፩ ሃይማኖት
8.91K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
#ሠለስቱ_ደቂቅን_ያዳናቸው_ማን_ነው?

@And_Haymanot

~► በድርሳነ ገብርኤል ላይ ገብርኤል
~► በድርሳነ ሚካኤል ላይ ሚካኤል
~► በድርሳነ ሩፋኤል ላይ ሩፋኤል ተብሎ መገለጹ ምሥጢሩ ምን ይሆን?
@And_Haymanot
“ታዲያ ሠለስቱ ደቂቅን ያወጣቸው ማን ነው?” ለሚለው የተሐድሶዎች
ጥያቄ የቀረበ መልስ በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ:

መጀመሪውንም መጽሐፍ ቅዱሱ ገብርኤል ነው አይልም፡፡ መጽሐፍ ቅዱሱ የሚለው የሚከተለውን ነው
‹‹ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ አማካሪዎቹንም፤ ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን? ብሎ ተናገራቸው። እነርሱም፦ ንጉሥ ሆይ፥ እውነት ነው ብለው ለንጉሡ መለሱለት። እርሱም፦ እነሆ፥ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል ብሎ መለሰ ›› /ዳን 3 ፤ 24 -25/ ፡፡
-
👉 በዚህ ገለጻ መሠረት አራተኛውን ያየው ንጉሡ ናቡከደነጾር ነው፡፡ እርሱም አየሁ ያለው አራተኛ ሰው ነው፡፡ የጨመረበት ቢኖር አራተኛው የአማልክትን ልጅ ይመስላል የሚለውን ነው፡፡ ለመሆኑ አራተኛውን ሰው እርሱ ብቻ ለምን አየ ? ሌሎቹ ለምን አላዩም ? አንደኛው የጥያቄው ቁልፍ ምስጢር ያለው እዚህ ላይ ነው
-
እውነቱን ለመናገር ይህ ሰው ጥንቱንም ሠለስቱ ደቂቅን ወደ እሣት የጣለው ራሱን ምስል አቁሞ ለምስሉ ሕዝቡን በማሰገድ ራሱን አምላክ አድርጎ ሊያስመልክ ነበር፡፡ ታዲያ ራሱንና እርሱን የመሰሉትን አምላክ አድርጎ የሚቆጥር ከሆነ የሚያየውን አራተኛውን ሰው ‹‹ የእኛን ልጅ ይመስላል ወይም እኛን ይመስላል›› ለምን አላለም? ከዚያ ይልቅ አርቆ ሌሎች አማልክትን የሚያመልክ አስመስሎ ‹‹ የአማልክትን ልጅ›› ይመስላል ያለበት ምስጢር ምንድን ነው ? ይህን ያለበት ምክንያቱ ያየው ነገር አራተኛው አካል ከህልውና ያለው በዘር በሩካቤ የተወለደ ሰው እነርሱ ሳያዩት እሳቱ ውስጥ ገብቶ ሳይሆን ነገሩ መገለጥ ስለሆነ ነው፡፡
+
👉 በብሉይ ኪዳን ከተገለጹት ታላላቅ ሦስት የእግዚአብሔር መገለጦች ውስጥ አንዱ ይህ የሠለስቱ ደቂቅ የድኅነት ታሪክ ነው፡፡
አንደኛው በመምሬ የአድባር ዛፍ ሥር እግዚአብሔር ለአብርሃም በሦስት ሰዎች አምሳል የተገለጠው መገለጥ ነው / ዘፍ 18/ ፡፡
ሁለተኛው ደግሞ አሁንም እግዚአብሔር ለአባታችን ለያዕቆብ በጎልማሳ አምሳል ተገልጾ ሲታገለው ያደረበት ታሪክና ያዕቆብንም መጀመሪያ ‹‹ ካልባረከኝ አልለቅህም ›› ከተባረከ በኋላም ‹‹ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሰውነቴም ድና ቀረች ሲል የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል ብሎ ጠራው ›› /ዘፍ 32 ፤ 25 - 32/ ያሰኘው መገለጥ ነው፡፡
ሦስተኛው ይህ ለባቢሎኑ አላዊ ንጉሥ ሠለስቱ ደቂቅን ወደ እቶን እሳት በጣለበት ወቅት ያደረገው መገለጥ ነው፡፡
-
ሦስቱም መገለጦች የሚያመሳስሏቸው ሁለት ጠባያት አሏቸው፡፡ የመጀመሪያው በሦስቱም ጊዜ እግዚአብሔር በሰው መልክና አምሳል መገለጡ ሲሆን ሁለተኛውና ዋናው ደግሞ ቃለ እግዚአብሔር በሥጋዌ ( ሰው በመሆን) ተገልጦ ለሰው ፍጹም ድኅነት የሚሰጥ መሆኑን አስቀድሞ በምሳሌ መግለጽ ነው፡፡ መሠረታዊ መልእክቱ ደግሞ አምላክ ሰው ከሆነ በኋላ የሚያድነው የተስፋውን ዘር እሥራኤልን ብቻ ሳይሆን አሕዛብንም ጭምር መሆኑን ለማሳየትና አሕዛብም የሥጋዌው ነገር ቀድሞ የተገለጸው ለእሥራኤል ብቻ ስለሆነ እኛ ልናምንበት አይገባም እንዳይሉ ለዚህ ደንዳናና ጫካኝ ናቡከደነጾርም ጭምር ገለጸለት፡፡
የእነ ነነዌ ታሪክም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሆኖ የተቀመጠውና እግዚአብሔር ለአሕዛብም ድኅነት ይፈጽም እንደነበር የተዘገበው እግዚአብሔር የእሥራኤል ብቻ ሳይሆን የሁሉም አምላክ የነበረ መሆኑን ራሱ ብሉይ ኪዳንም ምስክር እንዲሆን ነው፡፡ እነዚህን የመሰሉ ሌሎች ታሪኮችና ምሳሌዎችም በብዛት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ፡፡
ስለዚህ የዚህ በሠለስቱ ደቂቅ ድኅነት ውስጥ የታየው መገለጥ ዋናው ምስጢሩና መልእክቱም የአካላዊ ቃልን ሰው ሆኖ መገለጥና አዳኝ መሆኑንን በሐዲስ ኪዳንም እንደ ሠለስቱ ደቂቅ እሳትና ስለት፣ ሰይፍና ጎራዴ፤ እስራትና ግርፋት የሚቀበሉትን ሰማዕታት ሁሉ የሚያድናቸው እርሱ መሆኑን መግለጽ ነው፡፡
-
ታዲያ ዋናው መልእክቱና ምስጢሩ ይህ ከሆነ ገብርኤልም ሆነ ሌሎቹ መላእክት ለምን አዳኑ ይባላሉ? በቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት መሠረት ለሰዎች ከጊዜያዊና ምድራዊ አደጋና ሰዎች ከሚያመጡባቸው መከራ ድኅነት ሲደረግላቸው ድኅነታቸውን የሚፈጽሙላቸው ቅዱሳን መላእክት ማለትም ጠባቂ መላእክቶቻቸው ናቸው፡፡ ምንም አንኳ ይህ መሆኑን አንዳንድ ጊዜ በግልጽ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በምስጢር ቢገለጽም የእግዚአብሔር መላእክት ከሚጠብቋቸው ሰዎች ተለይተው አያውቁም፡፡
ለምሳሌ በሐዋርያት ሥራ ላይ ቅዱስ ያዕቆብን ያስገደለው ሔሮድስ ቅዱስ ጴጥሮስንም ለመግደል ባሰረው ጊዜ በዚያ ወቅት ሊሞት እግዚአብሔር ስላልፈቀደ መልአኩ እንዲያድነው አድርጓል፡፡ ‹‹ እነሆም፥ የጌታ መልአክ ቀረበ በቤትም ውስጥ ብርሃን በራ፤ ጴጥሮስንም ጎድኑን መትቶ አነቃውና። ፈጥነህ ተነሣ አለው። ሰንሰለቶቹም ከእጁ ወደቁ። መልአኩም። ታጠቅና ጫማህን አግባ አለው፥ እንዲሁም አደረገ። ልብስህንም ልበስና ተከተለኝ አለው። ወጥቶም ተከተለው፤ ራእይንም የሚያይ ይመስለው ነበር እንጂ በመልአኩ የሚደረገው ነገር እውነት እንደ ሆነ አላወቀም። የመጀመሪያውንና የሁለተኛውንም ዘብ አልፈው ወደ ከተማ ወደሚያወጣው ወደ ብረቱ መዝጊያ ደረሱ፤ እርሱም አውቆ ተከፈተላቸው፤ ወጥተውም አንዲት ስላች አለፉ ወዲያውም መልአኩ ከእርሱ ተለየ። ጴጥሮስም ወደ ልቡ ተመልሶ፦ ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንደ አዳነኝ አሁን በእውነት አወቅሁ አለ /ሐዋ 12፤ 7 - 11/ ተብሎ እንደተጻፈ ሙት ላነሣውና ስንት ተአምራት ላደረገው ቅዱስ ጴጥሮስ አሁን ግን ይህን ሁሉ የሚያደርግለት መልአኩ ነው፡፡ ይህ መልአክ የቅዱስ ጴጥሮስ ጠባቂ መልአክ እንደሆነ ብዙ ሊቃውንት በትርጓሜያቸው አስተምረዋል፡፡
በዚሁ ታሪክ ላይ ‹‹ ጴጥሮስም የደጁን መዝጊያ ባንኳኳ ጊዜ ሮዴ የሚሉአት አንዲት ገረድ ትሰማ ዘንድ ቀረበች፤ የጴጥሮስ ድምፅ መሆኑንም ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሣ ደጁን አልከፈተችም፥ ነገር ግን ወደ ውስጥ ሮጣ ጴጥሮስ በደጅ ፊት ቆሞ እንዳለ አወራች። እነርሱም፦ አብደሻል አሉአት። እርስዋ ግን እንዲሁ እንደ ሆነ ታስረግጥ ነበር። እርሱም፦ መልአኩ ነው አሉ ›› / 13-15 / ተብሎ እንደተጻፈው ውስጥ የነበሩት ጴጥሮስ አይሆንም ‹‹ መልአኩ›› ነው ያሏት እርሱን ሊመስልሽ የሚችለው ጠባቂ መልአኩ ነው ለማለት ነበር፡፡ ይህም የሆነው በጥንት ክርስቲያኖች ዘንድ የጠባቂ መላእክት ጥበቃና መገለጥ በሰፊው ይታወቅ ስለነበረ ነው፡፡
- @And_Haymanot
በመጽሐፈ ጦቢትም ላይ ቅዱስ ሩፋኤል ሰው መስሎ ለጦብያና ለቤተሰበው እንዲሁም ለራጉኤልና ለቤተሰቡ ቀድሞ ጸሎታቸውን በማሳረግ በኋላም ከፈተናቸው በማዳንና ሕይወታቸውን በመባረክ ተገልጾ አይተነዋል፡፡
-
እነዚህ ሁለት ታሪኮች የሚያሰረዱን ጠባቂ መላእክት በድሕነታችን ውስጥ ትልቅ ስፋራ የሚሰጣቸውና በርግጥም እነርሱ የሌሉበት ድኅነት የሌለ መሆኑን ነው፤ ልዩነቱ በአንዳንዶቹ ታሪኮች ላይ መገለጣቸው በአንዳንዶቹ ላይ ደግሞ ተገልጠው ለሰው አለመታየታቸው ብቻ ነው፡፡
-
👉 ጌታችንም በወንጌል ‹‹ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው
👍1