፩ ሃይማኖት
8.92K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
✞ ✞ ✞ ✞ ታቦት ✞ ✞ ✞ ✞

@And_Haymanot
(((((Share በማድረግ ምላሽ ላጡት እናድርስ))))))

ታቦት ማለት ቤተ፣ አደረ ከሚለው ግዕዝ ቃል የመጣ ነው ሲሆን ታቦት የፅላተ ኪዳኑ ማደርያና የእግዚአብሔር መገለጫ ነው፡፡
ማስረጃ እንመልከት
✞ ዘጸአት 24:12
✞ ዘጸአት 25-8፤
✞ ዘጸ 25:21፤
[የምንጠቅሳቸውን ጥቅሶች ከመ/ቅዱስ እያመሳከራችሁ አንብቧቸው]
👉 ከላይ ከተገለፁት ማሥረጃዎች በመነሳት ሙሉ ሀሳቡን እንመልከት
ታቦት በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ለሙሴ በዚህ ሆኜ እገለጥላችኋለው ሲል አስር ህግጋት የተፃፈባቸውን ሁለት ፅላቶችን ሰጥቶታል፡፡ ዘፀ 24:12 ዘፀ 28:7፡፡ ታቦት እግዚአብሔር 10 ህግጋት ያሥተላለፈበት ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር የክብሩ መገለጫም ጭምር ነው፡፡ እነ ሰለሞን ሌሎችም እስራኤላውያን ለታቦት የሰገዱት በታቦት ላይ ሥላለው ህግ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር ለምህረት በሚመጣበት ጊዜ ዙፋኑ ስለሆነም ነው፡፡ ኢያ 7:6

👉 ታቦት የእግዚአብሔር ስራ እንጂ ጣኦት አይደለም፡፡

ማሥረጃ እንመልከት
✞ ዘጸ 31:18 " እግዚአብሔርም ከሙሴ ጋር በሲና ተራራ የተናገረውን በፈጸመ ጊዜ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን ከድንጋይ የሆኑ ሁለቱን የምስክር ጽላቶች ሰጠው።"
✞ ኦሪት ዘጸ 32:15፤ ሙሴም ተመለሰ፥ ሁለቱንም የምስክር ጽላቶች በእጁ ይዞ ከተራራው ወረደ፤ ጽላቶቹም በዚህና በዚያ በሁለት ወገን ተጽፎባቸው ነበር።
16፤ ጽላቶቹም የእግዚአብሔር ሥራ ነበሩ፤ ጽሕፈቱም በጽላቶች ላይ የተቀረጸባቸው የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበረ።
✞ 2ኛ ቆሮንጦስ 6፥16-17 :- ”ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና፧ ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው? የእግዚዓብሔር ታቦትንስ በጣዖት ቤት የሚያኖር ማነው?”

👉 ለታቦት የሚደረግ ስግደትነና ክብር
✞ ኢያ 7:6 ✞ ዘኊ 7:89
✞ 1ኛዜና 13:10 ✞ ዘጸ33:10
✞ ፊል 2:3 ✞1ኛሳሙ 4:5

👉የተሠበረው ታቦት ድጋሜ ሥለመሠራቱ
ሙሴ የተቀበለውን ጽላት ተሠብሯል በማለት ይህን ይጠቅሳሉ
✞ ኦሪት ዘጸአት 32፥ 19 :- ”ጥጃውንም ዘፈኑንም አየ የሙሴም ቍጣ ተቃጠለ፥ ጽላቶቹንም ከእጁ ጥሎ ከተራራው በታች ሰበራቸው። የተሠበሩትም በድጋሚ እንዲሠሩ ታዟል፡፡
✞ ኦሪት ዘዳ 10:1፤ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር። እንደ ፊተኞች ያሉትን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠርበህ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፥ ለአንተም የእንጨት ታቦት ሥራ፤
2፤ በሰበርሃቸውም በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች በእነዚህ ጽላቶች እጽፋለሁ፥ በታቦቱም ውስጥ ታደርጋቸዋለህ አለኝ። 3፤ ከግራርም እንጨት ታቦትን ሠራሁ፥ እንደ ፊተኞችም ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠረብሁ፤ ሁለቱንም ጽላቶች በእጄ ይዤ ወደ ተራራው ወጣሁ።

👉 ታቦት በኦሪት(ክርስቶስ ከመወለዱ በፊት ) እንጂ አሁን(በሐዲስ ኪዳን) አይጠቅምም ለሚሉ

መልሳችን የማቴዎስ ወንጌል 5፥17 ነው:: የማቴዎስ ወንጌል 5፥17 :- ” እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ
አታልፍም” ብሎአል ኢየሱስ ክርስቶስ:: ኦሪት ዘጸአት 27:21 :- ”አንተም መብራቱን ሁልጊዜ ያበሩት ዘንድ ለመብራት ተወቅጦ የተጠለለ ጥሩ የወይራ ዘይት እንዲያመጡልህ የእስራኤልን ልጆች እዘዛቸው። በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ታቦት ፊት ባለው መጋረጃ ውጭ
አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት እንዲበራ
ያሰናዱት በእስራኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃቸው #የዘላለም ሥርዓት ይሁን ።” ይህን ጥቅስ ስንመለከት ለልጅ ልጃቸው የዘላለም ሥርዓት ይሁን። እንጂ ለኦሪት
(ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪወለድ) ብቻ አይልም። ዳዊትም ስለታቦት በመዝሙሩ እንዲህ ብሎአል መዝሙረ ዳዊት 132:7-9 :- ”ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን ። አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት። ካህናቶችህ ጽድቅን ይልበሱ” አንድ በእግዚአብሔር ስም የሚሰራ ቤት ታቦት ሊኖረው ይገባል።
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 22:19 :- ”አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትፈልጉ ዘንድ ልባችሁንና ነፍሳችሁን ስጡ ለእግዚአብሔርም ስም
ወደሚሠራው ቤት የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦትና የእግዚአብሔርን
ንዋየ ቅድሳት ታመጡ ዘንድ ተነሥታችሁ የአምላክን የእግዚአብሔርን መቅደስ
ሥሩ። ”

👉 ታቦትን ሌሎች ሃገራት እንዴት ይጠቀሙታል ?

የተሀድሶ መናፍቃን ታቦት በሀገራችን ብቻ ያለና ሌሎች ሀገራት በተለይም አምስቱ አብያተ ቤተክርስቲያናትም ጭምር የሌለ አድርገው ሲቃወሙ እንመለከታለን
✞✞ በኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት(oriental crurch) ታቦት የተለመደ ህግ ነው፡፡ ሥጋና ደሙንም የሚፈትቱት በታቦቱ ላይ ነው፡፡
ክርስቲያኖች አንድ ሊያውቁት የሚገባው ትልቁ ነገር በብሉይ ኪዳን የነበረው የታቦት አገልግሎት የበጎችና የጥጆች ደም በቅድስተ ቅዱሳን ፊት ለፊት የመሠዋት ስርዓት ነበር፡፡ ይህም በእውነተኛ አምላካችንና መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደም ተወግዶ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ ይለናል ዕብ 9:12 የኢየሱስ ክርስቶስ ደም እኛን ከሃጢአት ሁሉ በማጠብ የቀደመውን መስዋዕት አስወግዶ እርሱ መስዋዕት ሆኖ ከብሯል፡፡ በታቦቱም ላይ የማዳኑን ምሥጢር በመግለፅ ሰዎች ሁሉ ሥጋውን በልተው ደሙን ጠጥተው እንዲድኑ ይናገራል፡፡ ዮሐ 6:54 ይህን እውነት በመያዝ ታቦት በብሉይ ኪዳን የነበረ አገልግሎትና በአዲስ ኪዳን ያለው አገልግሎት ልዩነቱን በትክክል መረዳት ያሥፈልጋል፡፡
ለምሳሌ ግብጻውያን ታቦቱን #ሉሕ ይሉታል ፅላት ሠሌዳ ማለት ነው ያለሱ ሥጋና ደሙን አይፈትቱም፡፡
የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ተብለው የሚጠሩ የግሪክ የሩሲያ፣የሮማኒያ ሌሎችም ወደ ክርስትና የተመለሱት ከአረማዊነት ስለሆነ የታቦቱን ምሥጢር አያውቁትም በታቦቱ ፈንታ ከመንበር የማይነሳ እንደ ታቦት የሚከብር የጌታ የስቅለቱ ወይም የግንዘቱ ሥዕል ያለበት የነጭ ሐር መጎናፀፊያ አላቸው፡፡ ያለሡም ሥጋና ደሙን አይፈትቱም፡፡ ይህንንም በጽርዕ "እንደምኒሲዩን" ይሉታል፡፡ "ህንየተ ታቦት" ማለት ነው፡፡ የሮማ ካቶሊኮች 'ሜንሳ' Mensa ይሉታል፡፡ ጠረጴዛ ማለት ነው፡፡ ከአምስቱ አብያተ ክርስቲያናት በቀር አዲስ ቤ/ክርስቲያን በሚሠራበት ጊዜ የአጽመ ቅዱሳን ሽራፊ እንዲቀመጥ ያዛል

👉 በሰማይም ታቦት እንዳለ የሚከተለውን በማለት ሐዋርያው ዮሐንስ በራእይ ያየውን ጽፎልናል የዮሐንስ ራእይ11:19 :- ” በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፥ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።”
ይቆየን ....
ወስብሀት ለእግዚአብሔር
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የማርያም ልጅ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ከቤቱ አይለየን
@And_Haymanot
👉 ታቦትን ሌሎች ሃገራት እንዴት ይጠቀሙታል ?

@And_Haymanot

የተሀድሶ መናፍቃን ታቦት በሀገራችን ብቻ ያለና ሌሎች ሀገራት በተለይም አምስቱ አብያተ ቤተክርስቲያናትም ጭምር እንደሌለ አድርገው ሲቃወሙ እንመለከታለን
✞✞ በኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት(oriental crurch) ታቦት የተለመደ ህግ ነው፡፡ ሥጋና ደሙንም የሚፈትቱት በታቦቱ ላይ ነው፡፡ ክርስቲያኖች አንድ ሊያውቁት የሚገባው ትልቁ ነገር በብሉይ ኪዳን የነበረው የታቦት አገልግሎት የበጎችና የጥጆች ደም በቅድስተ ቅዱሳን ፊት ለፊት የመሠዋት ስርዓት #ነበር፡፡ ይህም በእውነተኛ አምላካችንና መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደም ተወግዶ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ ይለናል ዕብ 9:12 የኢየሱስ ክርስቶስ ደም እኛን ከሃጢአት ሁሉ በማጠብ የቀደመውን መስዋዕት አስወግዶ እርሱ መስዋዕት ሆኖ ከብሯል፡፡፡፡ በታቦቱም ላይ የማዳኑን ምሥጢር በመግለፅ ሰዎች ሁሉ ሥጋውን በልተው ደሙን ጠጥተው እንዲድኑ ይናገራል፡፡ ዮሐ 6:54
ይህን እውነት በመያዝ ታቦት በብሉይ ኪዳን የነበረ አገልግሎትና በአዲስ ኪዳን ያለው አገልግሎት ልዩነቱን በትክክል መረዳት ያሥፈልጋል፡፡
ለምሳሌ ግብጻውያን ታቦቱን #ሉሕ ይሉታል ፅላት ሠሌዳ ማለት ነው ያለሱ ሥጋና ደሙን አይፈትቱም፡፡ የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ተብለው የሚጠሩ የግሪክ የሩሲያ፣የሮማኒያ ሌሎችም ወደ ክርስትና የተመለሱት ከአረማዊነት ስለሆነ የታቦቱን ምሥጢር አያውቁትም በታቦቱ ፈንታ ከመንበር የማይነሳ እንደ ታቦት የሚከብር የጌታ የስቅለቱ ወይም የግንዘቱ ሥዕል ያለበት የነጭ ሐር መጎናፀፊያ አላቸው፡፡ ያለሡም ሥጋና ደሙን አይፈትቱም፡፡ ይህንንም በጽርዕ "እንደምኒሲዩን" ይሉታል፡፡ "ህንየተ ታቦት" ማለት ነው፡፡ የሮማ ካቶሊኮች 'ሜንሳ' Mensa ይሉታል፡፡ ጠረጴዛ ማለት ነው፡፡ ከአምስቱ አብያተ ክርስቲያናት በቀር አዲስ ቤ/ክርስቲያን በሚሠራበት ጊዜ የአጽመ ቅዱሳን ሽራፊ እንዲቀመጥ ያዛል..... በታቦት ዙርያ ለማንበብ
👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/361

ኦርቶዶክስ መልስ አላት
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የማርያም ልጅ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የጌቶች ሁሉ ጌታ ነው
@And_Haymanot