አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


...ምላሷን ሳየው ነጭ የሆነ ይመስላል እየፈራሁ ትራሱ ላይ አጠገብ ለአጠገብ ጋደም ያሉት ሁለቱ ትንንሽ ፊቶች ላይ አተኮርኩ። ለምንድነው እንዲያድጉና ትክክለኛ ዕድሜያቸው ላይ እንዲሆኑ የምፈልገው? ይህ ለረጅም ቀናት የቆየ በሽታ ትልልቅ ሰማያዊ አይኖቻቸው ስር ጥቋቁር ክብ በማድረግ ጤናማ ቀለማቸውን ሰረቀ ትኩሳቱና ማሳሉ ቅፅበታዊ የእድሜ ለውጥ አምጥቶ
ፀሀዩዋ ብትወጣ ባትወጣ ግድ የሌላቸው የደከሙ የአዛውንቶች አይነት እይታ ሰጣቸው አስፈሩኝ፡ አሳዛኝ ፊታቸው ወደ ሞት ህልም ወሰደኝ

በዚህ ሁሉ ንፋሱ መንፈሱን ቀጥሏል።

በመጨረሻ አልጋቸውን ለቀው በዝግታ መራመድ ቢጀምሩም፣ በአንድ ወቅት ጠንካራ፣ ለመዝለልና ለመሮጥ ይችሉ የነበሩ እግሮቻቸው አሁን ደካማ;
እንደ ሳር የቀጠኑ ሆነዋል አሁን የሚችሉት በመብረር ፋንታ መዳህ፣ በመሳቅ ፋንታ ፈገግ ማለት ብቻ ሆኗል።

በድካም አልጋው ላይ በፊቴ ተደፍቼ የልጅነታቸውን ውበት ለመመለስ እኔና ክሪስ ምን ማድረግ እንችላለን? እያልኩ ደጋግሜ እያሰብኩ ነበር
የእነሱን ጤና መመለስ ለማገዝ ሲል ለእኛ ጤና የሰጠን ቢሆንም፣ እኔም ሆንኩ እሱ ማድረግ የምችለው ነገር አልነበረም።

እኔና ክሪስ በመንትዮቹ መካከል ያለውን ጤናማ ያልሆነ ልዩነት ለማስተካከል እየታመምን ባለንበት ወቅት “ቫይታሚኖች!” ስትል እናታችን ጮኸች።
“የሚያስፈልቸው ቫይታሚኖች ናቸው፡ እናንተም ያስፈልጋችኋል: ከአሁን ጀምሮ እያንዳንዳችሁ በየቀኑ የቫይታሚን ኪኒኖች መውሰድ አለባችሁ” ይህንን ስትነግረን እንኳን ቀጭኑና ረጅሙ እጇ በሚስብ ሁኔታ የተያዘውን
የሚያንፀባርቅ ፀጉሯን እየነካ ነበር።

አቅራቢያዬ ባገኘሁት አልጋ ላይ አረፍ እያልኩና ችግሩን ለማየት ፈቃደኛ ያልሆነችው እናት ላይ እያፈጠጥኩ “ንፁህ አየርና የፀሀይ ብርሃንም በኪኒን
መልክ ይመጣሉ?” ስል ጠየቅኳት “እያንዳንዳችን በየቀኑ የቫይታሚን ኪኒኖች መዋጣችን አብዛኛውን ጊዜያችንን ውጪ በምናሳልፍባቸው ቀናትና ትክክለኛ ህይወት እንመራ በነበረበት ጊዜ የነበረንን መልካም ጤንነት ይሰጠናል?”እናታችን በንቀት እይታ ገረፍ አድርጋኝ “ካቲ፣ ለምንድነው ያለማቋረጥ
ነገሮችን ሁሉ ከባድ የምታደርጊብኝ? የቻልኩትን እያደረግኩ ነው እውነቴን
ነው እና አዎ እውነቱን ከፈለግሽ በምትውጧቸው ቫይታሚኖች ውስጥ የውጪው አየር የሚሰጣችሁን መልካም ጤንነት ይመለስላችኋል፡ ለዚያ
ነው ብዙ ቫይታሚኖች የሚሰሩት:" አለች:

ግዴለሽነቷ ልቤ ውስጥ ተጨማሪ ህመም ፈጠረብኝ አይኖቼን ወደ ክሪስ ወረወርኩ፤ ምንም ሳይናገር አንገቱን አቀርቅሮ ሁሉንም ያዳምጣል

“እስረኝነታችን መቼ ነው የሚያበቃው እማዬ?”
በአጭር ጊዜ ውስጥ ካቲ፣ አጭር ጊዜ! ብቻ እመኚኝ
“ሌላ ወር?”
“ሊሆን ይችላል‥”

“እንደምንም ተደብቀሽ መንትዮቹን ለጥቂት ጊዜ በመኪናሽ ወደ ውጪ
ልታወጫቸው ማመቻቸት ትችያለሽ? ሰራተኞቹ በማያዩበት ጊዜ ልታደርጊው ትችያለሽ፡ ትልቅ ልዩነት ይፈጥራል ብዬ አስባለሁ። እኔና ክሪስ መሄድ የለብንም:”

ታላቅ ወንድሜ እዚህ ሴራ ውስጥ ይኑርበት አይኑርበት ለማየት ተሽከርክራ ተመለከተችው፤ ነገር ግን መገረሙ ፊቱ ላይ በግልፅ ይነበብ ነበር፡ “አይሆንም፣
በፍፁም አይቻልም! እንደዚያ አይነት አደጋ አልጋፈጥም! እዚህ ቤት ውስጥ ስምንት ሰራተኞች አሉ ማደሪያቸው ደግሞ ከዋናው ቤት ቀጥሎ ነው:ሁልጊዜም የሆነ ሰው በመስኮት ይመለከታል እና መኪናውን ሳስነሳ ሊሰሙኝ
ይችላሉ: ከዚያ በየትኛው አቅጣጫ እንደምሄድ ያጣራሉ።" አለች።

ድምጼ ቀዘቀዘ፡ “እባክሽ ትኩስ ፍራፍሬ ማምጣትስ ትችይ ይሆን? እባክሽ? በተለይ ሙዝ፡ መንትዮቹ ሙዝ እንደሚወዱ ታውቂያለሽ እዚህ ከመጣን ጀምሮ በልተው አያውቁም::”

“ሙዝ ነገ አመጣላችኋለሁ አያታችሁ እንደሆነ ሙዝ አይወድም:"

“hሱ ጋር ምን ያገናኘዋል?”

“በዚያ ምክንያት ነው ሙዝ የማይገዛው፡”

“ወደዚያ ትምህርት ቤት በሳምንቱ ቀናት ሁሉ ትሄጃለሽ፡፡ ቆም በይና ሙዝ፣ተጨማሪ የለውዝ ቅቤና ዘቢብ ግዢ አንዳንዴ እንኳን ለምንድነው የካርቶን
ፈንዲሻ የማያገኙት? በእርግጠኝነት ጥርሳቸው እንዳይበላሽ አይደለም!”

ደስ በማይል ሁኔታ ጭንቅላቷን ነቀነቀችና ተስማማች: “ለራስሽስ ምን ትፈልጊያለሽ?” ስትል ጠየቀችኝ፡

“ነፃነት! መውጣት እንዲፈቀድልኝ እፈልጋለሁ፡ በተቆለፈ ክፍል ውስጥ መኖር ደክሞኛል። መንትዮቹም እንዲወጡ እፈልጋለሁ። ክሪስ እንዲወጣ
እፈልጋለሁ ቤት ተከራይተሽም ይሁን ሰርተሸ ወይም ሰርቀሽ ብቻ ከዚህ ቤት እንድታስወጪኝ እፈልጋለሁ!

“ካቲ…” ትለምነኝ ጀመር። “የምችለውን ሁሉ እያደረግኩ ነው: በመጣሁ ቁጥር ስጦታ አላመጣሁላችሁም? ከሙዝ ሌላ ምንድነው የጎደላችሁ? ንገሪኝ
“እዚህ የምንቆየው ለጥቂት ጊዜ ነው ብለሽን ነበር አሁን ወራት አለፉ::

እንደሚፀልይ ሰው እጆቿን አነሳችና “አባቴን እንድገድለው ትጠብቂያለሽ? አለችኝ፡ በዝምታ ጭንቅላቴን ነቀነቅሁ

የእሱ አማልክት ወጥታ በሩ እንደተዘጋ ክሪስ “ለምን አትተያትም?!” ሲል ጮኸ፡ “ለሁላችንም የምትችለውን እያደረገች ነው፡ አትጨቅጭቂያት
ልክ እንደማታምኛት ሁሉ የማያልቁ ጥያቄዎችሽን እየደረደርሽና ከጀርባዋ
አልወርድ እያልሻት ልታየን መምጣቷ ራሱ የሚገርም ነው: ምን ያህል እንደተሰቃየች እንዴት ታውቂያለሽ? አራቱ ልጆቿ አንድ ክፍል ውስጥ ተቆልፎባቸውና ጣራ ስር ያለ ክፍል ውስጥ ብቻ እንዲጫወቱ መደረጋቸውን
እያወቀች ደስተኛ ነች ብለሽ ታምኛለሽ?”

እንደ እናታችን ስላለ ሰው መናገር ከባድ ነው፡ ምን እንደምታስብ፣ ምን እንደሚሰማት ማወቅ አይቻልም: አንዳንድ ጊዜ ብቻ የደከማት ከመምሰሏ በስተቀር ስትታይ ሁልጊዜ ረጋ ያለች ናት ልብሶቿ አዲስና ውድ ሲሆኑ አልፎ አልፎ አንድን ልብስ ሁለት ጊዜ ለብሳ እናያታለን፡ ለእኛም
አዳዲስና ውድ ልብሶች ታመጣልናለች: ግን የምንለብሰው ልብስ ልዩነት አልነበረውም: ከአያታችን በስተቀር ማንም ስለማያየን ፊቷ ላይ የደስታ
ፈገግታ የሚያመጣላትን የነተቡ ቡትቶዎችንም መልበስ እንችላለን
ሲዘንብና በረዶ ሲጥል ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል አንሄድም: ዝናብ በሌለ ቀን እንኳን በሀይል እያፏጨ በአሮጌው ቤት ስንጥቅ በኩል የሚገባ ከባድ
ንፋስ አለ።

አንድ ሌሊት ኮሪ ከእንቅልፉ ባኖ ጠራኝና ካቲ ንፋሱን አባሪው" አለ
አልጋዬንና ኬሪን ትቼ ከኮሪ አጠገብ ብርድ ልብስ ውስጥ ገባሁና ጥብቅ አድርጌ አቀፍኩት ምስኪን ቀጫጫ፣ የሚነፍሰው ንፋስ ይዞት የሚሄድ ነው የሚመስለው፡ በእናቱ በጣም መወደድን ቢፈልግም ያለሁት እኔ
ብቻ ነኝ፡ ፊቴን ዝቅ አድርጌ ንፁህና ቆንጆ ሽታ ያለውን ፀጉሩን ሳምኩት
ልጅ ሆኖ አሻንጉሊቶቼን በእውነተኛ ልጆች የተካሁ ጊዜ እንዳደረግኩት እቅፍ አደረግኩት፡ “ንፋሱን ማባረር አልችልም ኮሪ ያንን ማድረግ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው''

“ታዲያ ለእግዚአብሔር ንፋሱን እንዳልወደድሽው አትነግሪውም? አለ።

“ለእግዚአብሔር ንፋሱ የመጣው ሊወስደኝ ፈልጎ እንደሆነ ንገሪው::”
እንደገና አስጠጋሁትና የበለጠ ጥብቅ አድርጌ አቀፍኩት ... በጭራሽ ንፋሱ ኮሪን እንዲወስደው አልፈቅድለትም: በጭራሽ!

“ንፋሱን እንድረሳው ታሪክ ንገሪኝ ካቲ"
👍34🥰2
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


....መጪውን እየፈራሁም ቢሆን እጇ ባዶ ሲሆን ልቀርባት እየጠበቅኩ ነበር። አያትየው ወደ ክሪስ ስለማትመለከትና መንትዮቹ ደግሞ ከመፍራታቸው
የተነሳ እሷ ስትኖር ስለሚንቀጠቀጡ፣ የሰራንላትን ስጦታ መስጠት የኔ ኃላፊነት ነበር. ግን እግሬን እንኳን ማንቀሳቀስ አልቻልኩም: ድንገት ክሪስ በክንዱ ጎሸም አድርጎኝ “ቀጥይ” ሲል አንሾካሾከልኝ፡፡ “በሆነው ደቂቃ ከክፍሉ ትወጣለች”

እግሮቼ ከወለሉ ጋር በሚስማር የተጣበቁ መሰለኝ፡ በሁለቱ እጆቼ ረጅም ቀይ እሽግ ይዣለሁ፡ ከቆምኩበት ቦታ ሲታይ መስዋዕት የማቅረብ ነገር ይመስል
ነበር ምክንያቱም እስከዛሬ ስትሰጠን የነበረው ክፋት ስለነበረና አሁንም የባሰ
ህመም ልትሰጠን እድል እየጠበቀች ያለች ስለሆነች ለሷ ስጦታ መስጠት ቀላል አልነበረ።

በዚያ የገና ጠዋት ካለ አለንጋና ካለ ምንም ቃል ለሁላችንም ህመም መስጠት ተሳክቶላት ነበር በትክክለኛው መንገድ “መልካም ገና አያቴ። ትንሽ ስጦታ ልንሰጥሽ ነበር። እንድታመሰግኝን አይደለም:: ችግር የለውም በየቀኑ ምግብ ስለምታመጪልንና መጠለያ ስለሰጠሸን ለማመስገን ያህል ትንሽ ስጦታ ልንሰጥሽ ነው:” ልላት ነበር፡ ግን አይሆንም እንደዚያ ብላት እያፌዝኩባት
ይመስላት ይሆናል፡ የሚሻለው ዝም ብዬ “መልካም ገና፣ ይህንን ስጦታ እንደምትወጂው ተስፋ አለን ኮሪና ኬሪን ጨምሮ ሁላችንም ነን የሰራንልሽ፡”

ገና ስጦታውን ይዤ ስቀርባት ስታይ እጅግ ተደነቀች።

“በቀስታ አይኖቼ በድፍረት አይኖቿን ለማየት ቀና እያሉ የገና መስዋዕታችንን አቀረብኩ፡ በአይኖቼ ልለምናት አልፈለግኩም ግን እንድትወስደው፣
እንድትወደውና ቀዝቀዝ ብላም ቢሆን “አመሰግናለሁ” እንድትል ፈልጌያለሁ።ዛሬ ማታ ወደ መኝታዋ ስትሄድ ስለኛ እንድታስብ መጥፎ ልጆች እንዳልሆንን
እንድትረዳ ፈልጌያለሁ፡ ለእሷ ስጦታ ለመስራት የለፋነውን እንድታስብና እኛን የምታስደናግድበት መንገድ ትክክል ነው ወይስ ስህተት ብላ ራሷን እንድትጠይቅ ፈልጌያለሁ።

እጅግ በከፋ መንገድ ቀዝቃዛና የንቀት አይኖቿን በቀይ ወዳሰርነው ረጅም ሳጥን ዝቅ አደረገች፡ ላዩ ላይ ካርድ አለ ካርዱ ላይ “ለአያታችን ከክሪስ፣
ካቲ፣ ኮሪና ኬሪ” የሚል ተፅፎበታል: በግራጫ ድንጋይ አይኖቿ ካርዱን ረዘም ላለ ጊዜ ተመለከተች። ከዚያ አትኩሮቷን ቀጥታ ወደ እኔ ተስፋ የተሞሉ፣ የሚለምኑ፣ ክፉ አለመሆናችንን ማረጋገጥ የሚሹ አይኖቼ ላይ
አደረገች ከዚያ ወደ ስጦታው፣ ከዚያ ሆን ብላ ጀርባዋን አዞረችና ቃል ሳትናገር ከበሩ ወጥታ በሩን በሀይል ወርውራ ዘጋችና ቆለፈችው: እኔም የብዙ ረጃጅም ሰአታት ውበት የመስጠት ትጋት ውጤት የሆነውን ስጦታ
በእጆቼ እንደያዝኩ ክፍሉ መካከል ቆሜ ቀረሁ።

ጅሎች! የማንረባ ጅሎች!

አላግባባናትም:: ሁልጊዜም ከሰይጣን የተፈለፈልን አድርጋ ነው የምትቆጥረን!
እሷን በተመለከተ እኛ አልተፈጠርንም ይጎዳል፡ እስከ ውስጥ እግሬ ድረስ ዘልቆ አመመኝ፡ ልቤ ወደ ደረቴ ህመም የሚልክ የተቀደደ ኳስ መሰለኝ፡
ከኋላዬ ክሪስ በፍጥነት ወደ ውስጥና ወደ ውጪ ሲተነፍስና መንትዮቹ ሲነጫነጩ ይሰማኛል።

ይህ ትልቅ የመሆኛ ጊዜዬ ነው፤ እናታችን በትክክልና ውጤታማ በሆነ መንገድ የምትጠቀምበትን ራስን የመቆጣጠር ዘዴ ተግባራዊ የማደርግበት ጊዜ ነው: እንቅስቃሴዬንና ፊቴ ላይ ያለውን ስሜት ከእናቴ ኮረጅኩ።
እጆቼን እሷ እንደምታደርገው አደረግኩ በቀስታና በማታለል አይነት እሷ እንደምታደርገው ፈገግ አልኩ

ከዚያስ? መብሰሌን ለማሳየት ምን አደረግኩ?

ስጦታውን ወለሉ ላይ ጣልኩት! ከዚህ በፊት ጮክ ብዬ ተናግሬያቸው የማላውቃቸውን ቃላት እየተናገርኩ፣ እግሬን አንስቼ ረገጥኩትና መያዣው ሲሰበር እየሰማሁ ጮህኩ! በሁለቱም እግሮቼ ላዩ ላይ ዘለልኩበት ጣሪያው ስር ካለው ክፍል ያገኘነውና ስጦታውን የሰራንበት የሚያምር ፍሬም እንክትክቱ እስኪወጣ ድረስ ላዩ ላይ ጨፈርኩበት ከድንጋይ የተሰራችን ሴት እንድናግባባ የመከረኝን ክሪስን ጠላሁት እንደዚህ አይነት ቦታ እንድንኖር ስላደረገችን እናቴን ጠላኋት!

እናቷን የተሻለ ልታውቃት ይገባ ነበር እዚህ አምጥታን ውርስ ከምትጠብቅ ሱቅ ውስጥ ጫማ መሸጥ ትችል ነበር። አሁን ካደረገችው የተሻለ ነገር
ማድረግ ትችል ነበር።

በአንድ እብድ አውሬ ጥቃት ስር ደረቁ ፍሬም ብትንትኑ ወጣ ልፋታችንም ሄደ፡

“አቁሚ! ለራሳችን እናስቀምጠዋለን፡” አለ ክሪስ

ሙሉ በሙሉ መበላሸቱን ለመከላከል ፈጥኖ ቢደርስም ስዕሉ ግን ተበላሽቶ
ነበር ለዘለዓለም ሄዶ ነበር አለቀስኩ፡

ስንሰቀሰቅ ክሪስ በክንዶቹ አቅፎኝ በአባትነት ቃና “አይዞሽ ምንም አይደል። ያደረገችው ነገር ችግር የለውም፡ እኛ ትክክል ነን፡ የተሳሳተችው እሷ ናት። እኛ ልንቀርባት ሞክረናል፡ እሷ ናት በፍፁም ያልሞከረችው" አለኝ:

በስጦታዎቻችን መካከል ወለሉ ላይ በፀጥታ ተቀመጥን፡ መንትዮቹ ትልልቅ አይኖቻቸው በጥርጣሬ ተሞልተው ፀጥ ብለዋል፡ በአሻንጉሊቶቻቸው
መጫወት ቢፈልጉም፣ የእኛ መስታወቶች በመሆናቸውና ምንም ብንሆን የእኛን ስሜት የሚያንፀባርቁ በመሆኑ መወሰን አልቻሉም: እነሱን የማየት
ሀዘን እንደገና አሳመመኝ።

እናታችን ፈገግ ብላና የገና ሰላምታዋን አስቀድማ ወደ ክፍላችን ስትመጣ ተጨማሪ ስጦታዎች ይዛ ነበር ከነዚያም መሀል ድሮ የእሷና በጥላቻ
የተሞላች እናቷ የነበረ ትልቅ የአሻንጉሊት ቤት ይገኝበታል። “ይሄ ለኮሪ ለኬሪ የኔ ስጦታ ነው:" አለችና ሁለቱንም አቅፋ ጉንጮቻቸውን ሳመች።ከዚያ እሷ የአምስት አመት ልጅ የነበረች ጊዜ ታደርግ እንደነበረው “የውሸት
ወላጆች፣ የውሽት ቤት” እያደረጉ እንዲጫወቱ ነገረቻቸው።

ብታስተውል አንዳችንም በዚያ የአሻንጉሊት ቤት አልተደሰትንም ነበር።አስተያየት አልሰጠችም: በደስታ እየሳቀች ወለሉ ላይ እንደመንበርከክ ብላ
ተረከዟ ላይ ቁጢጥ አለችና ይህንን የአሻንጉሊት ቤት እንዴት ትወደው እንደነበረ ነገረችን

“ካቲ” አለች እናቴ ክንዷን አንገቴ ላይ አድርጋ፣ “ይህንን ትንሽ ጨርቅ ተመልከቺ ከንፁህ ሀር የተሰራ ነው፡፡ በምግብ ቤት ውስጥ ያለው ደግሞ
ኦሪየንታል ምንጣፍ ነው" አለችኝ የአሻንጉሊቱ ቤት ውስጥ ያሉትን ዋጋ ያላቸው ነገሮች በመጥራት፡

“አሮጌ ሆኖ እንዴት አዲስ ሊመስል ቻለ?” ስል ጠየቅኳት።

በእናታችን ላይ ጥቁር ደመና ሲያጠላና ፊቷን ሲሸፍናት አየሁ። “የእናቴ በነበረበት ወቅት በመስተዋት ሳጥን የተሸፈነ ነበር። እንድትመለከተው እንጂ
እንድትነካው አይፈቀድላትም ነበር። ለእኔ ሲሰጠኝ አባቴ የመስተዋቱን ሳጥን በመዶሻ ሰበረውና እጄን መፅሀፍ ቅዱስ ላይ አስደርጎ ምንም ነገር
እንዳልሰብር ካስማለኝ በኋላ በሁሉም ነገር እንድጫወት ፈቀደልኝ

“ከማልሽ በኋላ የሆነ ነገር ሰበርሽ?” ክሪስ ጠየቃት።

“አዎ ከማልኩ በኋላ አንድ ነገር ሰበርኩ" አንገቷን ስላቀረቀረች ፊቷን ማየት አልቻልንም “በጣም ቆንጆ ወጣት ሆኖ የተሰራ ሌላ አሻንጉሊት ነበር እና ኮቱን ላወልቅለት ስሞክር እጁ ወለቀ ከዚያ አሻንጉሊቱን ስለሰበርኩ
ብቻ ሳይሆን ከልብሱ ስር ያለው ምን እንደሆነ ለማወቅ በመፈለጌ ጭምር ተገረፍኩ።"

እኔና ክሪስ ዝም ብለን ስንቀመጥ ኬሪ ግን ቀልቧ የሚያምር ባለቀለም ልብስ የለበሱት ትንንሽ የሚያስቁ አሻንጉሊቶች ላይ አረፈ፡ እሷ ፍላጎት ስላደረባት

ኮሪም በአሻንጉሊት ቤቱ ውስጥ ያሉትን ነገሮች መመርመር ጀመረ:

የዚህን ጊዜ ነው እናታችን ትኩረቷን ወደኔ ያደረገችው ካቲ እኔ ስመጣ ምን ሆነሽ ነው ቅር ብሎሽ የነበረው? ስጦታዎችሽን አልወደድሻቸውም? አለች:
👍431
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

.....የሚያንቀጠቅጥ ሀሳብ መጣብኝı ኬሪ ወይም ኮሪ የሆነ ነገር ሊሰብሩ ቢችሉ ቅጣቱ ምን ሊሆን እንደሚችል!.

እናታችን ቃሏን በመጠበቅ መንትዮቹ ከተኙ በኋላ ወደ ክፍላችን መጣች::በጣም ቆንጆ ከመሆኗ የተነሳ ልቤ በኩራት፣ በአድናቆትና በትንሹ በቅናት
አበጠ የለበሰችው ልብስ ጆሮዎቿ ላይ በረጅሙ ከተንጠለጠሉትና ከሚያበሩት የአልማዝና ኤሜራልድ የጆሮ ጌጦች ጋር አብሮ ያንፀባርቃል። ጠረኗ
በምስራቅ ያለ በጨረቃ ብርሀን የደመቀ ሽቶ ሽቶ የሚሽት የአትክልት ስፍራን አስታወሰኝ፡፡ ክሪስ ፍዝዝ ብሎ እሷ ላይ ማፍጠጡ ምንም አያስገርምም::
በከባዱ ተነፈስኩ፡ አምላኬ እባክህ አንድ ቀን… እንደ እሷ እንድመስልና ወንዶች እጅግ የሚያደንቁት ገባ ያለ ወገብ እንዲኖረኝ አድርግ።

ስትራመድ ግራና ቀኝ ያለው የልብሷ ዘርፍ እንደ ክንፍ ከፍና ዝቅ እያለ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዚያ ደብዛዛ ብርሃን ካለው ክፍል ወጣን፡ የእናታችንን ኮቴ
እየተከተልን በሰሜን አቅጣጫ ባሉት ጨለማማ ሰፊ አዳራሾች በኩል መሄድ ጀመርን፡ “ልጅ እያለሁ ትልልቅ ሰዎች ሲደንሱ ለማየት ወላጆቼ ሳያውቁ
የምደበቅበት ቦታ ነበር” ስትል አንሾካሾከች: “ለሁለታችሁ ይጠባችኋል። ግን ተደብቃችሁ ልታዩ የምትችሉበት ቦታ ያ ብቻ ነው: በምንም አይነት ሁኔታ ቢሆን አንድም ድምፅ እንደማታሰሙ እንደገና ቃል እንድትገቡልኝ
እፈልጋለሁ እንቅልፋችሁ ከመጣ ቀስ ብላችሁ ሳትታዩ ወደ ክፍላችሁ ሂዱ እንዴት እዚያ እንደምትደርሱ አስታውሱ:” መንትዮቹ ድንገት ከእንቅልቻቸው ነቅተው ፍርሀት እንዳይስማቸው ከአንድ ሰዓት የበለጠ
እንዳንቆይ አስጠነቀቀችን፡ ምናልባትም እኛን ፍለጋ ሊወጡና አዳራሹ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ሊሉ ይችሉ ይሆናል። እንደዚያ ካደረጉ ምን ሊፈጠር
እንደሚችል እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያውቀው።

በሚስጥር ከስሩ በሮች ያሉት ትልቅ ጠረጴዛ ስር ገባን፡ የማይመችና በጣም ጠባብ ነው፡ ግን ከጀርባው ባለው መስኮት መስል ክፍተት በደንብ መመልከት
እንችላለን፡

እናታችን በፀጥታ ሹልክ አለች።

እኛ ካለንበት በታች ራቅ ብሎ በሚያምር ሁኔታ በሻማ ብርሀን ያጌጠ ክፍል ተመለከትን፡ በህይወቴ እንደዚህ የበዙ ሻማዎች አንድ ላይ ሲበሩ አይቼ
አላውቅም! የሻማዎቹ ሽታ እንዲሁም ብርሃኑ ሴቶቹ ያደረጓቸው ጌጣጌጦች
ላይ ሲያርፍ ያለው ማንፀባረቅ ምትሀታዊና ፊልም ላይ ሲንዴሬላና ልዑሉ የደነሱበትን ቦታ ይመስል ነበር።

በመቶ የሚቆጠሩ እንደ ሀብታም የለበሱ ሰዎች እየሳቁና እያወሩ ነው: ጥግ ላይ ደግሞ ለማመን የሚከብድ የገና ዛፍ ተቀምጧል እጅግ በጣም ትልቅ ሲሆን ባለቀለም ጌጣጌጦች ተደርገውበታል፡ ላዩ ላይ የተደረጉት በመቶዎች
የሚቆጠሩ ወርቃማ መብራቶች አይን ያፈዛሉ በዳንሱ ክፍል ውስጥ ወጣ ገባ እያሉ በትሪዎች ላይ ምግብ ይዘው ትልቅ ጠረጴዛ ላይ ይደረድራሉ፡ ሁሉም
ነገር ውብ፣ የሚያምርና የሚያስደንቅ ነበር ... እናም ከተቆለፈ በር ውጪ ደስተኛ ህይወት መኖሩን ማወቅ ጥሩ ነው።

"ካቲ…” ክሪስ በጆሮዬ እያንሾካሾከ “ከዚያ ጥርት ካለው መጠጥ አንድ ጊዜ ፉት ለማለት ነፍሴን ለሰይጣን እሸጣለሁ” አለ።

የእኔም ሀሳብ ነበር ...

እንደዛሬ ርሀብ፣ ጥማትና መከልከል ተሰምቶኝ አያውቅም: ሆኖም ግን ሁለታችንም ታላቅ ሀብት ሊገዛውና ሊያስገኘው በሚችለው ድምቀት ተገረምን፡ ጥንዶች የሚደንሱበት ወለል በሰም ተወልውሎ እንደ መስተዋት
ያንፀባርቃል፡ ትልልቅ ወርቃማ ፍሬሞች ያሏቸው በክፍሉ ውስጥ ያሉት መስታዎቶች የዳንሰኞቹን ምስል ሲያንፀባርቁ ሲታይ የትኛው እውነተኛ ምስል እንደሆነ እንኳ ለመለየት ያስቸግር ነበር።

እኔና ክሪስ ወጣትና ቆንጆ በሆኑት ጥንዶች ላይ አፍጥጠን ነበር፡ ስለ
ልብሳቸው፣ የፀጉር አሰራራቸውና ስላላቸው ግንኙነት በመገመት አስተያየት እንሰጥ ነበር ከሁሉም በላይ ግን የትኩረት ማዕከል የነበረችውን እናታችንን እያየን ነበር፡ በአብዛኛው ከአንድ ረጅም፣መልከመልካም፣ ጥቁር ፀጉርና ረጅም ፂም ካለው ሰው ጋር እየደነሰች ነበር: የምትበላውንና የምትጠጣውንም
ያመጣላት እሱ ነበር ምግቡን ይዛ ሶፋ ላይ ተቀምጠው መብላት ጀመሩ።በጣም ተጠጋግተው እንደተቀመጡ አሰብኩ። በፍጥነት አይኖቼን ከእነርሱ መልሼ ከትልልቆቹ ጠረጴዛዎች ኀላ ወደ ቆሙት ሶስት ምግብ አብሳዮች
አተኮርኩ አሁንም ምግብ እየሰሩ ነው የምግቦቹ ሽታ ወደኛ ደርሶ የምራቅ እጢዎቻችንን በኃይል እንዲሰሩ አደረጋቸው፡

ከጊዜ ወደ ጊዜ እናታችን ከዚያ ሰው ጋር ትሰወራለች የት ነው የሚሄዱት?ምንድነው የሚሰሩት? እየተሳሳሙ ነው? ፍቅር ይዟታል? ካለንበት ከዚያ ርቀት ላይ ሆነን እንኳ ሰውየው በእናታችን እንደተማረከ መናገር እችላለሁ:
አይኑን ከፊቷ ላይ መንቀል አልቻለም፧ እጆቹም እሷን ከመንካት መከልከል
አልቻለም::

ቀስ ባለ ሙዚቃ ሲደንሱ፣ ጉንጯ ጉንጩን እስኪነካ ድረስ አስጠግቶ ይዟት ነበር ዳንሱን ሲጨርሱ እጁን ትከሻዎቿ ወይም ወገቧ ላይ ያደርጋል። አንድ ጊዜ እንደውም ጡቷን እስከ መንካት ሳይቀር ደፍሯል።

አሁን ይህንን መልከ መልካም ፊቱን በጥፊ ትለዋለች ብዬ አሰብኩ። ምክንያቱም እኔ ብሆን እንደዚያ ነበር የማደርገው: እሷ ግን ዞር አለችና ሳቀች ከዚያ ገፋ አደረገችውና በአደባባይ እንደዚያ እንዳያደርግ ማስጠንቀቂያ
ሊሆን ይችላል የሆነ ነገር አለችው: እሱም ፈገግ ብሎ እጇን ያዘና ወደ ከንፈሩ አስጠጋው ከዚያ አይኖቻቸው ረጅምና ትርጉም ያለው እይታ ተለዋወጡ:
ወይም እንደዚያ እንደሆነ አሰብኩ

“ክሪስ እናታችንን ከዚያ ሰው ጋር አየሀት?”

“አዎ አይቻቸዋለሁ ልክ እንደ አባታችን ረጅም ነው።”

“አሁን ያደረገውን አይተሀል?”
“ልክ እንደሌሎቹ እየበሉና እየጠጡ፣ እየሳቁና እያወሩ እንዲሁም እየደነሱ ነው: አስቢው ካቲ… እናታችን ያንን ሁሉ ገንዘብ ስትወርስ እንደዚህ አይነት
ድግሶች ለገና እና ለልደቶቻችን እንደግሳለን፡ አሁን ያየናቸውን እንግዶች ወደፊት እናገኛቸው ይሆናል። ግላድስተን ላሉት ጓደኞቻችን የግብዣ ወረቀት
እንልክላቸዋለን፡ አቤት! የወረስነውን ሲመለከቱ በጣም ነው የሚገረሙት"አለ፡፡

ወዲያው አያታችን ወደ ዳንስ ክፍሉ ገባች: ወደ ግራም ወደ ቀኝም አልተመለከተችም ለማንምም ፈገግታ አላሳየችም
ቀሚሷ ግራጫ አልነበረም።
እኛን ለማስደነቅ ያ ብቻውን በቂ ነበር ፀጉሯ በሚገባ ተሰርቷል። አንገቷ፣ጆሮዎቿ ክንዶቿና ጣቶቿ በአልማዝና በሩቢ ጌጣጌጦች አሸብርቀዋል።ያቺ አስደናቂ ንጉሳዊ ግርማ ሞገስ ያላት ሴት በየቀኑ የምትጎበኘን አስፈሪ
አያታችን መሆኗን ማን ያምናል?

ፈቃደኛ ባንሆንም አሁንም አሁንም በሹክሹክታ “እጅግ አስደናቂ ሆናለች '' ብለን አመንን

“አዎ በጣም አስገራሚ”

የዚህን ጊዜ ነው የማናውቀውን ወንድ አያታችንን ያየነው!

ወደ ታች መመልከቴ ትንፋሼን ቀጥ አደረገው ያየሁት ሰው በጣም አባቴን ይመስላል አባታችን እስከሚያረጅ ድረስ በህይወት ቢኖር ኖሮ ይህን ሰው
እንደሚመስል ማየት ይቻላል በሚገፋ ወንበር ላይ ተቀምጦ ነበር። ቶክሲዶ ለብሷል። ሸሚዙ ጥቁር ቁልፍ ያለበት ነጭ ሸሚዝ ነበር፡ የሳሳው ወርቃማ ፀጉሩ ነጭ ወደ መሆን ሄዶ፣ በብርሃን ሲታይ ብርማ መስሎ ያንፀባርቃል።
ቆዳው ደግሞ የተደበቅንበት ቦታ ላይ ሆነን በሩቅ እያየነው ስለሆነ ሊሆን ይችላል፣ አልተጨማደደም: እኔና ክሪስ በመደንገጥና በመገረም አንድ ጊዜ ካየነው ጀምሮ አይኖችንን ወዴትም አላንቀሳቀስንም፡
👍37🥰2👏2
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


የክሪስቶፈርፍለጋና ውጤቶቹ

ድንገት የሆነ እጅ ትከሻዬን እየወዘወዘ ቀሰቀሰኝ! በድንጋጤና በመርበትበት እናቴ መሆኗን እንኳን መለየት ያልቻልኳት ሴት ላይ በፍርሀት አፈጠጥኩ::
መልሳ አፍጥጣብኝ እጅግ በተቆጣ ድምፅ “ወንድምሽ የት ነው?" ስትል ጠየቀችኝ፡፡

በጣም ከቁጥጥር ውጪ ሆና ስትናገር ስሰማት እንዳትመታኝ እየተሸማቀቅኩ አይኖቼን ክሪስቶፈር ወደሚተኛበት አልጋ ወረወርኩ ባዶ ነበር። አምላኬ
በጣም ብዙ ቆይቷል።

መዋሸት ይገባኝ ይሆን? ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል ሄዷል ብዬ ልከላከልለት? አይሆንም እቺ እናታችን ናት፤ ትወደናለች… ትረዳናለች… “ክሪስ እዚህ ፎቅ
ላይ ያሉ ክፍሎችን ለማየት ወጥቷል” አልኩ።

ግልፅነት መልካም ነው አይደል? እርስ በርሳችን ተወሻሽተንም ሆነ ለእናታችን ዋሽተን አናውቅም፡ የምንዋሸው ለአያትየው ነው እሱም አስፈላጊ ሲሆን ብቻ።

“የተረገመ! የተረገመ! የተረገመ! ስትል እየጮኸች ወደ እኔ ባተኮረ አዲስ የቁጣ ማዕበል ነደደች ውዱ ትልቁ ልጇ፣ ከሁሉም የምታስበልጠው ልጇ፣ የዲያብሎስ ተፅዕኖ ካላረፈበት በስተቀር በጭራሽ አይከዳትም፡ ትከሻዬን ይዛ ልክ እንደሚራገፍ ጨርቅ አራገፈችኝ፡፡

“በማንኛውም ሁኔታ ሁለተኛ አንቺና ክሪስቶፈር ከዚህ ክፍል እንድትወጡ አልፈቅድላችሁም ሁለታችሁም ቃላችሁን ሰጥታችሁኝ ነበር ግን ቃላችሁን
አጠፋችሁ አሁን ታዲያ እንዴት ላምናችሁ እችላለሁ ላምናችሁ የምችል መስሎኝ ነበር የምትወዱኝና በፍፁም የማትከዱኝ ይመስለኝ ነበር!”

አይኖቼ ፈጠጡ እኛ ነን የከዳናት? እንደዚህ አይነት ሁኔታ ስላሳየችን
ደንግጫለሁ። ለእኔ እሷ የከዳችን ነው የመሰለኝ፡

“እማዬ ምንም መጥፎ ነገር አልሰራንም: የተደበቅንበት ቦታ የቆየነው በፀጥታ ነበር፡ ሰዎች በዙሪያችን ሲመጡና ሲሄዱ ነበር፡ ግን ማንም እዚያ መሆናችንን አላወቀም ማንም እዚህ እንዳለን አያውቅም: ሁለተኛ ከዚህ
አላስወጣችሁም ማለት አትችይም ከዚህ ልታስወጪን ግድ ነው፡ ለዘለዓለም እዚህ ውስጥ ልትደብቂንና ልትቆልፊብን አትችይም:” ምንም መልስ ሳትሰጠኝ በእንግዳና በንቀት አይን ተመለከተችኝ፡፡ በጥፊ የምትመታኝ መስሎኝ ነበር
ግን አላደረገችውም ትከሻዬን ለቀቀችኝና ለመውጣት ፊቷን አዞረች።

ልክ ክፍሉን ለቃ ወጥታ ራሷ ልትፈልገው ስትል በሩ ተከፈተና ወንድሜ ሹክክ ብሎ ወደ ውስጥ ገባ:: በሩን ለቀቀና ዞሮ ወደ እኔ ተመለከተ። ከዚያ ለመናገር ከንፈሩን አላቀቀ: የዚያን ጊዜ እናታችንን ሲመለከት እጅግ እንግዳ የሆነ ስሜት ፊቱ ላይ ታየ።

ለምን እንደሆነ ባላውቅም፣ እንደ ሁልጊዜው እናታችንን ሲያይ አይኖቹ በደስታ አልበሩም።

እናታችን በቅፅበት አጠገቡ ደረሰችና አንዴ በጥፊ አላሰችው: የንዴቷ ብዛት ከድንጋጤው ሳይመለስ ግራ እጇን አነሳችና ሌላኛው ጉንጩ ላይ በጥፊ
መረገችበት።

የክሪስ የገረጣ ፊት ሁለት ትልልቅ ቀያይ ምልክቶች አወጣ።

“ክሪስቶፈር ፎክስወርዝ፣ ሁለተኛ እንደዚህ አይነት ነገር ብታደርግ እኔ ራሴ ነኝ የምገርፍህ! አንተን ብቻ ሳይሆን ካቲንም ጭምር” ክሪስ የተፈጥሮ ቀለሙ ጠፍቶ ፊቱ በጥፊ የተመታበት ምልክቶች የደም አሻራዎች ሆነው
ይታዩ ነበር የራሴ ደም ወደ እግሬ ሲወርድ ከጆሮዎቼ ኋላ የሚያቃጥል ስሜት ተሰማኝ
ጥንካሬዬ እያነሰ መጥቶ እንግዳ እየመሰለች የመጣችው ሴት ላይ አፈጠጥኩ።

ልክ እንደማላውቃትና ለማወቅም ግድ የሌለኝ አይነት ሴት ሆነችብኝ፡ እውነት ይህቺ ሁልጊዜ በደግነትና በፍቅር የምታነጋግረን እናታችን ናት? ረጅም ጊዜ ተዘግቶብን በመቆየታችን የሚሰማንን ስሜት እጅግ ትረዳን የነበረችው
እናታችን ናት? ቤቱ እንደዚህ እንድትሆን የሆነ ነገር አደረጋት ይሆን? ፈጥኖ የመጣልኝ ሀሳብ ይሄ ነው ...ትንንሾቹ ነገሮች ሁሉ ተደምረው እንድትለወጥ አደረጓት
የሚለው፡ በፊት እንደምታደርገው ብዙ ጊዜ አትመጣም: መጀመሪያ አካባቢ እንደምታደርገው በቀን ሁለት ጊዜ ወይም በየቀኑ አትመጣም አሁን የምናምንበትና የምንጠጋበት ነገር ሁሉ ከእግራችን ስር ሾልኮ፣ ሁሉን ነገር አጥተን አሻንጉሊቶች፣ መጫወቻዎችና ስጦታዎች

ብቻ የቀሩን ስለመሰለኝ ፈራሁ።

በክሪስ የደነገጠ ፊት ላይ ንዴቷን የሚያጠፋ የሆነ ነገር አይታ መሆን አለበት በክንዶቿ አቅፋ የጎዳችውን ለመካስ በጥፊ ተመትቶ የቀላውን ፊቱን
በችኮላና በትንንሹ በመሳም ልታፅናናው ሞከረች። ሳመችው፣ ሳመችው፣ሳመችው ፀጉሩን በጣቶቿ አበጠረች ጉንጮቹን አሻሸች: ጭንቅላቱን ወደ ጡቶቿ አስጠግታ አቀፈችው

“ይቅርታ አድርግልኝ ውዴ” አይኖቿና ድምፅዋ ውስጥ እምባ አለ፡ “ይቅር በለኝ… እባክህ ይቅር በለኝ. ስለ መግረፍ ያወራሁት ከልቤ አይደለም:እንዴት እኔን ልትፈራኝ ትችላለህ? እወድሀለሁ እኮ ታውቃለህ አንተንም
ሆነ ካቲን በጭራሽ አልገርፋችሁም: ገርፌያችሁ አውቃለሁ? ራሴን ስላልሆንኩ ነው እንደዚያ የተናገርኩት። ሁሉም ነገር ባሰብኩት መንገድ
እየሄደልን ስለሆነ ያንን ለማበላሸት ምንም ነገር ማድረግ ስለሌለባችሁ ነው በጥፊ የተማታሁበት ብቸኛው ምክንያት ያ ብቻ ነው።” አለችው:

ፊቱን በመዳፎቿ መሀል ጥብቅ አድርጋ ይዛ፣ የተጨማደደ ፊቱን እያየች ጉንጩ ላይ ሳመችው: የሆነ ስሜት እየተሰማኝ ቁጭ ብዬ በመገረም እየተመለከትኩ ነበር… ግራ ከመጋባቴና ልጅ ከመሆኔ ውጪ ምን እየተሰማኝ እንደሆነ አላውቅም በዙሪያችን ያለው አለም ግን በሙሉ ያረጀ በጣም
ያረጀ ነበር።

ይቅርታ አደረገላት በእርግጥም ምን እየተካሄደ እንደሆነ ማወቅ አለብን። “እባክሽ እማዬ፣ ምን እንደሆነ ንገሪን እባክሽ?”

“ሌላ ጊዜ” አለች ወደ ዳንሱ ለመመለስ ጥድፊያ ላይ ነበረች: ሁለታችንንም እንደገና ሳመችን፡ “ሌላ ጊዜ ምናልባት ነገ ሁሉንም ነገር እነግራችኋለሁ"አለችና በችኮላ እየሳመችን የሚያፅናኑ ቃላት ነገረችን: በእኔ ላይ ተንጠራርታ ኬሪን ሳመቻት ከዚያ ወደ ኮሪ ሄዳ ጉንጩን ሳመች።

“ይቅር ብለኸኛል ክሪስቶፈር?”
“አዎ እማዬ፤ ልክ ነሽ እዚሁ ክፍል ነው መቀመጥ ያለብን ለማየት መውጣት አይገባኝም ነበር”
ፈገግ አለችና “መልካም የገና በዓል፣ በቅርቡ አያችኋለሁ:" ከዚያ ወጣችና በሩን ቆልፋ ሄደች።

እዚህ ከመጣን ያሳለፍነው የመጀመሪያው የገና በዓላችን አለቀ: አዳራሹ ውስጥ ያለው ሰዓት ሰባት ሰዓት መሆኑን አመለከተ: በስጦታ የተሞላ
ክፍል፣ ቲቪ፣ የጠየቅነው የቼዝ መጫወቻ፣ የሚሞቁ አዳዲስ ልብሶችና ብዙ የሚበሉ ጣፋጮች ነበሩን፡፡ እኔና ክሪስ ደግሞ አስገራሚ ግብዣ ነበረን
ሆኖም የሆነ አዲስ ነገር ወደ ህይወታችን መጥቷል የማናውቀው አዲሱ
የእናታችን ባህርይ ለአጭር ደቂቃ እናታችን ልክ አያታችንን መስላ ነበር።

በጨለማ አንድ አልጋ ላይ በአንደኛው ጎን ኬሪ፣ በሌላው ጎን ክሪስ ተኝቶ እኔና ክሪስ እጅ ለእጅ ተያይዘናል፡ ጠረኑ ከእኔ የተለየ ነው ጭንቅላቴ ደረቱ ላይ አርፏል። ከሩቅ ወደ ጆሯችን ከሚመጣው በትንሹ ከሚሰማው ሙዚቃ
“ ልቡ ሲመታ ይሰማኛል ፀጉሬን በጣቶቹ እያፍተለተለ ነበር።

ክሪስ ትልቅ ሰው መሆን በጣም የተወሳሰበ ነገር ነው አይደል?"

“ይመስለኛል”

“ትልቅ ሰው ስትሆን የትኛውንም አይነት ሁኔታ መቋቋም እንደምትችል አስባለሁ መቼም ቢሆን ስህተትና ትክክል ለሆነው ነገር ጥርጣሬ ገብቶህ አያውቅም ትልልቅ ሰዎች እንደኛ ይፍጨረጨራሉ ብዬ አልገምትም
👍33
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


...አሁን ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ ባለው ሚስጥር ላይ ቆሻሻና የሚሸቱ ጨርቆች በሻንጣዎቹ ውስጥ በመክተት ሌላ ሚስጥር ጨመርንበት.

ስለ ሁኔታው አብዝተን ባለማውራታችን ከነገሩ እጅግ አስፈሪ መሆን አመለጥን:
ጠዋት እንነሳና ፊታችን ላይ ውሀ ረጨት እናደርጋለን። ጥርሶቻችንን በባዶ ውሀ እናፀዳለን፤ ጥቂት ውሀ እንጠጣና ትንሽ ወዲያ ወዲህ እንላለን፡ ከዚያ ጋደም ብለን ቴሌቭዥን እናያለን ወይም እናነባለን፡

መንትዮቹ ምግብ ፈልገው ሲያለቅሱ መስማቴ ህይወቴን ሙሉ ልቤ ላይ የሚኖር ጠባሳ አስቀመጠልኝ፡ አያታችንን እንዴት እንደጠላኋት። ያቺ አሮጊት እና እናታችን ይህንን ስላደረጉብን ጠላኋቸው።

የመመገቢያ ሰአታችን ያለ ምግብ ሲያልፍ እንተኛለን፡ ለሰዓታት እንተኛለን::እንቅልፍ ሲወስደን የርሀብ ወይም የብቸኝነት ወይም የምሬት ስቃይ አይሰማንም በእንቅልፍ በውሸት የደስታ ስሜት ውስጥ እንሰምጣለን ከዚያ
ስንነቃ ስለምንም ነገር ግድ አይኖረንም።

እንደ ፈዘዝኩና እንደደከምኩ ጭንቅላቴን ዞር አድርጌ ክሪስንና ኮሪን እያየሁ ነበር ከዚያ ክሪስ ከኪሱ ሰንጢ አውጥቶ የእጁን አንጓ ሲቆርጥ ያለምም
ስሜት ጋደም ብዬ እየተመለከትኩ ነው። የሚደማ እጁን ወደ ኮሪ አፍ አስጠጋና ኮሪ ቢቃወምም እሱ ግን ደሙን እንዲጠጣ አደረገው: ከዚያ የኬሪ ተራ ሆነ ሁለቱ ምንም ነገር ያልበሉ በመሆናቸው፣ የትልቁ ወንድማቸውን ደም ጠጥተው፣ በደበዘዘ፣ በፈጠጠና በተቀባይነት አይን አተኩረው ተመለከቱት።

ማድረግ ባለበት ነገር የማቅለሽለሽ ስሜት ተሰምቶኝ ፊቴን አዞርኩ። ያንን በማድረጉ አድናቆት ተሰምቶኛል። ሁልጊዜ ከባባድ ችግሮችን ማቃለል
ይችልበታል።

ከዚያ ክሪስ ወደኔ አልጋ መጣና፣ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጦ ረዘም ላሉ ደቂቃዎች ሲመለከተኝ ከቆየ በኋላ አይኖቹ ወደተቆረጠው አንጓው ዝቅ
አሉ አሁን መድማቱን አቁሟል። እኔም ደሙን ጠጥቼ ረሀቤን እንዳስታግስ ሌላኛውን ደም ስሩን ለማድማት ሰንጢውን አወጣ እንዳያደርገው ነግሬ ሰንጢውን ቀምቼ ወረወርኩት። ብርታት ለማግኘት ስል የእሱን ደም
እንደማልጠጣ ምዬ ተገዝቼ ብነግረውም መሀላዬን ከቁም ነገርም ሳይቆጥር ሰንጢውን በአልኮል ማፅዳት ጀመረ።

“ተመልሳ ባትመጣ ምንድነው የምናደርገው ክሪስ?" ስል ጠየቅኩት አያታችንን ለሁለት ሳምንት አላየናትም: አይጥ ለማጥመድ ወጥመዱ
ላይ ያደረግነውን ቺዝ የሚላስ የሚቀመስ ባጣን ጊዜ በልተን ጨርሰነዋል።ምግብ የሚባል ሳንቀምስ ሶስት ቀናችን ሆኗል፡ መንትዮቹ እንዲጠጡት
የተውንላቸው ወተትም ካለቀ አስረኛ ቀን ሆኖታል።

“በረሀብ አትገድለንም” አለ ክሪስ አጠገቤ ተኝቶ በደካማ ክንዱ እያቀፈኝ። “እሷ ያንን እንድታደርግ ከፈቀድንላት ደደቦች ነን ማለት ነው ነገ ምግብ ይዛ ካልመጣች ወይ ደግሞ እናታችንም ብቅ ካላለች አንሶላ ተልትለን መሰላል
እንሰራና ወደ መሬት እንወርዳለን” አለ፡

ጭንቅላቴ በደረቱ ላይ ስለሆነ ልቡ ሲመታ ይሰማኛል። “ምን እንደምታደርግ ታውቃለህ? ስለምትጠላን እንድንሞት ትፈልጋለች። መወለድ የማይገባን
የሰይጣን ልጆች መሆናችንን ስንት ጊዜ ነው የነገረችን?

ካቲ፤ ያቺ ጠንቋይ አሮጊት ደደብ አይደለችም: እናታችን ካለችበት ከመምጣቷ በፊት ምግብ ይዛ ትመጣለች::”

የተቆረጠ እጁን ላሽግለት ተንቀሳቀስኩ ከሁለት ሳምንት በፊት እኔና ክሪስ ለማምለጥ መሞከር ይገባን ነበር። የዚያን ጊዜ ሁለታችንም ጥንካሬ ነበረን
አሁን ብንሞክር ግን በእርግጠኝነት ወድቀን እንሞታለን፡ መንትዮቹን
በጀርባችን አዝለን ከሆነ ደግሞ የበለጠ ከባድ ይሆንብናል።

በማግስቱ ጠዋት ምንም ምግብ እንዳልመጣ የተመለከተው ክሪስ ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል እንድንሄድ አስገደደን፡ እኔና ክሪስ ለመራመድ እጅግ ደክመው
የነበሩትን መንትዮች ተሸከምናቸው የመማሪያ ክፍሉ ጥግ ላይ ስናስቀምጣቸው አቅማቸው ስላልቻለ እንደመተኛት
እያሉ ግድግዳውን ተደግፈው ቁጭ አሉ። ክሪስ መንትዮቹን ጀርባችን ላይ የምናስርበትን ገመድ እያዘጋጀ ነው

“በሌላ መንገድ እናደርገዋለን” አለ ክሪስ እንደገና እያሰበ “በመጀመሪያ እኔ እሄዳለሁ መሬት ስደርስ ኮሪን ታስሪውና ቀስ እያልሽ ወደታች ትለቂዋለሽ
ቀጥሎ ኬሪንም እንደዚያው ታደርጊያለሽ: በመጨረሻ አንቺ ትመጫለሽ ስለ እግዚአብሔር ብለሽ የምትችይውን ጥረት ሁሉ አርጊ! አደጋ በሚደርስበት
ወቅት ከፍተኛ ንዴት ከሰው በላይ የሆነ ጥንካሬ እንደሚፈጥር ሰምቻለሁ።"

“አንተ የበለጠ ጠንካራ ስለሆንክ እኔ መጀመሪያ ልሂድ” አልኩት በድካም ስሜት “አይሆንም! ድንገት ፈጥነው ከመጡ ለመያዝ ታች መሆን አለብኝ ያንቺ ክንዶች የኔን ያሀል ጥንካሬ የላቸውም: ክብደቱ ሁሉ አንቺ ላይ
እንዳይሆን ገመዱን ጭስ መውጫው ላይ አስርልሻለሁ እና ካቲ ይvህ የአደጋ ጊዜ ነው!”

በአይጥ መያዣ ወጥመዱ ላይ አራት የሞቱ አይጦችን በድንጋጤ ተመለከትኩ።“ትንሽ ጥንካሬ እንድናገኝ እነዚህን አይጦች መብላት አለብን፡” አለ ኮስተር ብሎ፡ “ማድረግ ያለብንን ሁሉ ማድረግ አለብን::''

እነዚያን የሞቱ ትንንሽ ወፍራም ነገሮች በመጠየፍ እየተመለከትኩ “ጥሬ ስጋ? ጥሬ አይጥ? አይሆንም!" አልኩ በቀስታ:
በጣም ተናዶና አስገዳጅ በሚመስል አይነት መንትዮቹንም ሆነ ራሴን በህይወት ለማቆየት የሚያስፈልገውን የትኛውንም ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ነገረኝ፡ “ተመልከቺ ካቲ፣ መጀመሪያ እኔ ሁለቱንም እበላለሁ ገመዶቹን
በደንብ ለመቋጠርም የልብስ መስቀያ ስለሚያስፈልገኝ ላምጣ… ታውቂያላሽ ኬቲ እጆቼ አሁን በደንብ አይሰሩም” አለ፡

ሁላችንም በጣም ከመድከማችን የተነሳ የምንንቀሳቀሰው የግዳችንን ነው::

አየት አደረገኝና “በእውነት አይጦቹ በጨውና በበርበሬ በጣም የሚጣፍጡ ይመስለኛል” አለ፡፡

ጭንቅላታቸውን ቆርጦ ቆዳቸውን ገፈፈና አንጀታቸውን አወጣው: ትንንሽ ሆዳቸውን በመሰንጠቅ ረጃጅምና ቀጫጭን አንጀቶቻቸውን እንዲሁም ትንንሽ
ልቦቻቸውንና ሌሎች የውስጥ እቃዎቻቸውን ሲያወጣ እየተመለከትኩት ነበር ሆዴ ባዶ ባይሆን ኖሮ ሊያስመልሰኝ ይችል ነበር።

ክሪስ ጨውና በርበሬ ሊያመጣ ሲሄድ አይኖቼ ቆዳቸው ተገፍፎ ለምግብነት የተዘጋጁት አይጦች ላይ ተተክለው ቀሩ። አይኖቼን ጨፍኜ የመጀመሪያውን
ጉርሻ ለመጉረስ ሞከርኩ እርቦኛል ግን ይህንን ለመብላት የሚያክል አይደለም ረሀቤ።

ወዲያው እጅ ለእጅ ተያይዘው፣ ግንባራቸውን አጋጥመውና አይናቸውን ጨፍነው ጥጉ ላይ የተኙትን መንትዮች አሰብኩ በእናታችን ማህፀን ውስጥም እንደዚህ ተቃቅፈው የነበሩ ይመስለኛል: ምስኪን ልጆች! በአንድ ወቅት በጣም የሚወዷቸው እናትና አባት ነበሯቸው።

እነሱን በደህና መሬት ለማድረስና ከጎረቤት ምግብ ለማግኘት አይጦቹ ለእኔና ለክሪስ በቂ ጥንካሬ እንደሚሰጡን ተስፋ አድርገናል።

ክሪስ ቀስ እያለ ወደኛ ሲመለስ ሰማሁ። በሩ ላይ ቆም ብሎ አመነታ።ሽራፊ ፈገግታ እያሳየ ነው ሰማያዊ አይኖቹ ወደኔ እየተመለከቱ አንፀባረቁ።
በሁለት እጆቹ በደንብ የምናውቀውን ትልቅ የሽርሽር ቅርጫት ይዟል። ቅርጫቱ መክደን እስከሚያስቸግር ድረስ በምግብ ተሞልቷል ሁለት ትልልቅ
ፔርሙዞች አወጣ አንደኛው ውስጥ የአትክልት ሾርባ፣ ሌላኛው ውስጥ ወተት ነበረበት በማየው ነገር ግራ ተጋባሁ። እናታችን አምጥታልን ነው?
ከሆነ ታዲያ ለምን ወደታች እንድንሄድ አልጠራችንም? ለምንስ ደግሞ እኛን ፍለጋ ወደዚህ አልመጣችም?
👍252👏2
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


የመንግስተ ሰማያት ጣዕም

ክሪስ በቀስታና በጥንቃቄ እጁን ከእጁ ስር፣ እግሩን ከእግሩ ስር እያደረገ ወደ መሬት ወረደ እኔ ደግሞ ጣሪያው ጠርዝ ላይ በደረቴ ተኝቼ ወደታች ሲወርድ እያየሁ ነው እጁን አንስቶ ሲያውለበልብልኝ ጨረቃዋ ወጥታ ብሩህ ሆና እያበራች ነበር፡ እንድወርድ ምልክት እየሰጠኝ ነበር። ክሪስ
እንዴት እንደወረደ አይቻለሁ: ዥዋዥዌ ከመጫወት የተለየ አይደለም ብዬ
ለራሴ ነገርኩት። ቋጠሮዎቹ ትልልቅና ጠንካሮች ናቸው: በዚያ ላይ በበቂ ሁኔታ አራርቀን ነው የሰራናቸው አንድ ጊዜ ጣሪያውን ከለቀቅኩ በኋላ ወደ
ታች እንዳልመለከት አስጠንቅቆኛል መጀመሪያ አንደኛውን እግር ካሳረፍኩ
በኋላ በሌላኛው እግሬ የታችኛውን ቋጠሮ መፈለግ ላይ እንዳተኩር ነገረኝ።
እንዳለኝ እያደረግኩ ከአስር ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መሬት ላይ ከክሪስ አጠገብ ቆምኩ።

“ዋው!” አለ ወደሱ አስጠግቶ እያቀፈኝ ከእኔ በተሻለ አደረግሽው”

የፎክስወርዝ አዳራሽ የጓሮ አትክልት ቦታ ውስጥ ነን፡ ክፍሎቹ በሙሉ ጨለማ ውጧቸዋል። የሠራተኞቹ መኖሪያ መስኮቶች ሁሉ ደማቅ ቢጫ ናቸው፡ ዝቅ ባለ ድምፅ “በል መንገዱን ካወቅከው ወደ መዋኛው ምራኝ አልኩት:

በእርግጥም መንገዱን ያውቀዋል እናታችን እሷና ወንድሞቿ ከጓደኞቻቸው
ጋር እንዴት ተደብቀው ወደ ዋና እንደሚሄዱ ነግራናለች:
እጄን ይዞ በጣቶቻችን እየተራመድን ከትልቁ ቤት ወጣን በሞቃታማው
የበጋ ምሽት ውጪ መሬት ላይ መሆን ለየት ያለ ስሜት አለው መንትዮቹን ብቻቸውን የተቆለፈ ክፍል ውስጥ ትተናቸዋል፡ ትንሽዬዋን ድልድይ ስናቋርጥ አሁን ከፎክስወርዝ ግዛት ውጪ መሆናችንን ስላወቅን ደስታ ተሰማን:: ነፃ የሆንን መሰለን፡ ቢሆንም ማንም እንዳያየን ጥንቃቄ ማድረግ አለብን። ወደ ሜዳውና እናታችን ወደ ነገረችን ሀይቅ ሮጥን።

ጣሪያው ላይ ስንወጣ አራት ሰዓት ነበር: በዛፎች የተከበበውን ትንሽ የውሀ
አካል ስናገኝ አራት ሰዓት ተኩል ሆኖ ነበር። ሌሎች ሰዎች እዚያ ኖረው ምሽታችን ይበላሽብናል ብለን ፈርተን ነበር። ነገር ግን የሀይቁ ውሀ ፀጥ ያለና
በንፋስ እንኳን የማይንቀሳቀስና የሚዋኙም ሆኑ በጀልባ የሚቀዝፉ ሰዎች የሌሉበት ነበር።

በጨረቃ ብርሃን በኮከቦች በደመቀ ሰማይ ስር ሆኜ ሀይቁን እየተመለከትኩ እንደዚህ አይነት የሚያምር ውሀ አይቼ እንደማላውቅና እንደዚህ በሀሴት
የሞላኝ ምሽት ኖሮ እንደማያውቅ አሰብኩ።

“እርቃናችንን እንዋኛለን?” ሲል ክሪስ ለየት ባለ ሁኔታ እያየኝ ጠየቀኝ፡

“አይ የውስጥ ሱሪያችንን ለብሰን ነው የምንዋኘው” አልኩት።

ችግሩ አንድም የጡት መያዣ የሌለኝ መሆኑ ነበር። አሁን ግን እዚህ ደርሰናል: አጉል የሆነው የጨዋነት ጥያቄ በዚህ በጨረቃ ብርሀን በደመቀ ውሀ ከመደሰት አያስቆመኝም። ልብሴን አውልቄ የመርከብ ማቆሚያ ወደ
ሆነው ጥልቀት የሌለው ጥግ ጋ ሮጥኩ። ስደርስ ግን ውሀው እንደ በረዶ ይቀዘቅዝ ይሆናል ብዬ ስላሰብኩ በመጀመሪያ እግሬን ነከር አድርጌ አረጋገጥኩ እውነትም በጣም ቀዝቃዛ ነው! ክሪስን ሳየው ሰዓቱን ከእጁ ላይ ፈትቶ ወደጎን
በማስቀመጥ ወደ እኔ እየሮጠ መጣና ደፍሬ ወደ ውሀው ከመግባቴ በፊት ጀርባዬ ጋ ደርሶ ገፈተረኝ: ውሀው ውስጥ በደረቴ ወደቅኩና ሙሉ በሙሉ
ውሀ ውስጥ ጠለቅኩ።

ከውሀው ስወጣ እየተንቀጠቀጥኩ ነበር። ወደ ክሪስ ተመለከትኩ ከፍ ያለ ድንጋይ ላይ ቆሟል ክንዶቹን ወደ ላይ አነሳና ወደ ሀይቁ ተወርውሮ ገባ፡ በድንጋጤ አቃተትኩ። ውሀው በቂ ጥልቀት ያለው ባይሆንስ? መሬቱ
መትቶት አንገቱ ወይም ጀርባው ቢሰበርስ?

ክሪስ ወደ ላይ አልተንሳፈፈም: አምላኬ! ሞቷል ሰምጧል!

“ክሪስ!” እየጠራሁትና እያለቀስኩ ገብቶ ወደተሰወረበት ቦታ መዋኘት ጀመርኩ።

ድንገት የሆነ ነገር እግሬን ያዘኝ! ጮህኩና ወደ ውስጥ ገባሁ የጎተተኝ ክሪስ ነበር፡ በጥንካሬ እግሮቹን እያወራጨ ወደምንስቅበትና ውሀ ወደምንረጫጭበት ወጣን

“እዚያ የተረገመ የሚሞቅ ቤት ውስጥ ከመዘጋት ቅዝቃዜው አይሻልም? ሲል ጠየቀኝ፡ ልክ እንደ እብድ ዙሪያውን እየዞረ ሲጮህ ላየው ይህች ትንሽ ነፃነት እንደ ጠንካራ የወይን ጠጅ አናቱ ላይ ወጥታ ያሰከረችው ይመስል
ነበር። ዙሪያዬን እየዞረ ዋኘና እግሬን ይዞ ወደታች ሊጎትተኝ ሞከረ: አሁን
ግን አልቻለም:

ውሀ እየተረጫጨንና እየዘፈንን፣ ከዚያ ደግሞ አቅፎኝ ስንስቅና ስንጮ ነበር። ልክ እንደገና ልጆች የሆንን ይመስል ታገልን… አበድን ውሀ ውስጥ በጣም ጎበዝ ነው ልክ እንደ ዳንሰኛ: እየዋኘን እያለ በድንገት ደከመኝ::በጣም ከመድከሜ የተነሳ እንደ እርጥብ ፎጣ ሆኜ ነበር። ክሪስ በክንዱ ደግፎ ወደ ዳር እንድወጣ አገዘኝ።

ሁለታችንም ሀይቁ ዳር ላይ ያለው ሳር ላይ በጀርባችን ተጋድመን ማውራት ጀመርን።

“አንድ ጊዜ እንዋኝና ወደ መንትዮቹ እንመለስ” አለ ሁለታችንም
የሚያብረቀርቁና የሚጣቀሱ የሚመስሉት ኮከቦች ላይ አተኩረናል። ደስ የምትል ግማሽ ጨረቃ ደመናው ውስጥ ብቅ ጥልቅ እያለች ድብብቆሽ
የምትጫወት ትመስላለች፡ “ምናልባት ወደ ጣሪያው መውጣት ባንችልስ?” አልኩ

“እንችላለን፡ ምክንያቱም ማድረግ አለብን” ክሪስቶፈር ሁልጊዜ እንደሚቻል የሚያምን ልጅ ነው: ሰውነቱ በውሀ ረጥቦ፣ ፀጉሩ ግንባሩ ላይ ተጣብቆ አጠገቤ ተጋድሟል። አፍንጫው እንደ አባታችን አፍንጫ ቀጥ ያለ ነው: ከንፈሮቹ የሚያምር ቅርፅ አላቸው:: አገጩ አራት ማዕዘን ሲሆን ደረቱ መስፋት ጀምሯል። እያደገ ያለው ወንድነቱ በጠንካራ ጭኖቹ መሀል ማበጥ ጀምሯል። ስለ ወንዶች ሳስብ አንድ ነገር ይማርከኛል
ያም ጥሩ ቅርፅ ያላቸው ጭኖች ናቸው፡ ጥፋተኝነት ሳይሰማኝና ሳላፍር ቁንጅናውን በአይኖቼ ለመመገብ ባለመቻሌ አዝኜ ጭንቅላቴን አዞርኩ።

ፊቱን አዙሮ አይኖቼን ተመለከተ: እኔም አየሁት። ሌላ ቦታ መመልከት
የማንችል እስኪመስል ድረስ እይታዎቻችን ተቆላለፉ ለስላሳ የደቡብ ነፋስ ፀጉሬ ውስጥ እየተጫወተና ፊቴ ላይ ያለውን ውሀ
እያደረቀው ነው፡ ምሽቱ በጣም ጣፋጭና በጣም ደስ የሚል ቢሆንም ፍቅርን የመራብ ከፍተኛ ስሜት ውስጥ ባለ ዕድሜ ላይ ያለሁ በመሆኔ ብቻ ምንም
ምክንያት ሳይኖረኝ ማልቀስ ፈለግኩ: ከዚህ በፊት እዚህ የነበርኩ አይነት ስሜት ተሰማኝ፡ ከሀይቁ አጠገብ ሳሩ ላይ እንደተጋደምኩ እንግዳ የሆነ
ሀሳብ በመጀመሪያ እንደ ተሳዳጅ ወደዚህ ወደመጣንበትና ከማይፈልገን አለም ወደተሸሸግንበት ወደዚያ ምሽት መለሰኝ።

ክሪስ፣ አሁን አስራሰባት አመት ሊሆንህ ነው፣ አባቴ እናቴን በመጀመሪያ ሲያገኛት የነበረበት እድሜ ማለት ነው”

አንቺ ደግሞ አስራ አራት፤ ልክ በእሷ እድሜ” ድምፁ ጎርነን ብሎ ነበር።

መጀመሪያ እይታ በሚፈጠር ፍቅር ታምናለህ?”

“በዚህ ርዕስ ላይ ጠቢብ አይደለሁም ትምህርት ቤት እያለሁ፣ አመነታ አንዲት የምታምር ልጅ አይቼ ወዲያው ፍቅር ይዞኝ ነበር ስናወራ ግን የሆነች ደነዝ ነገር ሆና ሳገኛት ለሷ የነበረኝ ስሜት ጠፋ፡ ግን ውበቷ በሌሎች
ነገሮች ከተደገፈ በመጀመሪያ እይታም ፍቅር ሊይዘኝ ይችላል ብዬ አስባለሁ ነገር ግን እንደዚያ አይነት ፍቅር አካላዊ መሳሳብ ብቻ እንደሆነ አንብቤያለሁ።

“እኔስ ደነዝ እመስልሀለሁ?”

“በጭራሽ! እንደሆንሽ እንደማታስቢ ተስፋ አለኝ፡፡ ምክንያቱም አይደለሽም።ፈገግ ብሎ ፀጉሬን ሊነካ እጁን እየዘረጋ ችግሩ ካቲ፣ ብዙ ተሰጥኦዎች ስላሉሽ ሁሉንም መሆን ትፈልጊያለሽ ያ ደግሞ የማይቻል ነው:"

“ዘፋኝም ተዋናይም መሆን እንደምፈልግ እንዴት አወቅክ?”
👍332
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

አንድ ዝናባማ ከሰዓት

ሰማዩ ከብዶ ዝናቡ በጣም እየወረደ ነው: ክፍላችን ውስጥ ያሉ መብራቶች
ሁሉ በርተዋል፡ ቲቪውም እንደተለመደው ተከፍቷል። ክሪስ የመስኮቱን ከባባድ መጋረጃዎች በሁለት እጆቹ ከፈት አድርጎ ይዞ በመቆም ከሩቅ ትንሽ የአሻንጉሊት ባቡር መስሎ ሁልጊዜ አስር ሠዓት ገደማ አሳዛኝ ፊሽካውን እያሰማ የሚያልፈውን ባቡር ለማየት እየጠበቀ ነው:

በራሱ ዓለም ውስጥ ነው፧ እኔም በራሴ አለም ውስጥ እግሮቼን አጣምሬ እኔና
ኬሪ የምንጋራው አልጋ ላይ በመቀመጥ እናታችን ለመጨረሻ የመጣች ጊዜ
ካመጣችው መፅሄት ላይ ምስሎች እየመረጥኩ በውስጡ ያሉትን ፎቶግራፎች በጥንቃቄ እየቆረጥኩ የማልመውን አይነት በደስታ የምኖርበት ቤት፣ ሺ ሴቶችን በጎኑ የሚደርግ ሳይሆን እኔን ብቻ የሚወደኝ የምምኘውን አይነት ረጅም፣ ጠንካራ፣ ጥቁር ፀጉር ያለው ባል በማድረግ የቆራረጥኳቸውን የምስል ቁራጮች ሌላ መፅሀፍ ላይ እየለጠፍኩ ህይወቴን እየሳልኩ ነው።

ዳንሰኛ መሆን ሳቆም ባልና ልጆች ይኖሩኛል የማልመው አይነት ቤት ሲኖረኝ ደግሞ ከውድ ድንጋይ የተሰራ የመታጠቢያ ገንዳ ይኖረኛል ከዚያ ለውበት የሚሆኑ ዘይቶች አደርግበትና ማንም በሩን እያንኳኳ ፈጠን በይ
ሳይለኝ ከፈለግኩ ቀኑን ሙሉ ተዘፍዝፌ እውላለሁ። ከዚያ ቆዳዬ በጣም
ለስላሳና ምንም እንከን የሌለበት ጥርት ያለ ይሆንና ደስ የሚል ሽታ ያለው
የሽቶ ጠረን ይኖረኛል። ይሄ የበሰበሰ አሮጌ ደረቅ እንጨት ሽታና ጣሪያው
ስር ያለው ክፍል አቧራ ከነችግሮቹና አሮጌ እቃዎቹ ጋር እኛን ወጣቶቹን ልክ እንደዚህ አሮጌ ቤት ያለ ጠረን እንዲኖረን አድርጎናል

ክሪስ” አልኩት ጀርባው ላይ እያፈጠጥኩ። “አሁን ጠንካሮች ነን፤ ታዲያ
ለምንድነው እናታችን ተመልሳ እስክትመጣና ሽማግሌው እስኪሞት መጠበቅ ያለብን? ለምንድነው የማምለጫ መንገድ የማንፈልገው?” ቃል አልተነፈሰም። ግን እጆቹ የመጋረጃውን ጨርቅ ጨምድደው ሲይዙ ተመለከትኩ::

“ክሪስ...”

“ስለሱ ማውራት አልፈልግም” አለ በንዴት
“ስለመሄድ እያሰብክ ካልሆነ ታዲያ ለምንድነው እዚያ ቆመህ ባቡሩ እስኪያልፍ የምትጠብቀው?”

“ባቡሩን እየጠበቅኩ አይደለም! በቃ ዝም ብዬ ወደ ውጪ እየተመለከትኩ
ነው:”

በግንባሩ የመስኮቱን መስታወት ተደግፏል። ቅርብ ያለ ጎረቤት እንዲያየው የደፈረ ይመስላል

“ክሪስ ከመስኮቱ ዞር በል የሆነ ሰው ሊያይህ ይችላል”

“ማንም ቢያየኝ ግድ የለኝም!”

የመጀመሪያ ስሜቴ ወደሱ ሮጬ በክንዶቼ አቅፌ ከእናታችን ያጣቸውን
እነዚያን መሳሞች ለማካስ ፊቱን በሙሉ በሚሊየን በሚቆጠሩ መሳሞች
ማዳረስ ነበር እሷ እንደምታደርገው ጭንቅላቱን ደረቴ ላይ አስደግፌ ፀጉሩን እያሻሸሁ በፊት ወደነበረበት አይነት ደስተኛ፣ የሚናደድበት ቀን የሌለው፣ መልካም ነገር ብቻ የሚመለከት ሰው ወደመሆኑ ልመልሰው ፈለግኩ። ነገር ግን በፊት እናታችን ታደርግለት የነበረውን ነገር ሁሉ ባደርግለትም ተመሳሳይ
እንደማይሆን አውቅ ነበር፡ እሷን ነው የሚፈልገው: ተስፋዎቹ፣ ህልሞቹና
እምነቱ በሙሉ በአንዲት ሴት ውስጥ ታሽጓል በእናታችን፡፡

አሁን ከመጣች ሁለት ወር አልፏታል! እዚህ ቤት የምናሳልፈው አንድ ቀን በትክክለኛው ህይወት ሲለካ ከወር በላይ እንደሚረዝም አልገባትም
ስለኛ አትጨነቅም? እንዴት እንደምንኖር አታስብም? ያለምንም ማብራሪያ፣
ምክንያት ወይም ሰበብ ስትተወን እያየ ክሪስ ሁልጊዜ የሷ ቀንደኛ ደጋፊ
እንደሚሆን ታምናለች? ፍቅር በጥርጣሬና በፍርሀት በአንድ ጊዜ ሊፈርስ
እንደሚችልና በፍፁም ዳግመኛ ሊገነባ እንደማይችል አታውቅም?

"ካቲ” አለ ክሪስ ድንገት “የሆነ ቦታ የመሄድ ምርጫ ቢኖርሽ የት ትሄጃለሽ?

“ደቡብ” አልኩ “የሚሞቅና ፀሀያማ የባህር ዳርቻ ወዳለው… ሞገዶች ለስላሳ
ወደሆኑበትና ሀይለኛ ነፋስ ወደማይነፍስበት መሄድ እፈልጋለሁ በነጭ አሸዋ ላይ ጋደም ብዬ የፀሀይ ብርሃኔን እየጠጣሁ ለስለስ ያለ ንፋስ ፀጉሬ ውስጥና ጉንጮቼ ላይ ሲንሸራሸር መስማት ነው የምፈልገው”

“ልክ ነው…” ተስማማ፡ “የገለፅሽበት መንገድ አሪፍ ይመስላል እኔ ግን ልክ
እንደ በረዶ ሸርተቴ ሁሉ በሀይለኛ ሞገድ ውስጥ መንሳፈፍም እወዳለሁ።”

ምስሎቹን እየቆራረጥኩ የነበርኩበትን መቀስና መፅሄቱን አስቀምጬ ሙሉ
በሙሉ ክሪስ ላይ ትኩረት አደረግኩ፡ ክሪስ የሚወዳቸውን ብዙ ስፖርቶች አጥቶ፣ በአንድ ክፍል ውስጥ ታሽጎ፣ ከእድሜው በላይ አርጅቶና አዝኖ ስመለከተው ላፅናናው ብፈልግም እንዴት እንደማፅናናው ግን አላወቅኩም።

ክሪስ እባክህ ከመስኮቱ ጋ ተመለስ?” አልኩት።

“ተይኝ! ይሄ ቦታ እጅግ ሰልችቶኛል ይህንን አታድርግ፣ ያንን አታድርግ፣
ካላናገሩህ እንዳትናገር መባል፤ በየቀኑ እነዚህን በደንብ በደንብ የማይሰሩ ጣዕም አልባ ምግቦች መብላት ታክቶኛል
በምግብም እንኳን እንዳንደሰት ሆነ ብላ ነው እንደዛ የምታደርገው: ስለዛ
ሁሉ ገንዘብ ሳስብ ደግሞ ግማሹ የእናታችንና የእኛ በመሆኑ እንደሚገባን
አስባለሁ። ያ ሽማግሌ መቼም ለዘላለም መኖር አይችልም:"

“በዓለም ላይ ያለ ገንዘብ ሁሉ ቢደመር ያጣናቸውን የመኖሪያ ቀኖች ያህል
ዋጋ የለውም!” በቁጣ መለስኩለት ወደኔ ዞር አለ፤ ፊቱ ቀልቷል። “ምናልባት
አንቺ በተሰጥኦሽ ገንዘብ ታገኚ ይሆናል እኔ ግን ከፊት ለፊቴ የብዙ አመታት
ትምህርት ይጠብቀኛል፡ አባታችን ዶክተር እንድሆን ይጠብቅ እንደነበረ ታውቂያለሽ፡ እንደምንም ብዬ ያንን ማሳካት አለብኝ፡፡ ከዚህ ከኮበለልን ግን
መቼም ዶክተር መሆን አልችልም: አንቺንና መንትዮቹን እንዲሁም ራሴን
ማኖር ይኖርብኛል። እስቲ እኛን ለማኖር ልሰራ የምችላቸውን ስራዎች
ንገሪኝ… ፍጠኚ! ሳህን አጣቢ ወይም ፍራፍሬ ለቃሚ ሌላ ምን መሆን
እችላለሁ? እነዚህ ስራዎችስ የህክምና ትምህርት ቤት ያስገቡኛል?”

የነደደ ቁጣ ሞላኝ፡ እኔ ላደርገው ስለምችለው አስተዋፅኦ ትንሽ እንኳን
ዋጋ አልሰጠውም: “እኔም መስራት እችላለሁ!” አልኩት። “ሁለታችን
ሆነን ማስተዳደር እንችላለን፡ ክሪስ የተራብን ጊዜ አራት የሞቱ አይጦች
ስታመጣልኝ፣ እግዚአብሔር በትልቅ መከራ ጊዜ ለሰዎች ተጨማሪ ጥንካሬና
ችሎታ ይሰጣል ብለኸኝ ነበር፡ እኔም እንደሚሰጥ አምናለሁ: ከዚህ ወጥተን በራሳችን መኖር ስንጀምር በአንድም በሌላም በኩል መንገዳችንን እናስተካክላለን፡ እናም ዶክተር ትሆናለህ! ያንን ዶክተር የሚለውን ማዕረግ
ከስምህ በፊት ለማየት የትኛውንም ነገር አደርጋለሁ፡”

“ምን መስራት ትችያለሽ?" በጥላቻና በመመረር አይነት ጠየቀኝ፡ መልስ መስጠት ከመቻሌ በፊት ከጀርባችን ያለው በር ተhፍቶ አያትየው በሩ ላይ ቆመችና ወደ ክፍሉ ሳትገባ ክሪስ ላይ አፈጠጠች: እሱ ደግሞ እንደበፊቱ ለመታዘዝ ፈቃደኛ ባለመሆን ግትርና እምቢተኛ ሆነና ከመስኮቱ ጋር ሳይንቀሳቀስ ፊቱን መልሶ እንደገና ዝናቡ ላይ ማፍጠጥ ቀጠለ።

“ልጅ!” ተጣራች። “ከመስኮቱ ጋር ዞር በል አሁኑኑ!

“ስሜ ልጅ አይደለም፧ ስሜ ክሪስቶፈር ነው በተሰጠኝ ስም ልትጠሪኝ ትችያለሽ ወይም ጭራሽ አለመጥራት ትችያለሽ ... ግን እንደገና ልጅ ብለሽ እንዳትጠሪኝ፡”
👍38😁2
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


በመጨሻ እኖታችን

እኔና ክሪስ በግርፋቱ ቀን በመሀከላችን ስለተፈጠረው ነገር በፍፁም አላወራንም
በአብዛኛው አተኩሮ ሲመለከተኝ እይዘዋለሁ፧ ግን አይኖቼ አይኖቹን ሲመለከቱ አይኖቹን ያሸሻል እኔም ሳየው ከያዘኝ አይኖቼን ወዲያው እመልሳለሁ።

እኔም እሱም በየቀ እያደግን ነው፡ ጡቶቼ ሙሉ ሆነዋል። ዳሌዬ ሰፋ ብሎ ወገቤ ቀጠን ብሏል ግንባሬ አካባቢ የተቆረጠው ፀጉሬ አድጎ ደስ በሚል አይነት ተጠቅልሏል። ክሪስ ደግሞ ትከሻው ሰፍቷል። ደረቱና ክንዶቹ የበለጠ ወንዳወንድ ሆነዋል አንድ ጊዜ ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ
ሆኖ የተገረመ በሚመስል አይነት ወንድነቱን ወደታች ሲመለከትና ሲለካው
ይዤዋለሁ። ርዝመቱ ምን ጥቅም እንዳለው ለማወቅ ስለጓጓሁ “ለምን?” ብዬ
ስጠይቀው አንድ ጊዜ አባታችንን እርቃኑን ሆኖ እንዳየውና አሁን ያየው
ነገር መጠኑ በቂ እንደማይመስል ነገረኝና ፊቱን አዞረ። ልክ እኔ እናታችን የምትለብሰው የጡት መያዣ መጠን ስንት እንደሆነ ማወቅ እንደምፈልገው ማለት ነበር። “እንደገና እንደዚያ እንዳታደርግ።" አልኩት። ኮሪ ያለው የወንድ አካል ትንሽ ስለሆነ ክሪስን ተመልክቶ ልክ እንደ ክሪስ መጠኑ ትንሽ ነው
የሚል ስሜት ቢሰማውስ?

ድንገት የመማሪያ ክፍሉን ወንበሮች ማፅዳቴን አቁሜ ወደ ኬሪና ኮሪ ተመለከትኩ፡ አምላኬ! በጣም መቀራረብ እንዴት እይታን እንደሚያደበዝዝ!
ሁለት አመት ከአራት ወር የተቆለፈብን ቢሆንም መንትዮቹ እዚህ የመጣን
ጊዜ ከነበሩት አልተለወጡም ጭንቅላታቸው ተለቅ ብሎ ስለሚታይ የአይኖቻቸው መጠን ያነሰ ይመስላል፡ ሰውነታቸው ጭንቅላታቸውን መሸከም
የሚችል አይመስልም ፍዝዝ ብለው ወደ መስኮቱ ያስጠጋነው አሮጌ ፍራሽ
ላይ ተቀምጠዋል እስኪተኙ ጠበቅኩና ቀስ ብዬ ለክሪስ “ተመልከታቸው ምንም አላደጉም: ጭንቅላታቸው ብቻ ነው ትልቅ የሆነው:” አልኩት።

በከባዱ ተነፈሰ፤ ከዚያ አይኖቹን አጥብቦ ወደ መንትዮቹ ቀረበና የገረጣውን ቆዳቸውን ለመንካት ዝቅ አለ፡ “ውጪ ጣሪያው ላይ ከእኛ ጋር ወጥተው ፀሀይና ንፁህ አየር ቢነካቸው ጥሩ ይሆን ነበር ካቲ፤ ምንም ያህል ቢጮሁና ቢንፈራገጡ ወደ ውጪ እንዲወጡ ማስገደድ አለብን” አለኝ።

እንቅልፍ ላይ እንዳሉ ተሸክመን ወደ ጣሪያው ብንወስዳቸውና ፀሀይ ላይ ሆነው እኛ እንዳቀፍናቸው ቢነቁ ደህንነት ይሰማቸዋል ብለን አሰብንና ክሪ ኮሪን በጥንቃቄ ሲያነሳ፣ እኔም ኬሪን ብድግ አደረግኳት ወደ ተከፈተው የጣሪያው ስር ክፍል መስኮት ቀረብን፡ የጣሪያውን የኋላ ክፍል መጠቀም የተሻለ ነው: ቀኑ ሀሙስ ስለሆነና ሰራተኞቹ ቀኑን ሙሉ ከተማ ስለሚውሉ ጣሪያው ላይ ወጥተን የምንዝናናበት ብቸኛው ቀን ነው።

ክሪስ ቀስ ብሎ ኮሪን እንደያዘ መስኮቱን አልፎ ሲወጣ የበጋ ፀሀይ ኮሪን
ከእንቅልፉ አነቃው ዙሪያውን ሲመለከት እኔም ኬሪን ተሸክሜ ጣሪያው ላይ
ልወጣ መሆኑን ሲመለከት ጮኸ! ኬሪ ከእንቅልፏ ባነነች። ክሪስ ኮሪን ይዞ
ጣሪያው ጫፍ ላይ ሆኖ እኔ ደግሞ የት እየወሰድኳት እንደሆነ ስትመለከት
ጩኸቷን አቀለጠችው።

ክሪስ ጣሪያው ጫፍ ላይ እንዳለ “አምጫት! ለራሳቸው ነው ይህንን ማድረግ አለብን:” አለኝ፡ መጮህ ብቻ አይደለም እየተራገጡና እየመቱን ነበር።ኬሪ ክንዴ ላይ ስትነክሰኝ እኔም ጮህኩ። በጣም ትንንሾች ቢሆኑም አደጋ ላይ እንደሆኑ በማሰባቸው በጣም በጥንካሬ እየታገሉን ነበር። ፊቴን አዙሬ ወደ መማሪያ ክፍሉ መስኮት አቀናሁና እየተንቀጠቀጥኩ ኬሪን በእግሮቿ አቆምኳት እኔም አየር አጥሮኝ እያለከለክኩ ወንበሩን ተደግፌ በሰላም ወደ ውስጥ እንድመልሳት ስላደረገኝ እግዚአብሔርን አመሰገንኩ። ክሪስም ኮሪን
እህቱ አጠገብ መለሰው፡ ሙከራችን ጥቅም አልነበረውም እነሱን ጣሪያው ላይ እንዲወጡ ማስገደድ የአራታችንንም ህይወት አደጋ ላይ መጣል ነው።

በጣም ስለተናደዱብን በመጀመሪያ ቀን ወደዚህ ክፍል ስንመጣ ቁመታቸውን
ወደ ለካንበት ግድግዳ ምልክት ስንወስዳቸው ሁሉ እየታገሉን ነበር ክሪስ
ሁለቱንም ቦታው ላይ አድርጎ ሲይዝልኝ እኔ ምን ያህል እንዳደጉ ለማንበብ
ሞከርኩ፡

ሊሆን መቻሉን ባለማመን በድንጋጤ አፈጠጥኩ: በዚህ ሁሉ ጊዜ የጨመሩት
ሁለት ኢንች ብቻ ነው? ሁለት ኢንች! እኔና ክሪስ ከአምስት እስከ ሰባት
አመት እድሜያችን መሀከል ብዙ በጣም ብዙ ነበር ያደግነው ሲወለዱም
ክብደታቸው ትንሽ የነበረ ቢሆንም የተሻለ ማደግ ነበረባቸው።

የደነገጠና የፈራ ገፅታዬን ማየት እንዳይችሉ በእጆቼ ፊቴን መሸፈን ነበረብኝ፡፡
ከዚያ ሳግ ጉሮሮዬን ሲይዘኝ ጀርባዬን ሰጥቻቸው ፊቴን አዞርኩ።

“አሁን እንዲሄዱ መልቀቅ ትችላለህ” አልኩት ዞር ብዬ ሳያቸው ልክ እንደ ሁለት አይጦች በደረጃው እየተንደረደሩ ወደ ተወዳጁ ቴሌቪዥን ሮጡ።

ክሪስ hጀርባዬ ቆሞ እየጠበቀ ነው: “ምን ያህል ቁመት ጨምረዋል?” አለኝ:

ፈጠን ብዬ እምባዬን በእጄ ጠራርጌ ወደ እሱ ዞርኩ ከዚያ አይኖቹን እየተመለከትኩ ሁለት ኢንች እንደሆነ ነገርኩት᎓ አይኖቼ ውስጥ ህመም ነበር።
እሱም ያየው ያንን ነበር:

ጠደ እኔ ተጠግቶ አቀፈኝና ጭንቅላቴን ወደ ደረቱ አስጠጋኝ፡ አለቀስኩ በጣም
አለቀስኩ ይህንን በማድረጓ እናታችንን ጠላኋት የእውነት ጠላኋት! ልጆች እንደ አትክልት እንደሆኑና ለማደግ የፀሀይ ብርሃን እንደሚያስፈልጋቸው
ታውቃለች በወንድሜ እቅፍ ውስጥ እንዳለሁ ተንቀጠቀጥኩ። ነፃ ስንሆን
እንደገና ቆንጆ እንደሚሆኑ ራሴን ለማሳመን እየሞከርኩ ነበር። ቆንጆ ይሆናሉ፤ ያጡትን አመታት ያካክሳሉ፡ ልክ የፀሀይ ብርሃን ማግኘት ሲጀምሩ እንደ አትክልት ያድጋሉ። አዎ ያድጋሉ፤ ጎንጮቻቸው በጣም የጎደጎዱት፣አይኖቻቸው ወደ ውስጥ የገቡት ረጅም ጊዜ ቤት ውስጥ ስለሚቀመጡ ነው እና ያ ሁሉ ሊስተካከል ይችላል፤ አይችልም?

ከዚያ በሻካራ ድምፅ “ገንዘብ ነው አለምን የሚያሽከረክራት ወይስ ፍቅር? ለመንትዮቹ በቂ ፍቅር ሰጥተናቸዋል እናም ስድስት፣ ሰባት፣ ምናልባትም ስምንት ኢንች ቁመት መጨመር ነበረባቸው: ሁለት ብቻ አልነበረም" አልኩ፡

እኔና ክሪስ ወደዛ ወደ ደብዛዛው እስር ቤታችን ተመለስንና እንደ ሁልጊዜው
እጆቻቸውን እንዲታጠቡ ላክናቸው የምግብ ጠረጴዛችን ጋ በፀጥታ ተቀምጠን ሳንድዊቻችንን እየበላንና ወተት እየጠጣን ቲቪ ስንመለከት የክፍላችን በር ተከፈተ: መዞር አልፈለኩም ነበር። ግን ዞርኩ:

እናታችን እየሳቀች ወደ ክፍሉ ገባች የሚያምር ልብስ ለብሳለች የለበሰችው
ጃኬት አንገቱና እጆቹ ላይ ፀጉር አለው: “ውዶቼ!” አለች በመጓጓት አይነት
ሰላምታ: ከዚያ አንዳችንም ሰላም ልንላት ባለመነሳታችን እያመነታችና እርግጠኛ ባልሆነ ስሜት “መጥቻለሁ! ስታዩኝ ደስ አላላችሁም? ስላየኋችሁ እንዴት ደስ እንዳለኝ አታውቁም በጣም ስናፍቃችሁ፣ ስለናንተ ሳስብና ሳልም ነበር፡ እና በጣም በጥንቃቄ የመረጥኳቸው የሚያምሩ ስጦታዎች አምጥቼላችኋለሁ: እስክታዩዋቸው ጠብቁ፡፡ ረጅም ጊዜ የጠፋሁበትን ማካካስ እፈልጋለሁ፡ ለምን እንደምሄድ ልነግራችሁ ፈልጌ ነበር፣ እውነቴን ነው፣
ግን በጣም የተወሳሰበ ነው: ለምን ያህል ጊዜ እንደምቆይ አላወቅኩም
ነበር። ናፍቃችሁኛል! በደንብ ተይዛችኋል አይደል? አልተሰቃያችሁም
ተሰቃይታችኋል እንዴ?”

ተሰቃይታችኋል? ናፍቃችሁኛል? እሷ ማናት? አፍጥጬ እያየኋትና አራት
የተደበቁ ልጆች የሌሎችን ህይወት እንዴት አስቸጋሪ እንደሚያደርጉ እየሰማሁ
መጥፎ ሀሳቦች መጡብኝ፡ ሁለተኛ በጭራሽ እንዳትጠጋኝ ላደርጋት ፈለግኩ።ከዚያ አቅማማሁ በተስፋ ተሞልቼ እንደገና ልወዳትና ላምናትም ፈለግኩ
👍42👎2
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ



...“ክሪስቶፈር” አልኩ እየጮህኩ፤ ራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም አንዳንድ ጊዜ እናቴን እጠላታለሁ! ያ ብቻ አይደለም አንዳንዴ አንተንም እጠላሀለሁ አንዳንዴ ሁሉንም ሰው በተለይ ራሴን እጠላዋለሁ! አንዳንዴ በሞትኩ ብዬ እመኛለሁ:
ምክንያቱም እዚህ ቦታ በቁም ከመቀበር መሞት ይሻላል! እኛ የበሰበሰ፣ የሚራመድ፣ የሚያወራ አትክልቶች ነን!...

ሚስጥራዊ ሀሳቦቼ በሙሉ ይፋ ወጡ፤ ልክ እንደ ቆሻሻ ተዘርግፈው ሁለቱንም
ወንድሞቼን አስደነገጣቸው፡ ትንሸዋ እህቴ ደግሞ መንቀጥቀጥ ጀምራ የበለጠ ትንሽ መሰለች እነዚያ ጨካኝ ቃላት ከአፌ እንደወጡ ወዲያውኑ እንዲመለሱ ፈለግኩ በእፍረት ሰመጥኩ፣ ይቅርታ መጠየቅና መመለስ አልቻልኩም።ዞርኩና እየሮጥኩ ወደ ልብስ ማስቀመጫው ከዚያ ወደ ደረጃዎቹ ከዚያ ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል ሄድኩ። ስጎዳ፣ ብዙ ጊዜም እጎዳለሁ ሙዚቃ ፈለግኩ፤ የዳንስ ልብሴን ለበስኩና ችግሮቼን ሁሉ ለመርሳት መደነስ ጀመርኩ።
እስኪደክመኝ ድረስ መደነስ ቀጠልኩ፡ ከዚያ ድንገት ሙዚቃው ሲያልቅ
ቀኝ እግሬ ታጠፈና ወለሉ ላይ ወደቅኩ። ለመነሳት ብታገልም መራመድ
አልቻልኩም: ጉልበቴን በጣም አሞኛል: ሌላ አይነት እምባ ወደ አይኖቼ
መጣ እየተጎተትኩ ወደ መማሪያው ክፍል ሄድኩኝ፡ ጉልበቴ ለዘለዓለም
ባይሰራም ግድ አልነበረኝም መስኮቱን በሰፊው ከፈትኩና ወደ ጥቁሩ ጣራ ወጣሁ። እያመመኝ መታጠፊያው ጫፍ ደረስኩና በውሀ መውረጃው አሸንዳ
ጠርዝ ላይ ስደርስ ቆምኩ። ታች ያለው መሬቱ ነው። ፊቴ ለራሱ የማዘን እምባና ህመም ምልክት አወጣ፣ እምባዬ እይታዬንም ብዥ አደረገው አይኖቼን ጨፍኜ ሚዛኔን ሳልጠብቅ መወዛወዝ ጀመርኩ፡ በደቂቃዎች ውስጥ
ሁሉም ያበቃል። እሾሀማ የፅጌረዳ ተክሎቹ ውስጥ እወድቃለሁ።

አያትየውና እናቴ አንዲት የማትታወቅ ደደብ ልጅ ጣሪያው ላይ ወጥታ
ድንገት ወደቀች ሊሉ ይችላሉ። እናቴ ሞቼና ተሰብሬ የሬሳ ሳጥን ውስጥ
ተጋድሜ ስትመለከት ታለቅስ ይሆናል። ከዚያ ያደረገችውን ታስታውስና
ክሪስንና መንትዮቹን ነፃ ለማድረግ በሩን ከፍታ እንደገና እውነተኛ ኑሮ
እንዲኖሩ ታደርግ ይሆናል።

ያ ራሴን የመግደሌ ወርቃማ ጎን ነበር።

ሌላኛውን ጎን ማየት አለብኝ: ካልሞትኩስ? ብወድቅና አወዳደቄ የሚገል ሳይሆን ቀርቶ ህይወቴን ሙሉ አካለ ጉዳተኛ ወይም ጠባሳ ቢያደርገኝስ? ከዚያ እንደገና ምናልባት ብሞትና እናታችን ባታለቅስ ወይም ባታዝን ወይም ባትፀፀትስ? እንዲያውም እንደኔ አይነቷን ተባይ በማስወገዷ ደስ
ቢላትስ? ክሪስና መንትዮቹ ያለ እኔ እንዴት ይሆናሉ? ማን ይንከባከባቸዋል?
ለመንትዮቹ ማን እናት ይሆናቸዋል?

ክሪስ ምናልባት አይፈልገኝ ይሆናል፤ የሚገዛለት ትልቁ ውዱ መፅሀፍ የኔን
ቦታ ይተካለት ይሆናል ከስሙ በፊት ዶክተር የሚለውን ማዕረግ ሲያገኝ
ህይወቱን ሙሉ ለመርካት በቂ ይሆንለት ይሆናል ግን ዶክተር ቢሆንም በቂ እንደማይሆን፣ እኔ ከሌለሁ በጭራሽ በቂ እንደማይሆን አውቃለሁ።ሁለቱንም ገፅ ለማየት ባለኝ ችሎታ ከሞት ተረፍኩ፡

ህፃንነትና ሞኝነት እየተሰማኝ ከጣሪያው ጠርዝ ስርቅ አሁንም እያለቅስኩ ነበር ጉልበቴ በጣም ስላመመኝ የጭስ መውጫው ጀርባ ጋ እስክደርስ ድረስ ጣሪያው ላይ ዳዴ እያልኩ እየሄድኩ ነበር። ሁለት ጣራዎች ተገናኝተው ምቹ ጥግ የፈጠሩበት ቦታ ነው: በጀርባዬ ተጋድሜ የማይታየውና ግድ
የሌለው ሰማይ ላይ አፈጠጥኩ። እግዚአብሔርም ሆነ መንግስተ ሰማያት
እዚያ መኖራቸውን ተጠራጠርኩ።

እግዚአብሔርና መንግስተ ሰማያት እዚሁ ምድር ላይ በአትክልት ስፍራዎቹ፣
በጫካዎቹ፣ በመናፈሻዎቹ፣ በባህር ዳርቻዎቹ፣ በሀይቆቹና በአውራ ጎዳናዎቹ ውስጥ ናቸው።

ሲኦልም እዚሁ ነው… እኔ ያለሁበት ያለማቋረጥ የከበበኝ ወደ እሱ ሊወስደኝ
የሚሞክርና አያትየው እንደምታስበው የሰይጣን ዘር ሊያደርገኝ የሚጥር
ነው።

ጨለማ እስኪሆን ድረስ እዚያ ጠንካራና ቀዝቃዛ ጣራ ላይ ተጋደምኩ።
ጨረቃ ወጣች፣ ኮከቦቹም ምን እንደሆንኩ እንደሚያውቁ ሁሉ በቁጣ እኔ ላይ አበሩ የለበስኩት የዳንስ ልብስ ብቻ ነበር ከብርዱ የተነሳ ክንዶቼ ላይ ሽፍ አለብኝ አሁንም በቀሌን እያቀድኩ ነው፡ ከመልካም ወደ ክፉ የለወጡኝንና
ከዚህ ቀን ጀምሮ የምሆነውን አይነት ሰው ያደረጉኝን እበቀላለሁ። አያቴና እናቴ በመዳፌ ስር የሚሆኑበት ቀን እንደሚመጣ ራሴን አሳመንኩት አለንጋ
እይዛለሁ፣ ሬንጁንም እይዛለሁ፣ የምግብ አሰጣጥም እቆጣጠራለሁ።

ምን እንደማደርጋቸው ለማሰብ እየሞከርኩ ነው:: ትክክለኛው ቅጣት
ምንድነው? ሁለቱንም ቆልፌባቸው ቁልፉን መወርወር? እኛ እንደተራብነው ማስራብ?

ለስላሳ ድምፅ ምሽቱንና የተጠላለፉ ሀሳቦቼን አቋረጠ። ክሪስ እያመነታ
ስሜን እየጠራ ነው: ምንም አልተናገረም ስሜን ብቻ ይጠራል: መልስ
አልሰጠሁትም አልፈልገውም፣ አሳፍሮኛል ማንንም አልፈልግም ባለ መረዳቱ አልፈልገውም።
የሆነው ሆኖ መጣና አጠገቤ ጋደም አለ። ምንም ቃል ሳይናገር ይዞት
የመጣውን ሞቃት የሱፍ ጃኬት ደረበልኝ፡ ልክ እንደ እኔ ወደ ቀዝቃዛውና
የተከለለው ሰማይ ላይ አፍጥጧል በመከላችን አስፈሪና ረጅም ፀጥታ
ነገሰ። ስለ ክሪስ የምጠላው ወይም የማልወደው ምንም ነገር የለም ወደ እሱ ዞሬ ይህንን ልነግረውና የሚሞቅ ጃኬት ስላመጣልኝ ላመሰግነው በጣም
ፈልጌያለሁ። ነገር ግን አንዲት ቃል መናገር አልቻልኩም: የሚሰማኝን
እሱና መንትዮቹ ላይ ስለተወጣሁት እንደተፀፀትኩ እንዲያውቅ ፈልጌ ነበር።ማንኛችንም ሌላ ጠላት እንደማያስፈልገን እግዚአብሔር ያውቃል በጃኬቱ ውስጥ ሆነው የሚንቀጠቀጡት ክንዶቼ አቅፈው ሊያፅናኑት ናፍቀዋል ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ ከቅዠቴ ስባንን የሚያባብለኝ እሱ ነው ነገር ግን ማድረግ የቻልኩት ብቸኛው ነገር፣ እዚያው ጋደም ብዬ በብዙ ነገሮች የተያዝኩ መሆኔን እንዲረዳ ተስፋ ማድረግ ብቻ ነበር።

ሁልጊዜ አስቀድሞ ነጭ ባንዲራ የሚያውለበልበው እሱ ነው፡ ለዚህም
ለዘለአለም አመስጋኝ ነኝ። እንግዳ በሆነ ጎርናና እና ውጥረት በሚሰማበት
ከሩቅ የሚመጣ በሚመስል ድምፅ፤ እሱና መንትዮቹ ራታቸውን እንደበሉና
ለእኔ ድርሻዬን እንዳስቀመጠልኝ ነገረኝ፡ “እና ከረሜላዎቹን ሁሉ በላናቸው ያልነው እያስመሰልን ነው ካቲ ለአንቺ ብዙ ተቀምጦልሻል” አለኝ።

ከረሜላ? ስለ ከረሜላ ያወራል፤ አሁንም ከረሜላ የእምባ ማበሻ በሆነበት
የልጆች አለም ውስጥ ነው? እኔ አድጌ ለልጆች መደሰቻ ጉጉት አጥቼያለሁ።
የምፈልገው ሌሎች በእኔ እድሜ ያሉ ልጆች የሚፈልጉትን ነው፤ የምፈልገው ወደ ሙሉ ሴትነት ማደግ የምችልበትን ነፃነት ነው፤ ህይወቴን በሙሉ የምቆጣጠርበትን ነፃነት ነው፡፡ ይህንን ልነግረው ስሞክር ድምፄ ልክ እንደ እምባዬ ደረቀብኝ
ካቲ ያልሺው ነገር... ሁለተኛ አስቀያሚና እንደዚያ አይነት ተስፋ ቢስ ነገሮች አትናገሪ” አለኝ፡

“ለምን?” ተናነቀኝ “የተናገርኩት እያንዳንዱ ቃል እውነት ነው፡ የተናገርኩት በውስጤ የሚሰማኝን ነው ያወጣሁት አንተ በውስጥህ የቀበርከውን ነው
ከራስህ መደበቅህን ቀጥልበት እነዚያ እውነታዎች ወደ አሲድነት ተቀይረው ውስጥህን ሲበሉት ታገኛቸዋለህ!” “አንድ ጊዜም መሞት ተመኝቼ አላውቅም”
👍46🥰31
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


የእናታችን ድንገተኛ ዜና

እናታችን እንደገና ልታየን ከመምጣቷ በፊት ባለፉት በእያንዳንዱ አስር ቀናት
ውስጥ፣ እኔና ክሪስ ለምን አውሮፓ ሄዳ እንደቆየችና ከሁሉም በላይ ደግሞ
ልትነግረን የነበረው ትልቅ ዜና ምን እንደሆነ ለመገመት ለሰአታት እናወራ
ነበር።

አስሩን ቀናት እንደ ሌላ ቅጣት አሰብነው ቅጣትም ነበረ: እዚህ አንድ ቤት
ውስጥ ሆነን ልክ ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ያለን አይጦች እንደሆንን ሁሉ
ችላ ልትለንና ልትዘጋን ችላለች:

ስለዚህ ያን ያህል ቆይታ ስትመጣ እኔና ክሪስ በደንብ ስለተቀጣን የጥላቻ
ወይም የመውጣት ጥያቄያችንን ከደገምን ተመልሳ ላትመጣ ትችላለች ብለን በጣም በመፍራት ፀጥ ብለን እጣ ፈንታችንን ተቀበልን፡ ተመልሳ ካልመጣች ምን እናደርጋለን? መንትዮቹ ገና ጣሪያው ላይ ሲደርሱ ብርክ ከያዛቸው ከተተለተለ አንሶላ በሰራነው መሰላል ተጠቅመን ማምለጥ የማይታሰብ ነው።

ስለዚህ ለእናታችን ፈገግ አልንላት አንድም የማማረር ቃል አላሰማንም
ለወራት ጠፍታ ስለምታውቅ አስር ቀናት በመቆየት ለምን እንደቀጣችን
አልጠየቅናትም፡ ልትሰጠን የፈቀደችውን ተቀበልን፡ ከአባቷ ጋር ለመሆን
እንደተማረችው አይነት ታዛዥ የማይቃወሙ ቅን ልጆች ሆንን የሚገርመው እንዲህ መሆናችንን መውደዷ ነው: እንደገና የሷ ጣፋጭ አፍቃሪና ሚስጥራዊ “ውዶች” ሆንን።

አሁን በጣም ጥሩ፣ አስደሳች፣ ለእሷ አድናቆት ያለን፣ አክባሪና በእሷ
የምንተማመን መሆኑን ስታውቅ ጊዜውን ቦምቧን ለመጣል መረጠችው።
“ውዶቼ፣ ለእኔ ደስ ይበላችሁ! በጣም ደስ ብሎኛል!” እየሳቀች እጆቿን ደረቷ ላይ አድርጋ በክብ ተሽከረከረች: “ምን እንደተከሰተ ገምቱ ቀጥሉ… ገምቱ!” አለችን።

እኔና ክሪስ ተያየን “አያታችን ሞተ!” አለ። ልቤ ደስ የሚለውን ዜና ስትነግረን
ለመዝለልና ለመቦረቅ በመዘጋጀት በጣም እየደለቀ ነው።

“አይደለም!” አለች በድንገት ደስታዋ በጥቂቱ የደበዘዘ ይመስላል።

“ወደ ሆስፒታል ተወሰደ?” ብዬ ሁለተኛውን ምርጥ ግምት አቀረብኩ።
“አይደለም: አሁን አልጠላውም፧ ስለዚህ እናንተ ጋ መጥቼ በሞቱ መደሰቴን ልነግራችሁ አልችልም:”

“ታዲያ ለምን መልካም ዜናውን ራስሽ አትነግሪንም? ስለ ህይወትሽ ብዙም
ስለማናውቅም መገመት አልቻልንም” አልኳት።

ማለት የፈለግኩትን ችላ ብላ ቀጠለች፤ “ለረጅም ጊዜ የጠፋሁበትን ለመግለፅ አስቸጋሪ ሆኖብኝ የነበረው ምክንያት ባርት ዊንስሎ የተባለ ሰው ማግባቴ ነው። ጠበቃና በጣም ጥሩ ሰው ነው። ትወዱታላችሁ። እሱም ሁላችሁንም ይወዳችኋል። ጥቁር ፀጉር ያለው፣ በጣም መልከመልካም፣ ረጅምና የሚያምር ሰውነት ያለው ነው። ክሪስቶፈር፣ ልክ እንዳንተ የበረዶ ሸርታቴ ይወዳል፧ ቴኒስ ይጫወታል፤ ልክ እንዳንተ ጎበዝ ነው” ይህንን ስትናገር ወደ ክሪስ
እየተመለከተች ነበር።

በጣም ደስ የሚል ሰው ነው ሁሉም ይወዱታል። አባቴም ሳይቀር ይወደዋል
ወደ አውሮፓ የሄድኩት ለጫጉላ ሽርሽር ነበር። ያመጣሁላችሁ ስጦታዎች
ከእንግሊዝ፣ ከፈረንሳይ፣ ከስፔንና ከጣልያን የተገዙ ናቸው:” እኔና ክሪስ
በፀጥታ ተቀምጠን፡ ስለ አዲሱ ባሏ የምታወራውን እየሰማን ነበር።

እኔና ክሪስ ከገና በአል ግብዣ ምሽት ጀምሮ ብዙ ጊዜ ጥርጣሬዎቻችንን
አውርተናል: ልጆች ብንሆንም፣ እንደ እናታችን ያለች ወንዶች የምትፈልግ
ቆንጆ ወጣት ሴት ለረጅም ጊዜ ካለ ባል እንደማትቆይ እናውቅ ነበር። ሰርግ
ሳይደረግ ሁለት አመት ሲያልፍ ግን ያ ትልቅ ፂም ያለው መልከመልካም
ባለ ጥቁር ፀጉር ሰው ለእናታችን ብዙም አስፈላጊ ነው ብለን አላሰብንም
ነበር። በየዋሁ ልባችን እናታችን ለሞተው አባታችን አሁንም ታማኝ እንደሆነች ራሳችንን አሳምነን ነበር። ባለወርቃማ ፀጉር፣ ሰማያዊ አይኖች ያሉት አማልክትን የመሰለ የቅርብ ዝምድና እያላቸው እንኳን እሱን ለማግባት ከምክንያት ባሻገር ላፈቀረችው አባታችን ታማኝ ናት ብለን እናስብ ነበር::

የአባታችንን ቦታ ስለሚወስድ ሌላ ሰው ስትነግረን በጥላቻ የተሞላ ድምፅዋን ላለመስማት በመሞhር አይኖቼን ጨፍኜ ነበር: አሁን የሌላ ሰው ሚስት ናት ሙሉ በሙሉ የተለየ ሰው ሚስት ሆናለች: አሁን አልጋዋ ውስጥ
ይገባል፣ ከእሷ ጋር ይተኛል: እንግዲህ ከዚህ በኋላ ከምናገኛት ያነሰ ጊዜ
ነው የምትመጣው ማለት ነው: አምላኬ፣ እዚህ የምንቆየው ለምን ያህል ጊዜ ይሆን? ለምን ያህል?

ዜናዋና ድምፅዋ በደረቴ አጥንቶች ውስጥ የተያዘችና ልውጣ ልውጣ የምትል ትንሽ የፍርሀት ወፍ ፈጠረ።

“እባካችሁ…” ለመነችን፡ ፈገግታዋና ሳቋ ሀሴትና ደስታዋ እኛ ዜናውን
ባስተናገድንበት ቀፋፊና የተበላሽ አየር ላይ ለመቆየት እየታገሉ ነው::
“ለመረዳት ሞክሩና ለእኔ ደስ ይበላችሁ አባታችሁን እወደው እንደነበር
ታውቃላችሁ ግን እሱ ሞቷል። ከሞተ ረጅም ጊዜው ነው እና የምወደውና
የሚወደኝ ሰው ያስፈልገኛል።”

ክሪስ እንደሚወዳት፣ ሁላችንም እንደምንወዳት ለመናገር አፉን ከፈተ። ነገር
ግን ይህ ከልጆቿ የምታገኘው ፍቅር፣ እሷ የምታወራው አይነት ፍቅር
እንዳልሆነ ስለገባው ከንፈሮቹን ገጠመ እኔ ከአሁን በኋላ አልወዳትም።
ከዚህ በኋላ ትንሽ የመውደድ ስሜትም ለእሷ እንደሚኖረኝ እንኳን እርግጠኛ አይደለሁም: ግን መንትዮቹ በሁኔታዬ እንዳይደነግጡ መሳቅና ማስመሰል እንዲሁም ከአንገት በላይ መሆን እችላለሁ፡ “አዎ እማዬ፣ ለአንቺ ደስ ብሎኛል እንደገና የሚወድሽ ሰው ማግኘትሽ ጥሩ ነው።”

“ለረጅም ጊዜ ይወደኝ ነበር ካቲ፣” ተበረታታችና እንደገና በራስ በመተማመን
ፈገግ እያለች ቀጠለች “ወንደላጤ ሆኖ ለመቆየት ወስኖ ስለነበር ሚስት
እንደሚያስፈልገው ለማሳመን ቀላል አልነበረም: አያታችሁ ደግሞ በፊት
አባታችሁን በማግባት ለሰራሁት ኃጢአት ቅጣት እንዲሆን ሁለተኛ ጊዜ
እንዳገባ አልፈለገም ነበር። ግን ባርትን ይወደዋል፤ ብዙ ስለምነው ቆይቼ
በመጨረሻ እሺ አለኝ ባርትን ማግባትና ሀብቱንም መውረስ እንድችል
ፈቀደ” ንግግሯን ቆም አደረገችና የታችኛውን ከንፈሯን መብላት ጀመረች።
እንደገና ደግሞ በጭንቀት ተዋጠች ቀለበት ያጠለቀችበት ጣቷ ወደ ጉሮሮዋ ሄደና አንገቷ ላይ ያንጠለጠለችውን ጌጥ በጭንቀት ያፍተለትል ጀመር።“በእርግጥ አባታችሁን የምወደውን ያህል ባርትን አልወደውም” አለች።
የበራው ፊቷ አሁን ያላት ፍቅር በፊት ከምታውቀው እጅግ የበለጠ እንደሆነ
እያጋለጣት ነበር በረጅም ተነፈስኩ: ምስኪን አባቴ!

“ያመጣሽልን ስጦታዎች... ሁሉም ከአውሮፓ፣ ወይም ከእንግሊዝ ደሴቶች
አይደሉም: የስኳር ከረሜላው የመጣው ከቬርሞንት ነው: ቬርሞንትም ሄደሽ ነበር? እሱም ከዚያ ነው የመጣው?”

ልክ ቬርሞንት ብዙ ነገር የሰጣት ይመስል በደስታ ሳቀች። “አይ፣ እሱ የመጣው ከቬርሞንት አይደለም ካቲ፤ ግን እዚያ የምትኖር እህት አለችው ከአውሮፓ ከመጣን በኋላ በሳምንቱ መጨረሻ ልንጠይቃት ሄደን ነበር የስኳር ከረሜላ
ምን ያህል እንደምትወጂ ስለማውቅ ከዛ ነው ያመጣሁልሽ። ደቡብ የሚኖሩ ሌሎች ሁለት እህቶችም አሉት: ደቡብ ካሮላይና ውስጥ ካለች ግሪንግሌና ግሪንግሌና ወይም እንደዚያ አይነት ስም ካላት ከተማ ነው የመጣው: ግን በኒው ኢንግላንድ ብዙ ቆይቷል: የተመረቀው ከሀርቫርድ የህግ ትምህርት
👍393😁2