፩ ሃይማኖት
8.92K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
ድኅነታችን ሂደታዊ ነው! (Our salvation is a process)
@Konobyos
ያኔ ካቶሊኪን ተቃውመውና ታደስን ብለው ሲወጡ ካህን አልነበራቸውም(ተቃውሞአቸው የተወሰነ እውነትነት ቢኖረውም)! ስለዚህ ሊኖራቸው የሚችለውን ሁለት አማራጭ ተጠቀሙ! አንድ ሁሉም ካህን ነው አሉ (ይህ ግማሽ እውነት ነው) በአንፃሩ ደሞ ሐዋርያዊ ክህነትን (አያይዞም ምስጢራት ፈፃሚነትንና የቤተ ክርስቲያን ስልጣንን (authority of the church)) ካዱ! በመሆኑም ከቤተ ክርስቲያንና ከምስጢራት ተፋቱ! ጥምቀት ፣ንሰሀ ፣ ቁርባን (ስጋ ወደሙን መቀበል) ን ሁሉ ካዱ ና "ማመን" ላይ #ብቻ የሚል በአድ ቃል በመጨመር የራሳቸው ምስል ላይ ተንጠለጠሉ! "ያመንን ጊዜ ዳንን" አሉ! መፅሐፍ ደሞ "ያመነ የተጠመቀ ይድናል" ይልባቸዋል! ያመኑ ጊዜ ከዳኑ ቀጣዩን ትዕዛዝ (መጠመቅን) ሻሩ ማለት ነው! "ያመነ የተጠመቀ" አለ እንጂ "ያመነ ወይም የተጠመቀ" አይልምና! "ያመንን ጊዜ ዳንን ካሉ" መጠመቃቸው መዳን የለበትምና የጌታን ቃል ሻሩ! "አምነን ድነናል" ካሉ በኋላ ከተጠመቁ ደሞ "ባመን ቅፅበት ዳንን" ከሚለው ትርክታቸው ጋር ተጋጩ። (አሁን አሁን አሜሪካ ውስጥ ወደ ፓስተሩ ስልክ sms በመላክ ብቻ በጥምቀት የሚገኘውን ልጅነት (አዲስ ማንነት) ማግኘት ይቻላል! የሚል ተረት ተረት ተጀምሯል! One can't make this shite up እንዲሉ ፈረንጆች ይህን አይነት ውሸት ፍነሱ ካልሰሩት በቀር ማንም አስቦ ሊዋሸው አይችልም! ማረጋገጥ ለሚፈልጉ ደሞ ከፕሮቴስታንት መምህርነት ወደ ኦርቶዶክስነት የተቀየሩትን የኮፕት ቤተ ክርስቲያን አባላት (ባል እና ሚስት) Google ላይ ፈለግ አድርጎ የሚሉትን መስማት ነው)።

የሆነው ሆኖ... ጌታን በመፈለግ ውስጥ ላሉ ወገኖች ስለ መዳናችን እንዲህ ልናስታውሳቸው እንወዳለን! "ማመንን አጋንንትም ያምናሉ"(እንዲል ቅዱስ ያዕቆብ) ከነሱ የምንለይበትን ምስጢራት በመፈፀም ጌቴን ወደ መምሰል ልናድግ ይገባል እሱም! አንድ ጊዜ በተደረገው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የቤዛነት ሥራ በማመን፡ መጠመቅ! ከመጠመቅም በኋላ ባለው አዲስ ማንነት (ክርስቶስን በጥምቀት ከለበስን በኋላ) ከሀጢአት በመራቅ በተሰናከልንም ጊዜ ሀጢአትን የማስወገድ ስልጣን ከሊቀ ካህናችን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በተቀበሉት (በተሰጣቸው) ካህናት በኩል ንሰሐ በመግባት፡ ስለ ድካማችንም መጠን ያበረቱን ዘንድ በሃይማኖት የቀደሙንን ቅዱሳን ምልጃና በረከት በመጠየቅ፡ ወደ ክቡር ሥጋውና ቅድስት ደሙን ደርሰን በፍፁም ሀሴትና ትህትና ጌታ ስለኛ የተቀበለውን መከራ እያሰብን፡ ክቡር ሥጋውን ቅድስት ደሙን በመቀበል (ስጋዬን ያልበላ ደሜን ያልጠጣ የዘለዓለም ህይወት የለውም እንዲል እራሱ ጌታ) እሱን ወደ መምሰል እንድናድግና ከሥጋና ከደሙ ተዋህደን የአካሉ ብልቶች እንድንሆን፡ ድህነታችንንም እንድንፈፅም ይገባናል! ተወዳጆች ሆይ ድኅነታችሁን በመፍራትና በመንቀጥቀጥ እንፈፅም እንጂ ለሥጋ በተመቸ መሸንገል "ባመንኩ ጊዜ ዳንኩ" በማለት አይሁን!
Perfect your salivation!

የጌታ ምህረት የእናቱና የቅዱሳኑ ምልጃና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን!/ካሌብ ብርሃኑ/
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ላመስግንህ የኔ ጌታ
ላመስግንህ የኔ ጌታ ላመስግንህ
ልቀኝልህ የኔ ጌታ ልቀኝልህ
ህይወቴ ነው ዝማሬዬ ትሩፋቴ
የሰጠኸኝ እንዳከብርህ አንተ አባቴ
...................................................
ከኔ የሆነ የምሰጥህ ባይኖረኝም
ከሰጠኸኝ የአንተን መስጠት አይከብደኝም
ጥበቤ ነህ የምስጋና መሰረቴ
ዝማሬዬን ያፈሰከው በህይወቴ
አንደበቴን የቃኘኸው ለምስጋና
ይኸው ውሰድ ቅኝትህን እንደገና/2/
.......................................................
ባዶ እኮ ነኝ የኔ ጌታ ምን ልቅዳልህ
በእጄ ላይ አንዳች የለኝ የምሰጥህ
ላንተ ክብር የሚመጥን ህይወት የለኝ
ዝማሬዬን በቸርነት ተቀበለኝ
አንደበቴን የቃኘኸው ለምስጋና
ይኸው ውሰድ ቅኝትህን እንደገና
@And_Haymanot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#_ለመዳን_ኃይማኖት_ያስፈልጋል
ኃይማኖት ቡድን ነውን?
ኃይማኖት ለምን አይታደስም?
ወንጌል እና ኃይማኖት
Faith እና religion እንዴት ይታያል?
ኢየሱስ ክርስቶስ የጌቶች ሁሉ ጌታ ነው፡፡
በዲ/ን ቴዎድሮስ ዘለቀ
ሌሎች ምላሾችን ለማግኘት
👉 @And_Haymanot
👉 @Konobyos
ፈያታዊ ዘየማን አጭር ገለጻ


@And_Haymanot


ተወዳጆች ሆይ!ብዙ ጊዜ ከሚያስገርሙኝ ታሪኮች መካከል አንዱ የዚህ ታላቅ
ሰማዕት ታሪክ ነው።የተሐድሶ መናፍቃን ልባቸውን በክሕደት አጥረው የዚህን
ሰማዕት መከራ የሚያዩበትን ዓይነ ልቦናቸውን ዘግተው በእምነት ብቻ ዳነ
ብለው ሲሞግቱ ይሰማሉ ግን ተወዳጆቼ ሆይ!እንዲያ ነውን?ቅዱሳን
አባቶቻችን ስለዚህ ሰው በመደመም ተናግረውለታልና ትንሽ
እናብራራው።ቅዱስ ጄሮም ፈያታዊ ዘየማን ሰማዕት ነው ይለዋል ለምን ትሉ
እንደኾን ሰማዕትነት ከክርስቶስ ጋር ኾኑው የሚቀበሉት መከራ ሰቃይ ግድያ
ስቅላት ነው አንድም የራስን ሕማም ረስቶ መከራ ክርስቶስን ማሰብ ነውና
ፈያታዊ ዘየማንም ያደረገው ይህን አይደለምን?ተወዳጆች ሆይ በትሑት
ስብእና በንጹህ ልቦና ኾናችሁ ተመልከቱት በእውን አይሁድ ጌታን ሲያንገላቱት
መከራ ሲያጸኑበት አምላክነቱን ክደው በመስቀል ሲሰቅሉት የጌታን ንጹህነት
የመሰከረው ብቸኛው ሰው ጥጦስ ወይም ፈያታዊ ዘየማን አልነበረምን?
በሉቃስ 23፥41 "ይህ ግን ምንም የሠራው ክፉ ሥራ የለም"በማለት ነበር
የገለጸው።ክርስቶሳዊያን ኾይ! ክርስቶስ ንጹሀ ባሕርይ መኾኑን ማን ነግሮት
ይኾን?መምህራነ ወንጌል አስተምረውት ይኾንን?ወይንስ የኦሪትን መጽሐፍ
አንብቦ?ታዲያስ ማን ይኾን የነገረው?እስኪ እናንተ የተሐድሶ መናፍቃኖች
ሆይ ንገሩን እንጠይቃችሁ?እስከ ዛሬ ድረስ እናንተ አልገባ ያላችሁን ነገር
እንዴት እርሱ ወዲያው ሊረዳ ቻለ?በእውን ፈያታዊ ዘየማን ይህንን ቃል
ሲናገር አምላከ ቅዱሳን ምን እንዳለው አላነበባችሁምን?ቅዱስ ጳውሎስ ራሱ
የፈያታዊንን ክብር በመንፈሳዊው ቅናት የቀና ይመስላል! ምክንያቱም
ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ ብሎ ገላ 2፥20 ላይ ተናግሯልና!ተወዳጆቼ
ክርስቲያኖች ሆይ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አበው አባቶቻችን በምስጢር
እንዲህ ይሉናል ሰባቱ ተአምራቶች ናቸው አንድም የጌታ ጥላው ቢያርፍበት
ከታወረበት ዓይነ ልቦና ተመልሷል በማለት ይደነቃሉ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ደግሞ በታላቅ ፍቅር የተሞላው የጌታ ንግግር ነው "አባት ሆይ የሚያደርጉትን
አያውቁምና ይቅር በላቸው" የሚለው የጌታ ቃል የተዘጋውን የጥጦስን ልብ
ሰብሮ ገብቶ ከሽፍታነት አስወጥቶ ለታላቅ ሰማዕትነት አድርሶታልና! ተወዳጆቼ
ይህቺ ቃል ሽፍታ ለነበረው ጥጦስ ሕይወት ስትኾን የሃይማኖት ሽፍቶች
ለኾኑት የተሐድሶ መናፍቃን ግን ጥፋት ኾናባቸዋለች!!ዳግመኛም የጴጥሮስ
ጥላው ድውያንን ከፈወሰ የጌታ ጥላማ እንዴት ይልቅ!!ተወዳጆች ሆይ!
ሌላም ድንቅ ነገር ተናግሯል እንዲህም ብሏል"አንተ በዚህ ፍርድ ውስጥ
ሳለህ እግዚአብሔር አምላክህን አትፈራምን?" ሉቃ 23፥40 በማለት
ተናግሯል።የጥንቱ ሊቃውንት ይህንን ቃል ፈያታዊ ዘየማን ወንድሙን ለማዳን
ምን ያህል እየተጋ እንደኾ የሚገልጽ ነው፤ለጓደኛው ያለውን እውነተኛ ፍቅር
እርሱን ለመመለስ ባደረገው ትግል አሳይቷል።በሽፍታ ለሽፍታ ትምህርት
ቢቀርብም ክፉው አስተሳሰብ ከልቡ አልወጣ ያለው ያ በግራ በኩል ያለው
ሽፍታ ሊመለስ አልቻለም።እኔ ግን ይህ በግራ ያለው ሽፍታ እኛን የሚመስል
ይመስለኛል።በእውን ብዙ ድንቅ ነገር ተደርጎልን ሳለ ፍቅረ እግዚአብሔር
አልገባ ብሎን ከበጎ ምግበረራት የሸፈትን የለንምን?ተወዳጆቼ ሆይ ይህ
እንዴት ያለ ድንቅ ቃል ነው!ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ የእግዚአብሔር ልጅ
ነህ በማለቱ ከተመሰገነ ጥጦስስ እንዴት ይበልጥ ሊመሰገን ይገባው ይኾን?
የቀደመው የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት ዐይቷል ፈያታዊው ግን
መስቀል ላይ መከራ ሲቀበል ያለ በደሉም ሲሞት ነው ያየው እጅግ ድንቅ እኮ
ነው የፀሐይን ያለ ወትሮዋ መጽለም፣የከዋክብትንም መርገፍ የጨረቃን ደም
መምሰል የዓለት መሰንጠቅ የሙታን መነሣት ለፈያታዊ ዘየማን በቂ
መምህራን ነበሩ!እንዲያውም ፖፕ ሺኖዳ እንዲህ በማለት ይጠይቃሉ ይህ
ሰው እንዴት አመነ?እንዴትስ የመመለስ ዝንባሌ ታየበት?የቀኙ ወንበዴ ፊቱን
ወደክርስቶስ ያዞረው በምን ዓይነት ኹኔታ ውስጥ ነበር?ክርስቶስ በብዙ
ሕዝብ ታጅቦ በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች በታየበት ልዩ አጋጣሚ ወይስ መከራ
መስቀልን በሚቀበልበት የቀራንዮ አደባባይ!በትክክልም!ወቅቱ በበሽተኞች
ተከቦ ፈውስ በሚያድልበት የምሥጋ የሙገሳ ዕለት ሳይኾን ከሳሽ ካህናትና
ሰቃይ ጭፍሮች ተባብረው ያፌዙበትበነበረበት አስጨናቂ ሰዓት ነው።ይህ
የሚያሳየው የክርሰቶስ የመስቀል ላይ ቆይታ በተለይም ደግሞ ለሰቃዮቹ
ያሳየው ርኅራኄ በቀኝ በኩል በተሰቀለው ወንበዴ ደንዳና ልቡና ላይ ታላቅ
ተጽእኖ ማሳደር መቻሉ ነው።ኹል ጊዜም ቢኾን የእግዚአብሔር ፍቅርና
ደግነት ከሰዎች አረመኔያዊ ተግባር ና የጭካኔ ሥራ በላይ ጉልበት አለው"
በማለት ያደንቃል!የተሐድሶ መናፍቃን ሆይ ኢየሱስ ማን እንደኾነ ማወቅ
ትፈልጋላችሁን?በሉ ኦርቶዶክሳዊውን ፈያታዊ ዘየማንን ጠይቁት መልሱን
ይንገራችሁ!!!አማላጅ አላለም እግዚአብሔር አምላክ ነው አለ እንጂ!
ተወዳጆቼ ሆይ!እግዚአብሔርንስ አማላጅ የሚሉ የተሐድሶ መናፍቃን
መጨረሻቸው እንዴት ይከፋ ይኾን?አንድ ሊቅማ ሮሜ 10፥9-10 ያለው ቃል
በፈያታዊ ዘየማን ተፈጸመ በማለት ይደነቃል።በልቡም የኢየሱስ ክርስቶስን
አምላክነት አመነ በአፉም መሰከረ በሰውነቱም የሞትን መከራ ታገሰ!ተወዳጆቼ
ሆይ እንዴት ግን ፈየታዊ ዘየማን የራሱ ሕማም ምንም ሳይሰማው ቀረ?
አይደንቅምን?የራሱን ትቶ ስለጌታው ሲያወራ ስትሰሙ ምን ይሰማችሁ
ይኾን? ይህን የፈያታዊ መከራ ወይም እምነቱን በሥራ መግለጥን
አለመረዳታችን ያስገረመው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህም ይላል
እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ እንደሥራው ይሰጠዋል በጌታ ቀኝ የተሰቀለው
ወንበዴ እምነቱን የገለጠው በሥራ ነው ኹሉም ሰው ፈጣሪውን በረሳበት
በዚያ የጨለማ ቅጽበት በመስቀል ላይ በተሰቀለው በክርስቶስ ሳያፍር በሰው
ኹሉ ፊት መሰከለት መከራን በመቀበሉ ያለማጉረምረም ፈጣሪውን አመሰገነ
ይህ በውኑ ሥራ አልመስል አለንን? በማለት ተገርሟል።ሌላው ነገር ደግሞ
ራሱን መውቀሱ የተፈረደበትም ፍርድ ተገቢ መኾኑን ተናገረ።አንድ ሊቅ
ፈያታዊው ዘየማን ወድያውኑ ኃጢአቱን ጠላ ጌታም ምን ያህል ኃጥአን
ሲመለሱ እንደሚደሰት ይገልጥ ዘንድ ወዲያው ተቀበለው!በማለት
ይመሰጣል። ተወዳጆች ሆይ ጌታችን በወዳጅነት መንፈስ ወንበዴውን ማቅረቡ
ምንኛ ድንቅ ነው!ይህ ሰው የክርስቶስ ጥሩ የመስቀል ላይ ወዳጅ መኾን
ችሏል፤ጌታችንም የዚህ ሰው ወዳጅነት በመስቀል ላይ ብቻ ተወስኖ እንዲቀር
አልፈለገም።ለዚህ ዋስትና እንዲኾን ከእኔ ጋር ትኾናለህ በማለት የማይታጠፍ
ቃል ገባለት።አቤቱ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ አለው!ሲደንቅ ይህቺ
ቃል ብዙ ምስጢራት አሏት ሌላ ጊዜ በደንብ እናብራራታለን ኾኖም ኢየሱስ
ክርስቶስ መንግሥተ ሰማያት የሚያገባ የመንግሥተ ሰማያት ባለቤት መኾኑን
ማመኑን የሚያስረዳ እስካሁንም በቤተክርስቲያናችን በጸሎተ ቅዳሴ ላይ
የሚታወጅ ዕጹብ ድንቀ ቃል ነው!!!አንድ ሊቅ የሚለውን እንስማ ፈያታዊ
ዘየማን በቀኝ በኩል የተሰቀለ ወንበዴ ነው ሌላኛው ደግሞ በግራ ነው
የተሰቀለው ጌታ ያለው ደግሞ በመሀል ነው ይህ የሚያስረዳው የጌታን ዳኛነት
ወይም ፈራጅነት ፈያታዊ ዘየማንን ዛሬ በገት ከኔ ጋር ትኖራለህ እንዳለው
በዳግም ምጽአት ጻድቃንንም የአባቴ ብሩካን ኑ ዓለም ሳይፈጠር በፊት
የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ ብሎ የሚሰጥ መኾኑን ያሳያል በግራ
ያሉትን ግን በግራ ያለውን አላውቅህም እንዳለው አላውቃችሁም ይላቸዋል
በማለት ገልጸዋል።ብዙ ትርጓሜያት አሉት ለጊዜው ይቆየን!


ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም
ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቅዱሳን አባቶች ምስክርነት

@And_Haymanot


የተሃድሶ መናፍቃን እኛ ኦርቶዶክሳውያን መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት አድርገን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ አድርገን ስናከብራት አምላክ ያደረግናት እየመሰላቸው ማርያምን አታምልኩ መመለክ ያለበት እግዚአብሔር አምላክ ብቻ ነው ብለው ይተቹናል ነገር ግን አበው ሲተርቱ አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል እንዲሉ የተሃድሶ መናፍቃኑም የማያውቁትን በመዘባረቅ የማትታደስ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችንን ለማደስ ይጥራሉ ዳሩ ግን እኛ ኦርቶዶክሳውያን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለእግዚአብሔር ወልድ እናትነት ከአዳም ልጆች ሁሉ የተመረጠች በመሆኗ ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሆነውን ክብሯን እያሰብን እናከብራታለን፣ የፀጋ ስግደትን እንሰግድላታለን እንጂ አናመልካታም በመሆኑም ቀደምት ቅዱሳን አባቶቻችን ያስተማሩንን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ተከትለን ለትውልድ እናስተላልፋለን እንጂ ሃራጥቃውያን ስለተቹን አስተምሮታችንን አናቋርጥም ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችንም አትታደስም ነገር ግን ለተሃድሶ መናፍቃኑ ምላሽ ይሆን ዘንድ ቅዱሳን አባቶቻችንን ስለእመቤታችን ክብርና ቅድስና ከተናገሩትን ምስክርነት ውስጥ በጥቂቱ እነሆ፦


☞ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሊቀ ጳጳስ ዘቆጵሮስ፦ "ማርያምን አክብሩ፤ መመለክ ያለባቸው ግን አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ናቸው ማርያም ቅድስት፣ ክብርት እና ውብ ብትሆንም እንኳን አናመልካትም፣ ጌታን የሚያከብር ማንም ቢኖር ማደሪያውን ያከብራል የተቀደሰ ማደርያውን የማያከብር ግን ጌታን አያከብርም"።

☞ ቅዱስ አምብሮዝ፦ "በመንፈስ ቅዱስ ግብር ሰው የሆነውን ባመለክን ጊዜ መንፈስ ቅዱስንም እናመልከዋለን፤ ነገር ግን ይሔንን ለእመቤታችን ለማርያም ማንም እንዳያደርግ ይጠንቀቅ፤ እርሷ የጌታ የአምላክ ቤተ መቅደስ ናት እንጂ የመቅደሱ ጌታ አይደለችም፤ በመቅደሱ ውስጥ ሆኖ የሠራ እርሱም ብቻ ይመለካልና"።

☞ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፦ "የማይወሰን እግዚአብሔር በድንግል ማኅፀን እንደተወሰነ ማን አየ? ማን ሰማ? ሰማያት ለማይወስኑት ለእርሱ የድንግል ማኅፀን አልጠበበውም ባሕርዩ ሳይለወጥ ከእርስዋ ተወለደ እንጂ"።

☞ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፦ "እመቤታችን ሆይ!! ከፍጡራን ሁሉ ሰይጣን አንቺን ይጠላሻል፤ ካንቺ የተወለደው እራስ እራሱን ብሎ ቀጥቅጦታልና"።

☞ ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ፦ "አማኑኤል እግዚአብሔር ነው፤ እመቤታችንን ወላዲተ አምላክ አይደለችም የሚል፤ የእግዚአብሔርንም ቃል በሥጋ እንደወለደችው የማያምን ቢኖር የተወገዘ ይሁን"።

☞ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ፦ "እመቤታችንን ወላዲተ አምላክ መሆንዋን የማይቀበል ከእግዚአብሔር የተለየ ነው"።

☞ አባ ሕርያቆር ዘብሕንሳ፦ "የቀደሙት ሰዎች እነ አብረሃም ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት የተሸጋገሩብሽ አንቺ ነሽ"።

☞ ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ፦ "ማንም ለወላዲተ አምላክ የሚያገለግል ቢኖር ፈጽሞ አይጠፋም"።

☞ ቅዱስ አውግስጢኖስ፦ "ማርያም በሔዋን ውስጥ ነበረች፤ ነገር ግን ሔዋን ማን እንደሆነች ያወቅነው ማርያም ወደ እኛ ስትመጣ ነው"።

☞ ቅዱስ ኤፍሬም፦ "ድንግል ሆይ፣ ቅድስት ሆይ፣ ጌታን የወለድሽ ሆይ እኛን ለማዳን ድንቅ ምስጢር /ተዋህዶ/ በአንቺ ቢደረግ ንጉሡን ወልደሽልናልና ፍጥረታትን በልዩ መልክ የፈጠረ የእርሱን ነገር መናገር አይቻለንምና ዝም እንበል"።

☞ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ፦ " ...መልአኩ ባነጋገራት ጊዜ ርሷ ድንግል ነበረች፣ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ወልድን ስትቀበልም ድንግል ነበረች፡፡ የአብ ጸዳል በርሷ ባደረ ጊዜ ርሷ ንጽሕት ድንግል ነበረች፣ ሕጻኑ በማሕፀኗ በየጥቂቱ ያድግ በነበረበት ጊዜም ድንግል ነበረች፣ ድንግሊቱ ያንን ፍጥረትን የሚሸከመውን ኀያሉን ተሸከመችው፣ ኀይሉ ለአብ የተባለ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታን በወለደችውም ጊዜ እርሷ ድንግል ነበረች"፡፡

☞ ቅዱስ ያሬድ፦ "ማርያም ግን በአዳም ባሕርይ ውስጥ ከጥንት ጀምሮ እንደነጭ እንቁ ታበራለች"።

☞ ቅዱስ አትናቴዎስ፦ ... "ንጹሕና ያልተነካች ድንግል... የተከበርሽ የተደነቅሽ ድንግል ሆይ በእውነት አንቺ ከማንኛውም ሌላ ታላቅነት የበለጥሽ ነሽ፤ የቃለ እግዚአብሔር ማደሪያ የሆንሺው ካንቺ ጋር ማን በእኩልነት ይወዳደራል?፤ ድንግል ሆይ ከፍጥረታት ሁሉ አንቺን ከማን ጋር ላነጻጽርሽ? ፤ በቃል ኪዳን ከሁሉም በላይ የሆንሽ ሆይ በወርቅ ፈንታ ንጽሕናን የተጎናጸፍሽ አንቺ እውነተኛውን መና የያዘችውን የወርቅ መሶብ ነሽ ይኸውም መለኮት የተዋሐደው ሥጋ ነው"።

☞ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ፦ "ጸጋን የተመላሽ ሆይ ማኅበረ መላእክትና የሰው ዘር ፍጥረታት ሁሉ በአንቺ ይደሰቱብሻል፤ የተቀደሰች ቤተ መቅደስና ነባቢት (የምትናገር) ገነት የደናግል ክብራቸው ሆይ ከአንቺ ከዘመናት አስቀድሞ የነበረ እግዚአብሔር ሥጋን ተዋሕዶ ሕፃን ሆኗልና፤ ከአንቺ የነሣውን ሥጋ በዙፋን ላይ አኑሮታል፤ ማሕፀንሽንም ከሰማያት የበለጠ በጣም ምቹ መኖሪያ ስፍራ አድርጎታል፤ ፍጥረታት ሁሉ በአንቺ የሚደሰቱብሽ ምልእተ ጸጋ ሆይ ላንቺ ውዳሴ ይገባል"።

☞ ቅዱስ ጀሮም፦ "ድንግል ልጇን ፀንሳ ከወለደችልን በኃላ ርግማን ተወገደ፤ ሞት በሔዋን ሆነ፤ በማርያም ድንግል ግን ሕይወትን አገኘን"።

☞ ፕሮክልዩስ ዘቁስጥንጥንያ፦ "ያለ ስሕተት ከርሷ ተገኘ፤ ርሷንም ያለነውር እንድትሆን አደረጋት፤ እንዲሁም ማርያም የዐዲስ ፍጥረት ሰማያዊ ምልክት ምሕዋርን ሆነች፤ በዚህም ምሕዋር የጽድቅ ፀሓይ ለዘላለም ያበራል፤ ርሷንም የኀጢአት ጨለማ ፈጽሞ አላያትም... ከእግዚአብሔር እናት የምትበልጥ ታገኝ እንደሆነ ሰው ሆይ ፍጥረቱን ሁሉ በሐሳብህ ዞረህ እይ፤ ዓለምንና ውቅያኖሶችን ሁሉ ዙር፤ አየሩን ሁሉ መርምር፤ ሰማያትን ጠይቅ፤ የማይታዩትን ኀይላት ሁሉ ዐስብ፤ በድንቅ የሚመስላት ካገኘክ መርምር ርሷ ብቻ ከቃላት በላይ የሆነች መንገድ ናት፤ በሰርጓ አዳራሽ በማህፀኗ ፍጥረት ሁሉ በፊቱ በመፍራትና በመንቀጥቀጥ የሚንበረከኩለትን ያሳደረች ናት"።
.
.
.

ቅዱሳን አባቶቻችን ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ካስተማሩት ትምህርቶች ውስጥ በጥቂቱ ያህን ያህል ለምስክርነት ካየን የተሃድሶ መናፍቃኑም ይህንን እውነታና የአባቶቻችንን ምስክርነትን አምነው ወደ ማትታደሰው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ልብ ገዝተው ይመለሱ ዘንድ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ፀሎት ነው።


✞ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልመናዋ ፍቅሯ ረድኤት በረከቷ በሁላችን ላይ ይደር!!! አሜን ✞

@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ሞተሃል አትበለኝ

@And_Haymanot

ግእዝን መማር ማወቅ፤ ሲያቅትህ መራቀቅ፤
እንደ ሸማ መልበስ፤ በግእዝ ላይ መንገሥ
ከየት አመጣኸው ሞቷል የሚለውን ይህን የሞት መንፈስ።
ድንበር አበጅተህ ሞቷል ብትለኝም
አገር ተሻግሬ ባህር አቋርጬ
ከፈረንጆቹ አገር ኑሮ መስርቻለሁ
በጀርመን ከተማ ከእንግሊዘኛ ጋር እኩል ነግሻለሁ።
እንዲያውም ይግረምህ
ግእዝ የኛ እኮ ነው የሚል አግኝቻለሁ፤
አንተ እንደገደልከኝ ሳልሞት ሳልቀበር ትንሳኤ አግኝቻለሁ
ስለዚህ ወገኔ
ጠላትን ድል ነሥተው ቀኝ ገዢን አባረው
ግእዝን አንግሠው በሰማዕትነት እንደ ሻማ ነደው፤
ባቆሙልህ አገር በባህል ወረራ ቀኝ እየተገዛህ
ግእዝ ሞቷል አልክ ሞተህ እንዳትቀር ትንሣኤ ሳይኖርህ።
ይልቅስ ወዳጄ፤
በእኔ ምስጢርነት የተደበቀውን የአባቶችን ዕውቀት
ፈልፍለህ አውጥተህ ለዚህ ዘመን ትውልድ መልስ እንድትሰጥለት፤
ግእዝ ነኝ ተማረኝ
ግእዝ ነኝ ዕወቀኝ
ግእዝ ነኝ ተርጉመኝ
ግእዝ ነኝ አትራቀኝ
ያንተው ነኝ አራቀኝ
❖ ሽንፈትህን ይዤ እንዳልጠፋ አድርገኝ። ✞

ምንጭ፦ ሐመር ፳፭ኛ ዓመት ቁጥር ፮

@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ገዳማዊ ሕይወት

@And_Haymanot

የተሃድሶ መናፍቃን ገዳማዊ ሕይወትን አይቀበሉም ድንግልናዊ ሕይወትንም አይደግፉትም ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያናችን ግን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ ልጆቿ ከገዳማዊና ዓለማዊ ሕይወት የቻሉትን እና የመረጡትን እንዲኖሩ ታስተምራለች ከጋብቻና ከድንግልናዊ ሕይወትም በአንዱ ይኖሩ ዘንድ ታስተምራለች ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን ያስተምራልና ነገር ግን ለሃራጥቃውያን ምላሽ ይሆን ዘንድ የገዳሚዊ ሕይወትን አስተምሮ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንመልከት።


✞ ድንግልናዊ ሕይወት እግዚአብሔርን ያለ ተጨማሪ ሃሳብ የማገልገያ መሣሪያ ነው "ነገር ግን ያለ አሳብ ልትኖሩ እወዳለሁ። ያላገባው ጌታን እንዴት ደስ እንዲያሰኘው የጌታን ነገር ያስባል፤ ያገባው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ እንዲያሰኛት የዓለምን ነገር ያስባል፥ ልቡም ተከፍሎአል"። እንዳለው ቅዱስ ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮ 7፥32-34

✞ ገዳማዊ ሕይወት ራሳቸውን በፈቃዳቸው ጃንደረባ ያደረጉ ሰዎች ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል የሚተጉበት ነው "ደቀ መዛሙርቱም የባልና የሚስት ሥርዓት እንዲህ ከሆነ መጋባት አይጠቅምምን? አሉት። እርሱ ግን ይህ ነገር ለተሰጣቸው ነው እንጂ ለሁሉ አይደለም፤ በእናት ማኅፀን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ፥ ሰውም የሰለባቸው ጃንደረቦች አሉ፥ ስለ መንግሥተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ። ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው አላቸው"። /ማቴ 19፥10-12/

❖ ገዳማዊ ሕይወት ሰው ያለውን ሁሉ ሸጦ በሰማይ ያለውን መዝገብ የሚሰበስብበት ሕይወት ነው "ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ"። /ማቴ 19፥21/

ገዳማዊ ሕይወት እነ ኤልያስ፣ እነ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ይኖሩበት የነበረ ሕይወት ነው ኤልያስ ፀጉራም ነበረ በወገቡም ጠፈር ታጥቆ በበረሃ ይኖር ነበረ /2ኛ ነገ 1፥7/ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስም "የግመል ጠጉል ልብስ ነበረው፤ በወገቡ ጠፈር ይታጠቅ ነበረ፤ ምግቡም አንበጣና የበረሃ ማር ነበረ"። /ማቴ 4/

ገዳማዊ ሕይወት በክርስትና ሕይወት አስፈላጊ የሆኑ ሶስት ነገሮችን ለመፈጸም የሚያስችል ነው።

➊ በመንፈስ ድኾች የሆኑ ብፁዓን ናቸው በተባለው መሠረት ራስን በፈቃድ ደኻ ለማድረግ ያስችላል ይህም በችግር ምክንያት የሚፈጠር ድህነት ሳይሆን የሚያገኙትን ነገር ለሌላ ለተሻለ ተግባር በማዋል የተነሣ የሚፈጠር ድኽነት ነው።

➋ ድንግልናዊ ሕይወት ራስን በፈቃድ ጃንደረባ ማድረግ ወይም ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ "ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሊሆን እወዳለው"። /1ኛ ቆሮ 7፥7/ በማለት የተናገረለትን ሕይወት ለመኖር የሚያስችል ነው።

➌ "መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል"። /1ኛ ሳሙ 15፥22/ በተባለው መሠረት ገዳማዊ ሕይወት ለእግዚአብሔር ፍጹም ታዛዥነትን የምናሳይበት ነው።


ገዳማዊነት ተቋማዊ በሆነ መልኩ የተጀመረው በ305 ዓ/ም አካባቢ "አባ እንጦንስ" በተባለ አባት ግብጽ ውስጥ ነው በ318 ዓ/ም ደግሞ አባ ጳኩሚስ ማኅበራዊ የሆነውን ገዳማዊ ሥርዓት መሠረተ አባ መቃርዮስም በማኅበርና በተናጠል የሚኖርበትን ሥርዓት በማገናኘት መነኮሳት በሰንበት ዕለት ለትምህርትና ለቅዳሴ እንዲሰባሰቡ ሥርዓትን ሰራ።

አባ እንጦንስ የተወለደው በ251 ዓ/ም አካባቢ "ቂምን ኤል አሮስ" በተባለች መንደር ግብጽ ውስጥ ነው ቤተሰቦቹ ሀብታሞችና ድኾችን የሚረዱ ነበሩ የሃያ አመት ሰው እያለ ወላጆች በሞት ተለዩት ወላጆቹንም ሊቀብር ወደ ቤተ ክርስቲያን በሄደ ጊዜ በቅዳሴ ላይ "ፍጹም ልትሆን ብትወድ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ተከተለኝ"። /ማቴ 19፥21/ የሚለውን የወንጌል ቃል በቅዳሴ ላይ ሲነበብ ሰምቶ በመፈፀም ሀብቱን ሁሉ ሽጦ ለድኾች በመስጠት ወደ ግብጽ በረሃ በምናኔ ወረደ ገዳማዊ ሕይወትንም መሥርቶ በዚያ ኖረ።

✿ አባ ጳኩሚስ የተወለደው በ290 ዓ/ም አካባቢ "ቴቢስ" በተባለች ከተማ ግብጽ ውስጥ ነው ወላጆቹ ክርስቲያኖች አልነበሩም ወታደር እያለ በክርስቲያኖች ሕይወት ተማርኮ ክርስቲያን ለመሆን ወሰነ ከዚያም ተጠምቆ በረሃ በመውረድ ማኅበራዊ የገዳም ሥርዓትን መሠረተ።

ኢትዮጵያ ውስጥ ገዳማዊ ሕይወት ሥርዓት ባለው መንገድ የተስፋፋው በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን "በተሰዓቱ ቅዱሳን" አማካኝነት ቢሆንም እንደ እነ አባ አሞንዮስ፣ አባ ዮሐኒ፣ አባ ዘሊባኖስ ባሉ አባቶች ቀደም ብሎ ይታወቅ ነበረ።


☞ አባ አሞንዮስ፡- ሥርዓተ ምንኵስና ወደ ኢትዮጵያ ከመግባቱ በፊት "በተንቤን ቆላ ደብረ አንሣ" በተባለው በረሃ በጾም በጸሎት ተወስነው ይኖሩ ነበር፡፡

☞ አባ ዮሐኒ፡- ደግሞ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መግቢያ ላይ በትግራይ ተንቤን አውራጃ በሀገረ ሰላም ቀበሌ ተወለዱ በዚያን ዘመን ሥርዓተ ምንኵስና ወደ ኢትዮጵያ ባይገባም አበው በምናኔ በበረሃ ይኖሩ ነበር የአባ ዮሐኒ ቤተሰቦች ድሆች ስለነበሩ አባ አሞንዮስ ወስደው አሳደጓቸው ካደጉ በኋላም ከአባ አሞንዮስ ተለይተው ወደ በረሃ ለብቻቸው በመውረድ በተጋድሎ ሲኖሩ ከቆዩ በኋላ በተወለዱ በ3ዐ ዓመታቸው ኀዳር 5 ቀን እግዚአብሔር ወደ ብሔረ ሕያዋን በመላእክት እጅ እንደወሰዳቸው ገድለ አባ ዮሐኒ ይገልጣል፡፡

በአጠቃላይ ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያናችን ከላይ የተጠቀሱትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታዎች መሠረት አድርጋ ገዳማዊ ሕይወትን ልጆቿ እንዲኖሩበት ታስተምራለች የተሃድሶ መናፍቃንም ከስህተት ጎዳና ወደ ቀጥተኛዋና ርትዒት ወደ ሆነችው ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያናችን በንሰኃ ይመለሱ ዘንድ የቤተ ክርስቲያናችን ጸሎት ነው።

✞ በገዳም የሚኖሩ አባቶቻችን እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጥልን፣ በረከታቸውም ይደርብን✞ አሜን✞✞✞

@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የህይወትና የጽድቅ መንገድ ነኝ ማለቱ አማላጅ ያስብለዋልን?
በእኔ በቀር ወደአብ የሚመጣ የለም?
መንገድስ እንዴት ይገለጻል?

በዲ/ቴዎድሮስ ዘለቀ
Share @Konobyos
@And_Haymanot
የኔ አባት…. ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት
(ያንብቡ ለሌሎች ያጋሩ)

@And_Haymanot

☞ የኔ አባት ብዙ ጊዜ ሳዮት የሰንበት ትምህርት ቤት ነገር የገባዎት አልመሰለኝም... መቼስ ከርሶ ባላውቅም ጥቂት ልበልዎት.. አደራ ያስተውሉኝ!

ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የኔ አባት… እኛ ልጆችዎ ሰው የሆንበት ሥፍራ ነው። ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የኔ አባት… በፍቅር ወድቀን፣ በፍቅር ተነሥተን፣ በፍቅር ተርበን፣ በፍቅር በልተን፣ በፍቅር ተጣልተን፣ በፍቅር ታርቀን፣ በፍቅር ተኮራርፈን ፣ በፍቅር ተጨዋውተን፣ በፍቅር አልቅሰን፣ በፍቅር ስቀን፣ በፍቅር ኮርኩመን፣ በፍቅር ተኮርኩመን፣ በፍቅር ተፎካክረን፣ በፍቅር ተሸናንፈን፣ በፍቅር ተምረን፣ በፍቅር ተተራርበን፣ በፍቅር አጥፍተን፣ በፍቀር ታርመን እኛነታችን የተሠራበት ቦታ ነው፡፡ አባቴ ይሙቱ! … እኔ በርሶ ምዬ አልዋሽም፡፡

ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የኔ አባት… በፍቅር ባሪያ የሆንበት፣ በፍቅርም ገዢ የሆንበት ቦታ ነው፡፡ አሽከርም ንጉሥም ሆነንበታል፤ አባቴ አሽከርና ንጉሥ በአንድ ጊዜ ሆነው ያውቃሉ? በፍቅር ባሪያም ገዢም ሆነውስ ያውቃሉ? በእውነት እንደዛ ከሆኑስ እርሶም ሰንበት ተማሪ ኖት ማለት ነው፡፡ ነቃሁቦት፤ ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የኔ አባት ልጅ ሳለን ሥራ አመራርን ያጠናንበት፣ የሕዝብ አስተዳደርን የተማርንበት ፣ በተለያየ ሙያ ስብጥር የተሰባጠርንበት፣ ለአረንጓዴ ልማት አትክልትን የተከልንበት፣ በሀገር ፍቅር የነደድንበት፣ በዕቅበተ እምነት የበለጸግንበት፣ በበጎ አድራጎት ስለ ወገን ማሰብን ያየንበት፣ ለሀገር ጥሩ ዜጋ መሆንን የቀሰምንበት ቦታ ነው፡፡

ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የኔ አባት… ካለዘር ክፍፍል የተፋቀርንበት፣ እገሌ ከዚህ ነው እገሌም ከዚያ ነው ያልተባለበት ሰሜንና ደቡብ፣ ምዕራብና ምስራቅ የሌለው ቦታ ነው፡፡ ሰንበት ተማሪ ሲሆኑ አባቴ… ብሔሮ ክርስትና፣ ቋንቋዎ ፍቅር ፣ ሀገርዎ በሰማይ ፣ ንጉሦ ክርስቶስ ይሆናል፡፡

እመቤቴን! የኔ አባት… መቼስ ከእርሶ አናውቅም፣ እንደርሶ ሊቅም አይደለንም፣ ብሉዩን ከሐዲሱ ፣ ሊቃውንቱን ከመነኮሳቱም አናመሰጥር ይሆናል፤ ሰንበት ተማሪ ሲኮን ግን አባቴ… በሐዲስ ኪዳንና በብሉይ ኪዳን ያለው እንደ እሳት የሚንቀለቀል ፍቅረ ቤተ ክርስቲያን በውስጥዎ ይነዳል፡፡ ቤተ ክርቲያን ስትነካ አካሎ እንደተቆረጠ ያንገበግቦታል፤ ትምህርትዎን ሥራዎን እርግፍ አድርገው መፍትሔ ለመስጠት ይሮጣሉ፤…. ብቻ አባቴ ሰንበት ትምህርት ቤት የቅንዐተ ቤተ ክርስቲያን እሳት የሚንቦገቦግባት ምድጃ ናት፡፡
አባቴ… ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት፣ እርሶ የሚወዷቸው ትልቁ መምህር የተማሩበት ቦታ ነው፤ እርሶ የሚያከብሯቸው ትልቁ ሊቅም ማስተማርን የጀመሩበት ቦታ ነው፤ ያኔ ተኮለታትፈው ባያስተምሩን ኖሮ ዛሬ እርሶን የመሰለ አባት በተገኙበት ጉባኤ ለማስተማር መንፈሳዊ ልምድ አይኖራቸውም ነበር፡፡ እኛ አሜን ባንላቸው ኖሮ ዛሬ በሺ የሚቆጠር ምእመን አሜን አይላቸውም ነበር፡፡ ድንግልን! በዚህ ቅንጣት አልጠራጠርም፡፡

ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የኔ አባት… የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች የሆኑ ተኩላዎች እንደጉድ የሚፈሩት ቦታ ነው፤ የቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጆች አሉበታ፤ አባቴ… ሰንበት ትምህርት ቤት እንደ ጳውሎስና እንደ ሲላስ ሲያገለግሉ የሚታሠሩበት ቦታ ነው፤ ያኔ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች የእግዚአብሔር ቅዱሳንን ነገር እየጠመዘዙ ከነገሥታት ጋር እንደሚያጣሉና በምድራዊ ፍርድ ቤት እንደሚገትሩ… በሰንበት ትምህርት ቤትም እንዲሁ ነው፤ ለሃይማኖት ሲቆረቆሩ የፓርቲ አባል የመንግሥት ጠላት ተደርገው ይከሰሳሉ፤ የቤተ ክርስቲያንን መዘረፍ ሲቃወሙ በዓለማዊ ፍርድ ቤት አሸብረዋል ተብለው ይገተራሉ፡፡

ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የኔ አባት ወንድምዎ በኃጢአት ሲወድቅ እንደእነ ቅዱስ መቃርዮስ የወንድሞን ነውር ለመሸፈን ቅርጫት የሚደፉበት ቦታም ነው፡፡ በየቦታው ሲናቁና ሲባረሩም በፍቅር ተመክረው የሚመለሱበት ገዳም ነው፡፡ በወጣትነት ብዙ እያጠፉ በብዙ የሚማሩበት ቦታም ነው፡፡

አባቴ… እውነተኛ ወንድሞች አሉዎት? በሐዘንዎ ጊዜ ሳይለዮት ከልብ የሚያስተዛዝኖት፣ ማስተዛዘን ብቻም ሳይሆን በመንፈስ የሚያጸኑዎት… ወንድሞች አሎት? አብረው ውለው አብረው አድረው… እንግዳን አስተናግደው፣ ዕቃ አጥበው የሚያግዙዎትስ እኅቶች አሉዎት? በደስታዎ ጊዜ ከእርስዎ ጋር አብረው ከልብ የሚደሰቱ፣ ድግሶን ድግሳቸው አድርገው የሚንደፋደፉ ወዳጆች አሉዎት? እኚህ ከሌሉዎት የኔ አባት አንድ ነገር ጎሎታል ማለት ነው… ሰንበት ተማሪነት አልነካካዎትም ማለት ነው፡፡

ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የኔ አባት አንድነትና ኅብረት አካል ነሥቶ የሚያዩበት ቦታ፤ አባቴ ይሙቱ እውነቴን ነው፡፡ አንድነትና ንጹህ ፍቅር በስምንተኛው ሺ ገዝፎ የሚታይበት ገነት ነው ሰንበት ትምህርት ቤት፡፡ ለዛ ነው እኮ አባቴ… ሰነፍ ሆነን እንኳን እንደ ብርቱ የምንታየው፣ ምንም ሳንደክምበት እንኳን አገልግሎታችንና ሐሳባችን የሚሞላው… ምንም ሳናውቅ እንኳን ከአዋቂዎች በላይ የምናገለግለው… አባቴ ይሙቱ… ይኸው በርሶ ምያለሁ… ይሄ ሁሉ ስለአንድነታችንና ስለፍቅራችን ነው፡፡ እንጂማ እኛ አኮ ባዶ ነን…፤ ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የኔ አባት… ባዶ ሳሉ ምሉዕ የሚሆኑባት ሥፍራ ነች፡፡

ስለዚህ አባቴ… ቢቻሎ እርሶም ሰንበት ተማሪ ይሁኑ፤ አባል ሆነው ይቀላቀሉን፤ ካልተቻሎም አባል የሚሆኑትን አይከልክሉ፡፡ ቢቻልዎት ሰንበት ትምህርት ቤትን ከልቦ ይደግፉ፤ ባለዎት ነገር ሁሉ ያበርቱ፡፡ ካልቻሉም አደራ አገልግሎቱን ከሚያደናቅፉት ፣ አባላትን ከሚያንገላቱት ጎን አይሁኑ፡፡ ቢቻልዎት ስለሰንበት ትምህርት ቤት መልካምነት ያውሩ፤ ባይቻልዎትም ዝም ይበሉ እንጂ ልጆችዎን አይሙ፡፡
ቢቻልዎት በጸሎትዎ ሰንበት ትምህርት ቤትን ያስቡ፤ ባይቻልዎትም ቢያንስ አይርገሙ፡፡

(በዲ/ን ሕሊና በለጠ)

@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
"የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።
" (2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3:16-17)
@And_Haymanot
መቆም

@And_Haymanot

"መቆም" የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ 4 ትርጉሞች አሉት! እነዚህም፦

1)አለመቀመጥ፣ ቀጥ ብሎ መገተር፦
=>ማቴዎስ 27:11፦ ኢየሱስም በገዢው ፊት ቆመ…"
=> ራእይ 12:17፦ ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤ በባሕርም አሸዋ ላይ 'ቆመ'
2)መፍረድን ፦
=>መዝሙር 81፡1 "እግዚአብሔር በአማልክት ማኅበር ቆመ፥ በአማልክትም መካከል ይፈርዳል" የሚቆመው ለመፍረድ ነው እንጂ ለማማለድ አይደለም!
=>ሥራ 7፡55፦ መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእግዚአብሔርን ክብር ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ 'ቆሞ'
አየና።
3)በጽድቅና በቅድስና መኖርን፦
=> 1ቆሮ10፡12፦"ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ"
=> ይሁዳ 24 "ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ 'እንዲያቆማችሁ' ለሚችለው..."
4) ማማለድ፣ መጸለይ፣መለመን፦
=> ኢዮብ 1፡6፦ የአምላክ ልጆች (መላእክት) በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም(ለማማለድ፣ለመለመን) መጡ!
=> ዳንኤል 12፡1፦በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች 'የሚቆመው' ታላቁ
አለቃ ሚካኤል ይነሣል..."
=> መዝሙር 44፡9፦ የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ
ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ 'ትቆማለች'
=>መዝ 105፡23፦ እንዳያጠፋቸው ቍጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው
ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ 'ባይቆም' ኖሮ (ባያማልድ ኖሮ) ያጠፋቸው
ዘንድ ተናገረ።
=> ሉቃስ 1፡19፦ መልአኩም መልሶ፦ እኔ በእግዚአብሔር ፊት 'የምቆመው' (የምጸልየው) ገብርኤል ነኝ"
‹‹በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙ 7 መላእክትን አየሁ›› (ራዕ 8፡2)
ይቆየን....
@And_Haymanot
@Konobyos
ተወዳጆች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቤተክርስቲያናችን ስም የሚከፈቱና የቤተክርስቲያንን አሥተምህሮ ለምእመኑ የሚያደርሱ ቻናሎች እና ግሩፖች እየበዙ እንዳሉት ሁሉ በተመሳሳይ ምንፍቅናቸውን እንዲሁም አለማዊ ቧልትን
በቤተክርስቲያን ስም የሚዘሩም ሞልተዋል፡፡ በመምህራን እና በማህበራት ስም በተመሳሳይ ስም የተከፈቱም ስላሉ ተጠንቀቁ እያልን እንደምሳሌ በዲ/ን ዳንኤል ክብረት ስም የተከፈቱ ቻናሎችን ልናነሳ ወደናል እናም ትክክለኛውን ከሌላው እንለይ እንላለን በተመሳሳይ ስም ከፍታችሁ የምትሠሩም ከዚህ ተግባራችሁ ተቆጠቡ እያልን የቤተክርስቲያንን ትምህርት በማዳረስ ላይ ያላችሁ ቀጥሉበት እንላለን፡፡
በውስጥ የተላከልን መልእክት ነውና እናመሥግናለን፡፡ ለተጨማሪ @Ahati_Haymanot ፃፉልን
እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት?

@And_Haymanot

እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት
በማለት ኑፋቄያቸውን ለሚዘሩ ተሃድሶዎች በተከታታይ በዚህ ርእሥ መልሥ መሥጠታችን ይታወቃል በድጋሚ ክፍል አንድን እነሆ ብለናል

@Konobyos

ይህን ትምህርት የምታነቡ ሁሉ በማስተዋል እና በጽሞና ትረዱ ዘንድ አሳስባችኋለሁ፡፡ ለዘመናት የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዘለዓለማዊ ድንግልና ለመቃወም ዲያቢሎስ ያዘመታቸው መናፍቃን ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች ሁሉ የማያዳግም መልስ በዝርዝር እና በአንድምታ ቀርቧል ፡፡ ከጌታ ውጭ ከቅዱስ ዮሴፍ ልጅወልዳለች ብለው ለተሰናከሉ ሁሉ በዚሁ አጋጣሚ ስለ ዮሴፍ ማንነት ጭምር ትምህርቱ በጥቂቱ ይዳስሳል
መልካም ንባብ ፡-

‹‹‹ አረጋዊው ዮሴፍ ማነው ?
መናፍቃን ድንግል ማርያም ከጌታ ውጭ ከዮሴፍ እንደወለደች ሲናገሩ እንሰማለን ማስረጃ ባይኖረውም ፡፡ ነገር ግን የዮሴፍን ማንነት በጥቂቱም ቢሆን መረዳት ለስህተታቸው ማሰታገሻ መድኃኒት ነውና እነሆ ፡- አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ሀገሩ ናዝሬት ሲሆን ሐናፂም ነጋዴም ነበር ፡፡ ዘሩ ከዳዊት ወገን ነው ፡፡ ሦሰት ሴቶች እና አምሥት ወንዶች ልጆች ነበሩት ፡፡ ልጆቹ ገሚሶቹ ከ12ቱ
ሐዋርያት ገሚሶቹ ደግሞ ከ72ቱ አርድዕት ውስጥ የነበሩ ሲሆን ከሚስቱ ጋር 52 ዓመት ፤ ሚስቱ ከሞተች በኋላ
ደግሞ 40 ዓመት ኖሯል ፡፡ በድምሩ
92 ዓመት ከኖረ በኋላ ለእመቤታች ጠባቂ ሆኖ ተመረጠ ፡፡ ከእመቤታችን እና ከጌታ ጋር ደግሞ በስደት ፣ በመከራ 22 ዓመታትን አሳልፏል ፡፡ ሊጠብቃትም ሲመረጥ ከ1,985 ሽማግሌዎች
ውስጥ ዕጣ ደርሶት ነው ፡፡ በፈቃደ እግዚአብሔርም የከተሰበሰቡት ሁሉ የርሱ በትር ለሦስት ጊዜ ያህ በተደጋጋሚ አብባና ለምልማ ተገኘች ፡፡ አረጋዊ ዮሴፍ በ114 ዓመቱ ሐምሌ 26 ቀን አርፏል ፡፡ ከማረፉ በፊት ግን ጌታችንን ‹‹ ሥጋዬን በዚህ ምድር አታስቀረው ›› ብሎ ለምኖት ነበርና ዛሬም ድረስ ዮሴፍ መቀበሩን እንጂ ቅዱስ ሥጋው የት እንዳለ የሚያውቅ የለም ጌታ ስለ ጸሎቱ (ስለልመናው) ሰውሮታልና ፡፡ ‹‹‹ አረጋዊው ዮሴፍ ለምን ተመረጠ ? *ይህ ጻድቅና ንጹሕ አረጋዊ ዮሴፍ ድንግል ማርያምን ሊጠብቅ ስለተመረጠበት ምክንያን አስረጋጭ

ማስረጃዎች እነሆ ፡፡
1ኛ) አገልጋይዋ ተላላኪዋ ሆኖ
ሊጠብቃት ፡፡

2ኛ) መከራዋን እንዲጋራ ፡፡ አንድም ዮሴፍ ዘመዷ ነው መከራን ለብቻ አይዘልቁምና በልጇ አማካኝነት የሚደርስባትን ስደት እና መከራ አብሯት
እንዲካለፈል ነው ፡፡ ዝምድናቸው ሲዘረዘር የሚከተለውን ሃቅ ያስረዳናል ፡- + ግንዱ ‹‹ አልዓዛር ›› በሁለት
ወገን የሚከተሉትን ወልዷል ፡-
* ማታን = * ቅስራ*
* ያዕቆብ = * ኢያቄም *
* ዮሴፍ = * ድንግል ማርያም
(የነዚህ የዘር ሐረጋት ግንዱ ከላይ እንዳየነው * አልዓዛር * ነው
ስለዚህ የዘር ሃረጋቸው አንድ ነውና
ሊጠብቃት እንጂ ሊያገባት አይችልም)

3ኛ) ከመደብደብ ሊያድናት ፡፡ በኦሪ.ዘኁ 5፥19 በተጠቀሰው መሠረት አንዲት ሴት ከባልዋ ውጭ ጸንሳ ብትገኝ ማየ ዘለፋ ያጠጥዋት ነበር ፡፡ እንዲሁም አንዲት ሴት ባል ሳታገባ ብትጸንስ በሙሴ ሕግ
መሠረት ደብድበው ይገድሉአት ነበር
፡፡ ስለዚህ እመቤታችን ለዮሴፍ ሳትታጭ ቀርታ ቢሆን ለድብደባ ባበቁአት ነበር ፡፡

4ኛ) ትንቢቱ እንዲፈጸም ነው ፡፡ ጌታ ከዳዊት ቤት እና ወገን እንዲወለድ ኢሳ 11፥1 ፣ 10 ላይ ትንቢት ነበር ፡፡ ዮሴፍም የዳዊት ዘር ነውና ክርስቶስ በዮሴፍ የዳዊት ልጅ ተብሎ እንዲቆጠር ነው ፡፡ ምነው በእናቱ የዳዊት ልጅ አይባልምን? ቢባል አይሁድ ሴትን ከትውልድ ቁጥር አግብተው አይቆጥሩምና ነው ፡፡

5ኛ) ኃይለ አርያማዊት (ከሰማይ ወረደች እንጂ ምድራዊት አይደለችም) የሚሉ ወገኖች ነበሩና ምድራዊት
መሆኑኗን ለማጠየቅ ነው ፡፡ ሆኖም
ከምድር መገኘቷን ለመግለጽ እንጂ ድንግል ማርያም በክብሯ ሰማያዊት ናት ፡፡ የባሕርያችን መመኪያ መባሏም ከሰው ዘር መገኘቷን ልብ እንዲሉ ነው ፡፡ ስለዚህ ድንግል ማርያም ለዮሴፍ መታጨቷ ስለዚህ እና ይህን ለመሰለ ምክንያት ነው እንጂ ለሚስትነት አልነበረም ፡፡ አንድም ዮሴፍ እመቤታችን
ሊጠብቃት በተመረጠ ጊዜ ጀርባው ጎብጦ ፣ ጉልበቱ ዝሎ ፣ ዓይኑ ሞጭሙጮ ነበር 92 ዓመት አልፎት
ነበር አረጋዊ(ሽማግሌ) መባሉም ለዚህ ነው ፡፡ በሆኑም አረጋዊ ዮሴፍ ስለነዚህ ምክንያት ድንግል ማርያም ሊጠብቃት ተመረጠ እንጂ ሊያገባት አይደለም፡፡
ሊያገባት የተመረጠ ቢሆን ኖሮ ድንግል
ማርያም መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሊያበሥራት ሲመጣ ‹‹ ወንድ ስለማላውቅ እንዴት ይሆናል ›› ባላለችውም ነበር ፡፡ ሊያበሥራት የተላከው ለዮሴፍ ከታጨች በኋላ ነውና ፡፡ በዚህም ንግግሯ ለዮሴፍ የታጨችው ሊጠብቃት እንጂ ሊያገባት እንዳልሆነ አረጋግጣለች፡፡ ዛሬ የተነሱ መናፍቀን ምሥጢር ይጎድላቸዋልና ዮሴፍን እንደወጣት ሰው ቆጥረው ድንግል ማርያምን ሊያገባ እንደታጨ በደካማ
ጎናቸው ያስባሉ እውነቱ ግን ይሄ ነው ፡፡
ይቆየን ....
ወስብሀት ለእግዚአብሔር
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የማርያም ልጅ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ከቤቱ አይለየን
@And_Haymanot
@And_Haymanot
✞_✞_✞
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አጊኝቼሻለው በጎልጎታ
@And_Haymanot
ዘማሪ ሮቤል
​​እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት?

📕 ክፍል ሁለት

📜 @And_Haymanot

እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት(ወልዳለች) በማለት ኑፋቄያቸውን ለሚዘሩ የተሃድሶዎ መናፍቃን በተከታታይ በዚህ ርእሥ የቤተክርስቲያናችንን ምላሽ ማቅረባችንን ቀጥለናል

@Konobyos

‹‹‹ የእጮኛ ትርጉም ›››

እጮኛ የሚለው ቃል ጠባቂ ማለት ነው፡፡ ሌላ ከሰው ልብ የፈለቀ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም፡፡ 👉ለምሳሌ ‹‹እናንተን ለዘለዓለም ለእኔ እንድትሆኑ አጭቻችኋለሁ ›› ሆሴ 2፥21 ማለት ለጋብቻ ነውን? ያሳዝናል አጣመው ለተረጎሙት፡፡ 👉አሁንም ሐዋርያው ከጌታችን ጋር ስላዋሐዳቸው ‹‹ ለእርሱ አጭቻችኋለሁ›› 2ኛ ቆሮ 11፥3 ማለቱን እናስተውል፡፡
👉እንደገናም ምእመናንን የከበረች ማደርያው ስላደረጋቸው ‹‹ለሰማያዊው ክብር አጭቻችኋለሁ ›› ኤፌ 5፥26 ታዲያ እንዲህ ሲል ላጋባችሁ ነው ማለት ይሆን(ሎቱ ስብሐት) ፡፡
እመቤታችን ንግሥተ ሰማይ ወምድር ነችና በ15 ዓመቷ መለኮት ተዋሐዳት ፡፡ ሲዋሐዳትም ለዮሴፍ ታጨች ሉቃ1፥26፡፡ እንግዲህ እጮኛ ማለት ትርጉሙን ያላወቁ ይወቁ እንላለን ፡፡ ነገር ግን ሰው በራሱ ፍቃድ አይተርጉም !!! ሌላው እጅግ የሚደንቀው ነገር ደግሞ ድንግል ማርያም ክርስቶስን ከመውለዷ በፊት እንጂ ከወለደች በኋላ ዮሴፍ ‹‹ እጮኛ›› ተብሎ በአንድም ስፍራ አለመጠቀሱ ነው
👉ማስረጃ ‹‹ ሕጻንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ ›› ማቴ 2፥3 እንዲሁም በግብጽ 3 ዓመት ከ3ወር በስደት ከቆዩ በኋላ ይህንኑ ቃል ለዮሴፍ በህልም ተነግሮት ‹‹ ሕጻኑን የሚፈልጉት ሞተዋልና ሕጻንና እናቱን ይዘህ ወደ ናዝሬት ተመለስ ›› አለው እንጂ እጮኛህን (ሚስትህን) ይዘህ
ተመለስ አላለውም ማቴ 2፥20፡፡

‹‹‹ የበኩር ትርጉም ›››

የበኩር ልጇን ወለደች የሚለው ቃል ብዙዎችን አሳስቷል ፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው በተለምዶ የበኩር ልጅ የሚባሉ የግድ ተከታይ ያላቸው መሆን አለባቸው የሚል አስተሳሰብ በመናፍቃን ክፉ ልቦና ስለሰረጸነው፡፡ ነገር ግን በተለምዶ የሚባል ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ጋር አይሰራምና እንዲህ ይታረማል
👉፡- ‹‹ እግዚአብሔር ሙሴን ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ከሰውም ከእንስሳትም ማኅጸንን የሚከፍት በኩር ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ አለው ›› ዘጸ 13፥1-2 ይህ ቃል እንደሚገልጸው በኩር የሚባሉት ለመጀመርያ ጊዜ ከእናታቸው ማኅጸን የሚወጡ መሆናቸውን እንጂ ግዴታ ተከታይ ሊኖራቸው እንደማይገባ ያረጋግጣል ፡፡ አንድም ብቻ ቢሆን የእናቱም ማኅጸን ለመጀመርያ ጊዜ ከፍቶ ከወጣ ተከታይም ባይኖረው በኩር ነው ፡፡ ይሄ የበኩር ትርጉም ካልገባን ወደ ሌላ ፤ ይልቁን ወደ ማንወጣው አዘቅት መዘፈቃችን አይቀሬ ነው ፡፡
👉ለምሳሌ ቆላስየስ 1፥7 ላይ ስለ ክርስቶስ ሲናገር ‹‹ ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኩር ነው ›› ይላል እዚህ ጋር በኩር የሚለው ቃል ተወዳዳሪ ላላቸው ነገሮች የሚጠቀስ ሆኖ ከቀረበ ጌታን ፍጡር አድርጎ ከፍጡራን ጋር አነጻጽሮ እርሱ ከፍጥረታት በፊት ቀደም ብሎ የተፈጠረ ፍጡር ነው እንደማለት ይሆናልና(ሎቱ ስብሐት)፡፡
እንደገናም በኩር የሚለውን ቃል በሥጋዊ ደማዊ ሃሳብ ከተረጎምነው ዕብ 1፥6 ላይ 👉‹‹በኩርን ወደ ዓለም ሲያገባ ›› የሚል ቃል አለ እዚህ ላይ የክርስቶስ በኩር ተብሎ መጠራት አብ ቀዳሚ ተከታይ የሌለውን የባሕርይ ልጁን ወደ መሬት ሂድ ፣ ውረድ ተወለድ ፣ ሙት ተሰቀል ብሎ እንደላከው ለመግለጽ ነው ፡፡ ታድያ አብ በኩርን ወደ ዓለም ሲልክ በኩር የሚለው ቃል ተጠቅሷልና አብም ከክርስቶስ ሌላ ልጅ አለው ማለት ነውን? እናንት ግብዞች መናፍቃን የመጽሐፍን ቃል በግርድፍ መረዳት ምን ያህል እንደሚያስት ይረዱ ድንግል ማርያምን የነኩ እየመሰላቸው ባለቤቱን መንቀፋቸው ያሳፍራል !!!
እርሷስ ክብር ይግባትና በተቃዋሚዎች አፍ አትረክስም እርሱ ባለቤቱ አንዴ አክብሯታልና ፡፡ ‹‹ የበኩር ልጇን ወለደች›› መባሉ መጀመርያና መጨረሻ የሌለውን አምላከ አዶናይ ፣ ልዑለ ባሕርይን ወለደች ማለቱ ነው፡፡

ይቀጥላል
📝 ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
Join
@Konobyos
Join
@And_Haymanot
Join
@And_Haymanot

ለሌሎች ሼር በማድረግ ኑፋቄያቸውን አብረን እንዋጋ

የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡ ♥️
"የዛሬ 2000 ዓመት ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወለድ እጅመንሻ ይዛ ለተገኘች፡ ኢየሱስ ክርስቶስን በሕፃንነቱ ሲሰደድ ለተቀበለች፡ ኢየሱስ ባረገ በዓመቱ በጃንደረባዋ በኩል በስሙ ለተጠመቀች፡ ከማንም በፊት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያላትን እምነት በንጉሥዋ በኢዛና በኩል በይፋ ለገለጠች፡ በዓለም ጥንታዊዉን በእጅ የተጻፈ የኢየሱስ ወንጌል በአባ ገሪማ ገዳም ለያዘች፡ በዓመት ከ1825 ጊዜ በላይ የኢየሱስ ወንጌል እንዲነበብ ሥርዓት ለሠራች ኢትዮጵያ፡- "ኢየሱስ ጌታ ነው" የሚለው ሰበር ዜናዋ ሊሆን አይችልም፡፡ ደንቆሮ የሰማ ዕለት ያብዳል ሆኖ ነው እንጅ፡፡"
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
@And_Haymanot
@And_Haymanot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት?
@And_Hayamanot
የፓስተሩን አነጋጋሪ እውነታ እነሆ ብለናል ለሌሎቹም ልቦናን ይሥጥልን

ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ሙሉ ምላሹን ለማግኘት 👉 @And_Haymanot
​​እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት?

📕 ክፍል ሶስት(የመጨረሻ)

📜 @And_Haymanot

ተወዳጆች በዚህ ርዕስ ተከታታይ ምላሽ በመዳሰስ ላይ ነን ዛሬ ደሞ በቅርቡ መናፍቃኑን በዚህ ጉዳይ ያስደነገጠውን የፓስተር ወዳጄነህን ንግግር በጥቂቱ እነሆ ብለናል፡፡ https://tttttt.me/And_Haymanot/493 ይህ ሌሎችን ልንገፋበት ወይም ልንተች ያቀረብነው ሳይሆን የጠፋችሁ እህት ወንድሞቼ በማስተዋል እንድትጓዙ ብሎም እንድትነቁም ጭምር ነው፡፡
የማርያም ልጅ ልቦናን ያድልልን
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡

@And_Haymanot

‹‹‹ የ-እስከ-ትርጉም ›››

ሥጋውያኑ(መናፍቃን) ‹‹ እስከን ›› ተገን አድርገው ‹‹ እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም ›› የሚለውን ቃል ፍጻሜ ላለው ነገር በማስገባት ደግመው
ደጋግመው ተሰናክለውበታል፡፡ ትርጉሙ(ፍቺው) ግን ይህ አይደለም ፡፡
ለምሳሌ ፡-
1ኛ) የሣኦል ልጅ ሜልኮል ‹‹እስከሞተችበት ›› ቀን ድረስ ልጅ አልወለደችም 2ኛ ሳሙ6፥23 ፡፡ ይህም ማለት እስከመጨረሻው ልጅ አልወለደችም ማለት እንጂ ከሞተች በኋላ ወለደች ለማለት አለመሆኑ የታወቀ ነው ፡፡
2ኛ) ይህም ነገር በሠራዊት ጌታ
በእግዚአብሔር ጆሮ ተሰማ ‹‹ እስከሞቱ›› ድረስ ይህ በደል በእውነት
አየሰረይላቸውም ኢሳ 22፥14 ታዲያ የዚህ ትርጉም ከሞቱ በኋላ ይሰረይላቸዋል ማለት ነውን? እስከዘለዓለም አይሰረይላቸውም ለማለት እንጂ፡፡
3ኛ) ከአዳም ጀምሮ ‹‹ እስከሙሴ ›› ድረስ ሞት ነገሠ ሮሜ 5፥14 ታድያ ከሙሴ በኋላ ሞት ቀረ ማለት ነውን?
4ኛ) እግዚአብሐየር ጌታዬን ጠላቶችህ ለእግርህ መረገጫ ‹‹ እስካደርግልህ ›› ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው መዝ101፥1 ታዲያ ጌታችን ጠላቶቹን (አይሁደን) በሥልጣኑ ከረታ በኋላ በአብ ቀኝ መቀመጡ ቀረ ማለት ነው?
5ኛ) እነሆም እኔ ‹‹ እስከ ዓለም ፍጻሜ ›› ድረስ ከእናተ ጋር ነኝ ማቴ28፥20 ከዓለም ፍጻሜ በኋላ ከእናንተ ጋር አይደለሀም ማለት ነውን ?
6ኛ) ቁራውንም ሰደደው እርሱም ወጣ ውሃውም ከምድር ‹‹ እስከሚደርቅ ›› ድረስ ወዲያና ወዲህ ይል ነበር ዘፍ
8፥7 ሲል ውሃው ከደረቀ በኋላ ወዲያና ወዲህ ማለቱን ተወ ማለት ነውን?
እንግዲህ ከላይ በተዘረዘረው የእስከ ትርጉም መሠረት በማቴ1፥25 የተጠቀሰው ፍጻሜ የሌለው
‹‹ እስከ ›› መሆኑን ያስረዳል ስለዚህ ዮሴፍ እመቤታችንን እስከ ፍጻሜው ድረስ በግብር አላወቃትም ነበር ማለትነው፡፡ ከዚህ ውጭ በራሱ ፍቃድ የሚረተጉም ሁሉ የረተገመ ይሁን!!!

‹‹‹ የወንድሞች ትርጉም ›››

አዲስ ኪዳን በተለያዩ ቦታዎች ላይ ጌታችንን ‹‹ ወንድሞቹ ›› እንደሆኑ ከሐዋርያት ወገን የሚጠቅሳቸው አሉ ፡፡ ይህን በመያዝ ብዙ ጥራዝ ነጠቅ አንባቢያን (መናፍቃን) ጌታ ወንድሞች
እንዳሉት እና ድንግል ማርያም ከጌታ ውጭ ልጅ እንዳላት በማውራት አነስተኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀታቸውን ለማንጸባረቅ ይሞክራሉ ፡፡ ነገር ግን
ማንም የራሱን ግላዊ ሃሳብ ከማንጸባረቁ በፊት የመጽሐፍ ቅዱስን የአጻጻፍ ዘይቤ መረዳት ያስፈልገዋል እንላለን ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ
1ኛ) በምን ቋንቋ እንደተጻፈ ፣
2ኛ) በማን ባሕልና ዘይቤ እንደተጻፈ ፣
3ኛ) በየትኛው ዘመን እንደተጻፈ አስቀድሞ ማወቅ ለማነበብና ለመረዳት ያስችላል ምክንያቱም ሃይማኖት መሠረታዊ ጉዳይ ነውና !!! መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት ከ40 በላይ ቅዱሳን ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ አብዛኛዎቹ ዕብራውያን ናቸው፡፡ ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስን አንብቦ ለመረዳት የዕብራውያንን ባሕል በከፊልም ቢሆን መረዳት ያስፈልጋል ፡፡ ስለዚህም

በዕብራውያን ባሕል ፡-
1ኛ) አብሮ አደግና ዘመዶችን በሥጋ እንኳ ከአንድ እናትና አባት ባይወለዱም ‹‹ ወንድም ›› ይባላሉ ዘፍ 13፥11
2ኛ) በሃይማኖት የሚመሳሰሉም ‹‹ወንድሞች ›› ይባላሉ ገላ4፥1 ‹‹ ወንድሞቼ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ››
3ኛ) በሕብረት በአንድ (ማህበር) የሚቀመጡ ‹‹ ወንድሞች ›› ይባላሉ ‹‹ ወንድሞች በሕብረት ቢቀመጡ እነሆ መልካም ነው እነሆም ያማረ ነው›› መዝ 133፥1፡፡
በተጨማሪም ሐዋርያት እርስ በርስ ‹‹ ወንድሞች ›› ይባባሉ ነበር ፡፡ ከዚህ በመነሳት ለጌታ ‹‹ ወንድሞቹ ›› ተደርገው የተጠቀሱት ሦስቱ ሐዋርያት በሥጋ የተወለዱ አይደሉም፡፡ ድንግል
ማርያምም ከጌታ ውጭ ምንም ዓይነት
ልጅ የላትም !!! ልጅ ብቻም ሳይሆን ልጅ
የመውለድ ሃሳብም የላትም አልነበራትምም !!! በተጨማሪም ወንድሞቹ ተብለው የተጠቀሱት ‹‹ያዕቆብ ›› እና ‹‹ ይሁዳ ›› መልዕክቶቻቸውን ሲጽፉ ‹‹ የጌታ ባሪያ›› እያሉ ጻፉ እንጂ ‹‹ የጌታ ወንድሞች ›› ነን ብለው አልጻፉም
ማስረጃ ፡- የያዕቆብ መልእክት 1፥1 ‹‹የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ››
የይሁዳመልእክት 1፥1 ‹‹ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ ›› ስለዚህ እነዚህ ሐዋርያት ዮሴፍ ከሟች ሚስቶቹ የወለዳቸውና አብረውት ያደጉ እንጂ ከድንግል ማርያም የተወለዱ አይደሉም ፡፡ ‹‹‹እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም የሚለው ትርጉም ›››
ይህን ቃል በመጥቀስ ድንግል ማርያም ክርስቶስን ከወለደች በኋላ ዮሴፍ በግብር አውቋታል የሚሉ መናፍቃን አሉ
መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከወለደች በኋላ
ልጅ ወልዳለች የሚል ቃል አልተጻፈም እንጂ !!! ይህን ቃል መነሻ አድርጎ ለመጀመርያ ጌዜ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን የጠየቀው በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ንጉሥ አርቃድዮስ ሲሆን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አምሥት ነገሮችን ግልጽ አድርጎለታል ፡፡ አርቃድዮስም መልሱን በሚገባ
አምኗል ተረድቷል ፡፡ ዛሬም ጥያቄውን በድርቅና ሳይሆን ልክ እንደ አርቃድዮስ በየዋህነት ለጠየቀ ሁሉ መልስ የማያስፈልገው ጥያቄ ነው ፡፡ ሆኖም
ለዚህ ስህተታቸው መልስ መስጠቱ ተገቢ ነውና አነሆ ፡- ‹‹ የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ ዮሴፍ ድንግል
ማርያምን አላወቃትም ›› ማለት ፡- ዮሴፍ
ድንግል ማርያም ጌታን እስከምትወልድበት ቀን ድረስ ማን እንደሆነች አላወቃትም(ማንነቷን)
አልተረዳም ነበር ለማለት ነው ፡፡ ኋላ ግን ጌታን በወለደች ጊዜ በቤተልሔም እረኞች(ኖሎት) እና መላእክት በአንድነት ሲዘምሩ ፣ የሩቅ ምሥራቅ ነገሥታት(ሰብዓ ሰገል) እጅ መንሻ ይዘው መጥተው ሲሰግዱለት ፣ እንዲሁም ቤተልሔም ላይ የብርሃን ድንኳን ከምድር እስከ ሰማይ ተተክሎ ሲመለከት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት መሆኗን አወቀ
(ተረዳ) እስከዚያች ቀን ድረስ ግን ማለትም ጌታን እስከምትወልድበት ቀን ድረስ ዮሴፍ ድንግል ማርያም የአምላክ
እናት መሆኗን አላወቀም ፣ አልተረዳም ነበር ለማለት ነው ፡፡

አወቀ ማለት በግብር ተገናኘ ማለት አይደለም !!! እንዲህ ከታሰበ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ የሚል ቃል አለ ፡-‹‹ ከእነርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጦ ሳለ እንጀራውን አንሥቶ ባረከው፥ ቈርሶም ሰጣቸው፤ ዓይናቸውም ተከፈተ፥ አወቁትም››ሉቃ 24፥30-31 ይህም ማለት ጌታችን መሆኑን አወቁ (ተረዱ) ከማለት ውጪ ሌላ ምን ዓይነት ትርጉም ሊኖረው ይችላል ??? (ማዕዱን ቆርሶ እስከሚሰጣቸው ድረስ ግን ጌታን አላወቁትም ነበር)ስለዚህ ማወቅ ማለት
መረዳት እንጂ የግድ በግብር መገናኘት
ዓይደለም !!

‹‹ ቃየል ሚስቱን አወቀ ጸነሰችም ›› ዘፍጥረት 4፥17 የሚለው ቃል በግብር
እንደቀረባት(እንደተገናኛት) የታወቀ ነው
ምክንያቱም አወቃት ብቻ ብሎ አላቆመም ‹‹ ጸነሰችም ›› ይላልና !!! ነገር ግን ዮሴፍ ድንግል ማርያምን እስክትወልድ ደረስ አላወቃትም ካለ
በኋላ ሌላ ምንም ዓይነት ተቀጽላ ቃል የለውም ፡፡ መናፍቃን በግድ እናጋባ እና
፩ ሃይማኖት
​​እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት? 📕 ክፍል ሶስት(የመጨረሻ) 📜 @And_Haymanot ተወዳጆች በዚህ ርዕስ ተከታታይ ምላሽ በመዳሰስ ላይ ነን ዛሬ ደሞ በቅርቡ መናፍቃኑን በዚህ ጉዳይ ያስደነገጠውን የፓስተር ወዳጄነህን ንግግር በጥቂቱ እነሆ ብለናል፡፡ https://tttttt.me/And_Haymanot/493 ይህ ሌሎችን ልንገፋበት ወይም ልንተች ያቀረብነው ሳይሆን የጠፋችሁ እህት ወንድሞቼ በማስተዋል…
......አወቀ ማለት በግብር ተገናኘ ማለት አይደለም !!! እንዲህ ከታሰበ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ የሚል ቃል አለ ፡-‹‹ ከእነርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጦ ሳለ እንጀራውን አንሥቶ ባረከው፥ ቈርሶም ሰጣቸው፤ ዓይናቸውም ተከፈተ፥ አወቁትም››ሉቃ 24፥30-31 ይህም ማለት ጌታችን መሆኑን አወቁ (ተረዱ) ከማለት ውጪ ሌላ ምን ዓይነት ትርጉም ሊኖረው ይችላል ??? (ማዕዱን ቆርሶ እስከሚሰጣቸው ድረስ ግን ጌታን አላወቁትም ነበር)ስለዚህ ማወቅ ማለት
መረዳት እንጂ የግድ በግብር መገናኘት
ዓይደለም !!

‹‹ ቃየል ሚስቱን አወቀ ጸነሰችም ›› ዘፍጥረት 4፥17 የሚለው ቃል በግብር
እንደቀረባት(እንደተገናኛት) የታወቀ ነው
ምክንያቱም አወቃት ብቻ ብሎ አላቆመም ‹‹ ጸነሰችም ›› ይላልና !!! ነገር ግን ዮሴፍ ድንግል ማርያምን እስክትወልድ ደረስ አላወቃትም ካለ
በኋላ ሌላ ምንም ዓይነት ተቀጽላ ቃል የለውም ፡፡ መናፍቃን በግድ እናጋባ እናዋልድ ካላሉ በቀር ጸነሰችም ወለደችም አላለም አዚያው ላያ ያበቃል
አራት ነጥብ ፡፡ ‹‹‹ ድንግል ማርያም ከክርስቶስ ውጪ ልጅ የላትም ! ›››

ተጨማሪ ማስረጃዎች እነሆ ፡- ሲጀመር መጽሐፍ ቅደስ በአንድም ቦታ ድንግል ማርያም ከክርስቶስ ውጪ ልጅ አላት አይልም ብሎም አያውቅም !!! መጽሐፍ ቅዱስ እውነቱን እውነት ሐሰቱንም ሐሰት
የሚል መጽሐፍ ስለሆነ ያልሆነውን ሆነ አይልም የሆነውንም አይደብቅም !!! ወንጌልን ለዓለም የሰበኩ ቅዱሳን ሐዋርያትም ድንግል ማርያምን ማዕከል አድርገው አስተምረዋልና ከክርስቶስ በኋላ ልጅ ወልዳ ቢሆን ኖሮ ለምን ደበቁን ? ለምሳሌ ጌታችን ሲሰቀል በመስቀል ሥር ሆና ስማልቀሷ ፣ለዮሐንስ ስለመሰጠቷና መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ እርሷ በመሃከላቸው እንደነበረች ሲጽፉ ለምን ከጌታ ሌላ ልጅ መውለዷን አልነገሩንም? ለምንስ ደበቁን? አሁንም በዚህ አቋም ለጸናችሁ መናፍቃን እውን መለኮት ባደረበት ማኅጸን ሰው ያድርበት ይሆን? አዎ ከሆነ ያንተ ኢየሱስ ፍጡር እና ተራ ሰው እንጂ አምላክ አይደለም !!!
የኛ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ባደረበት ማኅጸን ግን ማንም….. !!! ማንም…. !!!
ማንም…. !!! አያድርበትም ፡፡ በድጋሚ
ልምጣባችሁ እውን ድንግል ማርያም ከክርስቶስ ውጪ ሌላ ልጅ ያስፈልጋት ይሆን ከዚያ በኋላ ብትወልድም ሰው አምላክ አይሆን? አበው እንኳ ‹‹ ሃምሳ
ቢወለድ …… ከተባረከ ይበቃል አንዱ ››
ብለው የለ ታዲያ ድንግል ማርያም ከአንዱ ከብሩክ ልጇ ከክርስቶስ ሌላ ምን ሽታ ትወልድ ይሆን ?

መጽሐፍ ቅዱስ ዘለዓለማዊ ድንግልናዋን እንዴት እንዳስቀመጠ ተመልከት ፡-
1) “እቴ ሙሽራዬ የተቆለፈች ገነት የተዘጋ ምንጭ የታተመች ፈሳሽ ናት”መኃ.ዘሰ 4÷12 (ዳዊት
የመንፈስ አባቷ ነውና ልጄ ይላት ነበር ሰሎሞን ደግሞ የዳዊት ልጅ ነውና እህቴ ያላታል የመንፈስ ወንድሟ ነውና)
2) “የምስራቁም በር ለዘለዓለም ተዘግቶ ይኖራል ሰውም አይገባበትም እግዚአብሔር አንዴ ገብቶበታልና” ት.ሕዝ
44÷1-2 (ምሥራቅ የተሰኘች ድንግል ማርያም ናት በርሷ ሰማይነት ክርስቶስ
ፀሐይ ሆኖ ወጥቷልና) ይህን ቃል ለቤተ መቅደስ ነው ብለህ የምትከራከር ካለህ ‹‹ ለዘለዓለም የተዘጋ ቤ/መ በዚህ ምድር ላይ የለምና እራስህን አታታል!!!
3) “ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆንልኛል” ሉቃ 1÷34(ይህ የእመቤታችን አስደናቂ ንግግር ለወደፊትም እራሷን አቅባ እንደምትኖር
የሚያረጋግጥ ቃል ነው ፡፡ አንድም ኃላፊ ግስ ነው የወደፊት ዓላማዋንም ያረጋግጣል) ‹‹‹ እርሱ ብቻ ልጇ እንደሆነ የክርስቶስ ምስክርነት›››
1ኛ) አይሁድ በምቀኝነት ክርስቶስን ሲሰቅሉት ከእግረ መስቀሉ ሥር የተገኘው ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ድንግል ማርያም ብቻ ነበሩ ፡፡ እመቤታችን ሌሎች ልጆች ቢኖሯት ኖሮ ‹‹ እነሆ ልጅሽ ›› ብሎ ዮሐንስን ጠብቃት ባላለውም ነበር ፡፡ በዚህ ላይ ዮሐንስም እኮ እናት ነበረችው ፡፡ ነገር ግን
ድንግል ማርያም አንድያ ልጇ በመሆኑ ጌታችን ለዮሐንስ አደራ ሰጥቶአታል ፡፡
2ኛ) የኢየሩሳሌም ሴቶች ጌታችን መስቀል ተሸክሞ ሲያልፍ ተመልክተው አዝነው ሲያለቅሱ ‹‹ ለራሳችሁ እና ለልጆቻችሁ አልቅሱ ›› ተብለዋል
እመቤታችንም መስቀል ሥር ሆና ታለቅስ ነበር ታዲያ ለምን ‹‹ ሄደሽ ለልጆችሽ አልቅሺ አላላትም ? ? ?
‹‹‹ ትልቅ እርምት የሚሻው የመናፍቃን ስህተት ›››‹‹ ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም
ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን? እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው? ተሰናከሉበትም›› ማቴ13÷56 የሚለውን ቃል ለማን እንደተነገረ እንኳ ሳያስተውሉ ጭራሽ
ድንግል ማርያም ከክርስቶስ ሌላ ልጅ እንዳላት አድርገው ይህን አሳፋሪ ቃል ሲጠቀሙበት አይቼ እኔም አፈርኩበት !!! የዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ዓላማ አይሁድ ክርስቶስን ወንድሞች አሉት ፤
ዮሴፍ ከሟች ሚስቱ የወለዳቸውን ሁሉ ከድንግል ማርያም ነው ብለው በማሰባቸው ወይም በመናገራቸው ተሰናከሉ(ተሳሳቱ) ማለት ነው ፡፡
ታዲያ እነርሱ ክርስቶስ የዮሴፍ ልጅ ነው ፤ ድንግል ማርያምም ሌሎች ልጆች አሏት ብለው በማሰባቸው ተሳሳቱ
ከተባለ ለምን አንተ ደግመህ ትሰናከላለህ??? ይህን ስህተታቸውን ሲያስረግጥ ትንሽ ወረድ ብሎ ‹‹ በአለማመናቸውም ምክንያት
በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም ›› ይላል ፡፡

‹‹‹ ስለ ዘለዓለማዊ ድንግልናዋ ማጠቃለያ ››› እመቤታችን እንደማንኛውም ሴት አይደለችም !!! ክርስቶስን የጸነሰችው ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ሲያበሥራት ነው ፡፡ ‹‹‹ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆንልኛል ››› በማለት እንደተናገረችው እንደሌሎች ሴቶች በዘር በሩካቤ አይደለምና ነው፡፡ ቅድስት ኤልሳቤጥም ‹‹ አንቺ ከሴቶች
ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ›› ሉቃ 13÷9 በማለት እንደተናገረችው፡፡ ቅዱስ ዳዊትም ‹‹ ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ኦ ሀገረ እግዚአብሔር ›› (የእግዚአብሔር
ከተማ ሆይ ባንቺ የተደረገው ምንኛ ድንቅ ነው) አንዳለ በእመቤታችን የተደረገው ልዩ ነው ፡፡ ለዚህ ዘለዓለማዊ ድንግልናዋ አንክሮ(ምሥጋና) ይገባል ፡፡

📝 ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
Join
@And_Haymanot
Join
@And_Haymanot
Join
@And_Haymanot

ለሌሎች ሼር በማድረግ ኑፋቄያቸውን አብረን እንዋጋ

የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡ ♥️