፩ ሃይማኖት
8.92K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
ድንግል ሆይ የልደትሽ ቀን ልደታችን ነው
@Konobyos
@And_Haymanot
እንኳን አደረሳችሁ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተዓምረ ማርያም ምዕራፍ 48:1-2
በተዓምረ ማርያም ላይ መናፍቃን እና አህዛብ ለሚጠይቁት ጥያቄ የተሰጠ ምላሽ
በዲ/ን ቴዎድሮስ ዘለቀ
👉 @Konobyos
👉 @And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት!
​​✞ ግንቦት ፩ እመ አምላክ ድንግል ማርያም ከኢያቄምና ከሐና ስትወለድ የሆነውን ነገር ሐዋርያው ያዕቆብ የጻፈው ጥንታዊ መጽሐፍ ሲገልጽ፡፦
@And_Haymanot
"And Joachim(ኢያቄም) said: Now I know that the Lord has been gracious unto me, and has remitted all my sins . And he went down from the temple of the Lord justified,
and departed to his own house. And her months were fulfilled, and in the ninth month Anna(ሐና) brought forth. And she said to the midwife: What have I brought forth? And she said: A girl. And said Anna: My soul has been magnified this day. And she laid her down. And the days having been fulfilled, Anna was
purified, and gave the breast to the child, and called her name Mary." The Protoevangelium of James, 5
👉 @Konobyos
👉 @And_Haymanot
​​የዛሬው ርዕሳችን

@And_Haymanot

👉 ኦርቶዶክሳውያን ለቅዱሳን ለምን ይዘምራሉ?
+++ ኦርቶዶክሳውያን ለቅዱሳን ለምን ይዘምራሉ? +++

@And_Haymanot
ክፍል ፩
ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ካሏት ብዙ መገለጫዎች አንዱና ዋነኛው ‹ምስጋና የሚገባውን› እግዚአብሔርን
ሳታቋርጥ የማመስገን አገልግሎትዋ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለማመስገን ለዓመታት የዜማ ስልት ተምረው የተመረቁ የስብሐተ እግዚአብሔር ሊቃውንት ያሏት ይህች ቤተ ክርስቲያን ዝማሬዋ ፣ማሕሌትዋና ቅዳሴዋ የሃያ አራት ሰዓታት ጊዜ የማይበቃው ፣
ለሰዓት ሲባል በንባብ እየተባለ ፣ ዜማው እያጠረ የሚተው በመሆኑ ፀሐይ በማይጠልቅበት በዘላለማዊው መንግሥት ለማመስገን ዝግጁ ሆና የምትጠባበቅ ቤተ ክርስቲያን
ያሰኛታል፡፡ ከዚህ እንደ ባሕር ጥልቅ ከሆነው ስብሐተ እግዚአብሔር ጋር የእግዚአብሔር ቅዱሳንንም በሰፊው
ታመሰግናቸዋለች፡፡ በዚህች አጭር ጽሑፍ ምስጋና የባሕርይ ገንዘቡ የሆነው
እግዚአብሔር ከሆነ ፍጡራን ለሆኑ ለቅዱሳን ሰዎች ፣ ለቅዱሳን መላእክትና ለድንግል ማርያም የሚዘመረው መዝሙርና የሚቀርበው ውዳሴ ምን ያህል ተገቢ ነው? ለቅዱሳን መዘመር
ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር ተገቢ ነው ወይ? የሚለውን እንመለከታለን፡፡
ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ሳስብ በመጽሐፍ ቅዱስ ወደር ያልተገኘለትን ዘማሪ ለመጠየቅ ወደድኩ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ በስሙ መቶ አምሳ መዝሙራት የተጻፉለት ፣ ራሱ ሰማኒያ ሰባት
መዝሙራትን የዘመረና በሥሩ ያሉ መዘምራን ደግሞ አብረውት ብዙ መዝሙራትን የዘመሩበት የዝማሬ ባለ ጠጋ ንጉሥ ዳዊትን ‹‹ #እውነት_ለፍጡራን_ምስጋና_ይገባል_ወይ ?›› ብዬ ልጠይቀው አስቤ ወደ መዝሙረ ዳዊት ገሰገስኩ፡፡ ፈጣሪ እንደ ልቤ ያለው ዳዊት የልቤን ማን እንደነገረው እንጃ የእኔን ጥያቄ ለመመለስ ቸኩሎ ጠበቀኝ፡፡ ገና የመጀመሪያው መዝሙሩን ‹‹ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሔደ ፣ በኃጢአተኞች መንገድ ያልቆመ ፣ በዋዘኞች ወንበር ያልተቀመጠ›› ብሎ ጀምሮት አገኘሁት፡፡ (መዝ. 1፡1) ዳዊት
በዚህ ዝማሬው ‹ምስጉን ነው› ያለው ፈጣሪን ነው ወይንስ ፍጡርን? እግዚአብሔርን ነው እንዳልል ‹በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል› ይላል፡፡ ስለዚህ ዳዊት ዝማሬውን የጀመረው ‹በክፉዎች ምክር ያልሔደ ፣ በኃጢአተኞች መንገድ ያልቆመ ፣
በዋዘኞች ወንበር ያልተቀመጠ›ን ሰው በማመስገን ነው፡፡ ወደ መዝሙሩ ስገባ ዳዊት ምስጋናውን ሰፋ አድርጎ ‹ለቅኖች
ምስጋና ይገባቸዋል› ‹ለችግረኛ የሚያስብ ምስጉን ነው› ‹አንተ የመረጥከው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልከው ምስጉን ነው› ‹እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ ምስጉን ነው› ‹እልልታን የሚያውቅ ሕዝብ ምስጉን ነው› ብሎ ከግለሰቦች
አልፎ ሕዝብን ሲያመሰግን አገኘሁት፡፡ ከሁሉ ያስደነቀኝ ግን ‹‹መተላለፉ የቀረችለት ፣ ኃጢአቱ የተከደነችለት ሰው ምስጉን ነው›› የሚለው ዝማሬው ነው፡፡ ኃጢአቱን እግዚአብሔር ይቅር
ያለውና በደሉን ፈጣሪ የሸፈነለት ሰው በታላቁ ዘማሪ በዳዊት አንደበት መዝሙር ከተዘመረለት በሃሳብዋ እንኳን ኃጢአትን
ስላልሠራችው ድንግል ምን ዓይነት መዝሙር ይዘመርላት ይሆን?
ንጉሥ ዳዊት ሕይወት ላላቸው ሰዎች ብቻ ዘምሮ አላቆመም ፤ለማትናገረውና ከእንጨት ከድንጋይ በሰው እጅ ለተሠራችው ከተማው ለጽዮን የእግዚአብሔር ማደሪያ በመሆንዋ ዝማሬን አዝንሞላታል፡፡
‹‹እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታል ፤ ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወድዷታል፡፡ እንዲህ ሲል ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት ፣ መርጫታለሁና በእርስዋ አድራለሁ›› ‹‹እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል ፤ የእግዚአብሔር
ከተማ ሆይ በአንቺ የከበረ ነገር ይባላል›› ‹‹በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን ፤ ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን ፤ የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል
ፈለጉብን ፤ የእግዚአብሔርን ዝማሬ እንዴት በባዕድ ምድር እንዘምራለን? ኢየሩሳሌም ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ፤ ባላስብሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ጋር ይጣበቅ ፤ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ›› ብሎ ስለ ቅድስቲቱ ከተማ ሲዘምር አገኘሁት፡፡ ከራሱ አልፎም በዙሪያው ላሉት በመዝሙሩ እንዲህ
ሲል ጥሪ አቀረበ ‹‹ጽዮንን ክበቧት በዙሪያዋም ተመላለሱ ፤ ግንቦችዋን ቁጠሩ ፤ በብርታትዋ ልባችሁን አኑሩ ፤ ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ›› የእግዚአብሔር ከተማ ጽዮንን
ለማይወድዱ ደግሞ በመዝሙሩ ‹‹ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ
ወደ ኋላቸውም ይመለሱ›› ብሎ ዘምሮአል፡፡ ዳዊት ስንት ኃጢአተኛ ሲራኮት ለሚውልና ለሚያድርባት ከተማ
የእግዚአብሔር ማደሪያው እንድትሆን እንደ መረጣት አውቆ እንዲህ ሲዘምር ማየቴ ‹መንፈስ ቅዱስ ይጸልልሻል የልዑል ኃይልም ያድርብሻል› ለተባለችዋ ቅድስት ድንግል ማርያም ‹የጌታዬ እናት ፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ፣ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ› ብዬ ለመዘመር እንድችል ኃይል የሚሠጥ ሆነልኝ፡፡ ባቢሎን በተባለ በኃጢአት ሥፍራ ሆኜ ድንግልን ባሰብኳት ጊዜ
እንዳለቅስና ‹‹ድንግል ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ባላስብሽም ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ›› ብዬ እንድዘምርላት ድፍረት ሠጠኝ፡፡ የዳዊት ሲደንቀኝ ልጁ ሰሎሞን ደግሞ ‹ከመዝሙራት ሁሉ የሚበልጥ የሰሎሞን መዝሙር› (መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን) በተባለ ውብ ድርሰቱ ከአባቱ የባሰ የመዝሙር ቅኔን ሲቀኝ
አገኘሁት፡፡ በዚህ ዝማሬው ላይ በፍቅረኛሞች መካከል የሚደረግን የፍቅር ቃል ልውውጥ ሰበብ አድርጎ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ሙሽራው ስላደረጋትና እርስዋም ‹ውዴ› ብላ
ስለምትጠራው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውብ ስንኞችን ጽፎ አገኘሁት፡፡
በዚህ ዝማሬው ላይ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውድዋ የሆነውንና ነፍስዋ የወደደችውን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስን ስትፈልገው ፣ በከተማ የሚጠብቁ ጠባቂዎች የተባሉ መላእክትን ስትጠይቅ ፣ ቤተ ክርስቲያን በቀዳም ስዑር የምትዘምረው ‹እርሱ እስኪፈልግ
ድረስ ፍቅርን እንዳታስነሡት› ብላ አልጋ በተባለ መቃብር ስለ ሰው ልጅ ፍቅር የተኛውን ክርስቶስን እርሱ ወድዶ ሞትን ድል አድርጎ እስከሚነሣ በእምነት እንዲጠብቁ ስትናገር ፣ ውዴ ወደ
ገነቱ ወረደ ብላ ነፍሳትን ይዞ ወደ ገነት ስለ መውጣቱ ስትዘምር በሰሎሞን ዝማሬ ውስጥ አገኘሁ፡፡ በዚህ ዝማሬ ላይ ሙሽራው ስለ ሙሽራዪቱ ቤተ ክርስቲያን ቅድስናና ውበት ፣ ጡቶችዋ
ስለተባሉ የቃሉ ወተት ስለሚፈስስባቸው ብሉይና ሐዲስ ኪዳን ማማር ፣ ድንቅ ቅኔ ሲዘምር አገኘሁት፡፡ በሰሎሞን መዝሙር ላይ ‹ወዳጄ ሆይ ነይ ውበቴ ሆይ ተነሽ› ‹ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም› የሚሉት
ውብ ዝማሬዎች ለፍጡር እንጂ ለፈጣሪ የቀረቡ ምስጋናዎች አይደሉም፡፡ ለዚህም ነው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህንን ውብ ዝማሬ ሁለተናዋ በቅድስና ለተዋበችው ድንግል ማርያም
መዝሙር አድርጋ የምትዘምረው፡፡ አባቱ ዳዊት ‹ልጄ ሆይ ስሚ እዪም ጆሮሽን አዘንብዪ› ብሎ ለጠራት ድንግል ልጁ ሰሎሞን ‹እኅቴ ሙሽራ ሆይ› ብሎ መዘመሩን የምንቀበለውም ከዚህ
ተነሥተን ነው፡፡ ቅዱሳንን ማመስገን በዳዊትና በሰሎሞን አላበቃም ፤
መላእክትም ለቅዱሳን ሲዘምሩ ታይተዋል፡፡ ይቆየን...
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
+++ ኦርቶዶክሳውያን ለቅዱሳን ለምን ይዘምራሉ? +++
ክፍል ፪
@And_Haymanot

..... መላእክትም ለቅዱሳን ሲዘምሩ ታይተዋል፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ‹ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ› ብሎ ለድንግል ማርያም ያቀረበው ሰላምታ ‹ከእንዴት ውለሻል› ሰላምታ ያለፈ ምስጋና አይደለምን? ለዘካርያስ ‹አንተ ከካህናት ተለይተህ የተባረክህ ነህ› ያላለው ይህ መልአክ ለድንግል ለይቶ ያቀረበው በእርግጥም ምስጋና ነበር፡፡ ስለሆነም የገብርኤልን ሰላምታ ተውሰን ድንግሊቱን ለዘወትር እናመሰግናታለን፡፡ ገብርኤል ያቀረበውን እኛ ማቅረብ አያስፈልገንም የሚሉ ሰዎች ይኖራሉ፡፡ ሆኖም ድንግሊቱ ‹ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል›
ብላ መናገርዋ ለማመስገናችን ምክንያት ነው፡፡ ‹ትውልድ ሁሉ› አለች እንጂ ሰው ሁሉ አላለችምና ከየትውልዱ የማያመሰግኗት ቢገኙ አይደንቅም ፤ ከእኛ የሚጠበቅብን እንደ ኖህ ‹በትውልዳችን ጻድቅ› ሆኖ መገኘት ብቻ ነው፡፡ መልአኩ ገብርኤል ‹ደስ ይበልሽ› ቢላትም እኛ ‹ደስ ይበልሽ› አንላትም
የሚሉ ሰዎች መላእክት ‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ› የሚሉትን እግዚአብሔርም ‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ› ለማለት እንዴት
ፈቃደኞች ሊሆኑ ይችላሉ? ለቅዱሳን የሚቀርበው ምስጋና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑን የምንደመድመው መድኃኔዓለም ክርስቶስ ራሱ ለመጥምቁ ዮሐንስ የተናገረው ምስጋና ነው፡፡ ‹‹ምን ልታዩ
ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን … እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም›› (ሉቃ. 7፡26-28) ከዚህ በላይ
ምስጋና ከየት ይመጣል? በዜማ መሆኑ ከሆነ ችግሩ በንባብ እንለዋለን።
የመጥምቁ ምስጋና በቅዱስ ገብርኤልም አንደበት ተነግሮ ነበር፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የዮሐንስን ልደት ሲገልጥ ‹‹በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል›› ብሎ ነበር ፤ ወደ መዝሙር ሲለወጥ ‹ዮም ፍስሓ ኮነ በእንተ ልደቱ ለዮሐንስ› እንደማለት ነው፡፡ አባቱ ዘካርያስ ደግሞ ‹‹አንተ ሕፃን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ›› ብሎ ነበር ይህም ‹ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል
ትሰመይ ፤ አርኩ ለመርአዊ ትሰመይ›› የሚለው መዝሙር ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዱሳን ስትዘምር ቃላትና ግጥም የምትዋሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ ‹‹ሐውፅ እምሰማይ ተክለ ሃይማኖት ፀሐይ›› (ፀሐይ ተክለ
ሃይማኖት ሆይ ከሰማይ ሆነህ ጎብኝ)
የሚል መዝሙር ቢዘመር ‹‹ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ
ፀሐይ ያበራሉ›› የሚለውን የተስፋ ቃል ይዞ ነው፡፡ (ማቴ.፲፫፥፵፫)
‹‹ጊዮርጊስ ኃያል ኮከበ ክብር›› ተብሎ ቢዘመር ‹‹ብዙዎችን ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ›› የሚለውን ይዞ ነው፡፡ (ዳን. 12፡3) ‹‹አቡነ አረጋዊ ሆይ ነፍሴ ዛሬ በአንተ ፊት የከበረች ትሁን!›› ‹‹ትክበር ነፍስየ በቅድሜከ ዮም ፤ ወባርከኒ አባ አረጋዊ›› ተብሎ ሲዘመር ብንሰማ አንድ የመቶ አለቃ በነቢዩ ኤልያስ ፊት
ተንበርክኮ ‹‹የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ነፍሴ አሁን በፊትህ የከበረች ትሁን›› ብሎ ካቀረበው ልመና ተወስዶ ነው፡፡
(2ነገሥ. 1፡13) በአንዳንድ ሥፍራ ለቅዱሳን በሚቀርቡ ምስጋናዎች ላይ ለፈጣሪ የቀረቡ የምስጋና ቃላት ተወስደው ለቅዱሳን ሲቀርቡ ይታያል፡፡ ይህንን የሚያዩ ሰዎች ቅዱሳን የተመለኩ ፣ የፈጣሪ የባሕርይ ክብሩ ለቅዱሳን የተሠጠ መስሏቸው ይተቻሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ለቅዱሳን በሚዘመሩ መዝሙራት ሁሉ ላይ የሚታረም ነገር
አያጡም፡፡ ሆኖም ይህንን ዓይነት እርማት ላድርግ ብሎ የሚነሣ
ሰው መጽሐፍ ቅዱስንም ማረም ሊኖርበት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ለእግዚአብሔር የተነገረን ቃል ለቅዱሳን ሲሠጥ በተደጋጋሚ እናገኘዋለን፡፡
ጥቂት ምሳሌዎችን እንመልከት ፡-
‹‹ገብረ መንፈስ ቅዱስ የዓለም ብርሃን ናቸው›› ሲባል ‹‹የዓለም ብርሃን ክርስቶስ ብቻ ነው›› ብሎ የሚቃወም ቢኖር ራሱ ክርስቶስ ለሐዋርያቱ ‹‹እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ ፤ ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ›› ብሏል፡፡ የእርሱ ብርሃንነት የባሕርይው የቅዱሳን ብርሃንነት ግን ከእርሱ የተሠጠ ነው ብለን እንከፍለዋለን እንጂ የቅዱሳንን ብርሃንነት አንክድም፡፡ (ማቴ. 5፡
14) አንዳንድ ምእመናን ስለ ድንግል ማርያም አማላጅነት ሲመሰክሩ
‹‹ለእመቤቴ የሚሳናት ነገር የለም›› ሲሉ የሚሰማ ሰው ራሱን እየነቀነቀ ‹የእኛ ሰው Bible ላይ ብዙ ይቀረዋል› ብሎ
ሊመጻደቅ ይችላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያውቅ ከሆነ ግን ‹‹እምነት ቢኖራችሁ የሚሳናችሁ ነገር የለም›› የሚለውን የጌታ ቃል ፣ ‹‹ኃይልን በሚሠጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ››
የሚለውን የጳውሎስ ቃል በሰማበት ጆሮው ‹ያመነችው ብፅዕት› ‹የልዑል ኃይል ያደረባት› ድንግል ‹የሚሳናት የለም ሲባል ከመቆጣት ይልቅ ለምእመናን የተሠጠውን እምነትና ማስተዋል ያደንቃል፡፡ (ማቴ. 17፡20 ፣ ፊል. 4፡13 ፣ ሉቃ.1፡35፣45)
ለእግዚአብሔር የተነገሩ ቃላት ለቅዱሳን ተደግመው ብናገኛቸው እንኳን ትርጉሙን እንረዳለን እንጂ የእግዚአብሔርን ክብር
ቅዱሳን ወሰዱ አንልም፡፡ ለምሳሌ ጌታ መጥምቁ ዮሐንስን ‹የሚያበራ መብራት ነበር ፤ በብርሃኑ ደስ ሊላችሁ ወደዳችሁ›
ሲለው ወንጌላዊው ደግሞ ‹‹እርሱ ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ ብርሃን አልነበረም›› ብሎታል፡፡ የማንን እንቀበል? የጌታችንን ንግግር ወይስ የወንጌላዊውን? ዮሐንስ ብርሃን ነው
ወይንስ አይደለም? መልሱ ግልጥ ነው ዮሐንስ ብርሃን ነው ፤ የዮሐንስ ብርሃንነት ግን ከክርስቶስ ብርሃንነት ጋር ሲተያይ
የሻማና የፀሐይ ብርሃን ያህል ነውና ብርሃን አልነበረም ተብሏል ብለን እንረዳዋለን፡፡(ዮሐ. 1፡8 ፤ 5፡35)
የእግዚአብሔርን ክብር አስጠብቃለሁ ብሎ የትርጉም ልዩነቱን ሳይረዳ ለቅዱሳን የሚቀርብን ምስጋና የመተቸት ዝንባሌ ያለው ሰው ግን ይህ አካሔዱ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚያጣላው ነው፡፡
ሰሞኑን አንዳንድ ሰዎች ‹የአዳም ፋሲካው ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ› የሚለውን ቃል በመጥቀስ እንዴት ድንግል ማርያም ፋሲካ ትባላለች ‹ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአል› ይል የለምን እንዳሉ ሰማን፡፡ ስለ እንክርዳድ ማውራት እንክርዳድን ዝነኛ
እንጂ ስንዴ ስለማያደርገው ተናጋሪዎቹን ትተን ጉዳዩን እናስተውለው፡፡
ወደ ሌላ ዝርዝር ሳንገባ አንድ ጥያቄ እናንሣ ፤ ክርስቶስ ፋሲካ ነው ወይንስ የፋሲካ በግ? ፋሲካ የሚባለው በዓሉ ነው? ወይንስ በጉ ነው? የታረደው በዓሉ ነው? ቢባል ምን ይመለሳል? "ፋሲካን እረድ" ሲል በጉን ነው (2ዜና 35:5)፣
"ይህ ፋሲካ ለእግዚአብሔር ተፈሰከ" ሲል በዓሉን ነው። (2ነገሥ 23:23)
ፋሲካ ሲል በዓሉን ከሆነ መሻገሪያ ፣ ደስታ ማለት ነውና ለድንግል ማርያምም ሊነገር ይችላል፡፡ ‹ታርዶአል› የተባለው
ግን በጉን ነውና እመቤታችንን እመ በግዑ (የበጉ እናት) እንጂ የታረደችው በግ ብለናት እንደማናውቅ ግልጥ ነው፡፡ ጨርሶ ለክርስቶስ የተነገረ ቃል ለእርስዋ ለምን ይደገማል? ከሆነ ደግሞ እስቲ የቅዱስ ጳውሎስን ንግግር እንመልከት፡-
ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ 2:20 ላይ ፡- ‹‹ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ›› ብሏል፡፡ አልፎ ተርፎም ‹‹እኔ ለዓለም
ከተሰቀልሁበት ከክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ›› ብሏል፡፡ (ገላ. 6፡14) የዚህ ንግግር ትርጉም ምንድን ነው? ቅዱስ ጳውሎስ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅሎ ነበር ማለት ነው? የተሰቀለው በቀኙ ነው
የግራው?"ለዓለም ተሰቀልኩ" እንዴት አለ? እውን ለዓለም የተሰቀለው ጳውሎስ ነውን? ክርስቶስ አይደለምን?
.......የፋሲካው ሲገርምህ ለዓለም ተሰቅዬአለሁ ያለ መጣ? ጳውሎስ የተሰቀለውን የክርስቶስን ክብር መሸፈኑ ነውን?
እንደዚያ እንዳንል ደግሞ ራሱ ጳውሎስ ‹‹ጳውሎስ ስለ እናንተ ተሰቅሎአልን? እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን›› ብሎ አሳርፎናል፡፡ (1ቆሮ 1፡13) ስለዚህ መተርጎም መብራራት
አለበት እንጂ ቃሉ ተመሳሰለ ተብሎ አይብጠለጠልም። ጫማ ይስተካከላል እንጂ እግር አይስተካከልም እንደሚባለው መስተካከል ያለበት የእኛ አረዳድ እንጂ የመጽሐፉ ቃል
አይደለም። ሐዋርያው ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ ሲል የክርስቶስን የመከራ
መንገድ ተከትያለሁ ፣ የመከራው ተሳታፊ በመሆን የክብሩ ተካፋይ እሆናለሁ ሲል ነው። "ለዓለም ተሰቅልኩ" ያለው ደግሞ
በክርስቶስ መከራ በማመኔ ለዓለማዊ የኃጢአት ሥራ ሙት ሆኜአለሁ ማለቱ ነው ብለን እናብራራለን እንጂ ጳውሎስ የጌታን ክብር ተጋፋ አንልም፡፡
ቅዱሳንን የምናመሰግናቸው የእግዚአብሔር ስለሆኑና ነቢዩ
እንዳለው "እግዚአብሔርም በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ስለሆነ ነው" ሥዕሉ ሲደነቅለት የሚበሳጭ ሠዓሊ እንደሌለ ሁሉ የእርሱ ድንቅ ሥራዎች ሆነው ፣ እርሱን አገልግለው ሲወደሱ ፈጣሪን ደስ
ይለዋል እንጂ አያዝንም። ጠርሙስ ሰብራ ሽቱን በእግሩ ላይ ላፈሰሰለች ሴት "ወንጌል በሚነገርበት ሥፍራ ሁሉ ያደረገችው ነገር ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል" ብሎ የተናገረ ጌታ
አንገታቸው ተሰብሮ ደማቸውን ስለ ስሙ ስላፈሰሱ ቅዱሳን በዓለም ሁሉ ቢነገርና ቢዘመር የሚከለክል አይደለም። (ማቴ
26:13) ምስጋና እንኳን ለቅዱሳን በሃይማኖታችን ከጸናን ለእኛም
ለደካሞቹም አልተከለከልንም ፣ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአልና :– "ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ" ቆላስ 2: 7
በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
Deaconhenokhaile@gmail.com
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
​​ለማርያም

@And_Haymanot

ለማርያም/2/ 
እንዘምራለን ለዘለዓለም/2/ 
የተዘጋች ደጅ ለዘለዓለም 
ሕዝቅኤል ብሏል  ለዘለዓለም
ንጽሕት ናት በእውነት ለዘለዓለም
በፍጹም ድንግል  ለዘለዓለም
አብነት አድርገን  ለዘለዓለም
እኛም እርሷን ለዘላለም 
በፍጹም ፍቅር አንዘምራለን /2/ 
የዋህት ርግብ ለዘለዓለም 
ሰላም አብሳሪ ለዘለዓለም 
ጨለማ ሕይወቴ ለዘለዓለም 
በርሃንን አብሪ ለዘለዓለም 
እማጸንሻለሁ ለዘለዓለም 
ድንግል ለነፍሴ ለዘለዓለም 
አደራ ቅድስት አንቺ ነሽ ዋሴ /2/ 
እጅግ የበዛ ነው ለዘለዓለም 
ያለኝ ፍቀር ለዘለዓለም 
አይወሰንም ለዘለዓለም 
አይነገርም ለዘለዓለም 
በእርሷ ደስ ይለኛል ለዘለዓለም 
ሐሴት አደርጋለሁ ለዘለዓለም 
ሰሟን እየጠራሁ እዘምራለሁ/2/ 
ነይ ነይ ስላት ለዘለዓለም 
ቀንና ሌሊት ለዘለዓለም 
አትለየኝም ለዘለዓለም 
ለእኔስ ቅርቤናት ለዘለዓለም
እጹብ እጹብ ብለው ለዘለዓለም 
እመሰገኗት ለዘለዓለም 
ክብሯን ሊገልጹት ቢያጥራቸው ቃላት /2/
ጌታ ሆይ ከአንተ ጋር ያልነበርኩበት ዘመን ብዙ ነው አንተ ግን ከእኔ ጋር ያለነበርክበት ዘመን የለም ›› ቅዱስ አውግስጢኖስ
@And_Haymanot
መልካም ዕለተ ሰንበት
👉 ታቦትን ሌሎች ሃገራት እንዴት ይጠቀሙታል ?

@And_Haymanot

የተሀድሶ መናፍቃን ታቦት በሀገራችን ብቻ ያለና ሌሎች ሀገራት በተለይም አምስቱ አብያተ ቤተክርስቲያናትም ጭምር እንደሌለ አድርገው ሲቃወሙ እንመለከታለን
✞✞ በኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት(oriental crurch) ታቦት የተለመደ ህግ ነው፡፡ ሥጋና ደሙንም የሚፈትቱት በታቦቱ ላይ ነው፡፡ ክርስቲያኖች አንድ ሊያውቁት የሚገባው ትልቁ ነገር በብሉይ ኪዳን የነበረው የታቦት አገልግሎት የበጎችና የጥጆች ደም በቅድስተ ቅዱሳን ፊት ለፊት የመሠዋት ስርዓት #ነበር፡፡ ይህም በእውነተኛ አምላካችንና መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደም ተወግዶ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ ይለናል ዕብ 9:12 የኢየሱስ ክርስቶስ ደም እኛን ከሃጢአት ሁሉ በማጠብ የቀደመውን መስዋዕት አስወግዶ እርሱ መስዋዕት ሆኖ ከብሯል፡፡፡፡ በታቦቱም ላይ የማዳኑን ምሥጢር በመግለፅ ሰዎች ሁሉ ሥጋውን በልተው ደሙን ጠጥተው እንዲድኑ ይናገራል፡፡ ዮሐ 6:54
ይህን እውነት በመያዝ ታቦት በብሉይ ኪዳን የነበረ አገልግሎትና በአዲስ ኪዳን ያለው አገልግሎት ልዩነቱን በትክክል መረዳት ያሥፈልጋል፡፡
ለምሳሌ ግብጻውያን ታቦቱን #ሉሕ ይሉታል ፅላት ሠሌዳ ማለት ነው ያለሱ ሥጋና ደሙን አይፈትቱም፡፡ የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ተብለው የሚጠሩ የግሪክ የሩሲያ፣የሮማኒያ ሌሎችም ወደ ክርስትና የተመለሱት ከአረማዊነት ስለሆነ የታቦቱን ምሥጢር አያውቁትም በታቦቱ ፈንታ ከመንበር የማይነሳ እንደ ታቦት የሚከብር የጌታ የስቅለቱ ወይም የግንዘቱ ሥዕል ያለበት የነጭ ሐር መጎናፀፊያ አላቸው፡፡ ያለሡም ሥጋና ደሙን አይፈትቱም፡፡ ይህንንም በጽርዕ "እንደምኒሲዩን" ይሉታል፡፡ "ህንየተ ታቦት" ማለት ነው፡፡ የሮማ ካቶሊኮች 'ሜንሳ' Mensa ይሉታል፡፡ ጠረጴዛ ማለት ነው፡፡ ከአምስቱ አብያተ ክርስቲያናት በቀር አዲስ ቤ/ክርስቲያን በሚሠራበት ጊዜ የአጽመ ቅዱሳን ሽራፊ እንዲቀመጥ ያዛል..... በታቦት ዙርያ ለማንበብ
👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/361

ኦርቶዶክስ መልስ አላት
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የማርያም ልጅ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የጌቶች ሁሉ ጌታ ነው
@And_Haymanot
ከዲላ፡-
የዲላ ደብረገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ን ሊቃነ ጳጳሳት ሊቃውንተ ቤ/ን ሰባኪያን ወንጌል ዘማሪያንና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት
ግንቦት 12/2010 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ይመረቃል።
የመልአኩ በረከት አይለየን
​​የፓስተሩ ጉድ
ይሄ ሰውየ አባ ጴጥሮስ ይባል የነበረ አሁን ፓስተር ሁኖ ቸርች ያቋቋመ ቦሌ አራብሳ ጎንዶሚንየም የሚኖር ዛሬ
ደግሞ በተክሊል አግብቶ ከች አለ ከምንኩስና ወደ ምንፍቅና ከምንፍቅና ወደተክሊል ቆቡን ጥሎ ክዶ በተክሊል ተዳረ ደግሞ ቦሌ አራብሳ አካባቢ የምትኖሩ ክርስቲያኖች ከዚህ ከሀዲ #ተጠበቁ
መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ሰላም ተወዳጆች በውሥጥ በጠየቃችሁን መሠረት ዛሬ ተከታታይ የውይይት መድረክን በድጋሜ ማቅረባችንን እንቀጥላለን ሙሉ ወይይቱን በ @Tewahdo_Haymanote ቻናል የምናቀርበው ሲሆን የሚለቀቁ ክፍሎችን በዙሁ ቻናል በ @And_Haymanot ሊንኩን እናቀርብላችኃለን፡፡
እነሆ ለዛሬ ክፍል ፩
@And_Haymanot
የኦርቶዶክሳዊ እና የፕሮቴስታንታዊ
የመዳን ትምህርት ልዩነት ላይ
ከፕሮቴስታንት ፓስተር ጋር የተደረገ
ውይይት…ሰው ሲያምን ‹‹ይድናል››
ወይስ ‹‹ድኗል››ይባላል? ክፍል 01/ስለ ነገረ እምነት/ July 16, 2014 at 3:57am የዚህ ጽሁፍ ዓላማ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያኖች በየመንገዱና በየቤቱ በየመስሪያ ቤቱ እና በየትምህረት ቤቱ በተደጋጋሚ ለሚነሱት የፕሮቴስታንት ጥያቄዎች ቀድመው በማወቅ መልስ ለመስጠት እንዲችሉ ማድረግ ነው፡፡ የጽሁፉ መነሻ የሶሪያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ የማስተማር መንገድ ሲሆን በውርስ ትርጉም አቀራረብ ለእኛ እንዲስማማ አድርጌ ለማቅረብ ሞክሪያለው
@Tewahdo_Haymanote
ሃና፡-ፓስተር እንዴት አለህ... ና ተቀመጥ መቼም ሰላም ነህ
ብዬ አስባለው
ፓስተር፡-እኔ በክርስቶስ ቡራኬ በጣሙን
ሰላም ነኝ ጌታ ይመስገን
ሃና፡-ዛሬ ምን እግር ጣለህ በሰላም ነው
ፓስተር፡- ሁሉም በእግዚአብሔር ጸጋ
ጥሩ እሄደ ነው፡፡ ነገር ግን እኔ ዛሬ የመጣሁት ጌታን እንደግል አዳኝ በመቀበል ድነሸ በስሙ በመጠመቅ
የመንፈስ ቅዱስን ቅባት እንድተቀቢ ነው
ሃና፡-እኔ ጌታዬን አምኜ በስሙ
ከተጠምኩ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ
ከተቀበልኩ በጣም ቆይቻለው ፓስተር፡-ጌታ ይመስገን….. ያ ግን በሕጻንነትሽ የተጠመቅሽው ነው፡፡እሱ በቂ አይደለም፡፡የእግዚአብሔር ልጅ
ለመሆን ደግሞ መጀመሪያ ካመነሽ በኋላ ነው መጠመቅ ያለብሽ በሕጻናነት
እድሜሽ ደግሞ እምነት ሊኖርሽ አይችልም…ጌታን እንደግል
አዳኝ አድርገሽ መቀበል አለብሽ ይሄ ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮ ነው
ሃና፡-መልካም……ለመነጋገር
እንዲያመቸን ቅደም ተከተል ብናስይዘው
ይሻላል ምክንያቱም አንተ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮ ነው እያልክ የምትለውን አሳብ እኔ በግሌ የምትናገረው አሳብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አለመሆኑን አሳይሃለው
ፓስተር፡- ይቻላል እሺ እንነጋገር
ሃና፡-መጀመሪያ ስለመዳን ትርጋሜ እንስጥ… ፓስተር ለአንተ መዳን ምን ማለት ነው እንዴትስ ነው የሚገኘው?
ፓስተር፡-መዳን ማለት የዘላለም
ሕይወት ማግኘት ማለት ሲሆን..ጌታ
ኢየሱስን እንደግል አዳኝ አድርጎ
የተቀበለ ሁሉ..ባመነ ጊዜ ያገኘዋል ሃና፡-መዳን ማለት የዘላለም
ሕይወት ማግኘት…. መንግስተ ሰማያትን
ለመውረስ መብቃት..መጽደቅ … ማለት
ነው ፡፡በዚህ ልዩነት የለኝንም ግን ፓስተር ሰው ስላመነ ብቻ ድኗል እንላለን ወይስ ከመዳን መንገድ ውስጥ ገብታል…ማለቴ እምነት የመዳን መንገድ ነው ወይስ የመጨረሻው የመዳን ማረጋገጫ… በሌላ መልኩ እስቲ እንየው ….ለምሳሌ አንተ ለምን መልዕክት እኔ ጋር መጣህ?
ፓስተር፡-ጌታን እንደግል አዳኝ አድርገሽ አምነሽ እንድትድኚ ነዋ
ሃና፡- አንተስ ፓስተር ድነኋል?
ፓስተር፡-ሃሌ ሉያ ጌታ ይመስገን እኔ
ድኛለው
ሃና፡- እንዴት አድረገህ?
ፓስተር፡ይሄ ይጠየቃል…ጌታን እንደግል አዳኝ አድርጌ በማንኩ ቀን ጊዜ እና ሰዓት ነዋ
ሃና፡-አንዱ ልዩነታችን ከዚህ ይጀምራል… መጽሐፍ ቅዱስ አንተ ከምትለው አሳብ የተለየ ነው
ፓስተር፡- እንዴት? ..እስቲ አስረጂኝ ሃና፡- መልካም..ይሔውልህ
መጽሐፍ ቅዱስ…ሰው ሲያምን ዳነ አይልም…
ፓስተር፡ታዲያ ምንድነው የሚለው?
ሃና፡- ይድናል ነው የሚለው
ፓስተር- ታዲያ ‹‹ዳነ›› በሚለውና
‹‹በይድናል›› መካከል ምንድነው ልዩነቱ?
ሃና፡-‹‹ዳነ›› ማለት የተጠናቀቀ ነገርን
ሲያመለክት ‹‹ይድናል›› ግን ሂደትን
ይወክላል በመሆኑም መዳን በእምነት
ቅጽበት ሳይሆን በሂደት የሚገኝ እንደሆነ
ያረጋግጣል ለማንኛውም ጥቅሶችን እንያቸው….
ፓስተር ፡- መልካም ይቻላል..ሃሌ ሉያ
ሃና፡- ‹‹ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥
ያላመነ ግን ይፈረድበታል።››በማር16፡
16 ጌታ ‹‹ይድናል›› ነው ያለው ‹‹ድናል›› አላለም… በሐዋርያት
ዘመን ወደ ክርስትና እምነት የሚገቡትን ሰዎች እንዲህ ነው መጽሐፍ
ቅዱስ የሚገልጠው ‹‹ጌታም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር››ነው የሚለው ሐዋ2፡47 ‹‹የሚድኑትን›› ነው የሚለው
‹‹‹የዳኑት›› አይልም
ፓስታር፡- የዳኑትን ነው የሚለው የእኔ
መጽሐፍ ቅዱስ
ሃና፡-ፓስተር አስጨርሰኝ..የእኔ መጽሐፍ
ቅዱስ ነው ያልከው? ፓስተር፡- አዎ
ሃና፡-ፓስተር ሲጀመር መጽሐፍ ቅዱስ
ያንተ አይደለም
ፓስተር፡-ማለት የፈለኩትን አልገባሽም
ሃና ፡-አሁን እኔ ልናገር ኋላ ታስረዳኛለህ….. ጊዜ አለን… በደንብ በሁሉም ነገር ላይ እንነጋገራለን…ምንም
የምናስቀረው ነገር አይኖርም …ዋናው
ትልቁ ነገር አንተ በእጅ ያለውን መጽሐፍ
ቅዱስ ነው…‹‹የእኔ›› እንዳልከው..ብዙ
‹‹የእኔ›› የሚባሉ ‹‹የግለሰቦች
ትርጓሜ›› የአዛነፏቸው ብዙ አይነት መጽሐፍ ቅዱሳት ተፈጥረዋል..
በእርግጠኝነት አንተ የያዝከው…
በ1927 የታተመውን GOOD NEWS BIBLE ነው አይደል
ፓስተር ፡- አዎ
ሃና - አንተ የያዝከው GOOD NEWS BIBLE were being saved >> እና
አዲሱ ዓለም አቀፍ ትርጋሜ/ New
International Version/
‹‹ who were being saved›› ቢልም
በአስራ 16ኛው ክፍለ ዘመን
የታተመውን የመጀመሪያውን ጥንታዊውን ‹‹KING JAMES
VERSION ››ብናይ እንዲህ ነው
የሚለው ‹‹ should be saved ››
ሌላም ልጨምር ሐዋርያው ቅ/ጳውሎስ
‹‹የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥
ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።››1ኛ ቆሮ 1፡18 ለእኛ ‹‹ለምንድን›› ነው ብሎ የገለጠው
‹‹ለዳንን›› አላለም በዚህ ጥቅስ ቅዱስ
ጳውሎስ ራሱን ከሚድን እንጂ ከዳነ
ወገን አድርጎ አለመግለጡን ያሳውቃል
የሚገርመው ልክ እንደቅድሙ የመጀመሪያውን‹‹KING JAMES
VERSION ››ብናይ እንዲህ ነው
የሚለው ‹‹ Who are saved›› ነገር ግን አንተ የያዝከው በ1927 የታተመውን
GOOD NEWS BIBLE ‹‹Who are
being saved›› ሲለው New International Version
ላይም በድጋሚ ‹‹who are being saved ›› ብሎ ቀይሮታል አየህ ፓስተር የእናንተ የፕሮቴስታንቱ ዓለም መጽሐፍ ቅዱስን በአዲስ ትርጋሜ ስም ለአስተምሮታችሁ ደጋፊ እንዲሆን እየበረዛችሁት ነው
ፓስተር፡-ጌታ ይገስጽሽ…. እኛ እንደዚህ
አይደለም ያደረግነው…..ሰው
እንዲረዳው በቀላል ቋንቋ ነው ትርጋሜ
የሰጠነው…. ለጌታ ክብር ይሁን
ሃና፡- መልካም ….ቀላል ትርጋሜ ማለት ‹‹ይድናል›› የሚለውን ‹‹ድናል››
በማለት በመቀየር ነው ?አየህ መጽሐፍ
ቅዱስ ሰው ሲያምን ይድናል ማለቱ
ለመዳን እምነት መጀመሪያ እንጂ
መደምደሚያ አለመሆኑን ሰው የሚድነው በሂደት እንጂ በቅጽበት ባመነ ጊዜ አለመሆኑን ያረጋግጣል…እናንተ
ግን በእምነት ብቻ የመዳን መንገድ
ይገኛል ለማለት እና እምነት የመዳን
ፍጻሜ በማስመሰል..ቅዱስ ቃሉን
‹‹ድኗል›› እያላችሁ ቀይራችሁታል
በዚህ አሳባቹ ሰው ለመዳን ማመን ብቻ በቂ ነው....ቤ/ክ በመዳን አስተዋጽኦ
ማለት….ምስጢራተ ቤ/ክ ለመዳን
ድርሻ አልባ አድርጋችሁታል
ለምሳሌ ቅዱስ ጴጥሮስ በመጀመሪያው
ቀን ስብከቱ << የጌታን ስም የሚጠራም ሁሉ ይድናል።>>የሐዋ 2:21 ነው
ያለው.. ‹‹ድናል›› አይልም…ስለሆነም መዳን ሂደት እንጂ ቅጽበታዊ ድርጊት
አይደለም
ፓስተር፡-...👇👇
👍1
ፓስተር፡-በወኅኒ ቤት ውስጥ ጠባቂው
ለጳውሎስና እና ሲላስ ‹‹እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል?›› ብሎ ለጠየቀው ‹‹በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ›› ሐዋ16፡30 አይደል ያለው
ሃና፡-መልካም ጥሩ ጥያቄ ነው…ነገር ግን ‹‹እመን…..ትድናላችሁ›› ማለት ውጤትን እንጂ ጊዜን ይገልጣል
እንዴ….ለምሳሌ አንተ ልጆችህ መዝናኛ
ውሰዱኝ ብለው ቢጠይቁ…እሺ ትሄዳላችሁ ብለህ ብትመልስ…..ቀጣዩ
የልጆችህ ጥያቄ ምን ይሆናል ብለህ
ታስባለህ
ፓስተር፡- ወደ ሽርሽር መቼ ነው
የምትወስደን ብለው ይጠይቁኛል
ሃና፡- እግዚአብሔር ይስጥልኝ….. ‹‹በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ›› ሐዋ16፡30 ማለት ‹‹ትድናላችሁ›› የሚለው ቃል በማመን መዳን የሚገኝበትን መንገድ ያመለክታል እንጂ ማመን የመዳን ጉዞ ፍጻሜን አያመለክትም፡፡
ፓስተር፡-እኔ እዚህ ላይ ጥያቄ አለኝ
ሃና፡- ጥያቄህን ቀጥል…….እኔም መልሳለው ፓስተሩ መጠየቁን ቀጥሏል እኛም ክፍል ሁለትን ማቅረባችንን እንቀጥላለን 👍
Share ማድረግ እንዳይረሳ
@And_Haymanot
@Tewahdo_Haymanote
@And_Haymanot
@Tewahdo_Haymanote
​​ገድሉ ተአምራቱ

@And_Haymanot

ገድሉ ተአምራቱ እጅግ ብዙ ነው 
ጣኦትን አዋርዶ የተሸለመው 
የተዋሕዶ ኮከብ ተክለሐዋርያ 
አባ ተክለ ሃይማኖት ዘኢትዮጵያ 
አዝ ------------------ 
ዳግማዊ ዮሐንስ ጠፈር የታጠቀ 
ንጹሕ ባህታዊ ጠላት ያስጨነቀ 
የጸጋ ዘአብ ፍሬ ዛፍ ሆኖ በቀለ 
በደብረ ሊባኖስ መናኝ አስከተለ 
አዝ --------------------- 
ደካማ መስሏቸው በአንድ እግሩ ቢያዩት 
ባላስድስት ክንፉ ጻድቁ የእኔ አባት 
እርሱስ አንበሳ ነው ትናገር ደብረ አስቦ 
ሌጌዎን ሲዋረድ እፍረት ተከናንቦ 
አዝ ----------- 
ከካህናት መካከል ኅሩይ ነው አቡዬ 
መጣው ከገዳምህ ልሳለለምህ ብዬ 
ኢትዮጵያዊው ቅዱስ አባ ተክለሃይማኖት 
ወልድ ዋሕድ ብለህ ምድሪቱን ቀደስካት 
አዝ ----------------- 
የባረከው ውኃ የረገጥከው መሬት 
ጥላህ ያረፈበት ሆንዋል ጸበል እምነት 
ኑና ተመልከቱ ድውያን ሲፈቱ 
ይሰብካል ተክለአብ ዛሬም እንደጥንቱ 
አዝ ------------------
@And_Haymanot
@And_Haymanot
aaa.jpeg
1.1 MB
የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች መንፈሳዊ ጉዞ በመርከብ....
@And_Haymanot
በቤቱ ያጽናችሁ!
ሁለት ሰዎች በአንድ ጉዳይ አብረው ይፀልያሉ አንደኛው ፀሎቱ ተመለሰለት አንደኛው ሳይመለስለት ቀረ። በዚህ ጊዜ ፀሎቱ ያልተመለሰለት ሰው "ጌታ ሆይ ሁለታችንም እኩል ፀልየን ለእርሱ ሰጥተኸው ለእኔ ከለከልኝ ለምንድ ነው?" አለው። እግዚዘብሔርም "ለእርሱ ባልሰጠው ይጠፋል፣ ላንተ ከሰጠሁህ ደግሞ ትጠፋለህ" አለው ይባላል። እግዚአብሔር ከራሳችን በላይ እኛን ያውቀናል። ለአንዳችን በመስጠት፣ አንዳችንን በመከልከል ዕድሜያችንን ያረዝመዋል። መስጠቱም መንሳቱም ሁለቱም በፍቅር ነውና በልመናችን
በፀሎታችን የአንተ ፈቃድ ይሁንልን ማለት ተገቢ ነው። ስለሁሉም የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን። አሜን!! (በሶሎሞን አያሌው)
Share
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ለመላው የተዋሕዶ ቤተሰቦች እኔ በምእራብ ሸዋ ሐገረ ስብከት በፊሊዶሮ ቅድስት ልደታ ማርያም ሰንበት ተማሪ ስሆን ለዚህ ግሩብ ተከታታዮች ቤተክርስቲያናችን ዛሬ ማለትም ግንቦት 15/2010 ዓ/ም በሙስሊም ተከባ መስጅድ ሰርተዉ ከባድ ሁኔታ ላይ እንገኛለን ዛሬም ብዙ ሕዝብ አልቋል እነሱም እናቃጥላለን ብለዉ እየፎከሩ ናቸዉ፡፡ እባካችሁ በልደታ በማርያም ቤተክርስቲያኗን እንታደግ የመጨረሻው ዘመን አስከፊ ነዉና አደራ አደራ አደራ ላልሰሙት አሰሙ፡፡ አድራሻ ኮልፌ ሰዋስወ ብርሐን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ተሻግሮ ፊሊዶሮ ቅድስት ልደታ ማርያም፡፡
@And_Haymanot
ፀልዩ በእንተ ሰላም ቤተክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ
ሐዋርያት ርትዕት በኅበ እግዚአብሔር! የሐዋርያት ጉባኤ
ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም
እንማልዳለን! (መጽሐፈ ሚስጢር)
አስተያትና መረጃን ለማቀበል
👉 @AHati_Haymanot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለይተን እንወቅ

ከተሃድሶዎች ጋር ያለንን መሰረታዊ ልዩነታችንን ካላወቅን
እንጠፋለን
@And_Haymanot
ተሃድሶዎች ማርያምን እንወዳታለን ሊሉ ይችላሉ ለማዘናጋትም ይላሉም፡፡ እንወዳታለን ስላሉ ከእምነት ያልወጡ
እንዳይመስላችሁ፡፡ መውደድ አለመውደድ አይደለም
የሚያለያየን፡፡ ማየት ያለባችሁ
ስላማላጅነቷ መመስከርና ማመናቸውን ነው ስለዘላለማዊ ድንግልናዋ መመስከርና ማመናቸውን ነው
የአዳም በደል(ጥንተ አብሶ) ያልነካት ንጽህት ዘር መሆኗን መመስከርና ማመናቸውን ነው፡፡ [ተሃድሶዎች በእነዚህ በስስቱ ነገሮች(በአማላጅነቷ፣
በዘላለማዊ ድንግልናዋ፣ ከጥንተ አብሶ ነፃ መሆኗ) በፍፁም አያምኑም ቢሞቱም አይመሰክሩም]

መውደድማ ፕሮቴስታንቶችም እንወዳታለን ይላሉ፤ ያው አለ
አይደል በጌታ የተፈጠረን ፍጡር መጥላት ስለሌለብን... 😁 😁

እናስታውስ የተሐድሶ መናፍቃን ከፕሮቴስታን ትምህርት ጋር ምንም ልዩነት የላቸውም ከእናት ተዋህዶ ትምህርት ጋርም አንድነት የላቸውም፡፡
@And_Haymanot
@And_Haymanot