አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
"ሰሎሜ አንተን ሁለቴ ከድታሀለች ..ከማንም አስበልጣ ብታፈቅርህም ልብህን ግን ደጋግማ ሰብራዋለች። ከእኔ መወለድ በፊትም ሆነ ከእኔ መወለድ በኋላ ያደረገችብህን ነገር ቂም በሆድህ ቆጥርህ ነበር፡፡ያንን ይቅር ማለት እና መርሳት አልቻልክም፣ ጁኒየር ግን እንደአንተ ስላልሆነ እሷን በደስታ ነው የተቀበላት ፡፡ ቀስ በቀስም ትኩረቷን ማግኘት ጀመረ እና ጥረቶቹ ውጤት አስገኙለት… አንተን ረስታ ከእሱ ጋር ፍቅር እንደያዛት ስታስተዋል ከነከነህ፣ይባስ ብለው ሊጋቡ እንደሆነ ደረስክበት ….ከዛ ምን አደረክ ቀጥታ ገድለሀት ከእነሱ አንዳቸው እንደገደሏት እንዲያስቡ አደረክ ወይስ ምን አይነት የበቀል ዘዴ ነው የተጠቀምከው…..?ምን አልባት እናቴን ብቻ ሳይሆን ጁኒዬርንም ተበቅለኸው ይሆናል…?››

"በጣም ጥሩ አቃቢ ህግ ነሽ።በእውነት አድናቂሽ ነኝ…. ግን በዚያ መላ ምትሽ ትልቅ አመክንዬ ጥሰት አለበት፡፡››አለና የተቀመጠበትን ኩርሲ ወደእሷ አስጠጋ ….ምን ሊያደርግ ነው በሚል ስጋት በትኩረት ተመለከተችው፡፡

"አንቺ ..በብዙ ግምቶች እየተወዛገብሽ ነው…አንዱንም ማረጋገጥ አትችይም…በእኔ ላይ ምንም መረጃ የለሽም…ስለዚህ, ለምን የሁላችንንም ህይወትን ቀላል አታደርጊልንም ››አለና እጆቹን ትከሻዋ ላይ ጭነ… ወደራሱ ጎተተና ጉንጮን ሳማት፡፡
"ምክንያቱም አልችልም።›› ከንግግሯ በስተጀርባ ያለውን የተስፋ መቁረጥ ስሜት ሰማ እና እሷን ለመስበር ከግማሽ በላይ መንገድ ላይ እንደደረሰ አወቀ።

"ለምን አትችይም?" ጠየቃት፡፡

‹‹ምክንያቱም እናቴን የገደላትን፤መገደሏን አውቆ ገዳዩን ለመታደግ የተባበረውን በጠቅላላ መቅጣት እፈልጋለሁ።››
እጁን ከትከሻዋ ላይ አነሳና …አይን አይኗል በትኩረት እያየ….."ይህን ለሰሎሜ ብለሽ አይደለም እያደረግሽ ያለሽው… ለራስሽ ነው የምታደርጊው"አላት፡፡

"ያ እውነት አይደለም!"

" አያትሽ በጭንቅላትሽ ውስጥ የፈጠረችብሽ የማይሆን ሀሳብ አለ ፡፡እናም በእናትሽ ህይወት ውስጥ በተሳሳተ ጊዜ በመምጣትሽ እና ኑሮዋን በማበላሸትሽ ራስህሽ ይቅር ማለት አልቻልሽም።"

"በፈጣሪ አንተው ነህ ስለ ስነ ልቦና ግጭት ለእኔ የምታወራው?" ብላ በቁጣ ጠየቀችው። ቀጠለችናም "ገመዶ ራስ ወዳድ መሆንህን ለማወቅ ስለአንተ በቂ እውቀት አለኝ። ሌላ ሰው እንደግል ንብረትህ ስለምትቆጥር  ሲነኩብህ ትበሳጫለህ ።››

"አገላለጿ  ፈታኝ ነበር። ››
"ገመዶ ፣እናቴን ይቅር ለማለት በጣም የከበደህ ነገር ለምንድን ነው? እሷ ከሌላ ወንድ ጋር ስለተኛች ነው? ወይስ እድሉ እያለህ እሷን ባለማግባትህ ራስህን ይቅር ማለት አልቻልክም?"
ገላዋን በእጁ ነቀነቀ፣ ከዚያም እስኪነካኩ ድረስ ወደ ፊት አዘነበለ። "አንድ ጊዜ አስጠንቅቄሻለሁ ….እናትሽ ከጁኒየር ጋር የነበራትን ግንኙነት ለማስቀጠል እና ለምን እንደዛ እሷን ሊያፈቅራት እንደቻለ ለማወቅ ያለሽን የማወቅ ጉጉት ማርካት እየጣርሽ ነው"

"አይ ..ያ እውነት አይደለም" ብላ በቁጣ ካደች

" አይመስለኝም።"

‹‹ አንተ ታመሃል…?"አለችው፡፡

አንገቱን ጎንበስ አድርጎ ሳማት። በዝምታ ተቀበለችው….ከንፈሮቹን ወደከንፈሯ አስጠጋት…
…ባለችበት ሳትነቃነቅ ጠበቀችው፡፡ ከንፈሮቾን በስሱ ይመጣቸው ጀመር … ከንፈሯቾ እርጥብ እና ሙቀት የሚረጩ ከመሆናቸውም በላይ ጣፋጭ ነበሩ፣ ቀኝ እጁን አንቀሳቀሰና
በለበሰችው ሹራብ ውስጥ ሰቅስቆ ጡቷን በእጁ ጨመቀ። የጡቷን ጫፎች በሁለት ጣቶቹ ማፍተልተል ጀመረ… ጩኸት የተቀላቀለበት የጣር ድምፅ ከጉሮሮዋ ወጣ።አንገቱን ቀና አደረገና ቁልቁል ፊቷን ተመለከተ። በእጁ መዳፍ ውስጥ ተፈጥርቃ እንደተያዘች ትንሽ የዱር ፍጡር ልቧን ሲንፈራገጥ ይሰማዋል። አይኖቿ ተጨፍነው ነበር። መልሶ ከንፈሯን ጎረሰ…ምላሱን ወደውስጥ ከተተ…ከተቀመጠችበት ኩርሲ ተንሸራተተችና ደረቱ ላይ ተለጠፈችበት….ከተቀመጠበት ተነስቶ ልክ እንደህጻን ልጅ አቅፎ ወደቤቱ ውስጥ ይዞት ሄዶ አልጋው ላይ ሊዘርራትና ያለምንም ገደብ ሙሉ በሙሉ ከእሷ ጋር ለመቅለጥ እና ከእሷ ጋር ለመጥፋት ከፍተኛ ፍላጎት ጉሮሮዋ ስር ተሰነቀረበት…..እንደዚህ ካደረገ ወደኃላ መመለስ እንደማይችል እና ምንም ነገር እስከአሁን እንደነበረው እንዳማይሆን ያውቃል፡፡ምን ያድርግ…ልቡና አእምሮው ከፍተኛ ፊልሚያ ላይ ገቡበት፡፡ በመጨረሻ አእምሮው በልቡ ተሸንፎ እሷን ወደውስጥ ተሸክሞ ሊገባ ሲንቀሳቀስ የውጭ በራፍ በሀይል ሲንኳኳ ሰማ….ሁለቱም ከገቡበት መደንዘዝ እኩል ነቁ…..የበራፉ መንኳኳት ቀጠለ….ገመዶና አለም ተላቀቁ….ከተቀመጡበት የተዘበራረቀ ልብሷንና የተጎሳቆለ ፀጉሯን ማስተካከል ጀመረች….እሷ ሙሉ በመሉ እራሷን እንዳስተካከለች እርግጠኛ ከሆነ በኃላ በንዴት ሄዶ በራፉን ከፈተው..አቶ ፍሰሀ ነበር፡


ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
58👍13🔥4👎1
አትሮኖስ pinned «#ቋጠሮ_ሲፈታ ፡ ፡ #ከሰፍል_ሀያ_አምስት ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ /// የዝዋዩን ስብሰባ ተሳትፈው በተመለሱ በማግስት ዋና አቃቢ ህጉና አለም በቢሮቸው ፊት ለፊት ተፋጠው ተቀምጠዋል፡፡ እሱ እጁ ላይ አንድ ደብዳቤ በትኩረት እየተመለከተ ትካዜ ውስጥ ገብቷል … ‹‹ክብሩ አቃቢ ህግ…ምነው ችግር አለ እንዴ?››ስትል ጠየቀችው፡፡ ‹‹ወደስራ ስትመጪ ከተማው ውስጥ የታዘብሽው ነገር የለም?›› …»
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


///
እሱ በራፉን ለመክፈት ሲሄድ አለም ቶሎ ብላ ቦርሳዋ ውስጥ ገባች እና በጣም የሚያምር ውድና ጌጠኛ ብእር አወጣችና ወደቤቱ በራፉ ፊት ለፊት በመወርወር ወደፊት ራመድ ብላ እስኪመለሱ መጠበቅ ጀመረች፡፡

‹‹እ..ሰላም ነው..?ስልክህ አይነሳም፡፡››አቶ ፍሰሀ ነው ተናጋሪው፡፡

‹‹ውስጥ ቻርጅ ላይ እርጌው አላየሁትም…ግባ››ኩማንደሩ መለሰለት፡፡ ወደውስጥ ሲገባ አለምን ስላያት ነገሩ ገባው፡፡

‹‹እንዴት ነህ አቶ ፍሰሀ?››

‹‹ሰላም ነኝ…አንቺስ?››

‹‹አለሁ..››አላችና ‹‹በሉ እንግዲህ መሄዴ ነው››ስትል አከለችበት፡፡

‹‹ምነው ..እኔ ስመጣ ነው እንዴ ምትሄጂው?››

‹‹አይ መጀመሪያውኑም ለመሄድ ስል ነው የመጣሀው…ጉዳዬን ጨርሼለው..ተራውን ለአንተ ልልቀቅ፡፡››አለችና ሁለቱንም ተሰናብታ ወጣች፡፡

ገመዶ እና አቶ ፍሰሀን አስከትሎ ወደውስጥ ለመግባት ሲራመድ በራፉ ጋር ሲደርሱ አቶ ፍሰሀ ጎንበስ አለና አይኑ የገባውን ብዕር አነሳ፡፡

‹‹ይሄን የመሰለ ብዕር ትጥላልህ እንዴ?››ብሎ ወደ ኩማንደሩ ዘረጋለት፡፡ኩማንደሩ ተቀብሎ አገላብጦ ተመለከተውና‹‹ወይ የእኔ አይደለም…የአለም መሰለኝ›››አለና ስልኩን አውጥቶ ደወለላት፡፡

‹‹ሄሎ››

‹‹ ምነው ከአሁኑ ናፈቅኩህ እንዴ?››
‹‹ባክሽ ሌላ ቦታ ጥዬዋለው ብለሽ እንዳትፈልጊ ነው…አንድ ብዕር ጥለሽ ሄደሻል..ካልራቅሽ ተመለሺና ውሰጂው››

‹‹ወይ  እንዴት  ጣልኩት…?ለማንኛውም  በጣም  ከምወደው  ሰው  የተሰጠኝ  ስጦታ ነው…ከኪስህ እንዳይወጣ …ስንናኝ ትሰጠኛለህ››አለቸው፡፡

‹‹እሺ ቻው››አለና ስልኩን በመዝጋት ብእሩን ደረት ኪሱ ውስጥ ሻጠውና ከአቶ ፍሰሀ ጋር ተያይዘው ወደውስጥ ገቡ….

‹‹ቢራ ልክፈትልህ››

‹‹በጣም ደስ ይለኛል››

ለሁለቱም ቢራ ከፈተና ፊት ለፊት ተቀመጠ፡፡

‹‹መጥፎ ሰዓት ነው እንዴ የመጣሁት?››አቶ ፍሰሐ ጠየቀ፡፡

‹‹አይ እንደውም በተቃራኒው ጥሩ ሰዓት ላይ ነው የመጣሀው..በጣም አደጋ ላይ ነን››

‹‹ማለት››

‹‹ይህቺ ልጅ ከጠበቅኳት በላይ አደገኛ ነች…ሳታጠፋን አርፋ አትቀመጥም….››

‹‹ማለት….አንተ እንዲህ ካልክ ነገሮች ከባድ ናቸው ማለት ነው››

‹‹አዎ…ስለእያንንድ  የሶሌ  ኢንተርፕራይዝ  የአክሲዬን  ድርሻ…ማን  ስንት  ፐርሰንት እንዳለው…አክሲዬኑ መቼ እንዳገኘነው….ዝርዝር መረጀ አላት፡፡››
አቶ ፍሰሀ ልብ ምቱ በደቂቃ ውስጥ ሲጨምር ታወቀው….

‹‹ምን እያልከኝ ነው?››

‹‹አዎ….የእናቴን ሞት ተከትሎ የአንዳችሁ አክሲዬን ተቀንሶ ለሌሎቻችሁ የተጨመረው ለምንድነው ብላ ጠየቀችኝ…?፡፡››

‹‹ይሄ እኮ ወደእውነት እየቀረበች መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡››

‹‹አዎ…አንድ ውሳኔ መወሰን አለብን፡፡››
አቶ ፍሰሀ ወዲያው ስልኩን አወጣ…መጀመሪያ ዳኛ ዋልልኝ ጋር ደወል…አሁኑኑ ወደቤት እንዲመጣ ነገረውና ስልኩን ዘግቶ መልሶ ልጁ ጁኒዬር ጋር ደወለ..ቤት እንደሆነ ነገረው…ሳይወጣ እንዲጠብቀው ነግሮ ዘጋውና‹‹በል ተነስ እንሂድ….አሁኑኑ ተነጋግረን አንድ ነገር ማድረግ አለብን፡፡››
///
ከምሽቱ አራት ሰዓት አራቱ ሰዎች ምድር ቤት በሚገኘው የአቶ ፍሰሀ ቢሮ ውስጥ ተቀምጠው ፊት ለፊት ተፋጠዋል…በጠረጴዛው መሀከል ሙሉ የውስኪ ጠርሙስ ሲኖር በመሀከላቸው ግማሽ ድረስ የተሞላ ብርጭቆ አለ….

‹‹እኔ  ከመጀመሪያውም  ነግሬችሁ  ነበር..ይህቺን  ሴት  አንድ  ነገር  አድርጓት  ስላችሁ ነበር››ዳኛው በንዴት ደነፉ፡፡

‹‹አሁን ያለፈውን ገር እያነሳን ልንወቃቀስ አይደለም የተገናኘው…አሁን እንዴት አድርገን እናሳቁማት የሚለው ነው ወሳኙ ነገር፡፡››

‹‹ለምን ሁችንም ባለንበት አግኝተናት ይሄንን ጉዳይ እንድታቆም ለመጨረሻ ጊዜ አናሳጠነቅቃትም››አለ ጁኒዬር፡፡

‹‹ትቀልዳለህ እንዴ….መቼስ ልጅቷን ግትርነት ከአንተ በላይ የሚያውቅ ያለ አይመስለኝም፡፡ እኔ በበክሌ እዚህ እግሯ ከረገጠበት ቀን አንስቶ በሰላምም በማስፈራራትም ይህንን ጉዳይ እንዳታቆም ያልጠየቅኳት ቀን የለም…አንድም ቀን ሽብርክ ስትል አልሰማዋትም…ዛሬም የነገረችኝ ጉዳዩን ከማቆም መሞትን እንደምትመርጥ ነው፡፡››ሲል አስተያየቱን ያቀረበው ኩማንደሩ ነበር፡፡

‹‹እሱማ ትክክል ነህ …እኔም ያልሞከርኩበት ቀን የለም…›አለ ጁኒዬር፡፡

‹‹አዎ…ይሄ ጉዳይ አይሰራም፡፡››
ዳኛው ትእግስት አልባ በሆነ ንግግራቸው‹‹በቃ በንግግር ማስቆሙ ካልሰራ …አስወግዷታ

…መቼስ ይሄንን ስታደርጉ የመጀመሪያችሁ አይደለም››አለ ፡፡

በገመዶና በጂኒዬር ላይ የተከሰተው ድንጋጤ የተለየ ነበር…..እርስ በእርስ ተያዩ….ከዛ ሁለቱም በእኩል ጊዜ ወደአቶ ፍሰሀ ዞሩ….አቶ ፍሰሀ አይናቸው ተጉረጥርጧል…ለመናገር እየፈለጉ እየተናነቃቸው ነው፡፡ከአንደበታቸው ቃል ማውጣት የከበዳቸው መሆኑን ያስታውቃል…ከዛ እንደምንም አሉና መናገር ጀመሩ፡፡

‹‹ይሄንን ለሁላችሁም ነው የምናገረው…ለሁላችሁም….እዚህች ልጅ ላይ የመግደል ሀሳብ አይደለም አንዲት ፀጉሯን ለመንቀል ብታስቡ ቀጥታ ፀባችሁ ከእኔ ጋር ነው፡፡ማንም እጣቱን በእሷ ላይ ሊያነሳ አይችልም፡፡››

ዳኛው አይናቸውን አጉረጠረጡ‹‹ለምን ተብሎ..ለአንድ ዲቃላ ልጅ ሲባል የእኛ ህይወት መመሰቃቀል አለበት፡፡.እናንተ ማድረግ ካልፈለጋችሁ እኔ አደርገዋለው፡፡››

አቶ ፍሰሀ ልክ እንደጎረምሳ ከተቀመጡበት ተስፈንጥረው ተነሳና ከወገቡ ያለውን ሽጉጥ መዞ ሽማግሌው ዳኛ መላጣ ጭንቅላት ላይ ደቀነው፡፡

ገመዶና ጁኒዬር በርግገው ከተቀመጡበት ተነሱ‹‹እንዴ አባዬ ….!ምን እያደረክ ነው?››

‹‹አንተ ፈርሳም ሽማግሌ….ከዛሬ ጀምሮ እንደውም ለልጅቷ ጠባቂ ቀጥረህ እንቅፋት እንኳን እንዳይነካት ብታስጠብቃት ይሻልሀል….በማንም ሆነ በማን አንድ ነገር ገጠማት ሲባል ብሰማ ይሄንን ምላጭ በአንተ ጭንቅላት ላይ ለመሳብ ለሰከንድ እንኳን አላቅማማም፡፡››

‹‹ጋሼ በቃ…..ወደመቀመጫህ ተመለስ..ተረጋጋ…››አለ ገመዶ፡፡

አቶ ፍሰሀ የደቀነውን ሽጉጥ መልሶ ወደ ወገብ ሻጠው እና መደመቀመጫው ተመለሰ

…..ሁሉም በፀጥታ ማሰላሰል ውስጥ ገባ…ገመዶ ከተቀመጠበት ተነሳና ወደመስኮቱ ተጠግቶ ሲጋራውን ለኮሰና እያጬሰ ማሰብ ጀመረ፡፡ሲጋራውን እንደጨረሰ ወደመቀመጫው ተመለሰና ከውስኪው አንዴ ጠቀም አድርጎ ከተጎነጨ በኃላ ‹‹እኔ አንድ ሀሳብ አለኝ››ሲል የሁሉንም ቀልብ ሳበ፡፡

‹‹ምንድነው እንስማው››ሁሉም ተነቃቁና ኩማንደሩ የሚለውን ለመስማት ዝግጁ ሆነ፡፡

‹‹የሚቀጥሉት ስድስት ወራት ወሳኝ ጊዜዎች ናቸው..ማለቴ ከጂኒዬር የምርጫ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ይሄ የክስ ጉዳይ ወደፊት ከገፋና እንዲህ አይነት ወሬዎች ህዝቡና ሚዲያው ጆሮ መግባት ከጀመሩ ነገሮች ድብልቅልቃቸው ነው ሚወጣው፡፡እንደእኔ ለተወሰነ ጊዜ ወደሆነ ቦት ዞር አድርገን ብናስቀምጣት፡፡››

‹‹ዞር አድርገን ስትል….?ግልፅ አድርገው?፡፡››

‹‹በቃ ከሰው እያታ ውጭ የሆነ ቤት ወሰድን እዛ ሁሉ ነገር እንዲሞላላት እድርገን ግን ደግሞ ከማንም የማትገናኝበትን ሁኔታ ብናመቻች ጥሩ ይመስለኛል፡፡››

‹‹ጥሩ…እኔም እስከዛ ጡረታ ወጣና ከዚህ ከተማ ዞር እላለሁ››በማለት ዳኛው ቅድሚያ ተስማማ፡፡

አቶ ፍሰሀ ‹‹ጥሩ ሀሳብ ይመስላል….እንደውም ይርጋ ጨፌ የቡና እርሻችን ያለበት ቦታ ብንወስዳት ማንም ሊያገኛት አይችልም……እዛ ሁሉን ነገር እናሟላላታለን…እኛም በየተራ እየሄድን እንጠይቃታለን..መጥፎ ሰዎች እንዳልሆን እንድታምን እናደርጋለን፡፡
51👍8😱2
‹‹እናንተ ሰዎች አብዳችኃል እንዴ…?ሴትዬዋ እኮ የዞኑ ምክትል አቃቢ ህግ ነች….ዝም ብላ ስትሰወር መንግስት ዝም የሚል ይመስላችኃል?፡፡››ጁኒዬር ነው ጠያቂው፡፡

‹‹ትክክል ነህ….ግን አሁን ልጅቷ ስራ ለቃለች፡፡››ኩማንደር መለሰ፡፡

‹‹ማለት..?ከመቼ ጀምሮ?››

ከዛሬ ወዲህ ወደስራ መግባት እንደማትፈልግ ታናግራ መለቀቂያዋን ለዋና አቃቢ ህጉ አስገብታለች…ስለዚህ ከነገ ጀምሮ ከተማ ውስጥ ባትታይ የሚገርም አይሆንም፡፡››

‹‹አዎ….እኔም መልቀቂያ እንዳስገባች ሰምቼለው››አሉ አቶ ፍሰሀ፡፡

‹‹ለምን ለቀቀች…?የደረሰባት መጥፎ ነገር አለ?፡፡››ጁኒዬር ነው በስጋት የጠየቀው፡፡

‹‹እኔና ኩማንደር ቀደም ብለን ተነጋግረን ከዚህ ምርመራዋ ዞር ለማድረግ በማሰብ እላይ ያሉ ወዳጆቻችንን አስቸግረን የውጭ እድል እንድታገኝና እዚህ ያለውን ስራ ለሌላ ሰው አስረክባ በሳምንት ውስጥ ከተማውን ለቃ እንድትወጣ አመቻችተን ነበር….እሷ ግን የውጭ እድሉን ውድቅ አድርጋ ስራዋና ለመልቀቅ በመወሰን እቅዳችንን ውድቅ እንዲሆን አድርጋለች፡፡››ሲሉ ስለሁኔታው ምንም መረጃ ለሌላቸውን ለዳኛውና ለልጃቸው አብራሩላቸው፡፡

‹‹እንዴ አባይ …?ይሄንን ሁሉ ስታደርጉ እኔ ጫፉን እንኳን ለምን ሳላውቅ?››ሲል ጁኒዬር በቅሬታ ጠየቀ፡፡

‹‹ልጄ ነገሩን እንድታውቀው ካላደረግን ለአንተ ጥቅም እንደሆነ ማወቅ አለብህ›› ጁኒዬር ግን በጣም ቅር እንዳለው ከፊቱ ላይ በግልፅ ማንበብ ይቻላል፡፡

አቶ ፍሰሀ ‹‹‹በቃ አሁን እሷን ከአካባቢው በጥንቃቄ ዞር ከማድረግ ውጭ የተሻለ መፍትሄ የለም… አሁን ስራ እንከፋፈል…ኩማንደር እና ጁኒዬር አንድ ላይ ሆናችሁ…እሷን በታማኝነት የሚጠብቁ አንድ አራት ሰዎች ምግብ የምታበስልላትና የምታወራት አንድ ሴት ፈልጋችሁ አዘጋጁ….ከዛ ውጭ የሚያስፈልጓትን እቃዎች ልብሶች ማንኛውንም ነገር አዘጋጁ..እኔ ነገ ለሊት ወደ ይርጋጨፌ ሄድና የቡና ጫካ ውስጥ ያለውን ማረፊያ ቤታችንን እንዲታደስና እንዲዘጋጅ አደርጋለው…ሁሉንም ነገር በ5 ቀን ውስጥ ማጠናቀቅ አለብን
….እና የዛሬ ሳምንት ኦፕሬሽኑን እናደርጋለን….ከተቻለ..ከሁለት አንዳችሁ አሳምኗትና ከከተማ ይዛችኃት ውጡ …››

‹‹እኔስ ምንድነው የማግዛችሁ?››ዳኛው በእፎይታ ጠየቀ፡፡

‹‹አንተ ባለመነጫነጭ እና አድበህ በመቀመጥ ተባበረን፡፡››ሲል አቶ ፍሰሀ በመሰላቸት መለሰለት፡፡

‹‹በቃ…..አሁን ወደ የቤታችን እንሂድ…ከነገ ጀምሮ ሚደረገውን እናደርጋለን፡፡››

‹‹ግን በዚህ አንድ ሳምንት ውስጥ የሆነ ነገር ብታደርግስ?፡፡››ዳኛው ናችው ጠያቂ፡፡

ኩማንደሩ‹‹እያንዳንዱን እንቅስቃሴዋን የሚከታተል ሰው መድቤለው…በጣም የሚያሰጋ ነገር ካለ ቀድመን እርምጃ እንወስዳለን››አለና ጃኬቱን ካተንጠለጠለበት አንስቶ ወደመውጫው መራመድ ጀመረ..ጁኒዬር ከኋላው ተከተለው፡፡
///
ሁሉም በተሰጠው ስራ መሰረት መደበኛ ስራቸውን ሳይቀር ሙሉ በሙሉ በመዘንጋት ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ሲሯሯጡ ነው የሚውሉት፣እንደዛም በመሆኑ አምስት ቀን ይፈጃል የተባለው አለም የምትኖርበትን ቤት የማዘጋጀትና የሚጠብቃት ሰዎችን የመመልመልና የመቅጠር ስራ በሶስት ቀን ውስጥ ተጠናቀቀ፡፡

አሁን ኩማንደር ቢሮው ቁጭ ብሎ ስልኩን አነሳና ይርጋአለም ወደሚገኙት አቶ ፍሰሀ ጋር ደወለ፡፡

‹‹ሄሎ ጋሼ..እንዴት ነህ?››

‹‹ደህና ነኝ.. ይመስገነው፡፡››

‹‹የላክናቸው ጠባቂዎችና ሰራተኛዋ ደረሱ?››

‹‹ከተማ ገብተዋል… የሚቀበላቸው ሰው ልኬላው …ከአንድ ሰዓት በኋላ ቦታው ላይ ይደርሳሉ››

‹‹ጥሩ ነው….አንተጋስ ነገሮች እንዴት ናቸው?››

‹‹ሁሉ ነገር ፐርፌክት ነው፡፡ቤቱን ለእሷ እንዲመች አድርገን አሳምረነዋል …..ግቢው በዛፎችና በአበቦች የተሞላ ስለሆነ ገነት በለው…በጣም ነው የምትወደው….ፏፏቴ ሳይቀር ግቢ ውስጥ አለ….እኔ ራሴ እዚሁ ኑር እዚሁ ኑር ነው ያሰኘኝ፡፡››

‹‹ተረጋጋ..መጀመሪያ ከዚህ ችግር እንገላገል..ከዛ በሰላም ጡረታ ትወጣና..ስራህን ለልጅህ አስተላልፈህ እንዳልከው ማድረግ ትችላለህ››አለው፡፡

‹‹እንደዛ ማድረጌማ አይቀርም…ለማንኛውም ከጁኒዬር ጋር ተማከራችሁ?፡፡››

‹‹ምንን በተመለከተ?››

‹‹እንዴት ወደ እዚህ ይዛችኃት ልትመጡ እንዳሰባችሁ ነዋ?፡፡››

‹‹አዎ…..ነገ ማታ ጂኒዬር አሳምኖ ወደ ጭፈራ ቤት ይዞት ይወጣና በደንብ እንድትጠጣ እናደርጋለን…ከዛ ለረጅም ሰዓት የሚያስተኛ መድሀኒት እንሰጣትና እንድትተኛ እናደርጋለን …ለሊቱን ይዘናት እንመጣለን....እና ጥዋት ስትነቃ እራሷን አንተ ያዘጋጀህላት ገነት ውስጥ ታገኘዋለች፡፡››

‹‹ጥሩ ነው በቃ…ቻው…ተጠንቀቁ፡፡››

‹‹ችግር የለም..አንተም ተጠንቀቅ፡፡››

‹‹ስልኩን ተዘጋ..ፈገግ አለ…..አለም ነገ ማታ ለመዝናናት ዝንጥንጥ ብላ ከቤቷ ወጥታ በማግስቱ ከእንቅልፏ ስትነቃ እራሷን ጥቅጥቅ ያለ ደን ውስጥ በጠባቂዎች ተከባ ስታገኘው እንዴት እንደምትናደድና ምን አይነት እርግማን እንደምታዥጎደጉድባቸው በምናብ አሰበና ፈገግ አለ…ስልኩን ወደራሱ አስጠጋና ደወለ፡፡

‹‹ሄሎ ሳጅን….››

‹‹ደህና ነኝ ኩማንደር››

‹‹እሺ …ተጠርጣሪያችን ምን እየሰራች ነው?፡፡››ሲል ጠየቀው፡፡

‹‹ኩማንደር ልደውልልህ ስል ነው የደወልክልኝ…ትናንትና ጥዋት ወደክፍሏ የገባች እስከአሁን አልወጣችም..በራፏም አልተከፈተም…››ሲል ያልጠበቀውን ዜና ነገረው፡፡፡

‹‹ምን ማለት ነው?››

‹‹እኔ እንጃ…ለሊቱን ሲጠብቃት ያደረው ፖሊስ ያለኝ እንደዛ ነው…እኔም ከተረከብኩት በኋላ በቤቷ ዙሪያ ምን አይነት እንቅስቃሴ አላየሁም፡፡››

ኩማንደር የሆነ ደስ የማይል ስሜት ተሰማው….‹‹ቆይ ሳጅን….አንዴ ስልኩን ዝጋው….ልደውልላትና መልሼ ደውልልሀለው››

ስልኩ ተቋረጠ…ወዲያው የአለምን ቁጥር አወጣና ደወለ…ጥሪ አይቀበልም ነው የሚለው…ደገመ…ተመሳሰይ ነው፡፡ከተቀመጠበት ተሸከርካሪ ወንበር ተነሳና ክፍሉ ውስጥ እየተሸከረከረ ማሰብ ጀመረ..መልሶ ሳጅኑ ጋር ደወለ‹‹ሳጅን ቀጥታ ወደቤቷ ሂድና አንኳኳ››የሚል ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡

‹‹ከከፈተችልኝስ?››

‹‹ጥሩ ነዋ…የምፈልገው ያንን አይደል?››

‹‹ማለቴ ምን እላታለው?››

‹‹ኩማደር በስልክ አገናኘኝ ብሎኝ ነው ብለህ ደውለህ ከእኔ ጋር ታገናኘናለህ››

‹‹እሺ በቃ ወደቤቷ እየቀረብኩ ነው፡፡››
ስልኩ ተቋረጠ…ኩማደሩ ከፊልድ ጃኬቱ ውስጥ ሲጋራ አወጣና ለኮሰ…..ወደ መስኮት ሄደና መስኮቱን ከፍቶ ውጭ የሚርመሰመሱትን መንገደኞች እየተመለከተ ሲጋራውን ማቡነንና መጥፎ መጥፎ ሀሳቦችን እየደራረበ ማሰቡን ቀጠለ፡፡ሲጋራውን አጭሶ ሳይጨርስ ስልኩ ተንጫረረ…ሳጅኑ ነው…አነሳውና የአለምን ድምጽ ለመስማት እየፀለየ ጆሮው ጋር አስጠጋ፡፡

‹‹አዝናለው ኩማንደር..ባንኳኳ ባንኳኳ ከውስጥ የሚመልስ ሰው የለም…..››

‹‹በቃ መጣው..እዛ በራፉ ጋር ሆነህ ጠብቀኝ››በማለት ግማሽ ሲጋራውን ወደ አሽትሬው ላይ ወረወረና ጃኬቱን ከወንበሩ ላይ አንጠልጥሎ ቢሮውን ለቆ ወጣ…ቀጥታ የመስሪያ ቤቱን ፒካፕ መኪና አስነስቶ ወደቤቷ መብረር ጀመረ፡፡ስልኩ መጥራት ጀመረ..ሲያየው ጁኒዬር ነው….በዚህ ሰዓት ከእሱ ጋር የማውራት አፒታይት የለውምና አላነሳም..ደግሞ ደወለ…..ልክ አለም ቤት ጋር ለመድረስ የሁለት ኪሎ ሜትር ርቀት ሲቀረው..ዳኛው ዋልልኝ ደወሉ…..‹‹ይሄማ በሰላም ሊሆን አይችልም አለና››የዳኛውን ስልክ ዘግቶ የመኪናውን ፍጥነት በመቀነስ ጁኒዬር ጋር ደወለለት…ወዲያው ነው የተነሳው፡፡

‹‹የት ነህ?››

‹‹ወደ አለም ቤት እየሄድኩነው››

‹‹አለች ግን?››
39👍8
‹‹እኔ እንጃ …ትኑር አትኑር አይታወቅም..ሰው ልኬ  ነበር… ሲያንኳኩ ከውስጥ የሚመልስ ሰው የለም አሉኝ…ግን ምንድነው? የተፈጠረ ነገር አለ እንዴ?››

‹‹ገመዶ ይህቺ የሰሎሜ ልጅ በጣም አደገኛ ነች..ቀድማ ጥቃት ጀምራለች….ሳታጠፋን የምታቆም አይመስለኝም››

‹‹ምን ተፈጠረ››

‹‹ቴሌግራምህን ክፈት የተፈጠረውን ልኬልሀለው….ዛሬውኑ አፍነን ወደተዘጋጀላት ቦታ መውሰድ አለብን…ቤት ካለች እንዳትለቃት ..እስክመጣ አብረሀት ሁን››ብሎ ስልኩን ዘጋው፡፡

ገመዶ መኪናውን ዳር አሲይዞ አቆመና ቴሌግራሙን ከፈተ …ከጁኒዬር አንድ ቪዲዬ ተልኳለታል፡፡

‹‹የሻሸመኔ ከተማ ወክሎ ለምክር ቤት የሚወዳደረው እጩ ተወዳዳሪው ስለእናቴ ግድያ ያውቃል!!››ይላል ርዕሱ…በንዴት እየተንቀጠቀጠ ከፈተው፡፡ሙሉ የአለም ምስል በእስክሪኑ ሞላ….፡፡በእናቷ እና በጁኒዬር..በእናቷ እና በገመዶ መሀከል ያለውን የልጅነት ግንኑኙነት ትዘረዝርና…እሷ እስከተወለደችበት ጊዜ ያለውን ታሪክ ተናግራ…ቀጣዩን ከሶስት ቀን በኃላ በተመሳሳይ ሰዓት ይጠብቁ በሚል ይቋረጣል፡፡ቪዲዬ ከተለቀቀ ገና አንድ ሰዓት ቢሆነውም..8 ሺ እይታ አግኝቷል…ከአንድ ከሁለት ቀን በኃላ በመላው ሀገር እንደሚዳረስ እርግጠኛ ነው…..ስልኩን ወደኪሱ አስገባና መኪናዋን አንቀሳቀሰ…አለም ቤት ጋር ሲደርስ ሳጂኑ በታዘዘው መሰረት በረንዳው ላይ ቆሞ እየጠበቀው ነበር፡፡

‹‹እ ምንም ነገር የለም››

‹‹አይ ምንም ነገር የለም››መለሰለት፡፡ኩማንደሩ ወደ ጓሮ ዞረ…ሳጅኑ ተከተለው….የጓሮውን በር ገፋ ሲያደርገው ተከፈተለት..ተንደርድሮ ወደውስጥ ገባ፡፡ በየክፍሉ እየተዘዋወረ ፈለገ…የለችም…መኝታ ቤቷ ገባና ቁም ሳጥኗን ከፈተ ባዶ ነው…ልብሷ ..ሻንጣዋ…ላፕቶፖ የለም፡፡አንድ ብጣሽ ወረቀት ጠረጴዛው ላይ ተቀምጧል፡፡አነሳና ተመለከተው፡፡በንዴት ወደሳጅኑ ዞረና፡፡‹‹ምንድነው ኦና ቤት ነበር እንዴ ስትጠብቁ የነበረው?››

‹‹ ሄዳለች ማለት ነው››ሳጅኑ በድንጋጤ እና ግራ በመጋባት መልሶ ጠየቀ፡፡

‹‹ብሽቅ ናችሁ….››አለና በንዴት የፊት ለፊቱን በር ከፍቶ ወደበረንዳ ሲወጣ ጁኒዬር እየተንደረደረ ሲመጣ ተገጣጠሙ፡፡

‹‹አገኘሀት…?የት አለች?››

‹‹የለችም?››

‹‹የለችም ማለት?››

ኩማንደሩ ለጁኒዬር ሌላ መልስ ከመመለሱ በፊት ወደ ሳጅኑ ዞረና ‹‹ሳጅን በቃ አሁን አታስፈልግም..እዚህ ያላችሁ ስራ ተጠናቋል መሄድ ትችላለህ›› በማለት አሰናበተው፡፡

‹‹ግን እኮ መኪናዋ እንደቆመች ነው፡፡››
ገመዶ ‹‹መኪናዋን ከተጠቀመችማ በቀላሉ እንደምንከታተላት ታውቃለች..ለዛ ነው ማንም ሳያያት በጓሮ በር ወጥታ የተሰወረችው፡፡እቅዳችንን በሆነ መንገድ ያወቀችብን ይመስለኛል››ሲል ጥርጣሬውን ተናገረ፡፡

‹‹እንዴት ልታውቅ ትችላለች…?.ማን ሊነግራት ይችላል?››

‹‹አላውቅም…ግን እቃዎቾን ጠቅልላ ማንም ሳያይ በጓሮ በራፍ ወጥታ ነው የተሰወረችው….እና መኝታ ቤቷ ይሄንን ወረቀት ጥላ ነው ሄደችው..››አለና አንድ ብጣሽ ወረቀት አቀበለው፡፡

ለገመዶ..ጁኒዬርና ለአቶፍሰሀ….
እኔን ከዚህ ጫወታ ገለል ማድረግ እንደዚህ ቀላል አይሆንላችሁም፡፡ከዛሬ ጀምሮ ከፍትህ ይልቅ በቀልን መርጫለው፡፡ አድናችሁ ካገኛችሁኝ ግደሉኝ….ግን ያንን ማድረግ ከመቻላችሁ በፊት በየቀኑ አንድ አንድ ክንፋችሁን....ቀጥሎ እጆቻችሁን …ከዛም እግራችሁን… ከዛም አይኖቻችሁን..እያልኩ አጠፋችኋላው…..፡፡በማንኛውም ሰዓት ከመሀከላችሁ(ማለት..ገመዶ፤ጁኒዬር፤ስርጉት፤አቶ ፍሰሀ፤ሳራ)ከአምስታችሁ እናቴን የገደለው  ሰው  ወንጀሉን  አምኖ  አጅን  ለመንግስት  ከሰጠ በቀሌን  አቆማለው
….ካለበለዚያ ሁላችሁንም አጠፋችኋላው….የማስጀመሪያው ርችት ተተኩሷል …ሰዓቱ እየቆጠረ ነው…ለእኔም ለእናንተም መልካም እድል፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍42😱2218🔥1
አትሮኖስ pinned «#ቋጠሮ_ሲፈታ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ስድስት ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ ፡ ፡ /// እሱ በራፉን ለመክፈት ሲሄድ አለም ቶሎ ብላ ቦርሳዋ ውስጥ ገባች እና በጣም የሚያምር ውድና ጌጠኛ ብእር አወጣችና ወደቤቱ በራፉ ፊት ለፊት በመወርወር ወደፊት ራመድ ብላ እስኪመለሱ መጠበቅ ጀመረች፡፡ ‹‹እ..ሰላም ነው..?ስልክህ አይነሳም፡፡››አቶ ፍሰሀ ነው ተናጋሪው፡፡ ‹‹ውስጥ ቻርጅ ላይ እርጌው አላየሁትም…ግባ››ኩማንደሩ…»
ቃል ሲጠፋ እምባም ፀሎት ነው!
👍33🔥3
ትልቅ ሰው ሲመክርህ
አድምጥ እንጂ ሁሉንም
ተግባራዊ አታድርግ
ምክንያቱም
ሞኝም ሰው ያረጃል።
15👍12
እግዚአብሔር በአንድ ነገር አይጠረጠርም
ደሀ ደሀው ሞቶ ባለጠጋው አይቀርም።
15
ምን እየሆንኩ ልጠብቅሽ?

ቅድ ሰማይ እየሰፋሁ ራስ ዳሽንን እየገፋሁ

ወይስ እየሰራሁ የኖኅ መርከብ

ሳፈላልግ የሰው ኮከብ..

ምን እየሆንኩ ልጠብቅሽ?

እየዘመርኩ?

እየዘፈንኩ?

እያረመምኩ?

ግራ ገባኝ እኮ ያልለየት ድል ነው ያልለየት ምርኮ።

ምን ስሆን ልጠብቅሽ?

አባይን ስጠልቀው

ኤርታሌን ስሞቀው

ቆዳዬን እንደጨርቅ ችሎ ቢተኩሰው ተዋነይ ጋር ልሂድ ዕፁን እንዲምሰው።

ማን ጋር ልጠብቅሽ?

ከጌታዬ ግራ ከጌታዬ ቀኙ በየት ትመጫለሽ ወይ አፍቃሪ ሞኙ።

ካብርሃም ቤት አጋርወይስ

ባቢሎን ግንብ ጋር።

የት ጋር ትመጫለሽ?

በዘመን የት ዘመን? በቦታ የት ቦታ?

ከንጉሥ የት ንጉሥ? ከባህር ምን ባህር? ከጫካ የት ጫካ? ከደብር ምን ደብር?

ከሶላት ምን ሰዓት?

ምን እያረግኩኝ ልጠብቅሽ? ከመላእክት ጋር ስገለፍጥ የዛፍ ቆዳ ስልጥ...

ግዙፍ ሆኜ ወይ ረቂቅ ንፋስ ሆኜ ወይስ ደቂቅ....

ወንዝ ሆኜ ወይስ አምባ ደስታ ሆኜ ወይስ ዕምባ...

ፀሀይ ግርጌ ወይ ጨረቃ
ግጥም ሆኜ ወይ ሙዚቃ...

ምን እየሆንኩ ልጠብቅሽ?

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
28👏8👍3
ፈጣሪን ለማን ያሙታል

ቤተ መንግሥቱ ጀርባ ያለው ቅዱስ ገብርዔል ቤተክርስትያን አንዳንዴ አመሻሻ ላይ አርምሞውን፣ ድባቡን፣ የዛፎቹን ሽውታ ስለምወደው ጎራ እላለሁ።

ይሄ ምዕመን ጸሎቱ አድርገልህልኛል እና ተመስገን ነው፤ ይኼኛው አሳካልኝ ተማጽኖ ነው እያልኩ የምዕመናኑን ጸሎት ከሁኔታቸው አንጻር እገምታለሁ፡፡

እዚ የቤተክርስትያን ቅፅር : ግቢ ስገባ ነፍሴ እርጋታ ይሰፍንባታል።

ዛሬ...

ሁልጊዜ ስመጣ የምቀመጥበት ደረጃው ላይ ቁጭ ባልኩበት እማማ ጀማነሽ መጡ። ልጃቸው ከሞተባቸው አራት ቀን ሆኗቸዋል፡፡

እማማ ጀማነሽ ብቻቸውን ሲያወሩ፣ ሳንቲም ሲለምኑ፣ ትክዝ ኩርምት ብለው መሬት ሲጭሩ፣ ማንን እንደሆነ እንጃ ሲሳደቡ ብዙ ቀን አይቻቸዋለሁ፡፡ ሳንቲም ሙዳዬ ምጽዋት ውስጥ ሲከቱም ተመልክቼ አውቃለሁ።

ይለምናሉ። ካሏቸው ሦስት ልጆች ሁለቱ ልጆቻቸው ትንሽ አእምሯቸውን እንደሚያምባቸው አውቃለሁ፡፡

የልጃቸው ቀብር ቀን አይናቸው ላይ ትኩስ እንባ እንዳልታየ በትዝብት የልጃቸውን ስርዓተ ቀብር ቆመው ካለ ዋይታ፣ ካለ እንባ አንጀት የሚበላ ፊት እየታየባቸው እንዳስፈጸሙ ሰምቻለው።

እማማ ጀማነሽ ትንሽ ብቻ ራቅ ብለው አጠገቤ መጥተው ቁጭ አሉ። ሰውነታቸው ደልደል ያለ፣ ፊታቸው ጥብስብስ ያለ፣ ጸጉራቸው በሙሉ የሸበተ፣ ጉስቁልና እያንዳንዱ ዳናቸው ላይ ያረፈባቸው፣ አሮጌ ያደፈ ሙሉ ቀሚስ የለበሱ፣
ሰማያዊ እንደነበረ የሚያስታውቅ የመነቸከ ሻርፕ አድርገው፣ ባዶ እግራቸውን ሆነው መከራ ራሱን መስለዋል።

እማማ ጀማነሽ ትንሽ ቁጭ እንዳሉ አንጋጠው ወደ ሰማይእያዩ፦

“ልጄን ወሰድክ አይደል?! ክፋት ካልሆነ በቀር የሚያምብኝን እዮብን ወይ ሚኪን አትወስድም?!” አሉ።

"ክፉ ሆነህ እንጂ!! አቅም የሌለው ፍጡር ላይ እንዲህ ይጨከናል?! የፈጣሪስ ባሕሪ ነው? ስንት ሰው ለመዳን እየለመነህ እኔ ግደለኝ ስል እምቢ ትል ነበር?

ምግብ የቆለፈውን፣ ሲጮህ የሚውለውን ልጄን ትተህ ሁለት ቀን ያልታመመውን ልጄን ትቀማኛለህ? ለፍቶ፣ ሮጦ በፌስታል እህል የሚያመጣልንን ልጄን፣ አንድ ምርኩዛችንን መቀማት ምን ይባላል?!

እ?!

ፍጡርን ማምለጫ ማሳጣት ምን የሚሉት ጥበብ ነው? እንኳን በሕልውናህ የሚያምን ቀርቶ የካደህስ ቢሆን እንዲህ ይደረጋል?

ይደረጋል ወይ? ክፉ ሆነህ አንጂ!!! እንኳንስ ፈጣሪ በዚህ መጠን ፍጡርስ የወደቀን ለመጣል ይታገላል?!

ለማርያምስ ስንቴ ነገርኳት፤ ሕመሜን፣ እጦቴን እሷ ናት የሚገባት ብዬ ተሳልኩ፣ ለመንኩ፣ ምንም የለም?

በድዬም እንደ ሆነ ይቅር እንድትለኝ ለመንኩህ! ተማጸንኩህ!

መልስ የለም።

ደግሞስ ልበድል! ላጥፋ እኔ ብቻ ነኝ ኃጥያተኛ? ሌላው በሕግህ ስለሄደ ነው ብቻዬን የምሰቀለው?

አንተ ግን ማሰቃየት፣ ምርኩዜን መስበር አይደክምህም ?!"

ከዚህ በላይ የሚናገሩትን ቁጭ ብሎ ለመስማት ፈጣሪን ራሱን መሆን ሳያስፈልግ አይቀርም።

ጌታዬ፣ አንተ ግን እኔ እንደሰማኋቸው ስትሰማቸው ምን ብለህ ይሆን??


🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😢278
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ



///
‹‹በተሰቀለው…አሁን ምንድነው የምናደርገው?››

‹‹አላውቅም…ለአባትህ  ደውልለትና  በአስቸኳይ  ይምጣ…እዛ  ይርጋጨፌ  ምንም አያደርግም››

‹‹ደውዬለታለው… እየመጣነው››ሲል መለሰ ጁኑየር

‹‹ዳኛውም እየደወለልኝ ነበር››

‹‹እሱን ተወው ባክህ..ከአሁኑ በልብ ድካም እስከወዲያኛው ማንቀላፋቱ አይቀርም..ለማንኛውም እዚህ ምንም አንሰራም ..ወደቤት እንሄድ›› ተባባሉና ሁለቱም ወደ መኪናቸው በመግባት ተከታትለው ወደእነ ጁኒዬር ቤት መጓዝ ጀመሩ፡፡

በማግስቱ ጥዋት  አንድ ሰዓት በሶሌ ኢንተርፕራይዝ ህንፃ የአቶ ፍሰሀ ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብለው እየተወያዩ ነው፡፡

‹‹ያሰማራናቸውን ሰዎች ምንም ፍንጭ አላገኙም››አቶ ፍሰሀ ናቸው ጠያቂው፡፡

‹‹እዚህ  ከተማ  ውስጥ  ያለች  አይመስለኝም….እያንዳንዱን  ሆቴል  እና  ፔንሲዬን አሳስሼለው….የለችም፡፡››ገመዶ መለሰ፡፡

‹‹ወደ አዲስአበባ ተመልሳ ሊሆን ይችላል?››

‹‹ወደዛም ሰው ልኬለው…..እንግዲህ የሚሆነውን እናያለን፡፡››

‹‹ጥሩ …ዩቲዬብ ባለቤትስ ማግኘት ችለናል…..?››አቶ ፍሰሀ ናቸው ሌላ ጥያቄ የጠየቁት፡፡

‹‹አዎ አናግሬው ነበር…የፈለገውን ያህል ብር እንደምንከፍለውና ቀጣዩን ስራ እንዳይለቅ ጠይቄው ነበር…››

‹‹እና?››

‹‹እናማ…ቀጣዩን አልሰጠችኝም…እራሷ ቀርፃ ነው የምትልክልኝ ….››የሚል መልስ ነው የሰጠኝ፡፡

እንደዛ ከሆነ እኮ አሪፍ ነው…ለልጁ ደህና ብር ስጡትና ቀጣዩን ታሪክ ልታስረክበው ስትቀጥረው ይደውልልን እና እናገኛታለን ማለት ነው››ዳኛው በአዲስ ተስፋ ተሞልተው ተናገሩት፡፡

ኩማንደር ፈገግ አለና‹‹ክቡር ዳኛ….ይሄንን ማሰብ የሚያቅተኝ ይመስልሀል?››

‹‹አይ በፍጹም እንደዛ አላልኩም….ውይይት ላይ ስለሆን የተሰማኝን በግልፅ ነው የተናገርኩት››

‹‹ጥሩ…ለልጁ ይሄንን ሀሳብ አቅርቤለት ነበር….ወዲያው ይሄንን መልእክት አሳየኝ፡፡››

‹‹ምንድነው?››

በዩቲዬብ የተለቀቀውን የወንጀል ታሪካችሁን መንደርደሪያ ስትሰሙ መጀመሪያ ምታደርጉት ወደእዚህ ዩቲዩበሩ ልጅ ጋር ሄዳችሁ በገንዘብም በማስፈራራትም ቀጣዩን እንዳይለቀውና በእሱ አማካይነት እኔን ለመያዝ እንደምትሞክሩ አውቃለው….ለዛም ነው ቀድሜ ይሄንን መልዕክት ልጁ ጋር የተውኩት፡፡አንደኛ ከአሁን በኃላ ቀጥታ ልጁን አላገኘውም .. የተቀረፀውን በሌላ መንገድ ነው ምልክለት፡፡ሁለተኛ ልጅን የምታቆሙት ከሆነ እየተቆራረጠ በአምስት ክፍል ይለቀቅ የነበረውን ለሌላ ዩቲዬበር አንዴ ሰጥቼው በአንዴ እንዲለቀቅና ነገሮች ፍርጥርጥ እንዲሉ አደርጋለው ….ያ ማለት ደግሞ ለማሰቢያ እና የተሻለውን መንገድ መምረጫ ጊዜ ያሳጣችኋላ..እንግዲህ ምርጫው የእናንተ ነው፡፡››ይላል፡፡

‹‹ምን አይነት ጉድ ልጅ ነች?››አቶ ፍሰሀ ነው የተናገረው፡፡

‹‹ብዬችሁ  ነበር..አልሰማ  ብላችሁ  ሁላችንንም  መቀመቅ  ውስጥ  ከተታችሁኝ….በጊዜ ትወገድ ብያችሁ ነበር፡፡››ዳኛው ተወራጩ፡፡

‹‹አንተ  ቀበተት  ሽማግሌ…በዚህ  እድሜህ  አንድ  ፍሬ  ልጅ  ትገደል  ስትል  ትንሽ አይቀፍህም?››አቶ ፍሰሀ በንዴት መለሰ፡፡

‹‹አሁንማ እንድትገደል ብንስማማስ የት እናገኛታለን?በዚህ ሁሉ እድሜዬ አንተንና ኩማንደሩን በእንደዚህ አይነት ጫወታ የበለጠች ብቸኛዋ ሴት እሷ ብቻ ነች፡፡በጣም ብጠላትም በጣም የምትደነቅ ጀግና የሆነች ልጅ ነች››ሲል ዳኛው ተናገረ፡፡

በዚህ ሰዓት ድንገት የኩማንደሩ ስልክ ጠራ ..ከኪሱ አወጣና አየው…..የማያውቀው ቁጥር ነው፡፡አነሳው‹‹ውዴ በጣም ናፍቀኸኛል››
በስልኩ በእግር በፈረስ የሚፈልጋትን የአለም ድምፅ እየሰማ መሆኑን ማመን አልቻለም

‹‹አንቺ…የትነሽ ያለሽው?››

‹‹ቅርብህ ነኝ….ጁኒዬርም አብሮህ ነው አይደል?››

‹‹ምን እያወራሽ ነው?››

‹‹ሁለችሁም ናፍቃችሁኛል?››

‹‹ቀለድሽብን ማለት ነው?››

‹‹አይደለም…መቼስ ሁለታችሁንም እንደምወዳችሁ አትጠራጠሩም አይደል..?ልክ እንደእናቴ… እኔም አፈቅራኋላው፡፡››
ሁሉም አፍጥጠው ይመለከቱት ነበር‹‹እና ምንድነው የምትፈልጊው?፡፡››

‹‹ምፈልገውንማ መጀመሪያ ከተገናኘንበት ቀን አንስቶ መች ደብቄችሁ አውቃለው››

‹‹እና አሁን ምን ይሁን ነው የምትይው?››

‹‹ምንም ….እኔ አሁን እየፈለኩት ስላላው ፍትህ ወይም በቀል ላወራችሁ አይደለም የደወልኩት ..ድምፃችሁን ልሰማ ነው..እባክህ ስልኩን ለጁኒዬር ትሰጠዋለህ፣በጣም ነፍቆኛል…››

‹‹ገደል ግቢ››አለና ስልኩን ጠረቀመው፡፡
‹‹ምንድነው ..ስልኩን ለምን ዘጋህባት?››ጁኒዬር በንዴት ጠየቀው፡፡

‹‹እሷ  ኮመዲ  እየሰራችብን  ነው..እንደናፈቅካት  ተናግራ  ካንተ  እንዳገናኛት  ነው የምትፈልገው››

‹‹ታዲያ ለምን ሳታገኛኘን?››

‹‹ምነው ?አንተም ናፍቃሀለች እንዴ?››

‹‹ተረጋጉ…ሁላችም ወደመቀመጫችሁ ተመለሱ››አቶ ፍሰሀ በመሀከል ጣልቃ ገብተው ሁሉም ወደቀልባቸው እንዲመለሱ አደረጉ፡፡

‹‹ልጆች አይታያችሁም እንዴ..?ይሄ እኮ የበቀሏአንዱ አካል ነው፡፡››

‹‹ማለት..?››ገመዶም ሆነ ጁኒዬር በአንድነት አቶ ፍሰሀ ላይ አፈጠጡ፡፡

‹‹በሁለታችሁ መካከል ቅሬታ በመፍጠር ኃይላችንን ለመበታተን እየጣረች ነው….›› ጁኒዬር ባለማመን ‹‹እንደዛ አስባ ይመስልሀል?፡፡››ሲል በጥርጣሬ ጠየቀ፡፡
‹‹ታዲያ ያንተን ስልክ እያወቀች ለምን ብላ ነው ለገመዶ ደውላ ከጁኒዬር ጋር አገናኘኝ ናፍቆኝ ነው የምትለው?››
‹‹አባዬ እውነትህን ነው….››
///
በተሰጣቸው ሶስት ቀን ውስጥ እሷን አድነው መያዝ አልቻሉም…እሷንም ቀጣዩን ክፍል በተመሳሳይ በዩቲዩብ ገፅ እንዳትለቅ ማድረግ አልቻሉም…ይሄ ሁለተኛው ግን ከመጀመሪያው በበለጠ ጫና ውስጥ ከተታቸው፡፡የከተማው የገዢው ፓርቲ ፅህፈት ቤትም ጁኒዬርን አስጠርቶ በሶሻል ሚዲያው ስለሚዘዋወረው ነገር ማብራሪያ እንዲያቀርብና በአፋጣኝ እየተሰነዘረበት ካለው ክስ ራሱ ነፃ እንዲያደርግ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው፡፡

‹‹አባዬ..ይህ ምርጫ ለምን አይቀርብኝም?››

‹‹ለምን እንደዛ አልክ?››

‹‹የፓርቲው ሰዎች እኮ ቁም ስቅሌን እያሳዩኝ ነው፡፡በአንድ ሳምንት ውስጥ በእኔና በቤተሰቦቼ ላይ እየተነዛ ያለውን ሀሚት ማጥራት ካልቻልኩ በእኔ ጉዳይ ላይ አቋም እንደሚወስዱ ነግረውኛል››

‹‹ምን አይነት አቋም››

‹‹ይመስለኛል..እጩ መቀየር የሚችሉት እስከዚህ ወር መጨረሻ ድረስ ነው፡፡እዚህ ከተማ ላይ በተቃዋሚዎች መሸነፍ አይፈልጉም ..ስለዚህ በሌላ እጩ ሊተኩኝ እያሰቡ ይመስለኛል፡፡››

‹‹ወይ ነዶ..ያን ሁሉ ብር ከስክሰን እንደዚህ ጉድ እንሁን…የክልል ወዳጆቻችንም ለእኔ ደጋግመው እየደወሉልኝ ነው፡፡ልጅቷን መያዝ ካልቻላችሁ እኛ እናግዛችሁ እያሉ ነው፡፡››

‹‹እንዴት አድርገው ነው የሚያግዙን››ጁኒዬር ጠየቀ፡፡

‹‹በአካባቢው ያሉትን የከተማ የፀጥታ አካላት በማነጋገር ፍላጋው ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ ነዋ››

‹‹ታዲያ አሪፍ እድል አይደል?››

‹‹አሪፍ እድል ነው..ግን ደግሞ እገዛቸውን አልተቀበልኩም››

‹‹ለምን?››

‹‹ምክንያቱም እሷን በማደኑ ላይ የመንግስት የፀጥታ አካላት ከገቡበት ድንገት ባልታሰበ ሁኔታ ልትጎዳ ትችላለች…ያንን ሪስክ መውሰድ አልችልም››

‹‹አባዬ..እዚህች ልጅ ላይ የምታሳየው የርህራሄ ስሜት ከእለት ወደእለት እያስደመመኝ ነው፡፡የተለየ ምክንያት አለህ እንዴ?››
51👍7😁1
‹‹ለእሷ ደህንነት ለመጨነቅ ምን የተለየ ምክንያት ያስፈልጋል…..አንዴ ስህተት ሰርተን እናቷን በጨቅላ እድሜዋ አሳጥተናታል….አሁን ደግሞ መልሰን እሷን ብንጎዳት ይቅር የሚባል ድርጊት አይሆንም..››

‹‹እና ምን ትላለህ…?.የሰራሁት ስህተት የምከፍልበት ጊዜ ደርሷል ..ከዚህ በላይ ቤተሰቤንም ሆነ በዙሪያዬ ያሉ ሰዎች ሲረበሹና ሲጎዱ ቁጭ ብዬ ማየት አልችልም፡፡››

‹‹ይሄ ደግሞ ምን ማለት ነው…?ምን ለማድረግ አስበህ ነው?፡፡››

‹‹በመጀመሪያ ነገ ጥዋት የፓርቲው ፅ/ቤት ሄጂ ከእጩነት እንዲያነሱኝና በእኔ ምትክ ሌላ ሰው እንዲተኩ ማመልከቻዬን አስገባለው፡፡ከዛ ቀጣዩን ደግሞ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አስብበታለው..ሶስተኛው ቪዲዬ ከመልቀቋ በፊት አንድ ሰው ኃላፊነቱን መውሰድና እሷንም ማቆም መቻል አለብን፡፡››

‹‹ልጄ ..እንዳልከው ከእጩነት እራስህን የማግለሉን ውሳኔ እኔም እቀበለዋለው…ከዛ ውጭ ግን በራስህ ምንም ነገር አታደርግም..እዚህ ጉዳይ ላይ ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ ሁላችንም አብረን ነበርን..አሁንም አብረን ነን … መደረግ ያለበትን ሁሉ ተነጋግረንና ተስማምተን ነው የምንወስነው፡፡››

‹‹አባዬ ለዛ የሚሆን ጊዜ እኮ የለንም››

‹‹አውቃለው…አታስብ ዛሬና ነገን የሆነ ነገር እናደርጋለን..በል አሁን ወደ ቤት ልሄድ ነው፡፡››

‹‹እሺ አባዬ እኔም የተወሰነ መስራት ያለብኝ ስራ አለ…ማታ እቤት መጣለው….››

‹‹ጥሩ ››አለና….ቢሮውን ለቆ በመውጣት ካለወትሮው መኪናውን እራሱ እያሽከረከረ ወደቤቱ ጉዞ ጀመረ፡፡

አቶ ፍሰሀ ቤቱ ከመድረሱ በፊት በጣም ተጨናነቀ … ወደአንድ ግሮሰሪ ጎራ አለና የሚፈልገውን መጠጥ አዞ እየተጎነጨ ይሄንን ከአልም ጋር ያለውን ችግር በምን ዘዴ ሊፈታው እንደሚችል ማሰላሰል ጀመረ..
….////

አለም እዛው ሻሸመኔ ከተማ በተከራየችው አንድ ክፍል ቤት ውስጥ ሆና ጥግ ግድግዳ ታካ በተነጠፈች አንድ ሜትር ፍራሽ ላይ ጋደም ብላ በቀጣይ ማድረግ ስላለባት ነገር እያሰላሰለች ነው፡፡አሁን የመጀመሪያ በቀሏን ባሰበችው መንገድ አሳካታለች…ጁኒዬር ከተማዋን ወክሎ ለፌዴራል ህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ለመግባት የነበረውን ሀሳብ ሰርዞ ከእጩነት እራሱን እንዲያገል ማድረግ ችላለች፡፡

በቀጣይ ደግሞ የበቀሏ ጅራፍ የሚለመጥጠው ኩማንደሩን ነው..እሱም ቢያንስ ስልጣኑን እንዲለቅና ከስራውም እንዲታገድ ማድረግ ነው የምትፈልገው…ከዚያም እንዲረዳት በቀጣይ እያዘጋጀች ያለችው በዩቲዬብ የሚለቀቀውን ሶስተኛ ቪዲዬ በእሱ ወንጀሎች ዙሪያ እንዲያጠነጥን እያደረገች ነው፡ሶሌ ኢንተርፕራይዝ ውስጥ ያለው ሚስጥራዊ የአክሲዬን ድርሻ ፤ እና ይሄንን ኢንተርፕራይዝ ለማሳደግ እድገትና ደህንት ለመጠበቅ ስልጣኑንና የመንግስትን ንብረት እንዴት አላግባብ ሲጠቀም እንደኖረ መረጃዎችን እያጠናከረችና እያደራጀች ነው፡፡

በቀጣይ ደግሞ ዳኛው ላይ ትዘምታለች..እሱም ለክብር ጡረታ ሳይበቃ ቀጥታ ከወንበሩ በውርደት ተሸቀንጥሮ ወደወህኒ እንዲወረወር ነው የምትፈልገው፡፡በመጨረሻ የአቶ ፍሰሀ ተራ ይሆናል፡፡ሁሉንም ቀስ በቀስ ክንፋቸውን በየተራ እየነቃቀለች በማድቀቅ መብረር የማይችሉ ተራ ሰው ታደርጋቸዋለች..አዎ እቅዷ እንደዛ ነው፡፡ሴቶቹን ለማጥፋት ጉልበቷን አታባክንም….ወንዶቹ ሲከስሙ እነሱም መደብዘዛቸው እና መንኮታኮታቸው አይቀርም…ከዛ በኃላ ምን አልባት ከተማውንም ሆነ ሀገሪቱን ለቃ ትሰደድ ይሆናል!!እዚህ ሀገር እንድትኖር የሚያበረታታ ምን ተዝታና ምን አይነት ተስፋ ይቀራታል?

ድንገት ብልጭ አለባትና ከተኛችበት ተነስታ ቻርጀር ላይ የነበረውን ስልኳን አነሳችና ክፍል ውስጥ ከነበረችው አንድና ብቸኛ አነስተኛ ጠረጴዛ ላይ ካሉ ከስምንት ከሚበልጡ ሲም ካርዶች መካከል አንዱን አነሳችና ስልኳ ውስጥ ከጨመረች በኃላ መደወል የምትፍገውን ቁጥር ፈለገችና ደወለች….ከአራት ጥሪ በኃላ ተነሳ፡፡

‹‹ሄሎ…ማን ልበል?››
‹‹እኔ ነኝ ..ጋሽ ፍሰሀ››

‹‹ይቅርታ የእኔ እመቤት …አላወቅኩሽም››

‹‹እንደው ብትረሳ ብትረሳ ይሄን ድምፅ ትረሳለህ..እርግጠኛ ነኝ ከመደወሌ በፊት እራሱ ስለእኔ ነበር እያሰብክ ያለሀው››

‹‹አለም ነሽ እንዴ?››
‹‹በትክክል ተመልሷል››
‹‹እንዴት ነሽ…?የት ነሽ?››

‹‹ተው እንጂ ጋሽ ፍሰሀ… አሁን እዚህ ቦታ ነኝ ብዬ የምገኝበትን ቦታ የምነግርህ ይመስልሀል?ባይሆን አንተ የት ነህ…?መኪና እየነዳህ ይመስላል?፡፡››

‹‹አዎ …ምንም እልተሳሳትሽም..ስለአንቺ እያሰብኩ እየነዳው ቤቴን አልፌ ከተማውንም ለቅቄ ወደ  ባሌ ጎባ የሚወስደውን  መንገድ ይዤ እየነዳው ነው፡፡››
‹‹በዚህ ማታ… ሁለት ሰዓት እኮ ሆኗል….››

‹‹አላስተዋልኩም ነበር..አሁን እማ እዚህ ሶሌ መድረሴ ካልቀረ ወደ ደን ማሳዬ እየገባው ነው….እዚሁ አድሬ ጥዋት እመለሳለው..ደኑ ውስጥ ማረፊያ ጎጆ አለን››
‹‹አይ ጥሩ ነው…እንደውም እኔን እንዴት በቀላሉ አጥምደህ በእጅህ ማስገባት እንደምትችል የሆነ ሀሳብ ብልጭ ሊልልህ ይችላል…እንደዛ አይነት በደን የተሸፈነ ፀጥ ያለ ቦታ ለማሰብ ጥሩ ነው ሲሉ ሰምቼለው››

‹‹ጥሩ እየተዝናናሽብን ነው አይደል?››
‹‹አረ ምን በወጣኝ››

‹‹እሺ..አሁን ለምን ፈልግሺኝ››

‹‹እንዲሁ ናፍቀኸኝ….››

‹‹ምን  አልሽ…?ቆይ  ወይኔ  አውሬ  ገባብኝ…አውሬ….››የመርበትበት  ድምጹን  ተከትሎ ከፍተኛ የመንጓጓትና የፍንዳታ ድምፅ ተሳማ…በድንጋጤ ከተቀመጠችበት ተነስታ ቤት

ውስጥ እየተዟዟረች ስልኩን ብትሞክር ይጠራል አይነሳም…..ምታደርገው ግራኝ ገባት
..ቀጥታ ቦርሳዋን ይዛ ከቤት ወጣች…ታክሲ ያዘችና መሄድ ወደማታስብበት ወደቀድሞ ቤቷ አመራች …እንደደረሰች ታክሲውን አሰናበተች እና ቀጥታ ወደግቢው ውስጥ ነው የገባችው…ምን አልባት የሆነ ከለላ ስር ተደብቆ የእሷን መምጣጥ የሚጠብቅ ሰላይ ሊኖር እንደሚችል ትገምታለች..ቢሆንም ግድ አልሰጣትም፡፡ቀጥታ ግቢ ውስጥ ወደቆመችው መኪናዋ ነው ያመራችው …ውስጥ ገባችና ሞተሩን አስነስታ እየነዳች ከግቢው ይዛ ወጣች
..ቀጥታ አቶ ፍሰሀ ወደነገራት አቅጣጫ መንዳት ጀመረች፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
56👍11🤩1
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
እሷ እንደጠረጠረችው…ልክ ግቢዋን ከፍታ እንደገባች በተጠንቀቅ ሲጠብቃት የነበረው ኩማንደር ያስቀመጠው ሰው ወዲያው ነበር ያያት…ስልኩን አንስቶ ኩማንደሩ ጋር ለመደወል ያባከነው ደቂቃ አልነበረም….

ኩማንደሩ ስልኩ ሲደወልለት ዳኛው ቤት ቁጭ ብሎ ማድረግ ስለሚገባቸው አንዳንድ ነገሮች እየተወያዩ ነበር….

‹‹በቃ ታክሲ ያዝና ተከታተላት..ከእይታህ እንዳትሰወር…ያለህበት ድረስ እመጣለው››የሚል ትዕዛዝ ነገረውና ስልኩን ዘግቶ ለዳኛው አለም እንደተገኘች ሲነግራቸው ዳግመኛ እንደተወለዱ አይነት እፎይታ ነው የተሰማቸው…

‹‹.እንዲከተሏት አድርጌያለው…አሁን መሄድ አለብኝ….. ››አለና ከተቀመጠበት ተነሳ፡፡

‹‹ለምን ሪስክ ትወስዳለህ..?ወዲያው እንዲይዞት ማድረግ ነበረብህ››ሲሉ አካሄዱ ላይ ያላቸውን ተቃውሟ አሰሙ፡፡

‹‹ይዘናትስ….?ምንም የሰራችው ወንጀል የለም እኮ…ዝም ብለን አንጠልጥለን ልናስራት አንችልም››

‹‹እስከዛሬ የምታስሯቸውን ሰዎች ሁሉ ወንጀል ሰርተው ነው?››ዳኛው ስትሰሩ የኖራችሁትን ማላውቅ መሰላችሁ የሚል ቃና ባለው ንግግር ታቃወሙ፡፡
‹‹ልጅቷ እኮ የዞኑ ምክትል አቃቢ ህግ የነበረች የህግ ባለሞያ ነች….ሌላ ሰው ላይ የምናደርገውን ሁሉ እሷ ላይ በቀላሉ ማድረግ አንችልም…በዛ ላይ መከተላችን…የትነው የምትሄደው…?አጋዥ አላት ወይስ ብቻዋን ነች?››የሚለውን ለማጥናት ይረዳናል….ምን
አልባት ከሌሎች ጠላቶቻችን ጋር ህብረት ፈጥራ የምትንቀሳቀስ ከሆነም እሷን ብቻ ነጥለን መያዝ ከምንም አያተርፈንም…..››

‹‹ጥሩ አስበሀል ..እንግዲያው እኔም አብሬህ መሆን ፈልጋለው….››

‹‹አረ በዚህ ምሽት ይቅርብህ…ባይሆን ሁኔታውን በየጊዜው እየደወልኩ አሳውቅሀለው…››

‹‹አረ እኔም ከእናንት ጋር እሄዳለው››

ፎቅ ላይ ሆና ንግግሯቸውን ስታዳምጥ የነበረችው ስርጉት የአለምን መገኘት ዜና ስትሰማ በደስታ ጃኬቷን ደርባ አምርራ የምትጠላትን ሴት መያዝ በቀጥታ በአይኗ ለመከታተል ዝግጁ ሆና ወደእነሱ ስትመጣ ተመለከተ…ብዙ ቢከራከራቸውም ሁለቱም ለመቅረት ፍላጎት ስላላሳዩ ምን አገባኝ በሚል መንፈስ አብረውት እንዲሄዱ ፈቀደላቸው፡፡በኩማንደሩ ሹፌርነት አባትና ልጅ ከኋላ ሆነው አለምን ለመከታል ወጡ ..አለምን የሚከታተላትን ታክሲ አዲሱ መነኸሪያ ካለፈ በኃላ ነበር የደረሱበት…ከዛ የአለምን መኪና ካሳያቸው በኃላ እሱ እንዲመለስ ነገረውና አነሱ የአለምን መኪና መከታተሉን ቀጠሉ..እሷ ቀጥታ ለዛ ምሽት ፈጣን በሚባል አነዳድ የቦሌን የአስፓልት መንገድ ይዛ እየነዳችው ነው፡፡

‹‹ልጅቷ ወደየት እየሄደች ነው?፡፡››ስርጉት ግራ በመጋባት ውስጥ ሆና ጠየቀች፡፡
‹‹ይመስለኛል…ግብረ አበሮቾ ጋር የምትገናኘው ከከተማው ውጭ ነው፡፡››አባቷ የመሰላቸውን ተናገሩ፡፡

‹‹አይመስለኝም››ኩማንደር ነው ተናጋሪው፡፡

‹‹ማለት…ምን አሰብክ?››

‹‹ትዝ ይላችኃላ እናቷ ኮፈሌ ዘመዶች ነበሯት…የአባቷም ዘመዶች እዛው ናቸው..እኛ በማናውቅበት መንገድ ከዘመዶቾ ጋር መገናኘት ጀምራ ነበር ማለት ነው..እና አሁን እነሱን ለማግኘት እየሄደች ያለ ይመስለኛል..››ሲል መላምቱን አስቀመጠ፡፡

‹‹እና ኮፈሌ ድረስ ልንከተላት ነው ማለት ነው?፡፡››

‹‹እንግዲህ ቀድሞውንም አትከተሉኝ ያልኩት ለዚህ ነው…እኔ እንኳን እዚህች ኮፈሌ ድረስ ይቅርና ሱማሌም ድረስ ከነዳችው ከመከተል ወደኃላ አልልም››ሲል ፍርጥም ያለ ውሳኔውን ነገራቸው፡፡
//

አለም መኪናዋን በፍጥነት እያበረረች እንኳን ደጋግማ አቶ ፍሰሀ ስልክ ላይ ከመደወል አልታቀበችም…ግን አሁንም ስልኩ ይጠራል እንጂ አይነሳም…‹‹ይሄ ማለት ሰውዬው ከባድ አደጋ ደርሶበታል ማለት ነው..?››ስትል አሰበችና ዝግንን አላት….በእሱ ላይ በሚደርስ አደጋ እንደዚህ አይነት ሽብር ውስጥ እገባለሁ ብላ አስባ አታውቅም ነበር….እርግጥ እንዲህ በድሎኛል ብላ አንድም ቀን አካላዊ ጉዳቱን ወይም ሞቱን ተመኝታለት አታውቅም
…ቢሆንም ደህንነቱ በዚህ መጠን እንዲህ ያሳስበኛል ብላም ግምቱ አልነበራትም፡፡እና የራሷ ሁኔታ በጣም ነው ያስገረማት፡፡

‹‹ፈጣሪ ሆይ እባክህ..ህይወቱን ጠብቃት››ከልቧ ፀለየች፡፡ለቤተሰቦቹ መሳወቅ እንዳለባት ትዝ ያላት ወደባሌ የሚያመራውን የአስፓልት መንገድ ለቃ ወደቀኝ በመታጠፋ ወደ  ሶሌ ደን የሚወስደውን ጥርጊያ መንገድ ከያዘች በኃላ ነበር፡፡የጂኒዬርን ቁጥር ፈለገችና ደወችለት፡፡

‹‹ሄሎ ጁኒዬር…. አለም ነኝ››

‹‹አለም ..ደህና ነሽ…?የት ነሽ….?እንዴት ነሽ?››የእሷን ድምፅ ሲሰማ የሚይዘው የሚጨብጠው ጠፋበት፡፡ስልኩ ሲደወልለት ቤት ከእናቱ ጋር ሳሎን ቁጭ ብሎ እየተጫወተ ነበር፡፡እሷ ለእሱ መርበትበት ቁብም ሳትሰጥ ንግግሯን ቀጠለች‹‹ጂኒዬር ልብ ብለህ አድምጠኝ…ከ30 ደቂቃ በፊት ከአባትህ ጋር በስልክ እያወራሁ ነበር…መኪና እየነዳ ሳያስበው ከከተማ እንደወጣ እና ወደሶሌ ደን እየተቃረበ መሆኑንና ከአሁን በኃላ ስለመሸ ወደከተማ እንደማይመለስና ማረፊያ ጎጆ ስላለው እዛው እንደሚያድር እየነገረኝ ነበር፡፡›

‹‹አዎ እዛ አልፎ አልፎ የምናርፍበት ጎጆ አለን….››

‹‹እና..ምን መሰለህ?››

‹‹እያስደነገጥሺኝ ነው..ስለምን ነበር እያወራችሁ የነበረው?››

‹‹እሱ ምን ይሰራልሀል…ለማንኛውም ንግግራችንን ሳንጨርስ አውሬ ገባብኝ የሚል ድምፅ እና ከፈተኛ ፍንዳታ የመሰለ ነገር ሰማው..እና ስልኩ ተቋረጠ.. መልሼ ደጋግሜ ብደውል ስልኩ ይጠራል… አይነሳም..፡፡››

‹‹ወይኔ ፈጣሪ…ምን እያልሺኝ ነው?››አጠገቡ የነበረችው እናቱ ሳራ የልጇ ጭንቀት በእሷም ላይ ተጋብቶባት…ስሩ ቆማ ትንቆራጠጥ ጀመር፡፡.

‹‹ለምንኛውም አሁን ቦታው ላይ እየደረስኩ ነው.. እንዳገኘሁትና ሁኔታውን እንዳየው እደውልልሀለው…ምን አልባት አንብላንስ ያስፈልግ ይሆናል››ስልኩ ተቋረጠ
‹‹ምንድ ነው ልጄ..?ፍሰሀ ምን ሆነ?››ሳራ ጠየቀች፡፡

‹‹አባዬ አደጋ ደርሶበታል መሰለኝ..ሶሌ ያለው ደን ውስጥ ነው…መሄዴ ነው››

‹‹እኔም አብሬህ እሔዳለው››

‹‹እማዬ አንቺ እዚሁ ሆነሽ ጠብቂ….››

‹‹እሔደለው..አልኩህ እሔዳው›› አጉረጠረጠችበት፡፡ምንም አላለም…በክርክር ጊዜ ማባከን ስላልፈለገ ቀጥታ ወደሳሎኑ መውጫ መራመድ ጀመረ… እናቱም ከኃላው ተከተለችው… መኪና ውስጥ ገቡ ..ወደባሌ ጎባ የሚወስደውን የአስፓልት መንገድ ይዘው ወደ ሶሌ ጉዞ ጀመሩ
///
አቶ ፍሰሀ አውሬውን አድናለው ብሎ መሪውን ሲጠመዝ ሙሉ በሙሉ ከመንገዱ ወጥቶ በግራ በኩል ባለው ገደል መሰል ጉድጓድ ውስጥ ነበር ጎማው ተንሸራቷ የገባው…ከዛ ፍሬኑን ለመያዝ ቢሞክርም የመኪናዋን ፍጥነትም ሆነ ባላንስ መቆጣጠር አቅቶት አንድ ዙር ተገለበጠና አንድ የብሳና ዛፍ ተደግፎ ቆመ….ለአምስት ደቂቃ ራሱን አያውቅም ነበር፡፡ከገባበት መደንዘዝ ሲወጣ ወንበሩ ስር ተወሽቆ ነው ራሱን ያገኘው…እንደምንም ታግሎ ቀበቶውን ከአንገቱ አወጣና በራፍን በእግሮቹ ገፍቶ ለመክፈት ሞከር..ቀላል ስራ እልሆነለትም፡፡እግሮቹ  ምን  እንደነካቸው  ባያውቅም  የሚያሰበውን  ያህል  ጥንካሬ
37👍4
የላቸውም፡፡ከ10 ደቂቃ ትግል በኃላ በራፉ ተከፈተለት….እንደምንም እራሱን ጎትቶ ወጣና መሬት ላይ ተዘረረ….ከግንባሩ የሚንጠባጠብ ደም ተመለከተ…እጆቹ ሁለት ቦታዎች በመስታወት ስብርባሪ ተቆርጠዋል…እንደምንም ራሱን አጠናክሮ ተነስቶ ቆመ …በሰማዩ ላይ ጨረቃዋ በግማሽ ወጥታ የተወሰነ ብርሀን እየረጨች ስለሆነ ሙሉ በሙሉ ድቅድቅ ጨለማ አይደለም…ከቦታው ተንቀሳቀሰ እና ወደጫካው ውስጥ ገብቶ በግምት 20 ደቂቃ ያህል ወደሚያስኬደው አቋራጭ ጠባብ የእግር መንገድ ገባና ወደ ጎጆው መራመድ ጀመረ…፡፡

በሰላሙ ጊዜ እድሜውን ሙሉ ሲወጣ ሲወርድበት የኖረበት ጥቅጥቅ ጫካ ቢሆንም በዚህ ጊዜ ሁሉም ነገር የተለመደ እና አሰልቺ የሆነበት ይመስላል፡፡ በጫካው ውስጥ የሚገኙትን ግዙፍ የጥድ ዛፎች መቶ ዓመት ያስቆጠሩ ሊሆኑ ይችላል፣ እና እነዚህ በተለያዩ ቁጥቆጦዎች የተሸፈኑ ጥንታዊ ዛፎች ግንዶቻቸው በውስጣቸው የበሰበሱ ነበሩ። አንዳንድ ዛፎች ወድቀው ግዙፍና አስቀያሚ ሥሮቻቸውን ወደ ላይ ተፈንቅለው ይታዩ ነበር፣ እና የስሮቹ ቅርፃች በዛ ጭለማ ድንገት ላያቸው አስፈሪ ጭራቆች ስለሚመስሉ ቅፅበታዊ ፍራቻ በሰው ደም ውስጥ ይረጫሉ፡፡ አብዛኛው ደን ግን በለምለም የባህር ዛው ዛፎች ተጠቅጥቆ የተሞላ ነው፡፡

አቶ ፍሰሀ በጫካው ውስጥ የሚንሾሹትን ዛፎቹ እያቋረጠ እና የረገፉ ቅጠሎች በእግሮቹ እያንኮሻኮሸ ሰሞኑን aስላጋጠሙት ችግሮች እያሰላሰለ ጉዞውን ቀጥሏል። እንደዛም ቢሆን በውስጡ የነገሰው መጨነቅ፤ውዝግቦች፣ ብስጭቶች እና ጭንቀቶች በጫካው ታላቅነትና ጥንታዊ ኃይል የተዳከሙ ይመስሉ ነበር። ከወራት በፊት እሱ ልክ እንደብረት ጠንካራ እና ጤናማ ሰው ነበር፡፡ያቺ ሴት ወደእዚህ ከተማ መጥታ ፊት ለፊቱ ከተጋገረጠችበት ቀን አንስቶ ግን እንደቀድሞ ብርቱ ሆኖ መቀጠል አልቻለም…በሙሉ አቅም ሊፋለሟት የማይችሉት ጠላት ነው የሆነችበት፡፡ ሰሞኑን ስለእሱና ስለቤተሰቦቹ በዩቲዩብ የለቀቀችው ሁለት ተከታታይ ቪዲዬ ቅስሙን ሰብረውታል…ከቀናት በኃላ በቀጣዩ ቨዲዬ በሚለቀቁ መረጃዎች ሙሉ በሙሉ ከቁጥጥር ውጭ ከመውጣታቸው በፊት ማስቆም ባለመቻሉ ነበር ተስፋ የቆረጠው።

‹‹ይሄ ምልክት ነው ››ሲል አሰበ…
‹‹ከደቂቃዎች በፊት ሞት ፊት ለፊቴ ቆሜ ነበር…ከእነ ሚስጥሬ እና ከነ ሀጥያቴ ሞቼ ነበር…አምላክ አሳይቶ የማረኝ ነገሮችን በትክክለኛው መንገድ እንዳስተካክል ነው››ሲል አሰበ….ነገሮችን በትክክለኛው መንገድ ለማስተካከል ግን የግድ በውስጡ ለአመታት የቀበረውን ሚስጥር ለመላ ቤተሰቡ በግልፅ መናገር አለበት….ያንን ማድረግ ደግሞ ምን አልባት ብዙ ነገር ሊያሳጣው ይችላል፡፡በዚህ የመጨረሻ የእድሜ ዘመኑ የሚያፈቅራት ሚስቱ ሳራ ልትፈታው ትችለች…ልጁ ጁኒዬርም መቼም ይቅር ላይለው ይችላል….‹‹ቢሆንም ይሄ ሁሉ ቅጣት ይገባኛል››ሲል ነገሩን ፊት ለፊት ለመጋፈጥ ወሰነ፡፡እንደዚህ በመወሰኑ የሰውነት ቅጥቅጥ ጥዝጣዜ ነፍሱን ጭምር እያነሰፈሰፈው ቢሆንም ከብዙ ወራቶች ቁዘማ በኃላ እየተረጋጋ ሲሄድ ተሰማው ..ከዚህ ውሳኔ በኃላ ነው ድንገት ከጅቡ ጋር በትንሽ ርቀት ተፋጦ ራሱን ያገኘው፡፡ አውሬው ጋር ፊት ለፊት እየተያዩ ቆሙ። በአቶ ፍሰሀ ሰውነት የፍርሀት ቅዝቃዜ ፈሰሰ። ‹‹እንዴ አምላኬ የሰጠኸኝን የንሰሀ ጊዜ መልሰህ ልትነጥቀኝ ነው እንዴ?…አረ አታድርገው››ከአመታት በኃላ እውነተኛ ፀሎት ፀለየ፡፡

‹‹ ምን ማድረግ አለብኝ?››እራሱን ጠየቀ፡፡ድንገት ጎኑን ሲዳብስ ሽጉጡ መኖሩን ተመለከተ፡፡ቶሎ ብሎ አወጣውና በእጁ አስተካክሎ ያዘው፡፡ተኩሶ ለመግደል አልፈለገም፡፡ እሱ ራሱ ከደቂቃ በፊት ነፍሱ ከሞት በተአምር ተርፏል.. ምንም እንኳን እንስሳ ቢሆንም አሁን መልሶ ሌላ ነፍስ አያጠፋም…ወሰነ‹‹እግዜር ያተረፈኝ ነፍስ እንዳጠፋ አይደለም››

‹‹ዞር ብዬ መሮጥ አለብኝ?››ሲል ራሱን ጠየቀ.. በዚህ ዕድሜው በዛ ላይ እንዲህ ሰውነቷ ደቆ በጫካ ውስጥ ህይወቱን ለማዳን ሲሮጥ በአይነ ህሊናው ሳለው፡፡
‹‹ፍሰሀ በጭራሽ አትሮጥም፡፡›› ለራሱ ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡ቀስ ብሎ ወደኃላው ማፈግፈግ ጀመረ…‹‹እውነት ነው፣ ጠላት ካንተ ሲበረታ አቅምን አውቆ ማፈግፈግ ብልህነት ነው። እና አንዳንዴ በጦርነት ጊዜ ሞኞች መንገድን ሲጠረቅሙት በብልጠት ከመንገድ ዞር ማለት ያስፈልጋል።››አለ፡፡

በራሳቸው የሚንከራተቱ ጅቦች በመንገዳቸው ላይ ያጋጠማቸውን ማንኛውንም ፍጥረት ሊያጠቁ እንደሚችሉ ከልምድ ያውቃል፡፡ በተለይ እንደተበደሉ ከተሰማቸው ቂመኞች እና ቁጡዎች ናቸው..አሁን ፊት ለፊቱ የተጋረጠው በጣም ወጣት ጅብ አይመስልም። እንስሳው ፍሰሀን በትኩረት ተመለከተው፣ ፍጹም የማይንቀሳቀስ ሆኖ ቆመ፣ አንድም ጊዜ እንቅስቃሴ አላደረገም።የሚንቀሳቀሰው ጅራቱ ብቻ ነው ። ለጥቃት ወይም ለማፈግፈግ በተከፋፈለ ልብ ተጨንቆ የነበረ ይመስላል?የሰው ልጅ ለመረዳት ቀላል ነበር፣ እና ሳያውቁ ጥቃት ካልደረሰበት እና ድንገት ከኋላው ቢላዋ ካልተሰካበት በስተቀር ራስን ለመከላከል ቀላል ነበር። ድንገተኛ ጥቃት ከሁሉ የከፋው ነበር ፡፡

‹‹እስከመቼ እንደዚህ ተፋጠን እንቆያለን?››መላሽ ባይኖርም ጠየቀ፡፡

እንስሳው ማጥቃት ሊጀምር መሰለ.. እና ዓይኖቹ ተጨፍነዋል…እና ሰውነቱ ሁሉ ሲወጣጠር በፊት ከነበረው የበለጠ ግዙፍ ሆኖ ታየ .፣ ዓላማው ገዳይ ለመሆን እቅድ ያለው አይመስልም ።ምናልባት ታሞ ይሆናል? እነዚህን የሩቅ ቁጥቋጦች ላይ በብቸኝነት ለመዝመት ፈልጎ ይሆን?

አቶ ፍሰሀ‹‹ በእውነት ወደ እዚህ ስፍራ የመጣኸው ለመሞት ከሆነ ንገረኝ ?››ሲል በውስጡ እንስሳው ላይ አጉረመረመ ፡፡

‹‹ተረድቼሀለው እና እውነቱን ማወቅ ከፈለግክ እኔ በአንተ በጣም በጣም እንደምቀና ልንግርህ ፈልጋለው። እኔም መሞት እፈልጋለሁ። አዎ እዚህ ጫካ ውስጥ. በፀጥታ ብሞት በጣም ደስተኛ ነኝ …ግን የሰራሁትን ከባድ ስህተት ማስተካከል አለብኝ፣ለዛ ደግሞ ጥቂትም ቢሆን ተጨማሪ ጊዜ እፈልጋለው። ››

በቅጽበታዊ ውሳኔ ሽጉጡን ወደሰማይ ከፍ አደረገና ቃታውን ተጫነና ሁለት ጥይቶች አከታትሎ ተኮሰ…. እንስሳው በሸኮናው መሬቱን በንዴት ቧጠጠ እና ራሱን ወደጫካው ወረወረ፣ ።አቶ ፍሰሀ በራሱ ብልህነት መገረሙን ማቆም አልቻለም። በአቅራቢያው ካለው ዛፍ ጀርባ ተወረወረ…ከዚያም ሸጉጡን እንደያዘ በጥድ በተሟላ ጥሻ ውስጥ ዘልቆ ገባና ተሸሸገ።በመጨረሻ ቆም ብሎ ሲያዳምጥ መንጋው ሆነው ወደእሱ እየመጡ መሰለው፡፡ የሰማው ነገር የመንጋ የእግር ኮቴ ሳይሆን የገዛ የልቡ ምቱ መሆኑን ለመረዳት ብዙ ጊዜ ወስዶበት ነበር። ደሙ ወደ ጭንቅላቱ ሽቅብ እየሮጠ ከመሆኑም በላይ በጆሮው አስፈሪ ጩኸት ይሰማው ጀመር….በአካባቢው ምንም አይነት የድሩ እንስሳት ድምጽ የለም። አውሬው አሁንም በመቶ ሜትር ርቀት ላይ ተሸሽጎ እየተነፈሰ ነው።አቶ ፍሰሀ መንገዱን አሳብሮ ተንቀሳቀሰ..አውሬው ሊከተለው አልደፈረም….ወዲያው የባትሪ መብራት በላዩ ላይ ሲወነጨፍ ተመለከተ….‹‹ማነው…?እባካችሁ እርዱኝ›› ድምጽ አውጥቶ ተማፀነ፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronosen
👍5027🤔4
አትሮኖስ pinned «#ቋጠሮ_ሲፈታ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሰባት ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ /// እሷ እንደጠረጠረችው…ልክ ግቢዋን ከፍታ እንደገባች በተጠንቀቅ ሲጠብቃት የነበረው ኩማንደር ያስቀመጠው ሰው ወዲያው ነበር ያያት…ስልኩን አንስቶ ኩማንደሩ ጋር ለመደወል ያባከነው ደቂቃ አልነበረም…. ኩማንደሩ ስልኩ ሲደወልለት ዳኛው ቤት ቁጭ ብሎ ማድረግ ስለሚገባቸው አንዳንድ ነገሮች እየተወያዩ ነበር…. ‹‹በቃ ታክሲ ያዝና…»
#እኛኮ_ተለያይተናል

አብረን ሆነን በቃሽ በቃህ ተባብለናል አብረን ሆነን እንዴት ቆምን በዚህ ርቀት አለን ስንል ምን ዳረገን ለዚህ ውድቀት?

ስር ስሩን በልቶን ጥላቻ እየሳቅን የምንታይ ለተመልካች አይን ብቻ ፍቅራችንን ዳባ አልብሰን አቅም እስኪያጥረን ለአቤት የተፋታን ግን በአንድ ቤት

ለህመማችን መዳኛ መድሀኔት መፈለግ ትተን ምን ይሉን የሚያቃትተን እኛኮ አልኖርንም ለኛ እኛኮ አልቆምንም ለኛ ቤታችን ሲፈርስ እንዳናይ ጀርባ ለጀርባ ስንተኛ

ምን ሆነን ነው?

ምን ነክቶን ነው?

"ምን እናድርግ" ማለት ትተን ይኸው አለን በአንድ ላይ በአንድ ቤት ተለያይተን

ይቅርታ...

እኛኮ ተለያይተናል አብረን ሆነን በቃሽ በቃህ ተባብለናል አብረን ሆነን እንዴት ቆምን በዚህ ርቀት አለን ስንል ምን ዳረገን ለዚህ ውድቀት?

ስር ስሩን በልቶን ጥላቻ እየሳቅን የምንታይ ለተመልካች አይን ብቻ ፍቅራችንን ዳባ አልብሰን አቅም እስኪያጥረን ለአቤት የተፋታን ግን በአንድ ቤት

ለህመማችን መዳኛ መድሀኔት መፈለግ ትተን ምን ይሉን የሚያቃትተን እኛኮ አልኖርንም ለኛ እኛኮ አልቆምንም ለኛ ቤታችን ሲፈርስ እንዳናይ ጀርባ ለጀርባ ስንተኛ

ምን ሆነን ነው?

ምን ነክቶን ነው?

"ምን እናድርግ" ማለት ትተን ይኸው አለን በአንድ ላይ በአንድ ቤት ተለያይተን

ይቅርታ...

"ይቅርታ" ምትለውን ቃል ማን ደፍሮ ከአፉ ይትፋት ማን አምኖ ቀድሞ ይፃፋት?

እኔ ከአንቺ ይምጣ እያልኩኝ አንቺ ደሞ ስትይ ከኔ ኩራት ይሁን ወይም እልህ አልያ ደግሞ አጉል ወኔ በአንድ የቃል እርቀት ከሁለት ጥግ እንደቆምን ይኸው ዘመናት አለፈ አልሸነፍም ስላልን የኛ ፍቅር ተሸነፈ ለአለም ይበቃል ያልነው ከጥላቻ እንኳን ኮሰሰ እንደ ነውር እንደ ሀጥያት በየሰዉ አፍ ታመሰ
14👍3🔥1
ኩራታችን ጎን ሞልቶ ላያሳድር አመቻችቶ መውደዳችን ወድቆ ሲቀር ኋላ ኋላ ሊፀፅተን ከአፈር አፍሶ ለማንሳት ጎምበስ የሚል ደረት አተን ይቅር ቃሉ ያሻፈረን አለን ይኸው በአንድ ላይ በአንድ ቤት ተለያይተን ክብርን መውደድ ላይ ደንቅረን

እና ባክሽ እንታረቅ እንደበፊታችን ነይ እንተሳሰርፍቅራችንን ተይው ስንት የለፋንበት ፀባችን አይክሰር

ያ ሁሉ መኳረፍ ያ ሁሉ መጣላት አይሁን ለጠላችው ወይ ደሞ ለጠላት ያፈሰስሺው እምባ ያለቀስሽው በኔ ተይ አይቅር በከንቱ እንታረቅ ባክሽ ናፍቀሺኛል እኔ

እንደ ልጅነቱ የማርያም ጣትሽን ዘርጊልኝ አንድ አፍታ ስንቱን ላሳለፈው ለምስኪን ፍቅራችን ይበዛል ይቅርታ?

አይበዛም... አይበዛም... ነይ ባክሽ ታረቂኝ ከመኖር ላስታርቅሽ ከህይወት አስታርቂኝ

እንዲያ ያኳረፈን... እንዲያ ያዛለፈን በረባው ባረባው እሾህ ቢመስለንም ጥለን የማንሄደው የኛ ነው አበባው

እና ለምን ብለን? ፍቅራችንን ወዲያ ጥለን በሁለት መንገድ እንሄዳለን እኔና አንቺኮ ቢከፋም ቢለማም ትልቅ ታሪክ አለን

ባክሽ እንታረቅ

🔘ዘዉድ አክሊል🔘
8👍4🔥1
#ባለመኖር_ስጋት

አብሬሽ እስካለሁ ''ፈልገሽ አትጪኝ''
ከሚል ምኞት በቀር ሌላ ሐቅ አላውቅም፣ በተፈለጉበት አለመኖር እንጂ
የሚፈልጉትን ማጣት ብዙ አይጨንቅም፡፡

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍62
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
‹‹ጋሽ ፍሰሀ..አንተ ነህ…?››

‹‹አዎ አለም…እዚህ ምን ትሰሪያለሽ?››አውሬው ካስደነገጠው በላይ የእሷ በዚህ ሰዓት እዚህ አካባቢ መገኘት አስደነገጠው፡፡

‹‹እንዴ ስልክ እያወራን ነበር እኮ የተቆረጠው….መኪናህ እንደተገለበጠች እርግጠኛ ስለነበርኩ ወዲያውኑ ወደእዚህ የመጣሁት…መኪናህን ቀድሜ ባገኛትም ውስጡ የለህም..ግን የሚንጠባጠበውን ደም እየተከተልኩ ደረስኩብህ››

‹‹ስሩ ደርሳ ደገፈችው››

‹‹አብሮሽ ማን አለ?››

‹‹አረ ማንም የለ….መንገድ ላይ ሆኜ ለጁኒዬር ደውዬለታለው..ይሄኔ እየመጡ ይሆናል፡››

‹‹ይገርማል..የሆነ ነገር ቢያጋጥምሽስ?››

‹‹ሀሳቤ ሁሉ ያንተን ደህንነት ማረጋገጥ ላይ ስለነበር እሱን አላሳብኩትም ነበር…እውነቱን ንገሪኝ ካልከኝ ግን አሁን በፍራቻ እየተንቀጠቀጥኩ ነው፡፡››

‹‹በጣም ነው ያስገረምሺኝ..አይዞሽ አሁን አምስት ደቂቃ ነው ደርሰናል….እንደውም እዛ መብራት ጭልጭል የሚልበት ቦታ ይታይሻል …?እዛ ነው ጎጆው…በአቅራቢያው የእኔ ሰራተኞች ቤትም አለ…››

‹‹ በአንድ እጇ ደግፋው በሌላ እጇ ደግሞ የስልኳን ባትሪ ከፊት ለፊት እያበራች ወደፊት በዝግታ መራመዳቸውን ቀጠሉ፡፡
አቶ ፍሰሀ ከአውሬው ጋር የነበረው መፋጠጥ አሁንም ከምናብ ሊደበዝዝ አልቻለም… ልቡ ለምን እንዲህ ከመጠን በላይ መታ? ጉዳዩ ምን ነበር? የዱር አውሬው በጣም አስፈርቶት ነው? አይደለም፡፡ እሱ ስለእነሱ አላሰበም። በህይወቱ የበለጠ አስፈሪ ነገሮችን አሳልፎ ያውቃል። ወዲያው ከኃላቸው እየተንሾካሾኩ የሚመጣ የእግር ኮቴ ሰሙ…መንገዱን ለቀቁና ጢሻውን ተከልለው ቆሙ..ሲጠጎቸው ማንነታቸውን በድምፅ ለዩ…‹‹ገመዶ››
ባትሪውን ሲያበራባት ፈጽሞ እዚህ አገኘዋለሁ ብሎ ያላሰበውን አቶ ፍሰሀን በአለም ተደግፋፎ ልክ እንደተወዳጅ ልጁ ስሩ ተሸጉጣ ሲያይ አይኑን ማመን አልቻለም፡፡

ሁሉም ተንደርድረው ከበቧቸው‹‹ጋሼ ምን እየተካሄደ ነው?››

‹‹አይዞችሁ አትደንግጡ… ተርፌለው››

‹‹ተርፌለው ማለት?››ኩማንደሩ በመገረም ጠየቀ፡፡

‹‹የመኪና አደጋ እንደደረሰብኝ ሰምታችሁ አይደለም እንዴ የመጣችሁት?››

‹‹አረ በፈጣሪ..ተርፍክ ታዲያ…?እኛ አልሰማንም..እሷን ከከተማ ስትወጣ አይተን ተከትለናት ነው የመጣናው…ከጠላቶቻችን ጋር ልትገናኝ መስሎን ነበር››

‹‹አይ እሷ እኔን ለማትረፍ ነው የመጣችው››

‹‹እንዴት ከእኛ ቀድማ ልትሰማ ቻለች?..ነው ወይስ በአደጋው ላይ የእሷ እጅ አለበት?››

‹‹እሱን ጎጆው ጋር  ደርሰን ትንሽ ካረፈ በኃላ ብትጠይቀው አይሻልም?››አለችው አለም በንዴት፡፡

‹‹ለምን ወደጎጆ እንሄዳለን? መኪናችንን እኮ በቅርብ ርቀት ላይ ነው ያቆምናት..እዚሁ ጠብቁኝና ይዣት ልምጣ..ቀጥታ ወደከተማ ሄደህ ህክምና ማግኘት አለብህ››

‹‹አይ ደህና ነኝ..አሁን ማረፍ ነው የምፈለገው..ወደጎጆ ውሰዱኝ››

‹‹ተው  እንጂ  ፍሰሀ  ..ሀኪም  ሊያይህ  ይገባል››ዳኛው  ጣልቃ  ገብተው  ለኩማንደሩ ድጋፋቸውን ሰጡ፡፡

‹‹የበለጠ  እያደከማችሁኝ  መሆኑን  ልብ  አላላችሁም  እንዴ..?ወደጎጆ  መሄድ  ነው የምፈልገው›› በማለት የማይቀየር አቋማቸውን አሰሙ፡፡

‹‹ይቅርታ ጋሼ..አንተ ካልክ እሺ ወደጎጆ እንወስድሀለን….እነ ጁኒዬርም አሁን ደውለውልኝ ነበር …መገንጠያው ጋር ደርሰዋል….ከደቂቃዎች በኃላ ይደርሳሉ..››አለና ሄዶ በሌላ ጎኑ አቶ ፍሰሀን ደገፈ….ከ5 ደቂቃ በኃላ ጎጆዋ ደረሱ፡፡ፋኖስ አበሩ፣ መኝታው ተስተካክሎ እንዲተኛ ተደረገና በቅርብ ርቀት ያሉ ሌላ የሳር ቤት ውስጥ ወደሚኖሩት የእነሱ ሰራተኞች ተቀስቅሰው መጡ..እሳት እንዲቃጣጠል ተደረገ…ጁኒዬርና ሳራ የመጀመሪያ ለእረዳታ መስጫ የሚያለግሉ ቁሳቁሶች ይዘው እያለከለኩ ደረሱ…ለተወሰነ ጊዜ ለቅሶና ግርግር በጠባቧ ጎጆ ነገሰ..ከዛ ቀስ በቀስ ወደመረጋጋት ቢመጣም በሰው ብዛት በታፈነችው ጎጆ ውጥረትና ጭንቀት ነግሶ ነበር፡፡

‹‹ቆይ እኔ ያልገባኝ…ምንድነው የሚያስጠብቀን..?ለምንድነው ወደከተማ ይዘነው ሔደን ሀኪማ የማያየው?››ሳራ ነች ግራ በመጋባት ተመሳሳይ አይነት ጥያቄ ለሶስተኛ ጊዜ ያነሳችው፡፡

‹‹ጋሼ አልፈልግም ስላለ እኮ ነው…ጋሼ አሁን ትንሽ አርፈሀል፣ብንሄድ ምን ይመስልሀል?››ኩማንደር ነው ተናጋሪው፡፡

‹‹አይ ዛሬ ማንም ከዚህ አይሄድም…አሁን ሰዎቹን ሸኞቸውና የምንነጋገረው ነገር አለ››ሲል ሁሉም በቀጣይ ምን ሊፈጠር ነው በሚል እርስ በርስ ተያዩ፡፡

ጁኒዬር ከጎረቤት ጎጆ የመጡትን ባልና ሚስቶች ከነልጆቻቸው አመስግኖ ወደቤታቸው እንዲሄዱ ካደረገ በኃላ የጎጆዋ ቤት ተዘጋ፡፡አሁን ስድስት ሰዎች ፊት ለፊት ተፋጠጡ …ሁለቱ ሴቶች እና አዛውንቱ ዳኛ አቶ ፍሰሀ ጎን የተቀመጠችውን አለምን በከፍተኛ ጥላቻን መጠየፍ ነበር የሚመለከቷት፡፡

አቶ ፍሰሀ ከትራሱ ቀና አደረገና አስተካክሎ በመደገፍ መናገር ጀመረ‹‹ዛሬ እየሆነ ያለው ሁሉ ነገር ተአምር ነው…እኔ እቅዴ እንደማንኛውም ቀን ስራ ውዬ ወደቤቴ መግባት ነበር….ነገር ግን የሰሞኑን ውጣ ውረድ እያሰላሰልኩ ሳላስበው ከከተማ ወጣሁና እራሴን እዚህ ሶሌ ደን አካባቢ አገኘሁት..እንዴት እዚህ ልደርስ ቻልኩ? ብዬ እየተገረምኩ ሳለ ያልጠበቅኳት አለም ደወለችልኝ..ከእሷ ጋር እያወራው ሳለ ድንገት ሳላስበው አውሬ ገባብኝና እሱን አድናለው ስል መኪናዬ መንገድ ስታ ተገለበጥኩ…እንደአደጋው መሞት ነበረብኝ..ግን ከተወሰነ ጭረት በስተቀር ምንም አልሆንኩም…እግዜር አሳይቶ ከሞት ደጃፍ መለሰኝ..ከመኪናው ወጥቼ በጫካው እያሳበርኩ ወደእዚህ እየመጣው ሳለ ከጅብ ጋር ፊት ለፊት ተፋጠጥኩ…እሱንም ወደሰማይ ተኩሼ አስበረገግኩትና ሁለተኛውን ፈተና አለፍኩ..ከዛ ወዲያው አለምን ከፊት ለፊቴ አገኘኃት..ወዲያው እነ ገመዶና መጡ…ጎጆው እንደደረስን ደግሞ ልጄና ባለቤቴ መጡ …እኔ ለማናችሁም አደጋ ደረሰብኝ ብዬ አልደወልኩም..በአደጋው ጊዜ ስልኬ ወደየት እንደጠፋም አላውቅም..ግን ሁላችሁም እዚህ ተገኝታችኃላ..ሁላችንን እዚህ ያለነው ለምክንያት ነው፡፡ከአለም ጋር የጀመርነው ድብብቆሽ እዚህ ጋ ማብቃት መቻል አለበት፡፡

‹‹አዎ ማብቃት አለበት …ይህቼ ሴት ከዚህ በፊት ንብረቴ እንዲቃጠል አደረገች… ዛሬ ባለቤቴን ገድላብኝ ነበር….››ሳራ ተንዘረዘረች…ዳኛውና ስርጉት አይናቸውን በማጉረጥረጥ እና በመገላመጥ ለሳራ ያላቸውን እገዛ አሳዩ ፡፡

‹‹ሳራ ተይ ..ዛሬ የምንበሳጭበትና ራሳችንን ሀጥያት ለመሸፈን ሌላ ስው በሀሰት የምንወቅስበት ቀን አይደለም..እኔ አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከሁለት ሞት ነው የዳንኩት…ይሄ ያለምክንያት አይደለም..ይህቺን ልጅ ሁላችንም በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ በድለናታል…ሁላችንም ለእሷ መናዘዝ መቻል አለብን..እውነቱን ልንነግራት ይገባል..ከዛ አመዛዝና ከፈለገች ትበቀለን… ከፈለገች ደግሞ ወደፍትህ አደባባይ ወስዳ ታሰቅለን፡፡

የአቶ ፍሰሀን ንግግር የሰሙት ዳኛው ጫንቃቸውን አላባቸው፡፡ይሄ ሰውዬ በተገበጠበት ወቅት ጭንቅላቱን ተመቶ ማሰቢያው ላልቶ ይሆን እንዴ?››ሲል አሰበና አይኑን ገመዶና ጁኒዬር ላይ አንከራተተ…የሆነ ነገር ብለው የጀመረውን ቅዠት የመሰል ድርጊት እንዲያስቆሙት ነው ፍላጎቱ.
45👍4
‹‹ቆይ ….ለምንድነው የተሰወርሽው…..?እስከአሁን የት ተደብቀሽ ነበር?››ኩማንደሩ ነው ሲያስገርመው የነበረ ጥያቄ አለምን የጠየቃት፡፡
‹‹የት ነበርሽ ላልከው..እዚሁ ሻሸመኔ ውስጥ ነበርኩ፡፡ለምን ላልከው ግን ሳትቀድሙኝ ልቀድማቹሁ ነው…..ረሰሀው እንዴ አፍናችሁ ይርጋጨፌ ጫካ ውስጥ ልታኖሩኝ እየተዘጋጃችሁ ነበር እኮ››

ቤት ውስጥ ያሉት ወንዶች በአጠቃላይ እርስ በርስ ተያዩ‹‹ያንን እንዴት አወቅሽ?››
ከተቀመጠችበት ተነሳች..ወደኩማንደሩ ተጠጋች….ምን ልታደርግ ነው በሚል ሁሉም በትኩረት እየተመለከቷት ነው….እጇን ሰነዘረችና ደረት ኪሱ ውስጥ ያለውን ብዕር መዛ አወጣች…ትዝ ይልሀል…ይሄ የእኔ ብዕር ነው…ከኪስህ እንዳትለየው ስንገናኝ ትመልስልኛለህ ብዬህ ነበር…አሁን ስለተገናኘን ወስጄዋለው››

‹‹እ..አዎ የአንቺ ብዕር ነው… እና ምን ይፈጠር?››

‹‹ምን ይፈጠር ትላለህ እንዴ….ውይይታችሁን በጠቅላላ በድምፅ እየቀረፀ የሚያስተላልፍልኝ መሳሪያ ነበራ…..››አለችና በእርካታ ፈገግ ብላ ወደመቀመጫዋ ተመለሰች…ኩማንደሩ ራሱን በመከራ ነው የተቆጣጠረው..በህይወቱ በዚህ መጠን ማንም ተጫውቶበት አያውቁም፡፡

የተወስነ ደቂቃ ሁሉም በፀጥታ ተዋጠ..ከዛ ድንገት ጁኒዬር መናገር ጀመሩ‹‹እንግዲህ እወነቱን እኔ ልንገርሽ…ምክንያቱም በእናትሽ ሞት ዋናው ተጠያቂ እኔ ነኝ..በእኔ ምክንያት ቤተሰቦቼና ወዳጆቼ ከዚህ በላይ እንዲሰቃዩ አልፈቅድም….እናትሽ ከአወቅኳት ቀን ጀምሮ እስክትሞት ቀን ድረስ ከዛም አልፎ እስከዛሬ ድረስ በጣም አፈቅራታለው..በእሷ ልክ ማንንም ሴት ማፍቀር አልችልም..››ትንፋሽ ወሰደነ በጨረፍታ ስርጉትን ተመለከታት..ይሄንን ሲል ውስጧ እንዴት ፍርስርስ እንደሚል ያውቃል..ቢሆንም ምንም ለማድረግ አይችልም..፣ዛሬ አባቱ እንዳለው ንፅሁን እውነት የሚናገርበት ቀን ነው፡፡በምራቁ ጉሮሮውን አረጠበና ንግግሩን ቀጠለ‹‹ይሄንን ለአንቺም ከዚህ በፊት ደጋግሜ ነግሬሻለው፡፡በዛን ቀን ህይወቴ በማይነጥፍ ብርሀን የሚሞላ መስሎኝ ነበር…በደስታዬ መላዕክቶች የሚዘምሩበት ለሊት መስሎኝ ነበር፤ በህይወቴ ዋነኛው በረከትና የመትረፍረፍ ቀን ይሆናል የሚል ግምት ነበር የነበረኝ…እናትሽን እንድታገባኝ ለመጠየቅ የዳይመንድ ፈርጥ ያለበት ቀለበት በልዩ ትዕዛዝ አዘጋጅቼላት ነበር፡፡ቆይ እንደውም…..›› አለና የጃኬቱ ኪስ ውስጥ ገባና የገንዘብ ቦርሳውን በማውጣት ውስጡን ከፍቶ ከአንደኛው ኪስ በነጭ ጨርቅ የተጠቀለለ ነገር በማውጣት ከጨርቁ ፈልቅቆ ወደእሷ ተጠግቶ ፊቷ አስቀመጠው…‹‹ቦርሳውና የሚጠቀለልበት ጨርቅ ቢቀያየርም ይህ ቀለበት ግን ላለፉት 25 አመት ከደረት ኪሴ ተለይቶኝ አያውቅም…እና ይሄ የአልማዝ ፈርጥ ያለው ቀለበት ስላለኝ በተወሰነ መልኩ አብራኝ ያለች ይመስለኛል፡፡››ከግራ አይኑ የመነጨው እንባ በግራ ጉንጩ ላይ ሲንኳለል የተመለከተችው አለም ውስጦ በሀዘን ራደ…

‹‹እንደዛ አይነት ዝግጅት በሚኖረን ጊዜ ለዘበኞችና ለሌሎች አዳሪ ሰራተኞች እረፍት እንሰጣለን…በዛን ቀን ሰራተኞች ሁሉ ከአራት ሰአት በኃላ በየቤታቸው ሄደው ስለነበር..በግቢው ውስጥ ቤተሰብ ብቻ ነበር የቀረነው….በኃላ ቆይተን እንደተረዳነው ግን እኛ ሳናስተውል ስራ ላይ የነበሩ አንድ ሁለት ሰዎች ነበሩ..አንደኛው የእንስሳት ደክተሩ ሲሆኑ ሌለኛው ደግሞ የከብቶቹን ተንከባካቢ ጋሼ ሙስጠፋ ነበር፡፡

እና ለሊቱ ደማቅ ነበር..ዝግጅቱም ሁሉም ሰው የተገኘበት ውብ ነበር፡፡የጋብቻ ጥያቄውን ጠይቄ ቀለበቱን ላጠልቅለት ያሰብኩት ግን ሁሉም ሰው የእርባታ ግቢውን ለቀው ከሄዱ በኃላ ነበር… ቀደም ብለን እዛው ባለው ማረፊያ ቤታችን ውስጥ ለማደር ተስማምተን ስለነበረ ቤቱን በልዩ ሁኔታ እንዲሸበርቅ አድርጌ ነበር፡፡እኩለ ለሊት ትንሽ እንዳለፈ እኔ ከአባዬ ጋር እየተጫወትኩ ሳለው እሷ ከእማዬና ከስርጉት ጋር እቤት ውስጥ ሆነው እያወሩና እየተጫወቱ ነበር….እያንዳንዷን ነገር በግልፅ አስታውሳለው…ከዛ ለአባቴ ነገርኩት…ቀለበት ላጠልቅላት እንደሆነ እና በቅርብ ቀናት ውስጥ ላገባት እንደምፈልጋት እዛ እሳት ዳር ቁጭ ብለን ጨረቃዋን ወደሰማይ አንጋጠን እያየን ነገርኩት…መጀመሪያ ደነገጠ‹‹የልጅ እናት እኮ ነች ይሄ ነገር እንዴት ይሆናል?›› አለኝ?፡፡
‹‹የግድ መቻል አለበት…መንታ ልጆችም ይዛ ቢሆን እሷን እስካገኘው ድረስ ግድ የለኝም አልኩት….ከምሬ ነበረ…‹‹ትንሽ ተረጋግተህ ብታስብብበት አይሻልም ወይ?›› የሚል ሀሳብ አቀረበልኝ….

‹‹ከዚህ በላይ መጠበቅ አልችልም…በፍቅሯ ላብድ ነው›› አልኩት….‹‹እንደዛ ከሆነ ጥሩ…ለማንኛውም እኔ ከጨረቃዋ ጋር እያወራው ትንሽ መቆየት እፈልጋለው…እናትህን ወደቤት መሄድ ፈልጋለው እያለች ነበር ..ደግሞ ብርድ ነክቷት ሳሏ እንዳይነሳባት እቤት አድርሳት›› አለኝ….እሱን እዛው እሳት ዳር ተውኩትና ወደማረፊያው ቤቱ ስሄድ ሶስቱ ሴቶች ነጭ ወይን እየጠጡ በወሬ ተጠምደዋል….‹‹አባዬ ስለሚያመሽ ወደቤት ልውሰዳችሁ አልኳቸው››ሁለቱም ተስማሙ.. እናቴንና ስርጉትን በእኔ መኪና ይዤ ወደቤት ሄድኩ..እንደምታውቂው ቤታችን ከእርባታ ድርጅቱ አስር ደቂቃ ብቻ የሚርቅ ስለሆነ ብዙም አልቆየው …ወዲያው አድርሻቸው ስመለስ አባዬና እና ሰሎሜ በረንዳ ላይ ፊት ለፊት ቆመው እየተመነጫጨቁ ሲያወሩ ደረስኩ…አባዬ ያልሆነ ነገር ተናግሯት እቅዴን እንዳያሰናከልብኝ በጣም ፈራው..የእኔን መምጣት በመኪናዬ ድምፅ ሲሰሙ ድምፃቸውን ቀንሰው ሁኔታቸውን በፍጥነት አስተካከሉ… እኔ ግን ወዲያው ነበር የተረዳሁት ‹‹አባዬ ገና አራስ ሆነሽ ፤የሌላ ሰው ልጅ ይዘሽ ..እንዴት እንደዚህ በፍጥነት ልጄን ታገቢያለሽ ብሎ እያናገራት እንደነበረ እርግጠኛ ነበርኩ..፡እኔ እንደደረስኩ አባዬ ወዲያው በቅጡ እንኳን ሳይሰናበተኝ ወጥቶ ሄደ…ወደበረንዳው ተጠግቼ ሰሎሜን ሳያት በንዴት የፊቷ ስሮች ተግተርትረው በለቅሶ አይኖቾ ደፈራርሰው ሌላ ሰው መስላለች፡፡ተጠመጠምኩባትና አቅፌ ምን እንደሆነች ጠየቅኳት…እየተንሰቀሰቀች ከማልቀስ ውጭ ምንም ልትለኝ አልቻለችም…ነይ ከብርዱ ላይ ወደ ውስጥ እንግባ ብዬ ይዤት ወደውስጥ ገባውና አልጋው ላይ አስቀምጬያት ተመለስኩና በራፉንና መስኮቶቹን ዘጋጋው….፡፡

ስመለስ ስታለቅስ የነበረችው ልጅ ተንከትክታ እየሳቀች ነበር…ሳቋ ከለቅሶዋ በላይ ነበር ያስፈራኝ….‹‹.ምን ሆነሻል?››ስል ጠየቅኳት፡፡

‹‹ልታገባኝ ነው አይደል?››
‹‹አዎ..አባዬ ነገረሽ እና ሰርፕራይዜን አበላሸብኝ አይደል?››አልኳት
‹‹አዎ…..ቀለበቱ የታል?››ስትል ጠየቀችኝ፡፡አውጥቼ ሰጣዋት፡፡ አገላብጣ አየችው..እጣቷ ላይ አድርጋ ተመለከተችው…ተንከትክታ ሳቀች…..ከዛ ቀለበቱን አወጣችና መልሳ በእጄ አስጨበጠችኝ..በጣም ደነገጥኩ..‹‹ምነው..አልወደድሽውም እንዴ?››ስል በፍርሀት ጠየቅኳት፡፡
‹‹ይሄን መሰለ ውብ ቀለበት እንዴት ላልወደው እችላለው?››ስትል መለሰችልኝ፡፡

‹‹እና እኔን ነው የማትወጂኝ?››

‹‹አንተንም በጣም ነው ምወድህ…ቤተሰቦችህን ግን ….››አለችና ከተቀመጠችበት ተስፈንጥራ በመነሳት ፊት ለፊት ግድግዳ ላይ ከነበረ የቁም መስታወት ላይ በግንባሯ ተላተመች፡፡ የመስታወት መፈረካከስና ፍንጥርጣሪ በመላ ክፍሉ ተበተነ…ከእሷ ግንባር የሚፈሰው ደም በአካባቢው ተረጨ…የምገባበት ጠፋኝ…ዘልዬ ያዝኮትና ወደአልጋው መልሼ ላስቀምጣት ስሞክር… ከእኔ ለማምለጥ ስትንፈራገጥ እኔ አንሸራተተኝና ይዣት ወደቅኩ..ማለቴ ስንወድቅ እሷ ከስር ነበረች..ከዛ እንቅስቃሴዋ እየቀነሰ ፣ድምጻም እየጠፋ ሲሄድ ምን እንደተፈጠረ ግራ ገባኝና ለቅቄት ገለበጥኳትና ሳያት..
36😱4😢2