አትሮኖስ
286K subscribers
117 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

..የሞተ ተጎዳ እንዲሉ ከአደጋው መድረስ በኋላ ሳምንት እንኳን ሳይሞላ ሀዘን በረድ፤ ቀዝቀዝ እያለ ሄደ። ድንኳኖች ሁሉ ተነቃቅለው ወደ መጋዘን ተመለሱ፡፡ ሀዘንተኛ ሁሉ ወደ ሥራ ገባ፡፡ ከሩቅ የመጣ ሁሉ ወደየመጣበት ተመለሰ፡፡
እንባ ቆሞ በንፈር መምጠጥ ተተካ፡፡ መብረድ ቀርቶ ይባስ
እየተቀጣጠለ የሚሄደው በሽዋዩ ቤት ውስጥ የተነሳው እሳት ብቻ።

ሔዋን ስደት ላይ ነች፥ በታፈሡ ቤት፡፡ አስቻለዉን በተመለከተ
የተፈጠረባት ጭንቅና ሥጋት በልሁ ከወደ አዲስ አበባ የስልክ መልዕክት ካስተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ ቀለል ያለላት ቢሆንም የወደፊት አኗኗሯ ግን ጨለማ
ሆኖባታል። አስቻለው በደረሰበት አደጋ ምክንያት ወድ ክብረ መንግስት ያሰበችውን
ጉዞ ለጊዜው ትተዋለች። ግን ደግሞ ወደ ሸዋዬ ቤት መመለሻው መንገድ ይጨንቃታል። ሸዋዬ ለቤተሰቦቿ የፃፈችባት ደብዳቤም የጎን ውጋት ሆኖባታል።በስጋት እንቅልፍ አጥታ ተቸግራለች፡፡ መንፈሷም ዕረፍት አጥቷል።
ሽዋዬ በበኩሏ በተምታቱ ሀሳቦች ውስጥ ገብታ ራሷም ተምታቶባታል። በአስቻለው መትረፍ ባትከፋም ከመትረፉ ጋር ተያይዞ የሚመጣባትን አደጋ
ስታስበው እንደ ገደል ፈርተዋለች:: ሔዋን አስቻለው ቤት በማደራ ምክንያት የወሰደችባትን ርምጃ ሲመለስ መስማቱ አይቀርምና ምናልባት አስቻለውም
ተናድዶ፤ ሔዋንም ወደ ቤቷ ለመመለስ ፈርታ በዚህ አጋጣሚ ቢጠቃለሉስ? ሽዋዬ ከቅናት በተጨማሪ ያ የምትፈራው የማህበራዊ ህይወት ቀውስ በአቋራጭ ከች ሊልባት ነው:: ከዚህ አደጋ ማምለጫዋ መንገድ አንድ ብቻ ሆኗል! እስቻለው
ህክምናውን ጨርሶ ሳይመለስ ሔዋንን በዚያም በዚህም ብላ ወደ ቤቷ መመለስና በእጇ ማስገባት፡፡ ምንም እንኳ ቀልቧ የጠላቸው ቢሆንም ሔዋንን ከታፈሡ ቤት አምጥተው ለማስታረቅ የሚችሉ ወይዘሮ ዘነቡ ብቻ መሆናቸውን በማመን ተስፋዋን በእሳቸው ላይ ጣለች። ልክ አደጋው በደረሰ ሳምንት በዕለተ ሐሙስ ዓይኗን በጨው
አጥባ ወደ ቤታቸው ጎራ በማለት
«እማማ ዘነብ!» አለቻቸው።
«ወይ የኔ ልጅ»
«መቼም የሰሞኑን ጉዴን ሳይሰመት አይቀሩም»
«የምን ጉድ?» አሏት ሆዳቸው እየጠረጠረ ነገር ግን እሷው ትዘርዝረው በሚል ሐሳብ።
«እህቴን ከቤት እንዳባረርኩ አልሰሙም?»
«መስማቱን ሰማሁ ልጄ! ግን ምን አድርጋ ይሆን?» አሉና ጉንጫቸውን በእጃቸው መዳፍ ደገፍ አድርገው ያዩዋት ጀመር።
«በጣም በጣም ባለገችብኝ፡፡»
«እንዴት?»
ሽዋዬ የነበረውን ሁኔታ ሁሉ ዝርዝር አድርጋ ከነገረቻቸው በኋላ «ታዲያ ይኸ አያናድድም እማማ ዘነብ?» ስትል ጠየቀቻቸው።

ወይዘሮ ዘነቡ ለሽዋዬ ጥያቄ መልስ ከመስጠት ይልቅ በውስጣቸው ይጉላላ ለነበረው ሀሳብ መልስ ለማግኘት ሲሉ «አሁን ታዲያ የት ነው ያለችው!» ሲሉ ጠየቋት።

«አንድ ታፈሡ የምትባል መርዝ አለች፡፡ እሷ ጋር ሳትሆን አትቀርም፡፡»
ወይዘሮ ዘነቡ በሽዋይ አነጋገር ውስጣቸው ቅይም አለ፡፡ ታፈሡን
ያውቋታልና የመርዘኛነት ባህሪ እንደሌላት ያውቃሉ፡፡ ይልቁንም ሲያዩዋትም ሆነ ሲያነጋግሯት ደስ ትላቸዋለች፡፡ የተዋወቁትም እዚያው ሽዋዬ ጋ ስትመጣ በነበረበት ወቅት ነው፡፡ አሁንም የሆዳቸውን በሆዳቸው አድርገው፡-
«ያቺ ደርባባ ጓደኛሽ?» ሲሉ ጠየቋት፡፡
«አንዳች ያንደርባትና ሲያዩዋትማ ትመስላለች፡፡» አለችና ሽዋዬ ከንፈሯን ንክስ አድርጋ ወደ ሰማይ አንጋጣ ማየት ጀመረች። ወይዘሮ ዘነቡ ግን ታፈሡን ….ደርባባ የምትመስሰው፡ በማለት ብቻ ሊረኩ አልቻሉም፡፡ እንደው ጥሎብኝ እወዳታለሁ ልጄ! ከመልክ ቢሉ መልክ፣ ከጠባይ ቢሉ ጠባይ፣ ትትናውንም ሁሉ
አስተካክሎ አንድዬ የሰጣት እመቤት» በማለት ለታፈሡ ያላቸውን ትክክለኛ ስሜት
ከገለፁ በኋላ «ከአንቺስ ጋር ሰላም አልነበራችሁም ነበር እንዴ?» ሲሉ ጠየቋት፡፡
«በዚችው በእህቴ የተነሳ ተጣላን፡፡» አለቻቸው ወይዘሮ ዘነቡ ስለ ታፈሡ የሰጡት አስተየየት ሆድ ሆዷን እየቆጫት፡፡ «እሷ አይደለች እህቴን እንደ ዓይን
እልም አድርጋ ያጠፋችብኝ» ብላ ፊቷን ወደ ወይዘሮ ዘነቡ መሰስ በማድረግ «አሁን ሽማግሌ ሁኑኝ፤» አለቻቸው፡፡
«የምን ሽምግልና?»
ይቺኑ እህቴን ከተወሽቀችበት ጎትተው ቢያወጡልኝ ብዬ ነዋ!
ያለበለዚያማ ትምህርቷም መቋረጡ ነው::»
ወይዘሮ ዘነቡ አሁንም ጉንጫቸውን በመዳፋቸው ደገፍ አድርገው ረጋ ባለ አነጋገር «ሰማሽ ልጄ!» አሏት ከአንገታቸው ዘንበል ብለው እያዩዋት።

«እ»
«ከአንቺም በኩል ጥፋት አየሁ፡፡»
«ምን አደረኩ?» አለቻቸው ሽዋዬ ፊቷን ኮስተርተር በማድረግ እያየቻቸው፡፡
«መቸም ሁላችንም ልጅ ሆነን አድገናል። ልጅነት ደግሞ የተስፋ ዘመን ነው። ልጆች ሁሉን ነገር የሚያዩት በበጎ ነው። መስሎ የታያቸውን ነገር ከመፈጠም አይመለሱም። በተለይ ሴት ልጅ አንዴ እግሯ ከወጣ የልቧን ሳታደርስ አትመለስም::
ስለዚህ ዘመድ ነኝ የሚል ሰው ከፊት ከፊቷ እየቀደመ መንገዷን
ቢያመቻችላት ይሻላል እንጂ ተመለሽ ብሎ ከእሷ ጋር እልሀ መያያዝ… » ብለው ሳይጨርሱ ሸዋዬ አቋረጠቻቸው::
«አልገባኝም!» አለች ቆጣ ባለ አነጋገር፡፡
«ትዳር ሳትይዝ እንዳትጠንስ መላ መላውን መንገር፣ የወደደ ቢጠላት
ተበሳጭታ አንድ ነገር እንዳትሆን ማጥናናትና --» ብለው ሳይጨርሱ ሽዋዬ አሁንም ቀደመቻቸው
«ቁም ነገሩን ብናወራስ እማማ!»
«የማወራሽ ቁም ነገር መስሎኝ!» አሏት እሳቸወም መነፅራቸውን ወለቅ አድርግው አየት እያረጓት።
«ያ ሁሉ የሚሆነው በእጀ ስትገባ አይደል!?» አለቻቸው አስተያየታች
የንዴት መስሏት ደንገጥ እያለች።
«ቁም ነገሩ በእጅ ማስገባቱ ብቻ አይደለም፣ ተመልሳ እንዳትወጣ ማድረጉ ነው።ለነገሩ እህትሽም ዕድለኛ ሳትሆን አትቀርም፤ ከእጅሽ ብትወጣም መውደቂያዋ
ያማረ። ያ ልጅ ደግሞ ባለሙያና ረጋ ያለ የልጅ አዋቂ ነው፡፡ እንዳይለያዩ ድንግል ትርዳቸው እንጂ ሁሉቱም መልካም ልጆች ናቸው:» አሏት፡፡
ሸዋዬ የበለጠ ውስጧ ጨሰ፡ በሆዷ ላይ ይቺ ፈልፈላ አሮጊት አለቻቸው በወይዘሮ ዘነቡ ላይ ዓይኗን ስክት አድርጋ።
«ለመሆን የዚያች ጓደኛሽ ቤት የት ይሆን?» ሲሉ ወይዘሮ ዘነቡ በመሀል ጠየቋት። በዚህ ጊዜ ሽዋዬ ወደ ዋናው ቁምነገር የተመለሰላት መስሏት ልቧ ትንሽ
ተንፈስ አለና እኔ ወስጄ ከሩቅ አሳይዎትና እመለሳለሁ፡፡» አለቻቸው ትንፍሿ በርክቶ አፍንጫዋ ሳብ ረገብ እያለ፡፡
«ይሁን ደግ ልጄ፣ ትንሽ፣ ጠሐዩ በረድ ይበልና ሄጄ እሞክራለሁ::»
«እንደ ምንም ብለው ይዘዋት ይምጡ፣ አደራ!»
የዚያኑ ዕለት ከአመሻሹ አሥር ሰዓት አካባቢ ሽዋዬ ወይዘሮ ዘነቡን ከታፈሡ ቤት አካባቢ አድርሳቸው ወደ ቤቷ ተመለሰች። ነገር ግን የወይዘሮ ዘነቡ
አመለካከት ቅፍፍ አላት፡፡ ሔዋንን በእጇ የማስገባት ዓላማዋ ቢሰናከል ችግሩ የከፋ
እንዳይሆን ፈርታ እንጂ ሽምግልናቸውም ቢቀርባት በወደደች ነበር።
ወይዘሮ ዘነቡ ከታፈሡ ቤት ሲደርሱ ቀኑ አሥር ሠዓት አለፍ ብሏል።
ታፈሡና ሔዋን ሶፋ ላይ ቁጭ ብለው እንጀራ በትሪ አቅርበው ሲበሉ አገኟቸው።
አስቻለውን ለመጠየቅ አዲስ አበባ ሰንብተው ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ነው ከቤታቸው የደረሱት:: ቡናም እየተፈላ ነው፡፡እራት ነው ምሣ የምትበሉት?» እያሉ ወይዘሮ ዘነቡ ወደ ቤት ገቡ።
👍12
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


....የወይዘሮ ዘነቡና የታፈሡ ውይይት በዚህ መልኩ እየተከናወነ ባለበት ሰአት
ሸዋዬ አልጋዋ ላይ ቁጭ ብላ በሁለት እጇ ጆሮ ግንዶቿን ጠፍራ በመያዝና አተርትራ በማሰብ ላይ ናት። ታፈሡንና ወይዘሮ ዘነቡን እያሰበች ልክ በመሀላቸው ቁጭ ብላ እንደምታዳምጣቸው ዓይነት ስለ እሷ ሲያወራ በሀሳቧ "ቀንታ ነው እኮ ተቀጥላ ይስሟታል!
ሰው እንዴት በእህቱ ይቀናል! አረ የሷ የብቻው ነው ። አስቻለውን እንደሆነ አታገኘው ምን ያስለፋታል?» የሚሏት ይመስላታል። ወይዘሮ
ዘነቡ ታፈሡን ሲያሞካሹ!
ለአስቻለውና ለሄዋን ለሔዋን ፍቅር መልካም ሲመኙ እሷ በእሳቸው ፊት የምታሳየውን ድንጋጤና የብስጭት ስሜት ለታፈሡ ዝርዝር አድርገው ሲያወሩባት ሁሉ ይታያታል፡፡ በዚያ ልክ ቅጥል ንድድ ትችላለች፡፡
ወይዘሮ ዘነቡ ግቢያቸው ውስጥ እንዴግቡ ወደ ቢታቸው ጎራ ሳይሉ
በቀጥታ ወደ ጓሮ ዞረው ወደ ሸዋዩ ቤት አመሩ። ሸዋዬ ድንገት የሰው ኮቴ ሰምታ ከአጎነሰችበት ቀና ስትል ወይዘሮ ዘነቡ ብቻቸውን ሲመጡ አየቻቻው። ወደ
ኋላቸው ዓይኗን ስታማትር ሔዋን የለችም። እንዴ አለችና እማማ ዘነብ! » ስትል ጠራቻቸው ገና ከሩቅ ሳሉ፡፡
«ወይ»
«አልተሳካሎትም?»
ወይዘሮ ዘነቡ ዝም ብለዋት ወደ ቤት ገቡና ዱካ ላይ ቁጭ ካሉ በኋላ ትሰሚያለሽ የኔ ልጅ!» አሏት ቀልብና ስሜቷን ሰብሰብ ለማድረግ፡፡
«እሺ» አለቻቸው በጉጉትና በፍርሀት ስሜት ተውጣ፡፡
ጓደኛሽም እህትሽሃም መልካም ሰዎች ናቸው። እህትሽ ጥፋቷን አምናለች፡፡ጓደኛሽም ተቆጥታለች። አንቺ የፈለግሽውን እርቅ እነሱ የበለጠ ፈልገውታል፡፡
እውነተኛ እርቅ ደግሞ አፍን ሳይሆን ልብን ከፍቶ ስለሆነ፣ ለዚህ ብርቱ ጉዳይ አንቺም ስትዘጋጂ እደሪና ነገ ሁለታችንም አብረን እንሂድና አንቺንም ከጓደኛሽ፣ እህትሽንም ከአንቺ በማስታረቅ ሁሉንም ነገር ፈጥሠን እንመጣለን። ከዚያ በኋላ እህትሽን ይዘናት እንመጣለን፡፡» ከማለት ውጭ ሌላ ምንም ሳይጨምሩ
ከተቀመጠበት ብድግ ብለው በይ ደህና እደሪl» ብለዋት ውልቅ አሉ፡፡
ሸዋዬ ድንግጥ አለች፡፡ እንዴ አለች በሆዷ፡፡ በዓይኗ ወይዘሮ ዘነቡን
እየተከተለች ይቺ አሮጊትና ያቺ ታፈሡ የምትባል መናጢ ምን ተማክረው ይሆን?' በማለት ብቻዋን ታወራ ጀመር። ሄደች በሀሳብ አሁንም ታፈሡ ከኔ ጋር
ታርቀ ሰላ እያለች ወደ ቤቴ በመምጣት የጀመረችውን ልትጨርስ!? እኔ ሳላውቅ
ከዚች አሮጊት ጋር ገጥማ ውስጥ ለውስጥ ሊያርዱኝ? በፍጹም ይህ የማይሆን ነው። ከታፈሡ ጋር እርቅ ብሎ ነገር የለም፡፡ ብቻ ያቺ ሰላቢ እህቴ እንደምንም ብላ
በእጄ ትግባልኝ፡፡ ይህ እንዲሆን የግድ ከታፈሡ ጋር ታረቂ ብባልም ለዚያች ቀን ብቻ በማግስቱ ግን አፈርሰዋለው በቃ።
ሸዋዬ ምሽቱን ሁሉ ስለዚሁ ስታስብ ቆይታ ሌሊቱንም ሳትረሳው መልሳ መላልሳ ስታመነዥገው አደረች። ፍላጎቷ አንድ! ሔዋንን በእጇ ማስገባት፤ ፉከራዋም እንድ፤ ከታፈሡ ጋር ፈጽሞ ከልብ ላለመታረቅ። ሀሳቧ ሁሉ ከዚሁ ሳይርቅ ሌቱ ነግቶ በጠዋቱ ፈረቃ ስራ ገባች፡፡
ከሰዓት በኋላ በታፈሡ ቤት የተያዘው የቀጠሮ ሠዓት ደረሰና ከወይዘሮ ዘነቡ ጋር ወደ ታፈሡ ቤት ጉዞ ጀመሩ።
«እማማ ዘነብ!» ስትል ጠራቻቸው ከጎናቸው ሆና እየተራመደች
«ወይ»
«ለመሆኑ ታፈሡ እኔን ምን አደረገችኝ እለችዎት?»
«እረ እሷ እቴ! ምንም ያለችው ነገር የለም::»
«ታዲያ ከእሷ ጋር መታረቁ ለምን አስፈለገ?»
«በአንቺ ሆድ ውስጥ ያለ ነገር ሊኖር ይችላል ብዬ ነዋ!»
«እሱማ ብዙ አለ። ግን ዝም ነው የምለው፡፡»
«ያማ ቂመኝነት ነው:: የነገር ብዛት ባይጠቅምም የቂም ቋጠሮ ካልተፈታ እርቅ አይኖርምና ቅር ያለሽን ነገር አጠር አርግሽ መግለጥ ይኖርብሻል፡፡»
«እኔና እሷን ያቀያየመን እኮ ይሄው የእህቴ ጉዳይ ነው::»
ወይዘሮ ዘነቡ ድንገት ቁጥት አሉ፡፡ «የእህትሽ ጉዳይ የአንቺና የእሷ ጉዳይ አይደለም የራሷ ብቻ ነው:: በእሷ አታሳቡ፤ ተዋት!! አሉ ጠበቅ ባለ አነጋገር፡፡
«እንዴት እማማ ዘነበ? እኔማ የእህቴ ጉዳይ ያገባኛል::»
«ስለምታበያትና ስለምታጠጫት ተሆነ ተሳስተሻል። ሆድ የትም ይሞላል፡፡
ጭንቅላት ግን ነጣነት የሚያገኝበትን መንገድ ይፈልጋል፡፡ አትሞኚ »
«መረን ልቀቂያት ነው የሚሉኝ!»
«ተይ አንቺ ልጅ! ኋላ እንዳልጠላሽ! እህትሽን እንኳን አንቺ እኔ አውቄአታለሁ፡፡ ሥነስራት ያላት ጨዋ ናት፡፡ የሆዷን አይታ ድንግል ያን የመሰለ ጨዋ ልጅ ሰጥታተለች:: እንደኔ ቢሆን በእነሱ መሀል ባትገቢ ጥሩ ይመስለኛል፡፡»
አሏት ፈርጠም ባለ አነጋገር፡፡
ሽዋዬ ወይዘሮ ዘነቡን ክፉኛ ጠላቻቸው፡፡ ዛሬ ሔዋንን በእጇ የማስገባት ዓላማ ባይኖርባት ኖሮ በዚያ ሠዓት ወደ ቤቷ ምልስ ብትል በወደደች ነበር፡፡ ከዚያ
በኋላ ፀጥ እንዳለች ከታፈሡ ቤት በር ላይ ደረሱ፡፡
የታፈሡ ቤት እንግዳ ለመቀበል ተዘጋጅቷል። ወለሉ ተወልውሎ- ፏ ብሏል::ከሰል ተያይዞ የቡና ዕቃዎች ቀርበዋል። ታፈሡም እምር ብላለች። ቀላ ያለ ጉርድ
ቀሚስ በነጭ ሽሚዝ ለብሳ ሀብሏ በደረቷ ላይ እንደ ፀሐይ ያበራል፡፡ ያን ረጅም የጥቁር ዞማ ፀጉሯን ጎንጉና በጀርባዋ ላይ ለቃዋለች፡፡ ወይዘሮ ዘነቡ ሸዋዬን አስከትለው ወደ ቤት ራመድ ሲሉ ፈልቀቅ ባለ ፈገግታ ተቀበለቻቸው፡፡ በዚያ
ሠዓት ሔዋን ድንግጥ ብላ ወደ ጓዳ ስትሮጥ ወይዘሮ ዘነቡ ተመልክተዋት ኖሯል።
«ዛሬ ፈርቶ መደበቅ፣ እኩርፎ መንጋደድ የለም፡፡» አሉና መሀል ወለል ላይ ቆመው «በሉ እናንተ ቀድማችሁ በይቅርባይነት ያለ ወቀሳ ተሳሳሙ፡፡» አሏቸው
ታፈሡና ሸዋዬን ግራና ቀኝ አየት አየት እያረጉ፡፡ ታፈሡ ሁለት እጆቿን ዘርግታ ወደ ሸዋዬ ጠጋ በማለት «ሸዋዬ!!
ከአጠፋሁ ይቅርታ!» ብላ እንገቷን እቅፍ አድርጋ በመሳም ጨመጨመቻት፡፡
ወይዘሮ ዘነቡ አጠገባቸው ቆመው «እሰይ እሰይ እልልል…» አሉ፡፡
ወይዘሮ ዘነቡ ታፈሡ በዚያ ዓይነት ፈገግታ እየሳመቻት ሳለች የሸዋዬ
ፊት ግን ፈታ አለማለቱ እያናደዳቸው ነገር ግን የጀመሩትን ለመጨረስ ሲሉ፡ «በይ ያቺንም አበባ ጥሪልኝ፡፡ በእህቷ እግር ላይ ትወደቅ» ብለው ሔዋን ወዳላችበት ጓዳ አይናቸውን ወረወሩ።
«አንቺ ሒዩ» ስትል ታፈሡ ተጣራችና ቀጥላም ነይ እማማ ዘነብ ይፈልጉሻል» ስትላት ሔዋን ሽቁጥቁጥ እያለች ከወደ ጓዳ ብቅ አሉች፡፡ ለአንዴም ቀና ሳትል አቀርቅራ በመራመድ ከመሀላቸው ደረሰችና ከሸዋዬ እግር ላይ ወደቀች፡፡ወይዘሮ ዘነቡና ታፈሡም እልልእልል» በማለት ዕርቁን አደመቁት ።
ወይዘሮ ዘነቡ አሁንም ሆዳቸው በገነ ሔዋን ያን ያህል በእግሯ ላይ
ስትደፋ ሸዋዬ ግን ለመግደርደር ስትል እንኳ ቀና እንድትል አልጋበዘቻትም።በሆዳቸው ምኗ ድንጋይ ናት በማሪያም አሉ፡፡
የእርቅ ስነ ሥርዓት በዚህ ሁኔታ ተጠናቆ ሔዋን ብቻ ወደ ጓዳ ፈጥና ስትመለስ ሶስቱም ሶፋ ላይ ቁጭ አሉ የታፈሡ ሠራተኛ ቡና መቁላት ጀምራለች
«ሰላም ነሽ ሸዋዬ!» አለቻት ታፈሡ ቀድማ ፈገግ ብላ እያየቻት»
«እግዜሔርን አይክፋው»
«ሰሞኑን እንደተበሳጨሽ ይገባኛል ሔዩ አጥፍታለች» አለቻት ታፈሡ
👍131
#ምንትዋብ


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

....ምንትዋብ፣ ኢያሱ ራቱን እስኪበላና እስኪተኛ ጠብቃ እሷም በድንጋጤና በለቅሶ የደነዘዘ ሰውነቷን ለማሳረፍ ከጎኑ ጋደም አለች። አካሏ ዝሎ፣ መንፈሷ ረግቦ፣ እንቅልፍ በዐይኗ አልዞር አለ። አእምሮዋ በውስጡ ያለተራ ብቅ ጭልጥ የሚለውን የሐሳብ ውዥንብር መቆጣጠር ተሳነው። መላ የጠፋው አእምሮዋ ቢሰክንልኝ ብላ ከመኝታ ክፍሏ ወደ ሰገነቱ ከሚያወጡት ከሶስቱ በሮች በመካከለኛው በኩል አድርጋ ሰገነቱ ላይ ቆመች። ባሏም ብዙ ጊዜ በዛ በር እየወጡ፣ አንዳንዴም አብረው እየሆኑ ከተማውንና ግቢውን ይቃኙ ነበርና እንባ ተናነቃት።

ለሰባት ዓመታት ያህል ከእሳቸው ጋር ያሳለፈችውን ሕይወት
በሐሳቧ መለስ ብላ አየች። ንጉሠ ነገሥቱ እንደ ተራ ሰው እናት አባቷ
ቤት መደብ ላይ ተኝተው ያስታመመቻቸውን አስታወሰች። ምንትዋብ ብለው ስም ያወጡላት፣ “የኔ ዓለም” እያሉ ያቆላመጧት ሁሉ በየተራ ፊቷ ድቅን አሉባት። ምነው እንዲህ ዕድሜያቸውን አሳጠረባቸው?
አለችና ምርር ብላ አለቀሰች።

ከቤተመንግሥት ግቢ አሻግራ ጥቅጥቅ ባለው ጭለማ ውስጥ ጐንደርን ለማየት ሞከረች። ማታ ማታ ጐንደርን ያለ ከልካይ ከሚፈትሹት ጅቦች ሌላ የሚንቀሳቀስ ነገር የለም። አልፎ አልፎ ጅቦቹን ከሚያስፈራሩት
ውሾች ጩኸት በስተቀር ድምፅም አይሰማም።
ምንትዋብ ከጐንደር ወደ ራሷ ተመለሰች። ሕይወት ያልታሰበ
ፀጋ አምጥታላት መልሳ መንጠቋ ገረማት። የሕይወት መንገዶች
አለመጣጣማቸው ደነቃት። ሞት ሌላው የሕይወት ገፅታ መሆኑን
አሰበች። ሕይወት ምስጢሯን ያካፈለቻት መስሎ ተሰማት። ነገ እዛ ራሷ ረጋፊ መሆኗ በአእምሮዋ ተመላለሰና ዘገነናት። ለጊዜውም ቢሆን የመኖር ትርጉሙ ተናጋባት። የሙት ሚስት መሆኗ ወለል ብሎ
ታያት። ሞት ተስፋዋን ሁሉ ሸራረፈባት።

በዚያች ቅጽበት ሕይወቷ ዳግመኛ እንደተለወጠ ተረዳች።

መኝታ ክፍላቸው ስትገባ እንደገና እንባ አሸነፋት። ቤቱ የሚበላት፣
አልጋው ብቻዋን በመምጣቷ የሚታዘባት መሰላት። ለባሏ እንደሚገባቸው ያላዘነች፣ ያላነባች መስሎ ተሰማት። ቆም ብላ ክፍሉን ቃኘች። በርካታ
ትዝታዎች በአእምሮዋ ውስጥ ተመላለሱ። ወደ ኢያሱ ስትመለከት ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ላይ ነው። ሆዷ ባባ። አባቱን ሲሰናበታቸው ምን ተሰምቶት እንደሆነ መገመት አቃታት። እመንናለሁ ብላ የእሱን ሕይወት አደጋ ልትጥል እንደነበር አስታወሰችና ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። ተጠግታው ራሱን እያሻሸች፣ በዚች ምድር ላይ ካሉ ክፉ ነገሮች ሁሉ፣ከሞት ጭምር፣ ልትደብቀው እቅፏ ውስጥ ሽጉጥ አድርጋው ጋደም
አለች።

አእምሮዋ እረፍት አጥቶ እንቅልፍ በዐይኗ ሳይዞር ወፍ ተንጫጫ።
ተነስታ ወደ ሰገነቱ ወጣች። ሰማይና ምድር ገና አልተላቀቁም።
ጐንደርም ገና እንቅልፍ ላይ ናት። በቦዘዙ ዐይኖቿ ዙርያውን አየች።
የጠዋቱ ቅዝቃዜ ፊቷን ሲዳስሳት፣ ነቃ አለች።

አሻግራ ጐንደርን ወደከበቧት ተራሮች ተመለከተች። ፍም እሳት
የከበባት የምትመስለውን ፀሐይ ብቅ ስትል ስታይ የጥድፊያ ስሜት
ተሰማት። በመመርያ ኸዋና ዋናዎቹ ግቢ አዛዥና ኸሊጋባው፣
እንዲሁም ኸመሣፍንቱና ኸመኳንንቱ ጋር መክራለሁ። ጃንሆይ አገር አለ ምክር፣ ቤት አለ ማገር ይሉ ማልነበር? ኸዛ በኋላ፣ ኢያሱ በምሥጢር ይነግሣል። የልጄቼን አልጋማ ለማንም አሳልፌ አልሰጥም

ለካንስ እሷም መንገሷ ነው! ደነገጠች።

ይህ ሳይታሰብ እላይዋ ላይ የወደቀው ኃላፊነት ከየት እንደመጣ ማወቅ አቃታት። ሃገር ልታስተዳድር መሆኑ ሲገባት ታላቅ የኃላፊነት ስሜት ተጫጫናት፡፡ እሳቸው ያሰቡትን ሁሉ ሳያሳኩ አለፉ፤ እኔስ ብሆን መቸ እንደምሞት በምን አውቃለሁ? ሞት እንደሁ ለማንም አይመለስ፡ ብቻ እንዳው አንዴ የሳቸውን ቀብርና የልጄን ንግሥ
ያለምንም ሳንካ ላሳካ እያለች አእምሮዋ ውስጥ የሚወራጨውን ሐሳብ ሁሉ በየፈርጁ ማስቀመጥ ሞከረች።

ድንገት ክፉኛ የመንገሥ ፍላጎት አደረባት። ባሏ፣ “እሷ አገር
ማስተዳደር ትችላለች” ያሉት በከንቱ እንዳልሆነ፣
ስለቤተመንግሥትም ጉዳይ ቢሆን ላለፉት ሰባት ዓመታት በቂ
እውቀት እንዳካበተች፣ በደጉ ጊዜ ቤተመንግሥት ውስጥ ቦታቸውን
ያመቻቸችላቸው የኒቆላዎስ፣ የወልደልዑል፣ የአርከሌድስና
የሌሎቹም መኖር ታላቅ ድጋፍ እንደሚሆናት ተረዳች። ኒቆላዎስ
እያረጀ በመምጣቱ፣ ወንድሟ ወልደልዑል ጉልህ ችሎታ በማሳየቱና ቤተመንግሥት ውስጥ የማይናቅ አስተዋጽኦም በማድረጉ ቀኝ እጇ ሊሆን እንደሚችል አመነች። ዐዲስ ማንነት ውስጧ ሲጠነሰስ ተሰማት።

ከፍተኛውን የሥልጣን ዕርከን ስትወጣ ታያት።

ልቧ መታ፤ መላ ሰውነቷ ተቅበጠበጠ። ዳግም የጥድፊያ ስሜት ተሰማት። ይህንን ዕድል ለማንም አሳልፋ ልትሰጥ እንደማትችልና የኢያሱን ሆነ የራሷን ንግሥ ለማስከበር በችሎታዋና ሥልጣንዋ ስር ያለውን ሁሉ ማድረግ እንዳለባት ለራሷ አስገነዘበች። አሁን ፊቷ ተደቅኖ
የሚታያት ምኞት ወይንም ተስፋ ሳይሆን በቅርብ ያለ፣ሊጨበጥ የሚችል በመሆኑና ከለቀቀችው፣ ካመነታች እዳው ለእሷ ብቻ ሳይሆን ለልጇ ጭምር በመሆኑ በአስቸኳይ እርምጃ መውሰድ
እንዳለባት ተረዳች።

እኔም ኢያሱም ኸነገሥን በኋላ፣ ኣመጥ እንዳይኖር ጥርጣሬ
አስወግጀ ሰዉ እኔ ላይ አመኔታ እንዲኖረው ማረግ አለብኝ። መቸም መልካም ሥራ ኸሠራሁና ጥሩ አርጌ ኻስተዳደርሁ ሰዉ ይደግፈኛል::እምነትም ይጥልብኛል አለች፣ ሞላ ባለ ልብ። ከሁን ታሪክ የምትሠራበት፣ ስሟን ካለፉት ነገሥታት ተርታ የምታሰልፍበት ወቅት
እንደተቃረበ አስተዋለች። ሃገሯ ታላቅ ጥንካሬ፣ ዘዴ፣ ቆራጥነትና
ቀናነት እንደምትጠብቅባት ተረዳች።

ከሐሳቧ ስትነቃ ምድር ለቋል፤ ጐንደር ብርሃን ለብሳለች፤ ነፍስ
ዘርታለች። ። ጐንደርን ለመጀመሪያ ጊዜ በተለየ ዐይን አየቻት። ጐንደር
ጐንደር! አለች፣ በለሆሳስ፡ ፊቷን እያዟዟረች ከተማዋን የከበቡትን
ሰንሰለታማ ተራራዎች ትክ ብላ አየቻቸው። በተፈጥሮዋ የጠላት
መከላከያ አላት አለች። እንደገና ከተማዋን ከላይ ወደታች ቃኘች።
ጐንደር... ያቺ የነገሥታቱ፣ የመሣፍንቱና የመኳንንቱ የትንቅንቅ ቦታ ሳትሆን የተለየች ጐንደር ሆና፣ እንባዋን ጠራርጋ ወጣ ገባ ስትል ታየቻት። የዕድል ማሳ ሆና እሷ ማሳው ላይ ስትዘራ ጐንደር ስታብብ፣ስታፈራ፣ ይበልጥ ገናና ስትሆን ታያት።

በራሷ አምሳል የቀረጸቻት ጐንደር ፊቷ ወለል አለች።

ጐንደርን በጃን ተከል በኩል ለማየት ወደ ላይኛው ሰገነት በደረጃ ወጣች። የሁሉ መኖሪያ፣ ሁሉን እንደ ሃይማኖቱ፣ እንደ ሙያውና እንደ ልማዱ የምታስተናግደውንና፣ መንፈሰ ለጋሷን ጐንደርን እንደ
ዐዲስ ወደደቻት፤ ከክፉ ልትታደጋት ፈቀደች። ምን ዓይነት ቦታ እንደሆነችና ሕዝቧም ምን ዓይነት እንደሆነ ይበልጥ ማወቅ ፈለገች።

ልክ በዛን ሰዐት የእሷም የጐንደርም ዕጣ የተለየ አቅጣጫ ያዘ።

እንዴ! አገሬ? አገሬስ? ጐንደር አላገር ትኖራለች እንዴ? አለች
ደረቷን እየመታች። አገሬ ውስጥ ሰላም አምጥቸ እኼ ነው ምኞቴ
አለች፣ ባሏ የነበረባቸውን ዓመጽ አስባ። ሃገሯን ልትታደጋት፣
ልታረጋጋት፣ ሰላም ልታሰፍንባት ወሰነች።

የደብረብርሃን ሥላሤ ደወል ሲደወል ከሐሳቧ ነቃች፣ ተረበሸች።

ደወሉ ለአባታቸው ለአፄ አድያም ሰገድ ኢያሱ ከሆላንድ ንጉሥ
የተላከ ነበርና ንጉሠ ነገሥቱ ደወሉን ሲሰሙ ከእንቅልፋቸው ብንን ብለው ሲያማትቡ፣ ተነሥተው ዳዊታቸውንና ውዳሴ ማርያማቸውን ሲደግሙ ፊቷ ላይ ድቅን አለ። አየ ያ ሁሉ ቀረ አለችና እንባዋን ጠራረገች።
👍132
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር


...«ዛሬ እንዳትለየኝ አለችኝ
እቅፍ አደረግኳት። ብዙ ነገር ልነግራት ፈለግኩ። ግን የመናገር
ጊዜ አልነበረም፡፡ እንደተቃቀፍን እንቅልፍ አቀፈን .

ቀኑን በብዙ ስትስቅና «ዥማንፉ» የሚለውን ፈረንሳይኛዋን
ስትደጋግም ዋለች፡፡ እኔ አንድ የሆነ ነገር በምመለከትበት ጊዜ እሷ ያላወቅኩባት መስሏት ስትመለከተኝ ብዙ ጊዜ ተሰማኝ፡፡ እንደዚህ ስትመለከተኝ፣ አንድ ሁለት ጊዜ ድንገት ዘወር ብዬ አየኋት ያዘነና የናፈቀ ገፅታ አየሁባት፡ በአይኗ እንደምትጠጣኝ ይመስል ነበር፡፡ የማላውቀው እፍረት ተሰማኝ። ይህን ያህል የሚወደድ ምን አለኝና ነው?

ማታ ከእራት በኋላ «ለቫር ሳን ሚሼልኦ ወሰድኳትና አንድ
ሁካታ ያነሰበት ካፌ ገብተን ቢራ ካዘዝን በኋላ፣ እጄን ዘርግቼ
ጉንጫን አየዳሰስኩ
«ዛሬ ምን ሆነሻል?» አልኳት
«እኔ እንጃ፡ አዝኛለሁ። እዝን ብያለሁ» አለችና፣ እጄን በሁለት
እጇ ይዛ ሳመችው:: አሁንም እፍረት ተሰማኝ። እጄን መሳሟ
ሳይሆን አሳሳሟ
«አውራልኝ አለችኝ
«ስለምን ላውራልሽ?»
«ስላንተ። ዛሬ ውስጤ አንድ ትልቅ ቀፎ ተከፍቷል፡ ባዶውን
ነው፡፡ ባንተ ልሞላው እፈልጋለው:: ከልጅነት ጀምሮ አውራልኝ።
ምንም ሳታስቀር በሙሉ ንገረኝ፡፡»
ጧት ልነግራት ፈልጌ የነበረውን ነገርኳት። ፍርሀቴን፣ ስጋቲን፣
ጭንቀቴን ዘረዘርኩላት። ስጨርስ አንድ እጄን እያሻሽች
«ውይ የኔ ካስትሮ! ሰው ነህ ለካ!» አለችኝ፡፡ በሊላው እጄ ፀጉሯን እየደባበስኩ
«ምን መስዬሽ ኖሯል?» አልኳት
«የማትፈራ፣ የማትጨነቅ፣ የማትታመም፣ የማትሞት መስለህ
ነበር ምትታየኝ፡፡ አትሳቅብኝ! ሰው እንደመሆንህ፣ ሟች መሆንህን
አውቅ ነበር። ግን እውቀት ዋጋ የለውም፡፡ ስሜት ነው ዋናው፡፡
ስሜቴ ደሞ ስላንተ ሌላ ነገር ነበር የሚነግረኝ፡፡ ተው አትሳቅ
እየው፤ እንዲህ አስበው እስቲ።
ጊ ደ ሞፓሳን የደረሰውን
«ቤል አሚ» የተባለውን ልብወለድ ታሪክ አንብበህ የለ? ቤል አሚ
እጅግ የተዋበ፣ ሽንቅጥ የሆነ ጎረምሳ ነው። ታስታውስ የለ፣ መፅሀፉ የሚያልቀው፥ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሄ አይናማ ጎበዝ በብዙ ሰው እየተደነቀ፣ ሀብታሟን ልጅ ሲያገባ ቄሱ ወዳሉበት ሲራመድ ነው።
ታድያ ቤል አሚን ባስታወስከው ጊዜ፤ ሲያረጅ ወይ ሲታመም ወይ
ሲሞት አስበኸው ታውቃለህ? ሁልጊዜ ወጣት እንደሆነ አይደለም የሚታይህ? . . እንደሱ ነው አየህ፡፡ ሳስብህ፣ ዘለኣለም ወጣት፣ ዘለአለም ጤነኛ ዘለአለም ኩሩ ሆነህ ነበር የምትታየኝ»

«አሁን ግን ሰው ሆነህ ትታየኝ ጀመር፡፡ ጧት እንደነገርኩህ!
ማንም ሰው፣ ምንም ነገር ሊያሸንፍህ የማይችል ይመስለኝ ነበር፡፡ የብረት ሰው ትመስለኝ ነበር። አሁን ግን እንደ ቢራቢሮ ሆነህ ነው የምትታየኝ። በጣም ቆንጆ ነህ፣ ነጭ ፈገግታህ ጥቁር ፊትህ ላይ ሲያበራ፣ አልማዝ መሳይ አይኖችህ በሳቅ ብልጭ ብልጭ ሲሉ ወይም በምኞት ሲግሉ፣ በወጣትነት ፀሀይ ውስጥ የሚበር ውብ ቢራቢሮ ነህ። እንደ ቢራቢሮ በቀላሉ የምትጠፋ ነህ። ከዚህ ወጥተን መንገድ ስንሻገር መኪና ቢገጭህ ትሞታለህ፣ በባቡር ስንሄድ ከሌላ ባቡር ጋር ብንጋጭ ትሰባበራለህ፣ በኤሮፕላን ብትበር፣ እና
ኤሮፕላኑ አንድ ነገር ቢሆን፣ እንደ ወረቀት ትቦጫጨቃለህ፡፡
አንዲት ጥይት ብትመታሀ ትሞታለህ፡፡ ...»
«አይዞሽ አይዞሽ»

«ምን አይዞሽ ትለኛለህ? መሞትህ ነው ። አይታይህም?»
ሌላውም ይሞታል ኮ፡፡ አንቺም ጭምር»

ሌላውን የት አውቀዋለሁ? ምኔ ነው? አንተ ግን አንተ ነህ፡፡
ማንንም አትፈራም፡፡ እንደ ሲራኖ ደ ቤርዤራክ ነህ፡፡ ጀግና ነህ።
ወንድ ነህ። የኔ ነህ። እወድሀለሁ፡፡ የኔን የራሴን ማርጀትና መሞት
በሀሳቤ ልቀበለው እችላለሁ፡፡ አንተ ታረጃለሀ ትሞታለህ ቢሉኝ ግን አልቀበልም፡፡ ይሄ አንፀባራቂ ፈገግታህ ሲጨልም፣ እነዚህ ብሩህ አይኖችህ ሲፈዙ ለማየት አልፈልግም፡፡ አልቀበልም፡፡ እምቢዮ! ኤክስ ውስጥ ፀሀይ እየሞቁ በባዶ ብርጭቆ አይን ሞታቸውን ከሚመለከቱት ሽማግሌዎች አንዱ እንድትሆን እልፈቅድልህም፡፡
አልፈቅድልህም! ይገባሀል? አልፈቅድልህም! ወጣት መአዛህን
ወስደው የእርጅና ሽታ ሲለጥፉብህ እንዳትቀበል!»

«እሺ የኔ ቆንጆ፣ እሺ ይቅር፣ ረጋ በይ አይዞሽ። አሁን
ወጣት ነኝ፣ ካንቺ ጋር ነኝ»
«አሁን ብቻ ነዋ!»
«አሁን ብቻ አይደለም፡፡ አይዞሽ አይዞሽ»
«ከዚህ ውሰድኝ»
«እሺ»
«ውሰደኝና ልብሴን አውልቀህ እቅፍ አርገኝ። ከድሮ ይበልጥ
እቀፈኝ፡፡ ፍርሀት ይዞኛል፣ ሀዘን ተጫጭኖኛል፡፡ መወደድ መታቀፍ
እፈልጋለሁ፡፡»
«እሺ የኔ ሲልቪ»
«እንሂዱ»
«እሺ»
«በል እንሂድ»
«እሺ የኔ ፍቅር፣ ይኸው መሄዳችን ነው።»
ሆቴላችን እንደደረስን፣ ቶሎ ልብሷን አውልቄ እቅፍ አረግኳት
«እወድሻለሁ የኔ ፍቅር፣ ከልቤ እወድሻለሁ» አልኳት
«በላ አሳየኝ፣ በስጋህ አሳየኝ፣ በነብስህ አሳየኝ
«ይኸው የኔ ፍቅር፣ ይኸው»
በጭለማው፣ በሹክሹክታ
«አማልክቱ ሁሉ ሞተዋል፡፡ እኛ ብቻ ነን የቀረነው:: አንተ ለኔ
አምላኬ ነህ። እኔስ አምላክህ ነኝ?»
«አዎን አምላኬ ነሽ»
«ድገምልኝ»
«አምላኬ ነሽ፡፡ አምላኬ ነሽ፡ የኔ አምላክ ነሽ»
አፌ ውስጥ እየተነፈሰች «በላ መስዋእት አቅርብልኝ»
«እሺ። ምን መስዋእት ትፈልጊያለሽ?»
«ሁልጊዜ ከላይ ሆነህ ወደታች ታየኛለህ፡፡ ዛሬ ታች ውረድና
እኔ አዘቅዝቄ ልመልከትህ ክብርህን ሰዋልኝ»
«እሺ፡፡ ክብሬን ውሰጂው:: ላንቺ ክብሬን ብሰዋ ደስ ይለኛል።
በጭለማው በሹክሹክታ
«በላ»
«እዘዢኝ»
«እንዳታመነታ ልባርግ»
«ዝግጁ ነኝ፡፡ ንገሪኝ፡፡ ምን ላርግሽ? ምን ልሁንልሽ?»
«ወደታች ውረድና ከእግሬ ጥፍር ጀምረህ እየሳምከኝ አየላስከኝ
ወደላይ ና፡፡»
«እሺ የኔ መቤት»
ከእግሯ ጥፍር ጀምሬ እስከ አፏ ሳምኳት ላስኳት። በአፉ
ተቀበለችኝና እየሳመችኝ፣ በጭለማው በሹክሹክታ
«ጥሩ ነበር፣ ግሩም ነበር፡፡ ግን አይበቃም። በጭራሽ
አይበቃኝም» አለችኝ
«የፈለግሽውን ንገሪኝ። አደርገዋለሁ፡፡ አምላኬ ነሽ»
«እንዴት ነው ጭኖቼ መሀል ስመኘኝ የማታውቀው?»
«አድርጌው አላውቅማ»
«በጭራሽ አርገኸው አታውቅም?»
«በጭራሽ»
«በጭለማው፣ በሹክሹክታ
ውረድና ጭኖቼ
ሳመኝ። ልክ አፌን
እንደምትስመኝ አርገህ ሳመኝ፤ በከንፈርህ፣ በጥርስህ፣ በምላስህ
ሳመኝ፡፡ አምላክህ ነኝ፡፡ ካንተ ምፈልገው መስዋእት እሱ ነው::»
«እሺ»
ሳረገው አልቀፈፈኝም፡፡ በጭራሽ አልቀፈፈኝም፡፡ እንዲያውም
በጣም ነው ደስ ያለኝ። ስስማት፣ በማክበርና በማምለክ ስስማት፣
እያቃሰተች ራሴን ስታሻሽ ቆይታ ቆይታ፣ በጭንቅላቴ ስባ ወደ ላይ
ወሰደችኝና
«ትወደኛለህ፡፡ በእውነት ትወደኛለህ፡፡ እንዴት ግሩም ነው!
ትወደኛለህ፡፡ አንተ እኔን ትወደኛለህ!» አያለች ስታቃስት
«አይዞሽ አይዞሽ፣ ያንቺው ነኝ» እያልኩ አባበልኳት
«እንዴት እድለኛ ነኝ! እንደ ዛሬ ደስ ብሎኝ ኣያውቅም»
«ገዝተሽኛል»
«ገዝቼሀለሁ። እወድሀለሁ፡፡ አንተም ገዝተኸኛል። እንዴት ጥሩ
«አሁን ተኚ። ደክሞሻል፡፡»
«እሺ፣ አቅፈህ አስተኛኝ።»
ከትንሽ ዝምታ በኋላ
«እንደዚህ ጥሩ ልጅ ሆነህ ሽርሙጣ መውደድህ አያሳዝንም?»
👍21😁1
#ምንዱባን


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


ለሞተ ሰው የገቡትን ቃል ማክበር

ሞንትፌርሜ የተባለ ከተማ የሚገኘው ከኮረብታ ላይ ሲሆን የከተማው ሕዝብ ውሃ ችግር አለበት፡፡ ውሃ ለማግኘት ሴቶች ራቅ ካለ ሥፍራ ይሄዳሉ፡፡ ከከተማው ራቅ ብሎ ከሚገኘው ጫካ ውስጥ ብዙ ኩሬዎች
ነበሩ፡፡ ከኩሬዎቹ ደግሞ ራቅ ብሎ የከተማው ሕዝብ የሚጠቀምበት
ምንጭ አለ፡፡ ምንጩ ያለበት ቦታ ከከተማው ቢያንስ አሥራ አምስት ደቂቃ ያስኬዳል፡፡

ስለዚህ በሞንትፌርሜ ከተማ ለአንድ ቤተሰብ የሚያስፈልገውን ውሃ ማሟላት ቀላል ሥራ አልነበረም፡፡ ሀብታሞች የመንግሥት ባለሥልጣኖችና
የእነቴናድዬ ሆቴል ቤት ባለቤቶች ውሃ እየገዙ ነበር የሚጠቀሙት:: አንድ ባልዲ ውሃ በአንድ ፔኒ ይገዛሉ፡፡ ውሃውን የሚሸጥላቸው አንድ ሽማግሌ ነው:: ሽማግሌው ውሃ ልማት መሥሪያ ቤት ውስጥ ሥራ ቢኖረውም ደመወዙ በጣም አነስተኛ ስለነበር ኑሮውን ለማሟላት ከተጠቀሰው ምንጭ
ውሃ እየቀዳ ይሸጣል፡፡ ሰውዬው አንዳንድ ቀን በጣም ከመሸ በኋላ እንኳን በጨለማ ውሃ ለመቅዳት ይሄድ ነበር ይባላል::

የሽማግሌው የኑሮ ውጣ ውረድ ምናልባት አንባብዬ ካልረሳት ከኮዜት የተለየ አልነበረም:: ኮዜት እነቴናድዬን በሁለት መንገድ ነበር
የምትጠቅማቸው:: ከእናትዋ ገንዘብ ይላክላቸዋል፡፡ በተጨማሪም ልጅትዋ
እቤት ውስጥ በሥራ ትረዳቸዋለች:: ምንም እንኳን የኮዜት እናት ገንዘብ መላክዋን ብታቋርጥም ኮዜትን ከቤታቸው እንዳላበረርዋት ቀደም ሲል
አንብበናል፡፡ ያላባረርዋት ሠራተኛ ከመቅጠር ስላዳነቻቸው ነበር፡፡ እቤት ውስጥ ውሃ ሲያልቅ ውሃ ለመቅዳት ወደ ምንጩ ትሄዳለች:: ማታ ማታ በጨለማ ወደ ምንጩ መሄድ በጣም ስለሚያስፈራት ውሃ ከመሸ እንዳያልቅ በጣም ትጠነቀቅ ነበር፡፡

በ1923 ዓ.ም የገና በዓል በሞንትፌርሜ ከተማ በጣም በደመቀ ሁኔታ ይከበራል፡፡ ሰው ሁሉ ከየቤቱ ወጥቶ መሸታ ቤቶችን ያደምቃል፡፡ በገናው
ዋዜማ ከነቴናድዬ ሆቴል ቤት ብዙ ጠጪዎች ሻማ በርቶላቸው ይጠጣሉ።ጫጫታው፣ ግርግሩ፧ ሁካታውና የሲጃራው ጭስ ሌላ ነው:: የሚስተር ቴናድዬ ባለቤት እራት እየሠራች ነበር:: ሚስተር ቴናድዬ ከጠጪዎች ጋር
አብሮ እየጠጣ የፖለቲካ ወሬ ያወራል፡፡

ኮዜት ዘወትር ከምትቀመጥበት ከእሳት ማንደጃ አጠገብ የተቀደደ
ልብስ ለብሳ ቁጭ ብላለች:: ከሚነደው እሳት አጠገብ ቁጭ ብላ ለእነቴናድዬ ልጆች ሹራብ ትሠራለች፡፡ አጠገብዋ አንዲት ትንሽ ድመት ከወንበር ስር
ብቅ ጥልቅ እያለች ትጫወታለች፡፡ ከሚቀጥለው ክፍል ውስጥ የሚጫወቱት ልጆች ሳቅና ጨዋታ በጉልህ ይሰማል:: የእነቴናድይ ልጆች ነበሩ ከክፍሉ ውስጥ የሚጫወቱት

ከጭስ መውጫው አጠገብ የለፋ የበሬ ቆዳ ተንጠልጥሏል፡፡ የሕፃን
ልጅ ለቅሶ መጠጥ ቤት ውስጥ የነበሩ ሰዎች ጫጫታን ዘልቆ ይሰማል፡፡ ክረምት ከመግባቱ በፊት የተወለደ ሕፃን ሲሆን «ብርዱ ስላየለበት ሳይሆን
አይቀርም የሚያለቅሰው» አለች እናቱ፡፡ እናቱ “እሹሩሩ» እያለች አባበለችው፡፡አሁንም ሕፃኑ እያመረረ ሲያለቅስ ጊዜ «ምነው ይህን ልጅ አንድ ብትዪው»
አሊ ሚስተር ቴናድዬ::

እባክዎን ይተውት! ስልችት ነው ያለኝ» አለች እናቱ፡፡፡ ልጁ ማልቀሱን ቀጠለ፡፡

አራት እንግዶች ገቡ፡፡

ኮዜት ተክዛ ቁጭ እንዳለች ነው:: ምንም እንኳን እድሜዋ ገና
ስምንት ዓመት ቢሆንም ሁኔታዋና አመለካከትዋ የአሮጊት ይመስላል:: «አሁን እንግዲህ ለእንግዶቹ እግር መታጠቢያ የሚሆን ውሃ አምጪ ሊሉኝ
ነው ፤ እንስራ ውስጥ ያለው ውሃ እንደሆነ አልቋል› በማለት ኮዜት
አሰላሰለች::

ወዲያው ከአንግዶቹ መካከል አንደኛው መጥቶ «ምነው ለፈረሴ
ውሃ ሳትሰጡት» ይላል፡፡

«ምነው ተሰጥቶት» አለች ሚስስ ቴናድዬ::

«የለም፣ አልተሰጠውም» ሲል እንግዳው ተከራከረ::

ኮዜት ከተቀመጠችበት ተነሳች::
«ምነው ጌቶች» አለች:: «ፈረሱ እንደሆነ ጠጥቷል፡፡ ባልዲ ሙሉ
ውሃ ሰጥቼው ጠጥቷል:: እኔ ነኝ ደግሞ የሰጠሁት::»

የተናገረችው ልክ አልነበረም፤ ኮዜት እየዋሸች ነበር፡፡

«ይህች ከእኔ ጭብጥ የማትበልጥ አንዲት ፍሬ ሕፃን ልጅ የምታወሪው ቅጥፈት ከጋራ ይበልጣል አለ መንገደኛው:: እመኑኝ ፈረሴ አንድ እፍኝ
ውሃ እንኳን አላገኘም:: ውሃ ሲጠማው የሚያሰማውን ድምፅ በትክክል አውቀዋለሁ::»

ኮዜት ሳታመነታ ቅጥፈትዋን በመቀጠል ማስተባበያዋን በጣም በደክመ ድምፅ ተናገረች፡፡

«ግን እኮ ብዙ ውሃ ነው የጠጣው::»
«በይ ነይ» አለ መንገደኛው:: ‹‹በቃሽ ብዙ አትለፍልፊ:: ለፈረሴ
ዓይኔ እያየ ውሃ ስጪው፤ ድርቅናሽን ግን ብትተዪው ይሻላል፡፡»

ኮዜት ቀደም ሲል ተቀምጣበት ከነበረው ጠረጴዛ ስር ሄዳ ቁጭ
አለች::

«ትክክል ነው፤ ፈረሱ ውሃ ካላገኘ ውሃ እንዲሰጠው ይገባል» አለች
ሚስስ ቴናድዬ::

ከዚያም በዓይንዋ አካባቢውን ቃኘች::

«ይህቺ ልጅ የት ሄደች?» ስትል ጠየቀች::

ከጠረጴዛ ስር ተወሽቃ አየቻት::
«ምን አባሽ ይወሽቅሻል፧ በይ ነይ ውጪ» ስትል ጮጮኸችባት::

ኮዜት ተነሳች ፣ የጠጪዎችን እግር ረግጣ ሌላው ደግሞ
እንዳይጮህባት እየተጠነቀቀች ተራመደች::

ሚስስ ቴናድዬ ጩኸትዋን ቀጠለች::

«አንች ውሻ» አሁን ቶሎ ብለሽ ለፈረሱ ውሃ እንድትሰጪው::

«ግን እሜቴ» አለች ስትፈራ ስትቸር፤ «ውሃው እኮ አልቋል::
«ታዲያ ወደ ምንጩ ቶሉ ወርደሽ ቀድተሽ አትመጪም!» ካለች
ቦኋላ በሩን ከፈተችላት::
ኮዜት ጭስ ቤት የነበረውን ባልዲ ይዛ ወጣች፡፡ የባልዲው ውፍረትና
ቁመት ከእርስዋው ቁመት ይበልጥ እንደሆነ ነው እንጂ አያንስም:: ከውስጡ ገብታ ተመቻችታ ለመቀመጥ ትችላለች::
ሚስስ ቴናድዬ የምትሠራው ሾርባ በስሎ እንደሆነ ለማየት የእንጨት
ማማስያውን ነክራ አውጥታ እያጉረመረመች ላሰችው::
«የምንጭ ውሃ እኮ ሾርባ አያጣፍጥም፤ ወይስ ይህቺ የተረገመች ልጅ ምናምን ትጨምርበት ይሆን! ወይስ ሽንኩርት አሳንሼው ነው!»
ኮዜት ባልዲውን ተሸክማ እንደቆመች፧ በሩም እንደተከፈተ ነው።
ጊዜው ስለመሽ አብሯት የሚሄድ ሰው እየጠበቀች ነበር፡፡
«ምን አባሽ ይገትርሻል፧ አትሄጅም እንዴ» ስትል ሚስ ቴናድዩ
ጮኸችባት::

ኮዜት ወጥታ ሄደች:: በሩ ተዘጋ፡፡

ከእነቴናድዬ መሸታ ቤት ፊት ለፊት የነበረው የአሻንጉሊት መሸጫ
ሱቅ ሻማ አብርቶ ስለነበር የሻማው መብራት መንገዱን ያሳያል እንጂ ጨለምለም ብሏል፡፡ እንዳጋጣሚ ደመና ዞር ኖሮ ሰማዩ ላይ አንድ ኮከብ እንኳን አይታይም፡፡ ከሱቅ ውስጥ አንድ ትልቅ ጨርቅ የለበለ ኣሻንጉሊት
ነበር፡፡ አሻንጉሊቱ በጣም የሚያምር ዓይነት ሲሆን ኃላፊ፣ አግዳሚ እንዲያየው ከመስኮት አጠገብ ተሰቅሏል፡፡ ነገር ግን ያንን የመሰለ አሻንጉሊት ለልጅዋ
ለመግዛት አቅም ያላት ወይም ያለአግባብ ገንዘብ የምታባክን እናት ሞንትፌርሜ ከተማ ውስጥ ስላልነበረች ኣሻንጉሊቱ ከሱቁ ውስጥ ለብዙ ጊዜ ተቀምጦአል፡፡ የእነቴናድዬ ልጆች ከቤታቸው በወጡና በገቡ ቁጥር ያዩታል፡፡ ኮዜትም ዘወትር ዓይንዋን ትጥልበታለች::

ያን እለት ማታ ኮዜት ባልዲዋን ተሸክማ ወደ ምንጩ ውሃ ልትቀዳ
ስትሄድ አሻንጉሊቱን ትኩር ብላ አየችው:: «እመቤቴ» ብላ ለአሻንጉሊቱ ስም አውጥታለት ነበር፡፡ እንደዚያን እለት ቀረብ ብላ አይታው አታውቅም::
👍14
#ገረገራ


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በታደለ_አያሌው

...“እኮ ልትገድሏት?” አልኋት፣ በምን ተአምር ከአልጋዬ እንደ ተነሳሁ ሳይታወቀኝ፡ በቂጤ ቁጭ ብያለሁ

“ሽዊት? ለካ እስከዚህ ድረስ ጨካኝ ሆነሻል?”

“መቼም እኔን ታዉቂኛለሽ:: እኔ በሙያም በእምነትም ዓይን ስለማየዉ፣ እንደማልስማማበት ታዉቂያለሽ: ግን በእሱ እምነት ይኼ መግደል ሳይሆን ማዳን ነዉ”

“ቆይ ቆይ! ለምንድነዉ ይኼን ለኔ የምትነግሪኝ አሁን?”

“እኔ እንጃ: ምናልባት እንዲህ ያለ እምነት ያለዉ ሐኪም መኖሩንም
ማወቅ ከፈለግሽ ብዬ እደሆነ”

“አወቅሁ: ከዚያስ?”

“እመኚኝ ዉቤ፣ እኔም አልተስማማሁበትም…”

“በቃሽ!”

ንዴት አቅሌን አሳተኝ፡፡

ክፉና ደጉን የተጋራኋት የቀድሞ ጓደኛዬ አስጠላችኝ፡ ብዙ የተፈተንሁባትን ልጄን መግደል እንደ ማዳን የሚቆጥር ወዳጅ እንዳላት ከነገረችኝ በኋላ፣ ፈጽሞ ዓይኗን አያሳየኝ አልሁ: ዉዬ አድሬ ሳብሰለስለዉ እንዲያዉም፣ ሐሳቡ የወዳጇ ብቻ ሳይሆን የእሷም ጭምር መሆኑን ስለጠረጠርሁ ለሆስፒታሉ አስተዳደር ሳይቀር ከሰስኋት። እሷ የነገረችኝ ለብቻዬ ቢሆንም፣ እኔ ግን ያላዳረስሁባት ሰዉ የለም፡፡

ጨርሼ፣ እንደ ቀዉስ ሆኜ ሰነበትሁ።

ቱናትን ከተገላገልሁ ዛሬ ኹለት ወር ስለ ሞላኝ ቱናትን ይዤ
ከሆስፒታል የምወጣበት ቀን መሆኑን ሰምቻለሁ ዛሬ፣ በጥልቀት
እንክብካቤ ይደረግላት ከነበረችበት ክፍል ወጥታ በእቅፌ ትገባለች ጡቶቼን አጉርሻት በእናት ስስት እያየኋት፣ እስከማጠባት ጓጉቻለሁ።በዚ ላያ ላይ የሆስፒታል ቆይታዬም ጉሮሮዬ ላይ ደርሷል፡ ከዚህ በላይ
እንደ እስረኛ በአንዲት ጠባብ ክፍል ተከልክዬ ለመሰንበት ቀርቶ
ለአንዲትም አዳር የሚበቃ ትዕግሥት የለኝም፡ ሙጥጥ ብሎ አልቋል።

“በሉ ልጄን አምጡልኛ፣ ልዉጣበት” አልኋት ነርሷን፣ መጥሪያዉን ደዉዬ እንደ መጣችልኝ፡

“ሂሳብ ክፍል ያለዉን ነገር ጨረስሽ? ከጨረስሽ መዉጣት ትችያለሽ''

ልክ ይኼን ብላኝ ስትጨርስና ባልቻ በሩን ከፍቶ ሲገባ አንድ ሆነ፡
ከሆስፒታሉ ያለብን ቀሪ ሂሳብ ቀድሞም ተነግሮን ስለነበር፣ ገንዘቡን ይዞልኝ መምጣቱ ነዉ፡ የሚከፈለዉን ከፍለን፣ የሚፈረመዉንም ሁሉ
ፈርመን ስናበቃ፣ ቱናት ኹለት ወር ሙሉ ጥልቅ እንክብካቤ ስታገኝበት ከነበረዉ ልዩ ክፍል በነጭ ፎጣ ተጠቅልላ መጣችልን፡፡ ያመጣችልንን
ነርስ ደህና አድርገን አመሰገንናት፡ ልጄን ተቀብዬ ላቅፋት እጄን ስዘረጋ ሁሉ፣ ቅር ብሏታል ነርሶች ግን ታድለዉ! ልበ ጥሩዋ ነርስ፣ ቱናትን የሰዉ ሰዉ ሳትል እንዴት እንደምትሳሳላት ሳይ እንደገና አመሰግንኋትአስከትላም ልናደርግላት የሚገባዉን ጥንቃቄ
አስረዳችን: ቱናት ራሷን ችላ ካካ ማድረግ ስለማትችል ትንሿን ጣታችንን እየተጠቀምን እንዴት ማጸዳዳት እንዳለብን አደራ አለችን በተጨማሪም ሌሎች ማስታወሻዎች በሥዕላዊ መንገድ የተገለጹበትን መጽሔት
ሰጠችንና፣ አስታቀፈችኝ፡፡
ልጄ ቱናትን ለመጀመሪያ አቀፍኋት፡

ከወለድኋት ከኹለት ረዣዥም ወራት በኋላ፣ ከቱናት ጋር ትንፋሽ
ለትንፋሽ ተገናኘን፡ ወደ ታች ተቀብሮ ግራና ቀኝ እንደ ነገሩ ከሚቃብዘዉ ዓይኗ እና ሲር ሲር ከሚለዉ የጭንቅ ትንፋሿ በቀር እንዲህ ነዉ የሚባል
እንቅስቃሴ የላትም፡ እግሯ አይላወስም፡ ጡቴን ዳብሳ ታገኘዋለች ብጠብቅም፣ አፏ ላይ አድርሼላት እንኳን ጎርሶ መጥባቱ አልሆንልሽ አላት፡ ዝም ብዬ ጭምጭም እያደረግሁ ሳምኋት
ትንፋሿን አሸተትሁት ደስ ይላል
“ወደ እመዋ ቤት አይደል?” አለኝ ባልቻ፣ መኪናዉ ዉስጥ እንደ ገባን የወንበሩን ቀበቶ በትካሻዉ ላይ እያዋለ፡፡ ቁልፉን ወደ ቀኝ ጠምዝዞ ሞተሩን አስነሳና፣ በፊተኛዉ መስታዎት ወደ ኋላ እያየኝ መልሴን
ተጠባበቀ

“አይ እኔ እንኳን ቤቴ ነበር መሄድ የፈለግሁት” አልሁት፣ ሲራክ ፯ ወደ ተከራየልኝ ምስጢራዊዋ የግሌ ቤት ለመሄድ በመምረጥ፡ “ለእመዋም ተጨማሪ ጫና ከምሆንባት፣ ፈተናዬ ራሴ ብወጣዉ ነበር የሚሻለኝ።
እሷን ለማሳመን የሚሆነዉን ምክንያት ግን ከየት ልዉለደዉ?”

“አለማፈርሽ!” አለ፣ ባልቻ “ሆ!”

“የአራስ ወጉ እዳይቀርብኝ ብለህ ነዉ?”

“ኧረ ተዪ አቺ! እናቷን አስቀምጣ ለብቻዬ ካልታረስሁ ያለችዋ
የመጀመሪያዋ እናት ልትሆኚነዉ እንዴ? ሆ! በይ ተይ፤ ዕድልሽንማ
አትቀልጅበት!''

“በል እሺ እንሂድ”

“ወደ እመዋ ቤት?”

“ይሁን”

ወደ እመዋ ቤት ሄድን፡፡ ልክ ከግቢዋ በር ስንደርስ በሕልሜም በዉኔም ያለልጠበቅሁት እልልታ መንደሩን አቀለጠዉ፡ መነሻዉን ለማወቅ ዞር ዞር ስል ያደገደጉ ቆንጆዎች እና ጎበዞች እርጥብ ጨፌ እየጎዘጎዙ ተቀበሉን፡፡ በአቀባበሉ እየተደነቅሁ ወደ ዉስጥ ብቅ ስል፣ የእመዋ ግቢ
ጭራሽ የጥምቀት አደባባይ መስሏል: ከግቢዉ ጫፍ እስከ ጫፍ የሚደርስ ዳስ ተጥሎበት፣ የንፋስ ማለፊያ እስኪጠፋ ድረስ በሰዉ ጢቅ ብሏል፡ ያልመጣ የአዲስ አበባ ሰዉ መኖሩን ሁሉ እንጃ፡፡ የእመዋ ጎረቤቶች፣ በቀጥታ እኔን የሚተዋወዉቁኝ፣ በባልቻ በኩል የሚያዉቁኝ፣
የእሸቴ ዘመዶች፣ በእህቶቼ በኩል የሚያዉቁኝ ሁሉም እዚህ አሉ፡
የንስሐ አባቴን ጨምሮ፣ በዛ ያሉ ካህናት ሁሉ ተገኝተዋል። ከሁሉም
ከሁሉም በላይ የገረመኝ ግን የተጣላኋት አዋላጅ ሐኪሜን፣ ሸዊትን እዚህ ማግኘቴ ነዉ፡ ተጣልቻት ንግግርም ከልክያት እንዳልነበር፣ ሚያሸንፍ ፈገግታዋ እንደዚህ ስታየኝ ግን አልቻልሁም: እኔም ፈገግ አልሁላት ወደ ዉስጥ በዘለቅሁ ቁጥር፣ ልክ ለንግሥ የወጣ ታቦት በአጠገባቸዉ የሚያልፍ ይመስል፣ጎንበስ ቀና እያሉ እልልታዉን አደበላለቁት “እንኳን ማርያም ማረችሽ” የሚል ምርቃት እንደ ጉድ ተዥጎደጎደ፡ እንደ ታቦትም፣ እንደ ሙሽራም፣ እንደ አራስም ነዉ የተከበርሁ፡ እመዋ በተለይ፣ አይቼባት የማላዉቀዉ ዓይነት ደስታ
ፈልቆባታል ልክ እንደ ልጅ አድርጓታል፡

ቱናትን ስታቅፋትማ ደስታ የሚያደርጋትን ነዉ ያሳጣት፡ ያዉም እኮ እንደ ተሸፋፈነች አቀፈቻት እንጂ ገና ገልጣ እንኳን አላየቻትም እንቅልፍ ወስዷት ስለነበር፣ ፀሐይም ላይ ላለመግለጥ ብላ እንደ
ተሸፋፈነች ከልቧ አጠገብ ደረቷ ላይ ልጥፍ አደረገቻት እና እኔን ወደ ዋናዉ ቤት ጎተተችኝ፡፡

ደስታ በደስታ ሆናለች ፍልቅልቅ ብላለች

“እመዋ”

“አቤት የኔ ልጅ”

“ምንድነዉ ጉዱ?”

“የምን ጉድ? ደስታ ነዉ ጂ! ሰርግሽም አይደል?''

“እ?” አልኋት፣ ከተናገረችዉ ያልስማሁት ቃል ያለ ይመስል
“ዓለሜን አሳየሽኝ ልጄ: ድሮዉንም ቢሆን ከአባትሽ ጋ እንጨቃጨቅ
የነበረዉ በአንቺ የሕይወት መንገድ የተነሳ አልነበር? እኔ ወትሮዉንም ዓለምሽን ማየት ነበር ምኞቴ: ይኼዉ ደራርበሽ አሳየሽኝ። ክብር አለበስሽኝ። ደግ አደረግሽ የኔ ልጅ! እልልልልል!”
ደስታዋ መረጋጋቷን ነጥቋታል: እያቻኮለች ወደ ዋናዉ ቤት አስከትላኝ ገብታ፣ ቱናትን ልታስተኛልኝ ክፍት ካሉት መኝታ ክፍሎች ያደረሳትን
መረጠች: እንዳደረሳት የመረጠችዉ ክፍል ግን የጃሪም መሆኑ የኔን ያህል ቀርቶ ምንም ያሰጋት አልመሰለኝም: በእርግጥ ይኼኛዉ ክፍል ለሳሎኑ ቅርብ በመሆኑ ቱናትን አስተኝቻት ብወጣ እንኳን ቶሎ ቶሎ እየመጣሁና እየሄድሁ በደህና መተኛቷን ለማየት ያመቸኛል: ችግሩ ግን
የጃሪም ክፍል ነዉ፡ ይኼን ጭንቄን ያላወቀችልኝ እመዋ፣ ዝም ብላ ቱናትን በጥንቃቄ አስተኛችልኝ፡ ከዚያ ቀዝቀዝ የምትልበት ትንሽ አፍታ
ከታገሰቻት በኋላ፣ ገለጥ አድርጋ አየቻት፡ እንደገና ሳመቻትና በንጹሕ
አዲስ ጋቢ ጥቅልል አድርጋ መልሳ አስተኛቻት፡፡ ቅሬታዬን እንኳን ለመግለጽ ፋታ ሳትሰጠኝ፣ ወዲያዉኑ እጄን ይዛ እንግዶች ወደ ሞሉት ዳስ ጎተተችኝ፡፡

“አንዴ? ልጄን ትቼ!?”

“ተኝታ የለ፤ ምንም አትሆንም”

“ብቻዋን?”
👍374👎1🔥1
#ሳቤላ


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

....እሱ የመንፈሷን መጨነቅ ለዚህ ጥያቄ ያበቃትን የውስጧን ስሜት ልብ ብሎ አለተገነዘበም ስለዚህ ጥያቄዋን ሰምቶ አዩ ጉድ ምን
ምን ነው ትናንት ጸጉሬን ሳልስተካከል ነግረሽኝ ቢሆን ኖሮ የተቆረጠውን አፍሼ እልክልሽ
አልነበረም በይ ልጄ ....ፊርማዬንና ጸጉሬን በመጠየቅ ወደ ወሊንግተን ከፍ ከፍ አታዳርጊኝ
ብሎ ተንኮል በሌለበት ፡ በቅን ልቡና ቀልድ መለሰላትና !በይ ከዚህ በላይ መቆየት አልችልም ደህና እደሪ '' ብሏት ሔደ ....

« ቶሎ ቶሎ እየተራመዶ ሔደ ባርባራ ፊቷን በሁሉ አጆቿ ሸፍኖ ቀረች።

"እንዴ ! ምን አደረሁ !ምን አጠፋሁ ?” አለች ለራሷ ድምጿን ከፍ አድርጋ እንደዚህ የግድ የለሽነት ጠባይ ማሳየት የተፈጥሮው ነው ስሜት የለውም
ግን ይደርሳል ዛሬ ማታ እንዴት ያለ ደስታ ሰማሁ ሚስት መምረጡን ቀልድ አስመስሎ የነገረኝ ከልቡ ነው ይኸን ምስጢር ከኔ በቀር ለማንም አልነግረወም እኔን የሚርበኝን ያህል ለኔ የሚያስብልኝን ለማንም አላደረገውም ስለዚ ማንን
እንደመረጠ ለመገመት ብዙ ምርምር አይጠይቅም ግልጽ ነገር ነው " አዬ አርኪባልድ ሚስትህ ከሆንኩ በኋላ ነው ምን ያህል እንደምወድህ የምታውቀው እስከዚያ ድረስ ግን ልታውቅ አትችልም "

የሚያምረውን ፊቷን ቀና አድርጋ ወደ ደማቁ ጨረቃ በተመስጦ ከተመለከተች በኋላ በአትክልቱ በኩል የሚያልፈውን የእግር መንገድ ተከትላ ወደ ውስጥ አመራች ያን ያህል ብቻዋን ስታወራ አንድ ሰው ካጠገቧ ከዱሩ ውስጥ ሆኖ ያያትና ያዳምጣት እንደነበረ አልጠረጠረችም ብትጠረጥር ደግሞ ያን ያህል አትለፈልፍም ነበር ።

ሚስተር ካርላይል ወደ ካስል ማርሊንግ በሔዶ በአምስተኛው ቀን ሚስተር ዲል ለሚስ ካርይል አንድ ደብዳቤ አምጥቶ'“ ፖስተኛው ከኛዎቹ ደብዳቤዎች ጋር አደባልቆ አምጥቶ ነው” ብሎ ሰጣት "

" ምን የሚያስጽፍ ነገር አገኘ ? መቸ እመጣለሁ ይላል ? '' አለችው "።

ብታነቢው ይሻላል .. ሚስ ኮርነሊያ ለኔ በጻፈልኝ ውስጥ ስለ መምጣቱ አላነሳምፀ።

ደብዳቤውን ከፍታና ገልጣ እንዳየችው አጠግቧ ከነበረው ወንበር ዘፍ ብላ ተቀመጠች በሕወይቷ ሙሉ እንደዚያን ጊዜ ደንግጣና ፈዛ አታውቅም "

ካስል ማርሊንግ ግንቦት 1 ቀን

“ ለምወድሽ እህቴ ለኮርኒሊ ከእመቤት ሳቤሳ ቬን ጋር ዛሬ ጠዋት ተጋባን ነገሩን እንድታውቂው ብዬ ባጭሩ በችኮላ ነው የጻፍኩልሽ " ነገ ወይ ከነ ወድያ ከዚህ ሰፋ አድርጌ እጽፍልሻለሁ " ምንጊዜም ውድ ወንድምሽ

አርኪባልድ ካርላይል "

መላ ነው ” አለች ሕሊናዋ ተመልሶ አንደበቷ መናገር ሲችል ሚስተር ዲል የድንጋይ ቅርጽ መስሎ ዝም ብሎ ቆመ "

“ ውሸት ነው ብያለሁ ! "አለችና ደነፋች “ ባንድ እግሩ የቆመ የዝይ
አውራ አስመስሎ የገተረህ ምንድን ነው ? " አለችና በዚያ ክፋት የለሽ ሰወዬ ላይ ዞረችበት "

“ውሸት ነው አይደለም ? "

“ እኔም በጣም ገርሞኛል ... ሚስ ኮርነሊያ ነገሩ ውሸት አይደለም " ለኔም ጽፎልኛል

“ እውነት ሊሆን አይችልም ከአምስት ቀን በፊት ከዚሀ ሲሒድ የማግባት ሐሳብ አልነበረውም "
“ እኛ እንዴት ልናውቅ እንችላለን ... ሚስ ኮርኒ ? ” የሔደው ሊያገባ እንደ ሆነስ ማን ያውቃል እኔ ይመስለኛል " "

“ ሊያገባ መሔድ አያደርገውም መቸ አበደና?ያቺን የሕፃን ወይዘሮ! የለም? የለም አያረገውም "

“ይኸውልሽ በጋዜጣ እንዲወጣ ይኸን ልኮልኛል " ብሎ አንድ ወረቀት ሰጣት መጋባታቸውስ እርግጠኛ ነው ” አላት "

ሚስ ካርላይል ተቀበለችና ዘርግታ ስትመለከተው እጇ በረዶ ሆነ " ልክ የሰነፈ ይመስል ተንቀጠቀጠ

“ ተጋቡ - የኢስትሊኑ አርኪባልድ ካርላይልና የሟቹ ማውንት እስቨርን ኧርል ዊልያም ቬን ብቸኛ ልጅ የሆነችው ወይዘሮ ሳቤላ ሜሪ ቬን በዚህ ወር የመጀመሪ
ያው ቀን ካስል ማርሊንግ ላይ የማውንት እስቨርን ኧርል ነፍስ አባት በተገኙበት ተጋብተዋል ።

ሚስ ካርላይል ወረቀቱን ብጥስጥስ አድርጋ ቀዳ በተነችው " ከዚያ በኋላ ሚስተር ዲል በቃሉ አስታውሶ ጻፈና ወደ ጋዜጣ እንዲወጣ ሰደደው - ይህ በዚህ አበቃ "

“ እሱንም ሆነ እሷን ይቅር አልላቸውም ! አንኗኗራትም " ይህ ልበ ውልቅ ደንቆሮ !ሔደና ገንዘብ የማይጠቅማትን የማውንት እስቨርን ኧርል ልጅ አገባልኛ !
ባለላባ ባርኔጣ ከቁመቷ በላይ ሦስት ሜትር ተርፎ የሚጐተት ቀሚስ አጥልቃ ቤተ መንግሥት የምትመላለስ ቅምጥል !

“ ደንቆሮ እንኳን አይደለም ... ሚስ ኮርነሊያ ” አላት ዲል። "

“እረ ይበሳል ክፉ ሰው ነው” አላችና በእንባና በንዴት መኻል ያዘች ለዚህ ብሎ ሲሔድ አብዶ መሆን አለበት » ትንሽ ጫፍ ሰምቸ ብሆን ኖሮ የዕብደት ወረቀት አስወጥቸ አስይዘው አልነበር " ለመሆኑ የት ሊቀመጡ ነው ? ”

“ ኢስትሊን ይሆናል እንጂ " "

“ ምን ! ” ብላ ጮኸች “ ከካሪው ቤተሰብ ጋር ኢስት ሊን ሊቀመጡ ነው ! አንተም ማበድህ ነው መሰለኝ "

ከካሪው ጋር የነበረው ንግግር ተሽሯል ... ሚስ ኮርነሊያ » ሚስተር አርኪባልድ በፋሲካ ከካስል ማርሊንግ እንደ ተመለሰ የውል መሻሪያ ደብዳቤ የጻፈላቸው መሆኑን ከቀሪው መዝገብ አይቸዋለሁ " ያን ጊዜ ኢስትሊንን ራሱ ሊገባበት የወሰነው ከመይዘሮ ሳቤላ ጋር ጨርሶ ስለመጣ መስለኝ አላት "

ሚስ ካርላይል ይኸን ስትሰማ አፏን ከፍታ ድርቅ ብላ ቆየች » ትንሽ ለቀቅ አድርጓት ሕሊናዋን በከፊል ስታውቅ ገርሞት ወደ ቆመው ሰውዬ ከበስተኋላሙ ጠጋ
አለችና የኮቱን አንገትያ በሁለት እጆቿ ጭምድድ አድርጋ ይዛ ለብዙ ዶቂቃዎች ንጣ ' ንጣ ' ንጣ ለቀቀችው " ያ ምስኪኑና ቀትረ ቀላሉ ሚስተር ዲል እንደዚያ
አድርጋ በዚያ ቁመቷና ኃይሏ ያን ያህል ስታወዛውዘው የትንፋሹ ነገር እስከ መጨረሻ ያከተመለት መስሎት ነበር "

“ባንተ ጭምር ነበር የዕብድ መያዣ ደብዳቤ የማወጣብሀ ... አንተ ሸረኛ ! አንተም አብረህ ዶልተህ በል በል ስትለውና ስትረዳው ነበር "ነገሩን የሱን ያህል
አውቀኸው ነበር "

“ ኧረ እኔ ምንም አላወቅሁም ” አለ ሚስተር ዲል ትንፋሹ ተስተካክሎ መናገር ሲችል „ “ እኔ በዚህ ነገር የለሁበትም ደብዳቤ ደርኝ ሳየው ከመደንገጤ የተነሣ በላባ ብትመችኝ እወድቅ ነበር ”

“ እኮ ለምን እንደዚህ ካለ ጣጣ ገባ ? ገንዘብ የማይጠቅማት ቤሳ የሌላት ሴት አንተስ ብትሆን ኢስትሊንን እንዲያከራይ የመከርከው ምንድነው? አንተ ባታ
ደፋፍረው ኢስትሊን እኖራለሁ ብሎ አያስበውም ነበር

“እኔ ንግግሩን ከመሻሩ በፊት ያወቅሁት ነገር አልነበረም ደሞ ባውቅም እኔ የሚስተር ካርላይል ትእዛዝ ፈጻሚ እንጂ አዛዥ ወይም መካሪ አይደለሁም ኢስት ሊንን ለራሱ መኖሪያ ባያስበው ኖሮ ስሙን • “አርኪባልድ ካርላይል የኢስትሊኑ ተብሎ አያውጅም ነበር " ደሞኮ . . ሚስ ኮርኒ ቢገባበት አቅሙም ይፈቅድለታል
ወለዷ አቻው አትሁን እንጂ የደስ ደስ ያላት ቆንጆና የምትወደድ ልጅ ናት ” አላት"

ደግ ነው " የዕብደቱን ዋጋ ከጐኑ ያገኘዋል "

“ በይ ሚስ ኮርኒ ! ወደ ቢሮ ቶሎ መመለስ አለብኝ ” አለ ሚስተር ዴል ሩን ሲደመድም ። “ በኔ ላይ ይኸን ያህል በመቆጣትሽ ግን በጣም ነው የተናደድኩት "

“ አሁንም እየመጣህ ከፌቴ ብትደቀንብኝ እደግምሃለሁ "
👍18😁1
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


...ምላሷን ሳየው ነጭ የሆነ ይመስላል እየፈራሁ ትራሱ ላይ አጠገብ ለአጠገብ ጋደም ያሉት ሁለቱ ትንንሽ ፊቶች ላይ አተኮርኩ። ለምንድነው እንዲያድጉና ትክክለኛ ዕድሜያቸው ላይ እንዲሆኑ የምፈልገው? ይህ ለረጅም ቀናት የቆየ በሽታ ትልልቅ ሰማያዊ አይኖቻቸው ስር ጥቋቁር ክብ በማድረግ ጤናማ ቀለማቸውን ሰረቀ ትኩሳቱና ማሳሉ ቅፅበታዊ የእድሜ ለውጥ አምጥቶ
ፀሀዩዋ ብትወጣ ባትወጣ ግድ የሌላቸው የደከሙ የአዛውንቶች አይነት እይታ ሰጣቸው አስፈሩኝ፡ አሳዛኝ ፊታቸው ወደ ሞት ህልም ወሰደኝ

በዚህ ሁሉ ንፋሱ መንፈሱን ቀጥሏል።

በመጨረሻ አልጋቸውን ለቀው በዝግታ መራመድ ቢጀምሩም፣ በአንድ ወቅት ጠንካራ፣ ለመዝለልና ለመሮጥ ይችሉ የነበሩ እግሮቻቸው አሁን ደካማ;
እንደ ሳር የቀጠኑ ሆነዋል አሁን የሚችሉት በመብረር ፋንታ መዳህ፣ በመሳቅ ፋንታ ፈገግ ማለት ብቻ ሆኗል።

በድካም አልጋው ላይ በፊቴ ተደፍቼ የልጅነታቸውን ውበት ለመመለስ እኔና ክሪስ ምን ማድረግ እንችላለን? እያልኩ ደጋግሜ እያሰብኩ ነበር
የእነሱን ጤና መመለስ ለማገዝ ሲል ለእኛ ጤና የሰጠን ቢሆንም፣ እኔም ሆንኩ እሱ ማድረግ የምችለው ነገር አልነበረም።

እኔና ክሪስ በመንትዮቹ መካከል ያለውን ጤናማ ያልሆነ ልዩነት ለማስተካከል እየታመምን ባለንበት ወቅት “ቫይታሚኖች!” ስትል እናታችን ጮኸች።
“የሚያስፈልቸው ቫይታሚኖች ናቸው፡ እናንተም ያስፈልጋችኋል: ከአሁን ጀምሮ እያንዳንዳችሁ በየቀኑ የቫይታሚን ኪኒኖች መውሰድ አለባችሁ” ይህንን ስትነግረን እንኳን ቀጭኑና ረጅሙ እጇ በሚስብ ሁኔታ የተያዘውን
የሚያንፀባርቅ ፀጉሯን እየነካ ነበር።

አቅራቢያዬ ባገኘሁት አልጋ ላይ አረፍ እያልኩና ችግሩን ለማየት ፈቃደኛ ያልሆነችው እናት ላይ እያፈጠጥኩ “ንፁህ አየርና የፀሀይ ብርሃንም በኪኒን
መልክ ይመጣሉ?” ስል ጠየቅኳት “እያንዳንዳችን በየቀኑ የቫይታሚን ኪኒኖች መዋጣችን አብዛኛውን ጊዜያችንን ውጪ በምናሳልፍባቸው ቀናትና ትክክለኛ ህይወት እንመራ በነበረበት ጊዜ የነበረንን መልካም ጤንነት ይሰጠናል?”እናታችን በንቀት እይታ ገረፍ አድርጋኝ “ካቲ፣ ለምንድነው ያለማቋረጥ
ነገሮችን ሁሉ ከባድ የምታደርጊብኝ? የቻልኩትን እያደረግኩ ነው እውነቴን
ነው እና አዎ እውነቱን ከፈለግሽ በምትውጧቸው ቫይታሚኖች ውስጥ የውጪው አየር የሚሰጣችሁን መልካም ጤንነት ይመለስላችኋል፡ ለዚያ
ነው ብዙ ቫይታሚኖች የሚሰሩት:" አለች:

ግዴለሽነቷ ልቤ ውስጥ ተጨማሪ ህመም ፈጠረብኝ አይኖቼን ወደ ክሪስ ወረወርኩ፤ ምንም ሳይናገር አንገቱን አቀርቅሮ ሁሉንም ያዳምጣል

“እስረኝነታችን መቼ ነው የሚያበቃው እማዬ?”
በአጭር ጊዜ ውስጥ ካቲ፣ አጭር ጊዜ! ብቻ እመኚኝ
“ሌላ ወር?”
“ሊሆን ይችላል‥”

“እንደምንም ተደብቀሽ መንትዮቹን ለጥቂት ጊዜ በመኪናሽ ወደ ውጪ
ልታወጫቸው ማመቻቸት ትችያለሽ? ሰራተኞቹ በማያዩበት ጊዜ ልታደርጊው ትችያለሽ፡ ትልቅ ልዩነት ይፈጥራል ብዬ አስባለሁ። እኔና ክሪስ መሄድ የለብንም:”

ታላቅ ወንድሜ እዚህ ሴራ ውስጥ ይኑርበት አይኑርበት ለማየት ተሽከርክራ ተመለከተችው፤ ነገር ግን መገረሙ ፊቱ ላይ በግልፅ ይነበብ ነበር፡ “አይሆንም፣
በፍፁም አይቻልም! እንደዚያ አይነት አደጋ አልጋፈጥም! እዚህ ቤት ውስጥ ስምንት ሰራተኞች አሉ ማደሪያቸው ደግሞ ከዋናው ቤት ቀጥሎ ነው:ሁልጊዜም የሆነ ሰው በመስኮት ይመለከታል እና መኪናውን ሳስነሳ ሊሰሙኝ
ይችላሉ: ከዚያ በየትኛው አቅጣጫ እንደምሄድ ያጣራሉ።" አለች።

ድምጼ ቀዘቀዘ፡ “እባክሽ ትኩስ ፍራፍሬ ማምጣትስ ትችይ ይሆን? እባክሽ? በተለይ ሙዝ፡ መንትዮቹ ሙዝ እንደሚወዱ ታውቂያለሽ እዚህ ከመጣን ጀምሮ በልተው አያውቁም::”

“ሙዝ ነገ አመጣላችኋለሁ አያታችሁ እንደሆነ ሙዝ አይወድም:"

“hሱ ጋር ምን ያገናኘዋል?”

“በዚያ ምክንያት ነው ሙዝ የማይገዛው፡”

“ወደዚያ ትምህርት ቤት በሳምንቱ ቀናት ሁሉ ትሄጃለሽ፡፡ ቆም በይና ሙዝ፣ተጨማሪ የለውዝ ቅቤና ዘቢብ ግዢ አንዳንዴ እንኳን ለምንድነው የካርቶን
ፈንዲሻ የማያገኙት? በእርግጠኝነት ጥርሳቸው እንዳይበላሽ አይደለም!”

ደስ በማይል ሁኔታ ጭንቅላቷን ነቀነቀችና ተስማማች: “ለራስሽስ ምን ትፈልጊያለሽ?” ስትል ጠየቀችኝ፡

“ነፃነት! መውጣት እንዲፈቀድልኝ እፈልጋለሁ፡ በተቆለፈ ክፍል ውስጥ መኖር ደክሞኛል። መንትዮቹም እንዲወጡ እፈልጋለሁ። ክሪስ እንዲወጣ
እፈልጋለሁ ቤት ተከራይተሽም ይሁን ሰርተሸ ወይም ሰርቀሽ ብቻ ከዚህ ቤት እንድታስወጪኝ እፈልጋለሁ!

“ካቲ…” ትለምነኝ ጀመር። “የምችለውን ሁሉ እያደረግኩ ነው: በመጣሁ ቁጥር ስጦታ አላመጣሁላችሁም? ከሙዝ ሌላ ምንድነው የጎደላችሁ? ንገሪኝ
“እዚህ የምንቆየው ለጥቂት ጊዜ ነው ብለሽን ነበር አሁን ወራት አለፉ::

እንደሚፀልይ ሰው እጆቿን አነሳችና “አባቴን እንድገድለው ትጠብቂያለሽ? አለችኝ፡ በዝምታ ጭንቅላቴን ነቀነቅሁ

የእሱ አማልክት ወጥታ በሩ እንደተዘጋ ክሪስ “ለምን አትተያትም?!” ሲል ጮኸ፡ “ለሁላችንም የምትችለውን እያደረገች ነው፡ አትጨቅጭቂያት
ልክ እንደማታምኛት ሁሉ የማያልቁ ጥያቄዎችሽን እየደረደርሽና ከጀርባዋ
አልወርድ እያልሻት ልታየን መምጣቷ ራሱ የሚገርም ነው: ምን ያህል እንደተሰቃየች እንዴት ታውቂያለሽ? አራቱ ልጆቿ አንድ ክፍል ውስጥ ተቆልፎባቸውና ጣራ ስር ያለ ክፍል ውስጥ ብቻ እንዲጫወቱ መደረጋቸውን
እያወቀች ደስተኛ ነች ብለሽ ታምኛለሽ?”

እንደ እናታችን ስላለ ሰው መናገር ከባድ ነው፡ ምን እንደምታስብ፣ ምን እንደሚሰማት ማወቅ አይቻልም: አንዳንድ ጊዜ ብቻ የደከማት ከመምሰሏ በስተቀር ስትታይ ሁልጊዜ ረጋ ያለች ናት ልብሶቿ አዲስና ውድ ሲሆኑ አልፎ አልፎ አንድን ልብስ ሁለት ጊዜ ለብሳ እናያታለን፡ ለእኛም
አዳዲስና ውድ ልብሶች ታመጣልናለች: ግን የምንለብሰው ልብስ ልዩነት አልነበረውም: ከአያታችን በስተቀር ማንም ስለማያየን ፊቷ ላይ የደስታ
ፈገግታ የሚያመጣላትን የነተቡ ቡትቶዎችንም መልበስ እንችላለን
ሲዘንብና በረዶ ሲጥል ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል አንሄድም: ዝናብ በሌለ ቀን እንኳን በሀይል እያፏጨ በአሮጌው ቤት ስንጥቅ በኩል የሚገባ ከባድ
ንፋስ አለ።

አንድ ሌሊት ኮሪ ከእንቅልፉ ባኖ ጠራኝና ካቲ ንፋሱን አባሪው" አለ
አልጋዬንና ኬሪን ትቼ ከኮሪ አጠገብ ብርድ ልብስ ውስጥ ገባሁና ጥብቅ አድርጌ አቀፍኩት ምስኪን ቀጫጫ፣ የሚነፍሰው ንፋስ ይዞት የሚሄድ ነው የሚመስለው፡ በእናቱ በጣም መወደድን ቢፈልግም ያለሁት እኔ
ብቻ ነኝ፡ ፊቴን ዝቅ አድርጌ ንፁህና ቆንጆ ሽታ ያለውን ፀጉሩን ሳምኩት
ልጅ ሆኖ አሻንጉሊቶቼን በእውነተኛ ልጆች የተካሁ ጊዜ እንዳደረግኩት እቅፍ አደረግኩት፡ “ንፋሱን ማባረር አልችልም ኮሪ ያንን ማድረግ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው''

“ታዲያ ለእግዚአብሔር ንፋሱን እንዳልወደድሽው አትነግሪውም? አለ።

“ለእግዚአብሔር ንፋሱ የመጣው ሊወስደኝ ፈልጎ እንደሆነ ንገሪው::”
እንደገና አስጠጋሁትና የበለጠ ጥብቅ አድርጌ አቀፍኩት ... በጭራሽ ንፋሱ ኮሪን እንዲወስደው አልፈቅድለትም: በጭራሽ!

“ንፋሱን እንድረሳው ታሪክ ንገሪኝ ካቲ"
👍34🥰2
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

ናንሲ ሌኔሃን በትዕግስት ማጣት ስትቁነጠነጥ የመርቪን ላቭሴይ ትንሽ
አይሮፕላን ለበረራ ተዘጋጀች፡፡ ላቭሴይ ለፋብሪካው ካቦ መመሪያ እየሰጠ ነበር፡፡ መርቪን የፋብሪካው ወዛደሮች እንዳመጹና ሰሞኑንም የስራ ማቆም አድማ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ነገራት፡
‹‹አስራ ሰባት የመሳሪያ ቴክኒሻኖች ቀጥሬአለሁ አንዱ እንኳን ስለፋብሪካው ግድ የለውም፡፡››

‹‹ምንድነው የምታመርተው›› ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ቬንቲሌተር፣ የአይሮፕላን ሞተር ክፍሎች፣ የመርከብ መፍቻዎች፣ የመሳሰሉትን፡፡ ኢንጂነሪንግ ክፍሉ ችግር የለውም፡ እኔን ያስቸገረኝ ሰራተኛ ማስተዳደሩ ነው፡፡ አንቺ ግን የፋብሪካ ውዝግብ ምንሽም አይመስልም›› ሲል
ጨመረ።

‹‹እኔም ችግሬ እሱ ነው፡፡ እኔም የፋብሪካ ባለቤት ነኝ››
ላቭሴይ በአባባሏ ተገረመ

‹‹ምን አይነት ፋብሪካ?››
‹‹በቀን አምስት ሺ ሰባት መቶ ጥንድ ጫማዎች አመርታለሁ››
ተደነቀ፡፡ ሆኖም የተበለጠ ስለመሰለው ‹‹አንቺ ጎበዝ ነሽ›› አላት አድናቆትና ለበጣ በተቀላቀለበት ድምጽ ናንሲ የእሱ ድርጅት ከእሷ በጣም እንደሚያንስ ገምታለች፡

‹‹አሁንስ ፋብሪካ አለኝ ባልል ይሻላል›› አለች ምርር ብሏት ‹‹ወንድሜ እኔ ሳላውቅ ድርጅቱን ሊሸጥ እየተሯሯጠ ነው›› አለችና አይሮፕላኗን በስስት እያየች ‹‹ለዚህ ነው የሰማይ በራሪ ጀልባው ላይ ለመሳፈር
የቸኮልኩት›› አለች፡፡

‹‹አይዞሽ ትሳፈሪያለሽ›› አላት በፍጹም ልበ ሙሉነት ‹‹ይቺ ሚጢጢዬ
አይሮፕላኔ ከሰማይ በራሪው
ጀልባ መነሻ አንድ ሰዓት ቀድማ ታደርሰናለች፡››

‹‹እስቲ እግዜሄር ይሁነና!›› አለች፡፡

አይሮፕላኗን ሲጠጋግን የነበረው መካኒክ ዘሎ ወረደና ‹‹ሁሉም ዝግጁ
ሁሉም ሙሉ ሚስተር ላቭሴይ›› አለው፡

ላቭሴይ ናንሲን ተመለከተና ‹‹ሄልሜት አምጣላት ይህን ባርኔጣ አድርጋ መብረር አትችልም›› ሲል አዘዘው መካኒኩን ናንሲ ወደ ቀድሞው መደዴ ባህሪው ወዲያው ሲመለስ ስታይ
ገረማት፡ ምንም የሚሰራ በሌለበት ጊዜ ከእሷ ጋር ለመጨዋወት ደስተኛ
ነበር፡ ነገር ግን የሆነ ጠቃሚ ነገር ሲከሰት ጣል ጣል ያደርጋታል፡ በስራ
ቦታዋ እንደዚህ አይነት ባህሪ ከወንዶች አልለመደችም:: ምንም እንኳ ስትታይ የወሲብ አማላይ ባትመስልም በቀላሉ የወንዶች ዓይን ውስጥ ትገባለች፡ በስራ ቦታዋም ተገቢውን ክብር የሚነፍጋት የለም፡፡ ወንዶች እንደ ላቭሴይ ናቅ አያደርጓትም:: ሆኖም በዚህ ጊዜ ምንም ተቃውሞ ማሰማት አትችልም:፡ ወንድሟ ላይ እስክትደርስበት የሚደርስባትን ውርደት መቀበል ይኖርባታል፡፡

ስለ ትዳሩ ማወቅ ፈለገችና ጠየቀችው፤ ‹‹ጥላኝ የሄደችውን ሚስቴን
እያሳደድኩ ነው›› ሲል የሆዱን ነገራት፧ ወዲያውኑ ሚስቱ ለምን ጥላው
እንደሄደች ገባት፡፡ ሴትን የሚያማልል መልከ መልካም ቢሆንም ስራው ላይ ብቻ የሚያተኩርና ለሴት ግድ የለሽ ይመስላል፡ ሚስቱን ለመከታተል
መነሳቱ ደግሞ ሌላው ግራ የሚያጋባ ገጽታው ነው፡፡ መቼም በጣም ኩሩ
ሳይሆን አይቀርም፡፡ ናንሲ ስታየው ሚስቱን ገደል ትግባ የሚል አይነት መስሏት ነበር፡፡ ነገር ግን ተሳስታለች፡፡

ሚስቱ ምን እንደምትመስል ለማየት ጓጉታለች፡፡ ‹ቆንጆ ትሆን የአልጋ ላይ ንግስት፣ ራስ ወዳድ፣ ቅምጥል ወይስ እንደ ቆቅ የምትደነብር? በቅርቡ ታያታለች አይሮፕላኑ ሳይነሳ ከደረሱ፡፡

መካኒኩ የብረት ቆብ አመጣላትና ራሷ ላይ ደፋላት፡

ላቭሴይ አይሮፕላኗ ላይ ወጣና ‹‹ናንሲን እንድትወጣ አግዛት›› ሲል መካኒኩ ላይ ጮኸበት፡፡

መካኒኩ ከጌታው በተሻለ ትህትና ‹‹የኔ እመቤት እዚያ ላይ ጸሐይም ቢኖር ብርድ አለ አለና ኮቷን አለበሳት ከዚያ አወጣና ከላቭሴይ ኋላ ካለው ቦታ ላይ
አስቀመጣት፤ሻንጣዋንም እግሯ ስር አኖረላት፡

ሞተሩ ሲነሳ ከማታውቀው ሰው ጋር አየር ላይ ልትወጣ እንደሆ ስታስበው ፍርሃት ጨመደዳት። መርቪን ላቭሴይ ብቃት የሌለው ፓይለት ወይም ደግሞ ነጭ ሴቶችን ለቱርክ ሴተኛ አዳሪ ቤቶች ወስዶ የሚሸጥ
ሊሆን ይችላል፤ ዕድሜዋ ለዚህ ያለፈ ቢሆንም፡፡ አይሮፕላኗ ደግሞ በደምብ
ያልተጠገነች ትሆን ይሆናል፡፡ ህይወቷን የሰጠችውን ላቭሴይን የምታምንበት ምንም ሁኔታ የለም፡፡ እንግሊዛዊና አይሮፕላን ያለው መሆኑን ብቻ ነው የምታውቀው:፡

ናንሲ ከዚህ ቀደም ሶስት ጊዜ በራለች፡ ሆኖም የበረረችባቸው አይሮፕላኖች ትልቅና ሽፍን ናቸው፡፡ ጊዜ ባለፈበት ባለ ድርብርብ የእንጨት ክንፍና በክፍት አይሮፕላን ስትሄድ
የመጀመሪያዋ ነው፡፡ ልክ በፈጣን ሽፍን ያልሆነ መኪና እንደመሄድ ይቆጠራል ሚጢጢዋ አይሮፕላን በአስፋልቱ ላይ ሮጣ እንደ ሰጋር በቅሎ እመር አለችና ወደ ሰማይ ተመነጠቀች ናንሲ በዚህ ጊዜ በፍርሃት ነፍሷ ውልቅ ልትል ምንም አልቀራት፡፡

የአብራሪነት ፈቃድ ይኖረው ይሆን?› አለች ለራሷ ደሞስ ከእንጨትና ከሸራ የተሰሩት የአይሮፕላኗ ክንፎች ቢቀነጠሱስ? ሞተሯ ቀጥ ቢልስ? ተሰብሮ መሬት ቢወድቅስ? ንፋሱ ወደ እነሱ አቅጣጫ ነፍሶ አይሮፕላኗ
ቢወዘውዛትስ? ጭጋግ ቢሆንስ? አቤት አምላኬ! እያለች ታስባለች ናንሲ¨
አይሮፕላኗ ግን አቅጣጫዋን ወደ አየርላንድ አድርጋ ሸመጠጠች¨
ጉዞው አስፈሪ ቢሆንም ደስ ይላል፡፡

ምዕራባዊ እንግሊዝን እንዳለፉ ናንሲ ውስጧ በድል አድራጊነት ሲሞቅ
ተሰማት፡ ፒተር ሆዬ ይሄኔ በሰማይ በራሪው ጀልባ ሊሳፈር እየተዘጋጀ ይሆናል፡፡ እዚያ ሲገባ ብልጧን እህቱን እንደሸወዳት ይረዳል፡፡ ነገር
ግን ደስታው የአጭር ጊዜ መሆኑን ስታውቅ ደግሞ አንጀቷ ቅቤ ጠጣ፡፡ ፎየንስ
መምጣቷን ሲያይ ምን ያህል እንደሚሸማቀቅ ለማየት ጓግታለች፡፡ ፒተር ላይ መድረስ ብቻ አይበቃም፡፡ ገና ከባድ ትልቅ ትግል ይጠብቃታል፡ በቦርድ ስብሰባው ላይ አክስቷ ቲሊንና ዳኒ ሪሌይን አክሲዮናቸውን
ከኩባንያው ጋር እንዲያቆዩና ከእሷ ጎን እንዲሰለፉ ማሳመን አለባት

ፒተር እህቱን እንዴት እንደዋሻትና ከእሷ ጀርባ ሲያሴር እንደነበር ለሁሉም ማሳወቅ ፈልጋለች፡፡ ምን አይነት እባብ እንደሆነ እንዲያውቁ ታደርጋለች፡ ነገር ግን ወዲያው ደግሞ አንድ ነገር ታሰባት፡፡ ንዴቷና በእሱ ላይ ያላት ጥላቻ በግልጽ ከታየ የኩባንያውን ውህደት የፈለገችው
በስሜታዊነት ነው ብለው ያስባሉ፡ ስለዚህ መጠንቀቅ አለባት፡ የፋብሪካው
የወደፊት መጻኢ እድል ምን እንደሆነና ከፒተር ጋር ያላቸው አለመግባባት
የስራ ብቻ እንደሆነ ቀዝቀዝ ብላ ማስረዳት አለባት፡፡ እሷ ከእሱ የተሻለ ድርጅቱን ማስተዳደር እንደምትችል ሁሉም ያውቃሉ፡፡

ክርክሯም በመጠኑ ስሜት ይሰጣል፡፡ለአክሲዮናቸው ሽያጭ የቀረበላቸው ዋጋ በኩባንያው አትራፊነት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በፒተር
ደካማ አመራር ደግሞ ትርፉ አሽቆልቁሏል። ሌሎቹ የቦርድ አባላት ፋብሪካውን በመዝጋትና ሱቆቹን በመሸጥ ጠቀም ያለ ገንዘብ ማግኘት
እንደሚፈልጉ ናንሲ ገምታለች፡፡ ነገር ግን እሷ የፋብሪካውን አሰራር
በማደራጀት ዳግም አትራፊ ለማድረግ አቅዳለች፡:

ሌላም ምክንያት አለ፡፡ ለጦር ሰራዊቱ ዕቃ የሚያቀርቡ እንደ ናንሲ ላሉ
ኩባንያዎች ጦርነት ጥሩ ነው፡፡ አሜሪካ ጦርነት ውስጥ አትገባም ይሆናል
ነገር ግን ለጥንቃቄ ሲባል የጦሩን ትጥቅ ለማሟላት እንቅስቃሴ መደረጉ
አይቀርም፡፡ ስለዚህ ኩባንያቸው ትርፍ ማግበስበሱን ይጀምራል፡ ለዚህም ሳይሆን አይቀርም
ናት ሪጅዌይ ብላክ ቡትስ ኩባንያን በእጁ ለማድረግ የቋመጠው።
👍27
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ልክ በስድስተኛ ወሩ እንግሊዝ አገር ውስጥ በሚገኘው የማንቸስተር ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ ሁለት ቆዳ ለባሽ ሴቶች፣ አንድ
ሳዳጎራ ያገለደመ ወጣት፣ ተቃቅፈው በመግባት ቦታቸውን ይዘዋል"
አፉን ከፍቶ የነበረው አዳራሽ ቀስ በቀስ ሞልቶ ተጨናነቀ" የዕለቱ
አንትሮፖሎጂካዊ ጥናት አቅራቢ የአፍሪካ ውስጥ ምርምሯን ይዛ ወደ መድረክ ወጣች።

«…ክቡራትና ክቡራን፣ በተመራማሪነቴ የሠለጠነው ዓለም
ከረሳው ተፈጥሮና ሕዝብ መካከል ተገኝቼ፣ ለዘመናት የዳበረ ባህልና ጥበብ ያለውን ክልል ለማየትና ሕይወቱንም ለመኖር ችዬ እኔ ያገኘሁትን ዕውቀት ለቀሪው ዓለም ሕዝብ ለመግለጽ በመብቃቴ
ደስታዩ ወደር የለውም።

«የሐመር ተፈጥሮ፣ ሰው ሠራሽ ብክለት ያልተጠናወተው ንጹሕ
ተፈጥሮ ነው። በዓለማችን ፍጹም ደስታ ያለው ሕዝብ አለ የሚል እምነት የለኝም" ደስተኛ ሕዝብ አለ ከተባለ ግን ከሐመር ሕዝብ
የበለጠ ደስተኛ፣ ግልጽ፣ በመካከሉ ጠንካራ መፈቃቀር ያለው ያለ
አይመስለኝም።

«በዘመናችን እንደ ብርቅ የሚታየው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ሐመሮች ለብዙ ዘመናት የሕልውናቸው የማዕዘን ድንጋይ አድርገውት ኖረዋል" ከዚህ በተጨማሪም፣ የሐመሮች የዳበረ የከብት አረባብ ዘዴ፣ የአመጋገብ ሥርዓት፣ ብሒሎችና ትውፊቶች ወዘተ.ዝብርቅርቁ የወጣውን የዘመነውን ዓለም ዓይነ ልቦና የሚስብ
እንደሆነ አምናለሁ።
«...ለማጠቃለል
ያህል፣ እኔ የምናገረው የማውቀውን ብቻ
ሳይሆን የሚሰማኝንም ጭምር ነው" በእርግጥ ሐመር ላይ ሊሻሻሉ፣
ሊያድጉና እገዛ የሚያስፈልጋቸው በርካታ ቁም ነገሮች እንዳሉ
አምናለሁ" ሆኖም ግን ከሠለጠነው ዓለም የአካባቢ ብክለት ችግር፣
የበሽታ መስፋፋት፣ ተፈጥሮአዊ ካልሆነ የአኗኗር ሥርዓት ችግር አንፃር የሐመር ተፈጥሮ ማራኪ ነው" ሕዝቡም ንጹሕ ሕሊና፣የዳበረ የአኗኗር ልምድ፣ ተፈጥሮአዊ ፍቅርና በራሱ የሚተማመን
ሕዝብ መሆኑን ሳረጋግጥ በዓለማችን እውነቱን በመመስከር ከታወቁት ምስክሮች ራሴን እንደ አንዱ እቈጥረዋለሁ።

«..ቀሪው ዓለም አፍሪቃውያንን መርዳት ብቻ ሳይሆን፣አሁንም ከአፍሪቃውያን ብዙ የሚማረው እንዳለ ማወቂያው ጊዜ
አሁን ነው» የሚለው፣ በጽሑፍና በተንቀሳቃሽ ሥዕል የተደገፈው
ጥናቷ ተመልካቿን ከመቀመጫው ናጠው።
ተመራማሪዋ በባዶ እግሯ፣ ቆዳዋን እንደ ለበሰች ጥናቷን ስታቀርብ ቆይታ ስታጠቃልል ያችን ችግርና ሰቆቃ ተቋቁማ፣ የሁለቱን ዓለም ልዩነትና አለመግባባት አስወግዳ፣ እውነተኛ ሰብአዊ ፍቅርንና ሕይወትን ያሳየች ተመራማሪ የአድናቆት ጭብጨባና ጩኸት ለደቂቃዎች በዩኒቨርሲቲው ታሪክ ታይቶ ተሰምቶ
በማይታወቅ መልክ ቀረበላት። ካርለት አልፈርድ ተባባሪዋንና ጓደኞቿን ይዛ ወደ መድረክ ስትወጣ ጭብጨባው ይበልጥ ጋለ"
ከሎና ጎይቲም ሕሊናቸው በደስታ ረካ።

ሦስቱም ጓደኛሞች በሐመር ደን መካከል እንዳደረጉት ሁሉ፣በማንቸስተሩ የጉባኤ አዳራሽም ተቃቅፈው አነቡ እየሣቁ አለቀሱ።
በአውሮፓ ሕይወት ከሎ ብዙውን ጊዜውን በትምህርት አሳለፈ
ጎይቲ ግን ከካርለት ቤተሰቦች ጋር ተቀመጠች" ጎይቲ በዓይን ማየት
ቀርቶ በወሬ እንኳን በአሳለፈችው ሕይወት ያልሰማችው ጉድ ውስጥ
ስትገባ በእውኗ መቃዠት አበዛች።

ከካርለትና ከከሎ ጋር መጀመሪያ ከሐመር ሲነሡ የመኪናው ጕዞ ደስ ብሏት ነበር" ከካርለት ጋር በመኪና መካ፣ ቱርሚ፣ ጂንካም
ሄዳ ስለነበር እንደ ልማዷ መኪናዋ ስትጓዝ የሐመር ሰዎችና እፅዋት ወደ ኋላ ሲሮጡ እሷ በሣቅ ፍርስ ብላለች" አንዴ ወደፊት፣ አንዴ ወደኋላ ስታይ እንደ ቆየች ግን የሆነ ነገር ሆዷን አሸበራት" ወዲያው
ለካርለትና ለከሎ፣ «ይእ! አያችሁልኝ የኔን ነገር አገሩን ሁሉ ስሰናበት አያ ደልቲን ግን ሳልሰናበተው ስመጣ? ምናለ እናንተዬ
ብትመልሱኝ? አሁን ባል በማግባቴ አንጀቱ የተኰማተረው አንሶት
መሄዴን ሲሰማ ሆዱ መንቦጫቦጩ ቀረ! ጀግና ሰው ልቡ ቶሎ
ይቀየማል» አለች።

«ጎይቲ አሁንማ ብዙ ርቀን መጥተናል" ቀደም ብለሽ አስበሽው ቢሆን ኖሮ ብንመለስም አይከብድም ነበር" አሁን ግን ብዙ ርቀናል" አንቺስ አያ ደልቲ የሚገኘው ከስኬ ወንዝ አሸዋ ላይ ተጋድሞ
መሆኑን እያወቅሽ ለምን ሄደሽ ሳትሰናበችው ቀረሽ?» አላት ከሎ
«ይእ! እናንተ ልቤን አጠፋችሁታ" እንዲህ አሁን ሆዴን ሊያጥወለውለኝ እዚች መኪናይቱ ላይ መውጣቱም አጓጓኝና
እረሳሁት እንጂ ምነው እናንተዬ ኧረ ኃዘኑ ቅስሙን ይሰብረዋል"ጀግና ሰው ዕድሜው አጭር ነውI መርቀኝ፣ ላገርሽ ያብቃሽ በለኝ ሳልለው ወጥቼ ስመለስ ባጣው ጸጸቱ ዕድሜ ልኬን ይወጣልኛል?» አለች"

«ጎይቲ አያ ደልቲን አሁንም ታልሚዋለሽ ማለት ነው። ድሮ የተቃበጣችሁት አይበቃም?» አላት ከሎ ፈርጠም ብሎ"

«ይእ! ኧረ እይልኝ የአያ ደልቲ ጨዋታ እንደ ከተማ ልብስ የሚወልቅና
የሚታጠብ መሰለህ! ሆድ ዕቃ ውስጥ ነው የሚቀመጥ ያ ደልቲ አንፈራጦ ብቻውን ይዞት የነበረውን ስፍራ አንተ ገብተህ እሱን ወደ ጥግ ወሰድከው እንጂ ከሆድ
አልጣልከው" እኔና እሱ የአንድ ጎሳ ልጅ መሆናችንና አንተ ባዕድ ሆንህ እኔና አንተን አገናኘን እንጂ የዚያ ጀግና ሎሌ ሆኜ ብኖር
ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር» ብላ በሣቅ ስትፍለቀለቅ፣ ካርለትና ከሎአብረው አጀቧት።

ካርለት ጎይቲ በሐመርኛ ቋንቋ የተናገረችውን ካዳመጠች በኋላ፣
«ምነው ሰው ሁሉ እንዳንቺ ግልጽ በሆነ፣ እውነተኛ ስሜቱን ባልደበቀ እዚህ ወርቅ መሳይ ብልጭልጭ ዓለም እውነተኛው ወርቅ
ሕይወት ሐመር ላይ አለ ቢሉት ማን ጆሮውን ይሰጣል" መተማመን
ቀርቶ መጠራጠር ዘውድ በጫነበት በዚህ የውሸት ዓለም እስከ መቼ መኖር ይቻላል?» ብላ፣ ስታስብ ካይኖቿ ስር መጀመሪያ ጉም መሰለ ነገር፣ በኋላ ተከታትሎ እየተስረገረገ የሚንኳለል ትኵስ እንባ
ዓይኗን ሲሞላ፣ መኪናዋን አቁማ መሪው ላይ ተደፍታ መንሰቅሰ ጀመረች።

ጎይቲ መጀመሪያ ካርለት እየሣቀች መስሏት ነበር" የቀላው? ፊቷንና የራሰውን ዓይኗን ስታይ ግን ልቧ በኃዘን ተሰብሮ ቆየችና፣
“ይእ! ምነው አይደክማት እሷ ብቸዋን ደፋ ቀና እያለች እኛ ዝም አልናት። በይ አንቺስ ከምታለቅሺ ዕርዱኝ አትይም? እንደ እርፍ
ወዲያ ወዲህ የምታማስይውን እንደሁ አያቅተኝም። መዘወሩንም
ቢሆን አላጣውም» አለቻት

«ጎይቲዬ አመሰግናለሁ" መንዳቱ ለአንቺ እንኳ ይhብድሻል ባይሆን መኪናውን ከሎ ያሽከርክር፣ ወደፊት ግን አንቺም
ታሽከረከሪያለሽ» ብላ ቦታዋን ለቀቀችለት"

ጎይቲ አንተነህ ደስ ያላት ጕ" እያንገሸገሻት ሄደ" አንገቷ
ደፍታ የማታውቀው ጎይቲ ሆዷን አቅፋ፣ አንገቷን አዘነበለች
ጎይቲ በአውሮፕላኑ ጕዞም ሆነ በአውሮፓው ሕይወት ቋንቋውን ገጽታውን የማታውቀው ትያትር ተመልካች ሆና ሁሉም ነገር
ታከታት። ኵሩው አረማመዷ ስብር ስብር አለ ጥርሶቿ በከንፈሮቿ በጥብቅ ተጋረዱ" የሐመሯን ሸጋ ህምታ ሰፈነባት" ፀሐይ ከእሷ በጣም ርቃ ሙቀቷ ሳይሰማትና ብርሃኗ ሳያስደስታት ወጥታ ገባች
ጨረቃን ከናካቴው ከሰማይ ላይ አጣቻት" ሲያዩት የሚያብለጨልጨውና የሚያምረው ሰው ሠራሽ ውበት፣ እየቆዩ በሄዱ ቁጥር
እያፈናት መጣ" መለምለም፣ ጠውልጎ መድረቅ፣ ተልሶ
መለምለም የማያውቀው የተፈጥሮ ቅመም የጎደለው የቴክኖሎጂው
ዓለም ለውጥ አልባ በመሆኑ እጅ እጅ አላቸው። ንጹሕ አየር፣ ተለዋዋጩ የተፈጥሮ ውበትና የሚያውደው መዓዛ፣ የአዕዋፍ ዝማሬና
የአውሬዎች ጩኸትና ግሳት፣ የጨረቃ ወቅት ዳንስና ጣፋጩ የጫካ
ውስጥ ፍቅር በእዝነ ሕሊናቸው ውል እያለ አስቈዘማቸው"
👍29😁1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

“እናቴም አባቴም ስለዚያ የልጅነት ስጦታዬ ትንፍሽ ሳይሉኝ ስጦታውን ግን እየተቀባበሉ ሲያዩት አይቻቸዋለሁ ይህ ደሞ አይወዱኝም ማት ነው የሚል ስሜት ፈጠረብኝና
ያልደነደነችው ልቤ ሐዘን እንደ ደሰቀ ዳቦ ነካከተች ከዚያን ቀን በኋላ ከነሱ የምለይበትን ቀን ማሰላሰል ጀመርሁ

“በየቀኑም ከነሱ ለመራቅና እነሱን ለመርሳት ስል የወንድ ጓደኛ ያዝሁ
የያዝኋቸውን የወንድ ጓደኞቼን እንድርቃቸው ተገደድሁ።

“እናቴ እንደነገርሁ የስነ አዕምሮ ትምህርት እውቀት
አላት ይሄ እከሌ የሚባለው የወንድ ጓደኛዬ ነው ስላት፡-

የጨካኝ ሰው መልክ ነው ያለው፡፡ ወንጀል ለመሥራት ወደ ኋላ አይልም…” ትለዋለች ወይም ደግሞ፡-ዠ

“ይኸ ጅላጅል ነው: የታወረ አዕምሮ ያለው ነው፡፡ እና
እሱን ስትመሪ መኖር ትፈልጊያሽ" ትለኛለች፡፡ ሌላውን ሳስተዋውቃት
ደግሞ፡-

ይኸ ጭልፋ አፍንጫ አንድ ቀን አይንሽን ያወጣዋል: እንደ ጣውላ የተላገ የሚመስል የወንድ ቅርፅ የሌለው... እኔ አንችን
ብሆን ኖሮ ከሱ ጋር በሆንሁ ቁጥር በጥላቻ አስመልስ ነበር….እያለች ስታጥላላብኝ ከያዝኋቸው የወንድ ጓደኞቼ በሙሉ ራቅሁ: በኋላ ግን ወደ ቤታችን አልፎ አልፎ ብቅ ከሚለው የእናቴ ጓደኛ
ልጅ ጋር ግንኙነት ጀመርሁ፡

ፔድሮ ይባላል፡ ሙልቅቅ ያለ ባህሪው መያዣ መጨበጫ የሌለው ነው፡፡ ከፍቅር ይልቅ የጦርነት ታሪክ ማውራት ይወዳል:
ህዝብ ከተጨናነቀበት መዝናኛ መሃል ይወስደኝና ጉሮሮው እስኪሰነጠቅ እየጮኸ ጩኸትና ሁካታ አልወድም' ይለኛል ማን
ለምኖህ መጣህ? ደሞ ማንስ ጩኸት ይወዳል እንዳንተ ካለው ደደብ
በስተቀር' እልና በሃሳቤ እነቂው እነቂው ያሰኘኛል፡፡ አማራጭ ግን አልነበረኝም፡፡ ወላጆቼን ለመርሳት ስል በሄደበት ሁሉ እንደ ግል
ውሻው ካለሰንሰለት እየተሳብሁ እሄድለታለሁ! ሁኝ ያለኝንም እሆንለት ጀመር፡፡ እናቴም ከእሱ ጋር መሆን ደገፈችልኝ
የማላይበትን ውበት እየደረደረች አይታይሽም፧ እስኪ ተመልከች
እያለች እራሴን አይነ ስውር እንደሆንሁ እስክቆጥር ድረስ ግራ አጋባችኝ፡፡ ስለዚህ ፔድሮን በእናቴ ግፊት ልወደው ሞከርኩ፡
“የግንኙነቴን ጥልቀትና እንደ እንቁላል ተጠንቅቄ
እንደያዝሁት የተገነዘበው
ፔድሮ ግን ልቡ እያበጠ
ለፍቅር የዘረጋሁሉትን ልቤን ይጠብሰው ጀመር! እየቆየም በመጥፎ ባህሪው እየወጋጋ ማድማቱን ቀጠለ፡፡ ከእሱ ከተለየሁ ብቸኝነቱን ስለማልችለውግን
ስቃዬን አምቂ በትዕግስት እየተለማመጥሁ
የሞዴሊስነት ፍላጎቴን ገትቼ ለሶስት ዓመታት የመከራ ጊዜ አሳለፍሁ?።

“ሶራ! የሚገርምህ ደግሞ ያ የጭራቅ ልጅ አንድም ቀን "ቆንጆ ነሽ" ብሎኝ አያውቅም፡፡እንደወላጆቼ እሱም  አሞካሽቶኝ
አለማወቁ ደግሞ ፍርሃት ለቀቀብኝ፡፡ ከውጪ ሰው ይልቅ እነሱ ቆንጆ ነሽ ቢሉኝ ደስተኛ እሆን ነበር፡ ይህን ባለማለታቸው ግን
እራሴን ለማወቅ ወደ ሞዴሊስትነቱ ሞያ ተመለስሁ፡፡ ጅምናዚዬም
መሄድ አዘወተርሁ፡ በቁንጅና ውድድር ከተመረጡት አንዷ ብሆንም
ማሸነፍ ባለመቻሌ በገንሁ፡፡ ፔድሮ ያኔም ይጀነንንብኝ ነበር በመጨረሻ በቁንጅና ውድድሩ ባሽነፍሁበት እለት እናቴ አበባ አበረከተችልኝ፤ እሱ ግን ሳይመጣ ቀረ፡፡

“የሚገርምህ ያን ጭራቅ እንዲያ አንጀቴን እየበጣጠሰ ሲጥለው ልርቀው አልቻልሁም፡፡ ስለዚህ ከስፔን ውጭ ሄዶ ሥራ መስራት ማስታወቂያ ሲወጣ ከቤተሰቦቼ ለመራቅና እፎይታን
ለማግኘት አመች በመሆኑ እሱም እንዲወዳደርና አብረን እንድንሄድ
ጠየኩት፡፡

“ምን እንዳለኝ ታውቃለህ? ማራኪዋን አገሬን ጥዬ የትም አልሄድም አለኝ፡፡ የዚያን ቀን ብቻ ደፍሬ ገሃነም ግባ ብየው
በማስታወቂያው መሰረት ሄጄ አፍሪካ በተለይም አያቴ አገር ኢትዮጵያ እንዲመድቡኝ ጠየኳቸው፡፡ ሆኖም አላሰመረም፡ ሌሎች የአፍሪካ አገሮች እንጂ ኢትዮጵያ ከዝርዝሩ
ውስጥ እንደሌለችበት ሲነግረኝ እጢዬ ዱብ አለች፡፡ ከዚያ በኋላ ግን
ምርጫዬ አስፈላጊ ስላልነበረ የትም መድቡኝ ስላቸው ቡርኪናፋሶ
መደቡኝ፡፡
ሶራ የሚሳዝንህ ፔድሮ ውጭ አገር እንደማይሄድ
እንዳልነገረኝ ሁሉ ሃሣቤን ቀይሬ ተወዳድሬ ላቲን አሜሪካ ብራዚልን አግኝቻለሁና አብረን እንሃድ' አለኝ፡፡

የዛኑ እለት እኔጋ የነበረውን የአፓርታማችንን ቁልፍ
ወርውሬለት ሁለተኛ አጠገቤ እንዳይደርስ አስጠንቅቄው ሄድሁ፡፡ ከሱ
ከተለየሁ በኋላ ግን አይኔ የፈረጠ እስኪመስለኝ ድረስ ሳለቅስ አደርሁ: ጠዋት ከመኝታዬ ስነሳ ትክክለኛ ውሳኔ መወስኔን በመረዳቴ ትልቅ እፎይታ ተሰማኝ፡፡

“በልጅነቴ የወላጅ.
ከአደግሁ በኋላ ደግሞ የፍቅረኛዬ 'አፈቅርሻለሁ' አለማለት የማልወደድ
ቢያደርገኝም ወደ አፍሪካ ከመሄዴ ሦስት ወራት በፊት
የተዋወኳቸው የተለያዩ ወንዶች ግን ውበቴን እያዩ የተንጠለጠለ ሥጋ እንዳየ ድመት እየተቁለለጩ  ሲያላዝኑ ስሰማና በተለይም
በጓደኝነት የያዝሁት ፎራንችስኮ መላ ሰውነቴን እየላሰ “ቆንጆ ነሽ…
ውሸት  ነው!.." እያለ  ደርቆ የነበረውን ሞራሌን  በፍቅር ዜማ ሲያረሰርሰው ድርቆሹ ሞራሌ እንደገና ለመለመ፤ እንደገና ታነፀ….አፍሪካ ሄጄ ስመለስ ግን የቁንጅናን ትልቁን ትርጉም አወቅሁት‥
አካላዊ ሳይሆን ህሊናዊ መሆኑን….

“ሶራ! ይታይሃል ከፊት ለፊታችን ሊዝበን ናት
የፖርቹጋል ዋና ከተማ፡፡ ወደ ጕብኝት ቦታችን እየደረስን ነው" ብላው ከመርከቡ መቀመጫ ተነሳችና ሄድ ብላ ወገቧን ለማንቀሳቀስ ከወገቧ እጥፍ ብላ ስፖርት ስትሰራ አየው  ጥቁር ፓንቷን…
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
"ሔሉ… ሔሉ… ካርለት አልፈርድ ነኝ ከአዲስ አበባ"

"ሃይ ካርለት! ደህና ነሽ? ስፖንሽኛውን ስታቀላጥፈው
ገረመኝ እኮ"

“እውነትሽን አመሰግናለሁ፡፡
አዲሳባ ከመጣሁ
አምስተኛ ቀኔ ነው፡፡ ወደ ሐመር ከአንድ ሣምንት በኋላ እሄዳለሁ፡፡ መቼ ልትመጭ አስሰሻል?"

“አዝናለሁ ላገኝሽ የምችል አይመስለኝም፤ ምክንያቱም እኔ ከማድሪድ ወደ ሮም ከዚያ ወደ አዲሳባ የምበረው የዛሬ አስራ
አምስት ቀን ነው፡፡ ባገኝሽ ደስ ይለኝ ነበር፡፡

“አልችልም ኮንችት ቶሉ መሄድ አለብኝ፡፡ ምናልባት…" ካርለት ፀጥ ብላ አሰበችናi “ምናልባት አዲሳባ ስትመጭ የሚቀበልሽ ሰው ላስተዋውትሽ እችላለሁ፡፡ ሔሎ! …”

“አመሰግናለሁ ካርለት፡፡ አንችን ማግኘት ካልቻልኩ ለጊዜው ችግር የሚያጋጥመኝ አይመስለኝም፧ አብሮኝ የሚመጣ ኢትዮጵያዊ
አለ  ሔሎ!"

“ሔሎ  ኢትዮጵያዊ!” ካርለት አዕምሮዋ ደነሰባት፡፡

“ጥሩI እንግዲያው እዚህ ከመጣሽ በኋላ" ተቀጣጠሩና ካርለት ስልኩን ዘጋችው፡፡ በአይነህሊናዋ ኮንችትን ልታስታውሳት
ሞከረች ረጅም ሸንቀጥ ያለች ውብ ጠይም! ካርለት ከንፈሯን እንደ ጡጦ ጠብታ እራሷን ወዘወዘች፡፡
::::::::::::::::::::::::::::::
ካርለት ዋና የለመደችበትን
ጊዜ አታስታውሰውም፡
ምናልባት በእናቷ ሆድ ካለበለዚያም ገና ጨቅላ እያለች፡ ቁም ነገር
ብሎ የነገራት የለም፡፡ ጥሩ ዋናተኛ ሆና ነው ራሷን የምታውቀው፡
ግዮን ሆቴል የሄደችውም ለመዋኘት ነው፡፡ ብቅ ጥልቅ, ብቅ ጥልቅ
ውሃው ውስጥ ግልብጥ እያለች የግዮንን ሆቴል መዋኛ በቁመትና በወርዱ እየዋኘች አሳ ሆና ለመቆየት፡፡ ከዚያ ፎጣዋን አንጥፋ ገላዋን
👍20🥰1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

////

ከጋሽ ሙሉ አለም ጋር ከተነጋገርን በኃላ አዎጪ ስራ ለመምረጥ ያልበረበርኩት ዌብ ሳይት ያላማከርኩት የቢዝነስ ሰው...በሰበብ አስባብ ያልጎበኘሁት የንግድ ተቋም የለም።ምንም ግን ልቤን እርግጥ አድርጎ ሞልቶ በቃ ይሄንን ነው ብዬ እንድወስን የሚያደርገኝ ስራ በቀላሉ ማግኘት አልቻልኩም። ሰው ደግሞ አላውቅም የሚለው ነገር የለውም፡፡ ትንሽ መንገድ ካሳዪት በማንኛውም ነገር ከኤክስፐርት በልጦ ይቦተረፈዋል።

"እኔነኝ ያለ አሪፍ ቡቲክ ብትከፍት በጣም ትርፋማ ነው የምትሆነው...በተለይ የሴቶች ካረከው ትርፍህ ባለሁለት ስለት ነው የሚሆነው..እነዚህ የሀብታም ቺኮችን ገንዘባቸውንም ውበታቸውንም እጥብ ነው የምታደርገው...››እንደዚህ የመከረኝ ጎረምሳ  ነጋዴ እንዳይመስላቹሁ  የአምስት ልጆች አባትና ባለሁለት ቀለም ፀጉር ባለቤት የሆነ አዛውንት ነው።
"ለምን ማሳጅ ቤት አትከፍትም›› ያለኝ ሰውም አለ...
"በአሁኑ ጊዜ አዎጪው ስራ ድለላ ነው፡፡ ፍቃድ አውጣና የውጭ ስራና ሰራተኛ አገናኝ ብትሆን አሪፍ ትሸቅላለህ..በጎንም ቤት መደለል ፤:መኪና መደለል ፤ሴት መደለል አይነት አዋጪ ስራዎችን ትሰራለህ

የሪል እስቴትና የባንክ ቤት ኤጀንቶችም "ከሰርኩ አልከሰርኩ እያልክ ምን አጨናነቀህ፡፡ በገንዘብህ አክሲዬን ግዛበት.፡፡ አንተ ዘና ብለህ በየአመቱ በምትዝቀው የትርፍ ድርሻ ብቻ  ዘና ብለህ መኖሮ ነው››ብለውኛል
"በአጠቃላይ በሰሞኑ ውጣ ውረዴ የተረዳሁት አንድ ነገር ቢኖር ከዚህ በፊት ስራ ለመጀመር ትልቁ መስፈርት መነሻ ካፒታል ማግኘት ብቻ ነበር የሚመስለኝ፤ለካ መጀመሪያ አውጥተን አውርደን ይሄንን ስራ በዚህ አይነት ሁኔታ  እንሰራለን የሚል ቢያንስ መነሻ የሚሆን ሀሳብ በውስጣችን ከሌለን  ገንዘቡ ቢኖር እንኳን  ትልቅ እራስ ምታት ውስጥ ነው የምንወድቀው ?
ስዞር ውዬ ደክሞኝ ወደቤት ገባሁና አልጋዬ ላይ በቁሜ ወደቅኩበት ...ተንሳጠጠ፡፡

"ጎረምሳው ቀስ..."

"አያቴ...ደክሞኛል"

""የትኛውን ተራራ ወጥተህ ነው ይሄ ሁሉ ማለክለክ?"

"አረ ተራራ መውጣት ይሻላል...ሰው የሚሰራበት ገንዘብ ለማግኘት ይባክናል እኔ የምሰራው ስራ ማሰብ ና መወሰን ያቅተኝ።አረ ምን አይነት ቀሺም ነኝ?››

"እንኳንም አቃተህ"

"እንዴት አያቴ?"

"አየህ ተጨንቀህ ተጠበህ ያፈለቅከው ሀሳብ ጥልቀትም ውጤትም ይኖረዋል።"

"አይ አያቴ እስከአሁን ምንሞ የረባ ሀሳብ ላይ አልደረስኩም እኮ...የማማክረው ሰው ሁሉ ሺ ሀሳብ ነው የሚሰጠኝ...አንድ አሪፍ ነው ይሄን ስራ ጀምር ብሎኝ አሳምኖኝ ዞር ስል ሌላው ደግሞ ያንን ስራ ተሳስተህም ቢሆን እንዳትጀምረው አገርምድሩ የከሰረበት ስራ ነው ብሎ ኩም ያደርገኛል።

"እንደዛ ከሆነ ከማንም ምክር መጠየቅ አቁም.."

"ማለት?"

"ስለቢዝነስ መሠረታዊ ግንዛቤ ለማግኘት ይሄው በዚህ 15 ቀን ውስጥ የጠየቅካቸውና ያማከሩህ ሰዎች ከዩቲዩቨ እያወረድክ ያየሀቸው ቨዲዬዎች በቂ ናቸው"

"እና ምን ላድርግ?"

"እየሠማሀኝ አይደለም እንዴ ..?ምክር መጠየቅ አቁም እያልኩህ እኮ ነው"
"አያቴ ደግሞ… እርሷ እኮ ሌላ ሰው አይደሉም የቢዝነስ  ፓርትነሬ ኗት"

"ቢሆንም ስራአስኪያጅና  ፈላጭ ቆራጩ አንተ ነህ"

"አያቴ ደግሞ..እሺ የመጨረሻ ምክር ከእርሶ ልወሰድና ከዛ ያሉኝን አደርጋለሁ።››

"እንደዛ ከሆነ ሶስት ምክር ልስጥህ "

‹‹ደስ ይለኛል"

"1 አንተ የተሻለ ግንዛቤ ወይም እውቀት ባለህ የስራ ዘርፍ ብትሰማራ ተመራጭ ነው።ቀጥረህ የምታሠራው ስራ ቢሆን እንኳን ለመቆጣጠር የተወሰነ ግንዛቤና እውቀት ሲኖርህ  ውጤታማ ይሆናል፡፡

2/የምትወደውና የምትደሰትበት...ትርጉም የሚሰጥህ ስራ ቢሆን የግድ ባይሆንም የተሻለ ነው"..ኢንጂነር ኮንትራክተር እንደሚሆነው...የህክምና ዶክተር ክሊኒክ እንደሚከፍተው ማለት ነው

3/ኪሳራ የሚባል ነገር  ከአዕምሮህ አውጣ...ፍፅም ኪሳራ የሚባል ነገር በህይወት የለም ..ይህ የመጀመሪያ የቢዝነስ ስራህ ነው፤ አሁን የምትጀምረውን ስራ ለሁለት አመት ከሰራህ በኃላ  ከስረህ ብትዘጋው ያጣሀው ገንዘብ ነው ግን ከፍተኛ ልምድ ታካብትበታለህ… ቀጣይ ስራ ሀ ብለህ ለመጀመር እንደአሁኑ ድንብርብርህ አይወጣም...በል አሁን ተኝተህ አስብ››

"እሺ አያቴ አመሰግናለሁ "

ይሄንን ከተነጋገርን ከአራት ቀን በኋላ የሚገርም አጋጣሚ ተከሰተ፡፡ አንድ አለማያ አብረን የተማርን የቢሾፍቱ ልጅ ነበር..ከዛ እንደወጣ ወላጆቹ የችግኝ ስራ ይሰሩ ስለነበር እሱም ተቀላቀላቸውና መስራት ጀመረ..ሞያው ስለሆነ በሁለት አመት የሚገርም ለውጥ አመጣ ፡በሶስተኛው  አመት 2 ሺ ካሬ  መሬት ተከራይቶ ...የተለያዩ የአበባ አይነቶች ፤ለግቢ ውበት ማስጌጫ ተክሎች፤ ለምግብ የሚሆኑ አትክልቶች  መንጎ፤ፓፓያ ፤አቡካዶ በስፋት አምርቶ ማቅረብ ጀመረ…

የዘንድሮውን ምርትም ለገበያ ለማቅረብ ሁለት ወር ሲቀረው  የውጭ እድል አገኘና  ጠቅላላ ልማቱን ባለበት ለመሸጥ ገዢ በማፈላለግ ላይ እንደሆነ ሰማሁና ደወለኩለት ..፡፡እርግጥ ከአንድ ሰው ጋር ተነጋግሬና ተስማምቼ ነበር፤ ቢሆንም.እኔ ስራውን ለሚያውቅና ለማውቀው ሰው መሸጤ ነው በጣም የሚያስደስተኝ…የአትክልት የማልማት ስራ ልጅ ከማሳደግ ጋር የሚያመሳስል ነገር አለው…ዝም ብሎ ብር የማግኛ ስራ ብቻ አይደለም…የተቀዳደደ እና የተቦተራረፈውን  የተፈጥሮ ልብስ በጥንቃቄ የመስፋትና የማደስ ፤ እፍረቷንም የመሸፈን ስራ ነው፡፡ ..ግን ትንሽ ተወደደብኝ ካላልክ.. እርግጥ ከሁለት ወር በኃላ ብሸጥ አገኘዎለሁ ካልኩት ብር  ከግማሽ በላይ ቀንሼ ነው የምሸጠው አለኝ
"መጀመሪያ ልየው አልኩት፡፡በፈለከው ሰአት ቢሾፍቱ ናና ደውልልኝ አለኝ..ጊዜ ሳልፈጅ እየበረርኩ ሄድኩና  አየሁት  ..ከገመትኩት በላይ በጣም ማራኪና አስደማሚ ሆኖ አገኘሁት ...እሱም በቦታው ላይ ስራ ከሁለት አመት በፊት  ሰራ ሲጀምር እንደዚህ አይስፋ እንጂ የተወሰነውን ባለበት ከሰው ገዝቶ እንዳስፍፍው አስረዳኝ ..በተቻለኝ መጠን ፎቶም ቪዲዬም አነሳሁ።አንዳንድ  ብቻውን በመኪና ተጭኖ ሄዶ ሲተከል መለስተኛ ዛፍ የሚሆንና ከ10 ሺ ብር በላይ የሚያወጡ በርከት ያሉ ዛፎች ያሉበት ነው። ዎጋውን የአምስት ወር ከተከፈለበት የመሬት ኪራይ ጋር 350 ሺ ብር አለኝ።  ከሸሪኬ ጋር ተማክሬ በአንድ ቀን ውስጥ አሳውቅሀለሁ ብየው   ወደአዲሳባዬ ተመለስኩ።

እቤት እንደደረስኩ .."አያቴ"
"አቤት መጣህ..የት ጠፍተህ ነበር?"
"የሆነ ቦታ ሄጄ ነበር፡፡ ቀላል እቃዎችን በምንቀባበልበት  ስንጥቅ እጄን አሸልኬ""እንኩ ይቀበሉኝ"
"ምንድነው...?ሞባይልህን ምን ላድርገው?።››
"አሁን ትክክለኛ የምንሰራውን ስራ ያገኘው ይመስለኛል...እስኪ ቪዲዬውንም ፎቶዎችንም ይዩት"
"ከተቀበሉኝ በኃላ..ለ15 ደቂቃ ንግግር አልነበረም... ዝም ማለታቸው ያልጣማቸው ነገር ስለአለ ነው ብዬ ደነገጥኩ .. ፈራሁም።ምክንያቱም ስራውን በጣም ከልቤ ነው የፈለኩት.ደግሞም በሙሉ የራስ መተማመንና በዕውቀት የምሰራው ስራ ነው….ይሄ ግን ለእሷቸው ካልተገለፀላቸው የእኔ መሻት ብቻ ዋጋ የለውም፡

"ለዚህ እኮ ነው የምወድህ?"

"ምን አሉኝ አያቴ?"

"ውብ የሆነ  ስራ መርጠሀል"

"ወደዱት..ልጁ ጓደኛዬ ነው ማለት አለማያ አብረን ነው የተማርነው ..አሜሪካ የመሄድ እድል ስላገኘ ባለበት ሊሸጠው ነው የፈለገው። ሌላ ሰው ሊገዛው ጠይቆታል እሱ ግን ሰውዬው የሰጠኝን ምትከፍለኝ ከሆነ ላንተነው መሸጥ የምፈልገው ብሎኛል››
👍735👏1
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


‹‹እና ምን እያልከኝ ነው››

‹‹አንቺም የተሰጠሸን ህይወት ሙሉ በሙሉ ተቀበይው፤ገዳይ ሆንሽ አስገዳይ….ፃድቅ ሆንሽ ሀጥያተኛ….መጀመሪያ ባለሽበት ሁኔታ እራስሽን ተቀበይ፡እናም ደግሞ ሁሉም ሰው ከውጭ እንደምትመለከቺው እንዳልሆነም እወቂ..ስለዚህ አንቺም እራስሽን እንደምታይው ብቻ አይደለሽም፡፡ ልዩ ማለት ከሺ በላይ በጣም ድንቅ የሆኑ መልካም ምግባሮችና ፀባዬች ያሏት እንዲሁም በመቶ የሚቆጠሩ ትንሽ ሚጎረብጡና መስተካከል ያለባቸው እንቅፋቶች የተጋረጡባት ወኔ ሙሉ እና በኃይል የተሞላች ወጣት ነች፡፡ይሄንን ካወቅሽ ከነዛ መቶ እንቅፋቶች ላይ በየጊዜው የተወሰኑትን እየቀረፍሺ ሺዎች ላይ እየጨመርሽ መሄድ ብቻ ነው የሚጠበቅብሽ፡፡

እወቂ መቼም መቶውንም እንቅፋት በአንዴ ማስወገድ አትችይም፡፡ በአመት 10ሩን እንኳን ካስወገድሽ በቂና ድንቅ ነዋ.. ዋናው ከአምናው በሆነ ነገር የተሻልሽ ሰው መሆንሽ ነው፡፡ ..እወቂ ሰው እስከሆንሽና በዚህ ምድር ላይ መኖር እስከቀጠልሽ ድረስ ፍፅም ሰው መሆን አትቺይም …ማንም ደግሞ እንደዛ እንድትሆኚ አንቺን የመጠየቅ ሞራል የለውም፡፡እሱም እንደዛው በመቶዎች የሚቆጠሩ የህይወት እንቅፋቶች በውስጡ ተሸክሞ ስለሚዞር ማለቴ ነው፡፡እና እራስሽን የተለየ ችግር እንዳለብሽ አድርገሽ በማሰብ ነፍስሽን ማሰቃየት አቁሚ…..››

በተመስጦ ቀል በባል ካዳመጠችው በኃላ‹‹አመሰግናለሁ..አንተ በጣም ጥሩ ሰው ነህ፡፡››አለችው

"እኔ ደጓች ስላሰደጉኝ ደግ ከመሆን ውጭ ምርጫ የለኝም። ››
"ልክ ለእኔ ደግ እንደሆንከው ማለትነው"
"ማለት?"

‹‹እንዴት ማለት አለ ስሰርቅህ ያዝከኝ ግን አብረኸኝ ተደበደብክ"
"አዎ ጥሩ ምሳሌ አመጣሽ ..ለአንቺ መስረቅ እኔም ከጥፋተኝነት እራሴን ንፁህ ማድረግ አልችልም፡፡ስልክ አያያዜ በጣም እንዝላልና ግዴለሽነቴን የሚያሳብቅ ነበር..አንቺ ለመስረቅ ስትመጪ እኔም ለመሠረቅ ዝግጅ ሆኜ ነበር እየጠበቅኩሽ ያለሁት፡፡ስለዚህ ከደሙ ንፁህ ነኝ ማለት አልችልም...ብደበደብም በገዛ ጥፉቴ ነው።››
‹‹አንተ መንፈሳዊና መልካም ሰው ከሆንክ ክፍትንና ክፉዎችን፤ ሀጥያትንና ሀጥያተኞችን አጥብቀህ ማውገዝና መኮነን አለብህ..አሁን ግን እንደማየው እየተከላከልክላቸው ነው"
"አደበላለቅሽው….እንዳልሽው ክፍትንና ፤ሀጥያትን አጥብቄ አወግዛለሁ። ክፍዎችንና ሀጥያተኞችን ላልሽው ግን አላደርገውም።እነዚህ ክፉና ሀጥያተኛ ሰዎች የሚያስፈልጋቸው መወገዝና መወቀስ አይደለም፡፡ መፈቀርና መደመጥ ነው የሚፈልጉት። ከልክፍታቸው ለመፈወስ ህክምናው ፍቅር ነው። ውግዘትና ስድብማ እሳት የሆነ ተግባራቸው ላይ ቤንዚል ጨምሮ ማቀጣጠል ማለት ነው።ደግሞ ማንም ከመሬት ተነስቶ በፍቃድ ገዳይም ዘራፊም አይሆንም...ትናንትናውን ያበላሸበት አንድ ሰው ወይም አንድ አጋጣሚ ይኖራል። እያንዳንድ ወንጀለኛ ሰው በግለሠብ ደረጃ ኃላፊነት ቢኖርበትም በየደረጃው ያሳደጉት ወላጆች፤ ያስተማሩት መምህራን ፤አብረውት ያደጉት ጓደኞቹ ፤በውስጡ አቅፎ ያሳደገው ማህበረሰብ..እየተመላለሰ ሲያመልክበት የነበረው የሀይማኖት ተቋም፤ሲያስተዳድረው የነበረ መንግስት እነዚ ሁሉ የየድርሻቸውን ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው።ለአንድ ገዳይ ተገዳዩን ጨምሮ ከላይ የዘረዘርኳቸው በሙሉ ንፁህ አይሉም።›
‹‹እንዴ ተገዳዩ ደግሞ በመገደሉ የተሠራበት ግፍ ሳያንስ የምን ተጠያቂነት መሆን ነው?።
"ታሪኩን ስትመረምሪ በግልፅ ታገኚዎለሽ...የሆነ ነገር አድርጎ ገዳዩን አነሳስቶታል..ወይ ከሚስቱ ጋር ያልሆነ ቀረቤታ ፈጥሯል..ወይ በእምነት ያበደረውን ገንዘብ ክዶታል..ወይ እሱ ቸግሮት ባለበት ወቅት የበሬ ማሰሪያ የሚያህል ሀብል አድርጎ ተፈታትኖታል፡፡
"እንደዚህ እኮ ምታስበው አንተ ብቻ ነህ...››
"አይ ጥቂትም ቢሆኑ ሌሎቹም አሉ...ደግሞም አንቺም ብትሆኚ ከአሁን በኃላ እንደዚህ ከሚያስብት መካከል አንዷ የምትሆኚ ይመስለኛል፡፡"
"አይ አንተ ..እስኪ መጀመሪያ ከተፀናወተኝ ከዚህ ሌብነት ልፈወስ"
"ትፈወሻለሽ አይዞኝ"
"አይ አንተ እንዲህ ቀልድ መሠለህ ..እናቴ ከየአድባራቱ አስመጥታ ያረጨችኝ ፀበል የለም..ህክምናም በጣም ብዙ ሳይካታሪስቶች ሊያክሙኝ ሞክረዋል ..የመስረቅ ረሀቤ ትንሽ ጋብ እንዲልና ፋታ እየወሰድኩ እንዳደርገው ማድረግ ቻሉ እንጂ ከስሩ መንግለው ሊገላግሉኝ አልተቻላቸውም"
"ስለዚህ እራስሽን በራስሽ አክሚያ"
‹‹እሺ እንግዲህ እንዳልክ››
ልዩ ለጊፍቲ ቃል ቤት ከተገናኙ ከሳምንት በኃላ ደወለችላት
‹‹ሄሎ››
‹‹ሄሎ ማን ልበል?››አለቻት ግራ በተጋባ ድምፅ
‹‹አዲሷ ጓደኛሽ ነኝ፡፡ ››
‹‹ይቅርታ አላወቅኩሽም፡፡››
‹‹በቀደም ቃል ቤት እራሱ ቃል አስተዋውቆን ነበር፡፡››
‹እእእእእ…››የጊፍቲ የንግግር ቃና ደቂቃዎች ውስጥ ተቀየረ
‹‹አወቅሺኝ?››
‹‹አዎ…እሺ ምን ልታዘዝ?››
‹‹አረ አይባልም.. መጀመሪያ ሰላም ነሽ ወይ አይቀድምም?›
‹‹ይቅርታ ሰላም ነሽ?››
‹አለሁልሽ..እንደው ጊዜ ካለሽ ላስቸግርሽ ነበር፡፡››
‹ምንድነው .?ግን አሁን ስራ ቦታ ነኝ፡፡››
‹‹እኮ አውቀያለሁ መስሪያ ቤትሽ አካባቢ ነው ያለሁት.. ከ30 ደቂቃ በኃላ ስትወጪ እንድንገናኝ ፈልጌ ነው፡፡›
ልታገኛት ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላት በሚያሳብቅ ንግግር‹‹እሺ..ግን ለምን ጉዳይ ነው…?ከስራ በኃላም ሚመቸኝ አይመስለኝም…ሌላ ቀጠሮ ነበረኝ›› አለቻት…፡፡
ይህቺ ሴት እራሷን እያዋደደች ስለሆነ ቀልቧን ልግፈፈው ብላ ስሌት ሰራች‹‹የቃልዬን ምርጫ እኮ ከእኔ በተሻለ አንቺ ስለምታውቂው ብዬ ነው››አለቻት፡፡
‹‹የምን ምርጫ….ምን ማለት ነው››እንደገመተችው ጊፍቲ በደንብ ተነቃቃች….
ልዩም ሙሉ ትኩረቷን እንዳገኘች እርግጠኛ ስትሆን ንግግሯን አራዘመች‹‹አስራ ሁለት ሰዓት ላይ እራት ልጋብዘው ቀጥሬዋለሁ..እና ዝም ብሎ እራት ብቻ ከሚሆን የሆነ ስጦታ ልገዛለት ፈልጌ ነበር…ግራ ስለተጋባሁ በምርጫው ብታግዢኝ ብዬ ነው፡፡››
‹‹አሁን መጣሁ. 5 ደቂቃ ጠብቂኝ››ብላ ስልኩን ጆሮዋ ላይ ጠረቀመችው፡
እንዳለችውም 5 ደቂቃ እንኳን ሳይሞላ መጠች…ልዩ የመኪናዋን መስታወት ወደታች በማውረድ እጇን ወደላይ በመቀሰር እንድታየት ምልክት ሰጠቻት ..የጨለመ ፊት ይዛ እየተውረገረገች ወደእሷ መጣች..ፈጠን ብላ የገቢናውን በራፍ ከፈተችላት… ገባቸ ና ዘጋችው፡፡
ለሆኑ ደቂቃዎች ዝም እንደተባባልን ተጓዙ.. በመሀል ጊፍቲ እንዳኮረፈች መናገር ጀመረች‹‹ ምን አይነት ዕቃ መግዛት ነው ምትፈልጊው?›› ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹ውይ ሳልነግርሽ ተውኩት እኮ››
‹‹ምኑን?›
‹‹ስጦታ ልገዛ ነው ያልኩሽን ነዋ›
‹እየቀለድሺብኝ ነው እንዴ?›


ይቀጥላል
👍10416🥰6😁2🔥1🤔1
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///
‹‹አይ እንግዲያው እኔም አልደከመኝም…ካንቺ ጋር ዞር ዞር ብል ይሻለኛል›› አላትና አብሯት ወደፊት መጓዝ ጀመረ..ፈገግ አለች…ከእሷ ጋር መለያየት ስላልፈለገ እንጂ እንደደከመው ሁኔታውን አይቶ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል…ሰዎች ካሉበት አካባቢ አንድ 200 ሜትር ያህል  ርቀው ከተጓዙ በኃላ ዞር ያለ እና ለመቀመጥ ምቹ የሆነ ቦታ ስታገኝ ቀድማው ሄደችና ቁጭ አለች…ከዚህ በላይ አድክማ ልታማርረው አልፈለገችም›፡፡በረጅሙ ተነፈሰና መሬቱ ላይ ከጎኗ ተቀመጠ..

‹‹እሺ ሶፊ…ሀገራችሁ ያምራል››አላት

‹‹እርግጥ አህጉሩ የእኔ  ነው…ግን ሀገሬ እዚህ አይደለም››

‹‹እና ከየት ነሽ?››

‹‹ኢትዬጵያን ታውቀታለህ?››

በአግራሞት አይኑን ከፈተ ..ምን እንዳስደነገጠው አልተገለፀላትም….‹‹ሺ  ውቃያኖስ አቆርጦ የመጣው ሳያስደንቅ እኔ ከዚህች ከኢትዬጳያ መምጣት እንዴት ሊያስገርመው ቻለ?›› ብላ በውስጧ ጠየቀች፡፡

‹‹ኢትዬጵያን አውቃታለሁ በደንብ…..ጎንደርን አክሱምን፤አዲሰአባን በደንብ አውቃቸዋለሁ››አላት

‹ደሎመናንስ?›

‹‹ደሎ መና …ታሪካዊ ቦታ ነች?››
‹‹አዎ እኔን ያበቀለች ለምለምና ልዩ ቦታ ነች›አለቸው ፡፡እሱ ኢትዬጵያን አውቃታለሁ ብሎ የጠቀሳቸው ገናና ቦታዎች እሷ በጥቂቱ ታሪካቸውን እንጂ በአካል አታውቃቸውም…እሷ  አብጠርጥራ የምታውቃቸውንና ተወልዳ ያደገችባቸውን ቦታዎቸ ደግሞ እሱ አያውቃቸውም ፤አረ ምን ማወቅ ብቻ  ስማቸውን እንኳን በስህተት ሰማቷቸው አያውቅም፡፡
ግን ሲያወራ አይኑ ላይ ያነበበችው የራስ መተማመን መላ ኢትዬጳያን አብጠርጥሮ እንደሚያውቅ ነው፡ከዚህ ጉዞ እንደተመለሰች በቀጣይ ሰሜን ኢትዬጵያን ሄዳ መጎብኘት እንዳለባት እዛው ወሰነችና..ሰለ ደሎ መና እና ስለጠቅላላ የደቡብ ኢትዬጵያ አካባቢዎች፤ባሌ ፤ቦረና ፤ሱማሌ፤ ኬንያ ፤ሲዳሞ በትና ስታስረዳው እሱም በአድናቆት አፉን ከፍቶ አዳመጣትና ወደፊት ቦታዎቹን ለማየት እንደሚሞክር ነገራት፡፡

‹‹ይሄ ጉዞዬ የተለየ እንደሚሆን ገና ከመነሳቴ በፊትም ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ ነበር››

‹‹እና ወደድከው፡፡››

‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ ..?.ለአመታት ስመኘው የነበረ የህይወቴ ትልቁ ጉዞ እንዲህ በስኬት አጠናቅቄ ተደስቼ ሳልጨርስ አንቺን የመሰለች መላአክ መሳይ ወጣት ተዋወቅኩ››ሲላት ቅድም እንዳገኘችው ሲሰማት የነበረ አዲስ አይነት ስሜት መልሶ ተሰማት…፡፡

እኔም ስለገኘሁህ ደስ ብሎኛል…ሀገርህ ግን የት ነው?›ስትል ጠየቀችው…ሀገሩ የትም ቢሆን ግድ የላትም….የራሷን የተዘበራረቀ ስሜት ለማስተካከል ጊዜ ለማግኘት ብላ ነው ጥያቄውን የሰነዘረችው፡፡

‹‹አውስትራሊያ ነው..ግን እናቴ አሜሪካዊ ስለሆነች እዛም ብዙ ኖሪያለሁ››

‹‹አይ አሪፍ ነው…አንድ ቀን  አውስትራሊያን ለማየት ስመጣ አገኝህ ይሆንል?››

‹‹በጣም ደስ ይለኛል..››እንደዚህ እያወሩ ድንገት በተተተት ብሎ የሚመጣ ነገር ሰሙ..እሱ ደንግጦ ተለጠፈባትና ወደራሱ አጣብቆ አቀፋት …እሷ ፈርታ ሳይሆን መታቀፏ በጣም አስደስቶት አንገቱ ስር ውሽቅ ብላ ትንፋሿን በጀሮ ለቀቀችበት..ስራቸው ዷ. ብሎ የሆነ ነገር ወደቀ…እንደምንም ድፍረቱን አስባስቦ ሲያየው ቅድም ያገኛት ቦታ ጥለውት የመጡት የእሷን ሻንጣ ነው…እንደምንም እራሱን አረጋጋና ከእቅፉ እሷን በማላቀቅ  ሻንጣውን አምጥቶ ስራቸው በመወርወር ያስደነገጣቸውን ሰው ለማየትና ፤ ስላስደነገጣቸው ለመውቀስ ዙሪያ ገባውን ቢመለከት የሰው ዘር በአካባቢው የለም….ዞር ሲል ከበላያቸው ባለ ጉብታ ላይ ቅድም ያየው ንስር ጉብ ብሎ በመቀመጥ ወደእሱ አፍጥጦበታል፡፡

‹‹አንቺ ያወራሺኝ እውነትሽን ነው እንዴ?››

‹‹ምኑ?››

‹‹ስለንስሩ ቅድም የነገርሺኝ …ይሄንን ሻንጣ ይዞልሽ የመጣው እሱ ነው?›

‹‹ሻንጣው ቀላል ነው…እኔንም ጨምሮ ከኢትዬጵያ ድረስ ይዞኝ የመጣው እኮ እሱ ነው››
‹‹እየቀለድኩ እኮ አይደለም?››

ይሄንን ሰው ወዳዋለች…እናም  ልታስደምመውና ይበልጥ ልቡንም ቀልቡንም ለመቆጣጠር ፈልጋላች፡፡
ቋንቋዋን ወደ ኦሮሚኛ ቀየረችና ‹‹ጀግናዬ ..ሰውያችን እንዴት ነው?›› ስትል ጠየቀችው፡፡አእምሮውን ከፈተላትና ስለእሱ በወፍ በር አስቃኛት… የዩኒቨርሲቲ መምህር ነው፤ሁለት መፅሀፎች የፃፈ ደራሲም ነው፤አለገባም ግን ሴት አውል ነው፡፡ሴት ወደ ህይወቱ ስቦ ሲያስገባ ሰዓታት አይፈጅበትም…ሲቀበልም ደግሞ በሙሉ ፍቅር እና ለጋሰነት   ነው፤እንክብካቤውም ወደር አልባ ነው፤ግን ደግሞ መልሶ ገፍትሮ ከልቡ ሲያወጣ አንድ ወር አይፈጅበትም፤ንስሯ የነገራት መረጃ መስማት ስለፈለገችው ጉዳይ ብቻ  ነው፡፡ከዚህ በፊት ስለእንደዚህ አይነት ጉዳይ የሰውን ታሪክ ልባቸው ውስጥ ገብቶ እንዲሰልልላት ጠየቃው አታውቅም… ወንዶችንም በተመለከተ በራሷ ያለት ልምድ ለዜሮ የቀረበ  በመሆነ  ባህሪውን ከሌላ ወንድ ጋር ልታነፃፅርና ፍርድ ልትሰጥ አትችልም…ደግሞ እሷ ከእሱጋር ቢበዛ  3 ቀን ብቻ ነው ልታሳለፍ የሚትችለው፡፡በዛ ሶስት ቀን የሚታወስና ሚያዝናና ቀን ከእሱ ጋር ካሳለፈች ከዛ በኃላ ለእድሜ ልክም አታገኘውም፡፡ ስለዚህ የእሱ ታማኝነት እና አለመታመን እንደማያስጨንቃት እራሷን አሳመነች..ንስሯ እዚህ ላይ አንድ ተንኮል ሰራባት ፤ሳትጠይቀው የብልቱን መወጣጠር በእመሮዋ ላይ ቦግ ብልጭ ቦግ ብልጭ እያደረገ አሳያት ..አፈረቸና በፈግግታ እንደታጀበች ፊቷን አዙራ አቀረቀረች..

‹‹ምን እየሆንሽ ነው..?ብቻሽን ትስቂያለሽ እንዴ?››

‹‹ንስሬ እኮ ነው››

‹‹ንስርሽ እኮ አርፎ ተቀምጦል …ምንም አይነት እንቅስቃሴ እያደረገ አይደለም››

‹‹ባክህ በእምሮዬ የሚያስቅ መልዕክት ልኮልኝ ነው››

‹‹ምን አይነት መልዕክት.እስቲ ልስማው?››

‹‹ስለአንተ ነው››
ይበልጥ ደንግጦ‹ስለእኔ ምን?››

‹‹ሴት ይወዳል እያለኝ ነው››

‹‹ይሄ ያንቺ ግምት ነወ››

‹‹የብልትህን ተገትሮ መቆሙን አሳይቶኛል››

ቶሎ ብሎ አይኖቹን ወደእግሮቹ መካከል ላከና አቀማመጡን አስተካከለ

‹‹ምትገርሚ ሰው ነሽ…እሱንም አይተሸ ነው…አንቺን ከመሰለች ውብ አፍሪካዊት ሴት ጎን ተቀምጬ ባይቆምብኝ ነው የሚገርመው››አላት፡፡

‹‹ካትሪንን ነው ወይስ ሱዛናን ማናቸውን ነበር ይበልጥ የምትወደው?››

ሆን ብላ የምትለውን እንዲያምናት ነው የቅርብ ጊዜ የፍቅር ተጣማሪው የነበሩትን ሴቶች ስም የጠራችለት፡፡ምንም ሳይናገር ዝም ብሎ አፍጥጦ  ያያት ጀመር…. የሚያያት በአድናቆት ብቻ ሳይሆን በፍራቻም ጭምር ነው፡፡

‹‹ጀግናዬ አንዴ ሽንቴ መጥቷል እታች ወደ ጨካው አካባቢ ትወስደኛለህ?›› ስትለው ንስሩ ከለበት ቋጥኝ ክንፉን እያማታ ወደላይ ተነሳና መልሶ ዳይቪ ገንዳ ውስጥ እንደሚገባ ዋናተኛ ወደታች እየተምዘገዘገ መጥቶ ከተቀመጠችበት ደረሰና እሷን ማጅራቷን ይዞ ወደ ላይ አንጠልጥሏት ሲነሳ እሱ በድንጋጤ አደጋ ላይ የወደቀች መስሎት ሊያስጥላት እግሯን ለመያዝ ቢሞክርም ንስሩ ከወዲህ ወዲያ እያወናጨፈ    ሸወደውና ሙሉ በሙሉ ወደላይ ይዟት በመነሳት በጉም በተሸፈነው ሰማይ ውስጥ ይዟት ገባ.፡፡
👍97😁128👏2🔥1🥰1😱1
#ትንግርት


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


‹‹በጊዜ ነበር እኮ መምጣት የፈለኩት ለሆነች ጉዳይ ከአንድ መስሪያ ቤት ወደ ሌላው ስሯሯጥ መሸብኝ›› ሠሎሞን ነው፡፡

‹‹ምንም አይደል ዋናው መምጣትህ ነው›› ፎዚያ መለሠችለት ከፍሪጅ ያወጣችውን ቀዝቃዛ ቢራ ከፍታ ፊት ለፊቱ እያስቀመጠች፡፡

‹‹ወድጄ መሠለሽ ፤ ያ እብድ ሳታያት እንዳታድር ብሎ ስላስገደደኝ ነው የመጣሁት፡፡››

‹‹ሁሴን እያት ባይልህ አትመጣም ነበር ማለት ነው?›› አለችው ትንሽ እንደማኩረፍ ብላ፡፡

‹‹አይደለም፤ እንዲሁ ነገፀሩን አልኩ እንጂ መምጣቱንማ እኔም እፈልገው ነበር ምነው ቆመሽ ቀረሽ አንቺም ያዥና ቁጭ በያ ::

ፍሪጁን ከፍታ ሚሪንዳ አውጥታ ከፍታ ፊት ለፊቱ ቁጭ አለች፡፡

‹‹አይ ይሄማ አይሆንም.ቢራ ከሌለ ወጣ ብዬ ገዝቼ እመጣለሁ ካለበለዚያ ግን እኔን አልኮል እየጋትሽ አንቺ ለስላሳ እንዳትከፍቺ››

‹‹እንዴ! አረ እኔ አልጠጣም ።.››

‹‹ይቅርታ እንደዛ ፓጋን መስለሺኝ ነው፡፡

‹‹እዚህ ጋር ወራጅ አለ…እኔ ፊት እሱን መተቸት ክልክል ነው፡፡.››

‹‹ተቀብያለሁ...ለመሆኑ ዛሬ ደውሎልሻል?››

‹‹አልደወለልኝም ትናንት ነው የደወለልኝ ፣እንደውልለት እንዴ?››

‹‹አይ ተይው አሁን ከሀያ ደቂቃ በፊት አናግሬዋለሁ፡፡.››

‹‹እንዴት ነው ተሳካለት?›› በጉጉት ጠየቀችው፡፡

‹‹አልተሳካለትም፡፡ዛሬማ ሊያብድ ደርሷል፡፡እኔ በበኩሌ ምን እንደሚሻለው ግራ ግብት ብሎኛል፡፡.››

‹‹ምን አንተ ብቻ ኧረ እኔም የማደርገው ጠፍቶኝ እንዴት እንደተጨነቅኩ ብታይ! ወይኔ ወንድሜን ምን አይነት ምትሀተኛ ልጅ ገጠመው?

‹‹ያን ያህል ትወጂዋለሽ ማለት ነው?››

‹‹ምን አይነት ጥያቄ ነው የምትጠይቀኝ? እሱ እኮ ለእኔ ወንድሜም፣አባቴም፣ መላ ቤተሠቤ ማለት ነው፡፡መውደድ የሚለው ቃል ብቻ ይገልፀዋል፡፡.››>

ሠሎሞን በስሜት እየተንዘረዘረ ስታወራው በአንክሮ እየተመለከታት ውስጡ ቅናት ነገር ብልጭ አለበት‹‹እኔን ይሄን ያህል ከልብ የሚወደኝ ሠው ይኖር ይሆን? >> ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡ ቢያስብ ቢያስብ ከልጆቹ በስተቀር ማንም ትዝ ሊለው አልቻለም፡፡ የቀረውን ቢራ
ጨለጠና እርሱ ተነስቶ ፍሪጁን ከፍቶ ድጋሚ ቢራ አውጥቶ ከፈተው፡፡

‹‹እኔ የሚገርመኝ ምን እንደሆነ ታውቃለህ?›› ፎዚያ ነች ንግግሯን የጀመረችው፡፡

‹‹ካልነገርሽኝ አላውቅም፡፡››

‹‹የትንግርት ነገር!››

‹‹የእሷ ነገር ስትይ?››

‹‹አብራው መንከራተቷ ነዋ፡፡ ምንም ቢሆን መቼስ አንሶላ መጋፈፋቸው አልቀረ፡፡ ያፈቀርኳትን ሴት አፋልጊኝ ሲላት እሺ ብላው አብራ መሄዷ፡፡

‹‹ምን ታድርግ! መቼስ የሚያፈቅሩት ሠው ሲያብድ ወይ በሠንሠለት አስሮ ህክምና መውሠድ አልያም ደግሞ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ በሄደበት እየሄዱ ባደረበት እያደሩ ደህንነቱን መከታተል ነው.…እሷም እያረገች ያለችው እንደዚሁ ነው፡፡››

‹‹በፊት ለእሷ ያለኝ ስሜት የቀዘቀዘ ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን እየወደድኳት መጣሁ፡፡››

‹‹በደንብ ውስጧን ብታውቂ ደግሞ ይበልጥ ታፈቅሪያታለሽ፡፡ ልዩ ሠው ነች፡፡ ምን እንዳደረገባት አላውቅም እንጂ እኔ እሱን ብሆን ዓይኔ ከእሷ ውጭ ሌላ ሠው አያይም ነበር፡፡ በስብዕናዋ፣በጥበብ አፍቃሪነቷ፣ በአስደሳች ገፅታዋ፣በምሁራዊ ምልከታዋ፣የሕይወትን ውስጠ ምሥጢር አብጠርጥራ በማወቋ በቃ በሁሉም ነገሯ ለእሱ የምትገባ ሴት ነበረች፡፡እንዴ! ትንግርት ማለት እኮ አንድ ሴት ሳትሆን አስር ሴት ነች፡፡››

‹‹ኤደንስ?››

‹‹የእሷ ትንሽ የተለየ ነው፡፡››

‹‹የተለየ ስትል?››

‹‹አየሽ ኤደን ስርዓቷም ሆነ አስተዳደጓ ለሁሴን የሚሆን አይደለም፡፡ ኤደን ማለት የተለመደች አይነት ሴት ነች፡፡ ቆንጆ ነች፣ ሃይማኖተኛ ነች፣ባህል አክባሪ ነች፣ አብዛኛው ህብረተሠብ በመኖር ላይ ያለውን ኑሮ መኖር የምትፈልግ ሴት ነች፡፡ ጋብቻ፣ ሠርግ፣ እቁብ፣ ዕድር፣ አራስ-ጥሪ፣ ክርስትና፣ ለቅሶ ... የመሳሠሉትን ማህበራዊ ሠንሠለቶችን ሳታዛንፍ መከወን የምትፈልግ ሴት ነች፡፡ ሁሴንን ተመልከተችው ከህብረተሠቡ ጋር ያለው ግንኙነት የላላ፣ ከባህሉ ጋር ያለው መስተጋብር የረገበ፣ እንዲሁም የግሌ ሃይማኖት አለኝ ብሎ የሚፈላሠፍ ግለሠብ ነው፡፡ ታዲያ እነዚህ በሁለት ጽንፍ ያሉ ግለሠቦች እንዴት ይጣመራሉ? መጀመሪያ እንደውም ለምን አታገባትም ብዬ እጨቀጭቀው ነበር፤ አሁን በደንብ ቀርቤ ሳያትና ልዩነታቸውን ስገነዘብ የእሱ ውሳኔ ትክክል እንደነበር ነው የገባኝ፡፡ እሷ ባይሆን ለእንደኔ አይነቱ ተመራጭ ነች፡፡›› በፈገግታ ንግግሩን አጠናቀቀና ቢራውን አንስቶ ተጎነጨ፡፡

‹‹ለእንደኔ አይነቱ ስትል?››

‹‹አየሽ እኔም እንደ እሷ የተለመደ አይነት ኑሮ ነው የሚመቸኝ፡፡ ፍልስፍና ቅብጥርሴ ያን ያህል አይደለሁም፡፡ አብዛኛው እሷን የሚመቿት ነገሮች እኔንም ይመቹኛል፡፡ በዛ ላይ ቆንጆ ነች፡፡ ገንዘብ አባካኝ አይደለችም፣ እንደውም ጠንካራ ሠራተኛ ነች፣ ታማኝ ነች፣ እነዚህ ነገሮች ደግሞ እኔ በጣም እምፈልጋቸው ናቸው››

ከመጠጡ ጋር ወደ ውስጡ የዋጠውን ንግግሩን ስታላምጠው የሆነ ነገር ጫረባት፡፡ ‹‹ያፈቅራት ይሆን እንዴ?›› ስትል አሠበችና ማረጋገጥ ፈለገች፡፡

‹‹መጀመሪያ የሁሴን ፍቅረኛ ባትሆን ኖሮ እሷን ማግባት ትፈልግ ነበር?››

መልስ ሳይሠጣት ለደቂቃዎች በአትኩሮት ተመለከታትና መናገር ጀመረ<<አዋ እሺ ካለችኝ ለሁለተኛ ጊዜ ላገባ የምፈልገው እሷን ነው፡፡ ደግሞም እሺ የምትለኝ ይመስለኛል›

ደነገጠች፡፡ የሠከረም መሠላት ‹‹ስለ ኤደን እኮ ነው የምናወራው››

«አዎ ምነው?>

‹‹አገባታለሁ ስትል ምን ማለትህ ነው? የሁሴን ፍቅረኛ እኮ ነበረች፡፡››

‹‹ነበረች፤ አሁን ግን አይደለችም፡፡ ከተለያዩ አመት ሊደፍን ነው›

‹‹ቢሆንም የሁሴንን አምቧረቀችበት፡፡

ፈገግ አለና ‹‹ባክሽ አታካብጂ .. በመጀመሪያ ሀሳቡን ያቀረበው እርሱ ነው፡፡ ሁሴን ማን እንደሆነ አታውቂም መሠለኝ›

‹‹ይሄንን ነገር እኔ አላምንም ደግሞም ያው እሱ እብድ ነው ሊልህ ይችላል፡፡ እሷ ግን በፍፁም እሽ አትልህም፡፡››

‹‹በተወሠነ መልኩ ትክክል ነሽ፡፡ እስከ አሁን አገባሀለሁ ብላ ቃሏን አልሠጠችኝም፤ግን
የተወሠነ መንገድ ተጉዘናል፡፡››

‹‹ምን ዓይነት መንገድ?››

የሁለት ወር ጉዞ፡፡ እርግጥ የመጀመሪያ ቀን አብረን ስናድር አቅደን አይደለም፤ በተለይ እሷ በአዕምሮዋም አልነበረም፡፡

እኔ ግን ሁሴን ከፈለክ ቀጥል ካለኝ በኃላ የተወሠነ ፍላጎት በውስጤ ተጭሮ ነበር፤እናም የዛን ቀን እሷ በእሱ ተናዳ፣ እኔ በሚስቴ ተንገብግቤ ተገናኘን ጠጣን እስክንበሠብስ ሠከርን፣ አብረን አደርን፤ ማደር መቼም ምን ማለት እንደሆነ ይገባሻል፡፡

‹‹ቆይ ጥዋት በንፁህ አዕምሮዋ ስታስበው ምን አለች?››

‹‹ተቆጣች፣ አለቀሰች፣ ብዙ ተፀፀተች፣ ለአንድ ሳምንት አኮረፈችኝ ፣ ግን ቀስ በቀስ ለቀቀ እያለች መጣች ደጋግመን ማደር ጀመርን››

‹‹ታዲያ እዚህ ደረጃ ከደረሳችሁ መጋባቱም ቀላል ነው በለኛ!››

‹‹እሱ ላይ እንኳን ትንሽ ችግር አለ፣ ሁሴን አግብቶ ያየሁ ቀን በማግስቱም ቢሆን አገባለሁ ብላኛለች

‹‹የሚገርም ጉድ ነው፤ ታዲያ ይቅናው ብለህ

አትፀልይም?››

‹‹ኧረ ምን ፀሎት ብቻ አዲስ አበባ ለሚገኙት ታቦቶች በጠቅላላ ተስያለሁ››

ይቀጥላል

ዩቲዩብ ቻናል  #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ ቤተሰቦች ዛሬም አንድ 10 ሰው እጠብቃለው👍  አሁንም እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #አድርጉ

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍13016😁16👎3