አትሮኖስ
286K subscribers
122 photos
3 videos
41 files
575 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
Forwarded from Quality Button
📚 የተለያዩ ድርሰቶችን ለማግኘት📚
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
#የዘንድሮ_ነገር

ሟችን ባጀብ መቅበር
ተከልክሎ ባገር
የዘንድሮ ነገር
ተጎልቶ መድከም
ሐዘንን እንደ ዘውድ ለብቻ መሸከም!
በየሰው ጉንጭ ላይ ፤እንባ ቀልጦ እንደ ሰም
ደረት ሳይጎሰም
ፍታት ሳይፈታ
ያለ ምንም ሙሾ፤ ያለምን ዋይታ
ብቻየን ቀብር ዋልሁ
ከእድሜየ መካከል፤ አንድ አመቴ ሞታ ።

🧿በእውቀቱ ስዩም🧿
#ሮዛ_2


#ክፍል_ሰባት(🔞)



#ሮዛ በመዘግየቱ ይቅርታችሁን አትንፈጉኝ ያው ለማዘጋጀት ጊዜ ይወስዳል አልመች ብሎኝ ነው አይደገምም ብዬ ተስፋ አድርጋለው #መልካምንባብ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ምንም ነገር እምቢ እንዳትይኝብሎ በለሆሳስ አንሾካሾከልኝ፤

what! ያመዋል እንዴ ይሄ ሰውዬ! ምን እያልክ ነው ዶክ ሚስትህ ጋ እኮ ነው ያመጣኸኝ

I know i know That is why i need you more እንደገና ወደ ጆሮዬ መቶ አንሾካሾከ ።

ኮቴዋን ከወደ ኪችን ሲሰማ ቶሎ ብሎ እጁን ከቂጤ ላይ አነሳና ወደ ሱሪ ኪሱ
ከተተው ቀጥሎም የሌለ የዩኒቨርስቲ የሚመስል ወሬ መቀባጠር ጀመረ።
who gave you that course? me? No way. It must be Sami Dr. Samuel yeah?!

ዶክተር ሳሙኤል መሰለኝ የሰጠን።” አልኩ በፈጣጣ « የት ሄደ ግን እሱ ሰውዬ?» is he teaching
now? አልኩ ስለማላውቀው ሰው፤
Oh no! He left the academia world and joined the dirty politics! I think he lives in
states now, establishing a new political party"

Oh really? I didn't know that Good for him" ከጀመረበት ቀጠልኩበትና ጎበዝ ተዋናይ
መሆኔን አስመሰከርኩ።

ማሪያ የትምህርት ቤት ወሬ እያወራን ሳይመስላት አልቀረም። ጣልቃ ገብታ ምን አይነት ምግብ እንደምፈልግ ጠየቀችኝ።

"What would you like to have: Roza?"

"Nothing especial, really! I am fine with anything you have!" አልኳት

እነሱ ሰላጣና ጎመን እንደሚበሉና እኔ ግን እንጀራ በወጥ የምፈልግ ከሆነ በአጭር ሰዓት ዉስጥ ልታዘጋጅልኝ እንደምትችል ተናገረች።

“በፍጹም ብዬ ተከራከርኩ። ዶክተር ቃልዓብ ለምን እንደሆነ አላውቅም ሚስቱ እንጀራና ወጥ እንድትሰራልኝ ፈልጓል። የሚስቱን ሙያ እንዳደንቅለት ፈልጎ ይሆናል ብዬ አሰብኩ። ነገሩ ሌላ እንደሆነ የገባኝ ግን ኋላ ላይ ነው፡፡

ማሪያ የባሏ ፍላጎት ገብቷት ነው መሰለኝ እንዲህ አለችው፡፡

"Honey! It seems you need to have Injera more than Roza! Don't worry l will start cooking
now. Just half an hour”ብላ የኪችን ፎጣ ለብሳ ጉድ ጉድ ማለት ጀመረት። ቃልአብ ቤቱን እንዲያዝጎበኘኝ ሀሳብ አቀረበችለት።

"Good Idea ማሬ You know how much I love you!?" አላት።

“No i don't until you come and kiss me! አለችው። ሄዶ ከንፈሯን በከንፈሩ በስሱ ቦረሽ አደረገላት ትንሽ እንደተራመደ ጎትታ በድጋሚ ከንፈሩን ጎረሰችው።ተቃቅፈው አስነኩት፤ ለምን
እንደሆነ አላውቅም ቅናት በስሱ ቁንጥጥ አደረገኝ። በሰው ሚስት መቅናቴ ግን እኔኑ ገርሞኛል።

ይዞኝ ወደ ሳሎኑ በረንዳ ወጣ። እሷ ወደ ኪችኗ ከተመች።

የተሳሳሙት ነገር ከአእምሮዬ አልወጣ አለኝ።

“አንተ! ለካ ፈረንጅ ሚስትህ ናት ያስተማረችህ።”

“ምኑን?”

“የምር በጣም ይገርመኝ ነበር ችሎታህ። ከሀበሻ ወንድ አንድ አንተን አየሁ መሳም የሚችል

“Oh see! Thank you and I am humbled! እስከዛሬ ግን ነግረሽኝ አታውቂም? ብሎ ሳቀ።

ቀጠለና ደግሞ “ሮዚ ቆንጆ! ታንኪው እሺ ዛሬ በጣም ደስ ብሎኛል።”

“ምኑ?”

እኔንጃ! ብቻ ይህን ቀን ለአመታት ጠብቄው ነበር።”

“የቱን ቀን?አልገባኝም…! እኔና አንተ ከተዋወቅን እኮ ገና አመት አልሞላንም።”
It doesn't matter!!” ብሎኝ በረንዳው ላይ በቆምንበት በሀሳብ የሆነ ቦታ ጭው ብሎ ሲሄድ አየሁት።

"ዶክ are you alright?"

"Yes i am! …ብቻ አንድ ጉዳይ ዝም ብሎ ይረብሸኛል።

"የምን ጉዳይ"

“ሮዝ Believe me its a long long-long story ብቻ ሌላ ጊዜ እነግርሻለሁ” ብሎኝ ቂጤን ቸብ አደረገውና እጄን ይዞኝ ወደ ሰገነቱ ወጣ።

ከቤታቸው ፎቅ ላይ የአዲስ አበባ አሮጌ ቤቶች ይታያሉ። የሁሉም ጣሪያ የዛገ ነው። እላያቸው ላይ ድንጋይ ተጭኖባቸዋል። ቆርቆሮዎቹ ኑሮ ከብዷቸዋል፤ እድሜ ተጭኗቸዋል። ንፋስን እግሩ ላይ ወድቀው “የዛሬን ማረን.ገንጥለህ አትውሰደን እያሉ የሚለምኑት ነው የሚመስለው። የእውነት አዲስ አበባ ከነ ዶክተር ቃለዓብ ቤት አናት ላይ ስትታይ በጣም ታስጠላለች። እየሱስም እንደዚህ ቁልቁል እያያት ከሆነ በእውነት ወስፋቱን የምትዘጋው ይመስለኛል። ወይም አዲሳባን በመፍጠሩ ተፀፅቶ ሱባኤ ገብቶ ይሆናል።

የራሴ ሀሳብ አሳቀኝ።

ስገነቱ ላይ እንደቆምን በድጋሚ እጁን አንሸራቶ ቂጤ አካባቢ በስሱ ደባበሰኝ።

ዝም አልኩት።

አንድ ፎቅ ወደ ታች ይዞኝ ወረደ። ደረጃው ላይ እያለን አንገቱን ወደታች በማድረግ ጮክ ብሎ «ማሬ! Is there anything I may help?» ብሎ ተናገረ!"

"No hony! Thanks! I love you! አለችው!” እሷም ጮክ ብላ።

አንድ ፎቅ ወደ ታች ይዞኝ ወረደ! ዛሬ የሚሰራውን አሳጥቶታል። ብቻ አንድ ነገር የፈለገ ይመስላል።

“የመኝታ ቤታችንን Terrace ላሳይሽ ብዬ ነው፤የተሻለ ቪው አለው” አለኝ።
“አትፈሩም ግን በዚህ ትልቅ ቤት ውስጥ ብቻቸሁን?” አልኩት።

ብቻችንን አይደለንም እኮ ሮዝ! በየክፍሉ አብሮን የሚኖር ጥሩ መንፈስ አለ፤ ስሙ ፍቅር ይብላዕ።

"you know what I mean ሃሃሃሃሃ"

ዶክተር ቀልዓብ ዛሬ ተለይቶብኛል። የጦዘ ዓይነት ሰው ነው የሚመስለው።እስካሁን ጣቶቹን በጣቶቼ ውስጥ ቆልፎ አልለቅ ብሎኛል። እንደ ህጻን ልጅ ነው እጄን ይዞኝ የሚንቀሳቀሰው። በዚያ ላይ
ቁና ቁና ይተነፍሳል። የሆነ ጥድፊያ ነገር ውስጥ ያለ ይመስላል።ሂል ጫማዬ በጣም ረዥም ስለሆነ እሱ በፈለገው ፍጥነት ደረጃውን ልወጣለትና ልወርድለት አልቻልኩም።

መኝታ ቤቱን በእግሩ ገፋ አድርጎ ከፈተውና ከውስጥ ገርበብ አድርጎ ዘጋው። በጣም የሚያምር
ትልቅ አልጋ አየሁ።አልጋው ከተወለድኩ ጀምሮ አይቼው የማላውቀው ነው። ክብ ቅርፅ ያለው እጅግ ሰፊ አልጋ ነው፣ ሁለት ዱካ ወንበሮችና አንድ ትንሽዬ ጠረጴዛ ይታያል። በሌላ ጥግ ከክር የተሰራ ዥዋዥዌ መጫወቻ ወንበር አለ።የመኝታ ቤታቸው ስፋቱ ከሳሎኑ እንደማይተናነስ ያወቅኩት ቲቪው የተቀመጠበትን ርቀት ሳስተውል ነው። ከአልጋቸው ጎን ከቀርከሃ የተሰራ ትንሽዬ የመጽሐፍ መደርደሪያ
ይታያል። የወለሉ ንጣፍ ንጣቱ በረዶ ላይ የመራመድ ያህል ስሜት ይሰጣል። በመኝታ ቤቱ ውስጥ ሌላ ምንም አይነት ኮተት አላየሁም።

የባለትዳር መኝታ ቤት ውስጥ ከወሲብ ደምበኛዬ ጋር እንደሆንኩ ውልብ ሲልብኝ ሰቀጠጠኝ።
የባለትዳር አልጋ አካባቢ መቆሙ ምቾት ስላልሰጠኝ ወደ ፊት ራመድ ብዬ የመኝታ ቤቱ ሰገነት ላይ ቆምኩ። እዚያ ደስ የሚል ነፋሻማ አየር እየተመገብኩ ሳለ ዶክተር ቃለአብ ከኋላዬ መጥቶ ወገቤን
በሁለት እጁ ያዘኝ። በጆሮዬ የማይሰማ ነገር አንሾኳሽከልኝ። ከዚያም አንገቴን በስሱ ይስመኝ ጀመር።
ልከላከለው ሞከርኩ…በምላሱ ጆሮዬን መላስ ሲጀምር ግን ጉልበቴ ተመናመነ።

እጆቹ ከወገቤ ተንሸራተው ቂጤን መነካካት ጀመሩ። በእጄ ተከላከልኩት። ሆኖም እጆቹ ወደ ጡቶቼ ላይ ወጥተው ያልሆነ ነገር ሲያረጉኝ አቅሜን አሳጡት። በምላሱ ቀኝ ጆሮዬን እየላሰ በሁለት
መዳፉ ሁለቱንም ጡቶቼን ጭምቅ ያደርጋቸዋል። መጮኽ ፈልጌ ትንፋሽ አጠረኝ።
👍81
እንደምንም ከእቅፉ አፈትልኬ ልቆጣው ፊቴን ሳዞር ከንፈሩና ከንፈሬ ተገጣጠሙ። ዶክ ሲስም አውቀዋለሁ።
ልብ ያቀልጣል። የኔም ልብ ወደ ውስጥ ፍስስ ሲል እርጥበቱ ይሰማኝ ጀመር። ልረዳው አልችልም ሳላስበው ከሱ ስሜት ጋር አብሬ መንጎድ ጀመርኩ። ለምን እንደሆነ አላውቅም ከንፈሬን ሲጎርሰው
ፍርሃቴ ሁሉ ብንን ብሎ ጠፋ። ሚስቱን መፈጠሯን ረሳኋት። የሆነች ትንሽዬ ሰይጣን በጆሮዬ መጣችና ፈረንጅ እኮ ብዙም ጣጣ የለውም፤ ዝምብለሽ ከንፈሩን አጣጥሚው! Relaxy baby አለችኝ። እሺ የኔ ቆንጆ!" አልኳት በሆዴ። ለሆኑ ደቂቃዎች ያህል ሁለታችንም በከንፈሮቻችን ማሰብ ጀመርን።

ከንፈሩ ማር ማር ይላል። ምላሱን አፌ ውስጥ አስገብቶ ሲያንቀሳቅሰው የወሲብ ሞተሬን ቀሰቀሰው።ሁሉንም ሰውነቴን እንዲነካካኝ ፈለኩ። አንዱን እጄን ወደ ሱሪው ዚፕ አንሸራትቼ
ዳበስኩት። ወንድነቱ ጂንስ ሱሪዉን ቀድጄ ካልወጣሁ ብሎ ግብግብ ይዟል፤ ወይም እንደዚያ መሰለኝ።
ከወትሮው ገዝፎ ተሰማኝ።

Hone are you there?” የማሪያ ድምጽ ከታች ከኪችን ተሰማ።

ሁለታችንም ሲሰርቅ እናቱ እንደደረሰችበት ህጻን በርግገን ቆምን። ቁና ቁና እንተነፍስ ነበር።

Hony! Roz! Are you there?” በድጋሚ ተጣራች፤

Yes! አልን ሁለታችንም የቀረችንን ትንፋሽ አሰባስበን።

"Good to know! Enjoy..guys! Almost done! 15minutes more please!"

"We are in the library Hony. Call us if you need help" ብሎ ዋሻት፣


W.h.a.t! I can't hear you!” አለችው። ሽንኩርት መፍጫውን ለኩሳው ስለነበረ የሚላት ነገር ብዙም አይሰማትም ነበር።

"I said I love you ማሬ!” አላት፤ መጀመርያ ያላትን እንዳልሰማችው ሲረዳ።

“Same here!” አለችው ድምፅዋን ጎላ አድርጋ።

ተጣድፎ እኔ የቆምኩበት ሰገነት ጋ ተመልሶ መጣና ከንፈሬን በከንፈሩ ከደነው። ታግዬ ከእቅፉ ወጣሁ፤

“ዶክ! ምን እያረክ ነው? በቃህ.! ሚስትህ ብታየን ምን እንደሚፈጠር ገብቶሃል?” ስል አንሾኳሸኩ፤
ደምጻችን ታች እንዳይሰማ በመስጋት ሁለታችንም ከትንፋሽ ባልበለጠ ድምጽ ነው የምናወራው።እየሰማኝ አልነበረም።

እጄን ይዞኝ 2ኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው የቤታቸው ቤተ መጽሐፍት ወሰደኝ። ስሮጥ ሂል ጫማዬ የሚፈጥረው ድምጽ ለማስወገድ ብዬ ላወልቀው ጎንበስ ስልዶክ ከለከለኝ። I love it this way
በሂል ጫማ ይበልጥ ትረብሺኛለሽ” አለኝ፤

እኮ እንዳይረብሽእኮ ነው ላውልቀው የምልህ”

“ሮዝ! መረበሽ ነው የምፈልገው ዛሬ፤ አይገባሽም?!”

የላይብረሪው በር ጋ ስንደርስ አንገቱን በደረጃው መደገፊያ ወደታች አስግጎ…"Take your time mare!
We are browsing the newspapers up here!" አላት።

Alright honey! I love you!

«ሎቭ ዩ!»ሎቭ ዬ» ተባባሉ በድጋሚ።ስንት ሺ ጊዜ ይህን ቃል እንደሚባባሉ ማመን ይከብዳል።

ቤተ መጽሐፍታቸው ውበቱን ለማድነቅ ጊዜ አልነበረኝም። ዶክተር ቃልአብ በጥድፊያ ወደኔ ተመልሶ ከንፈሬን ካቆመበት መሳም ቀጠለ።

“ወይኔ ጉዴ!ዶክ ዛሬ ልክ አይደለህም! በእውነት!”

“ልክ መሆን አልፈልግም ሮዝ ፊቱን ቅጭም አድርጎ እቁጩን መለሰልኝ፤

የራስህ ጉዳይ የኔ ትዳር የሚፈርስ መሰለህ እንዴ!”

መልስ ሳይሰጠኝ ከንፈሬን ጎረሰው። ዘለግ ላለ ሰዓት እየተሸሻን ተሳሳምን።

እጁን ወደ ቀሚሴ ውስጥ መክተት ሲጀምር ግን አስቆምኩት።

“ዋይ! እጮኻለሁ! በእውነት ካላቆምክ እጮኻለሁ።”

ፈራኝ መሰለኝ እጁን ሰበሰበ። ከዚያም ጥግ ላይ ወደሚገኘው የላይብረሪው ሼልፍ ጀርባ ጎትቶ ወስዶ ነካካኝ። ብልሽትሽትሽት አደረገኝ። ሁሉ ነገሬን አሳከከኝ። እሱም እንደዚያው የሆነ ይመስለኛል። ሁሉነገሬን ቢጎርሰው ደስታውን አይችለውም።

አንዳንድ አጓጉል ቦታዎቼን ሲነካካቸው እየተዳከምኩ መጣሁ፤ ልከላከለው አልተቻለኝም፡፡

የለበስኩትን ሸሚዝ ሁለት የላይኞቹን ቁልፎች ፈትቶ ወደ ሼልፉ አስጠግቶ አንገቴን፣ ከንፈሬን ከዚያም
ከሸሚዜ አፈትልኮ የወጣውን የቀኝ ጡቴን መላስ ሲጀምር ምን እየተካሄደ እንደሆነ አእምሮዬ ማሰብ አቆመ። የለበስኩትን ጥቁር ሚኒ ቀሚስ ገልቦ ከመቼው የሱን የሱሪ ዚፕ ከፍቶ …። አንድ እግሬን በእጁ ሽቅብ ከታፋዬ አንስቶ በእጁ ደገፈውና በአንድ እግሬ ብቻ እንድቆም ካረገኝ በኋላ የመጽሐፉን ሼልፍ እንደድጋፍ እንድጠቀምበት አረገኝ። የፓንቴን መሐል ዳንቴሉን ሲቀደው ይሰማኛል። ላስቆመው
ግን ጉልበቱም፣ ፍላጎቱም አልነበረኝም። በአንድ እግሬ አንካሴ እንደሚል ሰው አንጠልጥሎ ብሎኔን ይፈታኝ ጀመር። እኔ ደንባሪቱ ስሜት ዉስጥ ሆኜ ነው መሰለኝ እጄን ከሼልፉ አንስቼ በሁለት እጄ
የሱን አንገት ለማቀፍ ሞከርኩ። ሰውነቱ ወደፊት ሲገፋኝ የቆምኩበት ግራ እግሬ ሂል ጫማ አንሸራቶኝ
ባላንሴን ስቼ ሼልፉ ላይ ወደቅኩ። እግዜር ይስጠው ዶክተር ተንደፋድፎ ከከፉ አወዳደቅ አዳነኝ።
ከሼልፉ በላይኛው መደርደሪያ ላይ የነበሩት መጽሐፍት ግን በሙሉ ተናዱ።

መጽሐፍቱ ሲናዱ የፈጠሩት ከፍተኛ ድምጽ ለኛ እጅግ ተስፋ አስቆራጭ ነበር። እኔ በበኩሌ ለመሞት ጥቂት ደቂቃዎች እንደቀረኝ ተረድቼ ራሴን ማፅናናት ጀምሬ ነበር።

ልክ መጽሐፍቶቹ ሲናዱ የዶክ ወንድነቱ የእኔ እጢዬ እኩል ዱብ ያሉ ይመስለኛል። እኔ ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ። የዶክተር ቃለአብ ድንጋጤው ከኔ ብሶ ነበር።ወንድነቱ ሟሸሸ። በፍጹም አንድ ዶክተር የሆነ ሰው እንደዚያ የሚደነግጥ አይመስለኝም ነበር።አሁን በርግጠኝነት ይህንን ድምጽ ሚስቱ ስትሰማ
በሰከንድ ውስጥ ጦር ሰብቃ ትመጣለች። እኔማ እጅግ ከመፍራቴ የተነሳ ከአሁን አሁን ደርሳ በያዘችው ቢላ ፊቴን አበላሸችው ብዬ በር በሩን በተስፋ መቁረጥ አየዋለሁ። የሸሚዜን ቁልፍ ለማስተካከል እንኳ የሚሆን ተስፋ አልነበረኝም፡፡

Honey!Are you alright?” የሚል ድምጽ ከኪችን ሲሰማ የሁለታችንም ተስፋ ዳግም ለመለመ።

°Coming Marre Coming-corning." ድምፁ ቁርጥርጥ ያለና የሚያስቅ ነበር።

እሱ መጽሐፎቹን ከተበታተኑበት ማንሳት ሲጀምር እኔ የተዛነፉ የሸሚዝ ቁልፎቼን መቆለፍና ሚኒስከርቴን ወደታች እየጎተቱ ማስተካከል ጀመርኩ። ዶክተር ቃልአብ ሁሉንም መጽሐፍት ከመደርደርይልቁ ሼልፉ ላይ ከመራቸው። እንድ ትንሸዬ መጽሐፍ ግን መሬት ላይ ተረስታ እንደነበር አስተዋልኩ።

Transgender የሚል ጽሑፍ በቀይ ቀለም በጉልህ ተጽፎባታል።

ዶክተር ቃልዓብ በፍጥነት ወደ downstairs መውረድ እንዳለብን አሳሰበኝ፡ ከቤተመጽሐፍቱ ወጥተን
ደረጃውን መውረድ እንደጀመርን አንድ ጊዜ ቼክ እንዲያረገኝ ጠየቅኩት። የሸሚዜ የላይኛዎቹ ሁለት ቁልፎች እንደተዛነፉ ማስተዋል ቻለ። ቶሎ ብሎ በቆምንበት አስተካከለልኝ። እድለኞች ነን።እግዜርም ሰይጣንም ይወዱናል። ቁልፎቹ እንደተዛነፉ ወደ ማሪያ ጋር ወርደን ቢሆን ምን እየሆንን እንደቆየን
ለመረዳት ሰከንድ እይወስድባትም ነበር። በዚያው የኔን ሊፒስቲክ ቀለም ከሱ ከንፈር ላይ ሙልጭ ከድርጎ እንዲያስለቅቅ ረዳሁት።

እንደኛ ፎቅ ልንደርስ ስንል አንድ ሀሳብ ብልጭ አለለት። እኔ upstairs ወደ ላይብረሪው ተመልሼ ሄጄ ጋዜጣ እንደሚያነብ ሰው እዚያው እንድቆይና እሱ ምግብ ማብሰሉ ላይ ማሪያን እንዲያግዛት ተስማማን። ይህ ትርኢት ጥርጣሬዋን እንደሚቀንሰው አመንን።


እኔ ደረጃውን እየወጣሁ ሳለ እሱ already ኪችን ደርሶ ነበር። where is she?” ስትለው በስሱ ይሰማኛል። እሱ ምን ብሎ እንደ
👍92
መለሰላት ግን አልተሰማኝም። ወደ ላይብረሪው ገብቼ ቅድም ወድቆ አይቼው የነበረውን «transgender» የሚለውን መጽሐፍ ቦታው ከመለስኩ በኃላ ለመረጋጋት
ሞከርኩ። ራሴን በድጋሚ በደንብ ማስተካከል ጀመርኩ። ናፕኪን ከቦርሳዬ አውጥቼ ሊፒስቲኩን ሙልጭ አድርጌ ከጠረኩት በኋላ ሶፍቱን እዚያው ከሚገኝ ከቀርከሃ የተሰራ ባስኬት ውስጥ
ጨመርኩት። አዲስ ቻፒስቲክ ደመቅ አድርጌ ተቀባሁ።

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በዚህች ላይብረሪ ምን እየሆንኩ እንደነበረ ሳስታውስ ድንጋጤዬ አገረሸብኝ።
ፍርሃት ሁለመናዬን ዉርርር አደረገኝ። በዚያው ቅጽበት ማሪያ ስሜን ስትጠራው ሰማሁ።

“Comning!” ብዬ መልስ ሰጠሁ። ከዚያም እያነበብኩ የቆየሁ ለመምሰል አንድ VOGUE PARIS
የሚል ደማቅ የፈረንሳይ የፋሺን መጽሔትና ቅድም ባለጌ ነገር ስናረግ ወድቆ በኋላም ቦታው መልሺው
የነበረውን transgender የሚለውን መጽሐፍ በጄ ይዤ ደረጃውን መውረድ ጀመርኩ።

"You guys have amazing library. It took my breath away. Envy you guys! By the way,
was reading these two!” ብዬ መጽሔቱንና መጽሐፉን አሳየኋት። ዶክተር ቃልአብ በፍርሃት የታፈነሳቅ አፍኖት ፊቱን የኪችን ሲንክ ውስጥ ሲደብቅ አየሁት አንገቱን አቀርቅሮ ብርጭቆ በማለቅለቅ ላይ ነበር።

Wow! Thank you! This all has happened because of my beloved husband! ብላ ከንፈሩ
እስኪገነጠል ድረስ ሳመችው። ይህን ጊዜ ድንጋጤ ተፈጠረብኝ፡፡ ሚስቱ ስትስመው የተለየ ጣዕም ከንፈሩ ላይ ልታስተውል ትችላለች በሚል ነበር ስጋቴ፡፡ ምንም አላለችም። ተመስገን አምላኬ!

የረጠበውን እጇን ከሲንኩ ጎን በተንጠለጠለ ሰማያዊ ፎጣ ካደራረቀች በኋላ transgender የሚለውን
መጽሐፍ ተቀበለችኝና ለቃልአብ እያሳየችው በሳቅ መንከትከት ጀመረች። ቃልአብም “oh yeah! That
thing your story. oh no are you gonna tell her?!” ብሎ እሷን በሳቅ ማጀብ ጀመረ። ለምን እንደሚስቁ መጀመርያ አልተገለጠልኝም ነበር።እንዲያውም ፎቅ ላይ የሆነውን ነገር ያወቀችብን መስሎኝ በድንጋጤ ዉሀ መሆን ጀምሬ ነበር። ዶክተር አብሯት ሲስቅ ጊዜ ነው የተረጋጋሁት። በኋላ
ግን ነገሩን በጠቅላላ ሳስበው ቃልአብ እየሳቀ እኔ ለምን ድንብርብሬ እንደሚወጣ ግርም ይለኝ ጀመር።
የኔ ትዳር አይፈርስ ነገር ምን አሸማቀቀኝ!

What is funny?” ብዬ የሞት ሞቴን ጠየቅኩ።

"It is a Lo....g long story ሮዝ i will tell you over the lunch ብላኝ ምግቡን እያቀራረበች እንደ አዲስ በሳቅ መንፈር ጀመረች። ቃልአብም ሳቋን አጀበው። ሳስበው ቃልአብ ፍርሃቱን ለመሸፈን አሪፍ አጋጣሚ ተፈጥሮለታል።ለዚያም ነው ወሬዋን እያዳመቀ የሚስቀው። አሁን ስጋቱ ሁሉ በኖ ጠፍቶለታል መሰለኝ። ከደቂቃዎች በፊት ምንም እንዳልተፈጠረ ሆኖ ኪችን አብሯት ሲንጎዳጎድ ገርሞኝ ነበር። እኔ በጭንቀት መከሳት ጀምሪያለሁ፤ እሱ ሆዬ ይስቅልኛል።

ማሪያ ምሳችንን በሙሉ አቀራረባ ስታበቃ lunch is served!" ብላ ሁለታችንም ወደ dining room እንድንመጣ ጋበዘችን፤

ሶስታችንም ወንበሮቻችንን ስበን ተቀመጥን። ማሪያና እኔ ፊት ለፊት ትይዩ ተቀመጥን። እሱ ግን ከኔ
ጎን ያለውን ወንበር ስቦ ተቀመጠ። ከማሪያ ጎን ይቀመጣል ብዬ ነበር ያሰብኩት። ለምን እንደሆነ
ባላውቅም የመረጠው ቦታ ትክክል እንዳልሆነ ተሰምቶኝ ነበር።
ድንገት ሁለቱም ጣቶቻቸውን አጣምረው መጸለይ ጀመሩ። ከዚያም እኩል ««ኤሜን!» ብለው ምግቡን ባረኩት...

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍51
አትሮኖስ pinned «#ሮዛ_2 ፡ ፡ #ክፍል_ሰባት(🔞) ፡ ፡ #ሮዛ በመዘግየቱ ይቅርታችሁን አትንፈጉኝ ያው ለማዘጋጀት ጊዜ ይወስዳል አልመች ብሎኝ ነው አይደገምም ብዬ ተስፋ አድርጋለው #መልካምንባብ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ምንም ነገር እምቢ እንዳትይኝብሎ በለሆሳስ አንሾካሾከልኝ፤ what! ያመዋል እንዴ ይሄ ሰውዬ! ምን እያልክ ነው ዶክ ሚስትህ ጋ እኮ ነው ያመጣኸኝ…»
#ያንድ_ምሽት_ናፍቆት

ዛሬ ታምራለች ጨረቃ
ፊትሽን ፊቷ ላይ፥ እንደጭንብል አጥልቃ
እንሆ እኔም ቁምያለሁ
የዛፉን መልክ መልኬ አድርጌ
በሩቅ ማየት ተፈቅዶልኝ
መንካቱን ግን ተነፍጌ።
#ምኞት_እሽሩሩ

የምኞቴን ስእል፥ ከግንባሬ አንስቼ
ብብቴ ሥር ደበቅሁ
በስውር ጎምዥቼሽ፥ስንት ዘመን ማቀቅሁ
ሳትቀጥሪኝ ቁጭ ብየ፥አንቺን እየጠበቅሁ።
#ጫማ_ለዘመን_ሰው


#በናትናኤል

ፍትፍት አኩርፋኛለች። ለሁለት ሳምንታት ከቤቷ ተመላልሼ የለችም። ከቤተ ዘመዶቿ "አላየናትም" የሚል ምላሽ ተሰጥቶኛል። ናፍቃኛለች። ናፍቆቷ ደግሞ ብርቱ ነው፤ በበረዶ ዘመን የተወለደ ግመል በረሀ እንደሚናፍቀው አይነት ናፍቆት ነው ፣ ናፍቆቷ እንደ ውሀ ጥም ጉሮሮን የሚያንገበግብ አይደለም ፤ ፏፏቴ ከገደል ወደ ገደል እየዘለለ ሲተም ለማየት እንደመመኘት ነው።
በምን አስኮርፌያት ይሆን ? ምን ያህል ተቀይማኝ ይሆን? ልንጋባ ወስነን ፤ እንደ ደንቡ ፣ እንደ ወጉ ፤ ወደ ቤተሰቦቿ ሽማግሌ ልኬ ነበር። እኔ እንኳን በእንደዚህ አይነት ሂደት ትዳር ባይመሰረት እመርጥ ነበር። ባህል ፣ ወግ ፣ እሴትና ዘልማድ ፤ ከፍቅር ፊት ዋጋ ያላቸው አይመስለኝም። “ሁለት ልቦች ፍቅር ሲያጣምራቸው አንድ ይሆናሉ ፤ አንድ ሲሆኑ ደግሞ ይህ አንድ ልብ የማሰብን ወግ ዘወር ብሎ የሚያይበት አይን አይኖረውም” እንደዚያ ብያት ነበር። ጠይም ለስላሳ ከንፈሮቿን በከፊል ሸልቅቃ ፈገግታ ቸረችኝና “…ለአባባ እኮ ነው። እኔማ ምንም እንደማይመስለኝ ታውቃለህ” አለችኝ። እወዳታለሁ ፤ የምር እወዳታለሁ። በሆነ ምክንያት ፣ ልገልጸው በማልችለው ሚስጥር ተብትባ ይዛኛለች። አስቸጋሪው ጸባዬን(ሰዎች እንደሚሉኝ) ፈጣኑን ስልቹነቴን መግራት የቻለች ታጋሽ ሰው ናት።

ሽማግሌ ለመላክ የተስማማሁ ቀን ብቻዬን ወደ ቤቴ እያዘገምኩ ማንን እንደምልክ ሳስብ ነበር። ባወጣ ባወርድ ሁነኛ የምለው ሰው አጣሁ። ይሄኔ ክፍለ ሀገር ቢሆን ኖሮ አይወይ (አይወይ አያቴ ነው) እና አባቴ ይወጡት ነበር። እዚህ መሀል ከተማ ብቻዬን ሆንኩና አብዝቼ ተጨነኩ። ማታ እንቅልፍ የወሰደኝ ከብዙ ችግር በኋላ ነው። ጠዋት ቤቴን ስከፍት ጋሼ ዘበነ ከበራፌ ቁመው ተመለከትኩ ፤ “ሰላም አደርክ ልጄ” አሉኝ። “እንደምን አደሩ ጋሽ ዘበነ” ሞቅ አድርጌ ሰላም ብያቸው እንዲገቡ ጋበዝኳቸው። በተለመደው አረማመዳቸው ቀስ ብለው ገቡና ቤቷን መቃኘት ጀመሩ። “ሸጋ አድርገህ ይዘሀት የለም እንዴ?” አሉኝ በመደነቅ። “እንዲህ ቤት የሚንከባከብ ተከራይ የመጀመርያ አንተን እያየሁ ነው” አሉኝ ቀጥለው። ይኸው ስንት አመታችን ሁሌም ሲገቡ እንዲህ ይሉኛል። ልክ ነው ፤ ምንም ነገር ሲዝረከረክ አልወድም። በዚያ ላይ ደግሞ ፍትፍት ስለምትመጣ የጎደለውን ሳታስተካክልልኝ አትሄድም። አከራዬ ጋሽ ዘበነ ድንገተኛ ጉብኝታቸውን ጨርሰው ሊወጡ ሲሉ አስቆምኳቸውና ጭንቀቴን አካፈልኳቸው። “የረዥም ጊዜ አብሮነታችን ለዚህ ካልሆነማ ምኑን አብረን ኖርነው? አታስብ በኔ ጣለው ልጄ” አሉኝ። ደስ አለኝ።5 በአዳሩ የሀሳብ ናዳ የናወዘው አይምሮዬ ጥቂት እረፍት ስለተሰማው ከማለዳው ድብርት በጊዜ ተላቀኩ።

ፍትፍት !!እንደጨረቃ ክብ የሆነ ፊቷ ፣ አጭር ቁመቷ ፣ ቀጭን ወገቧና ሰፋ ያለ ዳሌዋ ፣ ትንንሽና ለስላሳ ጣቶቿ…ከዚያ ከዚያ በላይ ስትኮረፍ የሚኖራት ገጽታ ድንቅ ይለኛል። ስትኮረፍ እንደ ህጻን ልጅ ትንቡክ ትንቡክ የሚሉ ጉንጮቿ ውስጣቸው ጠይም መልክ ያለው ደም ይፈስበትና ቀይ ዳማ ያደርጓታል ፤ የታችኛው ከንፈሯ አለወትሮው ይወፍራል ፤ አይኖቿ በአንዳች ወዝ ማብለጭለጭ ይጀምራሉ….በብዙው በጣም በብዙው ናፍቃኛለች!! መንገድ ላይ ዜማና እንጉርጉሮ ስሰማ ሆዴን ይብሰዋል። የኔ ፍትፍት…እንዴት እስካሁን አልደወለችም? የላኳቸው ሽማግሌዎች ሁለት ግዜ እንቢ መባላቸውን ነግረውኛል። ጋሽ ዘበነ እንደውም “ምን ሁነሀል? እንኳንስ ያችን የመሰለች የቀን ጨረቃ ፣ ምን ፉንጋ ብትሆን ልጅን ያህል ነገር ባንዴ አይሰጥም! ጊዜ ይፈልጋል ፤ መመላለስ ይጠይቃል” ብለውኝ ነበር። እኔ ግን እንቢታ ከባድ ነውና ፣ ሁለቴ እንቢ ሲባሉ ሽማግሌዎቹ የሚሰማቸውን ስሜት አስቤ አዘንኩ።

በሌላ ቀን ጋሽ ዘበነ ፤ ንዴት አይናቸውን እንደ ፍም አብርቶት ፣ ፊታቸውን ሸክላ አስመስሎት ፤ እጃቸውን እያወናጨፉ መጡ።
“ኸረረረ…ምነው ልጄ ምነው? ሽማግሌ ሁኘ ልለመንህ ባልኩ ፣ እድሜ ጸጋ ነው ብዬ እግሬን ባነሳሁ….ምነው ልጄ ምነው እኔን ማዋረድ?” ተደናግጬና ግራ ተጋብቼ አየኋቸው።
“ምነው ልጄ ፣ ከልጄ ቆጥሬህ ፣ ወዳጄ ነህ ብዬ አክብሬህ ባምንህ … ሰው ወደማያከብሩ ዋልጌዎች ሰደድከኝ?”
“ጋሽ ዘበነ…ኸረ እባክዎ ይረጋጉና ይንገሩኝ ፤ የተፈጠረውን ለምን አይነግሩኝም?” አልኩ። ፈርቻለሁ። ግማሽ ልቤ ምን እንደተፈጠረ ይገምታል።
“ባለጌዎች ናቸው፤ ባለጌዎች! ሽማግሌ እንደዛ ይባላል? እንኳንስ ላንተ ቀርቶ ለስንቱ ይሰረግ የለ?”
“እኮ ምንድን ነው የተፈጠረው ? ጋሽ ዘበነ ኸረ አስጨነቁኝ”
“እንቢ ማለትኮ መብትም ወግም ነው። በተከበርንበት ሀገር ሽማግሌዎቹን እንደውሻ ተረባርበው አባረሩን ፣ ሰደቡን ፤ ረገሙን”
“ስድብ? እርግማን?” አልኩ
“አዎ ልጄ፣ ለሽምግልና የማትበቁ ቀሊሎች ናችሁ ፣ ዘራችሁ ለክብር አይበቃም ፣ አስተዳደጋችሁ ለትልቅ ሰው ወግ አይሆንም ፤ ብለው ሰድበው አባረሩን! ..አንተን ብዬ እንጂ ልጄ…አርፌ ቁጭ ብል በተከበርኩበት ሀገር…”
የምለው ጠፍቶኝ ክው ብየ ቀረሁ። ወደ ፍትፍት ስልክ ደወልኩ…አታነሳም! በተደጋጋሚ ሞከርኩ...አታነሳም።

ሳምንቱን ያሳለፍኩት በጭንቀት ነበር። አይምሮዬ በሀሳብ ፤ ልቤ በናፍቆት ተወጥሮ እናቱ የታረደችበት ጥጃ መስዬ ተኮራምቻለሁ። ለቅጽበት ከተዘረርኩበት ምንጣፍ ላይ ሁኜ ቤቴን አስተዋልኩት። ተዝረክርኳል። የኖርኩበት የኖርኩበት አልመስልህ አለኝ። አዝኛለሁ። አለም ትከሻዬ ላይ የተደፋች ያህል እንዲሰማኝ በቂ ምክንያት ያገኘሁ መሰለኝ። ፍትፍት ከኔ ሸሽታለች ፣ ትታኛለች ፤ ጋሽ ዘበነ ቤት እንድለቅ ነግረዉኛል። ሰው የጎረቤቱንም የራሱንም ፍቅር ሲያጣ ሀዘኑ ጥልቅ ይሆናልና በጽኑ ታመምኩ። እንዳለፈው ቀን ሁሉ ቀኑን ሙሉ ምንጣፌ ላይ ተዘርግቼ አሳልፌ ፤ ምሽቱ ሲቃረብ ወክ ለማድረግ ወጣሁ። ምሽቱ ስለተቃረበ አስፓልቱ እንደኔ ግራጫ መልክ ይዟል። ከአስፓልቱ ግራና ቀኝ በቆሎ ጠባሾች ተኮልኩለዋል። ትንሽ ወረድ ብሎ ደግሞ ቤተክርስትያን አለ። ቤተ ክርስትያኑን አልፌ ቀጥታ አስፓልቱን መከተል ጀመርኩ። ትንሽ እንደተጓዝኩ ስልኬ ድንገት ጠራ። ልዘጋው ነበር። ዝም ብዬ ማን እንደደወለ ሳይ ፍትፍት ናት። በደስታ አነሳሁት።
“ምን ሁነሽ ነው ግን? ይሄን ያህል ጊዜ?” ብዙ ወቀስኳት። ጭካኔዋን በዝርዝር ነገርኳት። ምንም አላለችኝም። ስታዳምጠኝ ቆየችና
“ቤት ሽማግሌዎቹ ጋር ጥሩ ነገር አልተፈጠረም ነበር … ሰምተሀል አይደል የተፈጠረውን?”
“አዎ ሰምቻለሁ … ባለን ግንኙነት ቤተሰቦችሽ ደስተኛ አይደሉም” አልኳት። ዝም አለችና በረዥሙ ትንፋሿን ስባ የተፈጠረውን በግልጽ አብራርታ ነገረችኝ። አፈርኩ። ተገረምኩ፣ ተጠራጠርኩ…. ምን እንደምል ግራ ገባኝ።
“…ብቻ አንተ ተረጋጋ ለትንሽ ጊዜ ነው ቤተሰቦቼ ቢናደዱ … እንዲያውም አባባ ተበሳጨ እንጂ እናቴኮ ምንም አልመሰላትም ነበር…”
ያለችኝን ብዙ አልሰማኋትም። ወደ ቤት መመለስ አልፈለኩም ። በጥዋት ቤቱን እለቃለሁ። የሚቀርበኝን ፔንሲዎን ኣስልቼ በመጣሁበት መመለስ ጀመርኩ። ቤተክርስትያኑ ጋር ስደርስ ጋሽ ዘበነን እየተሳለሙ አየኋቸው። ከርቀት ባይናቸው ሰላም ቢሉኝም ያላየኋቸው መሰልኩ።

ከቤተክርስትያኑ እንደቆምኩ ጋሽ ዘበነ ወደኔ ቀረብ ብለው “አይ ልጄ…እንደው ያሁን ልጆች ትቸኩላላችሁ ፤ ምናለ አሁን ደህና ቤተሰብ ያላትን ደህና ልጅ ብታፈላልግ? ‘ባልኮ የሚስት ቤተሰብንም አብሮ ያገባል’ ይባላል። አየህ ልጄ…እኔና ሚስቴ ስንጋባ ተጠናንተን ነው። ቤተሰብ ለቤተሰብ በደንብ ተዋውቀን ነው”
ብታዘባቸውም እድሜ ክቡር ነውና ዝም አልኳቸው።
👍5
በመሀል አያቴ የነገረኝ ታሪክ ትዝ አለኝና ፈገግ አልኩ። ባንድ ወቅት ሁለት ሰዎች ወደ ገበያ አቅንተው ነው አሉ። አንደኛው ነጠላውን ትከሻው ላይ አድርጎ ስለ ገበያው በተመስጦ እያወራ ይገሰግሳል። ያኛው ቀስ ብሎ ትከሻው ላይ ያደረገውን ነጠላ አንስቶ ራሱ ላይ ጠመጠመው። ጥቂት ከተጓዙ በኋላ ያ ነጠላው የተነሳበት ሰውየ ወደ ትከሻው እጁን ቢሰድ ነጠላውን አጣው። “ጓዴ! ጨርቄን ጉድ ተሰራውልህ …..ጉድ ተሰራውልህ” እያለ ሲጮህ… ያኛው ቀበል ብሎ “ጥፋቱኮ ያንተ ነው ፤ እንደኔ እራስህ ላይ አትጠመጥመውም ኑሯል?” አለው ይባላል። ጋሽ ዘበነ ሰፈርም አንዳንዴ ሲወራባቸው እሰማ ነበር። “ተማሪዎችን ይሸኛሉ ፤ ወጣቶች ጋር ይቀጣጠራሉ ” እየተባለ። በዚህ ምክንያት ከሚስታቸው ጋር ተጣልተው እንደነበርም አስታውሳለሁ። ብቻ ፍትፍት ያለችኝን ግን አልጠበኩትም ነበር። ሽማግሌ ሁኑኝ ብየ ልኬያቸው ፣ የፍትፍትን ደምግባት ያዩ ጊዜ … ሽምግልናውን ወደራሳቸው ሊያዞሩት... ፍትፍቴን ለራሳቸው ሊያደርጉ… ብቻ ያስጠላል። ከተማዋ አስጠላችኝ። ይረጋል ያሉት እየሞቀ ፤ የሰክናል ያሉት እየተንቀዠቀዠ …ከተማዋን ፈራኋት። ጋሽ ዘበነ ትልቁን ቆዳ ጫማቸውን ገጭ ገጭ እያደረጉ ወደ ቤተክርስትያኑ ሲገቡ ከኋላቸው ሁኜ በጸጥታ አየኋቸው። ወድያው ከ“ተንኮለኛው እግዜር” ከሚል የግጥም ስብስብ ውስጥ አንዲት ግጥም ትዝ አለችኝ። በውስጤ እያብላላኋት ጉዞዬን ቀጠልኩ።

#ጫማ_ለዘመን_ሰው

የቆምህባት ምድር
የተቀደሰች ናት ፥ ጫማህን አጥልቀው
ቅድስት ናት ብለህ ፥ ከቶ እንዳታወልቀው
ስንቴ እርቃን ሄደሀል ፥ ከአገልጋይህ አልጋ ?
ስንቴ ተራምደሀል ፥ ዝሙትን ፍለጋ ?
ስንቱንስ ጠልፈኸው ፥ ወድቆ ተዘረጋ ?
በል አጥልቅ ተጫማ ፥ ለቅድስቷ ምድርህ
ጫማህ ይሻላታል ፥ ከተረገመ እግርህ !!

💫አለቀ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ።
👍3
#ተኖረና_ተሞተ

ያኔ ድሮ ድሮ በአባቶቼ ዘመን
በአያቶቼ ወገን
መከባበር ነበር በፍቅር ተክኖ
በታመነ ዑደት በባህሪ ታጥኖ
ቁም ነገር ተግብሮ
ታለፈ ተኑሮ
በኛሚ…
ተኖረና ተሞተ
ዛሬስ ተተረተ
ጥንትማ ተኑሯል በጥበበኞቹ
ብሂል ቅጡን አጣ በስልጡኑዎቹ
Forwarded from Quality Button
📚 የተለያዩ ድርሰቶችን ለማግኘት📚
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
#ሮዛ_2


#ክፍል_ስምንት (🔞)


እኩል ኤሜን ብለው ምግቡን ባረኩት። ገረመኝ። ሃይማኖተኛ ይሆናሉ ብዬ በፍጹም አልጠበቅኩም ነበር። “
ደግሞ እሱን ብሎ ሃይማኖተኛ!"

ማሪያ የሚገርም ሽሮ ወጥ ሰርታ ነበር። ስቀምሰው ማመን ከበደኝ። የምር ነበር በሙያዋ የተደነቅኩት።እሷ አልሰራችውም እንዳልል ቤታቸው ሰራተኛ የላቸውም፡፡ ቀደም ሲል የተሰራ ነው እንዳልል ትኩስና ለኔ ሲባል የተሰራ እንደሆነ ከዲጂታል ስቶቩ ሲወርድ አይቼዋለሁ።

Mariya. You are an amazing cook You know that!” አልኳት ጥቂት ጉርሻዎችን አከታትዬ ከጎረስኩ በኋላ

"Oh! Do you like it?"

"Of course I do. It is so yummy!

«ለምዳዋለች ባክሽ አድናቆቱን! ሁሉም ሀበሻ እዚህ በተጋበዘ ቁጥር የምትሰራው ወጥ ተአምር ሆኖበት ነው የሚሄደው። እሷም ይሄንን ስለምታውቅ ነው ካልሰራሁልሽ ብላ ሙጭጭ ያለችው።›› አለኝ ዶክ በወሬያችን ጣልቃ ገብቶ።

What did you say?”አለችው አማርኛው ሲፈጥንባት

"Nothing just telling her how people admire your cooking..."
ዶክተር ቃለአብ የተናገረው ነገር እሷን ለማንኳሰስ መስሎ ስለተሰማኝ ቅር ተሰኘሁበት። እሷ ግን ያለው ስላልገባት ነው መሰለኝ ምንም አልመሰላትም። እንዳስተዋልኩት ከሆነ አማርኛ ግጥም አድርጋ ባትሰማም መንፈሱ ይገባታል። አንዲት የዶክ ተማሪ በፍቃደኝነት እየመጣች ማታ ማታ አማርኛ
እያስተማረቻት እንደሆነ ነገረችኝ።

«አማርኛ ጎበዝነው ኢኔ። am learning everyday! Now ጎበዝ ጎበዝ ኢናገራል! »አለችኝ።

ሳቅኩኝ!

አማርኛዋ ኩልትፍትፍ ያለና እንደ ሰራችው ሽሮ የሚጣፍጥ ነበር።

ሽሮ ላጉርስሽ አልኳት።

ዶክተር ጣልቃ ገብቶ እንጀራ እንደማትወድ ነግሮ አስጠነቀቀኝ።


"Oh Really? why እንጀራ የማይወድ ሰው አለ እንዴ ?" የምሬን ነበር የተገረምኩት።ፈረጆች ከኛ በላይ እንጀራ የሚወዱ ነበር የሚመስሉኝ።

See, I think the reason goes back to my first experience of Enjera in Frankfurt. That was even before meeting kalab..right honey ?

"Yeah I guess to አላት ምግቡ ላይ እንዳቀረቀረ።

So When I see it first, I thought it is a small traditional towel or something like that.
I am sorry to say this, but that was what I honestly felt at the time. So, when I tested
it then, I realized that it is too sour to have it on everyday meal. You may hate me for
saying this, but I can't help it Roz" ብላ በትልቁ ተነፈሰች።

«ዝምበያት ባክሽ! ዝምብላ ነው የምትቀባጥረው። ዋናው ምክንያቷ ምን መሰለሽ! የመጀርያ ቀን ተሸውዳ፣ ባህላዊ ፎጣ መስሏት ጭኗ ላይ ዘርግታው ስለነበረ ነው በዚያው ጠልታው የቀረችው፤ እኔ ደሞ ሁልጊዜ ያኔ ያረገችውን እያነሳሁ ስለማስቅባት ትናደዳለች፤ በዚያው እንጀራ የሚባል ነገር አልጥምሽ አላት። እንጀራ እንደማትወድ ለሰው እንዲነገርባት አትፈልግም፤ አንቺን ስለቀረበችሽ ነው
የምትነግርሽ» አለኝ።

እንጀራ ባለመውደዱ ትንሽ ቢከፋኝም ስሜቴ እንዳይታወቅብኝ ፈገግ አልኩላት።

እሷም በፈገግታ ምላሽ ሰጠችኝ።

"So about the book ...tell her Marre, please!"

"Which book?"

This bookብሎ ቅድም ከላይብረሪ ይዤው የመጣሁትን Transgender የሚለውን መጽሐፍ
ጠቆማት።

"Oh ok..! ሚን መሰለሽ ሮዝ You may find this story very shocking .l was freshman student at ludwig maximilan University munich at the time..."

ልትነግረኝ ካሰበችው ታሪክ ይልቅ «ሚን መስላሽ!» የሚለው አማርኛዋ ገርሞኝ አሳቀኝ።አማርኛ የማይችል ሰው ይለዋል ብዬ የማልጠብቀውን ቃል ስለተናገረች ነው መሰለኝ ሳቄ መላልሶ እስቸገረ"

"So to make the long story short...A close girl friend of mine convinced me to change
a matter of chance, all our guys at the time used to cheat on us or dump us lot reason. We were so offended by all these evil creatures called men, and started hating them all ha ha ha..."

አፏን ከፍታ ስትስቅ ጥርሷ ቢጫ እንደሆነ ገና አሁን ማስተዋሌ ነው። ጥርሷ በፍጹም አያምርም።

"...We decided to change our gender, yeah! Just like that. At that time the idea of tranesgender was very popular in Germany. I talked to my dad about my Decision he was so smart. He told me to change my mind before my gender. And showed me how silly
was.Then I started cheating on guys before they cheat on me.. Guess what?, men started loving me more and wanted me even so much more when start cheating see it worked! Then I thanked my father... And I cheated and cheated and cheated on me until I met Kaleb!

(ዶክተር ቃለአብን በስሙ ስትጠራው ካሌብ ነው የምትለው)

ይህንን ወሬዋን እያወራችን ሳለ ዶክተር ቃልአብን በዓይኔ ቂጥ እየተከታተልኩት ነበር። ፊቱ ጨጓራ ሲመስልና የዉሸት የሚመስል ፈገግታ ሊያሳያት ሲሞክር እጅ ከፍንጅ ይዤዋለሁ። በዚህ ታሪክ ዉስጥ የሆነ ያልገባኝ ነገር እንዳለ ተረዳሁ። ብቻ በሁለቱ ግንኙነት ውስጥ፣ በሁለቱ የሚያስቀና ፍቅር ውስጥ
መብራራት ያለበት አንድ ነገር ያለ መሰለኝ።
በዚህ መሐል ማሪያ ወጥ ያነሰኝ ስለመሰላት ልታመጣልኝ ወደ ኪቾን ስትገባ በዚያው ፍጥነት
ዶክተር ቃልአብ ግራ እጁን በፍጥነት ወደ ጭኖቼ ላከው። ስነ ስርዓት እንድይዝ ብዬ በጥፍሬ ከፉኛ ባጨርኩት። እሱ እቴ ዝምብ ያረፈችበት ሁሉ አልመሰለውም። የመሐል ጣቱን ላይብረሪ ውስጥ ተርትሮት ወደ ነበረው ፓንቴ ውስጥ ላከው።ብን ብን የምትል ሚኒ ማድረጌ እደፈንለገው ገብቶ እንዲወጣ ሳይመቸው አልቀረም።የ "ባብሼን” ከንፈሮች መነካካት ሲጀምር የማሪያ ኮቴ ተሰማ።
አውጥቶ በቀኝ እጁ በያዘው ሹካ አቀርቅሮ መጉረስ ጀመረ።

Roz You are not eating enough, are you? አለችኝ። እጅግ በጣም ደነገጥኩ። እኔ የመሰለኝ፣
you are not cheating enough, are you ያለች ነበር የመሰለኝ። የሌባ ነገር።

እንደገና የፊቴን መለዋወጥ አይታ “Roz Are you alright?” አለችኝ በድጋሚ።

"Yes I am, why do you ask?...) am over stuffed see my plate? It's too clean that you may
not need to do the dishes later." አልኳት

ንግግሬ አሳቃትና እንዲህ አለችኝ… “በደንብ ቢላ! የበላ and
👍92
ተማሬ ውድቅ የለም”

መጀመርያ ምን ማለት እንደፈለገች አልገባኝም ነበር፤ ለማለት የፈለገችውን ዶክ ሲተረጉምልኝ ነው በጣም የሳቅኩት። " ጥቅሶችን የመሰብሰብ ልምድ አላት። ከኢትዮጵያ አባባሎች በጣም የምትወደው ደግሞ አሁን ያለችሽን ነው«የበላና የተማረ ወድቆ አይወድቅም» ነው ያለችሽ፤ ሰምተሻታል? አሁንማ
ቅኔ መዝረፍ እኮ ነው የቀራት” አለኝ።
እግሬን ሰቅዬ ሳቅኩኝ።

You want ጉርሻ from me?” አለችኝ፡፡

No no! Not at all (አማርኛዋ በድጋሚ አስቆኛል፤ ጉርሻ የሚለውን ቃል እንዴት ለይታ እንደሸመደደችው ገረመኝ
ትራንስጀንደር የሚለውን መጽሐፍ ገጠመኝ ማውራት ስትቀጥል ዶክተር ቃለአብ እሷን የሚያደምጥ
መስሎ ስእግሩ እግሬን፤ በተለይም ባቴ አካባቢ ይነካካኝ ጀመር፤ ከጠረጴዛ ስር። ሚስቱ በሴንቲሜትሮች ርቀት እያለች ይሄን ማድረጉ እጅግ አስደነገጠኝ። ምናለ እስክትሄድለት እንኳ ቢጠብቅ። በድርጊቱ
ፊቱ ቀይ እንዳይሆን እየተጨነቅኩ ለማንኛውም ቅድም እንዳደረገው እጁን እንዳይሰድብኝ ጭኖቼን ግጥም አድርጌ ያዝኳቸው። ዶክተር ቃልአብ ግን የሚያደርገውን አሳጣው። ይባስ ብሎ እሷ እዚያው ከጠረጴዛው ሳትነሳ ግራ እጁን በድጋሚ በሆዴ በኩል ወደ ጭኖቼ ላከው። እሷ ዝም ብላ ይህን ወሬ ታንበለብለዋለች።

ወንበሩ እንዳልተመቸው ሰው ሆኜ አውቄ ከተቀመጥኩበት እንደመቁነጥነጥ አልኩና ፈቀቅ አልኩ። ይሄን ጊዜ ዶክተር ቃልአብ እጁን ሰበሰበ።



ተንኮሉ ግን በዚ አላበቃም ወድያው ማርያን"..Marre, do you have more of this, please ብሎ ሰላጣ እንድታመጣለት ተማፀናት።

Of course hony! Just a second ብላ ተነስታ ወደ ኪችን መራመድ ስትጀምር I love you for that" አላት።

Love you too" አለችው።

ከመቅጽበት ፊቱን ወደኔ መልሶ ጭኖቼን በግራ እጁ በኃይል ፈልቅቋቸው ገባ። ለመከላከል በጣም ዘግይቼ ነበር። በግራ እጅ ባለጌ ጣቱ የባብሼን ከንፈሮች ቦጫጨረኝ። ከመቼው ዉሃ እንደሆንኩ ለኔም ግራ ሆኖብኛል። ደጋግሞ አባለገኝ። በተለይ ሲቧጭረኝ የፈጠረብኝ ስሜት ከቁጥጥሬ ዉጭ አደረገኝ ጭኖቼን ሳልፈልግ ከፈትኩለት። ዐይኔ ከቁጥጥሬ ዉጭ ሆኖ መስለምለም ጀመረ። እንዴትም ብዬ አይኔን ገልጬ ቃልአብን ሳየው ራሱን ስቷል። የፊቱ ደም ስር ተገታትሯል። ጭምልቅልቅ አደረገኝ።
ደግሞ አሳመመኝ።ሳላስበው ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ ስሜት ውስጥ ገባሁ። እንደሚያለቅስ ሰው ክንዴን ተንተርሼ አንገቴን ጠረጴዛው ላይ ቀበርኩት። ተስፋ ቆርጬ ነበር። ወይም ግድ ማጣት ዉስጥ ገብቼ ነበር። ስዝለፈለፍበት ዶክተር ቃልአብ ይበልጥ ነጻነት በማግኘቱ ጣቶቹን አንቀሳቀሳቸው። ይህን ጊዜ ድምጽ የሰማሁ መሰለኝ። አፈርኩ፡አመመኝ። ከቁጥጥር ዉጭ በሆነ ስሜት አቃሰትኩ።
ብሎ ሰላጣ እንድታመጣለት ተማጸናት።

ይህ ሁሉ የሆነው ከአንድ ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ቢሆን ነው።

“Did somebody call my name?” አለች ማሪያ ከኪችን ሆና። የኔን ማቃሰት ሰምታ መሆን አለበት።
Yes ..sweet heart t's me , can I have more water please!” አለ ድምጹ እየተቆራረጠበት፡፤

Hony! It is already here on the table, can't you see it?” አለች በአንድ እጁ ሰላጣ በሌላ እጁ
የካርቶን ጁስ ጭማቂ ይዛ ወደ ሳሎኑ እየገባች፡፡

በዚህ ቅጽበት የዶክተር ቃልአብን እጅ ወጥ በነካው እጄ ከጭኖቼ መሐል መንጭቄ አወጣሁት። ደንግጦ
እጁን ሰበሰበ፡፡ ዉሀ ጠረጴዛው ላይ እያለ ዉሃ አምጪልኝ ማለቱ ሌላ ዉጥረት ውስጥ ከተተው።

ምን እንደተፈጠረ ጭራሽ ያልተገለጠላት ሚስት ገና ከመቀመጧ ዉሃውን ቀዳችለትና ያቋረጠችውን ወሬ መቀጠል ያዘች። ከድንጋጤዬ የተነሳ ለምታወራው ነገር ለእያንዳንዱ አንገቴን በአውንታ ከፉኛ መነቅነቅ ጀመርኩ። እግሮቼ ግን ከስር መንቀጥቀጥ ጀምረው ነበር። በምትለው ሁሉ ለመሳቅ ሞከርኩ።
ድምብርብሬ ወጥቷል። ቀና ብሎ ዶክተር ቃልአብን ለማየት የሚያስችል ጉልበት እንኳ አልነበረኝም። እሷን እሷን እያየሁ ወሬውን እንድትቀጥልልኝ በአውንታ ራሴን መነቅነቅ አላቆምኩም፡፡ እውነቱን
ለመናገር በወቅቱ ስለምን ታወራ እንደነበረም ትዝ አይለኝም።

ከእግሮቼ መሐል የተበላሸሁ ስለመሰለኝ ድንገት የማቅለሽለሽ ስሜት ተሰማኝ። አንድ ብርጭቆ ዉሃ ስጠጣበት ትንሽ ቀለል አለልኝ። ብርጭቆውን ሳነሳው ግን እጄ ይንቀጠቀጥ ነበር። ሆኖም ከደቂቃዎች በፊት እዚሁ ጠረጴዛ ላይ ምን እየሆነ እንደነበር ሳስብ መረጋጋት አቃተኝ፡

“Excuse me!"ብያቸው እጄን ለመታጠብ ስነላ እግሬ እየከዳኝ እንደሆነ ታወቀኝ። ከባብሼ ፈሳሽ
የወጣ ስለመሰለኝ ሳልዋረድ ቶሎ ብዬ መልሼ ተቀመጥኩ።

“Roz! Are you alright?” አለችኝ ማሪያ ነገረ ስራዬ አልጥምሽ ብሏት። ምግቡ ሳይስማማኝ ቀርቶ
ያመመኝ ሳይመስላት አልቀረም።

"No I am fine! Feeling a bit nausea...sorry!"

"Oh Gash! That may be from what you ate? Do you have allergic or something...Shall
We take you to the hospital?”

ተረበሸች መሰለኝ ነገሩን በጣም አካበደች።

ትንሽ አመም እንዳደረገኝና ሽንት ቤት ብቻ መሄድ እንደምፈልግ ተናግሬ ተነሳሁ።
"hay kalab why dont you move your ass. Are you sick too?" ብላ ባሏ ላይ አምባረቀችበት ያለወትሮው ፍዝዝ ሲልባት በንዴት ጦፈች።

"Please Maria, do not worry at all. I will be fine" አልኩ የሞት ሞቴን።

ወደ ዶክተር ቃልአብ ስዞር ሸሚዙ ወጥ ነክቶት እንደተበላሸ አስተዋልኩ። ለካንስ ቅድም እጁን ከጭኔ ለማውጣት ስመነጭቀው ወጥ በነካው ቀኝ እጄ አበላሽቼዋለሁ። ሚስቱ ካየች ሌላ ነገር እንዳትጠረጥር ስለፈራሁ ቶሎ ብዬ የሱን ወጥ ያበላሸውን ሸሚዝ ክንድ፣ ወጥ በነካው እጄ በድጋሚ፣ እሷ እንድታየኝ ሆኜ ተደግፊው ለመቆም ሞከርኩ።

“ይቅርታ ዶክተር ልብስህን አበላሸሁብህ አይደል? አልኩት የደነገጥኩ መስዬ።

«i ts ok! ዋናው ያንቺ ደህና መሆን ነው!» አለ የሞት ሞቱን፡፤

እዚያው ትንሽዬ ድራማ ሰራን። ድራማዋ ግቧን እንደመታች ሳውቅ ቀለል አለኝ።

በዚያው ዶክተር ቃልአብን ተደግፌ ወደ ባዝ ሩም ሄድኩኝ። እግሬ ከደቂቃ በፊት ድንግልናዋ እንደተወሰደ ኮረዳ ዉልግድግድ እያለ አስቸገረኝ። ጭኖቼን ሳላላቅቅ ለመራመድ ሞከርኩ። ፓንቴ
መቀደዱን ሳስብ ደግሞ እዚያው በቆምኩበት ሽንቴ የሚያመልጠኝ መሰለኝ። እንደገና ሀሳቤ ራሱ አሳቀኝ። እስከዛሬ በቁሜ ያልሸናሁት ፓንቴ እንደ ዳይፐር እያገለገለኝ ስለነበረ ነው እንዴ? ምኗ ደባሪት ነኝ?

ዶክተር ቃልአብ ሽንት ቤት አደረሰኝና የማሪያን አለመኖር አይቶ ነው መሰለኝ እንደገና ሊስመኝ ሲሞክር
በጥፊ አላስኩት። እንደ ህጻን ልጅ ደንግጦ ኩርምት አለ። አሳዘነኝ፤ ግን ምንም ማድረግ አልችልም።

ሽንት ቤቱን ከውስጥ ቆልፌ ሁለመናዬን ተጣጠብኩ። ባዝሩሙን ከውስጥ ስቆልፈው የተሰማኝ እፎይታ አሁን በቃላት ልገልጸው አልችልም። ዶክተር ቃልአብ የቦጫጨቀውን ፓንቴን አውልቄ
ቦርሳዬ ውሰጥ ያዝኩት። ፊቴን በቀዝቃዛ ዉሀ ስታጠብ ቅልል አለኝ። እግሬ በደንብ እንደሚራመድልኝ እርግጠኛ እስክሆን ድረስ ቧንቧው እንዲፈስ ከፍቼ ተውኩትና እዚያው ቆየሁ። ማሪያ እኔ ወዳለሁበት
ወደ ባዝ ሩም ተጠግታ ድምፅዋን ጎላ አድርጋ ደህና መሆኔን ጠየቀችኝ። አሁን የማቅለሽለሽ ስሜቱ ሙሉ በሙሉ እንደጠፋልኝ ነገርኳትና
👍102
በሩን ከፈትኩት። ፊቴ መረጋጋቱን ስታይ እፎይታ ተሰማት።
ሲያመኝ ከፍተኛ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰምቷት እንደነበር ገለጸችልኝ፡፡ በሷ ቤት የሷ ሽሮ ያሳመመኝ ነው የመሰላት የፈረንጅ ምስኪን!

ከባዝ ሩም ወጥቼ ስራመድ እግሬ እርስ በርሱ መምታታቱን እንዳላቆመ ተረዳሁ። ዶክ ባላንሴን የሚያስት የሆነ ብሎኔን "ባቢሼ" ውስጥ ገብቶ ሳይፈታብኝ አልቀረም።

ዶክተር ቃልአብ ወጥ ያበላሸው ሸሚዙን ቀይሮ የባስኬት ቦል ኳስ ፎቶ ያለበትን ቲሸርት አድርጎ ደረጃውን ሲወርድ አየሁት። ደህና መሆኔን በእንግሊዝኛ ጠየቀኝ። ፊቱ ላይ የሆነ ፈገግታ ብልጭ ሲል አየሁ ያሰበውን በማሳካቱ ደስ ሳይለው አልቀረም።በትክክል አላማው ምን እንደ ነበር ግን እስካሁንም አልተገለፀልኝም።

ለአንድ ሰአት ያህል ተረጋግተን ዉስኪ እየጠጣን ተጫወትን። በመሐል ቡችሎቹ እየመጡ እላዬ ላይ ሲመጡ እየፈራሁ ተቸገርኩ። ሆኖም እነሱን በፍፁም እንዳላመናጭቅ ዶክ አስጠንቅቆኝ ስለነበር እንደማጫወት እያረኩ ተከላከልኳቸው። ያማምራሉ። የሚደረግላቸው እንክብካቤ ግን ለሰው ልጅ ከሚያደርገው በላይ ነው።

ሳሎን ባር ቁጭ ብለን ዘና ብለን ማውራት ጀመርን።

Transgender የሚለው መጽሀፍ ሙኒክ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያለች በወንዶች ድርጊት ከመማረሯ የተነሳ ጾታዋን ለማስቀየር በወሰነች ጊዜ የገዛችው መጽሐፍ እንደነበረ ነገረችኝ። ሆኖም በኋላ ላይ በአባቷ ምክር ሀሳቡን እርግፍ አድርጋ እንደተወችው በድጋሚ ተረከችልኝ። ወንዶችን እንዴት መያዝ እንዳለባት አባቷ ድንቅ ምክሮችን መከራት። ምክሩን ተግባራዊ አድርጋ በአንድ አመት ውስጥ ዉጤት ካላገኘችበት ጾታዋን የመቀየር ዉሳኔዋን እንደሚያከብር በጊዜው አባቷ ቃል ገብቶላት እንደነበርም ደግማ አጫወተችኝ። እኔ በበኩሌ አባቷ አበሻ አባት ቢሆን ቀጥቅጦ ይገድላት እንደነበር
አስረዳኋት።ትስቃለች ብዬ ሳስብ ግን ደነገጠች።

ዶክተር ቃልአብም በየመሀሉ እየገባ ይቀልድባት ጀመር። ዉሳኔዋን ገፍታበት ቢሆን ኖሮ ዛሬ ቆንጅዬ
የወንድ ጓደኛው ልትሆን ትችል እንደነበር እያወራ አሳቃት።

እሷ በበኩሏ ወንዶች ሲባልጉ እሷም በምላሹ መባለግ ስትጀምር እንዴት የበለጠ እየወደዷትና እያከበሯት እንደመጡም ታስረዳኝ ጀመር። ይህን ስታወራ ዶክተር ቃለአብ ፊቱ ከአንዴም ሁለት ሶስት ጊዜ ሊለዋወጥ እያስተዋልኩ። በሁለቱ ግንኙነት ወስጥ የሆነ አንድ ያልገባኝ ነገር እንዳለ እርግጠኛ ሆኑክ...

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
2👍1
አትሮኖስ pinned «#ሮዛ_2 ፡ ፡ #ክፍል_ስምንት (🔞) ፡ ፡ እኩል ኤሜን ብለው ምግቡን ባረኩት። ገረመኝ። ሃይማኖተኛ ይሆናሉ ብዬ በፍጹም አልጠበቅኩም ነበር። “ ደግሞ እሱን ብሎ ሃይማኖተኛ!" ማሪያ የሚገርም ሽሮ ወጥ ሰርታ ነበር። ስቀምሰው ማመን ከበደኝ። የምር ነበር በሙያዋ የተደነቅኩት።እሷ አልሰራችውም እንዳልል ቤታቸው ሰራተኛ የላቸውም፡፡ ቀደም ሲል የተሰራ ነው እንዳልል ትኩስና ለኔ ሲባል የተሰራ እንደሆነ ከዲጂታል…»
#ከዚህ_ወድያ_አልወድሽም

ከዚህ ወድያ እልወድሽም
የለም እወድሻለሁ ገና
ማፍቀር አጭር ቢሆንም
መርሳት ረጅም ነውና።
#ስጦታሽን_እንኪ

እመቤት ተፈጥሮ፤ሰላም ሰላም ለኪ
እዳሽን በቁና
ጸጋሽን በቆርኪ
ስትሰፍሪ መቀበል፤ሰልችቶኛልና
ነፃነቴን አምጪ፤ስጦታሽን እንኪ።
#አልረሳሁትም !

#በናትናኤል

“ ምናልባት ሴት ልጅ ለመጀመርያ ጊዜ አንሶላ የተጋፈፋትን ወንድ ልትረሳው ትችላለች ። ምናልባትም ለመጀመርያ ጊዜ እግሯ ስር ተንበርክኮ በደብዳቤና በአካል እያነባ ‘አፈቅርሻለሁ’ ያላትን ወንድ ልትረሳ ትችላለች ። ነገር ግን እልሀለሁ የትኛዋም ሴት በየትኛውም ሁኔታ ለመጀመርያ ጊዜ "አፈቅርሀለሁ" ያለችውን ወንድ አትረሳውም!! እንደቁርአን በልቧ ተሸክማው ፣ እንደ ታቦት የነፍሷ ከፍታ ውስጥ የምትጨምረው ፣ ለአባቷ ካዘጋጀችው ውብ መንበር ሳታሳንስ የምታነግሰው ንጉስ ለመጀመርያ ጊዜ ‘አፈቅርሀለሁ’ ያለችው ወንድ ነው … እና በፍፁም ልትረሳው አትችልም ። “
ለስንተኛ ጊዜ እንደሆነ ባላውቅም ታሪኳን ስትነግረኝ እያዳመጥኳት ነው ። አዲስ ታሪክ እንደሚሰማ ሰው ጆሮዬን ቀስሬ አዳምጣታለሁ ። ሁሌም እንደምታደርገው አየር ወደ ውስጥ ከሳበች በኋላ ቀጠለች።
“….ልጁ መምህራችን ነበር ። የስምንተኛ ክፍል የህብረተሰብ ትምህርት አስተማሪ! ብዙ ጊዜ ጠቆር ያለ ቲሸርትና ሰማያዊ ጂንስ ሱሪ ይለብሳል። ክረምት ክረምት ከአጎቴ ሻይ ቤት አየዋለሁ ። ሌላ የምለው ነገር የለኝም …ወደድኩት ! ፣ እያክለፈለፈ አይኔን ከእሱ ላይ እንዳልነቅል የሚያደርግ የጦዘ የአይን ፍቅር ያዘኝ ።
ከአጎቴ ሻይ ቤት ውስጥ በአግዛለሁ ሰበብ እያስተናገድኩ ያይን ረሀቤን ማስታገስ ጀመርኩ ። ትምህርት ሲጀመር ደግሞ ለኔ የተባረከ ዘመኔ እንደተከፈተ ሁሉ ደስታ የምሆነውን አሳጣኝ ። ተማሪው ሁሉ ይሄ መከረኛ ትምህርት ተጀመረ እያለ ሲያላዝን እኔ ግን የደስታ ባህር ውስጥ ተንሳፈፍኩ ።
ወደ ስምንተኛ ክፍል መዘዋወሬን ገና ካርዴ ላይ እንዳየሁ እንደ ህፃን ልጅ ነበር የፈነደኩት። መዘዋወር ብርቄ ሁኖ አይደለም ። ሙሉ የት/ቤታችን ተማሪ ‘ማህሌት’ ን የሚያውቀኝ በጉብዝናዬ ነው ። ከመላው ሴክሽን አንደኛ ደረጃን በመያዝ ! ማሂ ማን ናት ከተባለ ‘ማሂ…ያቺ ቀለሜዋ ተማሪ! ያቺ የት/ቤቱን ሽልማት በየአመቱ የምትወስደው! ሽልማቱን ግን ለምን አስቀድመው ከሷ ቤት አያስቀምጡትም? ሌላ የሚወስደው የለ! ‘ የሚባልልኝ ጎበዝ ተማሪ !
እኔን ያስፈነደቀኝ መዘዋወሬ ሳይሆን መምህር ቶማስ ሊያስተምረኝ መሆኑን አስቤ ነው ። ‘እስከዛሬ በስርቆሽ የማየውን ፍቅሬን ቢያንስ በሳምንት ለአምስት ቀናት አየዋለሁ ። ሶስት ቀን ክፍል ውስጥ ቅዳሜና እሁድ ደግሞ ከአጎቴ ሻይ ቤት! ‘ ብዬ አስቤ ..’’
አንዳንዴ ወሬዋን ታቆምና ነፋስ የበተነው ጸጉሯን ወደ ኋላ ትመልሰዋለች ። ዩንቨርስቲው ውስጥ ድንቅ ጸጉር ያላት መምህር እሷ ብቻ ናት ። ዩንቨርስቲው ውስጥ እንደ ተማሪዋ ሳይሆን እንደ ጓደኛ ከልቧ አቅርባ የምታወራኝ መምህር እሷ ብቻ ናት ። ዩንቨርስቲው ውስጥ ካሉ ሴት መምህራን ቆንጆዋ እሷ ብቻ ናት ። ጸጉሯን እና ትዝታዋን ወደ ኋላ መልሳ ትረካዋን ትቀጥላለች ….
“አየህ ወደ ስምንተኛ ክፍል ሳልፍ ነገሮች የተመቻቹ ቢመስልም ህይወት ያስተማረችኝ አንድ ነገር አለ…ነገሮች ሁሌም እንዳሰብናቸው አይሄዱም! ። አመታችን የደስታ ይሆናል ብለን ስንተነብይ ደስታ ሳይጠጋን ያልፋል ። ጊዜው የሀዘን ነው ብለን ስናማርር ጨለማ ውስጥ እንደተለኮሰች ሻማ ድንገተኛ የተስፋ ብርሀን እናያለን ። ህይወት እንደዛ ናት ። ህይወት ነብያት የሌሏት ቤተ መቅደስ ፣ ጠንቋይ የማታውቅ ቤተ መርከስ ናት ። እኛ ያልነው አይሆንም ።
የመጀመርያውን ሴሜስተር አይኖቼን ከአይኖቹ ሳልነቅል ፍዝዝ ብዬ እያየሁት በደስታ አሳለፍኩ ። ሁለተኛ ሴሜስተር የሚኒስትሪ ፈተና እየተቃረበ ሲመጣ ግን አንድ ሀሳብ በመብረቅ የተመታሁ ያህል ክው እንድል አደረገኝ ። ከዚህ በኋላ መምህር ቶማስን አላየውም። ምክንያቱም የምዘዋወረው ወደ ዘጠነኛ ክፍል ነው ። ወደ ሀይስኩል ወደ ሌላ ት/ቤት!
በቅፅበት ውስጤን ጨለማ ሲሞላው ታወቀኝ። ብርሀን አይቼ የማላውቅ የጨለማ ዘመን ነዋሪ የሆንኩ ያህል ተሰማኝ ።’’ ማውራቷን አቁማ ከንፈሯን ነከሰች ። ከንፈሯን ስትነክስ እኔም የራሴን ከንፈር ነከስኩ ። ምንም ያልሆነው አፍንጫዋን እንደመጥረግ ካደረገች በኋላ በለዘበ ድምጽ መተረኳን ቀጠለች ።
“አየህ……ማንም ያልጠበቀውን ውሳኔ ነበር የወሰንኩት ። ወሬው ት/ቤታችንን አልፎ ፣ ሰፈራችንን ተሻግሮ በየቦታው ተወራ ። ለጥየቃ የሚመጡ ዘመዶቻችን ሳይቀር "አይይይ" ይላሉ ሲያዩኝ ። ከአጎቴ ሻይ ቤት ለመሄድ እንኳ አፈርኩ! ወሬው በቅፅበት ነበር የተዛመተው ። ማሂ ሚኒስትሪን ወደቀች! "
ክረምቱ አልፎ ት/ት ሲጀመር የቤተሰቦቼን ሀዘን ላለማየት የደፋሁትን አንገት ቀጥ አድርጌ መምህር ቶማስ ላይ ማፍጠጤን ቀጠልኩ ። የሆነ ተስፋ ታይቶኝ ነበር ። አለ አይደል ዘመኗን ሁሉ ጭጋግ የሸፈናት ጨረቃ ፍንትው ስትል አይነት ተስፋ ። እንደዛ ተሰምቶኝ ነበር ። የመጀመርያው ሴሜስተር ሲያልቅ ግን ጭጋጉ መልሶ አሸነፈ ። የሚኒስትሪ ፈተና መልስ መስጫ ወረቀት ጋር ስፋጠጥ እሱን ላለማየት የምፈርመው ፊርማ እየመሰለኝ ተሳቀኩ ። በድጋሚ ተወራ ‘ማሂ ወደቀች!’ አባቴ በንዴት እብድ ሆነ ። እናቴ አዘነች ።
በቤተሰቦቼ ያልተደረገልኝ ነገር አልነበረም ። ቢጨንቃቸው የግል መምህር ቀጠሩልኝ ። አስጠኚዬ የማውቀውን ነገር ሊያስረዳኝ ይጥራል ። እኔ ሀሳቤ ከፍቅሬ ጋር ነው ። ሁለተኛው ሴሜስተር ሲደርስ ግን ከጭንቀቴ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመገላገል ወሰንኩ ። ልነግረው ወሰንኩ ። ‘ ቀላልኮ ነው!’ አልኩት ራሴን ። ‘በቃ አንዴ ላናግርህ ትይውና ከዛ አፍቅሬሀለሁ ማለት !’ ግን አልሆነም ። እሱን ሳይ የምናገረው ይጠፋኛል ፣ ስሜ ይጠፋኛል ፣ የቆምኩበት ቦታ ይጠፋኛል ፣ሁሉ ነገር ይደበላለቅብኛል ። አልቻልኩም !” እያወራችኝ ፊቷ ሲዳምን የኔም ገጽ አብሮ ጨፈገገ ። ታሳዝነኛለች ። ብዙ ጊዜ እዚህ ቦታ ላይ ስትደርስ ምራቋን ትውጥና ካቆመችበት ትቀጥላለች ።
“እና …የሆነ ጊዜ የክፍል ስራ ሰጥቶን ሰርተን እስከምናሳየው ድረስ ወዲያ ወዲህ እየተንጎራደደ ነው። እንደመበሳጨት ብሎ ነበር ። ግራ ገብቶኝ አየዋለሁ ። ደብተሬን ብገልጥም እየሰራሁ አይደለም ። ምናልባት ሌላ መምህር ጋር ተጣልቶ ይሆናል ስል አሰብኩ ። ድንገት ግን ወደ እኔ ሲመጣ አየሁት …
‘አንቺ አትሰሪም እንዴ?’ አለና ደብተሬን ወደ ራሱ አዙሮ አየው። ምንም የፃፍኩት ነገር የለም ። የበለጠ ተቆጣ ።
‘አንዳንዶቻችሁ ግን ምን አይነት አይምሮ እንዳላችሁ ይገርመኛል!’ አለ ጮክ ብሎ

‘እኔ እንኳን እዚሁ ክፍል ውስጥ ሁለት ጊዜ አስተምሬሻለሁ ። አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ ልትወድቂ ነው ።’ ብሎ በቁጣ አፈጠጠብኝ። ተማሪዎች ከጀርባዬ ሲስቁ ይሰማኛል ። እንባዬ የሳር ጎጆ ላይ እንዳረፈች ጠብታ ኮለል ብሎ ወረደ ።
‘ምን አይነት ደደብ ብትሆኚ ነው ግን? የማይገባሽ ከሆነ ለምን ትማርያለሽ? ‘ አለኝ ቀጥሎ ። እኔንጃ ምን አይነት ስሜት እንደተሰማኝ ። የመቃጠል ፣አቅም የማጣት፣ የእልህ ብዙ የሚያንዘፈዝፍ ስሜት ተሰማኝ ። እስካሁን እንዴት እንደዛ እንዳልኩት አላውቅም ግን አልኩት ‘የማይገባህ አንተ ነህ!! አ…’ አልኩት ።
‘ የማይገባህ አንተ ነህ… አፈቅርሀለሁ’ አልኩት።
‘አፈቅርሀለሁ ‘ ስል ድምጽ ካፌ ሳይወጣ ነበር። ጎኔ የተቀመጡ ተማሪዎች ባያስተዉሉም እሱ ግን የአፌን እንቅስቃሴ አይቶ ገብቶታል ። ተደናግጦና ግራ ተጋብቶ ከክፍል ወጣ ። እኔም ከዛ በኋላ ወደ ክፍል ተመልሼ አላውቅም ። ሚኒስትሪን ግን ከፍተኛ ነጥብ አምጥቼ አለፍኩ ። ከዛ ት/ት ቤት ለሰአታትም ቢሆን መቆየት ያለብኝ መስሎ አልተሰማኝም ።
የሆነ ጊዜ ላይ ካጎቴ ሻይ ቤት ጥግ ላይ ተቀምጦ አየሁት ። እንዳየኝ ፈገግ ብሎ
👍1
በእጁ የነይ ምልክት አሳየኝ ። አልሄድኩም ። እሱን ወደ ኋላ ትቼው ትዝታውን ግን ተሸክሜ ከሻይ ቤቷ ወጣሁ ። ይህ ከሆነ ምን ያህል ጊዜ ሆነው? አስራ ሶስት አመት? እኔንጃ ! ግን አልረሳሁትም! ! “
ፍዝዝ ብዬ አየኋት … ውስጧ የሚብላላው የቁጭት ስሜት ምን አይነት ይሆን? ። ይህን ታሪክ ስንቴ ይሆን የነገረችኝ ? አንድን ኮርስ ሶስት አመት አስተምራኛለች። ገና መናገር ስትጀምር ሙሉ ሰውነቴን የሆነ ነገር ወረኛል ። ክፍል ውስጥ መምህር መተረብ የሚወዱ ተማሪዎች ቅጽል ስም ሲለጥፉባት እቃጠላለሁ ። ታሪኳን በነገረችኝ ቁጥር ፍርሀት ፍርሀት ይለኛል ። ኪሴ ውስጥ ያለውን ፎርም አሰብኩ። “ ለሶስተኛ ጊዜማ አይሆንም !….በዚህ አመት ዊዝድሮው አልሞላም!” አልኩት ራሴን ! ዘንድሮ ….እመረቃለሁ!!

💫አለቀ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ።
👍1
አትሮኖስ pinned «#አልረሳሁትም ! #በናትናኤል “ ምናልባት ሴት ልጅ ለመጀመርያ ጊዜ አንሶላ የተጋፈፋትን ወንድ ልትረሳው ትችላለች ። ምናልባትም ለመጀመርያ ጊዜ እግሯ ስር ተንበርክኮ በደብዳቤና በአካል እያነባ ‘አፈቅርሻለሁ’ ያላትን ወንድ ልትረሳ ትችላለች ። ነገር ግን እልሀለሁ የትኛዋም ሴት በየትኛውም ሁኔታ ለመጀመርያ ጊዜ "አፈቅርሀለሁ" ያለችውን ወንድ አትረሳውም!! እንደቁርአን በልቧ ተሸክማው ፣ እንደ ታቦት…»