✞"ማንም በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል።" ራዕ.
22፥18-20።
@And_Haymanot
የዚህ ገጸ ንባብ ትርጉም ምንድን ነው?
የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት የተጻፉት በልዩ ልዩ ዘመን በልዩ ልዩ ሰዎች በልዩ ልዩ ቦታ ነው። ለምሳሌ የሙሴ መጻሕፍት
ከጌታችን ልደት 1500 ዓመት በፊት ሲጻፉ የዮሐንስ ራዕይ ደግሞ በ 88 ዓ.ም አካባቢ ተጽፏል። በብሉይ መጻሕፍት
መካከል የኦሪት መጻሕፍት ከደብረ ሲና እስከ ከነዓን መግቢያ ባለው መንገድ ሲጻፉ ትንቢተ ዳንኤልና ትንቢተ ኤርምያስ
በባቢሎን ምርኮ ጊዜ በአሕዛብ ሀገር ተጽፈዋል። ከሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት መካከል የማቴዎስ ወንጌል በፍልስጤም፥ የማርቆስ ወንጌል በግብፅ፥ የጳውሎስ መልእክታት ደግሞ በታናሽ እስያና የአውሮፓ ከተሞች፥ የዮሐንስ ራዕይ ደግሞ በፍጥሞ ደሴት
ተጽፈዋል። ምንም እንኳን በተለያዩ ሰዎች፥ በተለያዩ ቦታዎች የተጻፉ
ቢሆኑም ቅዱሳት መጻሕፍት በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በመጻፋቸው ሐሳባቸው ሁሉ አንድ ነው። 2ኛ.ጴጥ.1፥20።
ለምክርና ለተግሣጽ፥ ልብንም ለማቅናት ተጽፈዋል። ሮሜ 13፥4፤ 2ኛ.ጢሞ.3፥15-17። በእግዚአብሔር መንፈስ ስለተጻፉ እርስ በርሳቸው አይጋጩም። በውስጣቸው ከያዙት ትምህርት መካከልም አንዳች ስህተት የለም። ሆኖም ግን እያንዳንዱ መጽሐፍ ከጸሐፊው ማንነት፥ ከተጻፈበት ምክንያት፥ ከተጻፈበት ቋንቋና ባሕል፥ ከተጻፈላቸው ሰዎችና ከተጻፈበት ዘመን አንፃር የአገላለጽ ልዩነት ሊኖረው
ይችላል። ለምሳሌ የማቴዎስ ወንጌል ጸሐፊ ማቴዎስ ሲሆን የጻፈው በዕብራይስጥ ቋንቋ በዕብራውያን ልማድ መሠረት ነው። በመሆኑም አንዳንድ ቦታዎችን ሲገልጥ ተጨማሪ ማብራሪያ አላስፈለገውም። ዕብራውያን ትንቢተ ነብያትን በሚገባ ስለሚያውቁ ከሌሎች ወንጌላውያን በተለየ ብዙ የትንቢት ቃሎችን/ወደ 150 የሚሆኑ ጥቅሶችን/ ጠቅሷል። የመጽሐፉ
ዓላማ ትምህርተ ሙሴን ለሚያውቁ አይሁድ ትምህርተ ክርስቶስ
ምን እንደሆነ መግለጥ በመሆኑ በአብዛኛው የወንጌሉ ክፍል
ከሌሎች በተለየ የጌታን ትምህርቶች ይዟል። የማርቆስ ወንጌል የተጻፈው ለሮማውያን በመሆኑ አጻጻፉ
ከማቴዎስ የተለየ ነው። ወንጌሉ የተጻፈው በላቲን ቋንቋ የዕብራውያንን ባሕል ለማያውቁ በመሆኑ አንዳንድ ቦታዎችንሲገልጥ ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥቷቸዋል። ለምሳሌ ማቴዎስ በምዕ. 3፥13-17 ስለ ጌታችን መጠመቅ
ሲገልጥ በዮርዳኖስ "ወንዝ" አይልም። "ዮርዳኖስ" እንጂ። ማርቆስ በዘመናቸው ኃያላን ነን ያሉ ለነበሩት ሮማውያን
የተጻፈ በመሆኑ የጌታችንን የተአምራትና የኃይል ሥራ በሰፊው በመጻፉ ለሮማውያን ከእነርሱ የበለጠ ኃያል መኖሩን ገልጦላቸዋል። በሌላም በኩል በሮማውያን ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ዓለምን የገዙ በንግድ፥ የሕንጻ ሥራ፥ በአስተዳደር፥ በውትድርና ወዘተ....የተጠመዱ ጊዜ የጠበባቸው በመሆናቸው ከወንጌሎች ሁሉ አጭሩና 16 ምዕራፎች ብቻ ያለውን ወንጌል
ጽፎላቸዋል። እነዚህ ሁሉ መጻሕፍት ከመጀመሪያው ጀምሮ አሁን ባለው
ሁናቴ መጽሐፍ ቅዱስ ተብለው በጥራዝ መልክ የተዘጋጁ አልነበሩም። አስቀድሞ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በብራና
በጥቅል መልክ የተቀመጡ ነበሩ። የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትም በተበታተነ መልክ ለየብቻቸው የተቀመጡ እንጂ በአንድነት የተጠረዙ አልነበሩም። ከ 2ኛው መቶ ክ/ዘመን ጀምሮ የተነሡ
መናፍቃን በሐዋርያት ስም የሐዋርያትን አስመስለው/የበርናባስ ወንጌል፥ የቶማስ ወንጌል... እያሉ/ እየጻፉ ሕዝቡን
በማወካቸው፥ አባቶች እውነተኛውን መጽሐፍ ከሐሰተኛው ለይተው ለሕዝቡ መግለጥ ግድ ሆኖባቸዋል። በመሆኑም በ 20ኛ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ በቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ አማካኝነት ለመጀመሪያ ጊዜ በ 367 ዓ.ም በጥራዝ መልክ ተዘጋጁ። ከዚህ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስን አሁን በምናየው መልክ
ማግኘት ተቻለ። ስለዚህ የዮሐንስ ወንጌላዊ "በዚህ መጽሐፍ"
ሲል በዚህ የራዕይ መጽሐፍ ማለቱ እንጂ በዚህ "የመጽሐፍ ቅዱስ" አጠቃላይ ጥራዝ ማለቱ አይደለም። ቅዱስ ዮሐንስ
ይህንንም ያለበት ምክንያት ማንም በገዛ ሥልጣኑ ትንቢትን ለመተርጎም፥ በትንቢት ላይ ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ
ሥልጣን ስለሌለው ነው። ወንጌላዊውም ከዚህ ቃል በላይ
"በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን የትንቢት ቃል ለሚሰማ ሁሉ እኔ እመሰክራለሁ" በማለት ቃሉ የሚመለከተው ትንቢቱን ብቻ እንደሆነ ገልጾታል። ራዕ. 22፥18።
እንደዚህ ዓይነት ቃል በኦሪት ዘዳግም ምዕ.4፥2 ላይም እናገኛለን። ይህ ቃል በኦሪት ዘዳግም የተጻፈው ሙሴ
ከእግዚአብሔር አግኝቶ በጻፋቸው ትእዛዛት ላይ መጨመርም
ሆነ መቀነስ ተገቢ እንዳልሆነ የሚያመለክት ነው። የመጽሐፍ
ቅዱስን አጠቃላይ ጥራዝ የሚመለከት አይደለም። ከሙሴ መጻሕፍት በኋላ የተጻፉትን መጻሕፍት በዚያ ዘመን ስላልተጻፉ ይመለከታቸዋል ማለትም አይቻልም።
❖ #ኦርቶዶክሳዊት_የተዋሕዶ_ቤተ_ክርስቲያናችን_በመጽሐፍ_ቅዱስ_ላይ_ትጨምራለች ? አንዳች! አንዳንድ ሰዎች ከላይ የተገለጸውን ቃል ባለመረዳት ቤተ ክርስቲያን የተቀበለቻቸውን ቁጥር 81
በመሆናቸው ከ 66ቱ ላይ የጨመረች ይመስላቸዋል። ቤተ ክርስቲያን የተቀበለቻቸው መጻሕፍት ያሉና የነበሩ፥ የሚኖሩም እንጂ የተጨመሩ አይደሉም። ለዚህም የያዙት ሙሉውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥራዝ አለመሆኑን የሚገልጹ አንዳንድ ምሳሌዎችን መመልከት ይቻላል።
፩. በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 4 የቃየን ሚስት ከየት እንደመጣች አይነግረንም። በዓለም ላይ የነበሩት ሰዎች ሦስት ናቸው
ይለናል። አዳም፣ ሔዋን፣ ቃየን /አቤል በመሞቱ/ ቁጥር 16 ላይ ግን "ቃየንም ሚስቱን ዐወቀ፥ ፀነሰችም" ይላል። ከየት
መጣች? ለዚህ ሙሉ መልስ የምናገኘው መጽሐፈ ኩፋሌን
ስናነብ ነው። ኩፋሌ 5፥8።
፪. በማቴ. 27፥9 ማቴዎስ የጠቀሰው የኤርምያስ ትንቢት በ 66ቱ
ውስጥ በሚገኘው ትንቢተ ኤርምያስ የለም። ታድያ ማቴዎስ ከየት አመጣው? ይህ ትንቢት የሚገኘው ከተረፈ ኤርምያስ መጽሐፍ ነው። ተረፈ ኤርምያስ 7፥31።
፫. በይሁዳ መልእክት ቁጥር 14-15 የሚነበበው የሄኖክ ትንቢት
ከየት መጣ? የተገኘው ከመጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ 1፥9 ላይ ነው።
፠ እነዚህ ከብዙ በጥቂቱ ናቸው። እናም የዮሐንስ ራእይ መልእክት ትርጉሙ ለጠቅላላው አይደለም። በዚያ ላይ ቤተ
ክርስቲያን ባለው ነገር ላይ የጨመረችው ወይም የቀነሰችው
ነገር የለም። እንዲያውም ሙሉውን መጽሐፍ ቅዱስ ምሥጢሩን
ጠብቃ ለእኛም አቆይታልናለች።
❖ #አዋልድ_መጻሕፍትን_መቀበላችን_መጽሐፍ_ቅዱሳዊ_አይደለምን?
የእግዚአብሔር ጸጋው አልተጓደለም። ጥበቡም አላለቀምና ሐዋርያትን እንዳስነሣ፥ ሊቃውንትንም እያስነሣ መጻሕፍትን አጽፏል፥ ያጽፋልም።
☞ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ያሉትን አዋልድ መጻሕፍት በቅዱሳት መጻሕፍት የተመሰለውን ምሳሌ ተርጉመው፥
የተጠቀሰውን ጥቅስ የበለጠ አብራርተው ብሉያትና ሐዲሳትን
አስማምተው የረቀቀውን አጉልተው መሠረቱን ሳይለቅ ለሰው እንደሚገባው በመተርጎም የተጻፉ ናቸው። በመሆኑም አዋልድ መጻሕፍት በእግዚአብሔር መንፈስ እስከተጻፉ ትምህርታቸውም
ከመሠረታዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር እስካልተጋጨ ድረስ ለትምህርትና ለተግሣጽ መጠቀም ከነቢያትም ከሐዋርያትም የተማርነው ትምህርት ነው።
፩. "ዳዊት ስለ ሳኦልና ስለ ልጁ ስለ ዮናታን ይህን የኀዘን ቅኔ ተቀኘ፥ የይሁዳንም ልጆች ያስተምሩ ዘንድ አዘዘ። እነሆ ይህ በያሻር መጽሐፍ ተጽፏል።" 2ኛ.ሳሙ.1፥17-18።
.....👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/565

Telegram
፩ ሃይማኖት
✞"ማንም በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል።" ራዕ.
22፥18-20። ....
፪. "የቀረውም የሰሎሞን ነገር ያደረገውም ሁሉ፥ ጥበቡም፥
እነሆ፥ በሰሎሞን ታሪክ መጽሐፍ ተጽፏል።" 1ኛ.ነገ.11፥41።
፫. "የቀረውም የኤላ ነገር፥ ያደረገውም ሁሉ፥ በእሥራኤል ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለም?" 1ኛ.ነገ.16፥14። እነዚህን ሁሉ መጻሕፍት እናነብ…