አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_ሰላሳ_አንድ ( #የመጨረሻ_ክፍል )
:
ድርሰት:-በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
:
ከአንደኛው መጽሀፍ መሀል ያየቻቸው ሁለት ፎቶዎች ግን ተስፈንጥራ አልጋዋን ለቃ ወለሉ ላይ እንድትቆም አደረጋት…፡፡.ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ ነው..የምታየውን ማመን አልቻለችም..የኮማንዳሩና የወላጅ እናቷ ፎቶ ነው…አንዱ ፎቶ ሁለቱም በዋና ልብስ ሆነው ሙሉ በሙሉ አቅፎት መዋኛ ገንዳ ውስጥ ሆነው የተነሱት ነው…ሌላው ደግሞ ከንፈር ለከንፈር እየተሳሳሙ…… ይሄን ያህል ሄደዋል ብላ አታስብም ነበር ..ስልኮን አነሳችና ደወለች..እሮዝ ጋር ነው..ተነሳ..?
‹‹አሁኑኑ እፈልግሻለው››
‹‹ምነው ልጄ ምን ሆንሺብኝ..?››
‹‹መቀባጠሩን ተይና በአስቸኮይ ኩማደሩ ቤት ነይ››ስልኩን ጠረቀመችው
ሮዝ የለበሰችውን የለሊት ቢጃማ እንኳን ለመቀየር ጊዜ ማባከን አልፈለገችም…ብን ብላ ነው ግቢውን ለቃ ወደኩማንደሩ ቤት የበረረችው ..ልጄን… ልጄን ምን አደረክብኝ....?የሳሎኑን በር በርግዳ ከፈተችና ወደውስጥ ገባች…
‹‹ምን አደረገብኝ ..?ምነ ሆንሺብኝ ..?ተንደርድራ ልትጠመጠምባት ስትል ገፍትራ ከላዬ አራቀቻት….››
‹‹ይሄ የመቼ ፎቶ ነው....?››ሄለን ነች ጠያቂዋ
‹‹የቱ..? እኔጃ..››ግራ ተጋብታ መለሰች
በእጇ የያዘችውን ፎቶ ወረወረችላት .ደረቷ ላይ አርፎ ወደመሬት ወደቀ… ጎንበስ ብላ አነሳችውና ተመለከተችው..
‹‹እሺ መንም አልጀመርንም ብለሽኝ አልነበር..?››ሄለን ነች በሽሙጥ የጠየቀቻት
‹‹ያው ድሮ እኮ ነው…ግን ከተለያየን ብዙ አመት አልፎናል..?››
‹‹በቀደምለታ የመጣሽው እንታረቅ ልትይው ነበር....?››
‹‹አረበፍጽም ..ስንለያይ ተጣልተን ስለነበረ ቂም ይዞብኛል..አንቺን በማጥቃት እንዳይቀለኝ ስለፈራው ከአንቺ እንዲርቅ ልለምነው ነው…››
‹‹ኦኬ አሁን በጣም ገባኝ….ለመሆኑ ኩማደሩን እንደማፈቅረው ታቂያለሽ..?››
‹‹አታደርጊውም ልጄ..እኔ በህይወት እያለው አታደርጊውም››
‹‹አትጠራጠሪ አደርገዋለው..እንደውም ማግባት ሁሉ የምፈልገው እሱን ነው››
‹‹አረ ተይ ልጄ…እራስሽን ወጥመድ ውስጥ ለምን ትከቺያለሽ....?እሱ እኮ ውስጡ በቀል እንጂ ፍቅር የለበትም…..››
እሱ እኔን አይመለከተኝም…እንደውም እኔም አንቺን ለመበቀል ስለምፈልግ ጥሩ አጋጣሚ ነው…ለመሆኑ ምን ያል ብትበድይው ነው .. ..?ለነገሩ አንቺ አይደለሽ ምንም ብታደርጊው አይደንቀኝም….ለማንኛመው ከዛሬ ጀምሮ በመሀከላችን እንዳትገቢ ልነግርሽ ነው..አሁን የድሮ ፎቶሽን ይዘሽ ወጭልኝ…;››
‹‹በፈጠረሽ ልጄ›› እግሯ ላይ ተደፋች..
‹‹ምንም ብታርጊ ሀሳቤን አታስቀይሪኝም…ምን አልባት በአንድ ነገር..››
‹‹ምንድነው ልጄ …የፈለግሽውን ጠይቂኝ..ከዚህ ሰይጣን ራቂለኝ እንጂ ያልሺኝን ሁሉ አደርጋለው››
‹‹ያው የእኔን ጥያቄ ታውቂያለሽ… ተመሳሳይና የማይቀየር ነው…የአባቴን ማንነት ከነገርሺኝ እተወዋለው…››
‹‹አባቴን....?››ከተደፋችበት ተነሳችና መቀመጫ ይዛ ተቀመጠች
‹‹አዎ ንገሪኝ..ከእሱ እንድርቅ ከፈለግሽ ንገሪኝ››
‹‹እሺ ቁጭ በይ….ነግርሻለው››
ሁለቱም ፊት ለፊት ተፋጠው ተቀመጡ
‹‹እንግዲያው ንገሪኝ ካልሽ ምርጫ የለኝም ነግርሻለው….ግን ለምትሰሚው ነገር እራስሽን አዘጋጂ››
‹‹ግድ የለሽም መግቢያውን ተይና ወደዋናው ታሪክ በቀጥታ ግቢልኝ››
‹‹ይሄውልሽ ልጄ ግማሽ ዕድሜዬን ይሄንን ታሪክ ለሌላ ሰው ይቅርና ለእኔው ለእራሴው ለመናገር ስሸሸው የኖርኩትን ነገር ነው፡፡ይሄው ዛሬ ሳልወድ በግድ ለመናገር ተገድጄያለው፡፡እስከዛሬ ነገሩን ሚስጥር አድርጌው የኖርኩት ለእናቴ ስል ነበር..አሁን ደግሞ ለመናገር የተገደድኩት ለአንቺ ለልጄ ስል ነው..ከእናቴ ስሜትና ደህንነት ይልቅ የልጄን ስሜት እና ደህንነት አስቀድሜ ነው..መቼስ አናቴ ልጅ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ስለምታውቅ ይቅር ትለኛለች ብዬ አስባለው፡፡
ማንኛውም የሰው ልጅ በትዝታ ፈረስ ፊቱን ወደ ኃላው አዙሮ ትናንትናውን ሲያይ መዝለል የሚፈልገው ወይም አለማሰብ የሚመኘው ወይም ምነው ባልኖርኩት ኖሮ ብሎ የሚጠየፈው በጊዜዎች ክፍተት መሀከል የተከወነ ጨለማ ታሪክ ይኖረዋል፡፡የእኔን የተለየ የሚያደርገው ግን ያለፈ ህይወቴ ውስጥ የተከሰተው ጠባሳ አይደለም መሰረዝ እንዲደበዝዝ ማድረግ እንኳን የማይቻል ስለሆነ ዕድለኛ አይደለውም፡፡
ልጄ አንቺ ለእኔ ማለት የበደሌ ምልክት፤ የክስረቴ ትርፍ ነሽ፡፡ሰው ህይወቱን የሚያሳጣው …ማንነትን የሚያወድመው ነገር ከስሮ በዛው ልክ ህይወቱን የሚያለመልምለት እና ለመኖሩ ምክንያት የሆነ ነገር ያተርፋል…እኔ ማለት እንዲያ ነኝ..የነገ ተስፋዬን፤ለመኖር የሚረዳኝን ሞራሌን፤ማንነቴን አጥቼ በምትኩ ግን አንቺን አገኘው፡፡
‹‹አረ የምትይው ነገር ምንም እየገባኝ አይደለም…››መለሰችላት ሄለን
‹‹የእኔ ህይወት ለእኔም ለእራሴ ብዙ ጊዜ አይገባኝም፡፡ግን ቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ልግባ፡፡አንቺን የወለድኩሽ ተደፍሬ ነው፡፡መቼ? ገና 15 ዓመት ሳይሞላኝ፡፡ማን የደፈረኝ ይመስልሻል..?የምትወጂው አጓቴ ነው፡፡ላስተምርሽ ብሎ ከእናቴ በአደራ ተቀብሎ አዲሳባ ወስዶ ደፈረኝ ..አስረገዘኝ …››
‹አጎቴ!!!!.. አጎቴ ማለት የማዬ ወንድም … አንቺን››
‹‹አዎ አጎቴ እኔን …ያ ማለት ደግሞ አንቺ የእሱ ልጅ ነሽ… አባትሽ ነው፡፡
‹‹እኔ አላምንም…››ሄለን ምትሆነው ምትናገረው ነገር ጠፋት
‹‹ልጄ ነፍስ ካወቅሽበት ጊዜ አንስቶ አባቴ ማን ነው ?ብለሽ ስትጠይቂኝ..የተለያየ ሰበብ እየፈጠርኩ ልነግርሽ ያልቻልኩት ነገሩ ለሰሚውም ግራ ሰለሆነብኝ ነው፡፡ ልጄ እስቲ አስቢው በገዛ አጐቴ ተደፍሬ አንቺን እንደወለድኩሽ ስትሰሚ በአንቺ ሰነ-ልቦና ላይ የሚያደርሰውን መረበሽና ተፅዕኖ በምን ማረጋገጥ እችላለው? እንደእኔ ስብርብር ብትይብኝስ.?.ከሁሉም በላይ ደግሞ ይሄ ጉዳይ እናቴ ጆሮ ይሄ ዜና ቢደርስስ ?የገዛ መንትያ ወንድሟ ከመሀጸኖ ፈልቅቃ አምጣ የወለደቻትን እና አደራ አሳድግልኝ ብላ ያስረከበቻትን ጨቅላ ልጆን በድልዱም ቢላዎ ገዝግዞ እንዳረዳት እና ህይወቷን እንዳበከተባት ብትረዳ በድንጋጤ ህይወቷ ባያልፍ እንኳን ጨርቋን ጥላ ማበዶ ይቀራል ብለሽ ታስቢያለሽ…?.ለዚህ ነው ከአንቺ ጋር ስጋጭ እና ስጣላ የኖርኩት፡፡ ለዚህ ነው እራሴን እንደ ጥፋጠኛ አስቆጥሬ ስባልግ እና ስንዘላዘል በገዛ ስህተቴ እደወለድኩሽ እዲታሰብ አድርጌ ግማሽ ዕድሜዬን እንደጋጠወጥ እና እንደ አለሌ ሸርሙጣ እየታሰብኩ በመኖር እራሴን ያሰቃየውት...እርግጥ አልዋሽም ሸርሙጣ የሚለው ስም አይገባኝም አልልሽም..በደንብ ይገባኛል..፡፡ግን በሽታ ሆኖብኝ ነው፡፡ከመደፈሬ ጋር የተፀናወተኝ እኔ እራሴ የምጠየፈው እና የምፀፀትበት ክፉ በሽታዬ ነው፡፡
ልጄ እንግዲህ እውነቱ ይሄ ነው፡፡አባትሽ የምትወጂው አጐትሽ ነው..ከአሁን ቡኃላስ እሱን መውደድሽን ትቀጥያለሽ…?እንግዲህ እሱ የአንቺ ጉዳይ ነው፡፡እኔን ግን ካጠፋውት በላይ ስቀጣ የኖርኩ ሚስኪን እናት ነኝና እባክሽ ይቅር በይኝ እና ቀሪ ህይወቴን ትንሽም ቢሆን ተስፋ እንዲኖራት እርጂኝ፡፡ከእዚህ ሰውዬ ራቂ..እሱን በጣም በድዬዋለው….ሊያገባኝ ሲዘጋጅ ነው ጥዬው ወደአዲስ አበባ የገባውት ..ስለዚህ ለአመታት ሊበቀልኝ ሲጥር እደነበረ አውቃለው..እና ልጄ ….
…ሄለን ከተቀመጠችበት ተነስታ ተንደርድራ ነው እግሯ ላይ የተደፋችባት….‹‹እማዬ የምትችይ ከሆነ ይቅር በይኝ..ባክሽ ይቅር በይኝ››እየነፈረቀች ተማፀነቻት
ሮዝ ከገባችበት መደንዘዝ ውስጥ እንደምንም ነቃችና እሷም ተከትላት ቁጢጥ በማለት ልጆን ከተደፋችበት አንስታት አቀፈቻት… አገላብጣ ሳመቻት ‹‹ልጄ ….ልጄ
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#በክፍለማርያም

...ያንቺ ነዉ ሲል አፋጠጣት
ቤዛዊት አንዴ ፍፁምን አንዴ አባቷን አፈራርቃ እያየች
የተረገመ ፍቃዱን በዉስጧ እየረገመች መሬት ላይ የወደቀዉን
ጡት ማስያዣ አንስታ እና ንዴቷ እየተቀሰቀሰ አይኗን
እያጉረጠረጠች
"ያንተ ነዉ ልስጥህ ...አንተ ሴታሴት ወረኛ" ጥፍሮቿን አሹላ ወደ ፍቃዱ ተጠጋችዉ
ፍቃዱ አዋረድኳቸዉ ብሎ መዋረዱ እየታየዉ አመጣጧ እያስፈራዉ ወደ አባቷ ቀስ እያለ መጠጋት ጀመረ
"አረ ተረጋጊ ሴትዮ"
አፉ ላይ የመጣለትን ቃል እያወራ
ፍፁም ለመገላገልም አልተነሳም አልጋዉ ጠርዝ ላይ ተቀምጦ
የጥፋተኝነት እና ደግ አረኩ በሚል ሁለት የተቃረኑ ሀሳቦች
ተዉጦ ከሀሳቡ ያነቃዉ ብርጭቆ ከግድግዳ ጋር ሲጋጭ
የሚያሰማዉ ድምፅ ነበር
"ኳኳ ከሽሽሽሽሽ"
ፍቃዱ በሩን በርግዶ እየተንደፋደፈ ወጣ አባቷ በድንጋጤ ተዉጠዉ አንገታቸዉን አቀርቅረዉ እና ፍጥርጣሪዉን ፈርተዉ።

አይናቸዉን ጨፍነዉ ቆይተዉ
ልጃቸዉን በልመና አስተያየት እያዩዋት
"ተረጋጊ ልጄ በቃ"
እያሉ መለመን ጀመሩ መታመሟ እየመሰላቸዉ እየፈሩ
በንዴት የጦፈችዉ ቤዛዊት የወረወረችዉ ብርጭቆ
ፍቃዱን ስላላገኘዉ እና እልኋ ስላሎወጣላት ግላ
"ሁለተኛ ይሄን የተረገመ ሰዉ ማየት አልፈልግም"
እጆቿ እየተንቀጠቀጡ እና የታችኛዉን
ከንፈሯን ወደ አፍዋ ዉስጥ ስባ በጥርሶቿ ነክሳ።
በትክክለኛዉ ስዓት አንዳንዴ ጥፋትን ለመሸፈን ሌላ ጥፋት
ማጥፋት የመጀመርያዉ ጥፋትን ያደበዝዝልናል
ሰዓቱን ካልጠበቀ ደሞ በሁለት ስህተት ቅጣት ያስጠይቀናል
መልካም ነገርም እንደዚህ ነዉ በትክክለኛዉ ስዓት
ጥሩ ነገር ላይ ሌላ ጥሩ ነገር ማስራት እና ድጋሜ ጥሩ ማሰብ
የመጀመርያ ደስታችንን አስረስቶ ወደ እጥፍ ድርብ ወደ ሆነ ደስታ ዉስጥ ይከተናል።

አባቷ ልጃቸዉ ቤዛዊትን እየለመኗት ይዘዋት እየወጡ ነዉ
ዞራ ፍፁምን ተመለከተችዉ ምን ማረግ ይችላል ከአባቷ ነጥቆ ማስቀረት አይችል እየከፋዉ እና እያዘነ ለመሰናበት
እጆቹን አየር ላይ አነሳ እስዋም በአይኖቿ እንባ እየቀረሩ እያየችዉ
አባቷ አቅፈዉ እንደያዟት ወደ ዉጪ ወጣች የቤዛዊት አባት እግሬ
አዉጭን ብሎ የሮጠዉን ፍቃዱን በአይናቸዉ እየፈለጉት ነበር
ቤዛዊት የአባቷ መኪና ዉስጥ ገብታ ስትቀመጥ ወረቀት እና
እስኪርቢቶ ስላገኘች ፊቷ ፈገግ እያለ የሆነ ነገር ሞነጫጭራ ፅፋ
ኪሷ ዉስጥ አባቷ እንዳያዩዋት ከከተተች በኋላ
"የረሳሁት እቃ አለ መጣሁ.."
አባቷን ብላቸዉ ከመኪናዉ ወርዳ ወደ ፍፁም ቤት መሮጥ ጀመረች።

ፍፁም ቤዛዊት እንደወጣች ብቸኝነት ቀንድ አዉጥቶ መልክ ኖሮት
ሰፈረበት ከፋዉ
ወራቶች እያለፉ ስለሆነ በዚህ ወቅት የትም ትምህርት ቤት
ተቀጥሮ ማስተማር እንደማይችል ሲያስበዉ ከአልጋ ወደ አልጋ
ቦታ እየቀያየረ እየመሰለዉ አዘነ
ቤዛዊትም የእሱ ትሁን አትሁን ግራ በገባዉ ሁኔታ ስትታመም
ሲሻላት አብሯት ከጎኗ እንዳይሆን መሰናክል ሲበዛበት
ይባስ ብለዉ ቤተሰቦቿ ጣልቃ እየገቡ እረፍት እና ደስታ ስለነሱት
ተስፋ ወደ መቁረጥ እየሄደ እየተጨነቀ ሲያስብ በሩ ተበርግዶ
ተከፍቶ ቤዛዊት እየፈጠነች ገብታ ሀይሏን በሙሉ ትከሻዉ ላይ
ጥላበት ካቀፈችዉ በኋላ እና ከንፈሩን በፍጥነት ለኮፍ አርጋ
ስማዉ እንደለመደችዉ ከኪሷ የተጣጠፈ ወረቀት አዉጥታ
ሰጥታዉ በገባችበት እየፈጠነች ወጣች።
ከወጣች በኋላ ወረቀቱን ገልጦ አነበበዉ የቦታ ስም ተፅፎበታል
አቅጣጫዉን እና ነገ ሶስት ሰአት እንገናኝ ይላል
አንብቦት ሲጨርስ ደስ እያለዉ በጀርባዉ ጋደም አለ።

ቤዛዊት ቤቷ ስትደርስ መሳቅ መጫወት አበዛች ቤተሰቦቿ
ደስ እያላቸዉ መሽቷ ለእንቅልፍ ወደየአልጋቸዉ ተለያዩ
እስዋ ግን ስለነገዉ እያብሰለሰለች የባንክ ደብተሯን ኪሶ ዉስጥ
ከትታዉ በለበሰችዉ ሱሪ አልጋዋ ላይ ወጣች።

ነፋሻማ አየር ከአዲስ አበባ ወደ ክፍለ ሀገር መዉጫ መስመር
በአካባቢዉ የበቀሉት ዛፎች በንፋስ ይወዛወዛሉ ዛፎቹ ላይ ያሉት
የወፍ ዝርያወች ቢንጫጩም ዜማ አላቸዉ
እማማ ስንቅነሽ ቤዛዊትን በራቸዉ ላይ ቆማ ሲያገኟት
የሞተች ልጃቸዉ መቃብር ፈንቅላ እንደወጣች ተደስተዉ እያዩዋት
"ልጄ ልጄ የምትመጪ አልመሰለኝም
የኔ የዋህ የኔ ምስኪን"
እያሉ አቀፏት

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ (የመጨረሻ ክፍል)


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

#ድህረ_ታሪክ

አራት አመት አለፈኝ፡፡ የህክምና ክትትል አደርጋለሁ፡፡ እድሜ ለነ ሃብትሽ፣ አደራ የሰጠኋቸውን የዶሮ እርባታ በቅንነትና በታማኝነት ሰርተው ከነ ፍሬው ጠበቁኝ፡፡ መልሼ ለመቋቋም በቃሁኝ፡፡ ለዶክተር
ለህክምናዬ ያወጣውን ግማሹን ቢሸፍን እንኳ ብዬ የተወሰነ ገንዘብ ላኩለት፡፡ አሁን ውስጤ በጣም የተረጋጋ ስሜት ይሰማኛል። የግል ስራዬን አስፋፍቼ ንሮዬን አዲስ አበባ አድርጌያለሁ፡፡ ነገሮች እንደበፊቱ ቶሎ አይረብሹኝም እንደውም፣ አሁን የሰዎችን ህመም አዳማጭና
መካሪ ሆኛለሁ፡፡ አንዳንዴማ፣ እንደ ዶክተርም ሊቃጣኝ ይሞክራል፡፡ሰዎች
በማይረባው ነገር ተረብሸው፣
ስራቸውን መስራት እስኪያቅታቸው፣ የማትረባዋን ነገር አግዝፈው ሲያኝኩ፣ ሲያብሰለስሉ ሳይ፣ ሰዎች ሁሉ ተደራጅተው ሊያጠቁኝ ነው ብለው እያሰቡ ሲጨነቁ ሳይ፣ ወደራሳቸው ማየት ሲያቅታቸው፣ ወላፈኑ እየለበለባቸዉ
ሲመስለኝ፣ ከነበልባሉ፣ ከእረመጡ ውስጥ ገብተው ሳይቃጠሉ፣ መፍትሄ
እንዲያገኙ ሃኪም እንዲያማክሩ እመክራለሁ፡፡

አሁን ዐይኔ በርቶልኛል፡፡ በአጠገቤና በአካባቢዬ በጣም ብዙ ሰዎች ላይ ምልክቱን አያለሁ፡፡ በተቻለኝ መጠን ልረዳቸው አዳምጣቸዋለሁ፡፡ አሁን ግን፣ ይሄ ብቻ በቂ እንዳልሆነ እየተሰማኝ ነው።
ቁጭ ብዬ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እያሰላስልኩ ነው፡፡ ከጎረቤት የተከፈተው የዳንኤል አምደሚካኤል መዝሙር ይሰማኛል፡፡ አብሬ ማንጎራጎር ጀመርኩ፡፡

“ዐይኔ በርቶልኛል፣ ሁሉን አይቻለሁ፡፡

ከዚህ የበለጠ ምን እፈልጋለሁ..::

እናገራለሁኝ...፣ አልታክትም ሁሌ..
.
ስለዚህ ሳወራ..አ..ሃ..ሃ፣ ከቶ አልደክምም እኔ።”

ከዶ/ር ሄኖክ ጋር እየተደዋወልን እንጠያየቃለን፡፡ በእድሜም ስለምንቀራረብ ነው መሰለኝ፣ ግንኙነታችን ጠብቋል፡፡ ከሳምንት በፊት፣
ደውሎልኝ ወደ አዲስ አበባ እንደተዘዋወረና ሊመጣ እንደሆነ ሲነግረኝ በጣም ደስ አለኝ፡፡ ውለታው የሚመለስ ባይሆንም፣ ለሱ ያለኝን ክብርና ፍቅር የምገልጥበት አጋጣሚ እንዳገኘሁ ተሰማኝ፡፡ ሲመጣ እኔ ጋር
እንዲያርፍ ተቀበልኩት፡፡ ተከራይቼ ምኖርበት፣ ሳር ቤት መቻሬ ኮንዶሚኒየም ወሰድኩት::


“ዶክ ተዋወቃት ባለቤቴ ናት፡፡”

“እንኳን ደህና መጣህ፡፡ ግባ፡፡ ማሂ እባላለሁ፡፡” አለችው ባለቤቴ
እየጨበጠችው፡፡

“እንኳን ደህና ቆየሽኝ፡፡ ሄኖክ፡፡ እንዴት ነሽ?"

“ዶክ ይህንንም ጎረምሳ ተዋወቀው፡፡ ልጄ ነው፡፡”

‹‹እንዴ! ከመቼው ይሄን አደረስክ?” ልጄን እየሳመው በመገረም ጠየቀኝ፡፡

ሁሌም ከአምናችን ይዘን ምንሻገረው ጥሩም መጥፎም ነገር ይኖራል፡፡ አንድ ጥሩ ነገር ቤቢ ነው፡፡ ይህ ትልቅ የፊቴ ጠባሳ ደግሞ ሌላው፡፡” ማሂ በፈገግታ ታስተናግደናለች፡፡

ዶክተርን ከማሂ ጋር ሆነን በምንችለው አቅም በደንብ አስተናገድነው፡፡ በህይወቴ ባሳየሁት ለውጥ በጣም ደስተኛ እንደሆነ
ደጋግሞ ነገረኝ፡፡ ለሳምንት የራሱን ቤት እስኪያመቻች ከኛ ጋር ቆየ፡፡ደስ የሚል ግዜን አሳለፍን፡፡ ቤት አፈላለኩለት፣ እቃዎችን አጋዛሁት፣ባገኘሁት አጋጣሚ ያለኝን ፍቅርና ክብር ለማሳየት ሞከርኩ፡፡ ያለኝን ትርፍ ሰዓት አብረን እናሳልፋለን፡፡ ወክ እናደርጋለን፣ ሃሳብ እንለዋወጣለን፡፡ ነገ ወደ ተከራየው አዲሱ ቤት ይገባል፡፡ ዛሬ የሰፈራችንን የመጨረሻውን ወክ ልናደርግ ወጣን፡፡

“ያቤዝ...”

“ወዬ ዶክ፡፡”

“ሰሞኑን አንተ ላይ ባየኋቸው ለውጦች ምን ያህል ደስተኛ እንደሆንኩ ስነግርህ ቆይቻለው፡፡ ዛሬ ግን፣ እንደ አዲስ ሙሉ የህይወት ታሪክህን እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ።”

“ማለት? አልገባኝም ዶክ፡፡”

“በቃ ህይወትህን፣ ከልጅነትህ ጀምረህ እንድትተርክልኝ እፈልጋለሁ።”

“እንዴ! ለምን?”

“ለምን እንደሆነ ባላውቅም፣ ካየሁህ፣ ካገኘሁህ ቀን ጀምሮ ስላንተ በጥልቀት ማወቅ ፈልጌያለሁ፡፡ ስላንተ ብዙ አስባለሁ፤ እገምታለሁ፡፡ እስከዛሬ ግዜው እንዳልነበር ይሰማኝ ነበር፡፡ ሰሞኑን ግን፣
ከመቼውም ግዜ በላይ ደስተኛና የተረጋጋህ እንደሆንክ አይቻለው፡፡
ስለዚህ ብትነግረኝና ብሰማኸ ደስ ይለኛል፡፡

“ዶክ፣ አንተን ይህን ያህል ካስደሰትህ፣ እንኳን ይሄን ሌላም
አደርግልሃለው፡፡ መቼም ከፍዬው ማልጨርሰው ውለታህ አለብኝ፡፡”

“ኧረ በፍፁም! እንደዛ ሁለተኛ እንዳትለኝ፡፡ እኔ ምንም አላደረኩልህም፡፡ አንተ ጎበዝና ጠንክራ ሰው ስለሆንክ ነው፡፡”

“እሺ እንዳልክ፡፡ ብቻ ግን ውለታህን ለመመለስ ያብቃኝ፡፡”

“አሁን የጠየኩህን፣ ታሪክህን ንገረኝ፡፡”

“እሺ! ያቤዝ እባላለሁ፡፡ ሰላሳ ስምንት አመቴ ነው። በልጅነቴ ዝምተኛም፣ አስቸጋሪም ልጅ ነበርኩ፡፡ ደግሞም ጎበዝ ተማሪ፡፡.” ከመቻሬ ኮንዶሚኒየም ወጥተን የጦር ሀይሎች አጥርን ታከን ቁልቁል
የካርል አደባባይን እየወረድን ነው፡፡ ዶ/ር ሄኖክ ዝም ብሎ ያዳምጠኛል፡፡ገብርኤልን አልፈን፣ በቶታል ማዞሪያ ቁልቁል ወደ መካኒሳ እየወረድን፣ከልጅነት እስከ ዩኒቨርስቲ፣ ከመመረቅ እስከ ከፍተኛ ሀላፊነት፣ ደስታና ሃዘን መውጣትና መውረዶች፣ ከእሱ ጋር እስከተዋወቅንበት ያለውን የማስታውሰውን ያህል ነገርኩት፡፡ በየመሀሉ የሚሰማኝን የጥፋተኝነትና
የቁጭት ስሜቶች ከፊቴ እንዳያነብብኝ፣ ቀና ብዬ ሳላየው በተመስጦ ተረኩለት፡፡ ስጨርስ ዝም አልኩኝ፡፡

“እንዙር፡፡” አለኝ፡፡ እርቀን ሄደናል፡፡ እሺ ሳልለው ዝም ብዬ ዞረኩኝ፡፡ ምንም እያወራ አይደለም፡፡

“በቃ ይኸው ነው፡፡ ከዛ ህይወቴን አንተ ቀጠልከው:: አሁን ደስተኛ ነኝ፡፡ ቀድሜ ህክምና ብጀምር ብዙ ጉዳቶቼን ማስቀረት እችል ነበር፡፡ ግን፣ ባለፈ ክረምት ቤት አይሰራም፡፡ እንዴት እንደምመልስው ባላውቅም፣ ውለታህ በህይወት ዘመኔ ሁሉ አልረሳውም፡፡”

“የምን ውለታ ነው ምትለው ያቤዝ፣ መልስህ እንዲህ ደስተኛና ስኬታማ ሆነህ በማየቴ ብቻ፣ በምንም ከፍዬ ማላገኘው ደስታ ነው::ታሪክህ ደግሞ ከጠበኩት በላይ ይገርማል፡፡ መፅሀፍ እየተረክልኝ
እስኪመስለኝ፣ ተመስጬ ነበር ያዳመጥኩህ፡፡”

“እንዴት..?”

“በህይወትህ የባይፖላር ምልክቶችን በተደጋጋሚና በተለያየ ጊዜ ተፈራርቀውብሃል፡፡በማህበረሰባችን የስነ አዕምሮ የግንዛቤ እጥረት ሰፊ ስለሆነ እንጂ፣ ይሄን ሁሉ ቀውስ ሳታሳልፍ በቀላሉ መቆጣጠር ይቻል ነበር፤” ብሎ ትክዝ አለ፡፡

“እውነትህን ነው፡፡ አሁን፣ እኔም የቀድሞ እኔን ካሁኑ ጋር ሳነፃፅረው እንደዛ ይሰማኛል፡፡ ግን ምን ማድረግ ይቻላል፡፡ ለበጎ ነው ብሎ ከማለፍ ውጪ፡፡”

“ማድረግማ መቻል አለብን፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣በሃገራችን ከአራት ሰዎች አንዱ የሆነ አይነት የአዕምሮ ችግር አለበት፡፡በዚህ ሰዐት እንዳንተ ብዙ ሴ ሰዎች፣ በስራቸው፣ በማህበራዊ ህይወታቸው ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው፡፡ ባለው የመረጃ እጥረትና የተዛባ አመለካከት፣ ብዙ ሰዎች ችግሩ እንዳለባቸው አይገነዘቡም፣ ችግሩም ህክምና እንዳለው አያውቁም፣ ማህበረሰባችን በዚህ ጉዳይ ሃኪም ማናገር ይፈራል፡፡ በዚህ ምክንያት ስንቶች፣ ከሚገባቸው ስኬት በታች ሆነው፣መድረስ ካለባቸው ከፍታ በታች ወርደው፣ በሚገፉት ህይወት
የሚሰማቸውን ቁጭትና ህመም ሳይ፣ ማድረግ ያለብኝን እያደረኩ እንዳልሆነ ይሰማኛል። በጣም አዝናለሁ፡፡ የችግሩን መጠንና ስፋት ስመለከት ደግሞ፣ ነብሴን ትጨነቃለች። የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ይሰማኛል፤” አለኝ አሁንም በትካዜ ውስጥ ሆኖ፡፡ እነዛ አስጨናቂና አስፈሪ፣ ላቆማቸው የማልችላቸው የባዶነት፣የተስፋ ቢስነት፣ ሀሳቦች ትዝ አሉኝ፡፡ አሁን የሉም፡፡ ጠፍተዋል።
ውስጤ ስላምና የተረጋጋ ነው፡፡ አሁን፣ ለእኔ አለም ጨለማ
👍2🥰2🔥1
#ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

በሩ ላይ ያለው ግርግር ሳያብዱ ያሳብዳል ። ቂቅ ብሎ ሙሉ ሱፍ ከነከረባቱ የለበሰ ሰውዬ በሌሎች ሰዎች ክንዶቹን ተይዞ እየጮኽና እየተሳደበ ይገባል ። ማንን እንደሚሳደብ እይታወቅም ፤ ብቻ ይሳደባል ያነበንባል እንደ ሕፃን የሚቦርቁ • ዕርቃናቸውን የሚንፏቀቁ ና የሚዘባርቁ እንደ ምሁር የሚፈላሰፉ በያይነቱ የተለያዩ ሰዎች ከውስጥ ብቅ እያሉ ሲጋራና ፍራንክ ይለምናሉ ። ዘበኛው እንዴ እንባርቆ ወደ ውስጥ ይወድሳቸዋል ። እነሱ ሳይ
ሲጮህ " ዘበኛው ራሱ ያበደ ይመስላል ። ያስደነግጣል ።

“ እዚሁ ይውረድ ወይስ ወደ ውስጥ ይግባ ? ” አለ አቤልን ያመጣው ሹፌር ፡ መኪናውን በሩ ላይ አቁሞ ።

“ እ ምንም አይል እዚሁ ይውረድ ” አለ አብሯቸው የመጣው አንድ የዩኒቨርስቲው የማኅበራዊ ሥራ ክፍል ባልደረባ ።

መኪናውን ውጭ አቁመዉ አቤልን
ግራና ቀኝ ደግፈው ወደ ዕብዶቹ ሐኪም ቤት ገቡ ።

“ እረ እባካችሁ ልቀቁኝ ፡ እኔ “ ኮ ደኅና ነኝ ” አላችው አቤል ፍጹም ጤናማ በሆነ ድምፅ።

እርስ በርሳቸው ተያይተው ዝም አሉት ።
“ ይልቅ እጄን ፍቱኝ ። አታሥቁብኝ ።
“ እሺ ቆይ ደርሰናል ፤እንፈታሃለን ” አሉት

አቤል እጁን ታስሮ ወደ ዕብዶች ሐኪም ቤት እንዲመጣ ያደረገው ነግር ምን እንደሆን በውል አያውቅም ።ከሚስተር ሆርስ ጋር ከተናነቁ በኋላ • እየጮኸና እየተንፈራገጠ አስቸግሯቸው ነው እጆቹን ያሰሩት ። በስሜቱ ሚስተር ሆርስ ትእግስትን ይዟት ሲሄድ የተሰበሰበው ሰው ሁሉ ያገዘው መስሎት ነበር የጮህው ሆኖም” ድርጊቴ ከተመስጦ
የመነጨ የቅዠት ያህል እንጂ የጸና ቀውስነት አልነበረም።አሁንም በጣጋ ደኅና ነው ። ጌና በመኪና ግማሽ መንገድ ሳይጓዙ ራሱ አውቆ ፥ “ አሁን ደኅና ነኝ ፣ ወደ ካምፓስ መልሱኝና ከፈለጋችሁ ልጁን ይቅርታ ልለምነው ” ብሎአቸው
ነበር ። ነግር ግን ሊያምኑት አልቻሉም ።

ከምዝገባው ክፍል ሲደርሱ ሰንሰለቱ ተፈትቶለት አስፈላጊውን ፎርማሊቲ እንዲያስሞላ ተጠየቀ ። ስሙን ዕድሜውንና አድራሻውን በትክክል ተናገረ ይዘውት የመጡት የዩኒቨርስቲ ሰይራተኛ ጤናማ መሆኑን ቢገምቱም። ሳያስመ
ረምሩት ለመመለስ ኣልደፈሩም ።

“ተራውን ጠብቆ ወደ ሐኪሙ ዘንድ ቀረበ ገና የሐኪሙን ፊት ሲመለከት፡እዕምሮው ውስጥ የማያጣበት ነገር የኤሌክትሪክ ሾክ ነበር ሰዎች አዕምሮአችውኝ ታመው
ወደ አማኑኤል ሆስፒታል ሲገቡነ ጭንቅላታቸውን በኤሌክትሪክ ጠዝጥዘው ያደነዝዟቸዋል ፤ ኤሌክትሪኩ ደሞ ኃይለኛ ነው ሲባል ይሰማ ነበር ። ይህን የኤሌክትሪክ ሾክ የሚጠቀሙት ለምን ዐይነት የዕብደት ደረጁ እንደሆን ጠንቅቆ ስለማያውቅ " በእሱም ላይ የሚጠቀሙበት መስሎት ፈራ ።
ሐኪሙ አጠገብ ያን አይነት የሚያስፈራ ግዙፍ መሳሪያ የለም ። ይልቅ አቤል “ ማሰቃያ ነች ” ብሎ የፈራት ከዚሁ ከሐኪም ክፍል ጋር የተያያዘችውን ጓዳ ነው ። ከሐኪሙ ፊት ቁጭ እንዳለ በዐይኑ እየሰረቀ ጓዳዋ ውስጥ ያለውን ነገር ለማየት ይሞክር ነበር።

ሐኪሙ ራሱ አንድ ሐሙስ የቀረው ሕመምተኛ ይመስላል ። የታወቀ ሳይካቲሪስት ነው ። የለበሰው ነጭ የሥራ
ካቦርት እንደ ኽብዛኛዎቹ ሐኪሞች ክብደት አልሰጠውም ።ተራ የጤና ረዳት አስመስሎታል ። በየዕለቱ ከሚቀርበለት
በርካታ ታካሚዎች የሚሰማው የተዘበራረቀ የችግር ዐይነት ወስፋቱን እየዘጋው ከእህል የተራራቀ ይመስላል ። ሺ ቀውስ ማነጋጎሩ ራሱ አያስቀውስም ? በየቦታው ፡ በየጎሬው ስንት ዐይነት መሥዋዕትነት የሚከፈልበት ሥራ አለ ! እንኳንስ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ችግር የአንድን ሰው ችግር ስቃይ መስማት ያስጠላል ። መንፈስን ይረብሻል ። ችግሩ
በሕያውነት ስሜት ተላልፎ ያቃጥላል ። አቤል ይህን ሲያስብ ለሐኪሙ ከልብ አዘነለት ።

ሐኪሙ የማንበቢያ መነጽሩን አውልቆ ከጠረጴዛው ላይ ቁጭ ሲያደርግ ፡ ትናንሽ ዐይኖቹ ከጉድጓዶቻቸው
ውስጥ ብቅ ብቅ አሉ ።

አቤል በሐሳቡ ዮናታን ትዝ አሉት ። ዕብዶቹ ሐኪም ቤት መድረሱን ቢሰሙ ምን ይሉ ይሆን ?

ሐሳቡን ለመቀጠል ሐኪሙ ጊዜ አልሰጠውም
“ እሺ ፥ ስምህ ማን ይባላል ? ”
አቤል ሙሉዬ ።
"የት ነው የምኖረው ? ”

“ እ ሀገሬ ጎንደር ነው ፤ አሁን ግን ያለሁት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስድስት ኪሎ ነው
“ ተማሪ ነህ ? ”
አቤል ራሱን በአዎንታ ነቀነቀ ።
« ስንተኛ ዓመት ደርሰሃል ? ”
“ በፍልስፍና ትምህርት አራተኛ ዓመት ።
“ ኦ! መጨረሻህ ነው? ” አቤል ዝም አለ

ይህ ሁሉ መግባቢያ ነው ። ሐኪሙ የታካሚውን ማንነት ወይም ችግር የሚረዳበት ጥያቄ አለ ፦ ። የአመላለስ
ሁኔታቸው በፍርሀት ፡ በጩህት በግዴለሽነት ወይም በአነጋገር ደረጃ ይለያይ እንጂ ፡ ብዙ ታካሚዎች የመግባቢያውን ጥያቄ በትክክል ይመልሳሉ ።

መልካም ነው አቤል ! ኧ፡ ወደዚህ ቦታ ለምን እንደመጣህ ታውቃለህ?

ሐኪሙ የዚህን ጥያቄ መልስ የሚጠብቀው በጉጉት ነው ። የሕመምተኞቹን ደረጃ ይገመግምበታል ። መቼም በተለያየ ጊዜ ከተለያየ ሕመምተኛ የሚቀርበው መልስ በየአይነቱ ነው።

ዝነኛ ሐኪም ነህ ሲባል ሰምቼ ነው ።
ፍቅረኛዬ ነች ለዚህ ያበቃችኝ ።
ያመጡኝን ሰዎች ጠይቅ ፥ እኔ ምን ዐውቃለሁ።
እንጃልህ የሚል መልስ የሚሰም አሉ ።

ታካሚዎቹ ከጥያቄው ጋር ፍጹም ያልተያያዘ ወይም የሚያሥቅ ወይም የሚያሳዝን መልስ ሊሰጡ ይችላሉ። ሆኖም ሐኪሙ አይሥቅም ። ረዳቶቹ አንዳንዴ ያመልጣቸውና ይሥቃሉ በሥራው ዓለም በሕመምተኛው መልስ መሣቅ ክልክል ነው ።

“ ግቢ ውስጥ ከአንድ ተማሪ ጋር በቼስ ጨዋታ ወጣላቴን ነው የማስታውሰው ” አለ አቤል ፥ ቀጥ ባለ ድምፅ ።

ምነው ? ምን አጣላችሁ ? ”
“በጨዋታው ሊያሸንፈኝ ሲል ተጣላን ለጊዜው ተመስጦ ውስጥ ነበርኩ ... አለና ሊናገር ያሰበውን አቋረጠ

አይኑን ከሐኪም ወደ ጠረጴዛው ወደ ሐኪሙ አንቀዋለለ ዳኛ ፊት የቀረበ ወንጀለኛ ይመስል አንገቱን ደፋ ።
ቼስ ጨዋታው ላይ ጸብ የፈጠረው በዓይኑ ያፈቅራት ልጅ የተመስጦ የቼስ ንግሥት ተመስላ ስሜቱ ውስጥ መጥታበት መሆኑን መናገር አልፈለገም ስለ ትዕግሥት ምንም ነገር ማለት አልፈለገም” ።ጸቡ የተፈጠረው መሸነፍ በሚያስከትለው ብስጭት ብቻ እንደሆነ አድርጎ ሊናገር አሰበ ።

በሌላ በኩል ደግሞ ዘመናዊ የማናዘዣ ዘዴ ( ሂፕኖቲዝም) መኖሩን ሲነገር በወሬ ሲለሚሰማ፥ ልቡ ምስጢሩን ለመደበቅ ፈራ በዚህ ዘዴ ሐኪሙ ምስጢሩን አንድ ሳይቀር ጎልጉሎ የሚያስወጣ መሰለው ። ዐይኑን እያስለመለመ ልቡ ምስጢሩን በማውጣትና በመደበቅ መሐል ተከፋፍሎ ቆየ " " ምነው ይህን ያህል ? ፍቅር ወንጀል ነው እንዴ ?” አለ በሐሳቡ ብናገርስ ምን ይመጣብኛል? ?

አቤል መደበቅ የፈለገው ወይም ያስጨነቀው ነገር እንዳለ ፡ ሐኪሙ ከገጽታውና ከሚስለመለሙት ዐይኖቹ
መረዳት ቻለ "

አይዞህ አቤል ነጻ ሁን !እዚህ እኔ ፊት የቀረብከው እንድረዳህ ነው ። ማናቸውንም ነገር እንደ ወንድምህ ወይም እንደ ባልንጀራህ ወይም እንደ ምስጢር ጓደኛህ ወይም እንደ ... እ... እንደ ሴት ጓደኛህ አርገህ አጫውተኝ ። ”

“ እሺ ” አለ አቤል እሁንም እየተቅለሰለሰ
“ ፍቅረኛ፡ የት ነው ያለችው ? ”
ሐኪሙ ይሆን የጠየቀው በአንድ በኩል ስለ ሴት ጓደኛ ሊያነሣበት ፥ በአቤል ፊት ላይ ያነበበምን ለውጥ አስቦ ሲሆን፥
በሌላ በኩል ደግሞ፡የፍቅር ትኩሳት የወጣትነት ዕድሜ አንዱና ዋናው ችግር መሆኑን ከሥራ ልምድ በማውቁ ነበር

አቤል ተደናግጦ ጭጭ አለ ፡ ምንም መልስ ሊሰጥ አልደፈረም”

“ እ እሷም ዩኒቨርስቲ ውስጥ ናት?”

ይህም ከገጠመኝ የመነጨ
👍1🔥1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ድርሰት_በትክክል_ገና

...ድሮ የሰማችው የንፁሁ የአቢላዛር ታሪክ ትዝ አላት፡፡ኤቢላዛር በሀሰት ውንጀላ በአባቱ ዘንድ እምነት ያጣና፤ባልሰራው ወንጀል፡ ከባድ ስቃይና ቅጣት የደረሰበት እናቱ በህጻንነቱ የሞተችበት ወጣት ነበር፡፡አቢላዛር በቁንጅናው ምክንያት በሕይወቱ ላይ ታላቅ ስቃይና
መከራ ደርሶበታል፡፡የአቢላዛር አባት ባትሮሊዮ ሕጻን ልጁን እናትም አባትም ሆኖ አሳደገው፡፡ አቢላዛር ዕድሜው ለአቅመ አዳም ሲደርስ አባቱ ባትሮሊዮ
ሚስት ለማግባት ፈለገ፡፡ሚስት ቢያገባ ለእሱም፤ ለልጁም፤ ረዳት - እንደምትሆን
በመገመት በዕድሜዋ ወጣት የሆነችውን ውቧ ጉቲኤራን አገባት፡፡ጉቲኤራ በቁንጅናዋ እዚህ ጉደለሽ የማትባል ብትሆንም፤ በራሷ ቁንጅና ላይ የነበራት ኩራት ወደታች የወረደው ፤ የባሏን ልጅ አቢላዛርን ያየችው ዕለት ነበር፡፡ በዚያን ዕለት በፍቅር የተነደፈ ልቧን ሐኪምም፤
ፀበልም፤ ማንም እንደማያድነው አወቀች፡፡ መድሃኒቱ አንድ ነው፡፡ እሱም
አቢላዘር ብቻ! ስሜቷን አምቃ እየተሰቃየች፣ በአንድ ወገን የእንጀራ ልጂ
የመሆኑ ጉዳይ ቢያስጨንቃትም፤ ፍቅሯን መቋቋም አልቻለችምና፤የእንጀራ ልጅነቱን ጉዳይ ችላ በማለት፤በፍቅር ልታጠምደው ቆርጣ ተነሳች፡፡
ጉቲኤራ በፍቅር የተረታችለት መሆኑን እንዴት አድርጋ እንደምትገልጽለት ጨንቋት ውስጥ ውስጡን ስትሰቃይ ኖረች።ቀስ በቀስ ውስጥ ውስጡን የሚያብሰለስላት፣ የሚያብከነክናት፤
የፍቅር መጋዝ፤ በአካሏም ላይ ለውጥ እያስከተለ ሄደ፡፡
አፏን ከፍታ ፍዝዝ፣ ድንዘዝ፣ ብላ የምትቀርበት ጊዜ ጥቂት አልነበረም፡፡ ይህ ሁኔታ ለአቢላዛር በፍፁም አልተገለጠለትም ነበር፡፡በእርግጥ አቢላዛር ማንም በቀላሉ አይቶት የሚያልፈው ልጅ አይደለም፡፡ ያጓጓል፡፡ በዚሁ መሀል ለጉቲኤራ አንድ አጋጣሚ ተፈጠረላት። በጣም አስደሳች አጋጣሚ፡፡
ባሏ ባትሪሊዮ ግመሎቹን በሙሉ እየነዳ
የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ለማምጣት ድንበር ጥሶ የሚሄድበት ቀን ደረሰ፡፡
ባትሮሊዮ ቢያንስ ከሁለት ወራት በፊት አይመጣም፡፡ በቃ በዚህ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ የሚያለቅሰው ልቧ ፈውስ ሊያገኝ ነው፡፡ እሺ አለም እንቢ፤ በውድም ይሁን በግድ፤ አቢላዛርን ማግኘት አለባት፡፡ እንቢ ቢል ልታስገድደው ወሰነች፡፡
አቢላዛር እናትም አባትም ሆኖ ላሳደገው ለአባቱ ያለው ፍቅር የተለየና በአለም ላይ ከሚያፈቅራቸው ነገሮች ሁሉ በላይ ነው፡፡
የአባቱ የጉዞው ቀን ደረሰ፡፡ አቢላዛር አባቱን በፍቅር ተሰነባበተው፡፡ ጉቲኤራ ደግሞ በቶሎ አይመልስህ ብላ ሸኘችው፡፡ ከዚያም ባትሮሊዮ በሄደ በሳምንቱ ጉቲኤራ ተቅበጠበጠች፡፡ ከዚህ በላይ ብትቆይ የምትፈነዳ መሰላት፡፡ከዚህ በላይ መቆየት መታገስ አቃታት፡፡ አቢላዛር
ደግሞ እስከአሁን ድረስ ቅንጣት ታክል ችግሯን አልተረዳላትም፡፡
በሣምንቱ መጨረሻ፤ ያ ምሽት፤ እንደወትሮው ሁሉ፤ አቢላዛር የመኝታ ክፍሉን በር ቀርቅሮ የተኛበት ምሽት ነበር፡፡ ጉቲኤራ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት አካባቢ ሲሆን የውስጥ ሱሪዋን ብቻ እንደለበሰች ወደ መኝታ ክፍሉ መጣች፡፡
“አቢላዛር! አቢላዛር ድረስልኝ! እባክህ በሩን ቶሎ ክፈትልኝ!”
እያለቀሰች በሩን በሃይል መታቸው፡፡
አቢላዛር በዚያን ሰዓት በሆነ ቅዠት ላይ ነበረ፡፡ በሩ በሃይል ተንኳኳ፡፡ ተንጓጓ፡፡ በዚህ ጊዜ ከእንቅልፉ ባኖ ቢያዳምጥ፤ የእንጀራ እናቱ በእንባ ሲቃ በታፈነ ድምጽ ስትጣራ ሰማ፡፡ በሁኔታው በጣም
ተደናገጠና በሩን ከፈተው፡፡
የሚያየውን ነገር ማመን አቅቶት፤ አሁንም በህልሙ እንዳይሆን ተጠራጠራና፧ አይኖቹን አሻሽ፡፡ በርግጥም በህልሙ አልነበረም፡፡ በውኑ ነው፡፡

የጉቲኤራ ራቁት ገላ፣ ያገጠገጡ ጡቶቿ፤ ባለጥንድ አፈሙዝ ድግን መትረየስ መስለው፤ ከፊት ለፊቱ ተወድረዋል፡፡
ዓይኖቿ በማያቋርጥ የእንባ ምንጭ ይዋኛሉ፡፡
“ምን ሆንሽ ጐቲኤራ?” ደንግጦ ጠየቃት፡፡
“አነቁኝ፡፡ መጡብኝ ሊበሉኝ ነው” ወተወተች፡፡
“እነማናቸው? ማን አባቱ ነው ሊበላሽ የመጣው?”
በእንጀራ እናቱ ላይ እጁን የሰነዘረውን ጠላቱን ሊተናነቀው አይኖቹ በንዴት ቀልተው ጠየቃት፡፡
“ግዴለም ቆይ ቁጭ በል፡፡ አሁን ሄደዋል፡፡”
“ጅል፤ ነገር የማይገባህ ደደብ” አለችው በልቧ፡፡ እኒያ የቆሙ ጡቶቿ ያ ውብና ማራኪ ራቁት ሰውነቷ የማይታየው እውር አናደዳት፡፡
“ሰይጣኖች ናቸው፡፡ ሰዎች አይደሉም፡፡ ይኸውልህ እዚህ ላይ ነው በጣም የትጫኑኝ፡፡ ተመልከት እዚህ ጋ” የቀኝ እጁን ይዛ ጡቶቿ መካከል አስቀመጠችው፡፡
አቢላዛር በየዋህነት እዚያ ጡቶቿ ሥር የሚሰማትን ህመም እንዲወገድላት አሻሻት፡፡
በዚያን ሰዓት ጉቲኤራ ጦፋ በሃሣቧ ከዚያ በኋላ በሚፈጠረው
ትርኢትና፤ በትርኢቱ ውስጥ የሚስማትን የእርካታ ስሜት እያጣጣመችው ነበር፡፡
“በቃ እዚሁ እሆናለሁ ከአሁን በኋላ እዚያ ዳፍንታም ክፍል አልመለስም” አለችውና ሄዳ እሱ አልጋ ላይ ቁጭ አለች፡፡
“ብርድ ይመታሻል ልብስ ልበስ” ብሎ የራሱን ሸሚዝ እላይዋ ላይ ጣል ቢያደርገው ፤ ወደዚያ ውርውር አድርጋ...
“ይልቁን እሱን በደንብ አድርገህ እሽልኝ፡፡ ያለበለዚያ ያመኛል
በታዘዘው መሠረት እዚያ ጡቶቿ
ሥር፧ሰይጣኖቹ ያሳመሟትን ቦታ፤ ለማዳን ማሻሸት ቀጠለ፡፡ጉቲኤራ ደግሞ እንደዚያ
ጡቶቿን ሲያሻሽላት የምትሆነውን አጣች፡፡ እንደሰም ቀልጣ መፍሰስ ጀመረች።
ሙሉውን ሌሊት በእንባ እየታጠበች ብትለምነው ንዴቱ እየባሰበት እንጂ ሃሣቡን የመለወጥ አዝማሚያ ሳያሳይ ቀረ። በዚህ ሁኔታ በተደጋጋሚ ፈተነችው፡፡ አቢላዘር ግን ወይ ንቅንቅ! አለ፡፡
በመጨረሻም እንዳልተሳካላት ቁርጧን ስታውቅ፤ ልትበቀለው ቆርጣ ተነሳች፡፡
ሴራዋን ስትጎነጉን ሰነበተች፡፡ ባሏ ከሁለት ወር በኋላ ሲመጣ፣በናፍቆት ከመቀበል ይልቅ፤ እሳት ጎርሳ፤ እሳት ለብሳ፤ ተቀበለችው:: የሁለት ወር ሙሉ ናፍቆት አቃጥሎት ሲስማት አመናጨቀችው፡፡
“የጋብቻ ውላችንን አፍርስልኝ” ስትል ጮኽችበት ባትሮሊዮ በነገሩ ተደናግጦ ምክንያቱን ቢጠይቃት...
“ምንም እንኳን ባልወልደው፤ ልጅህ ፤ ልጄ ይሆናል ብዬ ነበር እዚህ ጣጣ ውስጥ የገባሁት፡፡ እሱ ግን ለሚስትነት ፈለገኝ” ብላ ከፍላጐቷ ውጭ አስገድዶ በግብረ ሥጋ የተገናኛት መሆኑን እያለቀሰች ነገረችው፡፡
ባትሮሊዮ እንደ አይኑ ብሌን የሚያየው አንድዬ ልጁ፣ እናትም አባትም ሆኖ ተሰቃይቶ፣ በሽንት ተጨማልቆ ያሳደገው የሚወደው ልጁ ተመልሶ እጁን ስለነከሰው ፤ ሀዘኑ ጣራውን አለፈና፤ ለዚህ ወደር ለሌለው ጥፋቱ ቅጣቱን ሲያውጠነጥንለት ዋለ፡፡በመጨረሻ የመጣላት ሃሣብ መግደል ቢሆንም፧ መግደል ብቻውን አላረካህ አለው፡፡ ከዚያ በላይ በቁሙ እያለ እንዲቀጣ ፈለገ፡፡
እንደዚያ በጥጋብ እንዲያነጠንጥ፤ እንደዚያ ያለውን አፀያፊ ሥራ እንዲሠራ፤ የገፋፋውን ችግሩን ከላዩ ላይ ሊያስወግድለት ወሰነና፤ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ላይ የመኝታ ቤቱን በር አስከፍቶት ገባ፡፡
አቢላዘር ከእንቅልፉ ባንኖና፤ በሁኔታው ተደናግጦ፡
“ምነው አባባ?” ሲል ጠየቀው፡፡
“ዝም በል!! የምትታዘዘውን ብቻ ትፈጽማለህ!!” ሲል ጠንካራ ትዕዛዝ ሰጠው፡፡አባቱ እሳት ለብሶ፤ እሳት ጉርሶ፤ ሲያይ ልጁ በአባቱ አዲስ ፀባይ ተደናግጦና፤ ግራ ተጋብቶ፤ የታዘዘውን ሁሉ በአክብሮት ይፈጽም ጀመር፡፡ራቁቱን አስቁሞ እጁንም እግሩንም አሰረው፡፡ ያለተቃውሞ
በአባቱ ትዕዛዝ መሠረት እጁንም፤ እግሩንም፤ ለገመድ ሰጠ፡፡
“በሽንትህ ተጨማልቄ፤ ያለ እናት ያሳደግኩህ አባትህ መሆኔን አውቀህ ፤ ቤቴን ትዳሬን አክብረህ ስለቆየኸኝ ፤የረጅም ዘመን ድካሜን ዋጋ ለመክፈል እንቅልፍ አጥተህ ስለጠበቅከኝ፤ ይህንን የዋልክልኝን ከፍተኛ የልጅነት ውለታህን ተቀብዬ፤ እኔም የአባትነት ውለታዬን
🔥21👍1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ



#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ


....በጥፊ ጆሮ ግንዷን እናጋው፡፡
ለጥቂት ደቂቃዎች ያለችበት ጠፋት፤ዘሪያዋ ጨለማ ለበሰ፡፡ እዛው
አፓርትመንት ክፍሏ ውስጥ እጆቿንና እግርቿን ከአልጋዋ ጋር በአንሶላ
ጨርቅ ጥፍር አድርገው አስረው እንዳትጮህ አፏ ውስጥ ጨርቅ ጎስጉሰው ለጉመው አጋድመዋታል፡፡

“ንገሪኝ!” አለ ድጋሚ ሊያጣፋት እየተንጠራራ “የት ነው ያለው?
ትነግሪኛለሽ አትነግሪኝም?”
ጭንቅላቷን በጭንቀት አርገፈገፈችው:: ከተለጎመው አፏ ጀርባ ጉሮሮዋ . “የት እንዳለ አላውቅም:: እውነቴን ነው!” አለች:: ድምፅ ግን አላወጣችም፡፡

ውልብ አለባት ድጋሚ፡፡ ጆሮዋ ላይ ሌላ ጥፊ ደወለ፡፡
“ንገሪኝ!”

ዱላው እየጨመረ በመጣ ቁጥር እልኋና ቁጣዋ እንዴት ተደፈርኩ ባያነቷ እንደጨው እየሟመ ለማይታክተው እንባዋ እስረከበዋታል፡፡ ፀጉሯ
ሲጨመደድ ተሰማት::

“ንገሪኝ! የት ነው ያለው?”
ድጋሚ በጥፊ አይኖቿን ከደናቸው፡፡
“ንገሪኝ!”

ተከትሎ ምን እንደተናገረ አልሰማችውም:: ጆሮዋ ላይ የሚደውለውን ስቃይ ተከትሎ ዙሪያዋ ፅልመት ተከናነበ፡፡ አይኖቿን ድጋሚ ስትገልጣቸው ሰውነቷን ክፉኛ ቀዘቀዛት፡፡ለሶስተኛ ጊዜ ውሃ አፍስሰውባታል፡፡
አልጋዋ በየደቂቃው ህሊናዋን በሳተች ቁጥር በሚቸለስባት ቀዝቃዛ ውሃ
ረስርሳል:: የለበሰችው ስስ ቀሚስ እላይዋ ላይ ተጣብቋል፡፡

ዓይኖቿን ግርብብ አድርጋ ተመሰከተቻቸው፡፡ ሶስቱም በአልጋዋ
ዙሪያ ቆመው ቁልቁል ይመለከቷታል፡፡ ሁለቱን አታቃቸውም፡፡ ሶስተኛው
ግን ያው የህዋሷ መሪ ማርቆስ ነበር፡፡ በጠባሳ የተገመሰ ፊቱን ቁልቁል
አንዘርቦ ይመለከታታል፡፡ ደጉን የተወያየችው የገዛ ጓደኛዋ አልመስልሽ
አላት፡፡ አይኖቿን ጭምቅ አድርጋ ጨፈነቻቸው፡፡ በተንጋለለችበት እንባዋ
የገዛ አይኖቿን እንደጨው እየለበለበ ፈሰሰ፡፡

“ከሃዲ!” አለ ሰስተግራዋ የቆመ ሌሊቱን ሲጠፈጥፋት ያደረው ሰው ድንገት ፊቱን መልሶ የመኝታ ክፍሏን በር ከፍቶ እየወጣ፡፡

በክፍሉ ውስጥ የቀሩት ሁለት ሰዎች ለጥቂት ደቂቃዎች ያለ እንቅስቃሴ ቁልቁል ሲመለከቷት ቆዩ፡፡ ወዲያው ማርቆስ ጠጋ ብሎ አፏ የተለጎመበትን ጨርቅ መፍታት ጀመረ፡፡ ሽቅብ ፊቱን ስትመለከተው ከዓመት በላይ የምታውቀው አብራው የቀለደችና የሳቀች ያው የድሮው የህዋሷ መሪ ማርቆስ መሆኑን ማመን አቃታት፡፡

“ምን ማድረግህ ነው?” አለ ከበስተግርጌ የቆመው ጺማም ሰውዬ ማርቆስ አፏ የተለጎመበትን ጨርቅ ሲፈታላት ሲያይ እየተቁነጠነጠ።

ማርቆስ ለሰውየው መልስ ሳይሰጠው አፏን ሞልቶ ተርፎ የነበረውን ቡትቶ ጨርቅ ጎትቶ አወጣላት፡፡ ተበርግዶ የቆየ መንጋጋዋ የራሷ መንጋጋ እንዳልሆነ ሁሉ አልገጥምልሽ አላት፡፡ ደርቆ የቆየ ጉርሮዋ የገዛ ምራቋን አልውጥልሽ አላት፡፡ እንባዋ ብቻ ጉንጮቿን እየተለተለ መውረዱን
ቀጠለ፡፡

“ርብቃ …ለምን ለእኛም ለራስሽም አስቸጋሪ ትሆኛለሽ?” ማርቆስ
ቁልቁል እየተመላከተ ተማፀናት፡፡ “ርብቃ ልለምንሽ የት እንዳለ ንገሪንና
ይህ ሁሉ ያብቃ፡፡” ተለማመጣት፡፡

ለምን አይገባቸውም?! ናትናኤል የት እንደለ ኣላውቅም ስትላቸው ለምን አያምኗትም?! እንዴት አድርጋ ነው እውነቱን እውነት ነው የምትላቸው?

“የት እንዳለ አላውቅም፡፡” ልትል ፈለገችና ጉሮዋ አልታዘዝሽ አላት፡፡ በጀርባዋ በተንጋለለችበት ጭንቅላቷን ነቀነቀች፡፡
“ርብቃ ጊዜ በወሰድሽ ቁጥር ሁኔታው ለራስሽ እየከፋ ነው የሚሄደው፡፡ የምትጋፈጫቸው ሰዎች ትዕግሥታቸው ያለቀና ቁጣቸው ወደ ዕልህ የተቀየረ ራሳቸውን መቆጣጠር የማይችሉ ናቸው:: ርብቃ እነዚህ ሰዎች ሊያደርጉት የሚገፋፉትን ደግሞ ማንም አይወደውም፡፡ አንቺ ሴት ነሽ፡፡ እነዚህን ሰዎች የሚቋቋም የመንፈስ ጠንካራነት የለሽም:: በቀላሉ እንደቀርከሃ ሊሰባብሩሽ ይችላሉ፡፡ በቀላሉ! እባክሽን ንገሪኝ፡፡፡ ናትናኤል የት ነው?” የሌሊት ሁኔታዋን መቋቋም አቅቶት ሲቁነጠነጥ ያደረው
ማርቆስ የባሰ ከመምጣቱ በፊት ሊያሳምናት ታገለ፡፡

አ....አላውቅም፡፡” አለችው እንባዋን እያስተናገደች::
“ጥሩ፡፡ መስሪያ ቤትሽ ደውሉ ሲያጣሽና ስራ ከገባሽ ውሰሽ ማደርሽን ሲረዳ እንዴት እዚህ አልደወለም?”
“ፈርቶ ይሆናል... እኔ ምን አውቃለሁ፡፡” እውነተኛነቷን ይገልፅላት ይመስል ድምጿን አለሰለሰችው::

“ምን? ማንን ነው የሚፈራው?”
“እናንተን፡፡” አለች በለቅሶ መሃል፡፡

“አየሽ ይህ ማለት አንቺ ከእኛ ጋር ግንኙነት እንዳለሽ አውቋል ወይም በፊትም ያውቅ ነበር ማለት ነው፡፡ ይህን ሊያውቅ የሚችለው ደግሞ አንቺ....”

አልነገርኩትም!” አለች አቅጣጫውን ስትረዳ አቋርጣው፡፡ “እኔ አልነገርኩትም፡፡እኔ በእርሱ ላይ መረጃ ስስበስብ መቆየቴንም ጭራሽ አያውቅም፡፡ ግን እዚህ ሲመጣ ልታገኙት እንደምትችሉ ጠርጥሮ ይሆናል፡፡”
ለምን ድጋሚ መሥሪያ ቤትሽ ስልክ አልደወለም? ባለፈው ጊዜ ሲደውል ጓደኛሽ ቢሮ ከገባሽ ዉስሽ ማደርሽን እንድትነግረው አድርገናል፡፡እዚህ መደወል ወይ መምጣት ነበረበት፡፡ አልመጣም፧ አልደወለም:: መሥሪያ
ቤትሽም መልሶ አልደወለም:: ለምን?”

“አላውቅም::” እለች በማስተዛዘን፡፡

“ውሽት አውቋል… ሁሉንም ተረድቶታል:: ለዚህ ነው ሊገናኝሽ ያልሞከረ፡፡ ባያውቅ ኖር..”

“ውሸቴን አይደለም!” አቋረጠችው “እመኑኝ ናትናኤል ምንም የሚያውቀው ነገር የለም ናት…”

“ያውቃል! ያውቃል! ምንም የማያውቅ ሰው በጭካኔ የሁለት ሰው ነፍስ አጥፍቶ አይሰወርም፡፡ ትሰሚኛለሽ? የፈጸመው ወንጀል ምንም የማያውቅ ሰው የሚፈጽመው አይደለም!” ትከሻዋን በሁለት እጆቹ ይዞ ነቅነቃት፡፡

“ናትናኤል ሰው ፡ አይገድልም...ውሸት
ነው፡፡” ለራሷ ፡ ነበር የተናገረችው፡፡

“ርብቃ…. ሰዎቻችን ያውቁታል፡፡ ለይተው ስላወቁትም ነው የተከታሉት፡፡ ይገባሻል? የካልቨርትን አድራሻ ከሴትየዋ ማግኘት ስላልቻለ ምናልባትም አድራሻውን አስገድዶ ካውጣጣት በኋላ ነው ደረቷን በጥይት የበሳው፤ ገድሏት የሄደው፡፡
አስታውሽ እሷን ብቻ አይደለም ያጠፋው!
የኛንም ሰው ነው:: ርብቃ… እባብ ነው ሰውዬሽ፡፡ ሁላችንንም አታሎናል፡፡
ምንም የማያውቅ የዋህ መስሎ አታሎናል፡፡ አንቺንም አታሎሻል፡፡ አብረን
ልናቆመው ይገባናል፡፡ ንገሪኝ፤ የት ነው የተሸሸገው?”

“አላውቀውም አልኩህ፡፡”
ገፁ በንዴት ተኮማተረ፡፡

“ርብቃ” አይኖቹን አጥብቦ ተመለከታት፡፡ “በአንድ ወቅት ከጎናችን መቆምሽን አንዘነጋውም፤ ያ የሩቅ ትዝታ አይደለም፤ ግን ደግሞ መረባችን በከዳተኞች ምላጭ ሲበጣጠስና ውጥናችን በባንዳዎች ራስ ወዳድነት እርቃኑን ወጥቶ እያንዳንዳችን ለስደትና ለሞት ስንዳረግ በዝምታ መመልከት አንችልም፡፡ ይህ እንዳይሆን ደግሞ የምንጠላውንም ነገር ቢሆን ለማድረግ እንገደዳለን፡፡ ርብቃ ትሰሚኛለሽ? መንፈስሽ መኮሳሽት ካለበት እናኮላሽዋለን፤ሰውነትሽ መዋረድ ካለበት እናዋርደዋለን! ህሊናሽ መጨቅየት ካለበት እናጨቅየዋለን… የማታ ማታ የጠየቅንሽን ሁሉ ታወጪዋለሽ፡፡ ይህ ከመሆኑ በፊት አስተውይ፡፡ ናትናኤል አታሎሻል! የስጋ ፍላጎትሽን ተጠቅሞ
ምስጢራችንን ከቀዳ በኋላ አጋልጦሽ ተሰውሯል፡፡ የት ነው ያለው?
ናትናኤል የት ነው?”

“አላውቅም'ኮ” እንባዋ ገና ድሮ በቀደደው ቦይ ያንቆረቆር ጀመር፡፡

የመኝታ ቤቷ በር ተከፍቶ ሦስት ሰዎች ተከታትለው ገቡ፡፡ ሁለቱን አይታቸው አታወቅም አንደኛው ግን ከትላንት ጀምሮ ሲቀጠቅጣት የቆየ ነው ከፊት ቀደም ያለው ሰው በእድሜ ጠና ያለ ይመስላል፡፡ ወደፊት ራመድ ብሎ ወደ አልጋዋ ግርጌ ከተጠጋ በኋላ በክፍሉ ውስጥ ለተሰበሰቡት ሰዎች እንዲፈቷት ምልክት ሰጣቸውና ከማርቆስ ጋር በሹክሹክታ ይነጋገር ጀመር
1👍1
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው

....አውሮፕላን ጣቢያው ውስጥ ያየው የተሳቀቀ የባለቤቱ ሎሪያን ፊት ብቻ
ነበር እውነተኛ ነገር የመሰለው።

“ሜክሲኮ ሲቲ ከሚገኘው ኤምባሲያችን አንድ ስርአት የሌለው ሰው አንተ በዚህኛው አውሮፕላን ውስጥ እንዳለህ ነግሮኝ ነው የመጣሁት” ብላ በመቀጠልም ነገሩ ውሸት መስሎኝ ላለመምጣት ሁሉ አስቤ ነበር። በእየሱስ
ስም ዴሪክ ምን ተፈጥሮ ነው? ማን ነው እንደዚህ የደበደበህ?” ብላም
ጠየቀችው፡፡

“ማን እንደሆነ እርግጠኛ አይደለሁም” ብሎ ዊልያምስ ባበጠው ከንፈሩ
እና በተሰበረው አፍንጫው ምክንያት እየተነፋነፈ መለሰላት፡፡ “ከሆነ የቢዝነስ
ሰው ጋር ቀጠሮ ነበረኝ፡፡ ስለ ሰውዬው ካስታወስሽ በስልክ ነግሬሽ ነበር::
ሰውዬውን ቢሮው ውስጥ እየጠበቅኩት እያለሁኝ ሁለት ዕብድ የሆኑ ሰዎች
ሲቀጠቅጡኝ እና በግዴታ በአውሮፕላን አሳፍረው ወደ እዚህ እንደላኩኝ ብቻ
ነው የማስታውሰው፡፡”

“እሺ አሁን ግን ሀኪም ቤት ሄደህ መታየት አለብህ” ብላ ሎርያን ጫና በሚያሳድር ድምፀት “ወደ ቤት ስንሄድ መሃል ላይ ከሚገኘው ክሊኒክ አስገብቼህ ትመረመራለህ፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እወስድክ እና ማመልከቻህን ታስገባለህ፡፡ እንዴ አንተ እኮ የአሜሪካ ዜግነት ያለህ ሰው
ነህ፡፡ መብት አለህ፡፡”

“አይሆንም ፖሊስም ሆነ ዶክተር ማግኘት አልፈልግም”

“አብደሃል እንዴ የግድ የሆነ ሃኪም ሊያይህ ይገባል”

“አይሆንም!” ብሎ ጮኸባት እና “ይቅርታ ማሬ” አሁን የምፈልገው ቤቴ ሄጄ መተኛት ብቻ ነው ከዚያ በኋላ ደግሞ የቻርሎቴ ወላጆች ጋር ደውዬ ነገ ጠዋት ላይ ላገኛቸው እንደምፈልግ አሳውቃቸዋለሁ” አላት፡፡

ጠዋት ላይ የቻርሎቴን ወላጆች ካገኘ በኋላ ስለልጃቸው ነገራቸው፡፡ይሄኔም ተከር ክላንሲ በቁጣ ነድዶ ጮኸበት፡፡

“እንዴት ብትደፍረን ነው!” የቻርሎቴ አባት እጁን ጨብጦ በሚያስፈራ መልኩ እየተመለከተው “እኛ ወደ ሜክሲኮ የላክንህ እኮ ስለ ቻርሎቴ
መጥፋት ምርመራ እንድታደርግ እንጂ ስለ ልጁ ያልሆነ ታሪክ ፈጥረህ
ስሟን እንድታቆሽሽ አይደለም፡፡ ስለ ልጄ መጥፎ ነገር ስታወራ ከአሁን በኋላ ከስማሁ ግን እግዚአብሔር ምስክሬ ነው ፍርድ ቤት ገትሬክ ለምርመራው የከፈልኩህን ሰባራ ሳንቲም ሳይቀር አስመልስሃለሁ፡፡” አለው፡፡

“እባክህን ተረጋግተን እናውራ እኔ ለምን ስለ ቻርሎቲ ያላደረገችውን አደረገች ብዬ እነግርሃለው እስቲ አስብበት፡፡ በዚያ ላይ
ለእናንተ ለሁለታችሁ ብቻ አይደል ይሄንን ነገር የነገርኳችሁ? ደምበኞቼ
አይደላችሁም እንዴ?” አለው ዊልያምስ በትህትና ድምፅ ውስጥ ሆኖ፡፡

የቀድሞ ደምበኛ ብለህ ያዘው!! ከዚህ በኋላ አንፈልግህም፡፡”

“ይቅርታ ጌታዬ እኔ በልጅህ ለደረሰው ወንጀል ፍርድን ብቻ ነው የምፈልገው፤ ደግሞ ጉዳዩ ላይ በጣም ቀርቤያለሁ፡፡ በጉዳዩ ላይ መቅረቤን የሚያሳየው ነገር ደግሞ እኔ ላይ የደረሰው ድብደባ ነው፡ እኛ በጣም ሀይለኛ ከሆነ ሰው ጋር ነው ትግላችንን እያደረግን ነው ያለነው” አለው፡፡

“ምንም አይነት ጉዳይ ላይ አልቀረብንም!” ብሎ ተከር ክላንሲ ደነፋ፡፡

እሺ በቻርሎቴ መጥፋት ላይ ምርመራ ሲደረግባት እንደነበር ታውቁ ነበር?” ሲሉ ዊልያምስ ጠየቀ፡፡

“ምን ማለት ፈልገህ ነው?” ብሎ ተከር አይኑን አጥብቦ ጠየቀ፡፡

የቻርሎቴ ጓደኛ ፍሬድሪኩ ዚዳን ወ/ሮ ባደን እናንተ ጋር ከመምጣትዋ
በፊት አግኝታት ስለ ቻርሎቴ ጉዳይ እንዳወራቻት ታውቅ ነበር፡፡ ለምንድን
ነው ወ/ሮ ባደን ይህንን ነገር ለእናንተ ያልነገረቻችሁ?” ብሎ ሲጠይቃችው
ሜሪ ክላንሲ እና ባለቤትዋ ተከር ክላንሲ ግራ ተጋብተው እርስ በእርስ
ይተያዩ ጀመር፡፡

“አናውቅም” ብሎ ተከር ንዴት ውስጥ እንዳለ መለሰ እና ከንዴቱ ሳይበርድም “እኔ የማውቀው አንድ ነገር ቢኖር የፈረንሳዊቷ ወጣት ወይንም
ቫለንቲና ባደን ወይንም ደግሞ ሌላ ሰው ስለቻርሎቴ የነገሩህ ነገር በሙሉ
ውሽት መሆኑ ብቻ ነው፡፡ የኔ ልጅ በፍፁም ባለትዳር ከሆነ ሰው ጋር
በፍፁም ጓደኝነት ልትመሰርት አትችልም፡፡ በፍፁም! ቻርሊ እኮ ገና 18 አመትዋ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ስም ገና ድንግል ናት እኮ፡፡”

“ኦኦኦአ ተከር” ብላ ሚስቱ አይንዋን አሸች እና “ተው እንጂ ማሬ። ተው
ማለት ምን ማለት ነው?” ብሎ ሚስቱን ጠየቃት፡፡

“ድንግል አልነበረችም ከቶድ ጋር ለአንድ አመት ያህል ቆይተዋል፡፡” አለችው፡፡

“ያገኛት እንደነበር አውቃለሁ፤ ነገር ግን ይሄ ማለት እሷ” ብሎ ሲያወራ ሚስቱ በሃዘኔታ እያየችው “አሁን በእሷ ድንግልና ጉዳይ መጮህ አለመጮህ
ምንም ውጤት አያመጣም፡፡ ለማንኛውም ሚስተር ዊልያምስ ከሆነ
ከቻርሎቴ መጥፋት ጋር ግንኙነት ያለው ተጠርጣሪ ሰው አግኝተዋል እንበል፤ የእሷን መጥፋት አስቀድመው አውቀው ለእኛ ለምን እንዳልነገሩን ሊገባን አልቻለም፡፡”

ይሄንን ሲሰማ ተከር ክላንሲ ጠረጴዛውን በቡጢ መታ እና “ይህ ሰው ምንም ተጨባጭ እውነት ይዞልን አልመጣም፡፡ ለማንኛውም ከአሁን በኋላ አታስፈልገንም ሳምንቱ ሳያልቅ ከዚያ ከተረገመ ሃገር ተጠርዘህ እስከመጣህ ድረስ ለዚህ ሳምንት የከፈልንህን ክፍያ ትመልስልናለህ፡፡ ነይ ማሬ እንውጣ
ብሎ ተነስቶ በቁጣ መራመድ ሲጀምር ባለቤቱ ሜሪም ዊልያምስን በአይንዋ
ይቅርታ እየጠየቀችው ተያይዘው ከቢሮ ወጡ፡፡

የቻርሎቴ ወላጆች ከቢሮ ከወጡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ሚስቱ ሎርያን የቢሮውን በር ከፍታ ወደ ውስጥ ገባች፡፡

መልካም ሚስት የሰጠኸኝ እግዚአብሔር ሆይ ተመስገን አለ እና በውስጡ የቢጫ ሎሚ ካለው ሹራብ ስር የተወጠሩትን ጡቶችዋን ከእርሳስ ከለር ውስጥ ልክክ ብሎ የሚሞናደለውን መቀመጫዋን አደነቀ፡፡በማስቀጠልም በእርግዝና ያበጠው ሆድዋን ተመለከተ፡፡ የተቀጠረበትን ነገር በትክክል እየሰራ ባለበት ሰዓት በደምበኞቹ መባረሩን የምትረዳለት ሴት ብትኖር ምናልባት ሚስቱ ብቻ ናት፡፡ ደግሞስ ሚስቱ ለዚህ ጊዜ ካልሆነችለት ለመቼ ነው የምትሆነው? በዚያ ላይ ደግሞ ማታ ተኝተው ሳሉ በድብደባ የቆሰለውን ፊቱን እየነካካች ምን ያህል እንደምትወደው ትነግረው ስለነበረ ደስ ብሎት ነው ያመሸው፡፡

“ምንድን ነው ዴሪክ?” ብላ ነገር ባዘለ ድምፅ ስትጠይቀው ከቀን ቅዠቱ
ባነነ፡፡

“አባረሩህ? ገንዘብ እኮ ያስፈልገናል፡፡ ምን ያህል ብዙ ሊከፍሉን የሚችሉ
ደምበኞችን አንተ ሜክሲኮ ከነበርክበት ጊዜ ላይ ስመልስ እንደነበረ ታውቃለህ
ግን!?” ብላ በቁጣ ድምፅ ጠየቀችው፡፡

“ሜክሲኮ በነበርኩበት ጊዜ ላይ እኮ በጣም ጥሩ ስራ ነበር የሰራሁት!”
ብሎ ጮኸባት እና “ቢያንስ ለዚህ ብለሽ ትንሽዬ ማበረታቻ ያስፈልገኛል”
ብሎ በድብደባው ምክንያት ወደ ጠቆሩት ዓይኖቹና ወደ አበጠው ፊቱ አመለከታት፡፡

ሎርያን ግን ሳትረታ “እነዚህ ሰዎች ገና ለመጀመሪያ ጊዜ እዚህ ቢሮ እግራቸው ሲረግጥ ስራው መጥፎ ስራ እንደሆነ ነግሬህ ነበር።”

“ብለሽኛል እንዴ?” ብሎ ዊልያምስ ትግስቱን መጨረሱን በሚያሳይ ድምፅ
“እዚህ ጋር ምንድን ነው መጥፎ ነገሩ? ገና እኮ ጉዳዩ አላላቀም፡፡ ለማንኛውም ቻርሎቴ ክላንሲ ምን እንደደረሰባት እስከማውቅ ድረስ ምርመራዬን አላቆምም፡፡ ይሄንን የእሷን ፍቅረኛም ፈልጌ እደርስበታለሁ።ወ/ሮ ባደን ከእኔ ተደብቃ የምትኖር ከመሰላት ተሳስታለች፡፡ ያሸነፉኝ ይመስላቸዋል አይደል? በፍፁም አልሸነፍምም” አላት፡፡

“እንዲህ ነው ነገሩ? ስለዚህ ዴሪክ ዊልያምስ አስብበት ደሞስ ክፍያ
የሚያስገኙ ስራዎችን እየተወ ቤተሰቡን መደገፍ ከማይፈልግ ሰው ጋር
በጋብቻ የምቆይ ይመስልሃል? በፍፁም በዚህ አይነት አካሄድ
👍4🔥1
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


...ምን ብዬ እንደምጀምር ቸገረኝ፡፡ ቁርጤን ለማወቅና የምትመልስልኝን ለመስማት ያለመጠን ጓጓሁ። ከመኪናይቱ ውስጥ የመውጣት ፍላጎት ቢኖረኝም በዚያች ወቅት ረዳቴ ስለ መሰለችኝ ሙጢኝ አልኳት፡፡ ያወራነው ተራ ወሬ ሁሉ የአንጎል መርዝ ሆኖ ተሰማኝ፡፡ በመኪናይቱ ውስጥ የነበረው ሞቃት አየር እንዳይወጣ የተገዘተ ይመስል ወበቁ ፈጀን፡፡ ተነጋገርንና ከመኪናይቱ በስተምሥራቅ ኻያ እርምጃ ያህል ርቀን ተቀመጥን፡፡ እንደ ክረምት ደመና የጠቆረና የከበደ ሐሳብ አእምሮዩ ውስጥ ማንዣበቡን ቀጠለ።

ከአንድ አስፈሪ የኑሮ ገጽታ ጋር ጔተፋጠጥኩ፡፡ የጠወለገው ፊቴና በዝምታ
የተለጎመው አፌ በውስጡ አንድ ነገር እንደሚፈራገጥ ያስረዳል፡፡ ዝምታ
የሁኔታ ምልክት ነው፡፡ ጎንበስ ብዩ እንዲት እንጓ ሠርዶ አነሣሁ፡፡ አንድ
ጫፏን በፊት ጥርሴ ኣኘክሁት። የውብነሽ ዝምታዬ ስላሳሰባት «ምን ሆነሃል?
ምነው ዝም አልክ? ለዚህ ለዚህማ እዚያው እቤትህ አትጎለተውም ነበር?
ወንደላጤነት ሰለቸህ እንዴ? በጨለማ ተጻፍኖ የሚጠብቅህ ቤት አስጠላህ
መሰል?» አለችና የጥያቄ ጋጋታ አቀረበች፡፡
አነጣጥሬ መሳት ስላልፈለግሁ ከጥርጣሬና ካልባሰ ሐሳብ እንድርቅ
ፈገግ አልኩ፡፡ «ምንም አልሆንኩ እንድ ችግርና ሐሳብ ቢያጋጥመኝማ ኖሮ
እነግርሽ ነበር፡፡ እኔ የምፈራው አንቺን ሳይሆን እኔኑ ራሴን ነው። ውድቀቴንም
ሆነ ትንሣኤዬን የማፈልቀው እኔው ነኝ፡፡ ያም ሆነ ይህ ዛሬ በእኔና በአንቺ
እንድ ትልቅ ጉዳይ ያውም ሥርና ግንድ ያለው ቁም ነገር ይወጠናል።
የያዝኩትና የተለምኩት የሕይወት ጥርጊያ የልማትም ይሁን የጥፋት ፈር የሚይዘው ከእንግዲህ ወዲያ ነው፡፡ እስከ አሁን ድረስ ለመኖርና አካባቢዩን ለመምሰል ስል በምርም በቀልድም ባያሌው አታልያለሁ፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ ግን
በቃኝ፡፡ ዘወትር ከማነጣጠር አንድ ቀን መተኮስ አለብኝ። ሐሳቤ ቢስማማሽም
ባይስማማሽም፣ ዘላቂ ሰላምንና ፍቅርን ቢፈጥርም ባይፈጥርም፣ ቢያቀራርበንም
ቢያራርቀንም ዛሬ ግን ይለይለት ብዩ ላብራራልሽ ቆርጬ ተነሥቻለሁ።
ሕይወቴን በማያቋርጥ የጨለማ ኦና ውስጥ ማዴፈን ስለማልፈልግ የብርሃን
ጭላንጭል ፍለጋ በምወጣበት ጊዜ እንደምትከተይኝና ረዳቴ እንደምትሆኝ
ርግጠኛ ነኝ፡፡ ጋን በጠጠር ይደገፋል ይባላል ብዬ ሐሳቤን ለማቀነባበር እና
በጥንካሪ ለመቀጠል ጥቂት ዝም አልኩ። ብዙ ሰው የራሱን ክብርና ዝና ለመጠበቅና ለማስከበር ሲል በኣካባቢው መጥፎ ባሕልና ልምድ የተለያየ በዴል
ይፈጽማል፡፡ በአሁኑ ዘመን በምድራችን ላይ አጥቂና ተጠቂ፣ የበላይና የበታች፡
ኃይለኛና ደካማ የሌለበት አካባቢ ይገኛል ብዬ አልገምትም፡፡ የጥቃት አፈፃፀሙ
ግን ያንዱ ካንዱ የተለየ ይሆናል፡፡ የእያንዳንዱ ሰው እስተሳሰቡና ዝንባሌው
ይለያይ እንጂ ኑሮን በየግል ዐይኑ ይመለከታታል፡፡ አስጨናቂና አስቸጋሪ ሁኔታ ሲያጋጥም ሰው ሁሉ ኑሮን በጋራ ዐይን የሚያይበት ጊዜ ደግሞ ይመጣል።
እናቴም ትሁን ወይም ሌላ ሰው በየዋህነት በቂና ትክክለኛ ምክንያት ነው
ብለው ባመኑበት ሁኔታ ተነሳሥተው ቢበድሉኝና ክፉ ነገር ቢፈጽሙብኝ ነገር
ግን ስሕተታቸውን ዐውቀው ካረሙ በጥፋታቸው ደረጃ መጠን ይቅርታ
አልነፍጋቸውም፡፡ የቅርብ ዘመዱ እንዳይጠቃበት ብሎ የሩቅ ወገኑን የሚያጠቃና የሚያሳድድም አለ፡፡ ራስ ወዳድነት ካጠቃው የኑሮና የሕይወት አባዜ የፈለቀ ድርጊት፣ የመፍትሔው አቅጣጫ ሌላ ነው። ስንዴ ስጥ አጠገብ ያረፈችውን ርግብ ገና ለገና ጠቅ ጠቅ ታደርግ ይሆናል በማለት በድንጋይ እንከነችራት የለ? በትምህርት ወይም በትክክለኛ የሕይወት ልምድ ያልበሰለ ሕሊና የሚሰጠው መፍትሔና ውሳኔ በስሕተትና በጥፋት የተሞላ ሊሆን ይችላል። የበሰለ ሰፊ ሕሊና ግን የሚሰጠው ውሳኔ ለምንና እንዴት እንደተሰጠ ጉዳዩን በቅድሚያ
አጢኖ ይመረምራል። ባልበሰለና ከመጥፎ እምነት ባርነት ነጻ ባልወጣ ሕሊና ላይ የሚወሰድ ማናቸውም ርምጃ በአጥጋቢና ፍትሐዊ ምርምር ላይ የተመሠረተ ሊሆን ይገባል።» አልኩና እንደነገሩ ከዚህም ከዚያም አያይዤ ሰፊና ያልተጣራ የሐሳብ ዝብዝብ ካቀረብኩ በኋላ ዝምታ ጎራ ውስጥ ገባሁ፡፡ ዕቃ እንደ ጣለ ሰው ኪሴን መፈተሽ ጀመርኩ፡፡ የተናገርኩት ሁሉ ዝብርቅርቅ ያለና ግራ የሚያጋባ ስለ ሆነባት «የዛሬውስ ደግሞ የጉድ ነው፣ የተናገርከው ሁሉ አማርኛ አልመስል አለኝ፡፡ ምን ለማለት እንደ ፈለግህ ኣልገባኝም፡፡ ካልግባኝ ደግሞ መልስ ለመስጠት…» አለችና ንግግሯን ሳትጨርስ ጎንበስ ብላ ትናንሽ ጠጠሮች ለቅማ ያዘች። ሐሳቤን የምሰቀስቅበት የምክንያት ስንጥር በማጣቴ ሐሳቤ አእምሮዬ ውስጥ በጻዕር ተያዘ፡፡ በጻዕር አልኩ! እንዲያውም ሊበክት ተቃረበ። በቁሜ ተርበተበትኩ። መጀመር የመጨረስን ያህል ምንኛ አስቸጋሪ ነው? ድንገት እንደ ፈነዳ እሳተ ገሞራ የሐሳቤን ረመጥና አመድ ቋቅ አልኩት።

«በወላጆቻችን ቤት በሠራተኛነት ተቀጥራ በማገልገሏና ሠርታ በማደሯ አላፍርባትም ለወደፊትም አላፍርም» ብዬ በልበ ሙሉነት ጀመር ሳደርግ
ዐይኖቿ በድንጋጤ ቦዙ፡፡ ቀጠልኩ፡፡
የምወድሽ እኅቴ በመሆንሽ ምስጢሬን
በመሐላ አላስጠብቅሽም። በእኔ ላይ የደረሰና የሚደርስ መከራ ሁሉ ያንቺም
በመሆኑ የመከራዩ ቀንበር ተጋሪ ነሽ። እስከ ዛሬ ይህን ጉዳይ ካንቺ በመደበቄና
ሳላዋይሽም በመቅረቴ እንደ ክፉ ሰው ትቆጥሪኝ ይሆናል። ጉዙ የዋለ
መንገደኛ ሲርበው ስንቁን ይፈታል' ነውና እኔም ምቹና ትክክለኛው ጊዜ
ሲደርስና ሐሳቤ አብቦ በሚያፈራበት ወቅት ምስጢሬን ላካፍልሽ በመወሰኔ
ይኸው ዛሬ ልገልጽልሽ ነው። ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ለተናገርኩት ሐሰት
ሁሉ የእኅትነት ልቦናሽ ንጹሕ ይቅርታ አይነፍገኝም» ብዬ የሚቀጥለው
ንግግሬን ሐሳብ ለማቀነባበር ያህል ትንፋሼን ዋጥኩ። ሁለተኛዉን ምዕራፍ
ከፈትኩ። ሐሳቤን ባጭሩና በቀላሉ ለማስረዳት ስል ብዙውን የኑሮ እና የችግር ውጣ ውረድ በጥቂት ቃላት ኣጠቃለልኩት፡፡

«ከስድስት ዓመታት በፊት ያውም ይበልጣል፡ በወላጆቻችን ቤት ውስጥ
ስትሠራ የነበረችው የወዲያነሽ ብዙ ሥቃይና መከራ አሳልፋለች። ዕርጉዝ ሆና
መባረሯንም ታስታውሻለሽ፡፡ ከእኛ ቤት ተባርራ ከሄደች በኋላ ልጅ ወልዳ
በመጣሏ በወንጀለኛነት ተይዛ አምስት ዓመት ተፈረደባት። ተጥሎ የተገኘው ልጅ
አሳዳጊና ሰብሳቢ ባለማግኘቱ ለዕጓለ ማውታ ተሰጠ። አሁን ግን የእስራት ጊዜዋን ጨርሳ ከወህኒ ቤት ወጥታለች፡፡ በከባድ ችግርና በኑሮ ውጣ ውረድ በመጐሳቆሏ መልኳን እንኳ ለይቶ ስላላወቃት የገዛ አባታችን በአሁኗ ባለቤቴ ላይ አምስት ዓመት እሥራት ፈርዶባት ነበር፡፡ ሕግ የጥፋተኝነት ማረሚያ እና የኃይል ሚዛን
መለኪያና መሳያ መሣሪያ በመሆኑ የሆነው ሆኗል። የገዛ ልጄን የሙት ልጅ ነው እያልኩ በመናገሬ በርህራሄ ዐይን እንድታይው አድርጌአለሁ። አስፈላጊ ተንኮልና የልብ ማራራቂያ ዘዴ ነበር። ለየወዲያነሽ ያለኝ ፍቅር ጽኑ በመሆኑ ከወህኒ ቤት እንደ ወጣች ውድና ፍቅርት ባለቤቴ ብዬ ከእርሷ ጋር ጐጆ ወጥቻለሁ፡፡የሁለታችን የፍቅር ፍሬ የሆነውና ዕጓለ ማውታ ውስጥ ያደገው ልጃችን አሁን ከእኛ ጋር እየኖረ ነው:: ከትናንት ወዲያ በመንገድ ላይ እርሷን የምትመስል ሴት ከሩቅ አየሁ ያልሽኝም የልጀ የጋሻዬነህ እናት የማፈቅራት የኑሮ ጓደኛዬ የወዲያነሽ ነች፡፡ ባጭሩ ላጠቃልልሽ፡፡ ሦስታችንም በአንድ ላይ በመኖር ላይ ነን» ብዬ ለዓመታት በምስጢር እየቋጠርኩ ያጠራቀምኩትን ሐሳብ በደቂቃዎች ውስጥ
ዘረገፍኩላት። አንድ ግዙፍ ሽክም የተራገፈልኝ ያህል በጣም ቀለለኝ፡፡ በአካባቢዩ ያለው ነገር ሁሉ ደምቆና ፈክቶ ታየኝ፡፡ የተጠራቀመ
👍5
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ድርሰት_በትክክል_ገና


....ከአንበሳ መንጋጋ ፈልቅቃ የወጣችው ሌቱና፣ በሀብቱና በሥልጣኑ ከሚያስፈራው ከባላባት ቱሬ ተሰርቃ ወደ እውነተኛ ባለቤቷ እጅ የገባችው ሌቱና፣ የወደፊት ብሩህ ተስፋዋ ጨልሞ አካሏ ከስሞና ሞራሏ
ላሽቆ የሰነበተው ሌቱና በእውነተኛ ፍቅረኛ የዕድሜ አቻዋ በሆነው በጃኖ ሙቅ ሰውነት እየተሟሟቀች በእውነተኛ የፍቅር ፀበል እየለመለመች ወደ ቀድሞ ውበቷ ወደ ቀድሞ ድምቀቷ በማዝገም ላይ ነች። ምንም እንኳ ክብረ ንፅህናዋን ለምታፈቅረው እጮኛዋ ሳይሆን እንደ ተናካሽ አውሬ ለምትፈራውና ለምትጠላው ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ መስጠቷ ቢፀፅታትም ጃኖ ግን ንፁህ ክብረ ህሊናዋንና ንፁህ ፍቅሯን እንጂ ከአቅሟ በላይ በሆነ አስገዳጅ ሁኔታ ከፍላጎቷ ውጭ በተፅእኖ ስላጣው ድንግልናዋ አልተብከነከነም፡፡ ይልቁንም ባላባት ቱሬ ሊተናኮለው የሚመጣ
ከሆነ ለመመከት ራሱን ኣዘጋጅቶ እየጠበቀ ነው። የመጀመሪያ ፍቅረኛውን በአገር ሽማግሌ አስጠይቆ ንብረቱን ሽጦ ገብሮባት በወላጆቿ አንበት እጮኛነቷ ተመስክሮለት የጋብቻቸውን ቀን በተስፋ ሲጠባበቅ በሀብቱና በሥልጣኑ ተመክቶ ነጥቆት የሄደው ባላባቱ በመሆኑ በህግም በልበትም ራሱን ለመከላከል ቁርጥ ውሳኔ ላይ ደርሶ ዘወትር ጥንቃቄ አልጎደለውም ነበር፡፡

ጃኖ ሌቱናን አቅፎ ማደር ሲጀምር ባላባት ቱሬ ደግሞ ሌቱናን
ጠልፎ ያገባት ዕለት የነበረውን ደማቅ የሠርግ ትዝታ ታቅፎ ማደር
ጀምሯል። ሠርጉ እጅግ ደማቅና የተዋጣለት ነበር፡፡ ለተዝካሩም ለጋብቻውም እንዲሆን አስቦ ያዘጋጀው ድግስ ነበር የሚመስለው። በሱ ባላባትነት
ግዛት ውስጥ የሚኖረው ህዝብ ለመታያ ላምልጃ ይዞ የመጣው የምግብ ዓይነት ጥራቱ ለጉድ ነበር፡፡ እጅ የሚያስቆረጥም ደረቅ ባህላዊ ገንፎ ኩርኩቶ! ቅቤው ከዱቄቱ የበዛና ሲነቀንቁት የሚዋልል ከገብስ የሚሰራ
ምግብ፣ ቡራዩ፣ጭኮ በቆሬ! (ከእንጨት የሚሰራ ዋንጫ መሰል ዕቃ ወደር የማይገኝለት እንደ ዳቦ የተጋገረ እርጎ በጨሌ በተለበጠ ጮጮ እየተያዘ ወደ ሰርጉ ቦታ በብዛት ጎረፈ ጭፈራው፣ ዝላዩ፣ ፉከራው ተኩሱ ሁሉ ልዩ ነበር፡፡ ድብልቅልቅ ያለ ተአምር የተባለለት ደማቅ ሰርግ...ሰርደገኞች ባላባቱ ያገባትን አለላ የመሰለች ለጋ ወጣት አይተው ውበቷን አደነቁለት፡፡ አወደሱለት። ለሚስቱም ጀግናውንና ሀብታሙን ባላባት ማግባት ዕድለኛነት መሆኑን አበሰሩላት። አሞካሹላት፡፡ ዘለሉ፡፡ ጮሁ። በዚያ ዝላይና ጭፈራ ወቅት ባላባቱ በደስታ ተውጦ ፊቱ እንደ መስታወት
ያበራ ነበር፡፡ ጌሾ የሌለበት ጠላ (ቀሪቦ) ብርዝና ጠጅ አረቂው ሁሉም እንደፍላጎቱ ያለገደብ እየጠጣ ቦረቀ። ፈነደቀ፡፡ የተጣለው ሠንጋ ብዛት እንኳንስ ለሰው ልጅ ለሰማይ አሞራም የተትረፈረፈ ሆነ።ሌቱና ግን በእያንዳንዷ ደቂቃ በእያንዳንዷ ሰኮንድ ውስጥ በሰቀቀንና በሀዘን እየሞተች፣እየኮሰመነች፣ በፀፀት እንደ በረዶ እየሟሟች፣ ጃኖን በዓይነ ህሊናዋ እያንገዋለለች ዕይኖቿ እስከሚፈርጡ ድረስ በእንባ ታለበች። “ወግ ነው ሲዳሩ
ማልቀስ” ሆነና ማልቀሷን የነፈጋት አልነበረም፡፡ በዚያው ልክ ደግሞ
ቱሬ በቀዝቃዛ ሰውነቱ ውስጥ ትኩስ ደም ለማመንጨት የሚታገልበት፣ ሌቱናን ጨምቆ ሙቀቷን የሚስብበት፣ ጥንት የዘነጋውን የብር አምባር
ሰበረልዎን” ዘፈን የሚያዘፍንበት፣ ወይኗን ሎሚዋን አሽቶ የሚመጥበት ሰዓት እየደረሰችለት እሱም በናፍቆት እየተጠባበቃት ነው። የሰዓቱን መድረስ እሱ በጉጉት የሚጠባበቀውን ያክል ሌቱና ደግሞ በተቃራኒው
ቀኑ እንዳይመሽና ብርሃኑ እንዳይጨልም እየተመኘች ነበር፡፡ ሆኖም በምኞት ለአንድ ደቂቃ እንኳን ጊዜውን ሊያራዝሙት ወይንም ሊያሳጥሩት ሳይችሉ ጊዜው በራሱ ህግና ሥርአት እየተመራ እየመሽ እየጨ ለመ ሄደ።

አዛውንቱ ቱሬ ጫጉላ ቤት ሊገባ እንደገና ወጣት ሊሆን፣ “እስቲ አሳዩን የደሙን ሸማ! እስቲ አሳዩን የደሙን ሸማ” ሊያስብል፣ የልጅ ልጁ የምትሆነውን ጨቅላ በፍትወት ተገናኝቶ የወይን ጠጅ ቀለም ያለው ደም ሊያፈስና ሌደስት ሰዓቱ እየደረሰለት ነው። ሰውነቱ የከሳው፣ አጥንቱ
በዕድሜ ብዛት የገጠጠው፣ ፊቱ መጣጣ የሆነው፣ ከቁመቱ ዘለግ ብሎ ፀጉሩ የሸበተው ቱሬ ጫጉላ ቤት ውስጥ ሌቱናን ይዟት ገባ፡፡

ሠፊ የጠፍር አልጋ ነው። ከሥሩ የጭድ ፍራሽ ከላዩ ላይ ደግሞ
የጥጥ ፍራሽ ተደርቦበታል፡፡ ከጥጥ ፍራሹ በላይ ለረጅም ጊዜ በስው ገላ የታሽ የትልቅ በሬ ቁርበት ተነጥፏል፡፡ ቡልኮው በቅቤ ቀልጦ መልኩ ወደ ጥቁር አድልቷል፡፡ ሌቱና በዱላ ሲያስፈራሩት እንደሚሸጎጥ እንስሳ ሰውነቷ ሽምቅቅ ብሎ ፈራችና ወደ ግድግዳው ጥግ ሄዳ ተወሸቀች።ቱሬ ፈገግ አለና በደራቁቻ ክርኑ ጨመደዳት፡፡ እንደተራበ አንበሳ ዘሎ ወጣባት፡፡እንደ አልቂት ከላይዋ ላይ ተጣብቆ ተልሞዘሞዘባት፡፡ ልብሶቿን አስወልቆ ያንን እንቡጥ ገላዋን በጥፍሩ ቦጠቦጠውና ብዙ ቦታ ሞነጫጨራት። ከክብረ ንፅህናዋ በፊት የገላዋ ደም ቀድሞ ፈሰሰ፡፡ ቱሬ እጅግ
ከመስገብገቡ የተነሳ በአሰቃቂ ሁኔታ እጆቿን ሰባብሮ እንደ ነብርም እንደ አሞራም አድርጎት ተቀራመታት፡፡ በጥፍሩም ከመውለቅ በተረፉት ጥቂት
ጥርሶቹና በድዱ ጭምር ታገላትና እንደምንም ብሎ የሰቆቃ ጩኸት አስጮሀት፡፡ ሌቱና ባልተሟሟቀውና ለወሲብ ባልተዘጋጀው ሰውነቷ ላይ
የተፈፀመባት ድርጊት በጦር ከመወጋት ያላነስ የስቃይ ህመም ሆኖ ሲስማት ቱሬ ደግሞ እንደምንም ተሟሙቶ ከውርደት በመዳኑና ለድል በመብቃቱ ተደስቶ ግዳይ እንዳጣለ ጀግና ኩራት ልቡን አሞቀው። አቅመ
ቢስ ሽማግሌ አድርገው የገመቱትን በሙሉ ስላሳፈራቸው በደስታ ሳቀ።አሳሳቁ ግን ከድካምና ከእርጅናው ጋር ተደማምሮ የሚያዛጋ ጅብ አስመ
ስሎት ነበር፡፡

ጃኖ ሌቱናን ከዚህ ሁሉ የሥቃይ ኑሮ ገላግሎ ከእስር ቤት ነፃ አውጥቶ በእቅፉ ውስጥ አስገብቶ እውነተኛውን የፍቅር ህይወት ማጣጣም እንድትችል የአቻነት ትኩስ ፍቅሩን ያለአንዳች ገደብ እያስኮመኮማት ነው። ባላባት ቱሬ ዳግመኛ ሊነጥቀው ቢመጣ የሚያደርገው የሞትሽረት ትንቅንቅ ከወዲሁ እየታሰበው ሌቱናን በስስት አልጠግባት አለ።እሷም ከዛሬ ነገ ወላጆቿ ከባላባቱ ጋር ተመሳጥረውና ግንባር ፈጥረው
በጃኖ ላይ አደጋ ጥለው እጄን አንጠልጥለው ለዚያ ለአውሬ መልሰው ይሰጡኛል በሚል ስጋት ተወጥራለች።በመጨረሻም ከዚህ ሁሉ ሥቃይ ከዚህ ሁሉ ጭንቀት ለማምለጥ ብርር.. ብለው አገሩን ጥለው ለመጥፋት ተመካከሩና ተስማሙ ጃኖ የቀሩት ከብቶቹን ቀስ በቀስ እንዲሸጥ ጥሪቱን ሁሉ በገንዘብ እንዲለውጥና ሰው ሳያያቸው ሹልክ ብለው በመጥፋት የወጣትነት ትኩረቱን ጉልበታቸው እስከፈቀደ ድረስ ወደ አዲስ ስፍራ ሄደው ንፁህ አየር እየተነፈሱ አዲስ የኑሮ ትግል አድርገው አዲስ የህይወት ምዕራፍ ለመጀመር ንድፍ አወጡ፡፡ በሰቀቀን ውለው ማደራቸውን እየተጠራጠሩ ከዛሬ ነገ ምን ይመጣብን ይሆን?እያሉ በፍርሃት እንቅልፍ ከማጣት ይልቅ አገሩን ለቀው ለመሰወር ቆረጡ። ይህ ከዛሬ ነገ ምን ይመጣብን ይሆን? የሚለው ጭንቀት እነርሱን ብቻ ሳይሆን የሌቱናን ወላጆች ቤት ጭምር እያርበደበደው፣ እያራወጠው ነበር፡፡ ጃኖ ሌቱናን ይዞ መግባቱ እንደተሰማ ...
👍2
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

...«አምጡት እንግዲው!» አላች ታፈሡ በልሁና መርዕድን በፈገግታ አይን እያየቻቸው።.

መርዕድ አልዘገየም፤ የመቃሚያውን ቦታ በአዲስ መልክ አበጃጀው ጫቱን ከጋዳ ውስጥ አወጣ። ያ ቤት እንደገና ነፍስ ዘራ። የጫቱ መጀመር በተለይ በታፈሡና በሔዋን እናት መካከል ተጨማሪ ውይይት እንዲፈጠር ምክንያት ሆነ።
«በልሁ» ስትል ታፈሡ መጀመሪያ ጠራችው፡፡
«አቤት»
«የሒዩ እናት ትናንት ሸዌዬ ቤት እንዳደሩ ነገሩኝ፡፡ ነገር ግን ደስ ያላቸው አልመስለኝም፡፡» አለች በተለይ የሔዋንን እናት አየት እያደረገች::

«ከፋዎት እንዴ እማማ?» ሲል ጠየቃቸው በልሁ፡፡ቢከፋኝስ የት እደርሳለሁ ብለህ የኔ ልጅ አሉ የሔዋን እናት ጉንበሰ ብለው መሬት መሬት እያዩ።
ቀድሞ ነገር በልጅዎ ቤት ለምን ይከፋዎታል? አለ በልሁ አሁንም፡፡
«ምኑን አወቅት ብለህ የኔ ልጅ! እንግዲህ እያደር ሳውቀው ይገባኝ እንደሆነ እንጂ እስታሁንስ ነገሩ ሁሉ ግራ ግብት ነው ያለኝ» አሉ የሔዋን እናት::
ታፈሡ ወደ ሔዋን አየት እያረገች ሔዩ! ለእማማ ሁሉንም ነገር
ልነግራቸው ነው ከፋሽስት አልከፋሽ የራስሽ ጉዳይ» አለቻት በመቀለድ ዓይነት
ሔዋን አንገቷን ወደ መሬት ቀበረች፡፡ እናቷ ሳይቀሩ በልሁ፣ መርዕድና ታፈሡም ያዩዋት ጀምር። በዚህ ግዜ እናቷ፣
ነውር የሆነ ነገር ሰራሽ እንዴ እመ'ዩ?» ሲሉ ጠየቋት፡፡
የእርስዎ ልጄ ነወር ልትሰራ አልተፈጠረችም::» አለች ታፈሡ እንደገና ወደ በልሁና መርዕድ ዞር ብላ «ያ ሲያስጨንቀን የነበረ ሸዋዬ ስለ ሔዋን ለወላጆቿ
የፃፈችው ደብዳቤ እኮ አልተላከልንም» አሉ አለቻቸው ሁለቱንም አየት አየት
እያረገቻቸው
«ሙት በይኝ» አለ በልሁ።
አያችሁ! ሔዩም ስትጨነቅ፣ አስቻለውም እኛም ስንታመስ የኖርነው እንዲሁ በከንቱ ኖሯል» አለችና የተፃፈው ደብዳቤ ይዘት ምን እንደነበረ ዘርዘር አድርጋ ለሔዋን እናት አሰረዳቻቸው፡፡ ሸዋዬ ያን ደብዳቤ ሔዋንን ለማስፈራራትና ለማስደንገጥ እንጂ ልትልከው እስባ እንዳልነበር እንደ አዲስ ታሰባቸው፡፡
የሔዋን እናት የደብዳቤውን ይዘት ከታፈሡ ገለፃ ከተረዱ በኋላ “ይህን ነገር እሙዬ ፈፅማው ነው ወይስ ...» ብለው ታፈሡም ሔዋንንም ሲመለከቱ ታፈሡ ራሷ ቀጠለች::
«አዩ እማማ! መቸም ሔዩም ሽዋዬም ልጆችዎ ናቸው። በእርስዎ ፊት አንዷን ወግነን ሌላዋን ብናማ ትዝብት እንደሆነ እንጂ ሌላ እንደማናተርፍ
እናውቃለን፡፡ ግን ደግሞ እውነቱን ግልጥልጥ አድርገን ልንነግርዎት እንፈልጋለን።አለቻቸው አንድ የጫት እግር ይዛ ወዝወዝ ወዝወዝ እያደረገች፡፡
«በጄ» አሏት የሔዋን እናት ለነገሩ እየጓጉ።
«ሔዩና ሽዋዬ በሚያጣላ ነገር ተጣልተው ለማስታረቅ ብዙ ጥረን ነገር ግን በሸዋዬ እምቢተኝነት ሳይሳካልን ቀረ፡፡
«ምን አጣላቸው የኔ ልጅ?»
ታፈሡ ነገሩን ከሥሩ ጀመረችላቸው በቅድሚያ እሷና ሸዋዪ የትና እንዴት እንደሚተዋወቁ ሸዋዬ ከያቤሎ
ወደ ዲላ ስትመጣ ያደረገችላትን
አቀባበለ፤ ቀጥላም የእስቻለውን ምንነትና ማንነት፤ ከእሷ ጋር የነበረውን ግንኝነትም እንዲሁ ገለፀችላቸው፡፡ በመጨረሻም የአስቻለውንና የሔዋንን ጉዳዩ
ከአጀማመሩ እስከ የወደፋት አላማቸው ድረስ አስረዳቻቸው
ለዚህ ነገር የሸዋዬ አቋም ምን ይመስል እንደነበር ችግሩን ለመፍታት የተደረገውንና ሊደርግ
የነበረውን ጥረት ሁሉ ዘረዘረቾላቸው።
የሔዋን እናት በነገሩ መመሰጣቸው የተነሳ በወሬው መሀል ቢጠሯቸው
እንኳ "ወያ" የሚሉ አይመስሉም፡። እንዲያውም እንባቸው እየመጣ በለበሱት ነጠላ ዓይናቸውን ጨመቅ ያደርጋሉ፡፡ ሔዋንንም ዞር እያሉ ስሜቷን ሲሰልሉ እንባዋ
በጉንጯ ላይ ሲፈስ ያያሉ በዚያው ልክ ሆዳቸው ይንቦጫቦጫል የእሳቸው ሁኔታ የሁሉንም ቀልብ ስቦ ሁሉም በትካዜ አስተያየት ያዩአቸዋል፡፡
ታፈሡ አሁንም የሔዋንና የሸዋዬን ለየብቻ የመኖር ምክንያት ልትጠቁማቸው ፈልጋ ሸዋዬ ሔዋንና አስቻለውን ለመለያየት ያደረገችውን ጥረትና ሔዋንም በማትፈልገው ሰው ልታስደፍራት መሞከሯን ጭምር ነገረቻቸው።
የሔዋን እናት ነገሩ ሁሉ ግርም አላቸውና «እንዴት ነው ይኸ ነገር
እሙዬ» ሲሉ በተላይ ሔዋንን እያዩ ጠየቋት፡፡ ምናልባት እሷም በሆዷ ውስጥ ያለ ነገር ካለ ብለው ብትነግራቸው ፈለጉ።
«ሔዋን ፤ ኢይዞሽ ንገሪያቸው!» አለች ታፈሡ በልጃቸው አንደበት ቢሰሙ የበለጠ ላያምኑ እንደሚችሉ በመገመት።
ሔዋን ግን አልቻለችም። ለቅሶ ቀደማትና በእናቷ “ጭን ላይ ድፍት በማለት ትንሰቀሰቅ ጀመር፡፡ እናቷም ታፈሡም ቢያባብሏት ዝም ልትል አልቻለችም በመሀል በልሁ ተቆጣት።
“እንቺ ሔዋን» አለና ከመቀመጫው ብድግ አለ፡፡ «ቀና ብለሽ ቁጭ በይ።ለምን የእናትሽን ሆድ ታባቢያለሽ?» አለና አንገቷን ደገፍ አድርጐ ቀና አደረጋት፡፡
«እናትሽ የጠየቁሽን መልሽላቸው።» አላት እንደገና።

«አ- አንቺ ን- ንገሪያት ታፈሡዪ!» አለች ሔዋን ድምጿ እየተቆራረጠ፡፡ታፈሡ ቀጠለች:: በመሀል ደሞ አንድ ችግር ተፈጠረብን እማማ። ይህ
እስቻለው ያልከዎት ወንድማችን ሳያሰበው በዘመቻ ስም በግዳጅ ወደ ኤርትራ መሄድ ግድ ሆነበት።
ይህም አጋጣሚ የተፈጠረው በሸዋዬ አማካኝነት ልጁንና
ሔዋንን ለመነጣጠል የተዶለተ ሴራ መስሉ ታየንና ሔዋን ያለ ፍላጎቷ ከመደፈሯ በፊት ማሸሽ ፈለግን። ልጁም ደሞዙን ለእሷ መተዳደርያ እንዲሆን አድርጎ ስለነበረ ከሽዋዬ ቤት ወጥታ እዚህ ቤት እንድትኖር አደረግን፡፡ በቃ ሔዋን ከሸዋዬ ቤት የወጣችብት ምስጢሩ ይህ ነው የኔ እናት» አለቻቸውና ምላሻቸውን በመጠበቅ ዓይኗን በዓይኖቻቸው ላይ ስክት አደረገቻቸው።
ለልጁ መዝመት መዘዘኛዋ ያቸው የእኔ ልጅ ናት በይኛ» አሉና የሔዋን እናት ታፈሡን ያዩዋት ጀመር።
«እውነተኛውን ነገር እግዜር ይወቅ እማማ በኛ በኩል ግን እንደዚያ
ገመትን፡፡» አለችና ታፈሡ እጆቿን ጨብጣ አገጯን በማስደገፍ የሔዋንን እናት እየተመለከተች «አስቻለው ከመስሪያ ቤት አለቃው ጋር አይስማማም ነበር። ሽዋዬ
ደግሞ ከዚያ ሰው ጥብቅ የሆነ ግንኙነት ፈጠረች፡፡ እኛም በዚህ ጉዳይ የተነጋገሩበትና በጋራ የፈጠሩት መላ ሊሆን እንደሚችል ጠረጠር።አለቻቸው
የሔዋን እናት ያላሰቡት ስሜት ተፈጠረባቸው፡፡ በግራ እጅ መዳፋቸው ጉንጫቸውን ደገፍ አድርገው «እየየ እኔ! እየየ እኔ! ..» በማለት የተሰማቸውን ሃዘን ሲገልፁ እንባቸውም ከአይናቸው ላይ ድንቡቅ ብሎ ወረደ በዚህ ጊዜ በልሁ ብድግ ብሎ ወደ ጓዳ ገባና ቀድሞ የአስቻለው አሁን ደግሞ የሔዋን ከሆነው አልጋ የራስጌ ኮመዲኖ ላይ ሁለት ትላልቅ ፎቶግራፎች ይዞ ተመለሰ አንዱ አስቻለው ለብቻው የተነሳው ሌላው ደግሞ ወደ ኤርትራ ከመሄዱ አንድ ቀን በፊት ከሔዋን ጋር በመሆን በቁም የተነሱት ነበር። ሁለቱንም ፎቶግራፎች ለሔዋን እናት እየሰጠ እዩት እማማ! «ልጁም ይህ ነበር» አላቸው።
የሔዋን እናት ፎቶግራፎቹን በጭናቸው ላይ አስቀምጠው ልክ እንደ ፊት መስታወት እያዩ በቀኝ እጃቸው ቡጢ ደረታቸውን ደስቅ ደሰቅ እያደረጉ እ - እ እ ካሉ በኋላ ዓይኔ ይፍለስ! ዓይኔ ይፍስስ! ዓይኔ ይፍሰስ» አሉና «ምነው ይኽን ጉድ ሳነልሰማ ሞቼ አርፊው ቢሆን!» በማለት ከሁንም ዓይንና አፍንጫቸውን በነጠላቸው ይጠራቸው ጀመር።
👍91
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

....ሰሞኑን ቀለሞቹ ከደረቁለት በኋላ፣ እየተመላለሰ ሲቀባ፣ ሲያስተካክል፣ ሲያበጃጅና ሲሞሽር ቆይቶ ከአምስት ቀናት ድካምና ጥንቃቄ የተሞላው
ሥራ በኋላ፣ ሦስቱን ሥላሤ ሥሎ ጨረሰ። የመጨረሻው ቀን ራቅ
ብሎ ሥዕሉን ሲመለከት ተደነቀ። ሦስቱም በሁሉም አቅጣጫ እኩልና የተመጣጠኑ ናቸው። አንድም የተዛነፈና ከቦታው ውጭ የሆነ ነገር የለም። የፊታቸው ገፅታ ፍፁም ተመሳሳይ ነው። ፊታቸው ሙሉ ለሙሉ ይታያል። በሰማያዊ፣ በቢጫ፣ በነጭና በቀይ ቀለማት አምረዋል።

ተንበርክኮ ምስጋና አቅርቦ ወጣ።

በማግስቱ፣ አለቃ ግዕዛን ከሊቀጠበብት አዳሙ፣ ከአለቃ ተክለየሱስና ከሊቀጠበብት ያሬድ ጋር መጥተው ሥዕሉን ተመለከቱ። ጥላዬ፣ከኋላቸው ቆሞ፣ በእነዚህ ታላላቅ ሠዓሊዎችና የሥዕል መምህራን ላይ ያሳደረውን ስሜት ለማወቅ ተጠባበቀ።

መምህራኑ ፈዘው ተመለከቱ፤ የሚያዩትን ማመን አቃታቸው።

አለቃ ግዕዛን፣ “ጥላዬ፣ ይኸ የፍቅር ውጤት ነው። ፍቅር ብቻ ነው ይኸን የመሰለ ሥራ ሊያሠራ ሚችለው። እስታሁን በሥራህ ደስተኛ ነበርሁ። ዛሬ ግን ይኸን የመሰለ የላቀ ሥራ ስላሳየኸኝ አከብርሃለሁ።

ይኸን የመሰለ የጥበብ ውጤት እንዳይ ዕድሜ ለሰጡኝ ሥላሤ ምስጋናዬን ሳቀርብ፣ ላንተ ደግሞ አድናቆቴን ገልጣለሁ። አንተም ሥላሤን ብቻ ሳይሆን እኔንም ነው ያከበርኸኝ። እኔን እንዳከበርኸኝ አንተን ደሞ ሥላሤ ያክብሩህ። አንተ የሥዕል ንጉሥ ነህ። ከይኸ ቀደም ማንም አልቀደመህም፣ አሁንም ሚደርስብህ የለም ወደፊትም ሚተካህ ዠግና
ሚመጣበት ግዝየ ሩቅ ነው” አሉት፣ ደብቀውና ተጠንቅቀው የያዙትን፣ለማንም ተማሪ አድረገውት የማያውቁትን ምስጋና እያዘነቡለት።

ጥላዬ እግዚሐር ይስጥልኝ ማለት ፈልጎ፣ ልሳኑ ተዘጋበት። በዝምታ
እግራቸው ሥር ተደፋ።

“ተነስ ልዥ ። ንጉሥ እሰው እግር ሥር ኣይወድቅም” አሉት።

ሊቀጠበብት አዳሙም፣ “ውነትም የሥዕል ንጉሥ ነህ። አንተ ዛሬ
ግዕዛንን ብቻ ሳይሆን ሁላችንንም ነው ያከበርኸው፣ ያኮራኸው። ውበት ማለት ይኸ እንጂ ሌላ ምን አለ? አንተ ለብዙ ተማሮች አርአያ
ትሆናለህ። ሚያሳዝነው ሥዕል እንደዝኸ ድንቅ ነገር ሁኖ ሳለ እንደ ቅኔና ዜማ በርካታ ተማሮች የሉትም። ደብረ ወርቅ እንደመጣህና ትምርት እኔጋ እንደዠመርህ፣ ውነትም የሥዕል ንጉሥ እንደምትሆን አውቄ ነበር። የናትህ ማጠን ይለምልም። ዛሬ የአለቃ ሔኖክ ነፍስም በሰማይ ቤት ትዘምራለች። ሥላሤ እጅህን ያለምልሙት” ብለው
ሊስሙት ሲጠጉት፣ ፈጠን ብሎ እግራቸውን ሳመ።

አለቃ ተክለየሱስና ሊቀጠበብት ያሬድም አድናቆትና ምስጋና
አዥጎድጎዱለት፤ ባረኩት፤ እንኳን ደስ ያለህ ብለው ሳሙት። እሱም
እግራቸውን ሳመ።

በምስክር ፊት በሥዕል ትምህርት ተመረቀ።

የመመረቂያውን አነስተኛ ድግስ እንዲቀምሱለት ሁሉንም ወደቤቱ
ይዟቸው ሄደ። እንጎች ያዘጋጀችውን ምግብ በልተው፣ አረቄ ጠጥተው አመስግነውትና መርቀውት ሊሄዱ ሲሉ፣ ሊቀጠበብት ያሬድ በድንገት
ሲቆሙ፣ ሌሎቹም ቆሙ።
ሁሉንም በተራ እየተመለከቱ፣ “በሉ ወንድሞቼ ኸመኼዳችን
በፊት አንድ ቅር ያለኝን ጉዳይ ልናገር ነው” አሉ። “ተማሪ እናታባቱ ያወጡለትን ስም እየተወ ለራሱ ስም ያወጣል። ዜማ ሲማር 'ጥዑመ ልሳን ነኝ ይላል። ቅኔ ሲማር ባሕረ ጥበብ ነኝ... ማንቴስ ነኝ ይላል።አንዳንዴም እሰበሱ ስም ይሸላለማል። ይኸ ልዣችን ግን ትሑትና የሥራ ሰው በመኾኑ ይኸው የባላገር ስሙን እንደያዘ ጥላዬ እንደተባለ
አለ። ምሥጢሩ ደግ ነው፤ ጥላ ከለላ ትኾነኛለኽ ሲሉ ማዶል አባቱ
“ጥላዬ ማለታቸው? ድንቅ ስም ነው። ግና ለእንዳንተ ያለ ጠቢብ
ዛሬ እናንተ ወንድሞቼ ኸፈቀዳችኹልኝ 'ሥሙር' ብዬዋለኹ። ደሞም አይኾንም። ሠዓሊ ተኹኖ ጥላዬ መባል ምሥጢሩ አይገጥምም። ስለዚኸ
ፊቱኑ የነበረ ወግ ነው። መምህራን ለጥበብ ልዦቻቸው ይስማማል
ያሉትን ስም ይሽልማሉ። እና ምን ትላላችኹ? ሥሙር አይዶለም
ጥላዬ?”
ሁለቱም መምህራን በአንድ ድምጽ በደስታ አደነቁት፣ “ቃለ ሕይወት ያሰማዎ ጌታዬ፤ ድንቅ ነው፤ ሥሙር ነው፤ ስሙም አሰያየሙም የተገባ ነው” ብለው አጸኑለት።”

መምህሮቹ በደስታ እያውካኩ ሲሄዱ ሸኝቷቸው እንደተመለሰ መደብ ላይ ጋደም አለ። የተዋጣለት ሥራ እንደሠራ አረጋገጠ። ሕልሙ ሁሉ
እውን ሆነ። ቋራ እያለ ወለቴን ንጉሥ ኸወሰዳት እኔ የሥዕል ንጉሥ ማልሆን? ያለውን አስታወሰ።ምኞቱ ሠመረ።

ዝናው በደብረ ወርቅ ብቻ ሳይሆን፣ አድባራቱን አልፎ መርጡለማርያም ድረስ ዘለቀ። በየደብሩ ያሉት የሥዕል መምህራን እንዲያስተምር
ገፋፉት። ዝናውን የሰሙ የአካባቢው ባላባቶች ደብራቸውን እንዲያስጌጥ ተረባረቡበት።

እሱ ግን አንዴ ለአንዱ ባላባት አድሮ መሥራት ከጀመረ ወደሌላው መሄድ ስለማይችል ለማንም አልታዘዝ አለ። በተጨማሪ፣ ሥዕል ታሪክ
ተናጋሪ፣ አስተማሪ፣ አብራሪ፣ ስሜትንና አእምሮን ቀስቃሽ እንጂ ለስም መጠሪያ ቤተክርስቲያን ማስዋቢያ ብቻ ሆኖ መወሰድ እንደሌለበት ተናገረ። በባላባቱ ዘንድ ቅሬታን አተረፈ።

ጐንደር ተመልሶ መሄድ ፈልጎ ከሀያ ዓመት በላይ በመቆየቱ
ባይተዋር የሚሆን መሰለው። ጐንደርን እንደዛ ወዶ ይህን ያህል
ርቆ መቀመጡ አልገባ አለው። ደብረ ወርቅ ብዙ አስተምራዋለች።
በርግጥም የሥዕል ንጉሥ አድርጋዋለች። ሆኖም ደብረ ወርቅ
የሕዝብ ዓይነት አይታይባትም። ደብረ ወርቅ ነዋሪዎቿን
የጐንደርን ዓይነት ታላቅነትና ግርማ ሞገስ የላትም። እንደ ጐንደር አድርጋ የመቀመጥ ባህርይ ሲኖራት፣ ጐንደር አደባባይ አውጥታ ታሟግታቸዋለች፤ የቤተክርስቲያን ምርጫ ትሰጣቸዋለች፣ ለድሆቿ
የእንፋሎት መታጠቢያ እንኳን አዘጋጅታለች።
ታዲያ ይህችን ጐንደርን እንዴት አድርጎ ለዘላለም ይተዋት? እንደ
ወለቴ የልጅነት ፍቅሩ፣ የጎልማሳ ዘመኑ ትዝታው አይደለችምን?
ጐንደር ለመሄድ ባሰበ ቁጥር፣ “እቴጌ ኸባላቸው እት ልዥ ጋር
ወዳጅነት ያዙ” የሚለውን ወሬ መርሳት ስላልቻለ ልቡ ያመነታል።
ባሏ ከሞቱ ጊዜ የቀድሞው ስሜቱ አንሰራርቶ የነበረው ዜናውን
ሲሰማ ልቡ ተሰርጉዶ ምንትዋብ ላይ ቅሬታ አድሮበታል።

በምንትዋብ ቅር መሰኘቱ ቅር የሚያሰኘው አልፎ አልፎ ደግሞ
የሚያስቀው ነገር ሆኖ አግኝቶታል ቅሬታው የመነጨው እኔ ይህን
ያህል ስለእሷ ሳስብ እሷ እንዴት ሳታስፈልገኝ ቀረች በሚል ነው።
የሚያስበው ሁሉ ተገቢ እንዳልሆነ ቢያውቅም፣ “ውነት ትወደኝ ኸነበረ እንዴት አታስፈልገኝም?” ብሎ ደግሞ በስጨት ይላል። በሌላ በኩል አፄ በካፋ ሲሞቱ ልቡ ውስጥ የተስፋ ጭላንጭል የተቀረፀበትን ጊዜ ያስብና ከት ብሎ ይስቃል። ድጋሚ ሌላ ሥዕል ሊልክላት ወሰነ።ሆኖም እንደመነኩሴው ታማኝ ሰው እንዴትና የት እንደሚያገኝ ማሰብ
አቃተው።

ቀደም ብሎ ስለአብርሃ ወሬ ይሰማ የነበረውን ያህል ባለመስማቱም በሕይወት ይኖር ይሆን እያለ መጨነቁም አልቀረም። ካንድ ሁለት
ጊዜ መልዕክት ልኮበት ሳይደርሰው ቀርቶ ይሁን ወይንም ደርሶት ዝም ብሎት እንደሆነ ለማወቅ ተቸገረ።

አንድ ቀን፣ ደብረ ወርቅ ማርያም ውስጥ የቅኔ መምህር ከሆኑት
ከመጋቤ ሥነ-ጊዮርጊስ ጋር ቤተክርስቲያኗ ግቢ ውስጥ ያለ ጥድ ስር ተቀምጠው ሲጨዋወቱ በቅርቡ ጐንደር ሄደው እንደነበር ነገሩት።

“እደብረብርሃን ሥላሤ ደርሰው ነበር?” አላቸው።

“አዎን።”

“እንዲያው መጋቤ አብርሃ ሚባል ጓደኛ ነበረኝ። መልክትም
ብልክበት አልደረሰው ሁኖ ነው መሰለኝ መልስም አልሰጠኝ።”
“አሉ። መቸም ጐንደር ኻፈራቻቸው ሊቃውንት አንዱ ናቸው ነው ሚሉ።”

ጥላዬ ደስ አለው። ጐንደር የመሄድ ፍላጎቱ ተነሳሳ።

“እንዴት ያለ ጥሩ ነገር ነገሩኝ። እኔማ ተጨንቄ ቆይቻ።”
👍10
#ምንዱባን


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

የሁለት ከዋክብት መቀራረብ

አሁን እንግዲህ ማሪየስ አድጎ የሚያስቀና መልከ መልካም ወጣት ሆኖአል፡፡ አፍንጫው ስልክክ ብሉ ከቁመቱ ዘለግ ያለና በሩቁ የሴቶች ዓይን የሚስብ ጎረምሳ ነው፡፡ ረጋ ብሎ ሲራመድ የዋህነቱ ከፊቱ ይነበባል፡፡ ጭምትና አሳቢ ከመሆኑም በላይ ለአዋቂነቱ ወደር የለውም
ማሪየስ አንደበቱ የሚጣፍጥ፣ ከንፈሩ ወለላ፣ ጥርሱ ከወተት የነጣ ፈገግታው ውሃ የሚያደርግ ስለሆነ አሟልቶ የሰጠው ወጣት ነው::

ድኅነት አኮማትሮት የተቀዳደደ ልብስ ይለብስ በነበረበት ጊዜ እንኳ ልጃገረዶች በአጠገቡ ሲያልፉ ሰርቀው እንደሚያዩት ያውቃል፡፡ እርሱ ግን አቀርቅሮ በመሄድ ይሸሻቸዋል፡፡ የለበሰው ልብስ እያዩ የሚሳለቁበት እንጂ
በውበቱ ተስበው እንደሆነ አይገነዘብም ነበር፡፡ እውነታው ግን በውበቱ በቁመናው ተማርከው ነበር የሚያፈጥጡበት::

ከሚያፈጥጡበት ሴቶች መካከል ሁለቱን ግን አይሸሽም፡፡ እነርሱ
ባለጢማምዋ አሮጊት ሠራተኛውና አንዲት መንገድ የሚያያት ልጅ ናቸው ከአንድ ዓመት በፊት ጀምሮ ዘወትር ለሽርሽር በወጣ ቁጥር የሚያያት
አንዲት ልጅ ነበረች፡፡ በየቀኑ በአንድ በተወሰነ መንገድ ሲያልፍ አንድ ጠና ያለ ስልሣ ዓመት ገደማ የሚሆነው ሽማግሌና አንዲት ልጅ ዘወትር ከአንድ ቦታ ጎን ለጎን ቁጭ ብለው ያያቸዋል፡፡ ሰውዬው ኮስተር ያለና ጡረታ የወጣ ወታደር ይመስላል:: ሀዘን ከፊቱ ላይ ይነበባል:: እርሱን ደፍሮ
ለማናገር ያስፈራል::

አብራው የምትቀመጠዋን ልጅ ማሪየስ በመጀመሪያ ያያት እለት
አሥራ ሦስት ወይም አሥራ አራት ዓመት ቢሆናት ነው ብሎ ገምቷል
በመጀመሪያ ሲያያት ይህን ያህል መልክዋ የሚስብ አልመሰለውም ነበር በኋላ ስታድግ ግን በጣም ቆንጆ ሆነችበት:: ልብስዋ የገዳም ተማሪ ዩኒፎርም ነው። ሽማግሌውና ልጅትዋ ጎን ለጎን ቁጭ ብለው ለተመለከተ አባትና ልጅ ለመሆናቸው አያጠራጥርም።

ማሪየስ በአጠገባቸው ሲያልፍ ሁለትና ሦስት ቀን ድረስ እነዚ ሰዎች ምንድን ናቸው ብሎ ራሱን ከመጠየቅ ሌላ ብዙ አልተጨነቀበትም እነርሱ ግን እንዲያውም ያዩት አይመስልም:: ሁለቱ ሲገናኙ የራሳቸው
ጨዋታ ይጫወታሉ እንጂ ለአለፈና ለአገደመ ደንታ አልነበራቸውም ልጅትዋ እየሳቀች ሳታቋርጥ ለረጅም ጊዜ ታወራላች:: ሽማግሌው
በመጠኑ ነው የሚያወራው አስተያየቱ አባት ለልጁ ያለውን ፍቅር ያመለክታል፡:

በዚያ መንገድ በየቀኑ መጓዝ እንደልምድ አድርጎ ወስዶታል፡፡ በየቀኑ በዚያ ሲያልፍ ደግሞ እነዚያን አባትና ልጅ ከተወሰነ ቦታ ተቀምጠው ያያቸዋል፡፡ ማሪየስ በመንገዱ አንድ ጊዜ ብቻ ማለፍ ሳይሆን በቀን አምስት ወይም ስድስት ጊዜም የሚያልፍበት ቀን አለ፡፡ እንግዲህ ሰዎቹን በየቀኑ
አምስት ወይም ስድስት ጊዜ ያያቸዋል ማለት ነው:: ግን ሁለቱም ወገን ሰላምታ አይለዋወጡም፡፡ እርግጥ ነው ሁለቱ ሰዎች በየቀኑ በተወሰነ
ሰዓት ከዚያች ከተወሰነች ሥፍራ ስለሚቀመጡ የማሪየስን ብቻ ሳይሆን የሌሎችም ከዚያ ሥፍራ አየር ለመቀበል የሚወጡ ተማሪዎች ዓይን መማረካቸው አልቀረም፡፡ ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል ኩርፌይራክም ይገኛል:: ማሪየስ በልጅትዋ ስለተሳበና ዘወትር የምትለብሰው ልብስ ጥቁር ስለነበር «ወት/ጥቁር»፣ አባትየው ደግሞ ብዙውን ጊዜ ነጭ ልብስ ስለሚለብስ
«ክቡር ነጭ» የሚል ስም አወጣላቸው:: ስሞቹ እየተለመዱ ስለሄዱ ተማሪዎች በዚያ ባለፉ ቁጥር «ክቡር ነጭና ወት/ ጥቁር ሥፍራ ሥፍራቸውን ይዘዋል» እያሉ ይፎትቷቸዋል፡፡

እኛም ለአገላለጽ ስለሚያመች ስለታሪካቸው ስንናገር በዚሁ ስም
እንጠራቸዋለን፡፡ ማሪየስ በየቀኑ ለአንድ ዓመት ሙሉ ሲያያቸው ክቡር ነጭን ይወዳል:: ወ/ት ጥቁርን ግን እስከዚህም አላፈቀራትም፤ ግን አይጠላትም::

በሁለተኛው ዓመት ማሪየስ ለራሱ እንኳን ግልጽ ባልሆነ ምክንያት
በዚያ መንገድ ለስድስት ወር መንሸራሸሩን ያቆማል፡፡ ከስድስት ወር በኋላ አንድ ቀን በዚያ ያልፋል:: አየሩ ጥሩ ስለነበር ማሪየስ ደስ ብሎት ነበር
የሚራመደው:: ከዚያች ከተወሰነች ሥፍራ ሲደርስ አባትና ልጅ አሁንም ከዚያች ከተወሰነች ሥፍራ ተቀምጠው ይጫወታሉ፡፡

ሲቀርባቸው በሰውዬው ላይ ምንም ለውጥ አላየም:: ልጅትዋ ግን በጣም ተለውጣለች:: በጣም ቆንጆ ሆና ታየችው:: በአጠገባቸው ሲያልፍ
አቀርቅራ ስለነበር ዓይኖችዋን ለማየት አልቻለም::

በመጀመሪያ የልጅትዋ ታላቅ እህት እንጂ እርስዋ አልመሰለችውም::
ግን እየተመላለሰ ሲያያት ራስዋ መሆንዋን አረጋገጠ፡፡ በስድስት ወር ጊዜ እጅግ ውስጥ ትልቅ ሴት መሰለች:: የደረሰችበት እድሜ እንደ አበባ የምትፈነዳበትና
አምራና ደምቃ የምትታይበት ነበር፡፡ በድንገት የጽጌረዳ አበባ መሰለች::የትናንትናዋ የዋህ ሕፃን የዛሬዋ አደገኛ ሴት ሆነች::

ቁመትዋ ብቻ አልነበረም ያደገው መልኳም ጭምር ነበር የተለወጠው:: በዝናብ ወራት ዛፎች ብዙ ቅርንጫፎችን እ
አብቅለው በመስከረምና በጥቅምት ወራት በአበቦች ቅርንጫፎቻቸውን እንደሚያጌጡ
ሁሉ ልጅትዋም በአለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በመልክ አበባ አጌጠች፥ ተዋበች::

ጥቁር ልብስዋን አውልቃ ከቀለምዋ ጋር የሚሄድ ያሸበረቀ ልብ ለበሰች:: በአጠገብዋ ሲያልፉ የምትቀባው ሽቶ ያውዳል፤ የልጅነት ጠረንዋ ልብ ይሰነጥቃል::

በሁለተኛው ቀን ማሪየስ በአጠገብዋ ሲያልፍ ቀና ብላ አየችው::የተለየ ስሜት አልሰጣትም:: ማሪየስ ሌላ ነገር እያሰበ መንገዱን ቀጠለ። አራት ወይም አምስት ጊዜ እየተመላለሰ በልጅትዋ አጠገብ አለፈ።
እንደለመደው ለመንሸራሸር ነበር እንጂ ዞር ብሎ እንኳን አላያትም፡፡

በሚቀጥሉት ቀናት የሽርሽር ሰዓቱን ጠብቆ በዚያ አለፈ፡፡ ግን ወደ እነዚያ ሁለት ሰዎች ብዙም አልዞረም:: ልጅትዋ መለዋወጥዋንና ቆንጆ
መሆንዋን ካረጋገጠ በኋላ ከወጥመድዋ እንዳይገባ ቸለል ማለቱን መረጠ።የሚያልፈው ግን እርስዋ ከምትቀመጥበት መቀመጫ በጣም ቀርቦ ነበር፡፡

በጣም ደስ የሚል ቀን ነው:: ማሪየስ ልቡን ገልጦ የተፈጥሮ ውበት ራሱን አበርክቷል፡፡ የተፈጥሮ ውበት መላ ሕሊናውን ስለያዘበት ሌላ ነገር
ከጭንቅላቱ ውስጥ ሊገባ አልቻለም:: የተፈጥሮን ውበት እያሰላሰለ በተለመደው ሥፍራ ሲያልፍ የልጅትዋና የእርሱ ዓይን ግጥም አሉ፡፡ዓይንዋ ውስጥ ምን አለ? ማሪየስ እንዲነግረን ብንጠይቀው እንኳን ሊነግረን
አይችልም:: ልብን የሚሰልብ ነገር አለው:: ግን ዓይንነቱ ያው ዓይን ነው።
ሆኖም አንድ አይነት እንግዳ የሆነ ብልጭታ አለው።

ዓይንዋን መለስ አደረገችው:: እርሱም መንገዱን ቀጠለ፡፡

ዓይንዋን ሲያየው ያ የምናውቀው ገራገሩ የልጅ ዓይን አልነበረም፡፡
ምሥጢራዊ ጥልቀት ነበረው:: ገለጥ አድርጋ ወዲያው ነው የመለሰችው፡፡

እያንዳንድዋ ወጣት ልጃገረድ የዚህ የተለየ አስተያየት የምታይበት ጊዜ አላት:: በዚያች ሰዓት ከዓይንዋ ለሚገባ ወዮለት!

ገና ምንነትዋን የማታውቅ ነፍስ የመጀመሪያ እይታ ከጎሕ መቅደድ
ጋር ይመሳሰላል፡፡ ጎሕ ሲቀድ አንድ የማይታወቅና የሚያበራ ነገር ከእንቅልፉ ሚነቃበት ሰዓት ነው:: ጎሕ ሲቀድ ያልታሰበ ውበት፧ ያልታሰበ ድምቀት ያልተጠበቀ ነገር ያሳያል፡፡ እንዲሁም የፈነዳች አበባ የምትመስል ልጃገረድ እይታ ምንም ሳይታወቅ ካልታሰበ ወጥመድ ውስጥ ልብን አጥምዶና ያልታሰበ ጭንቀት ውስጥ ወዝፎ ካልተጠበቀ መንከራተት ያደርሳል:: ይህ
👍13😁2