፩ ሃይማኖት
8.92K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
​​#አስደሳች_የድል_ዜናዎች
ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምዕናን በሙሉ!

@And_Haymanot

✦́ # ድል # በድል ይሉሃል ይሄ ነው { 5 } #የድል ዜናዎች!
ክብሩ ይስፋ ለመድኃኔ አለም ሌላ ምን እንላለን፡፡
✦́ በል እንግዲህ # ጠላት ! # እሳቱን የለኮስከው አንተ በለኮስከው እሳት የተለበለብከውም አንተ ! የተዋህዶ ማዕበል በያቅጣጫው እየተፋፋመልክ ነው!
✢́✢✢ ✞✞✞ ✢́✢✢
¶ የደቡብ ኦሞ ህዝብ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የኦረቶዶክስ
ተዋህዶ መንጋ እየተቀላቀለ መምጣታቸው።
¶ በኢትዮጵያ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት የአዲስ አበባው የፀረ
ተሃድሶ መናፍቃን ጉበኤ 2ቀናት ቀሩት ።
¶ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚደረገው ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ
የክርስቶስ ወንጌለ መንግስተ ሰማያት የማስፋፋቱ አገልግሎት
መበሰሩ ። ወጣት የተዋህዶ አናብስት ልጆችም በክርምቱ
የእርፍት ጊዜያችሁ “ዘመቻ ተዋህዶ” እንድተቀላቀሉ ጥሪ
መቅረቡ ። ዳይ ! ዳይ ! ወደስራ ! የምን መፍዘዝ ነው !
¶ በምዕራብ ኢትዮጵያ ኢሉባቡር እና በምስራቅ ኢትዮጵያ
በሐረር ከተማ የመሸገው የተሃድሶ መናፍቃን መንጋ
የመጨረሻዎቹ መሽጎች እየፈራረሱ መምጣታቸው ፡፡
¶ በናዝሬት ከተማ የተመሰረተው የአባታችን የአቡነ ገብረ
መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን እናፈርሰዋለን ያሉት ፈራርሰው
፤ሐምሌ 5/2010 ዓ.ም ሊመረቅ መሆኑን፡፡
✢́✢✢ ✞✞✞ ✢́✢✢
# 1ኛ ) #“እኛም # ጥምቀትን እና # ቤተክርስቲያንን #
እንፈልጋለን “ በሚል መርሃ ግብር ፡ በደቡብ ኦም ሐገረ ስብከት
ሊቀጳጳስ በብጹ አቡነ ዕንባቆም መሪነት ፡ በማኅበረ ቅዱሳን
ዋናው መእከል እና በአዲስ አበባ ሐገረ ስብከት ጥምረት ፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን : መላው የደቡብ
ኦሞን ማሕበረሰብ እያካለለች መታለች ፡፡በዚህ አመት መጨረሻ
የክርምት ወር ላይ ለሚደረገው በሺዎች ለሚቆጠሩ የአዳዲስ
ምዕመናን የጥምቀት እና የክርስቶስ ተክክለኛው የወንጌል
የማስፋፊያ አገልግሎት የሚውል ድጋፍ ለማሰባሰብ በሰሜን
አሜሪካ በሲያትል (Seattle , Washington ) ከተማ ታላቅ
መንፈሳዊ ጉባኤ እና የድጋፍ መርሃ ግብር በደቡብ ኦሞ ሐገረ
ስብከት ሊቀጳጳስ በብፁ አባታችን በአቡነ ዕንባቆም አስተባባሪነት
በሰሜን አሜሪካ ለሚገኙ ማኀበረ ምዕመናን ተዘጋጅቷል ።
✢́✢✢ ✞✞✞ ✢́✢✢
ምዕመኑም ለመንፈሳዊ አገልግሎቱ ጥሪ ቆርጦ ተነስተዋል፡፡
በሰሜን አሜሪካ የምትኖሩ የእምዬ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ምዕመናን በሙሉ፤ ለዚህ ሐዋርያዊ አገልግሎት የበኩላችሁን
አስተዋጾ እንድታደርጉ እና ጥምር ኮሚቴው ለሚያሰራው ከ42
በላይ አዳዲስ ሕንጻ ቤተክርስያናት ድጋፍ እንድታደረጉ
በእግዚአብሔር ፍቅር ተጠርታቿል፡፡
✢́✢✢ ✞✞✞ ✢́✢✢
# 2ኛ ) ) በመምህር ምህረተአብ አሰፋ ጀማሪነት የሚደረገው
የገጠሪቱ ኢትዮጵያ ትክክለኛው ሉተር ያልበረዘው ኦርቶዶክሳዊ
የሆነ የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌለ መንግስተ ሰማያት
የማስፋፋት አግልግሎት በይፋ ተጀምሯል፡፡ለበርካታ ወራት
ከሀገር ውጭ የነበረው መምህራችን ፤ ወገቡን በአባቶች ልብስ
ታጥቆ ወንጌለ መንግስተ ሰማያትን ገጠር ላሉ ኢትዮጵያውያን
ለማዳረስ እና መንጋውን ወደቤቱ ለመመለስ ቆርጦ ተነስቷል ፡፡
በዚህም የተዋህዶ ማዕበል(ሐራ ተዋህዶ) የየሐገረስብከቱ
ስብከተ ወንጌል ሰራተኞች ፡ የማኀበረ ቅዱሳን አባላት እና
ወጣት የሰንበት ተምህርት ቤት ተማሪዎች ድጋፍ
እንደሚታከልበት ተጠቁሟል ።፡በአዲስ አበባ እና በሰሜን
ኢትዮጵያ ያላችሁ መምህራን ለ30 ዓመታት በሀገራችን ላይ
ተጋርዶባት የነበረውን ይሄንን የ ጨለማ የምንፍቅና አዚም
በትክክለኛው ወንጌል እንድታርቁት እና የገጠሪቱ ኢትዮጵያ
ምዕመናን እንድትታደጉ ጥሪ ቀርቦላቿል ።
✢́✢✢ ✞✞✞ ✢́✢✢
በል እንግዲህ እንደ ፓስተር በግ ዋሻው የአንድ ዘመን ድሪቶ ፥
5 star ሆቴል ካልተያዘልኝ ብለክ እምቡር እምቡር በል አሉክ ፡፡
ለክርስቶስ ወንጌል ፡ ለተዋህዶ ጥሪ ና ከተባልክ! በቃ ና፡፡ቆሎ
ቆርጥምህ ፡መቃብር ቤት አድረህ ህዝቡን ወደመንጋው
መልሰው፡፡በየከተማው ያላችሁ ወጣት የተዋህዶ አናብስቶች
በኦርቶዶክሳውያን መንፈሳዊ ማሕበራት ሆናችሁ የክርምት
ጊዜያችሁን በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ለሚደረገው የተዋህዶ ማዕበል
የማስፋፋት አገልግሎት እንድትሳተፉ ጥሪ ቀርቦላችኋል፡፡
✢́✢✢ ✞✞✞ ✢́✢✢
# 3ኛ ) ከመሐል ሐገር እና ከደቡብ ኢትዮጵያ አከርካሪው
ተሰብሮ የተገነደሰው የፕሮቴስታንቱ አለም አዲሱ ታርጋ ፡
የተሃድሶ መናፍቃን “# እንደገና # ማንሰራራት” በሚል መርህ
በሰዶማዊው ፓስተር አገሰግድ ሳህሉ እየተመራ መዳረሻውን
በምዕራብ ኢትዮጵያ ኢሉባቡር ዞን በመቱ እና አከባቢው አድርጎ
የነበረ ሲሆን ይህንን ምሽግ ብርቅዬው የተዋህዶ ልጅ መምህር
ምህረተአብ አሰፋ " ወንጌልን ለገጠሪቱ ኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ
ባደረገው የተዋህዶ ዘመቻ ፤ግሪሳዎችን እንከትክታቸውን
በእግዚአብሔር ቃል መዶሻነት አውጥቷል ፡፡በመሆኑም እነ
ፓስትር አሰግድ መጦሪያችን ይሆናል ያሉት አዳራሽ በመቱ እና
አከባቢዋ ባሉ የተዋህዶ ወጣት አናብስት በትላንትናው እለት
ተዘግቷል፡፡በተሳሳተ ተምህርትም የተወሰዱ 73 ምእመናን ወደ
እናታቸው ቤት ተመልሰዋል፡፡
✢́✢✢ ✞✞✞ ✢́✢✢
የመጨረሻው የፕሮቴስታንቱ አዲሱ ታርጋ የሆነው የተሃድሶ
መናፍቃን ምሽግ በሐርር እና በአከባቢዋ በሚገኙ ከተሞች ነበር
፡፡ይህንንም ምሽግ የማኀበረ ቅዱሳን ዋናው መዕከል መምህራን
ከምዕራብ ሐረርጌ ሐገረ ስብከት ሊቃውንት እና ወጣት አናብስት
የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ጋር በፈጠሩት አስደናቂ ጥምረት
ከሰሞኑን ባዘጋጁት የተዋህዶ የወንጌል አገልግሎት ግብአተ
ምድሩን እየፈጸሙ ነው፡፡ምጽ ምጽ የፕሮቴስታንት ተላላኪ
ተኩላዎች! እግዚአብሔርን ችላችሁ ልትዋጉት??? በማይሻር
ቃሉ እንክትክታችሁን አወጣልን !
✢́✢✢ ✞✞✞ ✢́✢✢
# 4ኛ ) በናዝሬት ከተማ በመናፍቃን የወያኔ ቅጥርኛ ቡድን
በ2009 ዓ.ም ሊፈርስ የነበረው የጻድቁ አባታችን የአቡነ
ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ፡ በአከባቢው የተዋህዶ
አናብስት ተጋድሎ እና በክቡር የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት በሊቀ
ዲያቆን በአቶ ለማ መገርሳ ቀጥተኛ ፍቃድ እነሆ ሐምሌ
5/2010 ዓ.ም ታቦተ ሕጉ በታላቅ ድምቀት አዲስ ወደታነጸለት
ሕንጻ ቤክርስቲያን ይገባል፡፡የሚገርመው የአከባቢው ምዕመናን
ልጆቻቸውን ድቁንና በማስተማር ለነገይቱ የተዋህዶ
ቤተክርስቲያን ሰራዊቶቿ እንዲሆኑ እያዘጋጇቸው ነው፡፡
✢́✢✢ ✞✞✞ ✢́✢✢
# 5ኛ ) በአዲስ አበባ ሐገር ስብከት በሚገኙ የቦሌ ደብረ ሳህል
ቅዱስ ሚካኤል እና የጉለሌ እግዚአብሔር አብ ደብራት ከፊታችን
አርብ ከሰኔ 12/2010 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት
የሚቆይ የተሃድሶ መናፍቃንን ሴራ ሚያጋልጥ ታላቅ መንፈሳዊ
ጉባኤ አዘጋጅተዋል፡፡ አዲስ አበቤዎችዎች ይሰማችሁዋል!
✢́✢✢ ✞✞✞ ✢́✢✢
የቦሌው የደብረ ሳህል ቅዱስ ሚካኤል ጉባኤ በአይነቱ እስካሁን
በኢትዮጵያ ከተደረጉት ልዩ የሆነና በቀጥታ ስርጭት በyou tube
ለመላው አለም ይተላለፋል፡፡ በተለይ ለስደስት የአፍሪካ ሐገራት
የሚሆን የ ኢየሱስ ክርስቶስ ትክክለኛው የመንግስቱ ወንጌል
በቀጥታ live streaming እንደሚተላለፍ የዝግጅቱ አስተባባሪ
ኮሚቴዎች ገልጸዋል፡፡
✢́✢✢ ✞✞✞ ✢́✢✢
ይህን ላደረገ ለአባቶቻችን አምላክ ለቅድስት ድንግል ማርያም
ልጅ ለቸሩ መድኃኔ አለም ክብር ምስጋና ይድረሰው፡፡
Share ፩ ኃይማኖት share
@And_Haymanot
@And_Haymanot