፩ ሃይማኖት
8.91K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
የውዳሴ ከንቱ አስከፊነት


✞ እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ፃድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ። አባ እንጦስ ✞


፩ ሃይማኖት
@And_Haymanot
@And_Haymanot

የአትሮኖሱ ንጉስና የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ ታላቁ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ውዳሴ ከንቱ አስከፊነት ሲያስተምር፦ ☞ ውዳሴን ከንቱን መሻት የገሃነመ እሳት እናት ናት ውዳሴ ከንቱን መሻት እሳቱ ለማይጠፋው ትሉ ለማያንቀላፋው ዓለም መጋቢዋ ናት ሌሎች ክፉ ምግባራት በሞት ይገታሉ ውዳሴ ከንቱ ግን አንድ ሰው ከሞተ በኃላ እንኳን ሊያደርገው የሚችለው የክፉ ክፉ ምግባር ነው በመሆኑም ውዳሴ ከንቱ የገሃነም እሳት እናት ናት እላለው ሌሎች ክፉ ምግባራት ሰው ሲሞት ይቆማሉ ውዳሴ ከንቱ ግን ከሞቱ በኃላ እንኳን የሚቀጥል ነው። ታዲያ ከዚህ የባሰ ምን አለ ልንል እንችላለን? ምን ማለቴ እንደሆነ እነግራችው ዘንድ ትሻላችሁን? እስኪ ወደ መካነ መቃብር ሂዱ ቢያንስ አሁን በአካል ባትሄዱ በዓይነ ህሊናችው ሂዱ ብዙ የብዙ ብዙ ሐውልቶችን አታገኙምን? አዎ! እነዚህ ሰዎች ከመሞታቸው በፊት የሚናዘዙት ሀብታቸው ለድሆች እንዲሰጥ አይደለም፤ ሀብታቸው ብል እንዲበላው ሐውልት እንዲቆምላቸው እንጂ። በቀብር ሥነ-ሥርዓታቸው ላይ ለየት ያለ ትርዒት እንዲፈፀምላቸው ነው የሚናዘዙት እነዚህ ሰዎች በዘመናቸው ድሆችን ሲሳደቡ የነበሩ ናቸው አንዲት ቁራሽ ዳቦ ለድሀ መመፅወት ሲያሳፍራቸው የነበሩ ናቸው የምድር ትላትል ይበሉት ዘንድ መቃብራቸው እንዲያምር ሲናገሩ ግን ምንም ሀፍረት ቢጤ አይሰማቸውም ለሰራተኞቻቸው ደሞዝ ለመጨመር ይንገበገባሉ እንዲሁ በከንቱ ለትላትል ለሚያወጡት ገንዘብ ግን እጅግ ይጨነቃሉ። ወዮ! በአርአያ ስላሴ የተፈጠረውን ሰው ረስቶ ለትላትል ከመጨነቅ በላይ ምን ከንቱነት አለ? ከዚህ የባሰ ክፉ ደዌ ምን አለ?... በማለት እኛ ኦርቶዶክሳውያን ከውዳሴ ከንቱ መጠንቀቅ እንዳለብንና ካልተጠነቀቅን ግን ይቺን አለም ተሰናብተን እንኳን ውዳሴ ከንቱ ተከትሎን እንደሚመጣ ያሳስበናል።

ተወዳጆች በተለይ እኛ ኦርቶድክሳውያን ሁሉ ነገራችን ኦርቶዶክሳዊ መምሰል ነው ያለበት አነጋገራችን፣ አካሄዳችን፣ አለባበሳችን ሁሉ ትህትናን የተሞላ ነው መሆን ያለበት ውዳሴ ከንቱ የነበረንን መልካም ምግባር ሁሉ የሚያሳምም ደግሞም የሚገድል ክፉ ደዌ ነው መጽሐፍ ቅዱሳችን በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሄር ዘንድ ግን የተዋረደ ነው እንዲል ውስጣችን በውዳሴ ከንቱ የተሞላ ከሆነ ብንሰብክ፣ ብንዘምር፣ ብንመጸውት፣ ብንጸልይ ስብከታችን፣ ዝማሬያችን፣ ምጽዋትችንና ጸሎታችን በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነው ውዳሴ ከንቱ ካለብን ውስጣችን ንፅህና የለውም ስለዚህ ሰው ንፅህናውን እንዲያጣ የሚያደርገው ዝሙት ወይም ማመንዘር ብቻ ሳይሆን ውዳሴ ከንቱምም ጭምር ነው።

✞ በአንድ ወቅት አባ ጵላን የተባለ ቅዱስ አባት ከእግዚአብሄር ዘንድ ውጣና አስተምር የሚል ትእዛዝ ደርሶት ነበረ እርሱ ግን ዝም ብሎ ተቀመጠ ውጣና አስተምር አላልሁህምን? ብሎ ሲጠይቀው አስተምር ካልከኝስ የትዕቢትን ሰይጣን ከእኔ አርቅልኝ ብሎ ለመነ ሰይጣነ ትዕቢትንም ከላዪ አወጣለት ይህ መንፈሳዊ አባት በማስተማር የሚመጣውን ፆር ፈተና ተረድቶ ስለነበረ አስተምር ሲባል በማስተማሩ ስለሚመጣበት ጉዳይ አጥብቆ ጠየቀ ይህ አባት እንዲያስተምር የታዘዘው በራሱ በፈጣሪ በመሆኑ እንኳን ልቡ በኩራት አልተሞላም በውዳሴ ከንቱም አልታበየም ከራሱ ከፈጣሪ ዘንድ ተልኬ ታዝዤ መጣው እያለ በሰው መካከል ለመኮፈስና ስለሱ ቅድስና ብቻ እንዲወራ አልቸኮለም ትምህርቱንም ሕይወቱንም ሊያበላሽ የሚችለውን መንፈሰ ትዕቢት አርቅልኝ አለ እንጂ።

እኛ ብንሆን ግን እንኳን ልዑለ እግዚአብሔር አምላካችን አዞን ቀርቶ የደብራችን አስተዳዳሪ የሆኑ አንድ አባት ቢያዙን እንኳን መሬት አትንካኝ፣ ከኔ በላይ ማን አዋቂ አለ በማለት ትእቢታችን አፍንጫችን ላይ ደርሶ በውዳሴ ከንቱ ታብየን ለመካሪዎች እንኳን እናስቸግር ነበረ። አንድ ሰው በውዳሴ ከንቱ ተወጥሮና ትዕቢተኛ ሆኖ በትህትናው ዓለምን ስላዳነው አምላክ ማስተማር አይችልም ስለጌታችን በትንቢት "ለአህዛብ ፍርድን ያወጣል አይጮህም ቃሉንም አያነሳም ድምፁንም በሜዳ አያሰማም የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም የሚጤስንም ክር አያጠፋም" ተብሎ በኢሳ 42፥1-4 ላይ ተጽፏል ይህም ጌታችን ሲያስተምር ውዳሴ ከንቱ የማይሰማበት፣ በጭምትነት የሚሄድ፣ ንግግሩ የለዘበ እንደነበረ ያስረዳል ቅዱሳን ሐዋርያትም እንኳን ራሳቸውን ሊሰብኩ ሌሎች ሲያመሰግኗቸው እንኳን ልብሳቸውን ቀድደው "እናንተ ሰዎች ይህንን ስለምን ታደርጋላችው? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይና ምድርን ባሕርንም በእነርሱ ያለውን ሁሉ ወደፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ዘወር ትሉ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን" ይሉ ነበር። ሐዋ 14፥15

✞ ትህትናን ስናስብ ፍፁም ከአይምሯችን የማትጠፋው ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሆነች እናታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በትንቢት መሲህ እንደሚወለድ ይጠበቅ ስለነበረ መሲህ ክርስቶስን ለምትወልደው ድንግል ባሪያ መሆንን ትመኝ ነበረ ዳሩ ግን ክርስቶስ በማይመረመር ምስጢር በፍፁም ተዋህዶ ማህተመ ድንግልናዋን ሳይለውጥ ከእርሷ እንደሚወለድ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሲበሰራት "እንደቃልህ ይደረግልኝ እኔ ለእግዚአብሄር ባሪያው ነኝ" አለችው እንጂ አምላክን በመፀነሷ አልታበየችም ታዲያ ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሆነችው እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትህትናን ካስተማረችን እኛ ማን ነንና ነው በትእቢት ታውረን በውዳሴ ከንቱ የምንጨማለቀው።

✞ ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ፣ ኢትዮጵያዊው ዮሐንስ አፈወርቅ እየተባለ የሚጠራውና ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ቄርሎስን፣ ዮሐንስ አፈወርቅን ወለደች እየተባለ ሀገራችንን ያስጠራው በ1357 ዓ/ም በወሎ ክፍለ ሀገር በቦረና ወረዳ ሸግላ/ሰግላ በተሰኘ ቦታ ከአባታቸው ሕዝበ ጽዮን እና ከእናታቸው እምነ ጽዮን የተወለደው ታላቁ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በህይወታቸው ፍፁም ትሁት ከውዳሴ ከንቱ የራቁ ታላቅ ሊቅ ነበሩ ታዲያ እኚህ አባት ድንቅ ድንቅ መፅሐፍቶችን ጽፈው እራሳቸውን ዝቅ ካደረጉ ዛሬ እኛ የሰናፍንጭ ቅንጣት ለማታክል እውቀታችን በውዳሴ ከንቱ ስንንገላታ ማየት ያሳፍራል

❖ ስለዚህ ተወዳጆች ጌታችን መድኃኒትችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስከፊ ከሆነው ከውዳሴ ከንቱ ይሰውረን ዘንድ የዘወትር ፀሎታችን ሊሆን ይገባል።


፩ ሃይማኖት

@And_Haymanot
@And_Haymanot

ወስብሃት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
ክርስቶስ ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን ማን ነው?
===≈===≈===≈===≈===≈
ኦርቶዶክሳዊ ክርስቶስን አያውቅም ብለው ለተነሱ ይድረስልን እንላለን ስለ መድሃኒታችንም እንዲህ እንመሰክራለን... ይህን ከተማርንባት ከአንዲቷ ሃይማኖት ከእናት ተዋህዶም አንሸሽም፡፡
@And_Haymanot
#ክርስቶስ_ለእኛ_ለኦርቶዶክሳውያን
•እርሱ የእግዚአብሔር በግ ነው፤ እርሱም መሥዋዕት ነው። ዮሐ 1÷29
•እርሱ ስለብዙዎች ኃጢአት የተሠዋ ፌሪዳ ነው፤ እርሱ መስዋዕትን የሚያቀርብ ሊቀ ካህናት ነው፤ መሥዋዕት ተቀባዩም እርሱ ነው። ዕብ 3÷1
•ስለእኛ መከራን የተቀበለ ነው፤ ስለእኛም የራራልን እርሱ ነው፤ 1ኛ„ጴጥ4÷1-2
•እርሱ መሽራ ነው እርሱ ራሱ ሙሽሪትም ነው። (ከእናታችን የነሣው ስጋ ግን አምላክ በመሆኑ ሙሽራ ሆነ፤ በሐዋርያትም እጅ ለእርሱ ታጨን ስለዚህም እሱ ሙሽራ ነው፤ እርሱ ራሱ ሚሽሪት ነው አልን) ሉቃ 5÷34
•እርሱ የሰርጉ ቤት ነው፤ እርሱ እራሱ ሰርግ ቤቱ አሳላፊ ነው። ራእ 9÷15
•እርሱ ገነት ነው፤ እርሱ ራሱ የገነት ዛፍ ነው። ራእ12÷14
•እርሱ ሰማያዊቱ ኢየሩሳሌም ነው፤ እርሱ ራሱ መቅደሳችንና ቅድስተ ቅዱሳናችን ነው።
በውኆች የተመስለ እርሱ ነው፤ እርሱ ራሱእኛ የምንኖርበት ዓለማችን።
•እርሱ ምግባችን ነው፤ እርሱ ራሱ ስለድኅነታችን የሚመግበን መጋቢያችን ነው፤
•እርሱ ሕያው የሆነ ኅብስት ነው፤ እርሱ የሕይወት ውኃችን ነው።
•እርሱ እውነተኛ የወይን ግንድ ነው፤ እርሱ ራሱ የደስታ ወይናችን ነው።
•እርሱ ዕንቊዋችን ነው፤እርሱ ራሱ የመዛግብታችን ነው።
•እርሱ መረባችን ነው፤ እርሱ ራሱ ተዋጊያችን ነው።
•እርሱ የጦር መሳርያችን ነው፤ እርሱ ሁሉን ድል የሚነሳ ነው።
•እርሱ ራሱ ግዝረታችን ነው: እርሱ ራሱ ሰንበታችንና ሕጋችን ነው።
•እርሱ የቅዱሳን ሕብረት ለሆነችሁ ለቤተክርስቲን ራስ ነው፤ እርሱ መልካሙ የስንዴ ቅንጣት ነው።
•እርሱ የወይን እርሻችን ነው፤ እርሻውም ባለቤት እርሱ ነው።
•እርሱ ግርማችን ነው፤ እርሱ እምነታችን ነው።
•እርሱ ሰርጋችን ነው፤ እርሱ የሰርግ ልብሳችን ነው።
•እርሱ የሕይወት መንገዳችን ነው፤ እርሱ በራችን ነው።
•እርሱ የጽድቅ ፀሐያችን ነው፤ እርሱ የነፍሳችን ብርሃን ነው።
•እርሱ ሕይወት ነው፤ እርሱ መንግሥተ ሰማያት ነው።
•እርሱ መጀመርያ የሌላው መጀመርያ ነው፣ መጨረሻ የሌላው መጨረሻ ነው፣"አልፋና ኦሜጋ ነው።

ስለዚህም እኛ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች የሆነን በክርስቶስ ከክርስቶስ ለክርስቶስ የሆንን በደም የተገዛን የሕያው የክርስቶስ ልጆች ነን።
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ብሂለ አበው

@And_Haymanot

👉 "መሬት ሁን ከመባል ያነሰ የውርደት ቋንቋ የለም ሰው አምላክ ሆነ ከመባል በላይ የሚበልጥ የክብር ቋንቋ የለም"።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
👉 "ከመጠኑ በላይ የሚመሰገንና የሚከበር ሰው ብዙ ኩነኔ ያገኘዋል ከሰው ዘንድ ከቁም ነገር ሳይቆጠር መልካም ሰርቶ ያለፈ ሰው ግን በሰማይ ታላቅ ክብር ይጠብቀዋል"። አባ አውር
👉 "በኃይል አብዝቶ መመገብ ከወጣትነት ጋር የኃጢአት ሐሳብን በግድ እንዲመጣ ያደርጋሉ"። ማር ይስሐቅ
👉 "ከሰዎች መካከል አንዱ እንደ ከንቱ እና ምንም እንደሌለህ እንደ አላዋቂ አድርጎ ቢቆጥርህ ከአፈር እንደተፈጠርህና ወደ እርሱም እንደምትመለስ ተናገር አንተ ወራዳ ከንቱ ብሎ ቢሰድብህም አንተ ራስህን አፈርና አመድ ነኝ ብለህ ጥራ እራሱን እንዲህ
ብሎ ከጠራው ከተከበረው አባት ከአባታችን አብርሃም የበለጥህ አይደለህምና"። ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ
👉 "ቤተ ክርስቲያን በጥምቀት አማካይነት አንድ የሆኑ ክርስቲያኖች የትንሳኤያቸውና የድኅነታቸው ምንጭ የክርስቶስ አካል ናት"። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
👉 "ከሰው ተለይቶ ወንድሙን የሚመክር ሰው እነሆ የፍቅሩን ጽናት ብዛት ያስረዳል፤ ባልንጀሮች ፊት የሚነቅፈው ግን የቅናቱን ጽናት ያስረዳል የምቀኝነቱን ጽናት ያስረዳል"። ማር ይስሐቅ
👉 "የመጠመቂያውን ውኃ ተራ ውኃ አድርገህ አትመልከተው፤ በውኃው አማካኝነት የሚሰጠውን ፀጋ እንጂ"። ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም
👉 "ቂመኛ ከመሆን ተከልከል፤ ቂመኛ ሰው ሥጋ የለበሰ ሰይጣን ነውና"። አረጋዊ መንፈሳዊ
👉 "ቤተ ክርስቲያን መጠጊያችን ነች፤ ቤተ ክርስቲያን የኖህ መርከብ ነች፤ በውስጧ እንጠለላለን፤ ከውጪዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል"። ቅዱስ እንድርያስ
👉 "የንጉሡ የክብር ዘቦች በፊት ለፊት በተጠንቀቅ ሲቆሙ ወደ ግራም ወደ ቀኝም አይመለከቱም ልክ እንደዚሁ አንድ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ሲቆም ሁል ጊዜ በፍርሃት ሆኖ እርሱን ሊመለከት ይገባል"። አባ ሰራጵዮን
👉 "ቅዱሳን ለመለኮታዊ ማዕጠንት የተቀጣጠሉ ዕጣን ሲሆኑ የተቀጣጠሉትም በፈጣሪያቸው ፍቅር ነው"። ማር ይስሐቅ
👉 "ሰው አገሩን ጥሎ በሔደ ጊዜ ሁሉ ያዝንለታል፤ ከርስቱ ከጉልቱ በተለየ ጊዜ ሁሉ ይራራለታል ያለቅሱለታል፤ ከመንግስተ ሰማያት ከተድላ፤ ከመዓዛ የተለየ ሰውማ ምን ያህል ለቅሶ ማልቀስ ምን ያህል ዕምባ ያፈስ ዘንድ የሚገባው ምን ያህል ይሆን"። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@And_Haymanot
የቅዱሳን አባቶቻችን ረድኤት በረከት አይለየን!!! አሜን
#መልካም_ዕለተ_ሰንበት
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
Join us
@And_Haymanot
@And_Haymanot
https://tttttt.me/Tewahdo_Haymanote/66
👆👆👆
ወደ ቅዱሳን መለመን ይገባል ወይስ አይገባም?
እነሆ ክፍል አንድ
Share
በእናታችን ስም ማታለል ይብቃ
@And_Haymanot
ይህ በአዲስ መልክ እየተሰራጨ ነው ብዙዎችም እያባዙት(Share) እያደረጉት ስለሆነ እባካችሁ አታባዙት ሌሎችም እንዳያባዙት ይህን ላኩላቸው...ለበለጠ መረጃ
👇👇👇👇
https://tttttt.me/And_Haymanot/194
ይህም አሁኑኑ ሊባዛ ይገባዋል
ሰላም የ ፩ ሃይማኖት የተዋህዶ ልጆች እንደምን ቆያችሁን አቀራረባችንን አያሰፋን እናንተንም አሳታፊ የሚያደርጉ ጥያቄዎችን ማዘጋጀት ጀምረናል በቅርቡም በ @And_Haymanot ቻናላችን ላይ ያላችሁን አስተያየት የምንቀበልበትን መድረክ የምናዘጋጅ መሆኑን እየገለፅን

? በምንጠይቃቸው ጥያቄዎች ጥሩ ተሳትፎ ላለው ወደፊት የምንሸልም መሆኑን ከወዲሁ እንገልፃለን
?? @And_Haymanot ??
እግዚአብሔር ይርዳን

የዛሬው ጥያቄያችን

ሃይማኖት ለቅዱሳን ሁልጊዜ የሚሰጥ ስጦታ ነው

▪️ 34% (68) እውነት
🔸🔸🔸🔸

▫️ 65% (128) ሐሰት
🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸
👥 196 - gross votes
፩ ሃይማኖት via @QuanBot
ሰላም የ ፩ ሃይማኖት የተዋህዶ ልጆች እንደምን ቆያችሁን አቀራረባችንን አያሰፋን እናንተንም አሳታፊ የሚያደርጉ ጥያቄዎችን ማዘጋጀት ጀምረናል በቅርቡም በ @And_Haymanot ቻናላችን ላይ ያላችሁን አስተያየት የምንቀበልበትን መድረክ የምናዘጋጅ መሆኑን እየገለፅን ? በምንጠይቃቸው ጥያቄዎች ጥሩ ተሳትፎ ላለው ወደፊት የምንሸልም መሆኑን ከወዲሁ እንገልፃለን ?? @And_Haymanot ?? እግዚአብሔር…
ሀይማኖት ለቅዱሳን አንድ ጊዜ የተሠጠ ልዩ ስጦታ ነው ይህንንም ቅዱስ ይሁዳ ፅፎልናል

" ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ #ለቅዱሳን_አንድ_ጊዜ_ፈጽሞ_ስለ_ተሰጠ_ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።"
(የይሁዳ መልእክት 1:3)

ሃይማኖትን በተመለከተ ለሚጠየቁ ጥያቄዎች ምላሽን በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ

👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/183

👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/79

ስለ ተሳትፏችሁ እናመሠግናለን ሌሎችም እንዲሳተፉ ጋብዙ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ድንቅ ልዩነት ተመልከቱ

@And_Haymanot

በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ ፈርዲናንድ ማጄላን ዓለምን በመርከብ ዞረ።

👉ሐዋርያቱ ደግሞ መርከባቸውን ጥለው ዓለምን ዞሩ!

ዛሬ ይዘንባል እያሉ ትንቢት የሚተነብዩ ሜትሮሎጂስቶች ሞልተዋል።

👉እንደ ኤልያስ ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን የዘጋ ዳግመኛም ዝናብን ያዘነበ ከቶ የለም።

በላብራቶሪው ተመራምሮ ህሙማንን የፈወሰ ሞልቷል።

👉እንደ ጴጥሮስ ጥላው ድውይ የፈወሰ ከቶ አላየሁም።

በዘፈኑ አጋንንትን የጠራ እንደ ማይክል ጃክሰን ሞልቷል።

👉እንደ ዳዊት በበገና መዝሙሩ አጋንንትን ያስወጣ እስከ ዛሬ አልተገኘም።

ከረቫትና ሱፉን ለብሰን የምንጎራደድ ሞልተናል።

👉የልብሱ ቁጨት አጋንንት ያስወጣ እንደ ጳውሎስ ከቶ አልተገኘም።

የግብጽ ነገሥታት አጽማቸው በክብር ይቀመጣል።

👉ዐጥንቱ ሙት ያስነሳ እንደ ኤልሳዕ ከቶ አላየንም።

በአሜሪካ የነገሥታትን ምሥጢር የሚሰልሉ ድርጅቶች ሞልተዋል።

👉እንደ ኤልሳዕ በእስራኤል ሆኖ በሶሪያ ቤተመንግሥት የሚደረገውን ምሥጢር ያወቀ አልተገኘም።

ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረቃን በእግሩ የረገጠ ዩሪ ጋጋሪ ዛሬ ብዙዎቹ አድርገውታል።

👉እንደ ኢያሱ ፀሐይን ያቆመ ከቶ አልተገኘም።

( በነገራችን ላይ በተፈጥሮ ሕግ መሰረት ፀሐይ በመሃል ቆማ መሬት ዙሪያውን ትዞራለች። በፀሐይ ፊት ያለው የመሬት ክፍል ቀን ሲሆን ሌላኛው ጎን ደግሞ ማታ ይሆናል።

እነ ኢያሱ በሚዋጉበት ጊዜ መሬት ከፀሐይ ፊቷን አዙራ ቀኑ ሊጨልም ነበር።

ኢያሱ ግን መሬት እንዳትዞር አደረጋት! ፀሐይን በገባኦን አቆመ ተባለ! መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 10

13 ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ። ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም።

14 እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበርና ((እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም።))
የዓለም መሪዎች ከአስር በላይ ቋንቋ መናገራቸውን እንጃ፤

👉ሐዋርያቱ ግን 72 ቋንቋ ተገለጠላቸው።

ኃያላን ነገሥታት ድውይ እንኳን መፈወስ አይችሉም።

👉ቅዱሳኑ ግን የ70 የ80 ዘመን ሬሳ አስነሱ።

ጠቢባን ነን የሚሉ ጸሐፍት ፈሪሳዊያንን ምላሽ ያሳጣቸው ዘንድ ጥበብ ያልነበራቸውን ዓሳ ወጋሪ የነበሩ ሐዋርያትን መረጠ።

ኃያላን ነገሥታት የመሰሉ መሪ ዳዊትን የመሰሉ ነገሥታትን የወለዱ የከበሩ እናቶች ሞልተዋል።

የነገሥታትን ንጉሥ ክርስቶስን የወለደች እናት ግን አንድ ብቻ ናት።

ይህችውም ከሴቶች መካከል ተለይታ የተባረከችው ድንግሊቱ ማርያም ናት። 👈

ክብር ለቅዱሳን አምላክ ይሁንልን
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
ቸር ያውለን
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ገዳማዊ ሕይወት

@And_Haymanot

የተሃድሶ መናፍቃን ገዳማዊ ሕይወትን አይቀበሉም ድንግልናዊ ሕይወትንም አይደግፉትም ኦርቶዶክሳዊ ቤተ
ክርስቲያናችን ግን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ ልጆቿ ከገዳማዊና ዓለማዊ ሕይወት የቻሉትን እና የመረጡትን እንዲኖሩ ታስተምራለች ከጋብቻና ከድንግልናዊ ሕይወትም በአንዱ ይኖሩ ዘንድ ታስተምራለች ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን
ያስተምራልና ነገር ግን ለሃራጥቃውያን ምላሽ ይሆን ዘንድ የገዳሚዊ ሕይወትን አስተምሮ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
እንመልከት።

✞ ድንግልናዊ ሕይወት እግዚአብሔርን ያለ ተጨማሪ ሃሳብ የማገልገያ መሣሪያ ነው "ነገር ግን ያለ አሳብ ልትኖሩ
እወዳለሁ። ያላገባው ጌታን እንዴት ደስ እንዲያሰኘው የጌታን ነገር ያስባል፤ ያገባው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ እንዲያሰኛት የዓለምን ነገር ያስባል፥ ልቡም ተከፍሎአል"። እንዳለው ቅዱስ
ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮ 7፥32-34

✞ ገዳማዊ ሕይወት ራሳቸውን በፈቃዳቸው ጃንደረባ ያደረጉ
ሰዎች ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል የሚተጉበት ነው "ደቀ መዛሙርቱም የባልና የሚስት ሥርዓት እንዲህ ከሆነ መጋባት አይጠቅምምን? አሉት። እርሱ ግን ይህ ነገር ለተሰጣቸው ነው እንጂ ለሁሉ አይደለም፤ በእናት ማኅፀን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ፥ ሰውም የሰለባቸው ጃንደረቦች አሉ፥ ስለ
መንግሥተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ።
ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው አላቸው"። /ማቴ 19፥10-12/

❖ ገዳማዊ ሕይወት ሰው ያለውን ሁሉ ሸጦ በሰማይ ያለውን መዝገብ የሚሰበስብበት ሕይወት ነው "ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት
ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ"። /ማቴ 19፥21/ ገዳማዊ ሕይወት እነ ኤልያስ፣ እነ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ይኖሩበት የነበረ ሕይወት ነው ኤልያስ ፀጉራም ነበረ በወገቡም ጠፈር ታጥቆ በበረሃ ይኖር ነበረ /2ኛ ነገ 1፥7/
መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስም "የግመል ጠጉል ልብስ ነበረው፤ በወገቡ ጠፈር ይታጠቅ ነበረ፤ ምግቡም አንበጣና የበረሃ ማር ነበረ"። /ማቴ 4/
ገዳማዊ ሕይወት በክርስትና ሕይወት አስፈላጊ የሆኑ ሶስት
ነገሮችን ለመፈጸም የሚያስችል ነው።
➊ በመንፈስ ድኾች የሆኑ ብፁዓን ናቸው በተባለው መሠረት
ራስን በፈቃድ ደኻ ለማድረግ ያስችላል ይህም በችግር
ምክንያት የሚፈጠር ድህነት ሳይሆን የሚያገኙትን ነገር ለሌላ
ለተሻለ ተግባር በማዋል የተነሣ የሚፈጠር ድኽነት ነው።
➋ ድንግልናዊ ሕይወት ራስን በፈቃድ ጃንደረባ ማድረግ ወይም
ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ "ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሊሆን
እወዳለው"። /1ኛ ቆሮ 7፥7/ በማለት የተናገረለትን ሕይወት
ለመኖር የሚያስችል ነው።
➌ "መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ
ከማቅረብ ይበልጣል"። /1ኛ ሳሙ 15፥22/ በተባለው መሠረት
ገዳማዊ ሕይወት ለእግዚአብሔር ፍጹም ታዛዥነትን የምናሳይበት ነው።
ገዳማዊነት ተቋማዊ በሆነ መልኩ የተጀመረው በ305 ዓ/ም አካባቢ "አባ እንጦንስ" በተባለ አባት ግብጽ ውስጥ ነው በ318 ዓ/ም ደግሞ አባ ጳኩሚስ ማኅበራዊ የሆነውን ገዳማዊ ሥርዓት
መሠረተ አባ መቃርዮስም በማኅበርና በተናጠል የሚኖርበትን ሥርዓት በማገናኘት መነኮሳት በሰንበት ዕለት ለትምህርትና ለቅዳሴ እንዲሰባሰቡ ሥርዓትን ሰራ። አባ እንጦንስ የተወለደው በ251 ዓ/ም አካባቢ "ቂምን ኤል አሮስ" በተባለች መንደር ግብጽ ውስጥ ነው ቤተሰቦቹ ሀብታሞችና ድኾችን የሚረዱ ነበሩ የሃያ አመት ሰው እያለ ወላጆች በሞት ተለዩት ወላጆቹንም ሊቀብር ወደ ቤተ ክርስቲያን በሄደ ጊዜ በቅዳሴ ላይ "ፍጹም ልትሆን ብትወድ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ተከተለኝ"። /ማቴ 19፥21/ የሚለውን የወንጌል ቃል በቅዳሴ ላይ ሲነበብ ሰምቶ በመፈፀም ሀብቱን ሁሉ ሽጦ ለድኾች በመስጠት ወደ ግብጽ በረሃ በምናኔ ወረደ ገዳማዊ ሕይወትንም መሥርቶ በዚያ ኖረ።

✿ አባ ጳኩሚስ የተወለደው በ290 ዓ/ም አካባቢ "ቴቢስ" በተባለች ከተማ ግብጽ ውስጥ ነው ወላጆቹ ክርስቲያኖች
አልነበሩም ወታደር እያለ በክርስቲያኖች ሕይወት ተማርኮ ክርስቲያን ለመሆን ወሰነ ከዚያም ተጠምቆ በረሃ በመውረድ
ማኅበራዊ የገዳም ሥርዓትን መሠረተ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ገዳማዊ ሕይወት ሥርዓት ባለው መንገድ የተስፋፋው በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን "በተሰዓቱ ቅዱሳን" አማካኝነት ቢሆንም እንደ እነ አባ አሞንዮስ፣ አባ ዮሐኒ፣ አባ
ዘሊባኖስ ባሉ አባቶች ቀደም ብሎ ይታወቅ ነበረ።

☞ አባ አሞንዮስ፡- ሥርዓተ ምንኵስና ወደ ኢትዮጵያ ከመግባቱ በፊት "በተንቤን ቆላ ደብረ አንሣ" በተባለው በረሃ
በጾም በጸሎት ተወስነው ይኖሩ ነበር፡፡
☞ አባ ዮሐኒ፡- ደግሞ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መግቢያ ላይ በትግራይ ተንቤን አውራጃ በሀገረ ሰላም ቀበሌ ተወለዱ በዚያን ዘመን ሥርዓተ ምንኵስና ወደ ኢትዮጵያ ባይገባም አበው
በምናኔ በበረሃ ይኖሩ ነበር የአባ ዮሐኒ ቤተሰቦች ድሆች ስለነበሩ አባ አሞንዮስ ወስደው አሳደጓቸው ካደጉ በኋላም ከአባ አሞንዮስ ተለይተው ወደ በረሃ ለብቻቸው በመውረድ በተጋድሎ
ሲኖሩ ከቆዩ በኋላ በተወለዱ በ3ዐ ዓመታቸው ኀዳር 5 ቀን እግዚአብሔር ወደ ብሔረ ሕያዋን በመላእክት እጅ
እንደወሰዳቸው ገድለ አባ ዮሐኒ ይገልጣል፡፡ በአጠቃላይ ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያናችን ከላይ የተጠቀሱትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታዎች መሠረት አድርጋ ገዳማዊ ሕይወትን ልጆቿ እንዲኖሩበት ታስተምራለች የተሃድሶ
መናፍቃንም ከስህተት ጎዳና ወደ ቀጥተኛዋና ርትዒት ወደ ሆነችው ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያናችን በንሰኃ ይመለሱ ዘንድ የቤተ ክርስቲያናችን ጸሎት ነው።

✞ በገዳም የሚኖሩ አባቶቻችን እግዚአብሔር እድሜና ጤና
ይስጥልን፣ በረከታቸውም ይደርብን✞ አሜን✞✞✞
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ቸር ያውለን
በፅኑ ታማችኃል

@And_Haymanot

''በአፍላ ትጀምራላችሁ በወረት ትተውታላችሁ ። ያወቃችሁትን ትረሳላችሁ: ያላወቃችሁትን ለማወቅ ትጥራላችሁ የያዛችሁትን ትረግጣላችሁ: የረገጣችሁትን ትይዛላችሁ ።
ምኞታችሁ ልክ የለውም አምሮታችሁ ብዙ ነው ። ያማራችሁን ስታገኙ ወዲያው ይሰለቻችኋል ። ተዉ የተባላችሁትን ትሽራላችሁ የተከለከላችሁትን ትደፍራላችሁ የተፈቀደላችሁን ችላ ትሉታላችሁ ። ቤተመቅደስ እንዳትገቡ ብትከለከሉ ወደፊት ቤተመቅደሱን
በመስታወት ሠርታችሁ መቅደስ ባትገቡም እንኳን ሁሉን ከውጪ
ሆናችሁ ማየት ትፈልጋላችሁ ። ሁሉን ማወቅ ትፈልጋላችሁ : በአንዱም ግን አትጠቀሙበትም ። ሁሉ አላችሁ ግን ባዷችሁን ናችሁ ።
ሃይማኖት እንጂ እምነት የላችሁም! .......
በፅኑ ታማችኃል !..... "
(ከእመጓ መፅሀፍ የተወሰደ)
@And_Haymanot
@And_Haymanot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ?


#ይድረስ_ለተሃድሶ_መናፍቃን

@And_Haymanot

☞ "አጥብቀህ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት ተማር፥ ብሉያትን ሐዲሳትን በኦርቶዶክሳዊ መንገድ ምሥጢር አደላድል፤ እናም ጸልይ፤ ከሐሰተኛ፥ ከክህደት
ጽሑፎች ውጭ ሌሎችን አንብብ።" ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም ✞✞✞


✞ በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ታላቁ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ አውግስጢን "መናፍቃንን ስለ ጥርጥር ጥያቄያቸው ሁሉ እናመሰግናቸዋለን፤ የበለጠ እንድናጠና፣ በጥልቀት እንድንመራመር አድርገውናልና" እንዳለው የመናፍቃን መነሣት ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ ጥቅም ነው ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስም "ስራ የሞላበት ታላቅ በር ተከፍቶልኛል ተቃዋሚዎች ግን ብዙ ናቸው" ብሏል ዛሬም በእኛ ዘመን የእናት ጡት ነካሾች የተሃድሶ መናፍቃን የነገረ ሃይማኖት ጥያቄዎቻቸውን በማትታደስ ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያናችን ላይ ማጉረፍ ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል ምንም እንኳን ጥያቄዎቹ የተለመዱ እና ከጥንት ጀምሮ ተመሳሳይነት ያላቸው ቢሆንም አዲስ ትውልድ በየጊዜው ይመጣልና በየጊዜው ኩላዊት ቤተ ክርስቲያናችን መልስ ስትሰጣቸው ቆይታለች ሃራጥቃውያኑ ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታን ተረድተው በንሰኃ ከመመለስ ይልቅ አሁንም የኑፋቄ ጭቃቸውን ማቡካት ነው የመረጡት።

ወደድንም ጠላንም በአሁን ጊዜ የቅዱሳንን ሕይወት ተረድተን መጓዝ ካልቻልን ወንጌልን እንፈጽማለሁ ማለት ውሸት ነው በየዓውደ ምሕረቱ ላይ ከገድላት የሚጠቀሱ ተአምራት ታሪኮች መብዛት ይገባቸዋል ሁሉንም ነገር በጥቅስ ለማስደገፍ መሯሯጥ የእምነታችንን መላላት ያሳያል እንጂ የሃይማኖት ጥንካሬያችንን አያመላክትም የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቢሆንም ያልተመዘገቡ በርካታ ነገሮች አሉ "ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ" ተብሎ ተጽፏል" /ዮሐ 14፥12/ ኃላ የሚነሱ ቅዱሳን ጌታ ካደረገው ተአምር የበለጠ በክርስቶስ ስም እንደሚያደርጉ ተጽፏል /ዮሐ 14፥12/ በቅዱሳን ሕይወት የሚመሰገነው ክርስቶስ ነው ቅዱሳን ዐርባና ሃምሳ ዓመት በጾም ተወስነው እንዲቆዩ የሚያደርጋቸው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው ቅዱሳን ለእግዚአብሔር የተመቹ ድንቅ ተአምራት የተደረጉባቸው ናቸው "እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቆ ነው" ተብሎ ተጽፏል /መዝ 67፥35/ ቅዱሳንን መንቀፍ፣ አያማልድም ብሎ ክብራቸውን ማቃለልም ባለቤቱን ቃል ኪዳን የሰጣቸውን እግዚአብሔርን መቃወም ነው።

እግዚአብሔር አምላክ ቃል ኪዳን ሰጥቶ ኃጥአንን ቢምር አንተ ምን ያበሳጭሃል? "ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ" ተብሎ ተጽፎ የለምን? /መዝ 88፥3/ ሰው ቢድን ለምን እንደ ሰይጣን ትቀናለህ? ክርስቶስን እስከመቼ ስታሳድድ ትኖራለህ? በቸርነቱ ሰው ይድን ዘንድ የዘረጋውን የማማለድ በረከት ለምን ትነቅፋለህ? "ባሪያዬ ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል" እንደተባለ፤ የባሪያዬ የተክለ ሃይማኖት ቃል ኪዳን የሌሎቹንም አልረሳም ቢል ምን ያበሳጭሃል? በቅዱሳኑ አድሮ የሰራ መንፈስ ቅዱስ ነው ቅዱሳንን መንቀፍና አለመቀበል መንፈስ ቅዱስን፤ ክርስቶስን አለመቀበል ነው በሐዋ.ሥራ 9፥4 ላይ ያለውን እስቲ በቅንነት እናንብበው " #ሳውል_ሳውል_ስለምን_ታሳድደኛለህ?" የተሰደዱት ሐዋርያት፣ ተናጋሪው ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር የሚሰደዱት ሐዋርያት ላይ ያደረው ኢየሱስ ክርስቶስ ነበርና " #አንተ_የምታሳድደኝ_እኔ_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ነኝ" ብሎታል ስለዚህ ቅዱሳንና እግዚአብሔር አይነጣጠሉም።።።።።። ደግሞስ "የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል" ተብሎ የለምን? /መዝ 111፥6፣ ምሳ 10፥7/ ከዚህ አንጻር የድርሻችንን እየተወጣን እያንዳንዳችን ልንዘክራቸው የሚገቡንን ቅዱሳን በመያዝ ገድላቸውን በማንበብ፣ በመጸለይ፣ በስማቸው ነዳያንን እያበላን በእምነትና በቃል፣ በሥራን ልንመስላቸው ይገባል። /1ኛ ጢሞ 4፥12/

ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክ በነቢዩ አድሮ እንደተናገረው ለመታሰቢያ፣ ለበረከት፣ ለፈውስ እንዲሆን የቅዱሳን ገድላቸው ተጽፏል መጠቀም የእውነተኛ ክርስቲያን ድርሻ ነው መጽሐፍስ "እግዚአብሔርንም ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ የመታሰቢያ መጽሐፍ በፊቱ ተጻፈ" ብሎ ትንቢት ተነግሮላቸዋል /ሚል 3፥16/ ገድላት ወንጌልን በተግባር የገለጡ የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች ናቸው ከዚህ ከማያልቀው የገድላት በረከት ለመሳተፍ ገድላትን እናንብብ፤ ቅዱሳንን እንዘክር አሁን በእውነት በእግዚአብሔር ቸርነት በቅዱሳን አማላጅነት ካልሆነ በቀር በዚህ ዘመን በሥራው የሚጸድቅ ይኖር ይሆን? ስለዚህ በዚህ ክፋት በሰለጠነበት ዘመን ወደ ቅዱሳኑ መጠጋት ይገባል ለዚህም የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን። አሜን።✞✞✞

☞ "አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና።" 2ኛ ጢሞ 3፥14 ✞✞✞

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
✞_✞_✞
✞ ✞ ✞ ✞ ታቦት ✞ ✞ ✞ ✞

@And_Haymanot
(((((Share በማድረግ ምላሽ ላጡት እናድርስ))))))

ታቦት ማለት ቤተ፣ አደረ ከሚለው ግዕዝ ቃል የመጣ ነው ሲሆን ታቦት የፅላተ ኪዳኑ ማደርያና የእግዚአብሔር መገለጫ ነው፡፡
ማስረጃ እንመልከት
✞ ዘጸአት 24:12
✞ ዘጸአት 25-8፤
✞ ዘጸ 25:21፤
[የምንጠቅሳቸውን ጥቅሶች ከመ/ቅዱስ እያመሳከራችሁ አንብቧቸው]
👉 ከላይ ከተገለፁት ማሥረጃዎች በመነሳት ሙሉ ሀሳቡን እንመልከት
ታቦት በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ለሙሴ በዚህ ሆኜ እገለጥላችኋለው ሲል አስር ህግጋት የተፃፈባቸውን ሁለት ፅላቶችን ሰጥቶታል፡፡ ዘፀ 24:12 ዘፀ 28:7፡፡ ታቦት እግዚአብሔር 10 ህግጋት ያሥተላለፈበት ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር የክብሩ መገለጫም ጭምር ነው፡፡ እነ ሰለሞን ሌሎችም እስራኤላውያን ለታቦት የሰገዱት በታቦት ላይ ሥላለው ህግ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር ለምህረት በሚመጣበት ጊዜ ዙፋኑ ስለሆነም ነው፡፡ ኢያ 7:6

👉 ታቦት የእግዚአብሔር ስራ እንጂ ጣኦት አይደለም፡፡

ማሥረጃ እንመልከት
✞ ዘጸ 31:18 " እግዚአብሔርም ከሙሴ ጋር በሲና ተራራ የተናገረውን በፈጸመ ጊዜ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን ከድንጋይ የሆኑ ሁለቱን የምስክር ጽላቶች ሰጠው።"
✞ ኦሪት ዘጸ 32:15፤ ሙሴም ተመለሰ፥ ሁለቱንም የምስክር ጽላቶች በእጁ ይዞ ከተራራው ወረደ፤ ጽላቶቹም በዚህና በዚያ በሁለት ወገን ተጽፎባቸው ነበር።
16፤ ጽላቶቹም የእግዚአብሔር ሥራ ነበሩ፤ ጽሕፈቱም በጽላቶች ላይ የተቀረጸባቸው የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበረ።
✞ 2ኛ ቆሮንጦስ 6፥16-17 :- ”ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና፧ ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው? የእግዚዓብሔር ታቦትንስ በጣዖት ቤት የሚያኖር ማነው?”

👉 ለታቦት የሚደረግ ስግደትነና ክብር
✞ ኢያ 7:6 ✞ ዘኊ 7:89
✞ 1ኛዜና 13:10 ✞ ዘጸ33:10
✞ ፊል 2:3 ✞1ኛሳሙ 4:5

👉የተሠበረው ታቦት ድጋሜ ሥለመሠራቱ
ሙሴ የተቀበለውን ጽላት ተሠብሯል በማለት ይህን ይጠቅሳሉ
✞ ኦሪት ዘጸአት 32፥ 19 :- ”ጥጃውንም ዘፈኑንም አየ የሙሴም ቍጣ ተቃጠለ፥ ጽላቶቹንም ከእጁ ጥሎ ከተራራው በታች ሰበራቸው። የተሠበሩትም በድጋሚ እንዲሠሩ ታዟል፡፡
✞ ኦሪት ዘዳ 10:1፤ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር። እንደ ፊተኞች ያሉትን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠርበህ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፥ ለአንተም የእንጨት ታቦት ሥራ፤
2፤ በሰበርሃቸውም በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች በእነዚህ ጽላቶች እጽፋለሁ፥ በታቦቱም ውስጥ ታደርጋቸዋለህ አለኝ። 3፤ ከግራርም እንጨት ታቦትን ሠራሁ፥ እንደ ፊተኞችም ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠረብሁ፤ ሁለቱንም ጽላቶች በእጄ ይዤ ወደ ተራራው ወጣሁ።

👉 ታቦት በኦሪት(ክርስቶስ ከመወለዱ በፊት ) እንጂ አሁን(በሐዲስ ኪዳን) አይጠቅምም ለሚሉ

መልሳችን የማቴዎስ ወንጌል 5፥17 ነው:: የማቴዎስ ወንጌል 5፥17 :- ” እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ
አታልፍም” ብሎአል ኢየሱስ ክርስቶስ:: ኦሪት ዘጸአት 27:21 :- ”አንተም መብራቱን ሁልጊዜ ያበሩት ዘንድ ለመብራት ተወቅጦ የተጠለለ ጥሩ የወይራ ዘይት እንዲያመጡልህ የእስራኤልን ልጆች እዘዛቸው። በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ታቦት ፊት ባለው መጋረጃ ውጭ
አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት እንዲበራ
ያሰናዱት በእስራኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃቸው #የዘላለም ሥርዓት ይሁን ።” ይህን ጥቅስ ስንመለከት ለልጅ ልጃቸው የዘላለም ሥርዓት ይሁን። እንጂ ለኦሪት
(ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪወለድ) ብቻ አይልም። ዳዊትም ስለታቦት በመዝሙሩ እንዲህ ብሎአል መዝሙረ ዳዊት 132:7-9 :- ”ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን ። አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት። ካህናቶችህ ጽድቅን ይልበሱ” አንድ በእግዚአብሔር ስም የሚሰራ ቤት ታቦት ሊኖረው ይገባል።
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 22:19 :- ”አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትፈልጉ ዘንድ ልባችሁንና ነፍሳችሁን ስጡ ለእግዚአብሔርም ስም
ወደሚሠራው ቤት የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦትና የእግዚአብሔርን
ንዋየ ቅድሳት ታመጡ ዘንድ ተነሥታችሁ የአምላክን የእግዚአብሔርን መቅደስ
ሥሩ። ”

👉 ታቦትን ሌሎች ሃገራት እንዴት ይጠቀሙታል ?

የተሀድሶ መናፍቃን ታቦት በሀገራችን ብቻ ያለና ሌሎች ሀገራት በተለይም አምስቱ አብያተ ቤተክርስቲያናትም ጭምር የሌለ አድርገው ሲቃወሙ እንመለከታለን
✞✞ በኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት(oriental crurch) ታቦት የተለመደ ህግ ነው፡፡ ሥጋና ደሙንም የሚፈትቱት በታቦቱ ላይ ነው፡፡
ክርስቲያኖች አንድ ሊያውቁት የሚገባው ትልቁ ነገር በብሉይ ኪዳን የነበረው የታቦት አገልግሎት የበጎችና የጥጆች ደም በቅድስተ ቅዱሳን ፊት ለፊት የመሠዋት ስርዓት ነበር፡፡ ይህም በእውነተኛ አምላካችንና መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደም ተወግዶ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ ይለናል ዕብ 9:12 የኢየሱስ ክርስቶስ ደም እኛን ከሃጢአት ሁሉ በማጠብ የቀደመውን መስዋዕት አስወግዶ እርሱ መስዋዕት ሆኖ ከብሯል፡፡ በታቦቱም ላይ የማዳኑን ምሥጢር በመግለፅ ሰዎች ሁሉ ሥጋውን በልተው ደሙን ጠጥተው እንዲድኑ ይናገራል፡፡ ዮሐ 6:54 ይህን እውነት በመያዝ ታቦት በብሉይ ኪዳን የነበረ አገልግሎትና በአዲስ ኪዳን ያለው አገልግሎት ልዩነቱን በትክክል መረዳት ያሥፈልጋል፡፡
ለምሳሌ ግብጻውያን ታቦቱን #ሉሕ ይሉታል ፅላት ሠሌዳ ማለት ነው ያለሱ ሥጋና ደሙን አይፈትቱም፡፡
የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ተብለው የሚጠሩ የግሪክ የሩሲያ፣የሮማኒያ ሌሎችም ወደ ክርስትና የተመለሱት ከአረማዊነት ስለሆነ የታቦቱን ምሥጢር አያውቁትም በታቦቱ ፈንታ ከመንበር የማይነሳ እንደ ታቦት የሚከብር የጌታ የስቅለቱ ወይም የግንዘቱ ሥዕል ያለበት የነጭ ሐር መጎናፀፊያ አላቸው፡፡ ያለሡም ሥጋና ደሙን አይፈትቱም፡፡ ይህንንም በጽርዕ "እንደምኒሲዩን" ይሉታል፡፡ "ህንየተ ታቦት" ማለት ነው፡፡ የሮማ ካቶሊኮች 'ሜንሳ' Mensa ይሉታል፡፡ ጠረጴዛ ማለት ነው፡፡ ከአምስቱ አብያተ ክርስቲያናት በቀር አዲስ ቤ/ክርስቲያን በሚሠራበት ጊዜ የአጽመ ቅዱሳን ሽራፊ እንዲቀመጥ ያዛል

👉 በሰማይም ታቦት እንዳለ የሚከተለውን በማለት ሐዋርያው ዮሐንስ በራእይ ያየውን ጽፎልናል የዮሐንስ ራእይ11:19 :- ” በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፥ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።”
ይቆየን ....
ወስብሀት ለእግዚአብሔር
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የማርያም ልጅ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ከቤቱ አይለየን
@And_Haymanot
የሚቀጥለው ርዕሳችን
#And_Haymanot

በታቦት ዙርያ የሚነሱ የተሐድሶ መናፍቃን ጥያቄዎች
ክፍል ፪
👉 ታቦት ተሽሯል?
👉 ይህ ሁሉ ታቦት ከየት መጣ?
👉 የሐዲስ ኪዳን ታቦታችን ክርስቶስ ነው ሌላውን ሽሮታል?
ኦርቶዶክስ መልስ አላት
@And_Haymanot
@And_Haymanot
አሜን❤️ አሜን❤️ አሜን❤️
@And_Haymanot
📊 ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል የሆነው የቱ ነው

ካለንበት አካባቢ አንጻር በሰዓቱ ባለማድረሳችን ይቅርታ [8]
‎├ NATTY ABRHAM
‎├ Mekdi Abi
‎├ temesgen atilaw
‎├ ሀብተማርያም ተመስገን
‎├ Mahi Eshetu
‎├ Michael
‎├ Simon Mulugeta
‎└ It'z mi......

ሀ/ ፺ = 80 [7]
‎├ sami ab
‎├ Biniyam Eyasu
‎├ Lidet
‎├ Tizita Abebe
‎├ Banana Banana
‎├ 64922
‎└ Rewina Awash

ለ/ ፴፮ = 56 [3]
‎├ Melat
‎├ Haftamu Getahun
‎└ wubet aniley

ሐ/ ፴፱ =39 [27]
‎├ Gelila Belete
‎├ ቅጣው ረምርም
‎├ Bad-man
‎├ Addisu Tesfaye
‎├ Biruktawit
‎├ Haymanot Gezhegne
‎├ Elbethel
‎├ Yam Luck
‎├ Kalkidan Tefera
‎├ ኬርሞን
‎├ Mitku Teshome
‎├ BA
‎├ Ma dina
‎├ Kefelegn Dejene
‎├ Yonatan
‎├ Tsehay Tade
‎├ ሞአ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ ስዩመ...
‎├ ሰላሜነሽ ድንግል ዋስትናዬ
‎├ Robel Ye Maryam
‎├ ተሻረ ቃል ኪዳኑ፡፡
‎├ Eleni Tadesse
‎├ Shefera Shefe
‎├ Birkty Ed
‎├ 01
‎├ Henok Asrat
‎├ tare
‎└ Eyob

መ/ ፸ = 90 [5]
‎├ Meboni Dere
‎├ Hela
‎├ Dereje Yosef
‎├ 08297 Tasew
‎└ ኤልሳ

👥 50 people have voted so far
🚫 This poll is closed...
📊 ተወዳጆች አንድ ጥያቄ ማሥቀደማችን እንዳለ ሆኖ ቃላችንን ለማክበር ጥያቄያችንን በድጋሜ እነሆ


ጌታችን መቼ ተወለደ ?


ሀ/ መስከረም [5]
‎├ Gelila Weretu
‎├ Gezahegn Demas
‎├ Banana Banana
‎├ M K
‎└ amani

ለ/ ህዳር [3]
‎├ TONIC
‎├ ሤራና አንዶ
‎└ leya leya

ሐ/ የካቲት [4]
‎├ Queen Bru
‎├ Du Man
‎├ Ab Cd
‎└ Demeke

መ/ ታህሳስ [36]
‎├ ሀብተማርያም ተመስገን
‎├ sis
‎├ NATTY ABRHAM
‎├ Haymanot Gezhegne
‎├ Eleni Tadesse
‎├ Mitku Teshome
‎├ maya maya
‎├ Shefera Shefe
‎├ Yam Luck
‎├ Ma dina
‎├ It'z mi......
‎├ Kefelegn Dejene
‎├ emawayesh fentaw
‎├ Helen
‎├ Jo
‎├ እናቴ ውስጤ ናት
‎├ Yemichael Ashenafi
‎├ Saba Akberom
‎├ Bad-man
‎├ 01
‎├ dereje betru
‎├ Elbethel
‎├ ፍቅር ትልቅ ሀይል አለው ህይወትም ...
‎├ Betelhem Handebo
‎├ Ermy Mak
‎├ የድንግል ማርያም ልጅ
‎├ ሰናይት አጸደ ማርያም
‎├ Kirubel Gizaw
‎├ ክብር ለድንግል ማርያም
‎├ ኬርሞን
‎├ Edle
‎├ Mafi Abay
‎├ tare
‎├ Romania Tam
‎├ Yonatan
‎└ Elade

👥 48 people have voted so far
🚫 This poll is closed...
የዛሬው ጥያቄያችን የመጀመርያ እንደመሆኑ ቀላል አድርገነዋል
የመጀመርያው ጥያቄ መልስ 👉 ሐ ሲሆን የሁለተኛው ጥያቄ መልስ ደግሞ መ ነው

ሽልማታችንን በመልስ አሠጣጡ ቅደም ተከተል ነውና ለዛሬ መጀመርያ የመለሡትን
#Gelila_Belete እና
#ሀብተማርያም_ተመሥገን ናችሁ ሁላችሁም ሥለተሳትፏችሁ ቃለ ህይወትን ያሠማልን እንላለን ተሳትፏችሁ ይቀጥል
✞ ✞ ✞ ✞ ታቦት ✞ ✞ ✞ ✞
(ካለፈው የቀጠለ)
@And_Haymanot
በታቦት ላይ የሚነሱ የተሐድሶ መናፍቃን ጥያቄዎች
1 ታቦት ተሽሯል?
2 ይህ ሁሉ ታቦት ከየት መጣ?
3 የሐዲስ ኪዳን ታቦታችን ክርስቶስ ነው ሌላውን ሽሮታል?

1 ታቦት ተሽሯል?

ተቃዋሚዎች ታቦት ተሽሯል በማለት የሚያቀርቡት አንዱ ማስረጃ በ2ኛ ቆሮ 3:3-18 ያለውን በመጥቀስ ነው፡፡ ይህ ቃል ሥለ ታቦት መሻር ሳይሆን የብሉይ ኪዳንን አገልግሎትና የሐዲስ ኪዳንን አገልግሎት በማነጻጸር የተጠቀመው ነው፡፡ እሥኪ ቃል በቃል እያየነው እንሒድ
+ " እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፡፡" ይህ ማለት በእግዚአብሔር መንፈስ ካለን ማገልገል እንችላለን በቀለም አይደለም ማለቱ እናንተን የቀረጻችሁ ልጆች ያደረጋችሁ ደሙ ነው እንጂ ቀለም አይደለም ማለት በተጻፈ ነገር (ሕግ) አልዳናችሁም በልጁ ደም እንጂ ብሎ ሊያነጻጽር ፈልጎ እንጂ ታቦት አያሥፈልግም አላለም፡፡ ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን በቀለም የተጻፈውን በመፈጸም እንደሚድኑ ስለተነገራቸው ነው አሁን ግን የእግዚአብሔር መንፈስ አጽንቶአቸዋል፣ቀድሷቸዋል ለማለት ነው፡፡
+ እኛ ታቦት ከዘላለም ሞት አዳኝ ነው አላልንም ታቦት የእግዚአብሔር የአምልኮት መሣርያ ስለሆነ ማክበር አለብን አምልኮታዊ ስግደት መሥገድ አለብን አልን እንጂ የክብሩ መገለጫ የአምልኮቱ መፈፀምያ ነውና፡፡
"..... ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው።"
+ በብሉይ ኪዳን አገልግሎት ውስጥ ጽላቱ ላይ የተጻፈውን ብቻ ያገለግሉ ነበር፡፡ ነገር ግን በልባቸው የተጻፈ ስላልነበረ እንደሚገባ አልኖሩበትም፡፡ አሁን ግን በአዲስ ኪዳን በልብ ጽላት ውስጥ መቀረጽ አለበት አለን እንጂ ፅላት አያስፈልግም አላለም፡፡ ጽላት አያሥፈልግም ማለትማ ሕጉ ትዕዛዛቱ አያሥፈልጉም ብሎ የእግዚአብሔርን ስራ መቃወም ነው፡፡
6",,,, እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንሆን ዘንድ አበቃን"
+ በጣም ግልጽ የሆነ ጽሑፍ ነው፡፡ የምናገለግለው በመንፈስ መሆኑን ነገረን በፊደል ለማይሆን ማለቱ ለገደለ መግደል ጥርስ ስለ ጥርስ ነበር አሁን ግን በመንፈስ ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች ሥላደረገን አዲሱ ቃል ኪዳን ደግሞ ክፉን በክፉ አለመቃወም ጠላትን መውደድ ስለሆነ ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንድንሆን የአገልግሎቱን መንፈስ ሰጠን ለማለት ነው፡፡ ማቴ 5:17 ከዚህም ጋር አያይዞ " ፊደል ይገድላል መንፈስ ግን ህይወትን ይሠጣል " ይላል፡፡ እንዲያውም ይህ ቃል ፅላትን ለመቃወም የተነገረ ከሆነ አባትና እናትህን አክብር የሚለው ህግ ይገድላል ማለት ነው፡፡ ከእኔ በቀር ሌላ አማልክት አታምልክ ያለው አማናዊ የሆነው በጽላቱ ላይ የተጻፈው ፊደል ይገድላል ስለዚህ ሌላ አምላክ ልናመልክ ይገባናል ማለት ነዋ! ግን አይደለም ቀደም ብለን እንዳየነው ህጉ መንፈስ ስላለነበረው ሰዎችን ከሞት ሊያድን እንዳልቻለ ገለጸልን እንጂ ለታቦቱ አለማሥፈለግ የተነገረ አይደለም፡፡
7",,,,, ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለ ተሻረው ስለ ፊቱ ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ፥ ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት በክብር ከሆነ፥
8፤ የመንፈስ አገልግሎት እንዴት ይልቅ በክብር አይሆንም?
9፤ የኵነኔ አገልግሎት ክብር ከሆነ፥ ይልቅ የጽድቅ አገልግሎት በክብር አብዝቶ ይበልጣልና።
+ ስለተሻረው ስለፊቱ ክብር ያለው ታቦትን ሳይሆን በሙሴ ፊት ላይ ታይት የነበረውን የእግዚአብሔርን ክብር ነው፡፡
ማሥረጃ ዘጸ 33:22 " የእስራኤልም ልጆች የሙሴን ፊት ቁርበት እንዳንጸባረቀ ያዩ ነበር፤ እርሱም ከእርሱ ጋር ሊነጋገር እስኪገባ ድረስ እንደ ገና በፊቱ መሸፈኛ ያደርግ ነበር። "
ቅዱስ ጳውሎስ ስለተሻረው የፊቱ ክብር ያለው ይህን የሙሴ ፊት ላይ ታይቶ ስለነበረው አንጸባራቂ ቁርበት(ቆዳው) እንጂ ስለ ታቦት አይደለም፡፡
👉በማያያዝም ያ በፊደላት ተድንጋዮች የተቀረጸ የሞት አገልግሎት በክብር ከሆነ የሚለው የታቦት አገልግሎት የሞት አገልግሎት ነው ለማለት ሳይሆን ያ የሙሴ ህግ(ሕገ ኦሪት) ሲሰጣቸው ክብር የነበረው ሆኖ ሳለ ከዘላለም ሞት ሊያድናቸው እንዳልቻለ ሁሉ በዘመናቸው መከራ ጸንቶባቸው እየተፈተኑ በታቦቱ ሀይል እየተቀጡ ስለተጓዙ አገልግሎቱ እነሱን ያዳነ ከዘላለም ጥፋት ማለትም ከአዳምና ሔዋን የውርስ ሀጢአት(original sin) ነጻ ያወጣቸው አለመሆኑን ለመግለፅ ነው፡፡ ይህማ ባይሆን ሙሴ ሞትና ኩነኔን አገለገለ እነጂ እግዚአብሔርን አላገለገለም ማለት ነውን? እነ ዳዊት እነ ሰለሞን ሌሎችም ነብያት ሁሉ ያገለገሉት ሞትን ነበር ማለት ነዋ? እግዚአብሔር የሠጠው የታቦት አገልግሎት የሞት ነበር ማለት ነዋ? ይህ ከሆነ ደግሞ እግዚአብሔር የሙታን አገልጋዮች አምላክ ሊሆን ነው፡፡ ይህ ሁሉ ግን ሐሰት ነው፡፡ ከዘላለም ሞት ሊያድናቸው እንዳልቻለ ለመግለፅ ነበር በክብር ከሆነ ብሏልና እግዚአብሔር ሞትን አክብሮ ሠጣቸው አንልም እነሡም ሞትን አላከበሩም ምሥጢሩ ግን ከዘላለም ሞት ከመዳን ምሥጢር ጋር የተገናኘ ስለሆነ ጳውሎስ አነጻጽሮ ጻፈው እንጂ ክብር የለውም አላለም፡፡
+የጽድቅ አገልግሎት አብዝቶ ይበልጣል ብሏልና ጽድቅን የሠጠን ለመንግስቱም ያበቃን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሆነ ይህ አገልግሎት ቤ/ክ እንደሚበልጥ አውቃ በታቦቱ ላይ ሥጋና ደሙን ፈትታ ታቀብላለች እንጂ ፍየልና ጥጃ አታርድም፡፡
+ በአጠቃላይ ያለው ንባብ ይህን አብራርቶ ለመግለጽ የተሞከረበት እንጂ ታቦት ተሽሯል አያስፈልግም አላለም፡፡ ይህማ ቢሆን ጳውሎስ በግልፅ ቋንቋ ተሽሯል ባለን ነበር፡፡ ነገር ግን ጌታ እንዳስተማረው " እኔ ህግንና ነብያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ " እንዳለ ፈፅሞታል፡፡ ማቴ 5:17 ተሽሯል ብሎ ማሥተማር ግን ታናሽ እንደሚያደርግ መጽሐፈ ቅዱስ ያረጋግጥልናል፡፡ ማቴ 5:20 ታቦት ደግሞ የጌታ ሕግና ትዕዛዝ ነው፡፡
2 ይህ ሁሉ ታቦት ከየት መጣ? በመሠረቱ እንዲህ ለሚሉት ሁለት ጥያቄ ብቻ እናነሳለን
፩ኛ የተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ በመጀመርያ ስንት ነበር?
፪ኛ የተሠራው የመጀመርያው መቅደስ ስንት ነው?
ብለን ብንጠይቅ መልሱ አንድ ነው የሚል ነው፡፡ ታድያ ይህ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ ከየት መጣ? ይህ ሁሉ ቤተክርስቲያን ምን ያደርጋል? ሰው እግዚአብሔርን ማምለክ ከፈለገ የግድ ኢየሩሳሌም መሔድ አለበት ማለት ነውን? ሰው ሁሉም ይቺን አንድ መጽሐፍ መጠቀም አለበት ማለትስ ነው? ግን አይደለም፡፡ መልሱ ለአገልግሎት የሚል ነው እንዲሁ የታቦቱ አገልግሎት እንደሚገባ ይዳረስ ዘንድ ያው አንዱን ታቦት በብዛት አገኘነው እንጂ የተለያየ ታቦት አይደለም፡፡
+ ለምን በቅዱሳን ስም ይሰየማል ለሚለው የመታሠቢያ ስማቸው እንዳይጠፋ ጌታ ቃል ገብቷልና ነው፡፡ ኢሳ 56:4

3 የሐዲስ ኪዳን ታቦታችን ክርስቶስ ነው ሌላውን ሽሮታል? ይህ ከመፅሐፍ ቅዱስ አንጻር ስህተት ክርስቶስም እኔ ታቦታችሁ ነኝ አላለም አምላካችሁ፣አባታችሁ ነኝ አለን እንጂ
ማስረጃ
ሮሜ 9:5 " አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን።"
+ ኢሳ 9:6 " ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም
አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።"
ወስብሀት ለእግዚአብሔር
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የማርያም ልጅ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ከቤቱ አይለየን
@And_Haymanot
@And_Haymanot
✞_✞_✞