጥ አጥቼዉ ስቅቅ እያልሁ። ልመለስ ስል፣ ከኋላዬ
መጥቶ አቀፈኝ፡
“አባትዮዉ፣ ቀጥረኸኝ የት ገብተህ ነዉ?”
“መንገድ ላይ እኮ ባጠገቤ ነዉ ያለፍሽዉ: ብጠራሽ ብጠራሽ ልትሰሚ„ ነዉ አንቺ?”
“ባክህ ነፍሴንም አላዉቀዉ: ይልቅ ከየት ልጀምርልህ?”
“ምኑን?”
“የእመዋን ነገር ነዋ”
“ቆይ: ቆዪኝ እሺ እመለሳለሁ: እዚሁ እኔ ቢሮ ጠብቂኝ: ከእሸቴ ጋ
አንዲት ጊዜ የማትሰጥ ሥራ ላይ ነበርን። እሷን ከዉነን ቶሎ
እንመጣለን: እምጷ!” ብሎኝ በአንድ ትንፋሽ፣ hፊቴ አጣሁት
በጉጉቴ ነበልባል ላይ እንትፍ ብሎበት እንደሄደ ግን ይወቀዉ!
ከቢሮዉ ገብቼ ብዙ ጠበቅሁት ለብቻዬ እየተቁለጨለጭሁ፣ ደቂቃዎች በሄዱ ቁጥር ይኼኛዉ ጉጉቴ እየቀነሰ፣ ወንድሜ በሐሳቤ እየሞላ መጣ:ወንድሜ ጃሪም: እንደ ዋንጫ ጠላ እህትነትሽ በቅቶኛል እያለ የሚግደረደርብኝ ወንድሜ፡ በሚያዉቀንም በማያዉቀንም ሰዉ ዘንድ
እህቱ አይደለችም ተብዬ የታማሁበት፣ ጃሪም
የዛሬ ኹለት ወር ገደማ፣ ዐመጸኞችን እየመራ የቅዱስ ዑራኤልን ካቴዴራል ለማቃጠል ሲመጣ፣ በዓይኔ በብረቱ ያየሁትን የማይታመን ነገርስ ለማን ነገርሁት? ያን ጊዜ የጃሪምን ምስሎች ለሲራክ ፯ ብልክም፣
የኔ ወንድም ስለመሆኑ ግን እስካሁንም የታወቀ አይመስለኝም: እኛ በዋናነት ከምንላፋቸዉ አካላት መካከል የኔ ወንድም ጃሪም እንዳለበት
ከእኛ ማን ያዉቃል? ባልቻ? እመዋ? ኧረ አይመስለኝም:
ይብላኝላት ለእመዋ፤ ከገዛ ልጇ ጋር ለምትዋጋዉ!
ታዉቅ ይሆን ግን ይኼን ጉዷን? ጃሪም ራሱስ ሲራክ ፯ን ያዉቀዋል? የእመዋን እና የኔን ምስጢርስ? የሲራክ ፯ አባል መሆናችንንስ?
ማለቂያ የሌላቸዉን ጥያቄዎቼን ተከትሎ፣ ደዉይ ደዉይ የሚል ስሜትዐተጠናወተኝ፡ ከመሬት ተነስቶ ወይ ደግሞ ሐሜተኞችን ሰምቶ፣ የእናቴ ልጅ አይደለሽም, ብሎ የገዛ ሰማዩን ሳይቀር ከነቀነቀዉ በኋላ እኮ ፊት
ፊት ተገጣጥመን አናውቅም: እንኳንስ እንደ እህትና ወንድም
ልንደዋወል ቀርቶ፣ በመንገድ ላይ እንኳን ላለመተያየት ያልበላነዉ ፍዳ የለም
ለምሳሌ ባለፈዉ ወደ ልደታ ቤተ ክርስቲያን እየሄድሁ ነበር ከርቀት
በመንገዴ ላይ እሱ ሲመጣ አየሁት: መንገዷ ደግሞ ቀጭን በመንደር መካከል መሿለኪያ ስለሆነች፣ ግንባር ለግንባር መገጣጠማችን የማይቀር
ነበር። ካየሁት በኋላ፣ ልክ አንድ ርምጃ በተራመድሁ ቁጥር ልቤ
መዉደቅ መነሳት ጀመረች: በዚያች ቅጽበት ስንቱን እንዳሰብሁት!ከልጅነታችን ጀምሮ ያሳለፍነዉ ጊዜ ሁሉ አንድ በአንድ እንደ ነፋስ ሽዉ እያለ አለፈብኝ፡ ከከተማ ከተማ፣ ከገዳም ገዳም፣ ከቤት ቤት፣ ከጨዋታ ጨዋታ እየተፍነከነክን የተሽከረhርነዉ ሁሉ መጣብኝ፡፡ ይኼንን
ለሚያህል ትልቅ ቤተሰብ የአንድ ሰዉ ያዉም የአንድ ካህን ደሞዝ
በቂያችን ሆና፣ ከእኛ አልፈን ወላጆቻችንን ጭምር የኑሮዉ ጫና እንዳይሰማቸዉ ማድረግ ችለን ነበር፡ ከሌሎች እህቶቼና ወንድሞቼ ጋር ክብ እየተቃቀፍን ጨለማዉን ቀን፣ ቀኑን ደግሞ ምርጥ ቀን አድርገን ያሳለፍነዉ ሳይቀር ትዝ አለኝ፡፡ ቀና ብዬ አየሁት እየተደራረስን ነዉ፡
እሱም እርምጃዎች ወደኔ ሲመጣ፣ እኔም ያን ያህል በተጠጋሁት ቁጥር፤
አሁን ግን ምን እንባባል ይሆን? የሚል ጭንቅ ዉስጥ ወደቅሁ።
መቼም ከአንዴም ኹለት ሦስት ጊዜ አፍ አዉጥቶ እህቴ አይደለሽም ብሎኛል። ካቴዴራል ሊያቃጥል ሲል ዓይኔ በብረቱ አይቶታል፣ ተፈራርተን ወር ሆኖናል፡ ታዲያ አሁን እንዲህ ብቻ ለብቻ ስንገናኝ፣ ምን ሊዉጠን ነዉ? ቆይ ምን ከመባባልስ ነዉ የምንጀምረዉ? በበኩሌ ለሰላምታ ራሴን እያረጋጋሁ ሳለ፣ እሱ አየኝ፡፡ ለካንስ እስከ አሁን አላየኝም ኖሯል፡ ልክ ሲያየኝ በምን ቅጽበት እንደ ተሸበለለ! ጥቅልል ብሎ ዞሮ ወደ መጣበት ፈረጠጠ፡ ልክ እንደዚህ ሁሉ ስንትና ስንት ጊዜ
ተመላልጠናል፡ በዚህ ሁኔታ መሆናችንን ሆዴ እያወቀዉም፣ ደዉይ ደዉይ የሚለዉ
ስሜት ለምን አሁን እንደ ተጠናወተኝ አልገባኝም: ብቻ ጸንቶብኛል ለነገሩማ ምንስ ቢሆን ወንድሜ አይደል? ያዉም ከፍ ዝቁን አብሮኝ ያየ የእናቴ ልጅ!
ደወልሁለት
አያነሳም
ደግሜ ብሞክርም፣ አያነሳም: ከተደጋጋሚ ሙከራ በኋላ በስልክ
የማግኘቱ ጉዳይ እንዳልሆነልኝ ሳዉቅ፣ ሌላ አማራጭ አጣበርሁ በአካል መፈለግ አማራጭ ሆኖ መጣልኝ፡፡ ነገር ግን፣ በዚህ ባሕር በሆነ ከተማ አንድ እሱን በእግር በፈረስ ፈልጎ ማግኘቱ፣ ባሕር ዉስጥ የወደቀችን ጠጠር ፈልጎ እንደ ማግኘት የማይሞከር ነገር ነዉ፡ ስለዚህ ከሲራክ ቢያንስ አንድ የሚረዳኝ ሰዉ ያስፈልገኛል፡

👍27👏4
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
...አነሱ በዚህ ጉይ ምን ማድረግ እንዳለባቸ ሲመካከሩ ፡ ሳቤላ በኀዘንና በሐሳብ ተውጣ ሰማይ ተደፍቶባት ተቀምጣለች ሎርድ ማውንት እስቨርን ከእርሱና ከሚስቱ ጋር አብራ መኖር እንዳለባት ነግሯታል ላፏ ብታመሰግነውም እሱ
ሲወጣ ዕንባዋ ዐይኗ እስኪፈርጥ ይወርድ ጀመር " « ከሚስዝ ቬን ጋር ከመኖር ለምን ለአንዱ ግርድና ተቀጥሬ ፍርፋሪ በልቸ ውሃ ጠጥቸ አልኖርም ከሏ ጋር ከመኖር መሞት ይሻላል » ይህ የወጣት ሴቶች ጠባይ ነው " የማይሆነው ሐሳብ ሁሉ ሲመጣላቸው የሚሆን ይመስላቸዋል " በተለይ ሳቤላ ደግሞ ታበዛዋለች " ከሰው ቤት ገብቶ እየሠሩ መኖር ሲያስቡት ቀላል ነገር ሊመስል ይችላል ነገር ግን ሐሳብና ተግባር የጨለማና የብርሃን ያህል የሚፈራራቁበት ጊዜ አለ " ደግነቱ አማራጭ አግኝታለች " ሎርድ ማውንት እስቨረን የሰጣትን ጥግኝነት ተቀብላ ከሚስ ሼን ጋር መኖር ነበረባት " እንዲያውም እሱስ ወዲያው አሳፍሮ ወደ ካስል ማርሊንግ ሊልካት ነበር » እሷ አይሆንም አለችና ከቀብሩ በኋላ እንድትሔድ ተወሰነ" ለጊዜው ስታስበው አንግፈግፋት - ነገር ግን የብሶቷን ያህል ብዙ ብትናገርም ከዛያ የተሻለ ዕድል እንዶሌላት ተንዝባ ለመሔድ ተስማማች "
ሚስተር ዋርበርተን ኧርሎ በሰጠው ሥልጣን እነዚያን ሬሳ አጋቾች ከዚያ ክፍል አስወጥቶ ቀብር እስኪፈጸም ድረስ ከአንድ ክፍል ዘግቶ አስጠበቃቸው .
ለዚህም ከአንዳንዶቹ ይሰማ የነበረው ምክንያት ወዲያው ነጻ ከተለቀቁ አሁንም ሌላ አፈና ያደርጉ ይሆናል የሚል ነበር።
ቀብሩ ዌስት ሊን በሚገኘው በቅዱስ ይሁዳ ቤተ ክርስቲያን ዐርብ ጠዋት ተፈጸመ ። ሳቤላ ማውንት እስቨርን ሔዶ መቀበር ነበረበት ብላ እንደገና ትክን ብላ አዘነች " ኧርሎ ግን እሷ እየሰማች አይዴለም እንጂ ለቀብሩ ሥርዓት የማያስፈልግ ወጭ መጨመር አያስፈልግም ብሎ ተናግሮ ነው የተወው » ቢሆንም ከሱ የሚፈለገውን ሁሉ በሚገባ ፈጽሞአል ።
የባለሱቆችን የዱቤ ዕዳ የአሽከሮቹን የአንድ ወር ደሞዝና እንደዚሁም በድንገት ስለ ተሰናበቱ በተጨማሪ የአንድ ወር ደሞዝ በቀለብና በመጠለያ ሒሳብ ስም ጨምሮ ከፈላቸው የቤት አዛዥ የነበረውን ፖውንድን እሱ ዘንድ አስቀረው "ለሳቤላም ከክብሯና ከደረጃዋ ጋር የሚመጣጠን ማንኛውንም ለኀዘን የሚያስፈልጋትን ልብስ ሁሉ እንዲኖራት አደረገ ። እገዳ ተደርጐባቸው የነበሩት ሠረላዎችና ፈረሶች በጥሩ ሁኔታ ስለነበሩ ዋጋቸውን ከፍሎ አስቀራቸው
አስክሬኑን የተከተሉት ዋና ኀዘንተኞች ሁለት ብቻ ነበሩ ። አዲሱ ኧርልሬይ ሞንድቬንና ሚስተር ካርላይል " ሁለተኛው በቅርብ ቀን የተገኘ ወዳጅ እንጂ ዘመድ ባይሆንም ምናልባት ኧርሎ የኀዘን ልብስ ለብሶ ብቻውን መታየቱን ስላልወደዶ
ሳይሆን አይቀርም እንዲያቋቁመው ጠይቆት ነበር» አስክሬኑን አንዳንድ የገጠር
መኳንንት ተሸከሙት ! ብዙ የግል ሰረገላዎችም አጀቡት።
በበነጋው ጧት ሁሉም ሽር ጉድ ይል ጀመር ኧርሉ ሊሔድ ተነሣ ሳቤላም ለመሔድ ተዘጋጀች " ግን መንገዳቸው ለየብቻ ነበር " አሽከሮቹም የሚበተኑበት
ቀን ነበር » ኧርሉ ወደ ሎንደን ለመሒድ ባቡር ጣቢያ ድረስ የሚወስዶው ሠረገላ ከበሩ ሲጠብቀው ሚስተር ካርላይል ደረሰ "
« አንተ ሳትመጣ መሔዴ ነው ብዬ ሠግቼ ነበር አሁንም ከአምስት ደቂቃ የበለጠ ጊዜ የለኝም ። ስለመቃብሩ ድንጋይ ግን በደንብ ገብቶሃል ? »
« አዎን በደንብ » አለ ሚስተር ካርላይል " « ሳቤላ እንደ ምን ናት? »
« ምን የሷ ነገር በጣም ያሳዝናል " ሰማዩ ተደፍቶባታል " ቁርስም አብራኝ አልበላችም ሜዞን እንደምትነግረኝ ኀዘኑ በጣም ጠንቶባታል " ምስኪን ልጅ
ክፉ ሰው ነበር አባቷ ! » አለ ንድድ ብሎ ደወሉን እየደወለ " በደውሉ ጥሪ የመጣውን አሽከር ሳቤላን እንዲጠራት ላከው "
« እሷ እስክትመጣ ድረስ ሚስተር ካርላይል ምስጋናዬን እንዳቀርብልህ ፍቀድልኝ " አንተን ባላገኝ ኖሮ ምኑን ከምኑ አደርገው እንዶነበር አላቅም መጥተ
እንደምታየኝ ነግረኸኛል ስለዚህ በቅርቡ እጠብቅሃለሁ » »
« አዎን ምናልባት እርስዎ ወዳሉበት አካባቢ የሚያስመጣ ጉዳይ ያጋጠመኝ እንደሆነ ነው ቃል የገባሁት »
ሳቤላም ለመነሣት ተዘጋጅታ ነበርና ለባብሳ መጣች " ፊቷን በኀዘን ዐይነ ርግብ ሸፍናው ስለ ነበር ' ስትቀርብ መሸፈኛዋን ወደኋላ ገለጠች።
« ሰዓት ደረሰብኝ ሳቤላ ... መሔዴ ነው የምትነግሪኝ ነገር አለሽ ? »
ለመናገር ከንፌሯን ስትከፍት ወደ ሚስተር ካርይል አየችና አመነታች
ጀርባውን ወደነሱ አድርጎ ከመስኮቱ አጠገብ ቁሞ ነበር
«የምትናሪው ያለሽ አይመስለኝም» አለ ለመውጣት የቸኮለው ኧርል «በይ የኔ ልጅ ከመንግድ ምንም ችግር አይገጥምሽም » ለማንኛወም ነገር ፖንድ ይረዳሻል ብቻ ከራት ሰዓት በፊት ካስል ማርሊዓግ መድረስ ስለማትችይ ከመንገድ መብላት አለብሽ " ለሚስዝ ቬን አሁን ጊዜ ስላጣሁ ከለንደን እንደምፅፍላት ንገርያት።»
ሳቤላ ግን አንድ ነገር ለመናር እንምትፌልግ ሁሉ እየተጠራጠረች ከፊቱ ቆሠች።
« ምንድነው ሳቤላ ? ልትነግሪኝ የፈለግሺው ነገር አለሽ ? »
በርግጥ አንድ ነግር ለመናገር ፈልጋ ነበር ግን እንዴት አድርጋ እንደምትነግረው ግራ ገባት በጣም ተጨነቀች " ሁኔታወን ያባሰው የሚስተር ካርላይል
መኖር ነበር " እሱ ደግሞ ይህን አላወቀም ።
« እኔ እንኳን ልጠይቅህ አልፌለግሁም ነበር ግን በእጄ ምንም ገንዘብ የለኝም » አለችው።
« እልም አድርጌ ረሳሁትኮ ... ሳቤላ " በይ እኔም ከመንገድ ከሚያስፈልገኝ የሚተርፍ የለኝም» ለጊዜው ሦስት ፓውንድ ይበቃሻል ለመንገድ የሚያስፈልገውን ወጭ የሚሸፍን ገንዘብ ለፖውንድ ስጥቸዋለሁ ካስል ማርሊንግ ከደረስሽ በኋላ ግን ወይዘሮ ማውንት እስቨርን የሚያስፈልግሽን ሁሎ ትሰጥሻለች ግን መናገር አለብሽ : አለበለዚያ እሷ አታውቅም » አላትና ከሚስተር ካርላይ ጋር እስከ ሠረላው ድረስ ሽኝቷት ተሰነባበቱ » ከዚያ ሳቤላ ወደ ነበረችበት ክፍል ተመለሰች።
«እባክህን አንድ ነገር ላስቸግርህ ... ሚስተር ካርላይል»
« የምችለውን ሁሉ አደርግልሻለሁ»
« በል እንግዲያው » አለችና አንድ ፓውንድ ተኩል አውጥታ « አንዱ ፓውንድ የቲኬቶቹ ዋጋ የቀረውን ፒያኖውን ለቃኘበት ለሚስተር ኬን ስጥልኝ " አንዱ አሽከር እንዳልሰጠው ለመሔድ ሲጣደፍ እንዳይረሳብኝ ፌርቸ ነው » አለችው
« ታዲያኮ ኬን አንድ ፒያኖ ለመቃኘት የሚጠይቀው አምስት ሽልንግ ነው አላት ሚስተር ካርላይል
« ብዙ ሰዓት ነው የፈጀበት » ቆዳውንም ጠጋግኖታል አይበዛበትም የበላውን እንኳን አላዘዝኩለትም ከኔ የባሰ ችግረኛ ነው የሱ ነገር ሆኖብኝ ነው
እንጂ ሎርድ ማውንት እስቨርንን ደፍሬ ገንዘብ አልለምነውም ነበር እሱን ፈርቼ ባልጠይቀው ኖሮ ገንዘብ ሳገኝ የምሰጥህ አንተ እንድትከፍልልኝ አደርግ ነበር ' '
ሳቤላና ካርላይል ፡ ስለዚህ ጉዳይ ሲነጋገሩ ሳቤላ ወደ ኢስት ሊን በገባችበ ክብር እንድትወጣ በማሰብ ይመስል ነበር ሎርድ ማውንት እስቨርን በአራት
ፈረሶች ይሳብ የነበረውን ያባቷን ሠረገላ ባቡር ጣቢያ ድረስ እንዲወስዳት ላከላት
ሠረገላው ተጫነ " ማርቭል በስተውጭ ተቀመጠች።
« እንግዲህ ሁሉ ነገር ተዘጋጀ » አለችው ሳቤላ የመሔጃዬ ሰዓት ደረሰ ሚስተር ካርይል ከጥቂት ሳምንቶች በፊት የገዛኹዋቸውን እነዚያን ወርቅማና ብርማ ዓሣዎቼን ላንተ ልተውልህ ነው ።
« ለምን ይዘሻቸው አትሔጅም ? »
« ለሚስዝ ቬን ይዣቸው ልሔድ አንተ ዘንድ ብተዋቸው ይሻለኛል አንዳንድ ጊዜ ፍርፋሪ ጣልላቸው»

👍16
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
አሁን ሙሉውን እውነት አውቀናል
ወንድ አያታችን እስኪሞት ድረስ እዚህ ክፍል መቆየታችን የማይቀር ነው::አንዳንዴ ሲከፋኝና ቅር ሲለኝ ምናልባት ገና ከመጀመሪያው እናታችን አባቷ ማንንም በምንም ጉዳይ ይቅር የሚል ሰው አለመሆኑን ታውቅ ይሆናል ብዬ
አስባለሁ፡
“ግን…” አለ ደስተኛውና በጎ አሳቢው ወንድሜ: “በሆነ ቀን ሊሞት ይችላል።የልብ በሽታ እንደዚህ ነው: የደም ስሩ ተበጥሶ ደሙ ወደ ልቡ ወይም ወደ
ሳምባው ይፈስና ልክ እንደ ሻማ ያጠፋዋል” አለ።
እኔና ክሪስ በመካከላችን ክፉና ተገቢ ያልሆነ ነገር እንባባልና በልባችን ግን እንታመማለን፡ እየደማ ላለው የራሳችን ክብር የሚሰማንን ህመም ሌላኛችንን
ባለማክበር እንዲሻለን መሞከራችን ቢሆንም ስህተት ነበር።
“አሁን ረዘም ላለ ጊዜ እዚህ መቆየታችን ካልቀረ፣መንትዮቹንም ሆነ ራሳችንን ዘና ለማድረግ ብዙ የሚያዝናኑ ነገሮችን ለማድረግ መወሰን ያስፈልጋል።ለዚያ ደግሞ የሆኑ አስደሳችና አሪፍ ነገሮችን ማለም እንችላለን” አለ፡
“እንደሚታየው ይህ ክፍል አስቀያሚና ቆሻሻ ነው፡ ግን ለምን እኛ በሆነ መንገድ የፈጠራ ተሰጥኦዎቻችንን ተጠቅመን ከአስቀያሚ አባጨጓሬነት
ወደሚያምር ቢራቢሮነት አንለውጠውም?” አለና ለእኔና ለመንትዮቹ በማራኪና
በሚያሳምን መንገድ ፈገግ አለልን፡ ይህንን የሚያስጠላ ቦታ ለማሳመር መጣርና መንትዮቹ ውበት እያደነቁ ዥዋዥዌ የሚጫወቱበት በቀለማት
ያሸበረቀ የውሸት የአትክልት ቦታ ማዘጋጀት ደስ የሚል ሃሳብ ነው እርግጥ ነው በማንኛውም ቀን አያታችን ሊሞትና ይህንን ቦታ ዳግመኛ ላንመለስበት
ለቀን ስለምንሄድ ሙሉውን ክፍል አስጊጦ ለመጨረስ አንችልም።
የዚያን ቀን ምሽት እናታችን እስክትመጣ መጠበቅ አልቻልንም: ልክ እንደገባች እኔና ክሪስ የጣሪያውን ስር ክፍል የማሳመር እቅዳችንን በጉጉት
ነገርናትና መንትዮቹ የማይፈሩት የሚያምር የአትክልት ስፍራ ልናደርገው እንደሆነ አስረዳናት ለቅፅበት አይኖቿ ላይ እንግዳ የሆነ እይታ ተንፀባረቀ
“ቦታውን የሚያምር ለማድረግ፣ መጀመሪያ ንፁህ ማድረግ አለባችሁ: እኔም ምን እንደምረዳችሁ አስብበታለሁ” አለች።
ከዚያ እናታችን መጥረጊያዎች፣ መሬት መፈግፈጊያ ቡርሾችና የዱቄት ሳሙና አመጣችና በጉልበቷ ተንበርክካ የጣሪያውን ስር ክፍል ጥጋጥጎች፣ ጠርዞቹንና
በትልልቆቹ ዕቃዎች ስር ያሉትን ቦታዎች አፀዳች: እናታችን እንዴት
እንደሚፀዳና እንደሚወለወል በደንብ ታውቃለች: ግላድስተን ውስጥ ስንኖር የእናታችንን እጅ የሚያቀላና ጥፍሮቿን የሚሰብርባትን ከባባድ ስራዎች ሁሉ የምታግዛት በሳምንት ሁለት ቀን የምትመጣ ሠራተኛ ነበረችን።
አሁን ግን እሷ ራሷ አሮጌ ስማያዊ ጂንስና አሮጌ ሸሚዝ ለብሳና በጉልበቷ ተንበርክካ ፀጉሯን ወደ ላይ ሰብስባ እያፀዳች ነው: አደነቅኳት። ከባድ፣ አድካሚና አሰልቺ ስራ ነው:: እሷ ግን አንድ ጊዜ እንኳን አላማረረችም:: ደስ
የሚል ነገር እንደሆነ ሁሉ እየሳቀችና እየተደሰተች ነበር።
ከአንድ ሳምንት ከባድ ስራ በኋላ አብዛኛውን ቦታ በተቻለ መጠን አፀዳነው።ከዚያ የነፍሳት ማጥፊያ አምጥታ ስናፀዳ ልናገኛቸው ያልቻልናቸው ነፍሳት የተደበቁበት ቦታዎች ላይ ሁሉ ረጨች᎓ የሞቱ ሸረሪቶችና ሌሎች ነፍሳትን
በባልዲ ውስጥ ሞልተን በጀርባ ባለው መስኮት በኩል ስንደፋው ታችኛው የጣሪያው ክፍል ላይ አረፈ፡ በኋላ ዝናቡ አጥቦ በአሸንዳው በኩል ወደታች
አወረዳቸው:: ከዚያ አራታችንም መስኮቱ ጠርዝ ላይ ተቀምጠን ወፎች ሲበሏቸው ተመለከትን፡፡
አሁን ቦታው ስለተፀዳ እናታችን አረንጓዴ ተክሎችንና በገና ወቅት የሚያብብ አበባ አመጣችልን: እዚህ እንደምንሆን ስትናገር ስሰማት ተኮሳተርኩ።
ጉንጬን እየነካካች “በመኮሳተር ያልተደሰትሽ አትምሰይ፤ ስንሄድ ይዘነው እንሄዳለን፡ ሁሉንም አትክልቶች ይዘናቸው እንሄዳለን፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ፀሀይን የሚወድ የትኛውንም ነገር ትተን መሄድ አንችልም:" አለች:
አትክልቶቹን በሙሉ ወደ ምስራቅ የዞረ መስኮት ባለው የመማሪያ ክፍል ውስጥ አስቀመጥናቸውና በጣም በመደሰት ሁላችንም በጠባቧ ደረጃ እየሮጥን
ወረድን: እናታችን ታጠበችና ድካም ስለተሰማት ወንበሯ ላይ አረፍ አለች።እኔ ለምሳ ጠረጴዛውን ሳዘገጃጅ መንትዮቹ ጭኗ ላይ ወጥተው ተቀመጡ፡ እስከ እራት ሰዓት አብራን ስለቆየች ደስ የሚል ቀን ሆኖልን ነበር፡ ከዚያ በረጅሙ ተነፈሰችና መሄድ እንዳለባትና አባቷ ስለእሷ እንደሚጠይቅ ሁልጊዜ ቅዳሜ ቅዳሜ የት እንደምትሄድና ለምን እንደምትቆይ ማወቅ እንደሚፈልግ ነገረችን
“ከመኝታ ሰዓት በፊት ተደብቀሽ መጥተሸ ልታይን ትችያለሽ?'' ክሪስ ጠየቃት።
“ዛሬ ማታ ወደ ሲኒማ እሄዳለሁ፤ ከመሄዴ በፊት ግን ላያችሁ ብቅ እላለሁ በምግብ ሰአቶቻችሁ መካከል የምትበሏቸው የካርቶን ዘቢቦች ገዝቼላችሁ ነበር። ሳላመጣ እረሳሁት" አለች።
መንትዮቹ በዘቢቡ እጅግ ደስ ሲላችው እኔም ለእነርሱ ደስ አለኝ። “ወደ ሲኒማ የምትሄጂው ብቻሽን ነው?” ስል ጠየቅኳት
“አይ አብራኝ ያደገች ልጅ አለች: የልብ ጓደኛዬ ነበረች: አሁን አግብታ እዚሁ አካባቢ ትኖራለች ወደ ሲኒማ የምሄደው ከእነሱ ጋር ነው:” ተነስታ ወደ መስኮቱ ስትሄድ ክሪስ መብራቱን አጠፋው: ከዚያ መጋረጃውን ገለጥ አድርጋ
የልብ ጓደኛዋ የምትኖርበትን ቤት አቅጣጫ አመለከተችን፡ “ኤሌና ሁለት ያላገቡ ወንድሞች አሏትı አንደኛው ጠበቃ ለመሆን እያጠና ነው ሀርቫርድ የህግ ትምህርት ቤት ገብቷል: ሌላኛው ደግሞ የቴኒስ ተጫዋች ነው:"
እማዬ ከነዚያ ወንድማማቾች ከአንዱ ጋር ቀጠሮ ኖሮሽ ነው?” ስል ጮህኩ።እየሳቀች መጋረጃውን ሸፈነችና “ክሪስ መብራቱን አብራው" አለችው: ከዚያ ካቲ እኔ ማንንም አልቀጠርኩም ኤሌና መውጣት አለብሽ ብላ ችክ አለች እንጂ፤ እውነቱን ለመናገር በጣም ደክሞኛል ቀጥታ ወደ አልጋ መሄድ ወይም ከልጆቼ ጋር መቆየት ይሻለኝ ነበር። ግን መውጣት አለመፈለጌን
ስነግራት ለምን እንደሆነ ከመጠየቅ አላቋርጥ አለች አልፎ አልፎ ወደ ሲኒማና ወደ መርከብ ሽርሽር የምሄደው ሰዎች ሁልጊዜ በሳምንቱ መጨረሻ ለምን ቤት እንደምቀመጥ እንዲጠረጥሩ ስለማልፈልግ ነው:”
ከጣሪያው በታች ያለውን ክፍል ማሳመርና በቀስተደመና ያጌጠ ቆንጆ የአትክልት ስፍራ ለማድረግ የማይታሰብ ይመስል ነበር: እጅግ በጣም ከባድ ስራና የፈጠራ ችሎታ የሚጠይቅ ነበር፡ ወንድሜ ግን ማድረግ እንደምንችል
አምኖ ስለነበር እናታችን በየቀኑ ወደ ትምህርት ቤት ስትሄድ ቆራርጠን የምንለጥፋቸው አበቦች የተሳሉበት መፅሀፎችና የስዕል ዕቃዎች ይዛ እንድትመጣ ሀሳብ አቀረበ፡ የውሀ ቀለሞች፣ በርካታ ብሩሾች፣ ሳጥን ሙሉ እርሳሶች፣ ብዙ የስዕል ወረቀቶች፣ ማጣበቂያዎችና አራት ጥንድ መቀሶች አመጣችልን።
“ለመንትዮቹ ከለር መቀባትና አበቦችን መቁረጥ አስተምሯቸው” ስትል አዘች፡ እና በምትሰሯቸው ነገሮች ሁሉ እንዲሳተፉ አድርጓቸው: የመዋዕለ
ህፃናት አስተማሪዎቻቸው እንድትሆኑ ሾሜያችኋለሁ:"
በሚቀጥለው ቀን የአንድ ሰዓት የባቡር መንገድ ርቀት ላይ ወደሚገኘው ከተማ ሄዳ መጣች: ጥሩ ጤንነት ላይ ነበረች ቆዳዋ ከውጪው አየር የተነሳ ትኩስ

👍35👎1
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ
ከሳውዝ ሃምፕተን ወደ ፎየንስ (አየርላንድ)
ባቡሩ ጫካውን እየሰነጠቀ ወደ ሳውዝ ሃምፕተን ሲያመሩ የማርጋሬት
ኦክሰንፎርድ እህት ኤልሳቤት አንድ አስደንጋጭ ነገር ለእህቷ ነገረቻት
የኦክስንፎርድ ቤተሰቦች በአየር በራሪው በተያዘላቸው ልዩ ፉርጎ ውስጥ ተቀምጠዋል፡ ማርጋሬት ፉርጎው መጨረሻ ላይ ተቀምጣ በመስኮት ውጭ ውጩን ታያለች፡፡ አገሯን በችግሯ ጊዜ ጥላት መሄዷ ክፉኛ ቢያበሳጫትም አሜሪካ የመሄዷ ነገር ደግሞ በሌላ በኩል ደስታ አጭሮባታል፡
እህቷ ኤልሳቤት ከቤተሰቡ ነጠል ብላ ወደ ማርጋሬት መጣችና
‹‹እወድሻለሁ ማጊ›› አለቻት።
ማርጋሬት በእህቷ አባባል ልቧ ተነካ፡ በዓለም ላይ የሚካሄደውን የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነትና ጦርነት መረዳት ከጀመሩ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተቃራኒ አቋም በመያዝ በነገር መጠዛጠዛቸው አራርቋቸው ነበር።ማርጋሬት ይህ የአስተሳሰብ ልዩነት ከእህቷ ስለነጠላት ታዝን ነበር
እንደገና ጓደኛ ቢሆኑ በወደደች፡፡ ‹‹እኔም እወድሻለሁ እታለም›› አለቻትና እቅፍ አደረገቻት፡፡
ትንሽ ቆየችና ‹‹አሜሪካ ከእናንተ ጋር አልሄድም›› አለች ኤልሳቤት ማርጋሬት ይህን ስትሰማ ደነገጠች ‹‹እንዴት እባክሽ?››
‹‹ለእማማና አባባ እንደማልሄድ በቀጥታ ልነግራቸው ነው፤ ሃያ አንድ
ዓመት ስለሆነኝ ሊያስገድዱኝ አይችሉም››
ማርጋሬት የእህቷ ውሳኔ ትክክል ይሁን አይሁን አላወቀችም ‹‹የት ነው የምትሄጂው?››
‹‹ወደ ጀርመን››
‹‹ሊሆን አይችልም ኤልሲ›› አለች ማርጋሬት በፍርሃት፡፡ ‹‹ትሞቻለሽ››
‹ሶሻሊስቶች ብቻ አይደሉም ላመኑበት ዓላማ የሚሰዉት››
‹‹ግን ለፋሺዝም ብለሽ?››
‹‹ለፋሺዝም ብዬ አይደለም›› አለች
ኤልሳቤት፡፡ ዓይኗ ላይ እንግዳ አመለካከት ይነበባል፡፡ ‹‹በጥቁሮችና በክልሶች የመዋጥ አደጋ ላንዣበበበት ንፁህ ነጭ ዘር ብዬ ነው፡፡››
ማርጋሬትን ያበሳጫት እህቷን ማጣቷ ብቻ አይደለም፡፡ በዚህ ሰይጣናዊ ዓላማ ከእህቷ መለየቷ ነው ያሳዘናት፡ ሆኖም የቀድሞውን ጊዜ የፖለቲካ ጭቅጭቃቸውን አሁን ማንሳት አልፈለገችም፡ አሁን ያስጨነቃት ጉዳይ
የእህቷ ደህንነት ነው፡፡
‹‹እንዴት ትኖሪያለሽ ጀርመን ውስጥ?›› ስትል ጠየቀቻት
‹‹ገንዘብ አለኝ››
ማርጋሬት አያታቸው ሲሞቱ ያወረሷቸውን ገንዘብ አስታወስች፡፡ ገንዘቡ
ብዙ ባይሆንም ያኖራል፡
ማርጋሬት አንድ ነገር በሃሳቧ መጣ፡፡ ‹‹ሻንጣሽ ወደ ኒውዮርክ ተልኳል እኮ››
‹‹ኒውዮርክ የተላኩት ሻንጣዎች የተሞሉት በጠረጴዛ ልብስ ነው::
ልብሴን በሌላ ሻንጣ ሞልቼ ሰኞ ዕለት ልኬያለሁ።››
ማርጋሬት በእህቷ ብልህነት በእጅጉ ተደነቀች፡፡ ኤልሳቤት ሁሉንም
ነገር አቅዳ በትክክልና በምስጢር አከናውናለች፡፡ እሷ ከዚህ ቀደም ያደረገችው የማምለጥ ሙከራ እህቷ ካደረገችው ጋር ሲነጻጸር ምን ያህል የተውሸለሸለና በሚገባ ያልታቀደ እንደሆነ ተረዳች፡፡ እኔ ምግብ አልበላም እያልኩ ስተክዝ እሷ ግን ለጉዞዋ ቦታ ለመያዝና ዕቃ ለመላክ ትሯሯጥ ነበር፡
እህቷ የያዘችው የፖለቲካ አስተሳሰብ የተሳሳተ ቢሆንም ከእሷ በተሻለ
ሁኔታ መንቀሳቀስ መቻሏ የዝቅተኝነት ስሜት ፈጠረባት፡፡ ወዲያው ደግሞ ከእህቷ ጋር እስከ ወዲያኛው መለያየቷ ገባት፡፡ ምንም እንኳን ብዙም ባይቀራረቡም አብረው አድገዋል፡ ብዙ ጊዜ በሃሳብ ሲከራከሩና አንዷ ያንዷን አስተሳሰብ ስታጣምም ቢኖሩም ማርጋሬት ይሄም ሊቀርባት ነው: በችግር ጊዜ ይረዳዱ ነበር፡፡ ኤልሳቤት የወር አበባዋ በመጣ ቁጥር ህመም ሲሰማት ማርጋሬት አልጋ ላይ አስተኝታት የሚጠጣ ትኩስ ነገርና የሚነበብ መጽሔት ታመጣላታለች፡ የማርጋሬት ፍቅረኛ ኢያን ሲሞት መሪር ሀዘን ላይ ወድቃ የነበረ ጊዜ ምንም እንኳን ኢያንን ባትወደውም ታጽናናት ነበር
ማርጋሬት ዓይኗ በእምባ ተሞልቶ ‹‹ትተሽኝ ልትሄጂ ነው?›› አለቻት እህቷን፡፡
‹‹ግርግር አታብዢ›› አለች ኤልሳቤት ‹‹ገና አልነገርኳቸውም››
ማርጋሬት መነፋረቋን አቆመችና ‹‹መቼ ልትነግሪያቸው ነው?›› ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹ መጨረሻው ደቂቃ ላይ፤ አንቺም እስከዚያው አታስነቂ››
‹‹እሺ እታለም›› ብላ የግድ ፈገግታ አሳየቻት፡
«አይ ማርጊ›› አለች ኤልሳቤት እምባ እየተናነቃት፡፡ ሳጓን ዋጥ
አደረገችና ‹‹እኔ እስከምረጋጋ ድረስ ሂጂና አዋሪያቸው::››
ማርጋሬት የእህቷን እጅ ጨበጥ አደረገችና ወደ መቀመጫዋ ተመለሰች
እናት የፋሽን መጽሔት ያገላብጡና የሚነገር ነገር ሲያገኙ ለአባት ያነባሉ ሎርድ ኦክሰንፎርድ ደግሞ ለማዳመጥ ፍላጎት የላቸውም፡፡ እናት
ግን ተስፋ ሳይቆርጡ ያነባሉ፡፡ ሎርዱ የንቀት ፊት ይነበብባቸዋል፡ ትልቋ
ልጃቸው የደገሰችላቸውን አያውቁም፡
ለማርጋሬት መንገር አንድ ነገር ነው፤ ለአባቷ መንገር ግን ሌላ ነገር.ነው፡፡ ኤልሳቤት በመጨረሻ ደቂቃ ለመንገር ድፍረት ታጣ ይሆናል፡፡
ማርጋሬትም ከዚህ ቀደም ከአባቷ ጋር እሰጥ አገባ ልትገጥም ነበር በኋላ
እጇን ሰጠች እንጂ፡
ኤልሳቤት ወንድ ወጥቷት ለአባቷ ከነገረች ወደ ጀርመን መሄዷ
የተረጋገጠ ላይሆን ይችላል፡ ሃያ አንድ አመት የሞላትና ገንዘብ ያላት
ብትሆንም እሳቸው ግን አቋመ ፅኑና ያሻቸውን ከማድረግ የማይመለሱ ሰው ናቸው፡ ኤልሳቤት ከፈቃዳቸው እንዳትወጣ ማቆም የሚችሉ ከሆነ
እንደሚያደርጉት ማርጋሬት አትጠራጠርም: በመርህ ደረጃ ኤልሳቤት
የፋሺስት ፓርቲን ብትቀላቀል አይጠሉም፤ ነገር ግን ትዕዛዛቸውን ጥሳና ቤተሰቡን ትታ ብትሄድ ግሥላ እንደሚሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡
ማርጋሬት ከአንዴም ሁለት ሶስቴ ከአባቷ ጋር ተጣልታለች። ያለሳቸው
ፈቃድ መኪና መንዳት በተማረች ጊዜ ተቆጥተዋታል፡ የእርግዝና መከላከያ ፈር ቀዳጅ የሆነችው የሜሪ ስቶፕስን ንግግር ለመስማት መሄዷን ያወቁ ጊዜ.ፊታቸው በንዴት በርበሬ መስሎ ነበር፡ አባቷ ሳያውቁ ካላደረገች በስተቀር ፊት ለፊት ተጋፍጣ እንደማይሆንላት ታውቃለች፡፡ የአስራ ስድስት ዓመት ኮረዳ ሳለች ከአጎቷ ልጅ ጓደኞች ጋር ትምህርት ቤት ሲዘጋ ሽርሽር ልሂድ
ብላ ስትጠይቃቸው አልፈቀዱላትም፡፡ ያልፈቀዱላት ከሴቶችም ከወንዶችም.እንዳትቀላቀል ነው: ትልቁ ጦርነት የነበረው ትምህርት ቤት ልሂድ ያለች
ጊዜ ነበር፡ ትምህርት ቤት ለመግባት እንዲፈቀድላት ብትለምንም፣ ብታለቅስም ወይም ብታኮርፍም አባት ጆሮ ዳባ ልበስ አሉ፡ ‹‹ትምህርት ለሴቶች ምንም አያደርግላቸውም ሴቶች ቤት ውስጥ አድገው ባል
አግብተው መቀመጥ ነው ያለባቸው›› ነበር ያሏት፡፡
ማርጋሬት እረፍት አጣች፡ አንድ ነገር አገኝ ብላ ተነሳችና ፉርጎው
ውስጥ ተንጎራደደች፡ የሰማይ በራሪው ጀልባ ተሳፋሪዎች ሲታዩ ገሚሶቹ
የተከፉ ከፊሎቹ የተደሰቱ ይመስላሉ፡፡
ከተሳፋሪዎቹ መካከል አንዲት በዓለም የታወቀች አሜሪካዊት ኮከብ የፊልም ተዋናይ ስላለች ሁሉም ስለእሷ በሹክሹክታ ያወራል፡ ሉሉ ቤል ትባላለች፡ ፔርሲ ከሷ ጋር ቁጭ ብሎ ልክ ረጅም ጊዜ እንደሚተዋወቁ ሁሉ
ያወራታል፡ ማርጋሬት ከተዋናይዋ ጋር ማውራት በወደደች፤ ነገር ግን
ዓይኗን በጨው አጥባ ሄዳ ልታወራት አልደፈረችም፡፡ ፔርሊ ዓይን ቀቅሎ
የበላ ነው፡፡
ሉሉ ቤል በፊልም ስትታይ ወጣት ብትመስልም በአካል ሲያይዋት ግን ያረጀች ትመስላለች፡ አንድ አርባ ዓመት ሳይሆናት አይቀርም ስትል ማርጋሬት አሰበች ምንም እንኳን ፊልሞቿ ላይ ወጣቶችንና በቅርብ ያገቡ
ሴቶች ገጸ ባህሪ ወክላ ብትጫወትም፡፡ ምንም ሆነ ምን አሁንም ውብ
ሽንቃጣና ተግባቢ ናት፡፡
ማርጋሬት ሉሉን ስታይ ፈገግ አለች፡፡ ሉሉም ‹‹ታናሽ ወንድምሽ ያጫውተኛል›› አለች፡፡

👍17🥰2
#ከቡስካ_በስተጀርባ
#ድንግል_ውበት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ካርለት ቆዳ ለባሽ፣ በባዶ እግሯ ተጓዥ፣ እንጨት ለቃሚ ብትሆንም ከዓለም ሕዝብ በመንፈስ አልራቀችም" ሕይወትን እስአ ሥሯ ድረስ ጠልቀው በማየት የኳተኑና የሰው ልጅን ውድቀትና ድል፣ ሽንፈትና ግብ፣ የሕይወትን ለስሳሳና ሻካራ፣አቀበት
ቁልቁለት ጐዳና እየለዩ ሳያሳርሩ ወይም በረዶ ሳያደርጉ የቀሩት
የታታሪ ሰዎች የሕሊና ጭማቂ የሆነውን መጽሐፍ ታነባለች" አዲሳባ
ከከሉ ጋር ስድስት ጊዜ ደርሳ ስትመለስ ይዛቸው የምትመጣቸው
መጽሔቶችም በዓለም ላይ በመከናወን ላይ ያለውን የፖለቲካ የኢኮኖሚ ለውጥ እንድትገነዘብ አስተዋጽኦ ከማድረጉ ሌላ ከተለያዩ
ጣቢያዎች የሬዲዮ ፕሮግራሞችን ትከታተላለች።
ካርለት በሐመር ለጥናት ለመቆየት ያሰበችው ጊዜ ስላነሳት እንዲራዘምላት ጠይቃ የተፈቀደላት ሲሆን፣ ለዓለም የሴቶች ድርጅት
ያቀረበችው የፕሮጀክት በጀትም ተቀባይነት በማግኘቱ በጀት
ተጨምሮላታል" ይህም ከሎና ጎይቲን የእንግሊዝን አገር አንዲጎበኙ ስቲቭ የተቻለውን ሁሉ እንዲጥርላት ለመንገር አደፋፈራት ካርለት በሐመር ኑሮዋ መጽሐፍ ከማንበቡ ሌላ ሙዚቃ ማዳመጥ
የምትወድ ሲሆን ከሦስት መቶ ዓመት በፊት የኖረውን የሐይደ ሲንፎኒ፣ የጀርመናዊው የባህን የባሮክ ሙዚቃ የሞዛርትንና የቤቶ ፒያኖ ሶናታና ኮንችት ከጥንቱ ሙዚቃ የምታዳምጥ ሲሆን፣ የተለያዩ ባለ ስርቅርቅ ድምፃውያን የአገረሰብ፣ ሮክና ሮል ሙዚቃ ከማዳመ
ጧም ሌላ በዘመናዊ መንገድ በኮምፒውተር፣ በሒሳባዊ ቀመርና
በአጋጣሚ የተቀነባበሩ «አጥንት በሽ» ሙዚቃ ሰው ሠራሽ እጅ ካልገባበት የተፈጥሮ አካባቢ ሆና ስታዳምጥ እሷም እውነተኛ
ስሜት ይሰማትና እንባዋ በእርጋታ እየተንኳለለ ሲወርድ ትንሽ ወንዝ
ዳር እንዳለች ሁሉ ኮለልታው ይሰማታል። ከስሜቷ ታዳምጣለች
ትመሰጣለች ትረካለች፤ ታነባለች ወደ ታች ጠልቃ ወደ ላይ መጥቃ ትጓዛለች" ትክክኛ ስሜት ንጹሕ አየር ይፈልጋል የተፈጥሮ መዓዛና ውበትን ይሻል" የሐመር ተፈጥሮ ደግሞ ለዚህ የተፈጠረ ነው አዕዋፍ በነፃነት የሚያዜሙበት፣ ዕጽዋት ጎንበስ ቀና
የሚሉበት፣ ንጹሕ አየር እንደ ጊሽጣ የሚገመጥበት ነው የሐመር ምድር!
በዓለማችን ስንቱ ሕፃናት፣ ሴቶች፣ አሮጊቶች,በጦርነት
የእሳት ላንቃ ተጠበሱ፤ dንትና ስንት ሰው በተፈጥሮ አደጋ አለቀ ስንቱስ በረሃብ ላንቃ ተቀጠፈ አቤት ይህች ዓለም ስንት ዋይታ
ተሰማባት? ስንቱ እንባውን አፈሰሰባት? እነዚያ ሁሉ እንባዎች እስከ አሁን ብዙ ውቅያኖስና ባሕር ፈጥረዋል፤ ወደፊትም ለቁጥር የሚታክት ውቅያኖስ መፍጠራቸው አይቀሬ ነው የዘመናችን
ውጣውረድና ጠባሳ ከቶ በምን ይለካ ይሆን?
ካርለት ዋይታው፣ ለቅሶው፣ የዝናቡ ነጠብጣብ ሳይቀር ሕሊናዋን እየሰረሰሩ የሚገቡ እስኪመስላት ተመስጣ ታነባለች የሙዚቃ
ቃናዎችን ትረዳለች። አዎ ማየትማ ሁሉም ያያል መስማትማ ሁሉም ይሰማል። ሁሉም አምስት የስሜት ሕዋሳት አለው።
ብዙዎቻችን ግን አምስቱን ሕዋሶቻችንን የምንጠቀመው ለየቅል
ተናጠል ነው ጥቂቶች ብቻ አንድ አድርገው ያዩትን ይዳስሱታል ያሸቱታል፤ ይቀምሱታል፤ ይስሙታል።
ካርለትና ከሎ ሆራ የታደሉት ይህን ጸጋ ነው" የሚፈልጉትን ነገር በመላ ሕዋስ መፈተሽ፣ በሥራ መበርታት፣ ለዓላማ ስኬት
መሞት፣ ያሰቡትን ከፍጻሜ ማድረስ መቻልን ከልምድ ተማሩ።
ስለዚህ ሲጀምሩት ራሳቸውን የወቀራቸው ጭንቀት በአእምሮ ፈውስ
ተተካ። ዛሬ ዛሬ ከነበሩበት ይልቅ እየፈሩ የገቡበት ሕይወት ጥልቅና እውነተኛ ነው። ካርለት የደልቲ ገልዲ ሚስት ሆና ለመገረፍ፣
በእንብርክኳ ትንባሆ ለማቀበል፣ ሸፈሮ ቡና ለማፍላት፣ የከብት አዛባ
ለመዛቅ ቸኩላለች። ካርለት አሁን የእውነተኛ አንትሮፖሎጂስትነት
ስሜት እየተሰማት፣ ራሷን በራሷ የማትደልል፣ ከሕሊና ወቀሳ የራቀችና ከአምላክ የተሰጠውን ጸጋ የተላበሰች ናት። ሁሉን ለማወቅ፣
ከባዱን ለመሞከር መቻሏን ፈትናለች ከእንግዲህ በዚህ ውድድሯ አሸንፋ ለመውጣት ከቻለች፣ «ለመሆኑ በማሸነፍሽ ለምን ደስ አለሽ?» ተብላ ብትጠየቅ መልሷ፣ «ምክንያቱም ውድድሩ አስቸጋሪ ስለሆነ ነው» ብላ መመለሷ አይቀርም" ማሸነፍ የሚያረካው ደግሞ
የውድድሩ ውጣ ውረድ ሲበዛና ተወዳዳሪዎችም ጠንክረው ሲገኙ ነው።
«በሕይወት ውድድር ላይ ያለ ሰው ውድድሩ ከራሱ ጋር እንጂ በምድራችን ያሉትን ቢሊዮን ሕዝቦች በማሰብ መሆን የለበትም"
ይህን ካሰበ ግን በጭንቀት ብቻ ተደናቅፎ ይወድቃል» በማለት ካርለት ከሎን ደጋግማ መክራዋለች።
ደልቲ ገልዲ ካርለትን ለማግባት ኮይታው በሽማግሎች እንዲወሰን አስደረገ። ጥሎሹ ብዙም ከባድ አልነበረም፤ ቢያንስ
አራትና አምስት ዓመት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ከፍሎ ሊጨርስና
እንግዳዋን የራሱ አድርጎ ያኔ በሚያውቀው ባህላዊ ደንብ ደህና አድርጎ ይገራታል።
ካርለት አሸዋማና ገላጣ ስፍራ ላይ፣ ዙሪያውን የፌጦ፣ የኩንኩሮ፣ የጠዬ የዝግባና ዋንዛ ዛፍና የሻንቆ መንደር ባለበት
የኢቫንጋዲ ጭፈራ ቦታ ከደልቲ ገልዲ ጋር ሲጨፍሩ በተለይም ወደ ጫካ ሲገቡ የምታወልቀው የውስጥ ሱሪ፣ ወደ ላይ ከፍ አድርጋ
የምትገልበው ልብስ፣ አሁን የላትም። የውስጥ ሱሪዋም ሆነ ልብሷ ቆዳዋ ነው፤ በውኃ መታጠቧን አቍማለች፤ ጸጕሯን በቅቤ የተለወሰ አፈር ትቀባለች። ይህን በማድረጓ የደረሰባት የጤና ችግር የለም"
በእርግጥ መጀመሪያ አካባቢ ቆዳዋ ለብ ለብ የተደረገ ለጋ ስጋ ጥብስ፣ ቀጥሎ ተዘልዝሎ የደረቀ ቋንጣ መስሉ ጠቁሮ ታይቷል።በተረፈ የቈሰለው ሁሉ ድኖላት፣ ወዟ እንደ ሐመር ልጃገረዶች ነው፤
ሕሊናዋም ደስተኛ ነው።
ደልቲ ገልዲ ግን አሁንም ብዙ የምታስተካክለው እንዳለ ያምናል" ያ ደግሞ የሚሆነው እሱ እሷን አጠቃሉ የራሱ ካደረገ
በኋላ ነው። ስለሆነም ጥሎሹን በቶሎ ለመጀመር ወስኗል።
በመካከሉ ግን፣ ከሎና ካርለት ከተመካከሩ በኋላ ከሎ ሆራ ደልቲ ገልዲ ዘንድ ሄደ። ደልቲ ገልዲ፥ ከሎ ሆራ የሱ ፍቅረኛ የሆነችውን
ጎይቲ አንተነህን ለማግባት የተሪ ቆዳ አጋድሞ፣ ኩርኩፋ
አጉርሷታል። ስታስደንሰው፣ ስታዝናናው የነበረችውን ፍቅረኛውን ሊነጥቀው ነው። ደልቲ ገልዲ እሷን ሊያጣ በመቃረቡ ልቡ እየዘለለ
ፈርጦበታል። ከከሎ ሆራ ጋር ግን ነገር የለውም። ከሎ ሆራ ሐመር ነው። በሐመርነቱም ብቻ ሳይሆን ባህላዊ ሥርዓቱንና ደንቡን
አሟልቶ እጮኛውን ለመምረጥ ዞሮ ጎይቲን መርጧል። ይህ መብት
የመላው ሐመር ማኅበረሰብ መብት ነው፣ «ፍቅረኛዬን ቀማኸኝ
እገላለሁ፤ እታነቃለሁ» እያሉ ማላዘን ንክ ያሰኛል" ጀርባን
ግርፋት፣ የበረት ከብትን ለጥፋት ይዳርጋል። በማኅበረሰቡ ትልቁ
ኃይል ያለው በዚያው በማኅበረሰቡ እጅ ነው። መሣሪያና ጕልበት
ያለው ጀግና የሚባለውም የማኅበረሰቡን ባህልና ደንብ ሲያከብር ነው። ካለበለዚያ ግን በኃይል የሚያምን ልብ እንደ ጌሾ በማኅበረሰቡ እጅ ይወቀጣል። «ከባሕር የወጣ ዓሣ» ይሆናል። ስለዚህ፣ ከሎ ደልቲ ገልዲ ዘንድ ሲሄድ በፍቅር ተቀበለውና ሲጨዋወቱ ቆዩ።በዚህ መልክ ትንሽ እንደ ቆዩ ከሎ ሆራ ወደ መጣበት ርዕሰ ጉዳይ
ተመለሰና፣ «...እንግዳዋ ለብዙ ጊዜ እዚህ አትቆይም። ከተወሰነ
ጊዜ ቆይታ በኋላ ትመለሳለች። ስለዚህ አንተን በቅርቡ ልታገባህና
ልታገለግልህ ትፈልጋለች» አለው፣ ከሎ።
«ይእ! ጥሎሹን ገና ሳልጀምር፤ እንዴት ሆኖ ይሆናል? መቆየት አለባት እንጂ። ደግሞስ የኔ ሚስት መሆን ከፈለገች የት ነው
የምትሄደው? እኔስ ይህን እፈቅድላታለሁ? የትም አትሄድም። እዚሁ ሥራ ትሠራለች» አለ ደልቲ።

👍18👎1👏1😁1
#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
“ነገ ማታ እደውልልሃለሁ በመጭው ሦስት ቀናት
አልኖርም:: ጓደኛዬን ለመጠየቅና እግረ መንገዴን ለመሰናበት ባርሴሉና እሄዳለሁ... መልካም ጊዜ ለማሳለፍ ሞክር አሁን
መተኛት እፈልጋለሁ ኦርቫ" ብላው ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደ መኝታ ክፍሏ ገባች:
በተቀመጠበት ህሊናው የስሜት ግጭት ተንቆራቆሰበት...
የሐሳብ ልዩነት.. ውሃና እሳት ትኩሳትና ብርድ... የስሜት
ጩሕት... የማይታኘክ ጉርሻ..
ከጥቁርና ነጭ ቀለም የተውጣጣው የቀይ ዳማ ቀለሟ ዞማ ፀጉሯ ከለግላጋ ቁመናዋ ጋር ፈጣን አስተሳሰቧ ሁሌም ጎልታ
እንድትታይ ያደርጋታል።
መርከበኛው አባቷ ፍራንሲስኮ ፔሶ ቤኒ በስራው ምክንያት
ከናቷ ከሎካዬ ጋር ለብዙ ወራት ተለያይቶ ሲቆይ ከህፃንነቷ ጀምሮ ናፍቆት ቢንጣትም እንኳን የተሟላው ኑሯቸው
ጨዋታ ወዳዱ አባቷ በየመዝናኛው ከናቷ ጋር ይዟት ስለሚዞር አብሯት
ስለሚቦርቅ ደስተኛ ሆና ለማደግ አስችሏታል።
በተማሪነቷ የስካውት አባል የነበረችውና በስካውትነቷ ብዙ ጉዞዎችን ከእድሜ እኮዮችዋ ጋር ያደረገችው ቅርፀ ማራኪዋ ኮንችት
ጊታር መጫወትን በጋራ ማዜምንና ከእስፔናውያን ባህላዊ ዳንስ በተጨማሪ የምዕራባውያንን ውዝዋዜ በስልት አጣጥማ የማቅረብ
ተሰጥኦዋ ተደጋጋሚ አድናቆትን ስላተረፉላት ከዘጠኝ ዓመት እድሜዋ ጀምሮ ጊዜዋ “የፋሽን ሾው" ስራ እየሰራች የራሷ ገቢ
እስከማግኘት አስችሏት ነበር።
አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ከፈፀመች በኋላ በባልትና ሳይንስ ትምህርት ሰልጥና ከሙያዋ ይልቅ በሞዴሊስትነት
ሥራ በመሰማራት በጂምናዚዬም አካላዊ እንቅስቃሴ በማድረግ
ለሚስስ ካታሉንያነት ሁለት ጊዜ ተወዳድራ በሶስተኛው ሚስስ ካታሉንያ በመባል የቁንጅና ዘውዷን ደፍታለች።
ኮንችት በህፃንነት ያየችው አፍሪካዊ አያቷ ኤድዋርድ ሎካዬ ብቸኝነቱ ዝምታውና ደስታ አልባ ሆኖ ኖሮ ከሚናፍቃቸው ዘመዶቹ
ተገናኝቶ ያሰበው ሳይሳካለት ማለፉ እንደ እግር እሳት ሁሌም
ያቃጥላታል። አይቶት በማያውቀው እንደ ሰማይ በተዘረጋ ውቅያኖስ ላይ ጭነው ፖርቶሪኮ ውስጥ ኗሪ ለነበረው ለኤድዋርድ ጃኒፌር የተሸጠው አያቷ ከአንዱ አለም ወደ ሌላ ዓለም ከተወሰደ በኋላ
በቋንቋም በአስተሳሰብም ልዩ ሆኖ ፖርቶሪኮ ውስጥ በተነሳው የርስ በርስ ጦርነት እንደ አባቱ የሚቆጥረው ጌታው ኤድዋርድ ጃኒፈር
ወደ አሜሪካ ሜሪላንድ ሸሽቶ በመሄዱ እንግሊዘኛና እስፓኒሽ ቋንቋ
አፍንጫውን ተይዞ ተምሮ የዕለት ፍላጎቱን ለማርካት የታክሲ ሾፌር ሆነ።
ከዚያ ከኮንችት ሴት አያት ከራሚሬዝ ኦርኔዝ አኜስ ጋር
በአጋጣሚ ተገናኝተው የኮንችት አያት አኜስና ሉካያ እናቷን ከሪናን በመውለድ ስፔን ውስጥ አ ብረው መኖሩ ጀመሩ። ሎካዬ በተለያየ ጊዜ በአፍሪካ ጉብኝት አድርጎ ዘመዶቹን ፈልጎ ለማግኘት ቢሞክርም
ሊሳካለት አልቻለም ነበር:
በስተ እርጅናው ጣልያን ሮም ላይ የተደረገውን የማራቶን ውድድር ለመመልከት ሄዶ ግን ባጋጣሚ የአገሩ ፍንጭ ቢታወቅም ሽምግልናውና ጤና ማጣቱ ተዳምረው
ምኞቱን አሰናከለባት።
ኮንችት አያቷ ለመሞት ቀናት ሲቀሩት ጠርቷት ወደ
አታክልቱ ቦታ ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ ወስዷት ትክ ብሎ እያያት።
“ለሰባት ዓመት ልጅ አደራ መተው ምንኛ ይከብዳል
መሰለሽ” አለና አፉን በመሀረብ ይዞ ሲስል ቆይቶ፡
“አሁ ካንች ሌላ ማንስ አደራዬን ሊቀበል ይችላል-" ሲል ኮንችት የሚለውን ነገር ስላልገባት ግራ ገብቷት ስትቁለጨለጭ፡-
“የዘመዶቼን አገር አላውቅም ነበር። ጠንካራነቴ አሁን
የነበረውን ፍንጭ የዛኔ ቢኖረኝ ኖሮ ምን ነበረበት ግን አልሆነም
የኔ ልጅ ይህች ትንሽ ባንዲራ በልጅነቴ አሁን ስሙን ከማላውቀው
የገጠር ከተማ ከአባቴ ጋር ሄጄ አይቻት ነበር። በህፃንነት ልቦናዬ ያን
ጊዜ ስትውለበለብ ያየኋት ባንዲራ ሮም ላይ ሯጩ ይዟት አየኋት እና እንኪ ያዣት በጥንቃቄም አስቀምጫት! ሲሆንልሽ ግን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ | ባንዲራ ወደ አለባት ኢትዮጵያ ወደሚሏት
ሃገር ሂጂ።
"ይህም መቀመጫ ስንተራሳት ስቀመጥባት ምንድናት?' እያልሽ የምትጠይቂኝ መቀመጫዬም 'በርኮቶ' ትባላለች በኮዬጉዎች።
“ምን?” አለች ኮንችት
ኩዬጕ ኩዬጉዎች… የኔ ዘመዶች የሚቀመጡባት
መቀመጫ ናት" ሳሉ እንደገና አሳለው ላቡ በግንባሩ ተንቆረቆረ
ወደ ሰማይ ቀና ብሎ፦
“ልዑል እግዚአብሔር! እባክህ ትንሽ ትንሽ ጊዜ ስጠኝ አለና እግዚአብሔርን ተማፅኖ፣ “አጠገባቸው ትልቅ ወንዝ አለ::
ሱርማዎች ኦሞ ይሉታል: ከወንዙ ተሻግረሽ ትንሽ ስትሄጂ ኩችሩ የሚባል መንደር አለ፡፡
ሰላም ሲሉ አሹቃ ይላሉ። አሳ አጥማጆች አትክልተኞች ከዱር ማር ሰብሳቢዎች ናቸው" እንደገና ሳለ፤ ቀና ብሉ ሰማዩን ተመለhተ።
ኮንችት የሚለው አልገባትም በጨቅላ ህሊናዋ ግን ስቃዩ
አሳዝኗታል።
“ሁሉንም ፅፌልሻለሁ ባንዲራዋን ከዘነጋኋት ዘመዶቼም ከመኖሪያቸው ለቀው ከሆነ ልፋትሽ መና ይቀራል። ወለላዬ እስቲ
እነዚያ ቆንጂዬ ጣቶችሽ? አላት ድንገት:: ሁለቱንም እጆችዋን ዘረጋችለት:: ጊዜ አልነበረውም መጣደፍ ነበረበት፡፡
ጳ..ጳ አርጎ በጥቁሩ ከንፈሩ በየተራ ሳማቸው: ጉንጯን
ሊስማት ፈለገ¦ ግን ፈራ ሳሉ ቢተላለፍባትስ:
“እንኪ በላስቲኩ
አሮጌ ካርቶን ውስጥ ይኸው ከትቼልሻለሁ። የኔ ልጅ እኒያን ዘመዶቼን ቀንቶሽ ካገኘሻቸው
እዘኝላቸው እንዳንች ንፁሆች ናቸው፡፡ ሎካዬ ናፍቋችኋል ሰላም
ብሏችኋል! በያቸው: ሞቷል አትበያቸው: ስንት ጊዜ በእኔ ይዘኑ ለእኔ ያልቅሱ አለ በያቸው ሲረጋጉ ደግሞ እኔ ነኝ ሎካዬ በያቸው እንደ ህፃን ያምኑሻል መጠራጠር አያውቁም ፤የሚጠራጠር ራሱ ሌባ ነው ይባል የለ! እነሱ ግን እንደ ዶሮ እየጫሩ
ተዛዝነው ያገኙትን ሲለቅሙ ይውሉና የኩችሩ ጫካ ክንፍ ውስጥ እንደ ጫጩት እየተሰገሰጉ ሙቀታቸውን እየተጋሩ ይተኛሉ…"
አሳለው! ሰውነቱ ራደ ላቡ ወረደ።
በይ ሄጂ ተጫወቺ እ..ኔ
ደ.ግ.ሞ እ ..ሁ ልረፍ” አላት ተስፋ በቆረጠ አስተያየት እያያት የአደራ ካርቶኗን ታቅፋ ስትሄድ ፈገግ ብሎ ከኋላዋ ለመጨረሻ ጊዜ ተመለከታት።

👍20
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
///
ከጄኔራሏ ጋር የነበረን የጋለ የፍቅር መሳሳብ ቀስ በቀስ እየተዳፈነ የጓደኝነት ቁርኝታችን እየጠነከረ መጥቶል፡፡ይሄን አይነት የስሜት ለወጥ በመከሰቱ ልደሰት ወይስ ይክፋኝ እስከአሁን መለየት አልቻልኩም፡፡ ነግቶ ከእንቅልፌ ስባንን እሷ ከጎኔ ተኝታለች..እስክትነቃ ጠበቅኩና
"ደህና አደርሽ?" በሚል በአክብሮት በታሸ ለስላሳ ንግግር ተቀበልኳት፡፡
"አዎ ..ደህና አድሬያለሁ..ነጋ እንዴ?"
አዎ ነግቷል.. አታይውም እንዴ? በክፍላችን ብርሀን ተጥለቅልቆ ደሰ ሲል፡›
‹‹ብርሀን ብቻ ነው እንዴ ደስ ሚለው?››.
‹‹ጨለማማ ያው ጨለማ ነው ምኑ ደስ ይላል?››
ጨለማ ያን ያህል አስፈሪ አይደለም።በድፍረት ላጣጣመው ጨለማ የራሱ ውበት አለው።ጨለማ ደግሞ ከብርሀን በላይ ፈጣን ነው።ሁል ጊዜ ብርሀን በጨለማ ቀድሞ የተያዘውን ግዛት አስለቅቆ ነው አለሁ እዚህ ነኝ የሚለው።እኛም ወረተኛና ፍርደ ገምድል ስለሆን ኃላ ስላየነው አንፀባራቂና ደማቁ ብርሀን አጋነን እናወራለን እንጂ ቀድሞ ቦታው ላይ የነበረውን ጨለማ ትዝ አይለንም፡፡
ከእሱ ማምለጥ ባንችልም መሞከራችን አይቀርም።ደግሞ እኮ የብርሀኑ ውበትና ድምቀት ሙሉ ሆኖ የሚታየው በድቅድቁ ጨለማ ሰንጥቀን ማለፍ ሲችል ነው።ደግሞ ወታደር ብትሆን ለጨለማ ያለህ እይታ ይቀየር ነበር፡፡
‹‹እንዴት?››
‹‹ጨለማ ወሳኝ ወዳጅህ የሚሆንበት ብዙ አጋጣሚዎች ይኖራሉ...ከጠላት አይታ ከልሎ ህይወትህን ያተርፍልሀል….ከብርሀን በተሻለ መረጋጋተትና ትንፋሽ መውሰጃ ሰላማዊ እረፍት ዕድሎችን ያመቻችልሀል…ኦ እኔ ጨለማ ወዳለሁ…በተለይ ድቅድቅ ጨለማ፡፡
‹‹በስመአብ በይ››
‹‹አልኩ.. አሁን ስንት ሰዓት ሆነ?››
"ሁለት ሰዓት ሆኗል"
"ስራ ትገባለህ እንዴ?"
"ማታ አስራሁለት ሰዓት ነዎ..አንችስ?"
"እኔኮ ስራ የለኝም.?."
"አንድ ጄኔራል ለዛውም በዚህ ጊዜ..."
እጄን ያዘችና ወደ ሆዷ ወሰደችኝ፡፡ ያሳረፈችኝን ቦታ ዳበስኩት፡፡ የታረሰ ቦይ መስሎ ያስታውቃል፡፡ ...ብርድልብስን ከነአንሶላው ገለጥኩና አየሁት እንብርቷን ከፍ ብሎ ወደታች በመውረድ ፓንቷ ውስጥ ድረስ የሚዘልቅ አስፈሪና ሰፊ ጠባሳ አለ፡፡
.‹‹..እስከዛሬ እንዴት ሳላየው?"
"አይኖችህ መቀመጫዬ ላይ ነበር የሚንከባለሉት..ለዛነው ያላየኸው"
"እውነቴን ነው ..ማታ እንኳን እርቃንሽን ሆነሽ ከስሬ ቆመሽ ነበር"
"ባክህ እንዳታየው በዘዴ ስለጋረድኩት ነው"
"ምን ሆነሽ ነው?"
"ቆስዬ ፡፡በጦርነቱ ላይ ቅስዬ ላለፍት ሶስት ወራት በከፍተኛ የህክምና ክትትል ጦርሀይሎች ተኝቼ ነበር...፡፡ገና ከወጣሁ አንድ ወር አይሆነኝም..፡፡.አሁንም ከሆስፒታል ወጣው እንጂ ህክምናውን ሙሉ በሙሉ አላጠናቀቅኩም ...በሳምንት አንድ ቀን ቼክአኘ አለኝ፡፡..እና በአጠቃላይ ከስራ ውጭ ነኝ፡፡
‹‹ስትድኚ ትመለሺያለሽ አይደል?››
‹‹ከዚህ በፊት እኮ ነግሬህ ነበር..መመለስ እንደማልችል ሀኪሞቹ ተስማምተው ፅፈውልኛል...መጀመሪያ ከፍቶኝ ነበር...ቆይቼ ሳስበው ግን ውሳኔውን በፀጋ ተቀብዬዋለሁ።››
"ይገርማል.. ታዲያ እንደዚህ ከፍተኛ ህክምና ላይ እያለሽ ነው እንደዛ አልኮል ስትጠቀሚ የነበረው ።››
‹‹አንድ ቀን ነው የጠጣሁት.. እሡኑም ቦርድ መውጣቴን የሠማው ቀን ..››..
"አረ ተይ...ከሰውዬሽ ጋር የመጣሽ ቀንስ..?"
"እ በቃ..የወታደር ነገር አንዳንዴ እንዲህ ነው...አየህ ከተወረወረ ቦንብ መሀል አምልጠህ የሚንጣጣ መትረየስ ሸውደህ፤ ታንክና ድሽቃ ሳይገልህ በህይወት ተርፈህ አሁን አልኮል በብርጭቆ ስለጠጣሁ ይገለኛል ብለህ ለማመን ይከብድሀል...እና መጠጣት እንደሌለብህ ብታምን እንኳን ትንሽ ከተበሳጨህ ወይም ድብርት ውስጥ ከገባህ እኔ እንዳደረኩት ታደርጋለህ...፡፡
"አሁን ቁርስ ልጋብዝሽ"
"የት እቤትህ ወስደህ"
"አረ እዚሁ ሆቴል"
"እቤትህ ስልህ ምነው ደነገጥክ...ሴትየዋ አለች እንዴ?"
‹‹አይ የለችም"ብዬ ስለጋሽ ሙሉአለም ታሪክ ስነግራት ማመን ነው ያቃታት።
"እሺ እኔ ቤት ሄደን እንዋላ"
"እኔ ቤት ...እዚህ አዲስ አባ ቤት አለሽ"
"አዎ ብዙም ባልጠቀምበትም ቤት አለኝ››
‹‹ታዲያ ቁርስ በልተን እንሂድ?..›
‹‹ምነው ቁርስ መስራት እትችልም አሉህ እንዴ?››
‹‹እስከዛ ይርብሻል ብዬ ነዋ;››
‹‹ለራስህ አስብ ..አንተ ወታደር እኮ ነኝ..አስርና ሀያ ቀን ያለምግብ ያሳለፍኩባቸው ብዙ አጋጣሚዎች አሉ...በል ተነስ ››አለችና …አልጋዋን ለቃ በመውረድ ልብሷን መለባበስ ጀመረች፡፡.
‹‹አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ››
‹‹ጠይቀኝ››
‹‹ስንት አመትሽ ነው?››
‹‹ምን?››ደንግጣ
‹‹አይ ለሌላ እኮ አይደለም….በዚህ ዕድሜሽ እንዴት ይሄ ሁሉ ብዬ ነው፡፡››
‹‹እስኪ ገምት ስንት እሆናለሁ?››
‹‹35››
‹‹ብዙም አልተሳሳትክም…10 ብቻ ጨምርበት፡፡››
‹‹የእውነትሽን ብቻ እንዳይሆን?››
‹‹ምነው አረጀሁብህ?››
‹‹አረ አቋምሽና ጠቀሽወ እድሜ ፈፅሞ አይመሳሰልም››አልኳት የእውነትም ተገርሜ፡፡
ትራስ አስቀምጣ የነበረውን ሽጉጥ አነሳችና የጃኬቷን የውስጠኛ ኪስ ውስጥ አስቀመጠች፡፡..እኔም ለብሼ ጨርሼ ስለነበረ .ተያይዘን ወጣን….ወደሆቴሉ የመኪና ማቆሚያ ፓርክ ነው የወሰደችኝ፡፡
.አንድ አይጣማ ቪታራ ጋር ስትደርስ ቁልፉን ከኪሷ አወጣችና ከፈተች.፡፡መኪና ይዛለች ብዬ ስላላሰብኩ ታክሲ ለመጥራት ስልኬን አውጥቼ ስልክ ቁጥር እየፈለኩ ነበር…ፈገግ አልኩና ገቢና ገብቼ ቁጭ አልኩ፡፡ከመንቀሳቀሳችን በፊት ግን ስልኬ ጠራ…ጋሼ ሰለሞን ነው የደወልኝ፡፡ አነሳሁት፡፡
‹‹ሄሎ ጋሼ››
‹‹እዬብ የት ነህ?››ኮስተር ያለ ጥያቄ ነው፡፡
‹‹ሆቴል ነኝ››
‹‹ቶሎ እቤት ና.. ፈልግሀለሁ›
‹‹እቤት ማለት.?››.ግራ ገብቶኝ ጠየቅኩ፡፡
‹‹.አንተ ቤት.. አባዬ አሞታል መሰለኝ››
‹‹መጣጣሁ መጣሁ›ስልኩን ዘጋሁት
‹‹ምነው ችግር አለ?…››
‹‹አያቴ ማለት ጋሽ ሙሉአለም አሞቸዋል መሰለኝ .›መሄድ አለብኝ ይቅርታ››
‹‹…ላድርስህ?››
‹‹ምን ታደርሺኛለሽ…..ከዚህ ገቢ ቀጥሎ እኮ ነው ቤታችን..ደውልልሻለሁ›ተንጠራርቼ ጉንጯን ሳምኳት፡፡
‹‹በቃ ቸው›
ገቢናውን በር ከፍቼ ወጣሁ‹‹..ቁርሱ ደግሞ ለሌላ ቀን ይዘዋወርልኝ.››
‹‹በተመቸህ ጊዜ ደስ ይለኛል.. ነገም ተነገ ወዲያም.. ደውልልኝ…መጥቼ ወስድሀለሁ…፡፡››
እየሮጥኩ ወደቤት ሄድኩ፡፡
//
አያት መድሀኒት ከወሰደና ቀኑን ሙሉ ስንከባከበው ከዋልኩ በኃላ አሁን ከመሸ ተሸሎታል፡፡በአካል ስሩ ባልሆንም ከግድግዳ ማዶ ሆኜ ደህንነቱን እንድከታተል በሀለቃዬ በአቶ ሰለሞን ተነግሮኝ የስራ ፍቃድም ተሰጥቶኝ ስራ አልገባሁም፡፡አሁን ከፍሌ አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ከእንቅልፌ ጋር እየታገልኩ አያቴም በክፍሉ ውስጥ በተኛበት የልጅና የአባት ወሬ እያወራን ነው፡፡
‹‹አያቴ እርሶ እኮ ፃድቅ ኖት››ድንገት ነው ይሄ አረፍተነገር ከአፌ ሾልኮ የወጣው..ግን ደግሞ ለሽርደዳ ወይም ለማስመሰል አይደለም..የእውነትም ከልቤ እንደዛ ነው የማምነው፡፡

👍42👏2❤1