አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


...«አስቻለው የሔዋን አባት መሆኑን ማን ነገረሽ አንቺ?» ስትል ጠየቀቻት።
«ነዋ! እንዴ ሆእ!» አለች ሕጻኗ አሁንም፡፡
ሸዋዬ የበለጠ ግራ ገባት፡፡ ህጻኗ ያለ አንድ መነሻ ያን ንግግር
እንዳልተናገረች ገመተች፡፡ ወይዘሮ ዘነቡንና ሰራተኛ'ቸውን አስበቻቸው፡፡ ለጊዜው
ግን «እንዴ! እንዴ.! እንዴ.! እያለች ቤቷን ከፍታ ገባች። አልጋዋ ላይ ቁጭ አለችና
«እንዴት ነው ይኸ ነገር? በማለት ቁና ቁና እየተነፈሰች ለረጂም ጊዜ ቆየች።
ሔዋን የገዛቻቸውን የወጥ ቅመማ ቅመሞች በዘንቢል ይዛ ወደ ቤት ስትገባ የሽዋዬ ዓይን ፈጥጦ አገኘችው፡፡ ሁኔታዋ አላማራትም'ና
«እት አበባ አለቻት ዘንቢሏን እንደያዘች ከፊቷ በመቆም። ሸዋዬ ግን ገልመጥጥ ከማድረግ በቀር ምላሽ ሳትሰጣት ቀረች::
«ምነው?» አለቻት ሔዋን አሁንም፡፡
«አትተይኝም? አለቻት ሽዋዬ ቁጣ በተቀላቀለበት አነጋገር፡፡ ወዲያው ወደ አልጋዋ በመውጣት አንሶላና ብርድ ልብስ ውስጥ ገብታ ሽፍንፍን ብላ ተኛች።
ሔዋን የእህቷ ሀኔታ ግራ አጋባት፡፡ በዚያው ልክ ፈራች፡፡ ድንጋጤም
ተሰማት፡፡ ወደ ጓዳ ገብታ ዘንቢሏን ከአስቀመጠች በኃላ ጓዳው በር በኩል አንገቷን ብቅ እያረገች የሸዋዬን ሁኒታ ትከታተል ጀመር፡፡ አይታ አይታ ምንም ለውጥ
ልታገኝ ባለመቻሏ የምሣሤ ወጥ ስራዋን ጀመረች፡፡
ሽዋዬ ከተኛች ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀስቀስ ያለችው የወይዘሮ ዘነቡ የቀትር ቡና ሲወቀጥ ነው፡፡

ወትሮም ቢሆን በተለይ ቅዳሜና እሁድ ከምሳ በኋላ ለሚጠጣው ቡና ሽዋዬ ወደ ወይዘሮ ዘነቡ ቤት ትጠራ ነበር፡፡ ዛሬ ግን ገና ሳትጠራ ለመሄድ ብድግ አለች፡፡ ያቺ ህጻን በዚያ ቤት ውስጥ ሲወራ ያልሰማችውን ነገር
ከየትም ከምጥታ ልትነግራት እንዳልቻለች ገምታ የወሬዉን ምንጭ ከስሩ ለመጎርጎር ወስነኝ፡፡ ፒጃማ ዓይነት ጀወለል ቢጤ የቤት ልብስ እንደለበሰች ነጠላ
ጫማ አድርጋ ወደዚያው አመራች በጓሮ በኩል ወደ ሳሎን በሚያስገባው የወይዘሮ
ዘነቡ ቤት በር በኩል እየገባች፡-
ደህና ዋላችሁ» አላቻቸው፡፡
ወይዘሮ ዘነቡ ነጭ በነጭ የሆነ የሐገር ልብሳቸውን ለብሰው ሶፋ ላይ ጉብ ተብለዋል ፡፡ ቀይ ናቸው:: የአንገታቸው ንቅሳት ከቅላታቸው ጋር አለላ መስሎ ይታያል። የአገጭ ስር ጅማቶቻቸው ገተር ገተር ማለት የዕድሜያቸውን መግፋት ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ጥቁር መነፅራቸው ከቀይ ፊታቸው ጋር ደምቆ ሲታይ ዕድሜያቸውን ወደ ኋላ ለመመለስ የሚታገል ይመስላል፡፡ ኑሮአቸውን የቤታቸው
ሁኔታ ያመለክታል፡፡ በዘመናዊ ዕቃ የተሞላ ነው። የሳሎኑ ስፋት ፈረስ ያስጋልባል የሚባል ዓይነት ነው፡፡ በቡና ንግድ የናጠጡ ሀብታም የነበሩት ሟቹ ባለቤታቸው
ያደራጁላቸው ንብረት ነው።
‹ደህና ዋልሽ የኔ ልጅ!» አሉና ወይዘሮ ዘነቡ «ይኸውልሽ፣ የጎረቤት ደንቡ ይኸ ነው፡፡ ጥሪ የሚፈልግ ከሆነ ግን ንፉግነቱን ያመለክታል፡፡» እሷት ሸዋዬ
ሳትጠራ በመምጣቷ የተሰማቸውን ደስታ ለመግለጽ::
«አንዳንዴም ቀላዋጭ ያሰኛል!»
«እሱም የስስታም ሰው አባባል ነው፡፡ በእኛ ቤት ደሞ እንደዚያ ብሎ ነገር የለም፡፡ ለወደፊቱም ይልመድብሽ፡፡» ብለው ፊታቸውን ከሶፋው አጠገብ በነጭ ረኮበት ላይ ወደ ተደረደረው ሲኒ መለስ አደረጉ ሰራተኛቸው ፋንትዩ ቡናውን ጀበና ውስጥ እየጨመረት ናት፡፡
ጉዳይ ስላለኝም ነው ቀድም ብዬ የመጣሁት፡፡» አለች ሽዋዩ በወይዘሮ ዘነቡ ፊትለፊት ሶፋ ላይ ተቀምጣ ዓይን ዓይናቸውን እያየች፡፡
"ምነው" ድህና አሏት ወይዘሮ ዘነቡ ፊታቸውን ወደ ሽዋዩ መለስ
አድርገው
«ተቀይሜብዎታለሁ::»
«ውይ ነኔ ልጅ!ድንግል ትባርክሽ ቅያሜሽን ፊት ለፊት ተነገርሽኝማ
ድንግልም ትወድሻለች፡፡» አሉና «ግን ሳላውቅ ምን እጥፍቼ ይሆን ሲሉ አንገታቸውን ዘመም አድርገው እያዩ ጠየቋት።
«አንድ ነገር እያወቁ ደብቀውኛል።»
«ምን ይሆን የኔ ልጅ»
«በኔ ሰበብ ግቢዎት ሲደፈር እያዩ ዝም ማለትዎ!»
«ምን ያገባው ሰው ነው ግቢዩን የሚደፍረው?»
ብልግና ከተፈጸመበት ያው ተደፈረ ማለት አይደል?»
«የምን ብልግና?»
«አይዋሹኝ እማማ ዘነቡ!»
«ድንግል ትመስክር ምንም የምዋሽው ነገር የለም፡፡ ከንቺ ግን ምን ሰምተሸ ነው?» ሲሉ መነፅራቸውን ወለቅ አድርገው እያዩ ጠየቋት::
«ይቺ የኔ እህት ከዚያ አስቻለው ከሚባል ልጅ ጋር እየባለገች መሆኑን ሳያውቁ ቀርተው ነው?» ስትል ጠየቀቻቸው አንገቷን ጠመም አድርጋ በጎ አስተያየት እየተመለከተቻቸው::
«ውይ! ይኼ ነው እንዴ ነገሩ?» አሉና ወይዘሮ ዘነቡ ቀለል አድርገው
«ለመሆኑ አንቺ እስተ ዛሬ ምንም የምታውቂው ነገር አልነበረም?» ሲሉ ጠየቋት፡፡

«ምኑን?» አለች ሸዋዬ እንደ አዲስ፡፡ ነገሩ እርግጥ መሆኑ ሲገባት በድንጋጤ ሰውነቷ ሁሉ ክፍልፍል ያለ መሰላት።
«ስለ ሁለቱ ልጆች ፍቅር ነዋ!»
ምናልባት እኩያሞች ስለሆኑ ነው መሰል የእነሱን ፍቅር ልቤ
ይወደዋል፡፡»
«እማማ ዘነቡ!» ስትል ጮኸች ሸዋዬ ድንገት። ዓይኗ በወይዘሮ ዘነቡ ላይ ፍጥጥ አለና መላ ሰውነቷንም ያንቀጠቀጣት ጀመር።
«ወይ የኔ ልጅ!»
«ምን እያወሩ እንደሆነ ያውቃሉ?»
«ዘባርቄ ይሆን እንዴ ልጄን» አሉና ወይዘሮ ዘነቡ እውነትም ድንግጥ
ብለው ሽዋዬን ትኩር ብለው ያዩዋት ጀመር።
«ቀላል!»
«ምን አልኩኝ?»
«ሊያጋቧቸው እስበዋል እንዴ?»
«ኧረ ምን ቁርጥ አድርጎኝ ልጄ! ቢሆን አይከፋም ማለቴ ነው
እንጂ!»
ሸዋዬ ውስጧ ተቃጠለ፡፡ አረረች። በወይዘሮ ዘነቡ ሀሳብ ከመበሳጨቷ የተነሳ ያን ከሰል ላይ የተጣደ ጀበና ብድግ አድርጋ በመሀል እናታቸው ላይ
ብትከስክሰው እየተመኘች «የሚሉት ነገር ሁሉ ሊገባኝ አልቻለም!» አለቻቸው
ዓይኗን ፍጥጥ፣ ጥርሷን ግጥጥ አድርጋ እያየቻቸው፡፡
ግልጥልጥ አድርጌ እየነገርኩሽ! እንዴት እይገባሽም?» አሏት የሸዋዬ የወስጥ ስሜት ያልገባቸው ወይዘሮ ዘነቡ፡፡
«ቆይ ግን አለችና ሸዋዪ ንዴት ያወላከፈውን ጉሮሮዋን «እህህ» ብላ ሞረደችና የሁለቱን መፋቀር እንዴት አወቁ?» ስትል ጠየቀቻቸው፡፡
«ድንግል ምስክሬ ናት፤ በበኩሌ ክርና መርፌ ሆንሁ በዓይኔ አላየሁም፡፡ ግን መቸም ትንሽ ሳይያዝ ብዙ አይወራም ብዬ ነው፡፡» ብለው ፊታቸውን ወደ
ረከቦቱ መለስ አደረጉ፡፡
ወይዘሮ ዘነቡ አንድ ነገር በሆዳቸው አለ። አንድ ቀን አስቻለውና ሔዋን ተዘናግተው ሳይሆን አይቀርም በሩን መለስ እንኳ ሳያደርጉት ቆመው ሲሳሳሙ
ሰራተኛቸው ፋንዩ በበር በኩል አለፍ ስትል አይታቸው ኖሯል። ወይዘሮ ዘነቡ በአቅራቢያዋ ስለነበሩ ወደ ጆሮትእው ጠጋ ብላ በሽንሹክታ ዓይነት እማማ ሂዱ
ወደ እታ አበባ በር አጠገብ፤ የሚያዩት ነገር አለ ብላቸው ነበር፡፡ እሳቸውም ሌላ ነገር መስሏቸው ቤቱን ሰለል እያረጉ በበሩ አጠገብ አለፍ ሲሉ ፋንትዩ ያየችውን
ያያሉ፡፡ በእርግጥ በወቅቱ በፋንትዪ ድርጊት ተቆጥተው ነበር፡፡ ግን ደግሞ ያዩትን
ማመን ችለዋል፡፡

«ለመሆኑ ይህን ወሬ የሚያወራው ማነው?» ስትል ሽዋዬ ጠየቀቻቸው፡፡
ሠፈር ሙሉ ነዋ! እኔ እንደውም የስማሁት በወይዘሮ እልፍነሽ ቤት
ውስጥ ሲወራ ነው፡፡» አሏት።
👍3
#ምንትዋብ


#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ


....“ጉድ! ጉድ!” አለ፣ ወይዘሮ ጌጤነሽ ሳይቀደሙ ለመቅደም። ቆመው እጅና እግራቸውን በእርጥብ እጃቸው ያባብሳሉ።

ባላምባራስ ዝም አሉ።
ወይዘሮ ጌጤነሽ ባላቸው፣ “ምንድርነው?” ሳይሏቸው በመቅረታቸው ቅር ተሰኙ። ወሬውን ለማውራት የነበራቸውን ጉጉት ስለአመከኑባቸው
ወሽመጣቸው ተቆረጠ። የባላቸውን ዝምታ አሰቡና ነገሩ ከነከናቸው።.

“ምንድርነውም አይሉ?” አሏቸው፣ የጎሪጥ እያይዋቸው።
“የትም አምሽተሽ መተሽ ደሞ ጉድ ትያለሽ?” አሉ፣ ባላምባራስ።

“ነገረኛ፣ ታሞ አይተኛ አሉ” አሉ፣ ወይዘሮ ጌጤነሽ፣ ድምፃቸውን
ዝቅ አድርገው።

“ምን አልሽ?”

“ምን እላለሁ ሳናግርዎ መልስ አይሰጡም ወይ ነው ያልሁት። ሌላ ምን እላለሁ?” አሉ፣ ራት ለመሥራት ምድጃ ላይ ድስት የጣደችውን የቤት አገልጋይ እያዩ።

“ሚሰማሽ ካገኘሽ ምላስሽ ረዥም ነው።”

“ኸርሶ አይበልጥ” አሉ፣ አሁንም ቀስ ብለው።

ባላምባራስ ቆጣ ብለው፣ “ምን አልሽ?” ካሉ በኋላ፣ ጉድ ከሰሙ
ስለ ሰነበቱ ጉዱን የመስማት ፍላጎት አደረባቸው። ቁጣቸውን ገታ አድርገው፣ “እና ምንድርነው ጉዱ?” አሉ፣ ለጠጥ ብለው እምብዛም ለወሬ የጓጉ እንዳይመስሉ።

ወይዘሮ ጌጤነሽ እንዳልሰማ ዝም አሉ፤ እንደ ማኩረፍ አድርጓቸዋል።

“ምንድርነው ጉዱ አልሁሽ እኮ” አሉ ባላምባራስ፣ ቆጣ ብለው።

ወይዘሮ ጌጤነሽ አሁንም ያልሰሙ መሰሉ።

“ሳናግርሽ መልስ 'ማሰጪ?” የባላምባራስ ቁጣ እየተጋጋለ ነው።

“ምን አሉኝ?” አሉ ወይዘሮ ጌጤነሽ። ፊታቸው ላይ ስስ ፈገግታ ይነበባል። ዛሬ አነስተኛ ቢሆንም ባላቸው ላይ ድል ተቀዳጅተዋል።

እነዚህን መሳይ ጥቃቅን ድሎች ናቸው አንዳንዴ ባላቸውን ያሸነፉ
እንዲመስላቸው የሚያደርጓቸው።

“ጉድ እያልሽ ገባሽ። ምንድርነው ብልሽ አለመጥሽ።” አሁንም
ድምፃቸው ገኗል፣ ባላምባራስ ሁነኝ።

“አልሰማሁ ሁኜ ነው” አሉ፣ ወይዘሮ ጌጤነሽ። የባላቸው ቁጣ
የሚገነፍልበትን አፍታ ስለሚያውቁ ያገኙትን ድል እያጣጣሙ፣
“የግራማች ልዥ ...” ሲሉ ጀመሩ።

“ግራማች?” ሲሉ አቋረጧቸው፣ ባላምባራስ። ወሬውን ለመስማት
ቸኩለዋል።

“ግራማች መንበር ናቸዋ።”

“ኸሷው ጋር ስታወሪ እንደቆየሽ አውቄያለሁ። ወልደልዑል ምንን
ሆነ?”

“ሴቷ ወለቴ።”

ጥላዬ፣ የሆነ ነገር እንዳለ ደመነፍሱ ነገረው። ነፍሱ ከዳችው። ጉዱን ለመስማት ቤት ውስጥ መግባት ፈልጎ፣ ወገቡ አልታዘዝ፣ ጉልበቱ አልንቀሳቀስ አለው። እንደምንም ብሎ ተነስቶ ውስጥ ገብቶ መደብ
ላይ ተቀመጠ።

ባላምባራስ በመገረም ተመለከቱት። እሳቸው ሳይተኙ ቤት ውስጥ ስለማይገባ፣ ዐይኑን ካዩት ከርመዋል። ሆዳቸው ተገላበጠ።

“እና ምንን ሆነች?” አሉ፣ መባባታቸው እንዳይታወቅባቸው
እየታገሉ።

ወይዘሮ ጌጤነሽ ከመናገር ተቆጠቡ። ጥላዬን ሰረቅ አድረገው አዩት።እሱ የሚሉትን ለመስማት ቢጓጓም ጎንበስ ብሎ መሬቱን በስንጥር መጫጫር ጀመረ።

“ዛሬ ምንን ነክቶሻል? ምንን ሆነች ስልሽ መልስ ማሰጪ?”

“በያ ሰሞን ንዳድ ይዟቸው ኸነሱ ዘንድ ተኝተው የነበሩት ለካስ
ንጉሡ ኑረዋል...”
“ንጉሠ?”
“አዎ።”
“አጤ በካፋ?”
“እሳቸው። ሌላ ንጉሥ አለ?”
“ምንድርነው ምታወሪው?” አሉ ባላምባራስ፣ የሚስታቸውን ትንኮሳ
ችላ ብለው።
መንን
“አጤ በካፋ ራሳቸው። ወለቴ አስታማቸው ስታበቃ ዛሬ ሰዎች
ኸጥሎሽ ጋር ሰደዱ።”
“ሊያገቧት?”
“ኋላ?”
ጥላዬ ዱብ ዕዳ ሆነበት፣ ድንጋጤ ሰውነቱን አብረከረከው። ተነስቶ
ሊወጣ ፈልጎ ወሬ ለመስማት ተቀመጠ።

“ሰው ለማንጓጠጥ ማን ብሎሽ። ወረኛ! ደሞ ማታመጪው የለ” አሉ
ባላምባራስ፣ ተደናግጠዋል፣ ንዴትም ተናንቋቸዋል።
“እንዴት በሉ? ምን ያልሆነ አምጥቸ አውቃለሁ? ኸመሽ አገር ሁሉ ሚያወራው እኼንኑ ማዶል? የጣ ፈንታ ነገር ይገርማል።”

“ውነት ነው፤ ዕጣ ፈንታ ነው” አለ ጥላዬ፣ የሞት ሞቱን። ሰውነቱ
እየራደ ነው። ለራሱ፣ እኔ ዕድል ፈንታየ ሁኖ ያልታደልሁ ሁኘ
የወፍታው እኼን አሰማኝ ብሎ በዐይኑ ውሃ ሞላ። እንባው እንዳይታይበት እደጅ ሲወጣ፣ አባቱ በዐይናቸው ተከተሉት።

“ያቺ አያትየው ኸደብተሮቹ ነው ውሎዋ። ኸተኙበት ቀባብታቸው
ይሆናል ይላል ድፍን ቋራ” አሉ ወይዘሮ ጌጤነሽ፣ አገልጋይዋ ራት
እንድታቀርብ በእጃቸው ምልክት እይሰጡ።

“ድፍን ቋራ ኸምኔው ሰምቶ ነው እኼን ሁሉ ሚለው? አንቺና
ጓደኞችሽ ጓሮ ሁናችሁ ያቦካችሁት ነው እንጂ። ለነገሩ ልዥቱ
ምንም አይወጣላት። ደማም... ቆፍጣና... ይገባታል፤ ይገባታል ::
ሚገባትን ነው ያገኘች። እኔ ለተክለሃይማኖት ተዋጋህ እየተባልሁ ስወቀስ የተክለሃይማኖትን ወንድም በካፋን አገባች?” አሉ ባላምባራስ፣
በመገረም ራሳቸውን እየነቀነቁ።

አገባች! እርምዎን ያውጡ እንግዲህ! በርሶው አጓጉል ጠባይ ነው እኼ ሁሉ የመጣው። እርስዎንስ ይበልዎ፣ ልጄን ጎዱብኝ እንጂ አሉ ወይዘሮ ጌጤነሽ፤ ለራሳቸው። ጮክ ብለው ሊናገሩ ፈለጉና በማታ ኸሳቸው ጋር ምን አጫጫኸኝ ብለው፣ “ኸቤታቸው ንግርት አለ ይባላል። ዘመዳቸው የሆነ ሰው ኸወለቴ ግንባር ጠሐይ ስትወጣ አይቷል” አሉ።
ባላምባራስ መልስ አልሰጧቸውም። ቁጭት ላይ ናቸው። ልዥህን ለልዤ ስባባል ቆይቶ፣ በትንሽ ነገር ኸጥብቅ ወዳጄ ተቀያይሜ፣ አሁን
እኼው ሌላ...ያውም ንጉሥ ወሰዳት። እንግዲህ ኸንጉሥ መንጋጋ አላስጥላት! ያቺ ቀን እንዴት ያለች የተረገመች ናት አሉ፣ ግራዝማች መንበርን የተቀየሙበትን ቀን አስታውሰው።

የጊዮርጊስ ማኅበር ነው። ግራዝማች መንበር ቤት ይበላል፤ ይጠጣል። ጨዋታው ደምቆ፣ እንደወትሮው ስለ ጦር ሜዳ ጀግንነት ይወሳል። ባላምባራስ ሁነኝ ራሳቸውን እንደ ጀግና ቢቆጥሩም፣ ስለ ጦር ሜዳ
ሲወራ አይወዱም።ከዚህ በፊት ሰድበውት የሚያውቁት ደብተራ ሞቅ ብሎታል። “አሁን በወፍታው ኸጦር ሜዳ ቋንጃውን የተመታ ዠግና ይባላል?” ብሎ በሳቅ
ተንተከተከ።

ማንም አልሳቀ። ሁሉም አንገቱን ደፋ። ሳቅና ቁም ነገር የሰፈነበት
ስብስብ ወደ መሸማቀቅ ተለወጠ።

ደብተራው የሳቀለት ሲጠፋ፣ “እኛ ባገራችን ምናቀው ሰው ቋንጃውን
ሚመታው ሲሸሽ ነው” አለ፣ የፌዝ ሳቅ እየሳቀ።
ባላምባራስ ከዓመታት በፊት ቋንጃቸውን ተመትተው ያነክሳሉና
እሳቸውን ሊነካ መሆኑን አውቀው ከተቀመጡበት ተነሥተው
ከዘራቸውን እየወዘወዙ፣ “አንት መተተኛ ደብተራ። እኔ ሁነኝ በንዳንተ ያለ ድግምተኛ አልሽረደድም። የት አባህ ጦር ሜዳ ውለህ ታውቃለህና
ስለ ጦር ሜዳ ታወራለህ? ጋን እያሸተትህ ኸድግስ ድግስ ዙር እንጂ።

ጥፋተኛው አንተ ሳትሆን አንተን ኸሰው መኻል የቀላቀለህ ነው” ብለው ከዘራቸውን ግራዝማች መንበር ላይ እየወዘወዙ፣ “መንበር አሰደብኸኝ ...
ያውም በዝህ በድውይ። ግድ የለም። እንዲህ ኻሰደብኸኝ ወዲያ እመቃብሬ እንዳትቆም... ኸዚህ ያላችሁ ሁሉ ቃሌን ቃል እንድትሉ”
ብለው እያነከሱ ወጡ።
ከዚያን ቀን ጀምሮ የግራዝማችና የባላምባራስ የረጅም ዘመን ጓደኝነት አከተመ፣ አብሮም የጥላዬና የወለተጊዮርጊስ ዕጮኛነት። ባላምባራስ፣
“በቤቱ አሰደበኝ” ብለው ቂም ያዙ። ግራዝማች፣ “ደብተራው ለሰደበው እኔ ምን አረግሁ?” ብለው ቅር ተሰኙ። አስታራቂ መሃከላቸው ቢገባ ባላምባራስ፣ “ሙቼ ነው ቁሜ ኸሱ ጋር ምታረቅ” አሉ። “ልዥህን
ለልጄ” የተባባሉት ጓደኛሞች ተቀያየሙ።

ግራዝማች መንበር፣ ሁነኝ ምንም ቢሆን የረጅም ጊዜ ወዳጄ ነውና
አንድ ቀን እንታረቅ ይሆናል እያሉ የወለተጊዮርጊስን እጅ ለጠየቀ ሁሉ አይሆንም እያሉ መለሱ።
👍15
#ትኩሳት


#ክፍል_አምስት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

...ካንድ ስምንት ቀን በኋላ፣ ማታ ተመስገን ክፍል ቁጭ ብዬ
ስስራ፣ ተመስገን መጣና አልጋው ላይ ዘጭ ብሉ ተጋደመ፡፡ እፎይ!
ብሎ ተነፈሰ
«ሲኒማ የገባችሁ መስሉኝ» አልኩት
«ሌሎቹ ገቡ፣ እኔ ግን ተውኩት»
«ለምን ተውከው?» አልኩት። ድምፄ «አንተ ተንኮለኛ!»
እንደሚል አይነት ነበር
«ደስ አላለኝማ!» አለኝ፡፡ ትንንሽ አይኖቹ ሊደበቁ ጀምረዋል፣
ግን ጥርሶቹ ገና መታየት አልጀመሩም
«ውሸታም! ቀጠሮ ቢኖርህ ነው እንጂ» አልኩት
«ከማን ጋር?»
«እኔ አውቃለሁ እንዴ ያንተን ተንኮል? ወይ ካንዷ ብሎንድ
(ፀጉሯ ብጫ ወይም ነጭ ብጤ) ጋር፣ ወይ ከሲልቪ ጋር»
«ሲልቪ!? አላወቅክምና!»
«ምን?»
«ቀርቶ!»
«ምነዋ?»
«ምን እባክህ የሴት ነገር» አለ «አገር ጤና ብዬ እንደ ሁልጊዜያችን ወዲህ አመጣሁዋት፡፡ ከሰአት በኋላ ነበር። የከሰአት በኋላው እንዴት እንደሚጣፍጥ ታውቅ የለ? ልብሷን አወላለቀችና
አልጋው ውስጥ ገባች። እየተንገበገብኩ ተከትያት ልገባ ስል፣
ከትራሱ ላይ ኣንዲት ፀጉር እንስታ አቀበለችኝ። ረዥም የፈረንጅ
ፀጉር ነው፤ ግን ጥቁር አይደለም፣ ቡና አይነት ነው»
«ይሄ የኔ ፀጉር እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ አለችኝ»
«ዝም ኣልኩ። አልገባኝም አየህ
«ተናገር እንጂ» አለችኝ። እግዜር ያሳይህ፡፡ በመጀመሪያ
አልጋው ውስጥ ልገባ ጎምበስ እንዳልኩ ኣሁንም አለሁ፡፡ ይታይሀል? ራቁቴን አልጋው ላይ ባራት እግሬ ቆሜ? እንደሚድህ ልጅ:: ልብሷን ስታወልቅ እያየሁና የሚጠብቀኝን ደስታ እያሰብኩ ግትር አድርጎ ቅንዝር ወጥሮኛል፡፡»

የተመስገን አይኖች ጨርሰው ጠፉ፣ ጥርሶቹ ተገለጡ፣ ይሰቅ
ጀመር፡፡ ከት ብሎ እየሳቀ፣ ሳቅ በሚቆራርጠው ንግግር
ገና አሁን ታየኝ ሀ! ሀ! ሀ! እንዴት እንዴት - ሀ! ሀ! U! እንዴት እንደነበርኩ ሁ! ሁ! ሁ! አንዲህ ነበርኩ» አለና በጀርባው ከተጋደመበት ተነስቶ ዞሮ በጉልበቱና በእጁ ተንበረከከ፡፡
ከስሩ ትራሱን አስተካከለና፣ ሌባ ጣቱን እያነጣጠረበት

«እኔ እንዲሀ ነኝ፣ ሂሂ!!» ትራሱን «እቺ ሲልቪ ናት።
ያቀበለችኝን ፀጉር ባንድ እጄ እንደዚህ ይዣለሁ። እንዳትበጠስ
ወይም ወድቃ እንዳትጠፋ እየተጠነቀቅኩ፣ ያቺን ነጃሳ ፀጉር እንዲህ ይዣለሁ። ቁላዬ ደሞ እዚህ ጋ ቆሞ ሲልቪን ቁልቁል ያያታል።አይ የኔ ቁላ! ቂል ነውኮ፡፡ ያንተም ቂል ነው?» እንደገና ሳቅ
አሸነፈው። አልጋው ላይ ተንከባለለ። ሳቁ ሲያልፍለት

«በኋላስ?» አልኩት

«በኋላማ ምን ልበልህ ልጄ? ቃል ሳትናገር ተነስታ ልብሷን
መልሳ ለበሰች፡፡ ረጋ ባለ ድምፅ 'የኔና ያንተ ነገር በዚሁ አለቀ”
ብላኝ ልትወጣ ስትል፣ እኔ እዚች ጋ ራቁቴን እንደቆምኩ
«ምን ነካሽ?» አልኳት፡፡ ሲያቀብጠኝ'ኮ ነው:: እስቲ ዝም ብላትስ?
«ዘወር አለችና፣ እሱ ጠረጴዛ ላይ ያለውን መፃህፍትና ደብተር
በአጇ አንዴ ገፍታ መሬት ላይ አዝረከረከችው:: እና ጠረጴዛውን
በተጨበጠ እጇ ደጋግማ እየመታች

«እኔ የእስላም ሀሪም ሴት - አይደለሁም!» ብላኝ ስታበቃ፣ ወጥታ በሩን በሀይል ጓ! አርጋው ሄደች። ልብሴን ልለብስ
ካናቴራዬን ሳነሳ በሩ ብርግድ ብሎ ተከፈተ። ማን ገባ መሰለህ?»
አለኝ

«ማን?» አልኩት

«ሲልቪ ራሷ ነቻ! የሴት ነገር! ከመቼው ሀሳቧን ለወጠች?!
እያልኩ ልገረም ስጀምር፣ ኣጠገቤ መጣች። አቅፋ ልትስመኝ
እንደሆነ ገባኝ፡፡ ትንሽ ልኮራባት አሰብኩ። ታድያ እሷ ምን አረገች
መሰለህ? እወቅ : ስቲ።»
«በጥፊ መታችህ?»
«ብጭራሽ!»
«አቅፋ ሳመችህ?»
«ትቀልዳለህ?»
«እንግዲያው ምን አረገች?» አልኩት
«ጫማዋን አረገች»
«ምን?»
«በንዴት ጫማዋን ረስታው ሄዳ ነበር፡፡ ተመልሳ አረገችውና
ወጣች። እኔ ራቁቴን ቆሜ ቀረሁ፡፡ ቁላዬ እስካሁን ተኝቷል፡፡ ከዚያ
በኋላ አናግራኝ አታውቅም»
«ጥፋቱ ያንተ ነው» አልኩት
«እንዴት?» አለኝ
«ያመጣሀቸው ሴቶች ሊሄዱ ሲሉ «ፀጉሮችሽን ሁሉ ይዘሻል?
ቁጠሪ እስቲ ለምን አትላቸውም?» አልኩት
«መቼ ሴት አመጣሁና?» አለኝ
«እ-ህ? ቡናማው ፀጉርሳ?»
«ከየት እንደመጣ እንጃለት:: ምናልባት ቤት የምትጠርገው
አልጋ የምታነጥፈው አሮጊት ያን እለት ታማ ኖሮ፣ በሷ ምትክ
ባለቡናማ ፀጉር ሴት አልጋዬን አንጥፋልኝ ይሆናል»
«ምስኪን ተመስገን!» አልኩት
ምስኪን ትላለህ ምስኪን። ይኸው እስከዛሬ ዖም ላይ እገኛለሁ
«ዛሬ ማታ ግን ለመግደፍ ያሰብክ ትመስላለህ»
«ነበር እባክህን። ፀጉሯን እንደ ወንድ ነው 'ምትቆርጠው፣
ቢሆንም ምንም አትል። ብቻ »
«ብቻ ምን?»
«የት እንደምወስዳት ጨንቆኛል»
ሲመሽ ፈረንሳዮች concierge
የሚሉት ዘበኛ ይመጣና' ወደመኝታ ቤቶቹ የሚያስገባው በር አጠገብ አንዲት ቢሮ አለችው፣ እዚያች ቁጭ ብሉ ወጪ ገቢውን ሁሉ ይመለከታል። ወንዶች መኝታ ቤት ሴት ማስገባት ክልክል ነው፡፡)

«የኔ ሆቴል አለልህ አይደለም እንዴ?» አልኩት
«አትጠቀምበትም?»
«እዚህ ልተኛ እችላለሁ»
እሱማ ጥሩ ነበር»
“ብቻ እንዳታስጮሀት አደራ፡፡ ካስጮህካትም ፎጣ አጉርሳት።
ብዬ የሆቴሌን ቁልፍ ሰጠሁት
ተመስገን ወደ ቀጠሮው ከሄደ በኋላ ተመልሼ ልስራ
በጠበጠኝ። ተነስቼ አሜሪካዊቷ ቤት ሄድኩ፡፡ ጉዳዬን አስረዳኋት።
አልቻልኩም፡፡ ሲልቪ ለኔ ስትል እንደተወችው ገባኝ፡፡ ይህ ሀሳብ
ከዚህ በፊት አገሬ እጮኛ አለችኝ ብያት ነበር፡፡ አሁን፣ እጮኛዬ
ካንቺ ጋር ያለኝን ግንኙነት አወቀች፡፡ ማን እንደነገራት እንጃ፡
ወረቀት ፃፈችልኝ። በአንድ ሳምንት ውስጥ ኣሜሪካንህን ትተሀታል
የሚል ወሬ ካልደረሰኝ ሌላ እኛ ፈልግ አለችኝ፣ ብዬ ነገርኳት።
«i derstand የዚህ መጥፎ ዜና ምክንያት በመሆኔ በጣም
አዝናለሁ» አለችኝ። ያቀድኩት ይህን ነግሬያት ደህና እደሪ ብያት
ሲልቪን ፍለጋ ለመሄድ ነበር። ግን ልጅቱ ጥቁር ስስ የሌሊት ልብስ
ለብሳ ስትራመድ በጣም ታስጎመጃለች፣ ገላዋን ታጥባ ቆዳዋን በታልከም ዱቄት አሻሽታው፣ ሽታው ይማርካል፡፡ ከሷ ጋር አደርኩ
«ራሷን በጣም ታዘብኩት። በጣም ፀፀት ተሰማኝ፣ ሲልቪን
የበደልኳት መሰለኝ»
በነጋታው ሲልቪን ከምግብ ቤት ስትወጣ ጠብቄ ኣገኘኋት።
ቡና ልጋብዝሽ አልኳት። ኤክስ ውስጥ የምወደው ካፌ የለኝም
አልኩህ? አለችኝ፣ እሺ ማርሰይ ልውሰድሽ አልኳት። መኪናዬ
ጋራዥ ናት አለችኝ፡፡ በኦቶቡስ ልውሰድሽ አልኳት። አልፈልግም
አለችኝ። እንግዲያው ምን እናርግ? አልኳት፡፡ እኔ ቡና ላጠጣህ፣ራሴ አፍልቼ፣ አለችኝ፡፡ ቤቷ ወሰደችኝ፣ ከኤክስ ትንሽ ወጣ ብሎ ባላገሩ ውስጥ ነው

«የሴዛን የነበረው ቤት በዚህ በኩል ነው። መሄድ ትፈልጋለህ?»
አለችኝ
«አልፈልግም» አልኳት
«እኔም ሄጀ አላውቅም» አለችኝ
እየሳቅኩ «Tut'en fous, ch?» አልኳት («ደንታ የለሽም፣ እ?»)
እየሳቀች፣ «Je m'en fous eperdument!» አለችኝ («እቺን ያህል እንኳ ደንታ የለኝም»)
ቤቷ ገባን። ሁለት ክፍል (አንድ መኝታ፣ አንድ ሳሎን) ወጥ
ቤት፣ መታጠቢያ ክፍል። በየግድግዳው የልዩ ልዩ አቢይ ስእሎች እትም ተለጥፏል። የቤት እቃው ዘመናዊ ነው፣ ሰማያዊና ወይን ጠጅ ቀለማት ይበዙበታል
👍25
#ምንዱባን


#ክፍል_አምስት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


.....ከተማውን ጥሎ ወጣ፡፡ ከተማውን ለቅቆ ገጠር እስከገባ ድረስ እየተጣራ ነበር የሚሄደው፡፡ ወዴት እንደሚሄድ ሳያስተውል መንገድ እንደመራው ዝም እያለ ተጓዘ፡፡ ከነጋ ጀምሮ እህል አልቀመሰም:: ሆኖም የረሃብ ስሜት አልተሰማውም፡፡ ቁጣ ቁጣ ብሉታል፡፡ በማን ላይ ወይም በምን ምክንያት እንደተቆጣ ግን አያውቅም:: የሚቀጥለው ምን ይሆን ሲል ራሱን ጠየቀ፡፡
የገጠር አየር የልጅነት ጊዜውን አስታወሰው:: የልጅነት ዘመኑን ካስታወሰ በጣም ቆይቶ ነበር፡፡ ከዚያም ብዙ ኣሳቦች ተፈራረቁበት፡፡»

ፀሐይ አሽቆልቁላ ገብታ ከአድማስ ውስጥ ልትገባ ስትል ዣን ቫልዣ
እልም ካለ ጫካ ውስጥ ከአንዲት ጉብታ ላይ ቁጭ ብሎአል፡፡ የአልፕስ ተራራ በሩቁ ይታያል፡፡ ከጫካው ወጣ እንዳለ አንድ ቀጭን የእግር መንገድ አለ፡፡

ከዚህ ቁጭ ብሎ ሲያሰላስል ደስ የሚል ድምፅ ይሰማል፡፡ ፊቱን
ሲያዞር ወደ አሥራ ሁለት ዓመት የሚሆነው ልጅ እየዘመረ ወደ እርሱ ይመጣል:: ልጁ በጭንቅላቱ ሣጥን መሳይ ነገር ተሸክሞአል፡፡ ልጁ ጥቂት
ከተራመደ በኋላ ቆም ብሎ በእጁ የያዘውን ሣንቲም ወደ ሰማይ እያጎነ ይጫወታል:: የልጁ ሀብት ምናልባት ይኸው ነጭ ሽልንግ ብቻ ሳይሆን አልቀረም::

ዣን ቫልዣ ከተቀመጠበት ሲደርስ የሰውዬው ከእዚያ መኖር ሳይገነዘብ ቆም አለ፡፡ እንደ ልማዱ ሣንቲሙን ወደ ሰማይ አጎነ፡ ሣንቲሙ አምልጦት
ከመሬት ሊወድቅ ዣን ቫልዣ ወደ ተቀመጠበት በረረ:: ዣን ቫልዣ
ሽልንጉን በእግሩ ረግጦ ያዘበት:: የልጁ ዓይን ሣንቲሙን ተከትሎ ስለሄደ የት ላይ እንዳለ ያውቃል፡፡ ልጁ አልፈራም፤ በቀጥታ ወደ ሰውዬው ሄደ::

«ጌታዬ ገንዘቤን» አለ ልጁ የዋህነትና ድንቁርና በተሞላበት አንደበት::

«ስምህ ማነው?» ሲል ዣን ቫልዣ ጠየቀው::

«ትንሹ ዥራቪ ነው ጌታዬ::»

«ቶሉ ከዚህ ጥፋ» አለው ዣን ቫልዣ ::

«ፍራንኬስ?» ሲል ልጁ ጠየቀ፡፡

ዣን ቫልዣ እንዳቀረቀረ ቀረ::

«ገንዘቤን» አለ ልጁ እምባ እየተናነቀወ :: ሽልንጌን!»

ዣን ቫልዣ ምንም ነገር እንዳልሰማ ሰው ፀጥ አለ፡፡ ልጁ የሰውየውን ሸሚዝ ኮሌታ በአንድ እጁ ያዘ፡፡ በሌላው እጁ ሣንቲሙን ለማስለቀቅ የሰውየውን እግር ለማንሳት ሞከረ::

«ገንዘቤን እፈልጋለሁ ፧ ሽልጌን!» ብሎ ከጮኸ በኋላ ትንሹ ዠራቬ
ማልቀስ ጀመረ:: ዣን ቫልዣ አንገቱን ቀና አደረገ፡፡ ከተቀመጠበት ግን አልተነሳም:: ፊቱ፡ በአሳብ የተዋጠና የተጨነቀ ይመስላል፡፡ በመገረም ልጁን
አትኩሮ አየው:: ዱላውን ሳብ ኣድርጎ «አንተ ማነህ? እህ! ምንድነው የምትፈልገው? እስካሁን አልሄድክም እንዴ» ሲል በሚያስፈራ ድምፅ ጮኸበት:: ሣንቲሙን እንደረገጠ ከመቀመጫው ብድግ ብላ «ራስህን ብትጠብቅ ይሻልሃል» አለው::
ልጁ በፍርሃት ተወጦ ቀና ብላ አየወ:: ሰውነቱ ይንቀጠቀጥ
ጀመር፡፡ ወዲያው ከጥቂት ሰኮንድ መርበትበት በኋላ ልጁ አግሬ አውጪኝ ብሎ ሸመጠጠ፡፡ ዞር ብሎ ለማየት ወይም ጩኸት ለማሰማት እንኳን አልደፈረም፡፡ ሆኖም ጥቂት እንደተጓዘ ትንፋሽ አጥሮት ቆም አለ:: ግን ብዙ
አልቆመም፧ መንገዱን ቀጠለ፡፡

ፀሐይዋ ጠለቀች፡፡ ዣን ቫልዣ ከተቀመጠበት አካባቢ ብርሃን ለጨለማ ሥፍራዋን ለቀቀች:: ቀኑን መሉ ምግብ የሚሉት ነገር አልቀመሰም::ምናልባትም ትንሽ እንደትኩሳት ብጤ ሳይሞካክረው አልቀረም::

ልጁ ከሄደ ጀምሮ ከተቀመጠበት ነቅነቅ አላለም:: በኃይል ነው
የሚተነፍሰው:: ከተቀመጠበት ጥቂት ራቅ ብሎ ከነበረው የሸክላ ስባሪ ገል ላይ ዓይኑን ተከለ፡፡ ስለገሉ ይመራመር ጀመር፡፡ ግን በድንገት መላ ሰውነቱ
ተንቀጠቀጠ፡፡ የሌሊቱ ቁር እየተሰማው ሄደ፡፡

ቆቡን ሳብ አድርጎ ግንባሩን ሸፈነ:: የሸሚዙን አዝራር ለመቆለፍ
ጣቶቹ አዝራር ፍለጋ ላይ ታች አሉ:: ብድግ ብሎ ወደፊት ራመድ ካለ ከኋላ መለስ ብሉ ዱላውን ለማንሳት ጎንበስ አለ፡፡

በእግሩ ረግጦ ይዞት የነበረው ሽልንግ በማብረቅረቁ ዓይኑ ወደዚያ ተሳበ፡፡ ኮረንቲ እንደያዘው ሰው ተሸማቀቀ፡፡ «ምንድነው ነገሩ?» ሲል ጥርሱን በማፋጨት ራሱን ጠየቀ:: እንደገና ወደኋላ መለስ ብሉ ሣንቲሙን በእግሩ በመርገጥ ሸፈነው:: ሣንቲሙ ዓይን አብቅሎ የሚያየው መሰለው::

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ እግሩን መነጨቀና ጎንበስ ብሎ ሣንቲሙን
አነሳ፡፡ ቀና ብሎ አካባቢውን ተመለከተ:: ጋራውና ሸንተረሩ ሁሉ የሚያየው ስለመሰለው በፍርሃት ተውጦ መወጊያ እንደምትፈልግ ዱኮላ ዓይኑ በፍርሃት ተቅበዘበዘ፡፡ ከቆመበት ተገትሮ ቀረ፡፡

ምንም ነገር አላየም:: ጊዜው እየጨለመና አየሩ እጅግ እየቀዘቀዘ ሄደ:: ሰማዩ በጭጋግ ተሸፈነ፡፡

«ወይ ጣጣ» ሲል ልጁ በሄደበት አቅጣጫ ጉዞውን ቀጠለ፡፡ አንድ
ሰላሳ - እርምጃ ያህል እንደተራመደ ቆም ኣለ፡፡ አካባቢውን ተመለከቱ።
ምንም ነገር የለም:: ድምፁን እጅግ ከፍ አድርጎ «ዠራቬ» ሲል ተጣራ፡፡ ከዚያም ድምፁ
አጥፍቶ አዳመጠ:: መልስ አላገኘም፡፡

አገሩ ጭር ያለና ጭጋጋም ቢሆንም አካባቢው በግልጽ ይታያል ከዝምታና ከራሱ ጥላ በስተቀር የሚንቀሳቀስ ፍጠር ጨርሶ አልነበረም ዣን ቫልዣ መንገዱን ቀጠለ፡፡ የሚወስደውን እርምጃ ፍጥነት በመጨመር እንደ መሮጥ አለ። አልፎ አልፎ ቆም እያለ በሚያስፈራ ሻካራ ድምፅ «ዠራቬ» ሲል እንደገና ተጣራ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ልጁ ቢሰማው
እንኳን በፍርሃት ስለሚዋጥ ይደበቃል እንጂ መልስ አይሰጠውም:: ነገር ግን ልጁ በርግጥም በጣም ርቆ ሄዷል፡፡
ዣን ቫልዣ እንደገና ልጁ በሄደበት ኣቅጣጫ መሮጥ ጀመረ
እየተገላመጠ፣ እየጮኸ፣ እየተጣራ ብዘ ተጓዘ፡፡ ግን ማንንም አላገኘም በደረቱ ተንፏቅቆ የሚሄድ ወይም ድምፁን አጥፍቶ ያደፈጠ እየመሰለ ከአንዴም ሁለቴ፣ ከሁለቴም ሦስቴ መንገዱን ለቅቆ ወደ ጥሻው ዞር እያለ
ተመለከተ፡፡ ግን ሰው የመሰለው ነገር ጠጋ ሲል ቁጥቋጦ ወይም ድንጋ ሆኖ ያገኘዋል፡፡ በመጨረሻ ሦስት መንታ መንገዶች ከሚገናኙበት ደረሰ ከመሐል መንገድ ላይ ቆመ:: ጨረቃዋ ብቅ ብላለች:: ለማየት እስከቻለ
ድረስ አርቆ ተመለከተ:: «ዥራቬ፣ ትንሹ ዥራቬ፣ ዠራቬ» በማለት
ሦስት ጊዜ ድምፁን ከፍ አድርጎ ተጣራ:: ድምፁ የገደል ማሚቶ እንኳ ሳያዕማ ከጭጋጉ ውስጥ ተውጦ ቀረ:: «ትንሹ ዥራቬ» ሲል ዝግ በደከመ ድምፅ አጉረመረመ:: ያ የመጨረሻው ሙከራ ነበር፡፡ በዓይ የማይታይ ኃይል በዱላ እንደመታው ሰው በድንገት እግሩ ተሳስሮ ጉልበቱ እጥፍጥፍ አለበት:: ፀጉሩን በእጁ ጨብጦና ፊቱን ጉልበቱ ላይ አሳርፎ
ከቋጥኝ ድንጋይ ላይ በመቀመጥ «ምን ዓይነት እድለቢስ ሰው ነኝ» አለ ጮኸ፡፡ ልቡ እያበጠ ሄደ፡፡ ምርር ብሎ አለቀሰ፡፡ ከአሥራ ዘጠኝ ዓመት ወዲህ ሲያለቅስ የመጀመሪያው ነበር:: ዣን ቫልዣ ብዙ አለቀሰ፡፡ ከሕፃኑ መባባትና ከሴቶች መርበትበት ይበልጥ በፍርሃት ተውጦ ከዓይኑ እምባ የወጣ እስኪመስለው ድረስ በማልቀስ አንጀቱን እርር ድብን አደረገ እያለቀሰ ሳለ ከሕሊናው ውስጥ የነበረው ብርሃን እየፈካ ሄደ፡፡

የተለየ ብርሃን ነበር፡፡ ያ ብርሃን አሳደደው፤ አስፈራራው፡፡ ያለፈው የሕይወቱ ዘመን፤ የመጀመሪያው ወንጀሉ፤ የረጅም ጊዜ ስቃዩ ፧ ጨካኙ ዓለም፤ የደነደነው ልቡ ፣ ከእስር ቤት ማምለጡ፤ ከጳጳሱ ቤት በእርሱ ላይ የደረሰው! የመጨረሻው አሳፋሪ ድርጊቱ ፤ ከሕፃን ልጅ ገንዘብ መዝረፉ፤
👍22😁1
#ገረገራ


#ክፍል_አምስት


#በታደለ_አያሌው

.....“ያንቺ ነዉ” አለችኝ፣ እኛ እያለን ራሷ ወደ ጀመረችዉ የምሳ ጉድ ጉዷ እየተመለሰች፡፡ “ታዲያ አደራሽን ምንድነዉ ቅብጥርሴ እንዳትጠኝ። እኔ ምኑንም አላዉቅልሽም። ስጭ ነበር የተባልሁት፣ ይኼዉ ሰጥቼሻለሁ።
አበቃሁ” በእራፊ ጨርቅ የተጠቀለለች ትንሽ ነገር መሆኗን ቀድሞዉንም ስትሰጠኝ
ኣስተዉያለሁ፡፡ ምን እንደሆነች ለማየት ገለጥ ባደርጋትም፣ ጥቅልሉ ስለበዛ ፍሬ እቃዋን ቶሎ ልደርስበት አልቻልሁም፡፡ ስቀበላት እምነት መስላኝ ነበር። አይደለችም ማለት ነዉ? በዚያ ላይ ስንት ዙር እንደ
ተጠቀለለች! ተርትሬ ተርትሬ ስጨርስ ያገኘሁት ግን ጥፍር እንኳን የማታህል ሚሞሪ ካርድ ብቻ ነበረች፡፡ መጠቅለያ ጨርቁን ባራግፈዉም፣ ከእሷ ሌላ ምንም የለም። እመዋ ደግሞ እንዳልጠይቃት ቀድማ መንገዱን
ሁሉ ዘጋግታብኛለች፡፡ ምን ቸገረኝ ብዬ ወደ ሞባይሌ ቀፎ ከተትኋት።
ከዚያም በድምፅ ማጫወቻዉ ከፈትሁት፡፡ ከትንሽ የነፋስ እና የወፎች ጺዉጺዉታ በኋላ፤ ማሲንቆ የሚያስንቅ አንቺሆዬ ዓይነት ፉጨት መጣ፡፡

የት ነበር የማዉቀዉ ይኼን ድንቅ ትንፋሽ?

መቼ አጣኋቸዉ! ወይዘሮ ብርሃኔ ናቸዉ፡፡ እሳቸዉ ናቸዉ ትንፋሻቸዉን እንደ ፈለጉ የሚያሽሞነሙኑት። እንኳን በሴት በወንድ እንኳን የማላዉቀዉን፣ ማንኛዉንም ዜማ በፉጨታቸዉ ብቻ ሲያወጡት አያድርስ ነዉ። በዘለሰኛ ጨዋታቸዉ የሁሉን ነፍስ የሚገዙት፣ በሸክላ ሥራ ጥበባቸዉ ሁሉን የሚያስደንቁት፣ ፉጨት እና ሽለላዉን
የሚያዉቁበት፣ ወይዘሮ ብርሃኔ ናቸዉ። አትጠገቤዋ፣ ደርባባዋ ሰዉ! በእርግጥ መጀመሪያ ያወቅኋቸዉ በእሸቴ በኩል ነበር። የእሱ እናት ናቸዉ፡፡ እንደ ጣና ሐይቅ የተረጋጉት፣ እንደ ዥማ ወንዝ የልብ የሚያደርሱት ሴት ናቸዉ በፉጨት የመጡብኝ። ጥሎብኝ አንጎራጓሪ ሰዉ
አይሆንልኝም፡፡ እጅግ አድርጌ እወዳለሁ። በተለይ ዘለሰኛ! ዘለሰኛ ለመስማት ስል ምንም ነገር ቢሆን እተዋለሁ። አሁን አሁን እንዲህ እሸቴ የሚባል ስም በአፍንጫዬ ይውጣ ልል፣ ያኔ ልቤን ወለል አድርጌ
እንድከፍትለት ካደረገበት ብዙ ምክንያቶቹ አንዷ እናቱ ነበሩ።

ልዩ ናቸዋ!

ፉጨቱን ተከትሎ በድምፃቸዉ ደግሞ መጡብኝ። ያ ከእሕልም
ከመጠጥም የሚጣፍጠዉ ዘለሰኛቸዉ!

ኧኧኧኧኧኧ...
ሸክላ ሠሪ አርገህ ሾመኸኛል
የሸክላ ጥበብ ይገባኛል፡፡
ኧኸ

ሸክላ ማለት የእጄ ሥራ
እኔ ደግሞ የእጅህ ሥራ፤
የእጄ ተሰብሮ ብመኝም ሞት
የእጅህን ማትረፍ ግን አወቅህበት!

ኧ ኸ ኧ ኸ ኧ.....

ምንም እንኳን ቀረጻዉ ጥራት ያልሞላለት ሆኖ ሞገዱ እንደሚዋዥቅበት ሬዲዮ ወስድ መለስ ሲያደርገዉም፣ እየደጋገምሁ አጣጣምሁት። ከምኔዉ እንደሆነ እንጃልኝ ብቻ አሁን መረጋጋት ይታይብኛል። አሁን ከፋኝ ብዬ ስነፈርቅ አልነበር እንዴ? ፊቴን ዳበስሁት፤ እንባ የሚባል ጠብታዉ ሳይቀር የለም። ወደ መስታዎት ሮጬ ዓይኔን አየሁት። እንኳንስ ደም
ሊመስል! ልክ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ ወደ ነባሩ ቀልቤ ተመልሻለሁ። ያውም ወደ ደስተኛዋ ዉብርስት። ጃሪም የለ፣ እሸቴ የለ፣ እርግዝና የለ
ሁሉም ደህና። ፍጹም ሰላም፡፡

“እመዋ?” አልኋት፣ እንጀራ ይዛ ወደ ሳሎን ብቅ ከማለቷ፡፡

ለወጉ ያህል ብቻ ቀና ብላልኝ፣ ወደ ማዕድ ቤት አልፋኝ ሄደች። ምን ላርግሽ፣ ይልቅ ማቀራረቡን አትረጅኝም? ማለቷ መሰለኝ። ከምኔዉ እንዲህ እንደ ተረጋጋሁ እሷንም ሳይደንቃት አልቀረም።

“ማነዉ የሰጠሽ ግን?” አልኋት፣

እግር በእግር እየተከታተልኳት።
“ማን ይመስልሻል?” አለችኝ፣ ፍርጥም ብላ።

“ብቻ እሽቴ ነዉ እንዳትዪኝ በማርያም”

“እሸቴ የሆነ እንደሆንስ? ስጦታ ሁሉ ያዉ ስጦታ አይደለም ወይ?”
“እህእ?”
ስጦታ ሁሉማ ያዉ አይደለም፡፡ ከእሸቴ ነዉ ማለት ነዉ? እንደ ፈራሁት መልሶ ከፋኝ፡፡ እንደገና ስምጥ ወደ ሆነዉ ድባቴ ዉስጥ ተወርዉሬ ወደቅሁ። መቼም ከእሱ ሌላ የእናቱን ድምፅ ቀርጾ በእናቴ በኩል የሚልክልኝ አይኖርም፡፡ ለዚያዉም ድምፁ ሌሊት ወፍ ጭጭ ሲል በድብቅ የተቀረጸ ነዉ የሚመስለዉ። ስለዚህ አብሮ የሚያድር ሰዉ ነዉ ማለት ነዉ የቀረጻቸዉ፡፡ ያም ሰዉ ከእሸቴ ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡ እሱ
ነዉ የላከልኝ። እጅ መንሻ መሆኑ ነዉ? የተጣላነዉ በእናቱ ይመስል፣ በዚህ ሊያባብለኝ መሞከሩ የበለጠ እልህ ዉስጥ ጨመረኝ፡፡

እናቱ ሌላ፣ እሱ ሌላ።

ራሴን ግን ታዘብሁት፡፡ ቶሎ የሚከፋኝ፣ ቶሎ የምደሰት ግልብ ሆኜ አርፌዋለሁ ማለት ነዉ በቃ? አሁን ለቅሶ፣ አሁን ሳቅ፣ እንደገና ለቅሶ?
ሰአሊ ለነ ቅድስት!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሐዘንም ሐፍረትም ቀላቅሎ ከመታኝ ይኸዉ ቀናት አለፉ፡፡ ያዉም እንደ ሙጀሌያም እየተሙጀለጀሉብኝ። በእነዚህ ቀናት ሁሉ በእመዋ ቤት ተደብቼ ራሴን አዳመጥሁት። እንደ ወትሮዬ ወደ አደባባይ ሳልወጣ፣
እንደ ድሮዉ በወዳጅ ሳልከበብ፣ እንደ ሁልጊዜዉ ወደ ሲራክ-፯ ማዕከል ሳልመላለስ ዐሥራ አንድ ረዣዥም ቀናት እያለፉኝ ሄደዋል። እንዲሁ አልፎ አልፎ ብቻ ሲልብኝ፣ ክራሬን አንስቼ ለብቻዬ እያንጎራጎርሁ በእናቴ ቤት ሰነበትሁ፡፡

በዚህ ምክንያት እመዋም ሁኔታዬን እያየች ስትብሰለሰል፣ እያሳዘነችኝ መጣች፡፡ ምናልባት ዘወር ብልላት ይቀላት እንደሆነ ብዬ፣ ሲራክ-፯ ለአንዳንድ ተልእኮዎች በማሰብ በምስጢር ቀድሞም ወደ ተከራየልኝ
ምስጢራዊዋ ቤት ደግሞ ሄድሁ። ይቺ ቤት፣ በተልእኮዬ ሂደት መሀል
እንድቀራረባቸዉ የሚያስገድዱ ሰዎች ቢኖሩ ቤቴ ብዬ የማሳያቸዉ ቤት ናት። እንደ ሁኔታዉ፣ እነዚህ ዒላማ የተደረጉ ሰዎች ረዥም ጊዜ እና የተለየ መቀራረብ የግድ የሚፈልጉ ስለሚሆን፣ የቤት ቡና የምጋብዛቸዉ በእመዋ ቤት ባለኝ ክፍል ሳይሆን፣ በዚሁ ምስጢራዊ የኪራይ ቤት ነዉ።

ወደ'ዚህ ቤት እንደመጣሁ፣ እመዋ አዘዉትራ እሸቴ ምን በደለሽ?»
ስትለኝ የሰነበተችዉ ጥያቂ ድንገት ሽዉ አለችብኝ፡፡ ገና ዛሬ፣ አሁን ገና። እንደገና አስብሁበት:: እዉነትስ ግን እሱ ምን በድሎኛል? ምንም። ምንም ወንጀል አጣሁበት። ቆይ እኔ ራሴ አይደለሁ እንዴ፣ ዓለም በቃኝ ብሎ
ከመነነበት የእናቱ ከተማ ሄጄ የተዋወቅሁት? እኔ ባልሄድበት እንኳንስ መበደል፣ ጭራሽ የት ያዉቀኝ ኖሯል? ደረስሁበት እንጂ አልደረሰብኝም እኮ፡፡ ይልቅስ ራሴ ነኝ በገዛ ሕይወቴ የተጫወትሁት። እኔን ማንም አልበደለኝም። ከተበደልሁም የተበደልሁት በራሴ ነዉ። እኔዉ ነኝ ራሴንም እግዚአብሔርንም የበደልሁት። ስለዚህ ራሴን ለካህን ማሳየት
አለብኝ።

ንስሐ ያስፈልገኛል።

ወዲያዉኑ ተስፈንጥሬ ተነሳሁና፣ ነጠላዬን እንደ ነገሩ አንገቴ ላይ ጥዬ ወደ መኪናዬ ሮጥሁ። ምስጢራዊዋ ቤቴ በአዲስ አበባ ልዩ ሰፈሩ ልደታ በሚባለዉ የምትገኝ ኮንዶሚኒየም ስለሆነች፣ ተዘግቶ እስከሚከፈት
የሚያጉላላኝ የአጥር በር የለብኝም፡፡ ይቺን መከራ ቻይ መኪናዬን ዛሬም ያለቅጥ ረግጬ አበረርኋት። የትራፊክ መብራት የሚባል ለቅጽበት አላስቆመኝም። ንስሐ አባቴ የሚያገለግሉት እዚሁ ልደታ ጎን ባለዉ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ቢሆንም፣ በዚህ አመሻሽ ግን እሳቸዉ የት
እንዳሉ አላዉቅም። በቤታቸዉ ሊሆኑ እንደሚችሉ በመገመት ነበር ቀጥታ ወደ መኖሪያ ቤታቸዉ የሄድሁ። እዚያ ስደርስ ግን አጣኋቸዉ።

አቤት ጥድፊያ! ስልክ ቁጥራቸዉ አለኝ አይደል እንዴ?
ደወልሁላቸዉ።
“እዚያዉ ልደታ እኮ ጉባዔ ላይ ነበርሁ። ምናለ ከመድከምሽ ፊት ደዉለሽ ብትጠይቂኝ ኖሮ ልጄ?” አሉኝ፣ በሐዘኔታ፡፡

“ግድየለም፡፡ እዚያዉ ልምጣ ታዲያ?”

“ምን ገዶኝ? ነይ በይ እዚሁ”
👍352
#ሳቤላ


#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


...አሮጌዉ ቤት በጨረቃ ብርሃን ሲታይ ጸጥ ቅዝቅዝ ብሎ ነበር " ያንለት ደግሞ ጨረቃዋ በጣም ደምቃለች « በብርሃንዋ ሰፊው ያታክልት ቦታም ዳር እስከ ዳር
ቁልጭ ብሎ ይታያል " በአየር ሁኔታ ማሳያው ያውራ ዶሮ ምሥል በበረንዳውና በባርባራ ላይም በማብራቷ ተለይተው ይታወቃሉ ባርባራ በረንዳውን ቀስ ብላ
አልፋ በፍርሃት ለጭንቀት እንዳፈጠጠች ከአትክልቱ ሥፍራ በታች ወደነበሩት እጅብ ያሉት ዛፎች ወረደች ያ ከዱሩ ወጥቶ እሷን በድብቅ ሲጠቅሳት የነበረው
ፍጡር ሌላ ተጨማሪ መዘዝ ይዞ የመጣ ሰው ይሆን ? ወይም †ፈጥሮው ከሰው የተለየ ልዩ ጉድ ነው ? ወይስ በውን የሌለ በሐሳብ ብቻ የተፈጠረ ባዶ ራዕይ ነው?
የሚሉ ጥያቄዎች በባርባራ አእምሮ ሲተራመሱባት አሁንም ቀረብ ብሎ ጠቀሳት ባርባራ ከፍራቷ የተነሣ እግሮቿ እየተንቀጠቀጡ ያንገት ልብሷን ጭምድድ አድርጋ ያዘች በጠራው ጨረቃ እሷ ወደሱ ስትጠጋ እሱ ደግሞ ወደ ዛፎቹ ጥላ አፈገፈገ" ባርባራ ቆም አለች

« ማነህ ? ምንድነህ ? » አለችው ድምጿን ዝቅ አድርጋ!«ምን ትፈልጋለህ ? »
« ባርባራ » ብሎ ጠራት በሹክሹክታ ድምፅ «አላወቅሽኝም ? » ገና ከመናገሩ
ድምፁ በትክክል ለየችው » ከደስታ ይልቅ ፍራት ያመዘነበት ድምፅ አሰምታ ተንደርድራ ወደሱ ሔዶች » በእርሻ ሥራ የዋለ ገበሬ የሚለብሰውን ዐይነት ልብስ
የለበሰ ሰው በክንዶቹ ዕቅፍ ሲያደርጋት ሥቅሥቅ ብላ አለቀሰች " የሥራ ካፖርት
ደርቦ የሣር ባርኔጣ ደፍቶ ሰው ሠራሽ ሪዝ አድርጎ ፍጹም ሌላ ሰው መስሎ ቢመጣም ወንድሟ መሆኑን ዐወቀችው

« ሪቻርድ ! ከየት መጣህ ? ከዚህ ምን አመጣህ ? እኔ ደግሞ ምናልባት ካንተ የተላከ ሰው እንደሆነ ብዬ ተጠራጠርኰ እንጂ እንደዚህ ሆነህ ትመጣለህ ብዬ
አላሰብኩም " አሁንም በጣም ነው ያስደነገጥኸኝ እውነት በጤናህ ነው ወይስ ዐብደህ የመጣኸው ? እዚህ ብትገኝ ሞት እንደሚጠብቅህ እያወቅህ እንዴት ደፍረሀ ትመጣለህ ? » አለችው እጆቿን እያፋተገች

«ያውም ከወንጀለኛ መስቀያ ላይ ነዋ እንደምገደል መች ጠፋኝ ባርባራ ዐውቀዋለሁ " »

« ታዲያ ለምንድን ነው ወደ መጥፈያህ ስተት ብለህ የመጣህ ? እማማ ብታይህ
በአድራጐትህና በድፍረትህ ደንግጣ ትሞታለች »

« ኑሮውን አልቻልኩትም ከወጣሁ ጀምሮ እስከ ዛሬ ለንደን ስሠራ ነበር ነገር ግን በዚሁ ዐይነት መግፋት አልቻልኩም
" ትንሽ ገንዘብ ባገኝ ግን ከዚህ የተሻለ ዕድል አለኝ " ስለዚህ አማማ ጥቂት ገንዘብ ብትሰጠኝ ለመጠየቅ ነው የመጣሁት»

« እስከ ዛፊ ምን ትሠራ ነበር ? »

« በአንድ የፈረሶች ጋጣ ውስጥ ነበር የምሠራው " »

« ምን ! በፈረሶች ጋጣ ? »
አለችው የእውነቷን ድንግጥ ብላ»
"ከዚህ የተሻለ ምን ዕድል ሊኖረኝ ይችላል ? ነጋዴ ? ባንከኛ ? መይስ የንድ ሚኒስትር ልዩ ጸሐፊ መሆን ? ነው ወይስ ንብረት ኖሮኝ በሀብቴ ልተዳደር?» አላት
የሆዱ ብሶት እየተናነቀው « አየሽ የምተዳደረው በሳምንት በማገኛት
ዐሥራ ሁለት ሽልንግ ብቻ ነው»

« አዬ ሪቻርድ ! » አለች እጁን ግጥም አድርጋ ይዛ እያለቀስች
« እንዴት ያሉ ጐደሎ ቀን ነው ? አየህ ......... እኛ የምንጽናናው ድርጊቱ በደም ፍላት እንጂ
ሆን ብለህ እንዳልፈጸምከው በማሰብ ብቻ ነው»

« ባርባራ እኔ እኮ ምንም ወንጀል አልፈጸምኩም »

« ምን? »

« በውነት እምልልሻለሁ ። ከደሙ ንጹሕ ነኝ እንዳያውም ሰውየው ሲገደል እኔ ከቦታወ አልነበርኩም " እስከማውቀው ድረስ በግምት ካልሆነ በቀር እገሌ ሲገድል አየሁ ብዬ በዐይን ምስክርነት መናገር እንኳ አልችልም " አላየሁም "
ግምቴ ግን ከማየት የማያንስ ትክክለኛ ነው »

ባርባራ አሁን በበላጠ አንዘረዘራት « መቸም ወንጀሉን የፈጸው ቤተል
ማለትህ እንዳልሆነ እርግኛ ነኝ »

« ቤተል ? እሱም በነገሩ የለበትም እሱ ለራሱ በድብቅ አውሬ ያድን
ነበር ፤ ወጥመዶቹን ነበር የሚከታተል »

« እማማ ግን በወንጀሉ የቤተል እጅ አለበት ያለች አላስቀምጠኝ አለች»

« ተሳስታለች እሱን እንድትጠረጥር ያዪረጋት ምንድነው ? »

« ከመጀመሪያ ይህ እምነት እንዴት እንዳደረባት ልነግርህ አልችልም እሷም ራሷ የምታውቀው አይመስለኝም " ወትሮም ቢሆን ምን ያህል ደካማ እንዶሆነችና በሐሳቧ የሚመጣባትን ሁሉ እውነት መስሎ እንደሚታያት አንተም ታስታውሳለህ አሁን ከዚያ አሠቃቂ ምሽት ጀምሮ ስለ ግድያው ሁልጊዜ ሕልም ታየኝ ትላለች በሕልሟ ውስጥ ሁሉ ቤተልም አብሮ ይታያታል " ስለዚህ ቤተል በነገሩ እንዳለበት ያለ ምንም መጠራጠር ታምናለች »

« ባርባራ እሱ በዚህ ጉዳይ አልነበረበትም »

« አንተ እንዳልነበርክበት ነው አሁን የምትነግረኝ ? »

« እኔ በዚያን ጊዜ ከሆሊጆን ቤትም አልነበርኩ " ወንጀሉን የፈጸመ ቶርን ነው»

« ቶርን ? » አለች አንገቷን ቀና አድርጋ « ቶርን ማነው ? »
« እንጃ ! ባውቀው ደስ ይለኝ ነበር ከገባበት መዝዤ ባወጣው በወደድኩ ሰውየው የአፊ ወዳጅ ነበር ። »

“ሪቻርድ !! ... ይህን ስም ስታነሣብኝ ራስህን የዘነጋህ መስልከኝ ” አልችው አንገቷን በቁጣ ወዶ ኋላ ምልስ አድርጋ

«እኔ!ኮ አንድ ጊዜ ያበላሸሁት ስለሆነ በጉዳዩ ለመነጋገር አልሻም " አሁን ስለ ንጽሕናዬ ብናገር ሪቻርድ ሔር ትንሹ በፈጸመው የግፍ ግድያ ተብሎ የተላለፈብኝን ውሳኔ ሊያስለውጥልኝ አይችልም። ግን አባባ ዛሬም እንደ ጠላኝ ነው »

«ከፊቱ ስምህን የሚያነሣ የለም " ከቤት አንድም ሰው ስምህን እንዳይጠራ ለአሽከርቹ በሙሉ ትእዛዝ ሰጥቶአል " ያቺ ኤልሳ መቸም የተነገረችውን ማስታወስ አይሆንላትም " መኝታ ቤትህን የሚስተር ሪቻርድ ክፍል " እያለች ስትናገር ሁለት ጊዜ ቢያስጠነቅቃትም እየረሳች መተው አልቻለችም " በሦስተኛው ከቤት አባረራት ። አባባኮ ምሏል ሰም†ሃል ? »

« ምን ብሎ ? እሱ ሁልጊዜ እንደማለ ነው »

« ያሁኑ ግን ከባድ መሐላ ነው ሪቻርድ።ፍርድ ከተሰጠ በኋላ ከ0ሥር ዓመት በኋላ ቢገኝ እንኳን አሳልፎ እንደሚሰጥህ ከዳኞቹ ፊት ቁሞ በመማል አረጋግጦላቸዋል እሱ አንድ ጊዜ ከተናገረ እንደማይመለስ ታውቀዋለህ » ስለዚህ ያንተ ከዚህ አካባቢ መገኘት አደገኛ ነው»

« እሱኮ ዱሮውንም እንዶ ልጁ እንዳልቆጠረኝ ሊያደርግልኝ የሚገባውን እንዳላደረገልኝ ዐውቃለሁ » አለ ምርር ባለ አነጋገር « እስኪ አንቺ ስታስቢው
ጤና በማጣቴ ምስኪኗ እናቴ ስለ ተንከባከበችኝ በየደረሰበት ላገኘው ሰው ሁሉ ተሞላቀቀ እያለ ሊያሥቅብኝ ይጥር ነበር እኔ ቢቴ የደስታ ቤት ቢሆንልኝ ኖሮ ይኸ ሁሉ መቸ ይደርስብኝ ነበር ? በይ አሁን ... ...ባርባራ እናቴ ጋር ዐይን ለዐይን ተያይተን መነጋገር አለብን»

ባርባራ ከመናገሯ በፊት ትንሽ አሰበች« እንዴት እንደ ምናሳካው አላውቅም»
« ለምን አንቺ እንደ መጣሺው እሷስ ወደኔ አትመጣም? ለመሆኑ ተኝታለች ወይስ ተነሥታለች ? »

« ዛሬ ከሷ ጋር መተያየት የማይሆን ነገር ነው አባባ ሳናስበው ሊመጣ ይችላል
አሁን ያለው ከቦሻ ቤት ነው»

« ዐሥራ ስምንት ወር ሙሉ ሳንተያይ ኖረን አሁን ደግሞ ሳላገኛት ብሔድ በጣም ከባድ ነገር ነው » አለ ሪቻርድ «የገንዘቡ ነገርስ? አንድ መቶ ፓውንድ ነውየምፈልገው »
👍24😁2
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_አምስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


ወደ ሀብታምነት ጉዞ

እናታችን እቃዎቿን ስታሽግ እኔና ክሪስቶፈር ደግሞ ልብሶቻችንን ከጥቂት አሻንጉሊቶችና ከአንድ መጫወቻ ጋር በሁለት ሻንጣዎች ውስጥ ማጨቅ ጀመርን: በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ አንድ ጓደኛችንን እንኳን ሳንሰናበት ታክሲ መጥቶ ወደ ባቡር ጣቢያ ወሰደን፡ እናታችን ማንንም ሳንሰናበት
በሚስጥር ሹልክ ብለን እንድንሄድ የግድ ያለችን ለምን እንደሆነ አልገባኝም።

ባቡሩ ብዙ ከተሞችና መንደሮች እንዲሁም እርሻ ቦታ ላይ ያሉ ቤቶችን እያቆራረጠ ወደ ቨርጂኒያ ግዛት ሲያመራ እኔና ወንድሜ አንድም ነገር እንዳያመልጠን ብለን መተኛት አልፈለግንም በዚያ ላይ ብዙ የምናወራችው
ነገሮች ነበሩን፡ ወሬያችን በአብዛኛው ስለዛ ትልቅ የሀብታም ቤት፣ ተንደላቀን ስለመኖር፣በወርቅ ሳህን ስለመመገብና የሚያምር ልብስ በለበሰ ሰራተኛ
ስለመስተናገድ ነበር ልብሶቼን የምታጣጥፍ፣ የገላ ውሀ የምታዘጋጅ፣ ፀጉሬን
የምታበጥርልኝና ባዘዝኳት ቁጥር ከች የምትል የግል ሠራተኛ እንደምትኖረኝ አሰብኩ ግን በጣም ክፉ አልሆንባትም በጣም የምወደውን ዕቃ ካልሰበረችብኝ
በስተቀር ሠራተኞች ሁሉ የሚመኟት አይነት ደግ እመቤት ነው የምሆንላት መቼም የማልወዳቸውንና የማልፈልጋቸውን ነገሮች መጣሌ ስለማይቀር በደንብ ነው የምከፍላት፡

በዚያ ምሽት ባቡሩ ውስጥ እያለን ጨለማውን ወደ ኋላ ስመለከት ምሽቱ ማደግና መፈላሰፍ የጀመርኩበት የመጀመሪያ ምሽት እንደሆነ አስተዋልኩ ሁሉንም ለማግኘት የሆነ ነገር ማጣት ስላለ እኔም የሚመጣውን ልለምደው
እና በጣም ጥሩ ላደርገው ያስፈልጋል እኔና ወንድሜ ገንዘቡ እጃችን ውስጥ ሲገባ በምን እንደምናጠፋው እየተነጋገርን
እያለ ፀጉሩ በመመለጥ ላይ ያለ የባቡሩ ሠራተኛ ወዳለንበት መጣ። የመጣበት ከመናገሩ በፊት እናታችንን በአድናቆት ከእግር እስከራሷ ተመለከታት። ከዚ
“ወ/ሮ ፓተርስን፣ በአስራ አምስት ደቂቃ ውስጥ መውረጃሽ ጋር እንደርሳለን አላት።

አሁን ደግሞ ለምንድነው “ወ/ሮ ፓተርሰን” ብሎ የጠራት? ግራ ገባኝ፡ ክሪስቶፈርን በጥያቄ አይን ተመለከትኩት እሱም ግራ የተጋባ ይመስላል።

ድንገት ስትነቃ የት እንዳለች ግር በመሰኘቷ የእናታችን አይኖች በሀይል ተከፈቱና ትኩረቷ ወደ ባቡሩ ሠራተኛ፣ ቀጥሎ ወደ እኔና ክሪስቶፈር ከዚያ ደግሞ ተስፋ በመቁረጥ እንቅልፍ ውስጥ ወዳሉት መንትዮች ተሻገረ። ወዲያው እምባዋ መጣና ከቦርሳዋ ውስጥ መሀረብ አውጥታ አይኖቿን ጠረገች። ሀዘን
በተሞላበት አይነት በከባዱ ስትተነፍስ ልቤ በሽብር መምታት ጀመረ።

አሁንም ቆሞ በአድናቆት እየተመለከታት ላለው የባቡሩ ሠራተኛ እሺ አመሰግናለሁ አትስጋ፣ ለመውረድ ተዘጋጅተናል” አለችው: የኪስ ስዓቱን ተመለከተና የጭንቀት እይታውን ወደ እኔና ክሪስቶፈር ከዚያ ደግሞ ወደ የተኙት መንትዮች አደረገ። ከዚያ “እመቤቴ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ነው ስትወርዱ የሚጠብቃችሁ ሰው አለ?” አላት።

“ችግር የለም” ስትል እናቴ አረጋገጠችለት።

“እመቤቴ በጣም ጨለማ እኮ ነው”

“የቤቴን መንገድ በእንቅልፍ ልቤ እንኳን አውቀዋለሁ።”

የአያት አይነት ባህርይ ያለው የባቡሩ ሠራተኛ የተናገረችው ነገር አላረካውም። “እመቤት፣ ቻርለትስቪል ከመውረጃችሁ የአንድ ሰዓት መንገድ ነው: አንቺንና ልጆቹን የምናወርዳችሁ ቤት የሚባል ነገር በማይታይበት ቦታ ላይ ነው አላት።

እናቴ ተጨማሪ ጥያቄዎችን ላለመፍቀድ በጣም ትዕቢት በተሞላበት አነጋገር
“የሆነ ሰው ይጠብቀናል” አለችው ባንድ ጊዜ እንዴት እንደዚህ ያለ ባህርይ ልታመጣና ወዲያው ደግሞ ልክ እንደ ኮፍያ በቀላሉ ልታወልቀው እንደቻለች ማየት ያስገርማል።

እውነትም ምንም ነገር በሌለበት ቦታ ደረስን ከባቡሩ ወረድን፡ ከባቡር ስንወርድ ሙሉ በሙሉ ጨለማ ቢሆንም ማንም የጠበቀን አልነበረም: የባቡሩ ሠራተኛ እንዳስጠነቀቀን አንድም የሚታይ ቤት የለም። በጨለማ ብቻችንን
የሰው ፍጥረት በማይታይበት ቆም ብለን የባቡሩ ደረጃ ላይ ለቆመው የባቡሩ ሠራተኛ የስንብት እጃችንን አውለበለብንለት ከገፅታው እንደተረዳሁት “ወ/ሮ ፓተርሰንን” ፦ሤከአራት እያንቀላፉ ካሉ ልጆቿ ጋር ትቶ መሄዱ ደስ አላሰኘውም።
ዙሪያውን ስመለከት ማየት የቻልኩት በአራት የእንጨት ምሰሶዎች የተደገፈ የዛገ የቆርቆሮ ጣራና አረንጓዴ አግዳሚ ወንበር ብቻ ነው፡ የባቡር ጣቢያው
መሆኑ ነው። ባቡሩ በጨለማው ውስጥ እስኪሰወርና መልካም ዕድል እየተመኘልን የሚመስል አንድ አሳዛኝ የጥሩምባ ድምፁን እስክንሰማ ድረስ ቆመን እያየነው ነበር።

በሜዳና በመስኮች ተከበናል ከባቡር መውረጃው ጀርባ ካለው ጫካ ውስጥ የሆነ የተለየ ድምፅ ስሰማ በድንጋጤ ዘለልኩና ምንነቱን ለማወቅ ዙሪያውን
ረስመለከት ክሪስቶፈር ሳቀብኝ።“ጉጉት እኮ ናት! ጣረሞት መስሎሽ ነበር?”
አለኝ።
እናታችን “አሁን ማንም የለም: በሹክሹክታ መናገር የለባችሁም: ይህ የእርሻ ሀገር ነው በአብዛኛው ያሉት የወተት ላሞች ናቸው። ዙሪያውን ተመልከቱ። የስንዴና የአጃ እንዲሁም የገብስ መሬቶች ናቸው። እዚህ ያሉት ገበሬዎች ናቸው ኮረብታው ላይ ለሚኖሩት ሀብታሞች ምርቶቻቸውን በትኩሱ
የሚያቀርቡት”

ተቀጣጥለው የቆሙ በጣም ብዙ ኮረብታዎች ሲኖሩ ኮረብቶቹ ላይ በንፋስ ላይና ታች የሚሉ በርካታ ዛፎችም ተደርድረዋል። የምሽት ዘበኞች ብዬ ጠራኋቸው። እናታችን ግን ተደርድረው የተተከሉት በርካታ ዛፎች ከባዱን
ነፋስ ለመከላከልና ከባድ በረዶ ሲመጣ እንዲይዙ መሆኑን ነገረችን። ንፋስና በረዶ ክሪስቶፈርን የማረኩት ትክክለኛ ቃላት ነበሩ። ምክንያቱም በበረዶ
የሚደረጉ ሁሉንም አይነት የክረምት ስፖርቶች ይወዳል። እና እንደ ቨርጂያ ያለ የደቡብ ክፍል ከባድ በረዶ ይኖረዋል ብሎ አላሰበም።

“እዚህም በረዶ ይጥላል” አለች እናቴ: “ያለነውኮ ከብሉሪች ተራራዎች ስር ነው: ልክ እንደ ግላድስተን እዚህም ብርድ አለ። በበጋ ቀኑ በጣም ይሞቃል፤
ምሽቱ ግን ሁልጊዜም ቢያንስ አንድ ብርድ ልብስ ብቻ የሚያስለብስ ቅዝቃዜ አለው አሁን ፀሀዩዋ ብትወጣ ኖሮ ውብ የሆነውን ገጠር ማየት ትችሉ ነበር።በዓለም ላይ የዚህን ያህል የሚያምር ቦታ የለም አሁን በጣም መፍጠን አለብን ቤት ለመድረስ በጣም ረጅም መንገድ ይጠብቀናል። ከመንጋቱና
ሠራተኞቹ ከመነሳታቸው በፊት መድረስ አለብን፡” አለችን፡።
በጣም ይገርማል፡ “ሰራተኞቹ ከመነሳታቸው በፊት? ለምን? የባቡሩ ሠራተኛ ወ/ሮ ፓተርሰን ብሎ የጠራሽ ለምንድነው?” ብዬ ጠየቅኳት፡፡

"ካቲ አሁን ለአንቺ የማብራራበት ጊዜ የለኝም:: እየፈጠንን መራመድ አለብን አለችና ሁለቱን ከባባድ ሻንጣዎች አንስታ ጠንhር ባለ ድምፅ እንድንከተላት
አዘዘችን፡ እኔና ክሪስቶፈር እንቅልፋቸው ከመምጣቱ የተነሳ ለመራመድ ሙከራ ማድረግ ያልቻሉትን መንትዮቹን ለመሸከም ተገደድን።

ትንሽ እንደተራመድን “እማዬ የባቡሩ ሠራተኛ የአንቺን ሁለት ሻንጣዎጆ ሳይሰጠን ረስቶታል” አልኳት።

“ምንም አይደል ካቲ፤ ሻንጣዎቹን ወስዶ ሻንጣ ክፍል ውስጥ እንዲያደርግልኝ ነገ እንደምወስደው ነግሬዋለሁ” አለችኝ: የያዘቻቸው ሁለት ሻንጣዎች ጥንካሬዋን እንደቀነሱት ሁሉ ትንፋሽዋ ቁርጥ ቁርጥ እያለ ነበር

“ለምንድነው እንደዚያ ያደረግሽው?” ሲል ጠየቃት ክሪስቶፈር።
👍33🥰41
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አምስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ


...ለሁለት ቀን ቤርጎ ትከራይና በሚቀጥለው ቀን ትወጣለች ምድር ጦር
መምሪያ ተመዝግባ ለሆቱሉ በመደወል የሆቴል ኪራዩን ደረሰኝ ለአባቷ ጠበቃ እንዲላክ ታደርጋለች፡
በረጅሙ ተነፈሰችና በሩን ከፍታ ገባች፡፡

ማርጋሬት በቀጥታ ወደ እንግዳ ተቀባዩ አመራች ከፍተኛ እረፍት ተሰማት። ፍርሃትና ቅዠቱ አብቅቷል።
አንድ ወጣት እንግዳ ተቀባይ ባንኮኒ ተደግፎ ያንጎላጃል። ማርጋሬት
‹‹እህምም›› ብላ ጉሮሮዋን ስትጠራርግ ወጣቱ ነቃ ድንጋጤ እና መደናገር
ፊቱ ላይ ይታያል።

‹‹ቤርጎ አላችሁ?›› ስትል ጠየቀችው፡
‹‹በዚህ ሰዓት?›› ሲል መለሰ።
‹‹ጨለማው አላስኬድ አለኝና እቤት መሄድ አልቻልኩም››
ወጣቱ ራሱን ገዛና ‹‹ሻንጣሽ የታለ?›› ሲል ጠየቃት።
<<የለኝም›› አለች ማርጋሬት በማፈር፧ ከዚያም አሰብ አደረገችና
‹‹የለኝም ጨለማው አያስኬደኝም ብዬ አላሰብኩም ነበር›› አለች
ወጣቱ ሁለመናዋን አስተዋለ። ፊቱን ደባበሰና መዝገቡን የሚያይ
መሰለ። ሰውዬው ምን ነካው? ስትል አሰበች።

‹‹ቦታ የለንም›› አላት።
‹‹አላችሁ››
‹‹ከአባትሽ ጋር ተጣልተሽ ነው አይደለም?›› አላት እየጠቀሳት።
‹‹አይደለም፣ እቤት መሄድ ስላልቻልኩ ነው›› ስትል ደገመች።
‹‹ታዲያ ምን ላድርግ ሂትለርን ጠይቂ››
ልጅነቱን አየችና ‹‹አለቃህ የት ነው?›› አለችው፡
የተሰደበ መሰለው ‹‹እስከ ጧቱ 12፡00 ሰዓት እኔ ነኝ ኃላፊው›› አላት
ማርጋሬት ዙሪያውን አየችና ‹‹እስኪነጋ እዚሁ እቀመጣለሁ›› አለች
በመሰላቸት፡
‹‹አይቻልም!›› አለ ወጣቱ ፈርቶ ሻንጣ ያልያዘች ኮረዳ እንግዳ መቀበያ
ክፍል ልታድር?› ሲል አሰበና ‹ቀዚህ ምክንያት ከስራ እባረራለሁ›› አላት።
‹‹እኔ ኮረዳ አይደለሁም›› አለች ብልጭ ብሎባት፤‹‹እኔ እመቤት ኦክሰንፎርድ ነኝ›› ማዕረጓን መጠቀም አልፈለገችም ነበር፤ ምን ታድርግ፡
ይህን ብትልም ምንም አልጠቀማትም፡ እንግዳ ተቀባዩ ገላመጣትና
‹‹ትቀልጃለሽ!›› አላት በማሽሟጠጥ።ማርጋሬትም ልትጮህበት አሰበችና መልኳን በመስታወት ስታይ ዓይኗ እንደጠቆረ ተገነዘበች ከዚያም በላይ እጇ ቆሽሿል፤ ቀሚሷም ተቀዳል፡
እንግዳ ተቀባዩ ቦታ የለንም ማለቱ አያስደንቅም: በተስፋ መቁረጥ ‹‹መቼም
ጨለማ ውስጥ ሂጂ አትለኝም!›› አለችው:
‹‹ከዚህ ሌላ የምልሽ የለም›› አላት።

ማርጋሬት ዝም ብዬ ብቀመጥና ከዚህ አልነቃነቅም ብል እንግዴ
ተቀባዩ ምን ይለኝ ይሆን? ስትል ራሷን ጠየቀች፡፡ ይኸው ነው ማለት የፈለገችው ምክንያቱም በጣም ደክሟታል፤ ሰውነቷም ዝሏል ለጠብ
የሚሆን ጉልበት የላትም፡፡ ከዚህም በላይ ውድቅት በመሆኑ ወጣቱ ምን
እንደሚያደርጋት አይታወቅም፡፡

ሰውነቷ እንደዛለ ጀርባዋን ሰጥታው እንደከፋት ወጥታ ጨለማ ውስጥ ገባች፡፡ እየሄደችም ከእንግዳ ተቀባዩ ጋር ልጣላ ይሆን?› ስትል ነገር ስታስብ ይበልጥ ኃይል ያላት የሚመስላት? አሁን እጅ ከሰጠች በኋላ
አሰበች፡፡ ግን ለምንድ ነው ከምታደርገው ይልቅ ማድረግ የምትፈልገው
ይበልጥ መናደዷ ገረማት፡፡ እንደ ንዴቷ ከሆነ ከእንግዳ ተቀባዩ ጋር ትጣላ ነበር፡፡ ተመልሳ ለመሄድ ፈለገች፡ ሆኖም ወደፊት መራመዷን ቀጠለች:: አዎን መሄዱ ነው የሚሻለው፡፡

ዳሩ ምንም መሄጃ የላትም፡፡ ከእንግዲህ የካትሪንን ቤት ማግኘት አትችልም፡፡ የአክስቷ ቤት ጠፍቶባታል፡ ሌሎች ዘመዶቿን አታምናቸውም ሰውነቷ ስለቆሸሽም ቤርጎ ማግኘት አልቻለችም፡

እስኪነጋ መዞር ትችላለች፡፡ አየሩ ጥሩ ነው፡፡ ዝናብ ስለሌለም ብዙም
አይበርድም፡፡ ያለማቋረጥ ከተራመደችም አይበርዳትም አሁን ያለችበት መንገድ ላይ ብዙ የትራፊክ መብራት ስላለ የምትሄድበትን መንገድ ማየት ትችላለች በየደቂቃው መኪና ይተላለፋል፡፡ ከየምሽት ክበቡ ሙዚቃና ሁካታ ይሰማታል፡፡ በየመንገዱ ሽክ ያሉ ሴቶችና በየፓርቲው ያመሹ ሱፍ ግጥም አድርገው የለበሱ ወንዶች በሾፌር በሚነዱ መኪኖች ሲሄዱ ታያለች፡፡ አለፍ እንዳለች ሶስት ብቸኛ ሴቶች አየች፣ አንዷ በር ላይ ሌላዋ ደግሞ ስልክ እንጨት ተደግፋ ቆማለች፣ ሶስተኛዋ መኪና ውስጥ ቁጭ ብላለች፡፡ በአንድ ወቅት እናቷ ኑሮ የጨለመባቸው ሴቶች ያሏት እነዚህን ሳይሆን አይቀርም፡
ድካም ተሰማት ጫማዋ ከቤት እንደወጣች ያደረገችው ነጠላ ጫማ
ነው: ያገኘችው ደጃፍ ላይ ቁጭ አለችና ጫማዋን አውልቃ እግሯን
አከከች።

ቀና ስትል ከመንገዱ ባሻገር ያለው ህንፃ ቅርፅ በመጠኑ ታያት፡፡ እየነጋ ይሆን? በጧት የሚከፈት ሻይ ቤት ታገኝ ይሆናል። ለቁርስ የምድር ጦር መምሪያው የምግብ ክፍል እስኪከፈት ትቆያለች፡፡ ምግብ ከበላች ረጅም ጊዜ በመቆጠሩ የአሳማ ስጋና እንቁላል ትዝ ሲላት በአፏ ምራቋ ሞላ፡፡

ድንገት ቁልቁል የሚያያት አመድ የመሰለ ፊት ድቅን አለባት በድንጋጤ ጮኸች፡፡ ሰውዬው ወጣት ነው፡ ታዲያስ ቆንጂት›› አላት፡

እመር ብላ ተነሳች፡፡ ሰካራም አትወድም፡፡ እነሱ ክብራቸውን የሸጡ ናቸው፡፡ ‹‹ሂድ ጥፋ ከዚህ!›› አለች ቆጣ ብላ፤ ድምጿ ግን ይንቀጠቀጣል፡ቀስ እያለ ተጠጋት ‹‹ታዲያ ሳሚኛ›› አላት፡፡
‹‹አላደርገውም!›› አለች በንዴት ከእሱ ለመሸሽ ወደኋላዋ ስትሄድ ጫማዋ ወለቀባት፡፡ ዞር ብላ ጫማዋን ፍለጋ ስታጎነብስ ወጣቱ አስካካና እጁን ጭኖቿ መሀል ሰዶ ጎነታተላት፡፡ ጫማዋን ይዛ በፍጥነት ቀጥ ብላ
ቆመችና ‹‹ሂድ ከአጠገቤ›› ብላ ጮኸች፡፡

እንደገና ሳቀባትና ‹‹ልክ ነሽ፤ ሴቶች እምቢ ሲሉኝ ደስ ይለኛል›› አለና
የጠጣውን አልኮል ሲተነፍስባት አቅለሸለሻት፡፡ አንቆ አፏን ግጥም አድርጎ
ሳማት፡፡

ሁኔታው ሁሉ የሚያስጠላ ነው፤ ሆዷ ታወከ፡፡ አጥብቆ ስለያዛት ለመታገል ቀርቶ ለመተንፈስ አቃታት፡፡ ለማምለጥ ሙከራ ብታደርግም ለሀጩን እያዝረበረበ ይስማታል፡፡ ከዚያም አንድ እጁን ወደ ጡቷ ሰደደና በእጁ ሲጨመድደው ላንቃዋ እስኪላቀቅ ጩኸቷን ለቀቀችው፡፡

‹‹ደህና፧ ልጎዳሽ አይደለም፧ አታምርሪ›› አላት፡፡ እሷ ግን ጩኸቷን ቀጠለች፡ ሰዎች ከየቦታው ብቅ ብቅ አሉ፡ ሰካራሙ ሰው መምጣቱን ሲያይ ጨለማው ውስጥ ገብቶ ተሰወረ፡ ማርጋሬትም ጩኸቷን አቁማ ለቅሶዋን
ተያያዘችው፡:

አንድ ፖሊስ ባትሪውን እያበራ መጣና ፊቷ ላይ አበራባት፡፡ ከተሰበሰቡት ሰዎች መሀል አንዲት ሴተኛ አዳሪ ‹‹እቺ ልጅ ሽሌ አይደለችም›› አለችው ፖሊሱን፡፡
ፖሊሱ ‹‹ስምሽ ማነው ልጅት?›› አላት
‹‹ማርጋሬት ኦክሰንፎርድ››
‹‹እመቤት ማርጋሬት ኦክሰንፎርድ ነሽ?›› ሲል ጠየቃት፡፡
ማርጋሬት ንፍጧን ወደ ውስጥ ሳበችና ራሷን ነቀነቀች በአዎንታ
‹‹ነግሬሃለሁ አይደል! ሸሌ አይደለችም›› አለችው ሴተኛ አዳሪዋ፡፡
‹‹ነይ እንሂድ የኔ እመቤት፣ አይዞሽ›› አላት በማጽናናት፡፡
ማርጋሬት በእጅጌዋ ፊቷን ጠርጋ ተነሳች፡:
ፖሊሱ ባትሪውን እያበራ አብረው ሄዱ፡በፍርሃት እየተርገፈገፈች ‹‹ሰውዬው እንዴት ያስፈራል!›› አለች፡፡
‹‹ሀዘኔታ የጎደለው ነው እሱ ምን ይፈረድበታል›› አለ ፖሊሱ ሳቅ እያለ፡፡ ‹‹ይህ ቦታ ከለንደን መንገዶች ሁሉ አደገኛው ነው፡፡ በዚህ ሰዓት
የምትጓዝ ሴት የምሽቱ እመቤት የሆነች ሴት ብቻ ናት፡››

ማርጋሬት ፖሊሱ ያለው ትክክል ነው አለች በሆዷ፡
‹‹ትኩስ ሻይ እንሰጥሽና ብርዱ ለቀቅ ያደርግሻል›› አላት ወደ ጣቢያው ገቡ፡፡ ከባንኮኒው ኋላ ሁለት ፖሊሶች ይታያሉ፡ አንዱ
ጎልማሳና ወደል ሲሆን ሌላው ደግሞ ወጣትና ከሲታ ነው፡፡ ክፍሉ ከጥግ
እስከ ጥግ በእንጨት ባንኮኒ ተገጥግጧል፡፡ ጣቢያው ውስጥ አንዲተ ሴት ትታያለች፡፡

‹‹እዚህ ቁጭ በይ›› አላት ፖሊሱ፡፡ማርጋሬት ተቀመጠች
👍28👎2
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አምስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


...ካለ ሽማግሌ ፈቃድ የተወለደ ግን እንደ እርኩስ ስለሚቈጠር የማደግ ዕድል አያገኝም" የማስወረድ ዘዴውም ልምድ ያላቸው ሰዎች በማኅፀን ውስጥ ያለውን ፅንስ  ጭንቅላት ከውጭ በኩል በመዳሰስ ሲያገኙ ጭንቅላቱን በሁለት አውራ ጣታቸው ውስጥ ደጋግመው በመጭመቅ..» ሲል ካርለት ፊቷ በስሎ የተበላሸ ቲማቲም መሰለ፣ ከንፈሮቿ ተንገረበቡ፣ መላ አካሏ ራደ"

ከሎ ግን ንግግሩን ቀጠለ፣ «...እድታስወርድ ይደረጋልI ከተወለደም ሕፃኑ ጫካ ይጣላል። ስለዚህ አንድ የሐመር ሴት በሽማግሎች ፈቃድ ማርገዟ ከታወቀ በኋላ ከባሏ ጋር ግንኙነት ሳታደርግ ፅንሱ አድጎ መውለጃዋ ሲደርስና ምጥ ቢይዛት በአካባቢዋ የሚኖሩ
ሴቶች ይሰበሰቡና እጅና እግሯን ጥፍር አድርገው ይዘው፣ አፍዋን ያፍኗታል" ይህም ልጁ የእናቱን ማኅፀን ለቆ ተፈትልኮ
እንዲወጣ ይረዳል» ሲል ካርለት ፍርሃት መላ አካሏን አንገጫገጨው። እሷም እንደታፈነች ሁሉ ልቧ ዘለለባት።

«ውልጃ ባፈና? በምጥ ላይ ሌላ ምጥ? » ከሎ ግን ጨዋታውን ቀጠለ።

«እንግዲህ እንደ ነገሩ ታርሳ ራቁቱን ለተወለደው ሕፃን መታቀፊያ፣ ፎጣ፣ ሙቀት፣ ጂኒ ጃንካ ሳያስፈልገው የቡና ውኃ በማጠጣት
አቀባበል ይደረግለታል። ልጁ ቁሩንና ሙቀቱን ተቋቁሞ አደግ እያለ
ሲመጣ ግን እናቱ ከማማጡ በላይ ትጨነቃለች አባትም ውስጥ
ለውስጥ ይሳቀቃል።

የሚጮኸው ጅብ ሆድ ዕቃዋን፣ የከሎ ወሬ ደግሞ ሕሊናዋ አተረማመሰባት። ትሰማዋለችI የምትሰማው ግን ለማወቅ ሳይሆን
በቃ ከአቅሜ በላይ የሆነ ‹አስፈሪ ነው ብላ መናገር ተስኗት ነው ደንታ ቢሱ ከሎ ግን ጨዋታውን ቀጠለ"

«በሐመር ማኅበረሰብ ላም፣ በሬ፣ በግ...ጥርስ የሚያበቅሉት በታችኛው ድዳቸው ስለሆነ ‹ቅዱስ› ሲባሉ አህያ፣ ፈረስ፣ ጅብ...
ጥርስ የሚያበቅሉት በላይኛው ድዳቸው በመሆኑ እርኩስ ይባላሉ"
የሰው ልጅም የመጀመሪያውን (የወተት ጥርስ ማብቀል የሚገባው
እንደ ቅዱሳን እንስሳት በታችኛው ድዱ መሆን ሲኖርበት፣ እንደ እርኩሳን እንስሳት በላይኛው ድዱ ካበቀለ ከእርኩሳን እንስሳት እንደ አንዱ ስለሚቆጠር ለማኅበረሰቡ አይበጅም ቢያድግም አባቱ
የሚጋፋ፣ የሚገድል፣ የሚበጠብጥ ስለሚሆን ገፊ ወይንም በአካባቢው አጠራር «ሚንጊ» ተብሉ ይጣላል።
«ጥርስ እንደማብቀሉ ሁሉ መውለቁ ላይም በቅድሚያ መውለቅ የሚገባው በታችኛው ድድ የበቀለው ጥርስ መሆን ሲገባው፣
በላይኛው ድዱ የበቀለው ጥርስ ቀድሞ ከወለቀ ሚንጊ ነው ተብሎ
አሁንም ይጣላል ከዚህ በተጨማሪም፣ ሕፃኑ የታችኛው ጥርሱ ከመውለቁ በፊት በአጋጣሚ እንኳ ወድቆ ወይንም በሌላ መንገድ
የላይኛው ጥርሱ ቢወልቅ ሚንጊ ተብሎ ከማኅበረሰቡ እንዲወገድ ይደረጋል» ከሎ ሆራ «ኢ ህ አለና፣

«እና እኔም እንደነገርኩሽ ሚንጊ ነኝ» አላት"

«ታዲያ አንተ ‹ሚንጊ ነህ› ተብለህ ተጥለህ ነበር?» ካርለት፣ ካለማብራሪያ መልሱን በአሉታ ወይንም በአወንታ እንዲመልስላት
በሕሊናዋ እየተማጸነች ጠየቀችው"

«አዎ!» ብሎ፣ ጭንቅላቱንና ትከሻው ላይ በጦር የተወጋውንና በድንጋይ የተፈነከተውን አሳያት" ከዚያ ቀና ብሎ ጨለማውንና
ከዋክብቱን ተመለከተና እንዴት አድርገው እንደ ጣሉት ጨዋታውን
ሲቀጥል ካርለት በሕሊናዋ «ከሎ ለእኔም የሚያዝን አንጀት ይኑርህ እንጂ» በማለት፣ እየተብሰከሰከች የማይቀርላትን ጨዋታ ለመስማት ጉንጯን በጣቶቿ ደግፋ፣ ዓይኖቿን በማፍጠጥ ዓይን ዓይኑን
ተመለከተችው"

«እኔ የተወለድኩት ሐመሮች ተሰባሰቡበት ከሚባለው የቡስካ ተራራ ስር ላላ ከተባለው መንደር ነው" እናቴ በንቲ ኃይሎ ትባላለች" አባቴ ደግሞ ሆራ ሸላ ይባላል። እናቴ ለአባቴ አምስተኛ ሚስት ስትሆን፣ አምስት ልጆችም ወልዳለታለች" እናቴ፣ በልጅነቴ ሁል ጊዜ በምትለብሰው ቆዳ ሸፈን አድርጋ ከሰውነቷ ጋር ትለጥፈኝና ስቅስቅ ብላ ስታለቅስ ቆይታ፣ «ጨዋንዛ» በሚባል ሸካራ ቅጠል
ጥርሴን ትሞርድልኝ ነበር" በወቅቱ ባይገባኝም ኋላ ኋላ ግን የተጣልሁበትን ምክንያት ስሰማ የጥርስ አበቃቀሌ በትክክለኛው መንገድ ማለትም መጀመሪያ በታችኛው ድዴ፣ ቀጥሎ በላይኛው ድዴ ነበር አሉ የበቀለው" ይሁን እንጂ፣ አንድ ጊዜ ጥጃ
ለመመለስ ስሮጥ ወድቄ የላይኛው ጥርሴ አንዱ ወለቀ፣ አንደኛው
ተሸረፈ። እንዳበቃቀሉ ሁሉ፣ በቅድሚያ የታችኛው ድዴ ላይ የበቀለው ጥርስ መውለቅ ሲገባው፣ የላይኛው ጥርሴ ቀድሞ
በመውለቁ፣ ለአደጋ ተጋለጥሁ" እናቴ፣ በሸካራው የጨዋንዛ ቅጠል
ጥርሴን ስትሞርድልኝ የነበረው ለካ የታችኛው ድዴ ጥርስ ቀድሞ የወለቀ ለማስመሰል ኖሯል"

«ይሁን እንጂ፣ ጥረቷ ከንቱ ነበር" ወድቄ ሳለቅስና ጥርሴ ወልቆ ያዩኝ ሰዎች ለሽማግሎች መንገራቸው አይቀሬ ነበር" እናም አንድ
ቀን አባቴ ባልነበረበት ወቅት፣ ሚንጊ የተባሉ ልጆችን የሚጥሉ
ሽማግሎች ወደ እኛ ጎጆ መጡ" እናቴ፣ ከርቀት እንዳየቻቸው ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ ሰውነቴን እንቦሳዋን እንደምትልስ ላም እየሳመችና እየላሰች አለቀሰች።

«ከእናቴ ጋር በተለያየ አጋጣሚ እንለያይ ነበር ከብቶች በድርቅ ጊዜ እርቀው ሲሄዱ፣ ወደ ማሳ፣ ለገበያ ወዘተ.ስትሄድ ሁለትና ሦስት ቀናት፣ አልፎ አልፎ ደግሞ ከዚያም በላይ እንለያያለን ታዲያ ስንለያይ እናቴ ታለቅሳለች እኔ ግን የእሷ ሁኔታ ቢረብሸኝም
ተሎ ወደ ጨዋታዬ እመለስ ነበር። የዛን ቀን ሽማግሎች፣ «ጥርሱ
አስወልቀን እናምጣው» ብለው፣ በጠንካራው እጃቸው ትንሿን እጄን በጨመቁ ቁጥር ግን እንባዬ ሳያቋርጥ ይንዠቀዠቅ ነበር"
«እናቴ ሽማግሎች ጥርሱን አስወልቀን እናምጣው ብለው ሲጠይቋት ካለምንም ተቃውሞ ገፋ አድርጋ አሳልፋ ብትሰጠኝም! ትከሻዋን በሁለት እጆቿ አቅፋ፣ ድምፅዋን አጥፍታ፣ አምርራ
ስታለቅስ ለአደገኛ ሁኔታ እንደተጋለጥኩ ገመትሁ" ሆኖም ግን ምን እንደሚደርስብኝና ለምንስ እንደምቀጣ አላወቅሁም ነበር"

«ሁለቱ ሰዎች ከመንደራችን እያራቁ ሲወስዱኝ እናቴ እጇ
እያርገበገበች ስታለቅስ ትታየኝ ነበር። እንዲያውም እስከ አሁን ድረስ እንኳ ሰው እንደ እሷ ስፍስፍ ብሎ ሲያለቅስ አይቼ
አላውቅም"

«ከመንደራችን ብዙ ርቀን ወደ ጫካው ውስጥ እስክንገባ ሽማግሎች ምንም ሳያወሩኝ ሄድንና የሆነ ገደል አጠገብ ስንደርስ ከፊለፊታቸው ወደነሱ ሳልዞር እንድቆም ነገሩኝ" እኔ ግን፣ ያሉኝን
ለመፈጸም ስላልተቻለኝ ዘወር ስል፣ አንደኛው ሽማግሌ ጦሩን ወደ
ትከሻዬ ሲሰድ ተመለከትኩኝ" ከዚያ በኋላ ሰውነቴን ሲወጋኝና
ለመጮህ ስሞክር፣ ገፍትረው ወደ ገደሉ ከተቱኝ ገደሉ ውስጥ የነበረው ድንጋይ ደግሞ እራሴን ተረተረኝ፤ ደም ፊቴን አለበሰው የሞት ሞቴን ግን የእናቴን፣ የወንድሜን፣ የአባቴን...ስም እየጠራሁ
ጮሁኩ" የደረሰልኝ ግን አልነበረም።

«ስለዚህ፣ ጉድጓድ ውስጥ እንደሆንኩ ስጓጉር ውዬ አድሬ፣ ጠዋት ላይ ድምፄ ተዘጋ። ረፈድፈድ ሲል የሰው ድምፅ ሰማሁ"
የሰማሁት ድምፅ ግን የሰው ቢሆንም ቋንቋው የማውቀው ሐመርኛ
አልነበረም" ለመጣራት ብሞክርም ድምፄ እምቢ አለኝ።

«የአጋጣሚ ጉዳይ ሆኖ፣ አንዷ በልቅሶ የተዘጋውን ድምፄን ሰምታ ኖሮ፣ አብረዋት ከሐመር ቆቄ ከተማ የመጡትን ሴቶች ጠርታ በድንጋጤ ተያይዘው ሄዱ መሰለኝ ድምፃቸው ጠፋብኝ" ብዙ ቆይቼ
ግን፣ እንደገና የወንዶችና ሴቶች ድምፅ ተሰማኝ ከወላጆቼ ጋር ሳለሁ፣ እነዚያን መሳይ ሰዎች ወደ መንደራችን ሲመጡ፣ በፍርሃት ፈርጥጬ እሮጥ ነበር" ሆኖም ግን፣ የማልፈራቸው የኔ ወገኖች
ስለጨከኑብኝ መሰለኝ፣ አለባበሳቸውንና ቋንቋቸውን የማላውቃቸው ሰዎች ከጉድጓድ ውስጥ አውጥተው የሚበላ ሲሰጡኝና ሲያሳክ
ሙኝ፣ አንድም ተቃውሞ አላሰማሁም"
👍23
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_አምስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ቀፎ ሰቃዮች የመድሃኒት ሥርና ቅጠል ፈላጊዎች...
ለመኝታ የሚጠቀሙበት ማማ ላይ ዳራና ደልቲ ቅጠል ጎዝጉዘው
ቅጠል ተንተርሰው የተፈጥሮ ግዴታቸውን ከተወጡ በኋላ ደልቲ
የወደቀበትን ሳያውቀው አድሮ ከተኛበት ነቃ።

ልጃገረዷ ከደስታዋ ብዛት ይመስላል ማማዋ ላይ ፈገግ እንዳለች ፊቷን ዞራ ተጋድማለች ወገቧ ተሰርጉዶ ዳሌዋ
የለበሰችውን የፍየል ቆዳ ወጥሮታል። እጅዋ ጡቷን ቢጫንም ጡቷ ግን እንደ ችካል እጅዋን ወጥሮ ይዟታል… ደልቲ ተኝቶበት ካደረው ከማማው ስር የንጋት ፀሐይ ተኮስ ስታደርገው ከተኛበት ተነስቶ
ሳዳጎራውን ባጭሩ ጠበቅ አድርጎ አስሮ ላዩ ላይ ዝናሩን እንደ ቀበቶ
ታጠቀበት።

ጉሬዛና ጦጣዎች ከዛፍ ዛፍ እየዘለሉ በቂንጥ
እየተንጨዋለሉ በመቦረቅ እንደ ህፃን ልጅ “የአላየን መሰላችሁ..."እንደሚሉ ሁሉ እያሽካኩ ይቀበጣጥራሉ። 'ፈታይ' የሚባሉት ወፎችም ክንፍና ክንፋቸውን ከአካላቸው ጋር እየጠበጠቡ ከዛፍ ዛፍ
ይበራሉ። ንስርም ሰማዩ ላይ ክንፉን አጠፍ ዘርጋ አጠፍ ዘርጋ ያደርግና አየሩ ላይ ይንሳፈፋል... አረንጓዴ የተላበሱት የግራር የጥድ... ዛፎችም የጠዋቷን የፀሐይ ሙቀት እየከመከሙ ጎንበስ ቀና ይላሉ።

የየአካባቢው ያ የጥንቱ የሐመር ቀዬ! ያ የጥንቱ ባንኪሞሮ በብብትና ብብቱ እበትና ንብ ይዞ የመጀመሪያውን የሐመር እሳት የለኮሰበት ቅዱስ ስፍራ ቡስካ ተራራ ሰው አልባነቱ ዉጦት  ሐመሮች ሜዳውን መርጠው በብዛት ቢሸሹትም ከአራስ ቤት
እንደወጣች ሴት ድንቡሽቡሽ ብሎ ያምራል።

ደልቲ ዕጽዋቱን ምድሪቱን ሰማዩን ቁልቁል
የተንጣለለውን የአባቱን አገር... ቃኝቶ ወደ ማማው ጠጋ ብሉ አየ።ማማው ላይ ያች የደም ገንቦ ዳራ ተጋድማለች። የተገጠሙ
አይኖችዋን ጉንጯን ከንፈሯን ሰርጓዳ ወገቧን ዳሌዋን አይቶ ስሜቱ ጎምዥቶ ተወራጭቶ ሊያስቸግረው ከመከጀሉ በፊት ዘወር ማለቱን መርጦ ጉዞ ሊጀምር ሲል ሻካራ እጅ ትከሻውን ያዘው።

ዘወር ብሉ አያት። ልጃገሪዷ ትስቃለች አይኖችዋ ግን
እንደተከደኑ ናቸው። ለጥቂት ጊዜ  አይን አይኗን
ሲያይ የሚንቦገቦጉት ትናንሽ አይኖችዋ ተከፈቱ። ልጃገረዷ የደልቲ ጉሮሮ
ምራቁን ሲያንጎራጉጭ ሰማችውና “አያ ደልቲ?" አለችው።

ከዚያ አይኖቹን የሰጎን ላባ የሰካባትን ጴሮ የወገኖቹ ጠላት የሆኑትን ሙርሲዎች ገሉ በአምስት ረድፍ መስመር መስመር
የተበጀበትን ሳንቃ ደረቱንና ፈርጣማ እጆቹን አየችና

“ቦርጆ ኢሜ" አለችው አመሰግናለሁ  ለማለት:: በሐመር ባህል ቦርጆ ፈጣሪ እድል የፈጣሪ ሃይል ደህንነት... ሲሆን
የእርካታ በሐመሮች የቀን ተቀን ህይወት የመልካም አጋጣሚ መግለጫ ነው። ስቃይ የተጠናወተው ወይም በሞት የተለየ ቦርጆ
ራቀው፤ እድል ጠመመችበትም ይባላል።

ዳራ ደግማ “አያ ደልቲ" ስትለው በአይኖቹ ወይ አላት እኒያ የወተት አረፋ የመሰሉ ጥርሶችዋን እያሳየችው ፍልቅልቅ
አለችና፡-

“አንተ ጀግና ነህ!  ልብህ
የብዙ ልጃገረዶችን ፍቅር
ሊያስተናግድ የሚችል ሜዳ ማዘጋጀት ሲገባው ለምን እንደ ፍየል ግንባር ጠባብና ለአንድ ሰው የተዘጋጀ መውጫ የሌለው ማማ ሆነ አለችው  ፊቷን ቅጭም አድርጋ
ጀግናው!  ተኩሶ የገደለው!  እጄን እንጂ ልቤ ግን ፈሪ
ቢሆን ይሆናላ” ብሎ ትክዝ ብሎ ቆየና “ለነገሩ ምነው ጅል ጥያቄ ጠየቅሽኝ? የማማውን መውጫ አንችስ መች አጣሽው ወጥተሽ
ተጋድመሽበት አይደል!” አላት።

የደም ገንቦዋ ደግማ ደጋግማ በሣቅ ተፍለቀለቀችና “አንተ!
አያ ደልቲ እኔንኮ ስሜን ጠርተህ ወደ ደረትህ አላስጠጋኸኝም።
"ጎይቲ" ብለህ ጎይቲን ያገኘህ መስሎህ ነው እኔን ወደ ጎዳናህ ያስገባኸኝ

እኔ ግን ስቋምጥለት የኖርሁትን መንገድ ሳገኝ ባገኘሁት ቀዳዳ እንደ እባብ እየተሳብሁ እንደ አንበሳ እየዘለለሁ ልብህ ውስጥ
ገባሁ::... ከተኛችበት ብድግ ብላ እንደ ቂብ ዶሮ እያሽካካች አካባቢውን በሣቅ አጥለቀለቀችው: በሐመር ባህል ሴት ልጅ የሣቅ ምንጭ ናታ። ፍልቅልቅ ስትል የተጠማው የhፋው ወንድ ሁሉ
ጥሙን የሚቆርጠው በሷ ፈገግታ ነው!

በዚህ መሐል ማር ጠቋሚ ወፍ አጠገባቸው ካለው ዛፍ ላይ ድንገት አርፋ ላባዋ እየተርገፈገፈ በከፍተኛ ድምፅ ማዜም ጀመረች።
ደልቲ የዛችን ወፍ ድምፅ ያውቀው ነበርና ዞር ብሎ በፈገግታ አያት: ወፏ ግን ጨኸቷን ይበልጥ ጨመረችው።

ደልቲ ወደ ልጃገረዷ ዞሮ “ዳራ?” አላት

"ዬ"  አለችው

“ደርሼ መጣሁ ብሏት መሣሪያውን ይዞ ሲንቀሳቀስ ወፏ ከተቀመጠችበ ተነስታ በረረች ተከተላት። እንደገና አርፋ እየተጣራች ጠበቀችው አጠገቧ ሲደርስ ተነስታ በረረች እሱም
ተከተላት ዳራም ወፏን የሚከተለውን ጀግናዋን
በአይኗ ተከተለችው፡ ወፏን እየተከተለ ወደ ጫካው ሲገባ የንብ ድምፅ ሰማ፡
ትልቅ : ግንድ ላይ ንቦች እየዘመሩ ይዟዟራሉ ወፏ ደልቲን እየመራች ወስዳ ንቦች ዘንድ ካደረሰችው በኋላ ፊረሱም ሜዳውም
ይኸው'' ብላ ፀጥ ብላ ዛፏ ላይ አርፋ ብብቷን በማንቁርቷ እየኮለኮለች
ተቀመጠች።

ደረቅ ያለ የዛፍ ቅርንጫፍ ዘነጠፈና ከወገቡ ላይ ጩቤውን አውጥቶ ፋቅ ፋቅ አድርጎ አሾለው: ከዚያ በአይኑ የተቆረጠ ደረቅ
ግንድ ሲያማትር ከሱ በስተቀኝ በኩል ግንዱን አዬና ግንዱን በጩቤው ትንሽ አጎድጉዶ...ደ የጠረበውን እንጨት በቀዳዳው ከለካ በኋላ ጣቶቹን በመዘርጋት በመዳፉ አጥብቆ ይዞ እያሽከረከረ ይሰብቀው ጀመር: ለጥቂት ጊዜ ሲሰብቅ እንደቆየ አንድ ነገር መርሳቱን ትዝ አለው
ደረቅ ሣር ወይም ቅጠል። ሄዶ ለማምጣት ቀና ሲል ዳራ ደረቅ ሳር
ይዛ ከፊት ለፊቱ ድቅን አለች:: ቀና ብሉ በአይኖቹ ሳቀላት: ከዚያ እሷ ሳሩን ወደ ጢሱ ቀረብ አድርጋ ስትይዘው ጢሱ ትጉልጉል አለና ነደደ:: ወዲያው ዳራ የደራረቀውን እንጨት አስግብታ እሳቱን
አያያዘች:

ይህን ጊዜ ደልቲ መሳሪያውን ግንዱ ላይ አስደግፎ ዝናሩንና
ሳዳጎራውን ፈቶ ምልምል ራቁቱን እንደሆነ ዳራ የያዘውን እንጨት
ልትሰጠው ዘወር ስትል ራቁቱን አየችው ወዲያው አይኖችዋ ቁልቁል ሽቅብ እንደገና ቁልቁል ሮጡ። ፈዛ ቆመች አይኖቿን ቡዝዝ አድርጋ አየችው ! አያት ተያዩ ጢሱ ይጤሳል: ንቦቹ
ከርቀት ይዘምራሉ። ወፏ ቸኩላለች ዳራ ከንፈሯ ቀጥቀጥ ያለባት
መሰላትና ሳቅ አለች የሳቱ ግለት ሲሰማት ከነበረችበት ነቃችና ዝቅ ብላ አየችው።

“ትሰጭኝ!" አላት ደልቲ እጆቹን ዘርግቶ ሽቅብ ወደ ንቦቹ እያየ: ፈገግታዋን ሳትቀንስ አቀበለችው ጀግናው እሳቱን እንደያዘ
ዘወር ብሎ ሳያያት ወደ ዛፉ ተገጋ እሳቱ ጠፍቷል። ጢሱ ግን እየጨመረ ነው:
ቀና ብሎ ዛፉን አይቶ በግራ እጁ እሳቱን ይዞ በቀኝ እጁ ወደ ዛፉ ቅርንጫፍ ወጣ ዛፉ ሲንቀሳቀስ የጭሱ ጠረን ሲሸታቸው ንቦች ቁልቁል መጡበት ነደፉት፡ ፊቱ ቅጭም ሲል
ዳራ አየኘው: እንደገና ተስቦ ሌላ ቅርንጫፍ ላይ ወጣ ንቦቹ እሾሃቸውን በሰውነቱ እየሰገሰጉ ተረባረቡበት
ስቃዩን ጥርሉን ነክሶ ችሎፀ ሽቅብ እየተሳበ ወጣ... ጢሱን ወደ ቀፎው ሲያስጠጋው ንቦች ጩኸታቸውን እየጨመሩ ሸሹ የድምፃቸው ቃና ተቀየረ: ኡ ኡ ኡ.." ሲሉ ደልቲ እጁን ወደ
ተፈጥሮዊ የግንድ ቀፎ ከተተ። እጁ የማር ሰፈፍ ይዞ ተመለሰ።
እንደገና ከተተው ከዚያ ሰፈፉን በዳራ የፍሬ መልቀሚያ ሾርቃ
ሞልቶ ወረደ:

ዳራ ደልቲ ከዛፉ እንደወረደ፡ “መቼም አልተረፍህም"
ፈርጠም ብላ ጠየቀችው:

“አዬ አስቀርተውኝ ነበር! እንዲያው የሞት ሞቴን…" አለ።ላመል ያህል ጉንጭና ጉንጩ ጨምድዶ ከንፈሩ ለጠጥ ጥርሉ ብልጭ ብሎ።

አይቀርም ኖሯል። የአንተን እንጃ እንጂ እኔ መቼም ማር
አላማረኝም ስትለው፡-
👍34