አትሮኖስ
286K subscribers
122 photos
3 videos
41 files
579 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#አልረሳሁትም !

#በናትናኤል

“ ምናልባት ሴት ልጅ ለመጀመርያ ጊዜ አንሶላ የተጋፈፋትን ወንድ ልትረሳው ትችላለች ። ምናልባትም ለመጀመርያ ጊዜ እግሯ ስር ተንበርክኮ በደብዳቤና በአካል እያነባ ‘አፈቅርሻለሁ’ ያላትን ወንድ ልትረሳ ትችላለች ። ነገር ግን እልሀለሁ የትኛዋም ሴት በየትኛውም ሁኔታ ለመጀመርያ ጊዜ "አፈቅርሀለሁ" ያለችውን ወንድ አትረሳውም!! እንደቁርአን በልቧ ተሸክማው ፣ እንደ ታቦት የነፍሷ ከፍታ ውስጥ የምትጨምረው ፣ ለአባቷ ካዘጋጀችው ውብ መንበር ሳታሳንስ የምታነግሰው ንጉስ ለመጀመርያ ጊዜ ‘አፈቅርሀለሁ’ ያለችው ወንድ ነው … እና በፍፁም ልትረሳው አትችልም ። “
ለስንተኛ ጊዜ እንደሆነ ባላውቅም ታሪኳን ስትነግረኝ እያዳመጥኳት ነው ። አዲስ ታሪክ እንደሚሰማ ሰው ጆሮዬን ቀስሬ አዳምጣታለሁ ። ሁሌም እንደምታደርገው አየር ወደ ውስጥ ከሳበች በኋላ ቀጠለች።
“….ልጁ መምህራችን ነበር ። የስምንተኛ ክፍል የህብረተሰብ ትምህርት አስተማሪ! ብዙ ጊዜ ጠቆር ያለ ቲሸርትና ሰማያዊ ጂንስ ሱሪ ይለብሳል። ክረምት ክረምት ከአጎቴ ሻይ ቤት አየዋለሁ ። ሌላ የምለው ነገር የለኝም …ወደድኩት ! ፣ እያክለፈለፈ አይኔን ከእሱ ላይ እንዳልነቅል የሚያደርግ የጦዘ የአይን ፍቅር ያዘኝ ።
ከአጎቴ ሻይ ቤት ውስጥ በአግዛለሁ ሰበብ እያስተናገድኩ ያይን ረሀቤን ማስታገስ ጀመርኩ ። ትምህርት ሲጀመር ደግሞ ለኔ የተባረከ ዘመኔ እንደተከፈተ ሁሉ ደስታ የምሆነውን አሳጣኝ ። ተማሪው ሁሉ ይሄ መከረኛ ትምህርት ተጀመረ እያለ ሲያላዝን እኔ ግን የደስታ ባህር ውስጥ ተንሳፈፍኩ ።
ወደ ስምንተኛ ክፍል መዘዋወሬን ገና ካርዴ ላይ እንዳየሁ እንደ ህፃን ልጅ ነበር የፈነደኩት። መዘዋወር ብርቄ ሁኖ አይደለም ። ሙሉ የት/ቤታችን ተማሪ ‘ማህሌት’ ን የሚያውቀኝ በጉብዝናዬ ነው ። ከመላው ሴክሽን አንደኛ ደረጃን በመያዝ ! ማሂ ማን ናት ከተባለ ‘ማሂ…ያቺ ቀለሜዋ ተማሪ! ያቺ የት/ቤቱን ሽልማት በየአመቱ የምትወስደው! ሽልማቱን ግን ለምን አስቀድመው ከሷ ቤት አያስቀምጡትም? ሌላ የሚወስደው የለ! ‘ የሚባልልኝ ጎበዝ ተማሪ !
እኔን ያስፈነደቀኝ መዘዋወሬ ሳይሆን መምህር ቶማስ ሊያስተምረኝ መሆኑን አስቤ ነው ። ‘እስከዛሬ በስርቆሽ የማየውን ፍቅሬን ቢያንስ በሳምንት ለአምስት ቀናት አየዋለሁ ። ሶስት ቀን ክፍል ውስጥ ቅዳሜና እሁድ ደግሞ ከአጎቴ ሻይ ቤት! ‘ ብዬ አስቤ ..’’
አንዳንዴ ወሬዋን ታቆምና ነፋስ የበተነው ጸጉሯን ወደ ኋላ ትመልሰዋለች ። ዩንቨርስቲው ውስጥ ድንቅ ጸጉር ያላት መምህር እሷ ብቻ ናት ። ዩንቨርስቲው ውስጥ እንደ ተማሪዋ ሳይሆን እንደ ጓደኛ ከልቧ አቅርባ የምታወራኝ መምህር እሷ ብቻ ናት ። ዩንቨርስቲው ውስጥ ካሉ ሴት መምህራን ቆንጆዋ እሷ ብቻ ናት ። ጸጉሯን እና ትዝታዋን ወደ ኋላ መልሳ ትረካዋን ትቀጥላለች ….
“አየህ ወደ ስምንተኛ ክፍል ሳልፍ ነገሮች የተመቻቹ ቢመስልም ህይወት ያስተማረችኝ አንድ ነገር አለ…ነገሮች ሁሌም እንዳሰብናቸው አይሄዱም! ። አመታችን የደስታ ይሆናል ብለን ስንተነብይ ደስታ ሳይጠጋን ያልፋል ። ጊዜው የሀዘን ነው ብለን ስናማርር ጨለማ ውስጥ እንደተለኮሰች ሻማ ድንገተኛ የተስፋ ብርሀን እናያለን ። ህይወት እንደዛ ናት ። ህይወት ነብያት የሌሏት ቤተ መቅደስ ፣ ጠንቋይ የማታውቅ ቤተ መርከስ ናት ። እኛ ያልነው አይሆንም ።
የመጀመርያውን ሴሜስተር አይኖቼን ከአይኖቹ ሳልነቅል ፍዝዝ ብዬ እያየሁት በደስታ አሳለፍኩ ። ሁለተኛ ሴሜስተር የሚኒስትሪ ፈተና እየተቃረበ ሲመጣ ግን አንድ ሀሳብ በመብረቅ የተመታሁ ያህል ክው እንድል አደረገኝ ። ከዚህ በኋላ መምህር ቶማስን አላየውም። ምክንያቱም የምዘዋወረው ወደ ዘጠነኛ ክፍል ነው ። ወደ ሀይስኩል ወደ ሌላ ት/ቤት!
በቅፅበት ውስጤን ጨለማ ሲሞላው ታወቀኝ። ብርሀን አይቼ የማላውቅ የጨለማ ዘመን ነዋሪ የሆንኩ ያህል ተሰማኝ ።’’ ማውራቷን አቁማ ከንፈሯን ነከሰች ። ከንፈሯን ስትነክስ እኔም የራሴን ከንፈር ነከስኩ ። ምንም ያልሆነው አፍንጫዋን እንደመጥረግ ካደረገች በኋላ በለዘበ ድምጽ መተረኳን ቀጠለች ።
“አየህ……ማንም ያልጠበቀውን ውሳኔ ነበር የወሰንኩት ። ወሬው ት/ቤታችንን አልፎ ፣ ሰፈራችንን ተሻግሮ በየቦታው ተወራ ። ለጥየቃ የሚመጡ ዘመዶቻችን ሳይቀር "አይይይ" ይላሉ ሲያዩኝ ። ከአጎቴ ሻይ ቤት ለመሄድ እንኳ አፈርኩ! ወሬው በቅፅበት ነበር የተዛመተው ። ማሂ ሚኒስትሪን ወደቀች! "
ክረምቱ አልፎ ት/ት ሲጀመር የቤተሰቦቼን ሀዘን ላለማየት የደፋሁትን አንገት ቀጥ አድርጌ መምህር ቶማስ ላይ ማፍጠጤን ቀጠልኩ ። የሆነ ተስፋ ታይቶኝ ነበር ። አለ አይደል ዘመኗን ሁሉ ጭጋግ የሸፈናት ጨረቃ ፍንትው ስትል አይነት ተስፋ ። እንደዛ ተሰምቶኝ ነበር ። የመጀመርያው ሴሜስተር ሲያልቅ ግን ጭጋጉ መልሶ አሸነፈ ። የሚኒስትሪ ፈተና መልስ መስጫ ወረቀት ጋር ስፋጠጥ እሱን ላለማየት የምፈርመው ፊርማ እየመሰለኝ ተሳቀኩ ። በድጋሚ ተወራ ‘ማሂ ወደቀች!’ አባቴ በንዴት እብድ ሆነ ። እናቴ አዘነች ።
በቤተሰቦቼ ያልተደረገልኝ ነገር አልነበረም ። ቢጨንቃቸው የግል መምህር ቀጠሩልኝ ። አስጠኚዬ የማውቀውን ነገር ሊያስረዳኝ ይጥራል ። እኔ ሀሳቤ ከፍቅሬ ጋር ነው ። ሁለተኛው ሴሜስተር ሲደርስ ግን ከጭንቀቴ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመገላገል ወሰንኩ ። ልነግረው ወሰንኩ ። ‘ ቀላልኮ ነው!’ አልኩት ራሴን ። ‘በቃ አንዴ ላናግርህ ትይውና ከዛ አፍቅሬሀለሁ ማለት !’ ግን አልሆነም ። እሱን ሳይ የምናገረው ይጠፋኛል ፣ ስሜ ይጠፋኛል ፣ የቆምኩበት ቦታ ይጠፋኛል ፣ሁሉ ነገር ይደበላለቅብኛል ። አልቻልኩም !” እያወራችኝ ፊቷ ሲዳምን የኔም ገጽ አብሮ ጨፈገገ ። ታሳዝነኛለች ። ብዙ ጊዜ እዚህ ቦታ ላይ ስትደርስ ምራቋን ትውጥና ካቆመችበት ትቀጥላለች ።
“እና …የሆነ ጊዜ የክፍል ስራ ሰጥቶን ሰርተን እስከምናሳየው ድረስ ወዲያ ወዲህ እየተንጎራደደ ነው። እንደመበሳጨት ብሎ ነበር ። ግራ ገብቶኝ አየዋለሁ ። ደብተሬን ብገልጥም እየሰራሁ አይደለም ። ምናልባት ሌላ መምህር ጋር ተጣልቶ ይሆናል ስል አሰብኩ ። ድንገት ግን ወደ እኔ ሲመጣ አየሁት …
‘አንቺ አትሰሪም እንዴ?’ አለና ደብተሬን ወደ ራሱ አዙሮ አየው። ምንም የፃፍኩት ነገር የለም ። የበለጠ ተቆጣ ።
‘አንዳንዶቻችሁ ግን ምን አይነት አይምሮ እንዳላችሁ ይገርመኛል!’ አለ ጮክ ብሎ

‘እኔ እንኳን እዚሁ ክፍል ውስጥ ሁለት ጊዜ አስተምሬሻለሁ ። አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ ልትወድቂ ነው ።’ ብሎ በቁጣ አፈጠጠብኝ። ተማሪዎች ከጀርባዬ ሲስቁ ይሰማኛል ። እንባዬ የሳር ጎጆ ላይ እንዳረፈች ጠብታ ኮለል ብሎ ወረደ ።
‘ምን አይነት ደደብ ብትሆኚ ነው ግን? የማይገባሽ ከሆነ ለምን ትማርያለሽ? ‘ አለኝ ቀጥሎ ። እኔንጃ ምን አይነት ስሜት እንደተሰማኝ ። የመቃጠል ፣አቅም የማጣት፣ የእልህ ብዙ የሚያንዘፈዝፍ ስሜት ተሰማኝ ። እስካሁን እንዴት እንደዛ እንዳልኩት አላውቅም ግን አልኩት ‘የማይገባህ አንተ ነህ!! አ…’ አልኩት ።
‘ የማይገባህ አንተ ነህ… አፈቅርሀለሁ’ አልኩት።
‘አፈቅርሀለሁ ‘ ስል ድምጽ ካፌ ሳይወጣ ነበር። ጎኔ የተቀመጡ ተማሪዎች ባያስተዉሉም እሱ ግን የአፌን እንቅስቃሴ አይቶ ገብቶታል ። ተደናግጦና ግራ ተጋብቶ ከክፍል ወጣ ። እኔም ከዛ በኋላ ወደ ክፍል ተመልሼ አላውቅም ። ሚኒስትሪን ግን ከፍተኛ ነጥብ አምጥቼ አለፍኩ ። ከዛ ት/ት ቤት ለሰአታትም ቢሆን መቆየት ያለብኝ መስሎ አልተሰማኝም ።
የሆነ ጊዜ ላይ ካጎቴ ሻይ ቤት ጥግ ላይ ተቀምጦ አየሁት ። እንዳየኝ ፈገግ ብሎ
👍1