አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
is what is happening now.
የምለው ካልተዋጠልሽ ታሪክን ወደ ኃላ ለማየት ሞክሪ። አስተውለሽ ከኾነ ብዙ ህዝብ ዉስጥ ዉስጡን መንጌን ይወዳል። መንግስቱ ኃይለማርያምን ሙሉ ስሙን ሰው ሲጠራ ሰምተሸ ታውቂያለሽ? ብዙ ሰው አሁንም ድረስ “መንጌ” እያለ ነው አቆላምጦ የሚጠራው። ለምን መሰለሽ…ቂጡን በሳንጃ እየወጋ ስለገዛው ነው። ሕዝባችን ገዳይ ይወዳል። ጀግና የሚለው ቀጥቅጦ የሚገዛውን ነው።

ሄይ ሄይ ሲስ! በናትህ ፖለቲካ አታውራብኝ…ራሴን ያመኛል። በናትህ…”
እኔ የምለውን ችላ ብሎ ማውራቱን ሲቀጥል አቋረጥኩት።

ደሞ ምንድነው የምትዘባርቀው? You are not making sense to me at all. ስለ መኪና አነሳህ ዞረህ ደሞ የሌለ ፖለቲካ ዘባረቅህ። ከዚህ በላይ ዲሞክራሲ ከየት ይምጣልህ…. ማክያቶ እየጠጣህ አፍህ እንዳመጣልህ ሕዝቡን እየተሳደብክ ዲሞክራሲ የለም ትላለህ እንዴ? ደግሞ ሕዝብ ሲባል እኮ አንተም አለህበት። …ደግሞ ቀስ ብለህ አውራ! …» አልኩ ዙርያዬን እየገላመጥኩ።

See Rozil Look at yourself now! በፍርሃት ዙርያሸን እየተገላመጥሽ እንደገና ደሞ ከዚህ በላይ ዲሞክራሲ ከየት ይምጣልህ ትይኛለሽ፡ ድምጽህን ዝቅ አርገህ አውራ እያልሽ፣ ዲሞክራሲ አለ ትያለሽ....

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
ይስቃል። ምንድነው የሚያስቅህ ብዬ ስጠይቀው አንድ የጅማ ነጋዴ ትዝ ብሎት እንደሆነ ነገረኝ።

ቡና ላኪ የአጋሮ ነጋዴ ነው። ያው እነሱ ታውቂያቸዋለሽ በጣም ብር አላቸው ግን ደህና ጫማ እንኳን አይገዙም። ሁለት ግራ እግር ነው የሚጫሙት። እና ይሄ ነጋዴ ጨክኖ መኪና ገዝቶ ቀስ እያለ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች እየነዳ ዓለሙን ይቀጫል። በእግሩ ሲሄድ ከሰው ቆጥረውት የማያውቁት የአዲሳባ ቺኮች ሁሉ መኪና ሲይዝ ከሱ አይናቸውን አልነቅል አሉ። እና … የአዲስ አበባ ሴቶች ደሞ መኪና ከያዝክና ክላክስ ካረክላቸው
ዐይናቸውን አያሹም፤ ይሰጡሃል ፤ እንዲያው ዘለው ነው መኪናህ
ዉስጥ የሚገቡት» ብለውታል ቀድመው የባነኑ ያገሩ ሰዎች።እና በዚህ በቦሌ አቅጣጫ ጥግ ጥጉን ቀስ እያለ እየነዳ ሲሄድ ድንገት «ታጥቦ የተፈጨ 1ኛ ደረጃ ቂጥ» ያያል። አጅሬው ከፊት ከፊቱ ሞንደል ሞንደል እያለ የሚሄደውን ቂጥ ቀስ እያለ ተከተለው። በዜሮ እየነዳ ይሄን ቂጥ እግር በእግር ይከተላል ይከተላል… ይከተላል። እየቆየ ሲሄድ አላስችል አለው። ነፍሱ ቂጥ አይታ ቀጥ ልትልበት ሆነ። የጅማ ጓደኞቹ ምከር ትዝ አለው። ክላክሱን ተጫነው። ጲ…ይ. ጵ! …”

ከላከስ ከኋላዋ ያንባረቀባት ባለቂጥ በድንጋጤ ዞር ስትል ፊቷ በጣም አስፈሪ ከመሆኑም በላይ
በፍጹም የዛ ሞንዳላ ቂጥ ባለቤት የማትመስል፣ እንዲያውም የቦክሰኛው የማይክ ታይሰን ታላቅ እህቱ የምትመስል አስፈሪ ሴት ትሆንበታለች። ይሄኔ ተፀጽቶ ምን ቢል ጥሩ ነው?
አንቺን ማን ጠራ...ሲሚሽ ጲጵ ነው ኢንዴ!?”

ሲስ ቀልዱን ሲያወራው እንዴት እንደሚያስቅ፡፡

ተንከትከቼ እየሳቅኩ ሳለ ዳሽ ቦርዱ ላይ ተቀምጣ የነበረችው የሲስ ሞባይል አንጫረረች። እየነዳ ስለነበረ እኔ አነሳሁለት።

“ሀሎ…ሲሳይ መኪና እየነዳ ነው።…ማን ልበል? "

ሴት ናት። የኔን ድምጽ ስትሰማ ደንግጣ ጆሮዬ ላይ ዘጋችው።
ሲስ የሆነውን ስነግረው መኪናውን ጥግ አሲዞ መልሶ ቁጥሩ ላይ ደወለ።

“በዚህ ስልክ ተደውሎ ነበር

“ተሳስተዋል፤ ይሄ ካልዲስ ኮፊ ነው።”


💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍2
ምድር ቤት ያስቀብራል እየተባለ ስለሚታማ ሀሜቱ ተጠናክሮ ቀጠለ። “ጥቁር ሴት ቅጠር ተብሎ በአውሊያ ተነግሮት ነው” ተባለ። “እህቱ ናት” ይሉ የነበሩ ሰዎች የሴት ቢዝነስ ሊያሰራት እንደሆነ ሲያውቁ አፋቸውን ዘጉ።

ደሜ ገንዘብ ያገኘው በመተት እንዳልሆነ አውቃለሁ። አዱንያ የዘነበለት ኤርትራዊያን ሲባረሩ ነው። ቄራ አንድ ጋራዥ ዉስጥ ይሰራ ነበር። የቤቱ ባለቤት አባ አስገዶም ይባሉ ነበር። ደሜ ያኔ የቅርብ ረዳታቸው ነበር። ኤርትራዊያን ከአገር ይዉጡ ሲባል ደሜ ጋራጁን በአደራ እንዲያስተዳድር ተሰጠው።
ከቀበሌ ጋር ተሞዳምዶ እንደኾነ ነገር አድርጎ ጠቀለለው። አሁንም ድረስ “የሱ አይደለም፣ ሚኒስትር የሆኑ የአገሩ ሰውዬ ናቸው በሱ ስም አድርገው የሚሸቅሉበት” ይባላል። እኔ ግን አይመስለኝም። አንድ ሚኒስትር ምንም ቢልከሰከስ ከአንድ ጋራጅ ቤት ምን ብር ያስለቅመዋል? ደሜ ጋራጁን ሸጦ እዚ
ሮማን ሕንጻ ዉስጥ አሪዞናን ከፈተ።

አሁን ደሜ ተወደደም ተጠላ የአሪዞና ጌታ ነው። በከተማው ቁጥር አንድ የሆነ፣ በየምሽቱ ብር፡ሪያልና ዶላር የሚታተምበት ክለብ ነው በባለቤትነት የሚያንቀሳቅሰው። እንኳን እሱ እኛ ለሱ የምንሰራው እንኳ አንዳንዴ ብር በዝቶብን ያስነጥሰኛል፤የሚሰራንን ያሳጣናል። እሱም እንዲያ አድርጎት ይሆናል።ዝናሽን እየቀጠራት ያለው።

አሁን ዞሮ ዞሮ ዝናሽ ሸሌ ልትኾን ነው። ደሜ ባቀናው “ክለብ አሪዞና” ዝናሽ ቢዝነስ ልትጀምር ነው
በውነቱ ይሄን ማን ያምናል?

ዝናሽ በሂል ጫማ

እውነትም ሰው ከጣራ የትም ይደርሳል ይኽው ዝናሽ በሂል ጫማ ተራመደች ተባለ። ያን ምሽት ሂልተን ቢዝነስ ወጥቼ
ስለነበረ አሪዞና አላደርኩም፡፡ ወሬውን ስሰማ ግን ሳቅኩኝ። መጀመርያ ስትራመድ በአይኔ በብረቱ ካላየሁ አላምንም ብዬ ድርቅ አልኩ። የምሬን ነበር። በፍጹም ዝናሽ በሂል ጫማ
ስትራመድ ማሰብ አልቻልኩም። በቃ ሊመጣልኝ አልቻለም። በቃ ሊዋጥልኝ አልቻለም፡፡ ሴቱ ሁሉ የውስጥ እጄን እየጠፈጠፈ ሲምልልኝ ግን ዝናሽ እውነትም በሂል ጫማ ተራምዳ ሊኾን እንደሚችል ጠረጠርኩ። ሁኔታውን እነ ሳሪ አዳምቀው ሲነግሩኝ በጣም በስሜት ተውጠው ነበር።

መጀመርያ ሁለት የአሪዞና ጋርዶች ማለትም ተሼና ሳሚ ባሪያው በግራና በቀኟ ቆመውላት እነሱን ተደገፈች ተባለ። ከዚያም ለአንድ ደቂቃ ያህል ሚዛኗን ለመጠበቅ ሞከረችና ልቀቁኝ አለቻቸው።
እርግጠኛ ነሽ ዝናሽ” አሏት ተባለ፤ እኵል ደንግጠው። “አዎ ግን ቀስ ብላችሁ ልቀቁኝ” አለቻቸው።ተሼና ሳሚ ባሪያው ሰፈሩና ሲቸሩ ቀስ ብለው ለቀቋት።

ከሳሚ ባርያው ተላቃ ስትቆም አሪዞና ፐብ ሴቶች ቤት በቀውጢ ጭብጨባ ተናጋ አሉ።

እንደገና ዝናሽ ሚዛኗን ጠብቃ ከቆመችበት አንድ እግሯን ስታነሳ የሴቶች ቤት በጸጥታ ተዋጠ ተባለ።
ትንሽ ከተንገዳገደች በኋላ ሁለተኛ እግሯን ስታነሳ የተሰበሰበው ሴት ባለማመን አፉን ከፍቶ ቀረ።እንደዚህ አይነት የአድናቆት አፍ አከፋፈት የታየው የኒውዮርክ መንታ ሕንጻዎች ላይ ጥቃት የደረሰ ጊዜ ብቻ ነበር ተባለ። ለሦስተኛ እርምጃ ቀኝ እግሯን ስታነሳ በደስታ እምባ የተናነቃቸው የአገሯ ልጆች ነበሩ ተባለ። ነገሩን አጋነው ሲያወሩልኝና ስስቅ ከረምኩ።

ብቻ ዞሮ ዞሮ “ዝናሽ በሂል ጫማ ተራመደች።

#ዝናሽ_አገባች

ቆይ እንጂ ወደ ትዳር ዝም ብሎ አይገባም። ትዳር ቀልድ አይደለም። ትዳር ብዙ ዝግጅት የሚፈልግ ነገር መሰለኝ። ትዳር ሾርት አይደለም ዝም ብሎ የሚገባበት። ስለዚህ “ዝናሽ አገባች” ከማለቴ በፊት፣ ዝናሽ ከማግባቷ በፊት ስለነበሩ ሰባት ወራት መናገር አለብኝ። ዝናሽ በነዚህ ወራት በክለብ አሪዞና ምን
አደረገች ? መጀመርያ እሱን ልፃፍ።

To make the short story even shorter እንዲሉ ፈረንጆት ዝናሽ ብሂል ጫማ መራመድ ቀስ በቀስ ቻለች። መጀመርያ አካባቢ ዩሪ ጋጋሪ ጨረቃ ላይ የሚራመድ እንጂ እሷ የምትራመድ አትመስልም ነበር። ከአንድ ጠረጴዛ ተነስታ ወደ ሌላ ስትራመድ ጠጪው ሁሉ በሰቀቀን በዐይኑ ይከተላት ነበር።ለቤቱ አዲስ የሆኑ ሰዎች ሰክራ ስለሚመስላቸው ብዙም አይደነቁም፤ እኛ ባልደረቦቿ ግን እሷን በማየት ስራ ፈታን ።

በነገራችን ላይ ገዝናሽ እንዴት ረዥም እንደሆነች ተናግሪያለሁ። በዚያ ቁመቷ ሂል ጫማ ስታደርግ G+3 ፎቅ ነው የምትመስለው። እንስራ የሚያህለው ጭንቅላቷ ደግም ፎቁ ላይ የተሰራ “ፔንት ሀውስ ይመስላል። እኛ የቤቱ ረዥም ሴቶች እንኳን ኮምፕሌክስ ነገር ስለሚሰማን ከጎኗ ደፍረን አንቆምም።
ታሳጣናለቻ። እሷ ግን ቁመት ብቻ ሳይሆን ጥቁረትም ውፍረትም ክብደትም የሚያህላት ስለሌለ ቤቱን እየረገጠች ታንቋቋዋለች። እሷ ስትራመድ ምድር ትንቋቋለች፤ ይቺ ምድር ስንቱን እንደቻለች ይቅር ይበለኝ።

ዝናሽ ከጡቷ ይልቅ ጎንጯ ጡት መያዣ ይፈልጋል። በዚያ ሰውነት ላይ ፈጣሪ ለምን ትንንሽ ጡቶች እንደተከለላት ይገርመኛል። ሰፊ ደረቷን አይቼ ትንንሽ ጡቶቿን ሳስብ አእምሮዬ ላይ የሚመጣው ሁለት 0 አምፖል የተገጠመለት ሠፊ የሰርግ አዳራሽ ነው ይቅር ይበለኝ።

ያም ኾኖ ሚኒስከርት አድርጋ፣ ሽቶ ተርከፍከፉ፣ የቢራ ጠርሙስ አንቃ ቁጭ ትላለች። ልክ እንደኛ ወንድ ፍለጋ! ባለጌ ወንበር ላይ። ባለጌ ወንበሩ እሷ ስትቀመጥበት ጨዋ ኾነ። ዱካ ኾነ። ረዥም ስለሆነች ቀርጩማ ላይ የተቀመጠች ነው የምትመስለው። ባለጌ ወንበሩ ላይ ምንም ሳትንጠራራ ነው
ሄዳ ጉብ የምትልበት። ሰው ባለጌ ወንበር ላይ ተንጠራርቶ ነው የሚወጣው፤ እሷ ግን እንዲያውም በርከክ ትላለች መሰለኝ
ይቅር ይበለኝ!

ብቻ ዝናሽ እንደምንም ተኳኩላ ቢዝነስ ጀመረች። የመጀመርያ ቀን ማንም ወንድ ቀና ብሎ ሲያያት ስላላየን ስላላየን በአንድ ድምጽ “የፈራነው ደረሰ" አልን። ከሷ ጋር የሚያድር ወንድ ካለ ሄጄ
አስፈርመዋለሁ ስትል ነበር ትምኒት። እውነቷን ነው። ይህ ነገር ለተከታታይ ሁለት ሳምንታት ቀጠለ።ሁላችንም ተደናገጥን። አሳዘነችን። ምንም ቢሆን እኮ ሴት ናት። የበታችነት ስሜት ተሰምቷት ራሷ ላይ አደጋ እንዳታደርስ ፈራን። እሷ እቴ ምንም አልመሰላትም። ትኩረቷ ሁሉ በሂል ጫማ እንደልቧ መራመድ መቻሏ ላይ ብቻ ነበር ፈ። አንድ ቀን ደፍረን ደሜን ነገርነው....

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍51😱1
ሞባይላችንን አውጥተን ዜናውን ባንድ ጊዜ ነዛነው፡፡ የደወልንላቸው ሁሉ ለተጨማሪ መረጃ እኛ ሴቶች ቤት ተንደርድረው መጡ። ግማሹ ሱዳናዊው ሰውዬ እጣን ነጋዴ ነው ይላል፤ ግማሹ ደቡብ ሱዳን ውስጥ የነዳጅ ማጣሪያ አለው ይላል። ግማሹ ባህርዳር ካርቶን ፋብሪካ አለው ይላል። ያየውም ያላየውም እኩል አውቀዋለሁ ማለት ጀመረ።

ዝናሽን የሰርጉ ቀን እስኪደርስ ሳር ቤት ካናዳ ኤምባሲ ጀርባ በአንድ ቪላ ቤት ውስጥ አሳርፏታል ተባለ። መጥቶ ከዚህ የወሰዳት እንዲያዉም በነጭ መርሴዲስ ነበር ተባለ። የገረመኝ ይሄ ሁሉ ሲሆን እኔ የት እንደነበርኩ ነው።

ከዚያ በኋላ ጆርዬ መስማት ከሚችለው በላይ መረጃ ደረሰኝ። የሰርጓን ቪሎ እንድትመርጥ ደቡብ አፍሪካ ይዞት ሊሄድ ነው ተባለ። ሰርጉ በአንድ ሳምንት ልዩነት ካርቱምና አዲስ አበባ ነው የሚካሄደው
ተባለ። ለሰርጉ እኔ ራሱ በጣም የምወደው አንድ ዘፋኝ ተጠርቷል ተባለ። የሰው ሰርግ ላይ ይዘፍናል ብዬ የማልጠብቀው ዘፋኝ ነበር።

የሱዳን ታዋቂ ዘፋኞችም አዲስ አበባ ይገኛሉ ተባለ። “ታዲያ በርበሬ መቀንጠስ እንጀምራ? ስንል ሰርጉን የሚያሰናዳ ድርጅት በብዙ ሺህ ብር ስለተቀጠረ ማንም ምንም ማድረግ አይጠበቅበትም
ተባለ። የሰርጉ ቀን እስኪቃረብ ለሦስት ሳምንታት ያህል ክለብ አሪዞና በጭራሽ ሌላ ወሬ አልተወራም ዝናሽ ነበረች በሁሉም ሰው አፍ ዉስጥ የምትታኘከው

#መደምደሚያ

ይሄን ማስታወሻ ስጽፍ ጎልፍ ክለብ ሰርጓን በልቼ መግባቴ ነው። በሕይወቴ ብዙ ሰርግ አይቻለው።እንዲህ ዊስኪ የተረጨበት፤ እንዲህ ሙዚቃ የተደለቀበት፤ እንዲህ ቁርጥ የተቆረጠበት፣ እንዲህ ሩዝ የተደፋበት ሰርግ ግን አጋጥሞኝ አያውቅም። ሦስት ታዋቂ የሱዳን የሰርግ ዘፋኞችና አንድ ሙሉ ባንድ
ከካርቱም አዲስ አበባ መተው ነበር። ስማቸውን እየጠሩ ዘፈኑላቸው።ዝናሽን በሱዳንኛ ዘይና እያሉ ነበር የሚጠሯት።እሷም ባሏም ሚዜ አልነበራቸውም።ለምን እንደዚሉ እንዳደረጉ አልገባኝም።ያለሚዜ ሰርግ ሲካሄድ ሳይ የመጀመርያየሰ ነው።ቢሆንም ቅልጥ ያለ ሰርግ ነበር።

በመስቀል ፍላወር አካባቢ ሴት አንዷም አልቀረችም።ሁሏም እስክትፈነዳ በልታ፤ እስክተሸና ጠጥታ ነው የሄደችው።ቀታሪክ ብዙ ሸሌ የተገኘበት ሰርግ ይመስለኛል።

አቤት ግን ዛሬ ሰውን እንዴት እንደታዘብከለት ዝናሽን እንደዛ እንዳላበጠለጠሏት እንደዚያ እንዳልሳቁባት እንዳላፌዙባት እንዳልሸሿት ሞጃ አግብታ ሞጃ መሆኗን ሲያውቁ ስሟን ከመቼው ከዝናሽ ወደ "ዜድ" እንደቀየሩት።ከመቼው ቁንጅናዋ እንደታያቸው።ከመቼው ከንፈሯ እንደሳሳባቸው ያ የምድር ወገብን የሚያክለውን ወገቧን እኮ "ችቦ አይሞላም"ሲሉት ምንም አላፈሩም። እነ ተሼ በሷ ዕይታ ውስጥ ለመግባት እንዴት በእስክስታ እንደተርገፈገፉ።እነ ውቢት እሷ እንድታያቸው እንዴት ቂጣቸውን እነደቆሉ። ይቺ ቅሳነት ድፍረቷ ድፍረቷ! የሷ እንኳን ለጉድ ነው።ሱዳንኛ በተዘፈነ ቁጥር ከሙሽራው ፊት እየሄደች " ኡ ያዙኝ ልቀቁኝ !" ስትል ሰው ይታዘበኛል እንኳን አትልም?የምር ሰውየው ሁለተኛ ሚስት አድርጎ እንዲወስዳት የፈለገች የሸመስል ነበር።

ለካስ ቁንጅና ማለት ገንዘብ ነው።ለካስ ውበት ማለት ሃብት ነው።እኔ ራሴ ዝናሽ እንዴት ያን ቀን ቆንጆ ሆና እንደታየችኝ ዐይኔ ተጭበረበረላት እኮ! ሳኩላት ቀናሁባት ብቻ ልእልት መስላ ታየችኝ።በአእምሮዌ ውስጥ ያቺ ጭስ ጭስ እየሸተተች ቢጫ ፊስታል ይዛ የዛሬ ሦስት ዓመት ያየኋት ባላገርና የዛሬዋ ሙሽራ ለየቅል ናቸው።ላመሳስላቸው ብሞክርም አልቻልኩም። ለካንስ ውበት ማለት አስተሳሰባችን ውስጥ ነው የሚሳለው።ዝናሽ ልቅም ያለቸሸ ቆንጆሆና ታየችኝ።

#ድህረ_ታሪክ

ዝናሽ ከዛ በኋላ ወደ ክለብ አሪዞና ብቅም አላለችም።ነገር ግን የክለቡ ጋርዶች የነበሩትን ተሼንና ሳሚ ባርያውን ሕይወተሸ ለወጠችላቸው።ሁለቱም የሷና የባሏ ረዳቶች ሆነው ካርቱም ሄዱ ከባሏ ጋር የምትዟዟርበት የዓለም ጥጉ ሁሉ አብረዋት ይሆናሉ።ደሞዛቸው ሲነገረኝ ስላላመንኩበት በማስታወሻዬ አልፃፍኩትም።ሳሚ ባርያው እንኳን አውስትራሊያ ለሽርሽር እስኪሄዱ ነው እንጂ እዚያ ሲደርስ እንደሚጠፋ እርግጠኛ ነኝ የሱ የአውስትራሊያ ፍቅር የአውስትራሊያ ዜጎች እንኳ የላቸውም

ደሜ ደግሞ በደቡብ ሱዳን ቅርንጫፍ የሀበሻ ክለብ እንደሚከፈትለትና ለዚህ ሁኔታዎች እንደሚመቻቹለት ቃል ተገብቶለታል፡፡ ይኸው ነው ዝናሽን ግን ምንም ብንጥር ያን ቀን ከሩቅ ከማየት ውጪ በቅርብ ልናገኛት አልቻልንም በሁላችንም እእምሮ ግን አንድ ነገር ሲብሰለሰል ቆየ ይህን ዲታ ሱዳናዊ ከመቼው በእጇ አስገባችው? እንዴት ነገሮች በዚ ፍጥነት ተለወጡ?ምኗ ማረከው?ምን አስነካችው?

መልሱን ያገኘሁት ከውቢት ነው።

እሷ እንደነገረችኝ ሰውየው አዲስ አበባ
በየጊዜው ለመዝናናት ይመጣል። ሀበሻ ሴት ደግሞ ነፍሱ ነው። ግን
ወሸላው ኢይቆምለትም። ለብዙ ዓመታት ተሰቃይቷል አይቆምለትም!

ዝም ብሎ ይዞሸ ይገባና ደባብሺኝ፣ ንከሺኝ፣ ቦጫጭሪኝ ብሎሽ ስሜቱ ሲመጣ በሱዳኛ እየጮኸ እየቀበጣጠረ ቂጥሽን ንክስ ያረግሽና ስሜቱን ይጨርሳል ስለነከሰሽ ብቻ ሞቅ ያለ ብር ይሰጥሻል።ታድያ ዝኑን እንደለመደው ሊነክሳት ሲል ወሸላውን ጭምቅ አድርጋ ይዛው አይኗን ጨፍና ትጮሃለች ይሄኔ ያልተጠበቀ ተዓምር ተፈጠረ ሰውየው ወሸላው ቆመለት ይታይሽ ከ 30 ምናምን ዓመት በኋላ ዘንድሮ Liverpool ዋንጫ እንደበላው ማለት ነው
የሱም ከ30 ዓመት በኋላ ነው ይሄ የሆነለት። በደስታ ሰከረ ደጋገሙት። ቁላው ሰራለት። ዝናሽ ይህን ያረገችው በመተት ይሁን ባጋጣሚ ግን የማውቅልሽ ነገር የለም ብቻ ስውየው በደስታ አለቀሰ። ሁለቱም ራቁታቸውን እያሉ እዛው አንደር ግራውንድ ቤት እግሯሥር ተንበርክኮ ለመናት፤ እንድታገባው እግኝታ ነው!! “ባንዳፍ
አለችው። ቁላው እንደቆመ በደስታ የሚያደርገውን አሳጥቶት፤ እስኪነጋ እንኳ መጠበቅ አቅቶት ያንኑ ምሽት በነጭ ማርቼዲስ ይዟት በረረ ወጀ ሳር ቤት።

“ ሮዝ! ይሄንንም ወሬ ብለሽ ልትጽፊው እንዳይሆን ደግም…”

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍5
ሴት ገነትን አትወርስም፡ንሰሀ ግቡ!ከዚህ ውጉዝና ቆሻሻ ህይወት ዛሬውኑ ውጡ!” ብሎ
የይምሰል መንፈሳዊነቱን በአደባባይ ሊያሳይ ይፈልጋል። አስቹ You tube ላይ በተለቀቀ አንድ ስብከቱ
"እውነተኛ ህይወት ያለው በሰማይ ቤት ነው” ሲል ቢታይም የሱ ቤት ግን ክለብ አሪዞና እንደሆነ ነው የምናውቀው፡፡ በክለብ አሪዞና መኪናና ቆነጃጅትን እንደ ሸሚዝ ሲቀያይር ነው የምናየው፤ ያማረውንና ያሻውን መጠጥ አስወርዶ በውስኪ ሲራጭ ነው የምናውቀው።

መምህር አስቹ ወደ ክለብ አሪዞና ሲመጣ ዘወትር እንደሚያደርገው ማንነቱ ለመቀየር ይታትራል።
የምታምር ሰማያዊ ስካርፍና ትልቅ መነጽር አድርጎ ነው የሚመጣው። እኛ ሁላችንም የክለብ አሪዞና ሴቶች ለይተን እናውቀዋለን። ከሱ ጋር ሾርት አዘውትራ የምትወጣው ግን ዉቢት ናት። አስቹ መጥቷል ስንላት እስቲ ሾርትና ንስሀ ገብቼ ልምጣ” ትለናለች። እንስቃለን፡፡

ሁልጊዜም ጋብዞን ነው የሚለየን። ንግግር ሲችልበት ለጉድ ነው። ሲያወራ አፍ ያስከፍታል። አማርኛው እንዴት ስክትክት እንደሚልለት ግርም ነው የሚለኝ። በከተማው አንድ ጥግ መሬት ገዝቶ የሚያምር ቪላ እያስገነባ እንደሆነ በአንድ አጋጣሚ አጫውቶኛል። ህይወት በሰማይ ቤት ነው እያለ ምድር ላይ
ቪላውን ያጣድፈዋል። መቼስ መምህር አስቹ ከፀደቀ እኛም ለመጽደቅ ተስፋ አለን ማለት ነው።

ግን አስቹን በምን አስታወስኩት? የሜርሲ ባል የገዝሽ ተለዋዋጭ ጠባይ ነው መምህር አስቻለውን

ያስታወሰኝ።መቼም ይቺ ፌክ አለምና ይህ ህይወት የማያሳየን ጉድ የለም።

ከፍሪጅ በረዶ አውጥቼ የሜርሲን የፊት እብጠቶቸ ነካካሁ። ፊቷን እያሻሸሁላትም መዛቷን አላቆመችም ከዚህ በኋላ አብራው እንደማትቀጥል ትምላለች።ነገር ግን ገዝሽ አብራው ካልሆነች በሽጉጥ ግንባሯን ሊያፈርሰው እንደሚቻል ትሰጋለች። ሜርሲ እንደምትለው የድሮ ቦይፍሬንዷ ሄኖክ “ለገና እንኳን አደረሰሽ የሚል መልእክት ልኮላት ገዝሽ ስልኳን ሲበረብር ይሄንኑ ሜሴጅ በማግኘቱ ነበር እንዲህ መቶ ንብ የነደፋት እስክትመስል የደበደባት።የፊት እብጠቶቿን በበረዶ እያሸሁላት ድንገት በሀሳብ ነጎድኩ። ሜርሲ እያወራችኝ እኔ ግን እንዴት እንደተዋወቁ፣ እንዴት እንደተጋቡ በማሰብ ተጠምጄ ነበር የሜርሲን በምስል የተደገፉ የህይወት ገፆች እየገለጥኩ ማሰብ ጀመርኩ...

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍1
የሰርጉ መርሀ ግብር እንደሚጠናቀቅ አወጀ፤
“.ከቡራትና ክቡራን -የፕሮግራማችን የመጨረሻ ሰአት ላይ ደርሰናል፤ አንድ ፕሮግራም ብቻ ነው የሚቀረን። there is a surprise guest አንድ ልዩ እንግዳ አለን.አንድ እጅግ የምትወዱት ልዩ እንግዳ አለን። ይህ የምንወደው፣ የምናደንቀውና የምናከብረው፣ እንደ አይናችን ብሌን የምንሳሳለት
እንቁ ወጣት አርቲስት በአጋጣሚ የሙሽራችን የገዝሽ አብሮ አደግና ቀዳሚ ሚዜ የልብ ወዳጅ ነው።አርቲስቱ የልብ ወዳጁን ጥሪ አክብሮ ከግማሽ ሰአት በፊት እዚህ ከመሀላችን ተገኝቷል። ይህ የአገራችን ቁጥር አንድ አርቲስት እዚህ መገኘትም ብቻ ሳይሆን ሙሽሮቹንና እንግዶቻቸውን ለማስደሰት ሁለት
የሰርግ ዘፈኖችን ሊያቀርብ ቃል ገብቷል። ሰርፕራይዝ ገስት ስለሆነ አሁን ስሙን አልነግራችሁም። ታውቁታላችሁ”

ከአፍታ በኋላ ልዩ እንግዳው ገና መድረኩን እንደረገጠ ሙሉ ታዳሚው ሆ ብሎ ተነሳ። አንድም ታዳሚ ከወንበሩ ያልተነሳ አልነበረም። ሁሉም ሰው ይህን ተወዳጅ አርቲስት ከበበው።

አስገራሚው ነገር የተፈጠረው ይሄኔ ነው። ሜርሲ የዘፋኙን ማንነት ስታይ ብድግ ብላ ወንበሯን ለቃ የስርግ ዘፈን ወደሚያቀርበው አርቲስት ቬሎዋን እየጎተተች በጥድፊያ ተመመች። ከምኔው ከአርቲስቱ
አጠገብ እንደተገኘች እግዜር ነው የሚውቅም። የሚገርመው አርቲስቱ ሁለቱንም የሰርግ ዘፈኖች ሲያቀርብ ከጎኑ አልተለየችውም ባሏን መፈጠሩንም ረስተዋለች።

በእውነቱ የሙሽራውን በጥልቅ የብቸኝነት፣ የሀዘንና የብስጭት ስሜት ከፉኛ የጨፈግግ ፊት ዞር ብሎ ያየ ማንም አልነበረም። አዳሜ በታዋቂው ዘፋኝ ዙርያ ይራኮታል። ከተቀመጠበት ወንበር ላይ
እንደሚስማር ተቸንክሮ የቀረው ሙሽራው ብቻ ነበር። ሙሽሪት ሜርሲ አርቲስቱ ሁለት የሰርግ ዘፈኖቹን ካቀረቡ በኋላም ወደ ቦታዋ አልተመለሰችም። አብራው የማስታወሻ ፎቶዎችን ለመነሳት
ከካሜራ ማኑ ፊት ተገተረች ሁሉም የሰርጉ ታዳሚ ከአርቲስቱ ጋ የማስታወሻ ፎቶ ለመነሳት ቋምጦ ይጠብቃል። ሙሽሪት ግን እርቲስቱን የሙጥኝ ብላ ቀረች። ሙሽራው ገዝሽ ከመንበሩ ላይ ለብቻው እንደተቀመጠ ተክዟል። በህይወቴ እንደዛ አይነት የእልህና የንዴት፣ የሀፍረት፣ የብስጭትና የበቀል
ስሜትን በአንድ ላይ ያቋረ ኮስታራና ጨፍጋጋ ፊት ተመልክቼ አላውቅም፡፡

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
1👍1
የምቀበል
ሸርሙጣ ስሆን እነሱ ትዳር መስርተው ወልደውና ከብደው የክብር ህይወትን ይመራሉ። በዚያ ቢያቆም ጥሩ ነበር። ዘመዶቼና ጓደኞቼ በሆቴሎች፣ በክለቦችና በሌሎች ስፍራዎች ከነጭ ሴቶች ጋ
ሲያግኙን የማያሳምን ሰበብ ፈጥሮ መዋሸቱ ታከተኝ። አዲሳባ እንደምናስበው ሰፊ አይደለችም፤ ጥቂት የመዝናኛ ስፍራዎች ስላሉ በሄድሽበት ሁሉ የምታውቂያቸውን ሰዎች ማግኘትሽ አይቀርም። አንድ እለት ከአባቴ ባልተናነሰ በድሃ አቅሙ ያሳደገኝ አጎቴ ከጨርጫሳ ጀርመናዊት አሮጊት ጋ ሂልተን የዉሃ
ና ፍል ዉስጥ አገኘኝ። አጎቴ ሀብታም ነጋዴ ሆኗል። እኔም ጀርመናዊቷም በዋና ልብስ ብቻ ዉሀ ዉስጥ እየተንቦራጨቅን ነበር። ያን እለት መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠኝ ወይም እዚያው ዉሀ ዉስጥ
ሰምጬ ብቀር ደስተኛ ነበርኩ። አየሽ ሮዚ! በሕይወታችን ደስታ የሚሰጡ የሚመስሉን ነገሮች ፍጹም ደስታ የሚያርቁን ናቸው፤ እኔ ሲኒማራስ በያይነቱና ሽሮ በልቼ ስውል የነበረኝ ደስታ ከኡስማን ያን ሁሉ ዶላር እያፈስኩ ከማገኘው ደስታ የበለጠ ነበረ። ፈጣሪ በማይወደው ስራ ዉስጥ እስካለሽ ድረስ
ህሊናሽ እንደመርፌ እየወጋ ሰላምሸን ይነሳሻል…”

ድንገት የኤርሚን ፊት ትካዜ ወረሰው፤ ለአፍታ በመካከላችን ዝምታ ሰፈነ። ዝምታውን መስበር ፈለግኩና አፌ ያመጣልኝን ጥያቄ ጠየቅኩት፤

"አጎትህ ሲያገኙህ ግን ምን አሉህ?"

ኤርሚ ባልጠበኩት ሁኔታ በቁጣ አፈጠጠብኝ፤

“ቆይ እኔ የምለው ሮዝ፤ ለምንድነው ጥያቄ የምታበዢብኝ?የሕይወቴን ሲሶ ከሴት ጋር ነው ያሳለፍኩት ያንቺን ያህል የምትጠይቅ ሴት አላየሁም።በፈጠረሽ ጥያቄ አታብዥብኝ ጥያቄ አልወድም በተጠየቁ ቁጥር ለፍረድ የቀረብኩ ይመስለኛል ህሊናዬ የሚጠይቀኝ አንሶ ደግሞ አንቺ..."

ክው ብዬ ቀረሁ። በሰላም እያወራኝ ድንገት ሲቆጣኝ ቀልቤን ገፈፈው፡፡ በሌላ እንዳይጠረጥረኝ ብዬ ዝምታን መረጥኩ፡ከአፍታ በኋላ የጨዋታ ርእሱን ቀየርከት። በራሱ ጊዜ ካላወራ ምንም ጥያቄ ላለማንሳት ወሰንኩ።ከብዙ ዚጠጥና ጨዋታዎች በኋላ ጥቂት የመቆስቆሻ ሀሳብ ሳቀርብለት ሳያስበው ምክንያቱን መናገር ጀመረ።

“በየሆቴሉ፣በየክለቡናበየመዝናኛስፍራው ከነጮቹ ጋ ሆኜ የማገኘው የቅርብ ሰው ሲበዛብኝ ከአዲሳባ ርቄ መሄድ እንዳለብኝ ተሰማኝ። ከቱሪስቶቹ ጋ ሆኜ የማገኛቸው ጓደኞቼና ዘመዶቼ ሁሉ ስራዬን የሚያውቁብኝ እየመሰለኝ በሀፍረት ልቀውስ ደረስኩ። ከፈረንጆቹ ጋ በመንገድ ላይ ስሄድ ለደቂቃዎች
የሚያፈጥብኝ ሁሉ ሸርሙጣነቴን ጠንቅቆ የሚያውቅ ያህል ተሰማኝ። በጣም ተጠራጣሪ ሆንኩ።
አዲሳባ መኖር የጀመሩት 2ቱ ታናናሽ እህቶቼ ስራዬን ሲያውቁ የሚሰማቸውን አስቤ ተረበሽኩ፣እንቅልፍ አጣሁ። ማንም የማያውቀኝ ሩቅ አገር መሄድ እንዳለብኝ ወሰንኩ። በዚህ መብሰልሰል መሀል ነበር ኑኑሻ ወደ አእምሮዬ የመጣቸው። ዱባይ አብረን እንድንኖር ብዙ ጊዜ ትወተውተኝ ነበር። ኑኑሻ በጣም እንደምትወደኝ አውቃለሁ፥ ሮዝ ሙች! በጣም ነው የምታፈቅረኝ። ከሷ ጋ የነበረኝን ግንኙነት
አለመቁረጤ ጠቀመኝ። ከዚያ ሁሉ ጊዜ በኋላ ደውዬ ሳገኛት ፊትዋን አላዞረችብኝም። የሌት ተቀን ሀሳቤ በተገኘው አጋጣሚ አዲሳባና ኢትዮጲያን መልቀቅ ነበር። ተሳካልኝ፤ ከዚያም በየሰከንዱ ህሊናዬን ክፉኛ ከሚቀጠቅጠኝና ቀና ብዬ እንዳልሄድ ካደረገኝ ቆሻሻ ህይወት ወጣሁ፤ አሁን የኑኑሻን ንግድ በበላይነት የማስተዳድር የቢዝነስ ሰው ሆኛለሁ…” ካለኝ በኋላ በረዥሙ ተነፈሰ። ዝም ተባባልን።

“..ይቅርታ ግን እሺ፤ሮዝ

“ለምኑ?”

ቅድም ሳላስበው ጮህኩብሽ መሰለኝ?”

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍21
ሸት

ጥገኝነት ያገኙ ነበር። አሁን ግን ያ ቀርቷል። ማኅበራቸው ነው የሚመሰክርላቸው። እና እሌኒ መኪናው የተሰጣት ከዚህ ማኅበር ነው። የመኪናዋ ቀለም ራሱ የቀስተደመና አይነት ናት። ለቡሽቲዎቹ ወንዶችን አማልላ በየቀኑ
እንድታመጣላቸው ይቺን መኪና አውሰዋታል። ለአገልግሎቷ ወፈር ያለ ክፍያ እንደሚፈጽሙላት

መረጃ አግኝተናል ነው ያለኝ ሀገዞም..."

እነኑ ደግሞ በየቀኑ የሚያገኟቸውን ወንዶች በአልኮል እስክረውና በመጠጥ ውስጥ የእንቅልፍ ኪኒን

መሲ እውነቷን ሳይሆን አይቀርም፡፡ የጠቀሰቸወም ክለብ ዉስጥ ሰዶሞች እንደሚበዙ አውቃለሁ።እነሱ ደሞ በየቀኑ የሚያገኟቸውን ወንዶች በአልኮል አስክረውና በመጠጥ ውስጥ የእንቅልፍ ኪኒን ጨምረው በማደንዘዝ ብዙ ወንድ ማጥመድ አይችሉም። ሁል ጊዜ በዚህ መንገድ የሚወስዷቸውን ሰለባዎች አያገኙም።እሌኒ ግን በሴትነቷ ተጠቅማና አማልላ በየቀኑ እነሱ ካሉበት ቤት ድረስ ለዚህ ተግባር በሰጧት መኪና ታቀርብላቸዋለች። መሲ እንደምትለው እሌኒ መኪና ይዛ ሲያዩ ወንዶች
በፍጹም አይጠረጥሯትም። ወንድ የጠማት ሀብታም ሴት ትመስላቸውና ሰተት ብለው ይገቡላታል። ይህንን በመረዳት ነው ቡሽቲዎቹ መኪና በሚስጢር ማሀበራቸው ስም ገዝተው በውሰት የሰጧት።

እሌኒን አምርሬ ጠላኋት። የሆነ ወቅት ላይ ከዚህች የሰይጣን ቁራጭ ጋር አብሬ መስራቴን ሳስብ ዘገነነችኝ። ሰው ሲባል ግን እንዴት አይነት ጨካኝ ፍጡር እንደሆነ….አሁን እሌኒ እዚህ ሁሉ ልቦለድ የሚመስል ወንጀል ውስጥ ትገባለች ብሎ ማን ያምናል?

መሲን ጠየኳት።ቆይ ግን ባልሽ ሀገዞም ይህን ሁሉ እያወቀ ለምንድን ነው እርምጃ የማይወስድባት?

“ሮዝ! እኔም ጠይቄው ነበር፤ ምን እንዳለኝ ታውቂያለሽ? መጀመርያ ሳቀብኝና…የዋህ ስለሆንሽ እኮ
ነው የምወድሽ ብሎ ከንፈሬን ከነከሰኝ በኋላ «ወንጀል ክትትል ዉስጥ አንድን ተጠርጣሪ አንድ ወንጀል ስለፈፀመ ብቻ ተንደርድሮ መያዝ ብዙ ዱካዎችን እንደማጥፋት ይቆጠራል እንደምታስቢውም ቀላል አደለም እዚህ ድርጅት ውስጥ ከተራ ሰው ጀምሮ ትላልቅ ባለስልጣናት አጅ አለበት በየቲቪው በከረባት ታንቆ የምናየው ባለስልጣን የማታ ማታ መዳርያቸው ነው አንድም ቡሽቲነትን ከሚያስፋፉት ሰዎች እነሱ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ እንጂማ እሌኒን ገና ድሮ ከሁለቱ ከፖሊሶች ጋር የምትፈጽመውን ወንጀል እንደደረስንበት በቁጥጥር ስር አውለናት ቢሆን ኖሮ
ከሰዶማዊያኑ ጋር ስለነበራት ግንኙነት ምንም ማወቅ አንችልም ነበር። አሁንም በሷ ላይ ለጥቂት ወራት ክትትሉ ይቀጥላል። ጊዜው ሲደርስ እሌኒም፣ ሁለቱ ፖሊሶችም፣ የምታገለግላቸው ሰዶማውያኑም ከነማኅበራቸው ተለቃቅመው እስር ቤት ይገባሉ፤ ባለቀስተደመናዋ ቶዮታ ቪትዝም ለመንግስት ገቢ ትደረጋለች።››

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍41
ወፈፌ ይመስል ነበር።በየተራ አፈጠጠብን፤

“እስቲ ንገሩኝ! እዚህ ሰፈር ውስጥ ምን አይነት ድግምት ነው የተደረገብኝ? ሺ ጊዜ ሰፈሩን በድጋሚ ላለመርገጥ ምዬ ብገዘትም አክለፍልፎ የሚያመጣኝ አዚም አለ። ምንድነው ያረጋቸሁብኝ? ምን
አይነት አፍዝ አደንግዝ ነው የነሰነሳችሁብኝ? ብሌን ምንም ሳትደብቂ ንገሪኝ የምትለማመኚው ቃል።
፣ ጠንቋይ ፣ ሼክ ወይም ቆሪጥ በኔ ላይ ምን እንድታደርጊ ነው ያዘዘሽ? ያው ባንቺ ቤት ስንት ዘመኔ ሌሎች የሰፈሩ ቡና ቤቶችና ፐቦች ጋ ቆይቼ አንቺ ቤት ነው ሁሌም የማሳርገው። ያንቺን ቤት ሳልሳለም ይህን ኩሻንኩሽ ሰፈር የተለየሁበት ጊዜ የለም። ይህን አንቺም አሳምረሽ ታውቂዋለሽ ስለዚህ የዚህ ሰፈር ሴቶች በኔ ላይ ምን እንዳደረጋችሁብን ሳትደብቂ ንገሪኝ ብሌን አንቺን ነው የማናግርሽ"

የሆነ ማይም ቲያትር የሚሰራ መሰለኝ። ፍቅሮቭስኪ አመልካች ጣቱን ብሌን ላይ ቀስሮ ረዘም ላለ ቅፅበት አፈጠጠባት።ብሌን አልፈራችውም ።እንዲህ እያማረረ ይህው ስንት አመቱ።ችላ ግን አላለችውም።ልታረጋጋው ሞከረች፣

“ምነው ፍቅሮቭስኪ….ምን ሆንክብኝ…ኧረ እኔ ካልካቸው ቦታዎች አንዱም ጋ ሄጄ አላውቅም፤ወላዲት አምላክን እኔ እንዲህ አይነት ልማድ የለኝም"

-ፍቅሮሽስኪ አሁንም እይኖቹን ከብሌን ላይ አልነቀለም፤

“ቀጣፊ ሸርሙጣ ነሽ፤ በመጀመሪያ አላመንኩትም እንጂ ሰናይ ሁሌም ቤትሸን ምሸት ላይ ልትከፍቺ ስትይ አዶ ከርቤ እንደምታጨሺና አውሊያሽን እንደምትለማመኚ ብዙ ጊዜ ነግሮኛል። እሱም በስንት ጸበል ነው ከዚህ ስፈር የተነቀለው።እምቢ አልኩት እንጂ ጻድቃኔ ማርያም አብሬው ጸበል እንድጠመቅ በተደጋጋሚ ወትውቶኝ ነበር።”

ፍቅሮቭስኪ እንደገና ባለጌው ወንበር ላይ ተቀምጦ ባንኮኒውን በቡጢው መድቃት ጀመረ፤ አይፎኑን በንዴት ወርውሮ ከአንዱ ግድግዳ ጋር አላተመው፤ ፊቱን በድጋሚ ወደኛ አዞረ። ደም ስሮቹ በቀይ ፊቱ ላይ ተገታትረው

በጉልህ ይታያሉ፤ይህን ጊዜ ሶስታችንም በድንጋጤ ደርቀን ቀረን።

"ወይዘሪት ብሌን! እያወቅሽ አትደብቂኝ፣ ይሄ ድግምታምና መተተኛ ሰፈር ምን አድርጎብኝ ነው ለዘመናት የሰፈሩ ቋሚ እስረኛ ያደረገኝ?! የቢዝነስ አጋሮቼ አርብና ቅዳሜን ሸራተን በጋዝላይት፣
በዱባይና በባንኮክ እየተዝናናን እንድናሳልፍ ለዘመናት በየሳምንቱ ሲወተውቱኝ አንድም ጊዜ እንኳን
ግብዣቸውን ሳልቀበል እዚህ ሰፈር ኩሽና በሚያካክሉ ቤቶች እንድልከሰከስ የሚያደርገኝ ድግምት ምንድን ነው? ብሌን ምንም ቢሆን የዘመናት ደምበኛሽ ነኝ፤ በፈጠረሽ ሚስጥሩን ንገሪኝ!”

ፍቅሮቭስኪ ከተቀመጠበት የባለጌ ወንበር ላይ ተነሳ፤ ሊረጋጋና ሊሰክን አልቻለም፤ ጥቂት የመቶ ብር
ኖቶችን ከቆጠረ በኋላ ባንኮኒው ላይ ወረወረ። ፊቱን ወደ ብሌን መለሰ፤
ብሌን ካንቺ ጋ እኮ ነው የማወራው ለምን እትመልሺልኝም? አልቀየምሽም እውነቱን ብቻ ንገሪኝ ይሄ ሰፈሩን ለመጨረሻ ጊዜ የምረግጥበት ሌሊት ነው። ከነገ ጀምሮ እንደ ሰናይ ለተወሰኑ ቀናት ጸበል
ለመግባት ቁርጥ ውሳኔ ወስኛለሁ። ስለዚህ አትፍሪ በግልጽ የምታውቂውን ንገሪኝ! ለምንድነው የዚህ ሰፈር ባርያና ምርኮኛ የሆንኩት? የትኛው ደብተራ ጋ ነው ያስደገማችሁብኝ? አርብ፣ ቅዳሜና
እሁድ ቤቴን፤ ሚስቴንና ልጆቼን እንድጠላና ከቤት ጥፋ ጥፋ የሚል ምን አይነት መስተባርር ነው ያረጋችሁብኝ? የትኛው ደብተራ ጋ ሄዳችሁስ ነው ለዘመናት ከዚህ ስፈር ጋ በፍቅር እንድወድቅ ያደረገ ማስተፋቅር ያሰራችሁብኝ? የቀራችሁ እኔን በድግምት ማሳበድ ብቻ ነው፡፡ ምኔ ሞኝ ነው!መስተአድርት አሰርታችሁ ሳታሳብዱኝ ነገ ጸበል እገባለሁ። መጥኔ ለናንተ! እኔስ በቃኝ…በቃኝ አልኩ።

ፍቅርቭስኪ ኮቱንና አይፎኑን ጥሎ ውጪ ወዳቆማት ቡናማ ፕራዶ መኪናው አመራ። ብሌን ኮቱንና ስልኩን ይዛ ወደ መኪናው ሄደች። ከአፍታ በኋላ ስጥታው ተመለሰች።

ብሴን በየተራ ተመልክታን ፈገግታውን ብልጭ አደረገች፤

“ፍቅሮቭስኪ በውሳኔው ከጸና ቺቺንያዊ የከብር ዜግነቱን በነገው እለት እንገፈዋለን።" በረዥሙ ሳቀች።

“በቃ ቤቱን ዘጋግተን ወደኔ ቤት እንሂድ። ጉዞ ወደ ብሌን ኮንዶሚኒየም ዳይ ዳይ….” በድጋሚ ሳቀች እኔ ግን ድንጋጤው አለቀቀኝም ነበር።

ሮዚ ደሞ፤ ፍቅሮቭስኪው ታውቂው የለ? ሁልጊዜም እንደዛተ ነው እኮ ሙዳችንን ሰለበው አይደል ይሄ ሰላቢ…ኑ ባካችሁ ቤት ሄደን የሆድ የሆዳችንን እንጫወት…"
ብሌን በራሷ ንግግር ፐቧ እስክትነቃነቅ በሳቅ አስካካች።ፍቅሮቭስኪ በተናገራት ነገር ዉስጥ ዉስጡን ተብከንከናለች ማለት ነው። የንዴት ሳቅ እንደሆነ ያስታውቅባት ነበር።

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍2
ር ምን መሰለሽ? እኚህ ኣዘውንት ሳቢ ላይ ፈታ ያሉ ናቸው ከላይ ከጠቀስኳቸው ትእዛዞቻቸው አንዱን ባሟላሁ ቁጥር 850 ብር ይለቁብኛል። ከፍያቸው ከዚህ ጨምሮም ቀንሶም
አያውቅም። እኚህ አዛውንት ለምንድነው ወሲብ የማይፈጽሙት? እያልኩ አስብ ነበር፡፡ ይህ ጥያቄ ለረጀም ጊዜ አዛውንቱን ባየሁ ቁጥር ሲያብሰለሰለኝ ቆይቷል አንድ ቀን የመጣ ይምጣ በሚል ጠየቅኳቸው።

በጥያቄዬ ምንም እልተገረሙም፡-

"ውይ የኔ ልጅ! ምን ነክቶሻል! እግዜሩስ ምን ይለኛል?! ከእግዜሩ መጣላት አልፈልግም። ስድስት
ለወግ ማእረግ የበቁ ልጆችን የሰጠችኝና ከቤት የማትወጣ ታማኝ ሚስት አለችኝ። አርባኛ አመት የትዳር ጥምረታችንን ልጆቻችንና ዘመድ አዝማድ በተገኙበት በድምቀት ድል ባለ ድግስ ዘከረናል።
በአክሊል ነው የተጋባነው። ቃል ኪዳኔን አፍርሼ ከሌላ ሴት ጋር ሩካቤ ስጋ ብፈጽም የእግዜሩን ቁጣና እርግማን እፈራለሁ። በንጹህዋ ሚስቴ ላይ ያን አይነት ውስልትና መሞከር ተይውና በፍጹም አላስበውም”

#የፓንት_ፖለቲካ


አንድ ቅዳሜ ከሰአት ከሲሳይ ራስተረ ጋር "ፒኮክ" መኪና ውስጥ ቁጭ ብለን አፕሬቲቭ እየጠጣን አንድ ካልሲ አዟሪ መጣ።ሲስ ሎተሪ ሻጭ፣ማስቲካ አዟሪ ኮንደም ቸርቻሪ ጋር ማውራት ሲወድ።"ምን ይሰራልሃል"ለምን ታደርቃቸዋለሁ፣ሰርተው ይብሉበት እንጂ" ስለው“ሮዚና ምን መሰለሽ… የድሮ
ነገስታት “አዝማሪ ምን አለ?” ይሉ ነበር። በኛ ዘመን የሕዝብ ብሶትን ለመለካት ከነዚህ ቸርቻሪዎች የተሻለ ቴርሞ ሜትር አይኖርም።ለዚህ ነው እህ ብዬ የምሰማቸው” ብሎ ያሾፍብኛል።

ይኸው ፒኮክ ፓርኪንግ መኪናችን ውስጥ ሆነን ሲስ ከአንድ ካልሲ አዘዋሪ ቆምጬ ጋር ይዳረቃል።

“ና እስኪ ጠጋ በል!”

“አቤት ጋሼ ምን ላሳይዎት፤ ካልሲ ላሳይዎት? ሸጋ ሸጋ ካልሲዎች አሉኝ.ፓንቶችም አሉኝ

“የየት አገር ልጅ ነህ”

“ማ! እኔ

ታዲያ ሌላ ሰው አለ እንዴ?

“ጎዣም"

“ባህር ዳር ነው?

እይ ከባህር ዳር እንኳ ትንሽ ወጣ ትላለች፣ ፍኖተ ሰላምን ያውቋታል ጋሼ”

“አላውቃትም፤ ስስም ነው የማውቃት፤ አንተ ባህርዳርን ታውቃታለህ?”

አዎ እንዴት አላውቃት ጌታው! አንድ ሁለት ጊዜ ሄጃለሁ፤ ሸጋ አገር ናት”

እኔ ምልህ! የዛ አገር ሴቶች ፓንት እንደማያደርጉ ታውቃለህ?”

ኧረ ጌታው እኔ በምን አውቄ፣ ገልጠው አያሳዩኝ ነገር." ልጁ ራሱ በተናገረው ነገር ሳቀ።

“ቆይ እሺ እዛ አገር ሴቶች ፓንት ገዝተውህ ያውቃሉ?”

ኧረ ጌታው እኔ እዛ አልነገድኩም፣ ኧረግ የሚያውቁኝ ዘመዶች አሉኝ እያልከዎ፤ ቤተሰቤን ለምን አዋርዳለሁ ጌታው?”

“ሥራ አይደለም እንዴ? ምን ችግር አለው?”

“ኧረግ ችግርማ ቢኖረው እይ እዚያ ማልነግድ፤ ምን ብዬ ነው በአገሬ ሙታንታ ምቸረችር? ምንስ ቢቸግር…”

“ለማንኛውም ጎዣም ብዙ ሴቶች ፓንት ማድረግ ትተዋል፤ ይሄን ታውቃለህ?

ኧረ እኔ አላውቅም? ግና ምነው አሉ ጌታው?”

“በል እንግዲያውስ እኔ ልንገርህ፤ ቅንጅት የተሸነፈ ጊዜ ነው የጎዣም ወጣት ወንድነቱ የተሸነፈ፣ ከ97 በኋላ ለፖለቲካም ለሴትም ያለው ስሜቱ አብሮ ነው የሞተ። ከዚያን ቀን ጀምሮ በከተማው አንሶላ የተጋፈፈ የለም ነው የሚባል።”

“እሱስ እውነት ነው ጌታው፤”
“ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጫት በባህርዳር ከድሬዳዋ ባልተናነሰ ይቃማል። ይሄን ታውቃለህ?

“ልክ ነው ጌታው"

"ታዲያ ሴቶቹን ማን ዞር ብሎ ይያቸው፤”

"አህ! ኧረ እኔን አያናግሩኝ ጌታው! እኔ የነሱን ጉዳይ የት አውቄ!"

እወቃ ካላወቅክ፤ እየነገርኩህ አይደል? እንድታውቅ እኮ ነው የምነግርህ። አሁን አንዲት የጎዣም ሴት አግኝተህ ብትጠይቃት ትነግርሀለች። ፓንት አታደርግም። ከአገሩ ጉብል ይልቅ የብስክሌት ኮርቻ የተሻለ ያስደስታታል። ከ97 በኋላ ብስክሌት ላይ መፈናጠጥ የተሻለ ሆኗል ይሉሀል። ሳትደብቅ
ትነግርሃለች።”

“ኧረ ጉደኛ ኖት ጋሼ! ዉስጠ-ወይራ ነው የሚናገሩ ጋሼ! ኧረግኝ! ተናግረው አያናግሩኝ ጌታው!”

“አሁን ግን ገባህ? ለምን ፓንት እንደማያደርጉ?”

አንገቱን በአዎንታ ነቀነቀና ዙርያ ገባውን መቃኘት ጀመረ።

አየህ ይሄ መንግስት ስንቱን ጉድ እንዳረገ! ስንቱን ያለ ፓንት እንዳስቀረ… "

ኧረ ጌታው እኔን ፖለቲካ አያናግሩኝ፣ ፓንት የሚገዙኝ ከሆነ ይግዙኝ."
ሲሳይ ሳቁ መጥቶበት እንደምንም ተቆጣጠረውና…።

እሺ ለሷ የሚሆን ሸጋ ፓንት አለህ? ሚስቴ ናት! እንደምታየው ቂጧ ትልቅ ነው፤ ከፈለክ እዚሁ ትለካዋለች።” አለው ወደኔ እያመላከተው።

“ልጁ አፍሮ አቀረቀረና ኧረ ጌታው የሴት ፓንት አልይዝም፣ እነሱ ባደባባይ መች ይገዙንና!”

“ግን እንዲሁ ስታያት አሁን ፓንት ያረገች ይመስለሃል? ገምት እስቲ”
ልጁ ሙሉ በሙሉ አፍሮ መሽኮርመም ጀመረ። ቀና ብሎ እኔን ማየት እንኳ አልቻለም።

ሁላችንም ሳቅን።

እሺ የወንድ ፓንት አለህ?ለኔ የሚኾን?”

“ሞልቶ ጌታው፣ ይኸው ይምረጡ!” ከፌስታሉ እያወጣ የፓንት መዓት ዘረገፈለት።

ለምን እንደሆነ አላውቅም የወንድ ፓንት ዉስጤ የሆነ የሚዝለገለግ ነገር ያለው ስለሚመስለኝ ተዘርግፎ ሳየው ይቀፈኛል።

አንተ እውነት ከጎጃም ነኝ የምትል ከኾነ ይሄን ጥያቄ መልስና ነው የምገዛህ”

እሺ ይጠይቁኝ ጌታው፤ ፖለቲካ ካልሆነ ምን ገዶኝ!”

“ኖ! ኖ! ፖለቲካ አይደለም። የአማርኛ ጥያቄ ነው የምጠይቅህ! ፓንት በአማርኛ ምንድነው የሚባል?”
እኛ እንግዲህ ሙታንታ ነው የምንል። አዋቂ ስንሆን ነው እይ ልጅ ሆነንማ ማን አስታጥቆን ጌታው”

“ሙታንታ አይደለም፤ ተሳስተኻል”
እና ምንድነው ጋሼ? ካወቁት እርስዎ ይንገሩና"

«ማኅደረ ቆለጥ» ነው የሚባል”
ልጁ የያዘውን ፌስታል ጥሎ በሳቅ ወደቀ፤ እኔም ሳቄን መቆጣጠር አልቻልኩም። ሲስም እኛን አጅቦ
ሳቀ።

ግማሽ ደርዘን ካልሲ ገዝቶ፣ በተጨማሪም 10 ብር ሸልሞ ሸኘው። በደስታ እየተፍለቀለቀ ጉዞ ሲጀምር
ሲስ እንደገና ጠርቶት ወደሱ ሲዞር በሩቁ የ "V" ምልከት አሳየው። ልጁም ጣቱን ሸሸግ አድርጎ ምላሽ ሰጠ።

ልጁ ሥራ ከጀመረ እንደዚህ ተደስቶ የሚያውቅ አይመስለኝም።


💫ይቀጥላል💫

#ሮዛ_2 ነገ ይጠናቀቃል ሌላ አዲስ ረጅም ድርሰት እንድንጀምር ገንቢም ይሁን የትችት አስተያየታችሁን ስጡን ማስተካከል ያለብንን እናስተካክላለን መልካም ጎናችንንም እናዳብራለን ከዛሬ ጀምሮ አስተያየት እየሰጣቹ መስጠጠት ካልቻላችሁ 👍 እየተጫናቹ።

Like 👍 እና #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍52