አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሮዛ_2


#ክፍል_አስራ_ስድስት (🔞)


...አንድ ቀን ደፍረን ደሜን ነገርነው፡፡ “በቃ የሆነ ነገር አድርግ፤ ለሞራሏ ጥሩ አይደለም፤ በሳምንት አንድ እንኳ ወንድ ስታጣ አይደብርም…?” አልነው። ዝም ብሎ የምንለውን ከሰማን በኋላ ቆጣ ብሎ “ሁላችሁም በማያገባችሁ ገብታችሁ አትፈትፍቱ፤ አርፋችሁ ሥራችሁን ሥሩ"ብሎን ጥሎን ሄደ። ምን ያስቆጣዋል ታዲያ? አኮረፍነው።

ከዚያ አንድ ቀን ጠዋት ስንነሳ ዝናሽን አጣናት። ማታ ላይም አላየናትም፡፡ በነገታውም አላየናትም።ደነገጥን! ራሷን አጥፍታ እንዳይሆን። ቶሎ ብለን ደሜን ነገርነው። “አገሯ እናቷን ልትጠይቅ ሄዳለች፤ትመለሳለች” አለንና እየተመናቀረ ሄደ። ምን ያመናቅረዋል? ደግመን አኮረፍነው።

አንድ ሳምንት ለሚሆን ጊዜ ቆየች። ስትቆይ ግን እኛም ረሳናት። ልክ ስንረሳት ደግሞ መጣች። የት ሄዳ እንደነበር ስንጠይቃት ብዙም ምቾት አልተሰማትም። “አገሬ!" ብላን ዝም አለች። እኛም ዝም አልናት።

ከዚያን ቀን ጀምሮ ግን ማታ ማታ ንቃት ይታይባት ጀመር። ማስቲካ በቄንጥ ማኘኸ ቻለች። ሲጋራ እንደነገሩ ማጨስ ጀመረች። ኾኖም ከዚያ ወፍራም ጥቁር ከንፈሯ ጭስ ስታስወጣ በጀበና ቡና እየፈላ እንጂ ሲጋራ እያጨሰች አይመስልም ነበር። ይቅር ይበለኝ፣

ሳታስል ማጨሷ በራሱ ለኛ ዜና ስለነበር ብዙም አልቦጨቅናትም። ቀስ በቀስ ሂል ጫማ ላይ በምቾት መራመድ ችላ ነበር። “ጉድ! ዝናሽ ሰለጠነች” ተባለ።

ቀጥሎ ከአዳዲስ ወንዶች ጋር እየተሳሳቀች መጠጣት ጀመረች። የውጭ ዜጎች ሁሉ ከርሷ ጋር ሆነው
ማስካካት ጀመሩ። ይሄ እንዴት ሊሆን ይችላል ብለን ስንጠጋ ያው የምናውቃት ጌጃዋ ዝናሽ ናት።ኾኖም ወንዶች በምታወራው ነገር ይስቁላታል። ምን እያለቻቸው ይሆን እያልን መመራመር ያዝን።አንድ በአንድ ይዛቸው ወደ ምድር ቤት ትሄድና ትንሽ ቆይታ ተመልሳ ትመጣለች። ትንንሽ ጡቶቿን
እያስተካከለች። ምድር ቤት በክለብ አሪዞና ሾርት የሚፈልግ ወንድ ብቻ ለ15 ደቂቃ 500 ብር ከፍሎ
የሚገባበት ምስጢራዊ ቤት ነው። ዝናሽ ባልተጠበቀ ፍጥነት ምድር ቤቱን ቢዚ አረገችው። ጉድ! አልን።

ይባስ ብለው የምናውቃቸው ደንበኞች ሁሉ ገና ክለብ አሪዞና ገብተው የቢራ ጠርሙስ አንገት እንዳነቁ
“ዝናሽ የለችም እንዴ ዛሬ?” ብለው መጠየቅ ጀመሩ። “አዎ ዛሬ አትገባም!” ስንላቸው ዉልቅ ብለው መሄድ! ጉድ ፈላ!
እንድ ቀን ሁላችንም ተሰብስበን ሺሻ እያጨስን፤ ይቺ እንደመጣላት የምትናገረው ትምኒት አንቺ
ወንዱን ሁሉ በድግምት እንበረከክሽው እይደል? እምስሽ እኮ እንደፉክክር ቤት አልዘጋ አለ፤ ኪኪኪኪኪ አለቻት። ሁላችንም ተደምረን ሳቅን፡፡ ምክንያቱም ትምኒት የተናገረቸው ሁላችንም ስናስበው የነበረውን ነገር ነበር ዝናሽ ግን አልሳቀችም ፊቷ ሁኑ በአንዴ ልውጥውጥ አለ። ጥቁር ግንባሯ ላይ
ከአውስትራሊያ አምጥተው የተከሉትን ዛፍ የሚያከል ደም ስር መጥቶ ተጋደመ።
ያ ወፍራም ከንፈሯ ተንቀጠቀጠ ነጫጭ አይኖቿ የሆን ቀይ መብራት የሚመስል ነገር አበሩ። በተለይ ትልቁ የግራ ዐይኗ በርበሬ መሰለ። ትምኒትን ሌላ ነገር አልተናገረቻትም፣ እንዲህ ብቻ አለቻት። " የኔስ ላይዘጋ ተከፍቷል ያንቺ ግን ላይከፈት ይዘጋል ዛሬም ድረስ ቃል በቃል አስታውሳለው።


ትምኒት ደነገጠች፣ የትምኒትን መደንገጥ አይተን እኛም ደነገጥን።ከዚያን ቀን ጀምሮ ዝናሽን ፊራናት።የሆኑ ጂኒዎች እንደሚታዘዙላት እርግጠኛ ሆንን።

ጥቂት ቀናት አለፉ። ትምኒት ቂጧ ላይ ኪንታሮት ወጣባት። አልነገረችንም። ደምበኞቿ ሸሽዋት አልነገረቻንም። ብር ቸገራት። ነገረችን። ያለንን ሰጠናት። ጨረሰችውና እንደገና ጠየቀችን፤ ሰጠናት።አሁንም ሳምንት ሳይቆይ “የሰጣችሁኝ ብር እኮ አለቀ” አለችን፤ተሳቃ። “ይቺ ትምኒት ብሩን የት
ነው የምትወስደው?” ብለን ስንገረም ራሷ ነገረችን። እየተርበተበተች፤ አንገቷን ሰብራ። “ኪንታሮት የወጣብኝ ቂጤ ላይ ሳይሆን ሌላ መጥፎ ቦታ ላይ ነው፤ ከአሁን በኋላ ቢዝነስ መሥራት የምችል
አይመስለኝም።” አለችን። ክው ብለን ቀረን። የሰጠናትን ብር ሁሉ ለባሕል ሐኪም እየከፈለቸው ነው ለካ በጣም አሳዘነችን ያለንን ሁሉ አውተን ሰጠናት።ብዙ ሺ ብር ሆነላት ያላዋጣችላት ዝናሽ ብቻ ነበረች።

ከወር ከምናምን በኋላ ትምኒት ከክለብ አሪዞና ተባረረች። ምነው ሲባል “ደምበኞች ቅሬታ አቀረቡ ተባለ።በግልጽ ያቀረቡትን ቅሬታ የሚነግረን ግን ጠፉ። ትምኒት ራሷ ናት ቅሬታው ምን እንደሆነ
የነገረችን። እምስሽ ይሸታል ይሉኛል። ለኔ ግን ምንም የሚሸተኝ ነገር የለም፤ እመቤቴ ትድረስልኝ እንጂ ምን አረጋለሁ” አለች። በጣም አዘንላት። ያን ሰሞን የሰራነውን ቢዝነስ ሁሉ ሰጥተን አልቅሰን
ሸኘናት። መልከ ሳያንሳት፣ ጨዋታ ሳያንሳት እንደዚያ ሳቂታ የነበረች ልጅ በአንድ ጊዜ ቅስሟ ተሰበረ።የዝናሽ እርግማን ደረሰ ተባለ። የትምኒት “ባብሽ” ላይከፈት ተደፍኖ ቀረ።
#ዝናሽ_ተሞሸረች

ትምኒት ላይ የደረሰውን ስለምናውቅ ለጊዜውም ቢኾን ዝናሸን ተንቀጥቅጠን ተገዛንላት። ስናገኘት ፀጉርሽ ያምራል!” እንላታለን። “ቴንክስ” ትለናለች “ስ”ን ጠበቅ አርጋ። ቻፒስቲክ እንገዛላታለን፤ አሪፍ ሽቶ እንሰጣታለን። በፍርሃት ተንከባከብናት። ሁላችንም አይደለንም ታዲያ። ማሂ ለምሳሌ ከዚች ጠንቋይ ጋር አንድ ቤት ዉስጥ አልሰራም ብላ አረብ አገር ሄደች። ሌሎቻችን ግን መኖር ስላለብን ይነስም ይብዛ ተንቀጠቀጥንላት አብረናት ገበታ መቅረብ ግን ፈራን። ሺሻ አብራን ታጨሳለች።ሲጋራም እንዲሁ። ምግብ ግን ከሷ ጋር የሚበላ ጠፋ። የኾነ ቁዝሚ አሰርታበት ቢኾንስ? የኛንም "ባብሽ" እንደ ትምኒት ብታሽገውስ ሆሆ!!

የገረመን ግን ዝናሽ ገበያዎ ለአንድም ቀን እለመቀዝቀዙ ነው። ሾርት እንጂ አዳር ስትወጣ አየኋት የሚል ግን የለም። አሪዞና ምድር ቤት የሷ ግዛት ሆነ። እንዳባቷ ርስት ተመላለሰችበት። ወንድ አሰለፈችበት።በተለይ ትልልቅ ሰዎች ከሷ ዉጭ ሴት ማየት አስጠላቸው። ሀበሻ ሲባል፣ አፍሪካ ቢባል፣ ፈረንጅ
ቢባል ሽበቶ ሼባዎት ሁሉ የሷ ቋሚ ተሰላፊ ኾኑ። ግራ ግብት ብሎን ነገሩን እህህ እንዳልን ተውነው።እኔ እንደውም ለሆነ ደቂቃ የወንድ ማስክ አድርጌ ብሰልላት ስል ተመኘሁ። ወንዶቹን ምንድነው የምታስነካቸው? እንዴት ወንድ በዝናሽ ሊከየፍ ይችላል? |

ከዕለታት አንድ ቀን ደሜ የሴቶች ክፍል መጥቶ አንኳኳ። ደሜ የሴቶች ከፍል ከመጣ አንድ ከበድ ያለ ጉዳይ እንዳለ እናውቃለን። ከበድ ያለ ጉዳይ ከሌለ ሰራተኛ ይልካል ወይ ቢሮው ያስጠራናል እንጂ እሱ አይመጣም።

“ዝናሽ ልታገባ ነው አለን።

ደሜን ለጊዜው ማንም ያመነው አልነበረም። ገብቶ አረቢያን መጅሊሳችን ላይ ቁጭ ብሎ ጥቂት ተጨማሪ
መረጃዎችን ጣለልን። ባሏ የናጠጠ ሱዳናዊ ሞጃ እንደሆነ፤ ነፍሱ እስኪወጣ ድረስ እንደሚወዳት፤በስሟ ኢትዮጵያ ኢንቨስት ሊያደርግ እንዳሰበ…ብቻ ዉሸት የሚመስሉ ነገሮችን ቶሎ ቶሎ ነገረን።
የት ተገናኝተው ነው” ስንለው እዚሁ መጥቶ ነበር፤ ብታዩት እኮ ታውቁት ይኾናል፤ ወፍራም ረዥም ግዙፍ ሽማግሌ ሰውዬ ነው፤ እኔ ራሴ ይሄን ያህል ሀብታም እንደሆነ አላውቅም ነበር” አለን። “ከአንድ
ሾርት በኋላ ነው ተንበርክኮ እንድታገባው የጠየቃት” ብሎን ስልክ ሲደወልለት የጀመረውን ወሬ ሳይጨርስልን ጥሎን ወጣ።

ደሜን በወቅቱ በፍጹም አላመነውም ነበር። እሱ ግን የሚነግረን የምሩን ነበር። እሱ ራሱ በአጋጣሚው የተደነቀ ይመስላል።ደሜ ነገር ሲደንቀው አይተን ስለማናውቅ ደግሞ አመነው የሱዳናዊው
መተዳደርያ ምን እንደሆነ ግን አልነገረንም የነገረን ነገር አጭር ስለሆነብን የምንገምተው ነገር በዛ።
👍21
#ሮዛ_2


#ክፍል_አስራ_ሰባት (🔞)


#መኪናና_እኛ_ሴቶች

ሲስና እኔ ቅዳሜ ቀን አልፎ አልፎ እንደምናደርገው ከቤ ኬክ ቤት ነበርን። ወደ ቤት ከመመለሳችን በፊት “ፒኮክ” ጎራ ለማለት ወሰንን። ያው የተለመደችውን አፕሬቲቭ ለመጠጣት። ወደዚያው ለማቅናት ሲስ መኪናውን እያስነሳ እንዲህ አለኝ።

"ሮዝ"

“ወዬ ሲስ ነፍሴ!”

“ሴቶች ከሰውና ከመኪና፣ መኪና እንደሚወዱ ላሳይሽ”

“ፒሽ! ጉረኛ! እናንተ አትብሱም?”

“ማ እኛ ወንዶች?! ተሳስተሻል! ለማንኛውም ተመልከች.! ከዚህ ከቦሌ እስከ መስቀል አደባባይ
እየነዳሁ ማን ለመኪና የበለጠ እንደሚደነግጥ አይተን ብንፈርድ አይሻልም?”

“እስኪ ዝም ብለህ ንዳ ሲስ! ስትሟዘዝ አያምርብህም!”

በአማካይ ፍጥነት የቀኝ መስመሩን ይዞ መንዳት ጀመረ። ምን ሊያደርግ ነው ብዬ ስጠብቅ መኪናዉን
እየነዳ እጁን ዝም ብሎ ለሚያዩት ሰዎች ሁሉ ማውለብለብ ጀመረ። የእግረኛ መንገድ ላይ ለቆሙና

እንዲሁም በእግረኛው መንገድ ወደተቃራኒ አቅጣጫ በቡድንና በተናጥል “ዎክ” እያደረጉ ለነበሩ
ሴቶች ሰላምታ ይሰጣቸዋል። ሲያዩት ዝም ብሎ እንደሚተዋወቅ ሰው እጁን ያውለበልብላቸዋል።
ይህን ጊዜ ያልተጠበቀ ነገር ማስተዋል ጀመርኩ።

ሴቶቹ መጀመርያ በጣም ድንግጥ ይሉና ፍጥጥ ብለው ማንነቱን ለማጣራት ይሞክራሉ ዎክ
የሚያደረጉት ደግሞ ሰላምታው ከባለመኪና በመምጣቱ ነው መሰለኝ ደንግጠው ጉዟቸውን ገታ
ያደርጋሉ። በቆሙበት ግራ በመጋባት ዉስጥ ሆነው ለሰላምታው በደመነፍስ ምላሽ የሚሰጥሞ ነበሩ
ቆም ካሎት ዉስጥ ብዙዎቹ በድንጋጤ የታጀበ ፈገግታን ያሳያሉ፤ በሆዳቸው "ታዲዬ! ባለመኪና ሰላም
አለኝ” የሚሉ ይመስላሉ።ሲስ ለተንኮሉ የመኪናውን ፍጥነት ቀነስ ያደርግላቸዋል። ይሄኔ ልሂድ
አልሂድ፣ ልግባ አልግባ እያሉ ሲያመነቱ በስፖኪዬ ይመለከታቸዋል። አንዳንዶቹ ጓደኞቻቸውን ባሉበት ጥለው ወደ መኪናው ለመምጣት ይዳዳቸዋል።የማየው ነገር ሊካድ የማይችልና በጣም አሳፋሪ ነበር።

በዚህ ሁኔታ ሲሳይ 8 ወይም 9 የሚሆኑ ሴቶችን ቆሌ ከገፈፈ በኋላ ወሎ ሰፈር ጋ በዛ ያሉ ተማሪ ሴቶች
መንገድ ዳር ተሰብሰብው አየ። እየተጯጯሁ እያወሩ ነበር። በአቅራቢያው ከሚገኝ የግል ትምህርት ቤት የወጡ ተማሪዎች መሰሉኝ። ሲስ ሆን ብሎ መኪናውን ወደነርሱ ቀረብ አድርጎ አቆመው። ሁሉም የሞቀ ወሬያቸውን ትተው የሲስን መኪና እንደ ሸንኩርት በዐይናቸው መላጥ ጀመሩ። እንድጊዜ ሲስን፣ አንድ ጊዜ መኪናዋን….የእውነቴን ነው፤ እኔ እነሱን ማየት ሁሉ ስላሳፈረኝ አንገቴን ሰበርኩ። እሱም
አውቆ እንዳላያቸው ለመምሰል ቴፑን ይነካካል። እንደገና ሞተር አስነስቶ ከአጠገባቸው ዞር እስከንል
ድረስ እንዳቸውም ወደ ወሬያቸው አልተመለሱም ነበር። ፖሊስ ሲመጣ ራሱ እንደዚህ ፀጥ ረጭ አይሉም። የሚያከብሩት አስተማሪ ከፍል ቢገባ እንኳን እንዲህ አይነት ፀጥታ አይታሰብም መኪና እንዴት ይህን ያህል ሊያሸፍት ቻለ?

“ሲስ!”

“እቤት ሮዝ!”

“በቃ አምኛለሁ!”

“ጌታ ይባርክሽ! አየሽ አይደል እንዴት ሴቱ ሁሉ ለመኪና…?”

" ባታሳየኝ አላምንም ነበር ምንድ ነው ግን ትራፊክ ይመስል መኪና ላይ ይሄን ያህል መጎምዠት!?

ምን ነካን?"

"Value ሲስተማችን እየተለወጠ መምጣቱ ነው የሚያሳይሽ። ሰው ሳያውቀው ቁስ አምላኪ እየሆነ መጥቷል በተለይ ሴቶች"

"ወይኔ ጉዴ! ይኸኔ እኔም እግረኛ ስሆን እንደዚህ እንዳይሆን የምሻፍደው ሲስ ሙት መኪና ዉስጥ ሆንህ ስታየው ነው ይበልጥ የሚያሳፍረው፤ አይደል?"

ሊሆን ይችላል! አስቢው ደሞ ሮዝ! ይህ ሁሉ የሆነው አንቺ ገቢና ቁጭ ብለሽ ነው። ብቻዬን ብሆን
ሴቶቹ ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ገምተሻል? አሁን አሁን ገብተው የሚደፍሩኝ ሁሉ እየመሰለኝ መፍራት ጀምሬለው።"

"ፒሽ አታካብድ እንግዲህ! አንተ ላይ አይደለም እኮ ድሮም የሻፈዱት! መኪናህ ላይ ነው ሲቁለጨለጩ የነበረው።

“ኖ! ማካበድ አይደለም፤ ስላየሁት ነው። ከሆኑ ዓመታት በፊት እኮ ሴት ልጅ መኪና ቆሞላት ከገባች
ሰው ሁሉ የትርፍ ሰዓት ሸሌ አድርጎ ነበር የሚስላት። ነውር ነበር! በደንብ አስታውሳለሁ፤ ሴት ልጅ
መኪና ቆሞላት ሰተት ብሎ መግባት! አይታሰብም። አይገርምሽም ብትሞት አታደርገውም። አሁን
ያ ቀርቷል። አሁን እናቶች ራሱ ልጃቸው መኪና ያለው ወንድ እንድትጠብስላቸው ስልጠና መስጠት ጀምረዋል ነው የሚባለው።”

አነጋገሩ አሳቀኝ

"ይሄን ሁሉ የምታወራው መኪና አለኝና… ለማለት ነው?”

"እና የለኝም ለማለት ነው ታዲያ? ስላለኝማ ነው ልምዴን የምነግርሽ። ሴቶች መኪና አምላኪ ሆናችኋል።
አሻሽሉ በአዲስአበባ የመኪና ቁልፍ የሴቶችን ጭን የሚከፍት ማስተርኪይ እየሆነ መጥቷል። በእውነት ይደብራል። ነገሮች በዚሁ ከቀጠሉ ፖሊስና ኅብረተሰብ ላይ የምንሰማው ዜና ምን ሊሆን እንደሚችል አስበሸዋል?

"አላሰብኩትም !"

ሁለት ወጣት ሴቶች እንድ ራስታ ጎረምሳ እስከ ጫፍ ሸኘን ብለው በማባበል ካሳመኑት በኋላ በገዛ መኪናው ውስጥ በተደጋጋሚ በማፈራረቅ ልጁን በመድፈራቸው እያንዳንዳቸው በ15 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ እንደተፈረደባቸው ጉዳዩን የያዙት መርማሪ ፖሊስ ሳጅን ገለጹ...."

ግን እኮ ሲሉ ማወቅ ያለብህ መኪና አዲስ አበባ ውስጥ በጣም ቁልፍ ጉዳይ ነው። መኪና ካለህ ወያላ
አፉን አይከፍትብህ። ተከብረህ ትኖራለህ፤ በአጭሩ አራት ጎማ ያለው ቤት ማለት እኮ ነው። ቤትህን እየነዳህ መሄድ ማለት እኮ ነው የሚሰጠውን ምቾት ግን አስበከዋል"

"ምቾቱን እኔ እየኖርኩት አይደል እንዴ ሮዝ! ለኔ ልታስረጅኝ ትሞክሪያለሽ እንዴ? ለዚህ ብለን
አይደል እንዴ ቀድመን የባነንነው? እንደምታውቂው እኔ ከስእሎቼ ሌላ ምንም ንብረትም፣ ሚስትም፣
ድስትም የለኝም፤ አንድዬ ንብረቴ መኪናዬ ናት። መኪናዬ የምትሰጠኝን ምቾት ሚስቴ የምትሰጠኝ አይመስለኝም። I think የማላገባውም ለዚህ ይመስለኛል።

"I know! Already እኮ ተነገረህ፤ “ሲስ መኪናዋን መንዳት ብቻ ሳይሆን ማታ ማታ ይበዳታል” የሚሉት ወደው አደለም።"

ሳቀ! ሲስ ከት ብሎ ሳቀ። ሲስ ያስቃል እንጂ አይስቅም። እሱ የሚስቀው አልፎ አልፎ ከስንት አንዴ ስለሆነ በሆነ አጋጣሚ ሲስቅ ፈገግታው ልብን ወከክ ያደርጋል።

ይህንኑ እያወራን ሳለ አንዲት በወንድ ደረት የተሸጎጠች ቀጭን ልጅ ቦይፍሬንዷ ክንድ ዉስጥም
ሆና ወደኛ መኪና አጮልቃ ስታይ አየኋት። ለሲስ ያየሁትን ከነገርኩት ለወሬው ብርታት ይሰጠዋል
ብዬ ዝም አልኩ። የልጅቷ ድርጊት ግን አስጠላኝ። የዉነት አስጠላኝ። ከወንድ ጋር ሆና እየሄደች
መኪና ውስጥ ያለ ሌላ ወንድ ማየት ምን ይባላል?! እኔ ባልኖር እሺ! ስታስጠላ! ሴት አሰዳቢ። በሆዴ
ረገምኳት

እግረኛ አንደሆንሽው ቆመሽ ቅሪያ ብዬ ረገምኳት።

"ሲሉ ረስቼው ግን ሳልነግርህ! ሴቶች መኪና ሲነዱ ወንዶች እንዴት እንደሚሆኑ አይተኸዋል?
ቀላቸው እኮ ነው የሚቆመው፣ እዚያው የቆሙበት መርጨት እኮ ነው የቀራቸው ለሃጫቸው ሁሉ
ተዝረክርኮ ጅል መስለው እኮ ነው የሚያዩት።…ሃሃ የሴቶች ሀጢያት ብቻ እንዳይመስልህ _!
ወንዶች " ራሴ በተናገርኩት ነገር ከት ብዬ ሳቅኩኝ

"እኔንጃ ሮዚ! እኔ እሱን ስላላየሁ መናገር አልችልም። እኔ መናገር የምችለው ያየሁትን ብቻ ነው
ያየህውነሸ ንገረኝ ካልሽኝ ደሞ እኔ ሴቶች ቆንጆ መኪና ሲያዩ እግራቸው መሃል ደጋግመው እንደሚያኩ ነው።
አንዳንድ ጊዜ መኪናው ራሱ ማርሹን ተጠቅሞ የሚበዳቸው ነው የሚመስለኝ።"

"በቃ በናትህ ተሟዘዝክ አታስጠላኝ ደሞ ሲስ ሙት መኪና በቅርብ ወራት ውስጥ ገዝቼ አሳይሃለሁ
ለማየት ያብቃህ!i mean it
👍7
እንዴት ከረማቹ ውዶቼ? ያው በ #ኢንተርኔት መቋረጥ ምክንያት ተቆራርጠን ሰነበትን ያው አሁን ተመልሰናል በዚህ በተቋረጠበት ወቅት ያው ይሄ ቻናል አንገሽግሿቹ(አስጠልቷቹ) የወጣቹ እንዳላቹ ሁሉ በከፊል ኢንተርኔት ሲለቀቅ ምነው ጠፋቹ የሚሉ የበዙ መልእክቶች ደርሰውኛል በደንብ ሲለቀቅ እንመለሳለን ብለን ዛሬ ላይ ደርሰናል ዛሬም እንደተለመደው #ሮዛ_2 በተለመደው ሰዓት ይዘን እንመጣለን ሌሎቹም ይቀጥላሉ አሁንም ግን አብሮነታችሁን እንፈልጋለን አትውጡብን ስትወጡ ይከፋናል ግን ሳትፈልጉንም እንድትቆዩ አንፈልግም ያው እንደ #ኢንተርኔት ፍቃድ አብረን እንቆያለን አሁንም ከኛ ጋር መሆናችሁን 👍 በመንካት አሳውቁን መልካም ቀን።
👍1
#ሮዛ_2


#ክፍል_አስራ_ስምንት(🔞)


የሜርሲን በምስል የተደገፈ የህይወት ገፆች እየገለጥኩ ማንበብ ጀመርኩ።

ሃይሚና ሚስጥረ የሜርሲ ግራ ቀኞች

ሜርሲ ሚስጥረና ሃይሚ የሚተዋወቁት በአንድ የግል ኮሌጅ ውስጥ ሲማሩ ነበር።የማይነጣጠሉ ጓደኛሞች ነበሩ። ሜርሲ ከመሀል ሃይሚና ሚስጥረ ግራና ቀኝ ሆነው ነው ሁልጊዜ የሚታዩት።
ሜርሲ፣ሚስጥረና ሃይሚ የሚተዋወቁት በአንድ የግል ኮሌጅ ውስጥ ሲማሩ ነበር፡፡የማይነጣጠሉ ሲቀመጡም እንደዚያ ሆነው ነው። ሁሉንም ያወቅኳቸው ወሎ ሰፈር ሙና ሺሻ ቤት ውስጥ ነበር።በየትኛው ሰአታቸው እንደሚማሩ ግራ እስኪገባኝ ድረስ ሶስቱም የሙና መቃሚያ ቋሚ ታዳሚዎች ነበሩ።በሂደት ከ ሦስቱም ጋር ነፍስ ለነፍስ ተግባባው።

ለነገሩ ሙና ቪላ ውስጥ የማይመጣ አይነት ሰው አልነበረም፤ አርቲስቱ፣ ነጋዴው፣ ፓይለቱ፣ጋዜጠኛው፣ ባለስልጣኑ፣ ካድሬው፣ ፓስተሩ፣ ደህንነቱ፣ ተቃዋሚው፣ ምሁሩ፣ የኤን.ጂኦ ሰራተኛው፣ዲያስፖራው፣ ኢንቬስተሩ፣ የባንክ ሰራተኛው፣ አርኪቴከቱ፣ መሀንዲሱ፣ ኮንትራክተሩ፣ ሴቱ፣ ወንዱ። የጋራ ጨዋታና የሀሳብ ሙግት የሚፈልገው ሰፊው ሳሎን ውስጥ ገብቶ አረቢያን መጅሊሱ ላይ በመቀመጥ ጀማውን ይቀላቀላል።

መነጠልንና ብቸኝነትን የመረጠውም ፕራይቬት ሰርቪስ ክፍሎቹ ውስጥ በር ዘግቶ ከግል ሀሳቡ ጋ እየተጫወተ ይቅማል፣ ሺሻውን ያጨሳል። ሙና ከቀናት በፊት ቦታ ሪዘርቭ የሚያስደርጉ በርካታ ቪአይፒ ደምበኞ አሏት። ወንዶቹ በተለያየ ቴክኒከና ብልሀት በዋናነት ሙና፣ ሜርሲና እኔ ላይ ወጥመዳቸውን ይጥላሉ። በሀሳብ ሙግቱና ፍጭቱ ወቅት ሁሉም ተከራካሪ የሙና “ፓርላማ”ን
አብላጫ ታዳሚ (በተለይ ቆነጃጅቱን) በንግግሩና በሀሳቡ ለመማረክ ይውተረተራል።
በሙግቱ ወቅት ጌቾን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰማ ታዳሚ ኢህአዴግ የቀናት እድሜ እንደቀረው ያስባል።ጌቾ ተርዚናውን ወጥሮ “ጌታቸው ምን አለ በሉኝ የኢህአዴግ ይህን ወር አይሻገርም። ህወሃትና ብአዴን መሀል ንፋስ ገብቷል” ይላል። ጌቾን ለበርካታ አመታት የሚያውቁት የሙና ፓርላማ ታዳሚዎች ግን በሀሳቡ ይሳለቁበታል። በተለይ ብዙ ማውራት የማይወደው ኡመር አስመጪው በአንድ ወቅት ጌቾን የተናገረው ነገር አይረሳኝም።

"አይ ጌቾ ብረት እኮ ነሽ፤ ህውሃትን በየእለቱ እየመረቀንሽ ስርአተ ቀብሯን ስትፈፅሚ ስንት ዘመን ተቆጠረ፤ ህወሀት ይኸው አስራ ምናምን አመት እንዳሸችን አለች። አንቺም ይኸው ህውሀትን እንደ
ሾላ ፍሬ ከመንበሯ ስታረግፊያ ስንትና ስንት አመታቹ። ጌቾ አንተ ጫቱም ሲጋራውም ተደማምሮ መሞትህ አይቀርም፤ ህውሃት ግን የአገዛዝ ከንዷን እያፈረጠመች እንጂ እየከሰመች አላየናትም። የህወሀትን ፍጻሜ ከመተንበይ ያንተን ሞት መተንበይ ነው የሚቀለኝ…” ብሎታል። ከዚች ቀን በኋላ
ጌቾና ኡመር ተነጋግረው አያውቁም። ጌቾ ግን አሁንም የሚናገረው የህውሃትን ፍጻሜ እንደተቃረበ ነው።
ፖለቲካ ማውራት የማይሰለቸው እሱን አየሁ። ሙና ቤት ሲመጣ ሁልጊዜ የቆዩ ምኒሊክ፣ ሳተናው፣ሰይፈ ነበልባል የሚባሉ ጋዜጦችን በብብቱ ዉስጥ ይዞ ነው። ከነሱ ጋዜጦች ትንሽ ያነብና ፖለቲካውን ያንበለብለዋል። ደግሞ ደኅንነቶች ሙና ቪላ ዉስጥ እንደማይጠፉ እያወቀ ነው እንዲህ ምርር ያለ ፖለቲካ የሚያወራው። እኔን የሚገርመኝ ግን ጫት ቤት ከሚመጣ ለምን ጫካ እንደማይገባ ነው።” ትል ነበረ ሚስጥረ።

ሜርሲና ገዝሸም ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙትና ፍቅራቸውን የጠነሰሱት በዚህ የሙና ፓርላማ ውስጥ ነበር። በቅርበት ለመነጋገር ረጅም ጊዜ ወስዶባቸዋል። ሜርሲ ፊት አትሰጠውም ነበር። ሜርሲ፣ሃይሚና ሚስጥረ ተጣብቀው የተወለዱ ነው የሚመስሉት። በፍጹም አይለያዩም። ሜርሲ በሙና
ቪላም ይሁን በምሸት መዝናኛ ስፍራዎች ለሚለክፉት ወንዶች ልቧን ከፍታ ፊት ለመስጠት የሚስጥረን ይሁንታ በቅድሚያ ማግኘት ይኖርባታል። ሜርሲ፣ሃይሚና ሚስጥረ በአሁኑ ጊዜ የማያቸውን ሴቶች ባህሪ በደንብ ይወክሉልኛል። መልክ፣ጭንቅላትና ገንዘብ በአንድ ሴት ላይ አንድ ላይ ስለማይገኙ አሁን አሁን ጓደኛሞች የሚሆኑ ሴቶች እርስበርስ ለመደጋገፍ አንድ ቆንጆ፣ አንድ ህብታምና አንድ ጎበዝ
ሆነው የሚወዳጁ ይመስለኛል።
ለምሳሌ ሃይሚን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያያት ወንድ ሁለት ጊዜ ያማትባል። አንዴ ተደንቆ፣ አንዴ ደግሞ ደንግጦ መጀመሪያ ከኋላ ሲያያት የወገቧ ቅጥነት፣ የዳሌዋ ስፋት፣ የመቀመጫዋ ትልቅነት ግርምትን ፈጥሮበት ያማትባል። ከአፍታ በኋላ ደግሞ የፊቷ ፉንጋነት አስደንግጦት ያማትባል። ይህ እንዳለ ሆኖ ግን ሃይሚ ሳቂታና ተጫዋች ስለሆነች ትንሽ ትልቅ ሳትል ከሁሉም ወንዶች ጋ በፍጥነት ትግባባለች፡፡
ቤተሰቦቿም እንደ ሚስጥረና ሜርሲ ድሆች ይመስሉኝም። ከነሱ ሳንቲም በመያዝ የተሻለቸው ሃይሚ ናት። ከአስር ደቂቃ በፊት ያግኛትን ወንድ ረጅም አመታት የሚያውቃት እንዲመስለው የማድረጉን ክህሎት ተክናበታለች።

ሚስጥረ ቆንጆም መልኩ ጥፉም የማትባል አይነት ሴት ናት። የሚስጥረ ትልቁ ሀይሏ ግን እውቀቷና
ለህይወት ያላት በሳል አመለካከት ነው።ለሜርሲና ሃይሚ የከበዳቸውን ትምህርት የምታስጠናቸውና
አሳይመንት የምትሰራላቸው እሷ ናት። እሷ የምታቀርበውን ማንኛውንም ሀሳብ ሜርሲና ሃይሚ ያለማንገራገር ይቀበሉታል። ጋባዣቸውንና የሚያዝናናቸውን ወንድ ሁሉ መርጣ የምታጸድቅላቸው አሷ ናት።

ሜሪሲ ማንም ባያት ቅጽበት በአድናቆትና በድንጋጤ ክው የሚልላት እንከን-የለሽ ውብ ሴት ናት።
በሙና ቪላም ሆነ በሚሄዱበት ስፍራ ሁሉ ሜርሲን ለመጥበስ ዘረ አዳም ከአጠገቧ የማይለዩትን ሀይሚና ሚስጥረን በድልድይነት ለመጠቀም ይገደዳል። ነዳጅ ለአረቦቹ የሀብትና የቅንጦት ምንጭ
የሆነውን ያህል የሜርሲ ምትሀታዊ ውበትም ለሚስጥረና ለሀይሚ ጋባዥን በየሄዱበት የሚያሰልፍ ሲሳይ ሆኗል። ወንዱ የሜርሲን ትኩረት ለማግኘት ሲል ሶስቱንም ያለስስትና ያለመታከት ይጋብዛል።

በወንዶቹ በኩል ሜርሲን ለማግኘት በየእለቱ የነበረው ፍልሚያና ትንቅንቅ እየበረታ እንጂ እየቀነሰ የሚሄድ አልነበረም። ብልህዋና ባለብሩህ አእምሮዋ ሚስጥረ በረቀቀ መንገድ የዘየደችው ቀመር ሰርቶላታል። ጋባዦቻቸው በጥቂት ሰአታት ውስጥ ለሶስቱም ሺዎችን ያለምንም ስስት እንዲያፈሱ ሆነዋል። ሜርሲ በሰልፍ ለሚጋደሉባት ጋባዥ ወንዶች የፍቅርና የወሲብ ጥያቄ እሺም እምቢም
ሳትል የምትቆይበትን የሚስጥር ቁልፍ የለገሰቻትም ሚስጥረ ናት። ወንዱ ሜርሲን የማግኘት የተስፋ ጭላንጭሉ ሳይከስም ልቡ ተንጠልጥሎ ብሩን ይረጫል። ሚስጥረና ሀይሚ ለሁለተኛ ጊዜ ለጋበዛቸው ወንድ ሁሉ የሜርሲ ልብ ወደሱ እያጋደለ እንደሆነ በረቀቀ የትወና ጥበብ ፍንጭ በመስጠት ኢንቨስትመንቱን በእጥፍ እንዲያሳድግ በሾርኔ ይጠቁሙታል።
የሜርሲን ቆዳ ለማካበድና ፍልሚያው የዋዛ እንዳልሆነ ለማሳየት ሶስቱም ጋባዣቸውን ውድ ቤቶቹ በመውረድ ኪሱን ያርዱታል። ውድ ውድ ምግብ፣ ውድ የአልኮል መጠጦች፣ አሪፍ አሪፍ ቄንጠኛ አልባሳት፣ ውድ ውድ ሽቶዎች፣ ቄንጠኛ የጸጉር አፈሻሽን፣ ማኒክዩር፣ ፔዲክዩር፣ ሳውና ባዝ፣ስቲም ባዝ፣ሞረኮ ባዝ.የሶስቱ ተዘውታሪ የህይወት ዘይቤዎች ነበሩ። ከኮሌጅ የሚተርፋቸውን ሰዓት በወንዶች በኩል በሚመጣ በመምነሽነሽ ነበር የሚያሳልፉት።

ገዝሽ በሜርሲ ፍቅር ጀዘበ

ገዝሽ ግን እድለኛ ነበር። ከዚህ ሁሉ ፍልሚያና ኢንቨስትመንት በኋላ እንደሌሎቹ እድለ ቢስ ወንዶች
ከፍልሚያ ሜዳው በባዶ አልተሰናበተም። ሜርሲ እልህ ውስጥ ከታው ነበር። “ገንዘብ፣ መልክና እውቀት ሳያንሰኝ እንዴት አንዲት የኮሌጅ ተማሪ እንዲህ ትንቀባረርብኛለች? “ ብሎ ለሙና ቤት ታዳሚ ተናረገ። በሙና ፓርላማ ቀርቦ ለራሱ ቃል ገባ። ሜርሲን የግሉ
👍52
#ሮዛ_2


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ (🔞)


#ኤርሚ_ጂግሎ

ዕሁድ ጠዋት…። ማንንም ማግኘት የማልፈልግበት የግል ክፍለ ጊዜዬ ናት። አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ስሞኑን የጀመርኳትን መጽሐፍ እያነበብኩ ነበር። አብሮ አደጌ ፌሩዝ ናት ከለንደን የላከችልኝን። “fifty Shades of Grey” ይላል ርዕሱ፡፡ አንድ ክርስትያን ግሬይ የተባለ የ27 አመት ወጣት ቢልዬነር
የሚመራውን ድብቅ የፈንጠዝያ አለም የሚተርክ መጽሐፍ ነው። ዋናው ባለታሪክ በወሲብ ወቅት ሴቶችን በማሰቃየት እርካታን የሚያገኝ ካዲስት ነው። ፌሩዝ «ብዙ ሚሊዮን ፈረንጅ በሸሚያ ያነበበው
ነው ሲባል ሰምቻለሁ፤ እኔ እንደምታውቂው ማንበብ አልወድም፣ አንቺ መጽሐፍ ማንበብ ስለምትወጂ
ነው የላኩልሽ» ብላኛለች። ምን አይነት መጽሐፍ ቢሆን ነው ብዬ ነበር የጀመርኩት።
ከጀመርኩት በኋላ ግን ታሪኩ ለማቆም ቸገረኝ፡፡

ሞባይሌ ስታቃጭል ያቆምኩበትን ገጽ ከአናቱ ላይ አጥፌ ከአልጋዬ በመውረድ ስልኬን ቻርጅ ወደ ሰካሁበት ቡፌ አመራሁ። ስልኬን ማጥፋት ረስቼ እንጂ እሁድ ጠዋት ማንንም ባላናግር ደስ ይለኝ ነበር።

የሞባይሌን ስከሪኔ "Ermi Gigolo” እንደደወለ ነገረኝ። ፈገግ አልኩኝ። እንደዚያ ብዬ ስሙን ሴቭ ማድረጌ ልክ አልነበረም።
ጂግሎ(Gigolo) የሚለው ቃል ኤርሚያስን የሚገልፅ ቢሆንም ስልኬ ላይ በዚያ ስም ሴቭ ማድረጌ ትክክል እንዳልሆነ ታውቆኛል። ጂግሎ ማለት በእንግሊዝኛ ከሴቶች ገንዘብ ተቀብሎ የወሲብ አገልግሎት የሚሰጥ ወንድን የሚወክል ቃል ነው።ስለዚህ ኤርሚን ይገልፀዋል።ሆኖም ይሄ ደዋዮቼን በቀላሉ ለማስታወስ በሞባይሌ ላይ ከዋና ስማቸው አጠገብ የማሰፍረው ቅጽል ከዚህ በፊት ብዙ መዘዝ አምጥቶብኛል

ለምሳሌ አንድ ምሽት ዳንኤል ከሚባል የብስኩት ፋብሪካ ያለው ወዳጄ ጋ እየተዝናናሁ ሳለ ሽንቴ መጣ ተነስቼ ባዝ ሩም ሄደኩ። ለካንስ ሞባይሌን እዚያው ጠረጴዛው ላይ ረስቼው ነበር። ከመጸዳጃ ቤት ስመለስ ዳኒ እሳት ለብሶና እሳት ጎርሶ ጠበቀኝ። የሚያስጠላ የስድብ ናዳም አወረደብኝ። መፃዳጃ ቤት
በሄድኩበት ቅጽበት ለካ የኔን ስልከ አንስቶ የራሱን ቁጥር ሲደውል እኔ የሱን ስልክ ሴቭ አድርጌዋለሁ።ሴቭ ማድረጌ አልነበረም ችግሩ። ሴቭ ያደረኩት «ዳኒ ቦርጮ ብዬ ነበር።

እኔ ምን ላድርግ ታዲያ! ሺ ዳንኤል ነው የማውቀው። “ዳኒ ኮንትራክተር” ፣ዳኒ አርቲስቱ” ኢምፖርተር”፣“ዳኒ ካናዳ"፣"ዳኒ ቦርጮ፣"ዳኒ ዲዛይነር”፣”ዳኒ ሸፋዳ”፣” ዳኒ ሾርት”፣ “ዳኒ ቆለጥ፣ "ዳኒ ፓስተር"

ዳኒ የበገነበት ምክንያት ከቁጣውና ከስድቡ በኋላ ግልጽ ሆነልኝ፤

“ብሽቅ ሸርሙጣ ነሽ! ያ ሁሉ እንክብካቤ እያረኩልሽ ከኔ “ቦርጩ” ብቻ ነው ትዝ የሚልሸ? ይሄ ለኔ ያለሽን መራር ጥላቻ ያሳየኛል። ድሮም ከሸሌ ምን ይጠበቃል! እናንተ ከልብ የሚወዳችሁና
የሚንከባከባችሁት አትወዱም…አንቺ ደህና ሰው ትመስይኝ ነበር፤ የሸሌና የሰይጣን ደህና የለውም "እውነተሸ ነው።"

በንዴት ስልኬን ከመሬት አጋጭቶ ሊሰብረው ሁሉ ቃጥቶ ነበር። ስኮሳተርበት ነው የተወው።

ኤርሚ ጂግሎም ስሙን ምን ብዬ ስልኬ ላይ ሴቭ እንዳደረግኩት ቢያውቅ ምን ሊሆን እንደሚችል ስገምት ዘገነነኝ። ነገ ማታ በመኪናው ከክለብ አሪዞና ፒክ እንደሚያደርገኝ ከተነጋገርን በኋላ ስልኩን ዘግቼ ወዲያው ስሙን ቀየርኩት። Ermi Stud ብዬ ሴቭ አደረኩት። ከgigolo ይልቅ Stud ቢባል ያኮራዋል እንጂ አያሸማቅቀውም።

ኤርሚ ጂግሎ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ላይ ከክለብ አሪዞና ይዞኝ ወደ ዮድ የባሕል ምግብ ቤት ወሰደኝ።
ዬድ አሪፍ ክትፎ ከበላን በኋላ ከክለብ ክለብ እየገባን፣ እየጠጣን፣ እየጨፈርን አሪፍ የማይረሳ ምሽት አሳለፍን

ኤርሚ ደም ግፊት ካለባት ሹገር ማሚ ወዳጁ ኑኑሻ ጋ ዱባይ አንድ ዓመት ቆይቶ መመለሱ ነበር።ከኑኑሻ ጋር የተዋወቁት ኤርሚ ጀንግል ጂም ፊትነስ ሴንተር ውስጥ ኤሮቢክስ በሚሰራበት ወቅት ነበር ኑኑሻ የዱባይን መሬት ለመጀመሪያ ጊዜ ከረገጡ የሀበሻ ሴቶች ኣንዷ እንደነበረች ነግራዋለች።
ሃብታም ነጋዴ ናት። እኔና ኤርሚ ጂግሎን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋወቀን ደግሞ ኡስማን ዘ ፒምፕ ነበር።

ኤርሚ ጂግሎ ፈረንጆቹ 'six pack የሚሉት የሚያምር የሆድ ቅርጽ አለው። ፈርጣማና ጡንቸኛ ሰውነቱ ከቁመናው ጋር ተደማምሮ የትኛዋንም ሴት ያፈዛል። አብረን በትዝናናንባት በዚያ ምሽት እንኳ
ብዙ ሴቶች ከቦይፍሬንዶቻቸው እቅፍ ዉስጥ ሆነው ኤርሚ ጂግሎን በስርቆሽ ሲያዩት ነበር።

ኤርሚን በአካል ሳላውቀው በፊት መጀመርያ ያወቅኩት በፎቶ ነው። አትላስ ኡስማን ዘ ፒምፕ የትራቭል ኤጀንሲ ቢሮ ዉስጥ ቁጭ ብዬ ኡስማንን እየጠበቅኩ እያለ ሼልፍ ላይ የሚያምር ካታሎግና
አልበም ተቀምጠው አየሁ። መዝዤ ስገልጠው ኤርሚ ጂግሎ የአልበሙን ግማሽ ሞልቶታል።በተለያዩ ፓንቶት፣ በቁምጣ፣ ጥብቅ በሚያደርግ ቦዲ፣ ወንድነቱጋ አበጥ ያለ ነገር እንዳለ በሚያሳብቅ የወንድ ታይት፣ ገጠር ውስጥ በሬ ጠምዶ ሲያርስ፣ ፈረስ ሲጋልብ.የሌለው አይነት ፎቶ…ያልተነሳው
አይነት አነሳስ የለም። መአት ፎቶ ነው ያለው። በሌላኛው አልበም ደግሞ የብዙ ሴቶችን ፎቶ የያዘ ካታሎግ ተመለከትኩ። እሱን ትቼ የኤርሚ ጂግሎን ካታሎግ በድጋሚ እያየሁ ሳለ ኡስማን ዘ ኪንግ
በሩን በርግዶ ገባ። ሰርቆ እንደተያዘ ሌባ ክው አልኩኝ። ምን እንዳስደነገጠኝ ገርሞኛል። ኡስማንም ድንጋጤዬ ገርሞት ምን እያረኩ እንደነበር ጠየቀኝ። ኤርሚ ጂግሎ ሞፈርና ቀንበር ተሸክሞ የሚያምር ገበሬ መስሎ ደረቱን አጋልጦ የተነሳውን እጅግ የሚያምር ፎቶ አሳየሁት። ኡስማን ነገሩ ገብቶት መሳቅ
ጀመረ። ምንድነው ሮዚ! በቆንጆ ወንድ ፎቶ ሴጋ መምታት ጀመርሽ ማለት ነው…” ብሎ የማያባራ ሳቅ ሳቀብኝ፣ በጣም ሳቀብኝ። ሲስቅብኝ ደግሞ ይበልጥ ተሸማቀቅኩ።

ፎቶው ላይ ስለተመለከትኩት ልጅ ጠየቅኩት። አጠር አድርጎ አብራራልኝ።

“ ኤርሚያስ ይባላል…ቱሪስት ሴት ክላይንቶቻችን ጠይም የሐበሻ ወንድ ካልወለድክ ብለው
እስጨነቁኝ፡፡ ጥያቄው ሲበረታብኝ ኤርሚያስን በስንት አደን አገኘሁት፡፡ እንደምታይው ጠይምነነቱና
ቁመናው ይማርካቸዋል ወንዶቻችሁ ጡንቻቸው ደቃቃ ነው» እያሉ ብዙ የመለመልኳቸውን
ወንደች አጣጥለውብኝ ነበር። ኤርሚያስ ነው በመጨረሻ የገላገለኝ…” አለኝ፡፡

ከዚያ በፊት እንደዚያ አይነት ነገር እዚህ እግር ዉስጥ ሰምቼ አላውቅ ስለነበር በጣም ተገረምኩ ኡስማንን አፍጥጬ ስመለከተው ሌላ ነገር የፈለኩ መስሎት
"ችግር የለውም ሮዚ፤ አንድ ምሽት እንዲቸገርልሽ ማድረግ እንችላለን” አለኝ። “ሂድ እዛ ሞዛዛ፣ አስቀያሚ” ብዬው ልወጣ ስል እጄን ይዞ
እስቀመጠኝ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኡስማን በኤርሚ ጉዳይ እንደሳቀብኝ ነው። “እኔ ቢሮ ዉስጥ በኤርሚ ፎቶ ሮዛ ምን ስታደርግ እንደያዝኳት ነገርኳችሁ?” እያለ ለነራኪ አሳልፎ ሰጠኝ። መሳቂያ አደረገኝ ።ራኪ እንኳን ይሄን ጮማ ወሬ አገኝታ....።

ከስንት ጊዜ በኋላ ኡስማን ደውሎ ጊዮን ቀጠረኝ። አብሮት መልአክ የመሰለ ጠይም ወንዳ ወንድ ልጅ
ተቀምጧል። ጥቁር መነጽር በማድረጉ ግን በደንብ አለየሁትም ነበር። ጠጋ ብዬ ሳየው ልቤ ቀጥ ልትል ምንም አልቀራት። ይህን ልጅ የት ነው የማውቀው ብዬ ስጨነቅ "ሮዝ ኤርሚያስ ይባላል...ተዋወቁ" አለኝ እየጠቀሰኝ። አሁን ማን መሆኑ መጣልኝ። ካታሎጎ ላይ ያየሁት ሰው ነው። ኤርሚ ጂግሎ።

ኤርሚን ሰኡስማን ያስተዋወቀችው ደግሞ ሳቢ ናት። ሳቢ ከኡስማን ወፎች ሲኒየሯ ናት። አንድም ቀን ያለማቋረጥ ኤሮቢክስ ስፖርት የምትሰራ ንቁና ታታሪ ሴት ጥሪ ብባል ከሷ ሌላ የማውቀው የለም የማውቃቸው ሰዎች ሁሉ ጀምረ
👍51😁1
#ሮዛ_2


#ክፍል_ሀያ(🔞)


#የዊንታ_ማንነት

ቦሌና አካባቢዋን የዊንታን ያህል የምታውቅ ሴት መኖሯን እጠራጠራለሁ። የቦሌ ዙርያን የሌሊት ጉድ እንደ ዊንታ የበረበረ ሰው መኖሩንም እንጃ! ለነገሩ ዊንታን የማታውቅ የዚያ አካባቢ ሸሌ አትገኝም።የአካባቢው ስትሪቶች፣ ኮድ ሶስቶች፣ የክለብና የቡና ቤት ሸሌዎች ጥሎባቸው ዊንታን አይወዷትም፣
ገና ሰፈሩን ስትረግጥ በአይናቸው ቂጥ ነው የሚመለከቷት። ለምን ቢባል ዊንታ እንደነሱ ታጥባ፣ታጥናና፣ ተኳኩላ በሸሌ ደንብ ለብሳ በየሌሊቱ ቢመለከቷትም ከወንድ ጋ ስትሄድ አየናት የምትል ሴት
ግን የለችም። ዝም ብላ በዙሪያቸው ታንዣብባለች። ሌሊቱን ሙሉ ቦሌና ዙሪያውን ታካልለዋለች።የቦሌ መድሃኒአለምና የቦሌ አትላስ ባለመኪኖች መኪናቸውን አቁመው ወይም መኪናቸው ውስጥ አስገብተው ያነጋግሯታል፣ ዋጋ ትደራደራለች፤ ግን ከባለመኪኖቹ ጋ አንድም ቀን ስትሄድ አትታይም።

የቦሌና ዙሪያው ውድ ክለቦች፣ ሆቴሎችና ቡና ቤቶች ውስጥ ገብታ የፈለገችውን ትጠጣለች፣ በወንዶች ትጋበዛለች፣ ከወንዶችና ከሴቶች ጋ እየተጫወተች አልኮል ትጠጣለች ግን ከግብዣው በኋላ ከማንም ወንድ ጋ ስትሄድ አትታይም። “ከዊንታ ጋ አንሶላ ተጋፍፌያለሁ” የሚል ወንድ በቦሌ ዙሪያ ተሰምቶ አይታወቅም። ይህ ጠባይዋ ለአካባቢው ሸሌዎች ውል አልባ እንቆቅልሽ ሆኗል። በዚህ ሁኔታዋ ግራ የተጋቡት ሸሌዎች ብዙ ነገር ያወሩባታል። ኤሚ በአንድ ወቅት ስለ ዊንታ ሳነሳባት ግንፍል ብሏት እንዲህ ብላኛለች፤

“ባክሽ እሷ ቢዝነስ የምትሰራ ሸሌ አይደለችም፤ እንደ ሸሌ አክት የምታደርግ የመንግስት ጆሮ ጠቢ ነች፤
መልክና ቁመና ሳያንሳት ቢዝነስ የማትሰራበት ሌላ ምን ምክንያት ይኖራታል ብለሽ ነው?እንደነ ኤልሳ
እኛንም እንዳታስቆጥረን ነው የምፈራው."

መሲን ደግሞ በአንድ ወቅት እየጠጣን የድሮ ጓደኞቻችን እያነሳን ስንጥል ስለ ዊንታ የሚገርም ነገር ነገረችኝ"
ሮዝ ሙች እየቃዠሁ አይደለም፤ የሰከርኩ ከመሰለሽም ተሳስተሻል። ከዋናዎቹ ሰዎች ጋ እሌኒን ስብሰባ ስትቀመጥ ሀገዞም አይቷት ነግሮኛል እኮ ነው የምልሽ፤ እኔ በጭራሽ ዊንታ ጆሮ ጠቢ
ስለመሆኗ ተጠራጥሬ ሁሉ አላውቅም። እንዴ ቆይ አንቺ ስታስቢው በሳምንት አንድ እንኳ ቢዝነስ ሳትሰራ እያደረች እንዴት ነው እንደዚያ እየተጫጫሰች፣ እየዘነጠች ልትኖር የምትችለው…። መሲን
ጥርጣሬዋን ሳጣጥልባት ሀገዞምን ስታገኘው ስለዊንታ በደንብ እንደምታውጣጣውና እንደምትነግረኝ ቃል ገባችልኝ።ሀገዞም የዊንታ የረጅም ጊዜ ደንበኛዋ ነው።እሷም "ባሌ" እያለች ነው የምትጠራ።መርማሪ ፖሊስ ሲሆን ሌሎች ግልፅ ያልሆኑ የደህንነት ስራዎቹንም ይሰራል ብላኛለች።

እኔ በበኩሌ መሲም ኤሚም ያሉትን ነገር ሙሉ በሙሉ ለመቀበል ከብዶኛል። በርግጥ የህውሃት ታጋዮች ድሮ በትግል ወቅት እብድ፣ ለማኝና ዘበኛ ሆነው ደርግን ይሰልሉት እንደነበረ ርእሱን ከማላስታውሰው መፅሀፍ ላይ አንብቤ አውቃለሁ።በዚህ ሰላማዊ ዘመን ግን ሸሌ ጆሮ ጠቢ በየአስፋልቱ እያቆሙ የሚሰልሉ አልመስልሽ አለኝ።

ለምን እንደሆነ አላውቅም ነገሩን አጥርቼ ለማወቅ የነበረኝ ጉጉት አላስቆም አላስቀምጥ አለኝ። ያን ሰሞን ደግሞ አጋጣሚ ሆኖ በሄርሜላ የልደት በዓል ላይ ዊንታ ተጋብዛ አላገኛትም! ነገሩን እንዴት ላነሳባት እንምችል ግን አልገለጥልሽ አለኝ። ቆይተን ጨዋታው እየደመቀ…ከመጠጡ እየደጋገምንለት
ስንሄድ ሁላችንም ሞቅታ ዉስጥ ገባን። ፈጠን ብዬ ከዊንታ ጎን ተቀመጥኩና ወሬ ጀመርኩ።

“ዊንታ ግን የውነት ጠፍተሻል፣ ደግሞ ባለስልጣን ሆናለች እያሉ እያስወሩብሽ ነው አልኳት።ስቃ ምንም መልስ ሳትሰጠኝ ሌላ ሌላ ወሬ መዘባረቅ ጀመረች። አንቺ በቃ ሁልጊዜ እንዳማረብሽ
ሮዚ ምንድነው ግን ምስጢሩ?…ብላ አሳሳቀችኝ። ወሬ ለመቀየር ያደረገቸው ጥረት ይበልጥ ጥርጣሬ ቢፈጥርብኝም ከዚህ በኋላ ነገሩን ማንሳት ለራሴም አደጋ እንዳለው ሰግቼ ተውኩት።

የሚገርመው ግን ስለ ዊንታ ነገሩ ሁሉ የተዳፈነ መስሎኝ በሌላ ጫወታ ዉስጥ ተዘፍቄ እያለሁ በራሷ ጊዜ ክፍለ-ከተማው በ”ኮምዩኒቲ ፖሊሲንግ” መልምሏት ከማህበረሰብ ደህንነት አጠባበቅ ጋር የተያያዙ ልዩ ልዩ ስልጠናዎችን በተለያየ ጊዜ መውሰዷን ነገረችኝ። እኔም ይህን ስልጠና መውሰድ
ከፈለኩ ልታገናኘኝ እንደምትችል ገለጸችልኝ። ይህን ጊዜ ጥርጣሬዬ ከፍ አለ። ማን ያውቃል?
Community policing የምትለዋን ነገር ያመጣቻት ሆን ብላ የሚወራባትን አሉባልታዎች እውነትነት ለማለዘብ ብላ ቢሆንስ? በዚያ ላይ ቅድም "ባለስልጣን ሆነሻል አሉ” ብዬ ሸንቆጥ ስላረኳት ለዚያ
ምላሽ እንዲሆን የፈጠረቻት ብልሃት ልትሆን እንደምትችል ጠረጠርኩ።

ከዊንታ ጋር ከሄርሜላ ልደት ምሽት የነበረንን ቆይታ ጨምሮ ነገሮችን በስክነት ለማያያዝ ስሞከር በሷ ዙሪያ የሚወሩት ነገሮች ሁሉ ሙሉ በሙሉ እውነት ባይሆኑም መነሻ እውነት እንዳላቸው ተረዳሁ።

ከስንት ጊዜ በኋላ ደግሞ ለምን መሲ ጮማ ጮማ መረጃ ይዛ አትመጣም። ሀገዞም በስካር መንፈስ ሆኖ ብዙ ነገር ዘባርቆላታል ለካ። መሲ እንደምትለው ከሆነ ሀገዞም ዊንታን በጣም ነው የሚጠላት።ምክንያቱም ከዚህ በፊት ለሴክስ ጠይቋት እስኪ መጀመርያ እከከህን አራግፍ” ብላዋለች።ይሄን በራሱ
አንደበት ነው የነገረኝ አለችኝ። መሲ ከሀገዞም የሰበሰበችው ወሬ ለማመን የሚከብድና ከጠበቅኩት በላይ ዝርዝር ነገር ሆኖ አገኘሁት። አንዳንዶቹ ነገሮች እሱን ራሱ የሚያስጠይቁትና በፍጹም ለመሲ መናገር የሌለበት አይነት ነበሩ። ምናልባት በዊንታ ላይ ቂም መያዙ ምን መደበቅና ምን መናገር እንዳለበት እንኳ እንዳያውቅ ሳይጋርደው አልቀረም።

መሲ ከሀገዞም የሰማችውን ተስገብግባ እንዲህ ተረከችልኝ።

ሀገዞም እንደነገረኝ ዊንታ የመጀመሪያ ተልእኮዋ በ'ክለብ ኤግዞቲካ” ተገኝታ ከጠጪዎቹ መሀል በመገኘት የእጽ ዝውውርን፣ የውጭ ምንዛሪንና ሰዶማውያንን የተመለከቱ መረጃዎችን መሰብሰብ ነበር። ለከለብ ኤግዞቲካ ባለቤቶች ለደህንነት ስጋት የሆኑ ወንጀለኞች በአካባቢው እንዳሉና ለሚልኳት መረጃ ሰብሳቢ ሴት አስፈላጊውን ትብብር ሁሉ እንዲያደርጉላትና ሽፋን እንዲሰጧት አስቀድሞ ተነግሯቸዋል። መረጃ ሰብሳቢ የተባለችው ዊንታ መሆኗ ነው። ለነገሩ ባለቤቱቹ የታጋይ ቤተሰብ ልጆች ስለሆኑ ሁልጊዜም ተባባሪዎች ናቸው ብሎኛል።

“በዚህም መሰረት ዊንታ በክለቡ ውስጥ በአልኮል የናወዘች ሴት መስላ የውጭ ምንዛሪ አቅራቢዎቹ፣ሰዶማውያኑና እጽ አዘዋዋሪዎቹ ቦታ እየጠቀሱ ሲቀጣጠሩ ትሰልላለች። አለቆቿ የሰጧት ሁለተኛው
ተልእኮ ደግሞ በግራንድ ሌከሰስ” ሆቴል ባር ውስጥ እየተዝናና የሚገኘውን ስመ-ጥር ዲያስፖራ ተቃዋሚ ፖለቲከኛን መከታተል ነበር። ፖለቲከኛው ሞቅ ብሎት ሲደንስ አብራው ከደነሰች በኋላ
ረጅም ሰአት አልኮል እየጠጡ ሲዝናኑ ነበር። ዲያስፖራው የአዲሳባ የቤት ልጅ የጠበሰ መስሎት በሱ ቤት በደስታ ሊሞት ደርሶ ነበር» ብሎኛል ሀገዞም።_ያረፈበት ሆቴል አልጋ ድረስ አብራው በመሄድም አለቆቿ ስለፖለቲከኛውና የግንኙነት መረቦቹ የሚፈልጉትን ወቅታዊ መረጃዎች እስከ ጥግ አቀብላቸዋለች

መሲ እንደምትለው ከሆን ዊንታ ከወንድ ጋር መኝታ ከፍል ድረስ ዘልቃ አንሶላ የምትጋፈፈው በእንደዚህ አይነት ልዩና ከባድ ተልእኮ ውቅት ብቻ ነው፡፡ ሀገዞም ለመሲ ከነገራት ተጨማሪ መረጃ እንደገባኝ ከሆነ ዊንታ ጀማሪ ጆሮ ጠቢ ሳትሆን አትቀርም።

መሲ ለባሏ ሀገዞም ይህን ስራ ዊንታ እንዴት እንደጀመረቸው ጠይቃው ነበር። ነገሩ ባልተጠበቀ ሁኔታና በአጋጣሚ እንደሆነ ነግሯታል።

" ከዚህ ቀደም ከእንድ መካከለኛው ምስራቅ ዉስጥ ከሚንቀሳቀስ አሸባሪ ቡ
#ሮዛ_2


#ክፍል_ሀያ_አንድ(🔞)


#ቺቺንያዊው_ፍቅሮቭስኪ


እግር ጥሎኝ ጆሲ ባር ገብቼ ስዝናና ሄለን ፒንክን አገኘኋት። ሄለን አሁንም ኩል ክለብ ውስጥ እንደምትሰራ ነገረችኝ። ማርቲ እዚሁ አዲሳባ መሆኗን እስክትነግረኝ ድረስ እንደሌሎቹ ጓደኞቻችን ዱባይ የገባች መስሎኝ ነበር። ከሄለን ጋር እየጠጣን የሆድ የሆዳችንን ተጫወትን። ሁለታችንም መጀመሪያ ስለተዋወቅንባት ቺቺንያ አንስተን ብዙ የጋራ ትዝታዎቻችንን አነሳን-ጣልን። ሄለን ፒንክ ጥቂት የድሮ ወዳጆቻችን አሁንም እዚያው ቺቺንያ እንዳሉ ስትነግረኝ ዛሬውኑ ሄደን እንድንጠይቃቸው
በሞቅታ ሀሳብ አቀረብኩ። እውነትም ሞቅ ብሎኝ ነበር። ሄለን ፒንከ አላቅማማችም።

ከሌሊቱ 8፡00 ሰዓት ሲል ጆሲ ባርን ለቀን ጥቂት የድሮ ወዳጆቻችንን ለማግኘት ወደ ቺቺንያ አመራን።
እንዲሁ ሳንተኛ ሌሊቱ ይነጋታል እንጂ ሄለንን ብዙ ክለቦች ልወስዳት እዚያው ጆሲ ባር ውስጥ እያለን አስቀድሜ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር። ምን ጣጣ አለው?! ሲነጋ እኔ አፓርታማ ሙሉ ቀን ተጋድመን
እንውላለን ብዬ አሰብኩ። የዛሬን አያድርገውና ሄለን ፒንክ ባለውለታዬ ነበረች። ሁላችንም በራሳችን
የህይወት ሀዲድ ላይ ፋታ አጥተን ስንጣደፍ በተለያየ ወቅት መልካም የዋሉልንን እንረሳለን።

ሰአቱ ገና ስለነበር እዚያው ቺቺንያ ትልቁ ክለብ ዉስጥ ገብተን በዲጄ ሙዚቃ ወለሉ ላይ በዳንስ እየሾርን ስንጠጣ እስከ ሌሊቱ 9፡30 ቆየን። እንደ ጆሲ ባር ሁሉ እዚህም የከለቡን ለፍዳዳ ወንዶች
ለከፋ እና ጅንጀና እንዲሁም የአብረን እንዝናና ጥያቄ መቋቋም ነበረብን ወንዶች መለፋደድ ከጀመሩ ደግሞ ቶሎ አይፋቱም፡ እምቢ ሲባሉ ይብስባቸዋል። እንደዉሻ ከቂጣችን ስር መርመስመስ ጀመሩ።በዚህን ጊዜ ክለቡን ጥለንላቸው ከትልቁ የቺቺንያ ክለብ ወጥተን ወደ ትንሿ ቪቪያን Tብ አመራን።ከዋናው የቺቺንያ አስፋልት የተወሰኑ ሜትሮችን ገባ ብሎ ነው የሚገኘው፡ ገና እግራችን ከመግባቱ ብሌን በጩህት ተቀበለችን።

"ሮዛ!!! እኔ አላምንም፤ በአገሩ አለሽ? ማርቲ ነግራሻለች? ብዙ ጊዜ ያለሽበትን ሁኔታ እጠይቃት ነበር፤ ከሄሊ ጋር እንኳን አልፎ አልፎ እንገናኛለን፤ ሄሊ ፒንክ እንዳንቺ አልረሳትንም ፤ እየመጣች ትጠይቀናለች ወይ ሮዚና እንዳጠፋፍሽ ግን አላማረብሽም ጥፍጥፍ..."

ብሌን ከባንኮኒው ውስጥ ወጥታ በደስታ ተጠመጠመችብኝ፤ ለደቂቃዎች አለቀቀችኝም። ከብሌን ጋር በጣም ነበር የምንዋደደው። ብሌን አልተለወጠችም፤ ውበትዋ፣ ፍልቅልቅነቷ፣ ሸንቃጣነቷ፣
ተጫዋችነቷና ማራኪ ለዛዋ አሁንም እንዳለ ነው። በህይወቷ ውስጥ የቱንም ያህል ሀዘን፣ ስቃይና መከራ ሲደርስ ብሌን እንደ አይሁዶቹ ቀልድ ፈጥራ ትዝናናበታለች። ይሄ የብሌን ልዩ ተሰጥኦ ነው። ምንም ቢደርስባት ሁሌም ሳቂታ፣ ቀልደኛና ተጫዋች ስለሆነች ሀዘን ለቅጽበት እንኳን ነክቷት የሚያውቅ አይመስልም።

እኔና ሄለንን በአሪፉ ለማስተናገድ ሽር ጉድ ስታበዛ አስቆምናት፡ ብሌን አሁንም ድረስ ያልተወጋና ንጹህ ውስኪ ከሚሸጡ እጅግ ጥቂት ታማኝ የቺቺንያ የባርና የፐብ ባለቤቶች ቀዳሚዋ ነች።

ከብሌን ባሻገር ባንኮኒው አጠገብ አንገቱን ደፍቶ በፍጹም ተመስጦ ጠርሙስ ጎርደን ጂን ወደ ሚጠጣው
ጎልማሳ ማተረች። በቪቪያን ፐብ ውስጥ ከሱ ሌላ ሰው የለም። ጂኑ አልቆ የጠርሙሱ ቂጥ ላይ ሊደርስ
ትንሽ ይቀረዋል፤

“ፍቅሮቭስኪን ልሸኝና ፐቤን ዘግተን ቤቴ እወስዳችኋለሁ፣ አሪፍ ኮንዶሚንየም ገዝቼያለሁ ደሞ።ሄልዬን አሳይቻታለሁ፤ ሮዝ ግን ዛሬ ትመርቂልኛለሽ እሺ!”

ብሌን ጉንጩን በለስላሳ መዳፏ መታ አድርጋኝ ያን ደማቅ ፈገግታዋን ለገሰችኝ፤ ፈገግታዋ አለም ሁሉ በጨለማ ቢዋጥ ለመላው አለም ብርሃን የመለገስ ሃይልና ጉልበት አለው። አይ ብሌን! ሁሌም
ፍልቅልቅ ናት። ግራና ቀኝ ከጉንጮቿ መሀል የተሰደሩት ዲምፕሎቿ በምትስቅበት ወቅት ፈገግታዋን
አድምቀውት የልእልት ገጽታን ያላብሷታል። ከበፊት ጀምሮ ከምትሀታዊ ፈገግታዋ ጀርባ አንድ ከባድ ሀዘን ወይም የማይሽር የህይውት ቁሰል እንዳለ ባስብም ያን ደፍሬ ሳልጠይቃት ነበር ከበርካታ አመታት በፊት ቺቺንያን የለቀቅኩት። በጨዋታ በጨዋታ እድርጌም ቢሆን ከደማቅ ፈገግታዋ አድማስ ማዶ የተደበቀውን የህይወት ስንክሳር ባውቅ ደስተኛ ነኝ። ከአንዳንድ ዝነኛ ኮሜድያን ህይወት ጀርባ ስፍር ቁጥር የሌለው ሀዘንና መከራ እንዳለ ሁሉ፣ የብሌን ውብ ምትሀታዊ ፈገግታ ምናልባትም በህይወት የደረስነባትን አንዳች ከባድ ስብራት መሸፈኛ ጭምብል ሊሆን ይችላል። በፊት የማውቀው ባህሪዋ አሁንም እንዳለ ነው።

ሰብለን ከቀልድና ጨዋታዋ ሌላ ልብ አንጠልጣይ የትርጉም ልቦለድ መጻህፍት መለያዎቿ ነበሩ።መጽሐፍ በማንበብ ከጓደኞቼ ብቸኛዋ ሳትሆን አትቀርም። ነገር ግን ልብ አንጠልጣይ ካልሆነ
አታነብም። የሳንድራ ብራውንን፣ የጃኪ ኮሊንስን፣ የኤሪካ ዮንግን፣ የዳኔላ ስቲልን፣ የአጋታ ክሪስቲን፣የሲድኒ ሼልደንንና የኬን ፎሌትን ስራዎች እንደዉስኪ አንጠፍጥፋ ነው የምትጠጣቸው።

ብሌን ከመደርደሪያው ላይ ሙሉ ሬድ ሌብል አውርዳ ለኔና ለሄለን ከዚያም ለሷ በብርጭቆ ቀዳች።ብርጭቆዎቻችንን አጋጭተን እየጠጣን መጨዋወቱን ቀጠልን። ደሞ ለጨዋታ! ብሌን ጋ ቀልድ፣
ጨዋታና ሳቅ በሽ ነው።

ብሌን እንደገና ወደ ጎልማሳው ጠጪ ማተረች፤

“ሮዝ! አላወቅሽውም እንዴ?”

ጎልማሳውን ገና አሁን ነበር በሙሉ አይኔ የተመለከትኩት። ፊቱን እንደ ሃምሌ ደመና አጨፍግጎታል፣ዝምታው የመርግ ያህል ይከብዳል። በራሱ አለም ውስጥ ነው ያለው። ባዶ ሊሆን ጥቂት የቀረው
የጎርደን ጠርሙሱ ላይ አፍጥጧል። ከገባንበት ቅጽበት ጀምሮ እይታውን ከጠርሙሱ ላይ አላነሳም።
በዙሪያው ያለውን ትእይንት ከነመኖሩም እስኪረሳ ድረስ በራሱ የሀሳብና የትካዜ አለም ተሳፍሮ ሩቅ የነጎደ ይመስላል።

አውቅኩት፤ ብረት አስመጪው ፍቅረዝጊ ነው። ተክለሀይማኖት አካባቢ ትልቅ መጋዘን እንዳለው ይወራ ነበር። አመታቱ የቱንም ያህል ቢረዝሙ ድሮ የሚያውቁት ሰው መሰረታዊ ገጽታ አይጠፋም።
ካልሰከረ እሱም እንደሚያውቀኝ እርግጠኛ ነኝ።

"ፍቅረዝጊ ነው አይደል ብሌን?"

ብሌን እንደ ድሮ አስካካች

ሮዝ ሰፈራችንን ከለቀቅሽ ብዙ ጊዜ ስለሆነሽ የስሙን ለውጥ አላወቅሽም ማለት ነው፡፡ ፍቅረዝጊን
| 'ፍቅሮቭስኪ' ብለን የቺቺንያን የክብር ዜግነት ሰጥተነዋል እኮ። ላለፉት አስር አመታት ዊከ ኤንዶችን ከቺቺንያ ርቆ አያውቅም፤-በተለይ ከዚህ ከቪቪያን ፐብ። በርካታ የቺቺንያ ቆነጃጅት በተገኙበትና ድል ባለ ድግስ ነበር የቺቺንያ ዜግነቱን ያቀዳጀነው”

የማስካካቱና በሳቅ የመንከትከቱ ተራ የኔ ተራ ሆነ። እንዲህ እንዲህ እያለ ጨዋታችን ደራ። ድንገት ብሌን ያልጠበቀችውን ጥያቄ አስከተልኩ፤

“የኔ ውብ! ትዳር መሰረትሽ?”

ብሌን እንደገና በሳቅ ተንከተከተች፤

“አይ ሮዝ፤ አላወቅሽም እንዴ?! ትዳር ማለት እኮ ሾርት ወይም አዳር ገብቶ እንደመውጣት ሆኗል።ባለትዳሮቹ ራሱ ሚስታቸውን እያስተኙ እኛ ጋር አይደል እንዴ የሚያመሹት? ለአንድ ለስድስት ወር ያህል ሞክሬው ነበር-ባል ተብዬው አስካሉ የተባለች ሰራተኛዬን በገዛ አልጋዬ ላይ ሲያንከባልል እጅ ከፍንጅ ይዤው በቀይ ካርድ አሰናበትኩት…” ጣሪያው እስኪሰነጠቅ በራሷ ንግግር ሳቀች።

ሶስታችንም በሞቅታ ውስጥ ነን፤ ብሌንን በሳቅ አጀብናት። ሆኖም የፍቅሮቭስኪ ጎርናና ብሶተኛ ድምጽ ከሳቅና ከጨዋታችን መለሰን። ፍቅሮቭስኪ ከባድ ሀዘን ባረበበበት ጨፍጋጋ ፊቱ ሶስታችንንም በየተራ ገረመመን።ቡናማ ኮቱን በንዴት መሬት ላይ ወረወረው። ባንኮኒውን በግዙፍ ቡጢው በተደጋጋሚ
ነረተው። ጨርቁን ሊጥል ቅጽበት የቀረው
👍2
#ሮዛ_2


#ክፍል_ሀያ_ሁለት(🔞)


#ቪላ_ኖቫ

ወይንሸት ወሬ ስታወራ አፍ ታስከፍታለች። ያየሁትን ፊልም ስትተርክልኝ ምንም ሳልሰለች እንደ አዲስ እሰማታለሁ። ግርም ነው የምትለኝ። አዳምቃ ስታወራ ትንሽ ታጋንናለች እንጂ ነፍስ ናት። ማንኛውንም ወሬ ስታወራ ልክ አሁን እንደሆነ፣ ወይም ትናንት እንደተከሰተ አድርጋ ነው። ስለ ቪላ ኖቫ ህይወቷ
አንድ ከሰአት ሙሉ ሺሻ ቤት ቁጭ አድርጋ የተረከችልኝን ነገር መቼም አልረሳውም። ያንኑ ቀን ምሽት
ነበር እንደወረደ ማስታወሻዬ ላይ ያሰፈርኩት። ወይኒና ቪላ ኖቫ።

ወይኒና ቪላ ኖቫ

"ሮዛ! "ታምኛለሽ? የኮሌጅ ትምህርቴን ካቋረጥኩ 6 አመት አለፈ። ተማሪዎች በተመረቁ ቁጥር እደነግጣለሁ፤ እንኳን ደስ አላችሁ» የሚለው መዝሙር ይረብሸኛል። ይሄኔ እኮ አሪፍ ስራ ይዤ
ጨዋ የቢሮ ሰራተኛ እሆን ነበር። ቢዝነስ ከጀመርኩ 5 አመታት ተቆጠሩ ማለት ነው አይደል? ወይኔ ጉዴ ጊዜው እንዴት እንደሚሮጥ.…!

ሽርሙጥናን በድብቅ ያስጀመሩኝ ጓደኞቼ አብዛኞቹ የሉም። ሀበሻ ደንበኞቻቸውን በአረብ እና በነጭ ተከተው ሁሉም ዱባይ ከትመዋል። እኔ ግን የዚህች አገር ቋሚ ንቅሳት ሆኛለሁ። ጓደኞቼ ይሄኔ
ከሰማይ ጠቀሶቹ የዱባይ ሆቴሎች፣ ክለቦችና የስርቆሽ ቪላዎች ዉስጥ ቢዝነሳቸውን አጡፈውታል።

ኪኪ፣ ሜሪና ኤልሲ በየሳምንቱ በፌስቡከ ላይ የሚለጥፏቸውን ፎቶዎችን አያለሁ። አምሮባቸዋል፤ወፍረውና ቢጫ ሆነው እነሱ ራሱ አረብ መስለዋል። ያን የአረብ መንዲ፣ ኩብዝና ፈጠራ በየእለቱ
እስኪሰለቻቸው እያግበሰበሱ እንዴት አይስማማቸው?

ሮዚ ሙች ቤተሰቦቼ አሁን የምሰራውን ስራ ቢያውቁ ምን ይውጣቸዋል?›› ብዬ ሳስብ ዛፍ ላይ ታናቂ ታንቂ ይለኛል አምስት አመት ሙሉ ስዋሻቸው ኖሬያለሁ እኔ የነገርኳቸውን አምነው በአንድ
የውጭ ድርጅት ወስጥ በደህና ደሞዝ ተቀጥሬ እየሰራሁ እንደሆነ ነው የሚያውቁት። በእርግጥ በአካል
እስካላገኙኝና እጅ ከፍንጅ እስኪይዙኝ ድረስ አይጠረጥሩም፡፡ በየጊዜው የምልከላቸው ገንዘብ ያን
እንዲጠረጥሩ ሊያደርግም፡፡ አራት ታናሽ ወንድሞቼን ያሻቸውን እያለበሰኩ እንቀባርሬ የማስተምረው እኔ ነኝ፡፡ ሁለቱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሆነዋል፡፡ በህይወቴ የሚያረካኝ ምንም ነገር ባይኖርም ዩኒቨርስቲ የገቡትን ታናናሾቼን ሳስብ ግን እጽናናለሁ፡፡ የመጀመሪያ ታናሼ ሲቪል ምህንድስና የሱ ታናሽ ደግሞ የህክምና ትምህርትን ያጠናሉ። ኮንትራክተርና ዶክተር ሊሆኑ እንደሚችሉ ሳስብ በደስታ እምባዬ ይመጣል። ገላዬን ሸጬ እንደማስተራቸው ቢያውቁ ምን ይሰማቸው ይሆን ? ብዬ ሳስብ ግን
እበረግጋለሁ። ስሜቴ ይረበሻል፣ ሞራሌ ይሰበራል፣ እንቅልፍ አጥቼ ስብሰለሰል አድራለሁ።

ስለ ቪላ ኖቫ ገፅታ

ሮዚ! ቪላ ኖቫን አታውቂውም አይደል? እድለኛ አይደለሽም። ቪላ ኖቫ ሳትሰሪ አዲስአበባን አውቃታለሁ እንዳትይ ደሞ። ቪላ ኖቫ ሁሉን አይነት አገልግሎት የሚሰጥ ሳርቤት ገብሬል የሚገኝ
ቪላ ነው። በቪላ ኖቫ ውስጥ ደምበኛ ፈልጎ የሚያጣው አንድም አገልግሎት አይኖርም። ቪላ ኖቫን ሚሊዮን ብር አየርባየር የሚያንቀሳቅሱ፣ ሳይታሰብ ባንድ ጊዜ በአቋራጭ ሞጃ የሆኑ “ስፓይደርማን ሃብታሞች"ያዘወትሩታል። ሺህ ብሮች እንደ ሳንቲምና እንደ ጉርሻ የሚታዩበት ሰፊ ቅጥር ነው፤ ቪላ ኖቫ።

በዉስጡ የከፍተኛ መደብ መቃሚያና ሺሻ ቤት አለው። መስቀል ፍላወር ጋዜቦ አካባቢ ካለው ጫት መሸጫ ውጭ የትም አይቼው የማላውቀው እስሩ 1200 ብር የሚሸጥ ጫት በቪላ ኖቫ ውስጥ ይገኛል። ጫቱ እስካሁን እንደነ ኮሎምቢያ፣ ቆቦ ፣ በለጬ፣ ገለምሶ፣ አወዳይ፣ ቁርጮ፣ አቡ ምስማር
ወንዶ፣ ባህርዳርና ጉራጌ ጫቶች መደበኛ መጠሪያ ስም አላገኘም። የምርቃና ከፍታው ለየት ያለ ስለሆነ እንፈራዋለን፣ ደፍረን ቅመነው አናውቅም። እንኳን ይህን ከሄሮይንና ኮኬይን የማይተናነስ ከባድ ስም የለሽ ዕጽ ቀርቶ ሊና ጓደኛዬ አንዴ ዋናውን የኮሎምቢያ ጫት ቅማ በምርቃና የሰራችውን በአይኔ
በብረቱ ስለታዘብኩ ኮሎምቢያ እንኳን ቅሜ አላውቅም፡፡ ሊና ሙሉ ከሰአቱን እሱን ጫት ቅማ አይደል እንዴ ማታውን "ይሄ ቤት በፕላን አልተሰራም” ብላ የቤቷን ግድግዳ ለማፍረስ ስትታገል ያደረቸው!(ተያይዘን ሳቅን)

በያንዳንዱ የቪላ ኖቫ የመቃሚያ ክፍል ውስጥ በአለም ዙሪያ የሚገኙ ውድ የአልኮል መጠጦችን የያዘ ፍሪጅ አለ። ሁሉም ክፍሎች ሙቅና ቀዝቃዛ ሻወር፣ ንጹህ የመቃሚያ ልብሶች፣ ሙሉ24 ሰአት ከመላው አለም የሚገኙ የዲሽ ፕሮግራሞችን የሚያስኮመኩሙ ባለ 41-ኢንች ፍላት ስክሪን ቴሌቪዥኖች፣ ውድ የአረቢያን መጅሊሶች፣ ሺሻ ማጨሺያዎች አሏቸው። የቪላ ኖቫ ደምበኛ ለአንድ ቡሪ ሺሻ 300 ብር
ይከፍላል፡፡ ሁሉም የቪላ ኖቫ ክፍሎች ለመንፈስ የደስታ ስሜትን በሚለግሱ ውብ የፋርስ ምንጣፎች ደምቀዋል። የቪላ ኖቫ ደመበኛ ቺቺንያ ውስጥ እንደሚገኙ ቪላዎች ከሳሎኑ የሚለቀቀውን ሙዚቃ በየከፍላቸው በሚገኘው ማስተጋቢያ በግድ እንዲያደምጡ አይደረጉም። በየክፍላቸው ውስጥ ጂ-ፓስ
ስላለ ፍላሽ ሜሞሪያቸውን ሰከተው የመረጡትን ሙዚቃ መኮምኮም ይችላሉ። በየከፍሉ ውስጥ
ደምበኞች ምንም ነገር ሲፈልጉ ወደ ሪሴፕሽን ደውለው የሚያዙበት ፊክስድ ላይን ስልክ አለ። በስልኩ ደረት ላይ ባለሶስት ዲጂት የሪሴፕሽን ስልክ በጉልህ ጥቁር ቀለም ተጽፏል።

የቪላው ምድር ቤት ስፊና ማራኪ ባር አለው። በባሩ ወስጥ ቆነጃጅቱ አለን። የቪላ ኖቫ ደምበኛ ምርቃና ወይም የአልኮል ሞቅታ ላይ ሆኖ ሴት ቢያሰኘው ወደ ሪሴፕሽኗ ስልክ መምታት ብቻ ነው
የሚጠበቅበት። ደመበኛው ኪሱን ይጭነቀው እንጂ ከሶስት እስከ ግማሽ ደርዘን ሴቶች ወደ ክፍሉ ቢያዝም ይችላል። ደምበኛውን የሚያነሆልለው የሚካኤላ ውብ ድምጽ ይቀበለዋል፤ “Your wish is our command. The girls will be in your room in just a few moments. Thank you for calling!"

አማርኛዋ ራሱ ቅንጦት የተጫነው እንግሊዝኛ ነው የሚመስለው፤ ሚካኤላ ጎላ ጎላ ያሉ አይኖች ያሏትና
የሞዴል ተከለ-ቁመና ያላት ሴት ናት፤ ያለ ቱፒስ እትለብስም፤ የእግሯን ውብት አሳምራ ስለምታውቀው እጅግ አጭር ቀሚሶችን ነው የምታዘወትረው። ሚካኤል ከብራንድምርቶች ጋር ክፉኛ በፍቅር የወደቀች ሴት ናት። የምትቀያይራቸው መነጽሮች፣ የጸጉር ቅባቶችዋ፣ የቆዳ ቅባቶችዋ፣ ሽቶዎችዋ ፣ሸሚዞችዋ፣ ሙሉ ልብሶቿ፣ ጫማዎቿ፣ ሴክሲ ስልኮቿ...ሁሉም ዝነኛ ብራንድ ናቸው። ዶልቼ ጋባና ነፍሷ ነው።

“ሮዚ አይሆንም” እና “የለም” የሚሉት ቃላት በቪላ ኖቫ መዝገበ በቃላት ውስጥ ጭራሽ እንዳይኖሩ የተቻላትን ሁሉ አድርጋለች። ብርቱ የብቸኝነት ስሜት የሚሰማቸው ደምበኞች ብዙ ሴቶችን አዘው ክፍላቸውን ሲያደምቁ ብዙ ጊዜ ታዝቤያለሁ ድንገት የደምበኞቹ የሴት ፍላጎት በዝቶ የቪላው ሴቶች ቢያንሱ እንኳን ተደውሎላቸው በግል መኪናቸውና በኮንትራት ታክሲ ከተፍ የሚሉ በርካታ ለአይን የሚያሳሱ የኮሌጅ ሴቶች አሉ። Escort service ነው የሚባለው።ሚካኤል ናት የነገረችኝ ውጭ ሃገር የተለመደ ነው ብላኛለች።በኛ አገር እሷ ናት የጀመረችው

ቪላ ኖቫ ማሳጅ ደረጃውን ጠብቆ ይሰጣል። ወደ ክፍሉ ከመግባቱ በፊት ወይም ከገባ በኋላ ሰውነቱን በመታሸት ዘና ለማለት የሚፈልግ ደምበኛ አንደኛ ፎቅ ላይ ባሉት ቄንጠኛ ክፍሎች ገብቶ በቆነጃጅት ከስዊዲሽ እስከ አሮማ ማሳጅ ያሉትን አገልግሎቶች አንድ ላይ ይሰጣሉ

የቪላ ኖቫ አንደርግራውድ ቁማር ቤት ነው ትንሹ የቁማር መደብ 5000 ብር ነው። ቁማርተኞቹ ሽጉጥ ከታጠቁ ወደ ሰፊው ቁማር ቤት ከመግባታቸው በፊት በራፍ ላይ ቀልሀዎቹን
👍4
ር ምን መሰለሽ? እኚህ ኣዘውንት ሳቢ ላይ ፈታ ያሉ ናቸው ከላይ ከጠቀስኳቸው ትእዛዞቻቸው አንዱን ባሟላሁ ቁጥር 850 ብር ይለቁብኛል። ከፍያቸው ከዚህ ጨምሮም ቀንሶም
አያውቅም። እኚህ አዛውንት ለምንድነው ወሲብ የማይፈጽሙት? እያልኩ አስብ ነበር፡፡ ይህ ጥያቄ ለረጀም ጊዜ አዛውንቱን ባየሁ ቁጥር ሲያብሰለሰለኝ ቆይቷል አንድ ቀን የመጣ ይምጣ በሚል ጠየቅኳቸው።

በጥያቄዬ ምንም እልተገረሙም፡-

"ውይ የኔ ልጅ! ምን ነክቶሻል! እግዜሩስ ምን ይለኛል?! ከእግዜሩ መጣላት አልፈልግም። ስድስት
ለወግ ማእረግ የበቁ ልጆችን የሰጠችኝና ከቤት የማትወጣ ታማኝ ሚስት አለችኝ። አርባኛ አመት የትዳር ጥምረታችንን ልጆቻችንና ዘመድ አዝማድ በተገኙበት በድምቀት ድል ባለ ድግስ ዘከረናል።
በአክሊል ነው የተጋባነው። ቃል ኪዳኔን አፍርሼ ከሌላ ሴት ጋር ሩካቤ ስጋ ብፈጽም የእግዜሩን ቁጣና እርግማን እፈራለሁ። በንጹህዋ ሚስቴ ላይ ያን አይነት ውስልትና መሞከር ተይውና በፍጹም አላስበውም”

#የፓንት_ፖለቲካ


አንድ ቅዳሜ ከሰአት ከሲሳይ ራስተረ ጋር "ፒኮክ" መኪና ውስጥ ቁጭ ብለን አፕሬቲቭ እየጠጣን አንድ ካልሲ አዟሪ መጣ።ሲስ ሎተሪ ሻጭ፣ማስቲካ አዟሪ ኮንደም ቸርቻሪ ጋር ማውራት ሲወድ።"ምን ይሰራልሃል"ለምን ታደርቃቸዋለሁ፣ሰርተው ይብሉበት እንጂ" ስለው“ሮዚና ምን መሰለሽ… የድሮ
ነገስታት “አዝማሪ ምን አለ?” ይሉ ነበር። በኛ ዘመን የሕዝብ ብሶትን ለመለካት ከነዚህ ቸርቻሪዎች የተሻለ ቴርሞ ሜትር አይኖርም።ለዚህ ነው እህ ብዬ የምሰማቸው” ብሎ ያሾፍብኛል።

ይኸው ፒኮክ ፓርኪንግ መኪናችን ውስጥ ሆነን ሲስ ከአንድ ካልሲ አዘዋሪ ቆምጬ ጋር ይዳረቃል።

“ና እስኪ ጠጋ በል!”

“አቤት ጋሼ ምን ላሳይዎት፤ ካልሲ ላሳይዎት? ሸጋ ሸጋ ካልሲዎች አሉኝ.ፓንቶችም አሉኝ

“የየት አገር ልጅ ነህ”

“ማ! እኔ

ታዲያ ሌላ ሰው አለ እንዴ?

“ጎዣም"

“ባህር ዳር ነው?

እይ ከባህር ዳር እንኳ ትንሽ ወጣ ትላለች፣ ፍኖተ ሰላምን ያውቋታል ጋሼ”

“አላውቃትም፤ ስስም ነው የማውቃት፤ አንተ ባህርዳርን ታውቃታለህ?”

አዎ እንዴት አላውቃት ጌታው! አንድ ሁለት ጊዜ ሄጃለሁ፤ ሸጋ አገር ናት”

እኔ ምልህ! የዛ አገር ሴቶች ፓንት እንደማያደርጉ ታውቃለህ?”

ኧረ ጌታው እኔ በምን አውቄ፣ ገልጠው አያሳዩኝ ነገር." ልጁ ራሱ በተናገረው ነገር ሳቀ።

“ቆይ እሺ እዛ አገር ሴቶች ፓንት ገዝተውህ ያውቃሉ?”

ኧረ ጌታው እኔ እዛ አልነገድኩም፣ ኧረግ የሚያውቁኝ ዘመዶች አሉኝ እያልከዎ፤ ቤተሰቤን ለምን አዋርዳለሁ ጌታው?”

“ሥራ አይደለም እንዴ? ምን ችግር አለው?”

“ኧረግ ችግርማ ቢኖረው እይ እዚያ ማልነግድ፤ ምን ብዬ ነው በአገሬ ሙታንታ ምቸረችር? ምንስ ቢቸግር…”

“ለማንኛውም ጎዣም ብዙ ሴቶች ፓንት ማድረግ ትተዋል፤ ይሄን ታውቃለህ?

ኧረ እኔ አላውቅም? ግና ምነው አሉ ጌታው?”

“በል እንግዲያውስ እኔ ልንገርህ፤ ቅንጅት የተሸነፈ ጊዜ ነው የጎዣም ወጣት ወንድነቱ የተሸነፈ፣ ከ97 በኋላ ለፖለቲካም ለሴትም ያለው ስሜቱ አብሮ ነው የሞተ። ከዚያን ቀን ጀምሮ በከተማው አንሶላ የተጋፈፈ የለም ነው የሚባል።”

“እሱስ እውነት ነው ጌታው፤”
“ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጫት በባህርዳር ከድሬዳዋ ባልተናነሰ ይቃማል። ይሄን ታውቃለህ?

“ልክ ነው ጌታው"

"ታዲያ ሴቶቹን ማን ዞር ብሎ ይያቸው፤”

"አህ! ኧረ እኔን አያናግሩኝ ጌታው! እኔ የነሱን ጉዳይ የት አውቄ!"

እወቃ ካላወቅክ፤ እየነገርኩህ አይደል? እንድታውቅ እኮ ነው የምነግርህ። አሁን አንዲት የጎዣም ሴት አግኝተህ ብትጠይቃት ትነግርሀለች። ፓንት አታደርግም። ከአገሩ ጉብል ይልቅ የብስክሌት ኮርቻ የተሻለ ያስደስታታል። ከ97 በኋላ ብስክሌት ላይ መፈናጠጥ የተሻለ ሆኗል ይሉሀል። ሳትደብቅ
ትነግርሃለች።”

“ኧረ ጉደኛ ኖት ጋሼ! ዉስጠ-ወይራ ነው የሚናገሩ ጋሼ! ኧረግኝ! ተናግረው አያናግሩኝ ጌታው!”

“አሁን ግን ገባህ? ለምን ፓንት እንደማያደርጉ?”

አንገቱን በአዎንታ ነቀነቀና ዙርያ ገባውን መቃኘት ጀመረ።

አየህ ይሄ መንግስት ስንቱን ጉድ እንዳረገ! ስንቱን ያለ ፓንት እንዳስቀረ… "

ኧረ ጌታው እኔን ፖለቲካ አያናግሩኝ፣ ፓንት የሚገዙኝ ከሆነ ይግዙኝ."
ሲሳይ ሳቁ መጥቶበት እንደምንም ተቆጣጠረውና…።

እሺ ለሷ የሚሆን ሸጋ ፓንት አለህ? ሚስቴ ናት! እንደምታየው ቂጧ ትልቅ ነው፤ ከፈለክ እዚሁ ትለካዋለች።” አለው ወደኔ እያመላከተው።

“ልጁ አፍሮ አቀረቀረና ኧረ ጌታው የሴት ፓንት አልይዝም፣ እነሱ ባደባባይ መች ይገዙንና!”

“ግን እንዲሁ ስታያት አሁን ፓንት ያረገች ይመስለሃል? ገምት እስቲ”
ልጁ ሙሉ በሙሉ አፍሮ መሽኮርመም ጀመረ። ቀና ብሎ እኔን ማየት እንኳ አልቻለም።

ሁላችንም ሳቅን።

እሺ የወንድ ፓንት አለህ?ለኔ የሚኾን?”

“ሞልቶ ጌታው፣ ይኸው ይምረጡ!” ከፌስታሉ እያወጣ የፓንት መዓት ዘረገፈለት።

ለምን እንደሆነ አላውቅም የወንድ ፓንት ዉስጤ የሆነ የሚዝለገለግ ነገር ያለው ስለሚመስለኝ ተዘርግፎ ሳየው ይቀፈኛል።

አንተ እውነት ከጎጃም ነኝ የምትል ከኾነ ይሄን ጥያቄ መልስና ነው የምገዛህ”

እሺ ይጠይቁኝ ጌታው፤ ፖለቲካ ካልሆነ ምን ገዶኝ!”

“ኖ! ኖ! ፖለቲካ አይደለም። የአማርኛ ጥያቄ ነው የምጠይቅህ! ፓንት በአማርኛ ምንድነው የሚባል?”
እኛ እንግዲህ ሙታንታ ነው የምንል። አዋቂ ስንሆን ነው እይ ልጅ ሆነንማ ማን አስታጥቆን ጌታው”

“ሙታንታ አይደለም፤ ተሳስተኻል”
እና ምንድነው ጋሼ? ካወቁት እርስዎ ይንገሩና"

«ማኅደረ ቆለጥ» ነው የሚባል”
ልጁ የያዘውን ፌስታል ጥሎ በሳቅ ወደቀ፤ እኔም ሳቄን መቆጣጠር አልቻልኩም። ሲስም እኛን አጅቦ
ሳቀ።

ግማሽ ደርዘን ካልሲ ገዝቶ፣ በተጨማሪም 10 ብር ሸልሞ ሸኘው። በደስታ እየተፍለቀለቀ ጉዞ ሲጀምር
ሲስ እንደገና ጠርቶት ወደሱ ሲዞር በሩቁ የ "V" ምልከት አሳየው። ልጁም ጣቱን ሸሸግ አድርጎ ምላሽ ሰጠ።

ልጁ ሥራ ከጀመረ እንደዚህ ተደስቶ የሚያውቅ አይመስለኝም።


💫ይቀጥላል💫

#ሮዛ_2 ነገ ይጠናቀቃል ሌላ አዲስ ረጅም ድርሰት እንድንጀምር ገንቢም ይሁን የትችት አስተያየታችሁን ስጡን ማስተካከል ያለብንን እናስተካክላለን መልካም ጎናችንንም እናዳብራለን ከዛሬ ጀምሮ አስተያየት እየሰጣቹ መስጠጠት ካልቻላችሁ 👍 እየተጫናቹ።

Like 👍 እና #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍52
#ሮዛ_2


#ክፍል_ሀያ_ሶስት( 🔞)
(የመጨረሻ ክፍል)


#የሰው_ ልጅ_ዓለምን_ አትርፎ #ነፍሱን_ቢበድል....

ቤይሩት፣ ራፊቅ ሀሪሪ አየር መንገድ

አርብ ሌሊት

በምድር ላይ እጅግ ከምጠላቸው ሕዝቦች መሀል እገኛለሁ፤ ሊባኖስ ቤይሩት አየር መንገድ ውስጥ፤
ወደ አቡዳቢ ለመብረር። አየርመንገዱ በአረቦች ታፍኗል። አረብ አረብ ይሸታል። የተቀቡት ሽቶ አልተስማማኝም፤ እነሱን እንዲህ በጅምላ ማየት ራሱ ያቅለሸልሻል። አመመኝ።

ክትፎ የሚወድ ሰው ጣባውን ሲከፍተው የሚዝለገለጉ ትላትሎች ታጭቀው ቢያይ ሊሰማው የሚችለው ስሜት እኔ አረቦችን እንዲህ ብዙ ሆነው በማየቴ ተሰምቶኛል። አዲስ አበባ በተናጥል አገኛቸው ስለነበር
ለነሱ ያለኝ የጥላቻ ስሜት የዛሬውን ያህል አልበረታብኝም ነበር። አሁን አንድ ሙሉ ተርሚናል በሺ በሚቆጠሩ አረቦች ተሞልቶ ብመለከት ምግብ አልረጋ አለኝ። አመመኝ።

ከአረቦቹ መሀል ብዙ መልካምና ደጋግ ሊኖሩ እንደሚችሉ እረዳለሁ፤ የበርካታ ሺህ ወገኖቼ ህይወት በነሱ ላይ እንደተመሰረተም አውቃለሁ፤ ወላጅ አልባ ህጻናት የሚያሳድጉ ደጋግ አረቦች ብዙ አሉ፤ ይህንንም አልከድም። በሀገሬም ሆነ በሀገራቸው ከወገኖቼ ጋ ፍቅር መስርተው የወለዱና የከበዱ አረቦች
እንዳሉም አልክድም።ለወደዱት ሰው ቤት ንብረታቸውን በሙሉ የሚሰጡ፣ ሀበሻ ሰራተኞቻቸው ሲታመሙ ሚሊዮን ብር ከስከሰው ያሳከሙ አረቦች እንዳሉም ከዚያ የተመለሱ ጓደኞቼ ሲያወሩ
ሰምቻለሁ። እርግጥ ነው፤ የትኛውም ህዝብ ሰናይና እኩይ ሰዎች አሉት፤ አረቦቹም ከዚያ የተለዩ እንዳልሆኑ ጠንቅቄ አውቀዋለሁ።ይህን ሁሉ እየተረዳሁ ግን ለአረቦች ስር የሰደደ ጥላቻ ደሜ ዉስጥ ገብቷል፤ ምን ላድርግ?

ህሊናዬን በብርቱ ከፈተነ ማሰላሰልና መብሰልሰል በኋላ የህይወቴ ቀጣዩ ምእራፍ በአረብ ምድር እንዲሆን ወሰንኩ። በተባበሩት ኢምሬትስ ርእሰ መዲና አቡዳቢ ሬስቶራንትና የውበት ሳሎን ያላትን የአብሮ አደጌን የቢዝነስ አጋርነት ግብዣ ለአመታት አሻፈረኝ ብልም ሰሞኑን ውሳኔዬን ከብዙ የአእምሮ
ጂምናስቲከ በኋላ ቀየርኩ፤ ከዚህ በኋላ እንዴትም ብዬ የህይወት አቅጣጫዬን መለወጥ እንዳለብኝ ተሰምቶኛል።

#ተርሚናሉ_ዉስጥ
.
አረብ ወንዶች ያለመጠን የተርከፈከፉት ሽቶ ራሴ ላይ ወጣ። ተርሚናሉ ዉስጥ እየተዝለገለጉ ወዲያ ወዲህ ሲሉ ሆዴ ታወከ። መታጠቢያ ቤት ሄጄ ፊቴን በቀዝቃዛ ዉኃ ነከርኩ። ትንሽ ሻል ያለ
ስሜት ሲሰማኝ በወርቅ የተለበጠ ከሚመስል አግዳሚ ወንበር ላይ አንድ ጥግ ይዤ አረፍ አልኩኝ።
ለጊዜው በዙርያዬ የሚሆነውን ከማየት ዉጭ ሌላ እድል አልነበረኝም። አይኔን ብጨፍንም አረቦችን አያለሁ። አይኔን ብገልጥም አረቦችን አያለሁ። አማራጭ አልነበረኝም። ለካንስ አይንን መጨፈን ማየት የሚፈልጉትን ከማየት አይጋርድም። ዳያሪዬን ከእጅ ቦርሳዬ ዉስጥ ብታቀፈውም አእምሮዬ ባልተለመደ ሁኔታ ደንዝዞብኛል። በአየር መንገዱ አግዳሚ ቁጭ ብዬ ወጪ ወራጁን ስሜት አልባ ሆኜ አያለሁ።
የአረብ ጎታታ ወንዶች፣ በዚያ በሚዝለገለግ ነጭ ቀሚሳቸው ዉስጥ ሆነው አውሮፕላን ለመሳፈር እንደ
ግመል ይጎተታሉ። የቀሚሳቸው መጎተት ላያንስ በሩዝ የተወደረ ከርሳቸውን ይጎትታሉ፤ የከርሳቸው ሳያንስ ኩንታል ሻንጣቸውን ይጎትታሉ። የሻንጣቸው ሳያንስ ነጠላ ጫማቸውን ይጎትታሉ፤ የነጠላ ጫማቸው ሳያንስ ከረፈፍ ሚስቶቻቸውን ይጎትታሉ፣ የሚስቶቻቸው ሳያንስ ያልተቆነጠጡ አስራ ምናምን ልጆቻቸውን ይጎትታሉ። አራት ሚስቶቻቸውን እየነዱም ቢሆን አምስተኛ ሴት ከማየት አይመለሱም። ከአንድም ሁለት ሦስት አጁዛ አረቦች ከወዲያኛው የተርሚናሉ ሬስቶራንት ሆነው

እየሰረቁ ሲመለከቱኝ ዐይቻለሁ፡፡

በድጋሚ መታጠቢያ ቤት ሄጄ ተመለስኩ። ዛሬ ምግብ አልረጋ ብሎኛል።

ቀልቤ አይወዳቸውም። በተለይ እንዲህ ነጭ ቆብ በነጭ ቀሚስ ለብሰው ሳያቸው፣ በነጭ ኩባያ ወተት ከአናታቸው እየፈሰሰባቸው ስለሚመስለኝ የዝንብ አየር ማረፍያዎች እንጂ ሰዎች ሆነው አይታዩኝም።ሰው ነጭ ለብሶም ንፁህ ሆኖ ካልታየኝ መቼስ የሆነ ችግር አለበት ማለት ነው። ለምንድነው ፈጣሪ እኛን
ድሐ እነሱን ሐብታም ያረገው? እግዜር ምናቸው ማርኮት ይሆን አሻዋቸውን የባረከው? በረሃቸውን ያረጠበው?!

“የአረብ ጥላቻ የተፈጠረብኝ መቼ ነው?” ብዬ ለማስታወስ ሞከርኩ። ትዝ የሚለኝ ነገር የለም። ምናልባት ኡስማን ዘ ፒምፕ ስለሚጠላቸው እሱ ሳያውቀው አጋብቶብኝ ይሆን? አይደለም። ኡስማንን
ሳላውቀው በፊት አረብ የሚባል ፍጥረት ያስጠላኝ ነበር። ልጅ እያለሁ የጀመረኝ ይመስለኛል። አያቴ በነበረችበት ሰፈር። ባደኩበት ሰፈር፣ በነእማማ ዙበይዳ ሰፈር።

ልጅ እያለሁ ለተወሰነ ጊዜ ሴት አያቴ ታሳድገኝ ነበር። በሰፈራችን የምንወዳቸው፣ እማማ ዙበይዳ
የሚባሉ ሴት ነበሩ። የሆኑ ደርባባ አሮጊት ሴትዬ። ሰው ዝም ብሎ ይወዳቸው ነበር። ጎመን መንገድ ላይ ይሸጣሉ። በክረምት ደግሞ በቆሎ ይሸጣሉ። እማማ ዙበይዳን ሰፈሩ ሁሉ ለምን ይወዳቸው እንደነበር ግን በትክክል አላውቅም። እኔም እወዳቸው ነበር። ለምን እንደነበር ግን አላውቅም። “ነይ እስቲ አንቺ
ጎራዳ!" እያሉ ግንባሬን ይስሙኝ እንደነበር ብቻ ነው ትዝ የሚለኝ።

እማማ ዙበይዳ ባልም ዘመድም የላቸውም። በምድር ላይ ያለቻቸው ፋጤ ቀጮ ናት። የሳቸው ብቸኛ ልጅ ፉጤ ቀጮ ጅዳ ሄደች ተባለ። ሰፈሩ ሁሉ እማማ ዙበይዳ በቃ ሻሩ፣ አሁን ወርቅ በወርቅ ሊሆኑ ነው ብሎ ተነበየ። እሳቸውን ያገኘ ሰው ሁሉ “ፋጤ ቀጮ ጅዳ ነው አይደል የሄደችው?”፣
ትደውላለች”፣ “ደህና ናት ታዲያ፣ “አሁን ለመድኩ አለችፖ፣ ግህም፣ “በርቺ በሏት እንግዲህ!
ይለመዳል.ይለመዳል”፣ “ዋናው መበርታት ነውታዲያ”፣ “እ!” እያለ ከእማማ ዙበይዳ የበቆሎ እሸት
ወይ ጎመን ገዝቷቸው ያልፋል። በበጋ ጎመን በከረምት የበቆሎ እሸት በመሸጥ ነበር የሚተዳደሩት።
በዚያ ሁሉ የሰፈር ሰው ሳይታክቱ በዚያ እናታዊ ፈገግታቸው ታጅበው ስለ ልጃቸው ደኅንነት ምላሽ ይሰጣሉ። “እላሙዲሊላ አላሂ ወላሂ ደህና ናት!ዱዋ አርጉላት." ይላሉ፤ መልሰው መላልሰው።

ሲኖሩ ሲኖሩ.…የሆነ ጊዜ ላይ ልጃቸው ስልክ ደውላ አለቀሰች ተባለ። “ምን ሆንሽ” ሲሏት አትናገርም
ሲኖሩ ሲኖሩ…የሆነ ጊዜ ላይ ደግሞ መደወል አቆመች ተባለ። ደህንነቷን የሚነግራቸው ጠፋ። ጎመን ወይ
በቆሎ ለሚገዛቸው የሰፈር ሰው ሁሉ “አረብ አገር ስልክ ማድረግ ታውቅበታለህ?” እያሉ ይጠይቃሉ።
የተማረ የሚመስል ወጣት ሲመለከቱ ደግሞ “ልጄ! እስኪ ባክህ የጅዳ ስልክ ቁጥር ጽፈህ አምጣልኝ? ልጄ ናፈቀችኝ ይሉታል። የሷ ስልክ ቁጥር ግን የላቸውም። አንዳንድ ሰው ነገሩን ሊያስረዳቸው ሞከረ።ኾኖም ሊገባቸው አልቻለም። የሰፈሩን ሰው መሄጃ መቀመጫ አሳጡት። እርስዎ ስልኳን ፈልገው ያምጡ! እኛ እንደውልሎታለን” ሲባሉ እኔ ቁጥሯን ከየት አዉቄ” ነው መልሳቸው። እሷ ካልደወለች
እሳቸው ወደየት ብለው ይደውላሉ? አድራሻዋ አይታወቅ ነገር።

የሰፈሩ ሰው በሙሉ እማማ ዙበይዳ ሲያዝኑ አይቶ አዘነ። እማማ ዙበይዳ የደግነት ምሳሌ ነበሩ። ፋጤ
ቀጮ እጅግ ስትናፍቃቸው ግን ሰው ሰላም ሳይሉ ማለፍ ሁሉ ጀመሩ። የሚሸጡት ጎመን ጠወለገ።
ወዲያው ደግሞ ወገባቸው ጎበጠ። ከመቼው በእድሜያቸው ላይ ምዕተ ዓመት እንደጨመሩ። ሰው የልጁ ናፍቆት እንደ ኤድስ አመንምኖ ሊገድለው እንደሚችል ያየሁት በእማማ ዙበይዳ ነው።

ከ5 ዓመታት በኋላ ልጃቸው ፋጤ መጣች ተባለ። በዊልቸር ላይ ሆና። በጣም ከመወፍሯ የተነሳ ዊልቸሩ ጠበባት። ፋጤ ቀጮ ትባል የነበረችው የሆነች ሲንቢሮ በረሮ ስለበረች ነበር።ታዲያ ለምን ወፈረች? ተስማምቷት ነበር ማለት ነው?
👍4